Telegram Web Link
#አሠላሙ_ዓለይኩም_ወራሕመቱሏሂ_ወበረካቱሁ
«««««««««««««««««««««««
🌺 #እንኳን_ለ1441ኛዉ_ዓመተ_ሂጅራ_በሰላም_አደረሳችሁ!🌺
#كل_عام_وأنتم_بألف_خير عام هجري مباركوالله متم نوره ١٤٤١ #ذكرى_الهجرة_النبوية_الشريفة

#በክፍል_161_የሬዲዮ_ፕሮግራማችንን በታላቁ የአድስ አመት የሂጅራ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይዘን መጥተናል፡፡ ዉድ አድማጮቻችን በዛሬዉ
#ክፍል 161 ልዩ የአድስ አመት የሬዲዮ ፕሮግራማችንን በተከታዩ ሊንክ ያገኙናል
ለWifi ተጠቃሚዎች👇👇👇
http://bit.ly/2LcAfeO
Or
https://sta.sh/074n8hai9w
ለData ተጠቃሚዎች👇👇👇
http://bit.ly/32bXKu6
Or
https://sta.sh/024uqcs6f1n8
_በዛሬው_ሙሉ_ዝግጅታችን_
በዓለም አቀፍ ዳዒ በዶ/ር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን ስለ #ስለ_ታላቁ_ነቢይ_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም_ሂጅራ ደርስ እንከታተላለን
በኢስላም_እና_ኪነ_ጥበብ_ዝግጅት
#ስለ_ነብያችን_ሂጅራ_አጠር_አጠር_ያሉ_መነባንቦች....
➳ እንዲሁም
#ምርጥ_ምርጥ_መንዙማዎችም_ተካተዋል
ከአድማጮች መድረክ ቀንብራችን፦
#የእናንተ_ጥያቄዎች_ከዶ/ር ሸይኽ አቡበክር መልሶች ጋር ተጠናቅረዋል
#ከምርጥ_ትውልዶች_አምባ ትረካ #ስለ_ሐቢባችን_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም_እና_ስለ_ሰዪዱና_አቡበክር_ሲዲቅ_ረዲየሏሁ_ዐንሁ_የሂጅራ ትረካ.......
ለሌሎች በማስተላለፍ ተደራሽነቱን እናስፋ
Share Share Share Share
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#ለተጨማሪ ትምህርቶች
ፌስቡክ Facebook lay
http://www.facebook.com/alhabesharadio
ከፔጃችን ገብታችሁ LIKE SHARE
በዉስጥ መስመር ለመግባት ጥያቄ አቅርባችሁ መማር ትችላላችሁ
በቴሌግራም TELEGRAM ከሆነ ምርጫችሁ
https://www.tg-me.com/habeshaislamicradio
JOIN በማድረግ መከታተል ትችላላችሁ
ዩቱዩብ YOUTUBE ከሆነም ፍላጎታችሁ በዚህ ብቻ
https://www.youtube.com/channel/
UChOJ_EttE1FMQx6QYrBULcQ
SUBSCRIBE የሚለዉን በመጫን ደርሶችን ማግኘት ትችላላችሁ
JOIN ብላችሁ መማር ትችላላችሁ፡፡
#የሐቢባችን_ሙሐመድ #ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም_ሂጅራ_ዓላማዉ_ምን_ነበር?? #ክፍል1
#كل_عام_وأنتم_بألف_خير عام هجري مباركوالله متم نوره ١٤٤١ - #ذكرى_الهجرة_النبوية_الشريفة
የአሏህ መልእክተኛ ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ለዓለማት እዝነት ተደርገዉ ሲላኩ መጀመሪያ የታዘዙት የአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላን አንድነት በማወጅ ኩፍርን ገርስሰዉ የኢማንን ብርሀን እንዲያደዳርሱ ነበር፡፡ #ለዚያም_ከሰይዲ_ስሞች_መካከል_አል_ማሒ-የሚለዉን ስማቸዉን ብናስተዉለዉ ትርጉሙ #ኩፍርን_ገርሳሽ_ኢማንን_ዘሪ_የሚለዉን_ትርጉም ይሰጠናል፡፡ የኛ ነብይ ለነብይነት ሲላኩ ወደ አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይጣሩም ነበር። ረሱሉ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀግንነታቸዉ ብቻ በጣም ዐጂብ ነበር!!
በእርግጥ ሁሉም ነብያቶች ጀግኖችና ሐቅን ለማስተላለፍ ብቻቸዉን ማንም ከጎናቸዉ ሳይኖር በአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁድራና እርዳታ ህዝቦችን ተዉሒዳቸዉን ያስተካክሉ ዘንድ ጥሪ ነበር፡፡ ልክ እንደዛዉ ሁሉ የኛ ነብይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደዚች ምድር አሏሁ ተዓላ የዓለማት እዝነት አድርጎ ሲልካቸዉ #ሜዳ_ሸንተረሩ_ጋራዉ_አዕዋፋት_በሙሉ_ሲደሰቱ_ሰማይ_በምድር_ስትፎክር_ምድር_ላይ_ግን አንድም አማኝ ሙስሊም አላገኙም ነበር!! ከጎናቸዉ ማንም ሳይኖርየአሏህን አንድነት ማወጅ ጀመሩ፡፡እያሉ እያሉም የዐረብ ሙሽሪኮች በበአላቸው ከተለያዩ ቦታዎች ሲሰባሰቡ በመሃላቸው እያለፉ እንዲህ ይሉ ነበር፦
#يا_ايها_الناس_قولوا_لا_إله_إلا_الله_تفلحوا
እናንተ ሰዎች ሆይ! ነፃ ትወጡ ዘንድ ከአሏህ በቀር በሐቅ የሚገዙት ጌታ የለም ብላችሁ መስክሩ በማለት ጥሪያቸዉን ማስተጋባት ጀመሩ፡፡ #እንደ_ሰይዲ_አቡበክር_ዑመር_ዑስማን_ዓሊይ_እና_ቢላል የመሳሰሉ አንዳንድ ጀግኖች ሲያምኑባቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ግን ከክህደታቸው አልተላቀቁም። ሶሓበቶቹንም መበደል ጀመሩ። ይህ በደል ሲጠናባቸው ከፊል የነብያችን (ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ሶሓበቶች ወደ ሃበሻና ወደ መድና(የስሪብ) ሂጅራ ወጡ።
#የስሪብ_ውስጥ_የአሏህ መልእክተኛ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንሳሮች(የአሏህን ዲን የረዱ ሰዎች) ድል አድራጊዎች ሲበዙ፤ አሏህ ሙስሊሞችን ወደ እርሷ ሂጅራ እንዲያደርጉ አዘዛቸው። ከዚያም ተከፋፍለው ወጡ፡፡  ከተወለዱባትና አሏህ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነችዉ ሐገራቸዉ ከመካ ከአቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ጋር በመሆን መንገድ ላይ ችግርን እየተቋቋሙ ሂጅራ ወጡ።ይህም ረሱላችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በመልእክተኝነት ተልከው መካ ውስጥ 13 አመት ከኖሩ በኋላ ነበር። ሂጅራቸው ከከሃዲያን ለማምለጥ ወይም እነሱን በመፍራት በጭራሽ አይደለም!!ለዚያም ነዉ ተሰደዱ የማይባለዉ፡፡ ስደት በእኛ ጠባብ አረዳድ ሽሽት ስለሚያስመስል በጭራሽ ተሰደዱ አይባልም፡፡ ይልቁንስ ከተወለዱባት ሀገር ወደ መዲና ጉዞ ያደረጉት የአሏህን ትእዛዝ ለመፈፀም ነበር። እንዲሁም የነብያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሂጅራ ዱንያን በመውደድና ልቦናዊ እረፍት ፍለጋም አልነበረም። #ምክኒያቱም_የዱኒያ_ፍቅር_ቢኖርባቸዉ_ኖሮ_እሷ_ራሷ_ለማን_ተብላ_ተፈጠረችና? ተራራዉ ወርቅ ልሁላችሁ ብሎ ሲንቀጠቀጥ ምን እየሰሩ? አሏሁ ተዓላ ከዓለማት አስበልጦ የፈጠራቸዉ ነቢይ ዱኒያን ቢፈልጉ ዓለም በሙሉ የእርሳቸዉ በሆነች ነበር ነገር ግን የኛ ነብይ ለዱኒያ ሐጃ አልነበራቸዉም ።
የቁረይሽ ትላልቅ መሪዎች ለአቡ ጧሊብ እንዲ ባሉ ጊዜ የሰይዲ ምላሽ ምን እንደነበር እናስተዉል!፦" #ለወንድምህ_ልጅ_እንዲህ_በለው!! #ሃብት_የሚፈልግ_ከሆነ_ከሁላችንም_በላይ_ሃብታም_እስኪሆን_ድረስ_ሃብትን_እንሰበስብለታለን_ስልጣን_የሚፈልግ_ከሆነም_ስልጣን_እንሰጠዋለን_ታሞም_ከሆነ_እናሳክመዋለን_አሉት፡፡ አቡ ጧሊብም ከረሱሉ ዘንድ ሄዶ ይህንን ንግግር ነገራቸው። ታላቁ ነብይ እኛ መልከ መልካም እንዲህ ብለው መለሱ ፦ #አጎቴ_ሆይ!!! #በአሏህ_እምላለው_ያለሁበትን_ሐቅ_እንድተው_ፀሃይን_በቀኝ_እጄ_ቢያስቀምጧት_ጨረቃን_ደግሞ_በግራ_እጄ_ቢያደርጓት_አሏህ_ይፍ_እስኪያደርገው_ድረስ_ወይም_እሞታለሁ_እንጂ_አልውተም_አሏቸው!! ሱብሓን አሏህ #ማን_እንደ_ሰይዲ? ለዚህም ለአሏህ ተብሎ የተወጣው ሂጅራ ፍትህና ሐቅን ለማስፈን፣ የእምነት ግዛትን ለመመስረትና፣ተውሒድን በመላው የዐረብ ሀገር፣ አካባቢዎችና ከተሞች ለማሰራጨት ነበር። የቁረይሽ ሙሽሪኮች የኛን ነብይ ለመግደል ተስማሙ ሲራ አሴሩባቸዉ፡፡
▬▬▬▬▬▬◈🌷◈▬▬▬▬▬▬
#ኢንሻ_አሏህ_ክፍል_ሁለት_ይቀጥላል...
▬▬▬▬▬▬◈🌷◈▬▬▬▬▬▬
▂▂▂▂
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
በቴሌግራም አድራሻችን👇👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
#የኛ_ነቢይ_ሂጅራቸዉ_የአሏህን_ትዕዛዝ_ለመፈጸም_እንጂ_ለሽሽት_ወይም_ለዱኒያ_ፍቅር_አልነበረም!! ክፍል2⃣
  #الهجرة_من_مكة_إلى_المدينة
የአሏህ መልእክተኛ ሐቢቡና ሙሐመድ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ለአሏህ ተብሎ የተወጣው ሂጅራቸዉ #ፍትህና_ሐቅን_ለማስፈን_ኢስላማዊ_የእምነት_ግዛትን_ለመመስረትና_ተውሒድን_በመላው_የዐረብ አገር አካባቢዎችና ከተሞች ለማሰራጨት ነበር። የቁረይሽ ሙሽሪኮች የኛን ነብይ ለመግደል ተስማሙ ሲራ አሴሩባቸዉ😭እናም ከሁሉም ጎሳዎች ጠንካራ፣ በዘር ሃረጉ የተሞገሰና ፣መካከለኛ የሆነ ወጣት መልምለው ነብያችንን የአንድ ሰው ምት መተው ደማቸው(የደም ካሳ) በሁሉም ጎሳ እንዲበታተን በማድረግ ሊገሏቸው አዘጋጁ ። ሆኖም ግን ሰይዱና ጂብሪል ከአሏህ ተልከዉ ወደ የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ በመምጣት ያድሩበት በነበረ መኝታ እንዳያድሩ አዘዟቸው። የጠነሰሱትን ሴራና ደባም ነገሯቸው። ነብያችንም ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብን ረዲየሏሁ ዐንሁን ጠርተው አልጋቸው ላይ ተኝተዉ እንዲያድሩና አረንጓዴ ሻላቸዉን እንዲለብሱ አዘዟቸዉ። እሳቸዉ ትእዛዛቸውን ፈፀሙ። ከዚያም ነብያችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በእጃቸው አንድ እፍኝ አፈር ይዘው፤ ሙሽሪኮች በራቸው ላይ ሳሉ ወጡ። አፈሩንም ጭንቅላቶቻቸው ላይ እየበተኑ ያሲንን እስከ ዘጠነኛው አያ እንዲህ ብለው ቀሩ።
 يس{١}والقران الحكيم{٢}إنك لمن المرسلين{٣}على صراط مستقيم{٤}تنزيل العزيز الرحيم{٥}لتنذرقوما ماأنذراباؤهم فهم غافلون{٦}لقد حق القول على أكثرهم فهم لايؤمنون{٧}إناجعلنا في أعناقهم أغلالا فهي إلى الأذقان فهم مقمحون{٨}وجعلنا من بين أيديهم سدا ومن خلفهم سدا فأغشيناهم فهم لايبصرون{٩}
እናም አሏህ ተዓላ ነብያችንን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ከዐይናችው ሰወራቸው።ሙሽሪኮቹ ሲያነጉ ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብን አገኙ ከዚያም ስለ ነብያችን ሲጠይቋቸዉ እንደወጡ ነገሯቸው ረሱሉን ፍለጋ በሁሉም አቅጣጫ ወጡ። የአሏህ መልእክተኛም ከሰይዲ አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ጋር ሆነው የሰውር ዋሻ ደርሰው አንድ ላይ ገቡ። ከዚያም ሸረሪቷ መጥታ መግቢያው ላይ ድሯን አደራች፤ እርግቧም መጥታ እንቁላሏን ጥላ ታቀፈች። ቁረይሾቹ ዋሻው ሲደርሱ ሰይዲ አቡበክር እንዲህ አሉ « #የአሏህ_መልእክተኛ_ሆይ_አንዳቸው_ወደ_እግሩ_ካየ ያየናል እኮ»። ሲሉ ነብያችንም ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም አቡበክር ሆይ ምን ይታይሃል? ስለ ሁለት ሰዎች በአሏህ ጥበቃ ስር ስለሆኑ?  ብለው በጥያቄ መለሱለት። በዚህ ሰዓትም " #አሏህ_ከእኛ_ጋር_ነው" በማለት አፅናኗቸው።ያ ማለት ግን በአካል በቦታ ሆኖ ነዉ ማለታቸዉ አይደለም፡፡አሏሁ ተዓላ በፍፁም ፍጡራኖችን አይመስልም በቦታም ሆነ በአቅጣጫ አይመሰልም፡፡ምክኒያቱም በቁርኣን እንዲህ ብሏል፦
 قال الله تعالى{ليس كمثله وهو السميع البصير}سورة الشورى(١١)
ትርጉሙም ፡«አሏህን የሚመስል በጭራሽ የለም»
የአሏህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰኞ እለት በረቢዑል አወል ወር መዲና ሲደርሱ ሙእሚኖች በደስታ ተቀበሏቸው፡፡ የመዲና ሰዎች የአሏህን መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መምጣታቸውን ማብሰር ተያያዙ። የአሏህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ወደ የስሪብ ሲገቡ የስሪብን አልመዲነቱል ሙነወራህ ( #ያበራች_መዲና)በማለት ሰየሟት። ሙሃጅሮችንና (ሂጅራ የወጡ የመካ ሰዎችንና )አንሷሮች ብለው የሰየሟቸውን የመዲና ሰዎችን አወዳጁ(ወንድማዊ ወዳጆች አደረጓቸው )። መስጂዳቸውንና ቤቶቻቸውንም ገነቡባት። ሙስሊሞች ሁሉም በአንድ ሰው ስር ሆኑ(በአንድ ሰው መሪነት) የዱኒያ ፍላጎት አለያያቸዉም፣ ምቀኝነትና ጥላቻም አላራራቃቸውም «አንሷሮች» (የመዲና ሰዎች)  ሙሃጂር ወንድሞቻቸውን (የመካ ሰዎችን)ተቀበላቸው፤የእርዳታ እጃቸውንም ዘረጉላቸው ።አንድ አንሷሪይ ሀብቱና ንብረቱን እሱና ሙሃጂር ወንድሙ ጋር እስከመከፋፈልም ደርሰው ነበር። « #አሏህ_ሆይ_ይህንን_የተቀደሰውን_ትውስታ_ከሰላምና_ከደህንነት_ጋር_ድገመን» የዓለማቱ ጌታ ነህና አሚን፡፡የሽብር ቡዲኖችን ከእኛ ገለል አድርገህ የስራቸዉን ዋጋ ስጣቸዉ።
 #طلع_البدر_علينا_من_ثنيات_الوداع
وجب الشكر علينا ما دعى لله داع
أيها المبعوث فينا جئت بالأمر المطاع
جئت شرفت المدينة مرحبا ياخير داع مرحبا ياخير داع

#ትርጉም#እልልልል_እሰየው_ብርሃን_ፈነጠቀ፣ በረሃውን ሰነጠቀ፣ የአሏህ ጥሪ አስተጋቢው አዋጅ ነጋሪው መጣ፣ በሉ እሰየው ምስጋና ይገባው አንተ ወደኛ የተላከው መጥተሃል፣ በሐቅበማንዋሸው በሚገባ አሚን ብለን።ልንፈጽም 🐪🐪🥁🥁🕸 ....
💗 ━━━━ 💗━┓
#كل_عام_بألف_خير
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
በቴሌግራም አድራሻችን👇👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
#አስ_ሱናዎች_ነጥቀዋል_በጣም_ማሻ አሏህ ይህን ነበር የናፈቅነዉ
ምርጥ መንዙማ ጋበዝኳችሁ እህት ወንድሞቼ Fb&Youtube በመግባት like..share...comment እናድርገዉ
You tube👇👇 Subscribe አንርሳ
https://youtu.be/sv5hzawDtYQ
Fb👇👇
https://www.facebook.com/2034568329953297/posts/2422190627857730/
#አሠላሙ_ዓለይኩም #ወራህመቱሏሂ
#ወበረካቱሁ

🍬🌹👭 🍬💕🌹 👭 🍬🌹 🍬🌹👭
#ከሴቶች_ለሴቶች_ክፍል 33
ዳዉሎድ ያድርጉ ይስሙ ለሌችም ያስተላልፉ
#1:18:07ሴኮንድ
🔍 #LINK

ከታች ባሉት ሊንኮች ዳውንሎድ ያድርጉ ያድምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇
ለማውረድ 🎧
ጥራት ያለው ድምፅ
data
http://bit.ly/2lTCxVP
Or
https://sta.sh/03wqgbq1d3q
Wi-Fi
http://bit.ly/2lyTHb2
Or
https://sta.sh/0ezcq9csp9e

🎧 #በዛሬዉ_ልዩ_ከሴቶች_ለሴቶች የሬድዮ ፕሮግራማችን ያካተትናቸዉ፦
📚 #ከእዉቀት_ማእድ_የደርስ_መሰናዷችን
☞ለቀለብ ጨለማ ሰበቦቹ ምንድን ናቸዉ? ለቀልብ ብርሀንስ ምክኒያቶቹ ምንድን ነዉ የሚለዉን የሚያስታዉስ ደርስ📚
🕌 #ኢስላምን_በጥበብ
☞የተለያዩ ስነ ፁሁፎች
☞ግጥሞች
💍 #የጥንዶች_ሚዛን💍
☞የፈቲያ የህይወት ጉዞዎች እዉነተኛ ታሪክ ክፍል 13
📚📿 #ከአሪፎች_መንደር
☞የኢስላም ታሪክ ከባለፈዉ ሳምንት የቀጠለ...
👩‍👩‍👦 #የኢስላም_እንስቶች
☞ስለ መይሙናህ ቢንት አልሐሪስ ረዲየሏሁ ዐንሃ ትረካ ክፍል ሁለት ||2||

🌎ሌሎች ምርጥ ምርጥ አባባሎች #ከጣፋጭ_መንዙማዎች_ጋር ተካተዉበታል ይከታተሉን...

#ስለፕሮግራሙ_ያላችሁን_አስተያየቶች
https://www.tg-me.com/maidaAhmed
ወይም 0936994553 ብላችሁ አድርሱን

🥇shar...share....Share.,
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
በYou tube አድራሻችን👇👇
https://youtu.be/W3lM_poPPyA
ኡሙ አካዳሚ👇
https://www.tg-me.com/umuakadami

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ልሞት እኮ ነው

ለመዳን እየጣርኩ ነው አግዙኝ

ኢምራን ሲሳይ እባላለሁ ለጋ የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ በዚህ እድሜዬ የማላስበው ከባድ በሽታ አጋጥሞኝ በፈጣሪ እና በናንተው እርዳታ ህክምና ጀምሬአለሁ።

ሆኖም ካለብኝ ከባድ የደም ካንሰር በሽታ ለመፈወስ ቀሪ ገንዘብ ያስፈልገኛልና ወንድሞቼ ያዘጋጁልኝ ልዩ የነሺዳ እና የመንዙማ ኮንሰርት እየታደማችሁ በጥቂት ገንዘብ እድሜ ግዙልኝ

እሁድ መስከረም 11 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በቢላሉል ሀበሽይ አዳራሽ(መካኒሳ መስጂድ አጠገብ)

ለ 10 ሰዉ በማድረስ ለህታችን መዳን

እርሶም የበኩልዋን አስተዋፅኦ ያበርክቱ

profile ማረግም አይርሱ

በጎነት መልሶ ይከፍላል !!



0939956510
0921244737
0930597875

በቴሌግራም

@Help_each_other1
🌬ወንድሜ ዝም በል!!
የራስህን ትተህ የሰው ስታቦካ
ጥሩ ወዳጅ መስለህ አስሩን ስትነካ
ሁሉን ስትኮንን መስለህ የጸደቀ በምላስህ ሾተል ስንት ሰው አለቀ
እባክህ ዝም በል ስለ ሰው አታውራ በተሰጠህ ጊዜ መልካም ፍሬ አፍራ፡፡
┏━ 🥀━━━━ 🥀━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለማቀላለቀል👇👇
https://www.tg-me.com/yeabderiyderesoch
┗━ 🥀━━━━ 🥀━┛
#ጠላት_ሚያስፈራ_ዘይኔ_ሙዕጅዛቸዉ
ገና ከሩቅ ሆነዉ ካፊር ሚረበሸዉ
የንፋስ ፈረስ ቢሰጠዉ ሱለይማን
አልቋቸዉ ረቢ የለም በላጭ ዘይኔን
#ፍትሃዊ_መሪ_ድሎት_የሌለቦት
ስራን የማይንቁ የሌላቸዉ እረፍት
ዲኑን ያቆሙት ነበር በልፋት
በአሏህ ታግዘዉ የዓለሙ ረሕመት
አሏህን የያዘ የለዉ ፍርሀት፡፡
ሙሐባሁ የያዘዉ ሆዱን እየባሰዉ
ሶብሩን ሲያሳጣዉ አልችልም ሲል ቁድራዉ
ሁሌም እያነባ ቀን ከሌት
ረሱለሏህ እያለ ባየሁኝ ያንቱን ፊት በጭንቀት
ዉደታዉ ይብሳል በየ እለት፡፡
ዘይኔ የአንቱ ፍቅር አያልቅም ቢዘራ
ሁሌም የሚያፈራ የሸይኾቹ እንጀራ
የማድሖች ቀለብ ኸይረል ወራ
ስሞት ሁሌ ሲጠራ ያንቱ ሻፊዓል ወራ ፡፡
#ከሁሉም_ነብያቶች_ያበለጠዎት ረቢ
ደግሞ አድርጎዎት ሐቢቢ ወዳጁ ዘይኑ ነቢ
ችግርንም ስቃይም ያዩ የእኛ ነቢና
በደል ደርሷል ደርሷል በእርሳቸዉ ደግሞም ብዙ ፈተና
በትእግስት እያዩ ያንን ሁሉ መከራ
በጥበብ አሳለፉት ዉዱ ያ ኸይረል ወራ
ሆዳቸዉ ድንጋይ አስረዉ አዝነዉ ለኡመታቸዉ
ሁሉን ቻሉት ታግሰዉ ነዉና ለማቅናት ሰዉ
ሶሐበቶች ሁላ በአንቱ ዉደታ
ዲኑ እንዳይረታ ሚለፉት ጠዋት ማታ
ለእርሶ ፊዳ ሆነዉ እጅግ ብርቱ
ምንም አያመነቱ አይከብዳቸዉ ልፋቱ
ናቸዉ ለአንቱ የዲኑ ምሰሶ ያቆሙት
ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም፡፡
#መልካም_ለይለተል_ጁሙዓህ❤️
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
#ያለ_ማስታገሻ_ተኝተህ_በሰላም_ከእንቅልፍህ_ነቅተህ_ነውርህን ማንም ሳያይብህ ጉዳይህን ፈፅመህ ፣ በሁለት እግሮችህ ቆመህ መሄድ ከቻልክ አንተ ከዱንያ ንጉሶች አንዱ ነህና
الحمد لله
በል!!
┏━ 🥀━━━━ 🥀━┓
https://www.tg-me.com/yeabderiyderesoch
┗━ 🥀━━━━ 🥀━┛
🌈 ━━━━ 🌈
#ዓሹራእ🍃-ሙሐረም 10
🌈 ━━━━ 🌈
 بسم الله الرحمٰن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله
#ኢስላም_ለሰዉ_ልጆች_ክበር_እንደሰጠ_ሁሉ_ኢስላምን_ደግሞ_አሏሁ_ሱብሓነሁ ወተዓላ በተለያዩ ነገሮች አልቆታል፡፡የሰዉ ልጆችን በሰዉ ልጅነታቸዉ፤ዓመቶችን ዞረዉ ሲመጡ፤ወራቶች ሞልተዉ ሲቆጠሩና ቀናቶችን መሽተዉ ሲነጉ በተለያዩ ድንቃ ድንቅ ታሪኮች ምክንያት ከፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ከአመታት ረሱሉ ሂጅራ ያደረጉበት፤የተወለዱበትንና ረመዷንን የመሰለ የራሕመት ወርን ከፍ አድርጓል፡፡ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሁለት ዒዶችን(ዒደል ፊጥርና ኢደል አዱሓ)ለሙስሊሞች ልዩ በአላትን አስቀምጧል፡፡ይህንንም አስከትሎ ምርጡ ነብዩን ነብዩሏህ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ከአይሁዶች ነፃ የወጡበትን ቀን ረሱሉ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተወለዱበትን ቀን እንዳላቀዉ ሁሉ ሙሐረም 10ን የዓሹራ ቀንንም አልቆታል ፡፡
ኢማም ቡኻሪይና ኢማም ሙስሊም እንደዘገቡት የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መድና ሲገቡ አይሁዶች የዓሹራን ፆም ሲፆሙ አገኟቸዉና ለምን እንደሚፆሙ ሲጠይቋቸዉ "አሏህ ፊርዑንን አስምጦ ነብዩሏህ ሙሳ ዐለይሂ ሰላምን ያዳነበት ቀን ስለሆነ እርሱን ለማመስገን ስንል እለቱን በፆም እናሳልፋለን አሏቸዉ፡፡ ሐቢቡና ሙሐመድም " #ለሙሳ_እኛ_ከእናንተ_ይበልጥ_የተገባን_ነን" አሉና የዓሹራ ቀን እንድፆም አዘዙ፡፡ ታላቁ ኢማም አል ኢማም ኢብን ሐጀር አልዐስቀላኒ ይህን ሐዲስ መሰረት በማድረግ ነብያችን አሏህ የዋለልንን ፀጋ በአመት አስቦ በተለያዩ ዒባዳዎች መዋል እንደሚቻል ስላስተማሩን የሳቸዉ መወለድ ደግሞ ለዓለም በሙሉ ብርሀን ነዉና መዉሊድም ልዩ ቀንና ለሙስሊሞች አሏህ ትልቅን ፀጋ የለገሳቸዉ ቀን ስለሆን መዉሊድን ማክበርም ከነዚህ ዉስጥ ይመደባል በማለት " #አስሉን_ሳቢት" ለመዉሊድ መታሰቢያ ሸሪዐዊነት ዋና መነሻ ካሉት በኃላ ሁለት መሰረታዊ ትምህርቶች እንደሚቀሰሙበትም ገልፀዋል፡፡
አሏህ በአንድ ታሪክ ወቅት ጸጋን በመለገስ ለዋለዉ ዉለታ በየ አመቱ በልዩ ሁኔታ ሹኩር ማድረስ እንደሚቻል፤ ምስጋናዉንም በፆምና በሌሎች ዒባዳዎች መግለፅ እንደሚቻል ሐቢባችን ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ ተግባራቸዉ ገልፀዉልናል፡፡ ለዚህም በታሪክ ዉስጥ ታላቅ የአሏህ ፀጋ የተከሰተባቸዉን ቀናት በየአመቱ በዒባዳና በመልካም ስራ አስቦ መዋል እንደቻል ከሰይዳችን ስራና ሐዲስ እንገነዘባለን፡፡
➊፦አሏህ በአንድ ታሪክ ወቅት ጸጋዉን በመለገስ ለዋለዉ ዉለታ በየ አመቱ በልዩ ሁኔታ ሽኩር ማድረስ እንደሚቻል፤
➋፦ምስጋናዉ በፆምና በሌሎች ዒቤዳዎች መግለፅ እንደሚችል፤ሐቢቢ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመወለዳቸዉ የበለጠ ለሰዉ ልጅ የተሰጠዉ ፀጋ የለም!!!ሐቂቀተን ምድሩም ሰማዩም ለሰይዲ ተብሎ ነዉ !የኛ ብርቅ ነቢይ ሁሌም እርሰዎ የተወለዱበት ቀን ሊናፍቀንና ሊያስደስትን ሲገባ መጮኹን ግን ሸይጧኖች ይሰማሩበታል!!አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርአን እንድህ ሲል ይገልፅልናል፦አሏህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸዉ የሆነን በእርሱ አንቀፆችንየሚያነብ፤የሚጠራቸዉም መፅሀፉንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉ የሆነን መልዕክተኛ በዉስጣቸዉ በላከ ጊዜ በእርግጥ ለገሳቸዉ፡፡እነርሱም ከዚያ በፊት በግልፅ ስህተት ዉስጥ ነበሩ፡፡አል ዒምራን86፡፡ ስለዚህ በታሪክ ዉስጥ ታላቅ የአሏህ ፀጋ የተከሰተባቸዉን ቀናት በየአመቱ በዒባዳና በመልካም ስራ አስቦ መዋል እንደሚቻል የሐዲሱም የቁርአኑም ማስረጃ በቂ ነዉ፡፡
➌፦አሏህ ዉለታ የዋለበትን ቀን በየአመቱ ማሰብ ሱና እንደሆነ
➍፦አሏሁ ተዓላ መልካምን ነገር ያስከሰተልንን ቀን የማሰቡና የምስጋናዉ አፈፃፀም በበጎ ስራ ማድረግ እንደሚቻል ነዉ፡፡
በሌላ ዘገባ ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ እንድህ ብለዋል፦ የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው በጉጉት ጠብቀው ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! )፡፡ ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላምም የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ )ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም፡፡የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያስሰርዛል በቀላል ስራ ይህን ያክል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን፡፡ዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር፡፡ አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞች የሰው ልጆች አያውቁም}፡፡ የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው?... የሚለዉን ብናይ የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል፡፡ምክኒያቱም ረሱሉ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሶሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው እንድህ አሉ፦ ( #አሏህ_ካለ_የሚመጣው_ዓመት_ላይ_9ኛውንም_ቀን_እንጾማለን ) ብለዋል፡፡ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክኒያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛ፡፡ ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
2024/11/16 12:59:33
Back to Top
HTML Embed Code: