Telegram Web Link
🔴 አዲስ ዝማሬ " እኛ ግን ስላንቺ " ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
🌹🌹🌹የነገስታት ንጉስ 🌹🌹

*የነገሥታት ንጉስ ፈጣሪን ወልደሽ*
*እንዴትስ መመስገን ማርያም ይነስሽ*
*አለም ለማመሰገን እውነቱ ቢከብደው*
*እኛ ግን ሰላንቺ የምንለው ብዙ ነው*



አዝ
ከሰማያት መጣ የሚደነቅ ክብር
ሰማን ከገብርኤል ላንቺ ሲነገር
እውነቱን ለማወቅ አለም ምን ጋረደው
የህይወት ምግብ ከማን ነው ያገኝው
*እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሺ*
*እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሺ*(2)

አዝ
ማንም ሰው ለእናቱ ክብር እንደሚሻ
ላንቺ ያለን ፍቅር ይለውም መጨረሻ
ስንዘምር ስንጠራሽ አለም ብዙ ቢለን
የገባንን እውነት እንዲያየው ወደድን
*እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሺ*
*እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሺ*(2)

አዝ
ዝም የሚል አንደበት ይለንም ለክብርሽ
በደማችን ሰረጾአል ስምሽና ፍቅርሽ
ፀሐይን ሰላይ አለም ደስ ካለው
አንቺን ለማመሰገን ሰለምን ከበደው
*እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሺ*
*እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሺ*(2)

አዝ💚🥀

ከቶ በሰው ፍቃድ ፍጹም ያላየነው
እናት ሆኖ ድንግል አንቺ ነው ያየነው
ገና ብዙ ብዙ ቃላት አለን
አንቺን ከማመሰገን ማን ነው የሚያሰተወን
*እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሺ*
*እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሺ*(2)


አብርን ኑ እመብርሃን እናመሰግን👏

*ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ ክብር መሰቀሉ ይቆየን አሜን*

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ እንዳስተማረው


ርዕስ:-ክፉ ሥራ የሚሠራ ካህን ስትመለከት
ንጉሰና ካህን ሲነጻጸሩ

የገዛ ራሱን ሰጠን

ለቤተክርስቲያን ለቅዱሳት ምሥጢራት ሊኖረን ሰለሚገባ ክብርጨ

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ለቤተክርስቲያን ለቅዱሳት ምሥጢራት ሊኖረን ሰለሚገባ ክብር

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ለቤተክርስቲያን ለቅዱሳት ምሥጢራት ሊኖረን ሰለሚገባ ክብር

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ለቤተክርስቲያን ለቅዱሳት ምሥጢራት ሊኖረን ሰለሚገባ ክብር

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር

31
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ለቤተክርስቲያን ለቅዱሳት ምሥጢራት ሊኖረን ሰለሚገባ ክብር

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Photo
=============
ምሁር ኢየሱስ ገዳም
============
ምሁር ኢየሱስ ገዳም የሚገኝው በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ ኢየሱስ ገዳም ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ207 ኪ.ሜ፣ ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ በ52.ኪ.ሜ፣ ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ሀዋርያት 3ኪ.ሜ ገባ ብሎ በስተሰሜን ምስራቅ በኩል ይገኛል፡፡

ገዳሙ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት መካከል በዋናነት ተጠቃሽ ሲሆን በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ዮዲት ጉዲት በፊት በ804 ዓ.ም እንደተተከለ ታሪክ ያስረዳል፡፡

በገዳምነት የተመሰረተው/ የተገደመው / ደግሞ በኢትዮጵያዊው ፃዲቅ በአቡነ ዜና ማርቆስ በ13ኛ ክ.ዘ /በ1250 ዓ.ም/ መሆኑን መዛግብት ይጠቁማሉ፡፡ አካባቢው ከባህር ወለል 2330 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡

የገዳሙ ይዞታ ስፋት ወደ 10 ሄክታር የሚጠጋ ሆኖ በጠቅላላው 3 ትላልቅ ግቢዎች ሲኖሩት እነዚህም ግቢዎች እንደገና በተለያዩ ትናንሽ ግቢዎች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ማለትም የዘመናዊ ትምህርት ቤት ግቢ፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ግቢ፣ የካህናት ማሰልጠኛ ግቢ፣ ሙዝየም ግቢ፣ የሴቶች መነኩሳት ግቢ፣ የዋናው ቤተክርስቲያን ግቢ፣ የወንዶች መነኩሳት ግቢ፣ የከብት ርባታ ግቢ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የገዳሙን ዕድሜ ረጅምነት የሚያወሱ ብዛት ያላቸው ሀገር በቀል የዝግባ፣የወይራ፣የፅድ ወዘተ ተፈጥሮአዊ ይዘት ያላቸው ዛፎች እጅብ ብለውና ግርማ ሞገስ ተላብሰው ወደ ገዳሙ የሚመጣውን ሰው በመጀመሪያ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ይቀበሉታል፡፡

ሌላው የገዳሙን ጥንታዊነት እና ታሪካዊነትን የሚያመላክቱ ተዳሳሽና የማይዳሰሱ ቅርሶች ሲገኙ ተዳሳሽ ከሆኑ ቅርሶች መካከል ለመጥቀስ ያህል የብር መስቀል፣ የብራና መፃህፍት፣ መቁራሪት፣ ጽዋ፣ ደወል፣ የቀደምት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ካባ፣ መለከት/ጡርንባ/፣ ውዥግራና ራስማር ጠመንጃዎች፣ ከአንድ ወጥ እንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ የመጾር መስቀል፤የቅዱስ ዳዊትን ታሪክ የያዘ በስዕላዊ መልክ የተዘጋጀ መፅሐፍ ከነማህደሩ፤የነገስታት ደብዳቤዎች … ወዘተ ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በአቡነ መልከ ፃዲቅ ጵጵስና ዘመን ከተለያዩ ሀገሮች በገጸ በረከትነት የተበረከቱ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትና ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ለአብነት በ1990 ዓ.ም ከሊባኖስ ለገዳሙ የተበረከተ የእጅ መቁጠሪያ ፣ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሱራፌል የተበረከተ የግሪክ ስዕል፣ የተለያዩ ጌጣጌጦች፣ የሰጎን እንቁላል እና መብራት ያላቸው መስቀሎች፣ ከግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢንቶኒዮስ የተበረከቱ የቤተ መቅደስ መገልገያ ጽዋ የስነ-ስቅለት ምስል ያለበት መስቀል ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጲያ ሰዓሊያን በእንጨት ላይ የሳሏቸው ስዕሎች፣ ኢትዮጲያ ፓትሪያርክ መሾም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩና አሁን ያሉ ፓትሪያርኮች ፎቶግራፍ በሙዝየሙ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ገዳሙ በአጠቃላይ ከሚሰጣቸው ኃይማኖታዊ፣ባህላዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ለመግለፅ ያህል በሃዋርያት ከተማ ውስጥ የመዋዕለ-ህጻናት ተምህርት ቤት፣ የእንግዳ መቀበያና ማረፍያ ቤት፣ በገዳሙ ግቢ ውስጥ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ት/ቤት፣ የተለያዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች ማምረትና መሸጥ፣ የእንግዳ ማረፍያ ቤቶች፣ በወልቂጤ ከተማ ደግሞ ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ 10ኛ ክፍል ባለሶስት ፎቅ ህንጻ ት/ቤት አስገንብቶ በማስተማር የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

ገዳሙ ዓመቱን ሙሉ የተለያዩ መንፈሳዊ ጎብኚዎች የሚጎበኙት ሲሆን በዋናነት ሶስት አበይት ክብረ በዓላት አሉት፡፡ እነሱም፡-
ታህሳስ ሶስት የአቡነ ዜናማርቆስ የእረፍት ቀን መታሰቢያ፣ ለረጅም አብይ ፆም አጋማሽ(ደብረዘይት) ልዩ የበገና ምሽት፣
በግንቦት ወር ውስጥ አብይ ፆም በተፈታ አርባኛው ቀን(የእርገት በዓል) ሲሆኑ በእነዚህ በዓላት ወቅት ቁጥሩ በዛ ያለ ከተለያዩ የአካባቢው፣ የሃገሪቱ ክፍሎች እና ከሃገር ውጪ በሚመጡ ቱሪስቶች በድምቀት ይከበራል፡፡

ገዳሙን ሊጎበኙ ሲሄዱ በተጓዳኝ ሊታዩ ከሚችሉ ስፍራዎች መካከል፡-
አቡነ ዜናማርቆስ ለ40 ዓመት የፀለዩበት፣ በውስጡ ጸበልና የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቅርሶች ያሉበትና በተፈጥሮ ደኖች የተከበበው ከሬብ ዋሻ፣በከሬብ ወንዝ ላይ የሚገኘው የሐረግ ድልድይ፣የጉራጌ ብሔር ባህላዊ አኗኗር እና የመንደር አመሰራረት(ጀፎረ) እና ሌሎችም ይገኛሉ።

ስለዚህ ይህ ታላቅና ጥንታዊው ሙህር እየሱስ ገዳም ይጎብኙ መልዕክታችን ነው።
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -አብያተ ቤተክርስቲያን

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ና በቆጵሮስ ደሴት ይኖሩ ሰለ ነበሩት ባሕቴውያን

ቤተክርስቲያን መከፋፈል ማለት

አታገኝውም

የእሳት ገሃናም ከባድነት

እግዚአብሔር በእሳት ገሃናም የሚያሰፈራን ለምንድነው ?

ባትመለሱ እግዚአብሔር ሰይፍን ይስላል መዝ 7÷12


ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ሞትን የምንፈራው ለምንድንነው


ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው፤ ኤልያስንም ያሳረገው፣ አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊያስነሣቸው ማንም አይችልም።
ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች፤ ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ፤ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ፤ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።
ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
እንግዲህ እናስተውል! ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ ”እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው‘ እንዴት አላት?። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት? ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት? አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ?
ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው? አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ? ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ነሐሴ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Photo
በዓለ ደብረ ታቦር
ነሐሴ ፲፫፤ ፳፻፲፬ ዓ.ም

በተከበረች በነሐሴ ፲፫ በታቦር ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ”በዓለ ደብረ ታቦር‘ ተብሎ ይከበራል፡፡
በዚህችም ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን ”የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ‘ አለ።
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ። ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው፤ ”አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን? ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፤አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።‘
በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ፤ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።
የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ”ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው፤  እርሱንም ስሙት።‘ ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ፤ ስለ እርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ፤ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው፤ ኤልያስንም ያሳረገው፣ አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊያስነሣቸው ማንም አይችልም።
ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች፤ ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ፤ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ፤ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።
ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
እንግዲህ እናስተውል! ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ ”እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው‘ እንዴት አላት?። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት? ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት? አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ?
ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው? አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ? ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ነሐሴ
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ጸሎተ ፍትሐት
ለምን እንሞታለን

በቀርብ ሥነ ሥርዐት ይህን አሰተውል

የነፍስ ሞህ ምንድን ነው

ለምንድን ነው የምንፈራው

ድርሳን በእንተ ሞት

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -ድርሳን በእንተ ሞት

ሁሉም ያልፍል ይረግፌል

አታልቅስ

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር
Audio
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወረቅ  እንዳስተማረው


ርዕስ: -አመስግን

የእርገት ድርሳን

ተርጉሜ :-ገብር እግዚአብሔር

የረዳን እግዚአብሔር ይመሰገን በዚህ ተፈጸመ
2024/10/02 20:42:13
Back to Top
HTML Embed Code: