Telegram Web Link
ካሊድ መሻል በነጮቹ በ1997 ነበር የተመረዘው። የካናዳን ፓስፖርት በያዙ ሁለት የሞሳድ ቅጥረኞች። ላኪው ኔትንያሁ ነበር። ቦታው ደግሞ ጆርዳን ኦማን ውስጥ።

ካሊድ መሻል በወቅቱ የሃማስ ፖለቲካ አመራር ነበር።ኑሮውን በስደት ጆርዳን አድርጓል። ከመኪናው ወርዶ ወደ ቢሮው በመሄድ እያለ ነበር በሞሳድ ሰዎች ግራ ጆሮው አካባቢ በኤልክትሪክ ንዝረት የተመረዘው። በረጅም ግዜ ውስጥ እያዳከመ የመተንፈሻ አካልን በመዝጋት የሚግድል መርዝ ነበር።
በወቅቱ ካሊድ መሻልን ሲመርዙት አብሮት የነበረው ጠባቂው ከመኪናው ወርዶ በመከታተል ሁለቱን የሞሳድ ሰዎች ተያያዛቸው። ረጅም ሰዓት ተደባደቡ። መንገደኛ ከበባቸው። በመጨረሻም አንድ ሲቪል PLA አባል አጋጣሚ ደርሶ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ የሞሳድ ሰዎች ታሰሩ።
:
በምርመራ ሂደትም ነገሩ የጆርዳን መሪ የነበሩት ንጉስ ሁሴንጋ ደረሰ። እሳቸው ቀጠናው ላይ በሳል ፖለቲከኛ ነበሩ። ኔትናያውጋ ደውለው ጉዳዩን አጣሩ።
የሃማሱን ማሻል ላስነካችሁት መርዝ ማርከሻ መድሃኒት ባስቸኳይ የማትልኩ ከሆነ ከእስራኤልጋ የጀመርነው ግንኙነት ወደ ዜሮ ይመለሳል አሉ። በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ክሊንተንም ደውለው ነገሩ። ክሊንተን የኔትናሁ ጨዋታ አልተመቸውም። ጎረበጠው።ይልቅ የጆርዳኑን የንጉስ ሁሴን ሃሳብ ደገፈ። ንጉስ ሁሴን ዲፕሎማሲያቸው ሰምሮ እስራኤል ማርከሻውን ተገዳ እንድትልክ ሆነ።
:
ካሊድ ማሻል እየተዳከመ መጥቶ በእለተ ሀሙስ ራሱን ስቶ ነበር።መድሃኒቱ ከተሰጠው በኃላ ቅዳሜ ነቃ። ከኮማ ሲነቃ እንደሌላው ግዜ ሃሙስ ተኝቶ አርብ የነቃ ነበር የመሰለው። ጁምዓ ሰግቼ ልምጣ በሚል ተነስቶም ቅዳሜ እንደሆነ ነግረው ነበር የመለሱት።

By abinet addis

@wegoch
@wegoch
@paappii
[እኔ አለሁ እንዳለሁ
እንዴት ነሽ እመ?]

ከጦርነት ቀጠና ወጥቼ አዲስ አበባ እንደገባሁ የመጀመሪያው ስራየ ስራቦታ ጎራ ማለትና ቤት መፈለግ ነበር። እውነት ለመናገር ከሆነ አዲስ በብዙ ግልምጫዎችና በሰቃዥ የኑሮ ውድነት የታጀበች እጅግ ባይተዋር ከተማ ሆና ነው የጠበቀችኝ።

አዲስ አበባ ቁመት ሙሉ እንባ ስጋ ሙሉ ኧረወይለሊቴ ሆናለች ወገን።

“ጃክሮስ ቆንጆ ቤት አግኝቼልሀለሁ” ደላላው ነበር

ሄድኩ

ቤቷ ሁለት በሶስት ናት። ጭራሽ መሀከሉ ላይ እንደሰፊው ህዝብ መድረሻ ያጣ የሚመስል ኮለን ተገትሯል።

“ኧኸ እንዴት ነው ወደድሻት? 3500 ናት”

ምን ነካህ ደላላ!? ይሄኮ እንኳን አልጋ ሊያዘረጋ ጠረንጴዛና ወንበር ሊይዝ ፍራሽ እንኳን ካላጠፍኩት አያስነጥፈኝም።

😳

የውሻውን ቤት ነው እንዴ ልታከራዮኝ ያሰባችሁት🤔

“ውሻውማ የተሻለ አግኝቶ ስለወጣ ነው እምናከራይህ” አከራዩዋ

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ደግሞ ሌላ ቤት መስቀል ፍላወር

“ድርድር የለውም። 6 ክፈል” ሸምገል ያሉ ናቸው አከራዮ

ቆንጀት ያለ ቤት ነው እሺ እከፍላለሁ

“ታመሻለህ?”

አዎ አንዳንዴ ሚቲንግ ሲኖረኝ እስከ 4 ምናምን ላመሽ እችላለሁ

“አይሆንም አይሆንም እስከ 2 ልፍቀድልህ”

እንዴ ልጅዎ አደረጉኝ እንዴ!

“ምን አልክ? ይሄንም እኔ ሆኜ ነው”

እንዴ ትራንስፖርቱ ራሱ ያስመሻል እኮ። ቁልፍ ካለ ይስጡኝ ላስቀርጸው።

“ቁልፍ? ለምንድን ነው ቁልፍ እምሰጥህ? አምሽተህ እየገባህ ልታዘርፈኝ!”

😳

“ተወው ለሌላ አከራየዋለሁ። በዚያ በኩል ውጣ”

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ከሰአቱን ድክም ሲለኝ ልረፍ ምሳም ልብላ ብየ የሆነ ሆቴል ገባሁ

ቅቅል ተፈርሾ አምጪልኝ።

By the way ቅቅል ኢዝ ማይ ተወዳጅ ምግብ

በድንች፣ በካሮት እና በሆኑ ቅጠላቅጠሎች የታጀቡ 3 ግድንግድየ ቅልጥሞች መረቅ ደፍቀው መጡ

ተጠራጠራጠርኩ

ሂሳብ ስንት ነው እናት?

“550”

😳

እንስቷ እንባዋ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ከጎጃም በእግርና በባጃጅ ያስወጣኸኝ አንድየ አንተ ታውቃለህ ብየ በላሁት

ሂሳብ ከፍየ ስወጣ ከጀርባየ የሆነ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል አስተጋጇ እጇን እያውለበለበች

“ዌል ካም ቱ አዲስ የዝቅተኛው ማህበረሰብ አባል” ስትለኝ ደረስኩ

እስኪ ሆዴ ቻለው ቻለው ቻለው እያልኩ ወደስራ ቦታየ ወክ አደርግ ጀመር

አለም ሲኒማን እልፍ ስትሉ ባስ መጠበቂያው አለአይደል፣ አንድ በግምት 60 ዎቹ አካባቢ የሆነ ሰውየ እግሩን አጥፎ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኑን ጨፍኖ
“ኦም…ኦ….ም…. ኦ….ም” ይላል

ሆዴ ቦጭ ቦጭ አለ
ዝርዝር የአምስት ብር ሳንቲሞች መፀወትኩት

ሰውየው ግን አንድ አይኑን ገልጦ
“ወንድም ዮጋ እየሰራሁ እንጂ እየለመንኩ አይደለም። አዲስ አበባ መቆየት ከቻልክ ይጠቅምሀል ገንዘብህን ያዝ” አለኝ

አደነጋገጤ😳

ህዝቤ እንዳለ ለቆ ነው🤔

ቢሮ ልደርስ አካባቢ የሆነ ሙዚቃ ሰመቼ ዞር ስል የሬሳ ሳጥን የሚሸጥበት ሱቅ ላይ ሁለት ወጣቶች እየቃሙ በትንሽየ ስፒከር

“ጉርምርሜ ና ጉርምርሜ ያሆ መሌ ያሆ መሌ ና ጉርምርምርሜ” የሚል ሙዚቃ ያዳምጣሉ

ጆሮየ ፕራንክ ነው በለኝ😳

እውነት ለመናገር የሬሳ ሳጥን መሸጫ ውስጥ ሙዚቃ ስሰማ ይህ የመጀመሪያየ ነው

“የኔ ልጅ ተውው አሽሙር ነው። መንገድህን ቀጥል” አሉኝ በአጠገቤ ሲያልፉ የነበሩ እናት

ወይ አዲስ አበባ እንዲህ ሁሉን ነገር ድብልቅልቅ አደርጋ ትጠብቀኝ። ታክሲዎች ትንሽ መንገድ አምቦራችተውህ 10 ብር አምጣ ይሉሀል። ከመሸብህ ይሄ ብር ሁለት እጥፍ ሁሉ ሊሆን ይችላል። ራይድ ልያዝ ካልክ happy textile road bruh በሶስት ቀን ሆድህ ፈርደሀል ማለት ነው!

ደግሞ ሰው ምንድን ነው እንዲህ የተፈራራው🤔ለንደን ያለህ ይመስል ማንም ሰላም ሊልህ አይፈልግም። ሰላምታ ብታቀርብም አበጀህ የሚልህ የለም።

ወንድም ሰአት ስንት ነ..?

“እግዜር ይስጥልኝ እኔ ራሱ የታክሲ ብቻ ነው የቀረኝ። እህል ከቀመስኩ ዛሬ ሁለት ወሬን ደፈንኩ”

😳

“ተወኝ በቃ እኔ የትኛውንም ፖለቲካ ፓርቲ አልደግፍም። የሁሉም ባንክ አካውንት አለኝ”

ዋ ኧረ ምንጉድ ነው ብየ ወደ ጎዳናየ ተመለስኩ

ወገን እንግዲህ አዲስ ጥይት አልተተኮሰባትም እንጂ ጦርነት ላይ ናት የሚባለው ነገር እውነት ነው መሰል…

ቢጨንቀኝ
እመ ጋ ደወልኩና
“እመ ለካንስ ይሆን መስሎኝ እንዲያው ሳላውቀው ከሞት ሸሽቼ ወደ ሞት ነው የመጣሁት” አልኳት

እመ ግን ሳግ በሚተናነቀው ድምፅ
ምን አለችኝ?

“ልጅ ታምሩ ምን የሚያጓጓ ህይወት ኖሮህ ነው ሞት የሚያስፈራህ!”

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Tamiru Temesgen
የምንወደው "The Lion king" የተሰኘው ፊልም ላይ ያለች አባት እና ልጅ ወግ ናት...

ትንሹ ሲምባ እድሜ አንበሳነቱ ውስጥ አውሬነትን ሳይከትበት ጊዜ ጉልበቱ ውስጥ ጭካኔ ሳይቀረቅርበት ከግዙፍ አባቱ ሙፋሳ ጋር እየተራመደ ሲሄድ በተኮላተፈ የደቦል አፍ አባቱን አንድ ጥያቄ ይጠይቀዋል...

"አባዬ ሚዳቋ እና አጋዘን የመሳሰሉትን እንስሳት ለምን እንበላቸዋለን" 🦁

ሲምባ እነዚህን እንስሳት የሚያውቃቸው ለአባቱ ንግስና ሲሰግዱ በመንገድ ሲያዩት ትንሽነቱን ሳይንቁ ለርሱ ሲያሸረግዱ ነውና ስጋቸው ተዘነጣጥሎ ለመበላት ደማቸው ተንቆርቁሮ ለመጠጣት የሚያበቃ በደል ቅን ልቡ ውስጥ አልታየውም

አባቱ ሙፋሳ ሲመልስ ምን አለው

"ልጄ አየህ እኛ መሞታችን አይቀርምና በማንኛውም ሁኔታ እንሞታለን ስንሞት ደግሞ ገላችን ይበሰብሳል ያ የበሰበሰ ገላችን ከቆይታ በኋላ ሳር ሆኖ ይበቅላል ሳር ሆኖ የበቀለን የኛን ገላ ደግሞ እነዚህ እንስሳት ይበሉታል... ስለዚህ እነሱም ስለሚበሉን ነው የምንበላቸው"

ይሄ ተረት ነው ልብ ወለድ ነገር... ግን የአለም እውነታ ከዚህ የሚሸሽ ሆኖ አይሰማኝም... የሰው ልጅ ሰው መሆኑ ውስጥ ለሚያሳድገው አውሬነት የሚሰጠው ምክንያት የዋህ ልቡን ለማጨከን የሚያቀርበው ማስተባበያ ከዚህ አያልፍም።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Biniyam behaylu
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
THE WINDS OF FERENSAI
Art exhibition by Hailemikael Wegayehu.

Opening 10th November 2023.
📍Tikimt, 2nd floor, ambassador mall, 4kilo

@seiloch
ከሰሚት ወደ ሀያት የሚወስደው መንገድ ላይ አንድ ባለ መኪና እና የምግብ ማድረስ/ ብዩ ደሊቨሪ የሚሰራ ባለ ሞተር ሳይክል ቆመው እያወሩ ነው

መንገዱ ተጨናንቆ ቆሜ ስለነበር ድምጻቸው ከፍ ብሎ ይሰማኛል:: እየተጣሉ ስለመሰለኝ ወደ መንገዱ ዳር ወጥቼ ሳጣራ ይህ ነው የሆነው


ባለሞተሩ በከፍተኛ ፍጥነት እጁን ለቅቆ ጭራሹኑም ስልክ እያወራ ሲነዳ ያየው ባለመኪና ከኃላው ተከታትሎ አስቁሞት ነው

ከዚያም ይህንን ታሪክ ይነግረዋል "እኔ እንዳንተ እሳት የላስኩኝ ባለ ሞተር ነበርኩኝ: በፍጥነትም ሆነ በብልጠት ማንም የማይስተካከለኝ:: ታዲያ በአንዱ ክፉ ቀን በከፍተኛ ፍጥነት ስበር ከመኪና ጋር ተጋጭቼ ከጥቅም ውጪ ሆንኩኝ:: ለህክምና ወጪ ያለኝን ሁሉ ሸጥኩኝ: አሁን እግሬ ውስጥ ብረት አለ:: እንደፈለግኩኝ አልንቀሳቀስም"

ባለሞተሩ ፉቱ ላይ ድንጋጤ ይነበባል: አመስግኖት እና "ለልጆቼ ስል ከዚህ በኃላ ተጠንቅቄ ነው የምነዳው" ብሎ ቃል ገብቶለት ሄደ

ሰውዬውን "ይህንን ሁሉ ህመም እንዴት ቻልከው?" አልኩት

"አደጋው እኔ ላይ አልደረሰም:: ነገር ግን ፍጥነቱን አይቼ ለህይወቱ ስላሰጋኝ ነው እንደዚያ ብዬ የመከርኩት: አንዳንዴ ሰዎች ከሌሎች መከራ ይማራሉ " አለኝ


አንዳንድ ሰው ብልህ ነው: ፈውስ ነው ❤️🙌🏼

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Andi lemenged
ድሮ አምስተኛ ክፍል ሳለን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ሁለት ዲያቆናት ነበሩ። ከአብነት ትምህርት የጀመረ ፉክክራቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርቱም አምጥተውት ነበር። በተለይ የሽምደዳ ትምህርቶችን የሚችላቸው አልነበረም። ልጅ እያሱ የት ተወልዶ.. .የት እንደሞተ ከነቦታው ከነ ዓመተ ምህረቱ ዱቅ ያደርጉታል። (በነገራችን ላይ አንድ ቀን ልጅ እያሱ ሀይቅ ዳር ተቀምጠው ሲፍታቱ መኮንኖች ከሩቅ ሾፏቸው ። ያን ጊዜ ልጅ እያሱ በርጫ እያደቀቁ ብን ብለው በምርቃና ፏ ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ቤተ መንግስት አካባቢ ልጅ እያሱ የእስላም ቅጠል ያላምጣሉ ተብሎ እንደተወራባቸው ታሪክ ይናገራል 😂 ልጅ እያሱ አንቱ ለመባል የማያበቃ ልጅነት ነበራቸው። ሀገራችን በዘመኗ ካጋጠሟት የህፃን ባህሪ ካላቸው ንጉሶች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ። በተለይ ጢዝ ያላት እንስት ካዩ ቅቤ እንደላሰ እባብ ይቅበዘበዛሉ ይባላል ። ብዙው የንግስና ዘመናቸው ላይ ሲወሸክቱ ራስ ተፈሪ በርቀት ይጠባበቋቸው ነበር። ራስ ተፈሪ ቤተስኪያን ተመሳም አንስቶ በቤተ መንግስት ዘንድ እጅግ የተወደደ ምግባር ነበራቸው። በንግስና ዘመናቸውም ትንሽ እንኳ ሳት ብሏቸው ከማጀት ሴቶች አንዷን ቢመቻቹ ለፀፀት ቅርብ ናቸው። ከአልጋ ወርደው ደበሎ አንጥፈው ጌታ ሆይ አፉ በለኝ ይላሉ በፍጥነት። ልጅ እያሱ ግን አንዷን ቆንጆ እየቀመሱ የሌላዋ እንስት ገላ ያሻፍዳቸው ነበር )

ወደ ዲያቆናቱ ልመለስ.. .

እንዳለ ተብየው አንዲት ሸጋ ወዶ ጠየቀ። መጀመሪያ ይሄ የማርተሬዛ ሽልንግ የሚደብቅ ተረከዝህን አለስልስ ብላ ኩም አደረገችው ቆንጆዋ!

እንዳለ ከዚህ የሞራል ስብራት በኋላ ሰይጣን በጆሮው አንድ በቀል ሹክ አለው።

ጱጵ የሚል ድምፅ ከጎናችን ሰማን ። ደግሞ ለክፋቱ እኔ ከቆንጆዋ ልጅ ጎን ነው የተቀመጥኩት። ቆንጆ ይፈሳል ተብሎ ስለማይገመት ተሜው ሁላ አይኑን አጉረጠረጠብኝ። አፍንጫዬን በሹራቤ ስሸፍን ደግሞ ከሱ ብሶ ፈስ እንደሸተተው ሰው አፍንጫውን በጨርቅ ይሸፍናል እንዴ? ተባልኩ...ከ አምስት ደቂቃ ለጥቆ ቆንጆዋ ልጅ ሌላ ጋዝ ለቀቀች። ከመቅፅበት ደንግጣ ክፍሉን ለቃ ሮጠች። ዞር ስል ደብተራው እንዳለ ሆዱን እስኪቆርጠው ድረስ ይስቃል።

የፈስ ድግምት ለቆባት መሆኑ ያኔ ገባኝ 🙂

በዚህ እውቀቱ የቀናው ደብተራው ሸዋ ሌላ ጉድ ይዞ ከተፍ አለ ።

የበቀል በትሩ አንዲት ምስኪን መምህራችን ላይ አረፈ ። ቲቸር አስካል መክራን ዘክራን አልሰማ ስላልናት ብዙ ጊዜ በአርጩሜ መከራችንን ታበላናለች። ተማሪው ግርፊያዋን ስለሚጠላ እሷንም አብሮ አይወዳትም ነበር። በተለይ ሸዋ ... የክፍል መልመጃ 3/10 ስላመጣ ክፉኛ ጥርስ ነክሶባት ነበር ። የታሪክ ትምህርትን እንደ ውሀ የሚጠጣው ጎበዝ ተማሪ የሂሳብ ትምህርት ግን አናቱን እንደ ሀበሻ አረቄ ይነካዋል።

በተለይ ማካፈል የሚባል ስሌት በቀን ሶስት ጊዜ አስረድተውት በቀን አስራ ሶስት ጊዜ ይስታል 😑

አሁን በምን ተዓምር ነው 19 /12.... 21 የሚመጣው ። መምህራችን በአዕምሮህ ነው ወይስ በእግርህ አውራ ጣት አስበህ ነው ይሄንን ውጤት ያመጣኸው ብላ ስትጣይቀው.. ." በ 16 ኪዳነምህረት ነች ። በ12 ሚካኤል ነው። እመቤቴንስ እንዴት ረሳታለሁ?" አለ አሉ 😑
በዚህ ጥርስ የነከሰው ሸዋ ዛዲያ አንድ ከሰዓት ላይ አደናግር ድግምቱን አነብንቦ ክፍል ውስጥ እንትፍ እንትፍ አለ።

ቲቸር አስካልዬ እጇ ቄጠማ ሆነባት። እግሯ እንደ ህልም ሩጫ አልታዘዝ አላት። ጠመኔው ተሰሌዳው እንዴት ታዋህደው?

አይነ አፋር ነች አይነ አፋርነቷ ጎልቶ አንገቷን ደፋች ።

ደግሞ ለዛን ቀን ያለወትሮዋ እንኳን ሂሳብ ዓ ነገር መፃፍ አትችሉም ብላ አማርኛም እያስተማረችን ነበር።

አማርኛ ብላ ለመፃፍ አገርኛ ብላ ስትፅፍ ሳቅንባት ። የግንባሯ ላቦት ተንዠቀዠቀ ። መልሳ መልመጃ ን ለመፃፍ መግለጫ ብላው አረፈች። ከተማሪው ሁሉ የሸዋ ሳቅ ጎልቶ ተሰማ ።

መጨረሻ ላይ የሰራችው ስህተት ሲታከል ደግሞ ክፍሉ በሙሉ እንደ አደዋ ማስጀመርያ መድፍ አጓራ!

አንብቡ አለችን ዓ ነገር ጥፋ.. .

ምድረ ውሪ ተሰሌዳው የጣፈችውን ጥሁፍ እኩል አነበበው።

"አበበ በሶ በዳ !"😆

ድንጋጤ ጨው አደረጋት ። የፃፈችውን ዞራ አነበችው ።

ቂ....ቂ...ቂ ...ቂ...ቋቂ

ሸዋንም ሳቁንም እኩል ጠላኋቸው 🙂

ሚካኤል .አ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ይሔ ዘፈን ስለምንድን ነው? ስለ አባቱ? ስለ ሙዚቃ? ስለ ህይወት? ስለ አምላክ? ስለውበት? መተው ስለማይችሉት ፍቅር? ስለ ፀፀት? ስለ ኑዛዜ? ስለ ዕጣ ፋንታ? ስለ ምርጫ? ከራስ ጋ እርቅ ስለማውረድ?

ስለሁሉም ነው በ'ርግጥ።

ግን እንዴት ነው በአንድ ርዕስ ውስጥ ሁሉንም ስሜት ማንሳት የቻለው? ይሔ'ኮ ነፍ ሙዚቃ ነው። ይሔ'ኮ የመጥፎ ስራ ባህሪ ነው። እንዴት አስማምቶ እና አዋድዶ ሊሰራቸው ቻለ? እንዴት ነው ያልተበላሸበት?

ሲገባኝ (የገባኝ ሲመስለኝ) መልሱ የጥያቄውን ያህል ውስብስብ አይደለም።

ይሔ ዘፈን... ስለአባቱ፣ ስለሙዚቃ... አልያም ደግሞ ስለ አምላክ የተዘፈነ አይደለም። ይሔ... ቴዲ የሚባለው ሰውዬ እነዚህ ነገሮች ጋር ስላለው ግኑኝነት የተሰራ ስራ ነው።

ስለ'ሱ ማወቅ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ እዚህ ውስጥ አሉ።

የሚፈራውን፣ የሚያፈቅረውን፣ የሚፀፅተውን፣ ራሱን ለማግኘት የሔደበትን ርቀት፤ ታግሎ የጣለውን ፈተና፤ ዛሬ ላይ የሚኖርለትን ፍልስፍና ጭምር ታገኟቸዋላችሁ። እጥር ምጥን ባለ መንገድ። ሳይጎረብጣችሁ። ሳያስጨንቃችሁ። የራሳችሁ ታሪክ እየመሰላችሁ።

ብዙ ሰዎች ትረካ ከተራኪው ጋ ሲያያዝ....ጉዳዩን ማሳነስ ወይም ማጥበብ መስሎ ይሰማቸዋል። ግን አይደለም። ይሔ ማጥበብ ሳይሆን ማጉላት ነው።

ለምሳሌ...ኤላ በመሰሉ ድምፅ "ወይ ምጣ ወይ ልምጣ" ሲል እንዴት ነው የሚጨንቅህ?
...ልጅ ሚካኤል ታቱውን እያሳዬ.."አትገባም አሉኝ" ሲልህ... "ኧረ በናታችሁ አስገቡት!" ብለህ ልትለማመጥለት አያምርህም? እንድታስብስ አያደርግህም? የወንዶች ጉዳይ ላይ እንዳለው ሰርግ ቤት "የእህቴ ልጅ ነው" ብለህ ይዘኸው መግባት አትመኝም?🙂
...ጂጂ "ናፈቀኝ" ብላ የጎረቤቶቿን ስም እየጠራች ስታለቃቅስብህ...ከሀገርህ ሳትወጣ ሀገርህ አይናፍቅህም?

ብቻ...ወዳጆቻችን እንደሚሉት..."The most personal is the most creative" ...
..."ሙዚቃ ህይወቴ" ደግሞ የቴዲ ፐርሰናል ስራው ነው። ምርጥ ስራው ነው። የቴዲ ምርጥ ስራው ነው ብቻ ሳይሆን ከምንጊዜም ምርጥ ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው።

አውቃለሁ'ኮ ስለቴዲ ብዙ ተብሏል። አሰልቺ ርዕስ ነው ሁላ። ግን ስለፖለቲከኝነቱ እንጂ ስለጥበበኝነቱ የሚገባውን ያህል አልተባለም። እኔ እንዲያውም ምንም አልተባለም ባይ ነኝ። በፖለቲካው በጣም ከመወደሱ የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ቴዲ ቴዲ የሆነው በፖለቲካ ተሳትፎው እንጂ.....ያን ያህል ጥበበኛ ስለሆነ እንዳልሆነ ለማስረዳት ሲጣጣሩ ታገኟቸዋላችሁ።

I am truly speechless እንደዚህ ለምታስቡ ሰዎች🙂

አንዱ እንዲህ ሲል ደርሼ አውቃለሁ እኔም። ያው በዝምታ ላልፈው ነው የሞከርኩት። ግን አስታወቀብኝ መሰል ልጁ ትንሽ ቆይቶ "ምነው ፊትህ ተቀያዬረ?...አይነኬውን ነክቼ አሳዘንኩህ እንዴ?" አለ የሹፈት ሳቅ እየሳቀ...
"ኧረ በጭራሽ ወንድሜ!..ለሟች ማዘን የለም ባለው መፅናናት ነው!" ብዬ በህይወት ወደቀሩት ወዳጆቼ ዞርኩ😑

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mickel azmeraw
ከሚስቴ ጋር በማይረባ ነገር ተጋጨን

👇🏾

ከነኩርፊያችን ሳንነጋገር ሁለታችንም ወደ ስራ አቀናን: እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን ሁለታችንም የምንሳፈረው በአንድ ታክሲ ነው

እኔ ካዛንችዝ ስወርድ እሷ ደግሞ ወደ ፒያሳ ትቀጥላለች

ቀድሚያት ከቤት ወጣሁኝ: በሮቹን ዘጋግታ ተከተለችኝ:: የታክሲው ሰልፍ ላይ ምንም አላወራንም:: ተራችን ደርሶ ስንሳፈር እኔ የታክሲው መጨረሻ ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ: እሷ ደግሞ ከእኔ ፊት ለፊት ካለው ወንበር ላይ ተቀመጠች

ታክሲው መንቀሳቀስ ሲጀምር ከሚስቴ ጎን የተቀመጠው ጎረምሳ ሚስቴን ማውራት ጀመረ

አጠገቧ ከተቀመጠበት ሰአት አንስቶ ሚስቴን በተደጋጋሚ ሲመለከታት አይቼዋለሁኝ: አንዴ ፀጉሯን ሌላ ጊዜ ደግሞ ፊቷን እያየ ምራቁን ሲውጥ ተመልክቼዋለሁኝ

ሚስቴን ወዴት እንደምትሄድ በመጠየቅ ነበር የጀመረው: ስራ እየሄደች እንደሆነ ስትነግረው ይሰማኛል

"ስሜ ሚኪ ይባላል: ለከተማው አዲስ ነኝ:: ለብዙ አመታቶች ውጭ ሀገር ትምህርት ላይ ነበርኩኝ: እዚህ ሰፈር ቤት ተከራይቼ ገብቼ ነው"

"በጣም ደስ ይላል: እኔ እንኳ እዚህ ሰፈር ከገባሁኝ ሁለት አመታቶች ሆኑኝ" ሚስቴ ፈገግ ስትል በጎን ይታየኛል

ሰውዬው አላቆመም

👇🏾

“ለምን ታዲያ ሰሞኑን አንገናኝም: ቤታችን አንድ ሰፈር በመሆኑ ተደዋውለን መገናኘት እንችላለን:: በዚያ ላይ በጣም ነው የምታምሪው

“አመሰግናለሁ በጣም"

የታክሲው ረዳት ሚስቴን ሂሳብ ሲጠይቃት ጎረምሳው ከፈለ

"ቁጥርሽን ልቀበልሽ?" ብሎ ስልኩን ለመመዝገብ ሲያዘጋጅ ጣልቃ መግባት እንዳለብኝ ተረዳሁኝ

ሚስቴን ጀርባዋን መታ አድርጌ ወደ እኔ ስትዞር "ለግፋባቸው ወተቱን በጡጦ አድርገሽለታል?" ብዬ ጠየቅኳት

ሚስቴ ግራ ተጋባች : ግፋባቸው ደግሞ ማነው ሳትል አልቀረችም

"አልጋነሽን ደግሞ ከትምህርት ቤት ማምጣት እንዳትረሺ" ጨመርኩኝ

ሚስቴ እንደ እብድ እያየቺኝ ሳቀች

"አዎን ፍቅሬ ወተቱን አዘጋጅቼ ነው የመጣሁት: አልጋነሽንም ከትምህርት ቤት አመጣታለሁኝ" አለችኝ

"ባልሽ ነው?" ጎረምሳው ጠየቀ

ሚስቴ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች

የእኔ መውረጃ ላይ ስንደርስ ይዣት ወረድኩኝ: እየሳቀች ተከተለችኝ

"ቆይ አንተ! ማነው ግፋባቸው ማናት አልጋነሽ?"

"የወደፊት ልጆቻችን ናቸዋ" እየሳቅኩኝ መለስኩላት

በሌላ ታክሲ አሳፍሪያት ወደ ስራ ቦታዬ አቀናሁኝ

👇🏾

በኩርፊያ መካከል ሰይጣን እንዳይገባ መጠንቀቅ ነው

ቢቻልስ ተኮራርፎ አለመቆየት መልካም ነው ❤️🙌🏼

(አንብቤ ወደ እኛ ሀገር ለዛ የመለስኩት ነው)

@wegoch
@wegoch
@paappii

By zemelak
ተካፍሎ የመብላት ፀጋ

-

አንድ የሕክምና ዶክተር አሜሪካ ውስጥ የሮዜቲ መንደር/ከተማ ነዋሪዎች የጤና ሁኔታ ይገርመውና ጥናት ይጀምራል። የዚያ ማህበረሰብ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ከእድሜ አቻዎቻቸው ሌሎች አሜሪካውያን በተለየ ሁኔታ የልብ ሕመም ወይም ችግር የለባቸውም። የሚሞቱት በዕድሜ አርጅተው ብቻ ነው። ፍፁም ጤነኞች ናቸው። ይሄ ያልተለመደ ነበረና ማጥናት ጀመረ።

መጀመሪያ ከጣልያን ሮዜቲ ከተማ የመጡ እንደመሆናቸው መጠን ሌሎች ጣልያናውያን የሚመገቡትን የወይራ ዘይት ለምግብነት ስለሚጠቀሙ ነው የሚል መላምት ይዞ ነበር የተነሳው። ነገር ግን ሲያያቸው ሌላው ሕዝብ የሚጠቀመውን ተራ ዘይት ነበር የሚጠቀሙት። ሌሎች የአመጋገብና የጤና ልማዳቸውን ቢያጠናም የተለየ ነገር አላገኘም።

ከሙያው አንፃር ብቻ ያደረገው ጥናት የትም አላደረሰውምና አንድ ሌላ አንትሮፖሎጂስት ወዳጁን ጋብዞ ጥናቱን ጀመሩ። በሂደት አንድ ነገር አገኙ። የሮዜቲ ማህበረሰብ አባላት ረጅምና ጤነኛ ሕይወት የሚመሩት ሌላውን የሚያስጨንቅ ሕይወት ስለሌላቸው ነው። ፉክክር የሌለበት ማህበረሰብ ነው። ከሀገራቸው የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞችም ሆኑ ነባሮቹ የከተማው ነዋሪዎች ለአንድ ተመሳሳይ ሕግ ይገዛሉ። ከሌላው የማህበረሰብ አባል በተለየ ሁኔታ ሀብትና ንብረት አጋብሰው ነጥረው አይወጡም። ሁሉም እኩል ኑሮ እንዲኖሩ የሚያደርግ ሥርዓት ነበራቸው። ይሄ የፉክክር ያለመኖር ነው አብዛኛውን ከ65 ዓመት በላይ የሆነ ግለሰብ የሚያጠቃው የልብ ሕመም እነሱን የማያጠቃው ሲሉ ይደመድማሉ። ይሄንን የሚነግረን ማልኮም ግላድዌል ነው - ካነበብኩ ረዥም ጊዜ በሆነኝ መፅሐፉ።

-

እኛ ጋር ~ ሀዋሳ

ሁል ጊዜ ሀዋሳ ስሄድ የማደርጋት አንድ routine አለ - አሞራ ገደል ሄዶ ጥሬ አሳ በብዙ ዓይነት ዳጣ እየተለበለቡ መብላት። እዚያ ስሄድ ታዲያ ሁሌ የሚገርመኝ አንድ የምግብ/የሥራ ሰንሰለት አለ። ገና በሩ ላይ ስትደርስ የሚቀበሉህ አሳ ገፋፊ አለ። ሥራው አሳውን ገፍፎና በላልቶ ማቅረብ ነው። ከቻለ ከሚያውቀው አሳ አጥማጅ/ሻጭ ያገናኝሀል፣ ካልፈለግክ ግን ራስህ የመረጥከው ቦታ ትሄድና ትመርጣለህ። ቢላውን ይዞ ይከተልሀል። በመሀል ግን ልጅ እግር ሴት ልጆች የውሀ ጆግና ጄሪካን ይዘው ውሀ ልሽጥልህ ይሉሀል። አሳው በንፁህ ውሀ መታጠብ ስላለበት ከጠያቂዎችህ አንዱን እሺ ትላለህ።

አሳ ሻጩን፣ በላቹንና ውሀ ቀጂዋን በእግርህ እየሄድክ ዞር ስትል ተጣምረው ታገኛለህ። ከዛ ቁጭ ብለህ የምትበላበት ቦታ ፍለጋ ዞር ስትል አሳውን የምትበላበት ቂጣ የሚሸጡ ሴቶች ታገኛለህ። መርጠህ ተናግረህ ታልፋለህ። ከዛ አምስት ስድስት ዓይነት ዳጣ የሚሸጡ ሴቶች ጋር ትሄድና ዳጣ ታዛለህ። ቀጥለህ ውሀ፣ ጠላ ወይም የአሳ ሾርባ የሚሸጡ ቤቶች ያዘጋጁት ወንበርና ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ትልና አሳህ አልቆ እስኪመጣ ትጠብቃለህ።

ከአንድ ምግብ ላይ ስንት ሰራተኛ፣ ስንት ለዕለት ጉርስ ተሯሯጭ ቆጠርክ? ሁሉም ተካፍሎ ነው የሚበላው። አንዱ የሌላውን ሥራ ጠቅልሎ ሊያቀርብልህ ይችላልኮ። ግን አያደርጉትም። ለዓመታት ታዝቤያለሁ። ይሄንን ሳስብ ደስስስስስ ይለኛል። ይሄንን ምግብ ጥንቅቅ ብሎ አልቆ አንድ ያማረ ሆቴል ላይ በተመሳሳይ ዋጋ ባገኘው ያን ያህል አልደሰትም።

ሁላችንም በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን፣ ሥራዎችን፣ ገቢዎችን፣ ሸክሞችን ወዘተ እንደነሱ ብናደርግ እንዴት አሪፍ ነበር! ሰላማዊ ሕይወት!

@wegoch
@wegoch
@paappii

By gemechu merara fana
በፍም እሳት ማቃመስ
(እንደ ማስተዋወቂያ እነሆ...)
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*

የሰውን ልጅ ከተራ አውሬነት ጎራ ነጥሎ ወደ መለኮታዊነት ያሸጋገረው እሳትን መፈልሰፉ ነበር፡፡ እሳትን ከማላመዱ በፊት የሰው ልጅ ከ20 በማይበልጡ ትንንሽ ቡድናት የሚንቀሳቀስ፣ የአዳኝ አራዊት ሰለባነትን ሽሽት የእውርድንብር የሚቃትት ድንጉጥ ፍጥረት ሆኖ አሳለፈ፡፡ እሳትን ማላመዱ ግን በአንድ ጊዜ ድርድርብ መሳሪያዎችን እንደመታጠቅ ሆነለት፡፡ አብስሎ መብላት ተቻለው፤ ጤናው ተሻሻለ፡፡ ምግቡም በረከተ፡፡ በአንድ ጊዜ ‹food chain›ኑ አናት ላይ ለመቀመጥ በቃ፡፡ እሳቱ ራሱን ከቅዝቃዜና ከአራዊት ጥቃት ለመከላከል እንደ ሁነኛ መሳሪያ አገለገለው፡፡

በእርግጥም የሰው ልጅ እሳቱን እስኪፈለስፍ ድረስ ለመጥፋት የተቃረበ፣ በስራ ፈትነት የሚንጀባረር ለአደጋ የተጋለጠ እንሰሳ ነበር፡፡ (Man was a meandering and jabbering around beast until he discover fire...) እሳትን ካላመደ በኋላ የሰው ልጅ ለስልጣኔው -ም-ት-ክ-የ-ለ-ሽ- መሠረቶች የሆኑትን የእሳት ግኝቶች -
ምድጃን (hearth) -
መሰዊያን (Altar) እና
ማቅለጫን (forge) ፈለሰፈ፡፡

ምድጃው ሁለተናዊ ደኅንነት እና መረጋጋትን አቀዳጀው፡፡ ምድጃው እንደ ‹ሴል› (cell) ሆኖ የሰው ልጅ በዙሪያው እንዲሰባሰብ ምክንያት ሆነ፡፡ ቤተሰብ እንዲመሰረት አገዘው፡፡ ከቤተሰብ አስር ሃያ እያለ ወደ ትንንሽ ማኅበረብነት አደገ፡፡ መረጋጋት ቻለ፡፡ ቀስበቀስ መንደሮችን መገንባት ጀመረ፡፡ በምድጃው ዙሪያ ብዙ ዓይነት ተረቶችን አደራ፡፡ የሰው ልጅ ተረቶች፣ ታሪኮች፣ ሚቶች በሙሉ የመነጩት ከምድጃው ነበር፡፡ ተረቶቹ አፈታሪኮቹ ምናቡን ለመሳል ጠቀሙት፡፡

መሰዊያው መንፈሳዊ በጎነትን አጎናጸፈው፡፡ የዓለም ኃይማኖቶች በሙሉ የመነጩት ከመሰዊያው ነበር፡፡
ማቅለጫው ቅኝቱ የፈጠራ ሆነ፡፡ ከጦር አንካሴና ማጭድ ጀምሮ እስከ ሮኬት ሳይንስ ዛሬም ድረስ እየተራቀቀ ለቀጠለው ቴክኖሎጂያዊ መራቀቁ መነሻው እሱ ማቅለጫው ነበር፡፡

ነገርግን በግሪክና መሰል ጥንታዊ ተረታዊ ትርክቶች እንደሚባለው የሰው ልጅ እሳትን ከአማልክት አልሰረቀም፡፡ የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ጫረውም... እሳትን ከክዋክብት ገጽ ለመጫር ደግሞ ከገል እና ኩበት ይልቅ ምናብ ያስፈልጋል፡፡

ምናብ ምንጊዜም አሸናፊ ያደርጋል፡፡ ጥቂትስ ስንኳ የተሳሉ ምናቦችን ከመካከሉ መፍጠር የሆነለት ሕዝብ ምንጊዜም የትርክት የበላይነትን ይቀዳጃል፡፡ ስለምናብ ሳወራ ስለድርሰት ብቻ እየተናገርሁ የሚመስለው ካለ መቸስ ምን እላለሁ፡፡ ነገርግን ቴሌስኮፕ፣ ማይክሮስኮፕ፣ የማተሚያ ማሽን፣ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክን ጨምሮ በጠቅላላው የኤሮፓ ሥልጣኔ ግኝቶች የምናብ ውጤቶች መሆናቸው እሙን ነው፡፡

የእሳትንም ያህል ፍጹም ቅን፣ ገር እና በስነተፈጥሮው ቀጥተኛ ነገር መኖሩን አላውቅም፡፡ እሳት ከብሉያት፣ ነብያት፣ ወንጌላዊያን፣ ከአፈታሪኮች እና ባለቅንያት ዘመን ጀምሮ ብዙ የተባለለት መለኮት አከል ረቂቅ ክንውን ነበር፡፡ እሳት ሲፈጅ፣ ሲበላ እንጂ ሲያርፍ ማደሪያው የት፣ ሲግለበለብ መከሰቻው ከወዴት እንደሆንስ ስንኳ የሚያውቅም የለም፡፡ እሳት ስሪቱ የነበልባል፣ የፍላጻ ብቻ አይደለም፡፡ የቃል፣ የቀለም፣ የመንፈስ ልዩ ልዩ ዓይነት አለው፡፡ እሳት ንጹህ ነው፤ ቅን ነው፤ ገር ነው፡፡ ግን ደግሞ አውዳሚ፣ ጨራሽ፣ ፈጅ፣ ቀሳፊ፣ ቁጡም ነው፡፡ የዚህ ረቂቅ የነበልባል ቅኝት ጥሪ እና ምሪት ሰብዓዊነትን ማበልጸግ መሆኑ ጥንት ከአፈታሪክ፣ ከነፕሮሚተስ ዘመን ጀምሮ ይታወቃል፡፡

አሳት ሥሪቱ የእንከንየለሽነት፣ የምኅረትየለሽነት መሆኑም እሙን ነው፡፡ እሳት በመንፈሳዊውም (spirited) ይሁን በገቢራዊ (empirical) ባህሪው የሚያሻግር (fire of transmuting) እና የሚያሳርር (fire of destruction) መንታ ጉልበት ያለው ረቂቅ ሁነት ነው፡፡ እሳት የነካውን ሁሉ የሚያነጻ (purifying) ወይም የሚያገረጣ (terrifying) አቅም አለው፡፡ ቁም ነገሩ ለየትኛው አሰልጥነሽዋል/ አሰልጥነኸዋል የሚለው ብቻ ነው፡፡
ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ያም በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈ - ምልክት ሆነለት - ... ነብዩ ኢሳያስ ለነብይነት የተመረጠበትን አኳኋን በሚናገርበት በትንቢተ ኢሳያስ ምዕ 6፡8 ላይ እንደምን በፍም እሳት መቃመስን ተቃምሶ መንጻትን እንደተቀዳጀ ሲገልጽ...
‹‹ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፡፡ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበረ፡፡ አፌን ዳበሰበትና ‹እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፡፡ በደልህም ከአንተ ተወገደ፡፡ ኃጥያትምህም ከአንተ ተሰረየልህ› አለኝ፡፡›› ይላል፡፡
የሰው ልጅም የእሳት አቀባበል እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ልክ የባላገር እናት የአራስ ቤት ጨቅላ ልጇን ወደ ሕይወት ለመጥራት በቅቤ እንደምታቃምስ እንዲያ የሰው ልጅ የነቢይ በሆነ በእሳት መቃመስን ተቃመሰ፡፡ ከእሳት ጋር መገናኘቱ ሁለንተናውን የሚያሻግር ክስተት ሆነለት፡፡ መቼ? የት? የሰው ልጅ ከእሳት ጋር ተዋወቀ ሳይንስ ባዝኖ ባዝኖ መልስ ቁርጥ ያለ መልስ ያጣላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በደፈናው እስከ 2 ሚሊዮን ዓመታት ይገመታል ብሎ ማለፍ ይሻል ይመስለኛል፡፡ ነገርግንስ የሰው ልጅ እሳቱን ማላመዱ፣ በትንታግ መፈተኑ፣ ነበልባሉን መግራቱ ራሱ የሰው ልጅ ብዙ ዓይነት ሞራላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሥነልቦናዊና አካላዊ ሽግግር እንዲያከናውን ረዳው፡፡
እሳትን ከፈለሰፉት የመጀመሪያዎቹ አውሬ መሰል የሰው ልጆች እስከ እሳትን ወደ ኤሌክትሪክ የቀሩት ድረስ ከ50 - 60 ሺህ ትውልዶች እንደተፈራረቁ ይገመታል፡፡ የእኛ ግን እርግማን ይመስላል፡፡ ሌላው ዓለም እሳቱን ከአመድነት ወደ ስማርት ምድጃነት ከፍታ ሲያሻግር እኛ ዛሬም ጉልቻዋን የሙጥኝ ብለናታል፡፡ ከጥንታዊነት (primitive sentiment) ያልተሻሻለ ቢሆንስ ስንኳ... ለዘመናት ጉልቻውን ታክከን ተረቱን ማንዘገጋችን አልቀረም፡፡ መሰዊያዎችንም (የአምልኮ ቦታዎች) በዓይነት እና በጥራት እየገነባን ስናደገድግ ምዕታት አልፈዋል፡፡ ለሰብዓዊ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረውን ዋነኛውን የእሳት ግኝት ማቅለጫውን (forge) ግን ሆነ ብለን ረሳን፡፡ ማቅለጫውን ሙሉ ለሙሉ ብንረሳ ከብዙ መቶ ሺህ ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሰው ልጅ በተጠቀመበት ጦር ጀት የታጠቀውን ጣሊያንን ለመግጠም ተገደድን፡፡

የኢትዮጵያን የሥልጣኔ ታሪክ በተለይ ከአክሱም ውድቀት በኋላ የነበረውን ሂደት በጥልቀት የሚመረምር ሰው የጎደለን ነገር ማቅለጫው እንደነበር ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ማቅለጫው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሌላም ሌላም ብዙ ነገር ነው፡፡ በዚህ መጽሐፌ ከተካተቱ አስራ አንድ መጣጥፎች ውስጥ ስድሳ ገጾችን በሚሸፍነው የመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የጎደለው የመሰለኝን የማቅለጫውን ነገር በጥድፊያም ቢሆን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ ሌሎች በዚህ መጽሐፍ ስር የተካተቱ ሌሎች አስሩም መጣጥፎቼ በልህቀት ለሚያነባቸው የእሳት ንክኪ እንዳላቸው አምናለሁ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ በየመደብሩ ትገ ኛለች!!!
በዓለም ላይ በጣም ብልህ ሰው

አንድ ዶክተር፣ ጠበቃ፣ ትንሽ ልጅ እና አንድ ቄስ በትንሽ የግል አውሮፕላን በረራ ላይ ነበሩ። በድንገት አውሮፕላኑ የሞተር ችግር አጋጠመው። አብራሪው ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም አውሮፕላኑ መውረድ ጀመረ። በመጨረሻም ፓይለቱ ፓራሹት ይዞ ተሳፋሪዎቹን ቢዘሉ እንደሚሻል ተናግሮ ጮኸ ወጣ ።

እንደ አለመታደል ሆኖ የቀሩት ሶስት ፓራሹቶች ብቻ ነበሩ።

ዶክተሩ አንዱን ያዘና "ሀኪም ነኝ ህይወትን አድናለሁ ስለዚህ መኖር አለብኝ" ብሎ ዘሎ ወጣ።

ከዚያም ጠበቃው "እኔ ጠበቃ ነኝ እና ጠበቆች በአለም ላይ በጣም ብልህ ሰዎች ናቸው መኖር ይገባኛል." ብሎ ፓራሹት ያዘና ዘሎ ወጣ።

ቄሱም ወደ ትንሹ ልጅ ተመለከተ እና "ልጄ ረጅም እና ሙሉ ህይወት ኖሬአለሁ አንተ ወጣት ነህ እና ሙሉ ህይወትህ ከፊትህ ይቅደም። የመጨረሻውን ፓራሹት ይዘህ በሰላም ኑር" አሉት ።

ትንሹ ልጅ ፓራሹቱን ለካህኑ ሰጣቸውና "አይጨነቁ አባቴ በአለም ላይ በጣም ብልህ እና አስተዋይ ሰው ያስፈልጋልና እርሶ ኖረው ትውልድ ያንፁ " ብሎ እርሱ ብቻ ሊቀር ሲወስን ቄሱም " አይ ልጄ ታላቅን የሚያከብር እና ምሳሌ የሚሆን ሰው ያስፈልጋልና በአንዱ ፓራሹት ለሁለት መዝለል እንችላለንና ና ልዘልህ ብለው ተያይዘው ወረዱ ።

ስራህ ሁል ጊዜ አይገልፅህም ጥሩ ሰው መሆን ግን ይገልፅሀል።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Tariku
#ማጣት እና ጊዜ

         ……..ጊዜ የሆነ የውሃ አካል አይነት ቅርፅ አለው፡፡ አንሳፎ ወይንም አጣድፎ መውሰድ የመሰለ፡፡ በሄደ ቁጥር እያገላበጠ ያበስለናል፡፡  እድሜያችንም ይቆጥራል፡፡ ትንሽ እንኳን ፍጥነታችን ከፍጥነቱ ካልተመጣጠነ ደሞ ደርሰን ላንደርስበት ቀናት እያደነቃቀፉን እንካለባለን፡፡ እንግዲህ ድንገት አዝግመን ጊዜ ካመለጠን እንዲህ ነው፡፡ አካልና ጥላ እንሆናለን፡፡ ይሄዳል፣ እንከተላለን፡፡ ላንቀድመው ወይ ላንተካከለው መሮጥና መከተል እያዛለን እናረጃለን፡፡ በመደበኛ ሁኔታ ጊዜ እንደ ጎርፍ እሽሩሩ በሚመስል አሳስቆ መውሰድ አዝሎን የሚሄድ ከሆነ ግን ነገሩ ጊዜን እንደ ጥላ ከሚከተሉት ይለያል፡፡

           ጊዜ ብቻውን ጊዜ ብቻ ሳይሆን የሁነቶች ጥርቅም ጭምር ነው፡፡ ከነዚያ ሁነቶች አንዱ አይሰብሩት ሊሰብረን ይችላል፡፡ ጊዜ ደግሞ ሁሌም የህመም እና የልብ ስብራት ወጌሻ ሆኖ ቶሎ ቁስልን መሻር አይቻለውም፡፡ ጊዜ እራሱ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ይሄኔ እኛም ማጣታችንን መቀበል ሲሳነን፣ ከምናፈቅረው መለየታችንን ለማመን ሲያቅተን በጊዜ ታዝለን አንሄድም፡፡ ወይንም ጊዜን እንደ ጥላ አንከተልም፡፡ በውስጡ ሰጥመን እንጠፋለንን፡ ወይንም ጊዜ ሲሄድ ተገትረን እንቀራለን፡፡ ስለ ነገ ግድ አይኖረንም፡፡ አሁን የሚባል የጊዜ ልክን ክደን ‹ዛሬ› ባልነው ትላንት ላይ እንቆማለን፡፡ ያፈቀርነውን ካጣንበት ቅፅበት ወዲህ ዐለም ምኅዋሯን ስታ መሽከርከር አልገታችም፡፡ ፀሃይና ጨረቃ፣ ወቅቶች መፈራረቅ አላቆሙም፡፡ ወንዞች ሽቅብ ፈሰው፣ ሰማይ አልታረሰም፡፡ ቀናትም ቢሆኑ እንደ ሃውልት ተገትረው አልቀሩም፡፡ ይሆን የነበረው ሳይሻ ቀጥሏል፡፡ ጊዜም መሳሳቡን አልገታም (አይገታም)፡፡ እኛ ግን ላንዘም፣ ላንነቃነቅ አንዳች ‹አፍዝ፣ አደንግዝ› የተደረገብን ያህል ተገትረን እንቀራለን፡፡ ቀናት እየተጎተቱ ወራትን፣ ወራትም አመትን ያህላሉ፡፡ ዘመን ሲሄድ አኗኗር በየጊዜው ይቀየራል፡፡ ይሄኔ ትላንት ላይ የቆምን እኛ ከዘመን እና ከአኗኗር መቃቃር እንጀምራለን፡፡ ድርጊቶቻችን ሁሉ ጊዜን እንደሚከተሉ ወይንም ከሱ እኩል እንደሚሄዱ ብዙኃን ስላልሆነ ማህበራዊነታችን ሳናውቀውና ሳናስተውለው እንሸረሽረዋለን፡፡ ከሰው ፈልገን እየሸሸን የተገፋን ይመስለናል፡፡ ቅርባችን ላሉ ሁሉ ትላንት የነበረው ትዝታ፣ ለኛ ግን ‹ዛሬ› ሆኖ ሰፊ ቦታ ይይዝብናል፡፡
‹ማጣት› እና ‹ጊዜ› በሆነ አይነት ቀጭን ክር ተጠላልፈው የተያያዙ ናቸው፡፡ ጊዜ ማጣትን አጠንክሮ የደደረ የሀዘንነት ቅርፅ ይሰጠዋል፡፡ ካልሆነም ደሞ ይሽረዋል፡፡ የጉዳቱ ልክም ጨምር የሚሰፈረው በጊዜ ነው፡፡ መቼስ በአብዛኛው ለአጭር  ወቅት ከምናውቀው ይልቅ ለረጅም ጊዜ አብሮን የቆየን ስናጣ ሀዘን ይበረታል፡፡ ቅርበትም ቢሆን እየተበበ የሚመጣው ጊዜ በገፋ ልክ ነው፡፡

         ብቻ ማጣት የሚሉት እዳ ከጊዜ ያጓድላል፡፡ ከመኖር ያቃቅራል፡፡ ሞትንም ያረክሳል፡፡ መኖርም፣ አለመኖርም ጣዕም ያጡብናል፡፡ ጣዕም በራሱ ምንነቱ ይጠፋብናል፡፡ እንደ ፈሰሰ ውሃ በማይታፈስ አካሄድ የተለየን ሰው የሚሄድ ጊዜ ትዝታውን እያደበዘዘ እንዳያስረጀው እና በለጋነቱ እንዲቆይልን ስንል ካጣንበት ቀን እንቆማለን፡፡ በገዛ ራሳችን ፈንታ ትዝታችንን ‹እሹሩሩ› እንላለን፡፡ ግን አባባይ የሚያስፈልገን አልቃሾች እኛ ነን፡፡


By #Lewi @Lee_wrld777


@wegoch
@wegoch
@paappii
ጀለስ . . .

ጀለስ ወደ ሸገር ሊሄድ ፕሌን ውስጥ መቀመጫውን አግኝቶ ቦታውን እንደያዘ አንዲት ቀሽት ቺክ አይቶ ልቡ መምታት ጀመረ። ወደሱ አቅጣጫ እየመጣች መሆኑን ሲያውቅ አይኑን በለጠጠ። አጠገቡ መጥታ ስትቀመጥማ መተንፈስ አቃተው።

እንደተቀመጠች በወሬ አጣደፋት።

«የአዲሳባ ልጅ ነሽ?»

«አይደለሁም»

«እና ለሥራ ነው ለመዝናናት?»

ፈገግ ብላ «አንድ በሥነ-ፆታ እና ወሲባዊ ግንኙነት ባለሙያዎች የሚደረግ ኮንፈረንስ ላይ ልሳተፍ ነው የምሄደው።»

ምራቁን ጉርጭጭ ሲያደርግ እየሰማችው ነበር። ቀሽት መሆኗ ሳያንስ ወሲብ ነክ ነገር ላይ ልትሳተፍ እየሄደች . . . . በለው! ሁኔታው እንደያስነቃበት ተጠንቅቆ ጠየቃት፣

«እና አንቺ ምን በምን አግባብ ተሳታፊ ሆንሽ ኮንፈረንሱ ላይ?»

«ጥናት አቀርባለሁ። ከሕይወት ልምዴ ተነስቼ በሕብረተሰቡ ውስጥ ሥነ-ፆታን እና ወሲብን በተመለከተ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስተካከል ነው የምሄደው።»

ጀለስ ምራቁን እየዋጠ «እንዴ? በሀገራችን ደግሞ ምን ዓይነት የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ?»

«ለምሳሌ በሀገራችን ትልቅ ቸንቸሎ አላቸው የሚባሉት ኦሮሞዎች ሲሆኑ እውነታው ግን ትልቅ ቸንቸሎ ያላቸው ወላይታ ወንዶች ናቸው። ሌላው ደግሞ ሴት አያያዝ ያውቃሉ፣ አፍቃሪ ናቸው የሚባሉት ተጋሩ ወንዶች ሲሆኑ እውነታው ግን አፍቃሪዎቹ ኦሮሞ ወንዶች ናቸው።» ይሄንን ካለች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ደንገጥ ብላ . . .

«ይቅርታ ምንም ለማላውቀው ሰው ስለራሴ ብዙ ነገርኩና uncomfortable አደረግኩህ መሰለኝ» አለችና አቆመች። ይሄኔ ጀለስ . . .

«ኧረ ጣጣ የለውም፣ ገመቹ እባላለሁ። ጓደኞቼ ግን “ጦና” ብለው ነው የሚጠሩኝ»

🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♂️

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Gemechu merera fana
የኢትዮጵያ ቡድን የዛሬ ምሽት ነገር ይህን አስታወሰን

ከአመታት በፊት ነው ። Charlton Athletic እና Chelsea በለንደኑ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ጨዋታ ነበራቸው ።
....
እና ጨዋታው ከተጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ ፡ ዝናቡ እየበረታ ፡ ጭጋግና ጉም ስታዲየሙን ሸፈነው ። ተጫዋቾች አደለም ኳሷን አይተው ፡ መምታት ፡ እርስ በርስ መተያየት ሁሉ እያቃታቸው መጣ ።
......
በዚህ ጊዜ ዳኛው ውጡ አሉ " ይሄ ጭጋግ እስኪገፍ ጨዋታው መቆም አለበት "

ልክ ከዳኛው ይህ ቃል እንደተሰማ ፡ በሜዳው ላይ የነበሩት የቼልሲና የቻርልተን አትሌቲክ ተጫዋቾች በፍጥነት ሜዳውን ለቀው ወደ መልበሻ ክፍል ገቡ ።
.....
ጭጋግና ጉሙ እየባሰ መጣ ። የስታዲየሙ ሜዳ የመጨለም ያህል ሆነ ። በሜዳው ላይ አንድም ተጫዋች የለም ። ከአንድ ሰው በስተቀር ።

ይህ ሰው የቻርልተን አትሌቲኩ በረኛ Sam Bartram ነው ። ሳም ፡ በድቅድቁ ጭጋግና ጉም መሀከል ካሁን ካሁን ኳስ ወደሱ ግብ ከተመታ በማለት ፡ የጎሉን በር ይዞ እየተጠባበቀ ነው ።
......
ሆኖም እስካሁን ምንም ኳስ አልተሞከረበትምና ፡ ጭጋጉ ባያሳየውም ቡድኑ የቼልሲን የግብ ክልል እያጠቃ እንደሆነ እያሰበ ፡ ምንም በማይታየው ጭጋግና ጉም ውስጥ ብቻውን ቆሟል ።
............
በዚህ ሁኔታ እያለ ፡ አስራምስተኛው ደቂቃ ላይ ግን በስታዲየም ውስጥ ከሱ ብዙም ባልራቀ ቦታ ላይ የነበረ ፖሊስ ፡ የበረኛው ቦታ ላይ የቆመ የሚመስል ብዥታ ተመለከተ ።
ፖሊሱ ለማረጋገጥ ወደ ግቡ ተጠጋ ። ግብ ጠባቂው Sam Bartram ጎሉን እየተጠባበቀ አገኘው ።
.....
ወደ መልበሻ ክፍል ይዞት ከተመለሰ በኋላ ሲጠየቅ ፡ ፖሊሱ መጥቶ እስከሚያገኘው ድረስ ተጫዋቾች መውጣታቸውን አያውቅም ነበር ። የክለቡ ተጫዋቾችም በረኛው አብሯቸው እንደሌለ ልብ አላሉም ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By wasihun
አህያ ላይ ከከረምን አይቀር . . .

ገሜ/ጦና ከተማ ውስጥ ዎክ እያደረገ አንድ ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን ላሳቀው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" የሚል ማስታወቂያ ያያል። ይገባና ባለቤቱን አናግሮ ወደታሰረው አህያ ሄደና በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። አህያው ፍርፍር ብሎ መሳቅ ጀመረ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሄደ።

በሳምንቱ እዚያው ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን መሳቅ ላስቆመው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" ተብሎ ተለጥፏል። ጦናም ባለቤቱን አናገረና ወደ አህያው ሄደ። ከደቂቃ በኋላ አህያው መሳቁን አቆመ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ባለቤቱ ተገርሞ ጠየቀው።

"እንዴት እንደዚህ ማድረግ ቻልክ?"

ጦና "ባለፈው በጆሮው የኔ ቸንቸሎ ከሱ ጀላ እንደሚበልጥ ነግሬው ነው የሳቀው" ሲል መለሰ።

"እሺ አሁንስ ሳቁን እንዴት አስቆምከው?"

"አውጥቼ አሳየሁት!" 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Gemechu merera fana
ጃፓን ውስጥ አንድ ሬስቶራንት አለ ።
እና የምግቡን ዝርዝር ወደኛ ቀይረን እንቀጥል
.....
በመጀመሪያ ቀን በዚህ ሬስቶራንት የተጠቀመ ሰው ሲናገር ፡ ወደ ምግብ ቤቱ ገብቶ አረፍ እንዳለ ፡ አንድ በእድሜ የገፉ አስተናጋጅ ተቀበሉት ።
ምን ልታዘዝ
" ምሳ ምን አላችሁ ? "
ትልቋ አስተናጋጅ ለሰውየው የሚፈልገውን ምግብ እንዲያዝ ሜኒውን ሰጡት
አተኩሮ ካየ በኋላ ፡ ...
"እሽ አንድ ጥብስና ፡ የሚጠጣ ደግሞ አምቦውሀ ያምጡልኝ "
....
አስተናጋጇ ትእዛዙን ተቀብለው ሄዱና ፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ ። ምግቡን ያዘዘው ሰው ፡ ባዶ እጃቸውን የመጡትን አስተናጋጅ እያየ ፡....
" ምነው አልደረሰም ? " ብሎ ጠየቀ .

ኸረ ደርሷል ይኸው ይዤ መጥቻለሁ አሉና የሂሳብ መጠየቂያ ቢሉን አቀበሉት ።
" ምንድነው ይሄ ፡ ከምግቡ በፊት ነው እንዴ ሂሳብ ? "

አስተናጋጇ ፈገግ እያሉ .... ኸረ በፍፁም ፡ አሁን የበላኸው ቅቅልና የለስላሳ መጠጡ ሂሳብ ነው

" እንዴ እኔ ያዘዝኩት ጥብስና አምቦውሀ ነው ፡ እሱም አልመጣልኝምኮ "

የዚህ ጊዜ ትልቋ አስተናጋጅ ስህተት እንደሰሩ ገባቸውና ፡ ይቅርታ ለካ ያንተ አይደለም ብለው ቢሉን ከሱ አጠገብ ላሉ ተስተናጋጆች ሰጧቸውና
ያንተን አሁን ይዤ እመጣለሁ ብለውት እየተቻኮሉ ወደ ኪችን ተመለሱ ።
.....
እና ብዙም ሳይቆዩ በእጃቸው ምግብ የያዘ ሰሀን ይዘው መጡና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠው ፡ ቆይ የሚጠጣውን ይዤልህ ልምጣ ብለው ሄዱ ።
......
ሰውየው የመጣለትን ምግብ አየው ። በቅቤ ያበደ የቋንጣ ፍርፍር ነበር ፡ አሁን ተናደደ እሱ ያዘዘው ጥብስና አምቦውሀ ነው ። በዚህ መሀል እያለ አስተናጋጇ የቀዘቀዘ ቢራ ይዘው ተመለሱና እየከፈቱ መልካም ምግብ ብለውት ሊመለሱ ሲሉ ፡ ጠራቸው ።

" እየውሎት እኔኮ ያዘዝኩት " .....ብሎ እየተናገረ እያለ ፡ አለመግባባት መኖሩን ያስተዋለው የሬስቶራንቱ ሃላፊ መጣና ቀረብ ብሎ የሆነ ነገር ነገረው ።

ሰውየው ልክ ይህን እንደሰማ መከፋቱን ትቶ እየሳቀ ምግቡን ተመገበ ።
........

በቃ እዚህ ቤት እንዲህ ነው ። የዚህ ቤት ደንበኞች በብዛት ስለቤቱ የሚያውቁና ፡ ዝናውን ሰምተው የሚመጡ ሰወች ናቸው ።
እና ምሳህን ቁርጥ ልትበላ ገብተህ ፡ ዱለት ሊቀርብልህ ይችላል ። የመጣልህን መመገብ ነው ። ብዙ ሰወች ፡ ክትፎ አዘው ፡ ተጋቢኖ መጥቶላቸው ያውቃል ።
እየሳቅህ በልተህ ትወጣለህ ።
......
ይህ ምግብ ቤት የተሳሳቱ ትእዛዞች ምግብ ቤት ( Restaurant of Mistaken Orders ) በመባል ይታወቃል ። የዚህ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ፡ Dementia በሚባል ፡ መርሳትን በሚያስከትል በሽታ የተያዙ ሰወች ናቸው ።
የምግብ ቤቱ ባለቤት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰወች የሚደርስባቸውን መገለልና ጭንቀት ለማስወገድ ሲል የከፈተው ነበር ።
.....
አላማውም ሰወች እነዚህን ወገኖች ከማግለል ይልቅ ፍቅር እየሰጧቸው የሳቅና የደስታ ምንጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ።
.......
እና በዚህ ቤት ስትመገብ እድለኛ ከሆንክ ከስንት አንዴ በትክክል ያዘዝከው ሊመጣልህ ይችላል ። ብዙ ጊዜ ግን ፡ ኬክ አዘህ ፡ ቁርጥ ከቢላ ጋር ወይም እንደሰውየው ጥብስ አዘህ ሳትመገብ የሂሳብ ቢል ይመጣልሀል ።
....
አሁን ላይ ይህ ሬስቶራንት በጃፓን ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡ ከሀገሬው ነዋሪ ሌላ ፡ ስለምግብ ቤቱ በሰሙ ቱሪስቶችም ይጎበኛል ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By wasihun tesfaye
' ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ። '
                                     ( ካሊድ አቅሉ)


ቤት ውስጥ አንዱን ጥግ ይዤ መፅሀፍ አነባለው ፣ ታላቅ እህቴ የሁለት አመት ልጅዋን እላይዋ ላይ አስቀምጣ ትመግባታለች ። ልጅትዋ እሺታን አታሳይም ምግብ ወደ አፍዋ ሲጠጋ ጥርሶችዋን ትገጥማለች ። የእናትዋን የበዛ ቁጥ ስታይ በየመሀሉ ፈገግ እያለች አፍዋን ትከፍታለች አየሀት ካሉ ልትሸውደኝ ስትሞክር አለችኝ  እኔም ስመለከታት ደገመችው አብረን ተሳሳቅን ወድያው አንድ ሀሳብ አይሞሮዬ ላይ ብልጭ አለብኝ እንዲህ የሚል ....

ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ፤ የራሱን ምቾት ለመጠበቅ ያንተን ፍላጎት በሳቅ ቃሬዛው ከፍኖ አርቆ ይቀብረዋል ። "አልሸወድም" ማለት በራሰ መሸወድ ቢሆንም የቅንነት መንገዳችንን ሊሸራርፉ የሚፍጨረጨሩ የመንገዳችን ተጓዦች መስመጫቸውን እያመቻቹ እንደሆነ ማስገንዘብ ያሻናል ።

by @kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
የሆነ ጊዜ አንድ ፍሬንዴ የሆነ ልጅ ትጠብስና ቤቱ ይወስዳታል:: ቁልፍ ይሰጣታል:: እንደቤትሽ እይው ብሎ::

ከዛ ዶሮ አሮስቶ እንደሚወድ ነግሯት ስለነበር ብትሰራልኝ ብሎ ከሱፐር ማርኬት ያለቀላት ዶሮ አምጥቶ ፍሪጅ ውስጥ አስቀመጠ::

ልጅት ቤቱ በሄደች ቁጥር ዶሮዋን ታያታለች: ፍሪጁን ልታፀዳ ታወጣትና : መልሳ ታስገባታለች::

ከሆነ ጊዜ በኃላ ልብ ስትል ዶሮዋ የለችም:: "ቤብ ዶሮዋስ?" አለችው::

እሱ:- "ውይ ሳልነግርሽ ተነሳች እኮ::"😂

ከዛ ብዙም አልቆዩ ተለያዩ::

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Mahi
text ገባልኝ :

"ግሩሜ ቸገረኝ ብር ላክልኝ "

"ስንት ብር ልላክልሽ?"

"አምስት ሺህ ብር
አካውንት ቁጥር 100056.... "

ቴክስቱን ሚስቴ አየቺው።
'ምን ማለት ነው ?! ፣ እ? ፣ ያልጨረሳችሁት ነገር አለ?!፣ በየግዜው ትገናኛላችሁ ማለት ነው ? ...." ብዙ ብላ በመጨረሻ "እንዳትሞክረው!" አለችኝ።

ዝም አልኳት : የመስማማት አይነት ዝምታ ።

እንደ ነጋ ባንክ ሄጄ አርባ ሺ ብር አስገባሁላት !

ሜሪ ላሁኑ ባሏ 'Achievement' ጥንካሬ ሰሊና ድርሻ ምን ያህል እንደነበር ብነግራት በሌላ ቀን ፣ በሌላ መንገድ ጭቅጭቅ ሆኖ ይመጣል ብዬ ነው ልቤ ውስጥ የቀበርኩት ! ።

ሰሊና እንዴት አይነት ደግ ፣ መለመን የማትችል ፣ ለገንዘብ ግድ የሌላት ፍጡር እንደሆነች፣ ይሄን ቴክስት ለመፃፍ ስንት ቀን እንደፈጀባት ፣ የላከችውን አሃዝ ለመፃፍ ስንቴ አሰላስላ እንደፃፈች እኔ ነኝ የማውቀው ።

እኔ አሁን የሆንኩትን እንድሆን የሆነችው መሆን ፣ የምወድቅ ሲመስላት ስንቴ እንደተጨቃጨቀች፣ እኔን ለማበርታት የሄደችው ርቀት፣ ሳገኝ በደስታ ፊቷ ላይ የሚነበበውን እልልታ ፤ማንም አያውቀውም ከኔ በቀር !።

ቸገረኝ ብላ ስትፅፍ እያለቀሰች እንደሆነ አውቃለሁ ፣ ስንት ብር ስላት እየተሳቀቀች እንደሆነ የፃፈችው ... ከስሜ በላይ እርግጠኛ ነኝ ።

የልብ እውነት ይኖራል እንጂ አይብራራም !!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/21 10:38:52
Back to Top
HTML Embed Code: