Telegram Web Link
በአጭሩ ዓረፍተ ነገሩ ሥጋ ወደሙን ዘወትር በመቀበል ሕይወት የሚኖርን ክርስቲያን የሚመለከት ቃል ነው፡፡ ይህ ክርስቲያን ፍጹም መንፈሳዊ ሕይወትን እየኖረ እንዳለ ምስክር የሚሆነው ሥጋ ወደሙን ከመቀበል የሚከለክለው ደዌ ወይም የታወቀ ምክንያት እንጂ አልቆርብም የሚል የኃጢአት ሰበብ አይደለም፡፡ እንዲህ ላለው ትጉሕ ቆራቢ ሰው ሁልጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየገሠገሠ መቁረብ ልማዱ ነውና አስቀድሶ አለመቁረብም ኀዘን ይሆንበታል፡፡ ለዚህ ሰው መቅድመ ተአምረ ማርያም ያጽናናዋል፡፡ ‘የታወቀ ምክንያት ወይም ሕመም ስለከለከለህ ባለመቁረብህ አትዘን ቢያንስ ተአምርዋን ሰምተህ ሒድ ፤ በዚያ ዕለት ልትቆርብ ተመኝተሃልና ሰምተህ በመሔድህ ያን ቀን ብትቆርብ የምታገኘውን በረከት አላስቀርብህም’ ነው፡፡ ይህ ግን ንስሓ አልገባም አልቆርብም ተአምርዋን ሰምቼ ይበቃኛል የሚል ብልጣ ብልጥ ትዕቢተኛ ሰው የሚሠራ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህንን ዓይነቱን ሰው ከመቁረብ የሚከለክለው ‘የታወቀ ምክንያት ወይም ደዌ ሳይሆን’ የኃጢአት ፍቅር ነው፡፡

ሦስተኛው ጥያቄ ‘ለሥዕልዋ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ የሚል እርግማን እንዴት በሐዲስ ኪዳን ይነገራል?’ ነው፡፡ ‘ለሥዕልዋ ስገዱ’ ማለት ለድንግል ማርያም ስገዱ ማለት ነው እንጂ እርስዋና ሥዕልዋን ነጣጥሎ ለማየት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ በእንተ ሥዕላት አምላካዊያት (On the Divine Images) ላይ ደጋግሞ እንደገለጸው በሥዕላት ፊት የሚደረግ ማንኛውም አክብሮትና ስግደት ለሥዕሉ ሳይሆን ለሥዕሉ ባለቤት ነው፡፡ ድርሳነ ሚካኤልም ‘ወሶበ ንሰግድ ቅድመ ሥዕላት አምላካዊያት አኮ ዘንሰግድ ለረቅ ወለቀለም ወለግብረ ዕድ’ ‘በእግዚአብሔር ሥዕል በተሳሉ በአምላካዊያት ሥዕላት ፊት ስንሰግድ የምንሰግደው ለወረቀቱ ለቀለሙ ወይንም ለሰው የእጅ ሥራ አይደለም’ ስግደትና ሥዕላትን በሚመለከት እነዚህን ቀደምት ጽሑፎች ይመልከቱ፡፡

‘በሐዲስ ኪዳን እንዴት እርግማን እንሰማለን’ የሚለው ተቃውሞ ‘እንዲህ የሚያደርግ መንፈስ የተወጋ ይሁን’ ‘ወግቼዋለሁ’ ሲሉ ከሚውሉ ሰዎች አቅጣጫ መነሣቱ አሁንም አስደናቂ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ጉዳዩ የሚረገመው አካልና እርግማኑ ተገቢነት ላይ እንወያይ እንጂ ሐዲስ ኪዳን ላይ ጨርሶ የግዝት ቃል ሥራ አቁሞአል ማለት አይቻልም፡፡ ጌታ በለስዋን ‘ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ ብሏታል’ /ማቴ. 21፡19/ ሐዋርያት ‘ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን’ ‘ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን’ ብለዋል፡፡ /ገላ.1፡8፣9/ እግዚአብሔር አያሰማን እንጂ በዕለተ ምጽአትም ‘እናንተ ርጉማን’ የሚለው ቃል የመጨረሻው ቃል ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ቃል ተራ እርግማን ሳይሆን በድርጊቱ የተገኙትን ከክርስትና ኅብረት የሚለይ በምድር ያሰረችው በሰማይ የታሰረ የሚሆንላት ቤተ ክርስቲያን የምትናገረው ቃለ ውግዘት (በግሪኩ Anathema) ነው፡፡ ይህም በተስፋ የምንጠብቃት መንግሥተ ሰማያት እስክትመጣና ‘ከእንግዲህ ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም፡፡ የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል ባሪያዎቹም ያመልኩታል ፊቱንም ያያሉ’ የሚለው ቃል እስከሚፈጸምልን ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ (ራእ. 22፡3)

የመጨረሻው ነጥብ ‘የድንግል ማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም እንጂ 16ቱን ትእዛዛት በመጠበቅ አይደለም እንዴት ይባላል?’ የሚለው ነው፡፡ መደጋገም ይሆንብኛል እንጂ አሁንም ጥያቄው ከእነርሱ መነሣቱ ያስደንቀኛል፡፡ ፕሮቴስታንቲዝም የትእዛዛት ተቆርቋሪ መሆን የጀመረው ከመቼ ወዲህ ነው? በማመን እንጂ ትእዛዝ በመጠበቅ አይዳንም በሚለው ትምህርት ምክንያት ስንት ውዝግብ አልተነሣም? ጳውሎስ የመገረዝን ሕግ ሥራ ለአሕዛብ ጽድቅ የግድ አስፈላጊ አይደለም ብሎ ያስተማረበትን ሮሜና ገላትያ ያለ አገባቡ በአጠቃላይ በጎ ሥራ አያፈልግም እንዳለ አድርገው በያዙት የተሳሳተ መረዳት ምክንያት በሰማይ በክብር አብረው የሚዘምሩትን ጳውሎስና ያዕቆብን ሳይጣሉ ያጣሏቸው እነርሱ አይደሉምን? አሁን ደግሞ ተአምረ ማርያምን ጎዳን ብለው እንዴት ትእዛዝ መፈጸም አያስፈልግም ትላላችሁ? ብለው ሲመጡ ማየት ምንኛ አስገራሚ ነው?

በመሠረቱ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እነሱ እንደሚሉት ሥራ ብቻውን ያጸድቃል ብላ አምና አታውቅም፡፡ ልጆችዋንም እኔ በጎ ሥራ አለኝ በእርሱ እጸድቃለሁ ብለው እንዳያስቡ ታስጠነቅቃለች፡፡ ጸሎትዋም መዝሙርዋም ‘ምግባር የለኝም’ ነው፡፡ ‘እንበለ ምግባር ተራድእኒ ፍጡነ ፤ ምግባርየሰ ኃጢአተ ኮነ’ ‘እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ ፤ ቦኑ በከንቱ ኪዳንኪ ኮነ’ ‘በምን ምግባሬ ፊትሽን አየዋለሁ’ ‘እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኜያለሁ’ ወዘተ የሚሉት እልፍ ምስጋናዎች ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋ በምግባሬ እጸድቃለሁ ብለው ተስፋ እንዳያደርጉና በክርስቶስ በማመናቸው (በሥጋ እንደመጣና ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ማመንን ይጨምራል) እና በእግዚአብሔር ጸጋ ወይም ቸርነት እንደሚጸድቁ (እምነት + ሥራ + ጸጋ) ታስተምራለች፡፡

የድንግል ማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም መባሉ የሚያበሳጨው ካለ መጽሐፍ ቅዱስ ‘ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ’ ይላል፡፡ ገላ. 5፡13 እንኳንስ ለአምላክ እናት አጠገብህ ላለው ወንድምህም በፍቅር ባሪያ ብትሆን ትጠቀማለህ እንጂ አትጎዳም፡፡ ለድንግል ማርያም ባሪያዋና ታዛዥዋ ብትሆን ግን ብዙ ትጠቀማለህ፡፡ ክርስቲያኖች ሆይ ልንገራችሁ ሁሉን ትታችሁ ለድንግል ማርያም ብቻ ታዘዙ፡፡ የእርስዋ ትእዛዝ አንድ ነው ‘የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ’ ዮሐ. 2፡5


+ ተአምራትን እንዴት እናያቸዋለን? +

መጽሐፍ ቅዱስ ‘የሐዋርያት ሥራ’ን የመሰሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል የሠሩትን ሥራ የሚተርኩ መጻሕፍት ያለበት መጽሐፍ ነው፡፡ ‘የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው’ በማለት ሕያዋን መጽሐፍት ወይም ተንቀሳቃሽ መጽሐፍ ቅዱስ /Living bible or moving bible/ ተብለው የሚጠሩትን የቅዱሳንን ሕይወት እንድናጠና እና በኑሮአቸው እንድንመስላቸው ያሳስበናል፡፡ (ዕብ. 13፡7) ቅዱስ ጳውሎስ ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ’ ብሎ እንደነገረን ክርስቶስን ለመምሰል የጳውሎስን የሕይወት ታሪክ ማጥናት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ (1ቆሮ. 11፡1) ራሱ ጳውሎስም ከእርሱ የቀደሙ የእምነት አርበኞችን አስደናቂ ታሪክ ከዘረዘረ በኋላ ‘ሁሉን እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል’ ብሏል፡፡ (ዕብ. 11፡32) ጳውሎስ የቅዱሳኑን ታሪክ ለመተረክ ያጠረው ጊዜ እንጂ ፍቅር አልነበረም፡፡

እግዚአብሔር በቅዱሳኑ አድሮ ያደረገውን መስማትም የቅዱሳን ታሪክ አካል ነው፡፡ ‘በሐዋርያት እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ’ ‘እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር’ እንደሚል እግዚአብሔር በባሪያዎቹ እጅ ታላላቅ ተአምራት ያደርጋል፡፡ (ሐዋ. 2፡42 ፣ 19፡11) የእስራኤል ንጉሥ ‘ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምር እስቲ ንገረኝ’ እያለ ግያዝን እየጠየቀ በደስታ ይሰማ እንደነበረ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያደረጉትን ተአምር መስማት ለምናምን ሰዎች እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ (2ነገሥ. 8፡4)
እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነውና እሱ ያደረገው ተአምር ምንም ቢሆን ከከሃሊነቱ አንጻር የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡ ለደካማው የሰው ልጅ ኃይል ሠጥቶ የሚሠራውን ነገር ስንሰማ ግን ኃይሉ በሰው ድካም ሲገለጥ ስናይ የበለጠ እናደንቃለን፡፡ የቅዱሳን ተአምር መቼም ቢደረግ በእግዚአብሔር እጅ የተደረገ ነው፡፡ ‘ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳችስ እንኳን ያለ እርሱ አልሆነም’ እንደሚል ድንግል ማርያም ያደረገችው ተአምር ሁሉ በእርሱ የተደረገ ነው፡፡ ተአምረ ማርያምም ራሱ ተአምረ ኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ተአምር ይሠራል ፤ ያለ ድንግል ማርያምም ተአምር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ድንግል ማርያም ግን ያለ እግዚአብሔር አንዳች ተአምር ልትሠራ አትችልም፡፡ ክርስቶስ ‘ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም’ ያለው ለዚህ ነው፡፡ (ዮሐ. 15፡5)

ኦርቶዶክሳዊያን ስለ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክዋን ፣ ዘለዓለማዊ ድንግልዋን ፣ መቼም መች መርገም ያልደረሰባት ንጽሕት መሆንዋ ፣ አማላጅነትዋን እናምናለን ፤ ከዚህ ፈቀቅ ሊያደርገን የሚሻ ቢኖርም እነዚህ የነገረ ማርያም መሠረተ እምነቶቻችን ናቸውና እስከ ሰማዕትነት ድረስ እንጸናለን፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል’ ‘የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም’ ብሎ ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. 12፡14 ፤ ማቴ. 17፡20) ስለዚህ ‘ያመነች ብፅዕት’ የተባለችው ድንግል ማርያም (ሉቃ. 1፡45) በልጅዋ አነጋገር ክርስቶስ የሚያደርገውን ተአምር ታደርጋለች ፣ ከዚያም የሚበልጥ ታደርጋለች ፣ የሚሳናትም የለም፡፡

ተአምራትን የሚያነብ ሰው በእምነት ካላነበበው ብዙ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ እውነት ለመናገር ይህ ከክህደት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊነት ደረጃችን ዝቅ በማለታችን የተነሣ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ በተአምራት መጻሕፍት ላይ ተደረጉ የሚባሉ ተአምራትን በእርግጠኝነት የሚያምን ልብ ቢኖረን ኖሮ ተአምራቱን እኛ ራሳችን ልንፈጽማቸው በቻልን ነበር፡፡ እኛ ግን እንኳንስ ተአምራቱን ልንፈጽማቸው ቀርቶ ተፈጽመዋል ብለን አምነን ለመቀበልም እንኳን ገና ነን፡፡ በዚህ የተነሣ የቅዱሳን ተአምራት ሲነበቡ ልባችን በጥርጣሬ ይናወጻል፡፡ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች ደግሞ ተአምራት ሲሰሙ ‘አቤት ተረት’ ለማለት ተነቦ እስከሚያልቅ ድረስ አይጠብቁም፡፡

በገድላትና ድርሳናት ላይ ያሉ ታሪኮችንና ተአምራትን ተረታ ተረት ናቸው ብሎ ለመደምደም ከቸኮልክ መጽሐፍ ቅዱስንም ማመንህ አስገራሚ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ? አንድ አባት ‘ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?’ ተብለው ሲጠየቁ ‘የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ’ ብለዋል፡፡ ‘አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው’ ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? ‘እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)

ወደ ተአምረ ማርያም እንመለስና ለመሆኑ ተአምረ ማርያምን ማን ጻፈው? ከየት መጣ? ተአምረ ማርያም ላይ የሚነሡ ብዙ ጥያቄዎች ሁሉም የተሳሳቱ ናቸው ሊባል ይችላል? ብፁዓን አባቶች "ተአምረ ማርያም ላይ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው" ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? በቤተ ክርስቲያንዋ በኩልስ በአዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ የሚነሡ ጉዳዮች የሉም? ሌሎች የሚያሳዩት ንቀትና ስድብ እንዳለ ሆኖ በአዋልድ በቤተ ክርስቲያንዋ እይታስ ምን እየተሠራ ነው? የዚህ ጽሑፍ ቀጣይ ክፍል ትኩረት ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት - ይቀጥላል
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 12 2015 ዓ.ም.

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
የፀሐይ ክብሩ ሌላ ነው
                         
Size 30.2MB
Length 1:26:39

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስ ፓትርያርኩ የጥምቀትን በዓል በማስመልከት መመሪያ ሰጡ።
ሰላም አምባዬ
(ኢኦተቤ ቴቪ ታህሣሥ  ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
                                             
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በካህናት አስተዳደር መምሪያ  በኩል የተዘጋጀው የ2015 ዓ.ም የበዓለ ጥምቀትን   አከባበር አስመልክቶ ከኦርቶዶክሳዊ ሕግና ሥርዓት አንጻር  ምን መምሰል እንደሚገባው  ከጠቅላይ  ቤተክህነት የሚተላለፈውን ሃይማኖታዊ  መልእክት እና አስተምህሮ እንዴት መተግበር እንደሚገባው  የሚዳስስ መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ  ታህሣሥ  ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ተካሔደ፡፡

የበዓለ ጥምቀት አከባበር   በቤተክርስቲያን ሕግና  ሥርዓትና መሠረት ኃላፊነት በተሞላውና ሥነ ምግባርን በተላበሰ  መልኩ   በሰላም ማክበር  እንደሚገባው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት   አባታዊ መልእክት  አስተላልፈዋል፡፡
ከቅዱስነታቸው በተጨማሪ ፣ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመ/ፓ/ጠ/ቤተክህነት  ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ  የአዲስ አበባ  ሀገረ ስብከት  ሥራ አስኪያጅ  እንዲሁም  የአዲስ አበባ  ገዳማትና  አድባራት  አስተዳዳሪዎች ፣ ቄሰ ገበዞች ፣ ሊቃነ ጠበብቶች እንዲሁም ሰባክያነ ወንጌል በተገኙበት  ምክክር ተደርጓል፡፡

በመርሐ ግብሩ   ላይ የበዓለ ጥምቀት አከባበር  ለኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  ያለውን  ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እና ማኀበራዊ ተግዳሮት መነሻ በማድረግ በበዓሉ አከባበር  ዙርያ ለሚታዩ    ችግሮች  የመፍትሔ  ሐሳብ የሚሆኑ አቅጣጫዎችን  የሚጠቁም  ጥናታዊ  ጽሑፍ  በዶ/ር በለጠ ብርሃኑ ቀርቧል፡፡
በጥናታዊ ጽሁፉ ላይ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልጠበቁ ቅዱሳት ስዕላትን ባልተገባ  ቦታዎች መስቀል ፣ ክብረ ክህነት በሌላቸው ግለሰቦች የሚከናወን የማእጠንት ሥነ ሥርዓትን  ፣አላስፈላጊ ጸብ ቀስቃሽ ከሆኑ በቲሸርት ላይ ከሚጻፉ ጥቅሶች እና ሃይማኖታዊ ትውፊትን ያልጠበቁ  ተግባራት መቆጠብ እንደሚገባ በጥናታዊ ጽሑፉ ተገልጿል፡፡
በጉባኤው  ብፁዕ አቡነ አብርሃም መ/ፓ/ጠ/ ቤተክህነት  ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጥምቀት በዓል አከባበር ዙርያ ሊኖር የሚገባውን ሃይማኖታዊ  የበዓል አከባበር  ሥርዓትን በተመለከተ  መልእክት አስተላልፈዋል  ፡፡
በተጨማሪም ቅዱስ ፓትርያርኩ  በዓለ ጥምቀትን ስናከብር ለሃይማኖታዊ  ዓላማችን ተሰልፈን የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች  የቅድስት ቤተክርስቲያን  ሕግና ሥርዓት ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ  መሆን እንደሚገባ  ገልጸው በቅዱስነታቸው  መልእክት እና ቃለ ምእዳን  የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡
  EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ እሴቶቻችንን እየጠበቅን በዓላትን ማክበር እንደሚገባ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተናገሩ ፡፡                 
መምህርት ኑኀሚን ዋቅጅራ
(ኢኦተቤ ቴቪ ታህሣሥ  ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  በሕገ ኦሪት ፣በሕገ ልቦና እና በሕገ ሀዲስ  ሕግና ሥርዓትን ሠርታ  ፊደላትን ቀርጻ ፣ ቁጥሮችን ቀምራ ለቤተክርስቲያንን እና ለሃገር ያስረከበች የታሪክ ባለውለታ  መሆንዋ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት ከሚታዩት አላስፈላጊ ኢ ሥነ ምግባራዊ ተግባራት በመቆጠብ ባህልና ሃማኖታዊ ትውፊትን በሚገባ  ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ  ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በካህናት አስተዳደር መምሪያ  በኩል በተዘጋጀው አጠቃላይ የምክክር  እና የውይይት ጉባኤ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሃ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ዘርፈ ብዙ አባታዊ መልእክታትን ያስተላለፉ ሲሆን በተለይም በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ ከዚህ በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ከስራ ገበታቸው የታገዱ አገልጋዮችን ከሚመለከታቸው አካላት በመተጋገዝ አሁን ያለንበትን ችግር በመፍታት በዓሉን በደስታና በፍቅር እንድናከብረው ይገባል ብለዋል፡፡

አያያዘውም  ብፁዕነታቸው  በአሁኑ ሰዓት  በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን  አስተምህሮ እና  እምነቷን በማይገልጹ  አላስፈላጊ  ተግባራትን  በማውገዝ  መልእክታቸውን ላስተላለፉት ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ምስጋናቸውን በማቅረብ በስፍራው ላልተገኙት የሃይማኖት ተቋማት ተወካይ አባላት ላይ የተሰማቸውን ቅሬታም ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ  በአሁኑ ሰዓት በሀገር እና በቤተክርስቲያን ላይ እየተንጸባረቁ  ያሉት  ችግሮች  አኗኗራችን በሙሉ   ክርስትያናዊ ሕይወታችን ከአንደበት በዘለለ በሕይወት መኖር ያለመቻላችን ውጤት መሆኑን   በመልእክታቸው አስተላልፈዋል ፡፡

በመጨረሻም በዓለ ጥምቀት በቤተክርስቲያን የአደባባይ  በዓል እንደ መሆኑ መጠን ብዙ ምእመናን  የምናስተምርበት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ  አስተምህራችንን ለዓለም  በተግባር  የምናሳይበት ሀማኖታዊ እሴቶቻችንን በተግባር የምናሳይበት በዓል እንደመሆኑ መጠን ሥነ ምግባር በተላበሰ መልኩ ልናከብረው እንደሚገባም  ብፁዕ አቡነ  ሄኖክ የአ/አ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ   ገልጸዋል፡፡
EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
መንግስትህ ትምጣ
                         
Size 22.6MB
Length 1:04:59

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሥርዓተ ትምህርታችን
(የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥርዐተ ትምህርት)
ሁላችሁም እንደምታውቁት ሥርዐተ ትምህርታችን
የእኛና የእኛዎቹ የኤርትራውያን የአብነት ትምህርት አሰጣጥ አቀራረጹ ልዩ ነው።ገና በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሲል ብቻ አፉን ሲፈታ የሶስቱን ስም በመጥራት የሥላሴን ሶስትነት፥ አሐዱ አምላክ በማለት አንድነታቸውን ፥በቅድስት ሥላሴ በማለት የሴት ቅጽል ለሥላሴ(ለሶስትነት)በመስጠት ለሥላሴ ሴት ወንድ ተብሎ ጾታ አይነገርላቸውምና እንደማይነገርላቸው ፥በስመ አብ ላይ ብቻ እንኳን በርካታ ትምህርተ ሃይማኖት አለን። ሲቀጥል አቡነ ዘበሰማያት ሲገባ
የማቴዎስ ወንጌል ሥድስተኛውን ምዕራፍ መማር ይጀምራል።በሰላመ ቅዱስን ሲማር፥የሉቃስ ወንጌልን ይማራል፤ጸሎተ ሃይማኖትን ባጠና ጊዜ በውስጡ ያሉትን አምስቱን አእማደ ምሥጢርና በሦስቱ አካላት ማመን እንደሚገባ ያጠናል።ቅዱስ ቅዱስን ሲማር ትንቢተ ኢሳይያስን ያገኛል።እሰግድን ስብሐትን ሲማርም ሃይማኖተአበው ጎርጎርዮስን ያጠናል።ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን ሲያጠና እመቤታችን በሉቃስ ወንጌል ላይ የተናገራችውን ያጠናል።በቀኑም ትምህርት ከመልእክት ለይተው መልእክተ ዮሐንስን አውጥተው ከታች ጀምረው እንድንማረው ሊቃውንቱ መምረጣቸው ድንቅ ነው።
በመልእክተ ዮሐንስ ውስጥ የሌለ ምን ድንቅ ምሥጢር ይኖራል?ቀደማዊነት ደኃራዊነት አለ።ነገረ ሥጋዌ በእርግጥ ተዳሷል ተተንትኗል።ለዚያ ነው።የሐዲስ ኪዳን ተማሪ የሚማረውን መልእክተ ዮሐንስን ከታች ከፊደል ቀጥሎ እንድንማረው ማድረጋቸው፥ ምሥጢሩ በአእምሯችን ታትሞ በጭንቅላታችን ተቀርጾ እንዲቀር ነበር።ከወንጌል ለይተው የዮሐንስን ወንጌል የላይኛውን ትምህርት ከታች ማውረዳቸው ከታች ንባቡን ከላይ ትርጓሜውን እንድንማረው ነበር።ነገር ግን ትምህርታችን በንባቡ ብቻ የሚጠናቀቅ ሆነ።ከዚህም የተነሳ አበው የሰሩት የትምህርት ካሊክረሙ እጹብ ድንቅ የሚያሰኝ ቢሆንም አንድ እክል ገጥሞታል ብየ አምናለሁ።እርሱም
የሚማሩትን ሳያውቁት መማር ፥የሚያጠኑትን ሳያውቁት ማጥናት ፥ይሸመድዱታል ግን ምን እንደ ሸመደዱ አለማወቅ፥ አደገኛ ምክንያት ሁኗል።ስልሳ አራት ውዳሴ ማርያም በጭንቅላቱ ሸምድዶ ይዞ አንዷን እንኳን ምን እያለች እንደሆነ አለማወቅ ያሳዝናል። መቶ ሃምሳ ዳዊት አንብቦ ጨርሶ ምንም አንዱን እንኳን ምን እያለ እንደሆነ ሳያውቁ መቅረት ያሳዝናል።አወ ንባቡ ተጣይና ሰያፉ ወዳቂዉና ተነሹ ራሱን የቻለ ከባድ ትምህርት ነው።ግን ደግሞ በዚሁ ብቻ መጠናቀቁ ያሳዝናል።የንባባቱን ምሥጢር ሳይረዱ መቅረቱ ፧ምናልባት አንድ ተማሪ
ከዘወትር ጸሎት እስከ መልክአ ኢየሱስ ድረስ ሁለት ዓመትም ሦስት ዓመትም ሊይዝበት ይችላል።ግን ሦስት ዓመት ሙሉ ሳይገባው ሲያጠና ይኖራል።በእሑድ ውዳሴ ማርያም ውስጥ ኦሪትን ተምሯል።ግን ምን እንደተማረ አላወቀም።በሰኞ ውስጥ ሥጋዌን ተምሯል ግን አላወቀም።በማግስተሰኞ ውስጥ ትንቢተ ነቢያትን ተምሯል
ግን አላወቀም።......ምን ያልተማረው ነበር?ግን ይደግመዋል ከመነጋገር ባለፈ ምን እያለ እንደሆነ ያውቀዋል ለማለት አልደፍርም።እኔ ወገኖቼን መተቼት ፈልጌ ሳይሆን ሂደቱን ነው እንዲታይ የምፈልገው።ሥር ዐተ ትምህርት አቀራረጹ ከሁሉም የተለየ ቢሆንም በተቀረጸው ልክ መራመድ ባለመቻላችን፥በሆነ ምክንያት የተሰራውን ነገር ይዘን መቀጠላችን አደገኛ ክስተቶችን ሲያስከትል ይታያል።ግን ለምን?እስቲ ሁላችሁም አስቡ ?ቁጥር ዘልቃችኋል፤ግብረ ድቁና ዘልቃችኋል ፤አቋቋምም ድጓም ዝለቁ፤ግን ትርጓሜውን ካልተረዳነው ምን እያዜምን እንደሆነ ማወቅ እንችላለን?ያንን ግሩም ዜማ ያንን ድንቅ ድጓ እያዜምን ምን እያለ እንደሆነ ካልተረዳን አደገኛ ሕይወት ሁኗል ጉዟችን።የድጓ የአቋቋም አጠቃላይ የዜማ ትምህርቶች ምን ያህል ፈታኝ አድካሚ እንደሆኑ የሚያውቅ ያውቃቸዋል።ግን አሥራ አምስት ዓመት ደክሞ ያንን የደከመበትን አለመረዳት አሳዛኝ ነው።ይህን ስል ብዙ ድጓ እስከ ትርጓሜ አሟልተው የያዙ አባቶቻችን እንደ አባታቸው እንደ ቅዱስ ያሬድ ያሉ መኖራቸውን አውቃለሁ።ሌሎቹም ድጓ አቋቋም መምህር ሁኖ ቅኔ ያልተቀኘ ብዙም አይኖርም
ይሁን እንጅ ከታች ጀምሮ ያለው የትምርት ሥርዓታችን የሚያስደንቅም የሚያሳዝንም ነው።ቅኔን መጽሐፍን በኋላ መማር የፈለገ ሰው አስቀድሜ ድጓ ልማር ብሎ ድጓ ቢማር ምናልባትም አሥር አሥራ አምስት ዓመት ምን እያዜመ እንደሆነ በዜማው ውስጥ ያለውን የንባብ ምሥጢር
ሳይረዳው ይደክማል።ልክ የዜማ ስልቱን ጉረሮውን ጭረት ድፋቱን ለመያዝ የሚደክመውን ያህል በመካከል ትንሽ ትርጓሜውን ፥ወይም የተማረው ምን ማለቱ እንደሆነ መረዳት ቢችል እንዴት በታደልን ነበር!ድጓን ያህል ያንን ግሩም ትምህርት በብሉይና በሐዲስ የተንቆጠቆጠ ። ትምህርት ተምሮ ሊቁ ያልተማረ ይመስል አንገቱን ደፍቶ የኔ ቢጤ ይጫወትበታል።ለምን ይህ ይሆናል?ቀዳሹ ዲያቆን አሥር ዓመት ቀድሶ ምን እንዳዜማ ምን እንዳነበበ ሳያውቀው እንደምን ይኖራል?ሕዝባችን እግዚኦ ሲባልና አሐዱ ሲባል ካልሆነ ምን እንደምንል፥ ያውቃል ወይ?አሁን አሁን ንባቦች በምናውቀው ቋንቋ እየተነበቡ ተደራሽ ቢሆኑም ነገር ግን ፈጽሞ እየተተገበረ ነዎይ?እስቲ ገጠር እንውጣ? ተአምረ ማርያም እንኳን በአማረኛ አይሰሙም ።ያሳዝናል ግን ለምን?ቤ/ክርስቲያናችን ሀገር አቀፍ የሆነውን ቋንቋ ግዕዝን ሁሉ ሲጥለው በጉያዋ ደብቃ ማትረፏ ድንቅ ቢሆንም ግን ደግሞ በውስጧ ያሉት ልጆቿ ሁሉም እርሱን አለመካፈላቸው ያሳዝናል።ስለዚህ ትምህርተ ሥርዓታችን አሳዛኝም አስደናቂም ነው።በዚህ ምክንያት ብዙ ጥቃቶች ይታያሉ በሽ የሚቆጠሩ ካህናት ዲያቆናት አሉን።ይህ እሰይ የሚያሰኝ ነው።ግን የተማሩትን ከሚረዱበት ትምህርት ሳይደርሱ በመደቆናቸውና በመቀሰሳቸው ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ተሸክመው ግን አላዋቂ ሲባሉ ይውላሉ።ብሉይ ሐዲስን አጥንተው እንዳላጠኑ ሁነው ይኖራሉ።ስለዚህ ይህ ነገር አሁንስ ለምን አይታይም? በውዳሴ ማርያም ፥በመልክአማርያም ፥በመልክአ ኢየሱስ መሀክል፥ ወይ በራሱ ውስጥ ያለውን ምሥጢር አልያም ካሊክረም ቀርጾ እየተማሩ መኖር አይገባቸውሞይ?እንዴት ስልሳ ዓመት ሃምሳ ዓመት ቀድሶ ምን እንደቀደሰ ምን እንዳነበበ ሳያውቀው ይሞታል?ያሳዝናል እኮ!ስለዚህ ቀዳሾችም አስቀዳሾችም በተለይም ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ !ንባቡንስ እየተረጎምን በቋንቋችን እናንበበው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ግን ጌታ ሲፈጥረው ባሕርዩን ግዕዝ አካሉን ዜማ አድርጎ ነው። ስለዚህ ባሕርይን ከአካል መለየት እንደማይቻል፥የያሬድን ዜማም ከግዕዝ መለየት አይቻልም። እንለይ ካልን ግን በፍጹም የያሬድን ዜማ ማግኘት አንችልም።ምናልባት ሌላ ምድራዊ ዘፈን ካልሆነ በስተቀር ፥ስለዚህ ስለ ብዙ ነገር ሲባል ግዕዝንም፥ቅኔንም መማር ይኖርብናል።ያለዚያ አገልግሎታችን ሁሉ ከነፋስ ጋራ እንደማውራት ሊሆን ይችላል።ወይ የመደቆኛ የመቀሰሻ መስፈርቶች አሁንም ይታዩ ይዳሰሱ።አልያም ደግሞ ከታች ስለሃይማኖታቸው የሚያውቁት ነገር መሰራት አለበት።ከዚህ በላይ የሚያስቡ አበው ይህንን ሳያስቡት ቀርተው እንደ አዲስ እያሰብኩት ሳይሆን፥ አዲስ ገጠመኞች ሲመጡ ይህንን እንዳወጣው አስገደደኝ።እና ምናልበት በአበው ዘንድ ቢታይ፥በሊቃውንት ጉባኤ ቢዳሰስ? እላለሁ።።።ከልጆች አንደበት!ለአበው፥
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/11/15 12:47:07
Back to Top
HTML Embed Code: