Telegram Web Link
እየጦሙ አለመጦም

ተወዳጆች ሆይ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

➛ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
➛ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
➛ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
➛ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

      አምላከ ቅዱሳን እየጦሙ ካለመጦም ይሰውረን!

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“ፆም የፀሎት ምክንያት ናት፤ የፀጋ ዕንብ መገኛ ናት አርምሞን የምታስተምር ናት፤ ለበጎ ስራ ሁሉ ታነቃቃለች፤ የፀዋሚ ስጋው ምንጣፉን አንጥፎ ሌሊቱን ሁሉ ተኝቶ ማደር አይቻለውም በምን ጎኑ ይተኛዋል? ሰው አብዝቶ በፆመ ያህል በዚህ መጠን በትህትና ሁኖ እያለቀሰ ይፀልያል፤ ፀሎታት ከልቡናው ይታሰባሉ አንድም ፀሎተ ልብ ይሰጠዋል፤ በፊቱ የትእግስት ምልክት ይታያል በሃጢአቱ ያዝናል ክፉ ህሊና ይርቅለታል የበጎ ነገር መገኛ መከማቻ በምትሆን በፆም ይኖራልና፤ ፆምን የናቀ ያቃለለ ሰው በጎውን ነገር ሁሉ ከራሱ አራቀ፡፡”

ማር ይስሃቅ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በገነተ አበው (Paradise of the fathers) እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል። ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።

ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ጠጥቶ ሊሰክር ወይም ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። ያ የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡"

(ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቅድሰት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ)

ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሑለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡ የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለሰዎች፡ ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ፡ ለዕለታት ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም ይህንን ሲያስተምረን ነው፡፡ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡

ብርሃን ከጨለማ ጽድቅ ከኃጢአት ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና›› ያለንም ለዚህ ነው፡፡ /1ተሰ 4÷7/ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች እንዲህ ገልጾላቸዋል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሰማያዊ ሥፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ብሎ ካመሰገነ በኋላ ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳን ንጹሐንና ያለነውር በፍቅር ያደርገን ዘንድ ለእርሱ መረጠን›› ኤፌ 1፡3-4 አስቀድሞ ስለወደደንና ስላከበረንም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጅቶ በእጆቹ ካበጀን በኋላ የሥነ ፍጥረት ዘውድ አድርጎ በገነት አኖረን ፡፡( ዘፍ 1፡26፤መዝ 8፡1)

የቀደመው አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረጉ በንዝህላልነትና በስንፍና በከይሲ ዲያብሎስም ምክር ተዋረደ፡፡ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ፤በርዕደተ መቃብር ላይ ርዕደተ ሲኦል ተፈረደበት፡ በባሕርዩ ሞት ገባበት፡ ተዳደፈ፡፡ ክፉ ፍትወታት የሚያጠቁትና የሚያሸንፉት የዲያብሎስና የኃጢአት ባርያ ሆነ፡፡ በማይለወጥ ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ግን ጠፍተን እንድንቀር አልተወንም፡፡ በሰጠን ተስፋ፡በተቆጠረው ሱባኤና በተነገረው ትንቢት መሰረት ዘመኑ ሲደርስ በተዋህዶ ሰው ሆነ፤ የተዋረደ ሥጋችንን አከበረ፡፡ በከበረ ደሙ ዋጀን፤ ከኃጢአታችን አጠበን፡፡ በእርሱ ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን ፡፡ጌታችንና መድኃኒታችን ሰው የሆነውና ለመዳናችን የሆነውን ዋጋ ሁሉ የከፈለው ለእኛ ያለውን ፍቅርና ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ለእኛ ለማሳየት ነው፡፡ ‹‹ ነገር ግን የኃጢአትን ሥራ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለውን አሮጌውን ሰውነታችን እንደሆነ ይህን እናውቃለን ›› የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ (ሮሜ 6፡6) እኛን ወደ ቀደመ ክብራችን ለመመለስ የተከፈለውም ዋጋ ታላቅ ከሆነው የጋብቻ ምስጢር ጋር በማያያዝ እንዲህ ገልፆታል ‹‹ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርሰቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና … ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ራሱንም ስለእርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ፡፡ በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳትና ያነጻት ዘንድ የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኩሰት እንዳይገኝባት ቤተ ክስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ…›› ኤፌ 5፡23-28 ስለዚህ ጌታችን በደሙ ኃጢአታችንን እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎናል፡፡ኤፌ 1፡7 ከእንግዲህ የራሳችን አይደለንም፡፡ በሰውነታችንም ኃጢአትና ዐመፃን ልናደርግበት አይገባም፡፡‹‹በዚህ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አታንግሷት፤ ለምኞቱ እሺ አትበሉት፡፡ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጉ እንጂ ሰውነታችሁን ለኃጢአት የዐመፅ የጦር መሣሪያ አታድርጉት፤ ሰውነታችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ የጦር መሣሪያ አድርጉ››ተብለናል፡፡ (ሮሜ6፡12-13)

የተወደዳችሁ ምዕመናን እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚቀበለውን ህይወት ለመኖር አንፈልጋለን ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብንመላለስ ነው? መልሱን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው፡፡ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ ርኩሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው፡፡›› በማለት ይመልስልናል( ያዕ 1፡26-27)፡፡ በክርስቶስ ደም የተቀደሰና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችንን በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መጠበቅ የሰማያዊ ርስት ወራሾች ያደርገናል፡፡ በዓለም የሚገኘውን ርኩሰትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋ ሥራ›› በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹እርሱም ዝሙት፣ርኩሰት፣መዳራት፣ጣዖት ማምለክ፣ሥራይ ማድረግ፣ መጣላት፣ ኩራት፣ የምንዝር ጌጥ፣ ቅናት፣ ቁጣ፣ ጥርጥር፣ ፉክክር፣ምቀኝነት፣ መጋደል፣ ስካር ፣ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው፡፡›› እነዚህን የሚያደርጉ ሰዎችም ከመንግስተ እግዚአብሔር በአፍአ ወይም በውጭ እንደሚቀሩ ሲያስረዳ ‹‹አስቀድሜ እንደነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም›› ብሏል ( ገላ5፡19)።

በሕይወታችን ሁሉ የምግባርና የሃይማኖት ፍሬ አፍርተን መገኘት ለቅድስና የጠራንን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ እነዚህንም ነገሮች ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የመንፈስ ፍሬዎች ›› ብሏቸዋል፡፡ እነርሱም  ‹‹ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ምጽዋት፣ ቸርነት፣ እምነት፣ ገርነት ንጽሕና›› ናቸው፡፡ ገላ 5፡22 እግዚአብሔር ማደርያው ይሆን ዘንድ የመረጠውን ሰውነታችንን እርሱ የሚከብርበትን ሥራ ልናደርግበት ያስፈልጋል፡፡ ‹‹በሕይወት የሚኖሩትም ስለ እነርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞተውና ለተነሣውም እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው የሚኖሩ እንዳይሆኑ እርሱ ስለሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ›› እንደተባለ በሕይወታችን ሁሉ ፋቃዱን በመመርመርና በመፈጸም በቅድስና ልንኖር ይገባናል፡፡ 2ቆሮ 5፡15 ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣በማኅበራዊ ኑሯችን፣ በምንበላው ምግብ፣ በምንለብሰው ልብስ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደንበፊታችን
ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል(ዕብ 12፡1)። ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡
                     ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
Audio
ሰማያትን ዝቅ ዝቅ አድርጎ ወረደ
                         
Size 39.3MB
Length 1:52:57

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ዐቢይ ጾምን እንዴት እንጹም
                         
Size 17.2MB
Length 49:15

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው።

በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም" የሚለው ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ ። አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም።

መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል ። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ።

ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በከንቱ እንዳንደክም መጾም እንደሚገባን እንጹም

በመጾም እየደከምን ሳለ የጾም አክሊልን ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበርና፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የኼደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነውና (ሉቃ.18፡12)፡፡ ቀራጩ ደግሞ በአንጻሩ አልጾመም ነበር፤ ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት [ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ በመፃዒ ሕይወቱም ጾም አላሻውም ለማለት ሳይኾን ከተአምኖ ኃጣውእ ጋር] ሌሎች ግብራት ካልተከተሏት በቀር ጾም ረብ ጥቅም እንደሌላት [እና ትሕትና የጾም አጣማጅ መኾኑን/ የምትሠምረው ከትሕትና ጋር መኾኑን] እንድታውቅ ነው፡፡

የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል (ዮና.3፡10)፡፡ እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም (ኢሳ.58፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ.9፡26)፡፡ ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለባቸው ለማያውቁ ሰዎች የጾም ጉዳቱ ትልቅ ነውና በጥርጣሬ እንዳንኼድ፣ እንዲሁ አየርን እንዳንደልቅ፣ እንዲሁ ከጨለማ ጋር እንዳንጋደል፥ ይህን የምናከናውንባቸውን ሕጎች ልንማር ያስፈልገናል፡፡

ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
መልካም ምግባር ሰዎች እንዲያዩልን ብለን አናድርግ፡፡ ብንጾምም፣ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም፣ ሌላም በጎ ምግባር ብናደርግ የተገለጠውንም የተሰወረውንም ሁሉ ለሚያውቅ እግዚአብሔር ብለን የማናደርገው ከሆነ ከሰዎች አንዳች ጥቅም አያስገኝልንም፡፡ እንዲህ በማድረጋችን ሰዎች ቢያመሰግኑን እየጎዱን እንደሆነ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ሰዎች እንዲጎዱን ምቹ ሁኔታዎችን የምንፈጥርላቸው? ትክክለኛ ማንነታችን የሚያውቀው፣ የዘለዓለምንም ሹመት ሽልማታችንን የሚሰጠን እግዚአብሔር አይደለምን? ታድያ ለምንድነው ጥቅም ከማይሰጠን ይልቁንም ከሚጎዳን አካል ውዳሴን የምንጠብቀው? ስለዚህ በቃላችንም፣ በግብራችንም፣ በሐሳባችንም እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ ልናሰኝ አይገባንም እላችኋለሁ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ዓድዋ#ሶሎዳ(በፎቶ ላይ የምትመለከቱትና ከዓድዋ ተራሮች ዋነኛው)፡፡
#ዓድዋ #፬ት #ታላላቅ_ነገሮችን_አስተባብራ_የያዘች_የኢትዮጵያ_ሕያው_ምስክር

1ኛ) ከ1500 ዓመትት በፊት ዓድዋ (ዖድዋ፥ ዖድዋ) ብለው የሰየምዋትንና ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸውን #የእንዳአባ_ገሪማን ገዳም የያዘች፤

2ኛ) በዓለም #ከ1500 #ዓመታት_በላይ ረዥም ዕድሜን ያስቆጠረውን የእንዳአባ ገሪማን #የብራና_ወንጌል ጠብቃ ያቆየች፤

3ኛ) ከዓድዋ በፊት በጥር 1878 ጣሊያንን ዶጋሊ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰው፡፡ የታላቁ አርበኛ #ራስ_አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ በክብር ያሸለበባት፤

4ኛ) ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገበትን #ሶሎዳ_ተራራና ሌሎችንም ተራሮች በጉያዋ ያቀፈች ናት፤ ዓድዋ።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#አድዋ#ሶሎዳ፡፡ #9ኛው #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት፡፡

9ኛ) #አድዋ#ሶሎዳ፡፡
ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ_ ተራራ ላይ ነው፡፡
#የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት_መነሻ
፠ ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡
፠ መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ (እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡
፠ ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጦርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡
 ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡
#ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤
/የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡/
 ከ1878-1888ዓ.ም. #ከዓድዋ_በፊት_የነበሩ_8ቱ_አድዋዎችና_የዓድዋ_ሶሎዳ_ውጊያ
1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ_ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡
2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ
3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ_መንደር_ ውጊያ፡፡
4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት_ ከጥር 13-15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡
5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ_ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡
6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡
7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡)
8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡
9ኛ) #አድዋ#ሶሎዳ፡፡

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 14:25:03
Back to Top
HTML Embed Code: