Telegram Web Link
✝️ኦርቶዶክስ pictures by Wina Gfx
🌿 #ሆሣዕና    ሆሣዕና ማለት አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህች ሰንበት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲገባ የእስራኤል ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በማለት እየዘመሩ ያጀቡበት ዕለት መታሰቢያ ሰንበት ናት፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ፋጌ በደረሰ ጊዜ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ልኮ የታሰረች አህያና ውርንጫዋን ይዘው እንዲመጡ አዘዛቸው፤ ካመጡለት በኋላም ጌታ ተቀመጠባቸው፤ ሕዝቡም ልብሳቸውን…
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ሰንበት ያደረጋቸው ነገሮች የየራሳቸው ትንቢትና ምሳሌ አላቸው፤ አህያዋና ውርንጫዋ የሁለቱ ኪዳናት (የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን) ምሳሌ ናቸው፡፡

አህያ የተመረጠችበት ምክንት
1. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፡- ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ እጅግ ደስ ይበልሽ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ የሆነው ትሑትም ሆኖ በአህያዋ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል›› (ዘካ 9፥9)፡፡
2. ትሕትናን ለማስተማር፡- አህያ በብዙዎች ዘንድ የተናቀች እንስሳ ነበረች፤ በአህያ መቀመጥም ራስን ማዋረድ ነውና ጌታም ትሕትናን ለማስተማር በተናቀችው አህያ ተቀምጧል፡፡ አንድም የዓለም ጥበብና ክብር በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነትና ውርደት መሆኑን ለማስረዳት ዓለም የሚያደንቃቸውን ትቶ ዓለም የናቀውን ተጠቅሞበታል፡፡
3. እኔ የሰላም አምላክ ነኝ ሲል፡- አህያ የሰላም ምሳሌ ነች፡፡ በጥንት ዘመን ነቢያት በአህያ ተቀምጠው የመጡ እንደሆነ መልካም የምሥራች ትንቢት ሊናገሩ መሆኑ ይታወቃል፤ በፈረስ ተቀምጠው ከመጡ ደግሞ ስለመቅሰፍት ወይም መአት ትንቢት እንደሚናገሩ ይታወቅ ነበርና፡፡
4. እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል፡- በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ቢያሳድዱት አያመልጥምና ብትፈልጉኝ እኔ ቅርባችሁ ነኝ ታገኙኛላችሁ ሲለን ነው፤ (ኤር 23፥23)
5. በትሑት ሰው ልቦና አድሬ እኖራለሁ ሲል፡- አህያ ብዙ ጫንክብኝ፣ ጎዳኸኝ ብላ ሳታማርር ራሷን ዝቅ አድርጋ ባለቤቷን ታገለግላለችና እኔም ራሱን ዝቅ አድርጎ በሚገዛልኝ ትሑት ሰው ልብ አድሬ እኖራለሁ ሲል ነው፡፡
አህዮቹን ፈትታችሁ አምጡ ለምን አለ?
   አባታችን አዳም ከዲያብሎስ እስራት የሚፈታበት ጊዜ መድረሱን ለማመልከት ነው፤ አንድም ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን (ሥልጣነ ክህነት) መስጠቱን ለማጠየቅ ነው፤ (ማቴ 16፥18-19 ፣ ዮሐ 20፥22-23)፡፡
ሕፃናቱ ለምን አመሰገኑት?
   አስቀድሞ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ ለራስህ ምስጋና አዘጋጀህ›› (መዝ 8፥2) ብሎ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህ የመዝሙር ክፍል የዚህች ሰንበት ምስባክም ነው፡፡

ሕፃናቱ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት ምክንያት
ሀ. ዘንባባ በእስራኤል ባሕል የሰላም የደስታ ምልክት ስለሆነ፤ (ነህ 8፥14-15)
ለ. የዘንባባ የሚዋጋ እሾህ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው፤ ‹‹እግዚአብሔር ተዋጊ ነው›› ይላልና ዘጸ 14፥14፡፡
ሐ. ዘንባባ የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ዘንባባ ቢደርቅ እንኳ በእሳት ይለበለባል እንጂ አይነድምና፡፡ የመለኮትንም ምጥቀቱንና ጥልቀቱን የሰው ኅሊና ሊመረምረው አይችልም፡፡
            ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጾምና ምጽዋት፣ ሰባቱ አጽዋማት
        ═══•꧁🌿🌿🌿꧂•═
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ጌታ ሆይ በድለናል #ማረን #ይቅር_በለን🙏

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story
On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ሰኑይ /ሰኞ/
ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ሠሉስ /ማክሰኞ/
ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡    ማቴ.21-23-27

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ረቡዕ
ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕለቱ የምክር ቀን በመባል ይጠራል፡፡

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
በስምዖን ቤት ሽቱ የቀባችውን እግሩንም በእምባዋ ያጠበችውን በራሷ ፀጉር የጠረገችውን ሴት #ብዙ_ሐጥያቷን_ይቅር_አላት_ብዙ_ወዳዋለችና

ከኢየሱስ እግር ስር ከመሆን በላይ ከፍ ያለ ቦታ የለም።

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ፋሲካ የሚባለው የቂጣ በዓል ቀረበ ፀሀፍት እና ሊቀ ካህናት ጌታን እንዴት እንደሚያሲዙት ሲያስቡ ሰይጣን ከ12ቱ አንዱ በሆነው በይሁዳ ገባበት ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ተዋዋለ 30ብር መዘኑለት #ስሞ_ይሰጣቸዋል_30ብር_ይሰጡታል

የዓለም ሁሉ መድኃኒት በ30 ብር ተሸጠ

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ሐሙስ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ በመባል ይታወቃል፡፡

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
2024/09/28 21:51:37
Back to Top
HTML Embed Code: