Telegram Web Link
#መዉሊድ_በመረጃ_ክፍል➊➊
بَيَانُ جَوَازِ الاحتِفَالِ بِالمَولِدِ وَأَنَّ فِيهِ أَجْرًا وَثَوَابًا
#መዉሊድን_ማክበር_በሸሪዓችን _እንደሚፈቀድና_በማክበሩም ምንዳና አጅር እንዳለዉ የሚገልፅ ማብራሪያ
#مولد_عمل_يحبه_الله_ورسوله
መውሊድ(ማክበር) አሏህ እና መልእክተኛው ዘንድ የተወደደ ስራ ነው!
ከክፍል ➓የቀጠለ........
#መዉሊድ_ማለት_አሏህ_ረሱሉ_ሙሐመድ_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላምን ብቅ ያደረገልን ይህን በረቢዓል አወል ወር በመሆኑ እርሱን ለማመስገን ነዉ የምናከብረዉ እንጅ የዘይኔ ጠላቶች እንደሚሉት እኛ ሐቢቢን ዒባዳ ለማድረግ አይደለም🙅🙅
እኛ ሙስሊሞች ነብዩ ሙሐመድን አናመልክም ከአሏህ በስተቀር ሌላን ያመለከ ኢስላም ተብሎ እንደማይጠራ ሁሉ ዘይኔን ፈጣሪ ናቸዉና አምልኮት ይገባቸዋል ብሎ የሚያምን ካለ ኢማኑ ስለተበላሸበት ሸሀዳ ይዞ ወደ እስልምና መግባት አለበት፡፡ስለዚህ እኛ ረሱሉ ሙሐመድ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላምን አናመልክም ነገር ግን ለእርሳቸዉ የሚገባቸዉን ከበሬታ ብቻ በመስጠት #ከእናት_ከአባታችን_ከወንድም_ከእህታችን_በላይ_እንወዶታለን፡፡#ሐቢቡና_ሙሐመድን ከአሏህ ቀጥለን ከሁሉም በላይ እኖዶታለን፡፡ከሌሎች ነብያቶች አስበልጠን እንወዶታለን እንድሁም ሁሉንም ነብያቶች እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን እንጅ ማናቸዉንም አናመልክም፡፡ #እኛ_ነብያችንን_ሙሐመድንም_ሆነ_መላኢካ_ኮከብም_ሆነ_ፀሀይ_ብሎም_ጨረቃን_አናመልክም፡፡ ከእኛ ከአህለል ሱናዎች ዘንድ የመጨረሻ የሆነ መተናነስ ለአሏሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ ብቻ ነዉ፡፡ለአሏህ ብቻ ነዉ ከፍጡራን እያጥራራን ግንባራችንን ሱጁድ የምናሳርፈዉ፡፡የመጨረሻ ደረጃ የልብና የሰዉነት መተናነስ ዒባዳ(አምልኮ)ይባላል፡፡ይህን ደግሞ ለሐቢቢ አናደርግም፡፡ዘይኔ ወደ አሏህ የሚጣሩ ናቸዉ አሏህን ተገዙ ብለዉ የሚጣሩ እንጅ እኔን ተገዙ ብለዉ አልተጣሩም እኛም እሳቸዉን ዒባዳ አናደርግም፡፡ሰዎችን ትክክለኛ መንገድ ስላስያዙ ከበሬታ ይገባቸዋል፤እርሳቸዉን ከማምለክ የራቀ(የዒባዳ ደረጃ)የማይደርስ በሳቸዉ የሚያመች ከበሬታ ይገባቸዋል፡፡አሏሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ ደግሞ በዘይኔ አምነዉ አልቀዉ ያከበሩትን በቁርአን ሲያሞግስ እንድህ ይላል፦
قال الله تعالى{ َاٱلَّذِينَ_آمَنُوا_بِهِ وَعَزَّرُوهُ_وَنَصَرُوهُ_وَاتَّبَعُوا_النَّورَ_أُنْزِلَ_مَعَهُ_أُولَئِك_هُمُ_ٱلْمُفْلِحُونَ}
ትርጉም፦እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ያከበሩት፤የረዱትና ከእርሱ ጋር የወረደዉን ብርሀን የተከተሉት፤እነሱ ናቸዉ የሚድኑት ፡፡ሱረቱል አዕረፍ/157
መዉሊድ ሲባል አሏህን በመታዘዝ መሰባሰብን ያካትታል፡፡እንድሁም በአሏህ ዉደታና በዘይንዬ ዉደታ መሰባሰብንም ያካትታል፡፡ #ይህም_ብቻ_ሳይሆን_መዉሊድ_አሏህን_ማዉሳት_የዘይኔን_ታሪክ(ሲራ)የዘር ሀረጋቸዉን መጥቀስ ፤ #ከተላበሱት_ስነምግባራቸዉና_መልካም_ገፅታቸዉን_በከፊሉ_ማስታወስንም_ያካትታል፡፡እንድሁም ለአሏህ ብሎ ምግብን ማብላት አለበት፡፡ይህንን በተመለከት አሏህም እንድህ ብሏል፦
قال الله تعالى{ َيُطِعِمُونَ_الطَّعَامَ_عَلَى_حُبَّهِ_مِسْكِيْنًا_وَيَتِيمًا_وَأسِيرًا}
ትርጉም፦ምግብን ከመዉደዳቸዉ ጋር ለሚስኪን፤ለየቲምና፤ለምርኮኛ ያበላሉ፡፡ #ታድያ_ከዚህ_በኃላ_እዉቀት_አለኝ_የዘይኔ_ወዳጅ_ነኝ_የሚል_ግለሰብ_የአሏህ_መልዕክተኛ_በመወለዳቸዉ_ምክንያት_ተደስተን_የምናከብረዉን_መዉሊድ_እንደት_ሐራም_ነዉ_ይላል??????!!!!😳
አሏህ ልብ ይስጣቸዉ፡፡እኛ ሙስሊሞች #በሙሐመድ_ፍቅር_አድገናል_የሙሐመድ_ፍቅር_ያሰባስበናል[ህይወታችን_የዘይኔ_ፍቅር_ነዉ፤በሙሉ አንደበቴ እንድህ ስል እናገራለሁ #እኔ የሙሐመድ ተከታይ ነኝ እንደትስ አልሆንም የዱኒያ ብርሀን የዘይኔ መንገድ ነዉ፡፡ #ሙሐመድ_የእዝነት_ነብይ_ሙሐመድ_የርህራሄ_ነብይ_ሙሐመድ_ቅን_መሪ_አዛኝ_ታማኝ_ነብይ_ሙሐመድ_ወደ_አሏህ_ተጣሪ_የሆኑን_አንፀባራቂ_ብርሀን_መሐመድ_መስካሪ፤አብሳሪ፤አስጠንቃቂ፤ሙሐመድ እዉነተኛ፤ሙሐመድ ቅን መሪ፤ሙሐመድ የትክክለኛ መንገድ ባለቤት፤ #አንቱ_የአሏህ_ነብይ_ሆይ_በአንቱ_ቅን_መንገድ_እንመራለን_አንቱ_የአሏህ_ተወዳጅ_ሆይ_በአንቱ_ቅኑን_መንገድ ተከትለናል አንቱ የአሏህ ነብይ ሆይ በአንቱ መንገዳችን አብርቷል #_የፍቅር_ተምሳሌታችን_የመኖር_ብርሀናችን_እርሶ ኖት ፊዳከ አቢ ወነፍሲ ያ ሐቢብ አሏህ😭ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም

▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
#....ኢንሻ_አሏህ_ክፍል (➊➋) ይቀጥላል...
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Facebook 👇
https://www.facebook.com/YeHaqiqawaMaidaAhmed
Youtube
https://youtu.be/Cz7tk898CXk
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#አሰላሙዐለይኩም_ወራሕመቱሏሂ_ወበረካቱሁ ዉድ የኒሳኡል መሻሪዕ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? አሏህ በያላችሁበት ይጠብቃችሁ ረሕመቱና ጥበቃዉ አይለያችሁ እያልን ኢን ሻአ አሏሁ ተባረከ ወተዓላ ከዛሬ ጀምረን በቋሚነት የሚኖሩንን ፕሮግራሞች ወደ እናንተ እናስተዋዉቃችሁና ከአሁን በኃላ በአሏህ ፈቃድ በጥበባዊነት መንገድ እንተዋወሳለን፡፡
አንድ አንዴ ባለመመቻቸት ፕሮግራሞች ሳይደርሷችሁ ቢቀሩ ወይም ሰዓታቸዉን ባይጠብቁ ዐዉፍታችን ከአሁኑ እየጠየቅን በዉስጥ እንድታስታዉሱን እንጠይቃችኃለን፡፡

#ሰኞ_ምሽት:-2:30 #ረሒቀል_መኽቱም ቀን ላይ ደርሱል ዓም

#ማክሰኞ :- ከሴቶች ለሴቶችና ደርሱል ዓም
#ረቡዕ ምሽት:- #ከስህተቶቻችን_ጓዳ፣ደርሱል ዓም፣ጥያቄና መልስ

#ኸሚስ ምሽት #ሐድራዎች፣ረሱላችንን የሚያወሱ ግጥሞችና የተለያዩ አጫጭር ፁሁፎች

#ጁሙዓህ : #አንዳንድ_መልዕክቶችና_ደርሱል ዓም

#ቅዳሜ ምሽት:- #ዐቂዳችን
ምሽት 3:00 ላይ የምስጋና(ለእናት፣ለአባት፣ለወንድም፣ለኡስታዝ። ለእህት፣ለጓደኛ፣ለባል እንድሁም ለሚስት) የምስጋና

#እሁድ ምሽት :- #ከዚህም_ከዚያም ልዩ ዝግጅት


ከዚህ የተለየ ነገር ይኑር ታላችሁ አሁንም በዚህ አሳውቁን https://www.tg-me.com/maidaAhmed
┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓

በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Facebook 👇
https://www.facebook.com/YeHaqiqawaMaidaAhmed
Youtube
https://youtu.be/Cz7tk898CXk
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ስትናገር ለንግግርህ ተጨነቅ!!ከአንተ አንደበት በሚወጡት ቃላቶች ሰዉን ለማሳመን ብለክ ከቀላቀልክ አለቀልህ! ከአሏህ ዘንድ ሐቁ አለና ተጠንቀቅ!
https://www.tg-me.com/yeabderiyderesoch
#መዉሊድ_በመረጃ_ክፍል➊➋
بَيَانُ جَوَازِ الاحتِفَالِ بِالمَولِدِ وَأَنَّ فِيهِ أَجْرًا وَثَوَابًا
#መዉሊድን_ማክበር_በሸሪዓችን _እንደሚፈቀድና_በማክበሩም ምንዳና አጅር እንዳለዉ የሚገልፅ ማብራሪያ
#مولد_عمل_يحبه_الله_ورسوله
መውሊድ(ማክበር) አሏህ እና መልእክተኛው ዘንድ የተወደደ ስራ ነው!
#መዉሊድ መልካም ሱና ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበሩት #ሙስሊሞች_ናቸዉ_እንጅ_የዘይንዬ_ጠላቶች እንደሚሉት የነብያችንን ሞት ያከብሩ በነበሩ ሰዎች የተወሰደ አይደለም🙅‍♀!
ሐፊዞች_የታሪክ_ባለቤቶች_ሌሎች_ምሁሮችም_እንደጠቀሱት ለመጀመሪያ ጊዜ መዉሊድን ያስጀመሩት በባለፈዉ ክፍሎቻችን እንዳየነዉ ታላቁ #ሐፊዝ_ሙዘፈር_የተባሉ_የኢርቢል_ሀገር_ንጉስ_የነበሩ_ታላቅ_ዐሊም_ተቅይ_አሏህን_ፈሪ_ሷሊሕና ጀግና የነበሩ ሰዉ ናቸዉ፡፡መዉሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመሩት ለመጀመሪያ ጊዜ እሳቸዉ ናቸዉ፡፡ ከዚያም ዑለሞችና የፊቂህ ምሁራኖች በዚህ ጉዳይ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ተስማሙ ከነሱም አልፎ በግዛቱ ያልነበሩ ዑለሞችም በዚሁ ስራ ተስማሙ፡፡ይህንን #አልሐፊዝ_አሲዩጢይ_አል_አዋኢል_በተሰኘዉ ኪታባቸዉ ገልፀዉታል፡፡ሙስሊሞች አሁንም ድረስ ከ900 አመት በፊት አንስቶ መዉሊድን በማክበር ላይ ሲገኙ የዘይንዬ ጠላቶች ደግሞ ከ300 አመት በፊት መጥተዉ የ700 አመት ሙስሊም #ዓሊሞችን_ሐፊዞችን_ተቅዮችን_ወልያቶችን_ለማስከፈር_መዉሊድን ሽርክ ነዉ ብለዉ እየፈረጁ ይገኛሉ፡፡ያ ጀመዓህ!! አስተንትኑ መዉሊድ ከመች ጀምሮ ነዉ የሚከበር??ከ900 አመት በፊት ጀምሮ መዉሊድ አይቻልም ሽርክ ነዉ የሚሉ ሰዎች መች መጡ!? ከ300 አመት በፊት #አይገርምም ጭቅላት ያለዉ ሰዉ ይህንን አይቶ ብቻ ስለ መዉሊድ መረዳት ይችላል፡፡ ማንኛዉም የሐቢቢ ኡመቶች መልካም ስራ ነዉ ብለዉ የተስማሙበት ነገር መልካምነቱ የተረጋገጠ ነዉ፤ማንኛዉም የዘይንዬ ኡመቶች መጥፎ ነዉ ብለዉ የተስማሙበት መጥፎ ነዉ፡፡ #የሰይዲ_ኡመቶች_ዐሊሞች_ተቅዮች_ወልዮች_ደግሞ በመጥፎ ነገር እንደማይሰባሰቡ ግልፅ ነዉ ምክንያቱም ሰይዲ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እነሱን በተመለከተ እንድህ ብለዋል፦
#قال_رسول_الله_صلى_الله_عليه_وسلم " #إنَّ_أُّمَّتِي_لَا_تَجْتَمِعُ_عَلَى_ضَلَالَةٍ" رواه ابن ماجه في سننه.
ትርጉሙም፦ኡመቶቼ በጥሜት ላይ ተስማምተዉ አይሰበሰቡም፡፡ኢብኑ ማጀህ በሱነናቸዉ ዘግበዉታል፡፡ስለዚህ መዉሊድ ደግሞ ሙስሊሙን ኡማህ ሰብስቦ የሚይዝ ልዩ ቀን ስለሆነ #ይህ_ሁሉ_ሙስሊም_የተሰባሰዉ_ለጥሜት_ነዉ_የሚል_ካለ_አዕምሮዉ_ቸክ_መደረግ አለበት፡፡ #እንድሁም_የዘይኔን_ሐዲሶች_ሀ_ብሎ_መማር አለበት፡: #አመታዊይ የዘይኔ የዉልደታቸዉን ቀን ማስታወስ የሳቸዉን ታሪክ በማንበብና በሌሎች ዒባዳዎች አስቦ መዋል ከሙዘፈር በፊት በታላላቅ ዐሊሞች የተለመደ ተግባር እንደነበር የሚያመላክቱ የሰነድ ማስረጃዎች አሉን፡፡ #ኢብን_ጀቢር_ረዲየሏሁ አንሁ(540 ሒጅሪያ)እንደፃፉት በረቢዓል አወል ወር ዘወትር ሰኞ የነብዩ ቤት ይከፈትና ታላላቅ ሰዎች ከዉስጡ በመግባት ለአሏህ ሹኩር በማድረስ ከበረካዉም በመቋደስ ያሳልፉ ነበር፡፡ #ኪታቡ_ሪሐል በተባለዉ ኪታባቸዉ አስፍረዉታል፡፡ #ኢብን_ጀቢር_ወደ መካ የተጓዙት በ579 መዲና የገቡት በ580 ሒጅሪያ ሲሆን መዲና ዉስጥ ለ5 ቀናት መቆየታቸዉ በጉዞ ማስታወሻ ኪታባቸዉ ተርከዋል፡፡ስለሆነም ከዚህ ዘመን በፊት በተቀደሰዉ የመካና የመድና ከተማ ዑለሞች የመዉሊድን ዕለት ማክበር ልምድ እንደነበራቸዉ የሳቸዉ ዘገባ ያስገነዝባል፡፡
#የነብዩ_ሙሐመድን_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም_የዉልደታቸዉንና የስነምግባራቸዉን ታሪክ ማዉሳት የአፍቃሪያንን ፍቅር፤የወዳጆችን ዉደታ፤የናፋቂያንን ናፍቆት😭😭😭ይጨምራል፡፡
ሙሐመድ
ዛፍ የመሰከረለዎት፤ሙሐመድ ድንጋይ ሰላምታን ያቀረበለዎት፤ሙሐመድ ጨረቃ ለሁለት የተከፈለለዎት፤ሙሐመድ ደረቁ የቴምር ግንድ ተሰቅስቆ ያለቀሶለት😭ሙሐመድ ዉሀ ከእጆ ጣቶች የፈለቀሎት፤ሙሐመድ ሁለ ነገሩ እርሶን እርሶን የሚለዉ😭ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም
┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
#....ኢንሻ_አሏህ_ክፍል (➊➌) ይቀጥላል...
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Facebook 👇
https://www.facebook.com/YeHaqiqawaMaidaAhmed
Youtube
https://youtu.be/Cz7tk898CXk
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#እንኳን_ለዚች_ልዩና_ዉድ_ቀን ለሐቢባችን ለሰይዳችን😍 ለዉዳችን😘 ከነፍሳችን ፣ከንብረታችን፣ከቤተሰቦቻችን በላይ አስበልጠን ለምንወዳቸዉ፣ዘወትር ለምንናፍቃቸዉና ለምናወድሳቸዉ #ለአሽረፈል_ኸልቅ_ለሰይዱል_ዓለሚን የዊላዳ ቀን በሰላም አደረሳችሁ፡፡

በያላችሁበት መልካም የመዉሊድ በዓል ይሁንላችሁ፡፡
መዉሊድ ሙባረክ❤️❤️
@nisaulmesharie
#አሠላሙ_ዓለይኩም #ወራህመቱሏሂ
#ወበረካቱሁ
🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺 #እንኳን_ለ1494ኛዉ_ለዉዳችን_ለሐቢባችን_የአይነታችንና_ለእንቁ_ነቢያችንሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የዊላዳ ቀን በሰላም አደረሳችሁ
🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺🍃🌺
#1:57:29 ሴኮንድ
🔍 #LINK

ከታች ባሉት ሊንኮች ዳውንሎድ ያድርጉ ያድምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇
ለማውረድ 🎧
ጥራት ያለው ድምፅ
Mobile Data
http://bit.ly/32yiQ5s
OR
https://sta.sh/01np2dgu6qil
Wifi
http://bit.ly/2qFj79O
OR
https://sta.sh/013xgzv2c20g
🎧 #በዛሬዉ_ልዩ_ከሴቶች_ለሴቶች የሬድዮ ፕሮግራማችን ያካተትናቸዉ፦
📚 #ከእዉቀት_ማእድ_የደርስ_መሰናዷችን
#ስለ_ሐቢባችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም መዉሊድ መፈቀድ የሚያስታዉስ ደርስ
#ስለ_ረሱላችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም የሚያወሱ ግጥሞችና መነባንቦች
#የእንኳን_አደረሳችሁ መልእክቶች
☞የበዓል እንግዳ ከኡስታዛ ዒናያ ጦልሰም ጋር የተደረገ ቆይታ
#ስለ_ታላቁ ነቢይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚያወሳ አጭር ታሪክ
🌎ሌሎች ምርጥ ምርጥ የመዉሊድ መንዙማዎችና ነሺዳዎች ተካተዉበታል ይከታተሉን...

#ስለፕሮግራሙ_ያላችሁን_አስተያየቶች
https://www.tg-me.com/maidaAhmed
ወይም 0936994553 ብላችሁ አድርሱን

🥇shar...share....Share.,
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
በYou tube አድራሻችን👇👇
https://youtu.be/W3lM_poPPyA
ኡሙ አካዳሚ👇
https://www.tg-me.com/umuakadami

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#ከዚህም_ከዚያም_ክፍል➊ ዘወትር እሁድ የሚቀርብ ለዛሬ በቀኑ ስላላቀረብን ይቅርታ ብለናል፡፡

ባጋጣሚ ዛሬ ትዝ ብሎኝ በድንገት
#የከዚህም_ከዚያም የምሽቷ ሰዓት
አረፋፈድኩና ጀመርኩኝ ዝግጅት
#ወደ_ወዳጆቼ_አሁን_አቀረብኩት

................ በሉ አታስለፍልፉኝ

ይህ ዘወትር በዚህ ቀን እንዲሁም ሰዓት የሚቀርብልን የ

#ከዚህም
_





#ፕሮግራም ነው።

አርሒቡ

#እርሷ_እንኳ_ጀነት_ውስጥ_ናት! ትላለች አንዷ ሴት....

ኻሊድ ብን ሶፍዋን በበስራ መስጂድ ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎችን በማግኘቱ ለምን ጉዳይ እንደተሰበሰቡ ይጠይቃል።

ሰዎችም በአንዲት ሴት በኩል ትዳር የሚፈልጉ በረካታ ሴቶች ወደ መስጂድ መምጣታቸውን ነገሩት።

ይህን የሰማው ኻሊድ ወደ ሴቲቷን ይቀርብና ከሴቶቹ አንዷን ማግባት እንደሚፈልግ ሲነግራት ምን አይነት ሴት ማግባት እንደሚፈልግ ጠየቀችው።

ኻሊድ የሚፈልጋት ሴት " #ቢክራ_የሆነች_ግን_ደግሞ_እንደ_ባለ_ትዳር_ሴት_ብልህ_የሆነች_ወይም_አግብታ_የነበረ[ግን_እንደ_ልጃ_ገረድ_የዋህና_ጭምት_የሆነች_አጠገቧ_ሲኾኑ_ጣፋጭ_ሲርቋት_የምትናፈቅ_ቀደም_ብላ_በድሎት_ትኖር_የነበረና_በኋላ_ድህነትን_የቀመሰች በዚህም የተነሳ የሀብታምም ሆነ የደሃ ባህሪ ያላት፤ ሀብታም ስንሆን የምድራዊያን ነዋሪዎች ገፅታ መላበስ የምትችል ስንደኸይ ደግሞ የጀነት ሰዎች ስነ ምግባር የሚኖራት " አላት።

ሴቲቷ መስፈርቶቹን ካዳመጠች በኋላ " #ላንተ_የምትሆን_የዚህች_አይነት_ሴት_አውቃለሁ" አለችው።

እሱም በጉጉት "ታዲያ የት አለች?" ሲላት

እሷም :- "#እርሷ_እንኳ_ጀነት_ውስጥ_ነው_የምትገኘው። ስለዚህ እንዳታመልጥህ በርታ" በማለት መለሰችለት።

ዓጂብ ነውስ!

#ከዚያም_አንድ_ምክር_አለ!

አቡ ለማህ አል-ጂርሚ አንጋፋ የታወቁ ኢማምና ዳኛ ነበሩ። በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምክር ሰጡ:-

" #ስለ_ወንድማችሁ_ወይም_እህታችሁ_ደስ_የማይል_ነገር_ብትሰሙ_በተቻላችሁ መጠን ዑዝር አፈላልጉላቸወለ። ዑዝር ልታገኙባቸዉ ካልቻላችሁም ይህ ወንድሜ ወይም ይህች እህቴ ምናልባትም እኔ የማላውቀው ወይም ያልደረስኩበት ዑዝር ይኖራታል/ይኖረዋል ብላችሁ አስቡ።"

#አቤት_የኛው_ነገር_ግን_ዓጃኢብ_ነው😔 ሁለት ሴትና ወንድ ሶስተኛቸው የባጃጅ ሾፌር ሆነው ሲንቀሳቀሱ ካየን #በዚና መፈረጅና መጥፎ ስም መለጠፍ ይታይብናል። አሏህ ይጠብቀን።

#አንድ ኸምር በሀይለኛው የሚሸጥበት አንድ ቤት ነበር። ዛኒያህ (የሴት ዝሙተኞችም) ይገኙበታል። እናማ አንድ #ሙስሊም ሰው በየ ቀኑ ይመላለስበት ነበር።
ሰውየው ሷሊሓ ሚስት ነበረችውና በተደጋጋሚ አትሂድ ብትለውም እሱ ግን አሻፈረኝ አለ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ያልታሰበ ነገር ተከሰተ...😭😭😭😭😭.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
#ሳምንት_በዚሁ_ቻናል_ጠብቁን😋

#ከዚያም_ጥያቄ!
እኛ የምንተኛበትን ሰዓትና ደቂቃ ማወቅ ከባድ ነው እሺ። አንዱ ምን አደረገ መሰላችሁ? ብርድ ልብሱን በበላዩ አደረገና ሊተኛ ሲል ሰዓቱን ስልኩ ላይ አየና አይኑን ጨፈነ። 😊😊😊

ይህ ሰውዬ
ሀ. የተኛበትን ሰዓት አውቆታል
ለ. የተኛውበትን ሰዓት ነገ እነግራቸዋለሁ ብሎ አይኑን ጨፍኖ እያሰበ ነው።😋

እኔ 'ለ' ን እመርጣለሁ።

#ከዚህ_ምጥያቄ :-

የማንጎላጀትንና የእንቅልፍን ልዩነት ተናገሩ?

እሺ ወዳጆቼ!

#ለማንም አትናገሩም አንድ ነገር ልንገራችሁ???




#ለሳምንት_ልንገራችሁ_አይደል?


" #አይ_አሁን_ንገሪን" _አላችሁኝ?
እሽ ምንም ማድረግ አልችልም ልንገራችሁ። ትንሽዬ ዝቅ በሉ
👇👇👇👇👇👇






👉 #ነገ_ሰኞ_ነው_የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታዉስ👈 ሐቂቀተን


አትርሱ እሺ



#ከዚህም_ከዚያም ነው!!


ደና ሰንብቱ😍😍😍
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Facebook 👇
https://www.facebook.com/YeHaqiqawaMaidaAhmed
Youtube
https://youtu.be/r-XXOJNwfF4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
የዘንድሮ የመውሊድ አከባበርን የየትኛውን ሀገር ሰፈር መውሊድ ማየት ይፈልጋሉ
10k ልንገባ ነው linkችንን ሼር በማድረግ ሀላፊነቷን ይወጡ👇👇👇👇👇👇👇
@ethiomewild2
@ethiomewild2
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#share and #join ያድርጉ።

@ethiomewild2
@ethiomewild2
@ethiomewild2
የእኛ ነቢይ ለባልደረቦቻቸዉ በነበራቸዉ ልዩ ፈገግታ ብቻ ሁሎችም ከእርሳቸዉ ዘንድ ከእኔ የበለጥ ተወዳጅ የለም እስከ ማለት ደርሰዋል፡፡
ፊትህን ከምታኮሳትርና የሰዎችን ቅስም ከምትሰብር ፈገግታን ልመድ፡፡
https://www.tg-me.com/yeabderiyderesoch
2024/09/27 20:16:34
Back to Top
HTML Embed Code: