Telegram Web Link
.   ነገረ ሃይማኖት ኮርስ ዛሬ ይጀምራል join በሉት👇👇👇
.         https://www.tg-me.com/fre_tewahdo
በዓለ ደብረ ታቦር

ክፍል አንድ


ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የምናከብረው የደብረ ታቦር በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት በመሆኑ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ (ማቴ .፲፯፡፩፣ ማር.፱፡፩፣ሉቃ.፱፡፳፰)፡፡

ደብረ ታቦር፡- ‹‹ደብረ ታቦር›› ደብር እና ታቦር ከሚባሉ ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ‹‹ደብር›› ማለት ተራራ ማለት ነው፤ ‹‹ታቦር›› ደግሞ በናዝሬት አካባቢ በሰማርያ አውራጃ በገሊላ የሚገኝ የረጅም ተራራ ስም ነው፡፡ የደብረ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ ፭፻፸፪ ሜትር ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” በማለት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪) ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ብርሃነ መለኮቱን በመግለጡ የነቢያት ትንቢት ተፈጽሟል፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሳራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነበር፡፡ (መሳ. ፬፥፮)፡፡ የዚህም ታሪክ ምሳሌነቱ ባርቅ የጌታችን ሲሳራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ነቢዩ ሳሙኤል ትንቢት ተናግሮበታል፡፡ ንጉሥ ሳኦልም ከሦስት ሰዎች ጋር ተገኝቶበታል (፩ኛ ሳሙ.፲፡፫)፡፡ ርእሰ አበው አብርሃምና ኖኅ በዚህ ተራራ ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ያዩ ሲሆን አባታችን ኖኅ ይህንን ተራራ ‹‹መካነ ብርሃን፤ የብርሃን ቦታ›› ብሎ ጠርቶታል፡፡
የሐዲስ ኪዳን ወንጌል ጸሓፊያን ግን ‹‹ረጅም ተራራ፣ ቅዱስ ተራራ›› በማለት ጠርተውታል፡፡ ሆኖም ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን እንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፣ በትውፊትም ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር እያለ በድጓው አስፍሮታል፡፡

በዚህ በዓል አምላክነት፣ ጌትነት፣ ንግሥና የባሕርይ ገንዘቡ መሆኑን፣ የድኅነታችን መሠረቱም የጌታችን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆን (የተዋሕዶ ምሥጢርን) የገለጸበት በዓል ነው፡፡ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር/ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፣ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ” (መዝ.፸፪፡፲፪) በማለት ትንቢት የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ ማእከለ ምድር በተባለች በቀራንዮ ሰው የሆነ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ቤዛነት ዓለሙን ሁሉ አድኗልና፡፡ ሆኖም ግን የጌታችን ነገረ ተዋሕዶ ምሥጢር በሥጋዊ ዕይታ ውስጥ ለሆኑት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል፡፡

ብርሃነ መለኮቱ የተገለጠበት ምሥጢር፡-

ሦስቱ ሐዋርያት በተራራው ሳሉ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልኩ በፊታቸው ተለወጠ፡፡ ይህ የብርሃነ መለኮቱ የመገለጥ የተዋሕዶ ምሥጢር እንጂ ውላጤ/መለወጥ/ አይደለም፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል፡፡(ሚል ፫፥፮)፡፡ ሦስት ክንድ ከስንዝር አካል ምሉዕ ብርሃን ሆኗል፡፡ ፊቱም እንደ ፀሐይ ብሩህ ሆነ፡፡ ልብሱም እንደ በረድ ጸዓዳ ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ነገረ ተዋሕዶን እንዲረዱ የተደረገ የተዋሕዶ ምሥጢር ነው፡፡ ሰውነቱን ባይክዱም አምላክነቱን ግን ተጠራጥረው ስለነበር እነር በሚያውቁት በባሕርየ ትስብዕቱ አምላክነቱን ከሰውነቱ አዋሕዶ ምሥጠረ ተዋሕዶን ገለጠላቸው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በ፴፪ ዓመት ከ፮ ወር ከ፲፫ ቀን፣ በዘመነ ማቴዎስ፣ በወርኃ ነሐሴ በዕለተ እሑድ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል፡፡

ሙሴንና ኤልያስን በደብረ ታቦር ለምን አመጣቸው?

ሙሴን ከመቃብር ጠርቶ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት ጌታችን አምለካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡ ሙሴ ከመቃብር ተነሥቶ ስለጌታችን የሰጠው ምስክርነት፡- “እኔ ባሕር ብከፍልም፣ውኃ ከዓለት ላይ ባፈልቅም፣ በዓመደ ደመና ዕብራውያንን እየመራሁ ጠላትን ድል ባደርግም፣ ደመና ብጋርድም፣መና ከደመና ባወርድም በአንተ መልካም ፈቃድ ነው፤ ብዙ ተአምራንት እንዳደርግ የረዳኝን የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ነው ይሉሃል? የሙሴ አምላክ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ሲል ኤልያስም ደግሞ “እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም፣ እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” በማለት የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ ሙሴና ኤልያስ የተጠሩበት ሌላው ምሥጢር ሙሴ “ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴን ግን አይታይም” ተብሎ ስለነበር (ዘፀ.፴፫፡፳፫) ከሞትም ከብዙ ዘመናት በኋላ ተነሥቶ ጌታን በአካል የማየትና ምስክርንት የመስጠት የቃል ኪዳን ተስፋ መፈጸሙን፣ ኤልያስም “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ሲሆን ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስን ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያት በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንና ሥርዐት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላን እንደሚወርሷት ለማስተማር ሁለቱን ወደ ድበረ ታቦር አምጥቷቸዋል፡፡

መድኃኒታችን ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን “መነይብልዎ ሰብእ ለወልደ እጓለ እምሕያው፤ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ብሎ ጥየቋቸው ነበርመና ሲመልሱ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ›› ብለውት ነበርና (ማቴ.፲፮፡፲፬)፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ‹‹በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር›› ያለውም የነበራቸውን ክብር ታላቅነት ያስረዳል፡፡

በባሕርዬ አይተህ ደንግጠህ እንዳትሞት በብርሃን ሠረገላ ሆኜ እስካልፍ ድረስ ቀዳዳ ባለው ዋሻ እሠውርሃለሁ፡፡ በብርሃን ሠረገላ ሆኜ ካለፍሁ በኋላ እጄን አንሥቼልህ ከወደ ኋላዬ ታየኛለህ እንጂ በባሕርዬ ግን ፊቴን ማየት አይቻልህም›› የሚል ምላሽ ሰጥቶት ነበር (ዘፀ. ፴፫፡፲፫-፳፫)፡፡ ይህም በፊት የሚሄድ ሰው ኋላው እንጂ ፊቱ እንደማይታይ ጌታም በባሕርዩ አለመገለጡን ያስረዳል፡፡ ምሥጢሩም አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም አምላክ ሰው ሆኖ ሥጋን ተዋሕዶ በደብረ ታቦር በባሕርዩ እስኪገለጥለት ድረስ ሙሴ በመቃብር ተወስኖ እንደሚቆይ ያጠይቃል፡፡ በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ከሙታን ተነሥቶ ከዘመናት በፊት የተመኘውን የአምላኩን ፊት ለማየት የታደለው ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተወለደውም በዚህች ዕለት ነው፡፡ ነቢዩ ኤልያስም “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” የተባለው ትንቢትም በዚህች ዕለት ተፈጸመ፡፡

ይቀጥላል...
በዓለ ደብረ ታቦር

ክፍል ሁለት

ሦስቱን ሐዋርያት ለምን ብቻቸውን ወሰዳቸው?

አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል፡፡(ገላ.፪፥፱) ስያሜውን ያገኙበት ምክንያት ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእርሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሄደ ነው (ማር.፭፥፴፬-፵፫)

በተጨማሪም ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ምድራዊ ሐሳብ እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሞቱ ድኅነት የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባለ ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ስለነበር እንዲህ ያለው ሐሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኅነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን መምኅሬ ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው? የሚለውን በማሰብ “አይሁንብህ” አለ፡፡ በሌላም ጊዜ እንደዚሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት በጠየቁት ጊዜ ጌታችን ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነግሯቸዋል፡፡
ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ማርያም ባውፍልያን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ እንዲሰጠቸው ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ይህ ምድራዊ ሐሳብ ከልባቸው እንዲጠፋ እነርሱን ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡

ሁለቱን ከነቢያት ሦስቱን ከሐዋርያት ለምን ወሰዳቸው?

በቤተክርስቲያን ነቢያት ያስተማሩት ብሉይ ኪዳንና ሐዋርያት የሰበኩት ሐዲስ ኪዳን ይነገራሉና ነው፡፡ በደብረ ታቦር ነቢያትም፣ ሐዋርያትም እንደ ተገኙ ሁሉ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ይሰበካል፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴ የሚፈጽሙ ልዑካን አምስት መሆናቸውም በደብረ ታቦር የተገኙትን ሙሴን፣ ኤልያስን፣ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ያስታውሱናል፡፡ ዘወትር በቤተ መቅደሱ የሚፈተተው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ደግሞ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠው የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡ ደብረ ታቦር የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ በሕግ በሥርዓት ያገቡ ሰዎችም፣ በንጽሕና በድንግልና በምንኩስና የአምላካቸውን ፈቃድ የሚፈጽሙ መናንያን፣ ባሕታውያን፣ መነኮሳት አንድ ሆነው መንግሥተ ሰማያትን እንደሚወርሷት ለማስተማር ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር ወስዷቸዋል፡፡ ሙሴን ከመቃብር አንሥቶ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ በደብረ ታቦር ተራራ አብረውት እንዲገኙ ያደረገው ሰዎች ሙሴ ነው ወይም ኤልያስ ነው በሚል ሲጠራጠሩ እንዳይኖሩ መለኮታዊ ምሥጢርን በተግባር ለማስተማር ነው፡፡

የደብረ ታቦር ምሳሌነት

"ደብረ ታቦር" የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከተራራ ላይ ሲወጡ ግን ሜዳና ገደሉን ሁሉ ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡ "ደብረ ታቦር" የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምሥጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ ሁሉ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት የላይኛው ጫፍ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ በላይ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል፡፡(ፊልጵ.፫፥፳)፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም "ለእኛ በዚህ መኖር መልካም ነው" ብሏል፤ ይህን ያለው ክርስቲያኖች የቤተ ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት አክብረን፣ በምግባር በትሩፋት አድገንና አፍርተን፣ በፍቅረ እግዚአብሔር በፍቅረ ሰብእ መኖር በሥጋዊ ዓይን መከራና ድካም መስሎ ቢታየንም ፍጻሜውን ግን ዘለዓለማዊ ሕይወት መሆኑን አምነን እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ በመንፈሳዊ ጥበብ እንዲንመራ ያስገነዝበናል፡፡

ጅራፍ፡-በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምሥጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምሥጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምሥጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍ ትውፊታዊነት ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምሥጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምሥጢር ተፋልሶ ያለው በመሆኑ ልናስወግደውና ምሥጢራዊ ትውፊቱን የስቀጠል ሥራ መስራት አለብን፡፡

ችቦ፡- ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት በመሆኑ ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሠርዓት የመጣው በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ስለቀሩ ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ስለሄዱ ያንን ታሪክ እያዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌለኛው ትርጉም ደግሞ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆናል፡፡

ሙልሙል፡-በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ቡሄ” በሉ እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ “ሙልሙል” ዳቦ ይሠጣል፡፡ ሕፃናቱም መጥተው ሲዘምሩ ዳቦ የመስጠት ልማዳዊ ብቻ አልነበርም፤ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ መሆናቸውንም ያመልክታል፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሄዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ….” ይላሉ፡፡

ጠቅልል ባለ መልኩ ሲታይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባህል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህ ደግሞ በቅብብሎሽ ለአዲሱ ትውልድ የሚቀጥለው ወጣቱ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ የማድረግ የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ማለትም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት ትኩረት ሊደረግብት የሚገባው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩት ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየበዛ መሄዳቸው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት በመሆኗ የምታከናውነውን ሁሉ አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ተጠግተን ከክፉ ነገሮች ሁሉ ተጠብቀን ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍሥሓ ተሰጥቶን፣ በማስተዋልና ሁሉን በማየት የሚጠቅመንን በመምረጥ በሥነ-ምግባር ታንጸን አገርንና ወገንን የምንጠቅም እንዲንሆን የአምላክ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ ቸርነቱም ይርዳን፡፡

ምንጭ፡- 1. መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መምህር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ ገጽ ፫፻፲፭-፫፻፲፯፡፡

2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤፳፻፯ ዓ.ም፣ ገጽ ፻፲፩፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ#ጅራፍ_ማስጮህ#ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ።

👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more

👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more

👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more



ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏

ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።
Audio
ጾም የምግባራት ሁሉ እናት

Size:- 12.9MB
Length:-56:31

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 14:38:12
Back to Top
HTML Embed Code: