Telegram Web Link
Campus love Stories
Photo
Hawassa lemtnoru Mekret aytasebm Ehud 3seat Sidama Bahl adarash gibi wst የደም ልገሳ ፕሮግራም
#ልለይህ_መርቄ 🙏🚶‍♂
ያን ሁሉ እየሆንኩኝ
ላንተው እየኖርኩኝ
መውደዴ ካልታየህ አንሶና ደብዞ
ማፍቀሬም ካልገባህ ባብሮነቱ ጉዞ
ደርሶ ካነሰብህ የሴትነት ልኬ
ላይኖችህ ካልሞላ ገፅታየ መልኬ
ለጆሮህ ካልጣመው የውስጤ ትርታ
ብሎ ቤት አልመታ
ላንተ ያለኝ ነገር ካልታየህ ተገልጦ
መሄድ ከፈለገ ልብህ ሌላ መርጦ
ምን እላለሁ ይሁን
ሀዘኔን ደብቄ ላንተ ደስታ ስቄ
ልለይህ መርቄ
በል እንግዲህ ይቅናህ ይሳካልህ አግኝ
ስትወጣም ስትገባ የምታቆላምጥ
ምርጫዎችህንም አብራ የምትመርጥ
ሲከፋህ ተከፍታ ስትስቅ የምስቅ
ካልወደድከው ነገር እጅግ የምትርቅ
ማይመስላት ሁላ በልተህ የምጠግብ
በእንቅልፍህ ሳየቀር ተጨንቃ ምታስብ
ቀድማ ምትረዳህ ገና ሳትናገር
ጥፋትህን ታጋሽ አመለ ገራገር
የት ገባህ የት ወጣህ የማትጨቃጨቅ
ውሀ ቀጠነ አይነት ምክኒያት የማታረቅ
እንኳን ሳቋ ቀርቶ ኩርፊያዋ ሚናፈቅ
አግኝ ይቅናህ እስኪ ቤትን ምታሞቅ
ዊግ ማትቀጣጥል ሜካፕ የማያቃት
ደርሳ የተዋበች በተፈጥሮ ቅባት
ቴሌግራም ፌስቡክ ማትጀናጀን
አግኝ ይቅናህ በቃ አቦ ፍቅር መጄን
የጉዞ ታሪክም የሌላት በጭራሽ
ማቆያም ያልሄደች ከቫይረሱ አዳራሽ
ማስክ የምትጠቀም ወዲህ ሳኒታይዘር
ከራሷ አስበልጣ ላንተ ምትሸበር
አግኝ ይቅናህ ቶሎ ምኞትህ ይሳካ
ጎጆህ ድምቅ ይበል ደስታህ ጣራ ይንካ
በል አሚን በል አንተም
ይሙላልህ ያንተ አለም
ደስታህ ደስታየ ነው እውነቱ ቢመርም
★★
🤷‍♀ ግን ውዴ ምን አልባት🤷‍♀
የድል ነገር ሁኖ ምርቃቴ ባይደርስ
አልተሳካም ብለህ ከኔ እንዳትመለስ
ምዕራፍ 2
ክፍል 16

ብሌን የቶማስን የእሽታ ቃል ስለስማች እጅግ ተደስተች በቃ ደስ አላት የሚገርም ምሽት በደማቋ ሀዋሳ የፍቅር ምሽት ,ፍፁም ስላም ፍፁም ደስታ የስፍነበር ምሽት ,.ቶማስ ብሌንን ሁሌም ያስደስታታል ግን በቃ የዛን ቀኑ ግን ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ መስሎ ታያት አመስግናለው አፍቅርሀለው ትለዋለች እየደጋገመች ልክ እንደስከር ስው እየተጠመጠመች ትስመዋለች ስው አለ የለም አትልም በቃ ደስተኛ ናት,.,,
ቶማስ የብሌን በደስታ እንደዛ መሆን ከምንም በላይ አስደስተው ,የሚስቴን ደስታ አጥፍቼው ነው የከርምኩት ለካ ብሎ ለራሱ አስበ .የይቅርታ አስተያየት ያያታል በቃ አፍቅርሻለው ይላታል ደስ ብሏቸው አመሹ ,ያልደርሱበት ቦታ የለም ከተማዋን ተሽከርከሯት ሀዋሳ በምሽት ውብ ከመሆኗ የተነሳ እነሱም አብርው ውብ ሆነው አመሹ '.,ከዙርት መልስ ቅድስ ገብርኤልን ተሳልመው ተመልስው ወደ መኝታ ክላሳቸው አመሩ,ሁለቱም ደክሟቸዋል ደስታ በውስጣቸው ስፍኖል,...
በማግስቱ ጠዋት ሁለቱም ተነስተው ቁርስ በሉ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ስለነበረባቸው እቃቸውን ስብስበው ደህና ሁኝ ውቢቷ ሀዋሳ ብለው መንገድ ጀመሩ ,ብሌን ደርሳ ልምምድ እስክትጅምርና ለስራ ጓደኞቿ እስክትነግራቸው ቸኩላለች ,በደስታ እየሳቁ,እየዘፍኑ ,ጉዟቸውን ቀጠሉ,....
ብሌንና ቶማስ አዲስ አባባ ደረሱ እቤት ደርስው ልብሳቸውን ቀይረው ብሌን ምሳ ስትስራ እሱ ቤቱን አስተካከለ ,በፍጥነት በፍጥነት ጨርስው ሻወር ወስደው ምሳ በሉ ,,.ቶማስ ቢሮ መግባት ነበርበት ,ብሌንም ልምምድ ቦታ መሄድ ትፍልግ ስለነበር ,በዛው አድርሷት እንዲሄድ ነገርችው እሱም ሳያቅማማ እሽ አለ ,ብሌንና ቶማስ ተያይዘው ወጡ ,,ብሌንም ወደ ልምምድ ቶማስም ወደ ቢሮ,,,,,
ቶማስ ብሌንን ልምምድ ቦታ አድርሷት ስትጨርሽ ደውይልኝ በዚህ መጥቼ አብርን እቤት እንሄዳለን አላትና በስሱ አንገቷን ስሟት ተለያዬ ,...
ቶማስ ብሌን ከመኪና ወርዳ የልምምድ ክፍሉ እስክትገባ ድርስ በአይኑ ተከተላት ,በቃ አንዴ እሽ ብያለው ምንም የምቀይረው ነገር አይኖርም ብሎ አስበ ,ግራ እየገባው ወደ ቢሮው አመራ,,
ብሌን ገና ልምምድ ክፍሉ እንደገባች ስርፕራይዝ !!ብላ ድምፃን ከፍ እድርጋ ጮኽች,ይለማመድበት የነበርውን ቴፕ ዘጋችው .ጓደኞቿ ብሌንሻ በማለት በየተራ ስላም አሏት ደስ አላቸው መምጣቷ ,ስርፕራይዝ ስትል ብዙም አለሰሟትም ነበር ስለዚህ እንደድሮው ስላም ልትላቸው የመጣች መስሏቸው ብዙም አልተደስቱም ነበር ,,
በብሌን ፊት ላይ የሚታየው የደስታ ፊት ግን ግራ አጋብቷቸዋል ,,ዮኒ ብሌንሻ እንዴት መጣሽ ዛሬ ስሞኑን ስልክሽ አይስራም ነበር በስላም ነው ?አላት ..ብሌን እየተጣደፍች ደስ ብሎኛል ልምምድ ልጅምር ነው "ሀኒ"ቶማስ ከእናንተ ጋር አብሬ መስራትና አብራችሁ መሄድ እንደምችል ነግሮኛል አለቻቸው ተደሰቱ የደስታ ጭፍራ የደስታ ፉጨት ደስ የሚል ጊዜ በቃ ወደ ልምምድ አለ ዮኒ ሁሉም ወደ ልምምዳቸው ተመለሱ ብሌንም አብራቸው መስራት ጀመርች።....
.
.
ይቀጥላል...
ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ
ፍቅርና እምነት //ፍቅር ባጋጣሚ
ምዕራፍ 2
ክፍል 17


ብሌን ወደ ልምምድ ቦታ ሄዳ ደስታዋን ከውዝዋዜ ባልደረቦቿ ጋር ሆና ከተደሰተች በኃላ ወደ ልምምድ ገብ በቃ ደስ በሚል ስሜት ልምምዷን ማድርግ ጅመረች ,የእልህ ልምምድ ,የደስታ ልምምድ ,ሁለቱም ስሜት ተፍራራቆባታል ,.,,ስትፍልገው የነበርው እድል ስለተገኝላት ቶማስም ስለፍቀደላት እሱን ለማስደስትና ፍላጎቷን ከግብ ለማድርስ በእልህ ትወዛወዛለች,,ቶማስ ስለፍቀደላት ወደ ቀድሞው ማንነቷ ስለተመለስች የደስታ ውዝዋዜ ትስራለች በቃ ብሌን ደስተኛ ናት,
-
ቶማስ ወደ ስራ ቦታው ሄዶ የሚያስርክባቸውን ወርቀቶች አስርክቦ የሚፍረም ነገር ፍርሞ ሊወጣ ሲል ,ቶሚ ?የሚል ድምፅ ስማ ጓደኛው ነበር ስላም ተባብለው የቶማስን የድካም ስሜት ከፊቱ ላይ እንብቦ የተርዳው ጓደኛው ና ሻይ ብና እንበል ብሎ አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ካፌ ይዞት ሄደ ,.
-
የቶማስ ጓደኛ በቶማስ እንደዚህ መሆን የተገረመ ,የተከዘ,ብቻ የተጨነቀ ይመሥላል፣ቶሚ በስላም ነው?ምንድነው እንደዚህ ያደርገህ ምን ተፍጠር? ብሎ ጠየቀው ?ቶማስ ዝም እንዳለ ነው።የቶማስ ጓደኛ መለስ አድርጎ ቆይ ለብሌንሻ አልፍቀድክላትም እንዴይ ምን ተፍጠር ስላም አይደላችሁም ?አለ በድጋሚ።
-
አይ አለ ቶማስ ፍቅጄላታለው እሱ ነው እኔን ያሳስበኝ ,እሷ የሌለችበት ቤት ,የሌለችበት አልጋ,የሌለችበት ኩሽና,እር ስንቱ .,ገና ሳስበው በጭንቀት ልፍነዳ ነው ብቃ ግራ ገብቶኛል አለ በተዳከመ ድምፅና ስሜት ,ቶማስ እንደዚህ መሆን ጓደኛውን ይበልጥ ግራ አጋባው ,ቆይ ግን መፍቀድህ ስህተት ነው ብለህ ታስባለህ?አለ ጓደኛው ፍቀድላት ስላለው እኔ ስላልኩት ይሆን የፍቀደላት እያለ እራሱን እየጠየቀ?, አይ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ዛሬ (እናቴ)ብሌንዬ ላይ ያየሁት ደስታ በጣም ያስደስት ነበር በቃ ደስተኛ ነች ስለዚህ ለደስታዎ መጥፍት መንስኤ አልሆንም ልርዳት ይገባል አለ።ቶማስ ቀጠለ ግን አፍቅራታለው ላጣት አልፍልግም ምናልባት ባጣትስ ብሎ ጠየቀ ?ለራሱ እራሱ መልስ ስጠ አይ አይሆንም አለ።
-
ብሌን ልምምዷን ጨርሳ ለቶማስ ሳትደውል ከልምምድ ቦታ ቶማስ በጣም ወደሚወደው አንድ ሆቴል አመራች ,ሆቴል ደርሳ ብዙ ነገሮችን ለማታ ትእዛዝ ስጥታ ወንበር አስይዛ ስርፕራይዝ አዘጋጅታ ወደ ሌላ ካፌ አመራች ,ካፌው እልምምድ ክፍላቸው አጠገብ ነው ,ለቶማስ ደወለችለት ልምምድ እንደጨርስችና መጥቶ እንዲወስዳት ነግራው ስልኩ ተዘጋ ካፌ ቁጭ ብላ ማኪያቶ እየጠጣች ቶማስ ደርስ በቃ ደስተኛ ነበርች ,ገና ስታየው ከመቀመጫዋ ተነስታ ሀኒዬ ብላ አቅፍ ሳመችው,.ሁለቱም ስላም ተባብለው ተቀመጡ ,ቶማስም ማክያቶ አዞ መጠጣት ጀመር .,
-
ብሌን ቶማስ ውስጡ ጥሩ እንዳልሆነ ስለተረዳች ሂሳብ ከፍለው ወደ ቤት መሄድ እንዳለባቸው ነግራው ሂሳብ ከፍለው ወደ ቤት ሄዱ ,.እቤት እንደደረሱ ቶማስ ሶፍው ላይ በቁሙ ወደቀበት በቃ የድካም ስሜት ይታይበታል ,ብሌን ቶማስን ተጠግታው ደርቱ ላይ ጋደም አለች (ሀኒ)አለች ድምፃን ቀነስ አድርጋ ,ምነው እናቴ አላት ፀጉሯን እያሻሽ ,ምን ሆነህ ነው ችግር አለ ለምንድነው የከፍህ አለችው ,?ቶማስም ምንም እናቴ ምንም አልሆንኩም ስለደከመኝ ይሆናል ስራፍበት ይለቀኛል አላት ,.,,
-
ብሌን የቶማስ መልስ አላስደስታትም ብቻ ግን ልትጫነው አልፍለገችም ,.እሽ ሀኒዬ ተነሳ ልብሳችንን ቀይረን እራት በልተን እንምጣ አለችው ከደርቱ ላይ ተነስታ ,አንገቱን በስሱ እየሳመችው,. ቶማስም እናቴ ዛሬ መውጣት አላስደስተኝም ይቅርብኝ እዚሁ ስርተን እንብላ ባይሆን እኔ እስራለው ከደከመሽ አላት,ሀኒዬ አይቻልም ውጭ እንድንበላ ነው የምፍልገው ተነስ ብላ የግዱን አስነሳችው ,ልብሱንም መርጠችለት እሷም ውብ ሆና የራት ቀሚስ ለብሳ የምገርም ሽቶ ተርከፍክፍ ወጣች የለበስችው ቀሚስ እሱ ከለበስው ጃኬት ጋር ይመሳሰላል አምሮባቸዋል ,ቶማስ ግራ ገባው ቆይ ዛሬ ምን ተገኝ እናቴ አላት ውበቷን እያደነቀ ,ምንም ሀኒዬ አንዳንዴ ዘና እንበል ብዬ ነው አለችው እሽ ተባብለው ከቤት ወጡ,,......

🔜ይቀጥላል
ከወደዱት ሏይክ እና ሼር ያድርጉ
ፍቅርና እምነት💖 //ፍቅር ባጋጣሚ//
ምዕራፍ 2
ክፍል18
-
ብሌን ለቶማስ ስርፕራይዝ አዘጋጅታለች ቶማስ ግን ውስጡ ምን ጥሩ ስሜት ስለሌለው ከቤት መውጣት አልፍለገም ነበር ለብሌን ሲል ግን ልብሱን ቀያይሮ ከቤት ውጡ ሁለቱም አምሮባቸዋል ብሌን ደስተኛ ነች ነገር ግን የቶማስ ደስተኛ አለመሆን ደስታዋን እያደፍረስው ነው.
-
ብሌን ከስአት ልምምድ ቦታ እንደሄደች ለማታ ቶማስን ስርፕራይዝ ለማድርግ ብላ ብዙ ነገሮችን ስታደርግ ነው የዋለችው በቃ ለጓደኞቻም ነግራቸው እነሱም የበኩላቸውን እርድተዋታል ብቻ በቃ ደስ የሚል ስርፕራይዝ እንደሚሆን እርግጠኛ ነች ብሌን ሲደስት ማየት ናፍቋታል ስለዚህም የቻለችውን አድርጋለች..
-
ብሌንና ቶማስ ከቤት ወጥተው ብሌን መኪናውን እያሸረከረ ስርፕራይዝ ወደ ተዘጋጅበት ሆቴል አመሩ ,ቶማስ አሁንም ውስጡ ደስተኛ አይደለም ከፍቶታል ብስስት ብሌንን ያያታል አፍቅርሻለው እናቴ ይላታል በአንድ እጅ እጃን ጥብቅ አድርጎ ይዞል በአንድ እጁ መሪውን ይዞል በቃ የሚያሳዝን አስተያየት እያያት ነው የቶማስ ስጋትና እንደዚህ መሆን ብሌንን ግራ አጋብቷታል ግን ለምን ትላለች መልስ ግን አታገኝም ..
-
ብሌንና ቶማስ ቦታው ላይ ደረሱ ገና ከመድረሳቸው የመኪናውን በር ከፍተው ወደ ውስጥ ሲገብ ሁለት ሴቶች በር ላይ ጠብቀው አበባ ስጧቸው ቶማስ ገረመው ወደ ውስጥ ገቡ ለብቻቸው እተያዘላቸው ክፍል ውስጥ ገቡ የሻማ መብራት ለስለስ ያለ ሙዚቃ ወይን በቃ ደስ የሚል ድባብ ያለው ደማቅ ምሽት ነው ቶማስ ገርሞታል ይሄንን ሆቴል በጣም ይወደዋል ግን እንደዚህ ሆኖበት አያውቅም ,. ገብተው ተቀመጡ መብራቱ ደብዝዛ ነው, ሁለት ወንዶች ቆመዋል ነጭ በነጭ ነው የለበሱት ,.ወደነ ቶማስ ተጠግተው እነቶማስን ማስተናገድ ጅመሩ ደስ የሚል ምሽት ሁሉም ነገር ብሌን ባዘዘችው መንገድ እየሄደ ነው ,.,
-
ብሌን የውዝዋዜ ጓደኞቿ በውዝዋዜ ምሽታቸውን እንዲያደምቁ ነግራቸው ስለነበር እራት ከበሉ በኃላ ተስጥቷቸው ከነበርበት ክፍል ወጥተው ወደ ሆቴሉ እንዲገብ ተደረገ ,ገብተው ተቀመጡ የብሌን የስራ ጓደኞች ያዘጋጅትን የውዝዋዜ ትእይንት በሚገርም ሁኔታ አቀረቡት ቶማስ በጣም ተደስተ ደስ የሚል ምሽት መሆኑን እያስበ ብሌንን አመስገናት በቃ ደስ አለው ሁሉንም ነገር እረሳው ,.,.
-
ብሌንም ዋንኛው አላማዋ ቶማስን ማስደስት ስለነበር መደስቱን ስታይ ተደስተች ምሽቱ ድምቀቱን ቀጥሏል በቃ ደስ የሚል ምሽት ቶማስ ብሌንን ደጋግሞ እንደሚያፍቅራትና እንደሚያመስግናት ነገራት ከልብ ደስ ብሎታል ,.-
-
ምሽታቸው ደስ ይል ነበር ሂሳብ ቀድማ ብሌን ስለከፍለች ወደ ቤት ለመመለስ ተነሱ ,መኪናው ጋ ሲሄድ የመኪናውን ቁልፍ ብሌን ከቶማስ ተቀበለችው ,ትንሽ ሞቅ ስላላቸው እሱ መንዳት እንደሌለበት ነግራው መኪናውን እንዲነዳ ለውዝዋዜ አስልጣኟ ዮኒ ስጠችው ,ዮኒም ተቀብሎ እነሱን ለማድረስ ወደነ ቶማስ ቤት ገስገስ ,.
-
እቤት አድርሷቸው ዮኒ ይከተላቸው በነበርው የጓደኞቹ መኪና ተመለስ ብሌንና ቶማስ ደስ የሚል ምሽት አሰለፍ ሁሉም ነገር ደስ ይል ነበር በቃ ደስተኛ ነበሩ ቶማስም ሁሉንም ነገር እረስቶታል ,.መኝታቸው ላይ እንደወደቁ ነጋ ,.
-
ጠዋት ብሌን ቀድማ ተነስታ ለቶማስ ቁርስ ስርታ ቶማስን ቀስቀስችው እሷም ለልምምድ ስለምትወጣ እሱም ስራ እንዳይረፍድበት ብላ አስባ ነው ተነስቶ ሻወር እስከሚወስድ እሷ ልብሷን ለባበስች ቁርስ በልተው ተያይዘው ወጡ ,. ቶማስ ወደ ስራ መኪናውን እያፍጠነ መንዳት ጀመረ በቃ ድጋሚ ወደ የብሌንን መሄድ እያስበ ነው ,በድንገት ስልኩ ጮኽ ,ስልኩን አነሳው የስቃ ድምፅ ነው መኪናውን እንደምንም አቁሞ ምን እንደተፍጠረ ጠየቀ የስማውን ነገር ማመን አቃተው ,........

ይቀጥላል ....
💖ከወደዱት ሼር & ላይክ💖
ፍቅርና እምነት💖
ምዕራፍ "2" ክፍል "19"
-
ቶማስ ብሌንን ወደ ልምምድ ቦታ አድርሷት ወደ ስራው መሄድ ጀመረ ,ብዙ ነገሮችን እያስበ በሀሳብ እሩቅ ቦታ ሄዷል ብቻ ግን ውስብስብ ስሜት ነው የሚስማው :ድንገት የስልኩ ጥሪ እርቆ ከተጓዘበት መንገድ ብንን አለ .ስልኩን አነሳው የስቃይ ድምፀ በመደንገጥ እንደምንም ብሎ መኪናውን አቆመው .የሆነውን ነገር ጠየቀ ,,,
-
የብሌን ድምፅ ነበር "ሀኒ" አለች እያለቀስች ቶማስ ደንግጧል ምንድነው እናቴ አላት "ሀኒ" ሳራ ሳራ አለች እየተርበተበተች ምንድነው "እናቴ" አለ ቶማስ ግራ ተጋብቶ ሳራ የመኪና አደጋ ደርሶባት ሆስፓታል እንደገባችና አሁን ደወለው እንደነገሯት ነገረችው ቶማስ ደነገጠ ,ብቃ መጣሁ እሱ ጋ ጠብቂኝ አላት ,
-
ቶማስ በጣም ደንግጣል የብሌን ብቸኛ እህት በመሆኗ ብሌን ምን ሊስማት እንዲችል አስበው በቃ ደንግጧል በፍጥነት ወደ ብሌን መኪናውን አስነስቶ ገስገስ ,ብሌን ኩርምት ብላ ታለቅሳለች ,ቶማስ ሲደርስ ተንደርድራ ተጠመጠመችበት ,እህቴ እህቴ ሳራ አለችው እያለቀስች ,ቶማስ ምን ይሁን አይዞሽ ምንም አትሆንም ነይ እንሂድ ብሎ ሳራ ወደ ተኛችበት ሆስፓታል አመሩ ,,,
-
ብሌን ሆስፓታል ደርሳ እናትና አባቷን ስታይ ይበልጥ ልቧ ተስበረ እናቷ ኩርምት በለው ያለቅሳሉ አባቷም ልጄ እያሉ ይቁነጠነጣሉ,.ብሌን እናቷ ላይ ተጠመጠመች ስሜቷን ለመቆጣጠር እየሞከረች እናቷን ማፀናናት ጅመረች ምንም አትሆንም እሽ እማ ተረጋጊ አለች ,ተነስታ አባቷንም አባ ሳራ ምንም አትሆንም እሽ አለችው ስሜቷን ዋጥ አድርጋው .,.
-
ብሌን መለስ ብላ ቶማስን አቀፍችውን ስቅስቅ ብላ አለቀስች አይዞሽ እናቴ ተረጋጋ አላት ,ሳራ ኦፕራሲዬን ክፍል ስለሆነች በሩ ላይ ቆመው ሰለ ሳራ የጤና ሁኔታ የሚነግራቸው ዶክተር እየተጠባበቁ ነው ሁሉም ተጨንቀዋል በየ ፊናቸው ይንጎራደዳሉ,ድንገት አንድ ዶክተር ከኦፕራስዬን ክፍል ወጣ ,ብሌን ተንደርድራ ሄደች ,እህቴ እንዴት ናት አለችው የዶክተሩን አይን አይን እያየች , ዶክተሩም ፍገግ ብሎ ደህና ናት ሁሉንም ነገር አድርግንላታል ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ወደ አልጋ ክፍል እንወስዳታለን አላቸው ,ሁሉም ተቃቅፍው የደስታ እንባ ተላቀሱ ,ደስ አላቸው ,..
-
ቶማስ በዛች ቅፀበት ብዙ ነገሮችን አስበ ህይወት እንደዚህ ናት ሳናስበው የሚፍጠሩ ብዙ ነገሮች አሉ ለምን ይሆን የምጨነቀው ለምንስ ፍቅሬን ሚስቴን እናቴ አስከፍለው ,ብሎ አስበ ብሌንን እናቴ ብሎ እቅፍ አድርጓት አለቀስ አፍቅርሻለው ምንም አትሁኝብኝ አላት ,ብሌን የሆነ ነገር እንደተስማው ስታውቅ ምንም አልሆንም ሀኒ አለችው አንገቱን በስሱ እየሳመች ,. ድንገት ሳራ ከኦፕራሴዬን ክፍል ወጣች ሁሉም አይዞሽ እሽ አሏት ,አብረዋት መኖናቸውን ስታይ ፍገግ አለች ,ሳራ ብዙም አልተጎዳችም ብቻ ግን መኪናው ሲገፍትራት አስፓልት ላይ ስለወደቀች ስውነቷን ስለቀጥቀጠውና አጋጫ ጋ ትንሽ የመስንጠቅ ነገር ስለደረስባት እሱን ነበር ያስተካከሉላት ብቻ ግን ደህና ናት ,., ወደ ክፍል አስገብተዋት ..
-
ብሌን እቤት ሄዳ ልብስ ይዛ ልትመጣ ከቶማስ ጋር ተያይዘው ወጡ ,ብሌን እናትና እባቷ ቤት ሄዳ የሚያስፍልጉ ነገሮችን ይዛ ተመለስች ,ቶማስም አድርሷት ወደ ስራ ሄደች ,ብሌንም ልምምዷት ትታ እህቷ ጋር ቆየች ብቃ አብራት ውላ አብራት አደረች ,በ 3ኛው ቀን ከሆስፓታል ወጣች እየተሻላት ነበር በቃ ደህና ናት ,ብሌንም ወደ ልምምዷ ተመለስች ,., ብሌን ከሁለት ቀን በኋላ ጉዞ ስላለባት መዘገጃጀት ጀመረች ብሌንም ውስጡ ፍራት ፍራት ቢለውም ምንም አላለም በቃ አብሯት የምትፍልገውን ነገር ያማላላታል.,.
-
ቶማስ ብዙ ጊዜ የሚያስበው በሌሎች ጓደኞቹ ላይ የደረስው ነገር በሱም እንዳይደርስ ስለሚፍራ ነው አንዱ ጓደኛው ከዚህ በፊት ለስራ ብላ ጅርመን እንደገባች አግብታ በዛው መቅረቷንና እንዱ ደግሞ አረብ ሀገር ሄዳ እዛው አረብ አግብታ እንደቀረች ስለሚያውቅ በቃ ያንን እያስበ ነበር የፍራው , ግን በልብ ትልቅ እምነት አለ ብሌን ታፍቅረዋለች የመጀመርያዋ ነው በቃ መቼም እንደማትለየው ያውቃል ግን ልብ ፍርቷል ያፍቅራታል ,. ብሌን ዝግጅቷን ጨረሳ ከጓደኞቿ ጋር ግዞ ዛሬ ማታ 1:00 ስአት ላይ ነው ሁሉንም ተስናፍታለች ,......

ይቀጥላል ....
ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ join 👉👉
ፍቅርና እምነት
ምዕራፍ 2
ክፍል 20
-
ብሌን ዛሬ ማታ 1:00 ስአት ላይ በረራ አለባት ,ቤተሰቦቿን
ሁሉንም ተስናብታለች ከቤት ለመውጣት እየተጣደፈች ነው
.ቶማስ ግን አሁንም ቁዝም እንዳለ ነው ምን ማድረግ
እንዳለበትም አያውቅም ብቻ ግን ዝምታን መርጧል.,
-
ሳራ እቤት ተመልሳለች ደህናም ነች ተሽሏታል .የገጫት ልጅም
እየተመላለሰ አሳከማት.. እየተመላለሰም ይጠይቃታል .መክሰስ
አልፍለገችምና አልከሰሰችውም ስለዚህም እሱ የሚችለውን
እያደርገ ነው አንዳንዴም ካፌ ይዟት ይሄዳል በጣም ተቀራርበዋል
,..
-
ብሌን ከቤት እቃዎቿን ይዛ ወደ ኤርፓርት ለመሄድ ከቤት ወጣች
ጓደኞቿም እዛው እየጠበቋት ነው .ብሌን ግን አንድ ነገር አስልበች
ኤርፓርት ከመሄዷ በፊት ወደ ቦሌ ሚካኤል እንዲነዳው ለቶማስ
ነገረችው ቶማስም እሽ ብሎ ወደዛው አመራ ,ቦሌ ሚካኤል
እንደደረሱ ብሌን ውረድ ብላው ወረደች .ቶማስ የግዱን ወረደ
አለም የተደፍችበት ያክል የብሌን መሄድ ከብዶታል .ተያይዘው
ወደ ውስጥ ገቡ ,ሁለቱም ተሳልመው በህሊናቸው ፀሎት
አደረሱ.. ልክ ፀሎት እንደጨረሱ ብሌን የቶማስን እጅ ያዘችው
,"አፈቅርሀለው የምሄደው ለስራ ነው ብዙም አልቆይም አንተን
ሳፍቅርህ እምነቴንም ጠብቄ ነው ፍቅርና እምነት አንድ ናቸው
እመነኝ ሁሌም ያንተ ነኝ ሁሌም አፍቅርሀለው " አለችው
አይናይኑን እያየች ,ቶማስ እንባ ተናንቆት ተንደርድሮ አቀት ,"እሽ
እናቴ አፍቅርሻለው እራስሽን ጠብቂ አላት እንባ እየተናነቀው"
-
ብሌንና ቶማስ ቤተክርስቲያኑን ተሳልመው ወደ መኪናቸው
ተመለሱ ጉዞ ወደ ኤርፓርት .,ብሌን ,"ሀኒዬ ቁርስ መብላት
እንዳትረሳ ምሳም እራትም እንደዛው እሽ ደግሞ ስልክህ በምንም
ምክንያት እንዳይዘጋ እሽ ስትናፍቀኝ ሁሌም በአገኝሁት አጋጣሚ
እደውላለው እሽ አለችው ,.እሽ እናቴ አታስቢ አላት ,.
-
እንዳንድ ነገሮችን እየተነጋገሩ ኤርፓርት ደረሱ እዛም ሲደርሱ
ጓደኞቿን ጠራቻቸውና አንድ ላይ ለመግባት ሻንጣቸውን አዘጋጁ
,ሁሉም ቶማስን ቻው ብለውት መግባት ጀመሩ ብሌንም ቶማስን
አቅፋው ያልኩህን አድርግ እሽ እኔ በቅርብ እመለሳለው አለችው
,አንገቱን,ሁለቱንም አይኖቹን,ከንፍሩን,ጉንጩን ሳመችው
በመጨረሻም ግንባሩን ስማው አፍቅርሀለው አለችው,እኔም
አፍቅርሻለው እናቴ እራስሽን ጠብቂ ብሏት ተለያዩ ,.
-
ብሌንም ተለይታው ወደ ውስጥ ገባች ቶማስ እጁን እያውለበለበ
ውስጡ ባዶነት እየተስማው በአይኑ እስክትስወር ድርስ ሽኛት
,ቶማስ ተመልሶ መኪናው ውስጥ ገባ ወዴት ልሂድ ብሎ አሰበ
ብቻ መኪናውን እስነስቱ ከኤርፓርት ውስጥ ወጣ ድንገት እሬድዮ
ሲከፍት,"የቦሌው ጎዳና ሽር የምንልበት እኔን መልሶኛል አንቺን
ሽኝቼበት "የሚለው ዘፈን ተከፍቷል 'በመበሳጨት እሬዲወኑን
ዘጋው ,.ዝም ብሎ ወደ ቤቱ ሄደ እየፍራ በሩን ከፍቶ ገባ እረጭ
ብሏል ያስፈራል .ዝም ብሎ ወደ መኝታ ክፍል ገብቶ ከነ ልብሱ
ጫማውን ብቻ አውልቆ ጥቅልል ብሎ ተኛ ,.,
-
ብሌን ብዙ እያሰበች የበርራውን ስአት ትጠባበቃለች ለቶማስ
ስትደውል አያነሳም እንደከፋው ስላወቀች ደጋግማ አልደወለችም
.የበርራው ስአት ደርሶ ጉዞ ጀመሩ ,.በሰላም ደርስው
የሚቀበሏቸው መጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሄዱ ስአቱ
በኢትዮጵያ ሊነጋጋ ነው ብቻ ግን ምንም ሳታቅማማ ስልክ ፈልጋ
ወደ ቶማስ ደወለች ቶማስ ማታ እንደተኛ ነው .የስልክ ጥሪ
ድንገት ቀሰቀሰው በደመነፍሱ ስልኩን አነሳው ,,,,,,.
በመጨረሻዉ ክፍል እንገናኝ ....
እንደወደዱት ላይክ እና ሼር ወይም @Juliiian ኮሜንት በማድረግ
ይግለጹልን
ፍቅርና እምነት💖
🔜 የመጨረሻ ክፍል🔚

-
ብሌን እንደደረስች ቶሎ ሞባይል ፍልጋ ወደ ቶማስ ደወለች,.ቶማስ ማታ እንደተኛ ነው ልብሱንም አላወለቀም ከነ ልብሱ ምንም ሳይለብስ ነው የተኛው .,ድንገት ግን የስልኩ ጥሪ ቀስቀስው ,እንደምንም ዳብሶ ስልኩን አነሳው "ሀኒ "የሚል የሚጣፍጥ ድምፅ ስማ ,ከመኝታው ብድግ ብሎ ቆመ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍበት " እ እ እናቴ? አለ እየተርበተበተ ,አወ ሀኒዬ እኔ ነኝ ደህና አደርክ ቀስቀስኩህ እንዴይ አለችው ?.አይ አልቀስቀስሽኝም ደህና ነሽ እናቴ ናፍቀሽኛል እኮ አላት ,እኔም ናፍቀኽኛል አለችው .,ትንሽ አወሩ ትንሽ ቆይታ ደግማ እንደምትደውልለት ነግራው ስልኩ ተዘጋ,...
-
ቶማስ ስልኩን እደረቱ ላይ ለጥፎ ቀስ ብሎ ከአልጋው ስር ቁጭ አለ ከፍለፊቱ የሱንና የሷን የስርግ ፎቶ ተመለከተ ፎቀቅ ብሎ አምጥቶት ወደ ደርቱ አስጥግቶ እቅፍ አደርገው ዘላለሜን አፍቅርሻለው ያላንቺ ቤቱ ብቻ ሳይሆን እኔነቴም ባዶ ነው አለ,ብሌን ስልኩን ዘግታ ሻንጣዋን ይዛ ወደ ክፍሏ ገባች ሻንጣዋን ከፍተችው ከልብሷ ውስጥ ፍልፍላ አንድ የቶማስን ቲሽርትና አንድ የቶማስን ሽሚዝ አወጣች ,ጭምቅ አድርጋ ወደ ድርቷ አስጠጋችው በደንብ ሽታውንም አሽተተችው ,አፍቅርሀለው እስከ እስትንፍሴ መጨረሻ ያላንተ ባዶ ነኝ አለች ,ከዛም ሻወር ወስዳ የቶማስን ቲሽርትና ሸሚዝ ለብሳ ከታች ቁምጣ አድርጋ ወደ ጓደኞቿ ተደባለቀች ,.
-
ብሌን ገና ከኢትዮጵያ ስትነሳ ነው ሴም ካርድ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቃት ያዘዘችው እሱም ተዘጋጅቶላት ነበር ስልኳን እምጥታ ሴም ካርዱን አስገብታ አፕልኬሽኖችን መክፍት ጀመረች ,ከዛም በእስካይፕ(skyp)ቶማስን አወራችው በጣም ገርመው ሽሚዙን ለብሳው ሲያያት በቃ ደስ አለው ,ብሌን ከዛን እለት ምሽት ጅምራ ስራ ጀመረች በአጋጣሚው ሁሉ ግን ታወራዋለች እሱም የምትለውን ሁሉ ይስማታል በቃ በጣም ብትናፍቀውም ችሎታል እሷም እንደዛው,
-
ብሌን እህቷ ጋ ደወለች ስለጤንነቷም ጠየቀቻት ተሽሏታል በጣምም ደህና ናት ,ብሌን ደስ አላት ,.ሳራ ተሽሏታል ግን ከገጫት ልጅ ጋር በጣም ከመቀራረባቸው የተነሳ ፍቅር ጀምረዋል ደስተኛ ሆናለች ስትናፍቀው የነበርውን ፍቅር አግኝታለች እንደ እህቷ እሷም ቤተስቧን ማስደስት ትፍልጋለች ,
-
ብሌን ስራዋን ስርታ ጨረስች አብረዋት የሄዱት ሁሉ ከአስልጣኛቸው በስተቀር ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይፍልጉ ነገሯት ሌላ ቦታ መስራት እንፍልጋለን አንመለስም አሉ ,ብሌን ግን ግዴታ መመለስ ነበረባት ውስጧም ጥሩ ስሜት የለውም በቃ ያላወቀችው ስሜት እየተስማት ነው ስለዚህ ሁሉንም ነገር ትታ ወደ ኢትዮጵያ ልትመለስ ወስነች ለቶማስም ነገርችው በጣም ደስ አለው ,ሁሉንም ትታ ከአስልጣኙ ጋር ተመልሳ ወደ ሀገሯ መጣች ,ቶማስ ኤርፓርት ሄዶ ተቀበላት ሲያያት ተንደርድሮ ተጠምጥሞባት የደስታ እንባ አለቀስ , እንዴ ሀኒ ስሄድ አልቅስህ ስመጣ አልቅስህ አለችውና ተሳሳቁ ,.
-
ብሌንና ቶማስ ,የብሌንን አስልጣኝ እቤቱ ካደረሱት በኋላ ጉዞ ወደ ቤት ,እቤት ስትደርስ የጠበቃት ነገር የሚገርም ነበር የቶማስ ቤተስቦች የሷ ቤተስቦች እንዲሁን የሳራ አዲሱ ፍቅርኛ ,በጣም ደስ ይል ነበር ደስ አላት ,አብረው ሲደስቱ አመሹ ደስ የሚል ምሽት ብሌን ግን የማታ ማታ ትንሽ አመማት ወደ ሆስፓታል ቶማስ ይዛት ሄደ .,.በደንብ ተመረመረች .,ከምርመራው በኃላ ውጤቱ ደረስ የሚገርም ነበር ለማመን የሚከብድ ብሌን የ 3 ወር ነፍስ ጡር ናት በጣም ተደሰቱ በቃ ቶማስ የደስታ እንባ ተንበርክኮ አለቀስ ብሌንም ሳታስበው እንባዋ ይወርዳል .,
-
ብሌንና ቶማስ ለቤተስብ ደውለው ተናገሩ በደስታ ላይ ደስታ በቃ ከዛን ቀን ጀምራ ቼክ አፕ ጀመረች በየወሩ ትመላለሳለች በመሀከል ሳራ መስፍንን አገባች መስፍን ማለት የገጫት ልጅ ነው ,ድል ባለ ስርግ ተጋቡ .,ብሌን የ 6 ወር ነፍስጡር ሆናለች አንድ ቀን ብሌንና ቶማስ የልጃቸውን የልብ ምት ለመስማት አብረው ሆስፓታል ሄዱ የሚገርም ተአምር ተፍጠረ ቢሌን ያረገዘችው አንድ ሳይሆን ሁለት ነው ,ቶማስ ማመን አልቻለም በቃ ደስ አለው,.
-
ቶማስ የብሌን የመውለጃ ቀን እስኪደርስ በጣም እየጓጓ ነው እሷንም በጣም ይንከባክባታል አንድ ቀን እንዲህ ሲል አስበ ልጆቼ ሲወለዱ ሁለቱም ሴት ስለሆኑ የመጀመርያዋን እምነት የሁለተኛዋን ፍቅር አላቸዋለው ብሎ አስበ ,.
-
ብሌን የመውለጃዋ ቀን ደርሶ በስላም ምንም ሳትሆን ልጆቿ ምንም ሳይሆኑ በስላም ተገላገለች የመጀመርያዋን እምነት ሁለተኛዋን ፍቅር አላቸው ,.ብሌን ለኔ ብዙ ነገር አስተምራኛለች ፍቅር ያለ እምነት እምነት ያለ ፍቅር ባዶ እንደሆነ አስተምራኛለች አለ ,.ብሌንና ቶማስ ፍቅራቸው ይበልጥ ደመቀ አንድ ቀን ቤተስብ ተስብስቧል የልጆቻቸው 6ኛ ወር እየተከበረ ነው ቶማስ አንድ ነገር መናገር እፍልጋለው አለ ብዙ ስዎች አሉ ,ቶማስ ድምፁን ከፍ አድርጎ የልጆቼ እናት የኔ የቤቴን የህይወቴም ድምቀት አንቺ ነሽ አፍቅርሻለው አላት የልጆቼን ስም እምነትና ፍቅር ያልኩት ,እምነትንም ፍቅርን እሷ ስላስተማረችኝ ነው ዘላለሜን አፍቅርሻለው አላት ,እሷም አፍቅርሀለው አለችው ,.
🔜 ተፍፀመ!!🔚 Join Join join


Any comments @Juliiian
የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️ እዉነተኛ ታሪክ ♥️
✍️አዲሱ የደናዋ እናት ልጅ (ግሬ)


...🖊ከአልጋዬ ፊት ለፊት የልብስ ማስቀመጫ ቁምሳጥን ላይ የሚገኘዉ መስታወት እኔ ስስቅም ሆነ ሳለቀስ መመልከትን ለምዶታል። አንዳንዴ ''መስታወት የልብ ጓደኛዬ ነዉ ምክንያቱም እኔ እያለቀስኩ እሱ አይስቅብኝም!'' የሚለዉ አባባል በልኬ ተሰፍቶ የተሰጠኝ ይመስለኛል... ሀዘን ደግሞ ከእኔ ፍቅር የያዘዉ ይመስል በተደጋጋሚ እየጎበኘኝና የማይድኑ የልብ ጠባሳዎችን እያስታቀፈ ወዳጄ የሆነዉ መስታወት ፊት ይገትረኛል... ከመስታወቱ ፊት ለፊት ቆሜ እራሴን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት ፀጉሬ ተንጨባሯል...በለቅሶ ብዛት የቀላዉ ዓይኔ እንኳን ለሌላ ሰዉ ይቅርና ለራሴም ፍርሀትን ስለለቀቀበኝ አይኔን ከመስታወቱ አሸሸሁ... ድካምና የእንቅልፍ እጦት ተደራርበዉ ሰላም ነስተዉ ጭንቀት ዉስጥ ከከተቱኝና ከቤት መዉጣት ካቆምኩ አንድ ሳምንት ተቆጠረ። ለቤተሰቤ የመጀመሪያም የመጨረሻም ብቸኛና ተወዳጅ ልጅ ብሆንም፤የቤተሰቦቼ ኑሮ ከራሳቸዉ አልፎ ለሌሎች ይተርፋል ከሚባል ደረጃ ላይ ቢመደብም ከልጅነቴ ጀምሮ አንድ የማዝንበት ምክንያት አለመጥፋቱ ይገርመኛል! ለነገሩ ሀዘን ጥሩ በሚባል የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይጎበኝም ያለዉ ማነዉ?። ስቃይ በገንዘብ ብዛትና በኑሮ ስኬታማነት የማይረታ መሆኑን ምስክር እንድሆንለት ያዘጋጀኝ ምስኪን ሰዉ መሆኔ ተስፋ ያስቆርጠኛል። አሁን ''የሰላም ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮከብ ተማሪ የሆነችዉ ቤዛዊት አለሙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዉጤቷ ተበላሽቶ ዩኒቨርሲቲ የመግባት ህልሟ የዉሃ ሽታ ሆነ!'' ቢባል ማን ያምናል?' ግን እዉነታዉ ይህ ነዉ! ስንት የደከምኩለትና ለስንቶች ምሳሌ የሆነዉ የትምህርት ላይ ጥንካሬዬ በአጭሩ ተቀጭቶ በሀዘን ከተለወጠ አንድ ሳምንት ተቆጠረ...

ይቀጥላል.....

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 2 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የደሃዋ እናት ልጅ (ግሬ)♥️

...🖊በጭንቀትና በሀዘን ከመስታወቱ ፊት ለፊት እንደቆምኩ እናቴ የመኝታ ቤቴን በር ሳታንኳኳ ከፍታ ገባች...

<<የዘንድሮ ልጆች ሁሉም ነገር በአንድ ጀንበር ካልተከናወነ ትላላችሁ! መታገስ እኮ ዋጋ አለዉ!''የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል!'' ሲባል አልሰማሽም? ቤዛዬ እንደ መታገስ ከባድ ስቃይ ያለዉ ነገር ባይኖርም መጨረሻዉ ግን ያማረ እንደሚሆን አትጠራጠሪ!>>
የእናቴ ምክርና የማፅናኛ ቃል የእናትነት ፍቅር የታከለበት ቢሆንም እኔ ግን እንኳን እሷ ቀርቶ ፈጣሪ ወደ ምድር ወርዶ አይዞሽ ቢለኝ እንኳን የምፅናና አይመስለኝም። ወላጆቼ በትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ክፉኛ ተደናግጠዉ ቢያዝኑም በሀዘኔ ላይ ሀዘን ላለመጨመር ሲሉ ብቻ ላይ ላዩን ደስተኛ መስለዉ ለመታየት ይሞክራሉ

<<ቤዛዬ... የአምላክ ስራዉ ድንቅ ነዉ!... ላንቺ ከዚ የተሻለና ጥሩ ነገር ቢያዘጋጅ ነዉ!....ሰዉ የሚያምርበትን ሲፈልግ.....የሚያሳምረዉን...ሰዉ የሚደምቅበትን ሲፈልግ...የሚያደምቀዉን...የሚያስከብረዉን...የሚያዛልቀዉን ማዘጋጀት የፈጣሪ ስራ ሲሆን ይህንን ድንቅ ነገር መሸለም ደግሞ የሰዉ ፀጋ ነዉና አትዘኚብኝ>> አለችኝ!!
ከአልጋዉ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠች። እናቴ ስለ እኔ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ መሆኑን አዉቃለሁ
<<ቤዛዬ አንቺን ከመዉለዴ በፊት ሶስት ጊዜ ፅንስ ተቋርጦብኛል አምላክ የእምነቴን ደረጃ ሊፈትን እንጂ ሊያሳዝነኝ እንዳልሆነ ልቦናዬ ስለሚያዉቅ አማርሬዉ አላዉቅም እርሱም የትዕግስቴን ጥግ አይቶ አመሰግንብሽ ዘንድ አንቺን ሰጥቶኛል እባክሽ ልጄ ሀዘንሽን በልክ አድርጊዉ>> አለችኝ።

እኔን ለማፅናናት የምታደርገዉ ሙከራ ስላሳዘነኝ ከአጠገቧ ቁጭ አልኩ
<<እማ...እማ...እ...እኔ..>> መናገር አቃተኝ!!

<<ቤዛዬ ዩኒቨርሲቲ ባይሆን ምን አለበት የፈለግሽዉ ኮሌጅ ገብተሽ መማር ትችያለሽ እኮ!!>>

<<አ.ዉ.ቃ.ለ.ሁ...እማ... ግን ይሄ ለእኔ አይገባኝም...እኮ!>>

<<ለማን ምን እንደሚገባዉ መወሰን የሰዉ ስልጣን አይደለም!! በእኔ ሞት ይሁንብሽ ይሄ ሀዘን በቃሽ!>> አለችኝ!!

እናቴ <<በእኔ ሞት!>> እያለች ስትለምነኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ካሰብኩት ከወሰንኩበት ነገር ሳይቀር ምልስ እላለሁ እሷም ይህን ስለምታዉቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስሆን
<<በእኔ ሞት!>> ትለኛለች
<<አሁን ተነሺ አባትሽ ሊያናግርሽ ይፈልጋል!>>
<<በእኔ ሞት>> ያለችኝ እናቴን ማሳዘን ስላልፈለኩ እጄን ይዛ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ልቃወማት አልቻልኩም...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 3 ከ300♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
አዲስ የጎሀው
እንሆ ጀመረ 👇👇👇
....የሀዘኔ መጨረሻ....

....ክፍል 1 .....

☺️☺️😍😍☺️☺️

.....ሰላም እባላለሁ ታሪኬን ላካፍላችሁ ያኔ 17 አመቴ ነበር የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ :: የምኖረው ከእናት አባቴ እንዲሁም ከወንድሜ ጋር ነበር፡፡ አባቴ የኮንስትራክሽን ባለሙያ ነበር፡፡ እናቴ የህክምና መስጫ ተቋም ውስጥ ዳይሬክተር ነበረች፡፡ ያው ዶክተር ማለት ነው፡፡ እሁድ እሁድ ከእንቅልፌ የምነሳው 4 ሰዐት ነበር ፡፡ በ1እሁድ ቀን ግን የተነሳሁት 2 ሰዐት ነበር፡፡ ምክንያቱም አቤል ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ስላለኝ፡፡

......አቤል የ 7 አወት ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡ አቤልን በጣም እወደዋለው፡እናም መኝታ ክፍሌ ገብቶ "ሰሊ ሰሊ ተነሺ" አለኝ አይኔን እያሻሸሁኝ "በጌታ ተወኝ" አልኩት፡፡"ተነሺ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ በናትሽ" አለኝ፡ ትንሽ ከተግደረደርኩኝ በኀላ "እሺ" አልኩት፡፡ ደስ ብሎት ከአልጋዬ ሊወርድ ሲል "ግን" ብዬ እጁን ያዝኩት ፡፡ዞር ብሎ "ምን" አለኝ እየተቅለሰለስኩኝ "ያው የሳምንት ብር ተሰቶሀላ"አልኩት"፡፡እናትና አባታችን የሳምንት ብለው እሁድ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ብር ይሰጡናል፡፡ አቤልም ድምፁን ቀነስ አድርጎ "አው"አለኝ፡፡ "እሺ የተሰጠህን ብር ግማሹን ትሰጠኛለህ"አልኩት "አልሰጥሽም" ሲለኝ ተመልሼ ተኛው::
...ትንሽ ከቆየ በኀላ ባዘነ ድምፅ "እሺ "አለኝ፡፡ ከዛ ተነስቼ ተጣጥቤ ሄድን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ሲያልቅ ትንሽ ቁጭ አልን፡፡ በድንገት የሆነ ልጅ መጣና እጄን ያዘኝ፡፡ዞር ብዬ በግርምት "አቤት" አልኩት ከዛ "ይቅርታ ከሰው ጋር ተመሳስለሽብኝ ነው" አለኝ፡፡ እኔም"እሺ ምንም ችግር የለውም "ብዬ ዞር አልኩኝ፡፡ ድጋሚ መጥና...........



ክፍል 2 እንዲለቀቅ like . Share ❤️በማረግ ተባበሩን....


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
...የሀዘኔ መጨረሻ.....

😌😌😍😍😌😌

.....ክፍል 2....
.
........ድጋሚ መጣና.."ይቅርታ ስንት ሰዐት ነው"አለኝ፡፡ የሚገርመው እጁ ላይ ትልቅ ሰዐት አለ፡፡ እጅ ላይ ያለውን ሰዐት እየተመለከትኩት "ያንተ አይሰራም" አልኩት፡፡ ደንግጦ እጁን አየው፡፡ ...ትንሽ ካፈጠጠበት በኀላ "አው አይሰራም" አለኝ፡፡

.....ከዛ ስልኬን አውጥቼ ልነግረው ስል"እንደውም ተይው "ብሎኝ ሄደ፡፡ በጣም ገርሞኝ ፈገግ አልኩኝ፡፡

.....ከዛም እኔና አቤል ወደ ቤት ተመለስን፡፡ እቤት እንደገባን ቤዚ እና ሙሌ ይጨቃጨቃሉ፡፡ ቤዛ እናቴ ናት እኛ ቤዚ ነው የምንላት፡፡ሙሌ ደግሞ አባታችን ነው፡፡.....እኔና አቤል በሩን ከፍተን ገባን..ቤዚ"አይሆንም ምን ሆነካል" አለችው ሙሌ ደግሞ ድምፁን እያቅለሰለሰ "ችግር የለውም የኔ ንግስት" አላት፡፡ከዛ አጅዋን ራስዋ ላይ አድርጋ ዞር ስትልእኛን አየችን፡፡ከዛጠ"ውይ መጣችሁ እንዴ" አለችን፡፡ ሙሌ እኛን እንዳየ በፍጥነት ከቤት ወጣ፡፡ "ቤዚ ምን ሆናችሁ ነው" አልኩዋት እሱዋም ሳቅ እያለች "አይ ምንም አልሆንም " አለቺኝ፡፡ ውሸትዋን እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ አቤል በጣም አዝኗል እኔም ደንግጫለው ሁለታችንም እንደዛ ሲሆኑ አይተናቸው ስለማናውቅ በጣም አዝነናል፡፡ቤዚ"አቤሌ ዛሬ አልደከመህማ" አለችው እሱም በአዎንታ አንገቱን ነቀነቀ፡፡ አቤል ቅዳሴ ላይ ስለሚደክመው ቁጭ ይል ነበር ለዛ ነው የጠየቀችው፡፡ ከዛ ቁርስ በላን አቤል ጓደኛው ቤት ለመጫወት ሄደ፡፡ እኔም ክፍሌ ውስጥ ሙዚቃ እየሰማሁኝ ነበር.....

......ወደ 8 ሰዐት አካባቢ ሙሌ ከአንድ ሰውዬ ጋር
ወደ ቤት መጡ፡፡ እኛም ምሳችንን አብረናቸው በላን ከዛ ሙሌ ለሰውዬው " እንግዲ ቤቱ ይሄ ነው"አለው፡፡ቤዚም ተመነጫጭቃ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ሙሌም በእፍረት ድምፅ "ጠዋት ራሴን አመመኝ ስትል ነበር ለዛ ነው ይቅርታ አድርግላት" አለው ሰውዬውም "ኧረ ችግር የለውም" አለው፡፡በችኮላ ድምፅ "አሁን ተስማምተናል በል ካርታውን ስጠኝ "አለው፡፡ ሙሌም "በሚገባ " ብሎ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደ፡፡ እኔና ሰውዬው ብቻችንን ቀረን.....


ክፍል 3 እንዲለቀቅ like ማረግ አትርሱ...❤️
💔የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የደሃዋ እናት ልጅ (ግሬ)♥️

ለዓይን ከሚማርከዉ ሳሎናችን ዉስጥ ካለዉ ባለግርማ ሞገስ ሶፋ ላይ አባቴ የንባብ መነፅሩን አድርጎ የስራ ወረቀቶችን ያገላብጣል። የተለያዩ አይነት የሚባሉ የጭነት መኪናዎች ዋነኛ የሚባሉ የቤተሰባችን የገቢ ምንጭ ቢሆኑም ከእነሱ በተጨማሪ ከምንኖርበት የጅማ ከተማ ዉስጥ በእናቴ ዋና ሀላፊነት የሚተዳደሩ ሁለት ሆቴሎች አሉን። አባቴ የእኔን ወደ ሳሎን መምጣት ሲመለከት ፈገግ አለ...
<< ዛሬም በፈተና ዉጤትሽ መበላሸት እያዘንሽ ነዉ?>>
<< እንዴት አላዝን! አባ! የለፋሁለትና የጓጓሁለት ዉጤት እኮ ነዉ!>>
<<በሀዘን የምትለዉጪዉ ምን አለና?... ነይ እስኪ>> ከጎኑ አስቀምጦ ፀጉሬን መዳበስ ሲጀምር...
<<ዛሬ ለምን እራት ዉጪ አንበላም?>> የእናቴ ሀሳብ ነበር እኔ ግን ከቤት መዉጣት እንደማልፈልግ ገለፅኩላት!
<<ዉጤትሽ የተበላሸዉ በስህተት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል እያጣራሁ ነዉ!...ግን በእንደዚህ አይነት ጭንቀት ዉስጥ መቆየቱ መፍትሔ ስለማይሆን ጠንካራ መሆን አለብሽ ደግሞ እናትሽ ጥሩ ሀሳብ ነዉ ያመጣችዉ ዛሬ እራት ዉጪ ነዉ መብላት ያለብን መንገደኛ ስለሆንሽ የመሰነባበቻ ይሆነናል>>
<<መንገደኛ...ማን ነዉ?...መንገደኛ?>>
<<አዲስ አበባ አክስትሽ ቤት የቀረችዉን የክረምት ጊዜ እንድታሳልፊ እኔና አባትሽ ወስነናል!... ላንቺም ቢሆን ከዚህ ጭንቀት እዛ ይሻልሻል!>>
ንግግሯ የጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ አዘል ስለነበር ዝምታን መረጥኩ።
<<በሉ አንድ የማገኘዉ ሰዉ አለ ለባብሳችሁ ጠብቁኝ!>> ብሎ አባቴ ጉንጬን ስሞ ወጣ።
<<በይ ተነሺና ገላሽን ታጠቢ ከዚህ በሗላ ሀዘን የሚባል ነገር የለም!!>> እናቴ ሳምንቱን ሙሉ የሆቴሉን ሀላፊነት ለማናጀሮቹ አስረክባ ከእኔ ጋር ነበር ያሳለፈችዉ። የምለብሰዉን ልታዘጋጅልኝ ወደ መኝታ ቤቴ አመራች እናቴ በእሷ ምርጫ ልብስ መልበስን አስለምዳኛለች... የግርግዳ ሰዐቱ 10:00 መሆኑን ያመለክታል በረጅሙ ተነፈስኩ...የሀምሌ ሰማይ በደመና ተከቦ ያስገመግማል...እዝን ጭፍግግ ያለ ቀን ነበር ልክ እንደኔ ልብ...

ይቀጥላል ...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 4 ከ👉 200 ♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️*አዲሱ የደሀዋ እናት ልጅ (ግሬ)♥️

...🖊<<ይህ ሁሉ ህዝብ በሚተራመስባት ዓለም ዉስጥ እንደዚህ ብቸኛ መሆን ያዋጣል?>>
ከጅማ ወደ አዲስ አበባ የማደርገዉ ጉዞ በዝምታና በሀሰብ መዋጡን ያስተዋለ ከጎኔ የነበረ መንገደኛ ነበር።
<<ይቅርታ እኔን ነዉ?>>
<<መቼም ከአንቺ ዉጪ በሀሳብ ተዉጦ ከጎኔ የተቀመጠ ሌላ ሰዉ አይኖርም ደሞ... ይህ ቁንጅና ምን ቢበድል ነዉ በዝምታ የምትቀጪዉ?>>
ጠየም ያለ ተጨዋችነቱ ፊቱ ላይ የሚነበብ የደስ ደስ ያለዉ ወጣት ነበር!
<<ዝም ስትል ማዳመጥና ምላሽ መስጠት ትችላለህ ዝምታን ላወቀዉና ለተረዳዉ ከራስ ጋር የመማከር ዘዴ ነዉ>> አይመስልህም?
<< እኔ ፍቅርና ፍልስፍና ላይ ብዙም አይደለሁም ነገሬ ሁሉ ቀጥተኛና ግልፅ ነዉ። አቤል እባላለሁ ምድር ላይ 27 አመታትን አስቆጥሬያለሁ ከአራዶቹ መንደር ሸገር!>> ብሎ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ!
<<ቤዛዊት! እንዳንተ አገላለፅ ምድር ላይ 24 አመታትን አስቆጥሬያለሁ ከአባ ጅፋር ሀገር ጅማ!>> ብዬ እጁን ስጨብጥ... ለረጅም ዘመን የማዉቀዉ ነገር ግን ከጎኔ ያልነበረ...በህልሜ በሀሳቤ የሚመላስ ነገር ግን እዉነታዉ ላይ የሌለ... ብቻ የሆነ የሚያደናግር ስሜት ተሰማኝ።
<<ሸገር ማንን ጥየቃ እየሄድሽ ነዉ?>>
<<የቀረችዉን የክረምት ጊዜ አክስቴ ጋር ለማሳለፍ! አንተስ ከጅማ ምን ጉዳይ ገጠመህ?>>
<< ታላቅ ወንድሜ በስራ ምክንያት ከአዲስ አበባ ጅማ መጥቶ ነበር ነገር ግን እዚሁ ትዳር ይዞ እየኖረ ነዉ የተወሰኑ ሳምንቶችን እሱ ጋር አሳልፌ እየተመለስኩ ነዉ!>>
<<እና ጅማን እንዴት አገኘሃት>>
<<በተደጋጋሚ ስለምመጣ ያንቺን ያህል ባይሆንም አዉቃታለሁ! ጅማ... አይናፋር ቆንጆ ሴትን ትመስለኛለች... ለመቅረብ የምታስፈራ ለመራቅ ደግሞ የምታሳሳ ልክ እንዳንቺ!>>
<<ከፍቅርና ፍልስፍና ይልቅ ቀልድ ይዋጣልሀል መሰለኝ?>>
<< ተሳፋሪዎች ለቁርስ 30 ደቂቃ አላችሁ!>>
የረዳቱ ድምፅ ጨዋታችንን አቋረጠዉ ለነገሩ እኔም ብሆን ማታ የሽኝት ብለዉ ቤተሰቦቼ እራት ቢጋብዙኝም የምግብ ፍላጎቴ ቀንሶ ስለነበር በደንብ አለመብላቴ አሁን የርሀብ ስሜትን ፈጥሮብኝ ነበር። ተሳፋሪዎቹ ለቁርስ መዉረድ ጀመሩ
<< ጨዋታችን ከቁርስ ጋር ይቀጥል?>> አቤል ነበር!...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 5 ከ👉♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የጎሀው

...🖊ለረጅም ጊዜ እንደማዉቀዉ የልብ ጓደኛ ነፃነት ስለተሰማኝ ለቁርስ የታዘዘዉን ምግብ በነፃነት እስከምጠግብ በላሁ። የሀምሌ የጠዋት አየር ከቅዝቃዜና ካፊያ ጋር ተዳምሮ ከአልጋ አትዉጡ አትዉጡ የሚያስብል ቢሆንም እኔ ግን ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በማደርገዉ ጉዞ ድንገት ከተዋወኩት ልጅ ጋር በነፃነት ቁርስ በላሁ!...ይገርማል! በህይወት ዘመኔ እንደዚህ ከሰዉ ጋር በፍጥነት ተግባብቼ አላዉቅም ለዛዉም ከወንዶች ጋር... ለቁርስ የተመደበዉ ሰዓት በመጠናነቁ ወደ መኪናዉ ተመለስን።
<<እና በትምህርት ዉጤትሽ መበላሸት ምክንያት ሀዘን ስለተሰማሽ አክስትሽ ጋር የተወሰኑ ጊዜያትን ለማሳለፍ ነዋ የአዲስ አበባ ተጓዥ የሆንሽዉ?>>
<< አዎ!>> አልኩት ምንም ነገር ሳልደብቅ ስለራሴ ሁሉንም ነገር በመናገሬ ሀፍረት እየተሰማኝ!
<<እኔ የምልህ...ቁርሱ ላይ...አልኮል ነገር ቀላቅለህበት ነበር?>>
<<እንዴት?>>
<<ስለራሴ ብዙ መናዘዜ የታወቀኝ አሁን ነዉ! አንተን እኮ ከስምህና ከጨዋታህ ዉጪ ብዙም
አላወኩህም!>>
<<ስለራሴ ነግሬሽ እንድታዉቂኝ አልፈልግም ድርጊት ከቃል ይበልጣል ድርጊቶቼን አይተሽ ታዉቂኝ ይሆናል... ''ነገም ሌላ ቀን'' ነዉ እኮ!>>
<<እና ሌላ ጊዜም እንገናኛለን እያልከኝ ነዉ?>>
<<አዲስ አበባን ከሩቅ ስትመለከቻት ነዉ ሰፊ የምትመስለዉ ቀረብ ብለሽ ከዉስጧ የምትፈልጊዉ ነገር ካለ ትጠብልሻለች... ሁለታችን ከተፈላለግንባት ደግሞ ምን ያህል እንደምትጠብልን አስቢዉ>> ፈገግ አልኩ!... ለቁርስ የወረደዉ ተሳፋሪ ሙሉ በሙሉ ወደ መኪናዉ ስለተመለሰ ጉዞ ተጀመረ...
ጨዋታ፣ቁምነገር፣ቀልድና ሳቅን ከአቤል እያገኘሁ የማልረሳዉንና ጥሩ ትዝታ ጥሎብኝ እንደሚያልፍ እርግጠኛ የሆንኩበትን ጉዞ እያከናወንኩ ነዉ። መኪናዉ ይሄዳል...ዛፎችና ሰዎች በፍጥነት ሽዉ እያሉ ወደ ሗላ ይቀራሉ...ተሳፋሪዎች ያወራሉ...እፎይታ ተሰምቶኝ ጉዞዬን ቀጥያለሁ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 6 ከ👉♥️ 50 ቡኃላ ይቀጥላል፡
የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የደሀዋ እናት ልጅ ግሬ♥️

...🖊መነሻዉ ከጅማ ከተማ ሆኖ ከንጋቱ 11:30 የተጀመረዉ ጉዞ ከቀኑ 8:00 አካባቢ መድረሻዉን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አድርጎ በሰላም ተጠናቀቀ። ከመኪናዉ እንደወረድኩ ለአክስቴ ልጅ ለእየሩስ ደወልኩላት መምጣቴ አስቀድሞ ስለተነገራት ኮንትራት ታክሲ ይዛ መስቀል አደባባይ አካባቢ እየጠበቀችኝ እንደሆነ ነገረችኝ። እኔ እንዲቸገር ባልፈልግም አቤል ግን የያዝኩትን ሻንጣ ተሸክሞ እየሩስ የቆመችበት ቦታ ድረስ አደረሰኝ። አቤልን ከእየሩስ ጋር አስተዋዉቄዉ እንዲደዉልልኝ የስልክ ቁጥሬን ከሰጠሁት በሗላ ቻዉ ብሎ መሰናበቱ ከበደኝ! በዝምታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ትኩር ብዬ ስመለከተዉ ሁኔታዬ ከእኔ አልፎ እየሩስንም ስለገረማት
<< እዚሁ የማደር ሀሳብ አለሽ እንዴ?>> አለችኝ!
ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰዉ ድንገት ከገባሁበት ዝምታ ብንን ብዬ ነቃሁ።
<<ስለ ሁለም ነገር አመሰግናለሁ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር! መልካም ቀን ይሁንልህ!>>
<<አሜን መልካም ቀን ይሁንልን!>>
አቤል ያልገባኝን ስሜት አስታቅፎኝ እኔና እየሩስን ተሰናብቶን ሄደ! ከእየሩስ ጋር በቀጥታ ሳሪስ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድን ከአቤል ጋር እንዴት እንደተዋወቅንና በአንድ ቀን የተሰማኝን ግራ የሚያጋባ ስሜት አጫወትኳት። እየሩስ የእናቴ እህት ልጅ ብቻ ሳትሆን የእድሜ እኩያ ጓደኛዬ፤የልቤን ሚስጥር ተጋሪ እህቴም ጭምር ነች።
<<አንዳንዴ ብዙ ግምት ሰጥተን ከጠበቅነዉ ነገር ይልቅ ድንገት የምናገኘዉ ደስታን ይሰጠናል>> አለችኝ!
<<እንዴት?>>
<<ልክ እንደ ፈተና ዉጤትሽና እንደ አቤል ማለት ነዋ!>>
እየሩስ የተናገረችዉ ነገር ሙሉ በሙሉ እዉነት ቢሆንም ደህና የረሳሁት ሀዘን ስለቀሰቀሰችብኝ
<<ከዚህ በሗላ ስለ ትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ማሰብ አልፈልግም የእሱን ሀዘን ሽሽት ነዉ እዚህ የመጣሁት !>>
<<እንጂ አንቺ ናፍቀሽኝ አይደለም እያልሽኝ ነዉ?>>
<<ከምልሽ በላይ ነዉ የናፈቅሽኝ የእኔ ዉድ እህት>> ብዬ እቅፍ አደረኳት።
በሰላም አዲስ አበባ መድረሴን ለማሳወቅ ወደ አባቴ ስልክ ብደዉልም ስልኩ አልሰራም አለኝ ምናልባት ኔትወርክ ይሆናል ብዬ ወደ እናቴ ደወልኩ ከተደጋጋሚ ጥሪ በሗላ ስልኳን አነሳች!
<<ሄሎ...እማ...አዲስ አበባ ደርሻለሁ...ከእየሩስ ጋር ወደ ቤት እየሄድን ነዉ!...ሄሎ..>>
<<...እሺ!...>> የእናቴ ድምፅ በለቅሶ የታጀበ ነበር!
<<እማ...ምንድነዉ...የተፈጠረ ነገር አለ?>>
<<ሄዷል!>> አለችኝ!
<<ማነዉ የሄደዉ?>>
<<አ.ባ.ት.ሽ ... ላይመለስ... ተሰናብቶን...ሄዷል!>>
ስልኬ ከእጄ ላይ ሸርተት ብሎ ወደቀ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 7 ከ50♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የደሀዋ እናት ልጅ♥️

...🖊እዉነትም ሀዘን ከእኔ ፍቅር ይዞታል! አልያም ደግሞ በእኔ ይቀናብኛል ማለት ነዉ! ትንሽ ፈገግ ስል ደስታዬን የሚያጠፋ ሳቄን የሚገድል ችግር መፍጠሩን ተያይዞታል። አባቴ <<ሰላም ሁኑ>> የሚል መልዕክት በቁራጭ ወረቀት ላይ አስፍሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን እናቴ ነገረችኝ! ያለችበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ዛሬን አድሬ ነገ እንደምመጣ ብነግራትም አሷ ግን መምጣቴን አጥብቃ ስለተቃወመች የተወሰኑ ቀናትን አዲስ አበባ ለመቆየት ወሰንኩ።
አድካሚ ህይወት...አድካሚ መንገድ...አድካሚ ቀን!... የእየሩስ ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
<<ምናልባት በስራ ምክንያት የሄደበት ጉዳይ ሊያቆየዉ ስለሚችል ሊያስጨንቃችሁ ስላልፈለገ ይሆናል መልዕክት የተወላችሁ!>>አየሩስ ነበረች!
መልስ ልሰጣት አልቻልኩም! ምን አይነት ምላሽ ልሰጣትስ እችላለሁ? በወቅቱ አልነበርኩ ሰዉ ስላልነበረበት ሁኔታ እንዴት በእርግጠኝነት መናገር ይቻለዋል?
<<ደ.ክ.ሞ.ኛ.ል! በህይወቴ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ችግሮች አድክመዉኛል!>> አልኳት! እንባዬ ያለ ከልካይ ይወርድ ስለነበር ሁኔታዬ እየሩስን አሳዘናት የተወሰነ እረፍት እንዳደርግ ከአልጋ ዉስጥ አስገብታኝ
<<አንድ ሁለት ቀናትን እዚህ እናሳልፍና ወደ ጅማ አብረን እንሄዳለን! አሁን ግን ተረጋግተሽ እረፍት ማድረግ ይኖርብሻል!>> ብላ ተሰናብታኝ ወጣች!
እኔ ቀጥ ብዬ መቆም ስፈልግ ህይወት ታንገዳግደኛለች! ይነጋል ሰዉም አብሮ ከንጋቱ ጋር ይነቃል፤ይመሻል ሰዉም አብሮ ከምሽቱ ጋር ይተኛል!... ህይወት በድግግሞሿ ዉስጥ የሰዉን ልጅ አቅፋ ትሽከረከራለች... የሰዉ ልጅም በህይወት አዙሪት ዉስጥ ይዞራል! ድካም...ለቅሶ...ሀዘን...ተደራርበዉ ለእንቅፍ አሳልፈዉ ሰጡኝ... ሽልብ አደረገኝ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል 👉60♥️ VOTE አርጉ፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

#ክፍል_

♥️አዲሱ የጎሀው♥️
#ክፍል_8

...🖊መሸትሸት ሲል ከእንቅልፌ ነቃሁ እየሩስ ከአጠገቤ ጋደም ብላለች። ስልኬ ላይ አምስት ሚስኮል አገኘሁ ሁለቱ የእናቴ ሲሆን የተቀረዉ አዲስ ቁጥር ነበር በቀጥታ ወደ እናቴ ደዉዬ ስለ አባቴ አዲስ ዜና ካለ ጠየኳት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ በሀዘን ተዉጣ ነገረችኝ እኔም እሷን ትቼ አዲስ አበባ ብዙ መቀመጥ እንደማልችል እንደዉም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ወደ ጅማ እንደምመለስ አሳምኛት ስልኩን ዘጋሁት።
<<...ምሳ እንኳን አልበላሽም አሁን ተነሺና እራት እንብላ>>
<<ይቅርብኝ አራበኝም! ...ይልቅ ነገን እዚህ አሳልፌ ከነገ ወዲያ መመለስ ይኖርብኛል አብረን እንሄዳለን?>>
እየሩስ ሀሳቤን አልተቃወመችኝም። ስልኬ ላይ ወዳገኘሁት አዲስ ቁጥር ደወልኩ አቤል ነበር ድምፁን ስስማ ልቤ ድንግጥ አለ! ልክ እንደተማረከ ወታደር ለምን የልቤን እንደምናዘዝለት ባላዉቅም አዲስ አበባ ከደረስኩ በሗላ የገጠመኝን ሁሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኩት!
<<ከቻልሽ ነገ ላግኝሽ እኔ ጋር የረሳሽዉ እቃ አለ>> አለኝ!
ግራ ገባኝ እስከማስታዉሰዉ ድረስ እሱ ጋር የረሳሁት ምንም ነገር የለም ቢሆንም ነገ ከእየሩስ ጋር ትኬት ለመቁረጥ ወደ መስቀል አደባባይ እንደምንመጣና በዛዉ ላገኘዉ እንደምችል ነገርኩት የሚሰራበት ቦታ ቦሌ አካባቢ እንደሆነ ነግርኝ እሱ ያለበት ቦታ ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ። እየሩስ እራት እንድበላ ብታስጨንቀኝም ፍቃደኛ ልሆንላት ስላልቻልኩ እሷ ጋር ያለዉን ለእኔ እኔ ጋር ያለዉን ደግሞ ለእሷ እያጫወትኳት እንቅልፍ ወሰደን... እንደሌላዉ የሀምሌ ቀን ዝናብ ያስጨነቀዉ ሳይሆን ቀለል ያለ ብሩህ ጠዋት ነበር ከእየሩስ ጋር አርፍደን ተነሳን ጥሩ ቁርስ...የሚገርም ምሳ...ቤተሰባዊ መስተንግዶ ስለተደረገልኝ በትንሹም ቢሆን ሀዘኔን ቀለል አደረገዉ።
ወደ ጅማ የምንሄድበትን የጉዞ ትኬት አክስቴ ከምትደክሙ ብላ ሰዉ አስልካ አስቆረጠችልን። ሲኒማ ፊልም ልናይ ነዉ በሚል ሰበብ ከእየሩስ ጋር 11:30 ላይ ተያይዘን ወጣን! ለአቤል ደዉዬ እየመጣሁ እንደሆነ ስነግረዉ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ አሳወቀኝ ስደርስ እንደምደዉል ነገርኩት...
እየሩስ<<ምናልባት ብቻሽን ሊያገኝሽ አስቦ ይሆናል እኔ እዛዉ አካባቢ ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ልቆይና ስትጨርሺ አብረን እንመለሳለን አይሻልም?>> አለችኝ!
ልቤን ፍርሀት... ፍርሀት እያለዉ እሺ አልኳት...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል 9 ከ200♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
💔የባከነች_ነብስ💔

♥️አዲሱ የጎሀው ♥️

#ክፍል_

...🖊አቤል የሚሰራበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫና መጠገኛ የሆነዉን ሱቅ አስጎበኘኝ ሱቁ የታላቅ ወንድሙ እንደሆነ ነገር ግን ከጅማ ድረስ እየመጣ ለመቆጣጠር ስለማይመቸዉ እሱ በሀላፊነት እንደሚያስተዳድርለት ነገረኝ።
ሱቁ አነስ ያለ ነገር ግን በርካታና ጥራት ያላቸዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለዓይን በሚማርክ ሁኔታ ተደርድረዉበታል የሱቁን ጉብኝት እንደጨረስን እራት እንድንበላ ጠየቀኝ ብዙ ማምሸት እንደማልችልና ነገ ተጓዥ ስለሆንኩ በጊዜ ገብቼ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ አስረዳሁት
<< ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ! ተረጋግቼ ላወራሽ የምፈልገዉ ነገር ስላለ ነዉ?>>
ሰዉን ቶሎ ከሚያምኑት ወገን ባልመደብም ብቻ አቤል ምን አይነት አስማት እንዳለዉ አልገባኝም ልቃወመዉ አልቻልኩም። ከሱቁ ወጥተን እዛዉ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ ተለቅ ያለ ሆቴል ገባን! ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮ ስለነበር በተለያዩ አይነት ከለር ብልጭ ድርግም የሚሉት መብራቶች ለስለስ ብሎ ከሚንቆረቆረዉ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ጋር ተዳምረዉ ለሆቴሉ ልዩ ዉበት አጎናፅፈዉታል። እኔና አቤልን ለተመለከተን በፍቅር ረጅም ጊዜ ያሳለፉ ጥንዶች እንጂ በጣት የሚቆጠር የትዉዉቅ ቀናቶች ያለን አንመስልም። <<በእኔ ምርጫ>> ብሎ ከታዘዘዉ የበግ ጥብስ ላይ ደጋግሞ አጎረሰኝ ለሴት ልጅ ያለዉ አክብሮትና ጨዋታ አዋቂነት አቤልን ያለ ምንም ፍርሀት ግልፅ ሆኜ በነፃነት እንዳወራዉ እያደረጉኝ ነዉ! የመጠጥ ተጠቃሚ አለመሆኑን ነገር ግን ይህ ምሽት ያለ ወይን አይደምቅም ብሎ ወይን ታዘዘ! በሁለታችንም ብርጭቆ ልዩ ስሜትን በሚሰጥ እርጋታ ወይኑን ቀዳዉ
<<እንግዲህ እኔ ጋር የረሳሽዉ...>> ንግግሩን እንደጀመረ ስልኬ ጠራ እየሩስ ነበረች አቤልን ይቅርታ ጠይቄ ላናግራት ወደ መፀዳጃ ሄድኩ ከ30 ደቂቃ በሗላ እንደምጨርስ ነግሬያት ተመለስኩ
<<ለጥሩ ምሽታችንና እኔ ጋር ለረሳሽዉ ነገር ፅዋችንን እናንሳ!>> እሱ ጋር ምን ልረሳ እችላለሁ? ዉስጤ የበለጠ ለማወቅ ስለጓጓ ብርጭቆዉን አንስቼ ተጎነጨሁ አቤል ምን እንደሚያወራ ባይገባኝም የሆነ ነገር ያወራልኛል ምስሎች ብዥዥ...ብዥዥ... እያሉብኝና የእንቅልፍ ስሜት ሲጫጫነኝ ይታወቀኛል
...ጠዋት እራሴን ከማላዉቀዉ ክፍል አልጋ ዉስጥ አገኘሁት ፊት ለፊቴ ካለዉ ወንበር ላይ አቤል ሲጋራ እያጨሰ ነበር መንቃቴን ሲመለከት ከት ብሎ ሳቀብኝ
<<ወፏ ወደ ወጥመዷ ገብታለች!>> አለኝ የማየዉ የምሰማዉ ህልም እንጂ እዉነት አልመስልሽ አለኝ
<<የት ነኝ?>> አልኩት
<<ሲኦል>>...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️ VOTE አርጉ፡፡ክፍል10 ከ100♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡
2024/06/29 02:59:12
Back to Top
HTML Embed Code: