Telegram Web Link
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው?

ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል።

ሰማዕቱ በግፍ የሚደበደቡ የካህናቱን እና የምእመናኑን እንባ ያብስልን!

#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

አዲስ አበባ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::" የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን

የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::

ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (President Pontifical Council for Prompting Christian Unity) እንደገለጹት "በተፈጠረው ችግር እና ሁኔታ ጥልቅ ሐዘን የተሰማን ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለንን አጋርነት በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረትን በሙሉ እንደግፋለን" ብለዋል::

በመልእክታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በላከው የመጀመሪያ መልእክት “አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።” 1ኛ ቆሮንጦስ 12፥26 ያለውን ጠቅሰው ሕመሟ ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው ሲሉ በአጽንዖት ገልጸዋል።

በመጨረሻም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እናት በምልጃዋ እጅግ የተከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ታድርግልን ብለዋል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የእሥር ዜና!

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን እንዲሁም ዋና ፀሐፊዋ ወጣት ብሩክታዊት ታሥረዋል።

ምንጭ፡ ተሚማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በየኔታ  ገብረ መድኅን እንየው

ቀጥሎስ????
ወደ እግዚአብሔር ስንጮህ ሰንብተናል ፦ጸሎታችንን ልመናችንን ሳናቋርጥ ቀጥሎስ ምንድን ነው የምንሠራው??
#1ኛ፦የብልጽግና መንግሥት በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ እያደረገ ባለው ፍጅት የተናበበ የመረጃ ልውውጥ ያስፈልገናል ፦ምንም ነገር ሳንንቅ የሰማነውን፣ ያየነውን፣የሆነውን፣ ጥርጣሬያችንን ለሚመለከተው ክፍላችን በፍጥነት ማሳወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሁሉም ነገራችን ንቁ መሆን አለበት፡፡
#2ኛ፦የቤተ ክርስቲያናችንን ድምጽ ብቻ በመስማት መተግበር ይጠበቅብናል፦ የተለያዩ ድንፋታዎችን በመስማት ምንም መጨነቅ የለብንም፦የማንሞትለት ሃይማኖት የለንምና፡፡
#3ኛ፦ የተሰለቡ ሀሳቦችን ማስወገድ ወይም ማራቅ፦ለምሳሌ ስንምት እንበዛለን፣ሊሆን ግድ ነው፣ምን ይደረግ ዘመኑ ነው፣እሱ ይሁነን፦ እና የመሳሰሉ ውስጣዊ አቅማችንን የሚሰልቡብንን ማራቅ፡፡
#4ኛ ፦ የተናበበ ኦርቶዶክሳዊ አደረጃጅት ማዘጋጀት ፦ ያሉንን አጠናክረን የሌሉንን ሠርተን በየአህጉረ ስብከታችን ክርስቲያናዊ ኅብረት ማዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡
  ኦርቶዶክሳዊነት ዘለዓማዊነትን በምድር ላይ የመኖር ጅማሬ ነው፡፡
የክርስቲያኖች  አሁን የነገ ኑሯቸው ነው፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

tikvahethiopia

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት #የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለፀ።

ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በዚህ ጉዳይ የቤተክርስቲያኗ የህግ ክፍል ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቅዱስ_ሲኖዶስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ ፦

" ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው።

የነበረን ጥያቄ አጠቃላይ በመንግስት ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲሁም በሌሎች እዛ ባሉት ተገቢ ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ስለዚህ ጉዳይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። የተገኘውን ውጤትም አጠቃላይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን።

ዛሬ ይሄን አጭር መግለጫ ለመስጠት የወደድነው ምእመናኖቻችን ህዝባችን ስለሚጠብቅ ፤ ህዝባችን ምንም ከቆምንበት ዓላማ ወደኃላም ሆነ ወደፊት እንዳላልን ሁል ጊዜ የህገ ቤተክርስቲያን አቋም የፀና እንደሆነ፣ የቀኖና ቤተክርስቲያን የፀና እንደሆነ ይሄንን ለማረጋገጥ ነው።

ይሄ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ስለዚህ ምእመናንን ወገኖቻችን ስለምታደርጉ የፀሎት ፣ የምክር አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ በቤተክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን።

በፀሎት ትጉ፣ በምዕላ ትጉ ፤ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቷል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አንዳንድ የምሰማቸው እና የምናያቸው ነገሮች ስላሉ ነው ዛሬ ጠቅላላ መግለጫ ያላወጣነው።

ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ መግለጫ እንሰጣለን። "

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ዛሬ የምነግርህ ነገር በልብህ ውስጥ ይቀመጥ
                         
Size 16MB
Length 46:01

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
© ዲ/ን ማለደ ዋሲሁን እንደጻፉት
ምን ተማርን (ምንስ ጸጋ አገኘን)?
1) የመንግሥትን ግብዝነት (አስመሳይነት) ለቤተክርስቲያን ያለውን ጥላቻ እግዚአብሔር ገልጾልናል (በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም ላይ ሲያመነቱ የነበሩና አንጀታቸው ያልቆረጠላቸው ሰዎች ከእውነታው ጋር ተዋውቀዋል፡፡)….መላ ይፈልጋል፡፡
2) መንግሥት (በተለይ የኦሮምያ ክልላዊ መግሥት፣ የአዲስ አበባ አስተዳዳር እና ፌደራል መንግሥቱ ለቤተክርስቲያን የደገሰላትንና ዛሬ ቢዳፈን እንኳን ነገ የሚነድ የመከራ ድግስ እንዳለ አውቀናል፡፡…መላ ይፈልጋል፡፡
3) ጉዳዩ የቋንቋና የባህል አለመሆኑን በኦሮሞ እና ኦሮምኛ በሚናገሩ አባቶችና አገልጋዮች ላይ የደረሰው እስር ወከባ እና እንግልት አረጋግጦልናል፡፡….መላ ይፈልጋል፡፡
4) በኦሮሞ ማኅበረሰብ ስም በጵጵስና ለማሾም ጎልተዋቸው የነበሩ እጩዎቻቸውን ማንነት ታዝበናል፡፡ ስለዚህም በወደፊቱ የጳጳሳት ሢመት ጉዳይ ሊፈጠር የሚችልን የመንግሥት ጣልቃ ገብነትና በአባቶች መካከል በጎሳ ፖለቲካ ለመስለብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ታውቋል፡፡ …መላ ይፈልጋል፡፡
5) ቤተክህነት አጣቂኝ ውስጥ ገባ ብለው እጅ ጥምዘዛ ውስጥ የገቡ የእኛ ቤተሰቦችንም ታዝበናል፡፡…መላ ይፈልጋል፡፡
6) የመንግሥት ሚዲያዎች ነጻነት ማጣት ጉዳይ ከምናስበው በላይ አይሏል፡፡…መላ ይፈልጋል፡፡
7) ከተወሰኑ ክልላዊ መንግሥታት በስተቀር በርካቶቹ በፌደራል መንግሥቱ የተሰጣቸው መግለጫ በማስተጋባት አሁንም ራስን በራስ የማስተዳዳር ነጻነትን ለመለማመድ ችግር ላይ መሆናቸው አስተውለናል፡፡….መላ ይፈልጋል፡፡
8) ‹‹ነብያት ነን›› በሚሉ ቀንደኛ የፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚ ፓስተሮችና በመንግሥት መካከል ያለውን የተቀናጀ ፀረ- ኦርቶዶክስ ዘመቻ አስተውለናል፡፡
9) ቤተክርስቲያን በመከራዋና በችግሯ ጊዜ የሚጮህላት፣ አይዟችሁ የሚል የመንግሥት ሹመኛ እንደሌላት አስተውለናል፡፡…መላ ይፈልጋል፡፡
ያስተዋልነው የቤተክርስቲያን ጸጋ
1) ምን አለባትም ቤተክህነቱንና የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ሳይቀር በሚያስደንቅ ደረጃ ቤተክርስቲያን በምንም ዓይነት የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ፣ በምንም ዓይነት የግብረ ገብ ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ ቤታቸው ቤተክርስቲያን ግን እንድትነካባቸው የማይፈልጉ ሚሊዮኖች እንዳሏት ተስተውሏል፡፡
2) ለኅሊናቸው ያደሩ፣ ለእውነት የሚመሰክሩ በርካታ ሙስሊምና ፕሮቴስታንቶች የሚችሉትን ያህል ከቤተክርስን ጎን ቆመዋል፡፡
3) አነስ በዛም የሌሎች ቤተእምነት መሪዎችም ይሄንን መንግሥት በስጋት እያዩት መሆኑን በሚያንጸባርቅ መልኩ ለቤተክርስቲያን ወግነው ባወጡት መግለጫ አሳይተውናል፡፡
4) በሲኦል ደረጃ በሚታየው የኦሮምያ ክልል ያሉ ምእመናን በክልሉ የአውሬነት ጠባይ እያሳየ ባለው የመንግሥት አካል ፊት ሕይወታቸውን እስከመስጠት ለክርስቶስ ታማኝ ሆነው መታየታቸው ታላቅ ጸጋ ሆኗል፡፡
5) በመላው ዓለም ያሉ ምእመናንን አንድነት አረጋግጧል፡፡
6) ቤተክህነት አባቶች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሸለ መናበብ፣ ታማኝነት፣ አንድነት፣ ጥብዓት አይተናል፡፡….
7)አኃት አብያተክርስቲያናት፣ የዓለም አብያተክርስቲያናት የነበራቸው ትኩረት የሚደነቅ ነበር (ከቤተክርስቲያን የውጪ ግንኙነትየእኛ የቤት ሥራ ገና ብዙ ነው፡፡)
8) የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳትፎና ቁጥጥራችን የተሻለ ነው፤ (ትዊተርን በመሰሉ ዓለም አቀፍ ጫና ለመፍጠር በሚረዱ ፕላትፎርሞች ላይ ያለብን ክፍተት መሞላት፣ የውጪ ቋንቋዎችን ተጠቅሞ መልእክት የማስተላለፍ ዝንባሌያችን ደካማ መሆኑ የሚታይ ሆኖ)፡፡

ስለዚህ ከዛሬው ይልቅ የነገው የከፋ ስለሚሆን የቤተክህነቱ፣ የቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ማኅበራት አገልጋዮች ፣ የመጣብንን ያስተዋሉ መላው ምእመናን ቤተክርስቲያን ያለባትን ሰፊ የቤት ሥራ ብዛት መቁጠር አለባቸው፡፡
ካህናት በሰሞኑ የመከራ ቅምሻ ውስጥ ሌሎች ወንድሞቻቸው ያጋጠማቸውን ሞትና መቁሰል፣ ጥፊና ካልቾ የእኔ ነው በሚል ራሳቸውን ለመከራ ማዘጋጀት መከራውንም ለመወጣት የሚያስችል ጽናት ለመላበስ መትጋት አለባቸው፡፡
ቤተክርስቲያንን ለመበታተን የተደገሰውን ሤራ በማወቅ እንዲሁም የክርስቲያኖች ስደት በሚገኙ ጊዜያዊ መፍትሔዎች ሳይዘናጉ፣ ዐቢይ ጾምን በብርቱ ጾም ጸሎት ማሳለፍ ይገባል፡፡
ለማንኛውም ቤተክህነት ራሱን ይፈትሽ፣ በእግዚአብሔር ረድኤት የአገልግሎት አቅሙን ያጎልብት፡፡
ማስዋሉን ይስጠን፡፡ አሜን፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የቅድስት ቤተክርስቲያን ትግል እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ይቀጥላል። ትግሏ የማያቋርጥ ነው። ሰይጣንም ዘመኑ እንዳለቀበት እያሰበ ፈተናውን እጅግ እያጠነከረ እና እያወሳሰበ ይመጣል እንጂ ዝም አይልም። በዚህ ጊዜ ምእመናን፣ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ ጳጳሳት ፈተናውን በድል ለመወጣት ልዩ ክርስቲያናዊ ጥበብ ያስፈልገናል። ትግላችን የ7515 ዓመት ሰውን በኃጢአት የመጣል ልምድ ካላቸው ረቂቃን ርኵሳን መናፍስት ጋር ነው። ከእኛ ያሉት ደግሞ ሰይጣንን በቅድስናቸው በረድኤተ እግዚአብሔር ያሸነፉ ቅዱሳን መለእክት፣ ቅዱሳን ሰማእታት፣ ሁሉም ቅዱሳን ናቸው። ከምንም በላይ የትግላችን መሪ ራሱ ክርስቶስ ነው። እና ሰይጣንን ለማሸነፍ የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ።
፩) እውነትን መያዝ
፪) ትሕትና
፫) ለበደልነው ንሥሓ መግባት
፬) ይቅርታ
፭) ፍቅረ እግዚአብሔር ወፍቅረ ሰብእ
፮) ኅብረታዊ መሆን
፯) እከብር ባይ ልቡናን መጣል
፰) ዘለዓለማዊነትን ማሰብ
፱) ረድኤተ እግዚአብሔርን መጠየቅ
፲) ክርስቲያናዊ ምግባራትን ሁሉ መፈጸም
ናቸው። ብንኖርም ለእግዚአብሔር እንኖራለን። ብንሞትም ለእግዚአብሔር እንሞታለን እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ። ኑሯችን ዘለዓለማዊነትን ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል። ሰይጣን በሰዎች አድሮ ሲፈትነን በጥበብ እናሸንፈው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 20:28:31
Back to Top
HTML Embed Code: