Telegram Web Link
“መንፈሳዊው ገበሬ”
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

“አንድ ገበሬ ዘር መዝራት ስላለበት ብቻ እንዲሁ አይዘራም፡፡ አስቀድሞ መሬቱን ማረስ፣ ማለስለስ አለበት፡፡ ካረሰ ካለሰለሰ በኋላ ዘሩን ይዘራዋል፡፡ አሁንም ግን መዝራቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የዘራውን ዘር አፈር ሊያለብሰው ይገባዋል፡፡ እንዲያ ካላደረገ ወፎች መጥተው ይለቅሙታልና፡፡ ልክ እንደዚሁ እኛ ክርስቲያኖችም በእኛ ላይ የተዘራውን ዘር (ቃለ እግዚአብሔር) በየጊዜው እንደ ገበሬው የማንከታተለው ከሆነ በአየር ላይ እንደተዘራ ዘር ይሆንብናል፡፡ ሰይጣን ይለቅምብናል፤ የራሳችን ስንፍና እንዲጠወልግ ያደርጓል፤ ፀሐይ ያደርቋል፤ ጐርፍ ይወስዷል፤ እሾክ አንቆ ይይዟል፡፡

ስለዚህ ዘር ዘርቶ ዞር ማለት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ በየጊዜው መኮትኮት፣ ወፎችን ማባረር፣ የበቀለ አረም ካለ ማረም፣ ጭንጫ የበዛበት አከባቢ ካለ የለሰለሰ አፈር መጨመር፣ በየጊዜው መከታተል፣ አጥር ማጠር፣ እንዲሁም ማንኛውም የተዘራውን እህል ሊያበላሹ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት በሰብሉ እርሻ የገበሬው ትጋት ብቻ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መሬቱ ግዑዝ ነገር ስለሆነ፡፡ በመንፈሳዊው እርሻ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ኃላፊነቱ የገበሬው ማለትም የመምህሩ ብቻ አይደለም፡፡ ከግማሽ ወይም ከዚያ በላይ የደቀመዝሙሩ (የምእመኑ) ኃላፊነት ነው፡፡ በርግጥ መምህሩ ዘሩን መዝራት አለበት፡፡ ነገር ግን ደቀ መዝሙሩ የተነገረውን ቃል ሁል ጊዜ መስማት ብቻ ሳይሆን ማድረግም አለበት፤ በግብር ፍሬ ማፍራት አለበት፤ የበቀሉ አረሞች ካሉ በየጊዜው መንቀል አለበት፡፡

የገበሬ ልጆች በሰብሉ መካከል የበቀለ አረም ካለ እንዲሁ ጫፍ ጫፉን ብቻ አይቈርጡትም፡፡ ከሥር ይነቅሉትና በመጨረሻም በእሳት ያቃጥሉታል እንጂ፡፡ በእኛ ላይ የበቀሉ አረሞችም (ጥርጥሮች፣ ክሕደቶች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ማነቆ የሆኑብንን ነገሮች…) ከሥራቸው ነቅለን ልናቃጥላቸው ይገባናል፡፡”
Audio
ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳሰተማረው

የህጻናት ልጆች አስተዳደግ


የልጆቻችን ገዳይ ማን ነው ⤴️
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው

መግቢያ እና መጻሕፍት ለሚያነቡ ኦርቶዶክሳውያን
የተሰጠ ተግሣጽ (1)⤴️

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


የተሰጠ ተግሣጽ (2) የጸሎት ጥበብ1 ~2#⤴️

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ

ዕንባ :ስብሐተ እግዚአብሔር :
ምስጋና ምንድነው?
ተዘክሮተ እግዚአብሔር
ሰለ የተኛው እናመሰግን ?
እግዚአብሔር ተጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመሰግነው ⤴️

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ :ደስተኛ መኸን ትፈልጋለህን?
አቤቱ ጌታችን ስምህ በምድር ሁሉ ምንኛ ድንቅ ነው መዝሙር 8÷1
ታሰበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው መዝ 8÷4

አቤቱ በፍጹም ልቤ ለአንተ እናዘዞለሁመ መዝ 9÷1

አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቆአልና መዝ 11÷1⤴️

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ :ለባል የተሰጠ ምክር?

ለምስት የተሰጠ ምክር?

በትዳር ውስጥ ማን ማን ይታዘዝ ?

ሳትጠብቅ ኃላፊነታችሁን ፈጽሙ?

ክፉ ሚስቱን አልፈታም ሰላለው ፈላስፋ ጥበብ ?

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ :ትዳር የመንፈሳዊ ሕይወት ዕንቅፋት አይደለም

ትዳር አንድ ማሠልጠኛ ማዕከል ሊኾን ይገባል

ሰለ ጌጠኛ ልብስ??

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ ሰለ ጌጠኛ ልብስ??

ባል ሆይ ??

ባልና ሚስት አይን እጅ??

ከምንም በፊት ባልና ሚስት ሊሹት የሚገባው ጉዳይ ???

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠
/ማቴ ፫:፫/

"" እነዚህስ ይሂዱ ተዉአቸው! ""
(ዮሐ. ፲፰:፰)

"ገድለ ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕት
(ዘኢትዮጵያ)"
(ሐምሌ 22 - 2014)


በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ :- የባልና የሚስት ፍቅር ውጤት!

ትዳር ደስታን የሚያመጣው በምን ሲኾን ነው?

ትዳር አንድ አያያዙ ነው!

ኃላፊነትን ሰለ መወጣት

ቅዱሳንን ማክበር ጥቅሙ ለማን ነው?

ቅዱሳንን የመዘከር ጥቅሙ

ሰለ ሰማዕታት ስናስብ

አንድ ጥበብ አሳያችኋለሁ

የሕይወታችን ጣራና ግድግዳ

የባለጽጎች ኃጢአት



ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
እስልምና እምነት ተከታይ ለአንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ለጠየቀቻት ጥያቄ

መልስ ነው

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
አረሳት ኢትዮጵያን በእርፈ መስቀል አባ ተክለሐይማኖት ሰባኪ ወንጌል
አረሳት ኢትዮጵያን

አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ

ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
አዝ
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ :- ለምን አንዳንድ ድኻ አንዳንድ ግን ባለጸጋ ሆነ ??

ገንዘብ ለምን አሰፈለገ??

ደኻ ነኝ አትበል??

ለምጽዋት የሚበልጥ የለም

ንብ

መተማመን ያለብን

ሀብቱንና ችሎታውን በነጸ የሚሰጣጥ ማኅበረሰብ

ፆም



ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር ኪዳን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
*ሂድና ራስህን ለካህን አስመርምር*
*(የማቴዎስ ወንጌል ፰፥፬)*
በመምህር በላይ ወርቁ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
ደቂቃው *//24:11//*
2024/10/02 20:40:55
Back to Top
HTML Embed Code: