Telegram Web Link
#ነበርኩ_መች_ያድናል


ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
________________

@yemariyam2121
"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፋ" ሆሴዕ 4÷6
በእጮኝነት ጊዜ
፩.ቃለ መሀላ/ ቃልኪዳን በመተጫጨት ጊዜ አያስፈልግም፡፡
✍ቃልኪዳን የሚፈቀደው በቤተክርስቲያን በጋብቻ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡
፪.ለጋብቻ ይሆናል ብለው የተሰጣጡት ስጦታ ካለ በጋብቻ ካልተፈጸመ ስጦታውን መመላለሱ ያስፈልጋል፡፡
፫.ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ሔዋን ሳይደርሱ መተጫጨት መጋባት አይቻልም፡፡
፬.ከስጋዊ ፈቃድ/ከግንኙነት መራቅ አለብን፡፡
✍ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ግንኙነት ዝሙት ነው ንስሐ ያስፈልገዋል፡፡
✍በጋብቻ እስካልተፈቀደለት ድረስ መሳሳምም የተከለከለ ነው ከተፈጸመ ንስሐ መግባት ያስፈልገዋል፡፡
፭.ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አያስፈልግም፡፡ በዛ ከተባለ 2 ዓመት መቆየት ይችላል ከዛ በላይ ባይበልጥ ይመከራል፡፡
❤️ይልቅ ሁለቱም አንድ እንዲሆኑ ዘወትር መጸለይ ያስፈልጋል፡፡

👑የአባቶቻችን ትምህርታቸው ይህ ነው የእነርሱን ትምህርት ብትቀበል ሕይወት ታገኛለህ ካልተቀበልክ ግን ሞትን ወደ ራስህ ታመጣለህ👑 🔥እሳት እና ውሃ ቀርቦልሀል ወደ ፈለግከው እጅህን ስደድ🔥
እኔ ግን ውሃውን ብትመርጥ የተሻለ ነው እልሃለው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤️ለሌሎችም አዳርሱ ላልሰሙ አሰሙ!!!
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@yemariyam2121 ❤️ @yemariyam2121 ❤️
👑👑👑👑👑👑👑
https://www.tg-me.com/yemariyam2121
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!! ""
አንድ ኩስምን ያለች ሴት ወደአንድ መንፈሳዊ
አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው
ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት .... "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ አንድ የቤት ስራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዬይቱም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ሀጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ሀጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እሱን ከነገረሽ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደቤቷ ሄደች።
ተመልሳ እንደማትመጣ ግን ገምተው ነበር አባ ... በበነጋው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴትየዬቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ሀጢያት ምን እንደነበር
ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ ... "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ... "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ... " # እረስቸዋለሁ አለኝ" አለቻቸው ....እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!
የሰው ልጅ ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብየሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል!
እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ! ስንቶቻችን እንሆን እግዚሀርን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ሀጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ሂፆጱ ያጠበውን ሀጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት እሾህ ራሳችንን የምንገርፍ?
ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት ቤት በቀለለ!በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳትኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነውኮ ...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን ... እግዚአብሔር የይቅርታን ልብ ይስጠን!
#ከበሮ - ማለት ከበረው ከሚል የግእዝ ቃልየተገኘ ሲሆን ደፋ፡መታ፡ከረከረ፡ቆረቆረ፡ ጎሰመ፡ማለት ነው፡፡


#ከበሮ - የጌታችን ተምሳሌት ነው፡፡
.የከበሮ ጠፈሩ -ጌታ በአይሁድ እጅ ሲገረፍ የወጣበት ሰንበር ተምስሌት ነው፡፡
.አንድም -ጌታችን የተገነዘበት ገመድ ምስሌ ነው፡፡
.አንድም - የታሰረበትና የተጎተተበት የተሰቀለበት ገመድ ምስሌ ነው፡፡

#የከበሮ_ጨርቅ - ቀይ ጨርቅ መሆን ይኖርበታል
.ቀይ መሆኑ - ጌታ ሲሰቀል ለብሶት የነበረ ቀይ ልብስ ከለሜዳ ተምሳሌት ነው፡፡
.አንድም የከበሮ ጨርቅ -ጌታ የተገነዘበት ጨርቅ ተምሳሌት ነው፡፡
.አንድም ጌታ ሲወለድ የተጠቀለለበት ጨርቅ ተምሳሌት ነው፡፡

#የከበሮ_ማንገቻ - ጌታ አይሁድ ሲጎቱቱት የነበረው ገመድ ምሳሌ ነው፡፡
.አንድም -ጌታ 6666 ጊዜ የተገረፈበት ጅራፍ ምሳሌ ነው፡፡
#ከበሮ ውስጡ ባዶ መሆኑ- የጌታችን መቃብር ምሳሌ ነው፡፡
.ከበሮ አንደኛው ገጹ ሰፊ መሆኑ - ጌታ መለኮቱ ሰፊ መሁኑ የሚያሳይ ነው፡፤
.ጌታ ሁሉን ማድረግ የሚችል አባት መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡
.ዓለምን ሁሉ በእጁ የያዘ ፈጣሪ መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡

#ከበሮ ሁለተኛ ገጹ ጠባብ መሆኑ - አለምን የፈጠረ ጌታ ለኛ ሲል ወደዚህ አለም በዝያች
ትንሽ የበጎች በረት ተወስኖ መወለዱ የሚያስታውስ ነው፡፡

#በከበሮ ውስጥ 7፣5፤3 ጠጠሮች ይቀመጣሉ
.7 መሆኑ- ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን

.5 መሆኑ- የአምስቱ ቅንዋተ መስቀል

.3 መሆኑ- የስላሴ ሰወስትነት
የሚገልጽ ምሳሌ ነው፡፡

#ከበሮ_ሲመታ -አይሁድ ጌታ የመቱት ያገላቱት የገረፉት ያቆሰሉት መሆኑ የሚያሳይ ምሳሌ አለው፡፡

#ከበሮ ስንመታ እነዛ ተምሳሌትዎችን በማስታወስ በማስበ ነው መምታት ያለብን፡፤ ጌታ መድሃኒአለም በትንሳኤ ብርሃኑ በእልልታ ደስ ብሎን እንድናመሰግንበትም አድርጎናል፡፡

#ከበሮ ስናያት ምንም ላትመስለን ይሆናል ነገር ግን እንደተመልከትነው ቡዙ ተምሳሌት ያላት የቤተክርስትያናችን ክብረ ንዋያተ ቅዱሳን የመዝሙር መሳርያዎች አንዱ ነው፡፡

#ስለ_ከበሮ በመጽሃፍ ቅዱስ የተወሰነውን እንመልከት
.መዝ- 80(81)፡2- "ዝማሬን አንሱ ከበሮውን
ስጡ፡፡"
.ዳን - 3፡10 - እዮ -21፡12 - "ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ በእምብልታም
ድምጽ ደስ ይላቸዋል፡፡"
.መዝ -150፡4 - "እግዚአብሔር በከበሮ
አመስግኑ"

#የከበሮ_አመታት ፦
ከበሮ ሲመታ ቀጥ ተብሎ አይመታም፤ መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ይመታሉ ይህም ጌታ
ከሐና ቀያፋ ፤ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ያደረገውን እንግልት ያስታውሰናል።
.ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ ይመታና በፍጥነት ይዘዋወራል ይህም ጌታችንን አይሁድ እንደያዙት
መጀመሪያ በቀስታ እየዘበቱ
ይመቱት ነበር፤ በኋላ ግን ጲላጦስ ተመራምሮ ነፃ ሳያወጣው የሰንበት ቀንም ሳይገባብን ኑ
እንደብድበው የማለታቸው ምሳሌ ነው።
.በማሕሌት ላይ ከበሮው መሬት ላይ ተቀምጦ ሲመታ ጌታችን መሬት ላይ ወድቆ
መንገላታቱን እናስባለን።

#የከበሮ 2 ክፍሎች፦
ከበሮ ስታስቀምጡ ሁልጊዜ ሰፊው አፍ ወደ ላይ መሆን አለበት፤ ትንሹን ክፍል ወደ ላይ
ካስቀመጥን ግን ስህተት
ነው።
ሰፊው የከበሮ ክፍል የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ይህም የጌታችንን የባህርይ አምላክነትና ምሉዕ
በኹለሄ መሆኑን ለሥላጣኑ ወሰን
ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው።
ጠባቡ የከበሮ ክፍል ደግሞ የትስብእት ምሳሌ ነው፤
ይህም ጌታችን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ሥጋን ተዋህዶ መገለጡንና የዮሐንስ
ወንጌልን ያስታውሰናል፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ
ቃልም እግዚአብሔር ነበረ … ቃልም ሥጋ ሆነ” [ዮሐ.1-14]
#ከበሮ የሚለብሰው ልብስ አይሁድ ጌታን ያለበሱት የቀይ ከለሜዳ ምሳሌ ነው።
.በከበሮው ላይ የተጠላለፈው ጠፈር በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌነው።
.የከበሮው ማንገቻ አይሁድ ጌታን የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለችና!!

2

ጽናጽል፡- ጸነጸለ - መታ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሸኩራ ቃጭል እንደማለት ነው፡፡ ከነሐስ፣ ከብርና ከሌሎችም ማዕድን ሊሰራ ይችላል፡፡ ጽናጽል ያማረ ድምጽ ያለው ሆኖ መልክና ልዩ ጌጥ ያለው ሲሆን በጥንት ዘመን ግብጻውያን እግዚአብሔርን ያመሰግኑበት ነበር፡፡

(መዝ150፡5) አሠራሩ ላዩ ቀስተ ደመና ይመስላል፡፡

ከታች መጨበጫው አንድ ሆኖ
የላም ምስል የነበረበት ነው፤ ዕብራውያንም ይገለገሉበት ነበር፡፡

ምሳሌነቱም ፡- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጽናጽል ላይ ቀስተ ደመና መምሰሉ ‹‹እሰይም ቀስትየ በውስተ ደመና››ብሎ በተናገረው መሠረት ነው፡፡(ዘፍ 9፡12) ይህም እግዚአብሔር ለኖኅ የገባለት ቃል ኪዳን ምሳሌ ነው፡፡

አራቱ ዘንጎች በአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ቅጠሎቹ የፍጥረታት ምሳሌ ይኸውም ከአራቱ ባሕርያት የተፈጠሩትን ፍጥረታት ‹‹ሰውንም አላጠፋም ብሎ ቃል ኪዳን እንደገባ ለማሰብ›› መሰላሉ
ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ድንጋይ ተንተርሶ ያየውን መሰላል ምሳሌ ነው፡፡

(ዘፍ 28፡ 11-13)


ሁለቱ ቀጫጭን ዘንጎቹ (ጋድሞች) የመወጣጫው ምሳሌዎች ናቸው፤ ቅጠሎቹ የመላእክት ምሳሌዎች ናቸው፤ በግራና በቀኝ የቆሙት ዓምዶች የብሉይና የሐዲስ ምሳሌዎች ናቸው
፤ሁለቱ ጋድሞች የፍቅረ ቢጽና የፍቅረ እግዚአብሔር ምሳሌዎች ናቸው፡፡

3 የይሁዳን መልዕክት የፃፈው የአስቆሮቱ ይሁዳ ሳይሆን የጌታ ዘመድ የሆነው ይሁዳ ነው የበለጠ ለመረዳት የማቴ ም 13÷55 ያንቡ ።
✥የመንፈስ ድህነት ❖

ቡጽዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ከጻፉት የተራራው ስብከት(Sermon on the Mount) ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ፡፡
“የመንፈስ ድህነት የቀደመ አባታችን አዳም ተፈትኖ ከወደቀበትና ሰይጣን ደግሞ ወድቆ ከቀረበት ሃጢአት እንዴት ራሳችንን እንደምንጠብቅ የሚያስረዳ ነው፡፡ ሰይጣን ታላቅ ለመሆን በመሻቱ እንዲህ አለ ”ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ።” ኢሳ.14፥14 የመጀመሪያ ቤተሰቦቻችንም(አዳምና ሔዋንንም) በተመሳሳይ ራሱ በወደቀበት ሃጢያት ፈተናቸው፤ እንዲህም አላቸው”እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ፡፡” ዘፍ.3፥5
የመንፈስ ድሀነታቸውን በማጣታቸው ምክንያት የመለኮትን አምሳልና አርአያ አጥተዋል፤ ገነትን የመሰለ ቦታ እግዘኢብሔርንም የመሰለ ጌታንም አጥተዋል፡፡ኢየሱስ ክርስቶስም የመጀመሪያ ሃጢያታቸውን(ጥንተ መርገማቸወን) ሊያነፃ መጣ፤ ወደ ቀደመ ቦታቸውም መለሳቸው፡፡ እናም በተራራው ስብከቱ በመጀመሪያው ትምህርቱ እንዲህ አለ፤”በመንፈስ ድሆች የሆኑ በጽኡን ናቸዉ፡፡” ማቴ .3፥ 5 የባሪያን መልክ ይዞ በሰወም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፤ ለሞትም ይሀወም የመስቀል ሞት እንካን የታዘዘ የሆነ” ፊል. 2 ፥7 አርሱ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።” ያዕ.4፥6
በዳዊት ህይወት ውስጥና በመዝሙሮች ውስጥ በግልጥ የመንፈስ ድህነትን እናገኘዋለን፡፡ ሁሌም በመንፈስ ድሃ ስለመሆኑ የአምላክንም እርዳታ ምንኛ እንደሚያስፈልገው ይናገራል፤ ሳያቋርጥ የጌታን እርዳታና ድል ይጠይቃል፤ተመልከት ለአምላክ ምን እንደሚል ”እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ አቤቱ፥ እርዳኝ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ አቤቱ፥ አትዘግይ።” መዝ. 70፥ 5 ዳዊት ታላቁ ንጉስ፣ የጦር ጄኔራል፣ ታላቁ ነቢይ እና የህብቦችሁ ዳኛው ይህንን ቃላት ሲናገር ግሩምና ድንቅ ነው! ታላላቅ ህዝቦች፣ ነቢያት፣ ንግስቶች፣ የሚንበረከኩለት ዳዊት! በፊቱ ነገስታት የሚንቀጠቀጡለት ዳዊት! በአምላክ ፊት ግን ችግረኛና ምስኪን ነው! ወደ ጌታ ሲጸልይ እንዲህ ይላል ”አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ችግረኛና ምስኪን ነኝና።”መዝ. 86፥1 ምንም እንኳን በህዝቡ ውዳሴ ቢጎርፍለትም ራሱን ምስኪንና ድሃ የመንፈስ ድሃና በመከራዎችሁ ምክንያትም ራሱን ምንዱባን አድርጓል፡፡
እግዚአብሔር ከጠፋው ልጅ ጎን ቆሞአል፤ ልጅ ልባል አይገባኝም ባሪያ እንጂ ካለው ጋር፡፡ ነገር ግን ታላቅ ወንድሙ በትምህከተኝነት ወደ ቤት አልገባም፣ወደ ድግሱም አልቀርብም አለ፤አባቱንም በድፍረት ተናገረ፤ ይሄ ድርጊቱ ምክንያታዊ አልነበረም መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ሰው ወደ ቤት መመለስ አልገለፀም፡፡
እግዚአብሔር ድሃውን ቀራጭ እረድቶታል፤ነገር ግን ለኩሩ ፈሪሳዊ ጸሎት”እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤” ሉቃ. 18፥11-14 ላለው ግን መልስ አልሰጠውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ቀራጩ ፃድቅ ሆኖ ወደ ቤት ገባ፡፡
እግዚአብሔር እኛ በራሳችን ሃጢያት ተቀጣን፣”ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤” ሉቃ. 23፥ 41 ካለው በጌታ ቀኝ ከተሰቀለው ፈያታዊ ዘየማን ጎን ነበረ፡፡ የራሱን ሃጢያት እረስቶ ጌታን ሲሳደብ የነበረው በግራ የተሰቀለው ወንበዴ ግን ጠፍቶ ቀርቷል፡፡
አምላክ ራሷን ድሃ ካደረገች ”ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ።” ሉቃ.15፥27 ካለች ከነነዊቷ ሴት ጎን ነበረ፡፡በዚች ሴት ራሷን ማዋረድ(ትህትና) ጌታ በእስራኤል ምድር ያላገኘውን እምነት አግኝቷል፤”አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት።”
በእርግጥም ጌታ የመጣው ለድሆች ነው እንዲህም ይላል ”የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።” ኢሳ.61፥1
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ለእኒዘህ ድሆች ሰዎች ነው፤ ለትእቢተኞች ለኩራተኞች ራሳቸውን ከሌላው ይልቅ ፃድቅ እንደሆኑ ከሚያስቡትና ከሌሎች ጋር ከሚወደዳድሩት ይልቅ! አንዴ ሰይጣን አንድን ፃድቅ በዉዳሴ ከንቱ ሊጥለው ፈተነው እንዲህም አለው “በጎች አነማን ናቸው ፊየሎችስ?” ያም ፃድቅ ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት ”እኔ የማውቀው ከፊየሎችሁ አንዱ እንደሆንኩኝ ነው፤ እግዘኢብሔር በጎችሁን ያዉቃቸዋል፡፡” ዲያቢሎስም በትህትና ፊት መቆም አይቻለውምና ወዲያው በንኖ ጠፋ፡፡
የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።ስለዚህ የዋህና በመንፈስ ድሆች ልንሆን ይገባናል፤ምክንያቱም እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበሩት ቅርብ ነውና፡፡ መዝ 51፥17 መዝ 34፥18”
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን፡፡
ገብርኤል
ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔርን ልጅ
የሚመስል፣ የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን ት.ዳን
3+25 ሕዝ 9÷2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ (የሐዲስ
ኪዳን አስተማሪ)፣ እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር
አደረገ) ማለት ነው፡፡
ከግብሩ በመነሳትም የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ለቅዱስ
ገብርኤል ሌሎች የተፀውኦ ስሞችን ስፕተውታል፡፡
ከነዚህም መሀከል ጥቂቶቹ
ሀ. ብስራታዊው (አብሳሪው) መልአክ -እመቤታችንንና
ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና፡፡
ለ. የአርባብ አለቃ- 3ቱ አለመ መላእክት እየተባሉ
የሚጠሩት ኢዮር ራማ ኤረር የየራሳቸው ክፍል ሲኖራቸው
በራማ ካሉት 3 ክፍሎች (የመላእክት ከተሞች) አንዱ
አርባብ እየተባለ የሚጠራው ሲሆን የዛ አለቃ ደግሞ
ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
3ኛ ጽኑው መልአክ- ‹‹ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረከቦ
ለአምላክነ›› በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ
አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ጸንተን እንቁም በማለት
መላእክትን አጽንቶአቸዋልና፡፡
4ኛ ተራዳዩ መልአክ- ዳን 3÷19-27፣ ዳን 8÷15 ፣ ዳን
9÷21 – 27
5ኛ ሊቀ መላእክ- ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነውና
6ኛ መኑ ከመ አምላክ (ማን እንደአምላክ)
ሀምሌ 19 እና የሊቀ መላእኩ በአል
‹‹ወደዚያ ወደጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውሀው ፍልሃት
እንደንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን
ሃይል አቀዝቅዞታልና›› መፀ.ስንክሳር ሐምሌ 19 እና
ድርሳነ ገብርኤል ሐምሌ 19
ቅዱስ ገብርኤል በአመት ውስጥ የሚከበሩ ሁለት አመታዊ
(የንግስ) በአላት አሉት ታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19፡፡
ሐምሌ 19 ቅዱስ እየሉጣንና ልጇ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን
ያዳነበት እለት ነው፡፡
ገድሉ የተፈፀመው በዘመነ ሰማዕተት ነው፡፡ በወቅቱ
ቂርቆስና ኢየሉጣ የሚባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሚያከብሩ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም
አንጌቤን ነው አባቱ ቆዝምሶ ይባላል እናቱ ኢየሉጣ
በትውልዷ ከአዝማደ ነገስት ነች፡፡ ዲዩቅልጥያኖስ በነገሰ
በ20ኛው ዓመት በክርስቲኖች ላይ ‹‹ቤተክርስቲኖችና
ቅዱሳት መጻህፍቶቻቸው ይቃጠሉ፣ ክርስቲያኖችም
ይገደሉ!›› የሚል አዋጅ አውጥቶ ነበርና በመፍራት እናት
ስለልጇ ስትል ወደ ኢቆንዩን ሸሸች፡፡
መስፍኑ ብሔሩ እለእስክንድሮስ ክርስቶስን ካጂ ለጣኦት
ስገጂ አላት፡፡ እርሷ ግን አይን እያለው የማያይ ጆሮ
እያለው ለማይሰማ አንተ ለቆምከው ምስል አልሰግድም
አለች፡፡ ንጉሱም በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ ቢያስፈራራት
ሀሳቧን ልትለውጥ አልቻለችም፡፡ ህፃኑም ቢጠየቅ እንደ
እናቱ መለሰላቸው፡፡
እሺ አለማለታቸውን ንጉስ ሲረዳ ለወታደሮቹ በብረት ጋን
ውሃ እፍሉ ብሎ አዘዛቸው፡፡ የውሃው ፍላት እንደ ክረምት
ነገድጓድ እስኪነድ ድረስ 42 ምዕራፍ ያህል ይሰማ ነበር፡፡
ወደውሃው ሊከቷቸው ባሉ ጊዜ ቅ.ኢየሉጣ ፈራች ነገር
ግን አጠገቧ ያለው ህፃን ‹‹ቂርቆስ እናቴ አትፍሪ ዳግመኛ
ሞት አንሞትም›› አላት አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ
አምላክ እኛንም ያድነናል ብሎ አፀናት፡፡ ከዚህ በኋላ
በፍፁም ልብ ተያይዘው ከእሳቱ (ውሃ) ገብተዋል፡፡ በዚህ
ጊዜ አናንያ አዛሪያ ሚሳኤልን የተራዳ ታላቁና ገናናው
መልአክ ቅ/ገብርኤል በመካከላቸው ተገኝቶ የፈላውን ውሃ
አቀዝቅዞላቸዋል፡፡
ከውሃ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው አንዳች
ሳይሆን ምዕመናን አዩ፡፡ እነርሱ በሚያመልኩት አምላክም
አምነው ብዞዎቹ በሰማዕትነት አርፈዋል፡፡
‹‹ ቂርቆስ እየሉጣ ያወጣ ከሳት (2×)
‹‹ እኛንም አድነን (2) ገብርኤል ሊቀ መላእክት››
ከእናታችን ከቅድስት ኢየሉጣና ከሰማዕቱ ቂርቆስ
ከታደጋቸው ከቅዱስ አብርኤል ረድኤት ፍቅር ያሳድርብን፡፡
★★ ★በንብ የሚጠበቀው እና አስክሬን የሚሰወርበት ታላቁ ደራ ገላውዲዮስ★★★
የአራት መአዘን ቅርፅ ያለውና ባለ ሦስት ጉልላት የሆነው ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተው በ1540–1559 እኤአ በደገኛው ንጉሥ አፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት ነው።የአፄ ልብነ ድንግል ልጅ የሆኑት አፄ ገላውዴዎስ የግራኝ መሀመድ ግፍ ባንገፈገፋቸው ጊዜ ብዙ ሰራዊት ብዙ ግመሎችንና የሰማእቱን ገላውዴዎስ ታቦት ይዘው ዘመቱ። ወደ አሁኑ የገላውዴዎስ ቀበሌ ከአሁኑ የገላውዴዎስ ቤተ ክርስቲያን በተሰራበት እረጅም ተራራ በደረሱ ጊዜ ግመሎቻቸው ደከሙ የያዙትንም ጦር ይዞ መቀጠል በተሳናቸው ጊዜ ለያዙት ታቦት ለገላውዴዎስ ብጽአት ገቡ (ስእለት ተሳሉ)" ግራኝን ድል ለማድረግ ብታበቃኝ ቤተ ክርስቲያንህን ከዚህ ቦታ ሰርቼ አስቀምጣለሁ" የሚል። የደከሙ ግመሎቻቸውንና ሰራዊቶቻቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ጎንደር አቀኑ በለስም ቀናቸውና በአሁኑ "ግራኝ በር" በተባለው ቦታ ላይ ሲደርሱ ግራኝ መሀመድንድል አደረገው። ቃላቸውንም ጠብቀው የገላውዴዎስን ቤተ ክርስቲያን ተከለ። ብዙ ግመሎችንና ብዙ አገልጋዮችን እንዲሁም የስጦታ እቃዎችን ሰጥቷል።
በቦታው ረጅም ዘመን ያስቆጠሩ ታሪካዊቅርሶች ንዋየ ቅድሳት በተለያዩ ነገስታት የተበረከቱ ስጦታዎች ይገኛሉ። ከነዚህም መካከል የአፄ ቴዎድሮስ ምንጣፍና መከዳ(ትራስ) ፣ የአፄ ገላውዴዎስ ቀንደ መለከትና ሰናፊ(ፈረስ ላይ ሲቀመጡ የሚለብሱት) ፣የግራኝ መሀመድ ካባ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ቤተ ክርስቲያኑን ልዩ የሚያደርገው በሌሎች አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ከትልልቅ ሰዎች በስተቀር በግቢ ውስጥ ማንም አይቀበርም በዚህ ድንቅ ቦታ ግን ይህ አይሰራም እድል ብሎለት በዚህ ቦታ የሚቀበር ወንዶች በስተሰሜን ሴቶች ደግሞ በስተደቡብ ግቢ ውስጥ ይቀበራሉ። ታዲያ ግቢው አይሞላም እንዴ?? የእርስዎ ጥያቄ ሊሆን ይችላል፣ መልሱም አይሞላም ነው እንዴት ካሉ አንድ ሰው ቢያንስ አንድ ሳምንት ቢበዛ ደግሞ አንድ ወር ድረስ ነው ተቀብሮ የሚቆየው ከዛ ማን እና እንዴት እንደተሰወረ ማንም አያውቅም እዚ ጋር (ሰሜን ሸዋ አርባሓራ መድኃኔአለም በታች ካለው ዋሻ ላይ በየቀኑ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ አስክሬኖች ተጥለው ይሄዳሉ) በተጨማሪም አምና ያረፉት ብፁእ አባታችን አቡነ ኤልሳእ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያረፉት በዚህ ታላቅ ቦታ ነው።
ቦታውን ሌላው ለየት የሚያደርገው ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመሰረት አብራ የገባች ንብ አለች አባቶች እንደሚናገሩት ከገባች እስከአሁን የማትራባው ንብ በግቢ በስተቀኝ ትገኛለች የምትሰጠው ማርም ለህሙማን ሁነኛ ፈውስ ነው እንዲሁም ምግብ በልቶ ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን መግባት አይቻልም ደፍሮ የሚገባም ካለ ንቢቱ ፋታ ሳትሰጥ ታባርረዋለች። በቦታው ባለው ፀበል መፍትሄ ስራይ የተባለ ድንቅ መፅሀፍ እየተነበበ ይጠመቃሉ በሽታ ችግር ወዘተ ተጠራርጎ ይጠፋል።
እንደዚሁም ቦታው የሊቃውንት መፍለቂያም ጭምር ነው የዘመናችን አራት አይናው ሊቅ የጎንደሩ የኔታ አክሊሉ ከዛ ቦታ የተገኙ ናቸው።
በአላቸው ታህሳስ 11
ቦታው ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ገላውዴዎስ ቀበሌ ከአርብ ገበያ ወደ እስቴ ሲሄዱ ከ 10 ኪሜ ጉዞ በኋላ ይገኛል።
@yemariyam2121
ኤረር ተራራ
💒የድንግል ማርያም ልጆች💒
📕ኤረር ተራራ📕

⛪የንጉስ ቴዎድሮስ መምጫ⛪

🎙ዮሴፍ ሙሉጌታ እንዳነበበው
2025/02/23 16:41:00
Back to Top
HTML Embed Code: