Telegram Web Link
በሳዑዲ አረቢያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች በሰቆቃ ውስጥ ይገኛሉ ተባለ።
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ከቀዳሚዎቹ አገሮች ተርታ የምትሰለፈው ሳዑዲ ዓረቢያ ኢሰብዓዊውን የእስረኞች አያያዝ ለማሻሻል ቃል ብትገባም በቃሏ አለመገኘቷን ዘቴሌግራፍ በዘገባው ጠቁሟል።
የ1997 የኮንዶሚኒየም ቤት ተመዝጋቢዎች አቤቱታ በ15 ቀናት ውስጥ መፍትሔ ካልተሰጠው ለፓርላማ እንደሚቀርብ ተገለጸ።

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለ20 ዓመታት ቤት ይደርሰናል ብለው የቆጠቡና ከመንግሥት ምላሽ አላገኘንም ያሉ ቢያንስ 67 ሰዎችን አቤቱታ ተቀብሎ እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።
በትግራይ ባለው የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ ባለስልጣናት ጭምር ተሳታፊ መሆናቸውን የክልሉ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

በትግራይ ክልል በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ያለው ወርቅ ከህጋዊው በአራት እጥፍ ይበልጣል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከ ኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ አትልም ሲሉ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ።

ከተፈረመ ከአስር ወር በላይ የሆነው የሃገራቱ ስምምነት ፤ ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቀሌ ከተማ ከንቲባን የማገድ ሥልጣን የለውም ተባለ

የመቀሌ ከተማ ምክር ቤት በፕሪቶሪያው ስምምነት የፈረሱት የትግራይ ክልል ምክር ቤትና የክልሉ ካቢኔ ብቻ በመሆናቸው፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የመቀሌ ከንቲባን ከኃላፊነት የማንሳት ሥልጣን የለውም ብሏል።

YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X
Arts Tv አርትስ ቲቪ
ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከ ኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ አትልም ሲሉ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ። ከተፈረመ ከአስር ወር በላይ የሆነው የሃገራቱ ስምምነት ፤ ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X
አሜሪካ የቻይናን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ፍራቻ መርከቦቿን ፓትሪዮት የተሰኘ ጸረ ሚሳኤል ለማስታጠቅ ደፋ ቀና እያለች መሆኑ ተነገረ።

ይህንን ተከትሎም አሜሪካ መርከቦቿን ጸረ ሚሳኤል ለማስታጠቅ ደፋ ቀና እያለች ነው መባሉ እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ እንዲሉ ውጥረቱን ከፍ አድርጎታል።

YouTube
| Facebook | Instagram | TikTok | X
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” ሽልማት መቀዳጀቱን ተገለፀ። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ  የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር የወደብ ተጠቃሚ መሆኗ የግዴታ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠ/ሚኒስትሩ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚ መሆኗ የማይቀር መሆኑን ዓለም ሁሉ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል።
የተለያዩ መጭበርበሮች በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በኩል እየተበራከቱ መሆኑ ተገለፀ።

ማህበረሰቡ የአገልግሎቱን ትክክለኛ ገጽ በመለየት ከአጭበርባሪዎች እንዲጠበቅ ተገልጿል።
የደሞዝ ጭማሪው እስካሁን ተግባራዊ ያልሆነው የመንግስት ሰራተኞች ዳታ በተገቢው መንገድ ባለመሰብሰቡ ሀብት በተሳሳተ ቦታ እንዳይውል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ከደሞዝ ጭማሪው ባለፈ የዋጋ ግሽበቱን በማረጋጋት እየደገፈ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
2024/11/16 13:33:46
Back to Top
HTML Embed Code: