Telegram Web Link
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፳፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ አሳውቁን)
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፲፫) #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ካዛንቺስ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ካዛንቺስ፡፡
፪. ኤረር በር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል፡፡
አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ኤረር በር፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ→ ኤረር በር፤
፫. አዲስ ሰፈር አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል፣ መጥምቁ ዮሐንስና ልደታ ለማርያም፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አዲስ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ኮልፌ → አንፎ፡፡
፬. ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ፉሪ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ኮልፌ → ፉሪ፡፡
፭. ጎፋ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም መካነ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ
አድራሻ፤ ጎፋ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጎፋ ካምፕ →  ጎፋ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#እንዲሁም_በድርብነት_
፮. ድልበር መካነ ጎልጎታ መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቶታል/ድል በር/ (ጎጃም በር)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → አዲሱ ገበያ → ቶታል፡፡
፯. አስኮ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለምና ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንየ ክፍለ ከተማ፥ አዲስ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ /ከአቡነ ጴጥሮስ/ → አስኮ፡፡
፰. አውግስታ ደብረ ጽዮን ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ኮልፌ → አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ፡፡
፱. ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ታቦት ማደርያ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ኮልፌ → ታቦት ማደርያ፡፡
፲.  ቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤ ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ቱሉ አቦ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → አቃቂ → ቱሉ አቦ፡፡
፲፩. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚከኤል፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ፡፡
፲፪. ላፍቶ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለምና መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መካኒሳ → ላፍቶ፡፡
፲፫.  ሐመረ ወርቅ ማርያምና አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወርቁ ሰፈር፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ፡፡

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፮ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩ መንዝ ዕመጓ ደብረ ቆጵሮስ ኢየሱስ ቅዱስ ዑርኤል ገዳም፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መንዝ፡፡
፪. ግሸን ቅዱስ ዑርኤል፤
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ግሸን ደብረ ከርቤ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ግሸን፡፡
፫. ጎንደር ደብረ ኀይል ቅዱስ ዑርኤል ወበዓታ፤
አድራሻ፤ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥  ጎንደር ከተማ
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፬. ደብረ ታቦር አንቀፀ አድህኖ ቅዱስ ዑርኤል፤
አድራሻ፤ ደ. ጎንደር ሃገረ ስብከት፥  ደብረ ታቦር ከተማ
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ታቦር፡፡
፭. የወልዲያ ቅዱስ ዑርኤል ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥  ወልዲያ  ከተማ
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ወልዲያ ፡፡
፮.  ደብረ ብርሃን ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል ፤
አድራሻ፤ ሰ. ሸዋ ሃገረ ስብከት፥  ደብረ ብርሃን  ከተማ
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን፡፡


ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከበርባቸው_ #፫ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ጀርመን ደብረ ኃይል ቅዱስ ዑርኤል ወቅዱስ ያሬድ፤
አድራሻ፤ ጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
፪. ደብረ ብርሃን ቅዱስ ዑርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አሜሪካ ሜንሶታ
፫. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አሜሪካ ሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
የኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ የቀረበው የረከሰ ድርጊት ሲታይ በተቀደሰው ምሥጢረ ቊርባን ላይ የተፈጸመ የድፍረት ኃጢአት ነው

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በ2024 የዓለም ኦሎምፒክ ስፓርታዊ ውድድር መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የተካሄደውን አስነዋሪ ትዕይንት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ  መግለጫ ተሰጥቷል።

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።

“ይእዜ ኀሥረ ክብሮሙ ወተኀፍረ ገጾሙ ወተቃወመቶሙ ኀጢአቶሙ ከመ ኀጢአተ ሰዶም ወገሞራ አስተርአየት ወተዐውቀት ላዕሌሆሙ፤ አሌ ላ ለነፍሶሙ እስመ መከሩ እኩየ ምክረ ላዕለ ነፍሶሙ፡- ዛሬ ክብራቸው ተዋረደ፣ የፊታቸውም ዕፍረት ይመሰክርባቸዋል ኀጢአታቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ኀጢአት ተቃወመቻቸው በላያቸውም ተገልጣ ታወቀች፡፡ ክፉ ምክርንም መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት፡፡
ኢሳ.3 ፥ 9”

የ2024 የዓለም ኦሎምፒክ ስፓርታዊ ውድድርን በማስመልከት ባለፈው ዓርብ በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር July 26 በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የሚሠጠውን ምስጢረ ቊርባንን ያቀለለ፣ የተመሳስይ ጾታ ጋብቻን፣  የግብረ ሰዶማውያንን እኩይ ተግባር በወገንተኛነት የተደገፈ ትርኢት ማሳየታቸውን በዓለም ዜና ማሰራጫ ተመልክተናል።

በየዐራት ዓመቱ በሚከናወነው የዓለም ኦሎምፒክ ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የቀረበው የረከሰ ድርጊት ሲታይ በተቀደሰው ምሥጢረ ቊርባን ላይ የተፈጸመ የድፍረት ኃጢአት ነው፡፡

በተጨማሪም የሃይማኖትን ነጻነት የሚጋፋ፣ ጾታ የሚለውጡ ሰዎችን የሚያበረታታና በአጠቃላይ በክርስትና ሃይማኖትና በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመ ቀጥተኛ ጥቃት ስለሆነና ከሰለጠነው ዓለም የማይጠበቅ፣ የሌሎችን የእምነት የባህልና የማኅበራዊ ዕሴት ማክበር ልዩ ቦታ በሚሰጠው የኦሎምፒክ ስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በሰው ልጅ ሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም አንዱ የሌላውን የእምነትና የአምልኮ ነጻነት በማክበር እንዲኖር በሃይማኖት ቀኖናት ብቻ ሳይሆን በዓለማችን ላይ ባሉት ሀገራት የሰብአዊ መብትና የእምነት ሕግጋት የተደነገገ ሆኖ ሳለ ከኦሎምፒክ ስፖርት ጋር በማይገናኝ ሁኔታ በውድድሩ መክፈቻ ትዕይንት የተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር ሃይማኖታችንን የሚጋፋ፣ መንፈሳዊ እሴቶቻችንን የሚያጠፋ ክብረ ነክና ሊወገዝ የሚገባው ሰይጣናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡

የዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ኮሚቴና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላትም ይህንን በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ የቀሰቀሰውን ጸረ-ሃይማኖት የሆነ አስነዋሪ ድርጊት በመኮነን የአምኮልን መብትና ነጻነት እንዲያስከብሩ፣ ድርጊቱን በግልጽ እንዲቃወሙ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

                ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም.
                    አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Statement from the Permanent Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Regarding the scandalous scene 
at the opening ceremony of the 2024 World Olympic Games

The shew of their countenance doth witness against them; and they declare their sin as Sodom, they hide it not. Woe unto their soul! For they have rewarded evil unto themselves.  (Isa. 3:9)
In the opening ceremony of the 2024 World Olympic Games, that took place on Friday, July 26 2024 in in the city of Paris, France, we saw a scandalous scene that degrades the sacrament of Holy Communion, which is highly respected by all Christians and promotes same-sex marriage, homosexual activities and anti-Christian cults.
The act of showing such scene is a blasphemous sin against the sacrament of Holy Communion; it violates religious freedom and encourages transsexuals. In general, the scene is a direct attack on the Christian religion and Christians. Such act is unacceptable both in human life style and Christian scriptures.
The shown disgraceful act is forbidden and condemned not only by religious canons but also by the laws of the various countries in the world. The disgraceful act that was openly broadcasted on the world stage is a satanic act that should be condemned. Therefore, the Permanent Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church strongly condemns and sends a spiritual call to all affiliated bodies to condemn the disgraceful act that has aroused great anger among the Christian religion and all Christians, to respect the rights and freedom of worship, and to openly oppose the act.

July 29, 2024
Addis Ababa, Ethiopia
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ወርኀ_ሐምሌ_የሰማዕታት_መታሰቢያ_ወር (ሐምሌ 5 ጴጥሮስና ጳውሎስ፤ ሐምሌ 15 ቂርቆስና ኢየሉጣ፤ ሐምሌ 24 አባ ኖብ ድንግል፤ ሐምሌ 25 መርቆሬዎስ) 
   #share
#ሐምሌ_፳፭_የምናከብረው_ክብረ_በዓል፤ ፨ ታላቁ ሰማዕት (‹‹ካልዕ ሊቀ ሰማዕታት››) ቅዱስ #መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) ዓመታዊ የዕረፍት በዓሉ
1.  ✤ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ልደቱ ሲሆን ድንቅ ተአምር ያደረገበትና ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡ እንዲሁም በሐምሌ 25 ዓመታዊ በዓላቸው የኾነ ቅዱሳንም የሚከተሉት ናቸው፡፡
2.  ✤ዳግመኛም ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉት የኢትዮጵያዊው የአቡነ ሕፃን ሞዐ ዕረፍታቸው ነው፡፡
3.  ✤የነቢዩ ሄኖክ ዕርገቱ ነው፡፡
4.  ✤የቅዱስ ጳውሎስ ረዳት የነበረችው የሰማዕቷ የቅድስት ቴክላ ዕረፍቷ ነው፡፡
5.  ✤ሰማዕቱ ቅዱስ ዱማድዮስ ዕረፍቱና ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡
6.  ✤ሰማዕቱ ቅዱስ አበከረዙን ዕረፍቱ ነው፡፡
7.  ✤ሰማዕቷ ቅድስት ኢላርያ ዕረፍቷ ነው፡፡
8.  ✤ሰማዕታቱ ቅድስት ቴክላ እና ቅድስት ሙጊ ዕረፍታቸው ነው፡፡
9.  ✤ሰማዕቱ ቅዱስ እንዲኒና ዕረፍቱ ነው፡፡
10.  ✤ሰማዕቱ አቡነ ይስሐቅ ዕረፍቱ ነው፡፡
11.  ✤የ600 ሰማዕታት መታሰቢያቸው በዓላቸው ነው፡፡
12.  ✤እንዲሁም ዛሬ የ25 ሺህ የአትሪብ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው፡፡
በዚህ ወርም (ሐምሌ 22 ዕ ብጽዑ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ   በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ ፣ ወጣቶች ፣ መዘምራን ወ.ዘ.ተ  ይዘከራሉ )
#በሃገራችን_ከሚገኙ_የቅዱስ_መርቆሬዎስ_ክብረ_በዓል_ከሚከብርባቸው_ዋነኞቹ፡፡
✥1. ደብረ ጽባሕ ጸዶየ መርቆሬዎስ፤ በአጼ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡
✥2.ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም፤ ‹‹ደጃች ውቤ ደረስጌ ደብረ ጽዮንን በወርቅና በዕንቊ ከመሥራታቸውም በላይ ታቦተ መርቆሬዎስን ማምጣታቸው ተብሎ የሚነገርለት›› ተዓምር አድራጊ ስዕል የሚገኝበት ቤ.ክ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠበት)፤ ራስ ደጀን አጠገብ፤ ጃናሞራ (መካነ ሰላም ከተማ)
✥3. ጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋም ማርያም፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ
✥4. ጋሹ አምባ አርማንያ ቅዱስ መርቆሬዎስ (ሰሜን ሸዋ፤ ደብረ ሲና)፤ ስዕሉ በበዓለ መርቆሬዎስ ቀን የሚያሸበሽበው፡፡
✥5. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኡል (አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ
✥6. ደብረ ሲና ቅ.እግዚአብሔር አብ(አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ
✥7. አዲስ አበባ ጎፋ ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ ወዮሐንስ መጥምቅ ቤ.ክ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር ይኑራችሁ
        
Size:-26.4MB
Length:-1:15:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Forwarded from Ab 1st Sam 7:12
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች

👉 Youtube
https://www.youtube.com/@eotc-gssu

👉 Telegram
https://www.tg-me.com/eotcgssu21

👉 Tiktok
https://www.tiktok.com/@eotc_gssu

👉 Facebook
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
Forwarded from Ab 1st Sam 7:12
Forwarded from Ab 1st Sam 7:12
ኹለተኛው የአኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) 27/11/2016 ዓ.ም

ኹለተኛው የአኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር  ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መ/ፖ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የባ/ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ቀለሚንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋሪያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የማደራጃና የድርጅት ሐላፊዎች ፤ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሐላፊዎች አባቶች ካህናት መምህራንና ተመራቂ ተማሪዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሒዷል።

በመርሐ ግብሩም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሐላፊ የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት  ለተማሪዎች ያስተላለፉ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ የሆኑት ዲያቆን ስንታየሁ ምስጋናውም የሥልጠናውን ዓላማና ጠቀሜታ በአጭሩ ለታዳሚዎች ገለፃ አድርገዋል።

"ለራሳችሁ አይደላችኹም ስለዚህ፥በሥጋችኹ እግዚአብሔርን አክብሩ።" 1ቆሮ 6፥20 መነሻ በማድረግ የዕለቱን ቃለ ወንጌል ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ አብርሃም  "ቤተ ክርስቲያን ከናንተ ብዙ ትጠብቃለች በሔዳቹበት ሁሉ አገልግሎታችሁ በትዕግስትና በፍቅር ይሁን" በማለት አባታዊ ቡራኬና መመሪያ ለተመራቂ ተማሪዎች አስተላልፈው  ለተማሪዎች የምሥክር ወረቀት ሰጥተዋል።

ተመራቂ ተማረዎች መሠረተ ሃይማኖት ፣ አስተዳደር፣ ክህሎትና ሥርዓተ ት/ትን በሚመለከቱ 3 ዘርፎች ከ 20 በላይ ኮርሶችን በተከታታይ ለ20 ቀናት በቀንና በማታ መርሐ ግብር የወሰዱ ሲሆን በምርቃት መርሐ ግብራቸውም ላይ አጠቃላይ ቆይታቸውን በሪፖርት መልክ እንዲሁም ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok
Forwarded from Nigatu Ye Enatu Lij
2024/09/25 16:29:43
Back to Top
HTML Embed Code: