Telegram Web Link

ስርዓተ ደመራ ዘመስቀል
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ከሁሉ አስቀድሞ ጸሎት ከተደረሰ በኃላ ዲያቆን መስቀሉን ይዞ ምስባክ ይስበክ

ይ.ዲ

ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፣
ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅሥት፣
ወይድኅኑ ፍቁራኒከ።
መዝ ፶፱፤፬

ወንጌል ከተነበበ በኃላ

እስመ ለዓለም
መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ እምኲሉሰ ፀሐየ አርአየ፤ መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ።


አንገርጋሪ
🕊🕊🕊
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ፤ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየ፤አበርሕ በመስቀልየ

🌼🌼🌼🌼🌼
ስርአተ ምልጣን፦
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
መሪ-ሃሌ ሉያ
ተመሪ-ሃሌ ሉያ
መሪ- ይቤሎሙ ኢየሱስ
ተመሪ- ይቤሎሙ ኢየሱስ
መሪ- ለአይሁድ
ተመሪ-ለአይሁድ
መሪ- እመኑ ብየ
ተመሪ- እመኑ ብየ
መሪ- ወእመኑ በአቡየ
ተመሪ- ወእመኑ በአቡየ
መሪ- ዮምሰ ለእሊአየ
ተመሪ- ዮምሰ ለእሊአየ
መሪ- አበርሕ በመስቀልየ
ተመሪ- አበርሕ በመስቀልየ

ከዚህ በኃላ "ሃሌ ሉያ" ብሎ ዝማሜውን ይዘምማሉ፤ ንሺው ጋር በመሄድ ለሁለት ረዘም ባለ ዜማ ይመራራሉ

መሪ- እመኑ ብየ
ተመሪ- እመኑ ብየ
መሪ- ወእመኑ በአቡየ
ተመሪ- ወእመኑ በአቡየ
መሪ- ዮምሰ ለእሊአየ
ተመሪ- ዮምሰ ለእ

በዝማሜ ሁሉም - አበርሕ በመስቀልየ

ሁለተኛ ሰው ከንሺው ጀምሮ ያነሳል

እመኑ ብየ፤ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየ

በዝማሜ ሁሉም - አበርሕ በመስቀልየ

ሶስተኛ ሰው አሁንም እንዲሁ ንሺውን ያነሳል

በመቀጠል  "ዮምሰ ለእሊአየ አበርሕ በመስቀልየ "  የሚለው በዝማሜ ተብሎ ከጽናጽል ና ከከበሮ ጋር ይቀርባል

አባባሉም፦
በጽፋት የከበሮ አመታት ፩ ጊዜ

ዮምሰ ለእሊአየ አበርሕ በመስቀልየ

ከዚያ በቁርቋሮ እና በጽፋት

ዮምሰ ለእሊአየ....     ፩ዴ በቁርቋሮ
ዮምሰ ለእሊአየ....    ፩ዴ በጽፋት

አበርሕ በመስቀልየ....     ፩ዴ በቁርቋሮ
አበርሕ በመስቀልየ....    ፩ዴ በጽፋት

አመላለስ አባባል ፦

ዮምሰ ለእሊአየ /፪ ጊዜ/
አበርሕ በመስቀልየ አበርሕ በመስቀልየ /፪ ጊዜ/

አመላለሱ ተብሎ እንዳለቀ በጽፋት የከበሮ አመታት

እመኑ ብየ፤ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየአበርሕ በመስቀልየ

ዝግ አባባል

እመኑ ብየ እመኑ ብየ
ወእመኑ በአቡየ እመኑ ብየ

ዮምሰ ለእሊአየ አበርሕ በመስቀልየ

ከዚ በኃላ በጽፋት ፦
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ፤ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየ፤አበርሕ በመስቀልየ

ወረቡ እዚጋ ይባላል፦
"ይቤሎሙ ኢየሱስ"/፪/ ለአይሁድ/፪/
እመኑ ብየ ወእመኑ በአቡየ አበርሕ በመስቀልየ ለእሊአየ/፪/

በጽፋት ይሉትና ወረቡን አንስተው ስርዓቱን ይፈጽማሉ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
EOTC ቤተ መጻሕፍት pinned « ስርዓተ ደመራ ዘመስቀል 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ከሁሉ አስቀድሞ ጸሎት ከተደረሰ በኃላ ዲያቆን መስቀሉን ይዞ ምስባክ ይስበክ ይ.ዲ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፣ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅሥት፣ ወይድኅኑ ፍቁራኒከ። መዝ ፶፱፤፬ ወንጌል ከተነበበ በኃላ እስመ ለዓለም መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ እምኲሉሰ ፀሐየ አርአየ፤ መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ…»
​​#የደመራው_ምሥጢር

በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክትነት ነው፡፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ በታዘዘ ጊዜ የሞርያን ተራራ የመረጠው እግዚአብሔር በተራራው ላይ ካሳየው ብርሃን የተነሣ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ መስቀልም የድኅነታችን ምልክቶች ናቸው፡፡ የአሮንና የሙሴ በትሮች፣ የይስሐቅ ቤዛ የሚኾን በግ የተገኘባት ዕፀ ሳቤቅ ደግሞ የእመቤታችንና የመስቀል ምልክቶች ነበሩ፡፡ ወደ ፊት የምንወርሰው መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነው፤ እርሱን ደግሞ ያገኘነው ከመስቀል ላይ ነው፡፡

ጥንተ ጠላት ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ቅዱስ መስቀሉን አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡ በመሠረቱ ለሰይጣን ምሥጢሩ ስለማይገባው ነው እንጂ የመስቀሉ ትክክለኛ መቀበሪያ ሥፍራ የምእመናን ልቡና ነው፡፡ ቀራንዮ ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡

ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡ ይህች ሴት ቤቷ በሀብት፣ በንብረት ሞልቶ በነበረበት ጊዜና በገረድ፣ በደንገጡር በምትንቀሳቀስበት ወቅት ምን እንደ ሠራች አልተመዘገበላትም ነበር፤ ከክብሯ ወርዳ በተጣለችበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ለሚፈልገው ሥራ ምቹ ኾና ተገኘች፡፡ እርሷ በተጣለችበት ባዕድ አገር ውስጥ ኾና የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች፡፡

መስቀልና ደመራ እንዲህ ነበር የተገናኙት፡፡ ደመራው ለመስቀሉ መገኘት፣ መስቀሉም ለደመራው መሠራት ምክንያት ናቸው፡፡ በዚህ አንጻር መለኮትና ትስብእት በአንድነት መደመራቸው መስቀሉ እንዲሠራ ምክንያት ኾነዋል፡፡ አምላካችን ሥጋ ለብሶ ‹ክርስቶስ› በሚል የተዋሕዶ ስም ሲጠራ ለመከራ መዘጋጀቱን እንረዳለን፡፡ መስቀሉ የሥጋ ብቻ ነበረ፤ አሁን ግን መለኮትም በሥጋ ባሕርይ የመስቀሉ ተካፋይ ኾነ፡፡ ይህም የደመራው ውጤት ነው፡፡ መለኮት አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን መስቀል የተሸከመ ሥጋን ሲዋሐድ መስቀሉን አስወግዶ አልነበረም፡፡ ይኸው በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከምነው መስቀል ነው፡፡ ሥጋ ዓቅም አጥቶ መስቀሉን ከትከሻው ላይ ሳያወርድ ለዘመናት የተጓዘውን ጕዞ መለኮት ኀይል ኾኖት ድካሙን ሳይለቅ ኀያል፤ ኀይሉን ሳይለቅ ደካማ ኾነ፡፡ መስቀል ትርጕሙ መከራ ቢኾነም ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያመጣውና ሰው ሲያመጣው ግን ትርጕሙ ይለያያል፤ ሰው ያመጣው መስቀል ኹላችንን ለመከራ፣ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር መስቀል ግን መከራነቱ ለሰይጣን እንጂ ለእኛ ሕይወታችን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል ብሂል ዕፀ ሕይወት ብሂል፤ መስቀል ማለት የሕይወት ዛፍ ማለት ነው›› በማለት የመስቀልን ትርጕም ነግሮናል፡፡

አዳም ከገነት ሲወጣ በመላእክት እንዲጠበቅ የተደረገው የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ኹላችንም እንደ ተጎዳን በዕፀ ሕይወቱም ተጠቃሚዎች ኾነናል፤ አስቀድመን በአዳም መከራ እንደ ተባበርን አሁን ደግሞ በደስታው እንተባበራለን፡፡ ሞትም ሕይወትም አንድ አድርጎናል፡፡ የክርስቶስ መስቀል ኹሉንም በሕይወት አስተባብሯልና፡፡

በአንጻሩ ሰውና ዲያብሎስን ለያይቷል፡፡ የኀጢአት ቁራኝነትን አጥፍቷል፡፡ ጌታችን በማኅፀን ሲፀነስ ጀምሮ የእኛን መስቀል መሸከም ሲጀምር የእርሱ የኾነውን ለእኛ ስለ ሰጠን ከሰይጣን ጋር መለያየታችን በመስቀሉ ተረጋግጧል፡፡ የአምላካችን መስቀል ምልክቱ ደመራ መኾኑ የእኛን ወደ እርሱ መሰብሰብና የጠላታችንን መበተን የሚያረግጥልን ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወብየ ካልዓትኒ አባግዕ እለ ኢኮና እምዝንቱ ዐፀድ ወኪያሆንሂ ሀለወኒ አምጽኦን ዝየ፤ ከዚህ በረት ያልኾኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ላመጣቸው ይገባኛል›› በማለት ሊሰበስበን እንደ መጣ ነግሮናል /ዮሐ.፲፥፲፮/፡፡ መስቀሉ ፍጥረት አንድ ደመራ ኾኖ የተሠራበት ስለ ኾነ በደመራ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ኾነ፡፡
መስቀሉ አንድ ደመራ ያደረጋቸው ፍጥረታት

፩. ነቢያትና ሐዋርያት

ነቢያት የሚባሉት ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉ አባቶች ሲኾኑ፣ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የወንጌልን የምሥራች እንዲነግሩ የተላኩ አባቶች ደግሞ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የኾነ ነቢይ የለም እንጂ ነቢይ የኾነ ሐዋርያ አለ፡፡ ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣ በክብር እና በግብር የማይገናኙ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መንፈሰ ረድኤት የተሰጣቸው ነቢያት ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ ልደት ለማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ ሐዋርያት ግን ኹሉንም አንድ አድርገው ይዘዋል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› በማለት አጕልቶ የተናገረው /ዮሐ.፲፥፲፰/፡፡ ነቢያት በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን መንግሥት በመፈለግ ብዙ ደክመዋል፡፡

ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት፣ ሐዋርያትን በበጋ ገበሬ ይመስሏቸዋል፡፡ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ፣ ታቹ ውሃ ኾኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባም ሚስቱ ጨምቃ ያቆየችለትን ጐመን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፡፡ ነቢያትም በዚህ ዓለም በጣዖት አምላኪ ነገሥታት፣ በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ኖረው ሲሞቱም ሲዖል ይገባሉ እንጂ ገነትን አይወርሱም ነበር፡፡ የበጋ ገበሬ በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ከቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ ጠላው በማቶት፣ ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ሐዋርያትም ልጅነትን አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፤ በሔዱበት ኹሉ ተአምራትን እንዲያደርጉ፣ ልጅነትንም እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡
ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡

፪. ሙታንና ሕያዋን

አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡

፫. ጻድቃንና ኀጥአን

የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡

የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡

ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ምስባክ_ዘበዓለ_መስቀል

"ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም
ንበውእ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር
ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ"

ትርጕም:- "በበረሃ ዛፍ ውስጥ አገኘነው
እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ቤቶች እንገባለን
የጌታችን እግር በቆመበት ቦታም እንሰግዳለን።"
መዝ 131:6፡፡

#በቤተ_ክርስቲያናችን_አስተምህሮ መሠረት ከመስከረም 17 ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ድረስ ያለው ጊዜ መስቀል በመባል ይታወቃል እነዚህ ቀናት ተለይተዉ ለመስቀል መታሰቢያ የተሰጡ ይሁኑ እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን መስቀል ጭራሽ ሳይታሰብበት የሚውልበት ቀንና ሰዓት የለም፣ አይኖርምም፣ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሁም በምእመናን ሕይወት ውስጥ መስቀል የሌለበት እንቅስቃሴ የለም፣አንገታችን ላይ የተሸከምነው የጌታ መስቀል መከራውንና ስቃዩን እያስታወስን ለመኖርና የስሙ ተሸካሚዎች ምርጥ እቃ መሆናችንን ለማረጋገጥ ነው (ሐዋ 9:15)።

በተለይም ሰሞኑን የመስቀል በዐል ንግሥት እሌኒ ደመራውን ያስደመረችው(መስከረም 16) እና ቁፋሮ ያስጀመረችው (መስከረም 17) መነሻ በማድረግ በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች በድምቀት ይከበራል።

#በኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በዓል ሲከበር ፦
------ ጸሎተ ምኅላ ይደርሳል( ምቅናይ ፣መሀረነ አብ .....)
------- ልዩ ልዩ ያሬዳዊ ፀዋትወ ዜማ
--------ምስባክና ወንጌል ይነበባል
ምስባክ ማለት ልበ አምላክ ነቢዩ ንጉሠ እስራኤል ዳዊት ከተናገረው የሚወጡ ሦስት መስመሮችን የያዘ ማለት ነው፡፣ዛሬና ነገ የሚሰበከው ምስባክ መግቢያችን ላይ የጠቀስነው ሲሆን ትርጓሜውን እንመልከተው።

-- ➊ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም (በበረሀ ዛፍ ውስጥ አገኘነው)፦

መጀመሪያ አዳም ከበደለ በኋላ ቅጠል ታጥቆ፣በገነት ዛፎች መካከል መሸሸጉን ልብ ይሏል (ዘፍ 3:7-9) ። ጫካ ውስጥ የተደበቀውን ለማውጣት ጫካ መግባት ግድ ነውና ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋዕለ ሥጋዌው ይህንን ሁኔታ ተከትሎታል።

1 . በበረት ሲወለድ ቅጠል ለብሷል ፣ ከደነቶ እሙ ቆፅለ በለሶን ( እናቱ የበለሶን ቅጠል አለበሰችው እንዳለ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ)፣ ሉቃ2:7፡፡

2. በግብፅ በረሀ በስደት አገኘነው፣ ማቴ 2:13፡፡

3. ከተጠመቀ በኋላ በቆሮንቶስ አገኘነው፣ማቴ 4:1፡፡

4. ቀን ቀን በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ውሎ ማታ ማታ በደብረ ዘይት ሲያድር ወይራ ዛፍ ሥር አገኘነው ፣ሉቃ 21:37፡፡

5. በጸሎተ ሐሙስ ማታ አትክልት በበዛበት በጌቴሴማኒ "ተከዘት ነፍስየ እስከለሞት" (ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች) እያለ ሲጸልይ አገኘነው፣ ማቴ 26:37፡፡

6. መጨረሻ ላይ ከሰባት ዕፀው በተዘጋጀ መሰቀል ላይ ተሰቅሎ አገኘነው፣ አዳምን እየጠራ የአዳምን ጩኸት እየጮኸ አገኘነው፣ከተሸሸገበት አወጣው፣ከተቀበረበት አነሣው፣አዳምን የገደለውን ከይሲ ዲያብሎስን በመስቀል ራስ ራሱን ቀጥቅጦ ገደለው፣መዝ 67:21

—----➋ ንበውእ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር
(እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ቤቶች እንገባለን)፦

በመስቀል ጠላት ጠፋ፣ሞታችን ተገደለ፣ ሕይወታችን ተመለሰ፣ መስቀል ሥር እንደገና ተፈጠርን ታደስን፣ሐዲስ ልደት ረቂቅ መንፈስ ቅዱስ ተሰጠን፣ከጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ተጠራን፣ እርሱንም "አባ አባት" ብለን መጥራት ቻልን። ልጆች ከሆንን ደግሞ ወራሾች ነን፣ ወራሾች ስለሆንን እርሱ ወዳዘጋጀልን ቤቶች እንገባ ዘንድ ተፈቀደልን፣ እርሱ በበረሀ ተንከራቶ ፣ ቤት መጠለያ፣ሀብት ንብረት ሳይኖረው በደብረ ዘይት ዋሻ ውስጥ እያደረ ፣ በመስቀል ራቁቱን ተሰቅሎ ፣ ተሰደን ጠፍተን፣ በኃጢአትና በደል ጫካ ውስጥ ተሸሽገን የነበርነውን እኛን "ወደ እኔ ኑ!" (ማቴ 11:29) ብሎ ጠርቶ ወደቤቱ አስገባን (ዮሐ 14:1-5) ። ይህንን ሲያይ ወደ
እግዚአብሔር ቤት እንገባለን አለ ።

-------➌ ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ (የጌታችን እግር በቆመበት ቦታም እንሰግዳለን)፦

ለመስቀል ስንሰግድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያደረገውን ታላቅ ሥራ እያሰብን ነው፣መከራውን ስቃዩንና ሞቱን እያዘከርን ነው፣መስቀል ሥር ነው መገናኛችን ፣ መስቀል ሥር ነው የክርስትናችን ጽዋ የተደቀነው፣መስቀል ሥር ነው የእንደገና መፈጠራችን ታሪክ በደም ተጽፎ የረቀቀውና የጸደቀው ፤ መስቀል ሥር ነው አሁን ያለችው ቤተ ክርስቲያን (3ኛዋ ቤተ መቅደስ) የተመሠረተችው፣፣ደሙ የሚንጠባጠበው፣ መላእክት በብርሃን ጽዋ ደሙን የሚቀዱት መስቀል ሥር ነው፣ ዲያብሎስ የጌታችንን ፈጣሪነት አምኖ ሥልጣኑን ያስረከበው መስቀል ሥር ነው።ድንግል ማርያምን በእናትነት የተቀበልናት እዚሁ መስቀል ሥር ነው።
ነቢያት እስከ መስቀል ድረስ ትንቢት ተናገሩ፣ ሐዋርያት ይህንን መስቀል ተሸክመው በዓለም ዞሩ አስተማሩ፣ሊቃውንቱም መስቀሉን ተረጎሙ አመሰጠሩ፣ ሰማዕታት ራሳቸውን ክደው ይህን መስቀል እያዩ ተገደሉ፣ ዛሬም የእኛም የክርስቲያኖች መገኛ ስፍራ ይህ ነው። ይህን የመስቀል በዓል ስናከብር ከመላእክት ጋር ፣ከነቢያት ጋር፣ከሐዋርያት ጋር፣ ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር ያለንን አንድነት እንሰብካለን ይህችውም መስቀል ሥር የተተከለችው ቤተ ክርስቲያን ናት።

መስቀል ሌሎች እንደሚሉት እንጨት ሳይሆን ሰማያዊ፣መለኮታዊ ፍቅር የተገለጠበት የአንድነት አርማ መገለጫ ነው፣ሠርግ ነው፣ዝማሬ ነው፣ መሥዋዕት ነው፣ክርስቶስነት በሥጋ መከራ የተገለጠበት፣ በግዕ ሆኖ የታረደበት፣ሊቀ ካህናት ሆኖ የዘለዓለም መሥዋዕት ያቀረበበት፣ በአምላክነቱ ደግሞ ራሱ (ራሱን)ያቀረበውን መሥዋዕት የተቀበለበት ድንቅ ምሥጢር የተገለጠበት ነው!!!!!! ለዚህ መስቀል እንሰግዳለን፣ የጌታ የከበሩ እግሮች በደም አጊጠው ተቸንክረውበታልና .............
ይህንን መስቀል ዛሬም እንደ አይሁዳውያን ሊቀብሩት ጥራጊ ወይም ቆሻሻ ሊደፉበት ፤ የማይረባ ሀሳበ ኑፋቄ ሊጭኑበት የሚፈልጉ አሉ

ነገር ግን መስቀሉ ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ ስላልሆነ በፍጹም አይችሉትም!!!!!

"ዝንቱ ውእቱ መስቀል ዘቦቱ ፀጋማይ የማናየ ኮነ
ወታሕታይ ከመ ዘላዕላይ
ወደኃራይ ከመ ዘቀዳማይ
ወንዑስ ከመ ዘዐቢይ .........."

የመስቀሉ ኃይል ከሁላችን ጋራ ይሁን!!!

የመስቀሉ ኃይል ጠላቶቻችን ሠራዊተ አጋንንትን ይቀጥቅጥልን!
ሀገራችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይታደግልን!
ጠላቶቿን ከእግሯ በታች ይጣልልን!

ሠናይ በዓለ መስቀል

አሜን!


መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው መካከል የተወሰደ ፦

" እባካችሁ ንስሐ ገብተን በመስቀሉ ቃል ተቀራርበንና ተስማምተን ይቅር ተባብለን በአንድነት በእኩልነት በሰላምና በፍቅር እንኑር።

በምድራችን ፍትሕ ርትዕ ይንገሥ፥ ሰብአዊ መብት ይከበር፥ የተበደለ ይካስ ፥ እግዚአብሔር ይደመጥ መስቀል ማክበር ማለት ይህ ነው፡፡

ይህ ሲሆን ሀገር በመንፈሳዊና በቊሳዊ በረከት ትባረካለች፤ ትለማለችም፤ ታድግማለች፤ እግዚአብሔርም በተግባሩ ወይም በፍጥረቱ ይደሰታል፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

Grap. Tikvah Family

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
በዕለተ ምጽአት ጌታችን በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት ከአእላፋት መላእክቱ ጋር ሲመጣ የሚሆነውን ሲናገር :-

"የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል" ብሎአል:: ማቴ. 24:30

የሰው ልጅ የተባለው መድኃኔዓለም ክርስቶስ በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ከመምጣቱ በፊት ፣ የምድር ወገኖች ዋይታ ከመሰማቱ በፊት አንድ ነገር ይከሰታል?

"የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል!"

ይህ የሰው ልጅ ምልክት ምንድር ነው?

"ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው" ተብሎ የተነገረለት ቅዱስ መስቀሉ ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን የወንጌል ክፍል ሲተረጉም ከጌታችን መምጣት ቀድሞ በሰማይ ስለሚታየው የሰው ልጅ ምልክት (መስቀል) እንዲህ ይላል:-

"መስቀል ከፀሐይ ይልቅ ብሩሕ ይሆናል:: ፀሐይም ትጨልማለች ብርሃንዋንም ትሰውራለች:: ከዚያም በተለምዶ በማትታይበት ሰዓት ትታያለች:: ይህም የአይሁድ ጠማማነት ይቆም ዘንድ ነው" (Homily on Matthew 24)

ጌታችን በምድር ላይ ከተመላለሰ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው መስቀል ዳግም ሊፈርድ ሲመጣ ግን መስቀሉ ሐዋርያ ሆኖ ቀድሞ በሰማይ ላይ ያበራል::

"መስቀል አብርሓ በከዋክብት አሰርገወ ሰማየ"
"መስቀል በከዋክብት [ዘንድ] አበራ ሰማይንም አስጌጠ" ብሎ ከቅዱስ ያሬድ ጋር መዘመር ያን ጊዜ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2015 ዓ.ም. ተጻፈ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴየሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው ስሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል ሰሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
አመታዊ እቅድ.docx 2016.docx
18.3 KB
shere አድርጉት ለሁላችንም ሚጠቅም እና ለራሳችን ልናደርገው ሚገባ አመታዊ እቅድ ነው
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
Audio
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ 
                                                  
Size:- 34.2MB
Length:-1:38:04
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ጸሎተኛው ፣ ደጉ ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን  የምናሳውቅ ይሆናል።

  የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን አሜን!!!
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
+ የመስቀሉ ደም +

መስቀል ደም አለው ወይ? ከእንጨት የተሠራ ነገር ቢወጉት ይፋፋቅ ይሆናል እንጂ አይደማም::

ስለ ክርስቶስ መስቀል ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ግን "በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ" አለ:: (ቆላ. 1:20)
"ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ"

የመስቀሉ ደም የሚለው ቃል መስቀሉ ደምቶአል ለማለት አይደለም:: ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ጠዋት ሦስት ሰዓት ሊቶስጥራ ላይ ጌታን ሲያሸክሙት የመስቀሉ ቀለም የእንጨት ብቻ ነበረ:: ክርስቶስ መስቀሉን ተሸክሞ ለሦስት ሰዓታት ከወጣና ለሦስት ሰዓት ተሰቅሎ ነፍሱን ከሠጠ በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀሉ ሲያወርዱት የመስቀሉ መልክ የእንጨት አልነበረም:: በጥሩ ባለሙያ ቀይ ቀለም የተቀባ እስኪመስል ድረስ መስቀሉ በክርስቶስ ደም ታጥቦ ነበር:: እሾህ ከደፋው ራሱ ፣ ከተቸነከሩት እጆቹ ፣ ከተገረፈው ጀርባው ፣ ሚስማር ከያዛቸው እግሮቹ እንደ ውኃ የፈሰሰው ደም በመስቀሉ ላይ ፈስሶ ነበር::

መፍሰስን ለመግለፅ በግእዝ ሁለት ቃላት አሉ "ክዒው" እና "ውኂዝ" የሚሉ:: ወደ አማርኛ ሲመለሱ ሁለቱም መፍሰስ ቢሆኑም ግን ልዩነት አላቸው:: አንድ ሰው በብርጭቆ ውኃ ቢያፈስስ ውኃው ፈሰሰ ይባላል:: የወንዝ ውኃ ሲፈስስም ፈሰሰ ይባላል:: ግእዙ ግን ከአንድ ብርጭቆ ለሚፈስሰው ውኃ "ተክዕወ" ሲል እንደ ወንዝ ላለው ብዙ ፈሳሽ ደግሞ "ውኅዘ" ብሎ ይለየዋል::

ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ብለው አንገታቸው ተሰይፎ እንደሞቱ ሲናገር "ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት" "ስለ መንግሥተ ሰማያት ደማቸውን አፈሰሱ" ይላል::

ይኸው አባት ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ክርስቶስ ደም መፍሰስ ሲናገር ግን "በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሃይምናን" "በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ያመኑትን አነጻቸው" ብሎአል:: የጌታችንን ደም መፍሰስ ለወንዝ ፈሳሽ በሚነገርበት ቃል ውኂዝ የተባለው ከጌታችን የፈሰሰው ደም ከመላው ሰውነቱ ስለነበረ ነው::

መስቀሉን ለዓመታት መፈለግ ፣ ማክበር ግድ የሆነውም መስቀሉ ዓለም በተገዛበት በከበረ ደም ስለተቀደሰ ነው:: (እስመ ተቀደሰ በደመ ክርስቶስ መድኅን)

ወዳጄ ሆይ በደም የታጠበ መስቀል ስታይ ምን ይሰማሃል? በደም የተቀደሰው የመስቀሉ ክብር አይታይህም? አዎ መስቀል ክቡር ነው::

የመስቀሉ ደም ሌላ የሚያሳየው ክብርም አለ:: እርሱም የእኔና የአንተን ክብር ነው:: ምክንያቱም ያ ሁሉ ደም የፈሰሰው ለእኔና ለአንተ ነው:: በሰዎች የመጠሪያ ስምህ ማን ነው? ማን ብለው ሲጠሩህ አቤት ትላለህ?

ቅዱስ ጳውሎስ ግን ለእኔም ለአንተም ስም አውጥቶልናል:: ጳውሎስ አንተን ለሰዎች ሲያስተውቅህ እንዲህ ብሎ ነው :-

"ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" 1ቆሮ.8:11
ወዳጄ የአንተ ክብር እዚህ ድረስ ነው:: አንተ ክርስቶስ የሞተልህ ወንድም ነህ:: አንቺ ክርስቶስ የሞተልሽ እኅት ነሽ::

ቅዱስ ጴጥሮስ ጨምሮበታል :-

"በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ" 1ኛ ጴጥ. 1:18-19 ቅዱስ ያሬድም "አኮ በወርቅ ኃላፊ ዘተሳየጠነ አላ በደሙ ክቡር ቤዘወነ" ብሎ ዘምሮታል::

የእኔና አንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው::
ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ" ብሎ ነበር:: (ማቴ.18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን?

ውድ ክፍያ ተከፍሎ ልብስ የተገዛለት ልጅ ልብሱን ስለተከፈለበት ዋጋ ሲል ተጠንቅቆ ይለብሰዋል:: በውድ የተገዛ ዕቃ የተሠጠው ሰው በጥንቃቄ ይጠቀምበታል:: የእኛ ሰውነት ግን የተገዛው በአምላካዊ ደም ነው:: እንደተከፈለልን እየኖርን ይሆን?

ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ዲቃላ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ "ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል" አሉ ይባላል::

የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም "ክርስቶስ የሞተልን ነን"
ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል::

"በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ"
1ኛ ቆሮ.6:19

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ዜና እረፍት

መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
*****************
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
*************************

ጸሎተኛው፣ደጉ፣ርህሩሁ፣ታጋሹና አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን

የብፁዕነታቸው የትምሕርት ሕይወት
ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኅንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ቦታው በዓታ ለማርያም በተባለው ቦታ 1934 ዓ.ም ተወለዱ።

ፊደልና ንባብና የቃል ትምሕርት በመማር ለግብረ ዲቁና የሚያበቃቸውን ትምሕርት ከየኔታ ክንፈ ገብርኤል በመማር ማዕረገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ዜማ ከየኔታ ተክለ ማርቆስ ማየ አንበሳ ገዳም ተንቤን፤ ቅኔ ከየኔታ ንጉሤ መነዌ ገዳም ተንቤን እንዲሁም ቅኔን ከየኔታ አክሊሉ ደበጋ ጎንደር ትርጓሜ መጻሕፍት፣ እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ማርያም ቀረፃ ማርያም ከምትባል ገዳም ፤ ቅኔና ትርጓሜ መጽሐፍት እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ልሣነ ወርቅ ጎጃም ፤ ቅኔ ከየኔታ ዲበኩሉ ጎጃም በሚገባ ከተማሩ በኋላ ለመምህርነት በቅተዋል፡፡

በተጨማሪም መዝገብ ቅዳን ከየኔታ ልዑል ቦረራ ሚካኤል ተምረዋል፡፡በወቅቱ የጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ የቅስናና የቁምስና ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡ብፁዕነታቸው በሊቀ ጵጵስና በአክሱም፣በምሥራቅ ሐረርጌና በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም አገልግለዋል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በዚ ቻናል ደስተኛ ኖት ???
Anonymous Poll
74%
ሀ' በጣም ደስተኛ ነኝ
26%
ለ'አይደለሁም ይሻሻል
Forwarded from Quality Button
🧿ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ያሉትን የteacher guid እና textbook እንድሁም shortnote ምትፈልጉ ተማርዎች ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ🧿
👇👇👇👇👇👇
ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብርን አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጠ።
ዘጋቢ መ/ር አቤል አሰፋ
(#EOTC TV ኢኦተቤ ቴቪ //መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም)
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++!
ብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 6 ሰዓት ይፈጸማል ሲሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገለጹ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) እንደገለጹት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ክቡር አስክሬን ነገ ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 9 ሰዓት ከሀሌሉያ ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም የሚመጣ ሲሆን ለሊቀ ጳጳስ በሚመጥን ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐት ሲፈታ አድሮ በማኅሌትና በቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎቱ የሚከናወን ይሆናል።
እሑድ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቅዳሴ በኃላ የብፁዕነታቸው ክቡር አስክሬን ወደ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚሄድ ሲሆን በዚያ አስፈላጊው መንፈሳዊ ሥርዓት ተከናውኖ ግብአተ መሬት እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል ዘመድ ወዳጆቻቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በመርሐ ግብሩ መሠረት ተገኝተው አባታችንን እንዲሸኙ ጥሪ ቀርቧል።
EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 12:32:38
Back to Top
HTML Embed Code: