Telegram Web Link
Forwarded from 1,000-20,000 Promotion via @SmartButton_Bot
📱ለስልካችሁ ገራሚ APPLICATION ከፈለጋችሁ JOIN የሚለውን በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ 🛑
በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ድርጊት አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት የተሰጠ መግለጫ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ድርጊት አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ምሥረታ ጀምሮ ያለችና መንግሥትን ያጸናች፣ የራሳቸው የጽሑፍ ቋንቋ ካላቸው ጥቂት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ እንድትሆን ፊደል ቀርፃ ያስተማረች፣ መንግሥት የአረንጓዴ አሻራን መርሐግብር ከማስጀመሩ ከሺህ ዓመታት በፊት የአካባቢ ጥበቃን ስትሠራ የኖረችና አሁንም በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና አድባራት የአካባቢ ጥበቃ ሥራን የምትሠራ፣ ዘመናዊ ትምህርት ከመጀመሩ ከሺህ ዓመታት በፊት ሥርዓተ ትምህርት ቀርፃ ያስተማረችና የሀገር መሪዎችን፣ የስነ ህንፃ ባለሙያዎችን፣ የመድኃኒት አዋቂዎችንና ተመራማሪዎችን ያፈራች ቤተ ክርስቲያን ከመሆኗም በላይ ተቋም መሥርታ ለዘመናት የተቋምን ምንነት ያስተማረች ራሷ ሀገር የሆነች ናት፡፡
በተለይም ደግሞ መላው የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ግዛት በተያዙበት፣ አውሮፓውያን ኢትዮጵያንም ለመቀራመት ተስማምተው በፋሺስቱ የኢጣልያ መንግሥት አማካኝነት ሀገራችንን በወረረበት ጊዜ የንጉሱን የክተት አዋጅ ተከትሎ ሕዝቡ ለነፃነቱ እንዲዋደቅ የሀገር ፍቅር ለምእመኗ ያስተማረች በመሆኑ እና የንጉሱም ጥሪ ሀገራዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖትን የመጠበቅ ጥሪም የነበረ በመሆኑ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ንጉሱን እንዲከተል ከማድረጓም በላይ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን በካህናቱ አጅባ የጦር ግንባር ድረስ በመዝመት፣ ምእመኑን እና ህዝቡን በማጽናናትና ፀሎተ ፍትሀት በማድረግ በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ሀገራችን ድል እንድትቀዳጅና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የነፃነት አርማ እንድትሆን በማድረግ ትልቁን የታሪክ ድርሻ እንደምትወስድ የታወቀ ሀቅ ነው፡፡
ከዚህ የድል በዓል በኋላም ኢትዮጵያ በነፃነት በቆየችባቸው ዓመታት ሁሉ ይህን የአድዋ የድል በዓል ቤተ ክርስቲያን የሰማእቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦተ ሕግ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ህዝቡን በመባረክ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በታላቅ ምሥጋና እና መዝሙር በመላ ሀገሪቱ ስታከብረው የኖረች፤ወደፊትም እየፈጸመች የምትጸናበት አኩሪ ታሪኳ ነው፡፡ 
ይሁን እንጂ ይህ በዓል ላለፉት ጥቂት ዓመታት የድል በዓል መሆኑ ቀርቶ የጠብ እና የጥላቻ በዓል እየሆነ መምጣቱ ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይም ትላንት የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በተከበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያን ላይ የአድዋ የድል በዓልን አስታኮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመው እጅግ አሳዛኝ ድርጊትን ግን ቤተ ክርስቲያን ሰምታና አይታ በዝምታና በሀዘን ብቻ  የምታልፈው ጉዳይ አልሆነም፡፡  
በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ ፫፡፲፭ ላይ ታቦተ ሕጉ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገና ሕዝቡን ባርኮ በዐውደ ምህረቱ ላይ ከቆመ በኋላ ሊቃውንቱ ያሬዳዊ ወረብ በማቅረብ ላይ እንዳሉ ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልናን ተላልፈው በሰሜን በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ፪ ጊዜ በተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የንግሥ በዓሉ በመረበሹ በዓሉ ተቋርጦ ከጠዋቱ ፬ ሰዓት ላይ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበሩ ተመልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት እስከአሁን በደረሰን መረጃ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ከፍተኛ ረብሻ በመፈጠሩ ምክንያት ፩ ምእመን በተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ ታፍነው ህይወታቸውን ማጣታቸውን፣ አገልጋይ ካህናት አባቶች፣ ምእመናን እና ምእመናት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከ፲፭ ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ 
ይህ ድርጊት ከተፈፀመ በኋላም መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ልዕልና በመዳፈር በቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን በደል የፈፀሙ የጸጥታ መዋቅር አካላትን ለሕግ ያቀርባል፣ እንደ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወጣል ብለን ብንጠብቅም የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ በዓሉን አስመልክቶ በዕለቱ ባወጣው መግለጫ ችግሩን የፈጠሩት አካላት ‹‹የአደባባይ በዓሉን ለመረበሽ ሲያቅታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚደረገውን ኃይማኖታዊ በዓል ለመረበሽ ሞክረዋል፡፡ የጸጥታ መዋቅሩ ችግሩን ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ ጉዳቱን ለመቀነስ ችሏል›› ሲል የችግሩን ሁኔታ ገልጧል፡፡ በዚህ መግለጫውም ላይ አሁንም ችግሩ የሌሎች ቡድኖች እንደሆነና የቤተ ክርስቲያኒቱን በዓል የረበሸው የእነዚህ አካላት እንቅስቃሴ ነው በማለት የሰጠው መግለጫ በቦታው ላይ ከነበረው እውነታ በእጅጉ የራቀ እና ድርጊቱ የተወሰኑ ግለሰቦች ሳይሆን የመንግሥት እውቅና ያለው መሆኑን እንዲሁም መንግሥት ችግሩን ለማረም እና መፍታት ፍላጎት የሌለው መሆኑን እንድንረዳ አድርጎናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን በዓል እንዲረበሽ እና ምእመናን ህይወታቸውን እንዲያጡ እንዲሁም እንዲጎዱ ያደረገው ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መሆኑ ለሁሉም የታወቀ ሆኖ እያለ ጉዳዩን ወደ ሌላ አካል ለማላከክ የተሄደበትን ርቀት ቤተ ክርስቲያን በፍፁም የምትቀበለው አይሆንም፡፡
የመንግሥት የፀጥታ አካል በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ምእመናን ላይ ጉዳት ሲያደርስ እና የቤተ ክርስቲያንን ክብር ሲያጎድፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በጥር ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በተሰበሰቡ ምእመናን ላይ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ብዙ ምእመናን እንዲጎዱ የተደረገ ሲሆን በጊዜው መንግሥት ይህን ድርጊት በፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ልክ እንደአሁኑ ችግሩ የሕገ ወጦች ነው በማለት ለድርጊቱ እውቅና ሰጥቶት አልፏል፡፡ በዚህ ድርጊት መንግሥት በጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ እና መንግሥትንና ሕዝብን እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ያለመግባባት የሚያባብሱትን ግለሰቦች እና አመራሮች ለይቶ እርምት ከመውሰድ ይልቅ ሕዝብና መንግሥትን ሆድና ጀርባ የሚያደርግ ተግባሩን አስፋፍቶ ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም መንግሥት ለዘመናት የኖረች እና ከግማሽ የሀገሪቱ ህዝብ በላይ የያዘችን ቤተ ክርስቲያን ክብርና ልዕልና በሚዳፈር መልኩ በተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ እና ይህን ድርጊት የፈጸሙ የጸጥታ አካላትና እንዲፈፀም ያዘዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን በ፲፭ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለይቶ በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ እና ይህንንም ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በግልጽ እንዲያሳውቅ እንዲሁም በተለመደው የሀሰት ውንጀላ በዓላችንን በማክበር ላይ እያሉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በተፈጠረው ግርግር መነሻት የታሰሩ ምእመናንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ
እርምጃዎች የምትገባ መሆኑን በአክብሮት እያሳወቅን ይህንንም ድርጊት ተከታትሎ የሚያሳውቅ እና የሚያስፈጽም የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደሥራ እንዲገባ የሚደረግም መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡ በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት የሊቀ ሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር በመምጣት ህይወቱን ላጣው ልጃችን እግዚአብሔር ነፍሱን በአብርሃም፣ በያዕቆብና በይስሐቅ እቅፍ ያኑር፣ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ያድልልን እያልን ቀላልም ሆነ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ የቤተ ክርስቲን የጭንቅ ቀን ልጆች ደማችሁን እና መከራችሁን እንደ ሰማእታት ዋጋ ይቆጥርላችሁ ዘንድ ጸሎታችን ነው፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ተወዳጅ ሆይ! ክርስቶስ ኢየሱስ እንዲህ ይልሃል፦

✟ አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡
✟ የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ፡፡
✟ የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡
✟ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡
✟ በቦታው ኹሉ የራቅሁ አይደለሁም፡፡ ትእዛዜን በምትፈጽምበት ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር እኖራለሁና ችግረኞችን የምረዳቸው እኔ ነኝና፤ ለድኾች የምታደርገው ኹሉ ለእኔ ማድረግህ ነው፡፡ እኔም በእርሱ ፈንታ በጎ ዋጋ እከፍልሃለሁና፡፡
✟ በቤትህ ውስጥ እንግዳ በአሳደርክ ጊዜ እነሆ ከእንግዳው ጋር በማደሪያህ አስገባኸኝ፡፡
✟ እንደዚህ ለሚያደርግ ቁጣዬ ከእርሱ ይርቃል፤ ወደ ሕይወት ወደብም አደርሰዋለሁ፡፡ ከክፉ ነገር ኹሉ እጠብቀዋለሁ፡፡ እባርከዋለሁ፡፡ ዘሩንም አበዛለሁ፡፡ ዋጋውንም በሰማይ ባለው በአባቴ ዘንድ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡ ዘለዓለማዊ ዕረፍትንም እሰጠዋለሁ፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ፣ ድርሳን 3፥8
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
የመካሪዎችን ምክር የሚሽር ጥበበኛ
                         
Size 25.6MB
Length 1:13:25

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰላም የ EOTC ቤተ መጻሕፍት chanal ቤተሰቦች
እንኳን ለታላቁ አብይ ፆም አደረሳችሁ እያልቁ 1 ትልቅ የበረከት ስራ ልንሰራ አስበናል እሱም
ለድሬደዋ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ለሰሞነ ሕማማት መገልገያ የሚሆን ጥቁር ልብሰ ተክኖ ስለሌለው በዘሁ chanal አባላት አስተባብረን አሰፍተን ልንሰጥ ስላሰብን ይሕን የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ ምትፈልጉ በውስጥ መስመር @yesadikusitota ላይ ያናግሩን አልያም በስልክ ቁጥር 0943896021 ላይ ያናግሩን
ለምታደርጉት ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ
Audio
ምን ምልክት ታሳያለህ?
                         
Size 44.8MB
Length 2:08:34

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቅዱስ_ሲኖዶስ_የተሰጠ_መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በማድረግ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና አስተዳደራዊ ጥሰት በመፈጸም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰዶ ዳጩ ወረዳ በሀሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሕገ-ወጥ አድራጐት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ፡-
ሕገ-ወጥ ሹመቱ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ ሕገ-ወጥ ሹመቱን ያከናወኑት 3ቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ተሹመናል ባዮችን 25 ግለሰቦች ከዲቁና ጀምሮ ያላቸውን ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት በማውገዝ መለየቱ ፤
ምንም እንኳን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁሉንም አውግዞ የለየ ቢሆንም እናት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ለሰላም በሯ ክፍት እንደመሆኑ መጠን የተወገዙት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰላም ጥሪ ተቀብለውና የተከናወነው ድርጊት ሕገ-ወጥ መሆኑን አምነው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለፈጸሙት ሕገ-ወጥ አድራጐት የሚሰጣቸውን ቀኖና ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑና ይህንንም ሐሳባቸውን በጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በማቅረብ ሪፖርት ካደረጉ የቤተ ክርስቲያናችን የሰላም በር ክፍት መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ መግለጹን እናስታውሳለን፡፡
በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሰላም በሩን ክፍት በማድረግ ትዕግስት የተሞላበት ጥረት ቢያደርግም የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከመቅረብ ይልቅ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ሕጋዊ የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር የሆኑትን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤትና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መንበረ ጵጵስና ቁልፍ በመስበር የንብረትና የመዋቅር ወረራ በመፈጸም በሕገወጥ አድራጐታቸው በመቀጠላቸውና በተከፈተው የሰላም በር ተጠቅመው ለሰላም ዝግጁ ባለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያናችን በሀገሪቱ ሕግ የተረጋገጠ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ሕጋዊቱን ቤተ ክርስቲያን በሕገ-ወጥ መንገድ ተቋሞቿ የተያዙባት መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ያለበትን ሕግን የማስከበር ኃላፊነት በመወጣት ተቋማዊ ክብራችንና ሕጋዊ ባለቤትነቷን እንዲያረጋግጥ ያደረገችውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በቅድሚያ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችን በማነጋገርና ለቀጣይ የውይይት አቅጣጫ በሰጡት አመራር ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የቀድሞውን ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት በ10 ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት መድረሱን እናስታውሳለን፡፡
እናት ቤተ ክርስቲያን በተደረሰው ስምምነት መሠረት አሥሩን የስምምነት ነጥቦች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ ቢሆንም 25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በመዋቅራችን ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በአዲስ አበባና በአካባቢው የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለስብሰባ በመጥራት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሦስቱ የቀድሞ ብፁዓን አባቶች በአካል ቀርበው በሰጡት ቃል በተከናወነው ድርጊትና ድርጊቱን ተከትሎ በተፈጸሙት ክስተቶች ማዘናቸውንና በቀጣይ ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንደሚቃወሙና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን መመሪያ አከብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱም የሦስቱን የቀድሞ አባቶች ሐሳብ በመቀበል ጉዳዩን አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተለውን የሰላም ጥሪ አስተላልፏል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣
ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣
ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያናችን ምስጋናዋን እያቀረበች በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን በድጋሚ ታስተላልፋለች፡፡
በተደረሰው ስምምነት መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ አህጉረ ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሰብረው የያዙ ግለሰቦችን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት ከቤተ ክርስቲያናችን ይዞታ በማስወጣት ለቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ የሥራ ኃላፊዎች በማስረከብ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእለት ከእለት ተግባርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከናወን እንዲሁም በተደረሰው ስምምነት መሠረት እስከአሁን መፈታት ሲገባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ምእመናን እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ክቡር ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለሰማን የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያናችን እያመሰገነች ያልገቡትንም ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ
በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣

ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል፣

መጋቢት 6 ቀን 2015ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

(ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ጸሎት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምታደርስ ቀጭኗ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት በመራቅ የሚቀርብ ጸሎት ፍጹም የሆነ ሥራን ይሰራል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እኖርክ በእግዚአብሔር ስም ለጸሎት የምትቆም ከሆነ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ ህሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ በጸሎት ተመስጠህ ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ፡፡

አጠገብህ ስሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠኸው ቁጥር ነው፡፡ ጥላቻ በልቦናህ ነግሶ ከሆነ የዳቢሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡

የተንኮል ቃልን አትናገር፤ ለባልንጀራህ ጉድጓድ አትቆፍር፤ ወደ አመንዝራም ሴት አትመልከት የፊቷም ደምግባት አያጥምድህ፡፡ በእርሷ መረብ እንዳትጠመድ ከአንደበቷ ከሚፈልቁት ጣፋጭ ቃሎች ተከልከል፡፡ ከእርሷ ፈጽሞ ሽሽ፡፡

በሰዎች ውድቀት አትደሰት፡፡ በደለኛ እንዳትሆን ጠላትህ ክፉ ሲደርስበት አይተህ ደስ አይበልህ፡፡ ጠላትህ በኃጢአት ተሰነካክሎ ብታይ ስለ እርሱ እዘንለት አልቅስለት፡፡ እጆችህን ለሥራ አትጋቸው፤ ከንቱ ንግግር አትውደድ ለነፍስና ለሥጋ ብሩህነት በሥራ መጠመድን ውደድ፡፡

(ምንጭ፡- ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም፣ በመ/ር ሽመልስ መርጊያ፣ ገጽ 65-66)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ጾም በአንተ ውስጥ የሆነ አንድ ነገር መለወጡን ተመልከት።

ከጾም የምታገኝው ነገር የምግብ ለውጥ መሆኑን ብቻ አትመልከት። ለተሻለ ህይወት የሚደረግ ለውጥ መሆኑን ተመልከት። ይህም ማለት በአንተ ውስጥ ያለ ጉድለትንና በውስጥህ እንዳለ የሚሰማህን ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር የሚሆን ድክመት ተመልከት ማለት ነው። ይህ ሳይሆን ከቀረ በሃምሳ አምስቱ የሁዳዴ ጾም ቀናት ውስጥ ራስህን አሸንፈህ ከቆየህ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ዝምድና እና የተረጋጋ ግንኙነት ሳትፈጥር ከጾሙ አስቀድሞ የነበረህን አቋም ሙሉ ለሙሉ ይዘህ ለመውጣት ከሆነ የነፍስህ ጥቅም ምን ሊሆን ነው? አንተ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣና አስቀድመህ በነበርህበት ሁኔታ ውስጥ እያለህ እስከ አሁን ድረስ ስንት አጽዋማት እንዳለፉህ አስብ!

በሁሉም አጽዋማት ውስጥ ፈቃድህ ደካማ ጎንህን ለማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆን አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቅ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም የእርሱን ፈቃድ ጣፋጭነት እንድትቀምስ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሔር። ጋር የሚኖርህ ዝምድና እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር!

ስለዚህ ንስሃ በመግባት ጾምህን ጀምር። ጾምህን በጸሎት በምጽዋት በስግደት በመንፈሳዊ ንባባት በቅዳሴ በኪዳን ጸሎቶች አጅበው። እነዚህን ሁሉ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ጋር ትወዳጃለህ የሁዳዴ ጾም የያዛቸው በረከቶች ብዙ ናቸውና። እኒህን ካደረክ በመጨረሻ ላይ ውጤቱን ከአምላክህ ትቀበላለህ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ቀድሞ የገባ ሰው ይፈወሳል
                         
Size 58.7MB
Length 2:48:30

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
" ጾምን አጋመስነው አትበሉ"

ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው፡- “ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ” ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡ እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይኾን የኃጢአታቸው እኩሌታ መኼዱን [መወገዱን] ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡ ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፡፡ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው።

ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል፣ ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት፣ ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል [በዓለ ትንሣኤን] እንድናከብር ነውና፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡

ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ኾነ፣ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡ የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡ የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡ በወርሐ ክረምቱ በብዛትም በዓይነትም የተለያየ ዓይነት የዝናብ ጠብታዎችን ተቀብለናል፤ ብዙ ተከታታይ ትምህርቶችን ተምረናል፤ መንፈሳዊ አዝርእት ተዘርተዉብናል፤ የቅምጥልነት እሾኽም ቆርጠን ጥለናል፡፡

ስለዚህ ጾሙ በተፈታ ጊዜ የጾሙ ፍሬ ይከብበን ዘንድ፣ ከጾሙ የሰበሰብናቸውን መልካም ነገሮችም ጾሙን ራሱን እናስታውሰው ዘንድ የሰማነውን ነገር አጽንተን በመያዝ እንትጋ፡፡

(ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት፣ 18፥1-2)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 12:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: