Telegram Web Link
ዓለም ዐይኑን ተክሎ ጆሮውን አቁሞ በጉጉት የሚጠብቀው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል።

አሜሪካውያን ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የሚመራቸውን ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

ሪፐብሊካኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዲሞክራቷ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን አንገት ለአንገት ተናንቀዋል።

ከ1984 ጀምሮ ላለፉት 40 አመታት በተካሄዱ ምርጫዎች ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ማን እንደሚሆን ባስቀመጧቸው ትንበያዎች ተሳስተው የማያውቁት ዕውቁ አሜሪካዊ የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር አለን ሊችማን የአሸናፊነቱን ቅድመ ግምቱን ለዲሞክራቷ ካማላ ሐሪስ ሰጥተዋል፡፡

የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያም የካማላ ሐሪስ የመመረጥ ዕድል 70 በመቶ ነው ብሏል።

ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ፕሮፌሰር አለን ሊችማን እንደገመቱት አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዝደንት ይኖራታል ወይስ ከእሳቸው ግምት በተቃራኒ ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ መንበረ-ሥልጣኑን ይቆናጠጡታል?

አብረን የምናየው ይሆናል!

በዚህ ዘገባ ዙሪያ በመደበኛ የዜና ሰዓታችን ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለስበታለን!
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጎዴ ከተማ እና አከባቢው የአራተኛ ትውልድ ኔትዎርክ አስጀመረ።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ እና አከባቢው የአራተኛ ትውልድ ኔትዎርክ የማስፋፊያ ስራ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዊም ቫንሄልፖት ቀደም ሲል በጅግጅጋና አከባቢው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመሩን ተናግረው አሁን ላይ የማስፋፊያ ሥራው ተጠናቆ በጎዴ ከተማ እና አከባቢው የ4ጂ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቀዋል።

አገልጎሎቱን ያስጀመሩት ሥራ አስኪያጁ "ለዚህች ቀን በመብቃታችን በጣም ደስተኞች ነን" ብለዋል።

ከስልክ አገልግሎቱ በተጨማሪ ገንዘብ መላላክን ጨምሮ የተለያዩ ግብይቶችን በኤምፔሳ መፈጸም መቻሉ ለአከባቢው ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ በ5 ነጥብ5 ሚሊዮን ብር የ100 ላፕቶፕ እና 20 የዋይፋይ ራውተር ከ6 ወር ያልተገደበ አገልግሎት ጋር ለአከባቢው ትምህርት ቤቶች በስጦታ መልክ አበርክቷል።

YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
ያለፈው የጥቅምት ወር ከሌላው ግዜ በተለየ ከባድ የእሳት አደጋዎችን የተስተናገዱበት ወቅት መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ያለቀው የጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ከሌላው ግዜ በጨመረ መልኩ ከባድ የእሳት አደጋዎች የተከሰቱበት ወቅት ሆኖ ማለፉን አስታውቋል።

YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
መቀሌ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ለመሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 811 ተማሪዎችን አስመርቋል።


YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
ብሔራዊ ባንክ የአገር ውስጥና የውጪ ምንዛሪ ኖቶችን ከውጪ ሲያስገባ ወይም ወደ ውጪ ሲልክ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን መውላት እንደማይገደድ የሚጠቅሰው አንቀጽ ጥያቄ አስነሳ።


YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ የሰራውን የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስመረቀ።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ ጨፌ ቆንቦዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ያካሄደውን የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት በዛሬው እለት አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።

ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሰባት አዳዲስ የትምህርት ክፍሎችና ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ቤቱን የተማሪዎች የመቀበል አቅም ማሳደግ መቻሉም ተነግሯል።

የትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቱ በሐዋሳ ፣ በኮምቦልቻ ፣በዘቢዳርና ባቱ ከተሞች ለሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶችን ያካተተ ነው።

በስድስት ወራት የተጠናቀቀው የጨፌ ቆንቦዬ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ቢጂአይ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ላደረገባቸው የማሆበራዊ ኃላፊነት ድጋፎች ውስጥ አንደኛው ነው ተብሏል።

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኸርቬ ሚልሃድ በሐዋሳ ከተማ ያስመረቅነው ትምህርት ቤት የመጪውን ትውልድ ለመቅረጽ የትምህርት ቤቶችን አቅም ለማሳደግና ለማህበረሰቡ ዘለቄታዊ ስራዎችን ለመስራት ያለንን ዓላማ ያሳካንበት ነው ብለዋል።

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ በበኩላቸው ቢጂአይ ዛሬ ያስመረቀው ፕሮጀክት በትምህርት መስክ ለሚሰራው ስራ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን ተናግረው በቀጣይ በጋራ በሰፊው ለመስራት ከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል።

YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የተሽከርካሪ ማቆሚያ የስማርት ፓርኪንግ ሲስተም በሸገር ከተማ በይፋ አስጀመረ።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ በአቅራቢያ የሚገኙ የፓርኪንግ ቦታዎችን ከማወቅ ባሻገር ያልተያዘ የማቆሚያ ቦታን በቀላሉ በመለየት ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያጠፉትን ጊዜ እና ጉልበት ለመቀነስ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ አገልግሎት ለማግኘት፣ ትክክለኛ ተመን ያለው የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር በመፈጸም ከተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ እና ከዚሁ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አለመግባባቶች፣ ካልተገባ ወጪ እና እንግልት ይጠብቃቸዋል የተባለ ሲሆን በቴሌብር የክፍያ ደረሰኝ ለማግኘት ያስችላቸዋልም ነው የተባለው።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ የከተማው አሥተዳደር ሕጋዊ የፓርኪንግ አገልግሎት ሰጪዎችን በአግባቡ ለመለየት እና ወደሕጋዊ ማዕቀፍ ያልገቡትን ለማስገባት፣ ከመኪና ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ህገወጥነቶችን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር፣ የአገልግሎት ሰጪዎችን መረጃ በቀላሉ በኦንላይን በማግኘት ቀልጣፋ አሠራርን እንደሚዘረጋም ተነግሯል።

የስማርት ፓርኪንግ ሲስተሙ ለስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በቴሌብር ሱፐርአፕ ሾፌር መተግበሪያ እንዲሁም ለመደበኛ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ባለሙያዎቹ የፓርኪንግ አገልግሎት ጥያቄን/ትዕዛዝ ለመቀበል የሚያስችላቸው የባለሙያ ሲስተም አለው፡፡

ይኸው አገልግሎት ስማርት የሞባይል ቀፎ ወይም መተግበሪያ የሌላቸው ተገልጋዮች በአጭር ቁጥር መልዕክት አማካይነት አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
2024/11/16 06:42:16
Back to Top
HTML Embed Code: