Telegram Web Link
ድክመትክን አውቆ ሚቀርብክ ሰው በህይወትክ ውስጥ ረጅሙን ጉዞ አብሮክ ይሄዳል።
አላህ በጀነቱል ፊርደውስ ያስደስትክ
ሰለፊ ኢስላም
ክፍል 1
‹ሰለፊዝም› ምንድን ነው? የጋራ ስምምነት ያለው ትርጓሜ በሌለበት ፣ የዘመናዊውን የሰለፊ ክስተቶች ከጅማሬው አንስቶ በውስጡ ያሉትን ዝርዝር ባህሪያት በመገምገም ፣ በተለያዩ ወቅቶች የነበሩ ቡድኖችን ለመግለጽ አወንታዊው የሆኑ ውይይቶች ቢደረጉ ብዬ አስባለው፤ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥልቅ የሆኑ ግንዛቤዎችን ያመጡ ዘንዳ ።
በዘመናዊው ዓለማችን አውድ ውስጥ ላለፉት ግማሽ ምዕተ -ዓመታት ‹ሰለፊ› የሚለው ቃል በእስልምና የመጀመሪያዎቹን ትውልዶች ምሳሌ በማድረግ የእስልምናን ዘይቤ ለመቀየስ የመጣ አካሄድ ነው። ። ምክንያቱ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ ሦስት የእስልምና ትውልዶች ከሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ከዋሂይ ዘመን ጋር በጣም ቅርብ በመሆናቸው የነብይነት ሱናን በጥሩ ሁኔታ እንዲያዙ ሰፊ እድል ስለነበራቸው ነው።
ከስርወቃሉ እንደምንረዳው የአሠራር ዘዴን ለማመላከት የመጣ እንጂ አንድን የተለየ የማኅበረሰብ ወይም የአማኞች ቡድን ለመግለጽ ነው ተብሎ አይታመንም። በዚህ ቃል ግን የተለያዩ ቡድኖች እራሳቸውን በሰለፊ ማንሃጅ (ዘዴ) ላይ እንደሆኑ በማመናቸው በዚህ ቃል ሌሎች አካላት ሲጠሯቸው ብዙም ተቃውሞ አያሳዩም የዚህን ቃል አጠቃላይ ተፈጥሮኧዊነት የበለጠ በመግለጹ፤ እነሱ ራሳቸው ባይጠቀሙትም እንኳ። ይህንን ካልንም በኋላ፣ ሁሉም የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢዎች ‹የእውነተኛ ሳላፊዝም› ተወካዮች አይደሉም በማለት እያንዳንዱን ቡድኖች እያንዳንዱ ሰው የቃሉን ትክክለኛ አተገባበር ለራሱ ብቻ ማሰቡን ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። ይህ የሆነው ፣ በሰላፊ እስልምና ዘርፎች መካከል የተለያዩ የስምምነት ነጥቦች እና አለመግባባቶች ስላሉ ስለ‹ሰላፊዝም› አጠቃላይ ግንዛቤ ያስፈልጋል።
በዶ/ር ያሲር ቃዲ

ትርጉም ብሩክ ፈቃዱ
በሰለፊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ የጋራ መግባቢያ ሰነዶች
ክፍል 2
እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት ጥቅል መግባቢያዎች ሁሉም ሰለፊ ያለምንም ተቃርኖ የሚስማማባቸው ነጥቦች ናቸው።
1) እነሱ እራሳቸውን የሰለፍ አል-ሷሊህ ትምህርቶችን እና እምነቶችን በትክክል የያዙ እንቁዎች አድርገው ይቆጥራሉ። በተለይም ከእነሱ የተተረጎመውን ሥነ -መለኮታዊ እምነትን ያረጋግጣሉ (በተለምዶ ‹አትሃሪ› እምነትን ›)
2) እንደ ሙእተዚላ እና እንደ አሽʿአሪያህ ያሉ ቡድኖች በሚሰጡት መለኮታዊ ስሞች እና ባህሪዎች (ተውሂድ አል-አስማʾ ዋአል-ሲፋት) ትርጓሜ ለይ ከመቃረን አንስቶ በፍፁም ውድቅ ያደርጋሉ።
3) የፈጣሪን በብቸኝነት የመምለክ መብት (ተውሕድ አሉሉሂያህ) ሙሉ በሙሉ ያረጋግጣሉ እና ይህንን በቀጥታ የሚያበላሸውን ወይም ወደ ጥፋት ሊያመራ የሚችል ማንኛውንም መንገድ በፍጹም ለድርድር አያቀርቡም። ስለዚህ የተወሰኑ የሱፊዮችን የማመሳሰል ልምዶች (እንደምሳሌ እጅግ ቅዱስ አክብሮቶችን ፣ የሙታንን ምልጃ ፣ ወዘተ) ያወግዛሉ።
4) ሁሉንም ፈጠራዎች (ቢድዓን) ይቃወማሉ ከዚያም አልፎ ከሚቅርቡላቸው ነገራቶች (አህል አል-ቢድዓ) ይርቃሉ። በተለይ የሺዓ አስተምህሮ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አላቸው እንድ ምክንያትም በሺዒዝም አስተሳሰብ መሰረት ብዙዎቹ ሶሓቦች ውድቅ ማድረጋቸው ነው።
5) የሼህ አል-ኢስላም ኢብኑል ተይሚያ ሕጋዊ እና ሥነ-መለኮታዊ አስተያየቶችን ያከብራሉ፣ ይወዳሉ። ሆኖም እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት አንኳር ጉዳይ ቢኖር ኢብኑ ተይሚያ የዘመናዊው የሰለፊ እንቅስቃሴ ቅድመ አያት ተደርገው መውሰድ እንደሌለባቸው እና ራሳቸውን ከነብዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ አንድም መስራች እንደሌላቸው አድርገው መመልከታቸው ስህተት መሆኑን ማስተዋል አስፈላጊ ነው።

በዶ/ር ያሲር ቃዲ
ትርጉም ብሩክ ፈቃዱ
ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
ጁሙዐ ቀን ከዐስር በኋላ
================
ኢማም አድ‐ዳረቁጥኒ፣ አልሐፊዝ አስ‐ሰኻዊ፣ ኢማም አል‐ገዛሊ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በጁሙዐ ቀን ሰማንያ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያደረገ ሰው የሰማንያ ዓመት ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል።»
ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዴት ብለን ሶለዋት እናድርግቦት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «እንደዚህ በል አሉ: ‐
" اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ"
«አላሁም‐መ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ዐብዲከ ወነቢይ‐ዪከ ወረሱሊከ አን‐ነቢይ‐ዪል ኡም‐ሚይ‐ይ»

ይህንን አንድ ብለህ ቁጠር።»
:
ሰማንያ ስትሞላ በአላህ መልክተኛ ላይ ሰላምታን በማድረግ ጨርስ። «ሶለ‐ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም» በል።»
ብዙዎቻችን ተሽክመን ስለምንዞረው Ego እስኪ ትንሽ ልበል☺️
ለዚህ ቃል ተስማሚ የሆነ አማርኛ ስርወ ቃል ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር። Ego ማለት ለራሳችን ከፍተኛ ግምት ከመስጠጥም አልፎ በዙርያችን ያለው ሠው ከኛ የተለየ ምንም እውቀትም ሆነ ችሎታ እንደሌለው በአደባባይ ለማሳየት መሞከር ነው። ምናልባት የህክምና ባላሙያዎችን ላስፈቅድና በሽታ ነው ብል ደስ ይለኛል፤ አንዳንዱ በአደባባይ ሊያስወጣ የሚችለው እውቀት ውስን ሆኖ በሰዎች ሞቅታና ሆይሆይታ መድረኩን ሲያገኝ self confidence እና Ego ተምታቶበት እኔ ማለት ኦኮ እያለ የሌለውን ማንነት እኛ ለምናውቀው ማንነቱ ጆሮኧቹ የኔ ካልሆነ የማን ሊሆን? ብሎ በጥሩ ወኔ ውስጥ ተደብቆ ባለው መርዙ ሲለክፈን ይውላል። Ego ሁሌ ደበቅ ብሎ ሚኖር አውሬ ነው፤ ሚሸሸገው ደግሞ የሰው ልጅ በተሰጠው ጸጋ ስር መሆኑ መጠንቀቅ ይገባናል።ለምሳሌ ከሃብት ፣ ከእውቀት ፣ ካለን የሰውነት ጉልበት እና መሰል ጥሩ ነገሮች ነው። ለዚህም አይደል እንዴ አላህ (ሱ ወ) በሃዲሰል ቁድሲ ቁጥር 6 ላይ አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ብለዋል ሃዲሱ ረዘም ስላሚል አጠር አድርጌ ላቅርበው እና በትንሳኤ ቀን ፍርድ ከሚሰጣቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች መካከል ሸሂድ ሆኖ የሞተ ፣ ሃብታም ሆኖ ሲለግስ የኖረ፣ የእውቀት ባለቤት ሆኖ ሲያስተምር ህይወቱን ያሳለፈ ሆኖ ሚገርመው ግን በትግል ወቅት መስዋት የሆነው፣ ሃብታም ሆኖ ቸር የነበረው፣ አዋቂ ሆኖ ሲያስተምር የኖረውም፣ ከፈጣሪው ውዴታ ይልቅ በሰዎች ስለነበረው ቀበሌታ መጨነቁ ታላቁ ጌታ ፊቱን እንዲያዞርብን ምክንያት ይሆናል።
አላህ ይጠብቀን🙏🏻
......ካወቅነው ያላወቅነው ሲበልጥ፣ የተደበቀው ግልፅ ከሆነው የገነነ ጊዜ፣ እይታችን በአይናችን ብሌን ስፋት ያክል ይሆናል።
ብዙ አሻግሮ ማየት ይሰወርብናል እያዩ እንዳላዩ እንሆናለን። መዳረሻውን ሳያነጣጥር የሚተኩስ አላሚ ጥይቱ ለራሱ ሆኖ ሳለ ግን ይተኩሳል.....
ብዙ ልናቃቸው የምንጓጓላቸውን እውቀቶችን ለማወቅ የታደልን አይመስልም ለመራመድ የፈለግናቸውን መንገዶች በእሾህ ያጠርነውስ እኛነን?
በርግጥ ማወቅ ሰው ማንነቱን የሚገነባበት መሳሪያ ነው የሚዳሰሰው አካላችን በምግብ ሲገነባ ድብቁ ማንነታችን ግን ስውሩን እውቀት ይሻል። አንዳንዴ ብዙ ለማወቅ ብዙ ርቀትን መጓዝ ላያስፈልገን ይችላል።በዙሪያችን ያለውን ካስተዋልን በቂ ነው።
ስለየትኛውም የእውቀት ዘርፍ ማውራትን አልሻትኩም። ነገር ግን ሰወችበራሳቸው እውቀትናቸው(ማንነታቸው፣ስነምግባራቸው፣አኗኗራቸው፣ውስጣዊም ውጫዊም ስሜታቸው)ባጠቃላይ ረቂቅ የሆነን መገለጫ ይዘዋል።
መፅሀፍ እና ሰው ተገናኝቶ የሚያሰታርቃቸውም የሚያለያያቸውም ድንበር አለ። ሁላችንም እየሆንን ባለነው ልክ የተመጠነው የሌለን ማብቀል ማፍራትም ስለማንችል ነው።
እንደዐበቃዩ አረም ማለት ነው።አረም ሲበቅል እንክብካቤን አይሻም እንዳሰኘው ይበቅላል።
አስተዳደጉም ብዙ የሚያዛልቅ አይደለም በእንጭጩ እዚያው የቀረ ቢሆን እንጂ
ሲበለፅግ እና ሲፋፋ የታየ አረምም እስካሁን የለም። እኛም በዚሁ አረም የተቃኘ ስነምግባር እና ስነስርአት የተላበስን ተንቀሳቃሽ ......
ለራሳችን አረም የሆነውም እኛ አይደለን?በንቃት ያልጠበቅነው ማንነታችን እየቆየ ሲሄድ የአረሙ እድል ይገጥመዋል።ከዚያም ማስተዋል እምንችለው ባወቅነው ልክ ብቻ ሳይሆን ልናቅ በምንፈልገውም ልክ ጭምር ይሆናል።ማወቅ እየፈለግን የምንሸሻቸው አያሌ እርምጃዎች አሉን። እንዲገባን ፍቃደኛ ያልሆናቸው ደግሞ ብዙዙዙ ናቸው......
ሰው ሰዋዊነቱን የተቀናጀው በእውቀቱ ብቻም አደለም።
አመተላህ (ኡሙል በናት )
አልሐምዱ ሊላህ
****
አባት ሁለት ሴት ልጆቹን ዳረ፡፡ አንዷን ለገበሬ፤ አንዷን ደግሞ ለሸክላ ሠሪ ነበር የዳረው፡፡ ከዓመት በኋላ ሊዘይራቸው ብሎ ከአገሩ ወጣ፡፡ የቤቱ ታላቅ ነበረችና ዚያራዉን ለገበሬ ከዳራት ልጁ ጀመረ፤ እሷ እጅግ በደስታ ተቀበለችው፡፡
“እንዴት ነሽ፣ ኑሮ እንዴት ይዞሻል፣ በምን እየኖርሽ ነው” ብሎ ስለኑሮዋ ጠየቃት፡፡
“ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ ነው ያረሰው፤ እህሉን ደግሞ በብድር ነው የወሰደው፤ አሁን ዘርቶታል፡፡ ዝናብ አየጠበቅን ነው፤ ከዘነበ ኢንሻአላህ ምርቱ ጥሩ ይሆናል፣ ኑሯችንም ይሻሻላል፤ ካልዘነበ ደግሞ አደጋ ዉስጥ ነን፡፡” አለችው፡፡

ወደ ሁለተኛይቱም ልጁ ሄደ፡፡ እሷም እጅግ በደስታ ተቀበለችው፡፡
“ኑሮ እንዴት ነው በምንስ ነው የምትኖሩት” አላት፡፡
“ባለቤቴ በብድር ነው የሸክላ አፈር የገዛው፡፡ አሁን ብዙ የሸክላ ምርት አዘጋጅቶ መድረቁን እየተጠባበቀ ነው፡፡ በየቀኑ ፀሐይ የሚወጣ ከሆነ ምርቱ ይሄድለታል፤ በኑሯችን ላይም ለውጥ ይኖራል፡፡ የሚዘንብ ከሆነ ግን ሸክላው ይበላሻል፡፡” አለችው፡፡
አባት ልጆቹን ከጎበኘ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ እቤት ሲደርስ የልጆቹ እናት ስለ ሁኔታቸው ጠየቀችው፡፡ እንዲህም አላት፡-
“ከዘነበም አልሐምዱ ሊላህ በይ፤ ካልዘነበም አልሐምዱ ሊላህ በይ፤ በሁሉም ሁኔታሽ ዉስጥ አልሐምዱ ሊላህ በይ፡፡”
ይህ የዚህች ዓለም ሁኔታ ነው እንግዲህ፡፡ አንዱ የሚፈልገዉን ሌላኛው አይፈልገዉም፡፡ ላንዱ የተመቸ ለሌላው አይመችም፤ ላንዱ መሰናክል የሆነው ለሌላው የስኬት መንገዱ ነው፡፡

ቢመቸንም ባይመቸንም በሁሉም ሁኔታችን ዉስጥ አልሐምዱ ሊላህ፡፡
በምስጋና አላህ ብዙ ነገራችንን ያስተካክላል፡፡

http://www.tg-me.com/MuhammedSeidABX
አብራሪው ማን እንደሆነ እንኳን ሳናውቅ አውሮፕላን ዉስጥ እንተኛለን፣ ዘዋሪዉን ሳናውቅ መርከብ ዉስጥ ለጥ ብለን እናንቀላፋለን።
ሕይወታችንን ማን እንደሚዘዉረው እያወቅን ተረጋግተን መኖርና መተኛት እንዴት ያቅተናል?።

http://www.tg-me.com/MuhammedSeidABX
የፍካቴ አለቃ

ተስፋ ቆርጣ ነፍሴ አምላኬን ልትረሳ
ደካማ አንደበቴ ሀሜት ስታወሳ
ዓይኔ ተጭበርብሮ በሀራሙ ማሳ

አመፄ ብርታቱ አይሎ ሲኩራራ
ትንፋሼ ታምቆ አንተን በምን ይጥራ
ሸሽገህ ዉሰደኝ ወደ እዝነትህ ቄራ
ወንጀሌን ፊዳ አርገው ልቤ እስኪበራ

ሊቀለኝ ነው መሠል ትልቁ ጎባጣ
መቃናቱ ይሳካል ወዳንተ ብመጣ
ህልሜም ይታረማል ከበፊቱ ጣጣ
ይቅርታህ ያርዘኝ ከጥላህ ሳልወጣ

እዝነትህ መታለች በዉዴታህ ደምቃ
ክለላክ አጅቦኝ ልቤም ተነቃቃ
ነፍሴ ትሠዋልክ የፍካቴ አለቃ
Brook.F
ቤትህ ገብቻለዉ

ጉዞ አንተን ፍለጋ እግሬ የኳተነዉ
መድረሻ ሲፈልግ ሀቅ ድንገት ያዘዉ
ልፋቴስ ግድ የለ ጉልበቴ የዛለዉ

ተጠግኖ አድሯል ቤትህ ገብቻለው
ዙፋን በማርከሴ ይቅርታ እላለው
ከስጦታክ ማዕድ ዉዱን መርጫለዉ

ልቤ ታጥቦልኛል መንበሩ ያንተ ነው
ከእንግዲህ ታዛዥ ነኝ ፀጋህ ነፍሴን ረታዉ
ባርያህ ተመልሷል ቃልህን ሊገዛዉ

እገዛህ ይክበበኝ ሞቼም አርገኝ ህያው
በእዝነትህ ልቅና ፊርደዉስን ብትቸረዉ
ደስታው ጥጉን ነክቶ ጌታዉን አሳቀዉ
ርዕሰ ላጣሁለት ፅሁፍ ሀሳቤን መግለፅ እጅግ ይከብደኛል። በዚህች ዓለም ያለኝን እድሜ አሠብኩና ምንስ አገኘሁ ፣ ምንስ አጥቻለሁ በሚል መንፈስ ታጥሬ ትንሽ ሞነጫጨርኩ። አንዳንድ ፀጋዎች በዋጋ ሊተመኑ ማይችሉ ከመሆናቸውም ጋር መልሠን መላልሰን ብናስባቸዉም የጣዕማቸዉ ለዛ የልብ ብርሀን ነው።
ዛሬ ደግሞ ስለምንድነው ምታወራው ሚል ጥያቄ እንዳለ አዉቃለሁ ..... ብዙ ወንድም እና እህቶቼ ሙስሊም ስትሆን የተሠማክን ስሜት ብታጋራን ብለዉ ይጠይቁኛል? ከመነሻው ተነስቼ ላብራራና አንድ ሠዉ በህይወቱ ከመሚወሰናቸው ከባድ ዉሳዎች መካከል ሀይማኖትን መቀየር ከባድ ዉሳኔ ይመስለኛል .... ለምን?
ሀይማኖት ጥቅል የሆነ የሠዉነት መገለጫ ከመሆኑም ጋር ባንተ ዉስጥ ሚወክለው ማንነት ሠዋች ስምህን ጠርተክ ከምታስተዋዉቃቸዉ ስብዕና በላቀ መልኩ አንተን መግለፁ ነው! ስለዚህ አንተ ከአንድ ሀይማኖት ወደ ሌላ ስትሄድ ብቻህን አትሄድም .... ቤተሠብክን፣ ጓደኛህን፣ ጎረቤትህን፣ ባህልና መንደር ሳይቀር ባንተ ህይወት ዉስጥ ይቀየራል። ወደ እስልምና ስትገባ ሚሠማክን ለመረዳት ያለችው ቅፅበት ፍፁም የተለየች ናት! በቃ እኮ ህልምህ ተሳካ፣ በቃ እኮ ሚዛን ላይ ሆንክ፣ በቃ የባከንክለት ዓለም ማረፊያው አማረ። ምንም ቃላት ላይ ተመፃድቄም ሆነ በአንደበቴ እየተናገርኩ ብዉል ልዪ ስሜት ነዉ፤ያ ረብ የእስልምናን ፀጋ በታላቁ ወር አስታዉሠዉ ከሚጠቀሙት አድርገን።
Forwarded from Minber TV
#ቅኝተ_መጻሕፍት

ዛሬ ምሽት 02:15 በሚንበር ቲቪ!
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን || 2014

★★★★★
📡 የሚንበር ቲቪ ስርጭት በኢትዮሳት
ለመከታተል:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

YouTube👉 https://www.youtube.com/channel/UCQQWZ1IeswjheSTSEXKcQsA

Facebook👉
https://www.facebook.com/minbertv/

Telegram👉
https://www.tg-me.com/minbertv

Website 👉
https://www.minbertv.com/


#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
2024/11/15 09:22:39
Back to Top
HTML Embed Code: