Telegram Web Link
Audio
እንደዚህ ያሉትን እወቋቸው 
                                                  
Size:- 27.8MB
Length:-1:19:49
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
1ኛ. የፍሥሓ ያዜን የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ የልብ ወለድ መጽሐፍ እውነት አድርገው የያዙ ሰዎች ያሳዝኑኛል።

2ኛ. ኢትዮጵያን ከዓለም ሁሉ በንጽሕና የተለየች ቅድስት ሀገር እንደሆነች የሚናገሩ ሞኞችም ያሳዝኑኛል። ኢትዮጵያ ማለትኮ አሁን ላይ ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ሰው በቋንቋ በብሔር እየተለየ የሚጨፈጨፍባት፣ የሰባት ዓመት ሕፃን የሚደፈርባት፣ የሁለት ዓመት ሕፃን የሚታፈንባት አሳዛኝ ሀገር ናት። እንኳን የዓለም ብርሃን ልትሆን ጨለማው በርትቶባት እየማቀቀች ያለች ሀገር ናት።

3ኛ. የካህናትን፣ የጳጳሳትን ችግሮች ጠቅሰው ምእመኑን አስኮብልለው ለራሳቸው ዓላማ የሚያታልሉ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባሉ ነቀዞች አሉ።

4ኛ. ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ሥጋዊ ሞትን የሚፈራ ለትክክለኛ ነገር ሰማዕትነትን የማይወድ ሆዳም ማኅበር ነው። ሥጋዊ ምቾትን ፈልጎ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ተደብቆ የሚኖር የፈሪዎች ስብስብ ነው።

5ኛ. ለችግሮች መፍትሔ መስጠት የምንችለው እኛው ተመካክረን እንጂ ከእኛ ውጭ የሆነ ቴዎድሮስን በመጠበቅ እኛ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሳናደርግ በማለፍ አይደለም።

6ኛ. ቴዎድሮስን የሚያነግሥ እግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር በላይ እኛ ካላነገሥነው ብላችሁ ልባችሁ ውልቅ ያለ ሰዎች አትልፉ። ግላዊ ፍላጎታችሁን በቴዎድሮስ አታሳቡ።

7ኛ. አለቃ አያሌው አቡነ ጳውሎስን አውግዘዋል የሚሉ አስቂኝ ሰዎችም አሉ። ቄስ ጳጳስን የማውገዝ ሥልጣን የለውም። ዐይነ ሥውርም ቄስ መሆን አይገባውም።

8ኛ. የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ታሪካዊ ስለሆነ እንወደዋለን። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ስለዚህ በምንወደው ባንዲራ ሕዝብን ማጭበርበር ቢቆም።

ከዚህ የነቀዘ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ስብስብ ራሳችሁን አድኑ።

© በትረ ማርያም አበባው

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ክርስትናና ሚዲያ እንዴት? 
                                                  
Size:- 102.2MB
Length:-1:50:26
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ጳጕሜን_3
#ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት_ወመልከጼዴቅ_ካህን
‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤::

#እንኳን_ለቅዱስ_ሩፋኤል_በዓለ_ሢመትና_ለቅዳሴ_ቤቱ_በ4ኛው_መቶ_ክ_ዘመን_በቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ዘእስክንድርያ_አማካኝነት_በሚደንቅ_ተዓምራት_በአሣ_አንበሪ_ጀርባ_ደሴት_ላይ_ለታነጸው_ቅዳሴ_ቤት

#እንዲሁም_ለካህኑ_መልከጼዴቅ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን_፡፡

# ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው። ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው። (“ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ” እናዳለ /ጦቢ ፲፪፥፲፭/፡፡

✤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::
✤ ለሄኖክ ወልደ ያሬድ 6 ዓመት በእግረ ገነት ወድቆ ሳለ ኅበዓቱን ክሡታቱን አሳይቶታል። መ.ሄኖክ 8፡5
ቅዱስ ሩፋኤል ሰማያውያን መዛግብትን በእጁ የሚጠበቁ በመሆናቸው "ዐቃቤ ኖኅቱ ለአምላክ" ይባላል፡፡ እግዘአብሔር እንዳዘዘው የሚዘጋቸው የሚከፍታችው እርሱ ነው፡፡
✤✤✤ ቅዱስ ሩፋኤል ሰውን በመርዳት ሲኖር የነበረውን የጦቢትን ዓይን ያበራና፤ ሣራ ወለተ ራጕኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው አስማንድዮስ ጋኔን (ያገባችውን ባል የሚገድል) አላቅቆ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት ያደረገ በመኾኑ “ፈታሔ ማሕፀን (መወልድ/አዋላጅ፥ ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
” ና ‹‹መልአከ ከብካብ›› ተብሏል (ዛሬም ድረስ የእናቶች ሐኪም ነው)፤ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ቤቱንም በበረከት ሞልቶታል፤ በዚህም ፈዋሴ ቊስል (ድውያን)፥ ዐቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ) ተብሎ ይጠራል፡፡
#ጦቢት ልጁን ወደ ሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ወደ ገባኤል ቤት ሲልከው መንገዱን የመራው አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ ነው፤ በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡
#ቅዱስ ሩፋኤል በራማ ሰማይ ሁለተኛ ክፍል ላይ የሰፈሩትንና መናብርት በመባል የሚጠሩትን 10ሩን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ነው፤ በዚህም ‹‹ሊቀ መናብርት›› ተብሎ ይጠራል፤ መናብርት የሚባሉት መላእክት ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ፥ የእሳት ጦር ይዘው፤ ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ፤ ከእነዚኽ 10ር ነገደ መላእክት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡


በኢትዮጵያ በቅዱስ #ሩፋኤል ስም ከተሰየሙት ቤተ ክርስቲያን መካከል፤
1,ጎንደር ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሩፋኤል  ወአቡነ ሐራ ድንግል  ወቅዱስ ያሬድ  ቤተ ክርስቲያን (ጐንደር)፤ በአፄ በካፋ የተመሠረተና ዚቅ እንደተጀመረባቸው ከሚነገርላቸው ቦታዎች አንዱና ታላቁ ደብር፡፡
2,አዲስ አበባ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፤ በ1878 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የተመሠረተና ባላ አንድ ጣሪያ ያለው ቀደምት የአዲስ አበባ ደብር፡፡
3,ደብረ ዘይት (አየር ኃይል) ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ.
4,ወላይታ ዳሞት ፑላስ ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ.



#በብዙኃን_ዘንድ_ለሚነሱ_ጥያቄዎች_መልስ_፡፡
#መልከ ጼዴቅ ማነው?
#አባትና እናትስ የሉትምን!?፤
#የሰው ዘር አይደለምን!!?፤
#እውን መልከ ጼዴቅ ክርስቶስ ነውን?!!!!

✤✤ #መልከ_ጼዴቅ_ማነው_?
መልከ ጼዴቅ በዘመነ አብርሃም የነበረ የሳሌም ንጉሥ እንዲሁም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነው /ዘፍጥ.14፤ ዕብ. 7/፡፡ ይህ ሰው አብርሃም ጠላቶቹን ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን ድል አድርጎ ዮርዳኖስን ተሻግሮ በተመለሰ ጊዜ አብርሃምን ሊቀበለውና ሊባርከው ኅብስትና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ ባረከውም አብርሃምም ደግሞ ለመልከ ጼዴቅ ከምርኮው ዐሥራት አወጣ፡፡
(ኅብስትና ወይኑ የቅዱስ ቊርባን፣ መልከ ጼዴቅ የካህናት፣ አብርሃም የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌዎች ናቸው)፡፡
ካህኑ መልከ ጼዴቅን ‎ቅዱስ ዻውሎስ         "የትውልድ ቊጥር የለውም፤ ለዘመኑም ጥንትና ፍጻሜ የለውም" ብሎ ያስቀመጠው /ዕብ.7፥3/፤ ለወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሲያደርገው እንጂ ትውልዱ ከነገደ  ‎ካም ነው፡፡ ወላጆቹም ‹‹#ሚልኪና #ሰሊማ  ›› ይባላሉ፡፡

በፋሬስ ደግሞ፤ ፋሬስ የኦሪት ዛራ ደግሞ የወንጌል ምሳሌዎች ናቸው፤ ዛራ እጁን አውጥቶ መመለሱ ወንጌል በመልከ ጼዴቅ ታይታ የመጥፋቷ ምሳሌ፤ ፋሬስ ጥሶ እንደወጣ በመሀል ኦሪት ተሠርታለች፤ ዛራ ሁለተኛ እንደመወለዱ ወንጌልም ቆይታ ተሠርታለች፡፡
   
#መልከ ጼዴቅ ክርስቶስን በአራት ነገሮች ይመስለዋል፤

#1. መልከ ጼዴቅ ማለት የጽድቅ ንጉሥ የሰላም ንጉሥ ማለት ነው፤ ክርስቶስም ደግሞ አምላከ ጽድቅ አምላከ ሰላም ነው፣
#2. መልከ ጼዴቅ በኅብስትና በወይን ያስታኵት /ያመሰግን/ ነበር፤ ክርስቶስም ሥጋና ደሙን በኅብስትና በወይን ሰጥቶናል፣
#3. መልከ ጼዴቅ በመጽሐፍ ቅዱስ እናቱና አባቱ አልተጠቀሱም ክርስቶስ ደግሞ ለሰማያዊ ልደቱ እናት ለምድራዊ ልደቱ አባት የለውም፣

በዓለማችን በመልከ ጼዴቅ ስም የተሰየመው ብቸኛው ቤተ ክርስቲያን፡፡ ደብረ ዘይት ሂዲ መልከጼዴቅ፡፡


‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤
የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግበት፥
አራተኛው መጋቤ ኮከብ (ሕልመልመሌክ) የሚያልፍባት፤
ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት
ሰማይ የሚከፈትባት ቀን፤ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ጸሎት የሚያርግባት፤ በዚህም ‹‹መዝገበ ጸሎት›› /የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው/ ይባላል፡፡
የጌታችን ዳግም ምጽአት የሚታሰብባት ዕለት፤
በዚህም ምክንያ አባቶቻችን በዚህች እለት 365 አቡነ ዘበሰማያት ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
" የልባችሁን አእምሮ አድሱ " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት " ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብ እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ " በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም " በገሃዱ ዓለም የማያረጅ እና የማይታደስ የለም መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መካከል መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስ የስነ ፍጥረት አንዱ አካል ስለሆነ በየጊዜው ይታደሳል። እኛ ሰዎችም በየጊዜው እንድንታደስ እግዚአብሔር አዞናል ፤ ዘመንም እንደሌላው ያረጃል ይታደሳል ፤ ዛሬ አሮጌውን ሸኝተን አዲሱን የምንቀበልበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

የተወደዳችሁ ምእመናን ፍጥረታትን ማደስ የእግዚአብሔር ሥራ ቢሆንም ከፈጣሪ በተሰጠው ሥልጣን ሰውም የማደስና የመምራት ሥልጣን አለው። ዛሬ ዓለማችን በመታደስ ሳይሆን በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሳ ነው። እየተፈጠረ ያለው ችግር ከሰው አጠቃቀም ስህተት እንደሆነ እየሰማን እና እያየን ነው።

ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ሰው ምደረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት የሚቀይርበትንም ሁኔታ እያየን ነው ፣ይህ ሰው የማልማትም ሆነ የማጥፋት ሚና እንዳለው ያሳያል። ሰዎች የላቀ እድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል። የዚህን ተቃራኒ ይዘው የተጓዙ ከሆነ ማርጀትን ይዘው እየተጓዙ ስለሆነ በመታደስ መኖር አለብን።

የተወደዳችሁ ምእመናን የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻ ግብ የፍጥረታት መታደስ ነው። ከሞት በኋላ ትንሳኤ ፤ ከዚያም እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘለዓለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው። ከዚህ አንጻር ሰው ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንዳለበት ፤ እግዚአብሔር የፍጥረቱን መታደስ በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድርም ስለሚፈልገው ዘመንን እየለወጠ ይመግበናል። ስለዚህ እኛስ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ ብለን ራሳችንን መጠየቅና መልሱን ማግኘት ወሳኝ ነው። ለመታደስም ቆራጥ ውሳኔ በመወሰን አዲሱን ዘመን ልንጠቀምበት ይገባናል።

እኛ ኢትዮጵያን ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩት ሁሉ ወደ ኋላ እየቀረን ከችግሮቻችን ላለመላቀቅ ውል የገባን እስኪመስል ድረስ እየቀጠልንበት ነው። ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን እንዲህ ሆነን ስንገኝ ከስንፍናችን በቀን ምንም የጎደለን እንደሌለ ሌሎችም የሚያውቁት ነው። ስለዚህ ለእኔ ለእኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃ አናስረዝም። ኢትዮጵያ የሁሉም ናት ፤ በእኩልነት እና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከ3000 ዓመታት ውስጥ ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም። በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተገጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም ፤ ሕዝቡም በፈጣሪው የሚያምን ስለሆነ ከዚህ ውጭ እንምራው ብንል ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው ስለዚህ የሁሉም መነሻ ውጣዊ አእምሮአችኝ ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት ሀገራችንን እንድናድስ ጥሪ እናቀርባለን።

አዲሱ ዘመን በውይይት ፣ መለያየትን በአንድነት ፣ አለመግባባትን በእርቅ ፈትተን ሁላችንም በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረሰብን ለመገንባት ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።"

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#በዓለ_ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት_ዮሐንስ_ወቅዱስ_ራጉኤል
#እንኳን_አደረሳቹ

#ዐዲስ_ዓመት

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና /ሔኖክ. 21፥49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ በፍል ውኃ አጥለቅልቆ በኃጢአት ሕይወት ይኖሩ የነበሩት የኖኅ ዘመን ሰዎች ቀጥቶ ካጠፋ በኋላ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው /ኩፋሌ. 7፥1/፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስቀምጣሉ፡፡


የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በክታባቸው እንዳስቀመጡት በአራቱ ወንጌላውያን ዘመኑን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ በዘመነ ማርቆስ ተጠምቋል፡፡ በዘመነ ሉቃስ ተሰቅሎ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ አውጥቷል፤ እያሉ ታሪካዊ ሐረጋቸውን ጠብቆ አራቱ ወንጌላውያን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ::

#እንቁጣጣሽ

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ስትመለስ “እንቁ ለጣትሽ /ለጣትሽ እንቁ/ በማለት ከእንቁ የተሠራ የጣት ቀለበት ንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ እንዲሆናት አበርክቶላት ነበርና ይህን ታሪክ መነሻ አድርገው “እንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ ከዚያ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ያስረዱናል ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ምድሪቱ በክረምቱ ዝናብ ረስርሳ ድርቀቷ ተወግዶ በአርንጓዴ እጸዋት ተውባ ሜዳው፣ ሸለቆውና ተራራው በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠው የሚታዩበት ወቅት በመሆኑ ዕለቱ “እንቁጣጣሽ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ ወቅት ሕፃናትና ልጃገረዶች ነጭ ባሕላዊ ልብስ በመልበስ ለምለም ቄጤማና አደይ አበባ በመያዝ በአካባቢያቸው በመዞር አዲስ ዘመን መበሠሩን “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት በቸርነቱ ዓመታትን የሚያፈራርቀውን እግዚአብሔርን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡

መልካም_አዲስ_ዓመት

#ራጉኤል ሊቀ መላእክት:-

ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው።

አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው።  በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23) አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው።  በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል።

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/24 04:18:10
Back to Top
HTML Embed Code: