Telegram Web Link
ሥርዓተ ማህሌት አመ ፲ወ፫ ለጥር እግዚአብሔር አብ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

ነግስ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ነአምን በ፩ዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኩሉ፤ገባሬ ሰማያት ወምድር፤ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ቅዱስ እግዚአብሔር እማርያም ተወልደ፤ቅዱስ እግዚአብሔር በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

መልክዐ እግዚአብሔር አብ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስቡሕ ወውዱስ፤ዘትሴባሕ ወትረ በአፈ ኩሉ ዘነፍስ፤እግዚአብሔር እስመ አልብከ ተጽናስ፤እምቅድመ ዘመን ዘመናዊ ወድኅረ ዘመናት ሐዲስ፤እንዘ ለዘመናት አንተ ሕገ ዛኅን ወመርስ።

ዚቅ
ስቡሕ በውስተ ቅዱሳን በመንክር ኃይለ ስብሐቲከ፤ዘትገብር መድምመ።

መልክዐ እግዚአብሔር አብ፦
ሰላም ለቀራንብቲከ ወለአዕይንቲከ ብሩሃት፤ዘኢይትጋወሮን ጽልመት፤እግዚአብሔር አብ አበ ብርሃናት፤አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት፤እስመ ለከ ኀይል ወለከ  ስብሐት።

ዚቅ
ንስግድ ለአበ ብርሃናት ወለወልዱ ዋህድ፤ወለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ሥሉስ ዕሩይ።

መልክዐ እግዚአብሔር አብ፦
ሰላም ለልብከ ጻድቅ ወየዋህ፤ወለሕሊናከ ዓዲ ማእምረ ዘመን ነዋኅ፤እግዚአብሔር አብ በአፈ ኩሉ ስቡሕ፤እስመ ሣህልከ ወምሕረትከ ብዙኅ፤የማንከ ለምሕሮ ኩለሄ ስፋሕ።

ዚቅ
ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ፤አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ፤ትሰፍሕ የማነከ፤ወታጸግብ ለኵሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ።

ዓርኬ
እግዚአብሔር አብ አኃዜ ዓለም በእድ፤እግዚአብሔር አብ አቡሁ ለወልድ፤እግዚአብሔር አብ ዘዓረፍተ ቤትከ ነድ፤ፈቃድከ ይኩን እግዚኦ ለዘይመጽአ ነገድ፤እስመ መልዓ ስብሐቲከ በዛቲ አጸድ።

ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ዓረፍተ ጽርሑ ዘነድ ወጸፍጽፈ ቤቱ በረዱ፤ኅቡር ህላዌሁ ዘኢይትበዓድ ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ሰጊድ።

ምልጣን
ኅቡር መንበሩ ምስለ አቡሁ ዘዕሩይ ምስለ ወላዲሁ ዘእምቅድመ ዓለም መንግስቱ ሰፋኒት ለቅዱሳን እዘዝ፤እንዘ ነአምን ወንገኒ ከመ ውእቱ ረዳኢ ወመድኅን አማን እደ መዝራዕቱ ለእዱ ለልዑል።

አመላለስ
አማን በአማን እደ መዝራዕቱ/፪/
እደ መዝራዕቱ ለልዑል/፬/

እስመ ለዓለም፦
አመ ሣልስት ዕለት ከብካብ ኮነ፤በቃና ዘገሊላ፤ዘረሰዮ ለማየ ወይነ፤ወሀለወት ህየ እሙ ለኢየሱስ፤ወትቤሎ እሙ ወይንኬ አልቦሙ፤ወትቤሎ ሐልቀኬ ወይኖሙ፤ወይቤሎሙ ቅዱሑ ማየ ወምልዕዎን ለመሳብክት እስከ አፉሆን፤ቀድሑ ወወሀብዎ ለሊቅ ምርፋቅ፤ጥዒሞ አንከረ ሊቀ ምርፋቅ በረከት ዘአምላክ ገብረ፤እስመ በረከተ ይሁብ መምህረ ሕግ።
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ዋይዜማ አመ ፲ወ፭ ለጥር ቂርቆስ



መኃትዉ በ፪
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ውእቱ ኮከብ መርሆሙ፤ወአብጽሖሙ ኀበ ሀለዉ፤ሕፃን ወእሙ፤ቆመ መልዕልቴሆሙ ወአምጽኡ አምኃሆሙ ወርቀ፤ቆመ መልዕልቴሆሙ  ወአምጽኡ ከርቤ ወስሂነ፤ቆመ መልዕልቴሆሙ ወአምጽኡ አምኃሆሙ ፈትሑ መዛግብቲሆሙ፤ወይቤሉ ኵሎሙ፤ወልደ እግዚአብሔር ጽኑዕ ውእቱ።

ዋዜማ በ፩
ይቤላ ሕፃን ለእሙ፤ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ ዮም፤ንፈጽም ገድለነ ከመ ናሥምሮ ለአምላክነ፤ለዘሐወፀነ እምአርያም።
#ዘአቋቋም:-ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ፤ከመ ናሥምሮ ለአምላክነ፤ለዘሐወፀነ እምአርያም።

ምልጣን
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ፤ከመ ናሥምሮ ለአምላክነ፤ለዘሐወፀነ እምአርያም፤ለዘሐወፀነ እምአርያም።

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
ሰአል ለነ ሕፃን ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፤ሰአል ለነ ሕፃን።

እግዚአብሔር ነግሠ
ዘምስለ እግዚኡ ኪዳነ ዘዓቀመ ወብዙኃነ ሕዝበ አእመነ ለብፁዕ ቂርቆስ አልቦ ዘይሞግሶ አክሊለ ነሥአ ዲበ ርእሱ።

ይትባረክ
ልህቀ ሕፃን ወጸንዓ በመንፈስ ቅዱስ፤ነበረ ኃቅለ እስከ አመ ያገይስዎ ኀበ ፳ኤል፤ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ዓቢየ ፍሥሐ ዘይከውን ለኵሉ ዓለም፤ክብረ ቅዱሳን አስተርአየ።

፫ት
ይገንዩ አሕዛብ ለስምከ እግዚኦ፤ወነገሥትኒ ለስብሐቲከ፤እስመ ልህቀ ሕፃን፤ወአስተርአየ በብርሃነ ስብሐቲሁ።

ሰላም
ዘይሥእሎሙ ለሕፃናት፤ወይነግሥ ለሰማዕት፤በደብረ ጽዮን በሀገር ቅድስት፤ነቢያት ሰበኩ ምጽአቶ፤መላእክት ይሰግዱ ሎቱ፤ሐዋርያት ኮንዎ ሰማዕቶ መጽአ ኀቤነ፤ትእምርተ ሰላምነ ወልድ ተወልደ ለነ።
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፲ወ፭ ለጥር ቂርቆስ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቊያጺክሙ እለ ተኀብዓ እም ዐይን፤አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን፤ልብሰ ሰማዕትና ይኩነኒ ምህረትክሙ ኪዳን፤ላእሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን፤ወስርጋዌሁ እሣት ለቂርቆስ ህፃን።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ሐይቀ ባሕረ ገሊላ እምአመ ረከቦ እንዘ ያንሶሱ፤ቂርቆስ ለኢየሱስ ተለዎ እምንእሱ፤ለመንገለ ጽድቅ አቅነያ ለነፍሱ፤ሀገረ ብርሃን ፈለሰ እምዓለም ዘይኄሱ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።

ዚቅ
ይቤሎ ኢየሱስ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስእለተከ፤እምብዙኅ ፃማ አአርፈከ፤ኀበ ሀሎ ፍሥሐ አነብረከ።

ምልጣን
ኀበ ሀሎ ፍሥሐ አነብረከ፤ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስእለተከ፤እምብዙኅ ፃማ አአርፈከ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ጻድቃን ይበውዑ ውስቴታ የዋሃን የዓውዱ መሠረታ ሠማዕት ይቀውሙ አውዳ በዕለተ ቂርቆስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን፤ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን፤ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን፤ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን፤ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ
ሕፃነ እምከርሠ እሙ ሰመዮ፤አዕበዮ እግዚአብሔር፤ወኃረዮ ለመንግሥተ ሰማያት።

ወረብ
ሕፃነ ሰመዮ እምከርሠ እሙ አዕበዮ እግዚአብሔር/፪/
ወኃረዮ ለመንግሥተ ሰማያት ለመንግሥተ ሰማያት/፪/

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለክሣድከ ለሰይፈ ሐራዊ በልሳኑ፤እንተ ተወቅየ ድኑኑ፤እምኀበ እስክንድሮስ አብድ ወዓላውያን ተዓይኑ፤ዘረከበከ ሕማመ ወምንዳቤ ዘበበዘመኑ፤ሕፃን ቂርቆስ እስፍንተ እዜኑ።

ዚቅ
ቅዱስ ቂርቆስ ሶበ ተከለለ፤ደም ወማይ ወኃሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ።

ወረብ
ቅዱስ ቂርቆስ ሶበ ሶበ ተከለለ/፪/
ደም ወማይ ወኃሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ/፪/

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለከርሥከ ወለልብከ ኅቡረ፤ኅብስተ ኵነኔ ወሕማም እለ ረሰዩ ድራረ፤ረሲ ቂርቆስ ቃለ አፉየ ሥሙረ፤ወዘሰአልኡከ ብዙኅ ነገረ፤አዘክሮ ለአምላክ ወንግሮ ወትረ።

ዚቅ
ሕገ አምላኩ ውስተ ልቡ፤ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ፤ሣህል ወርትዕ ተራከባ፤ጽድቅ ወሰላም ተሰዓማ።

ወረብ
ሕገ አምላኩ ውስተ ልቡ ሕገ አምላኩ/፪/
ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ ውስተ ልቡ ሕገ አምላኩ/፪/

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ ቀቲሎቴ ዘኢክህለ፤መኰንን ዓላዊ አመ ሥጋከ ቀተለ፤ሰሚዓከ ቂርቆስ ረዳኢ ዘአሰአልኩከ ስኢለ፤ዕሥየኒ ጽድቀ እምጽድቅከ ወእምነ ሣህልከ ሣህለ፤አኮኑ እምነ ኵሉ እፈርህ ሲኦለ።

ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡

ወረብ
እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ/፪/

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ በሠረገላሁ ዘተኀብአ፤ለነቢይ ኤልያስ በሕገ አምላክ ዘቀንዐ፤መምሕረ መምህራን ቂርቆስ እንተ ታጸድቅ ኃጥአ፤ጌጋይየ ሥረይ ለአባሲ ከመ መምህርከ ሠርዐ፤ወኅድግ አበሳነ በበስብዕ ስብዓ።

ዚቅ
ባረኮ ለሕፃን፤አንበረ አክሊለ ዲበ ርእሱ፤ባረኮ ለሕፃን አክሊለ ስምዕ ዘክርስቶስ፤ባረኮ ለሕፃን ወይቤሎ ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለሕማምከ ወለግፍዕከ ብዙኅ፤እንተ ያበኪ አልባበ ከመ ግፍዐ ክርስቶስ ርኅሩኅ፤ክረምተ ፍሥሓየ ቂርቆስ ለብእሴ ሰቆቃው ወላህ፤ያንጠብጥብ በላዕሌየ መጠነ ሠለስቱ አዉራኅ፤ነጠብጣበ ትፍሥሕት በረከትከ ወዝናም ንጹሕ

ዚቅ
ሕማሙ ዘኮኖ ረባሐ ለብዙኃን ፍሥሐ፤በብሩህ ገጽ ቅድመ እግዚአብሔር በጽሐ።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለነቅዐ ደምከ ዘተቶስሐ በደሙ፤ለበግዐ መስቀል ክርስቶስ እንተ ያደነግፅ ዜና ሕማሙ፤እኅወ ሰማዕታት ቂርቆስ ወለሐዋርያት ወልዶሙ፤ለእለ ገብሩ ተዝካረከ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሀቦሙ፤ወእሤተ ጽድቅ በሰማይ አስተዳሉ ሎሙ።

ዚቅ
ሰማዕታተ ክርስቶስ በእንተ ስሙ፤ህየንተ ደሙ ከዓው ደሞሙ፤ይብጽሐነ ወትረ ጸሎቶሙ።

መልክአ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ፤ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ፤ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ፤ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ፤ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት፤ሰላም ለኪ፤ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ምስለ ኵልነ፤ኢየሉጣ እምነ፤ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ፤ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ፤ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

አመላለስ
ኢየሉጣ እምነ ኢየሉጣ እምነ/፪/
ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ
አንገርጋሪ
ዘንጉሥ ኄጣ ጸለየ ላቲ ወልዳ ተዝካሮሙ ንግበር ለቂርቆስ ወለኢየሉጣ፤እለ በተአምኖ ወረሱ ተስፋሆሙ፤ፈድፋደ እምሰብእ የዓቢ እሤቶሙ።

ምልጣን
እለ በተአምኖ ወረሱ ተስፋሆሙ፤ፈድፋደ እምሰብእ የዓቢ እሤቶሙ።

ወረብ ዘአንገርጋሪ
ዘንጉሥ ኄጣ ጸለየ ላቲ ወልዳ/፪/
ተዝካሮሙ ንግበር ለቂርቆስ ወለኢየሉጣ/፪/

እስመ ለዓለም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ፤ሰብአ ሰገል አምጽኡ ጋዳ፤ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት፤እንዘ ይወርድ ውስተ ምጥማቃት፤በአምሳለ ርእየተ ርግብ፤ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት በከመ ይቤ እግዚእነ በወንጌል፤ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ዘኪያሁ ሠመርኩ፤ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት፤ቂርቆስኒ ይቤ ለልየ ርኢኩ፤ወአነ ሰማዕቱ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ፤ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት፤ወአስተርአዮሙ ለሐዋርያት፤ወአንሶሰወ ምስለ መላእክት፤ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት፤ወአስተርአየ ዘበመልክዓ ራእዩ ለአቡሁ።

ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ሰብአ ሰገል ጋዳ ያመጽኡ/፪/
ወተወልደ ወተወልደ እምኅቡዕ ውስተ ክሡት/፪/

አመላለስ
ቂርቆስኒ ይቤ ለልየ ርኢኩ/፪/
ወአነ ሰማዕቱ ከመ ወልደ እግዚአብሔር/፬/

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ባለፈው ዓመት በሕገወጥ መንገድ "ጵጵስና  ተሹመናል በማለት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት በዛሬው ዕለት በዚሁ ሕገወጥ መንገድ በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ሕገወጥ ቤተ ክህነት መሥርተናል አሉ !



ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


+++


በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ካባ የደረበ አጀንዳ ይዘው የኢትዮጵቻ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተንበሳበሱ የሚገኙት በቀድሞ ስማቸው "አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ እና ግብረ አበሮቻቸው ሕገወጥ ተግባራቸውን በመቀጠል "መንበረ ጴጥሮስ" የተባለ ቀኖናዊ መሠረት የሌለው እና ሕገወጥ የሆነ ቤተ ክህነት መሥርተናል ሲሉ ስትራቴጂክ አጋሮቻቸው በሆኑ የሚዲያ ተቋማት አማካይነት በሰጧቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል።

 
በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል በሚል ሀሰተኛ ሽፋን ይህን እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ነውጠኛ መነኮሳት በመንግስት አደራዳሪነት ችግሩ ተፈትቷል ከተባለ በኋላ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነቱን የጣሰ እና በሚዲያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት በሚጥሩ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ማሳያ ነው።

ልክ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገኸጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመፈፀም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ በሚል "አብዮታዊ ዴሞክራሲን" እናት ፍልስፍና አድርጎ ተመሠረተ የተባለው የመነኮሳት ስብስብ በአሁኑ ወቅትም ከ5 በማይበልጡ የቀድሞ መነኮሳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የውክልና እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

"ለትግራይና ለአማራ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ተፈቅዷል" በማለት ሀሰተኛ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ያልተደረገን ነገር ማስተላለፋቸው ሳያንስ "ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ" እንዳትገዙ በማለት ጭምር ሕዝብን በሕዝብ ለማነሳሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የጦርነት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ።


ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እርሱም እሺ ብሎ ንስሐቸውን ከተቀበለ በኋላ ሲፈታ ለሊቀጳጳስ ይነግርላቸዋል።በእነርሱ ሥርዓት ጳጳሱ ንስሐ ወይም ምሕረት የሚገባው ኃጢአት ሆኖ ካገኘው ሰውየው ቢሞትም ጸሎተ ንስሐ ደግሞ ሥርየት ይሰጠዋል። የማይገባው ከሆነ ግን ዝም ብሎ ይተወዋል። በዚህ ጊዜም ጳጳሱ ከሰማ በኋላ ምሕረት የሚገባው አይደለምና ጸሎተ ንስሐ ሳይደግምለት እንደ ቀረ ታሪኩ ይናገራል። በርግጥም ቤተ ክርስቲያን ላይ እንደሚደረግ ዐመፅ እና ክህነት ላይ እንደሚፈጸም በደል ንስሐ እንኳ የሌለው ኃጢአት ሊኖር የሚችል አይመስለኝም።
         በእኛ ቤት ግን ክህነት በይፋ መቀለጃ ከሆነ የሰነባበተ ይመስላል።ዛሬ ይህችን ክታብ ያመጣሁትም የአምናውን የለየለት ከፋፋይነት ጥር 14ን በማሰብ ነው።ችግሩ የተፈታ ቢመስልም እነሆ በሁለት አቅጣጫ ጥፋቱ እንደ ቀጠለ ነውና። አንደኛው:-ይቅርታ ሳይጠይቁ በቀሩት ስድስቱ ተሹመናል ባዮች እና ቆይቶም አክሱም ላይ በተፈጸመው ሕገወጥ ሢመት ቤተ ክርስቲያን አሁንም እዚያው ልዩነት ውስጥ አለች።

    በእርግጥ ይህ ሁሉ የሆነው እና እየሆነም ያለው:-  እግዚአብሔርም አሳልፎ የሰጠን በተከማቸ በደላችን ሊሆን ይችላል።ስለዚህ የሚያዋጣን በእምነት፥ በሥርዓት እና በምግባርም ከልብ በመመለስ ሐዋርያዊ መሠረታችንን ጠብቀን መጓዝ ብቻ ነው። ካለበለዚያ ከዚህም የከፋ ሊገጥመን ይችላል።

     “የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።” /1ኛ ቆሮንቶስ 3፥10/ እንዳለ ቅዱሱ ሐዋርያ  አሁንም ለምናደርገው ሁሉ ልንጠነቀቅ ይገባል።
“እያንደ‍ኣንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።”፩ኛ:ቆሮ:፫፥፲።
በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ፤

ስለ ሩሲያ ኦርቶዶክስ ካሉኝ ውስን ምንባባት መካከል በአንዱ መጽሐፍ ላይ ያነበብሁት እጅግ አስገርሞኛል።

ቦልሸቢኮች እምነትን ይልቁንም ክርስትናን ከሩሲያ ምድር ለማጥፋት ከነደፏቸው ስልቶች መካከል አንዱ ከጳጳሳት መካከል መርጦ "ሕያዋ ቤተ ክርስቲያን" (The Living Church) የሚል የተሐድሶ ቡድን በማቋቋም እርስ በእርስ በማማታት አዳክሞ ጥፋቷን ማፋጠን ነበር። ታዲይ ይህን የተሐድሶ ቡድን የተቀላቀሉ አንድ ጳጳስ ብዙ የጥፋት ተግባራትን ሲፈጽሙ ከቆዩ በኋላ እርሳቸውም ታስረው መሰቃየት ይጀምራሉ። እኒህ ጳጳስ በአንደኛው የማሰቃያ ካምፕ ውስጥ እያሉ ሊሞቱ ሲያጣጥሩ ከእውነተኞቹ አባቶች አንዱ የነበሩት አባ አርሳንዮስ (Father Arseny) በዚያ የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ነበሩ።ታዲያ እኒያ ተሐድሶን የተቀላቀሉ ጳጳስ በቤተ ክርስቲያናቸው ላይ በፈጸሙት ጥፋት ተጸጽተው ንስሐ ለመግባት አባ አርሳኒን ይጠይቃሉ። አባ አርሳኒ ግን በሁለት ምክንያቶች ንስሐቸውን አልቀበልም አሉ። ዋናው ምክንያታቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የተነሣ ሰው ዐመፃው በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለ ሆነ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር “መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ኃጢአቱ አይሰርይም፤”ስለሚል ንስሐውን ልቀበል አልችልም የሚል ነበር።በዚያውም ላይ ምንም ቢሆን ሊቀ ጵጵስናውን የተሾመው ከመሳቱ በፊት በትክክለኛው መንገድ ስለ ነበረ ንስሐውንም ከተቀበለ ሊቀበለው የሚገባው ጳጳስ መሆን አለበት በሚል ነበር። ጳጳሱ ግን “በዚያ እስር ቤት ጳጳስ ስለ ሌለ ንስሐዬን ተቀብለህ ከእስር ስትፈታ ለጳጳስ ንገርልኝ እና ሥርየት አልሰጠውም ካለ እርሱ ይበል እንጂ አንተ ቀድመህ አትከልክለኝ፤”ይሉታል።
እንኳን አደረሳችሁ!

☞ጥር17 ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ፥ ለአገልግሎት መጠራቱ ይታሰባል! (ሐዋ. ፱/9)

=>የቅዱስ ዻውሎስ የክብር ስሞች በጥቂቱ:-

1.#ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4. #ብርሃነ_ዓለም
5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6. #የአሕዛብ_መምሕር
7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8. #አእኳቲ (በምስጋና የተሞላ)
9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11. #መርስ (ወደብ)
12. #ዛኅን (ጸጥታ)
13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15. #ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ)
16. ጼው (ጨው) . . .


=>ጌታችን እግዚአብሔር ብርሃኑን ያብራልን!

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/21 09:39:03
Back to Top
HTML Embed Code: