Telegram Web Link
Allstudents list to use the new studentportal.xlsx
1.5 MB
Student Portal

የሁሉም ተማሪ መረጃ የሚካተትበት የተማሪዎችን User name እና password የያዘ ፋይል ከላይ ተያይዞላችኋል።

በID ሊስት ስር የራሳችሁን user name ካገኛችሁ በኋላ https://studentportal.dbu.edu.et/ በመግባት የራሳችሁን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

እንደ password የምትጠቀሙት username በSmall latter በማድረግ እና በመጨረሻም ከusername በኋላ ከሚገኘው ቁጥር ቀጥሎ # በማስገባት ነው።

ለምሳሌ
user name= Dbu612673
Password= dbu612673#

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለክረምት ነባር ተማሪዎች
@DBU11
@DBU11
ፈተናው በሰላም ተጠናቋል!

በደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ ሐምሌ ከሀምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለ3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ማጠቃለያ ፈተና በስኬት፣በሰላምና በጥሩ ስነ-ምግባር ተጠናቋል፡፡ከሁሉም ወረዳዎች የመጡ ተፈታኝ ተማሪዎች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም

@dbu11
#ማጭበርበር

እየተከናወነ ያለው ተመራቂ ተኮር ሌብነት ምን ይመስላል?

ይህም ሰራ ፈጠራ መሆኑ ነው እንግዲህ..

በተቀናጀ መልኩ የስራ ማስታወቂያዎችን በማውጣት በ0 ዓመት የስራ ልምድ ለስራ እናወዳድራለን በሚል ውሸት ብዙ ተመራቂ ስራ ፈላጊ ተማሪዎች እየተሸወዱ እንደሆነ ይስተዋላል።

ውድ ስራ ፈላጊ ተመራቂዎች ስራ ለመወዳደር የምትገኙበትን ቦታ እና ቀጣሪዎቻችሁን በውል ሳታረጋግጡ ክፍያን አትክፈሉ።

@Dbu11
#Alert

ማጣት ለማጣት ምክኒያት አይሁን!

ከትንንሽ ገቢ፣ወይም ከቤተሰብ ድጋፍ ላይ የምንቀራርማት ሳንቲም ላይ አሰፍሳፊው ብዙ ሆኗል

ለጥንቃቄ እንዲሆናችሁ ዛሬ የቅርብ ጓደኞቼ ጋር ለማጭበርበር የደረሳቸውን Scam ላስተዋውቃችሁ።

ዌብሳይቱ registers.infinitypowersvip.com ነው። እንሰራለን የሚሉበት መንገድ የሆነ ያህል ሺ ብሮችን ከእናንተ ኢንቨስት እንድታደርጉላቸው እና ኢንቨስት ባደረጋችሁላቸው ብር መጠን በ% ታስቦ ትርፋችሁ እንደሚደርሳችሁ ያሳውቋችኋል።

ለመተማመን እንዲሆን የመጀመሪያዎቹን ዙሮች በእርግጠኝነት ትርፍ ልታዩ ትችላላችሁ። ከተወሰኑ ዙሮች በኋላ ግን የምትመድቧቸው ብሮች አይመለሱም።ተጠንቅቃችሁ ከሰራችሁ ሳይቀድሟችሁ ልትቀድሟቸውም ትችላላችሁ።

እንድታውቁ ምፈልገው ግን ስካም ነው!

እስኪ ለማረጋገጥ አንዳንድ የ ስካም ቼክ መንገዶችን ላሳያችሁ።

ማረጋገጫ
  Trust Score (የእምነት ውጤት) በ scamadviser.com እይታ መሰረት የእምነት መጠኑ ዝቅተኛ የሚባል ነው።


Source Code and Registry:  The algorithm scans the source code, terms, conditions, and registry information to assess legitimacy


Negative Highlights:
ማንኛውንም site whoIs (xxxx) x ቦታ ማረጋገጥ የምትፈልጉትን አስገብታችሁ ሰርች ብታደርጉ የዚያን ሳይት ትክክለናነት ታረጋግጣላችሁ.

በተጨማሪም scam-detector.com  ላይ በቀጥታ ስካም ነው የሚል ሜሴጅ አለው።

The Tranco rank (traffic) is low.

በዚህ ሳይት ላይ  iframe ወይም inline frame ተገኝቶበታል። ይህ ማለት እናንተ ከምትጠቀሙት ገጽ በተጨማሪ የምትጋሩት ገጽ አለ ማለት ነው። ይህ መጥፎ ነገር ባንለውም  ግን በስካም ስራ ውስጥ የመጀመሪያው መንገድ ተጠቃሚውን ያለፍቃዱ ወደሌላ ገጽ መክተት ነው።

Consumer Reviews:
   የተጠቃሚዎች ምላሽ በሚታይበት ሰዓትም whatsapp ላይ በተሰራው ጥናት መሰረት ከፍተኛ የተካዱ ፈንዶች ፈጻሚ ስር ተካቷል።

በአጠቃላይ እንዲህ አይነት ስካም ሳይቶች የበዙ በመሆናቸው እያንዳንዳቸውን ጠቅሶ ማረጋገጥ ስለሚታክት በራሳችሁ መንገድ ጥናት ብታደርጉባቸው እና ከዘራፊዎች እንድትጠበቁ ምክራችን ነው።

ደሞ እናንተ ማን ስለሆናችሁ ነው ምንም ሳትሰሩ ብር ምትጠብቁት ... እ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
እንኳን ደስ አለን!

#Internet

ለረጅም ወራት በአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት ከዛሬ ጀምሮ በቋሚነት ተለቋል!

@DBU11
@DBU_entertain
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲተ ለ2016 ዓ.ም የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጻ አደረገ።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለመጡ የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን 6-8/11/2016 ዓ.ም ተቀብሎ ሀምሌ 08/2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚሰጡ አገልግሎቶችና አጠቃላይ ስለፈተናው ሂደት ገለጻ አደረጓል፡፡

በገለፃው ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንዳሉት ተፈታኝ ተማሪዎች በዚህ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆናችሁ ለፈተና በመቅረባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ለዚህ ስኬት ያበቋችሁ ወላጆች፣መምህራንና የትምህርት አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የነገው ሃገር ተረካቢ ትውልድ በመሆነችሁ ራሳችሁን አረጋግታችሁ ትኩረታችሁን ፈተናው ላይ በማድረግ የሀገሪቷን ከፍተኛ ውጤት እንደምታስመዘገቡ ምኞቴ ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

ለተፈታኝ ተማሪዎች  በዋናነት ስለ በመብትና ግዴታቸው፣ስለጊዜ አጠቃቀም፣የፈተና ወረቀት አጠቋቆር እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮችንና ተዛማጅ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፈተና ማዕከል አስተባባሪ አቶ አማን ወርጂ  ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአጠቃላይ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ከ8000 በላይ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ታውቋል፡፡

ሐምሌ 2016

@dbu11
base.apk
7 MB
የደብረብርሐን ዩንቨርስቲ Route finding system application ነው።

በዩንቨርስቲው ውስጥ ያሉትን አድራሻዎች ሙሉ በሙሉ የያዘ የቦታ(መዳረሻ) ጠቋሚ
ሲሆን ከተወሰኑ የ ትምህርት ክፍል አድራሻ (ብሎክዎች) ቅያሪ ውጭ ማንንም መጠየቅ ሳያስፈልገን በትክክል የፈለግነው ቦታ ለመሔድ እጅጉን የሚያገለግል አፕልኬሽን ነው
ተጠቀሙበት።

አፕልኬሽኑ በአጋጣሚ የሌላችሁ ቤተሰቦች አውርዳችሑ መጠቀም ትችላላችሁ ለጓደኞቻችሁም አጋሯቸው።
አፕልኬሽኑ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አማራጮች ሲኖሩት አማራጩን አፕልኬሽኑን እንደከፈታችሁ Top right corner(በስተቀኝ የራስጌ ማዕዘን) ላይ extra የሚለውን icon ስትነኩት ታገኙታላችሑ።



@DBU11
@DBU_entertain
ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ና የታሪክ ትምህርት ክፍል እንዲመልሱ ወሰነ ።

የደብረ ብረሃን ዩኒቨርስቲ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ማዕከል እንደገና መደራጀቱን አስታወቀ። ብዙ ወዝግቦችና የትችት አስተያየቶች ሲሰጡበት የነበረው የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ፣በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪ እንደ ነበር ያትወሳል ።

ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲው የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫና ተልኮ መሰረት በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ አራት ኮሌጆች ውስጥ ያሉ 18 የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መወሰኑን ይታወቃል ።ዩኒቨርሲቲው ወሳኔውን ዳግም በማጤን የታሪክንና የአማርኛ ቋንቋን በማካተት አንድ ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቋል ። የትምህርት ክፍሎቹ ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር ማሟላት የሚችሉ ከሆነ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ድግሪ እንዲማሩ ይደረጋል ሲል ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ አስፍሯል ።

የዐማራ ክልል የመንግሥትዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበርም፣ “ውሳኔው፥ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለበት ነው ሲል መቃወሙ ይታወሳል።
@DBU11
@DBU11
ክፍት የስራ ቦታ

ሞክሩት 📌
🔊 Paid Internship Opportunity

Organization: Center of Excellence International Consult

Eligible applicants: Fresh graduates who have a degree and/or interest in the stated position.

Positions:
🎯Marketing
🎯Accounting
🎯Sociology
🎯Statistics
🎯Gender studies

🖍How to apply: Send your CV and Cover letter to the email address  [email protected] with the subject "Center of Excellence International Consult"

📅 Duration: 3 months
💰 Paid Internship
📈 Benefit: Employment opportunity based on performance.

@DBU11
@DBU11
''ለክረምት ተማሪዎች ከተጠቀሰው ቀን ዘይግይቶ የሚመጣ ተማሪን አላስተናግድም 'ዩኒቨርሲቲው

ሙሉ መረጃው በምሰሉ ላይ ተያይዟል 👆👆
@DBU11
@DBU11
ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች :ሀምሌ 22 ወደ ዩኒቨርሰቲው ግቡ ተብሏችኃል ።

@DBU11
@DBU11
#Notice

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 24 ይጀምራል ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

፨ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

@dbu11
2024/11/16 05:36:47
Back to Top
HTML Embed Code: