Telegram Web Link
Audio
አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን 
                                                  
Size:- 60.3MB
Length:-43:55
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
​​​​ጾመገሀድ
በየኔታ ዘለዓለም ሐዲስ


ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው።

እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ #ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።

በሌላም በኩል #ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡

ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡

ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ በማለት ይገልጸዋል፡፡

ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የመሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው።

በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡

ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡

በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሐም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳፁ አንዳስቀመጠው "ስለ ፆም ክርክር በተነሳ ጊዜ ሁሌም ቢሆን ለፆም አድሉ "

"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡

የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)
Audio
ጥምቀተ ባሕር 
                                                  
Size:- 13.6MB
Length:-59:12
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ዋዜማ ዘጥምቀት 'ጥር ፲'


ዋዜማ
ሃሌ ሉያ
ሐዳፌ ነፍስ ለጻድቃን ወተስፋ ቅቡጻን፤ ክርስቶስ አስተርአየ ውስተ ዓለም፤ እምድንግል ተወልደ ክሡተ ኮነ፤ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ፤ ከዊኖ ሰብአ፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ምልጣን
እምድንግል ተወልደ ክሡተ ኮነ፤ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ፤ ከዊኖ ሰብአ በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ ከዊኖ ሰብአ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
መዝ: ፳፫
በዮርዳኖስ ተጠምቀ ፈጺሞ ሕገ ወአስተርአየ ገሃደ፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

እግዚአብሔር ነግሥ
መዝ: ፺፪
አስተርእዮ ኮነ ዘክርስቶስ ስነ መለኮት፤ ከመ ርግብ ውስተ ምጥማቃት፤ እንዘ ይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር።

ይትባረክ
ጸሎተ ፫ቱ ደቂቅ: ፱
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገጹ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።

፫ት
አርአየነ ፈቃዶ በከመ ሥምረቱ ለአምላክነ፤ ወረደ ወተወልደ እምብእሲት፤ ወአንሶሰወ ዲበ ምድር፤ ወአስተርአየ ከመ ሰብእ፤ በበህቅ ልህቀ፤ በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ሰላም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
በሰላም አስተርአየ ወልደ አምላክ ፍጹም፤ ወተወልደ በሀገረ ዳዊት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይቤዝወነ፤ ወልደ አምላክ ፍጹም አስተርአየ።

ክብር ይእቲ
ኲሎሙ ማኅበረ መላእክቲሁ፤ ይሴብሑ ወይዜምሩ ለዘበሥጋ ሰብእ አስተርአየ፤ ንዑ ንስግድ ሎቱ ሃሌ ሉያ።

ዝማሬ
ኅብስተ ሰማያዌ ወጽዋዓኒ ዘእማየ ሕይወት፤ ጠዓሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ።

ዕጣነ ሞገር
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ፤ ወሀበነ ማየ መንጽሔ ዚአነ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት፤ በፍሥሐ ወበሰላም።

ምልጣን
በፍሥሐ ወበሰላም ወረደ ወልድ እምሰማያት፤ ውስተ ምጥማቃት።

ወረብ ዘማዕከለ ባሕር
'በፍሥሐ'/፪/ ወበሰላም/፪/
ወረደ ወልድ ውስተ ምጥማቃት/፬/

     🌺መልካም በዓል🌺

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት
💧💧💧💧💧💧💧💦💦💦💦💦
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤ ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ፤ በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ፤ ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ፤ ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ።

ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤ እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤ እለ አሐዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤ እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ይቀድስ ማያተ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ጸጋ ወጽድቅሰ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ።

ነግሥ
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤ መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ።

ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።

ወረብ
ርእዩከ 'እግዚኦ'/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/
'ደንገፁ'/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/

ትምህርተ ኅቡዓት
እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤ በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ ወማየ መንጽሔ ዚአነ።

ወረብ
'ወደሞ ክቡረ'/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/
ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/

አንገርጋሪ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤ እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።
አመላለስ፦
አማን በአማን መንክር ፤
መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።

ወረብ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/
'ወለደነ ዳግመ'/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/

እስመ ለዓለም
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።


አመላለስ፦
መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤
ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።(4)
ወረብ
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/

ዕዝል
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ወተገሠ በሥጋ፤ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ ወረደ ዲበ ምድር፤ ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ምልጣን
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ።

አመላለስ
ወገብረ መንጦላዕተ/፪/
ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፪/

አቡን
በ፭: እስመ ሰምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ ዘኪያሁ ሠምርኩ ይቤ፤ ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ።


ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ምልጣን
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ወረብ
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር።
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
2024/09/21 11:36:17
Back to Top
HTML Embed Code: