Telegram Web Link
ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ አረፉ!


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ መምህር የነበሩት እና ፖለቲከኛው ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በ74 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት “ረዘም ላለ ጊዜ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ” ብለዋል።

ከመሞታቸው ቀደም ብለው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ(ኢሶዴፓ) ሊቀመንበር እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።

ፖለቲከኛው በየነ ጴጥሮስ ከ1983 እስከ 1987 በነበረው የሽግግር መንግሥት ወቅት የትምህርት ምክትል ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

አርትስ ቴሌቪዥንም በእኚህ አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ምሁር ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የጤና ይሁንላችሁ!

መልካም በዓል
2024/09/28 08:24:46
Back to Top
HTML Embed Code: