Telegram Web Link
••ዝምብያለሁኝ••


ስም ላውጣልሽ ብዬ
ቃላትን ባሰላ
አጣሁልሽ ፊደል
ሚሄድ ካንቺ ጋራ
ፍቅሬ እንዳልልሽ
ከፍቅር አልፈሻል
ህይወቴ እንዳልልሽ
በጣም ያንስብሻል
ስም ልሰጥሽ ብዬ
ቃላት ስላጣሁኝ
በቃ የኔ ፍቅር
ዝም ብያለሁኝ።
◆━━━✎✦✎━━━◆
                
ሼር አደራ🙏
መልካም የእናቶች ቀን ይሁንልን!

በኮሜንት ላይ ሁላችሁም የእናታችሁን ስም
እየገለፃቹ መልካም ምኞት ተመኙ
😞 ደህና ነኝ

ደህና መሆን ማለት በስቃይ ላይ ስቃይ በህመም ላይ ህመም ማለት ከሆን እውነት ነው ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት እየሳቁ መስሎ ማልቀስ ተደብቆ ማንባት ከሆነ የምር ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት ሰው ሁሉ እያለ እየከፋኝ መደበቅ ከሆነ እውነት ስላቹ ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት ውስጥ እያለቀሰ ልብ እየደማ ከላይ መሳቅ ከሆነ እመን ደህና ነኝ ። 100 ሚሊዮኖች በሞሉበት ሀገር የልብን ሚጋራ የውስጥን ሚረዳ አንድ ሰው እንኳን ማጣት ደህና መሆን ከሆነ ደህና ነኝ ። ግን እውነት ደህና አደለሁም ደህና ነኝ ደህና ነኝ ያበዛሁት ቢያንስ ደህና አለመሆኔ ከገባቹህ ብዬ ነበር...... ግን ሚገባቹ አይመስለኝም
እስኪ እንደኔ ደህና የሆናችሁ ደህና ነኝ በሉ
               
                    . . .
#ፍቅርሽ_ነው . . .

            እሳት ነው ፍቅርሽ ልቤን አነደደው
         የንፋሱ ድምፅሽ ቀልቤን የወሰደው

     በውሁው ማእበልሽ ያመጣኝ አንሳፎ
          ብርሀን ያሳየኝ ጨለማውን አሳልፎ

          ፍቅርሽ ነው ደመና ያራሰኝ በዝናብ
        ጥማቴን አስታግሶ ያወጣኝ ከረሀብ

   አዎ ፍቅርሽ ነው እስትንፋሴ የልብ ምቴ
         ነብሴን ያቆየልኝ ፍቅርሽ ነው እናቴ፡፡

      ♥️
#እናቴ_ሁሌም_ወድሻለው! ♥️
ስንፍና ባንተ አያምርም

ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ቤተሰቦችህን መቀየር አትፈልግም?እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ!

ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም
          ~_~_~ 'አፋልጉኝ' ~_~_~
.
ልቤ አካሉን ነስቶ  መኖር ከጀመረ ፣
በትዝታ አክናፍ  በሀሳብ ከበረረ ፣
አመታት ነጎዱ  ዘመን ተቆጠረ ፡፡
.
ስደተኛዉ  ልቤ ፣
ምፃተኛዉ  ልቤ ፣
እንደወጣ ቀርቷል  ቤት አልተመለሰም ፣
'ራቁቱን ነበር  ምንም አልለበሰም ፡፡
ከሀገሩ ቆንጆ  አንድም አልቀመሰ ፣
በፍቅር ነበልባል  ቅንጣት አልታመሰ ፣
እዛች ጋር አልሄደ  እዚህ አልደረሰ ፡፡
.
ይሄ ታማኝ ልቤን.. .. ..
ከአፍቃሪዉ አካል ጋር   ወስዶ ላገናኘዉ ፣
የልቡ ባለቤት   ወሮታ ከፋይ ነዉ ፡፡
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
ንገሪኝ ካልክ ዛሬም እንደዛው ነኝ

የኔ ደህና መሆን ምን
#ያሳስብሀል
ፍቅር ነው እንዳልል
#ትተከኝ ሂደሃል😔
ደግሞ ድንገት መጠክ
#አዛኝ ያደርግሀል
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
ንገሪኝ ካልክ ግን
አንተን እያሰብኩኝ ዘመናት ቆጠርኩኝ
እኔነቴን ትቼ ባንተ ውስጥ አለሁኝ

አመታቶች አልፈው ዘመናት ቢመጣ
አንተን
#ከማፍቀር ውጭ ለውጥም አላመጣ
ህመሜን ብነግርህ መተህ
#ላታድነኝ
ድንገት እየመጣህ ምነው
#ባታደማኝ
🔥
እንደተለመደው ምርጥና አጓጊ የፍቅር ታሪክ ለመጀመር አስበናል vote በማድረግ አብራችሁን ሁኑ
Anonymous Poll
43%
ደስ ይላል
57%
ቶሎ ይጀምር
​​  ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 1

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by yohannis 

     
    ገና በልጅነቴ ነበር አባቴ ለሀብታም ጓደኛው እኔን እንደሚድረው ቃል የገባለት
እኔ ባባቴ ሀሳብ ባልስማማ አማራጭ አልነበረኝምና ባልፈልገውም ሁለተኛ ጀረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ያባቴ ጓደኛ ከዚህ በኃላ እንድማር ባለመፍቀዱና ካባቴ ጋር በመስማማታቸው እንዳገባ ተወሰነ .....
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ አለሜን ሳላይ አለምሽ ተብሎልኝ ተጋባን...ለመጀመሪያ ቀን ባሌ ቤት ስገባ የእስር ቤት ህይወት አንድ ብዬ መጀመሬን ለራሴ አሰብኩት...

መረረኝም ጣፈጠኝም አማራጭ አልነበረኝምና የቤት እመቤትነት ኑሮ ሳልፈልግ አንድ ብዬ ጀመርኩት.. ..
ቀናቶች ተቆጥረው ወራትን ወለዱ ባሌ ትልቅ ሰው ከመሆኑ ባሻገር ለኔ መልካም ለመሆንና ካለሀብት የሀዘን ኑሮ ሊያወጣኝ ይጥራል... እውነት ለመናገር ክፋ የሚባል አይነት ሰው አይደለም አንዳንዴ ፈገግ ብዬ ካየኝ በደስታ የሚሆነውን ነው የሚያጣው......
የሚጎድልብኝ አንድም ነገር የለም ባዶ የሚባል አይነት ኑሮ ልኑር እንጂ ማንኛዋም ሴት የምትመኘው አይነት የድሎት ህይወት ነው የምኖረው፡፡
ያልኩትንም ነገር በመፈፀም ሆነ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በማሟላት ወደኋላ አይልም ግን እኔ ከአባቴ እኩያ ጋር በፍቅር አብሮ መክነፍ የማላስበው ሆነ...በቃ ጭራሽ የሚሆንልኝን ነገሮች አባት ለልጁ የሚያደረገው እንክብካቤ አድርጌ እስከመቁጠር ደርሻለሁ .....

ከባለቤቴ አቶ ሽፈራው ጋር እስካሁን አንሶላ አልተጋፈፍንም ለየብቻ ነው የምናድረው እንዲህ ፍላጎቴን ማሟላት ከዚህ ከባድ መስዕዋትነት ይጀምራል እኔ ፍቃደኛ ባለመሆኔና ለዚህ ነገር ዝግጁ እስከምሆን እንዲታገሰኝ ስነግረው ቅር ቢለውም ፍላጎቴን አልተቃወመም ለዛም ነው ጥሩ ሰው መሆኑን ባንደበቴ የምመሰክረው ..... ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ እንደሚወደኝ... አንድ ቀን አባቴ ሊጠይቀኝ ሲመጣ እኔ ሌላ ክፍል እንደምተኛ አውቆ በጣም ተበሳጨ..... ይህን አይነት ወርቅ ህይወት ሰጥቼሽ ምን ፈልገሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው አለኝ...... ያባቴ እንደዛ መበሳጨት አልገባኝም......

✎ ክፍል ሁለት  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
  
​​​​​​
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 2

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


    ባለቤቴ እንኳን የሱን ያህል አልተማረረብኝም ነገሮችን ገና መቀበል እንዳልቻልኩና ትንሽ ጊዜ እንዲታገሰኝ ለባሌ ነግሬው መስማማቱን ስነግረው....
እስከመቼ ነው የሚታገስሽ አመት ሊሞላችሁ ምን ቀረ ባይሆን ውለጂና ይሄን ሀብት የሚወርስ ልጅ ሰጥተሽ አስደስችው አለኝ እኔ ብወልድ ሀብቱ የሱ የሚሆን ይመስል ነገሮችን እንደማስተካክል ቃል ገብቼለት ከስንት ጭቅጭቅ በኃላ አሳመንኩት ባሌ ደውሎ የመጨረሻ ልጁ ነገ ከአውስትራሊያ እንደሚመጣ እና የሚያስፈልግ ነገር ካለ ለሰራተኞች ነግሬ እንዲያስተካክሉ በትህትና ጠየቀኝ ፡፡ ሁሉን እንደማሟላና እንዳያስብ ነግሬው አመስግኖኝ ስልኩ ተዘጋ.....ዛሬ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል! በጠዋት ተነስቼ ቤቱ መስተካከልና አለመስተካከሉን ቼክ አደረኩ ፡፡
ምሳ ምን መዘጋጀት እንዳለበት ነግሬያቸው ተጣጥቤ ፀጉሬን ልሰራ ወደፀጉር ቤት ሄድኩ... ከፀጉር ቤት እንደጨረስኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ገዛዝቼ እቤት ስገባ ነበር ባየሁት ነገር ባለሁበት ደርቄ የቀረሁት... ሀይ እንዴት ነሽ ሄዋን አለኝ ደስ የሚል ቃና ባለው ጎርናና ድምፅ.. .. እ..እንኳን ደህና መጣህ  ማክቤል?? አሀ ማክቤል ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋልኝ.... ለደቂቃዎች እጁን ሳለቅ ፈዝዤ በቆምኩበት ቀረሁ... ዋው አባቴ ሚስቱ ቆንጆ እንደሆነች ቢነግረኝም እንደዚህ አልጠበኩሽም ነበር አለ እጁን ከጄ እያላቀቀ...
እ...አመሠግናለሁ እባክህ አረፍ በል መኝታ ቤት ገብቼ መጣሁ ብዬው የመሮጥ ያህል ካጠገቡ ጠፋሁ....
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ የማክቤልን ውበት ከፎቶ ይበልጥ በአካል እንደሚያምርና የኔ ሳየው መደንገጥ እያሰብኩ ነበር ድንገት በሬ የተንኳኳው... ሄዋን... የባሌ ድምፅ ነበር...አቤት አልኩት በድንጋጤ ካልጋዬ እየተነሳው ...
ነይ እንጂ ምሳ እየጠበቅንሽ ነው አለኝና ወደታች ወረደ .... ሊያምርብኝ የሚችለውን ቀሚስ በመምረጥና እራሴን በማስዋብ ጊዜ ወሰደብ...  ልክ ወደ ታች ስወርድ ማክቤል ፊት ለፊት ነበር የተቀመጠው እግሬ ሲተሳሰር ታወቀኝ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ስላስቆየኃቹ ይቅርታ ብዬ ከባሌ አጠገብ ተቀመጥኩ....ባሌ ዛሬም እንደሁልጊዜው አምሮብሻል አለኝ እጄን እየሳመኝ ... ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ ሲያረግ !
ደንግጬ እጄን ከእጁ መነጨኩትና የማክቤልን ገፅታ ተመለከትኩ ምንም አልመሠለውም.... ሚስትህ ቆንጆ ናት አባዬ ለራስህ ታውቅበታለህ አለው እየቀለደ.... ለምን እንደሆነ ባላውቅም በንግግሩ ተናደድኩ ብሽቅ አልኩ በውስጤ.... ምን ነካሽ ሄዋን አንቺ ያገባሽ ሴት ነሽ...አልኩ ለራሴ
ምሳ ተበልቶ እንዳለቀ ማክቤል ማረፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወደክፍሉ ገባ ሳላስበው ባይኔ ተከተልኩት... ቆሞ ሁኔታዬን ሲመለከት የነበረው ባሌ ....
"ዛሬ ደስ ያለሽ ትመስያለሽ "....አለኝ የባሌ ድምፅ ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ... ... ም ..ምምን ተገኝቶ ያው እንደበፊቱ ነኝ.... ል....ልግባና ልረፍ ትንሽ እራሴን አሞኛል አልኩት እየተርበተበትኩ ... ...
መድሀኒት ውሰጅ ምን አልባት ፀጉርሽን ስለተሰራሽ ይሆናል አለኝ ይሆናል ልግባና ልረፍበት ብዬው ወደክፍሌ ሄድኩ.....
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ነኝ .... የማላውቀው የተዘበራረቀ ስሜት ይሰማኛል ደጋግሜ ማክቤልን አስብና ፈገግ እላለሁ.....


          ꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል ሶስት ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
   ​ 
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
#የኔ አዳም❤️

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል😘
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ🤗
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም #ወዴት ነህ?🤷‍♀


           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​​​
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 3

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


በራሴ የባህሪ ለውጥ ግራ ብጋባና ማክቤልን ላለማሰብ ብሞክር ሊሆንልኝ አልቻለም ቀን ከለሊት እሱን ብቻ ነው የማስበው በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለው ቀናቶች ተቆጠሩ፡፡ ማክቤል ያሉት ጓደኞች ውስን በመሆናቸውና እነሱም ከስራ ውጪ ብቻ ስለሚያገኙት አብዛኛውን ጊዜ ብቻውን ነው የሚያሳልፈው አንድ ቀን ታዲያ ወደ ውጭ ስወጣ ስፖርት ሰርቶ ደክሞት በጀርባው መሬት ላይ ተኝቷል በላብ የራሰው ሰፊ ደረቱና ተክለ ሰውነቱ ከከለሩ ጋር ታይቶ አይጠግብም እዛው እንደተኛ ቀና ብሎ እያየኝ እንደምን አደርሽ አለኝ፡፡
ሰላም እንዴት አደርክ ደክሞህ ነው አልኩት አዎ ትንሽ አለ ለመነሳት እየሞከረ በናትሹ በድብርት እኮ ልሞት ነው ላባቴ ልንገረውና ከፈቀደ ምን ይመስልሻል ዛሬ ከእንጀራ እናቴ ጋር ምሳ ውጪ አብረን ብንበላ አለኝ አባባሉን ስላልወደድኩት ቀና ብዬ አይቼው ወደ ውስጥ ልገባ ስል እየሮጠ መጥቶ እጄን ያዘኝ ልቤ በሀይል ሲመታ ይታወቀኛል ፕሊስ እንዳይከፋሽ ለመቀለድ ያህል ነው ይቅርታ እሺ በልምምጥ እሺ ግን ሁለተኛ እንዳትደግመው አልኩት አልደግመውም እና ተስማማሽ አባቴን ላስፈቅደው አለኝ እሱ እንደምንሄድበት ቦታ ይወሰናል አልኩት ቁርስ ላይ ተቀምጠን አባዬ ዛሬ ሚስትህን ባስኮበልልብህስ እቤት መቀመጥ ሰልችቶኛል ብቻዬን ደግሞ ምንም አላውቅም ምሳ አብረን ብንበላና አንዳንድ ነገሮችን አብረን ብናይስ አለው ባለቤቴ ቀና ብሎ ሲያየኝ ምንም አይነት ቅር የመሰኘት ነገር የለብኝም እንደውም ፈገግ ሁላ ብያለሁ ባይሆን የሱ ገፅታ ተቀያይሯል ግን ምንም ማለት ስላልቻለ ባይፈልግም ጥሩ ግን አትቆዩ አለው በውስጤ ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም  እረ ፊቴ ላይ ሁላ ያስታውቃል የማክቤል ውበቱ እርጋታውና ስርአቱ ከቀን ወደቀን ልቤን እየገዛው ነው፡፡ ቁርስ በልተን ስንጨርስ ባለቤቴ ተሰናብቶን ወደቢሮው ሄደ ማክቤልም እስከምንወጣ ጓደኞቼን በስካይፕ ላውራ ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ እኔም ወደ ክፍሌ ገብቼ የምለብሰውን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ የቁምሳጥኑ ልብስ አንድ አልቀረኝም በየተራ ሁሉንም ሞከርኩት በመጨረሻ ያመንኩበትን አዘጋጅቼ ሰአቱ እስከሚደርስ አላስችል ስላለኝ ልዋኝ ወደውጪ ሄድኩ በደስተኝነቴ አደለም ባለቤቴ ሰራተኞቹ ተገርመዋል፡፡ ሁሌም ካጠገቤ የማጠፋውና የሚሠማኝን ሁላ የማልደብቃት አዛለች ሄዋንዬ አለችኝ የሚጠጣ ይዛልኝ እየመጣች ከሷ ጋር ማውራት ደስ ይለኛል እንደ እናት ነው የምታዝንልኝ ወዬ አዙ አመሠግናለሁ አልኳት ብርጭቆዬን እየተቀበልኳት አለሜ ምን ተገኝቶ ነው እንደዚህ በደስታ የከነፍሽው አለችኝ በደስታዬ መደሰቷ ፊትዋ ላይ እያስታወቀ አዙ ብነግርሽ አታምኚም አልኩዋት ከገንዳው ወጥቼ አጠገቧ እየተቀመጥኩ አቤት አቤት ንገሪኝ ልስማው ታዲያ አለች እንደናት እየደባበሰችኝ ከማክ ጋር ለምሳ ልንወጣ ነው አልኳት እንደህፃን እየፈነደቅኩ ኧረ ቆይ ..ቆይ ..ቆይ ..እንዴት ሆኖ አለች ፊቷን ፈታ ኮስተር እያረገች.....


ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
         
🤷‍♂🤷‍♂አዳም ግራ ገባው🤷‍♂🤷‍♂


ሜላትን በfacebook ሞትኩልሽ እያለ
ቅድስትን በviber ባፉ እያታለለ
ሓናንን በSkype ሁሌ እያማለለ
ሳባን በwhat's up እያቀማጠለ
ከለታት ባንዱ ቀን እንዲህ ተፈጠረ...
*
ሜላት ልትመጣ ነው ወዳለበት ስፈራ
ቅድስት ተዘጋጀች ልትሆን ሙሽራ
የሓናን ቤተሰብ አድምቀው ጭፈራ
ጫጉላዋን ለማድመቅ ተዘጋጀች ሳባ
አዳም ግራ ገባው የትኛዋን ያግባ
የሚያደርገው ሲያጣ እኛ channel ገባ
😂😂😂😂😂😂😂

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 4

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


  አዙ ሆነ ማክ ሽፈራውን አስፈቀደ እሱም ተስማማ ደስ አይልም አልኳት እረ እኔስ ምኑም ደስ አላለኝም ሄዋንዬ ምን አስበው እሺ አሏችሁ ጋሼ ለማንኛውም ተጠንቀቂ አለሜ ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ እኔም ተመልሼ መዋኘቴን ጀመርኩ ግን የአዛለችን ንግግር እያሰብኩ ነበር የዛሬው ደስታዬ ምንም ነገር እንዲያጠወልገው አልፈልግም እቤት ገብቼ መዘገጃጀት ጀመርኩ
አንዲት ሙሽራ እንኳን ለሰርጓ እኔ ያባከንኩትን ሰአት አታባክንም በጣም ለማማርና ቀልቡን ለመሳብ የቻልኩትን ያህል ለፋሁ ልክ እንደጨረስኩ በሬ ተንኳኳ ማክቤል ነበር  አልጨረሽም አለኝ ኧረ ጨርሻለሁ አልኩት መኪናው ጋር እጠብቅሻለሁ እሺ መጣው አልቆይም አልኩት የት መሄድ እንደምፈልግ ጠይቆኝ በኔ ምርጫ ወደ አንድ ሬስቶራንት እየሄድን ነው ስትዋኚ ጎበዝ ነሽ አለኝ ድንገት ነበር የተናገረው አባባሉ አስደነገጠኝ እ...የት አየኸኝ አልኩት እንደማፈር እያልኩ ቅድምም ሌላም ቀን አይቼሻለሁ ማን አስተማረሽ አለኝ ትምህርት ቤት እያለን አንድ ዋና በጣም የምትወድ ጓደኛ እንደነበረችኝና እሷ እንዳስተማረችን ነገርኩት አሪፍ ነው እኔም ዋና እወዳለሁ አለኝ እንደዚህ እያወራንና ስለግል ታሪኬ አንዳንድ ነገሮችን እየተጫወትን ደረስን ከመኪናው ወርዶ በር ከፍቶ እጄን ይዞ አወረደኝ
ማክቤል ስርአቱ በጣም ነው የሚገርመው ምሳ እየበላን ድንገት ለምንድነው አንቺና አባዬ የተለያየ ክፍል የምትኖሩት አለኝ ጥያቄው ድንገተኛ ስለሆነ የጎረስኩት ትን አለኝ እንዴ ምነው ጥያቄዬ የዚህን ያህል ያስደነግጣል አለኝ  ውሀ እያቀበለኝ አ..አይ እንደሱ ማለቴ አይደለም አልኩት እና እንዴት ነው አለኝ ለመስማት የጓጓ በሚመስል ድምፅ?
እስኪ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ አለኝ ተመቻችቶ እየተቀመጠ ያለውን ነገር በግልፅ ነገርኩት ላባቱ የሚሰማኝ ነገር አባት ለልጁ ከሚያደርገው እንክብካቤ ያልዘለለ እና የኔም እዛ ቤት ኑሮ ከስር ቤት ያልተናነሰ መሆኑንም ጭምር በሀዘኔታ እያየኝ አይዞሽ እሺ አለኝ ከዚያ ሌላ እኔን የሚያፅናናበት መንገድ የለምና እሺ አልኩት አንገቴን ደፍቼ እንዴ ከድብርት እንድታሶጭኝ ይዤሽ ብመጣ ጭራሽ ልታስደብሪኝ ነው እንዴ አለ ለመቀለድ እየሞከረ ይቅርታ አልኩት ፈገግ ብዬ ታዲያ አሁን የት እንሂድ ዛሬ በአንቺ ምርጫ ነው አለኝ ዛሬ የምትለዋ ቃል ሌላም ጊዜ አብረን እንደምንወጣ ተስፋ ሰጠችኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱን እያስፈቀድን አንዳንዴ ዝም ብለን እየወጣን መዝናናቱን ተያያዝነው ሲለንም እያመሸን መግባት ጀመረናል በቃ የማንሄድበት ቦታ የለም ከማክ ጋር ስሆን ሁሉን ነገር እረሳለሁ ህይወቴ በደስታ ተሞላች ቅልጥ ያለ ፍቅር ይዞኛል ቀንም ሌሊትም የማስበው ስለማክ ብቻ ሆኗል
ማክም ፍቅር ሳይዘው አይቀርም......



✎ ክፍል አምስት ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
#የኔ አዳም❤️

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል😘
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ🤗
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም #ወዴት ነህ?🤷‍♀

           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 5

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


  የምገዛቸውንም ሆነ የምለብሳቸውን ልብሶች የሚመርጥልኝ የፀጉር ስታይሌን የሚመርጥልኝ እሱ ሆኗል የማክ አባት ጭራሽ ባሌ መሆኑን እረስቼዋለሁ አንድ ቀን አምሽተን ከውጪ እንደገባን ከመኪና ሳንወርድ ሄዋኔ ብሎ ጠራኝ ወዬ ማክ አልኩት በፍቅር እያየሁት ነይማ የሆነ ነገር አለ ፀጉርሽ ላይ አለኝ ወደኔ እየተጠጋ ወደሱ ስቀርብ ድንገት ሳመኝ በደስታ ልሞት ምንም አልቀረኝም ጉንጮቼ ቀሉ ሲያልበኝ ይታወቀኛል ክፍሌ ገብቼ በደስታ አልጋዬ ላይ ዘለልኩኝ ወንድ ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ነው እሱም ብቻ ሳይሆን እኔ የምወደው ቀን ከሌሊት የማስበው ማክ እኮ ነው የሳመኝ!!! በደስታ የምሆነውን አጣው ልብሴን ቀይሬ ለመተኛት ብሞክር አልቻልኩም የማስበው ማክንና የማክን የመጀመሪያ ኪስ ብቻ ነበር ድንገት መደወልና ድምፁን መስማት ፈለኩ ልደውል ስል ደውዬ የምለው ነገር ግራ ገባኝ ስልኬን ይዤው ለብዙ ደቂቃዎች ማሠብ ጀመርኩ በመሀል ስልኬ ጠራ ማክ ነበር ሴኮንድ አላባከንኩኝም ማክ አልኩት ወዬ አልተኛሽም እንዴ አለኝ እንቅልፍ እንቢ አለኝ አልኩት ለምን ምን እያሰብሽ አለኝ አንተን አልኩት ድንገት ከአፌ ያመለጠ ቃል ነበር ስለኔ ምን አለኝ አፍሬ ዝም አልኩት እኔም ስላንቺ እያሰብኩ ነበር
የዛን ቀን ለረጅም ሰአታት አወራን ሌሊቱ አላልቅ ብሎኝ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ማክን እያሰብኩ ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ አሸለበኝ ጠዋት የአዙ ድምፅ ነበር ያነቃኝ  ሄዋንዬ ዛሬ ተኝተሽ ልትውይ ነው እንዴ አለችኝ መጋረጃውን እየከፈተች በይ ተነሽ አለችኝ የለበስኩትን እየገለጠች በግድ አይኔን ገልጬ እንዴት አደርሽ አዙ አልኳት ለመነሳት እየተንጠራራው እግዛሄር ይመስገን ጎሽ ተነሽ! ጋሽዬ ለቁርስ እየጠበቁሽ ነው አለች ልነሳ የነበረው እንደዛ ስትለኝ ተመልሼ ተኛሁ በግድ አስነሳችኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሄድኩ ትላንት የሆነውን እየፈነደኩ ነገርኳት
አንቺ ልጅ እኔ አላማረኝም አለች የመከፋት ፊት እየተነበበባት እኔ ንግግሯን ከምንም ሳልቆጥር አዙ ደግሞ ዝም ብለሽ ታካብጂያለሽ አልኳት የምለብሰውን እየመረጥኩ አዙ ይሄ ያምራል ወይስ ይሄ አልኳት በሁለት እጆቼ የያዝኩትን ልብስ እያማራጥኳት ኤዲያ እኔ ምኑም አላማረኝም አንዱን ልበሽና ይልቅ ተከተይኝ አታስጠብቂያቸው ብላኝ ጥላኝ ወጣች እኔ እየዘፈንኩና በደስታ እንደ ህፃን እየፈነደኩ ወደታች ስወርድ የማክ አባት ፊት ተቀያይሯል ምነው ደና አይደለህም እንዴ አሞሀል አልኩት መልስ የለም ዛሬ ከቤት እንዳትወጪ አለኝ ማስጠንቀቂያ በሚመስል ድምፅ እንዴ ለምን አልኩት ግራ እየተጋባው ባልሽ መሆኔን ላስታውስሽ አለኝ ቀና ብሎ ያልተለመደ ፊት እያሳየኝ በዚህ መሀል ነበር ማክ እንደምን አደራቹ እያለ የወረደው የማክ አባት ምንም ሳይመልስ ከተቀመጠበት ተነስቶ ያልኩሽን እንዳትረሺ መልካም ቀን ብሎኝ ወጣ
ማክ ግራ በመጋባት እያየኝ ምን ሆኖ ነው ተጣለቹ አለኝ ያለኝን ነገርኩት ማታ ስስምሽ አይቶ ይሆን እንዴ አለኝ ባባቱ ሁኔታ ግራ እንደተጋባ እ ይሆናል አሁን ምን እናድርግ አልኩት ትንሽ እስከሚረጋጋ በቃ አንወጣም ነገሮችን እናስተካክላለን አይዞሽ አለኝ ተነስቶ በድጋሚ እየሳመኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱ እስኪረጋጋ ከቤት ባንወጣም ግን አንድ ላይ ሆነ የምናሳልፈው ሁለታችንም በፍቅር ከንፈናል አባቱ ሲመጣ ፊት ለፊቱ እንደበፊቱ እናወራለን ግን በቃ ቤቱን በአንድ እግሩ ስናቆመው ነው የምንውለው የቤቱም ሰራተኞች በእኛ ሳይድ ነበሩና ማንም ለማን ምንም አይናገርም ነበር እኛ በድብቅ ፍቅራችንን እያጣጣምን ነው ከማክ ጋር ከመሳሳም ውጪ ምንም አናደርግም ሲውል ሲያድር በድብቅ አንድ ቀን እኔ ጋር ሌላ ቀን እሱ ጋር ነው የምናድረው እስከምንጋባ ምንም ላናደርግ ወስነናል በቃ በጣም የሚያስቀና ፍቅር ውስጥ ገብተናል ማክ ወደ አውስትራሊያ ላለመመለስ ከተመለሰም አብረን እንደሆነ ወስኗል
አንድ ቀን እሁድ የማክ አባት እንደሚፈልገኝ በአዙ በኩል ልኮብኝ ስሄድ በረንዳ ላይ አኩርፎ ተቀምጧል ሄዋን አለኝ የሆነ ቁጣ ባዘለ ድምፅ አቤት አልኩት ምን ሊለኝ ነው በሚል ፍራቻ እንደተጋባን ዝግጁ አይደለሁም ምናምን በሚል ተራ ምክንያት እስካሁን ለብቻሽ እየተኛሽ ነው እኔም ስለምወድሽና ስሜትሽን ላለመጋፋት ታግሼሻለሁ አሁን ግን የሚበቃ ይመስለኛል የማሰቢያ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ ካልሆነ ግን ወደ ነበርሽበት ህይወት ትመለሻለሽ አለኝ ዛቻ ባዘለ ድምፅ ንግግሩ አናዶኝ ልሄድ ስል አልጨረስኩም አለ ቆጣ ብሎ ከልጄ ጋር ያለውን ነገር የማላውቀው እንዳይመስልሽ ከዚህ ቤት ብወጣ እሱ አለልኝ ብለሽ ከሆነ እንዳታስቢ ሁሉን ነገር አሰቤበታለው ደግሞ ማክቤል ለአንቺ የሚሆን ልጅ አይደለም አባትሽን በማታገኚው ነገር ላይ ተማምነሽ እንዳታሳዝኚው የአባትሽ ከባድ ሚስጥር በእጄ ላይ ነው አለ አንቺ አይሆንም የምትይ ከሆነ ባባትሽ ፈርደሽ ነው አለኝ.....

✎ ክፍል ስድስት ️ ......  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 6

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ አምላኬ ሆይ አንተ ትግስቱን ስጠኝ አልኩኝ በውስጤ ደስታዬ ላይ ውሀ ቸለሰበት ክፍሌን ዘግቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ምንድነው የማረገው አሁን ለማክ ልንገረው ወይስ ይቅር እያልኩ ሳስብ ማክ ደወለ ሄዋንዬ እስካሁን ተኝተሻል እንዴ አለኝ ገና መነሳቱ ነበር አይ ቆየው አልኩት ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ በስልክ አይሆንም ናና እናወራለን አልኩት ደቂቃ አልፈጀበትም ነበር አባቱ ያለውን ስነግረው በጣም ደነገጠ ምን ማድረግ እንዳለብን እያሰብን በቃ አይዞሽ አንቺ ብቻ አትከፊ መፍትሔ አናጣም አለኝ
ድንገት ለምን አባትሽ እና አባቴን የሚያስተሳስራቸውን ነገር አባትሽን አጠይቂውም ከዛ በምንችለው መንገድ ዶክሜንቱን መውሰድ ከዛ በኃላ ያለውን ነገር እንጋፈጣለን አለኝ አባቴ ለነገሮች ድብቅና ሀይለኛ እንደሆነ ባውቅም በማክ ሀሳብ ተስማማው ጥሩ በቃ ዛሬ ከአባቴ ጋር እናወራለን አልኩት ተነስቼ እንድተጣጠብና አባቴ ጋር አብረን እንደምንሄድ እሱ ውጪ እንደሚጠብቀኝ ተነጋግረን እሱም ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡
በተባባልነው መሠረት ወደ አባቴ ጋር ለመሄድ ስንወጣ የማክ አባት ወዴት ነው አለን ከላይ መኝታ ቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ
እንዴ አባዬ አለህ እንዴ አለው ወደ አባቱ እየተመለከተ አዎ አለው ወዴት ነው አለ ደግሞ እየጠየቀ ምን ትላንት ለሰው መስጠት የነበረብኝ እቃ ነበር ቦታውን ስላላወኩት አሁን ሄዋንን አሳይኝ ብያት እሺ ብላኝ እየሄድን ነው እንዳለህ አላወኩም ነበር አለው ጥሩ ቶሎ ተመለሱ አለው ፊቱ ሳይፈታ ዋናው መፍቀዱ ነው አልኩ ተመለሽ የሚለኝ መስሎኝ በጣም ፈርቼ ነበር ከግቢ እንደወጣን ተረጋጊ የኔ ቆንጆ ብሎ ሳመኝ
ማክ ፈራሁ አልኩት እጁን አጥብቄ ይዤ
አትፍሪ ምንም አይመጣም መቼም አንለያይም ካልሆነ እንጠፋለን አለኝ ለመቀለድ እየሞከረ እስኪ አትቀልድ ለራሴ ጨንቆኛል አልኩት አይዞሽ የኔ ቆንጆ ሁሉም ይስተካከላል አለኝ አባቴ ቤት ደረስን አናግረሻቸው ነይ አለኝ ማክ እሱም ጨንቆታል አባቴ ቁጭ ብሎ ስልኩ ላይ ካርታ ይጫወታል አባዬ አልኩት እንዴ ሄዋኔ ምን እግር ጣለሽ ለምን መጣሽ አለኝ ቀና ብሎ እየሳመኝ እንዴ እንደዚህ ይባላል እንዴ አልናፍቅህም አልኩት አይ እንዴት ሳትነግሪኝ ብዬ ነው አለኝ ምንም ሳይመስለው አባቴ ለኔ ግድ የለውም ሁሌ ይገርመኛል እናቴ ከሞተች በኃላ ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው ያደኩት
ፈልጌህ ነበር አባ አልኩት አሁንም ቀና ብሎ ሳያየኝ ምነው በሰላም አለኝ  አዎ ምንድነው አቶ ሽፈራው አንተን የሚያስፈራራበት ሚስጥር ምንድነው አልኩት የሰማውን ማመን አልቻለም በጣም ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለና አንቺ እንዴት አወቅሽ ሊመታኝ በሚመስል ሁኔታ አፍጥጦ እንዴ አባ የዚህን ያህል ከባድ ሚስጥር ነው እንዴ ለኔ ለልጅህ የማይነገር ?? አልኩት ልጅ ያሳጣሽ ዝም በይ ብሎ ጮኸብኝ ሁኔታው በጣም ነበር የሚያስፈራው ምንም ሳልተነፍስ ጥጌን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ ነኝ አባቴ በንዴት ቤቱን እየዞረው ነው ድንገት ቆም ብሎ ቆይ አንቺ በመሀላችን ሚስጥር እንዳለ በምን አወቅሽ አለኝ ስሩ እስጊገተር እየጮኸ
እ ....ያው ሽፈራው ነው የነገረኝ አልኩት እየተንቀጠቀጥኩ እኮ እንዴት አለኝ አይኑን እንዳፈጠጠ እ ...አብረን መተኛት አለብን ነው የሚለው አልኩት ቃላቱን ለመጨረስ እየፈራው ያባቴ ንዴት ይባስ ጨመረ እና ለምን አተኝም ታዲያ ያገባሽ የቤቱ ጌጥ ሊያረግሽ ኖሯል አንቺን ቤቱ አስቀምጦ የሚቀልብበት ምንም እዳ የለውም ትሰሚኛለሽ ምንም ጊዜ ሳታባክኚ አሁኑኑ ሄደሽ ይቅርታ ጠይቀሽ የሚልሽን ካለምንም ድርድር ፈፅሚ አለኝ ቁርጥ ባለ ድምፅ ጌታዬ ሆይ መፍትሔ ፍለጋ መጥቼ ጭራሽ አጣብቂኝ ውስጥ ልግባ አልኩኝ ለራሴ፡፡ አሁን ማጉረምረሙን ትተሽ ዳይ ወደ ባልሽ ደሞ ከኔ ጋር እንዳወራንም ሆነ እንደመጣሽ እንዳትነግሪው አለኝ
ቦርሳዬን አንሴቼ ሳልሰናበተው እንኳን እየሮጥኩ ወጣሁ......


✎ ክፍል ሰባት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 7

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺

ማክ በሩቅ ሁኔታዬን አይቶ ከመኪናው እየወረደ ምነው ፍቅር ምን ሆንሽ ተረጋጊ እንጂ ታውቆሻል እንዴት እንደሆንሽ ብሎ አቀፈኝ ማክ እባክህ አርቀህ ከዚህ ውሰደኝ አልኩት ምን እንደሚል ግራ ገብቶት ካስገባኝ በኃላ ወዴት እንደሚሄድ እንኳን ሳያውቅ ነዳው መንገድ ከጀመርን በኃላ ነበር ወዴት ልንዳው ብሎ ጠየቀኝ ደስ ወዳለህ ግን በቃ ፀጥ ያለ ቦታ አልኩት በሚያስገርም ፍጥነት ከከተማ የሚያስወጣውን መንገድ ያዘ፡፡ እኔ ዝም እንዳልኩኝ ነኝ ማክ አልፎ አልፎ ምን እንደሆንኩ እየጠየቀኝ ነው ማልቀስና ዝም ብቻ የሆነ ጭር ያለ ቦታ ላይ ስንደርስ አቆመ ምንድነው የኔ ቆንጆ በጭንቀት ልትገይኝ እኮ ነው አለኝ ማክ ሁሉም ነገር ተስፋ የለውም አልኩት እያለቀስኩ በጭንቀት እያየኝ የሆንኩትን ጠየቀኝ አባቴ ያለውን ስነግረው ለደቂቃዎች ዝም ብሎ ባባቢና ባባትሽ መካከል ያለው ሚስጥር ከባድ ነው ማለት ነው አለኝ አዎ በትክክል አልኩት
ስለዚህ አባትሽ ለሱ ሚስጥር ብሎ ለሚስጥሩ ከሸጠሽ አንቺ ለምን ተባባሪው ትሆኛለሽ ከኔ ጋር ነሽ በሀሳቤ ትስማሚያለሽ አለኝ በቆራጥነት የአባቴ የጭካኔ ፈተና ሁኔታው ታወሰኝ አዎ ማክ ከአንተ ጋር ነኝ አልኩት እንግዲያውስ ነይ ብሎ መኪናውን አዙሮ ተመለሠ ማክ ምን ሰልታደርግ ነው አልኩት አባቴን ላናግረው ነው እንደምንዋደድ ነግሬው ያመጣውን ያምጣ ካስፈለገውም ቤት ለቀን እንወጣለን አለኝ ማክና አባቱ በእኔ ምክንያት እንዲጣሉ አልፈልግም ማክን በስንት ልመና አባቱ የሰጠኝ ገደብ ስላለ እስከዛ ተረጋግተን መፍትሔ እንፈልጋለን አሳምኜ ሀሳቡን አስቀየርኩት ወደ ቤት ስንመጣ የማክ አባት ቤት አልነበረም እንደምንም ወደ በፊት ደስታችን ለመመለስ ሞከርን ምሳ እየተሳሳቅን በፍቅር በላን ትንሽም ቢሆን ካለንበት ሙድ ወጣን ማክ ሻወር እስከሚጨርስ ያባቴን ንግግር ማሰብ ጀመርኩ ምንድነው የአባቴ ከባድ ሚስጥር
ለምንስ እንደዛ ደነገጠ የኔ የልጁ ሚስጥሩን ማወቅ ቢረዳው እንጂ ምንድነው ጉዳቱ ይሄን እያብሰለሰልኩ ማክ በሩን ከፍቶ ወጣ ማክዬ ይሄን ደረት እንዴት እንደምወደው እኮ አልኩት ከንፈሩን እየሳምኩ አስቀናሽኝ እኔንስ አለ እየቀለደ አይ ....አይ አንተንኳን አይመስለኝም አልኩት በዚህ እየተቃለድን ቤቱን ስንዞረው አዙ ድንገት በሩን በርግዳ ገባች ጋሽዬ መጡላችሁ አለችን ማክም እኔም ወደየክፍላችን እሮጥን ይሄ የቃቃ ጨዋታ መቼ እንደሚያልቅ ጨነቀኝ
ያባቴ የክፋት ፊትና የሽፈራው ዛቻ ሳስበው እንባዬ ሳይታወቀኝ ሲወርድ ተሰማኝ አባቴ ለኔ ግድ የለውም ቢሆንም እኔ ግን አባቴ ነውና እወደዋለው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የአባቴንም ሆነ የኔን ህልውና ልታደግ የምችልበት መፍተሄ እንዴት እንደማገኝ ማሰብ እንዳለብኝ ወሰንኩ ያባቴ ለኔ ያለው ጥላቻና ግዴለሽነቱ ምንነቱን በማላውቀው ሚስጥር ምክንያት እንዲጎዳው መፍቀድ እንደሌለብኝ ወሠንኩ፡፡ ያባቴ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን አሳልፌ ልሰጠው አልፈቅድም፡፡ ምንም ቢሆን አባቴ ነዋ......!! ግን በዚህ ባንድ ሳምንት ውስጥ ምን አይነት ተአምር መፍጠር እና ከዚህ ችግር ማምለጥ ይቻላል ግራ ተጋብቻለሁ ይህን እያሰብኩ ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ አሳለፍኩ ማክም እኔም በጭንቀት የማይገፋ ለሊት አሳለፍን
በማግስቱ ጠዋት ሁላችንም ለቁርስ ተሰብስበናል ድንገት የማክ አባት......


✎ ክፍል ስምንት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
🚫#​​እሱን_ተይው ..... 🤦‍♀

ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ
   
      💓አይሆንሽም እሱን ተይው
      አትድከሚ ላታገኚው
      ማፍቀርሽን እያወቀ
      በፍቅራችሁ ካልፀደቀ💔

💞በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው💞💔💘

━━━━━━🌹✦✗💔✦━━━━━━━
  
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 8

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
  ❦መንታ ልቦች❦


የማክ አባት ለማክ ወደ አውስትራሊያ መቼ ልትመለስ አሰብክ አለው ማክ አባቱ ቶሎ ሊገላገለው መፈለጉን ቢረዳም እንዴ አባዬ ሰለቸውህ እንዴ አለው በቀልድ መልክ አይ ነገሩን ነው ለእህቶችህ የምትወስደውን ነገሮች እንድናዘጋጅልህ ነው አለው ለመሄድ እየተነሳ ሽፈራው እንደወጣ ካረጋገጥን በኃላ እኔና ማክ ልክ ከተገናኘን የቆየን ይመስል ተናንቀን ተሳሳምን ማክ ይሄ የድብቅ ህይወት ማብቃት አለበት አልኩት ልክ ነሽ የኔ ፍቅር እኔም እያሰብኩበት ነው አለኝ
ግን እንዴት እንደሆነ ለሁለታችንም ግራ ገብቶናል ማክ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ ለምን አንወጣም አልኩት አዎ እንደውም ልወስድሽ ያሰብኩበት ቦታ አለ ዛሬ አለኝ
የት አልኩት እንደህፃን እየተቁነጠነጥኩ
እሱማ ሰርፕራይዝ ነው ባይሆን ተነሽ ልበሽና እንውጣ አለኝ ጊዜ አላባከንኩም እየፈነደኩ ወደ ላይ ስወጣ ማክ በግርምት ቆሞ ያየኛል ልብሴን ለመልበስ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበር ለባብሼ ከመቅፅበት ወጣው አቤት ፍጥነት ይሄኔ ሰርፕራይዝ ባይሆን ባመትሽም አትወጪም ነበር አለኝ ከእቅፉ እያስገባኝ
ታዲያ ሁሌ ቶሎ እንድወጣ ለምን ሰርፕራይዝ አታዘጋጅም? አልኩት እየሣምኩት እኔና ማክ ብቻችንን ስንሆን አለምን እንረሳለን በቃ ምንም ትዝ አይለንም አሁን እንኳን እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ እያለፍን እንኳን በኛ ፍቅር መካከል ምንም የተቀየረ ነገር የለም
እንደውም ፍቅራችን በጣም እያማረበት ነው አንዳችን ካላንዳችን መኖር እስከማንችል እስከሚመስለን ድረስ ፍቅር ጨምረናል ልክ ማክ ያለኝ ቦታ ልንደርስ ስንል አይኔን እንድጨፍን ነገረኝ
ማክዬ ቸኮልኩ አልኩት ደርሰናል ብሎ መኪናውን ሲያቆም ተሰማኝ አይኔን እንደጨፈንኩ በማክ መሪነት ወደሚገርመው የማክ ሰርፕራይዝ አመራን አይኔን ማመን ነበር ያቃተኝ እኔ አላምንም ብዬ ማክ ላይ ተጠምጥሜ የደስታ እንባ አነባሁ ማክ ወደገዛው አስደናቂና ውብ ቤት ስንገባ እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልዕልት የሚል በሰፋፊው ተፅፏል ቤቱ በሚያማምሩ የቤት እቃዎችና አበባዎች አሸብርቋል፡፡
ደስታዬ ወደር አጣ የምናገረው ጠፋብኝ ማክ ላይ ተጠመጠምኩበት እንደኔ የታደለች ሴት አለም ላይ የለችም እኮ አልኩት እየሳምኩት እኔም እድለኛ ነኝ አባቴ አንቺን ስላመጣልኝ አለኝ ወዲያው ደስታዬ ጠፋ የረሳሁትን ነገር አስታወሰኝ
ማክ የፊታችን ገፅታ መቀያየር አይቶ አትዘኝ የኔ ማር የምታዝኚበት ቀን አብቅቷል አለኝ እንዴ ማክ አልኩት ሽሽሽ....አለኝ ወዳንገቱ ስር እያስገባኝ
በቃ አብቅቷል አለኝ ያባትና የልጅ ፍልሚያ ተጀመረ የዛን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ውጭ አደርን፡፡ ሽፈራው ደጋግሞ ቢደውልም አላነሳንም ማክ ሁሉንም ነገር ተዘጋጅቶበት ነበር እኔ ሳላውቅ ከአዙ ጋር   ተመካክረው ጠቃሚ የምላቸውን ነገሮችና ልብሶች በሻንጣ አዘጋጅተዋል
እሱም እንደዛው በሁኔታው መገረሜን እስካሁን አላቆምኩም ሁሌም የማክ መልካምነት ይገርመኛል ቤታችን የመጀመሪያዋን ለሊት አሳለፍን የነፃነት ትንፋሽ እየተነፈስኩ አደርኩ ከማክ ውጪ የነበርኩዋቸው አስቀያሚ ትርጉም አልባ ጊዜቶች ሳስታውስ ይበልጥ ነፃነት ታወቀኝ ማክን እንደተኛ ይበልጥ እቅፍ አደረኩት ማክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ አትተኛም እንዴ የኔ ውድ አለኝ ደረቱን ተደግፌ አሸለበኝ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችንን አስቆጥረናል ከቤት ከወጣን ሽፈራውና አባቴ እያፈላለጉን እንደሆነ አዙ ነግራናለች ማክ አባቱን ማናገር እንዳለበትና ነገሮችን በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማይችሉ ነግሮኝ ከቤት ወጣ፡፡ ማክ አባቱን አናግሮ እስከሚመጣ በጭንቀት ሞትኩ በተደጋጋሚ ስደውልለት አያነሳም ሲጨንቀኝ አዙ ጋር ስደውል ማክና አባቱ ለረጅም ሰዓት ሲጨቃጨቁ ቆይተው በመጨረሻም ተጣልተው እንደተለያዩ እና ከቤት ከወጣም እንዳልቆየ ነገረኝ......


✎ ክፍል ዘጠኝ ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
2024/06/26 02:54:49
Back to Top
HTML Embed Code: