//ዲያቆን ዳንኤል ክብረት//
+ ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና
ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ክርስትናን መግደል
የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና
ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡ ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች
መቃጠል፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መቆነጻጸል የሚያበቃለት
ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት
ነበር፡፡ ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ክርስትና
እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ እዚህ እሳት ላይ ሦስቱ
ሕጻናት ተጥለው ነበር፣ እዚህ እሳት ውስጥ ቂርቆስና እየሉጣ
ተወርውረው ነበር፡፡ ይኼ እሳት ቅዱስ ፖሊካርፐስን በልቶት
ነበር፡፡ ክርስትና ግን ይኼው አለ፡፡ ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ
ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ
ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን
አይደርሱበትም፡፡ ንብረታችንን ይወስዳሉ፣ እምነታችንን
አያገኙትም፤ እኛን ይገድላሉ፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ
ናት፡፡ ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ
በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ
እናውቅ ነበር፡፡ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› ተብለናልና ተዘጋጅተን
ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረዪስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ
በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን
በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን
በእርጋታ የሚሠራውን ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር
ያውካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡
ዛሬ በምድር ላይ የለኮሱትን እሳት ብዙዎች በሰማይ እነርሱው
ይቀበሉታል፡፡ አይቀርም፤ አምላካችንም ዝም አይልም፡፡
እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን
እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን
ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡፡
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ
መልካም ምሽት ይሁንላችሁ፡፡
ይንን ፅሑፍ የምታነቡ ወይም የምትመለከቱ ሰዎች ወደ channelu join ታደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
✞አሜን✞

አሽተን ማርያም ገዳም ላሊበላ
ይሄን የተቀደሰ ቦታ ፈጣሪ ፈቅዶ ለማየት ለመሳለም፣ በረከትን ለማግኘት ያብቃችሁ።
በጣም ድንቅ ስፍራ የእግዚአብሔርን ጥበብ የምታዩበት የመንፈስ እርካታን እምታገኙበት ቅዱስ ቦታ ነው።
ቦታው በከባባድ ተራራዎች የተከበበች አለቶች እና ታላላቅ ድንጋዮች ሰው ያስቀመጣቸው እንጂ በተፈጥሮ የተቀመጡ አይመስልም።
ጥቅጥቅ ያለ ደን ቁጥቋጦዎች ሞልተውታል
በዚህ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ አባቶች እንደሚገኙና በፆም በፀሎት ለሀገር እንደሚፀልዩ አባቶች ይናገራሉ
እረድኤት በረከቷ ይደርብን
ደጇን ለመርገጥ ያብቃችሁ።🙏🙏🙏
እንደዚህ አይነት ገዳማትን ለህዝበ ክርስትያኑ እናሳውቅ

➕✝️ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ምንድነው? ️✝️➕
➩ 'ኦርቶዶክስ' የሚለው ቃል 'ኦርቶ(Ortho)'ና 'ዶክሲ(doxy)' ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተገኘ ሲሆን 'ኦርቶ' ርቱዕ፥ ቀጥተኛ፥ ትክክለኛ' ማለት ሲሆን 'ዶክሲ' ማለት ደግሞ እምነት፥ ሃይማኖት፥ አስተሳሰብ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ እምነት፥ ትክክለኛ ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ 'ተዋሕዶ' የሚለውም 'ተዋሐደ' ከሚል የግእዝ ግስ ሲገኝ 'መለኮት ከሥጋ ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ' የሚል ትርጉም ያዘለ ነው።
➩ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን 'ኦርቶዶክስ' የሚለውን ስያሜ ያገኘችው በጉባኤ ኒቂያ(325 ዓ.ም) 'ወልድ ፍጡር' ብሎ የካደውን አርዮስንና ትምህርቱን አውግዛ በለየችበት ጊዜ ነው። 'ተዋሕዶ' የሚለውንም 'ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሕዶ ከበረ' የሚለውን ጽኑ የምሥጢረ ሥጋዌ እምነቷን ልትገልጽበት ከጉባኤ ኤፈሶን(431 ዓ.ም) በኋላ ትጠቀምበታለች።
➩ ኦርቶዶክሳዊነት፦ ክርስቶስ ያስተማራትን፥ ቅዱሳን ሐዋርያት የሰበኳትን፥ ሐዋርያዊያን አበው የጠበቋትን፥ ሰማዕታት የሞቱላትን፥ ሊቃነ ጳጳሳት ያቆዩአትን እውነተኛዋን ትምህርተ ሃይማኖት አምኖ መቀበል ነው። ነገር ግን አምኖ መቀበል ብቻ 'ኦርቶዶክሳዊ' አያሰኝም። ሕይወቷን መኖርም ያስፈልጋልና። የባሕር ማዶ ሊቃውንት 'Orthodoxy is not a Noun You call your self, It's Life you Live' ማለታቸው ለዚያ ነው።
➩ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከሌሎች 'ቤተ እምነቶች' የምትለይበት ዋናው ነጥብ 'ሐዋርያዊት' መሆኗ ነው። ከሐዋርያት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላት፥ ሐዋርያዊ ቅብብል ያልተቋረጠባት፥ ሐዋርያዊ ሥልጣነ ክህነት ያላት፥ የሐዋርያት ሥልጣን ወራሽ በሆነው ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ መሆኗ ነው።
➩ አንዳንድ ሰዎች ኦርቶዶክስ መሆን 'የሃይማኖት ተቋም አባል መሆን፥ የድርጅት አባል መሆን' ይመስላቸዋል። ፈጽሞ ስህተት ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ከምድራዊ ተቋምና ከድርጅት አባልነት እጅግ ከፍ ያለ ነገር ነው። ኦርቶዶክሳዊነት በሐዋርያዊ ትምህርት፥ በመንፈሳዊ ሕይወት፥ የክርስቶስ አካል ለሆነች ቤተክርስቲያን ብልቶቿ መሆን ማለት ነው።
➩ እኔ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ፥ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል የቀናውን የአባቶቼን እምነት የማምን፥ በሥርዓታቸው የምመራ፥ በቅድስት ቤተክርስቲያን ያለሁ ነኝ ማለቴ ነው። አንዳንዶች ይህ ሲሰወርባቸው 'ሃይማኖት አያድንም፥ ሃይማኖትን አትስበክ፥ ዋናው ማመን ነው' ሲሉ ይደመጣሉ፥ በእውነት ለእነዚህ ሰዎች ከልቤ አዝንላቸዋለሁ፥ እግዚአብሔር ያብራላቸው።
➕ የኦርቶዶክሳዊያን መመኪያ ቅድስት ድንግል ሆይ ሕይወቴና ኑሮዬ በሙሉ ኦርቶዶክሳዊ ይሆን ዘንድ፥ ከቅድስት ቤተክርስቲያን እንዳልለይ ጸሎትሽና ረዳትነትሽ ዘወትር ከኔ ከደካማው ልጅሽ አይራቅ፥ እናቴ ሆይ! እኔ ኃጢአት ያደከመኝ ልጅሽ ያለ አንቺ ርዳታ በልጅሽ ሀሳብ መጽናት አይቻለኝምና ከኔ አትራቂ። አሜን!!!
@yemariyam2121

አቦዶን ሙሉውን አንብቦት ከጨረሰው ውንድማችን ብዙነህ አስተያየት
በቅድሚያ አባታችንን
ላመሰግን እወዳለሁ ምክንያቱም እረቂቅ የሆነውን የአውሬውን ሴራ ተረድተው ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ በማድረጋችው በጣም በጣም
ሊመሰገኑ ይገባል ይህንንም ሁሉ ያደረጉት ለሰው ልጆች ካላቸው ፍቅር የተነሳ ነው ያዳም
ዘር ሁሉ በአጥፊው መልአክ እንዳይጠፋ ከማሰብ አንጻር ነው ለአባታችን ዋጋቸውን እግዚአብሔር ይክፈልልን እላለሁ !!!
የጥፋቱ ምንጭ የጥልቁ አለቃ
መርዙን እረጨ ተነሳ በቃ
ምህረት የለለው አጥፊ መልአክ ነው
እወቁት እስኪ ስሙ አባዶን ነው
ለኢሎሚናቲ መረብ የሰፋ
መርዝ እየረጨ ህዝብ የሚያጠፋ
የሰለጠነ በብዙ በደል
አወ ! ተረዱት ይህ ነው አባዶን
በወንድም መሀል መርዝን የረጨ
ተዋዶ ነዋሪን ሁሌ እያጋጨ
ጸብ ያነገስ ደም ያፈሰሰ
የንጹሀንን ደም እየላ ሰ
ይህን ያረገ ማነው ቢሏችሁ
የጥፋት መልአክ ይሁን መልሳችሁ
ሰው ፍቅር አጥቶ የሆነው ባዶውን
ነጥቆት እኮ ነው አጥፊው አባዶን
በክብር ተፈጥረንየደም ዋጋ ሆነን
ይህን ሁሉ ክብር ከምንረሳ
አንዳችን ላንዳችንሰይፍ ስናነሳ
እንድህ ንባላ በቋንቋ በጒሳ
አንዱ እየወደቀ አንዱ ሳያነ ሳ
በማይገቡት ገብተንስንጋግር ስናቦካ
የዝህ ሁሉ ምንጩ አባዶን ነው ለካ
ዓለም ያለወትሮው ምነው ጨልማለች
በአጥፊው መልአክ በጣም ተጨንቃለች
ቃሉ የእብራይስጥ ትርጉሙ ጥፋት ነው
የፍጻሜው ዘመን የምጡ ግዜ ነው
እንግድህን በርቱ ቀኑ እየመሸ ነው !!!
##
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክቡር አሜን ይቆየን ይቀጥላል

††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ †††
†††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:-
¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ጌታውን ያጠመቀና
¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:-
ነቢይ:
ሐዋርያ:
ሰማዕት:
ጻድቅ:
ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት:
ጸያሔ ፍኖት:
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::
††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ †††
††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:-
¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
¤መናኔ ጥሪት የተባለ
¤በድንግልና ሕይወት የኖረ
¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::
ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል::
ቅዱስ ዮሐንስ
¤ቁመቱ ልከኛ
¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ
¤የራሱ ጸጉር በወገቡ
¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ
¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር::
ቅዱስ ኤልሳዕ
¤በጣም ረዥም
¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ)
¤ቀጠን ያለ
¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር::
በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት::
ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት::
ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል::
በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል::
††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን::
†††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ)
3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ
†††ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
†††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" †††
(ማቴ. 11:7-15)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

እንቁራሪቶች አብዝተው ስለጮሁ
ሀይቁ የነሱ ከመሰላቸው ተሳስተዋል
፣ ስለክብራቸው ዝም ያሉ አሳዎች ሀይቁ
ውስጥ በብዛት አሉና
ሌላው ኖሮት አንተ የሌለህን
ነገር አትመልከት
ምቀኛና ክፉ ትሆናለህ
አንተ ኖሮህ ሌላው የሌለውን ነገር
ተመልከት አመስጋኝና ታላቅ ትሆናለህ!
ከዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
ሀይቁ የነሱ ከመሰላቸው ተሳስተዋል
፣ ስለክብራቸው ዝም ያሉ አሳዎች ሀይቁ
ውስጥ በብዛት አሉና
ሌላው ኖሮት አንተ የሌለህን
ነገር አትመልከት
ምቀኛና ክፉ ትሆናለህ
አንተ ኖሮህ ሌላው የሌለውን ነገር
ተመልከት አመስጋኝና ታላቅ ትሆናለህ!
ከዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል ገዳም ያሳተመው የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ገድል እንዲህ ይላል፦ ‹‹ሰውም ሆነ እንስሳ ቢታመም በጽኑ እምነት ይደረግልኛል ብሎ አምኖ ያለ ጥርጥር ውኃ አቅርቦ የገድልህን መጽሐፍ በላዩ ላይ አንብቦ የተነበበበትን ውኃ ቢታጠብበት ወይም ቢጠጣ ያለ ጥፋት ፈጥኖ ከደዌው ይፈወሳል፡፡››
‹‹የገድልህ የተአምርህ መጽሐፍ የተነበበትን ውኃ እኔ እንደተጠመቅሁበት እንደ ማየ ዮርዳኖስ አደርገዋለሁ፡፡ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት ውኃ የተጠመቀበት ሰው ቢኖር የሰማንያ ዓመት ኃጢአቱን አስተሠርይለታለሁ፤ ወንዱን የአርባ ቀን፣ ሴቷን የሰማንያ ቀን ሕጻን አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ በተጠመቅሁበት ማየ ዮርዳኖስ እንደተጠመቀ ሆኖለት ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡››
‹‹የገድልህ መጽሐፍ የተነበበትን ማየ ጸሎት በቤቱ ውስጥ ቢረጭ ከዚያ ቤት በረከቴን እመላበታለሁ፤ ተድላን፣ ደስታን፣ ጥጋብን በዚያ ቤት አሳድራለሁ፤ እስከ ዘለዓለም ድረስ በቤቱ ውስጥ የእህል መታጣትና ረሀብ፣ የውኃ ጥማት፣ ተላላፊ በሽታ አይገባበትም፤ ፈጽሜም አላመጣበትም፡፡››
‹‹ቤተክርስቲያንህ ከታነፀችበት፣ ስምህ ከሚጠራበት፣ መታሰቢያህ ከሚደረግበት፣ የተአምርህ ዜና ከሚነገርበት፣ የገድልህ መጽሐፍ ተነቦ ከሚተረጎምበት፣ እኔ በረድኤት ከዚያ እገኛለሁ፤ ከዚያ ቦታ አልለይም፡፡ የገድልህ መጽሐፍ ከሚተረጎምበት ቦታ አጋንንት አይደርሱም፤ ከዚያ ቦታ ሰይጣናት ይርቃሉ፡፡››
ገድል በተነበበበት ውኃ ብዙ ተአምር እንደሚሠራ በተለያዩ የቅዱሳን ገድል ላይ ተጽፏል። ገድል በተነበበበት ውኃ ሙታን ተነሥተዋል፣ ድውያን ተፈውሰዋል፣ የማያምኑ አሕዛብና ዐረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፣ ድኅተነ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ ያገኙ ብዙዎች ናቸው። የአባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን!
ይኽች ዕለት (ሰኔ 2 ቀን) የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ሥጋ ከነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ ሥጋ ጋር በአንድነት የተገኘበት ዓመታዊ የመታሰቢያው ዕለት ናት። የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡