Telegram Web Link
KASAT VOCAL WAV
<unknown>
By a popular demand (as dem say) Acapela for kasat, for all djs out there!!!! Do ur own remix!!
@yohanaoriginal
Channel photo updated
New single Endelebua out now!! Enjoy & share!! https://youtube.com/watch?v=qPwYA9ntN4c&feature=share
YOHANA-ENDELIBUA.wav
27.8 MB
Only for DJs
Wave file
@yohanaoriginal
@djmilla
Endelebua
አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ

(አዝማች) 2x
ላይጠቁም ያንተ ባይ የሷም ሰው ላይገባ
ሳላይ ፍፁም ሌላ ሳይርቅ ከኔ ቀልቧ
ግማሽ በሀሳቧ ሄጄ ለኔም ግማሽ ቀርባ
የኛ ቤት የኛ ነው ነው እንደልቤ እንደልቧ

በግፊት ያልመጣ ፍቅራችን በምልጃ
ሆኖ በኔ በሷ ፍፁም ይሁን ፍርጃ
ከእኔ ከእሷ ውጪ ሳታደርስ ደጇ
ጣልቃም ገቢ ሳይኖር ብለን እንጃ እንጃ

ትቶ ጎረቤቱን ሰው ሊኖር እንደቤቱ
ያስገድደዋል አለም ያስገድዳል እውነቱ
ሁሉም እንደዕውቀቱ ሲሆን ማገር ለቤቱ
ያወጣል ከመንቀዥቀዥ ያዋጣዋልም ቤቱ

ወላጅነት መልካም ጓዳ አልፎ ካልነካን
ወዳጅነት ጥሩ ቤት ካላለካካን
አይቅርብን ያረጉት ቅብጠት ያልነካካን
ላይሰፋን ላይጠበን ነን በልክ የለካን

አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ
(አዝማች) 2x

የራስ መንገድ አይቶ ጎጆ መስራት እንጂ
አብሮ ከማይኖር ሰው ደግሞ ምን ሊረባ ቅጂ
ጀርባስ ለምን ይሰጥ ልሁን ላለ ነጂ
ያበዛ አይን ኑሮ ውሎ አድሮ ከርሞ ሊል እጅ እጅ

ትቶ ጎረቤቱን ሰው ሊኖር እንደቤቱ
ያስገድደዋል አለም ያስገድዳል እውነቱ
ሁሉም እንደዕውቀቱ ሲሆን ማገር ለቤቱ
ያዋጣል ከመንቀዥቀዥ ያዋጣዋልም ቤቱ

ወላጅነት መልካም ጓዳ አልፎ ካልነካን
ወዳጅነት ጥሩ ቤት ካላለካካን
አይቅርብን ያረጉት ቅብጠት ያልነካካን
ላይሰፋን ላይጠበን ነን በልክ የለካን

አይገደን የመጠን ስፋት ጥበቷ
ጎጇችን ግልፅነት ጌጧ ውበቷ

@yohanaoriginal
#ዕረፍት - አዲስ አልበም
ለሰጣችሁኝ ክብር መልስ እንኳን ባይሆን ክብሬን ይገልፅ ዘንድ ለሠው ሳላወራ ለናንተ ለ አድናቂዎቼ ለቀቅኩት።
ከወደዳችሁት እናንተ አጋሩት።
አልበም ከኔ
ማስታወቂያ ከናንተ
https://www.youtube.com/watch?v=olLmJFZLQvE&list=PLcbfJMczr9FHHNW4ZRseAqfFFEDM37aYQ
Forwarded from Radar | ራዳር
⚠️ማሳሰቢያ⚠️

ውድ የራዳር አይድል ታዳሚዎች
ከላይ የተዘረዘሩትን የመጀመሪያ ዙር ምድብ 1 ተወዳዳሪዎች ለመምረጥ ያሉት 5 ቀናት ብቻ ናቸው።

ለሁሉም ተወዳዳሪዎቻችን መልካም ዕድል እንመኛለን!
Coming soon
የካሴት የኦድዮ ስራዎች መሸጫ ቴሌግራም ቦት ብራንድ አምባሰደር በመሆኔ ደስ ብሎኛል፡፡ ይህ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አርቲስቶች ስራዎቻችንን ለአድማጭ የምናደርስበት ተጨማሪ መንገድ ሲሆን ከዩትዩብ የበለጠ ገቢ የማስገኘት አቅም ያለው መሆኑ ደግሞ ልዩ ያደርገዋል፡፡

ምንም እንኳን ዩትዩብን መጠቀም አይቀሬ ቢሆንም የሚወዱትን ባለሙያ ስራ ገዝቶ ማበረታት ለሚፈልጉ እውነተኛ ወዳጆች ግን ይሄ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡

ለአዲሱ አልበም ማቆያ ይሆን ዘንድ እስከአሁን ከለቀቅናቸው ስራዎች ውስጥ ምርጥ 10 ኮሌክሽን ስብስብ ያዘጋጀን ሲሆን ካሴት ቴሌግራም ቦት በመቀላቀል ደስ ያላችሁን መጠን በመክፈል እንደትሞክሩት እጋብዛለሁ፡፡ https://www.tg-me.com/kasetrobot?start=album-19

በቅርብ አዲስ ስራዎችን የምትለቁ ባለሙያዎች ካሴት ቦትንም በተጨማሪ እንድትጠቀሙ እመክራለው፡፡
2024/09/26 04:42:50
Back to Top
HTML Embed Code: