Telegram Web Link
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 16- ዓሥራ ኹለት ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡
+ ዕውቀትን ከልቡ ያፈለቀ የኢየሩሳሌሙ ሰው የአልዓዛር ልጅ ኢያሱ ሢራክ ዐረፈ፡፡
+ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡ ይኸውም በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸውም ባሉ አገሮች ሁሉ ወንጌልን ስለመስበኩና ስለደረሰበት መከራ ስላደረጋቸውም ብዙ ተአምራት ነው፡፡ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡
+ + +

አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ፡- አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ መርሐ ቤቴ ነው፡፡ እንደ እነ ኤልያስና ሄኖክ ተሰውረዋል እንጂ በምድር ላይ ሞትን አልቀመሱም፣ ገና ወደፊት መጥተው በሰማዕትነት ይሞታሉ፡፡ ልደታቸው ሐምሌ 16 ቀን ነው፡፡ የነበሩበት ዘመንም በጻድቁ ንጉሥ በዐፄ ገብረ ማርያም ሐርበይ ዘመን ነው፡፡ ጻድቁን መልአኩ ከሚያገለግሉበት ከወሎ የህላ ሚካኤል ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ወስዷቸው እንዲመነኩሱ አድርጓቸዋል፡፡ የቆረቆሩት ‹‹አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ገዳም›› ወሎ መሐል ተከዜ ውስጥ ይገኛል፡፡ የበዛው ገድላቸው በዝርዝር ተጽፎ አይገኝም፡፡ ተከዜ በረሃ ላይ እጅግ አስደናቂ ትልቅ የአንድነት ገዳም አላቸው፡፡ 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ በዛሬዋ ዕለት ነው የተሠወሩት፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፡- ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡
እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ ‹‹በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን›› እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም ‹‹አይዞሽ አትዘኚ›› አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ ‹‹እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን›› ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ›› አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስታል፡፡ ዛሬ ግንቦት 16 ቀንም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡ ይኸውም በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸውም ባሉ አገሮች ሁሉ ወንጌልን ስለመስበኩና ስለደረሰበት መከራ ስላደረጋቸውም ብዙ ተአምራት ነው፡፡ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡

ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…›› ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ ‹‹ምን ማድረግህ ነው›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው›› ሲለው ዮሐንስም መልሶ ‹‹ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹አዎን›› አለው፡፡ ዮሐንስም ‹‹በከንቱ ደከምክ›› አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ ‹‹አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ ‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..› ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ›› አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ ‹‹ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…›› ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ
ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ ‹‹በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?›› ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ ‹‹እንዴት አድርጌ ልሳልህ?›› ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም ‹‹ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ›› አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡ በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር ‹‹ፍቁረ እግዚእ›› ተባለ፡፡ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል ‹‹ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ›› ተባለ፡፡ ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ ‹‹ወልደ ነጎድጓድ›› ተብሏል፡፡ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ ‹‹ነባቤ መነኮት ወይም ታኦሎጎስ›› ተብሏል፡፡ ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ ‹‹አቡቀለምሲስ›› ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ ‹‹ቁዱረ ገጽ›› ተብሏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡

(ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርሃ ጥር፣ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ፣ የቅዱሳን ታሪክ-30)
✞ የያሬድ ውብ ዜማ

የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሽ በምን አንደበቴ
እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ

ምድርና ሰማዩ ታምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ሥራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሽን በዓይኔ አይቻለሁ
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ

አዝ_________________

የእግዚአብሔር ጥበቡ ባንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽ እንድቆም በምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህተና

አዝ_________________

ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ታምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነሽ ስልሽ እጽናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉን አልፈዋለሁ

መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የያሬድ_ውብ_ዜማ
መዝሙረ ዳዊት {በቴሌግራም}
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••
የጠሩሽ

አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
የበላዔ ሰብ እመቤት
የአምላክ እናት ድንግል አዛኝት
ማርያም ቅድስት (፪)

በቃል ኪዳንሽ ብዙዎች ድነዋል
በምልጃሽም ፈዉስን አጊኝተዋል
የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል(፪)

የእሳቱን ባህር ባንቺ ተሻግረዋል
የሰይጣንን ጾር ባንቺ ድል ነስተዋል
ለሰማያዊዉ ክብር በቅተዋል(፪)

ነፍሳቸውም ጽድቅን አጊኝታለች
ሕይወታቸዉም ባንቺ ትድናለች
ድንግል ሆይ አትጣይኝ ስላለች(፪)

እኔም በአንቺ እታመናለሁ
የአምላክ እናት አሳስቢ እላለሁ
ባማላጅነትሽ እድናለሁ(፪)

እኛም በአንቺ እንታመናለን
የአምላክ እናት አሳስቢ እንላለን
ባማላጅነትሽ እንድናለን(፪)

ምዕመናኑም በአንቺ ያምናሉ
የአምላክ እናት አሳስቢ ይላሉ
ባማላጅነትሽ ይድናሉ(2)

@yemariyam2121
አልረሳዉም ያንን እለት
አልዘነጋም ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነምህረት
ስላለኝ ነዉ ምክንያት
====አዝ ======
ለሰዉ ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
እባዬ በመሬት ከአይኔ የሚፈሰዉ
የቤቴን ገበና ሁሉ ስነግርሽ
አዛኝ ነሽና እራራ ልብሽ
አረሳዉም መቼም ያንቺን ደግነት(2)
ዉለታ አለብኝ ኪዳነ ምህረት
==== አዝ =======
ልቤ በሀዘን ጠቁሮ ዉስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስጎዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብየ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሰምተሽ ፀሎቴን(2)
አልተፀየፍኝም ብቼኝነቴን
==== አዝ ======
እናት የለኝ ብየ ከቶ አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ሰትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊ እናቴ ለጊዜዉ ነዉ ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዬ ነዉ እረ ስንቱን ላዉራ
ማርያም ማርያም ብል አልሰለችሽም (2)
በልቤ ፅላት ስለታተምሽ
=== አዝ ======
ሲርበኝ መተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለዉ ቤቴ በረከት ሆነሻል
ያስጨነቀኝ ጠላት እራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ (2)
ይህንን ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቁሜ

🙏መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን🙏

......................................................................
ደጅ ጠናሁ
ዝማሬ ዳዊት
#ደጅ_ጠናሁ

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
ልቤ ባንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ የታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹኝ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ሰጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
በአውደ ምሕረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችን ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
ኪዳነምህረት እናቴ
የ መዝሙር ግጥሞች
✞ኪዳነምህረት እናቴ✞

ኪዳነምህረት እናቴ አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የፍቅር እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ(፪)

የተገለጠው ብርሃን ከምስራቅ የተወለደው 
በፍቅር ሠንሰለት ታስሮ ዓለምን ሁሉ አዳነው(፪) 

ኪዳነምህረት እናቴ አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የፍቅር እናት ነሽና አስታርቂኝ እኔን ከልጅሽ 
የሰላም እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ

በረሃውን ባሰብኩት ጊዜ የግብፅን የአሸዋ ግለት 
አንቺ ትንሽ ብላቴና ኧረ እንዴት ቻልሽው በእውነት(፪) 

ኪዳነምህረት እናቴ አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የፍቅር እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የሰላም እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ

ዝም ብዬ ይደንቀኛል የአምላክን ሥራ ሳስበው
ምክንያት አንቺን አድርጎ ይህንን ዓለም አዳነው(፪)

ኪዳነምህረት እናቴ አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የፍቅር እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የሰላም እናት ነሽና አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ

መዝሙር
ይልማ ኃይሉ

​​"ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ"
መዝ ፰፱፥፫
በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።
ትንቢተ ኢዮኤል ምዕ. 2 ቁ12-13
አንጎልላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳም
የነገሯትን የምትሰማ ያሰቡትን የምታሳካ
ተአምረኛ ገዳም ናት
ኪዳነ ምህረት ባላችሁበት ፀሎት ልመናችሁን ትስማችሁ🙏🙏
Channel name was changed to «💎የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች»
​​ የሕይወት ምክር

👉 ደካማነትህን አስታውስ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።

👉 የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።

👉 የሰዎችን ፍቅርና ከአንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል የአንተንም ቁጣ ያበርዳል። ሞት እንዳለ ስታውስ ፣እንዲሁም በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው" መክ 1፥14 ማለትን ትረዳለህ።

👉 በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ያኔ ኃጥአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

👉 የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን አስታውስ። በዚህ ከጭንቀቶችህ ሁሉ ትጽናናለህ። ከዘነጋሃቸው ግን ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለውን አስታውስ "ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ። ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።" መዝ 118፥49-50

👉 ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ። በዚህ ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህ በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ " በዋጋ ተገዝግታችኋልና " 1ኛ ቆሮ 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

👉 በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ድያብሎስን ፣ ስራዎቹን ሁሉ ፣ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።

👉 በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

👉 በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው አልፈኸው ሂድ ከእሱም እራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።

👉 ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ ፣ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።

👉 የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ።

👉 እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።

👉 የመንፈስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ በውስጥህም ያለውን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን ። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።

🙏 ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን።

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

#ሼር
Audio
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══
#እኔ_ነኝ😢😢
ለሞቴ መሞትህን ዘንግቼ
በፍቅርህ መዳኔን ረስቼ
ይቅርታህ ደጋግሞ ቢምረኝ
በሀጥያት ሁሌ እንደቆሸሽኩኝ
አለሁኝ ከቃልህ እርቄ ወድቄ
ፍቅርን ስትሰብከኝ ጥላቻን አርግዤ
ይቅርታን ስትሰብከኝ ቂም በሆዴ ይዤ
ቸርነት እንዳደርግ ሁሌ ብትመክረኝ
ራስ ወዳድ ቆንቋና ስስታም የሆንኩኝ
ወንድምህን ውደድ ብለህ ብትለኝም
ጥላቻዬ ገፍቶት ወንድምም የለኝም
ከቶ እንዳትጨነቅ ብለህ አጽናንተህኝ
ዛሬም ጭንቀታም ነኝ ከቶ ተስፋ የለኝ
ማታ ከዳንኪራ ጠዋት ከመቅደስህ
ማዳንህ አጽናንቶ ፍቅርህ ያላደሰኝ
ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ብዬ
ሰው መስዬ ምታይ ሀጥያትን አዝዬ
ሀጥያቴን ሸፍነህ ይቅር ብትለኝም
የወንድሜን ጉድፍ ማየት አልተውኩኝም
ኗሪ መሳይ ከንቱ ቋሚ መሳይ ሟች ነኝ
ከንሰሃ ይልቅ ልብሴን የማጠራ
አምሮ ለመታየት በሰው ልጆች ጎራ
የውልደትህ በአል የስቅለትህ በአል
ሁሌ የማከብር እያልኩ እልል
ሞትህ ግን ያልገባኝ አማኝ መሳይ ከንቱ
ሌላ ማንም አይደል እኔ ነኝ አቤቱ
ይቅር በለኝ🙏🙏
ትንቢት_ስለ_ቴዎድሮስ_ሳልሳዊ_ከድርሳነ_ዑራኤል_የተወሰደ1.pdf
245.9 KB
ትንቢት_ስለ_ቴዎድሮስ_ሳልሳዊ_ከድርሳነ_ዑራኤል_የተወሰደ1.pdf
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ግንቦት 17-ገርዓልታ እና ሐውዜን ላይ እጅግ አስገራሚ ሁለት ታላላቅ ገዳማትን የገደሙት አቡነ ገብረ ሚካኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ የከበረና የተመሰገነ የቆጵሮሱ ቅዱስ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
አቡነ ገብረ ሚካኤል፡- እኚህ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በታላቅ ተጋድሎአቸው ይታወቃሉ፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ ሚካኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማርና አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደሶችን በማነጽ ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እጅግ አስናቂው ገዳማቸው ገርዓልታ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡

ከገርዓልታ በደቡባዊ አቅጣጫ የሚገኘው ይህ የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ገዳም እንደ ደብረ ዳሞ በገመድ ብቻ ከሚወጣው ከአቡነ ገብረ ናዝራዊ ገዳም ጋር የሚዋሰን ሲሆን ገዳሙ ለመድረስ የመኪናውን መንገድ ከጨረሱ በኋላ በእግር አንድ ሰዓት ይፈጃል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ጻድቁ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ብዙ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ የጌታችን የሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውና ጻድቁ ያደርጉት የነበረው የድንጋይ ቆብ፣ መቋሚያቸው፣ የእጅ መስቀላቸውና መጻሕፍቶቻቸው ይገኛሉ፡፡ ሌላው አስደናቂ ነገር ሀገሩ በረሃ ቢሆንም ጻድቁ ከኢየሩሳሌም ዮርዳኖስ ያመጡትና ዋሻው ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ያጠራቀሙትን ውኃ መነኮሳቱ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ውኃው ግን ከዓመት እስከ ዓመት መጠኑ አይቀንስም፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆርዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክና ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በሚሉት ሁለት መጽሐፎቻቸው ላይ እንደጠቀሱት በገዳሙ ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት የምትበራው አንዲት ጧፍ ብቻ ናት፡፡ ጧፏ ነዳ የማታልቅ ስትሆን አለቀች ትቀየር ሳትባል አስገራሚ በሆነ ተአምር ከዓመት እስከ ዓመት ትበራለች፡፡ ሌላኛው የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ከሀውዜን ከተማ በስተደቡብ አቅጣጫ ከአስደናቂው የአቡነ ይምዓታ ጎሕ ገዳም 16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ነው፡፡ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ይሄኛውም ገዳማቸው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂውን ዋሻ ፈልፍለው ከጨረሱ በኋላ ግድግዳውና ዓምዶቹ ላይ የሳሏቸው የሐዋርያትና የቅዱሳን ሥዕላት ከጥንታዊነታቸው በተጨማሪ እጅግ ውብና አስደናቂ ናቸው፡፡ ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ጻድቁ ቅዱሳት ሥዕላቱን የሳሏቸው በሸራ ላይ ሳይሆን በአሸዋማው የዋሻው ፍልፍል ግድግዳ ላይ መሆኑ ነው፡፡
የአቡነ ገብረ ሚካኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +

የቆጵሮሱ ቅዱስ አቡነ ኤጲፋንዮስ:- ‹‹ኤዺፋንያ›› ማለት የመለኮት መገለጥ ማለት ሲሆን ‹‹ኤጲፋንዮስ›› ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ሲሆን ቤተሰቦቹ አንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድኆች ነበሩ፡፡ በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረኃብ ሊያልቁ ሆነ፡፡ ሕጻኑ ኤጲፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና በእናቱ ምክር ሊሸጠው ገበያ አወጣው፡፡ ሊሸጠውም ከአህያው ጋራ ሲጓዝ ፊላታዎስ ከሚባል ጻድቅ ክርስቲያን ጋር ተገናኘ፡፡ ፊላታዎስም ሊገዛው ፈልጎ ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤጲፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ጻድቁ ክርስቲያን ፊላታዎስ ‹‹በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ›› ብሎ በትእምርተ መስቀል አማትቦ በቅፅበት ኤጲፋንዮስን አዳነው፡፡ አህያውንም ‹‹ስለ እኛ በተሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትሞት ዘንድ ይገባሃል›› ብሎ በቃሉ እንዲሞት ቢያዘው አህያው ወዲያው ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም እነዚህን አስገራሚ ሁለት ተአምራት ካየ በኋላ ጻድቁን ክርስቲያን ‹‹በስሙ ተአምራት የምታደርግበት የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው?›› አለው፡፡ ፊላታዎስም ክርስቶስን ሰበከለትና ኤጲፋንዮስ እያደነቀ ሄደ፡፡
ከወራት በኋላ ሀብታም አይሁዳዊ አጎቱ ኤጲፋንዮስን ወሰደውና ገንዘቡን ሁሉ አውርሶት ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ፡፡ የኦሪትን ሕግ ሁሉ እየተማረ ቢያድግም ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም ስሙ ሉክያኖስ ከሚባል ጻድቅ መነኩሴ ጋር ተገናኘ፡፡ አብረው ሲሔዱም አንድ ነዳይ አገኙና ምጽዋትን ጠየቃቸው፡፡ ጻድቁ ሉክያኖስም ገንዘብ ስለሌው የሚለብሰውን የጸጉር ዐፅፉን አውልቆ ለድኃው መጸወተው፡፡ በዚያን ጊዜ የብርሃን ልብስ ከሰማይ ሲወርድለት መላእክት ሲያለብሱት ኤጲፋንዮስ ተመለከተ፡፡ ይህንንም ድንቅ ነገር ከተመለከተ በኋላ ኤጲፋንዮስ ከመነኩሴው እግር ሥር ሰግዶ ክርስቲያን እንዲያደርገው ለመነው፡፡ መነኩሴውም ወስዶ ለኤጲስቆጶሱ ሰጠውና አስተምሮ አጠመቀው፡፡ መመንኮስም እንደሚፈልግ ቢነግረው ‹‹ሀብት ንብረት እያለህ መነኩሴ መሆን አይገባህም›› አሉት፡፡ ከዚህ በኋላ ኤጲፋንዮስ እኅቱን አምጥቶ አስጠመቃትና ገንዘቡን ሁሉ ሸጦ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች መጸወተው፡፡ በተረፈው ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ገዛ፡፡ ከዚህም በኋላ መነኮሰና ለእርሱም ለእኅቱም ለጥምቀት ምክንያት ወደሆነው ስሙ ሉክያኖስ ወደተባለው መነኮስ ገዳም ገባ፡፡ በዚህም ጊዜ ዕድሜው 16 ብቻ ነበር፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሽማግሌውን አባ ኢላርዮስን አገኘውና ሕግጋትን ሁሉ አስተማረው፡፡ ከዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና በተጋድሎ ኖረ፡፡ ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፡፡ ድውያንን ፈወሰ፣ በጸሎቱ ሙታንን አስነሣ፣ ከደረቅ መሬት ላይ ውኃን አፈለቀ፡፡ ያለጊዜውም ዝናም አዘነመ፡፡ ብዙ አይሁዶችንም ተከራክሮና በተአምሩ እያሳመነ አጠመቃቸው፡፡

ከዚህም በኋላ መምህሩ ኢላርዮስ በነገረው ትንቢት መሠረት በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ ብሉይን ከሐዲስ የወሰነ እጅግ ምጡቅ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ፡፡ በሺሕ የሚቆጠሩ እጅግ ጠቃሚ ድርሳናትን ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአፍም በመጽሐፍም እየጠቀሰ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ሊቃውንት ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ›› ይሉታል፡፡ ከደረሳቸው በርካታ መጻሕፍት መካከል ‹‹ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት በዝርዝር የሚተነትን) በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይም አክሲማሮስ በተሰኘው ድርሰቱ ላይ ስነ ፍጥረትን እንዴት አድርጎ እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ እንዳብራራው በቃላት ለመግለጽም አስቸጋሪ ነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ሲያገለግል ኖሮ በ406 ዓ.
ም ዐርፏል፡፡ የዕረፍቱን ሁኔታ በተመለከተ ከዮሐንስ አፈወርቅ ጋር የተገናኘ ታሪክ አለው፡፡ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የነበረችው ጨካኟና አረመኔዋ ንግሥት አውዶክሲያ የድሃ ንብረት እየቀማች ተወስድ ስለነበር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ዘወትር ይመክራትና ይገሥጻት ነበር፡፡ አንድ ቀን አንዱ ድሃ ሄዶ ለዮሐንስ አፈወርቅ ነግሮት ሄዶ ‹‹የድሃውን ንብረት መልሺለት›› ቢላት እምቢ ስትለው ከቤተ ክርስቲያን እንዳትገባና ከክርስቲያኖችም ኅብረት እንዳትቀላቀል አወገዛት፡፡ እርሷም ‹‹ከግዝትህ ፍታኝ›› ብትለውም ‹‹የድሃውን ገንዘብ ካልመለሽ አልፈታሽም›› ስላላት ‹‹በከንቱ አወገዘኝ አባት ያስተምራል እንጂ እንዲህ አያደርግም›› እያለች ታስወራበት ጀመር፡፡ ለቅዱስ ኤጲፋንዮስም ‹‹ዮሐንስ ያለ አግባብ አውግዞኛልና መጥተህ አስፈታኝ አለዚያ ሃይማኖቴን እቀይራለሁ፣ ቤተ ክርስቲያንንም አቃጥላለሁ›› ብላ ላከችበት፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ሄዶ ዮሐንስ አፈወርቅን ‹‹ሰይጣን በልቧ አድሮባታል ያሰበችውንም ያስፈጽማታልና ለአገልግሎታችንም እንቅፋት እንዳትሆን ፍታት›› ቢለው ቅዱስ ዮሐንስም እምቢ አለው፡፡ እርሷም በየከተማው እየዞረች ‹‹ተመልከቱ ዮሐንስ ኤጲፋንዮስንም አወገዘው›› እያለች በውሸት ታስወራ ጀመር፡፡

ቅዱስ ኤጲፋንዮስም እንዲህ ማለቷን አልሰማም ነበርና ከዮሐንስ ጋር በኋላ ተሰነባብተው ሊለያዩ ሲሉ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ለምን በነገሬ ገባህብኝ?›› አለው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ‹‹አልገባሁም›› ቢለው በንግግር ሳይግባቡ ቀርተው ተጣሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ሁለቱም የሚሞቱበት ጊዜና የሚሞቱበት በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሆነ ተገልጦላቸው አንዳቸው ለአንዳቸው ትንቢት ተነጋግረዋል፡፡ ዮሐንስ ኤጲፋንዮስን ‹‹ሄደህ ከቤትህ አትገባም ከመንገድ ላይ አንበሳ ሰብሮ ይገድልሃል›› አለው፡፡ ኤጲፋንዮስም ዮሐንስን ‹‹የእኔን ትላለህ አንተም እንጂ ደግሞ ተግዘህ በከሃዲዮች ተወግዘህ በአንጾኪያ ደሴት ታስረህ ተሠቃይተህ ትሞታለህ›› አለው፡፡

በተነጋገሩትም ትንቢት መሠረት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ወደ በዓቱ ሲሄድ አንበሳ ገደለውና የአንበሳ ሆድ መቃብሩ ሆነለት፡፡ ስንክሳሩ ግን በመርከብ ሲሄድ እንዳረፈ ይገልጻል፡፡ ዮሐንስም በግዞት ታስሮ ብዙ ከተሠቃየ በኋላ ግንቦት 12 ቀን ዐረፈ፡፡ ጨካኟና አረመኔዋ ንግሥት አውዶክሲያም ‹‹ዮሐንስ ኤጲፋንዮስን አውግዞት ወደ ሀገሩ አባሮት በመንገድ ላይ እንዲሞት አደረገው›› እያለች በሀሰት አስወርታ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሆኑትን ሰዎች ሰብስባ ዮሐንስን እንዲያወግዙት ካደረገች በኋላ በግዞት ታስሮ እንዲኖርና ተሠቃይቶ እንዲሞት አድርጋዋለች፡፡
የአባ ኤጲፋንዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + +

የዛሬ ወር ሰኔ 17 የተሠወሩበትን ዓመታዊ በዓል የምናከብርላቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገሪማ በጠዋት ስንዴ ዘርተው ዕለቱን በሰርክ አዝመራውን ሰብስበው በማስገባት ከእርሱ መሥዋዕትን ያሳረጉትና በግራር ዛፍ ላይም በሬዎችን አውጥተው የስንዴውን ነዶ ያበራዩት እንዲሁም ፀሐይን እንደ ኢያሱ ቀጥ አድርገው ያቆሟትና ወንጌልን የጻፉበት ብዕራቸው ዛፍ ሆኖ የበቀለላቸው እጅግ ተአምረኛ አባት ናቸው። እኚህም አባት ዛፎችና ድንጋዮች ተነቅለው ተነሥተው ተከትለዋቸው እየሄዱ ጽድቃቸውን በመግለጥ ‹‹ገሪማ ገረምከኒ›› እያሉ አፍ አውጥተው በሰው አንበት ያመሰገኗቸው ጻድቅ ናቸው፡፡ አምላካቸው የዛሬ ወር ከተሠወሩበት ዕለት ያድርሰንና እንደማር የሚጣፍጠውን ሙሉ ገድላቸውን እናየዋለን፡፡
2025/02/24 23:34:19
Back to Top
HTML Embed Code: