Telegram Web Link
​​​
ፈ ተ ና🌺
:¨·...............:¨·.

♥️ ክፍል 6

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺


ልኡሌንና እናቱን ትቻቸው ስሮጥ ለሚያየኝ ሰው እብድ እመስል ነበር ልኡልም ተከትሎ እጄን ያዘኝ እንባዬ ይጎርፋል እሱም በጣም ደንግጦ ይቅርታ አጥፍቻለውኮ ግን እባክሽ ይቅርታ አርጊልኝ አለ እኔም እንባዬን እየጠራረኩ እኔ ይቅር ብልህ ባንተ ምክንያት የተመሰቃቀለው ህይወቴ ይቅር የሚለኝ ይመስልሃል አልኩት እባክሽ እክስሻለው ደግሞ እመኚኝ የጠፋሁብሽ ላንቺ ስል ነው ብዙ ማስተካከል የነበረብኝ ነገር ነበር አለ አይደል እኔም ሁሉንም አውቄዋለሁ ዳግም ግን አትምጣብኝ የኔ ልብ ስትፈልግ የምትወጣበት ስትፈልግ ደግሞ የምትገባበት መሸታ ቤት አይደለም እንዳትከተለኝ ብዬ በጩኸት ከተናገርኩ ቡሃላ በድጋሜ ትቼው ሄድኩ
ከዛ ቀን ቡሃላ ደግሞ ፍቅር በድጋሚ ያገረሽብኝ ጀመር ስለልኡል ማሰብ ለማቆም የግድ ሌላ ወንድ መተዋወቅ ነበረብኝ እናም ስራ ቦታ አብሮኝ ካለ አንድ ወንድ ጋር ፍቅር ጀመርኩ በእውነቱ
ቆንጆና እረጋ ያለ ባህሪ አለኝ ለዛም ይመስለኛል ወንድ ልጅ ለመማረክ ግዜ አይወስድብኝም እናም ከአዲሱ ፍቅረኛዬ ሱራፌል ጋር ጥሩ ግዜን ማሳለፍ ጀመርኩ በርግጥ ሱሬን አላፈቀርኩትም እሱ ግን በጣም ይሳሳልኝ ጀመር ሁሌም ለኔ አዲስ ነገሮችን ያዘጋጃል ሁሌም ይሸኘኛል ልኡል ደግሞ እኔን መከታተል ስራው
አርጎታል ... ከናቲ ጋርም እደመጀመርያው አንገናኝም ምክንያቱም እሱ የሚሰራው ከአዲስ አበባ ውጪ በመሆኑ ነው...
አንድ ቀን ልደቴ ነበር እናም ሱሬ ሰርፕራይዝ አርጎኝ በጣም ደስተኛ ነበርኩ ሱሬ ከብዙ ነገሩ ውስጥ ለኔ ያለው ክብር
የእውነት ይገዛኛል እናም ዛሬ ለመጀመርያ ግዜ ሱሬን ከንፈሩን ሳምኩት ይሄኔ ሉሌ ባይኑ በብረቱ ተመለከተኝ ተመልክቶም ዝም አላለም ከሱሬ ጋር የቆምንበት ቦታ ጋር ከጓደኞቹ ጋር መጣ ከዛ ጓደኞቹ ሱሬን እናናግርህ አሉት ልቤ በፍርሃት ራደ ምንድን ነው ብዬ ዞር ስል ለኔ ሲል የተወውንና እናቱን ያስደሰተበትን ሲጋራ
ለኩሶ ሲምገው አየሁት የምሬን ፈራሁት ከዛም ሱሬን እጁን ይዤ ታክሲ የሚይዝበት ቦታጋ ወሰድኩት ግራ እንደተጋባ ያስታውቃል ይሄኔ ልኡል ሰምተሃላ ድጋሚ ካጠገቧ ባይህ እገልሃለው አለው እኔም እልህና ንዴት መላ ሰውነቴን ተቆጣጥሮት ሱሬ እስኪሄድ ዝም ካልኩ ቡሃላ...
ቆይ ምንድን ነህ ህይወቴን ለመመሰቃቀል የተፈጠርከው ምን
አረኩህ ብዬ ጮህኩ ይሄኔ እንደ ህፃን እምባው እየረገፈ አንቺስ እንደመልአክ ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ካስተካከልሽኝ በኋላ እንደ ሴጣን መልሰሽ የከዳሽኝ አለ እኔም ንዴቴ ሳይበርድ በኔ አታሳብ
ሲጀመር የልጅ አባት መሆንህን አትርሳ ደግሞ ልንገርህ አላፈቅርህም አርፈህ ልጅህን አሳድግ አትድረስብኝ አልኩት ይሄኔ የምን ልጅ ነው የምታወሪው እኔ አፈቅርሻለው ካንቺ ውጪ ሴት ልጅ በፍቅር ቀርቤ አላውቅም ሙሉ በሙሉ ማጨስና አጉል ሱስ የተውኩት አንቺን ሳገኝ ላንቺ ነበር አለ ውሸታም ጭራሽ ከዛች ሴት መውለድህን ካድክ አልኩት የቷ አለ ለማስታወስ በሚመስል መልኩ ፊቱን ጭፍግግ አርጎ ይበልጥ አናደደኝ........



ክፍል 7 ከ20 Share በሀላ ይለቀቃል



━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
•●◉ @Juliiian
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​ፈ ተ ና🌺
:¨·...............:¨·.

♥️ ክፍል 7

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ነገ የመጨረሻው ክፍል ይለቀቃል።


እኔና ሉሌ እረጅም ሰአት ተጨቃጨቅን ከዛ የዛን ቀን ስለመሸብኝ ትቼው ሄድኩ በሁለተኛው ቀን ስራ ልገባ ታክሲ ስጠብቅ ልኡል መጣ ይሄኔ ከልኡል አርግዣለው ስላለችኝ ልጅ ነገርኩት
በመጀመርያ አላመነኝም ነበር ከዛ ግን የተፈጠረውን በሙሉ ነገርኩት የእውነቱን ተናዶ ፊቱ ተለዋወጠ ቀይ ፊቱ ሚጥሚጣ
መሰለ እገላታለው አለኝና በቆምኩበት ትቶኝ ሄደ ... ግራ ስለገባኝ ምንም አልመለስኩለትም ... ቀጥታ ወደስራዬ ሄድኩ ... ቀኑን ሙሉ ስለልኡል ሳስብ ዋልኩ ለምን እንደዛ ሆነ ምናልባት
ልጅቷ ዋሽታኝ ይሆን? ግን ለምን ብላ ደግሞም አብረው አይቻቸዋለው ... ብቻ ከራሴ ጋር ስሟገት ዋልኩ በጭንቀት
እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ በርግጥ ከበፊቱ አሁን ደና ነኝ ማለትም ማምሸትና ባመሸሁበት ማደር ትቻለው እድሜ ለሱሬ ከኔ ምንም ምላሽ ሳይጠብቅ ከልቡ ይወደኛል ይንከባከበኛል ... ያ ደግሞ
እኔን ከመጥፎ ጎዳና መልሶኛል እማዬም እፎይ ብላ በኔ ደስተኛ ሁናለች ስለዚህ ምንም ሆነ ምን ዳግም ልኡልን አልቀርብም ሲቀጥል ደግሞ ምንምኳ መጠጥ ጭንቀቴን ቢያስረሳኝም
አልጠጣም ... ይህ በንዲህ እንዳለ ማታ ላይ ከስራ ስወጣ ብቻዬን ነበርኩ ሱሬ
ስራ አመሻለው ስላለኝ ብቻዬን ወደቤት መሄድ ጀመርኩ ይሄኔ ልኡል ሁሌም እንደሚያረገው ውጪ ይጠብቀኝ ነበር ዛሬ ግን ለየት የሚያረገው ሉሌ ከልጁ እናት ጋር ነው ሳያቸው ሊነግሩኝ
የሚፈልጉት ነገር እንዳለ ገባኝ ከዛም ወደኔ ሲመጡ ቆሜ ጠበኳቸው ልጅቷ ታለቅሳለች ለምን እንደምታለቅስ ባይገባኝም ዝም ብዬ መከታተል ጀመርኩ በይ ንገሪያታ አላት ለመስማት ብዙም አልጓጓው ይሄኔ አንዱ የልኡል ጓደኛ መጣ ሁላችንንም ሰላም ካለን ቡሃላ ቅድስቴ እሷ ህይወት ትባላለች የልጄ እናት ነች
አለኝ ... ከት ብዬ ሳኩና የተሻለ ድራማ የላቹም አልኩት ... 3ቱም በየተራ እኔን ለማሳመን ማውራት ጀመሩ ማንንም
አልሰማም በቃ የኔና ያንተ ግንኙነት አብቅቷል ብዬ ትቻቸው ሄድኩ..
ይሄኔ ልጅቷ ሮጥ ብላ ያዘችኝና እባክሽ ይቅርታ አርጊልኝ እናም ልኡል ያፈቅርሻል ፍቅራቹን ቀጥሉ አለች በጣም ስለተናደድኩ በጥፊ መታኋትና ያኔ ምን ብለሽኝ ነበር አንቺ ምን አይነት ሰው ነሽ
ሁለተኛ ብትደርሺብኝ እገልሻለሁ ብያት ጥያት ሄድኩ........

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
•●◉Join us @Campus_love stories
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
ፈ ተ ና🌺
:¨·...............:¨·.

♥️ የመጨረሻው ክፍል


ልኡልን ከዛ ቡሃላ ለረጅም ግዜ ሳላገኘው ቆየው በመሃል አክስቴ ደቡብ አፍሪካ ወስዳኝ እዛ ለአንድ አመት ቆየሁ ይሄኔ ነበር በደምብ የተራራቅነው ከሱራፌል ጋርም እንደመጀመርያው መሆን አልቻልንም በስልክ ብቻ ሲሆን ግንኙነታችን ፍቅር ቀዘቀዘ እኔ ችላ
ስለው እሱም እኔን ለመርሳት ሌላ ሴት መተዋወቅ ጀመረ ... ከአንድ አመት ቡሃላ ወደ ሀገሬ ስመለስ የመጀመርያው ባህሪዬ ጠፋ አዲስ ሰው ሆንኩኝ ወንድ ልጅን በፍቅር መቅረብ አቆምኩ ሱሬም እንዳዲስ ሲያገኘኝ ፍቅር አገርሽቶበት ኖሮ አንዳዲስ እንጀምር የሚል ሀሳብ አቀረበልኝ እኔ ግን ከልኡል ቡሃላ ወንድ
ልጅን ማመን ከበደኝ ማፍቀር ፈራሁ እናም እራሴን ከዚ አግልዬ ህልሜን ማሳካትና ስራዬን ባግባቡ እየሰራሁ መኖር ጀምሬአለው እናም ሱሬን የራሱን ህይወት እንዲጀምር ነገርኩት...በዚ ሁሉ
መሀል ግን ልኡል ያለበትን ፈፅሞ አላውቅም አጋጣሚ እንኳ አይቼው አላውቅም ... በርግጥ ሉሌ ልጁ የሱ አለመሆኑን አረጋግጫለው ግን የይቅርታ ልብ አጣሁ ያኔ ስለተጎዳሁ ልኡልን
ደግሜ በፍቅር ማሰብ አቃተኝ... ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ከስራ ወጥቼ ወደ ቤት ለመግባት ብቻዬን ወክ አደርጋለሁ ሰአቱ ጨለምለም ብሏል እኔም የጆሮ ማዳመጫዬን በጆሮዬ ሰክቼ ማንንም ላለመስማት ይመስል ድምፁን ከፍ አድርጌ የታምራት ደስታን "ከዚያ ሰፈር " የሚለውን ዜማ አዳምጣለሁ
ምን ሊያምርብኝ ብዬ ሳትኖሪ ከጎኔ
ደሞስ ምን ሊጠቅመኝ ያንን ሰፈር አየዋለሁ ባይኔ
.
.
ይቅር ይቅር እንኳን ሌላው አንቺ ቀርተሻል"
.
እያለ በሚያምር ድምፁ በሚያምር ዜማ ያዜማል እሱ ዘፈን ሁሌም ትዝታዬን ይቀሰቅስብኛል ከልኡል ጋር ያለፍናቸውን ግዚያቶች ያስታውሰኛል በዚ መሃል አንድ ሰው ከኋላ ጎንተል አረገኝ ወንዶች ያው በተለምዶ ለከፋ ደስ ስለሚላቸው አንዱ ወንድ ነክቶኝ ይሆናል በሚል በንዴት ምን ላርግህ አይነት አስተያየት ዞር ብዬ ሳይ ልኡል ነው አይኔን አላመንኩም ግን እውነትም ሉሌ ነበር ምን እንደማወራ ግራ ገባኝ በጣም ተጎሳቁሏል አሳዘነኝ በኔ ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈ ይባስ ብሎም እኔን ለመርሳት በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሲወጣ ሊቢያ ላይ ተይዘው እንደተመለሰ ነገረኝ ለነ ብሎ ያደረጋቸውን የሳለፋቸውን ፈተናዎች ከእግሬ ስር ተደፍቶ ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎኝ ሲለምነኝ በጣም ነበር ያዛዘነኝ ግን ይቅርታ ለማድረግ አልቻልኩም እሱን እንደ ጥፋተኛ አድርጌው እሱ ግን ምንም ነገር ብለው ከእግሬ ስር ተንበርክኮ አውነትሽን ነው አሁን ያለፈው አልፎል ከአሁን በኀላ ግን አዲስ ህይወት መጀመር አለብን እስካሁን ላደረኩብሽ በደል እክስሻለው እያለ እያለቀሰ መቀባጠር ጀመረ ከእግሬ ስር እንዲነሳ አደረኩትና አንተ ምን ስለሆንክ ነው በህይወቴውስጥ እየገባ የምታስቸግረኝ ብዬው አንድ ነገር ነገርኩት እኔ አንተን ብዬ እስካልመጣው ድረስ አትምጣብኝ ብዬው ጉንጩን ሳም አደረኩትና ጥዬም እሮጥኩ.... ከዛም ለሊቱን በሙሉ ስለሱ ሳስብ ስላደርኩኝ መሰለኝ ከነጋ በኀላ ስላሳዘነኝ ብቻ መገናኘት ጀመርን እሱ አሁንም ከኔጋር በፍቅር ቢቀጥል ይመርጣል እናም እሺ ብለሽኝ ፍቅር ከሰጠሽኝ ወደ ጥሩ መንገድ መጓዝ እጀምራለው እንደቀድሞ ተው ያልሽኝን እተዋለሁ አለኝ እኔ ግን አሁንም ልኡልን በፍቅር መቅረብ አልፈልግም ያሳዝነኛል
ካለበት ሁኔታ ባወጣው ደስ ይለኛል ግን ደግሞ እሱ በፍቅር እንድንቀጥል ብቻ ነው የሚፈልገው እኔ ግን አልቻልኩም
ሱራፌልንም ባላፈቅረውም ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ይሄው
መሀል ላይ ቀርቼ የማን እንደምሆን ግራ መጋባት ጀመርኩ እናም እኔ ልዑሌን በጣም ነው የምወደው ግን እሱን አምኖ ለመቀበል ከብዶኛል ሱሬ ደስ የሚልና አዛዛኝ ሰው ነው ግን እሱ ይወደኛል እኔ እኔም እወደዋለው ግን ለማን መሆን እዳለብኝ እየለፈፈፍኩኝ ከቤቴ ወጣው ወዴት እንደምሄድ ግን አላውቅም ግን እግሬ ወዳመራኝ መንገድ ብዙ ጎዳናዎች ከተጓዝኩ በኀላ እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ወደኩ ግን ግን የሚያነሳኝ ሰው ጠፋ ምክንያቱም ከቤት ስወጣ የረባ ልብስ እና ጫማ ስላላደረኩኝ የጎዳና ተዳዳሪዎች አድርጎ ስላሰቡኝ ምሽት አካባቢ ሲሆን ከወየኩበት ነቃውኝ ነገር ግን ያለወበት የት እንደሆነ ስላላወኩኝ አገር ምድሩ ነበር የዞረብኝ በጣም እርቦኝ ስለነበር ምግብ ፍለጋ ወደ ጥጋጥግ ፍርፋሪ መፈለግ ጀመርኩ ግን ላገኝ አልቻልኩም ወደፊት ብዙ እርምጃዎችን እንደተራመድኩኝ በጥግ በኩል በፌስታል የተከለለ ቤት ውስጥ ስገባ ሰው የሌለውም ስለሆነ በፌስታል የተቆጣጠሩትን ነገሮችን አንድ በአንድ እየፈታው ሳይ የሚበላ ምግብ ግን ላገኝ አልቻልኩም ከትንሽ ደቂቃ በኀላ ኮቴ ሰማውኝ በድንጋጤ ዘልዬ ስወጣ ውስጥ ይኖር የነበረው ሰውዬ እጄን አድርጎ አትፍሪ ብሎን የሚበላ ሰቶኝ ውስጥ ገብቼ እንድተኛ ነግሮኝ ጥሎኝ ሄደ በንጋታው ከዛ ውስጥ ወጥቼ ብር ምናምን ለምኜ ባገኘውት ብር ወደ ማለውቀው ቦታ ተሠድጄ መኖር ጀመርኩ.........


꧁༺༒༻꧂


ውድ♥️ አምባብያን ታሪኩ በዚ ያበቃል ሁላችሁም እናንተ ብትሆኑ ምን እንደምታደርጉ ሀሳብና አስተያየታችሁን @Juliiian ብትሰጡኝ ስል በቻናሌ ስም ባክብሮት እጠይቃለሁ🙏🙏🌺🌺
የባል ገበያ
(ክፍል አንድ)

እንዴት ተጣበሳችሁ?” ብላ ዛሬም አፋጠጠችኝ። ምን ቀን አቅለብልቦኝ ቋንቋውን የምማረው ለቪዛ መሆኑን እንደነገርኳት እንጃ……

“እስቲ መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝ።” ጥያቄዋን ሽሽት እንጂ የሷን የጠበሳ ታሪክ የመስማት ጉጉት ኖሮኝ አልነበረም። እንኳን ተጠይቃ እንዲሁም ምላሷ ሞት አያውቅም።

“እኔማ ዴቲንግ ሳይት ላይ ነው የጠበስኩት። …… እኛ ክላስ ከሰላምና ከኤልሳ በስተቀር ሁሉም በ ‘balshemeta.com‘ ዴቲንግ ሳይት ነው የጠበሱት። …” አፀደ ስታወራ መወራጨቷ እና ቅብጥብጥነቷ ልትበር የምታኮበኩብ ያስመስላታል። …… ያንጨፈረረችው ፀጉሯ ሳይቀር እየፈጠነች ከከንፈሯ ከምታግተለትላቸው ቃላት ጋር ብን ትን ይላል። ቢሆንም ወሬዋ ጆሮና ቀልቤን ጠለፈው…… በዴቲንግ ሳይት የውጪ ሀገር ሰው መጥበስና ወደውጪ ሀገር ለመውጣት መታተር የኔ ብቻ ታሪክ ነበር የመሰለኝ።

“እና ሁላችሁም ቋንቋውን የምትማሩት አግብታችሁ ከሃገር ለመውጣት ነው?”

“አወና! አንቺም እንደዛው አይደል?”

“እ…ሱ…ማ ነው! በተመሳሳይ መንገድ ለተመሳሳይ ዓላማ አንድ ክፍል መገኘታችን ገርሞኝ ነው።” አልኳት

አንባቢ እህቴ ሆይ የምፅፍልሽ ዶሮ ፣ ሽንኩርት ፣ ቄጤማ፣ መከለሻ…… ስለሚሸመትበት የበዓል ገበያ አይደለም። በቆዳ ቀለም፣ በእድሜ፣ በዜግነት፣ በኑሮ ደረጃ ፣ በቁመት፣ በውፍረት……… ብቻ ባሻሽ መስፈርት ባል የሚሆን ወንድ ስለሚሸመትበት የገበያ ማዕከል እንጂ…… ለመገበያየት የሚያስፈልግሽ አውድማው ላይ ዘው ብሎ መዝለቅ ብቻ ነው።… …
balshemeta.com dating site ‘ ይሰኛል መደብሩ። (ሄዋኔ ይሄን ፅሁፍ አንብበሽ ስትጨርሺ የጎልጉል ፍለጋ ሳጥን ውስጥ ‘ፈልግ‘ን እንደምትጠነቁዪ በመጠርጠር በዚህ ተረክ ውስጥ የተጠቀሰው የሳይቱ ስም ተቀይሯል። …… ሃሃሃሃ)

የዳሌ ቁጥርሽ ሳይቀር ስለራስሽ የጠለቀ ጥያቄ እና የመልስ ሳጥን ይከታተልልሻል። … … ይሄ ብቻ በቂ አይሆንም። ባልሽ እንዲሆን የምትፈልጊውን ሰው ገላው ላይ ያለ የማሪያም ስሞሽ ጭምር በመጥቀስ መስፈርትሽን ታኖሪያለሽ። …… አክለሽ አምስት ቄንጠኛ ፎቶግራፎችን ትለጥፊያለሽ። (በእርግጥ የፎቶው ቄንጥ ግዴታ አይደለም።) አከተመ። ገበያው ውስጥ መሰስ ብለሽ ገብተሻል። …… በተለያየ የዓለማችን ክፍል ካሉ ወንዶች(አብዛኛዎቹ አዛውንቶች እና ለአዛውንትነት የቀረቡ ናቸው) መልዕክቶች ይደርሱሻል። …… የመረጥሽውን ታናግሪያለሽ።

በተመሳሳይ መንገድ አንድ አሜሪካዊ አግብታ የሄደች ወዳጄ (እንደመታደል ሆኖ እኩያዋን ነው ያገኘችው።) በጠቆመችኝ መሰረት በአንድ ያበደ ቀን ሸመታው መሃል ዘመትኩ። …… ከእብድ እስከ ስድ፣ ከአይንአፋር እስከ አደንቁር፣ ከአዋቂ እስከ ልብ አውላቂ፣ ከአስተዋይ እስከ ደም–አፍይ… …… ሳምንታት ከፈጀ አሰልቺ የንግግር ልውውጦሽ በኋላ ከሁለት ሰወች ጋር በቋሚነት ተግባብቼ ማውራት ስለቻልኩ ከሳይቱ ወጥቼ በቫይበር እና በፌስ ቡክ ማውራት ጀመርኩ። አንደኛው ፎቶግራፍ ካለመለጠፉም በላይ እንዳየውም ሆነ እንዲያየኝ ፍላጎት የለውም። የሚፅፍልኝ ቁምነገር ግን ችላ እንድለው አላደረገኝም።

አንደኛው ፈረንሳዊ ጎልማሳ ነው። ከእርሱ ጋር በስካይፒ አወራን። መወሰን ስለነበረብኝ መረጥኩ።…… ከወራት በኋላ ልቀበለው ቦሌ አየር ማረፊያ ተገኘሁ። ……

በአካል የማያውቁትን ሰው ፍቅረኛዬ ብሎ አስቦ ለመቀበል መሄድ የሆነ የማያውቁት ሰው ቀብር ላይ ተገኝቶ ከሬሳው ቀድሜ ጉድጓድ ውስጥ ካልተነጠፍኩ ብሎ ለያዥ ለገናዥ እንደማስቸገር ያለ የቂልነት ዓይነት ስሜት ነበር የፈጠረብኝ። …… ሳየው ምንድነው የማደርገው? አቅፈዋለሁ? እስመዋለሁ? ኸረ ከነጭራሹ በአካል ሳየው ባላውቀውስ? …… በአካል ስንገናኝ ቢያስጠላኝስ? …… እሱስ ካገኘኝ በኋላ ባስጠላው? እኔን ለማግኘት አህጉር ማቋረጡ ቢፀፅተውስ? ………

ክብ ፊቱንና አፍንጫና አይኑን ያጣበበ ሰፊ ጉንጩን እንዳየሁ አወቅኩት። …… ሳይደናገር ሻንጣውን እየገፋ በፈገግታ ወደኔ አቅጣጫ ቀረበ። ሲስቅ ጉንጩ ይንጠለጠልና ሊወድቅ እየመሰለኝ ልደግፍለት መዳፌን ማቅረብ እየቃጣኝ ከብዙ የመተቃቀፍ ሰላምታ በኋላ ሆቴል ደረስን። …… በእርግጥ ከጠበቅኩት ክብደት በላይ አንድ ጎረምሳ ያህል ጨምሮብኛል።(ወደ 30 ኪሎ የሚሆን)

ከፊት ለፊቱ ሲታይ ጥቅጥቅ ብሎ ሙሉ የሚመስለው ፀጉሩ የመሃል አናቱ አመላለጥ የሚቀመጠው በቂጡ ሳይሆን በአናቱ አስመስሎታል።……

አብረን በነበርንባቸው ሳምንታት ለመላመድ ጊዜ አልፈጀብንም። ቁጥብ፣ ስነስርዓታም እና ፈገግታም ነው። ሳቄ ሊያመልጠኝ እየታገለኝ ልለምደው ያልቻልኩት የአልጋ ላይ ባህሪውን ነበር። … …… ጉዳዩን እየከወነ እንደላንቲካ ተኮሳትሮ ሲያፈጥብኝ ከፀበኛው ጋር መንገድ ላይ ድንገት የተፋጠጠ እንጂ ፍቅር እየሰራን አይመስልም። በየመሃሉ የመሳደብ አይነት ምላሱን ብቅ ጥልቅ የማድረግ ልምዱ ሳቄን ያታግለኛል። …… ወደ ሀገሩ ሊመለስ በረራው ሰዓታት ሲቀሩት እንደተለመደው በምላሱ ‘እየተሳደበ‘ ሲተጋ … የጠጣሁት ወይን ተደምሮ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ። ……… ይሄኔ ተበሳጨ። …… ብስጭት ግን በእንግሊዘኛ አይመስጥም። …… ‘ኤጭ‘ ሳይባል ብስጭት ምኑን ብስጭት ሆነ? ‘ኤድያ‘ ካልገባበት ምኑን ተበሳጨ?

ትጋቱን አቁሞ ታሪክ ይሉት ትንግርት አወጋኝ። …… ከአመታት በፊት በአደጋ የዘር ፍሬውን ላጣ ጓደኛው የቀኝ ፍሬውን መለገሱን እና ከዚያ ወዲህ ለመርካት እንደሚቸገር የነገረኝን ቀልድ ነው ብዬ እንዳላልፍ እንባ ካዡ አይኖቹ የምሩን መሆኑን ተረድቻለሁ።…… የሰማሁትን እርግጠኛ መሆኔን በመጠራጠሬ ነክቼ ‘ይሄንን ነው የለገስከው?‘ ማለት ሊቃጣኝ ስዳዳ… … ገበያ እንደቀረበ ቲማቲም ፍሬዎቹን ለቀም አድርጎ ሰብስቦ

“አየሽ አንዱ ፍሬ የለም። እንቺ ነክተሽ አረጋግጪ! ” አለኝ። ‘ንኪ‘ ያለኝ የሎሚ ፍሬ ይመስል ቀለል አድርጎ

“አንዳች መዓት ይንካህ!” አልኩኝ በሆዴ እየዘገነነኝ…… ለአራት ሳምንታት አብሬው የነበርኩት ሰው ሳይሆን የሆነ የሚሸክክ ፍጡር ሆነብኝ። …… ምኑ እንደዘገነነኝ አላውቅም። ፍሬ— አልባ መሆኑ? አሁንም አሁንም አፍንጫውን እየሞዠቀ ቆለጡን እየነካካ ማለቃቀሱ? ብቻ የሰውነቴ ቆዳ ሽፍ እስኪል ሸከከኝ…… ጥዬው ብሄድ ደስ ባለኝ።

👉🏽👉🏽👉🏽አልጨረስንም👈🏽👈🏽👈🏽
★★የባል ገበያ ★★
(ክፍል ሁለት)

ጥዬው ብሄድ ደስ ባለኝ። …… እንደምንም ለሁለት ሰዓታት ታግሼ አየር ማረፊያ ድረስ ሸኘሁት። …… እቅዳችን የነበረው ከወር በኋላ ተመልሶ መጥቶ ልንጋባ ነበር።…… ፊቴን ሳዞር የመጀመሪያ ስራዬ ሊያገኘኝ የሚችልበትን መንገዶች በሙሉ መዝጋት ነበር። ………
……
……
"አዚቲ እኮ ቪዛዋ ተሰጣት።" አለች አፀደ እንደ ልምዷ እየተቅለበለበች። ክላስ ውስጥ ያለው ሴት በሙሉ በቄንጥ ተንጫጫ

"ምን ያደርጋል ግን……" ቀጠለች ሴቱ ለ ‘ኦ ማይ ጋድ‘ ቄንጥ የሰቀለውን እጁን ከአየር ላይ ሳያወርድ

በአንድ የአውሮፓ ቋንቋ ትምህርት ቤት ውስጥ ቋንቋ ለመማር ነው የተሰበሰብነው። …… በሚገርም ሁኔታ ከአንድ ወንድ በቀር ሁላችንም ሴቶች መሆናችን ሲገርመኝ። ሁላችንም ለቪዛ ከትምህርት ቤቱ የቋንቋ ብቃት ሰርተፊኬት ስለሚያስፈልግ የምንማር ነን። ከዚህ በላይ የደነቀኝ ግን ከሁለት ሴቶች በቀር ሁላችንም በተመሳሳይ የሳይበር ጠበሳ ትዳር መስርተን በጋብቻ አመሃኝተን ከሀገር ለመውጣት የሚጠበቅብንን እያሟላን መሆናችን ነው።

አዚቲ (ቪዛዋ የተፈቀደላት) ከወራት በፊት ነበር ያገባችው። ጓደኞቿ ሲያላግጡባት
‘ባሏ ከመምጣቱ ሳምንት በፊት አስቀድሞ ከዘራውን ነው የላከው። ከዘራውን ይዛ ሄዳ ነው ቦሌ የተቀበለችው‘ ይሏታል። እሷ በራሷ የምትፎግር ፍሪክ ናት። ትስቃለች።
ያገባችው ሰው ከተጋቡ ጀምሮ ቪዛው እስኪፈቀድ ሀገሩን ትቶ ገስትሀውስ ተከራይተው አብሯት እየኖረ ነበረ።

አዚቲ እንኳን በደሞዝ በእቁብ የማትቻል ወመኔ ሱሰኛ ናት። …… ሰውየውን በስተርጅና ቃሚና ቀምቃሚ አደረገችው። …… እንደአፀደ ገለፃ ቪዛው መፈቀዱን በሰማ እለት በከፍተኛ ምርቃና ውስጥ ሆኖ አንድ ነገር ተከሰተለት። …… ኢትዮጲያን ወዷታል። …… አዚቲን የመሄዱን ሀሳብ ትተው እዚሁ እንዲኖሩ ቢያማክራት ‘ነብር አየኝ በል‘ አለች።(በእርግጥ በእንግሊዘኛ እንዴት እንዳለችው እንጃ!) በመጨረሻ ሰውየው ውሳኔውን አስተላለፈ።

"ከፈለግሽ አንቺ መሄድ ትችያለሽ! እኔ ከዝች ሀገር እግሬ ንቅንቅ አይልም!"
አፀደ ወሬውን ከአፏ ቀምቶ ሌላ ሰው የሚያወራባት ይመስል እየተሽቀዳደመች አውርታ ስትጨርስ ፍርፍር ብዬ መሳቅ አምሮኝ ነበር። ከሀብቴ(የክፍላችን ብቸኛ ወንድ) በቀር ሁሉም የለቅሶ ቤት ፍራሽ ላይ የተቀመጡ ያህል ተክዘው ሳይ ሳቄን ዋጥኩት። ……
……
……
ባለአንድ ፍሬውን ተጣማሪዬን ከተለየሁ በኋላ ለቪዛ እየተማርኩ የመገኘቴ ኋሊት እንዲህ ነው። ……
ሸኝቼው ስመለስ የምቀጥለው ኑሮ እንዳልነበረኝ ገባኝ። የሆነ መንገድ ላይ መኖሬን ቀጥ አድርጌዋለሁ…… የሆነ ሩቅ መንገድ ላይ…… መኖር ወደውጪሃገር መሄድ ሆኗል። …… እዛች ቦታ ላይ ኢትዮጲያ ውስጥ መኖር አቁሚያለሁ። …… መኖር ከሃገር ለመውጣት መሰናዳት ሆኗል። …… …… ይሄን አቁሜ እዛጋ የሰበርኩትን ድልድይ ገጥሜ መኖር እንደማልችል የገባኝ…… ፈረንጅ መጥበሴን እናቴ በሰማች ማግስት ስልክ ደውላ

"እልልልል ልጄ ከሰው እኩል ልታደርጊኝ ነው?" ስትለኝ

"ፈረንጅ ካገባሽ ሳይክል ትገዢልኛለሽኣ?" ታናሽ ወንድሜ በለሊት ቀስቅሶኝ ሲጠይቀኝ

"አሰይ ልጄ የአባትሽን መቃብር አሳድሽለት!" ስትለኝ አክስቴ

"መድሃኒያለም ሳልሞት ያንቺን ዓለም ሊያሳየኝ ነው።… …እንደው ልጄ የምትታለብ ላሜ ሞታብኛለች ደህና ላም አይተሽ ግዢልኝ። እመርቅሻለሁ።" ስትል አያቴ
ይሄኔ ለራሴ ወሰንኩ። በየትም መንገድ ከሀገር እወጣለሁ። …… ከውሳኔዬ እኩል መፃፃፍ አቁሜ ከነበረው አንደኛው ሰውጋ መፃፃፌን ቀጠልኩ። ……
መልኩ ምን እንደሚመስል አላውቅም።የውጪ ዜጋ ከመሆኑ ውጪ ስለራሱ የነገረኝ ነገር የለም። ሲያወራኝ (በፅሁፍ) ግን የማውቀው… … የሚያውቀኝ…… ረዥም ጊዜ አብረን የሆንን አይነት ነው የሚሰማኝ። …… ሰው የማያውቀውን ሰው ይለምዳል? ለመድኩት። …… የእውነት ያለ ሰው መሆኑን እንኳን ማረጋገጥ የማልችለውን ሰው አመንኩት። …… ጣቶቼ ከስልኬ ላይ ሳይነሱ ይመሻል። ……… ስለብዙ ነገር በማውራታችን የተዋወቅን መሰለ። …… ሰው ይሁን ማሽን፣ ሴት ይሁን ወንድ፣ እብድ ይሁን ጤነኛ… … የማላውቀው ሰው ትንፋሽ ይሞቀኛል። በህልሜ ሁሉ አየዋለሁ። …… ጠዋት ያየሁትን ፊት ለማስታወስ ብሞክር አይመጣልኝም። …… እበሳጫለሁ። …… ራሴ ያበድኩ ያበድኩ ይመስለኛል። ……
መጥቶ እንደሚያገባኝ ቃል ገባልኝ። …… ላላምነው ብፈልግም አመንኩት። …… ቋንቋውን እንድማር በአካውንቴ ብር አስገባልኝ። …… የማደርገው ሁሉ መጃጃል እንደሆነ እየገባኝ ተመዝግቤ መማር ጀመርኩ።……
እመጣለሁ ያለበት ቀን ስምንት ቀን ብቻ ቀርቶታል። …… መጃጃሌን አላቆምኩም። …… ስቀበለው ምን እንደምለብስ፣ የምሰጠውን አበባ፣ የቀኑን እርዝመት…… አስባለሁ። …… ባይመጣስ? እላለሁ መልሼ። ምን ስለመምሰሉ ቦታ ያለመስጠቴ ይገርመኛል። ላስብም ብሞክር ወዲያው ተወዋለሁ።
አራት ቀን……
ሶስት ቀን……
ሁለት ቀን……
አንድ ቀን……
አንድ ሰዓት ሲቀረው ቦሌ ተገኘሁ።…… ትምህርት ቤት ስለሰማኋቸው የሴቶች ገጠመኝ እያሰብኩ ‘እንዲህ ቢሆንስ?‘ ‘እንዲያ ቢሆንስ?‘ ሀሳብ እገምዳለሁ።
……
👉🏽👉🏽👉🏽አልጨረስንም👈🏽👈🏽👈🏽
ለመላው የእሥልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1ሺ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሠላም አደረሣችሁ #Eid_Mubarak


@Campus_love stories
@Juliiian
ፍቅርና እምነት
በእውነተኛ ህይወት ላይ የተመስረተ

ክፍል አንድ 1

ሁለቱን ፍቅርኛሞች ላስተዋውቃችሁ ብሌን እና ቶማስ ይባላሉ
ብሌን ለቤተስቦቿ የሁለተኛ ልጅ ነች ቶማስ ደግሞ ለቤተስቦቹ
የመጀመርያም የመጨርሻም ልጅ ነው ።
ብሌን ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ሳር ቤት አካባቢ ነው
ለቤተስቦቿ የሁለተኛ ልጅ እንደመሆኗ ብዙም የቤተስብ ክትትክና
ቁጥጥር አይጠነክርባትም ቤተስቦቿ በኑሮ ደርጃቸው ድሀም
ሀብታምም አይደሉም ግን ለስው የሚሰጡት ባይኖር ለራሳቸው
የሚሆን ነገር ጠፍቶ አያውቅም ከምንም በላይ ግን በጣም
ደስተኛ ቤተስብ ነው ታላቅ እህቷ ሳራ ትባላለች በጣም ጥሩና
ምርጥ ባህሪ ያላት ከስው ጋር ተግባብታ መኖር የምትችል አይነት
ናት .ብሌን የትምህርት ደርጃዋ ብዙም አይደል ከትምህርት ይልቅ
ወደ ጥበብ ትያትር ውዝዋዜ ትወና ታዘወትራለች ብዙ ግዜዋንም
ፍልም በማየት ውዝዋዜ በመስራት ነው የምታሳልፍው
.ቤተስቦቿም ፍላጎታን ላለመጋፍት ብለው ምንም ነገር ከማለት
ተቆጥበዋል .
ቶማስ ለቤተስቦቹ የመጅመርያም የመጨርሻም እንደመሆኑ
ቤተስቦቹም ትንሽ ሀብታም የሚባሉ ናቸው ተወልዶ ያደገው ልደታ
ክፍለ ከተማ ነው የትምህርት ደርጃው ጎበዝ ከሚባሉት ስለነበር
በድግሪ ነው የተመርቀው አሪፍ ስራም አለው .ቤተስቦቹ ብቸኛ
ልጃቸው ስለሆነ እንደ እንቁላል ነው የሚንከባከብቱ.
ብሌንና ቶማስ የተገናኙበት አጋጣም በጣም በሚገርም አጋጣሚ
ነበር ።ብሌን ወደ ጓደኛዋ ስልክ ልትደውል ፈልጋ ቁጥር አሳስታ
ደውላ ነበር የተገናኙት በስአቱ ብሌን ለወንድ ልጅ ያላት
አመለካከት በጣም የወርደ ስለነበር ብዙም ቦታ አልሰጠችውም
በዚያው ቅስበት ስልኳን ሴቨ አድርጎ በተደጋጋሚ መደወልን
ቶማስ ስራው አድርጎታል .ብሌን በስአቱ በጣም ከምትወደውና
ከምታፈቅረው ፍቅርኛዋ ተለይታ ስለነበር ፍቅርና ወንድ ለምኔ
ብላ እርግፍ አድርጋ ለመተው በወሰነችበት ሰአት ነበር ።ቶማስ
በበኩሉ ብዙ የሴት ጓደኞች ቢኖሩትም ስለ ፍቅር ግን አስቦ
አያውቅም ነበር ባልታስበ አጋጣሚ የስማው የብሌን የሳቅና
የስላምታ ድምፅ ግን እሷን ለማግኝትና ምን አይነት ሴትና ማን
እንደሆነች ለማወቅ በጣም ጉጉት ነበርው ።ብሌን በበኩላ
ከምንም አልቆጠርችውም ነበር ስልኳን ከምታነሳው ይልቅ
የማታነሳው ግዜ ይበልጥ ነበር ።
ሲደውል አንስታ ይቅርታ ጠየቅሁህ አይደል ለምን አትተወኝም
ከማለት ውጪ ምንም ነገር አትናገርም ነበር .የእንገናኝና ላይሽ
እፍልጋለው በተደጋጋሚ ጥያቄ እሷም ምን አይነት ስው እንደሆነ
ለማወቅ ጉጉት ያድርባት ጀመር .አንድ ቀን ግን በቃ እሽ እንገናኝ
ብላ ቀጠርችው ቀኑ እስኪደርስ ድረስ ቶማስም ብሌንም
ለመተያየት ጉጉት አደርባቸው በስልክ ለወራት የቆየው ግንኙነት
በአካል ለመገናኝት ስአታት ቀርተውታል.........
ይቀጥላል.....

Join us @Campus_love stories
:¨·.·¨:
ያሜናዳብ ♥️
┈┈••◉❖◉●••┈🌺

💢ክፍል1

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ

ሰላም🙏 ለናተ ይሁን ጓደኞቼ ዛሬም በሌላ ታሪክ ተመልሼ መጥቻለው በጣም ገራሚ እና አስተማሪ የሆነ የፍቅር ታሪክ ነው ሼር💌💌 ማድረግ አትርሱ

ትዙ እባላለሁ ተወልጄ ያደኩት በባህርዳር ከተማ ነው ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ገጠመኝ አለው የአንዱ ህይወት ለአንዱ አስተማሪ ነው ከእኔ ህይወት ትማራላቹ ብዬ አስባለሁ አንደ ማንም ኢትዮጲያው
በስፈር ፍቅር ነው ያደኩት ግን ከሆነ ግዜ በኋላ አሜርካ የሚባል በሽታ ታጋባብኝ በዚች ምድር ላይ እንደ እኔ አሜርካ ለመሄድ የሚፈልግ አለ ብዬ አላስብም ሲበዛ እልኸኛ ነኝ ግቢያችን በጣም ሰፊ
ነው ሚከራይ ዶርሞችም አሉን እናቴ እኔን ወደ ውጭ ለመላክ ያልቆፈረችው ጉድ ጓድ የለም ግን ምን ያደርጋል ይታደሉታል
እንጂ አይታገሉትም በዚህ መሀል ነው እንግዲህ ጆን ወደ ህይወቴ የመጣ
የመጣው እቤት ሊከራይ ነበረ በደላላ ነው የመጣው 8 የሚከራይ ቤቶች አሉን ሁሉም ፅዳቱን የጠበቀ ነው ብዙዋቸ እቤቱ ላይ ብዙ የቆዩ ናቸው ልክ እንደ ቤተሰብ ነን አምስቱ ተከራዮች ባለ ትዳር ሲሆን ሶስቱ ወንደ ላጤ ነበሩ እንዱ ግን
በስራ ምክንያት ዝውውር ወደ አ/አ
ስሄድ ነው እንግዲህ ቤቱን ለጆን ያከራየነው ከገባ ሶስት ሳምንት ሁኖታል እኔ ግን የሚገርነው አንድም ቀን አይቼው አላውቅም ጥዋት ይወጣል ማታ ይገባል እናቴ ቀንም እኮ ይመጣል ትለኛለች አክስቴ ደግሞ እንዴት እንደ ተመቸኝ አጠይቂኝ ትለኛለች እኔም በርግጥ ዙረታም ነኝ መቀመጥ የሚባል አልውድም በዚህ መሀል ነው
እንግዲህ ከገባ ወር ሞልቶት የቤት ክራይ ሊከፍል ማታ ላይ እቤቱን አንኳኳ ቡና እየጠጣን ነበረ አቤት አለች እናቴ ደህና ዋላቹ ማዘር እያለ ገባ ቀልቤ ግፍፍ ነው ያለው ሲጀመር እንደዚህ አይነት ወንድ አይቼ አላውቅም ሁሉን ሰላም ሲል እኔ ግን ፈዝዤ ሰላም አላልኩትም ይቅርታ ጥዋት ወጥቼ ማታ እየገባሁ አልገናኝ አልን እኮ ሲል እንዴ ልጄ ስራም
አይደል ቆይ ምን አዲስ ወሬ አለ ስለ ወንድምህ አለችው ያው በቀደም የነገርኩሽ ጓደኛውን ስልኩን አግቼ ዛሬ ደውዬለት ነበረ ነገ ለንገናኝ ተቀጣጥረናል አለ እኔ ግን አይኔን ከአይኑ ላይ አልነቀልኩም ቡና እየጠጣ ቀና ሲል አይን ለአይን ተጋጨን እኔ አይደለም እንደዚህ አይነት ወንድ ይቅርና የለበሰውን ልብስ እንኳ ገበያ ላይ አይቼው አላውቅም ለናቴ የቤት ኪራይ ሶቶ ብዙም ሳይቆይ ወጣ ሲሄድ ልቤ አብሮ እሱ ጋር ሄዴ ምን እንደተፈጠረ እንኳን አላቅም ማታ ምንም ሳልተኛ አደርኩ በጣም ገርሞኛል በቃ ሁሉ ነገሩ ተመችቶኛል እሱን ለማዬት ብዬ በጧት ተነሳሁ እናቴ የኔ በጧት መነሳት ሳይገርማት አልቀረም በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ብዙ ሰአት ተቀመጥኩ ግን አልወጣ አለ ወቶ ይሆን አልኩ በልቤ ሶስት ሰዓት ሲሆን ጓዴኞቼ ቤት መጡና ይዘውኝ ወጡ እነሱ ጋር ቆየሁ ግን ጆን ከውስጤ አልወጣ አለኝ እስከማዬው ቸኩያለሁ በጊዜ ወዴ ቤት መግባት አለብኝ ብዬ 10 ሰዓት ላይ ተመልስኩ እናቴ ቤት የለችም አክስቴ ናት ያለችው ስታዬኝ እሩጣ ወዴኔ መጣች ማታ ምን አባሽ ሁነሽ ነው እንዴዛ ልጁ ላይ ያፈጠጥሽበት አለችኝ እየሳቀች እኔም ሳቄ መጣብኝ ልጁ ግን እንዴት ነው ተመቸሽ አይደል አለችኝ ነገሮች ቶሎ ነው የሚገባት እንዳትፎግረኝ ብዬ ያው ብዙም አይደል አልኳት እና ለዛ ነው ጧት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለሽ ያረፈድሽው ባክሽ ገብቶኛል ብለ ሳቀችብኝ እኔም እንዴማፈር ብዬ ቀርቀር ብዬ ሳኩ ሻወር ወስጄ ቢጃማዬን ለብሼ በረንዳ ላይ አንድ መፀሀፍ ይዤ ቁጭ አልኩ ልክ 11 ሰዓት
ላይ የግቢያችን በር ሲከፈት የልቤ ምት ጨመረ ጆን ነው ገና ጫማውን ሳየው አንገቴን ዴፍቼ መፀሀፌን አየሁት መፀሀፉ ያነበኛል እንጂ አላነበውም ጆን ቀጥ ብሎ ወዴኔ መጣ .....

✎ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
ፍቅርና እምነት
ክፍል 5
ብሌን ቶማስ ወደ አለበት ቦታ ስትደርስ ከታክሲ ወርዳ እየሮጠች
ወደ ቶማስ ተጠጋች...
ቶማስ ፍቱን አዙሮ ነበር የተቀየጠው ስትደርስ ጅርባው ስጥቶ
ነበር የተቀመጠው ቶሚ ብላ ጠራችው ከመቀመጫው ቀስ ብሎ
ተነሳና ወደሷ ዞሮ ቆመ ብሌን ስሜቷን መቆጣጠር ስላቃታት
ተንደሪራ ተጠመጠመችበት በሁለቱም እጆቿ ጉንጭና ጉንጩን
ይዛ ምን ሆነህ ነው ምንህን ነው ያመመህ ብላ በጥድፊያ
ጠየቀችው .
ቶማስ በተረጋጋ አነጋገር ልቤን ነው ልቤን አላትና አንደኛውን
እጃን ከፊቱ ላይ አንስቶ እደርቱ ላይ አደርገው አየሽው እንዴት
እንደሚመታ ለወራት ሲያመኝ የከረመው ይህ ነው ይሄውልሽ ልቤ
ታሟል አላ .
ብሌን በጣም ግራ ገብቷን ታዲያ ለምን ሆስፒታል አንሄድም
ለምን አትታከምም እንሂድ እዚህ ምን እንስራለን ፍጠን ቶሚ
አለችው እያጣደፍች .
ቶማስ ቆይ አላት ብሌኔ እኔን ያመመኝን በሽታ መድሀኒቱ አንቺ
ጋር ነው ያለው ሆስፒታል ብሄድ መድሀኒት የለውም እስኪ አይኔን
እይው ምን ይታይሻል አላት ,ብሌን ደንግጣ አይን አይኑን
እያየችው ለምን በግልፅ አትነግርኝም አስጨነቅኽኝ እኮ
ምንድነው የሆንከው ቶሚ አለችው።
ቶማስ ብሌኔ ለወራት አብሬሽ ባሳለፍኳቸው ግዜ ደስተኛ ነኝ ነገር
ግን የልቤን ለመግለፅ ደፍሬ አላውቅም ምናልባት የልቤን
ብነግራት የባስ ትርቀኛለች ብዬ አስቤ ዝም ብያለው አሁን ግን
አልቻልኩም ብሌኔ """ አፍቅርሻለው"" አላት አይን አይኖን እያየ
ብሌን የስማችውን ማመን ስላቃታት ሳታስበው እንባው ይፍስ ነበር
.በሁለቱም እጆቹ ከአይኗ የሚፍስውን እንባ ይጠርግላት ጀመር .
ብሌን ምንም እንኳን ለወንድ ልጅ ያላት አመለካከት የወርደ
ቢሆንም ቶማስን ካወቀችው ቀን ጅምሮ ግን ለሱ የተለየ ስሜት
ነበራት ፍቅርም እንደመያዝ እያለ የገዛ ስሜቷ ይፍታተናት ነበር
.ብሌን ሳታስበው ቶማስን ተንደርድራ እቅፍ አድርጋው እንባዋን
ዘርገፍችው"" አፍቅርሀለው ቶሚ ግን ግን ግን አደራ
እንዳትጎዳኝ እሽ"አለችው አልጎዳሽም አልጎዳሽም አላት ።
ቶማስ የብሌንን የእሽታ ቃል ስለስማ ደስታው ወደር የለውም
ከእቅፉ ቀስ ብሎ አወጣትና አይኗን እያየ ታውቂያለሽ አንቺ ለእኔ
ከዚህ በኃላ ሁሉ ነገሬ ነሽ በህይወቴ ከእናቴ ውጪ ሌላ ሴት
አፍቅሬ አላውቅም ነበር አንቺ ለእኔ ልክ እንደናቴ ነሽ ከዚህ በኃላ
ሁሌም ቢሆን ""እናቴ "" ነው የምልሽ እናቴ ነሽ አላት .
ብሌን እንባዋን መቆጣጠር አልቻለችም ቶሚ አፍቅርሀለው
አለችው።
ቶማስና ብሌን ከዛች ቀን ጀምረው እሷ "ሀኒ" እሱ "እናቴ"
እየተባባሉ ለብዙ ግዜ በፍቅራቸው መሀል ምንም ነገር ሳያስገብ
አንተ ትብስ እኔ ተባብለው ለብዙ ግዜ በፍቅር ቆዩ ቶማስ ሁሌም
ቢሆን ስለሚያፍቅራትና ሁሌም እሱ ጋር እንድትሆን ስለሚፍልግ
ሁሌም ቢሆን አብርው ውለው አብረው ቢያድሩ ደስ ይለው ነበር
ይሄንን ደግሞ ለማድርግ ቶሎ መጋባት እንዳለባቸው ያስብ ነበር
ቤተስቦቹም ብሌንን ስላስተዋወቃቸው በጣምም ስለወደዷት
ቢጋብ ደስተኛ ናቸው ።
ቶማስ ሁሌ ብሌንን ስርፕራይዝ ማድርግ ይወዳል ሁሌም ቴያትር
ፊልም ማየት ስለሚያስደስታቸው ቴያትር ለማየት እንደወትሯቸው
ተያይዘው ወደ ቴያትር ቤት አመሩ ቶማስ በልብ አንድ ነገር ያስብ
ነበር .
እንደተለመደው በትያትሩ ሲደስቱ ሲስቁ ከቆዩ በኃላ ቴያትሩ አለቀ
ቶማስ ብሌንን የምወደው ተወናይ ስላለ አንዴ መጣሁ ብሏት ወደ
መድርኩ አመራ .
ቶማስ ልክ መድርኩላይ እንደደረስ የቲያትር ቤቱ መብራት ባንዴ
ድርግም ብሎ ጠፍ ቲያትር ቤቱ ውስጥ የነበሩት ስዎች በሞላ
በጩኽትና በፍጨት ቀውጢ አደርጉት ሁሉም የየራሳቸውን ስልክ
ማብራት ጀመሩ ብሌን ግራ ገብቷት ሀኒ ሀኒ እያለች መጣራት
ጀመረች.........
ይቀጥላል ....
ፍቅርና እምነት
ክፍል ስድስት
የትያትር ቤቱ መብራት መጥፍት ያስደነገጣቸው ተመልኳቾች
ትያትር ቤቱን በፉጨት ና በጩኽት ቀውጢ አደርጉት ብሌን
በሁኔታው ተደናግጣ ' ሀኒ ሀኒ.... እያለች መጣራቷን
ቀጠለች.......
ቶማስ መድረኩላይ እንዳለ በትንሽዬው ቶማስን ብቻ የሚያሳይ
መብራት በራ የትላሲካል ድምፅም ተስማ ስው በፀጥታ ዝም
ብሎ የቆመው እንደቆመ የተቀመጠውም እንደተከመጠ ዝም አሉ
...ብሌን በድንጋጤ ምን እያደረገ ነው ብላ ከመቀመጫዋ ወደ
ፊት ጠጋ ብላ ተቀመጠች ...
ወዲያው "የግረማ ተፍራ " ዘፍን ተለቀቀ ቶማስ ማይክ ይዞ
ከዘፍኑ ጋር አብሮ መዝፍን ጀመር " ታድያለው ፍቅርሽን መልካም
ምግባርሽን የሚወደድ የሚያምር ሽጋ ውብ ገላሽ......" እያለ
መዝፍን ጀመረ ብሌን እሱን እያየች በደስታ እንባዋ ይፍሳል .
ቶማስ ቀስ ብሎ ወደ ብሌን መቀመጫ መጣ ስው በግርምትና
ምን እያደረገ ነው እያለ ያየዋል በዘፍኑ የተደስተም አብሮ
ይዘፍናል ወደ እሷ ከተጠጋ በኃላ አጠገባ በርከክ ብሎ ይዘፍንላት
ቀጠለ ....
ዘፍኑ እንዳለቀ እዛው እንደተንበረከከ የስውን ጩኽትና ፊጨት
ለማስቆም አመስግናለው አለ ስው መልሶ ዝም ሲል ..እናቴ አንድ
ጥያቄ ልጠይቅሽ አላት እሷም አይናይኑን እያየችው ፍዛ
ቀርታለች ... እናቴ አፍቅርሻለው አላት በህይወቴ ሁሉ አብረሽኝ
እንድትሆኚ እፍልጋለው አላት ...እናቴ.... ታገቢኛለሽ? ብሎ
እንደተንበረከከ ጠየቃት
የብሌንን መልስ ለመስማት ትያትር ቤቱን የሞላው ስው በጉጉት
ይጠብቁ ጀመር ...
ብሌን በጣም ተደናግጣለች ግራ ገብቷታል እንደተንበረከከ
ምንም ድምፅ ሳታስማ እሳም ከመቀመጫዋ ሸርተት ብላ
ተንበረከከች እቅፍ አድርጋ አንገቱን ሳመችው በአንገታም
የእሽታዋን መልስ ስጠችው ....
ቶማስ ያንን ሲስማ እሽ አለችኝ ብሎ ድምፅን ከፍ እድርጎ ተናገር
...እሳም አወ ሀኒዬ አገባሀለው ሁሌም ያንተ ብቻ እሆናለው አወ
አገባሀለው አለችው ..
ትያትር ቤቱ በጩኽት ,በፊጨት ,በእልልታ ና በጭብጨባ ቀውጢ
አደረጉትፍ .. ቶማስም አመስግናለው እናመስግናለን አላቸው
ብሌንና ቶማስ አንገት ለአንገት ተቃቅፍው ከትያትር ቤቱ የእንኳን
ደስ የማይላቸው አልነበረም ብሌን በበኩሏ በጣም ደስተኛና
ፍፁም ስላማዊ ስው ሆናለች እየደጋገመች ሀኒዬ አፍቅርሀለው
ትለዋለች
ብሌንና ቶማስ እራታቸውን በልተው ብሌንን ወደ ቤት አድርሷት
በደስታ ወደ ቤቱ ገገስ እቤት ገብቶ ለቤተስብ እስኪናገር ቸኩላል
እናቱም ሆነች አባቱ እሱ አግብቶ ልጆች ወልዶ በስላም
እንዲኖርና አያት መሆንም ናፍቋቸዋል .
ብሌን እቤት ገብታ እህቷን ሳራን ጠርታ ስለተፍጠረው ነገር ሁሉ
ነገረቻት በጣምም ደስተኛ እንደነበረች ነገረቻት ..ሳራ በጣም
የምትወደውና የምታፍቅረው ፍቅርኛ ከፍቅረኛም አልፎ ባል
ነበራት በጣም ታፍቅረው ነበር ሁሌም ስርፕራይዝ ያደርጋት ነበር
ነገር ግን በመሀከላቸው በተፍጠረ አለመግባባት ተለያይተው
እሱም የራሱን እሷም የራሷም ህይወት በየ አቅጣጫው
ጀምረዋል ..ሳራ ግን ታፍቅረውና ትወደው ስለነበር ከሱ
ከተለያየች በኃላ ሌላ ወንድ መቅረብ አይደለም ማየት
አትፈልግም ..የእህቷ ደስታ ቢያስደስታትም ልቧ ግን ፈርቶባታል
,ምንም ከመናገር ተቆጥባለች ደስ ይላል ፍጣሪ ከናንተ ጋር
ይሁን አለቻት ለቤተስቦቻቸውም እንደሚነግሩ ተስማሙ. የብሌን
ቤተስቦች የሳራ ልብ መስበርና ሌላ ወንድ አልፈልግም ብላ
መቀመጥ ተስፍ አስቆርጧቸዋል የልጅ ልጅ የማየት እድላቸውም
ብሌን ብቻ እንደሆነች ነው የሚያስቡት ..
ብሌንና ሳራ ለቤተስቦቻቸው የተፍጠረውን እየሆነ ያለውን ነገር
ባጠቃላይ ልታገባው እንደምትፍልግም ጭምር ተናገሩ የብሌን
ቤተስቦች በተለይ እናቷ በጣም ተደስቱ ፍጣሪ ፀሎቴን ስምቷል
ተመስገን ተመስገን ብለው ፍጣሪን አመስገኑ ብሌን ፍፁም
ደስተኛ ሆነች የቤተስቦቿ መደስት በጣምም አስደስታት ..
ቶማስ ወደ ቤቱ እንደደረስ ብሌን ደወለች ደህና ገባህ ሀኒ
አለችው አወ ደህና ገብቻላው እናቴ .አላት ብሌንም ለቤተስቦቿ
እንደነገረቻቸውና ደስተኛ እንደሆኑ ነገርችው ቶማስም ደስ አለው
እሱም ለቤተስቦቹ ሊናገር እንደሆነ ነግሯት ስልኩን ዘጋው..
ቶማስ ወደ ቤት በፍጥነት ገባ ሳሎን ማንንም አላገኝም ነበር
ማሚ ዳድ ብሎ ተጣራ ለወትሮው ምንም አዲስ ነገር ቢገኝ
ሳሎን እስኪመጡ ድረስ ይጠብቅ ነበር ዛሬ ግን አልቻለም ቀጠለ
ዳዲ ማማ ብሎ ተጣራ እናቱ ያለወትሮው ሲጣራ ምን ተፈጠረ
በማለት ደንግጣ ወደ ሳሎን በፍጥነት ወጣች.....
ይቀጥላል ....
ከወደዱት ላይክ እን ሼር ያድርጉ
ፍቅርና እምነት
ክፍል 7
ቶማስ ወደ ቤት ሄዶ ሳሎን ሲደርስ ማንንም አላገኝም ነበር
ድምፁን ከፍ አደርጎ ማሚ ዳዲ እያለ ይጣራ ጀመር የሚስማ
ሳጣ ደጋግሞ ተጣራ ዳዲ ማሚ እያለ ይጣራል...
እናቱ ና አባቱም መኝታ ክፍል ስለነበሩ ያለወትሮው ድምፁን ከፍ
አድርጎ የሚጣራው ምን አግኝቶ ነው በማለት እየተጣደፍች ወደ
ሳሎን አመራች ...ቶሚ ምንድነው ልጄ ምን ሆነህ ነው አለችው
ደንግጣ ማሚ ማሚ ምንም አልሆንኩም አላትና አቅፎ ሳማት
ዳዲስ ብሎ ጠየቃት አባቱም ወደ ሳሎን እየመጣ ነበር ጅግናው
ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እባክህ እንደዚህ ቤቱን ባንድ እግሩ
ያቆምከው ብሎ ፍግግ አለ ቶማስ ከመቀመጫው ተነስቶ አባቱን
ስላም ብሎ ተቀመጠ እናትና አባቱ ቶማስ ምን ሊነግራቸው
እንደፍለገ ለማወቅ በጣም ጓጉተዋል ....ቶማስም ቀጠለ
በነገራችን ላይ ትልቅ የምስራች ነው የምነግራችሁ እላቸው እናቱ
ለመስማት የባስ ጓጓች ...ንገርን ልጄ ምንድነው አለች አላስችል
ብሏት... በቅርቡ ሽማግሌ ፍልጉ አላቸው የምን ሽዋግሌ ነው
ከማን ጋር ተጣላህ አለች እናቱ ቸኩላ... አባት ነገሩ ስለገባው
እር ር ር ር ልጄ እንኳን ደስ ያለህ ተመስገን ልጄ አለ አባቱ...
እናትየዋም እንዴይ ቶማሴ እንኮ አላምንህም በቅርብ ሙሽራ
ልሆን ነው እያልክ ነው በማለት እልልልታዋን አቀለጠችው ሁሉም
ተደስቱ ...የቶማስ ቤተስቦች ብሌንን ያውቋታል ካንዴም ሁሌቴ
እቤት ተጋብዛለች ቤተስቦቹም ወደዋታል ለዛም ነበር ቶማስ እሷን
ማግባትና ከሳ ጋር መኖርን ይፍልግ እንደነበር ስለሚያውቁ
ለመጋባት መወስናቸውን ሲስሙ የተደስቱት ቤተስቦቹ ..... ሁሉን
ነገር ከነገራቸውና ከተደስቱ በኃላ ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ ብሌን
ጋ ደወለ .... እናቴ የኔ ፍቅር አላት ... ወየ ሀኒዩ የኔ ፍቅር
አለችው... እናቴ በጣም ደስ ብሎኛል ለእነ ማሚ ስነግራቸው
በጣም ደስተኛ ሆነዋል አላት እየተፍለቀለቀ እሷም ደስ አላት
የሆድ የሆዳቸውን አውርተው ፍቅራቸውን ተገላለፁ ነገ ከስራ
ሰወጣ ላግኝሽና ጓደኞቼን ላስተዋውቅሽ አላት ጓደኞቹን ብዙም
ባይሆኑ የተወስኑትን ታውቃቸዋለች ግን ሁሉንም ባንድ ላይ
አድርጎ ነገ አብርው ማምሽት እንደሚፍልግ ነገራት እሷም እሽ
ብላው ስልኩ ተዘጋ.....
ቶማስ ጓደኞቹ አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው ብዙውን ግዜም ስራ ላይ
የሚውለው ከሴቶች ጋር ነው .... ብሌንም የምታውቃቸው ሴቶች
ናቸው ያለወቀቻቸውም ሴቶች እንደሆኑ ነግሯታል .....
ብሌንም በበኩላ የሴት ጓደኛ የለትም አብራቸው ውዝውዜ
የምትስራቸውም ወንዶች ናቸው ውሎዋም ከወንድ ጓደኞቿ ጋር
ነው .....
ጠዋት ቶማስ ስራ ከመሄዱ በፊት ለብሌን ሜሴጅ ላከላት ""
እናቴ የኔ ፍቅር እንዴት አደርሽልኝ መልካም ቀን አፍቅርሻለው""
የሁል ቀን ተግባሩ ነች ሊረሳውም ሊተወውም አይችልም
..ብሌን ጠዋት ስትነሳ የሱን ሜሴጅ ስታነብ ደስተኛ ሆና
ትነሳለች ...የዛን ለትም በጠዋት ትሬሊንግ ስለነበራት በጠዋት
ነበር የተነሳችው ሜሴጁንም አንብባ ""እኔም አፍቅርሀለው""
አለች ለራሷ ደወለችለት .....እናቴ አላት ወዬ ሀኒ እንዴት
አደርክልኝ አለችው ስላም አደሬልሻለው የኔ ፍቅር እናቴ ዛሬ
ለምን ጠዋት ተነሳሽ አላት ...ብሌንም ልምምድ እንዳለባትና
ልትሄድ እንደሆነ ነገርችው ...እሽ ብሏት ፍቅሩን ፍቅሯን
ተገላልፀው ማታ እንደሚገናኙ ምሳ ስአትም እንደሚደዋወሉ
ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ ... ብሌን ልምምድ ቦታ ሄዳ ስትስራ
ቆየች ብሌን በጣም ጎበዝ ተወዛዋዥ ናት ስትወዛወዝ ያያት ሁሉ
ዋውውው ብሎ ከማድነቅም ባለፍ አጥንት የላትም እንዴ እያለ
መገርሙም አይቀርም በጣም ጎበዝ ናት ..... ቀኑን በየፊናቸው
ውለው ማታ ደረስ ብሌን እራሷን አዘገጃጅታ ትጠብቀው ጅመር
ቶማስም እቤት መጥቶ ብሌንን ይዞ ወደ ጓደኞቹ አመሩ......
ይቀጥላል .....
❤️ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ❤️
ክፍል 8 ከ 100like ብኋላ ይቀጥላል
ፍቅር እና እምነት (ፍቅር ባጋጣሚ)
ክፍል 8
ቶማስ ብሌንን ይዞት ወደ ጓደኞቹ አመራ........ የቶማስ ጓደኞች ቶማስ የአሁን ፍቅርኛው የወደፌት ሚስቱን ሊያስተዋውቃቸው መሆኑን ስላወቁ ደስ የሚል ምሽት ለማሳለፍ የሚመች ቦታ ነበር የተቀጣጠሩት ....
ብሌንና ቶማስ የቶማስ ጓደኞች አሉበት ቦታ ደረሱ ብሌን ሁሉንም የምታውቃቸውንም ለመጀመርያ የምትተዋወቃቸውን ሁሉንም ስላም አለችና መቀመጫ ተስጥቷቸው ተቀመጡ ቶማስ 1 የወንድ ጓደኛ ብቻ ነው ያለው እሱም የመስሪያ ቤት ጓደኛው ...ብሌን ሁሉንም ተመለከተች አብዛኞቹ ባለትዳር ናቸው ያላገብም አሉ ሁሉንም ቀስ በቀስ ታያቸዋለች በቃ ሁሉም በጣም ይገራርማሉ እራሷን ታዘብች .....የእነሱን እርጋታና ፀባይ የአነጋገር ለዛ ቁጥብነታቸው በቃ ሁሉ ነገር .....ብሌን ትንሽ ቸኮል ስለምትል የነሱ እርጋታ ገርሞት ዝም ብላለች .....ይስቃሉ ይጫወታሉ ቶማስም እናቴ ተጨዎች እንጂ ይላታል .....እሽ ሀኒዬ ብላ ፍገግ ማለታም አልቀርም ......ምሽቱ እንደዛ እንደዛ እያለ የመለያያቸው ስአት ደርሶ ተለያዩ ቶማስም ብሌንን ወደ ቤት ሊያደርሳት መንገድ ጀመሩ ......እናቴ የኔ ፍቅር ደበረሽ እንዴ አላት በአንድ እጁ እጃን ይዞ......ሀኒዬ የኔ ፍቅር እር አልደበርኝም አለችው የሚያምርውን ፍገግታዋን እያሳየች ....እቤት አድርሷት መለያየት ግድ ሆነና የፍቅር አስተያየት አይታው ስላም እደር ሀኒዬ ብላ በስሱ ከንፍሩን ስማ ወደ ቤቷ ገባች .....ቶማስም መኪናውን አስነስቶ ጉዞዎ ወደ ቤቱ አቀና ......ብሌን እቤት ገብታ ቤተስብን ስላም ብላ መኝታ ክፍሏ ገብታ ልብሷን ሳትቀይር ጫማዋን እንኳን ሳታወልቅ በደርቷ ጋደም ብላ በሀሳብ ነጎደች ......ቶማስ እቤቱ ደርሶ ስላም መግባቱን ሊነግራት ስልክ ደወለ ብሌን አታነሳም ደግሞ ደወለ አሁንም አታነሳም ግራ ገባው....ብሌን ከሄደችበት የሀሳብ ጎዳና የቶማስ የስልክ ጥሪ ሊመልሳት አልቻለም ሄዳለች ...ቶማስ ግራ ገባው ሜሴጅ ላከ መልስ የለም ግራ ቢገባው ሳራ ጋ ደወለ እሷም ስላም ካለችው በኃላ ምን እንደሆነ ጠየቀችው ግራ ገባት ...ሳራ እናቴ ስልክ አታነሳም በስላም ነው አላት ....ሳራ ብሌን ስትገባ ምንም ነገር አላወሩም ...እንዴይ ስላም አይደላችሁም እንዴ አለችውና ቆይ እስኪ ልያት ብላ ወደ ብሌን የመኝታ ክፍል ሄደች ....ብሌን አሁንም ከሀሳቧ አልተመለስችም ብዙ ነገር ታስባለች እንዴይ ቆይ ግን እኔ ለምንድነው እርጋ ያልኩ ሴት ያልሆንኩት ለምንስ ዝምተኛ አልሆንኩም ብላ እራሷን ትጠይቃለች በቶማስ ጓደኞች ፀባይ እየተገርመች ...ሳራ ደርሳ በሩን ስታንኳኳ ብሌን ከወስዳት የሀሳብ መአበል ተመልሳ በሩን ከፍተች ...በስልክ ቶማስ እንደሚፍልጋት ነግራት ስልኩን ስጥታ ሳራ ከክፍል ወጣች...ሀኒዬ አለችው ....እናቴ ምን ሆንሽብኝ ለምን ስልክ አታነሽም ሲላት ደነገጠች ..ይቅርታ ሀኒዬ ደውለህ ነበር አለችና ከቦርሳዋ ውስጥ ስልኳን አውጥታ አየችው ይቅርታ ሀኒዬ ሳይለንት ስለነበር አልስማሁትም አለች በሀዘኔታ ድምፅ ,,....... ችግር የለውም እናቴ እኔ ደግሞ ምን ሆንሽብኝ ብዬ ደንግጬ ነበር አላት ...ደህና እንደገባ ነግሯት ፍቅራቸውን ተገላልፀው ደህና እደር ስላም እደር ተባብለው ስልኩ ተዘጋ .......ብሌን ደንግጣለች ምን ሆኜ ነው ብላ ተነሳችና ፊት ለፊቷ የሚገኝው መስተዋት ስር ሄዳ ቆመች .....በሩ ተንኳኳ ሳራ ነበርች ...እሽ ውዷ እህቴ ምንድነው እባክሽ እንደዚህ ያስቆዘመሽ አብርሽ አምሽተሽም ናፈቀሽ ብላ ቀለደችባት...... ምን እንደሆነች ደግማ ጠየቀቻት ግን ብሌን ምንም እንዳልሆነችና ትንሽ እንደደከማት ብቻ ነግራት ልብሴን ልቀይርና ልተኛ አለች ....ሳራም እሽ ብላ ደህና እደሪልኝ ውዷ እህቴ ብላ እየሳቀች በሩን ዘግታ ወጣች.....ብሌን ልብሳን ቀይራ ፀሎቷን አድርጋ ተኛች .....በነጋታው ቶማስ ያስለመዳትን ሜሴጅ አንብባ ወደ ልምምድ ቦታ አመራች ... ቀኑ ይደብር ነበር ጓደኞቾም ግራ ግብት አላቸው ....ቶማስ ደውሎ ምሳ አብርው እንደሆኑ ነገራት እምቢ ላለማለት እሽ አለችው .....ልምምዷን ጨርሳ ከቶማስ ጋር ተገናኝተው ምሳ በልተው ትንሽም ቢሆን ደስተኛ ሆነው ቆይተው ተለያዩ ....... ብሌን ውስጧን የረበሽው ነገር ለሷም አልገባትም ግን በቃ ውስጧ ጥሩ ስሜት የለውም የማይሆንላትን የመርጋጋት ባህሪ ለማምጣት ጥረት ጀመረች በመሀከል ግን የልጠበቀችው ነገር ተከስተ ለማንም ሳትናገር እራሷው ደብቃው ከረመች..........
..... ይቀጥላል✍🏼
💖 ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ💖
ፍቅር ባጋጣሚ (ፍቅርና እምነት)❣️
ክፍል 9
ብሌን እራሷን ለማረጋጋት በምትጨነቅበት ስአት ያልታስበ ነገር ገጠማት ለማንም ሳትናገር ብቸዋን ከረመች,.....ብሌን በጣም ስለምትጨነቅና ስለምታስብ በዛላየ በተደጋጋሚ የመድረክ ስራዎች ላይ በመስራት ብቻዋን በማሳለፍ ውስጧ ስላም ከማጣቱ የተነሳ ሁል ግዜ ያማታል ህመሟን ግን ለማንም ሳትነግር ደብቃው ከረመች,.
ቶማስ በበኩሉ የሷ እረጋ ማለት አስጨንቆታል ነገር ግንከመጋባታችን በፊት ያስፍልገናል የሚላቸውን የቤት እቃዎች እንዲሁም ሌላ ቁሳ ቁሶችን በማሟ ተጠምዷል ብሌንን ቀን በቀን ያገኛታል የውስጧን መረዳት ባይችልም የሆነ ነገር እንደሆነች ገብቶታል ቢጠይቃትም ምንም እንዳልሆነች እንጂ ምንም ነገር ልትነግርው ፍቃደኛ አልነበረችም ,,
አንድ ቀን ግን ቶማስ ሁሉንም ነገር እንድትነግረው አጥብቆ ለመናት ሁኔታዎቿ ሁሉ እንዳስፍራውም ነገራት ብሌንም መጨነቁና ግራ መጋባቱ ስለገባት አንዳንድ ነገሮችን ጠየቀችው በተለይ የሚወድላትን ነገር እንዲነግራት ጠየቀችው ,,, በፍቅር አይን አይናይኑን እያየች እጆቹን በእጆቿ ይዛ ,,, እናቴ አለ ቶማስ የኔ ፍቅር ሁሉ ነገርሽን በቃ ሁሉ ነገርሽን አወደዋለው ዝምታሽን ግን አልወደድኩትም ስትስቂ,ስትጫወቺ .በቃ ፍንድቅድቅ ስትይ ደስ ይለኛል ሳቅሽን ፍጣንነትሁ በቃ ባጠቃላይ ሁሉ ነገርሽን እወደዋለው አፍቅርሻለው እናቴ ,, ብሎ እጆቿን ሳም አድርገው .. ብሌን ቶማስን እኔም አፍቅርሀለው አለችው .. ሀኒዬ የእውነት ለመናገር ስሞኑን ጥሩ ስሜት የለኝም ምክንያቱም አንተ እወዳቸዋለው ያልከኝን ባህሪዎች ከእኔ ለማስወገድ ከራሴ ጋር ሙግት ይዜ ነበር ለዛ ነው እኔ ስላም አጥቼ አንተንም ስላም የነሳሁህ አለች እንዳቀረቀረች....ቶማስ በእጆቹ የብሌንን ፊት እየዳስስ ካጎነበስችበት ቀና አደረጋት ....የኔ ፍቅር እናቴ አፍቅርሻለው ካንቺ ምንም የምጠላው በሀሪ የለም እንዲያውም የለመድኩት ሲቀር ይከፍኛል አላት ... ብሌን ፍገግ አለች ሀኒዬ አፍቅርሀለው አለችው .,,,,,
ብሌን ከዛች ቀን ጀምራ ወደ ራሷ ተመለስች የድሮ በሀሪዋን ቀጠለችበት ,,, እንዳንዴ ግን ህመም ቢስማትም ለማንም ግን አልተናገረችም ,,,, ቀናቶች እየገፊ ወራት ተተኩ ብሌንና ቶማስም ዝግጅታቸውን አጠናቀው የባህሉን ሽማጌሌ ተልኮ ሁሉም ነገር ተጠናቆ ነበር ,,,,,ለስርጉ ሽር ጉዱም ቀጥሏል ,,የብሌን ህመምም መፍትሄ ሳይፍለግለት ለማንም ሳትናገር ደብቃው ተቀምጣለች እንዳንዴ ምኗን እንደሚያማት እንኳን እሷም አታውቀውም .....
ቶማስ ብሌንን አግብቶ አንድ ቤት ውስጥ የሚያድሩበትና አንድ ላይ የሚውሉበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀ ነው ቤተስቦቹም የስርጉን ቀን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ....
ብሌን የስርጓ ቀን እየደረስ ሲሄን ግዜ ፍራት ወረሳት ሲደሩ ማልቀስ ወግ ነው እንደሚባለው ሆኖባት የምታደርገው ሁሉ ግራ ገብቷታል ,,,ቤተስቦቿ ደግሞ ቶሎ አግብታ ልጅ ወልዳ አያት የመሆን ህልማቸው እውነ የሚሆንበትን ቀን ናፍቀዋል ሳራም የእህቷን ደስታ የስርጓን ቀን ለማየት ጓጉታለች ,,,
የስርጉ ቀን ደረስ "የኛማ ሙሽራ "ተብሎ ሊዘፍንላቸው ነው ሽር ጉዱ ቀጥሏል ደስታ በደስታ ሆነዋል ሙሽራና ሙሽሪት ከነ ሙዚዎቻቸው አምረው ተውበዋል .... ቤተ ዘመድ ተስብስቧል ....
......ይቀጥላል✍🏼
💖ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ💖
ፍቅርና እምነት💖
ክፍል 1⃣1⃣
ቶማስ ብሌን የውዝዋዜ ስራዋን እንደታቆምና እቤት እንድትውል አስፍላጊ ከሆነም የራሷን ስራ ከፍታ እንድትስራ ነገራት ብቻ ግን ውዝዋዜውን ማቆም እንዳለባት ነገራት ብሌን ግራ ገባት።
ብሌን ውዝዋዜ ወይም የጥበብ ስራ ለሷ ምን ማለት እንደሆነ እያወቀ እንዴት አቁሚ ይለኛል እንዴትስ ከህልሜ እርቃለው እንዴትስ ችዬ ብዙ ጊዜ የለፋሁበትን እተዋለው ለምንስ እንደዚህ አለኝ ብላ ግራ ገብቷታል...
ቶማስ ብሌንን ያፍቅራታል ያከብራታል ሚስቱም እናቱም ስለሆነች ፍላጎቷን ሁሉ ቢያሟላላት ደስ ይለዋል ነገር ግን ውዝዋዜን ማቆም እንዳለባት ወስኗል።
ቶማስ የብሌንን መልስ እየተጠባበቀ ነው በፍራት ጠጋ ብሎ "እናቴ" አላት በስስት እያያት አውቃለው ለውዝዋዜ ያለሽን ፍቅር ግን ግን እናቴ እኔ ከስራ ስመጣ እቤት ላገኝሽ እፍልጋለው ስራ ሳይኖረኝ ሙሉ ግዜየን ካንቺ ጋር ማሳለፍ እፍልጋለው ስለዚህ ውዝዋዜውን ትተሽ እቤት ብትውይ ይሻለኛል አላት...
ብሌን ቶማስ መልሷን እየተጠባበቀ እንደሆነ ገብቷታል ግን ምን ብላ እንደምትመልስ ግራ ገብቷታል.. እሽ እንዳትል የምትወደውን ስራ ልትርቅ ነው እምቢ እንዳትል ደግሞ የምታፍቅርውን ስው ልታስከፋ ነው.. ስለዚህ ምንም ሳታቅማማ እሽ ማለትን መርጠች.. "እሽ ሀኒ" አለችው ውስጧን ቅር እያለው።
ቶማስ የብሌንን እሽታ መስማት ቢያስደስተውም ውስጧ ግን ጥሩ ስሜት እንደሌለው ገብቶታል ,ቶማስ ብሌን ውዝዋዜ እንድትተው የፈለገው በጣም ሰለሚያፍቅራት መድርክ ላይ ስትጨፍር አብሯት የጨፍረ ገንዘብ የሽለማት ያደነቃት ሁሉ የሚወስድበት እየመስለው ይፈራ ነበር ለዛ ነው ውዝዋዜን እንድትተው የፍለገው ,
ብሌን የውዝዋዜን ስራ ትታ እቤት መዋል ከጀመረች ቀናቶች ተቆጥርዋል ደስተኛ ባትሆንም ደስተኛ ለመሆን እየጣረች ነው.. ብሌን ስለምትጨነቅና እቤት ውስጥ መዋል ስላልለመደች ጥሩ ስሜት የላትም ድሮ ያማት የነበር ህመም ቀስ በቀስ እየባስባት መጥቷል ,
ቶማስ ብሌንን በፈለጋት ሰዓት ስለሚያገኛት በጣም ደስተኛ ሆኗል። የብሌን ደስታ ማጣት ግን አልታየውም ነበር ህመሟም አልተስማውም ነበር ሁሌ ያዝናናታል ግን ብሌን ለሱ ብላ ፍገግ ትል ነበር ..
ብሌን እንደወትሮዋ ጥዋት ትነሳና ቶማስን ወደ ስራ ከሽኝች በኃላ እቤት ውስጥ ልምምድ መስራቷን አላቆመችም ነበር ,ብሌን እንደተለመደው ልምምዷን እየስራች ድንገት ........
✍🏼ይቀጥላል....
**** በፍቅርህ ታስሬ ****


🌹🌹 📝📝 🌷🌷


እጅጉን ተስቤ በማንነትህ ላይ
ፈርሜ ገባሁኝ ለመቋቋም ስቃይ
እጅጉን ሀያል ነው ከባድ አቀበት
ገብቼ ለመስራት ከልብህ ላይ ቤት
አንተን ስንከባከብ እርቄ ከራሴ
እጅጉን ስወድህ አብልጭ ከነብሴ
ሁሌ ስከተልህ በሄድክበት ቦታ
እያደረ ጠና የልቤ ትርታ
...

አበደች ይሉኛል ሲያዩኝ በመንገድ
ሳስታውስህ ስስቅ ስቆም ስራመድ
ይሄ ሁሉ ድርጊት እኔን መች አንቅቶኝ
ቁሜ ሳንቀላፋ ፍቅርህ ስቦ አስቀምጦኝ
....

በደመ ነፍስ እንጂ በአካል መች ተጉዤ
በሀያሉ ፍቅርህ እየኖሩኩ ደንዝዤ
ፍቅር የታለ ስል ስፈልግህ ፍቅሬ
ሁሌም እኖራለሁ በፍቅርህ ታስሬ።

••••••\\\•••••

@Campus_love stories
ፍቅርና እምነት💕
!ክፍል 12
ብሌን እንደወትሮዋ በጠዋት ተነስታ ቶማስን ከሽኝች በኃላ የተለመደውን ልምምድ ማድርግ ቀጠለች ,,, ብሌን ልምምዷን እየስራች ሳታስበው በጠዋት የስልኳ መጮህ አስደነገጣት ,,,,,,ስልኳን ስታየውም ማመን አቃታት የውዝዋዜ አስልጣኟ ነበር የደወለው,,,
ብሌን ግራ በተጋባ ስሜት ስልኳን አንስታ
ሄሎ አለች ...በሚያምር ድምፁ ብሌንሻ ስላም ነው የጠፍ ስው በቃ እንደዚህ ጥፍት ይሻላል አለ ፍጠን ፍጠን ብሎ!!.....እር አለው ዮኒ ስላም ነው አለች ...የአስልጣኛቸው ስም ዬናስ ይባላል ላጤ ነው ብሌንን የራሱ ማድርግ ያስብ ነበር ግን ቶማስ ስለወስደበት ቢበሳጭም ምንም ማድርግ አልቻለም ...ብሌን ዮኒን ልክ እንደ ወንድሟ ነው የምታየው አንዳንዴ አስልጣኝ መሆኑንም ትርሳለች ....
ብሌንሻ ዛሬ የደወልኩት ትልቅ የምስራች ልነግርሽ ነው አላት,,,, ከልብ የደስታ ሳቅ እየሳቀ ,... አንቺ ብትጠፊም ስራ ብታቆሚም ይሄ እድል ግን እንዲያመጥሽ አልፍልግም አላት....
ዮኒ ቁም ነገርኛ ነው አስተዋይም ነው ,,ስው አክባሪ ከትንሹ ትንሽ ከትልቁ ትልቅ ሆኖ ሙኖር ይችልበታል በልጅነቱ እናት አባቱን በሞት ስላጣ በጣም ጠንካራና ጎበዝ ነው ,ከስው ጋር ተስማምቶ መኖርን ይችልበታል.
ብሌን ዮኒ ምን ሊነግርኝ ይሆን ብላ ግራ ገብቷታል ,...ብሌን ካገባች ቀን ጅምሮ ብዙም አይደዋወሉም በተለይ የውዝዋዜ ስራን የተወችው በቶማስ ምክንያት መሆኑን ,,ዮኒን ስላወቀ ምልባት መደወሌም ፀብ እንዳይፍጥር በማለት ነበር.....
ዮኒ የምን የምስራች ልትነግርኝ ነው ? አለች ብሌን,ለመስማት ተቻኩላ..ዮኒ ሊነግራት ገና ምን መስለሽ ብሌንሻ ....ብሎ ሳይጨርስ የነብሌን የሳሎን በር ተንኳኳ ...ብሎን በጣም ተደናግጣ ማን ይሆን በማለት ...ዮኒ ቆይ ብላ ወደ በር አመራች,,,,,,,,,,
....ይቀጥላል✍🏼
ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ
ፍቅር ባጋጣሚ (ፍቅርና እምነት)💖
ክፍል 13
ዮኒ ለብሌን የምስራቹን ሊነግራት ሲል የነ ብሌን የሳንሎን በር ተንኳኳ... ብሌን ዬኒን ቆይ መልሼ እደውላለው ብላ ስልኳን ዘግታ በሩን ከፍተቸው ቶማስ ነበር ቶማስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በስራ ስአት ወደ ቤት የመጣው ..

ቶማስ ወደ ቤት የተመለስው ከከተማ ውጪ ለስራ ደርሶ መልስ መሄድ ስለነበርበት ሊነግራትና ልብስ ሊቀይር ነበር ወደ ቤት የመጣው ,በጣም በመጣደፍ ደወ ቤት ገብቶ የሆነውን ከነገራት በኃላ ወደ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ልብሱን ቀይሮ እየተጣደፍ ብሌንን ተስናብቷት እንደሚያፍቅራትና እንደምትናፍቀው ምግብ በስአቱ እንድትበላና ቶሎ ከተመለስ እራት ውጪ እንደሚጋብዛት ቃል ገብቶ አቅፎ ከሳማት በኃላ ተጣድፎ መኪናውን አስነስቶ ሄደ .,

ብሌን ቶማስን ከበር ቆማ በአይኗና እጇን በማውለብለብ ከተስናበተችው በኃላ እቤቷ ገብታ ወደ ዮኒ ደወለች,,ይቅርታ ዮኒ አለችው ችግር የለውም ብሌንሻ አላት ዮኒ ,,

ዮኒ ብሌንሻ ምን መስለሽ አለ ሊነግራት እየተጣደፍ ,ብሌንሻ አውቃለው ልምምድ አቁመሻል ግን ይሄንን እድል ማጣት የለብንም አላት,

ብሌን ከመቸኮሏ የተነሳ ዮኒ ምንም አልገባኝም የት ነው ያለኽው አለችው ልምምድ ቦታ እንደሆነ ሲነግራት ስልኩን ዘግታ ልብሷን ቀይራ ከቤት ወጥታ ሄደች,

ብሌን ልክ ልምምድ ቦታ እንደደረስች ሁሉም ተስብስብው ስላም አሏት ስላም ካለቻቸው በኃላ ዮኒም ስላም ሊላት ወደ እሷ መጣ ብሌንም ወደሱ ተጠግታ ስላም አለችውና መቀመጫ ወንበር ፍልገው ተቀመጡ,

ዮኒ ብሌንን ስለ ኑሮዋ ስለ ትዳሯዋ ከጠየቃት በኃላ ስለመጣላቸው እድል ነገራት ,በውጪ ሀገር የሚገኝ ኢንተርቴይመንት የነሱን የውዝዋዜ ብድን ለመውስድና ስራ ለማስራት እደፍለግ ና ውዝዋዜ ብድኑም ውስጥ እሷ መካተት ,እንዳለባት ነገራት,,

ብሌን በስማችው ነገር በጣም ተገርመችም ደነገጠችም ብሌን ትንሽ ካስበች በኃላን ዮኒ ምንም ልልህ አልችልም ምናልባት እስኪ ሀኒን ላማክርውና መልሱን እነግርሀለው ብላው ሁሉንም ተስናብታ ወደ ቤቷ ለመመለስ ታክሲ ውስጥ ገባች ,,

ብሌን የስማችው ነገር በጣም አስገርሟታል ለብዙ ጊዚያት ስትናፍቀውና ስታስበው የነበረውን እድል ዛሬ ላይ መገኝቱ በጣም አሳዝኗታል ቶማስ እንደማይፍቅድላት ስታስብ ደግሞ እንባ እንባ ይላታል ብሌን በሁለት ልብ ሆና እቤት ደርሳ የውጭውን በር ከፍታ ስትገባ ያየችውን ማመን አልቻለችም ...

.....ይቀጥላል✍🏼
💖ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ💖
ፍቅር ባጋጣሚ
ክፍል 14
ብሌን የስማችውን መልካም ዜና እያብስለስለችና ለቶማስ ብትነግርው እንደማይፍቅድላት እያስበች እቤት ደርስች ......እቤት ደርሳ የውጭውን በር ስትከፍት ያየችውን ማመን አቃታት ,,,,,, የቶማስ መኪና ግቢ ውስጥ ቆማለች ,,

ብሌን በጣም ግራ ገባት እንዴት ሊሆን ቻለ ሄጃለው ብሎኝ አለነበር? ለምንስ ተመለስ ?እቤት ሲያጣኝ ለምንስ አልደወለም ? እያለች እራሷን በጥያቄ አፍጠጠችው ግራ ገባት ውደ ቤት ቀስ ብላ ምን እንድምትል እያስበች ውደ በሩ ተጠጋች,

ቶማስ ይሄድበት የነበርው ስራ ለነገ ተዘዋውሯል ስለዚህ ዛሬን እርፍት አድርጉና ነገ በጠዋት ተነስተን እንሄዳለን ሲባል ጊዜ የሆነ ሀሳብ ድቅን ሲልበት ወደ ቤቱ ተመለስ ነገር ግን ብሌንን እቤት አላገኛትም ነበር ስልኩም ባትሪ ዘግቶበት ስለነበር እቤት ገብቶ ስልኩን ቻርጅ እያደርገ ሶፍ ላይ ጋደም ብሎ ነበር...

ብሌን ቀስ ብላ የሳሎኑን በር ከፍተችው ፊት ለፊት ሶፍ ላይ ቶማስን አየችው ,,ሀኒ,አለች በፍርሀት ድምፅ ,ቶማስ ሲያያት እፊቷ ላይ የሚታየውን ፍርሀት ተመለከተ ከድምፃም ተርዳ,ሊያስጨንቃት ስላልፍለገ ከተኛበት ተነስቶ ,,እናቴ,,ጠፍሽብኝ እኮ የት ሄደሽ ነው ?እያለ ወደሷ ተጠግቶ አቅፎ ሳማት ,,

ብሌን ደንግጣለች ,ሀኒ ,በስላም ነው ምነው ተመለስክ ?ምን ተፍጠር?ችግር አለ?ለምንስ አልደወልክልኝም?እያለች የፍቅር አይን እያየችው ጥያቄዋን አዘነበችው.,ቶማስ ለነገ እንደተባለና የተመለስውም እሷና እሱ ቀድመው ሄደው ዛሬን እንዲዝናኑ ና ነገ ከስራ መልስ ትንሽ ተዝናንተው እንዲመለሱ ፍልጎ ነበር ,ቶሎ ወደ ቤት የተመለስው ,ሲያጣት ያልደወለው ስልኩ ባትሪ ስላልነበርው እንደሆነም ነገራት,,

ቶማስ ለስራ የሚሄደው ውብና ማርኪ ወደ ሆነችው ሀዋሳ ከተማ ነበር ብሌንን ይዞ ሄዶ ዘና ማለት ይፍልግም ስለነበር ይሄንን አጋጣሚ በስበብ መጠቀም ስለፍለገ ነበር ወደ ቤት ቶሎ የተመለስው ,

ብሌን ለስራ ካንዴም ሁለቴ ሀዋሳ ሄዳ ታውቃለች ለመዝናናትና ዞር ዞር ብሎ ለማየት ግን እድሉ አልነበራትም ሄዳ ብትዝናና ግን ደስ ይላታል የቶማስ ሀሳብንም ደግፍዋለች ቢያንስ ለሁለት ቀን ዘና እንላለን ከቻልኩም ስለ መጣው እድል እነግረዋለው ብላ አስበች , ሀኒ , ታዲያ ለምን አንሄድም አለችው እርግጠኛ ነሽ እንሂድ አለ ቶማስ ደስ እያለው ,አወ እንሂድ ምን እንስራለን አለች ብሌን ,ሁለቱም ተጣድፍው መቀየርያ ልብስ ይዘው ጉዟቸውን ወደ ውቧና ምርጣ ከተማ ሀዋሳ አደርጉ.,

ብሌን ድሮ ለስራ ስትሄድ ባዛር ሲኖር በሚኒባስ ብዙ ሆነ ስለሚሄዱ አብዛኛውን መንገድ በእንቅልፍ ነበር የምታሳልፍው ዛሬ ግን በባሏ መኪና የምትፍልገውን ዘፍን እየስማች እየሳቀችና እየተደስተች መንገዳቸውን ቀጥለዋል መንገድ ላይ ያማራት ነገር ካየች ቆመው ከፍለጉ ገዝተው ካልፍለጉም አይተው በቃ በደስታ ጉዟቸውን ቀጥለዋል ምግብ ከአዲስ አበባ ሳይወጡ ስለበሉ አልራባቸውም መንገድ መንገዱንም የሚበላ እየገዙ እየበሉ ስለነበር ምንም አላስፍለጋቸውም ,,

ጉዟቸው በደስታ ቀጠለ የሀዋሳ መዳርሻ የሆኑትን ትናንሽ ከተማዎች አልፍው ሻሽመኔ ደርሱ ሻሽመኔም ውብ ሀገር ነች እዛ ሲደርሱ ስአቱም እየመሽ ነበር መብላትም ፍልገው ስለነበር ወደ አንዱ እሪስቶራንት አመሩ መኪናቸውን አቁመው እየተፍለቀለቁ ከመኪና ወርደው ወደ ውስጥ ገብ የሚፍልጉትን በልተው ጠጥተው ትንሽ ካርፊ በኃላ ጉዟቸውን ቀጠሉ,,

ሻሸመኔ ለሀዋሳ ቅርብ ናት ብዙም ሳይቆዬ ፍንትው ወደ አለችው ደማቋ ከተማ ሀዋሳ ደርሱ (ሀዋሳን እኔን ስለምወዳት ነው መስለኝ ገፀታዋን ብገልፅ አልጠግባትም ሀዋሳ ምርጥ ሀገር ናት ለኔ ) ሀዋሳ እንደደርሱ በጣም ተደሰቱ የት ማርፍ እንዳለባቸው አሰብ ብዙም ሳያቅማሙ ወደ "OSS international hotel " አመሩ ሆቴሉ ልዬ ነው " ከውጪ እስከ ውስጥ እጅግ ያምራል በቃ ውብ ነው(ዋውው ብታዬት ደግሞ ትደስታላችሁ ከለዊ እሪዞርት ግን አይበልጥም እመስክራለው)"፦

እዛ ገብተው እቃቸውን እስቀምጠው ሻወር ወስደው ትንሽ ካርፍ በኃላ ወደ ፍቅር ሀይቅ ተያይዘው ወጡ ምሽት ላይ ፍቅር ሀይቅ አካባቢ ትእይንት ይኖራልና በስአቱም ደስ የሚል ትዕይንት ነበር እሱ ሲያዬ አምሽተው እዛው የአሳ እራታቸውን በልተው ወደ ክላሳቸው ከመሄዳቸው በፊት ወደ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አደርጉ ',,..ገብርኤልን አመስግነው ተመልስው ወደ OSS ጉዟቸውን አመሩ ,,,,


ክፍላቸው እንደደርሱም ሁለቱም ደክመው ስለነበር አልጋቸው ላይ ወደቁ ፍፁም ደሰተኛ ፍፀም ስላም በፍታቸው ላይ ይነበባል ብሌን በዚህ ደስታ መሀል ለቶማስ የመጣልኝን መልካም እድል ብነግርውስ ብላ አስበች ደስታ ማድፍርስ ይሆናል ብላ ዝም አለች ,,,,,,

ቶማስ ብሌን ልትነግርው የፍለገችው ነገር እንዳለ ስለተርዳ እንድትነግርው ወደ ድርቱ አስጠግቶ በማከፍና ፀጉሯን በማሻሸት እንድትነግርው ጠየቃት ....

.....ይቀጥላል✍🏼
ከወደዱት ላይክ እና ሼር ያድርጉ
ፍቅርና እምነት(ፍቅር ባጋጣሚ)💖
ክፍል 15
የ ምዕራፍ 1 የመጨርሻ ክፍል
ብሌንና ቶማስ ሀዋሳን በትንሹም ቢሆን አየት አደርገው ወድ መኝታ ክፍላቸው OSS international hotel ገብተው ደክሟቸው ስለነበር ሁለቱም በቁማቸው ወደቁ ..ብሌን ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነበርች ከከተማ ወጥተው መዝናናታቸው አዲስ ባይሆንም ዛሬ ግን ደስተኛ ነች ,,,ግን ቀን የስማችውን መልካም ዜና እንዴት ብላ እንደምትናገር ግራ ገብቷታል ...በመሀከል ግን ቶማስ ብሌንን .እናቴ ...ልትነግሪኝ የፍለግሽው ነገር አለ እንዴይ? ብሎ ጠየቃት ከሁኔታዋ ተርድቶ.
ብሌን ቶማስ እንደዛ ብሎ ስለጠየቃት በይበልጥ ደነገጠች ግራ ገባት ግን በዚህ አጋጣሚ ካልነገርችው መቼም አትነግርውም ብቻ በውስጧ ብዙ አይነት ስሜት ተመላለስ ስነግርው እስካሁን የነበርውን ደስታ ያበላሽበት ይሆን ,ዝም ብል ደግሞ መቼ እነግረዋለው ,እያለች ብቻዋን ትጨነቅ ነበር ,ግን መናገር እንዳለባት ወስነች'.
ብሌን ከተኛችበት ቀና ብላ ተስተካክላ ትራሷን ተደግፍ .ሀኒ አለችው ,ቶማስም ወደሷ ተጠግቶ ትራሱን ደገፍ ብሎ አይናይኗን እያየ ,ወዬ እናቴ.አላት ብሌን እየተቅለስለስች .ሀኒዬ አውቃለው ምናልባት የምነግርህ ነገር ላያስደስትህ ይችላል ግን ሳልነግርህ ማለፍ አልፍልግም አለችው ,
ቶማስም ወደ እሷ ጠጋ ብሎ አንገቷን በስሱ ሳም አደርጋትና ,እናቴ የሆነ ያስጨነቀሽ ነገር እንዳለ ይገባኛል ብትነግሪኝና መፍትሄ ብንፍልግ ይሻላል ደግሞ ደስተኛ መስለሽ ለመታየት እየጣርሽ እንደሆነ ገና ከቤት ስንወጣ ትርድቻለው ምን ተፍጠር ብዬ እንዳልጠይቅሽ ያጨናነቅሁሽ መስሎ ስለተስማኝ ነው ዝም ያልኩት ግን በቃ ያለውን ነገር ሁሉ ንገሪኝና እንወያይበት አላት አይንይኗን እያየ'.,
ብሌን የቶማስን ንግግር ከስማች በኃላ .ሀኒዬ ቀን ከቤት ያላገኝኽኝ ዮኒ ደውሎልኝ የልምምድ ቦታ ሄጄ ነበር አለች እየፍራች እየስጋች.ቶማስ ፍራቷን ስለተርዳ ልምምድ ስራ እንዳቆምሽ ያውቅ የለ እንዴይ ለምን ደወለልሽ ምን አዲስ ነገር ተገኝ አላት ለስለስ ባለ ድምፅ,.. ብሌን ይሄንን ስትስማ የተፍጠርውን የመጣላቸውን አዲስ እድልና ይሄንን እድል በጣም ትፍልገው እንደነበር አሁንም ይሄ እድል እንዲያመልጣት እንደማትፍልግ ነገርችው....
ቶማስ ደነገጠ ግራ ገባው የስማውን ማመን አልቻለም ,ሀገር ውስጥ ሆና መድርክ ላይ ስትስራ አብረዋት በሚጨፍሩ ና በሚሽልሟት ስዎች የሚናደድ ጅግና ከሀገር ውጪ ልሂድ ስትለው በድንጋይ አናቱን የተባለ ይመስል ደርቆ ቀር ..የቶማስ ዝምታ ብሌንን ፍርሀት ውስጥ ከተታት ዝም አለች ሁለቱም ዝም አሉ ክላሱ በዝምታ ተሞላ ሁለቱም የሚወስኑት ግራ ገብቷቸው በሁለት አለም ውስጥ ተከፍለው በሀሳብ ጭልጥ ብለው ሄዱ .....
ድንገት እንደባነነ ስው ሆኖ ቶማስ .እናቴ ..እና አንቺ ምን አስብሽ ?አላት ብሌን ሀኒዬ እኔ ግራ ገብቶኛል ያንተን ውሳኔ ነው የምጠብቀው ምንም ሳልል ነው ከነ ዮኒም ጋ የተለያየንው አንተ ግን የስራ እድሉን እንዴት አየኽው አለችው ..ቶማስ ..የኔ ፍቅር እናቴ አውቃለው ለዚህ ሞያ ያለሽን ክብር ግን አሁን ምንም ልወስን አልችልም አላት ።.
ብሌንም እሽ ችግር የለውም እንሄዳለን የተባለው ከሳምንት በኃላ ነው ስለዚህ አስብበትና ውሳኔህን ትነግርኛለህ እሽ ሀኒዬ አለችው ለስለስ ባለ አነጋገር ሁለቱንም አይኖቹን እየሳመች በስስት እያየችው ""አፍቅርሀለው የብቻዬ"" አለችው ...በድጋሚ ሁለቱንም አይኖቹን ሳም አድርጋ እደርቱ ላይ ልጥፍ አለች ,,,
ቶማስ የስማውን እያብስለስለ ማን አይበለው ታደር ጠዋት ተነስቶ ቁርስ በልተው እሷን ሆቴል ውስጥ ትቶው ወደ ስራው ሄደ ,,ስራ ቦታም ይሄንን ያብስለስል ነበር ,,ቶማስ አብርሀም የሚባል አንድ ወንድ የልብ ጓደኛ አለው ,አብረሀምም እንደ ቶማስ ለስትራ ሀዋሳ መጥቷል,የቶማስ ሁኔታ ያላስደስተው አብረሀም ,ቶማስን ቀርቦ ምን እንደሆነ ጠየቀው ,
ቶማስም ለአብረሀም የተፍጠርውን ሁሉ ነገርው ,አብረሀም ግን ነገሩን ቀለል በማድርግ የምትወዳትና የምታፍቅራትን ሚስትህን የአካልክን ክፍይ ደስታ እንደማየት የሚያስደስትህ ነገር አለን?ብሎ ለቶማስ ጠየቀው አይ ደስታዋን ማየት ያስደስተኛል ካልክ ፍቀድላትና ህልሟን ታሳካ "ፍቅር በእምነት ካልታስር ዋጋ የለውም"አለው ካፍቀርካት ያንተ ብቻ እንደሆነች እመን ,ከዚያም የፍለገችውን እንድታደርግ ፍቀድላት አለው...
ቶማስ አብረሀም ያለውን ሁሉ ከስማ በኃላ "ፍቅርና እምነት "አንድ ናቸው ስለዚህ "እናቴን አፍቅራታለው ስለዚህም አምናታለው ትሂድና ሀሳቧን ታሳካ ሲል ቶማስ ወስነ በቃ ስራውን ሲስራ ቆይቶ ወደ ቤት ከመሄዱ በፊት ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሄዶ ተሳልሞ ፀሎት አድርጎ ወደ ብሌን መንገዱን ቀጠለ....
ብሌን ቀኑን ሙሉ ጨንቋት ነው የዋለው መልሱን መቼ እንደሚነግራትና መልሱ ምን እንደሚሆን እያስበች እያለ ስልኳ ጮኽ ቶማስ ነበር ከክላስ ወጥታ እንድትወርድና እሱ ሆቴል ውስጥ እንደሆነ ምሳ መብላት እንደፍለገ ነገራት ,ብሌንም ስልኳን ዘግታ ልብሷን ለብሳ እየጠበቀችው ስለነበር ከክላስ ወጥታ ወርደች ,..ቶማስን ስላም ብላው ተቀመጠች ምንም አልተነጋገሩም ,ምሳቸውን በልተው ነገ ወደ አዲስ አበባ ስለሚመለሱ ማምሻቸውን ዘና እንደሚሉ ተነጋግርው ከሆቴል መክናቸውን አስነስተው ጉዞ ወደ አሞራ ገደል....
ብሌንና ቶማስ ከአሞራ ገደል ,በጅልባ ለዊ እሪዞርት ,ከለዊ እርዞርት ፍቅር ሀይቅ,ከፍቅር ሀይቅ ሀይሌ እርዞርት ,እንደፍለጋቸው ተዝናኑ በቃ ተደስቱ ,ደስ የሚል ቀን ደስ የሚል ምሽት ,ምሽት ላይ ግን ቶማስ ብሌን እንደጨነቃት ስለተርዳ እራት በልተው ሲጨርሱ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ይዟት ሄዶ ,ወደ ስራዋም እንድትመለስ የብዙ አመት ህልሟን እውን እንድታደርግ መፍቀድን ነገራት ,ብሌን ተንበርክካ የደስታ እንባ አለቀስች ,,..........
ይቀጥላል✍🏼.....
ምዕራፍ 2 በቅርብ ቀን
ከወደዱት ላይክ እና ሼር ሟድረጎን አይርሱ 👉👉
2024/07/01 06:58:55
Back to Top
HTML Embed Code: