Telegram Web Link
💔የባከነች_ነብስ



#ክፍል_

...🖊ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
<<አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
<<ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!>>
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
<<እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...>>
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
<<አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...>>
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
<<አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር!>> የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
<<መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል!>> አለኝ
<<የ.ም.ን ቀ.ብ.ር?>>...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል 👉♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 11 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

♥️ እዉነተኛ ታሪክ♥️

#ክፍል_➊➊

...🖊ከሆስፒታል አልጋ ላይ እራሴን አገኘሁት። እናቴ ላይ ጨክኖ አፈር ማልበሱ ክፉኛ ሰቀቀን ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ድካም፣ሀዘን፣ብስጭትና ረሀብ ተደማምረዉ እራሴን እንድስት ስላደረጉኝ እጅግ የምሳሳላት እናቴን እንደ ወጉ አልቅሼ መቅበር ተስኖኝ በቀብሯ ማግስት እራሴን ስቼ ለህክምና ከገባሁበት ሆስፒታል ዉስጥ ነቃሁ። መጀመሪያ ላይ የአባቴ መጥፋት የሄደበት የገባበት አለመታወቁ ክፉኛ ያስጨንቃት ነበር ምናልባት ሰዎች አደጋ አድርሰዉበት እንዳይሆን ብላም ትሰጋ ነበር እዉነታዉ ግን አባቴ በእድሜ እጅግ ከምታንሰዉ እንደዉም እንደሰዎች አባባል ከእኔ እኩያ ከምትሆን ሴት ፍቅር ይዞት ቤት ንብረቱን በትኖ ከእሷ ጋር መኮበለሉን ስትሰማ ድንጋጤ ከነበረባት ግፊት ጋር ተዳምሮ ለሞት ዳረጋት።አሁን በህይወት ለመቆየት ምን ምክንያት ይኖረኛል? ህይወት እራሷ በሀዘኔ ዳንኪራ ልትመታ!፤በለቅሶዬ ጭቃ አቡክታ ቤቷን ልትሰራ!፤የእኔን ዉጣ ዉረድ እንደ ኮሜዲ ፊልም ልትኮሞኩም ስቃይና ሀዘንን ለግሳ ለዚህች ጠማማ ዓለም ካስረከበችኝ በሗላ ጭላጭ ተስፋን እንደማትሰጠኝ ልቦናዬ ከተረዳ ሰነባብቷል። እየሩስ ከአጠገቤ ነበረች መንቃቴን ስትመለከት በፍጥነት ሄዳ ዶክተሯን ጠርታ መጣች
<<እንዴት ነሽ? ምን አየተሰማሽ ነዉ?>>
ተስፋ መቁረጥና የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት መጓጓት! ነዉ የሚሰማኝ ብዬ ለዶክተሯ ብነግራት ምነኛ ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህንን ለመረዳት እኔ የቆምኩበት ላይ ልትቆም እኔ የሚሰማኝ ሊሰማት እንደማይችል ልቦናዬ ስላወቀዉ
<<ደ.ህ.ና ነ.ኝ!>> አልኳት
በእጆቿ ግንባሬን ከነካካችና የሙቀት መጠኔን ከለካች በሗላ
<<አሁን ደህና ነሽ ነገር ግን ሰዉነትሽ ስለተጎዳ ፈሳሽ ነገሮች በብዛት መዉሰድ ይጠበቅብሻል የማዝልሽንም መድሀኒት በአግባቡ መዉሰድ ይኖርብሻል!>> አለችኝ! ከእየሩስ ጋር የታዘዘልኝን መድሀኒት ተቀብዬ ወደ ቤት አመራን። አክስቴ ባለቤቷና ከአዲስ አበባ አብረዉን የመጡት ሰዎች ሀዘንተኞቹን ምሳ ሲመግቡ ደረስን! አብዛኞቹ እኔን ሲመለከቱ በሀዘን ደረታቸዉን መምታት ጀመሩ እየሩስ በፍጥነት ወደ መኝታ ክፍሌ ይዛኝ ገባች... መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ባማረ ፍሬም የተሰቀለዉን የአባቴን ፎቶግራፍ ስመለከት የንዴትና የበቀል ስሜት በደም ስሬ ዉስጥ ይሯሯጥ ጀመር...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 12 ከ60♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

♥️ እዉነተኛ ታሪክ♥️

#ክፍል_➊➋

...🖊''ሀዘን በጊዜ ክንፎች ይበራል'' የሚባለዉ ለካ እዉነት ነዉ! የአባቴ ክህደትና የእናቴ ሞት እድሜ ዘመኔን ከልቤ ታትሞ የሚኖር የስቃይ ጠባሳ ቢሆንም በዘመድ አዝማድ ልመናና ቁጣ በየቀኑ ማልቀሴን ቀነስኩ። ቀን በቀን እየተተካ አዲስ ሳምንት ይወለዳል... ሳምንትም እራሱን አሳድጎ ወር ይሆናል... እኔም የእናቴን አርባ ካወጣሁ በሗላ የነበሩንን ንብረቶች ሙሉ በመሉ ሽጬ እናቴን የነጠቀኝን ከተማ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቼ አዲስ አበባ አክስቴ ጋር ኑሮዬን ከጀመርኩ ቀናቶች ተቆጠሩ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ዉስጥ ታዲያ የአቤል ደብዛ መጥፋት ይገርመኝ ያስጨንቀኝም ነበር። ያ ሁሉ ዛቻና ማስፈራሪያዉ እንደዘበት ቀርቶ የዉሃ ሽታ የሆነዉ ምናልባት ሌላ ተንኮል እያሰበ ሊሆን እንደሚችል እንጂ እንዲሁ ዝም ብሎ እንደማይተወኝ ዉስጤ ካመነ ሰነባብቷል። ስለ አባቴ ይህን ሰማሁ... እዚህ ቦታ አየሁት... የሚል አንድም ሰዉ አልተገኘም ብቻ አባቴን ሳስብ የእናቴ ገዳይነቱ እንጂ ወላጅነቱ አልታይሽ እያለኝ በሌላ በኩል እንደ አቤል አይነት የሰዉን እምነት ከአፈር የሚቀላቅል ወንድ በምድር ላይ እስካለ ድረስ እኔ ያለቀስኩትን እንባ፤የተሰቃየሁትን ስቃይ ዳግም ሌላ ሴቶች መቅመሳቸዉ የማይቀር መሆኑን ሳስብ የበቀል እሳት በዉስጤ ይርመሰመሳል። ለእየሩስ አቤል ያደረገኝን ነገር በሙሉ አንድም ሳላስቀር በዝርዝር ባስረዳትም
<<ለምን አንከሰዉም?>> ከሚል ሀሳብና እጅግ በጣም ከማዘን የተሻለ አማራጭ ልትሰጠኝ አልቻለችም። ምን ብዬ እከሰዋለሁ? በምን ማስረጃ? መንፈሴ ላይ ላደረሰዉስ የጥፋት አለንጋ ማን ምስክር ይሆነኛል? ይልቅ መዉጫ መግቢያዉን የሚኖረበትን ሰፈር በአጠቃላይ ስለ እሱ የሚያጣራ ሰዉ እንደትፈልግልኝ እየለመንኩ ጠየኳት አላሳፈረችኝም! ሰፈራቸዉ የሚገኝ ኤልያስ ከተባለ ልጅ ጋር አስተዋወቀችኝ የጠየኩትን ነገር እንደሚያከናዉንልኝ እኔም ለሚያደርግልኝ ነገር ጥሩ ክፍያ ልፈፅምለት ተስማማን። አቤል ከሚኖርበት ፒያሳ አካባቢ በጠዋት ተነስቶ ቦሌ ወደሚገኘዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ ሱቅ እንደሚሄድ ማታ 2:30 አካባቢ ሱቁን ዘግቶ ወደ ሚኖርበት ፒያሳ እንደሚመለስ አብዛኛዉን ጊዜ ድርጊቶቹ ተመሳሳይ እንደሆኑና በብዛት ሴቶች ወደ ሱቁ እንደሚመላለሱ በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ አጣርቶ ነገረኝ። እየሩስን አቤል ወደሚሰራበት ሱቅ መሄድ እንደምፈልግ ስነግራት በሀሳቤ እንደማትስማማ ገለፀችልኝ የቱንም ያህል ብትቃወመኝም ልታሳምነኝ ስላልቻለች ያላት አማራጭ ሀሳቤን መደገፍ ብቻ ሆነ። ሙሉ ጥቁር በጥቁር የሀዘን ልብሴን እንደለበስኩ ከሳሪስ ወደ ቦሌ የሚሄድ ታክሲ ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ገባን።
በዳይ ይረሳል
ቀን ቀን ወልዶ
ቀን ሲጨምር ቀን ሲተካ
አይረሳም ተበዳይ ለካ
የበደልሽኝ እንዳልረሳ ሆኛለሁ
ከልቤ እንዴት እስቃለሁ?
በሚያሳዝን ቅላፄ ከታክሲ ዉስጥ የሚንቆረቆረዉ የመልካሙ ተበጀ ዜማ ውስጤን ያላዉሰዉ ጀመር...
ልቤ ቆስሎ
ዉስጥ አንጀቴ እርር ብሎ
ፍም መስሎ ተቀጣጥሎ
በደል ረመጥ ሆኖ አቃጥሎኝ
ስንገበገብ ጥርሴን ባሳይሽም
ልቤ አይስቅልሽም!

<<ቦሌ ወራጆች መጨረሻዉ!>> የማይስቅ ልቤን ይዤ ከታክሲዉ ወረድኩ
የበቀሌ የመጀመሪያ ቀን...ወደ አቤል ሱቅ በድፍረትና በልበ ሙሉነት ነበር የምራመደዉ...


For any comments inbox 📥

👇👇

@Juliiian

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 13 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
💔የባከነች_ነብስ💔

♥️እዉነተኛ ታሪክ♥️

#ክፍል_➊➌

...🖊እንግዳ ከሌለበት ሱቅ ዉስጥ አቤል ለብቻዉን ቁጭ ብሎ አገኘሁት። ገና ሲያየኝ ፊቱ ላይ የሚታየዉ ንቀትና ትዕቢት የንዴቴን መጠን በእጥፍ ቢጨምረዉም አራሴን አረጋግቼ በእናቴ ሞት ምክንያት ወደ ጅማ ሄጄ እንደነበረ አሁን ሙሉ ገንዘቡን ልከፍለዉ እንደምችልና በምትኩ እሱ ጋር ያለኝን ፎቶና ቪዲዮ እንዲያጠፋዉ ጠየኩት። እየሩስ ወደ ሱቅ ዉስጥ መግባት ስላልፈለገች ከዉጭ ቆማ እኔና አቤልን የምናደርገዉን እንቅስቃሴ ትከታተላለች።

<<አሁን ፋይሎቹን አልያዝኳቸዉም ነገ እደዉልልሽና የትና እንዴት ተገናኝተን ገንዘቡንና ፍይሉን እንደምንለዋወጥ አሳዉቅሻለሁ!>> አለኝ

<<ግን...አንተ...ሙሉ በሙሉ ፋይሎቹን እንደምትሰጠኝና አንተ ጋር ኮፒ እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለኝ?>>

<<ማረጋገጫ አይኖረኝም! አንቺ ግን ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እኔን ማመን ብቻ ነዉ!>>
ዉስጤ ያለዉ የጥላቻና የበቀል ስሜት አንጀቴ ሲያላዉሰዉ ይታወቀኛል
<<ስለየትኛዉ እምነትና መታመን ነዉ የምታወራዉ ከሀዲ!!>> ብለዉ ዉስጤ ያለዉ ህመም በትንሹም ቢሆን እርጋታ እንደሚያገኝ ባዉቅም ቸኩዬ ነገሮችን ማበላሸት ስላልፈለኩ

<<እሺ!>> አልኩት!

<<ምንም አይነት ብልጠት ወይም ደግሞ ተንኮል አስባለሁ ብትዪ አሁን ካለሽበት ሁኔታ የባሰ መቀመቅ ዉስጥ እንደምከትሽ አትርሺ!>>
በእናቴ ሞት የተሰማኝ ሀዘን ላይ ሲያንጓጥጥ መመልከቱ ከሞትም በላይ ሞት ቢሆንም ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ትዕግስት ስለነበረ የሚናገራቸዉን ንግግሮች እየመረረኝም ቢሆን መዋጥ ግዴታ ሆነብኝ። በግምት በእድሜ አቻ ልትሆነኝ የምትችል ጠቆር ብላ የደስ ደስ ያላት ወጣት ሴት ወደ ሱቁ ገብታ በፓስታ የታሸገ ነገር አቀበለችዉ አቤል ደግሞ በምትኩ የሚሞሪ ካርድ ሲሰጣት ተመለከትኩ! ፊቷ ላይ ይታይ የነበረዉ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እሷም እንደኔ የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆኗ ምስክር ነበር። <<እስከመች?>> አልኩኝ በዉስጤ! ለሴት ልጅ ህመምና ሀዘን እየሰጠ በምትኩ ገንዘብ እየተቀበለ የሚኖረዉ እስከመች ነዉ?

<<ነገ ከሰአት 8:00 ሰዓት ላይ የምትችል ከሆነ እዚሁ ሱቅ መጥቼ ገንዘቡን ላቀብልህና ፋይሎቹን ስጠኝ?>>
<<እደዉልልሻለሁ!>> ብሎ አሰናበተኝ! ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን
አክስቴ ፈቃደኛ ባትሆንም በብዙ ልመናና ለቅሶ ከጅማ ሽጬ ከመጣሁት ገንዘብ ላይ የተወሰነዉ በእናቴ ስም የሚጠራና በአክስቴ ባለቤትነት የሚተዳደር ሆቴል አዲስ አበባ ዉስጥ እንድትከፍት አስማምቼያት የተቀረዉን ገንዘብ የእናቴ የዘወትር ህልም የሆነዉና ሳትፈፅመዉ ሞት የቀደማት የእርዳታ ድርጅት መክፈት በእኔ አቅም የማይቻል ስለሆነዉ ገንዘቡን ለእርዳታ ድርጅት ለመስጠት መወሰኔን ገለፅኩላት!
<<ስለ እራስሽም የነገ ህይወት ማሰብ ይኖርብሻል?>>

<<አስቤያለዉ አክስቴ አሁን ለእኔ ገንዘብ ሳይሆን ማረፊያ ነዉ የሚያስፈልገኝ የማይከፈልበት ማረፊያ!>>

<<አልገባኝም!>>

አክስቴ እንደማይገባት አዉቃለሁ ሊገባትም አይችልም እኔ ግን ነግቶ ነገ ላይ ለመቆም ልቤ ቆሟል ሁሉም ነገር ፍፃሜዉን ሊያገኝ አንድ ምሽት ብቻ ፊት ለፊቴ ተደንቅሯል እንዳረጀ ዉሻ ሂድ ብሎ ይህንን ምሽት በካልቾ መቶ የሚያባርርልኝ ማን ይሆን? ማንም!
<<አይገባሽም አክስቴ ተይዉ!>>...

🕹የመጨረሻው ክፍል ከ400♥️ VOTE ቡኃላ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
💔የባከነች_ነብስ💔

♥️እዉነተኛ ታሪክ♥️

🛎የመጨረሻው ክፍል🛎

...🖊 <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

❇️//ተፈፀመ//❇️

🔮የባለታሪኳ መልዕክት

👉 የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!


💈ምስጋና
👉ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

📮በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት መስጫ የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡

@Juliiian

,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 3

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ



እንዴውም ተይው እኔው እራሴ ብላ ሳትጨርስ ከክላሴ ወጣች ደንግጬ ተከትያት ወጣሁ ኤልሲ ያሰበችውን ነገር ከማድረግ ወዴ ኋላ አትልም እንዴምንም ብዬ በሩ ጋ ስዴርስ እጇን ያዝኳት እህህ… አለች ፈገግ እንደ ማለት ብላ እሺ ልቀቂኝ ልቀመጥበት ብላ ሂዳ አጠገቡ ተቀመጠች ነገሮቿ ሁሉ ምንም አላመሩኝም ጆን ፊት ለፊቴ ነበር የተቀመጠው እሷ ታወራው ጀመር ሁሉም እያወራ ነው፡፡ አክስቴ አጠገቤ ተቀምጣ ታወራኛለች እኔ ግን አንዲም አልሰማኋትም ልቤ እነ ኤልሲ ጋ ነው በመሀል አክስቴ እንዴዛ ነው ስትለኝ
እሺ አልኳት፡፡ ሷቋን እንዴት ትቻለው እንዴ ምን ሰምተሽ ነው እሺ የምትይኝ አለችኝ፡፡ሳቅ ብዬ የሰማሁትን ሰምቼ አልኳት ላለመበላት ብዬ እናቴ ጆንን ስለ ወንድምህ ምን አድስ ነገር አለ አለችው አገኘሁት እኮ ሲላት እናቴ ድንግጥ አለች ግን ያው ባለፈው እንዴነገርኩሽ እሱ ያለበት ሁኔታ ያው እንዴ ትናቱ ነው
ሲላት ያው የበፊቱ ነገር በውስጡ ላይ ስላለ ይሆናል አትናዴድበት ልብ እስኪ ገዛ ነው አለችው እስቲ ይሁና አለ በረጂሙ እየተነፈሰ ኤልሲ በቃ አስቃ ልትገለኝ ነው አይን፡፡ አይኑ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም፡፡ የዛን ቀን እንዴምንም ብለን አሳለፍነው እናቴ ጆንን እንዴ ወዴድኩት ሳትጠረጥር አልቀረችም እኔ ሁሌም.እቤት አልቀመጥም ነበር ጆንን ካየሁ ቀን ጀምሮ ግን ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን ውጭ መቆዬት አስጠልቶኛል በዚህ ባህሪዬ ዴግሞ አይዴለም እናቴ ለተከራዮቻችን እንኳን ግርምት ፈጥሮባቸዋል፡፡ እኔ ግን ይሄ ነገር ከቀን ቀን ሌላ ነገር ውስጥ እየከተተኝ ነው እናቴ ያለውን ነገር በግልፅ ጠየቀችኝ ግን ምን ብዬ ልንገራት ጨነቀኝ እናቴን ምንም ነገር ይሁን ዋሽቻት አላቅም ዋሸኋት ብል እንኳን ቁርስ በልተሻል? ስትለኝ ሳልበላ አዎ በልቻለሁ እላታለሁ እሱንም ቶሎ ከቤት መውጣት ከፈለኩኝ ከዚህ የዘለለ ግን እናቴን ዋሽቻት አላቅም አሁን ግን ወገቤን ያዘችኝ የምላት ጠፋኝ ተይው በቃ አትጨነቂ አለችኝ እና ግን ዴጋግመሽ አስቢበት አለችኝ ውስጤ ጥብብ አለኝ የምለው አጣሁ ጆን ደሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀረበኝ መጣ ግን ግልፀኝነቱ ይገርማል ከነገረኝ ነገር ውስጥ ግን ስለ ወንድሙ የነገረኝ ነገር ነው ባ/ዳር ድረስ ለወንድሙ ብሎ እንፈመጣ ሲነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ ለወንድሙ እንዴት ይሄንን ያህል መስዋዕትነት ሊከፍል ይችላል አልኩ በልቤ ጆን ከንግግሮቹ ብኋላ ዝምታን ያበዛል ስለ ወንድሙ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ያለውን ነገር ሲነግረኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው ጆን ከወንድሙ ጋር በእናት ይለያያሉ በጣም የገረመኝ ወንድሙ ጆንን በጣም ብዙ በደል በድሎታል ታድያ ጆን እንዴት ያንን ሁሉ በደል ይቅር ብሎ እዚህ ድረስ መቶ ወንድሙን ይፈልገዋል? የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ ምን አይነት ልብ ቢኖረው ነው? አልኩ በልቤ የወንድሙን ፎቶ ሲያሳዬኝ ዴርቄ ቀረሁ...ከአንድ አመት በፊት ነበር ፌቨን የምትባል ጓዴኛዬ ጋር የተለያዩት ፌቨን የጆንን ወንድም በጣም ነበር የምትወዴው ግን ምክኒያቱን በማናቀው ምክኒያት ነበር የተለያዩት በዛ ላይ በጣም የገረመኝ ጆን ጋር እንኳንስ የአንድ አባት ልጂ ይቅርና ዘመድ እራሱ አይመስሉም
ጆን ቢነኩት እንኳት የሚቆሽሽ ነው የሚመስለው ወንድሙ ግን ወዙን የተሰረቀ ነው የሚመስለው ግን ሀብታም ነገር ነው ቆይ ትዙ ግን ምን አስዴነገጠሽ ስታይው? አለኝ የት እንዴማውቀው ነገርኩት ፌቨን የምትባል ጓዴኛዬ ፍቅረኛው እንደነበረች አሁን ግን እንደተለያዩ ነገረኝ ከደስታ ብዛት
አቀፈኝ ግራ ገባኝ አሁን ፌቨን የት ነው ያለችው አለኝ አክስቷ ጋር ሀዋሳ እንዳለች
ነገርኩት በቃ ደስታው ይሄ ነው አይባልም
መጣላታቸው ነው ያስደሰተህ? ወይስ ምንድን ነው? ያስደሰተህ አልገባኝም? አልኩት ሁሉንም ነገር እነግርሻለሁ ብሎ ወደ ክላሱ ፈጠን ብሎ ገባ ሁኔታው ግራ አጋባኝ ተመልሶ መጣ እና ማዘር ትቆያለች እንዴ ሲለኝ አሁን ትመጣለች ግን ጆን ለምንድን ነው ወንድምህ የዚህን ያህል የሚሸሽህ? አልኩት በቃ ሲፈጥረው ለራሱ ጥቅም ካልሆነ በቀር ሰው መቅረብ አይወድም አለኝ ታድያ እሱ
አንተን ካልፈለገህ ለምን አተወውም? አልኩት ሁለተኛ እንድህ እንዳትይኝ አለኝ! ደነገጥኩ ጆን ወንድሙን እንዴ አይኑ ብሌን ነው የሚያዬው እኔማኮ አንተ ይሄንን ያህል እየፈለከው እሱ ካልፈለገህ ብዬ ነው አልኩት ምንም መልስ ሳይሰጠኝ ወዴ ክላሱ ሄደ እኔም ምን አልባት ስለሚወደው ይሆናል በሱ
ዙሪያ ምንም ነገር እንዲወራ የማይፈልገው አልኩኝ በእንድህ እንዳለ እናቴ እንደመጣች ድምጿን ሰምቶ ወጣ ማዘር ብሎ ጠራትና ወደ እሱ ሄዴች......


✎ ክፍል አራት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 4

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ

በእንድህ እንዳለ እናቴ እንዴመጣች
ድምጿን ሰምቶ ወጣ ማዘር ብሎ ጠራትና ወዴ እሱ ሄዴች ምን እንዴ ሚያወሩ አላቅም ብዙ ካወሩ ብኋላ ጆን ተመልሶ ወዴ ክላሱ ገባ ምንም አልገባኝም እናቴ መጣችና አንዴዬ ጆን ጋር ሀዋሳ አብረሽው ሂጂ እና የጓዴኛሽን ጉዳይ ጨርሽለት አለችኝ በቃ ከዴስታዬ ብዛት በቃ መጫህ ብቻ ነው የቀረኝ ቆይ እኔ ምንድን ነው የምሰራው? አልኳት እንዴ መግዴርዴር ብዬ ጆን ወንድሙ የሆነውን ለማወቅ ግዴታ ፌቨንን ማግኘት አለበት አለችኝ ካልሽ እሺ አልኳት ጆን ከሰዓት ወደ አ/አ በረራ እንደ ምናደርግ ነገረኝ እውነት ለመናገር ከእሱ ጋር መሆኔ ደስታው ከቃል በላይ ሆነብኝ ሻወር ምናምን ወስጄ ጨረስኩ እሱም ሁሉን ጨርሶ ወጣ እና ፌቨን ሀዋሳ መሆኗን
አረጋግጭልኝ አለኝ በተደጋጋሚ ስዴውልላት አታነሳም እኔ እና ጆን ወደ ባ/ዳር ኤርፖርት እየሄድን እያለ ፌቨን ደወለችልኝ እና ሳይለት አድርጋ እንደተኛች ነገረችኝ ሀዋሳ እንዳለች ስጠይቃት አዎ እዛ ነኝ ግን ለምን ጠየቅሽኝ? ስትለኝ እየመጣሁ ነው አልኳት በጣም ደስ አላት እና ስደርስ እደውልልሻለሁ ብያት ስልኩን ዘጋሁት ጆንም መኖሯን ሲያውቅ በጣም ተደሰተ እውነት ለመናገር ጆንን አይደለም ሴት ወንድም ጭምር ነው ከላይ እስከ ታች የሚያየው እኔም እራሱ እሱ ጋር በመሆኔ ብቻ የሆነ ደስታ እና ኩራት ተሰማኝ ልክ አ/አ እንደ ደረስን አንዷ መታ ጆን ላይ ጥምጥም አለችበት...አሁን ምን ይሉታል የሰው ሰው ላይ መለጠፍ? አልኩ በልቤ አጥብቃ ሰላም አለችው እንዴት ነህ? ሰላም ነህ? መቼ መተህ ነው? በቃ በሰላምታ አዋከበችው አሁን በቅርብ ነው የመጣሁት ብሎ ደበስበስ አድርጎ ሊያልፍ ሲል ታድያ መቼ ነው የምትመለሰው? ስትለው በቅርቡ እመለሳለሁ አንቺ ከዬት እየመጣሽ ነው? ወይስ እየሄድሽ? ሲላት እኔማ ከእስታፑል ትራንዚስት አድርጌ ነው አለችው ነው በቃ አለሁ እንገናኛለን ብሏት ተለያዩ እዚህ ጋ ደነገጥኩ ጆን ከዬት ነው የመጣው? ወዴትስ ነው የሚመለሰው? ልቤ ፍርሀት ፍርሀት አለኝ ብቻ ምንም ጥያቄ መጠየኩ አልፈለኩም በኦላይን ትኬት ስለቆረጠ አልቆየንም ልክ ሀዋሳ እንደገባን ሀይሌ ሪዞርት አልጋ ያዝን
አንድ ክላስ ሆኖ ደብል አልጋ ያለው ነበር የያዝነው ፌቨንን ደውዬ ጠራኋት ብዙም ሳትቆይ መጣች ጆንን ስታዬው ትንሽ አይኗን ጣለችበት ፌቨን በጣም ወፍራለች በፊት ቀጫጫ ነበረች መቼም ሴቶች ስንባል በውስጣችን ስላዬነው ሰው አቋም ማውራት እንወዳለን ሰዓቱ ወዴ 11 ሰዓት አካባቢ ስለ ነበር መክሰስ አብረን በላን እና የሀዋሳ ጎዳናዎች ላይ
ወክ ወጣን ጆን መሀላችን ላይ ነው እውነት ለመናገር እኛ እሱ ጋር ስንታይ ተለጣፊ ነገር ነው የምንመስለው
የሚያዬን መንገዴኛ ፊት ለፊት ማየት አልበቃው ብሎ አልፎ ዞሮ ያየናል
የጆን ቀልድ ፌቨንን ጥርሷን አላስከደናትም በጣም ሳቂታ ናት ጆንም ቢሆን ተጎዘጎዘባት እየመሸ ሲሄድ ፌቨን ወደ ቤት መሄድ አለብኝ ስትል ጆን እራት ካልበላሽ አላት መሄድ አለብኝ ስትል ግድ ካልበላን አላት ቅርብ ሰዓት አይደል መክሰስ የበላነው እንደጠገብኩ ነኝ በዛ ላይ አክስቴ እቤት ደለችም ስትል እሺ ብለን በኩንትራት ባጃጂ ሰዴድናት ጆን ዛሬ እንድህ ከተግባባን ነገ ደሞ የበለጠ እንቀራረባለን አለኝ አዎ ልጂቷ ባህሪዋ አስቸጋሪ አይደለም አልኩት እሱ ጋር በዚህ ሰአት መሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አየሩ ቀዝቃዛ ቢሆንም ፍቅር ስለ ሸተተኝ ግን ቅዝቃዜውን እረስቼዋለሁ ደጋግሜ በመዳፌ እጆቼን ሳሽ ስላዬኝ ጃኬቱን
አውልቆ አለበሰኝ፡፡ የምሆነው አጣሁ አመሰግናለሁ ብዬ ደስታዬን በውስጤ እንደምንም ቻልኩት የያዝነው ሆቴል ስንደርስ ቀጥታ ወደ ሩም ገባሁ እሱም ትንሽ ቆይቶ ተከትሎኝ መጣ የእውነት ለመናገር ባሌ በሆነ ብዬ ተመኘሁ ነይ እራት እንብላ ሲለኝ የቅድሙ እንዳለ ነው ይለፈኝ አልኩት እሺ እኔ እበላለሁ ነይ አብረሽኝ ሁኚ እስከምበላ አለኝ አግኝቼ ነው ብዬ አብሬው ሄድኩኝ ሆቴሉ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ትልቅ ነው በዛው ልክ ይሄ ነው የማይባል ሰው አለ ለካስ ቅድም እኔ ወደ ሩም ስገባ እሱ ወደ ኋላ የቀረው ወንበር እየያዘ ነበር አልኩ በልቤ አስተናጋጁ ልክ እንዳየን ወፈኛ መጣና የተያዘውን ወንበር አሳየን ብዙ ሰው እያየን ነው እኔ የሰው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንዴምንም እራሴን አረጋጋሁ
በተለይ ጆን ወንበር ስቦ ልክ እንዴ ፍቅረኛው ሲያስቀምጠኝ የሆነ ነገር ውስጤ ላይ ተሰማኝ የሚገርመው ነገር……
ያሜናዳብ ♥️ 👍 ይቀጥል ወይስ 👎
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 5

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ

ብዙ ሰው እያየን ነው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንደ ምንም ራሴን አረጋጋሁ በተለይ ጆን ወንበር ስቦ ልክ እንደ ፍቅረኛው ሲያስቀምጠኝ የሆነ
ነገር ውስጤ ላይ ተሰማኝ የሚገርመው…
እና በጣም ያሸማቀቀኝ ነገር ቢኖር ፍቅረኛዋ ጋርቁጭ ብላ ስጠቅሰው አይን በአይን አየኋት ከምንም በላይ ያናደደኝ መጥቀሷ ሳይሆን ፍቅረኛዋ ጋር ቁጭ ብላ ይሄን ማሰቧ ትንሽ ውስጤ ላይ ንዴት ነገር ፈጠረብኝ ትዙ ምነው ችግር አለ አለኝ እረ የለም አልኩ ፈገግ ብዬ ፊትሽ ላይ ጥሩ ስሜት አይታይም ሲል እሷ
ናት አልኩ አንገቴን እንደ መድፋት ብዬ ሳቄን መጦኝ እእእ ምንም ማድረግ አይቻልም መቻል ነው አለ እየሳቀ አልበላም ያልኩትንስ አንድ በአንድ በላሁ በዛ ላይ ጫዋታው በትንታ ገሎኝ ነበረ ልክ እንደኛ የተቀመጡ ሁሉ ሰረቅ እያደረጉ ያዩናል እኔም በልቤ ይታደሉታል
እንጂ እይታገሉትም እያልኩ ጫወታችንን ቀጠልን የጠጣሁት መጠጥ ግን በጣም ራሴን ያዘኝ ለካስ ስልፈው የነበረው ቮድካ ነው እኔ በስም እንጂ ቮድካን የት አውቄው እንደ ምንም ብዬ ልነሳ ስል ራሴን ሊያዞረኝ ፈለገ ቀስ ብዬ ራሴን አረጋግቼ ተነሳሁ ክፍል እንደ ደረስኩ አልጋው ላይ ተዘረርኩ ጆን በሁኔታዬ ይስቃል መጠጥ ነገር አትሞክሪም
እንዴ ብዙም እኮ አልጠጣሽም በትንሹ ደፍቶሽ ነበር አለ እየሳቀ እረ ተውኝ ባክህ ይሄንንም እኔ ሁኜ ነው አልኩ ብርድ ልብስ ውስጥ ገብተሽ ተኚ ብሎ ወጣ ወዴት እንደ ሄደ አላውቅም በቃ አልጋው ላይ ራሴን እንኳ ማንሳት አቃተኝ ቆይቶ ሲመጣ እንደ ነበርኩ አገኘኝ በጉልበቱ አልጋው ላይ እንደ መደገፍ አለና ወገቤን እና ጭኔ ይዞ ወደ ላይ አስጠጋኝ በህይወቴ ለመጀምርያ ግዜ ነው ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲይዘኝ በቃ ውሀ ሆንኩ ወደ ላይ አስጠጋኝና ጫማዬን አውልቆልኝ
አስተኛኝ ድንጋጤም አለ ደስታም አለ ብቻ ካስተኛኝ በኋላ ንቅንቅ አላልኩም እሱ ከራሱ አልጋ ላይ ተኛ ጥዋት ስነሳ በጣም ራሴን አመመኝ ጆንን አልጋው ላይ ሳየው የለም ሻወር ቤት ውስጥ እየታጠበ ይሆናል አልኩ ድምፅ ስሰማ ግዜ
ትንሽ ቆይቶ ከሻወር ቤት ሲወጣ ደረቱን ሳይ ልቤ ድንግጥ አለ አንደ ግጥም ትዝ አለኝ ደረትህ ሰፊ ነው እንደ ንጉስ አልጋ ጎንህ ተሸጉጬ ዘላለም አይንጋ እያልኩ እንዳላዜምልህ እንዳልቀኝልህ በልቤ ነው እንጂ መቼ የኔ ሆንክና አለች በለግጥሟ
የእውነት በቃ ተመኘሁት ኧረ አይንሽ ንቀይ አለኝ አፍሬ አንገቴን ደፋሁ ሳቀብኝ ተነሺ ሻወር ግቢና ቶሎ እናግኛት አለኝ እኔም ጨራርሼ እንደ ወጣሁ ክላስ ድረስ ቁርስ መጣልን ሴትን ልጅ በፍቅር ነው ሚንከባከብ ምን ማድረግ አይቻልም ያልክ አንተ ነህ እያልኩ በልቤ እኔም ሚያደርግልኝን ሁሉ መቀበል ጀመርኩ ልክ ረፋዱ ላይ ፌቨንን አገኘናት አምሮባታል ሰላም ስትለኝ ጠጋ ብዬ በጆሮዋ ኧረ ሚስ ሀዋሳ ሆንሽብኝ አልኳት በጣም ሳቀች መጨረሻ ላይ ጆን ያለውን ነገር ነገራት ፊቷ ተለዋወጠ እኔ ወሬያቸው ምንም አልገባ አለኝ ያን ታክል አመት በቤተሰብ ፍቅር ሲሰቃይ የት ነበራቹ
አለች ፊቷን አጥቁራ ሁሌም ቢሆን ወንድሜ ራሱን ጥፋተኛ ማድረግ አይወድም አላት በቃ ብዙ ተጨቃጨቁ
ዛሬም ድረስ እንደዚህ ትወደዋለች እንዴ አልኩ በልቤ እሺ እውነቱን ልንገርሽ እናቱ ለእኔ እንጀራ እናት ናት ሲል ደነገጠች ታድያ እሱ እስከ ዛሬ ድረስ እኮ የአባቴን ልጅ በደልኩት እያለ እኮ ነው ራሱን የሚወቅስ አለች ጆን አንገቱን ደፋ ቆይ ቆይ አንተ ዘንድ አባትህ የሰጠህ ደብበዳቤ አለ እንዴ አለችው ጆን
በድንጋጤ አዋ አላት ከግዜ በኋላ አንድ ሊያደርገን የሚችል ቢኖር ያደብዳቤ
ነው ብሎ ነግሮኛል አለች ጆን ተነስቶ ሁለት እጆቿን ሳመው ደነገጠች እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ.....
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 6

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ

እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ የፈራሁት ደረሰ ልቤ ደንግጧል ምክንያቱም ጆን ውጭ ሀገር እንደ ሚኖር ብጠረጥርም እርግጠኛ አልነበርኩም አሁን ግን
ከአንደበቱ ሰማሁ አሜርካ ማለት ለእኔ ከምንም በላይ ነው እስትፋንሴ እስኪ መስል ድረስ ነው የተመኘሁት ፌቨንን ምሳ ጋብዘናት ምናምን መጨረሻ ላይ
ተሰናብተናት ቀጥታ ወደ ባ/ዳር በረራ አለ ተብሎ ሀዋሳ ኤርፖርት ውስጥ ነን እኔ ትኬቱን መቼ ነው የቆረጠ እላለሁ ግን እሱ በኦንላይን ኢንተርኔት ጨርሶታል በዚህ መሀል ወደ ባ/ዳር እንደ ገባን እሱ ኩንትራት የያዘው ሹፌር ነበር እየጠበቀን ነው እኔ ግራ የገባኝ መቼ ደውሎ እንደ ጠራው ነው ትኬት ሲቆርጥ አልጋ ሲይዝ
በቃ ብዙ ነገሮችን ሲያደርግ አላየውም ግን ተደርጎ አየዋለሁ እቤት እንደ ደረስን አክስቴን ሰላም ብሏት ወደ ክፍሉ ሄደ እናቴ ቤት የለችም ክላሴ ውስጥ ተኝቼ ሁሉም ነገር እየገረመኝ ነው በቃ እሱ ጋር በአንድ ቀን ውስጥ ይሄን ታክል ስንቀራረብ ከምንም በላይ ነው ደስ ያለኝ
ቢጃማ ለብሼ ኤድፎኔን ሰክቼ በረንዳ ላይ ቁጫ አልኩ እሱም ጃኬት ነገር ደርቦ ወጣ ስንተያይ ፈገግ አለ ትዙ ሻይ ቡና አለኝ አመስግናለሁ አልኩ ግድ የለም እንደ ትናቱ አትሆኚም አለኝ ሳቄን
ለቀኩት ይዘህልኝ ና አልኩ እረ ባክሽ ከፈልግሽ አትመጪም ብሎ ነይ ቶሎ
ነው ምመለስ ብሎ ወጣ የእውነት ለመናገር ልቤ አብሮት ወጣ በቃ አስጠላኝ ከእሱ ለደቂቃም ቢሆን
መለየትን አልፈልግም በፍቅር እንደ ወደኩ አውቂያለሁ ግን በቃ ምሆነው አጣሁኝ እስኪ መጣ ብዬ ተኛሁኝ ከደቂቃዋች በኋላ እናቴ መጣች ስታየኝ ደስ አላት
የሄዳቹበት ጉዳይ ተሰካላቹ አለች አዋ አልኳት እና ጆን የት ሄደ አለች አሁን
ቅርብ ሰአት ነው የወጣ እልኳት ሀሳቤ ጆን ላይ ነው ብቻ በቃ አላውቅም ትንሽ ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ለራት ነው ያስነሱኝ ወጥቼ የጆንን ክላስ ሳየው መብራቱ በርቷል በቃ የእውነት ለመናገር በሰአታት ውስጥ ናፍቆኛል ቀጥ ብዬ ወደ ክፍሉ ሄድኩ ሳንኳኳ አቤት አለ ገርበብ አድርጎ ነበር የዘጋው ገባሁኝ እንደ ልማዱ ቁምጣ ለብሶ ወንበሩ ላይ እግሩን ዘርግቶ ለፕቶፑን ይነካካል ትዙዬ አለኝ እቤቱ ግቢያችን አልመስለኝ አለ ሲበዛ በጣም ይስባል ብዙ ዕቃ የለውም ግን ያሉት
የዕቃዋች አቀማመጥ በጣም ልዩ ነው አክስቴ ከውጭ ስትጠራኝ ሰምቼ ወጣሁ ወደ ላይ ቤት ስሄድ ቡና ተፈልቷል
አክስቴ ጆንን ጠራችው ሆነ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁና ጆን ሲመጣ ጠብቄ እራቴን ይዤ ወጣሁ ጆን ጋር ቁጭ አልኩ
እኔ እልበላም አለ ማን ብላ አለህ አልኩ ሳቀብኝ እናቴ ከውስጥ ስትመጣ አንቺ ብላ አትይውም ምን ሆንሽ አለችኝ
አልበላ አለኝ አልኳት የግዱን በላ በቃ እያጎረሰኝ ነው የጨረሰ ነገውን ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ…


✎ ክፍል ሰባት ከ70 like♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
For any comments inbox @Juliiian


┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄
Campus love Stories pinned «​​   :¨·.·¨: ያሜናዳብ ♥️ ┈┈••◉❖◉●••┈🌺 💢ክፍል 6 እውነትኛ የፍቅር ታሪክ እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ የፈራሁት ደረሰ ልቤ ደንግጧል ምክንያቱም ጆን ውጭ ሀገር እንደ ሚኖር ብጠረጥርም እርግጠኛ አልነበርኩም…»
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 7

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ
°
°
°
ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ በቃ ምለው ሁላ ጠፋኝ እንደ ምንም ብዬ እሺ ዛሬ እኔ ጋር
ዋል አልኩት ትንሽ ካቅማማ በኋላ እሺ በቃ ግን ማታ ላይ እሄዳለሁ አለኝ ደስ ብሎኝ እሺ አልኩ በቃ ጆን ካየሁበት ቀን ጀምሬ ብዙ ጓደኞቼ ጋር ተላያይቻለሁ ድሮ ያሉበት ድረስ እሄድ ነበረ እሱ ከመጣ በኋላ ግን አይደለም እነሱ ዘንድ ልሄድ ይቅርና ፈልገውኝ ራሱ አጡኝ ድንገት
ስደውልላቸው ዛሬ ከየት ትዝ አልንሽ
ወይስ ምንድ ነው ጉድ ኤልሲ የነገረችን ነገር እውነት ነው እንዴ አሉ ሙድ እየያዙብኝ እሱን ተውትና የት ነው ያላቹ ስላቸው አዶቭ ካፌ ነን አሉ ጆንን ይዤው ሄድኩ ልክ እንደ ደረስን ሲያዩን ጓደኞቼ ጆንን ሲያዩ ሁሉም ፀጥ አሉ በቃ ግርምትም አለ ብቻ ስሜታቸውን ለመግለፅ ትንሽ አንገራገራቸው ሁሎችንም አስተዋወኩት እናቴ ሰደውልልኝ ከነሱ ትንሽ ራቅ አልኩኝ ትንሽ ቆይቼ ስመለስ ጆን በሳቅ ሊገላቸው ነው ከምንም በላይ ደግሞ ደንግጬ የቆምኩ አመለ ምትባል ጓደኛችን ስትስቅ ሳያት ነው በህይወቴ አንድም ቀን አይደለም ስትስቅ ፈገግ ስትል እንኳ አይቻት አላውቅም ይሄ ልጅ ምን አስነካት አልኩኝ እኔ ብቻ አደለም እነሱም አስገርሟቸዋል ምንም አይነት ቀልድ አያስቃትም ብቻ የዛሬው ሁኔታዋ በጣም ተለየብኝ በዚህ መሀል ኤልሲ ከሩቅ ስትመጣ አየኋት ልክ ጆንን ስታይ ቆመች በቃ እንደ ምናምን
አደረጋት በኮሪደሩ ጥግ ይዛ መጣችና በጆን ጀርባ ሂዳ ግጥም አድርጋ ጉንጩን ሳመችው የእውነት ለመናገር በጥፊ ብላት ደስታዬን አልችለውም አንቺ ውልብልብ አላት ብናደድም ሳቄን ግን
አልቻልኩም በዚህ መሀል አጠገቤ የተቀመጠች ጓደኛዬ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ ዘንድሮ በለስ ቀንቶሻል ደግሞ ስትፈዢ አስበይው አሉሽ አለችኝ አሳቀችኝ የእውነት በቃ ወደ ውሰጤ ተመለከትኩ ልቤ ያለ እሱ ባዶ ሁና አገኘኋት ብቻ ፈጣሪ ይርዳኝ ምን ብዬ እንደ ምነግረው ሳስብ እንኳ ይጨንቀኛል ቀኑን ሙሉ እኛ ጋር ዋለ ጓደኞቼ የማይጠይቁት ጉድ የለም እሱም ለመመለስ ደከመኝ አይልም በዛ ላይ በቃ ጆን ማለት ልዩ ሰው ነው አብረን ውለን ልክ ቤት እንደ ገባን ትንሽ ሻንጣ ነገር ይዞ ወጣ እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ጩሂ ጩሂ አለኝ ግን አትሂድ
ማለት አልችልም እናቴ በስተ ጀርባ ነበርች ቻው ብሏት ወጣ የክላሱን ቁልፍ ሰጠኝና ነገ እንድታፀጂው አለ እየሳቀ በይ ቻው ሲለኝ እንባዬ ሲተናነቀኝ ይታወቀኛል በሩ ዘንድ ደርሶ ተመልሶ ሲመጣ እንባዬ ይፈሳል እንቺ ያምሻል እንዴ ሁለት ቀን እንጂ ሁለት አመት እኮ አላልኩም ብሎኝ ግንባሬን ስሞኝ ሄደ ኡፍ ምን አለ የወዱት ሰው ለደቂቃ ባይለዩት አልኩ በልቤ ክላሴ ገብቼ ተኛሁ በቃ ከዛን ቀን በኋላ ጆን በጣም ነበር የናፈቀኝ ሁለት ቀን ሞላ ግን አልመጣም እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ትዝ ሲለኝ የክላሱን ቁልፍ ሰጦኛል ቁልፉን ፈልጌ አግቼ እንደ ምንም ሩጬ ክላሱ ገባሁ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ሹራብ ሳወጣው ምንም ነፍስ የለኝም በቃ እንደ
እስትፋንስ አፍንጫዬ ጭምቅ አደረኩት ውስጤ ግን እኮ በስንቱ ታዝቦኛል በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....


✎ ክፍል ስምንት ከ100 like♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 8

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....እብድ ሆንኩ በራሴ ያዘንኩኝ እናቴን ምንም ስትለኝ እሺ ምላትን ዛሬ ግን እሷ ጋር ጭቅጭቅ ሆነ ስራዬ በቃ ያለ እሱ መኖር እንደ ማልችል ውስጤ አምኖ ተቀብሏል ያፈቀሩትን ሰው በቀላል እንዴት ከውስጥ በቀላል ማውጣት ይቻላል የደረሰበት ነው ጉዳትቱን የሚያውቀው ኤልሲ እንደ ምወደው አውቃለች በቃ ልታፅናናኝም ብትሞክርም ውስጤ ግን ይሄ ነው ለማለት ይከብዶኛል ግን ግፍ ይሆን አልኩ በልቤ ስንት ወንድ እንዳል ለመነኝ ዛሬ እኔ በተራዬ እለምናለሁ ለምኜም አላገኘሁ ሁሌም በአንድ ነገር አምናለሁ ግዜ ሁለት ነው አንድ ለእኔ አንድ በእኔ ለእኔ ሲሆን ሰው ላይ ኮራሁ በእኔ ሲሆን
ግን እኔ ራሴ ለመንኩ በዚህ እንዳለ ሁለት ሳምንት አለፈው እናቴ ግን የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ልቤ ይጠረጥራል በቃ ሁሌም አትጨነቂ ይመጣል ነው ምትለኝ ከሁለት ሳምንት በኋላ ጓደኞቼ እቤት መጡ ጆን ከሄደ በኋላ ከግቢ አልወጣሁም በግድ ይዘውኝ ወጡ ሁሌም ወደ ምንዝናናበት ባህር ዳርቻ ሄድነ በቃ ሁሌም ወደ ዚህ ቦታ ስመጣ ውስጤ እረፍት ያገኝ ይመስለኛል ብቻ ውስጤን በጣም ደስ ይለዋል በዚህ መሀል ጓደኞቼ አንድ ልጅ አስተዋወቁኝ ሊያወራኝ ዳር ዳር ይላል ከአድናቆት ጀመረ እኔ በህይወቴ ሰው ሲክበኝ አልወድም ስለ ራሱ ሳልጠይቀው
ይለፈልፍ ጀመረ ጓደኞቼ ከእኔ ትንሽ ራቅ ብለዋል ውሀው ውስጥ ይሮጣል እኔ ደግሞ ሁሌም ባህር ውስጥ እግሬን ነክሬ
መቀመጥ እወዳለሁ አጠገቤ ቁጭ ብሎ እያወራ ነው ግን ረስቼዋለሁ ምን አልከኝ ስለው የት ሄድሽ አለኝ ፈገግ እያለ ይባስ በነፃ ሀሳብ በትንሽ ትዝታ በብዙ ፍቅር ሸኘኝ ጆንን ከፊቴ አመጣው ካልተጠየቅ የማያወራው አንቺ በሎ እጄን ነካ አደረገኝ ከሀሳቤ ቀሰቀሰኝ እና ባንክ ቤት ነው ምሰራው እልሻለው አለ ፈገግ እያለ
በምን እንደ ጀመረው ራሱ አላውቅም በዚህ መሀል ብዙም ባይሆን ድብርቴ ለቀቀኝ በሳምንቱ ሁሉም ልደቴን ሊያከብሩልኝ መጡ የእውነት ለመናገር በየ አመቱ ልደቴን ሳከብር ከምንም በላይ
ደስተኛ ሁኜ ነው ዘንድሮ ግን ወደ ህይወቴ መጦ ሳላስበው በሄደ ሰው ትንሽ ተከፍቷል ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅም
መጧል ነገሩ ትንሽ ግራ ቢገባኝም ምንም አላልኩም ሁሉም ያመጣልኝን ስጦታ ይሰጡኛል የዛሬ አመት ከማልረሳ ውስጥ ኤልሲ በጣም ትልቅ ካርቶን ውስጥ አንድ ደስታ ከረሜላ አድርጋ ሰጣኛለች ክርቶኑን
ላየው ግን ሌላ ነገር ነው የሚያስመስለው ከሁሉም ጓደኞቼ በላይ እሷ የምትሰጠኝ ነገር ይነስም ይብዛም ምንም ይሁን ብቻ
ያጓጓኛል በዚህ መሀል ሁሉም ከሰጠኝ በኋላ የእሷን እየጠበኩ እያለ ትንሽ የተጠቀለለ ነገር በእጇ ይዛ መጣች አይንሽን ክደኚ አለችኝ ልክ እንደ ከደንኩ ከሰከንዶች በኋላ የሆነ ጠረን አፍንጫዬን
አወደው አሁን ለመጨሁ ትንሽ ቀረኝ በቃ ውስጤ በሰከንድ ውስጥ ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ
አይኔን ስገልጠው.......


✎ ክፍል ዘጠኝ ከ120 like♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ለ ሀሳብና አስተያየታችሁ @Juliiian በዚህ ያድርሱን።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 9

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ አይኔን ስገልጠው ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅ ፊቴ ላይ ተደቅኗል ነገሩ ግራ ገባኝ ትዙ ወድጄሻለሁ እባክሽን አብረን እንሁን አለኝ አንቺም በብቸኝነት ነው ያለሽው እኔም እንዳንቺው አለኝ በጥፊ ብለው ደስ ባለኝ ነበር እንደ ምንም ራሴን አረጋግቼ እኔ እኮ የራሴ የምወደው እና የማፈቅረው ሰው አለ በዛ ላይ እኔ እና አንተ የተዋወቅ ነው ትናት ነው አልኩት ምንም አለለኝም እንደዛም እያወራሁት
አፍንጫዬን ያወደኝ ጠረን አሁንም አፍንጫዬ ላይ ነው በዚ መሀል የሙዚቃውን ድምፅ ከፍ አደረጉት ሁሉም በየ ራሱ ጥሩ ሙድ ላይ ነው ኤልሲ ከውጭ ስልክ ስታወራ ቆይታ ወደ
ውጭ እንድወጣ በእጇ ምልክት ጠራችኝ
ስሄድ አናግሪው ይፈልግሻል አለችኝ ማነው ልላት ስል ስልኩን ሰጣኝ ዘላ ገባች ደጋግሜ ሄሎ ስል ዝም ነው መልስ የለም ተናድጄ ስልኩን ልዘጋ ስል ትዙ አለኝ ጆን ነው እጄ ስልኩን ለመያዝ ከበደው ማውራው ጠፋኝ ደህና ነሽ ግን አለኝ ምን አድርጌ ነው ግን አልኩት
ጫጫት ነገር አለ እስቲ ትንሽ ተንቀሳቀሺ አለኝ ሩጬ ክላሴ ገባሁ እንኳን ተወለድሽልን አለ በቃ የእውነት ለመናገር ከምንም በላይ ደስ አለኝ እንባዬ ይፈሳል የተወሰነ አወራሁትና ማታ እደውልልሻለሁ ወደ ፕሮግራምሽ ተመለሺ አለኝ ደስታው እጥፍ ሆነልኝ በቃ ጆንን ካገኘሁ በኋላ ያዩኝ ራሱ ምን አገኘሽ እስኪሉኝ ደስ አለኝ
ቀኑን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍን ግን ሚገርመ ው ቀን ላይ አፍንጫዬን ያወደው መአዛ አስካሁን አልተረሳኝም ማታ ለይ ጆን ደውሎልኝ ብዙ አወራን በቃ የልደቴን ቀን ተከፋሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ተስምቶኝ የማያውቅ አይነት ስሜት ተሰማኝ ልደቴን በዚም በዚያም ብዬ አሳለፍኩ ለጆን ግን ከዛን ቀን በኋላ በተደጋጋሚ ብደውልለት ስልኩ አይሰራም በቃ ከአይኔ ከተለየ አርባ አምስት ቀን ሞላው እኔ ግን ለሰከንድ ከውስጤ አላወጣሁትም ብቻ ቀናት ተቆጠሩ እኔም በመሀል ሁሉም ነገር
አስጠላኝ በቃ አምላኬን አማረርኩ ምን ብበድል ነው ብዬ አለቀስኩ ሁሉም ነገር ግራ ገባኝ ሰው የወደዱት ከአይን በራቀ ቁጥር ይረሳል ይባላል ታድያ ምነው የኔ በረታብኝ ተቃራኒ ሆነብኝ እቤት ማንንም ማውራት አስጠላኝ ልክ ጆን ጋር በተለያየን ሁለተኛ ወሩ በቃ ቀኑ ትዝ ሲለኝ እንደ ማበድ አደረገኝ ጥዋት ላይ ክለሴን ዘግቼ ማንም እንዳይጠይቀኝ ብዬ ተኛሁ ቢቆፍ ቁፍ ቢለምኑኝ አልሰማ አልኩ እንባዬ እስኪ ደርቅ አለቀስኩ ቀኑን ሙሉ ክላሴን ዘግቼ ወደ ማታ ላይ አክስቴ በቃ አለቀሰችብኝ አትልፊ ሂጂ አልኳት ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ
መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ እንደዛ ተኝቼ የዋልኩትን ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ቀስ ብዬ በሩን ስከፍተው ጆን ከፊቴ ላይ ቁሟል ዘልዬ ተጠመጠምኩበት በቃ በጣም ደስ አለኝ ደረቱ ላይ ማስቲሽ ሆንኩበት በይ ልብስ ቀይሪና እራት ልጋብዝሽ አለኝ ብቻ ደነግጫለሁ እሺ ብዬ እስክ ቀይር በጓሮ እናቴ ዘንድ ሂዶ እግሯ ስር ቁጭ ብሎ
ያወራል በቃ እሱ ካለ ግቢው ሰላም አለው ተያይዘን ወጣን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እራት ጋብዞኝ ትንሽ መጠጥ ነገር ጠጥቼ ለው ብያለሁ በተላይ ስጠጣ ሁሌም ይስቅብኛል ምናለ የሱን ሳቅ
ለማየት ስል ሁሌም በሰከርኩ እላለሁ በውስጤ ልክ ወደ አራት ሰአት አከባቢ ተመለስን ጆን ሰላም እደሪ ብሎ ወደ ክፍሉ ገባ እኔ ግን ንፋስ እንዲ ልቀበል ብዬ በረንዳ ላይ ቁጭ አልኩ ሰአቱ እየሄደ ነው ልክ ሳስነጥስ ጆን ወጣ ምነው ምን ሆንሽ ብሎ ወደ እኔ መጣ አጠገቤ ቁጭ አለ እረ ተነሽና ግቢ አለኝ መልስ አልሰጠሁትም ብቻ በስስት አይኑን ነው የማየው አንቺን እኮ ነው ምልሽ አለኝ ፈገግ ብዬ ሳመኝና ልግባ አልኩት እረ ድፍረት ሚስቴ እንዳሰማሽ አለኝ ቆሌዬን ሳይሆን ቆዳዬን ነው ግፍፍ ያለ ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ.....


✎ ክፍል አስር ከ130 like♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። @Juliiian


┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 10

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ራሴን አለመሳቴም እኔ ሁኜ ስለው ስቆ ስቀልድሽ ነው ብሎ ግንባሬን ሳመኝና ከተቀመጥኩበት አስነሳኝና ወደ ቤት
አስገባኝ እኔም ልቤ ቅር እያለኝ ገባሁ ግን በቃ ማታውን አልተኛሁም ሚስቴ ያለው ነገር ሲከነክነኝ አደረ ወደ ጥዋት አከባቢ እንቅልፍ ጣለኝ ወደ አምስት ሰአት ላይ ተነሳሁ ልክ እንደ ነቃው ወደ ጆን ክላስ ነበር የሄድኩ ግን ዝግ ነው ቅር አለኝ አክስቴ ካኋላ እያየችኝ ነበር ሳቀችብኝ ፎንቃ ይሉሻል ይሄን ነው አለች እየሳቀችብኝ እኔም ሳቄ አመለጠኝ ቀን ላይ ደውዬለት ትንሽ ስራ ይዤ ነው እንደ ጨረስኩ እመጣለሁ አለኝ እኔም ቀኑን ሙሉ ስጠብቀው ዋልኩ ማታ ላይ እቤት እራት አብረን በላን ልክ በዚህ መሀል ከሳምንት በኋላ ነገ አንድ ማስተዋውቅሽ ሰው አለ አለኝ ደስ ይለኛል አልኩ ነገውን ልክ ወደ ማታ አከባቢ ደውሎ ግራንድ ሚባል ሆቴል ጠራኝ እኔም ለባብሼ ሄድኩ ሆቴሉ እንደ ደረስኩ እንግዳ ማረፍያ ክፍል ውስጥ ሁኜ ደወልኩለት እንደ መጣ ይዞኝ ወደ ላይ ወጣ ቦታው በጣም የሚያምር ግራፊክስ አለው የሆነች ልጅ ጀርባዋን ሰጣ ተቀምጣለች ልዩ አላት ወዬ ብላ ዞር አለች እረ በፈጣሪ አልኩ በልቤ ደነገጥኩ በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ይሄ ነገር እንዴት ነው አልኩ በልቤ
የዘር ነው ወይስ ተፈላልገው ነው የተገናኙ አልኩ ትዙ ያልኩሸ እሷ ነው ሲላት የምርህን ነው ብላ ተነስታ ሳመችኝ እኔም ውስጤ ትንሽ ደስ አለኝ ሁሌም የማያውቁን ሰዋች ስለ እኛ በተነገራቸው መጠን ነው በህሊናቸው ሊስሉን የሚችሉት ጫዋታዋ ደስ ይላል ልክ እንደ
ስሟ ልጅቱም ልዩ ናት ከሰአታት በኋላ እራት በልተን ጆን ወደ መታጠብያ ክፍል ሲሄድ እንድ ጓደኛዋ መጣች አንቺ እንቅልፋም ተነሳሽ አለቻት ሰላም ብላኝ ቁጭ አለች ከእንቅልፏ እንደ ተነሳች ያስታውቅባታል ፍቅር የት ሄደ አለች አለ ይመጣል አለቻት ግራ ገባኝ ማንን ነው
ፍቅር ብላ የጠራችው እልኩ በውስጤ ጆን እንደ መጣ ፍቅር አለችው ቲቲ ተነሳሽ አላት እናቴ ድረሽ አልኩ እንዴት እንደዛ ብላ ትጠራዋለች ፍቅረኛዋ ቢሆን እንጂ ብዬ በቃ ተረበሽኩ ስልኬ ሚሴጅ
ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰዓቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል.....


✎ ክፍል አስራ አንድ ከ #150 like7 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️share ማድረግ አይርሱ።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 11

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ

ስልኬ ሚሴጅ ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰአቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል እንዴ ፍቅር ጥለክን ልትሄድ አለች ቅብጠቷ ቅጥ
የለውም ምን ትመስላለች ሞልቃቃ አልኩ በልቤ ልዩ በቃ ሂዱ ስትል ልንሄድ ስንነሳ ቆንጂዬ አደራ ፍቅርን አለችኝ አታስቢ አልኩ ጥርሴ ነክሼ ግን ለጆን ጓደኞቹ ይሁኑ ምኑ ይሁኑ ማውቀው ነገር የለኝም እሱም አልነገረኝም ግን በቃ ጆንን ከሆቴሉ ይዤው ስወጣ በቃ ከነጣቂዋች እጅ አውጥቼው ጉያዬ ውስጥ ያስገባሁ
መሰለኝ ጆን መንገድ ላይ ትንሽ ለው ላድርገሽ ብሎኝ ወደ ባህል ምሽት ቤት ጎራ አልን የተወሰነ ተጫወትን እየመሸ ስለ ሆነ ብዙም አልቆየንም ልክ እቤት እንደ ደረስን አክስቴ እና እናቴ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሏል እናቴ ስታየን ፈገግ አለች በቃ እኔ ጆን ጋር ስላለኝ ቀረቤታ ደስተኛ ናት አክስቴ ጠቀሰችኝ ፈገግ አልኩ
የእውነት ለመናገር በረንዳ ላይ ባይቀመጡ ደስተኛ ነበርኩ እንደ ሚስመኝ እርግጠኛ ነበርኩ ብቻ አመለጠኝ አልኩ በልቤ ግን ያቺ የልዩ ጓደኛ ፍቅር ብላ ስለጠራችው ውስጤን ከነከነኝ በዚህ እንዳለ ሰፈር ላይ በጆን ታማሁኝ መቼም ቢሆን በሚወዱት ሰው መታማትን የመሰለ ነገር የለም እሁድ ቀን ላይ ወደ ጢስ አባይ ጆን ጋር ልንዝናና ሄድነ ብዙ አዋራን በቃ ሰላሳለፋቸው ፈተናዋች ሲነግረኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው እሱ ያሳለፈውን ህይወት እኔ
ለመስማት ከበደኝ ወንድሙ ጋር እንደ ታረቀ ሲነግረኝ ግን ከምንም በላይ ደስ አለኝ ወደ ኢትዮጲያ የመጣበትን ጉዳይ እንደጨረሰ ሲነግረኝ ልቤ ተረበሸ ፍረሀት ፍረሀት አለኝ ባይነግረኝ አልኩ ግን ትዙ ባለፎው ልዩ ጋር ሳስተዋውቅሽ ጥሩ ስሜት እንዳልተሰማሽ አውቂያለሁ ይቅርታ ግን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ ሲለኝ ተቀምጬ እንኳ ጉልበት አጣሁ
በቃ ደንዝዣለሁ ምን መሰለሽ ትዙ ልዩ እኮ ለእኔ እህቴ እኮናት ሲለኝ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ እሺ ቲቲ ያልካትስ ስለው እሷም እህቴ ናት ልዩ ጋር የእንድ አባት የአንድ እናት ነን ቲቲ ጋር በአባት ብቻ ነው ምንገናኘው ሲለኝ ተመስገን አልኩ በልቤ በቃ የዛን ቀን ደስታዬ ወደር የለውም ከሳምንት በኋላ ፌቨን ከሀዋሳ መጣ አየኋት በጣም ነበር ደስ ያለኝ በቃ እቤት አብረን ሂደን ብዙ አዋራን ጆን ሚኪ ጋር እንዳስታረቃቸው ነገረችኝ ከምንም በላይ ደስ አለኝ እስቲ ንገሪኝ ጆን ፍቅረኛሽ ነው አለችኝ ደነገጥኩ ምን እንደ ነካኝ ባላውቅም እረ አይደለም ኖርማል ጓደኛዬ ነው አልኳት ነው እንዴ ፍቅረኛሽ መስሎኝ ነው አለች በራሴ በጣም ተናደድኩ በጆን አፍሬ ወይስ በራሴ አፍሬ ነው አይደለም
ብዬ የተናገርኩት እያልኩ ራሴን ወቀስኩ እሁድ ቀን ከኤልሲ ጋር ከጓደኞቻችን ጋር ውለን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ ጆን ደወለልኝ ሳነሳው ወደ ጎን ተመልከቺ አለኝ ዞር ስል ወንድሙ ጋር ካፌ ላይ ቁጭ
ብሏል ሻይ ቡና ብሎ ጠራን ቅድሙንም ናፍቆኝ ነበር ሄድን የእውነት ለመናገር የእናት ሆድ ዝንጉርጉር ሚባለው በጆንና በወንድሙ ላይ በሚገባ ሰርቷል እንኳን ወንድማማች ሊመስሉ ሆድና ጀርባ እንኳ አይሆኑም በፊትም የጆንን ወንድም ፌቨን ጋር እያሉ ድንገት ሳየው ማነው ግን ውቃቤውን የገፈፈው እላለሁ ቢነኩት እጅ ላይ ሰበብ ሚሆን ነው ሚመስለው ጀን
ትክሻዬን ነካ ሲያደርገኝ ከሀሳቤ አነቃኝ በሁለተኛው ቀን ጥዋት ላይ ጆን አ/አ ደረሰን እንምጣ አለኝ ትንሽ ልቤ ደነገጠ እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት......


✎ ክፍል አስራ ሁለት ከ150 ♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 12

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት አዋ ነግሮኛል ሂዱ አለች ምን ግዜ ነገረሽ አልኳት ማታ ላይ ነግሮኝ ነበር ልነግርሽ ነበር ተኝተሻል አለችኝ እናቴ ጆን ላይ የጣለችው እምነት
ይሄ ነው ለማለት ይቸግረኛል ከምንም በላይ ታምነዋለች ስድስት ሰዓት እንደ ሆነ ባህር ዳር ኤርፖርት ደረሰን ሰላሳ ደቂቃ አላቹ ሲባል ቁጭ አልን አንድ ያልተመለሰልኝ ነገር ቢኖር በቃ የሆነ ነገር ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅ በትም ምንም ነገር ሲያደርግ ለማንም አይናገርም
አድርጎት ወይም ፍፅሞት ነው ማገኘው ማያደርገውን ይቅርና የሚያደርገውን እንኳ መናገር አይፈልግም ከደቂቃዋች በኋላ በረራ አደረግን ልክ ከአርባ ዲቂቃ በኋላ አ/አ ደረስን ምሳ በልተን ወደ ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ላይ ወደ አሜርካ ኢንባሲ ሄድነ በቃ ኢንባሲውን ሳየው ትዝ አለኝ ለአመታት አሜርካ ለመሄድ ስል ከጣልያን እስከ ሱዳን ድረስ የሄድኩት ስንት ብሬን
የጨፈጨፍኩበት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ግን ጆን ለምን መጣን አልኩት ሳቀብኝ ምትፈርሚው ነገር አለ አለኝ ምን አልኩ በቃ ውስጤ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ደንግጫለሁ ልክ እንደ ገባን ፎቶ አነሱኝ በተላያየ ቦታ አስፈረሙኝ ሜድካል ተብሎ ወደ ምርመራ ክፍል ሄድኩ ብቻ ምን ያላረጉኝ ነገር አለ ለምን እንደ ሆነ አላውቅም ብቻ ጆን ከአጠገቤ ስላል ተለየ ምንም ፍረሀት አልተሰማኝም ውስጤ ከመደንገጥ በስተቀር ልክ እንደ ጨረስን ቁጭ ብለን እያለ አንዱ መጣና ጆን በቃ ሂዱ ያለውን ነገር አሳውቅሀለው ሲለው እሺ ብሎ ወጣን አ/አ ውስጥ እየዞርን አመሸን ጆን ጋር አንድ ክፍል ውስጥ እንደ ምናድር ሳስበው ደስ አለኝ
ሀርሞኒ ሆቴል ሩም ይዘናል አለኝ እህ መቼ ስለው ኦንላይን ኢንተርኔት ላይ ነዋ አለ እየሳቀ አንቺ ከዚህ ነገር ነፃ ነሻ አለ እያፌዘብኝ እንኳን ሆንኩ አልኩት ሰአቱ እየመሸ ሲሄድ ወደ ሆቴሉ ሄድነ ደብል አልጋ ነበር የያዘው እራት ሰዓት እስኪ ደርስ ሻወር ወስደኩ ምናምን ልክ ራታችንን በልተን እንደ ጨርሰን ሩም ገባን
ትንሽ ሚጠጣ ነገር ቀምሼ ስለ ነበረ ወሰወሰኝ ጆንን የቅድሙ መጠጥ አማረኛ አልኩት አረ አንቺ ልጅ እያለ ሩም ድረስ አስመጣ በቃ ማታ ምን እንደ ተፈጠረ አላውቅም ጥዋት ስነሳ ከጆን ደረት ላይ ተለጥፌ ተኝቻለሁ በቃ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ በቃ ምን እንደ ተከሰተ ማወቅ አልቻልኩም ራሴን በጣም አሞኛል የሞት ሞቴን ከደረቱ ላይ እንደምንም ብዬ ተነሳሁ በጣም ራሴን ይዞኛል እንደ ምንም ብዬ ቀና ለማለት ሞከርኩ ልብሴ አልወለቀም የጆን ልብስም አልወለቀም ታድያ እንዴት እሱ ጋር ልተኛ ቻልኩ ብዬ በጣም ነበር ግራ የገባኝ ነገሩ ግርምት ፈጥሮብኛል ማታ በጣም የጠጣሁ መሰለኝ ራሴን በጣም አሞኛል ስንቀሳቀስ ጆን ነቃ አንቺ ሰከራም አለኝ ምንድ ነው የሆንኩት አልኩኝ ለካስ እንደዚህ ሰከራም ነሽ አለኝ አፈርኩኝ እየሳቀብኝ ተነስቶ ሻወር ገባ በጣም ስላመመኝ ሻወር መግባት አልፈለኩም እስኪ መጣ ልብሴን ቀያየርኩ ልክ ሲመጣ አይኔ ደረቱ ላይ አረፈ ይሄ ደረት ላይ ተኝቼ ነዋ የሆንኩትን ሁሉ የረሳው አልኩ በልቤ እረ አይንሽን ንቀይ አለኝ ባክህ ዝምበል የግልህ አደረከውሳ አልኩት ሳቄን አያፈንኩት በለው ማነው የልብ ልብ የሰጠሽ አለኝ እእ አንድ ጢባራም አለ አንድቀን አስተዋውቅሀለው አልኩት እየሳቀብኝ ከሆቴሉ አቅፎኝ ወጣ ልክ ባ/ዳር ገብተን ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን
ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ...........


✎ ክፍል አስራ ሶስት ከ150 like👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 13

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ እኔ ደነገጥኩ ጆን ምንም አልመሰለውም ከፈ አደረገውና ተቃቀፉ ወንድሙ እንባውን እንዴት ይቻለው ግራ ብጋባም ምንም አላልኩም እቤት ድረስ አደረሰን ጆን በኋላ እደውልልሀለው ሲለው እኔ ራሴ እመጣለው ብሎት ተለያየን በጣም አሞኝ ስለነበር ተኛሁ ልክ ከዛን ቀን በኋላ ለሁለት ሳምንት ያህል እንደ ቱሪስት ጆን ጋር ዞርን ያልሄድንበት ሀገር የለም እናቴ የማትመክረኝ ምክር የለም ነገሩ ግራ ገብቶኛል በቃ ህይወቴን ከአሁን በኋላ እንዴት መምራት እንዳለብኝ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከአሁን በኋላ ህፃንነት እንደሌለ ህይወትን ራሴ መኖር እንደምችል አስቀምጣ ነገረችኝ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ውስጤ ፍረሀት ፍረሀት
ብሎኛል እናቴ በህይወቷ አቋም የሌለው አንዱን ሚጥል እንዱን ሚያነሳ ሰው አትወድም እኔ ደግሞ የእሳት ልጅ አመድ እንደሚባለው ሁሉም ነገር አይናዋጅ ይሆንብኛል ቢሆንም ግን እስከዛሬ ከኖርኩት በላይ ጆንን ካገኘው በኋላ ውስጤ ላይ ያለው ደስታ ልዩ ነው በዚህ
መሀል ጆን ወደ አ/አ ልሄድ ነው አለኝ ደነገጥኩ አሁንም ሊጠፋብኝ ነው አልኩ እንባዬ መጣ ይሄውልሽ ትዙ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጓደኞችሽን ተሰናበቺ ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ ምይዘውን አጣሁ ወዴት ለመሄድ አልኩት እሱን ስትደርሺ ታውቂዋለሽ አለኝ በቃ ደስታዬን አልቻልኩም ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆነ እሱም ወደ አ/አ ሊሄድ ብሎ ቦርሳውን ሲያወጣው እንደ ማይመለስ አወኩ አንዳለ ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ እናቴን እንደ ነገርኩሽ አድርጊው አላት እሷም እሺ አለችው ልክ ሊወጣ ሲል አክስቴ ቡና ደርሷል ጆን ግባ አላችው ቦርሳውን በረንዳ ላይ አድርጎ ገባ እኔ እስካሁን ምንም አልተናገርኩትም ግራ
ተገብቻለሁ ወደ ቤት ሲገባ ተከትዬው ገባሁ ከምንም በላይ ሀሳብ የሆነኝ አይኑን ሳላየው እንዴት አድርጌ ሳምንት እቆያለሁ የሚለው ነገር ነው የያዘኝ ጆን ልክ አንድ ቡና እንደ ጠጣ ሹፌሩ ደርሻለሁ አፍጥነው ሰዓት እያለፈ ነው አለው ቶሎ ወጣ እኔም ልሸኝህ ብዬ
አብሬው ወጣሁ በቃ እንባዬ እየተናነቀኝ ነው ትዙ አለቃስላው ብትይ የእውነት
አቀይምሻለሁ አለኝ እኔም እኮ ትናፍቂኛለሽ አንቺ ብቻ አደለሽም ለእኔ ምታስቢው እኔም እኔም እነዳንቺው ለስሜትሽ እጨነቃለሁ አለኝ በቃ ይሄን ከእሱ በመስማቴ ብቻ ደስ አለኝ
በዚህ መሀል ጆን ከሄደ በኋላ ማስተካከል ያለብኝን ሁሉ አስተካከልኩ ጆን በየደቂቃው ይናፍቀኛል ሚገርመው እንደዛ በቀን ስንቴ እየደወልኩ አስለቸውት ይሆን እላለሁ ግን ከእኔ ብሶ አረፈ እኔ ጋር ያለ እስኪመስለኝ ድረስ ሙሉ ጓደኛቼን ተሰናበትኳቸው ብዙም ወከባ ስለ ማልወድ ባሉበት ሂጄ አዲስ አበባ ለተወሰነ ግዜ እቆያለሁ አልኳቸው ለኤልሲ ብቻ ነው እውነቱን የነገርኳት የእውነት ለመናገር ወዴት እንደ ምሄድ አላውቅም ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን..........


✎ ክፍል አስራ አራት ከ150 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። for any comment👉👉 @Juliiian👈👈


┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄
@Juliiian
​​  
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል 14

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን ህይወት መቼስ እንደ ፈለጉት አይኖር አ/አ ስገባ ጆን ተቀበለኝ ሳየው በቃ ነፍሴን ያገኘውት ያህል ነበር ደስ ያለኝ ውበቱ ለጉድ ነው በጣም አምሮበታል አቅፎ ሰላም አለኝና ሻንጣዬን መኪና ውስጥ ከተተልኝ መኪና ውስጥ እንደ ገባን ሹፌሩ ሰላም አለኝ ሳየው ከዚህ በፊት ከሀዋሳ ስንመጣ የተቀበለን ሹፌር ነው ሰላም አልኩት ካፒታል ሆቴል ነበር ክላስ የያዘው እኔ የገረመኝ እና ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር ጆንን እስካየሁት ድረስ ትላልቅ ሆቴል ነው ለማረፍም ለመመገብም የሚይዘው ታድያ እንዴት እኛ ቤት ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በተደጋጋሚ ራሴን እጠይቃለሁ በዚህ መሀል ከሁለት ቀን በኋላ ዛሬ በረራ ታደርጊያለሽ አንቺ ሲለኝ ደነዘዝኩ በጣም ግራ ተጋባሁ ወዴት ነው ብቻዬን የምሄድ አልኩት ወደ ምትፈልጊበት ነዋ አለኝ ጀን አትቀልድ አልኩኝ እየሳቀ ባክሽ አብረን ነው ምን ሄድ እንዴት ብቻሽን እለቅሻለሁ አለኝ ተመስገን አምላኬ አልኩኝ ሁሉም ነገር ከአቅሜ ባለይ ሁኖብኛል ጆን ያደርገልኝን ሳስብ ለመናገር አቅም ያንሰኛል በቃ ጆን ማለት ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት ሄድን ውስጤ ምን እንደ ሆነ ባላውቅ በፍረሀት ተንዘፍዝፏል ልክ ወደ ፍተሻ እስክን ደርስ ምንም የማውቀው ነገር የለም ፖስፖርቴን እና ቪዛዬን የያዘው ጆን ነው ልክ Backgroundu ላይ ሳየው ወደ አሜርካ መሆኑን አወኩ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ
ፍተሻው ላይ ፖስፖርቴን ሰጠኝ ጆን አልኩኝ ደንግጬ ትዙ አለኝ መልሶ እዛው ላይ ተጠመጠምኩበት ያቀን ለእኔ ከምንም በላይ ነበረ በልቤ ደስታዬን እንደበዛከው ፈጣሪ ደስታህን ያብዛልህ ጆን አልኩኝ ብቻ ሁሌም በሱ ደስተኛ ነኝ በዚህ መሀል ስንት ነገር አልፌ texas ገባሁ እድሜ ልኬን አልሜ ያልተሳካልኝን ጆን ህልሜን አሳካልኝ በቃ ሁሉም ነገር ብርቅ ሁኖብኛል ከምንም በላይ የገረመኝ ግን ጆን የሚኖርበት ቤት ነው አሜርካ ላይ እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ የሚኖር ልጅ ሳይቸግረው እንዴት እኛ ዘንድ ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በጣም ጥያቄ ፈጠረብኝ አሁን በዚህ ሰዓት ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም በርግጥ አይደለም የሚፈልጉት ሰው ጋር በአንድ ቦታ መኖር ይቅርና ቀጣይ ህይወታችን የምንወደው ሰው ጋር እንደ ምናሳልፍ ስናውቅ ራሱ በተሰፋ
እንሞላለን በዚህ መሀል ጆን አዲስ ሲምካርድ ና ሞባይል ሰጠኝ አመስግኜ ተቀበልኩ ቶሎ የደወልኩ ለእናቴ ነበረ ድመጿን ስሰማ በጣም ደስ አለኝ ዛሬ ብሞት አይቆጨኝም አለችኝ ሁሌም ምኞቴ አንቺ የምትፈልጊውን ነገር ላደርግልሽ ነው ልጄ ዛሬ ይሄው የፈጣሪ ፍቃድ ሆነና ተሰካልሽ አለችኝ እናቴ ምንም ከሀገር እንድወጣ ከአይኗ እንዳልርቅ ብትፈልግም ፍላጎቴ ስለ ሆነ ብቻ መቃወም አልፈለገችኝም እናቴን አውርቼ እንደ ጨረስኩ አክስቴ ስልኩን ተቀብላ እንዳትዘጊው አለችኝ ቆይኝ እዳሪ ልውጣ ብላ እንደ ልማዷ እዳሪ ወጣች ማንም ይሁን ሰው ጋር ተቀምጣ ስልክ ማውራት አትወድም አክስቴ ጋረም ብዙ አዋራን በደቂቃዋች ውስጥ የሰጠችኝ ምክር ለነገሮች ቦታ እንድሰጥ አድርጎኛል በዚህ መሀል የጆን አህት ልዩ ስታየኝ ጨወች በጣም ነበረ ደስ ያላት አቅፋ አለቀኝ አለች ወይኔ አምላኬ አውቀህ መስሎኝ ነበር እኮ አለችው ጆንን በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር…


✎ ክፍል አስራ አምስት የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍ማድረግ አይርሱ።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
​​ያሜናዳብ

ክፍል 15
እውነትኛ የፍቅር ታሪክ
የመጨረሻ ክፍል 15


በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር አየሁ ፌቨን ከጓደኛዋ ጋር ፊቴ ላይ ቁማለች
ደነገጥኩ እንዴት ሊሆን ቻለ አልኩ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ የምወዳት ጓደኛዬ ፊቴ ላይ
ሳገኛት ሁሉም ነገር የተሳካልኝ መሰለኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩባት በዚህ መሀል ጆን ት/ት
እንድማር አደረገኝ ሁሌም ጆንን ከአይኔ ተለይቶ እስካየው እጓጓለሁ አንድ ቀን በዚህ እንዳለ
ፌቨን ጋር ቁጭ ብለን እያወራን ሁሉንም ነገር ትነግረኝ ጀመር እኔ አፌን ከፍቼ ቀረሁ ጆን
ከወንድም ጋ የተጣላበት ምክንያት አባታቸው ሲሞት ሙሉ ውሩሱን ለጆን ብቻ ነበረ
ያወረሰው የጆን አባት በጣም ብዙ ግዜ ታሟል ተሰቃይቷል ሁሉም ሰለቸው ጆን ግን
ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ ከአጠገቡ አልተለየውም ነበር በዚህ ምክንያት ጆንን አስበልጦ
ሰለ ሚወደው ሁሉንም ሀብቱ በእሱስም አዞረለት ከዛን ቀን ጅምሮ የጆን ወንድም
ቂመኛ ሆነ ጆንን በሚፈልገው ነገር ሁሉ ጎዳሁ ስንት አመት የተማርበት የደከመበትን ፋይል
ሳይቀር አቃጠለበት ጆን ይሄንም ችሎ ዝም አለ ይሄ አልበቃ ብሎት ጆንን ለማስገደል
ለቅጥረኛ ነፈስ ገዳይ ብር ሰጣቸው የጆን አባት ሁሉንም ነገር ሲሰማ አስጠራው ያሜናዳብ
እና አንተ ለእኔ ልጆቼ ናቹ ግን ምግባራቹ ባህሪያቹ ለየቅል ነው አይኔን በመርፌ እየነካህብኝ
ነው እጆችህን ሰብስብ አለ በለዚያ መቼም ይቅር አልልህም አለው በዚህም የተነሳ ደነገጠ
አባቱ ጆንን ያሜናዳብ ብሎ ነው ሚጠራወ በእምነቱ በጣም ጠንካራ ነው ሁሌም ስለ ጆን
ሲጠየቅ #የእሴይ_ሥር_ያሜናዳብ_ሰረገላ_የዳዊት #መሰንቆ_የሰለሞን_አክሊ
ል_የታጠረች_ተክል_የተዘጋች #የውኃ_ገድጓድ_አንቺ_ነሽ_አመቤቴ ይላል እና የእኔ
የምድር #ያሜናዳቤ እሱ ነው ይላል ልክ አባቱ እንደዚህ ባለው
ማታውን ነፍሰ ገደዮች ጆንን ደብድቦ ሊገሉት ሲሉ ደውሎ ካልነካቹት ተውት አላቸው እንደ
ደበደቡት ሲነግሩት ከአከባቢው ጥፉ አላቸው እነሱም እንደ ተባሉ አደረጉ መጨረሻ ለይ
ጆን በወደቀበት ሰው አይቶት ሆስፒታል አስገባው በጣም ስለ ተጎዳ ወደ ውጭ ሀገር ሂዶ
እንዲታከም ተነገራቸው በዚህ ግዜ ልዩ ደውላ አሜርካ ላለው ሀያታቸው ነገረችው ለረጅም
አመት አሜርካ ነበር ሚኖረው እንደዛ እንደ ሆነ ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው ወዲያው ወደ
አሜርካ እንዲልኩት አደረገ ጆን ከዛን ቀን በኋላ አባቱ ሲሞት ብቻ ነው ወደ ኢተዮጲያ
የመጣ እሱንም አልቆየም አባቱ ለእሱ ያወረሰውን ሙል ሀብት በወንድሙ ስም አዞረለት
በሰአቱ የጆን ወንድም ማመን ነበር ያቃተው ያን ካደረገ በኋላ ሁለት እህቶቹን ወደ አሜርካ
ይዞ ወጣ በሰአቱ የወንድሙ ሁኔታ ምንም ስላል ተመቸው ያን ሁሉ አመት አሳልፎ ከአመታት
በኋላ ወንድሙ ጋር
ሊታረቅ ወደ ባ/ዳር መጣ ወንድሙም ለብዙ አመት ጆን ለይ የፈፀመውን ነገር እያሰበ
ብቻውን ነበር ሲያለቅስ የኖረው ጆንን ለመጀመርያ ግዜ ሲያየው በጣም ደንግጧል ይቅር
በለኝ ብዬ መሄድ ያለብኝ እኔ እንጂ እሱ አደለም ብሎ በጣም አዝኖ ነበር በራሱ እናንተ
ቤት ዶርም ሊይዝበት የቻለው ደግሞ ከእናተ ቤት ዶርም ተከራይቶ የነበረው የጆን ጓደኛ
ነው ጀን ወደ ኢትዮጲያ ከመምጣቱ በፊት ስለ ወንድሙ እንዲያጣራለት ነግሮት ነበር
በሰአቱ እኔ አንቺ ኤልሲ እና ኪያ ወይም የጆን ወንድም አብረን ነበረ ምንጓዝ ያሰለሆነ
ወንድሙን ለማግኘት ባንቺ መጣ አለችኝ እኔ ደርቄ ቀረሁ ጆን ይሄን ሁሉ ነገር ማሳለፉ
በጣም ገረመኝ ምን አይነት ትዕግስት ነው አልኩኝ በጣም ደነቀኝ እኔም ሁሉ ነገሬን ለጆን
አሳልፌ ሰጠሁት ፍቅርን ከምገልፀው ባለይ አስተማረኝ
ዛሬ ያሁሉ አልፎ ጆን ጋር ልንጋባ ወራት ነው የቀረን ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም
ህይወት እንደ ፈለጓት ሳይሆን የህይወታችን ደራሲ
የሆነ ፈጣሪ ያሰበልንን ሲሰጠን ብቻ ነው ልባችን የሚያርፈው ማንም ሰው የሚመኘው ነገር
ይኖራል
በዛ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ የለባቹም እኔ አሜርካ መሄድ የምፈልገውን ያክል ማንም
ፈልጎ አያውቅም
ነገሮች እንደ ማይሆኑ ባውቅም ተስፋ ግን አልቆረጥኩም ይሄው ፈጣሪ መሻቴን አይቶ
አልከለከለኝም ሁሌም ተስፋ አትቁረጡ አመሰግናለሁ


ሀሳብ አስተያየት እጠብቃለሁ
👉 @Juliiian 👈 ከመሀላችሁ በሌላ ታሪክ እስከ ምን ገናኝ ሰላም ሁኑልኝ። ሌላ የፍቅር ታሪክ በቅርብ ስለሚለቀቅ ቶሎ እንዲደርሳቹ ላይክ እና ሼር አትርሱ @Campus_love stories
2024/06/26 08:10:51
Back to Top
HTML Embed Code: