Telegram Web Link
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ከፊትሽ ለፍርድ ቆመናል!
ያጠፋም እንዲማር የማረም እንዲካስ ፍቃድሽ ይሁን!!
.......
ከአጭር ታሪክ የተወሰደ...
©Ribka Sisay
Feb, 06, 2022
@ribkiphoto
ሌላ ቀንም የአማን ጥያቄ ይከተለዋል ።

“አይ በዚህ ሰሞንማ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ! ሎተሪ ወይ ዲቪማ ወቶልሀል 

መሰለኝ ”

ማርኮን በውስጡ የሚጮኸው መልሱ እንዲህ ይላል ። ሎተሪ ምንድነው ? በዛ 

ቢባል ገንዘብ ... የተሻለ ቤት መኖር የተሻለ መኪና መያዝ ። ይሄ ማለት ግን 

የተሻለ ሰውን የማየት ያህል አያስደስትም ። ዲቪስ ምንድነው? ሀገርን ጥሎ 

መኮብለል ፣ ድህነትን ደህና ሰንብት ለማለት የሚጓዙት ዘመናዊ ባርነት ! ይሄስ 

በበረሀ መሀል የፈለቀችን ምንጭ ከማየት በላይ እንዴት ደስ ሊል ይችላል ?

በረሀው እነ ሳባ ናቸው ። ሁሉ ነገራቸው ግለት ነው ፣ ሁሉ ነገራቸው ወከባ 

ነው ። ይስቃሉ ፣ ሲስቁ ይጮሀሉ …….. ካ ካ ካ ብለው ሲገለፍጡ ሲያይ እንደ ካካ ይጠየፋቸዋል ። ሲያወሩ ለአፋቸው ልጓም የላቸውም ። ለፋሲካ እርድተገዝቶ ገበያ መሀል ውስጥ እንደደነበረ በግ መቆሚያ የላቸውም ። ያንን ያነሳሉ ፣ ይሄን ይጥላሉ ፣ ሰው ያንጓጥጣሉ ፣ ከእነሱ የበለጠች ሴት ስትመጣ ስሟን ያብጠለጥላሉ ።

ሁሉ ነገራቸው ትኩረት መሳብ ነው ። እዚህች ምግብ ቤት ውስጥ የምትመገቡ 

ክቡራን ተማሪዎች ሁሉ እኛን ብቻ እዩን የሚል ስግብግብ የታዋቂነት ስሜታቸው 

በግልፅ አፍ አውጥቶ ይጮሀል ።

እኛ ስልጡን ነን ፣ የተሻለ እንለብሳለን ፣ የተሻለ ሽቶ እንቀባለን ፣ የተሻለ ሜካፕ 

እንለቀለቃለን ፣ ከሁሉ እንበልጣለን ፣ ከሁሉ እንለያለን ፣ ፊታችሁን አመድ 

በወረሳችሁ ተማሪዎች መሀል ለተዓምር የወረድን ንግስቶች ነን ፣ የውበት 

ሹሞች ነን እወቁልን የሚል ጩኸት !

እሱ በጩኸታቸው መሀል በተዓምር የወረደ ፅሞና ይታየዋል ፤ ፀጉሯን ተኩስ 

ሳይነካት ተፈጥሮ ያለሰለሰላት ሴት ትታየዋለች ፣ የእግር ጣቶቿ ቀለምም 

ይሁን የሚለጠፍ ጥፍርን አይሹም ፤ ብቻቸውን ውበት ናቸው ። ተረከዟ እንደ 

በረሀ እንቧይ ይቀላል ። ቆዳዋ እንኳን ተነክቶ ታይቶ ራሱ ትንቡክ ብሎ እንደ 

ቲማቲም የሚፈርስ ይመስላል ።

ዝምታዋን ተሻግረው በስልት ከምትገልጣቸው ከናፍሮቿ መሀል ላይ እንደ ነጭ እርግብ ክንፍ የነጡ ጥርሶች አሉ ። አቀማመጣቸው እንደ ሰሜን ኮሪያ ወታደር 

በእኩልነት ነው ። ስድር ናቸው ። ፈገር ስትል ከጥርሶቿ ፍካት በላይ የተወቀረ 

ድዷ የውበት ፍላፃ ይወረውራል ። እንደ መጥቆር ያለ ድድ በስልት ከተሰደሩ 

ጥርሶች በላይ ሲታይ አጃኢብ ያሰኛል ። ዓይኗ አይቅለበለብም ፣ አይቅበዘበዝም። 

ቅርዝዝ ብሎ ይጮሀል ። ከዓይኗ ቆብ ላይ የሚታዩት የሽፋሽፍት ፀጉሮች 

አርቴፊሻል ከሚተከለው ምናምንቴ በላይ ውበቱ ይጎላል። የእጅ ጣቶቿን በርቀት 

አይቶዋቸዋል ። ትንሿ የግራ እጇ ጣት አናት ላይ ቢንቢ የነከሰቻት ምልክት አለ ። ምናባሽ ነው አለቅጥ እንደዚህ የምትቆነጂው? ብላ ቢንቢዋ ቀድማው ስለነከሰቻት ለመጀመያ ጊዜ ሰውነቱን ትቶ ቢንቢ መሆን ተመኘ። እሷ የነካችውን የእንጀራ ጠርዝ ፣ እሷ የተቀመጠችበት ብርኩማ ፣ እሷ የተራመደችበት መሬትን ባደረገኝ ምናለበት ? አለ። ደግሞስ ምን ያለው የወንበር ነፈዝ ነው ተቀምጣበት ስትነሳ ይዞ የማያስቀራት ? ምን ያለው ገልቱ እንጀራ ነው ገና ስትቆርሰው እኔ ልብላሽ ብሎ የማያሰፈስፈው ?

እሺ ከሷ በላይ ውበት ከየት ይምጣላቸው ? ሌላው ቢቀር እሷን የሚያስተምረው 

ጅማ ዩንቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስን ለምን ዓለም ተሰብስቦ አይሸልመውም 

? ለምን የምርጦቹ ምርጥ መዝጋቢው ጂንየስ ቡክ የእሷን ስም ከደረቱ ላይ 

አልተነቀሰውም ?

ዓለሙን ምን ነካው ? ሰው ፣ ተማሪው ፣ መምህሩ እና ሀገሬው እሷን አይቶ 

እንደዚህ እንደቀልድ ማለፍን እንዴት ቻለበት ? ወይስ ይህች ሴት ለእኔ ብቻ 

የምትታየኝ መንፈስ ናት ? ራሱን ጠየቀ።

“ እንጃ !” መልሶ ለራሱ ጥያቄ ራሱ መልስ ሰጠበት ።
Forwarded from Sunset Hiking
#Sunsethiking is hosting a day hike to " ENSARO"

💡Hiking Date :- July 10, 2021 (Hamle 03, 2014)

💵 Hiking Cost:- 900 ETB only

🛫Departure: Piasa (Taitu Hotel)
@12:30 LT

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 Guide + scout
🍂 photography 📷
💐 Breakfast
🏖 lunch
🧜‍♂️ Swimming
☕️ Coffee

💦Sanitizer & facemask mandatory!
☘️walking hour: 3 hour (up to 5 km of walking)
Hiking Level: Medium !

for more join the
🎸@sunsethiking👣
🏓@sunsetphotography📸
🍿@sunsethikers

🎫 tickets available at
@Paappii ( +251922303747)
አንዳንድ ትዝታ አለ
-ዝምታችን -ከዝምታ ገዝፎ በአርምሞ በተዘጋንበት ጊዜ :በዕዝነ ልቡናችን በኩል <<ኡኡ>> ብሎ የሚጮህ ፡፡ በለሆሳስ ÷በዝግታ ካሳለፍነዉ የእድሜ ዘመን፡ ቅፅበቶቻችንን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ ፡በልቦቻችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነዉ ፡ ተናፋቂ ትዝታወች መሀል ፡ ምናለ በደገምነዉ እያልን የምንመኘዉ፡፡
ከትላንት ትዝታወቻችን ጋር ፡ ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረዉ፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ ፡ እንደወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር ፡ በእምባ በተምሸርንበት ጊዜ እንኳ ÷ በሐዘን ወህኒ ተወርዉረን ፡ መረሳት ክፋ እድል ፊት ለፊታችን ሲጋረጥ፡ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ ÷በእቅፋ ሚያስጠልለን፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን ፡ የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ ፡፡ አነዳንድ ትዝታ አለ --- አየ ጉድ - ትዝ አለችኝ መሰል፡፡

ያብስራ እዮብ(ደብተራዉ)፡፡

@wegoch
#ዋንጫው
(ሚካኤል.አ)
"ቲቲን ቤቴ ልጋብዛት ነው" አለኝ ላሎ ።
በሀሳቡ ለመስማማት ታከተኝ...
"ዛሬ ብር አንባሩን ልደረምስላት ነው። የሆነ ፍንዳታ ከሰማህ እንዳትሳቀቅ" አለኝ ቀጥሎ ...ላሎ ዘናጭ ነው ። ሱፉን ግጥም አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተላከ ባለስልጣን ይመስላል ።
ደግሞ ቲቲን ሲተዋወቃት ደህንነት ነኝ ብሎ ነው። የሆነ ሰማኸኝ በለው ስልክ አለው ።
በዚህ ስማርት ዘመን ያን ስልክ ይዞ ሲንቀሳቀስ ያሳዝነኛል ።
የሆነ ቀን አንድ ግሮሰሪ ስንዝናና አንድ ለፍዳዳ ሰካራም እየደነሰ ላሎን ገፈተረው ።
ላሎ የመጀመርያውን ግፊያ በትዕግስት አለፈ ... ሰካራሙ ሰውዬ ጭራሽ እየተለፋደደ.. ."ወያኔዎችን ያባረርነው እንደዚህ መደነስ አምሮን ነው ... ኢንሶዳቲን " አለን። (አትፍሩ ለማለት የተጠቀማት የኦሮምኛ ቃል ነች። አካም አካም አትበሉ ብለው ጠሚው ፓርላማ ውስጥ የተናገሩትን አልሰማም መሰለኝ :) )
ሰካራሙ ጭራሽ ታስራ እንደተፈታች ጥጃ ፊታችን ቧረቀ...ደግሞ ላሎን ገፋው ... (ይቅርታ ደረመሰው ) ... የላሎ ትዕግስት ሙጣጯ ተፈፀመ ።
ከኪሱ ያን ድንጋይ ስልክ አንስቶ የሰካራሙ ግንባር ላይ አስቀመጠው ። ሰካራሙ ሊታረድ እንደተዘጋጀ በሬ አጓርቶ ወደቀ ።
ጭራሽ ከሰውየው ይልቅ ለስልኩ ተጨንቆ ተሯሩጦ አነሳት ።
ያ ስልክ ምን ይሆናል ብሎ እንደሆነ እንጃ!
ስልኩን ሲያነሳው እንኳን ሊሰበር ጭራሽ ከጥግ በኩል የተፈገፈገው ምልክት ጠፍቶ አዲስ ሆኖ አረፈው :)
በቃ ታድያ ላሎ ይሄን ስልክ ሲይዝ ደህንነት ነኝ የሚለው ጨረሩን ይለቃል።
"ተው ቲቲ ደህንነት ሳትሆን መምህር መሆንህን ያወቀች ቀን ጉድህ ይፈላል" ብለውም አልሰማ አለኝ። አሁን ደግሞ ጭራሽ ቤቴ ልጋብዛት ነው ሲል ከማርስ ላይ እንደመጣ ዩፎ ትኩር ብዬ አየሁት ።
ስጋቴን አልመከርኩትም...ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው ! ብዬ ንቄ መተዌ ነው ።
ከዛ በኋላ ስሰማ አምስት ኪሎ የምትገኘው ደሳሳ የኪራይ ቤቱ ሊወስዳት መንገድ እየሄዱ ሳለ አንዲት ሰይጣን የላካት ፈልፈላ "ቲቸርዬ " ብላ ተንደርድራ አቀፈችው ።
ቲቲ መብረቅ የወደቀባት ይመስል ክው አለች። የሎጥ ሚስትን ይመስል የጨው ሀውልት ሆና ቀረች ። (ምስኪን ቲቲዬ !)
ከዛ እንደምንም አምጣ "አስተማሪ ነህ እንዴ? " ብላ ጠየቀችው ።
እሱ ደረቱን ነፋ አድርጎ ...
"ይሄ ከቨር ነው...ደህንነት ሆነሽ በሽፋን ነው መስራት ያለብሽ " አላት.. . ተንደርድራ የተጠመጠመችበትን ፈላ እንደ ሎሚ አሽቶ እየጨመቃት ። (በውስጡ ልጅቷን እንደ ኳስ ማንጠር ሁሉ ከጅሎ ነበር )
ሀውልቷ ቲቲ የእየሱስ እስትንፋስ እንደደረሰው በሽተኛ ነፍስ ዘራች ና መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ልክ የላሎ ቤት ሲደርሱ ማመን አልቻለችም ።
ከቤቷ ጥበት የዝርክርክ ካልሲዎቹ ጥንባት ዊድ ሆኖ አዞራት ። ወደ ኋላ ተወነጨፈች።
እንኳን እግሯን ልትከፍትለት የልቧን በር ከርችማ ጥላው ፈረጠጠች (ያው ያለችውን መናገር ለሞራሉ ይከብዳል እንጅ እጅ ማስታጠቢያ ውስጥ እየኖርክ እኔን ስጀነጅን አይከብድህም ? ብላ ቅስሙን ከሽክሻለታለች)
በቃ !
ፍቅር በህንድ ፊልም ላይ ብቻ ያለ መንፈስ መሆኑ ያልገባው ላሎ ሱሰኛ ሆኖ አረፈው።
ሲጃራ እና ሺሻ ሲያንቦለቡል ትንሽ የገጠር ጎጆ ቤት የተቃጠለ ይመስል ነበር :)
ከዚህ ሙድ እንዲወጣ ብመክረው ብዘክረው እንደልማዱ አሻፈረኝ አለ ።
ዛድያ..ያ የተከበረ አስተማሪ ታድያ አንድ ቀን ሺሻ ቤት ሲያውደለድል በሰፈር ሚኒሻና በፖሊስ ተቀበደደ።
ሺሻ ቤቷ መልካቸው ከመወየቡ የተነሳ ያንድ አባትና እናት ልጆች በሚመስሉ ሱሰኞች ተሞልቶ ነበር ።
ከቤቷ ሲወጡ ...እንደ ዳርፉር ስደተኛ በሰልፍ ተቀጣጥለው ነው።
ለክፋቱ ደግሞ ሁሉንም የሺሻ እቃ አሸክመዋቸው በሰፈራችን በኩል ነበር የሚያልፉት ።
አቤት ሀፍረት !
አቤት ውርደት!
ምድር ደግሞ ለክፋቷ ተከፍታ አልውጥም አለቻቸው። ስንት ዶክተር ስንት ጠበቃ እየተግተለተለ ወጣ።
የላሎ አከራይቶ ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲከታተሉ ቆዩና ወደኔ ጠጋ ብለው.. .
"ላሎ የምን ዋንጫ ነው የያዘው ?" ብለው ጠየቁኝ።
"የዓመቱ ምርጥ አስተማሪ ተብሎ ተሸልሞ ነው"
"ፎሊሶቹስ ምንድናቸው?"
"ዋንጫው የወርቅ ስለሆነ እንዳይዘረፉ እየጠበቋቸው ነው "
እልልልልልል አሉ እትዬ...
"ላሎ ድሮውንም የሚያኮራ ልጄ ነው ... ተመስገንልኝ ያኔ መድሀኒተ ዓለም :) "

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
"አሹ ሁለት ብር ይዘሀል?" አለኝ የመንደራችን ቀፋይ፣ ከሁለት ቀናት በፊት
'ምን ይሠራልሀል?' አልኩት የሁል ጊዜ ሠበቦቹ ስለሚያዝናኑኝ
"እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው" አለ ሳቅ እያለ
ከኪሴ ድፍን አሥር ብር አውጥቼ እየሰጠሁት
'ካሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ ታገኛለህ፤ ሁለት ሜትሩን በሁለት ብር ይሸጥልሀል' አልኩት
"ታድያ አስር ብር ለምን ትሰጠኛለህ?" አለኝ ግራ ተጋብቶ
'በሥድሥት ብሩ ሶስት ሲጋራ አጭስ፤ በአንድ ብሩ መናዘዣ ወረቀት ግዛ' ብዬው ላልፍ ሥል
"የቀረችውን አንድ ብርስ ምን ላርጋት?" አለኝ በጭንቀት
'ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም!' አልኩት ኮሥተር ብዬ

ከሰዓት በሁዋላ ቀፋዬ ራሡን መሥቀሉን ሠማሁ።

ዛሬ፥ በሠልሥቱ ድንኩዋን ውሥጥ ካርታ እየተጫውትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ሥፖንሠር ሥላደረኩለት ማመሥገኑ ነበር!
.
.
.
.
'ማነህ ... ዳኛው፣ .... እስቲ ቦነስ ጻፍልኝ!'

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Ashenafi melese
" እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ ። በሳቁ ፣በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሬን ሳያበዛ ጭጭ ያረገኝ ። ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ? "

"የቱጋዬን ገድላ ሄደች? "

" ማን ?"

መልስ ፦ ተከሳሽና ተፈቃሪ


ካሊድ አቅሉ


ዳኛው ፦ " ተከሳሽ የክስ ማቅለያ አለሽ ?"

ተፈቃሪ ፦ " አዎ በጣም ያፈቅረኝ ነበር በህይወት ኖሮ ይሄን ቢያይ እንኳን ሞትኩ ነው ሚለው። "

ጠበቃ ፦ " እድሜ ልክ ነው መፈረድ ያለበት ሟችን ከሞት በላይ ገላዋለች "

እሷ የሞት ፍርዱን ትፈልጋለች ።
ለምን ቢባል አፍዋን ሞልታ ምትመልሰው መልስ አላት ።

"ለምን ? "

ከኔ ጋር ሰማይ ቤት ለመገናኘት ቀጠሮ አለን ያውም በግዜ ከሞትኩ ልትከተለኝ ከሄደች ቀድማ ልከተላት ።
" ያፈቀሩትን ሲያጡ ያገኙትን ይለማመጡ " በፍቅር አይሰራም በፍቅር ሚሰራው " የሚያፈቅሩትን ሲያጡ እራስን ማጣት ወይም እውነተኛ አፍቃሪ መፈለግ ነው ። "

አብዝቼ ወዳታለው አልፎም ገነት ላይ እየጠበኳት ነው ። የእሱ ገዳይ ተብላ እጇ ላይ ካቴና ታስሮ ፍርድ ቤት ገትረዋታል ።

እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ በሳቁ ፣ በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሪን ሳያበዛ ጭጭ አረገኝ ። ሳቅ አብዝታ ባጠገቤ እኔም ስርዋን ስምግ ሄድኩ እንደ ቀልድ ምድርን ትቼ . . .

ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ?

" ለመሞት ቀድሞ የወጣውም ጥፋተኛ ነው። "

ሊፈርዱባት ዳር ዳር ሲላቸው በድኑ አካሌ በር ከፍቶ ገባ ። " ነፍሴን ሰውታ አካሌን ለማን ነው ያስቀረችው ?"

"እንጃ "

አያለው ግን አላስተውልም ሰማለው ግን አላዳምጥም አለ አካሌ እኔው ጋር እኔው ነኝ እኔው ጋር የሌለውት ።
( ነፍሴ ተነጥቃለች )

አካሌ የሷ ጠበቃ መሆን ዳዳው መቼስ ነፍሴን ሰርቃለች ተብሎ አካልዋ አይቀጣም ።

ዳኛው ጎሮሮዋቸውን ጠርገው " ግራና ቀኙን አይተናል ፍርዱን ለከሰአት ።
አሉ የመዶሻውን ድምፅ በማስከተል ።


ይቀጥላል ክፍል 2 . . . . .

@wegoch
@wegoch
@paappii
ክፍል (2)
የመጨረሻው ክፍል

በተባለው ሰአት ፍርድ ቤት ቀረብን የሷን ፀጋ እነሱ ዘነጉት እንጂ የከሰመን ነፍስ ማፍፍት ድቅድቅን የምትሰልብ ፍፁም ስራ መሆንዋን እረስተዋል ወይንም አያውቁም አካሌ በድን የነበረውን የሷን ፍቅር ነስንሳበት ነፍሴን ፍክት አድርጋ ሙሉ አርጋ መልሳለች ። በነፃ ቢለቅዋት እንኳን ፍርድ ቤቱን ከሳ ካሳ መቀበል ያስፈልጋታል ።

" ለምን? " ቢባል

አማርሽ ብሎ መክሰስ ሳቅሽ ብሎ መውቀስ ምን ሚሉት ፈሊጥ ነው ?

ሰው በፀዳልዋ መቆም አቅቶት ከወደቀ እሷ ምን ታርግ አትራመድ አትናገር አትሳቅ አይባል . . .

በዚህ መሀል ከባድ የአላርም ድምፅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ አሻግሬ ሰአቱን ሳይ ሁለት ሰአት ከሀያ ደቂቃ ይላል ድንግጥ አልኩ ከህልም ችሎት ወደ መኝታዬ ምድር ስመጣ ።

አምስት ሚስኮልና አንድ መልዕክት አለህ ይላል ስልኬን ድጋሚ ሳበራው "ሶስት ሰአት ላይ የተለመደው ካፌ ጠብቅሀለው"
ይላል የተላከው መልዕክት ። የህልሜን አለም ለመንገር ወደምንገናኝበት ካፌ ነፍሴን ጥዬ እሮጥኩ . . . . .
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
በመፅሀፍ የሚገኝ ደስታ
ብሄራዊ ትያትር.. . Tommorow afternoon local 7.00
ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው ። መነሻችን የሰው ማህፀን መድረሻችን የሰውነት ስሪት ቀመር ነው።
ከሰው ማህፀን ተፈጥረን በሰውነት አፈር ውስጥ እንደበቃለን።
መድሀኒቴ እናንተ ናችሁ ... ስፅፍ የምናቤ ግብዓት ናችሁ ።
የፅሁፌ ትርፍ ገንዘብ አይደለም...አንድ መፅሀፍ ፅፈህ.. .ሀገር ምድሩ እስኪታዘብህ ፕሮሞት አድርገህ.. . ለሳምንት ምሽቶች መዝናኛ የሚሆን ትርፍ እንኳ አታገኝበትም።
ብዙ ደራሲዎች ለምን ትፅፋላችሁ ብትሏቸው መልሳቸው ምንም ነው። ስነ ፅሁፍ ልክፍት ነው... እያንዳንዱን ስራህን ቅርፅ አስይዘህ መሬት ስታወርደው አዲስ ፍጥረት ፕላኔቷ ላይ ያመጣህ ያህል ይሰማሀል።
ትርፍህ የሰው ሀሴት ነው። ለምሳሌ ሸግዬ ሸጊቱን ያነበቡ ሰዎች ሲደውሉ አንተ በፈጠርካቸው ታሪኮች ላይ በስሜትና ደስታ ሲያጫውቱህ የሚሰማህን እርካታ ብዬ ልገልፅልህ እችላለሁ?
...
ሸግዬዋን ነገ እንመርቃታለን። ሁላችሁንም ጋብዣችኋለሁ...ለብዙዎች በስልክም በቴክስትም እንዳትቀሩ ብያለሁ። ሌሎቻችሁም በስጋ ስራ ተወጥሬ ዘንግቻችሁ ቢሆን ይሄን ተረድታችሁ ነገ ተገኙልኝ።
ስትገኙ ከእናንተ የሚጠበቀው ፅሞናችሁን ይዛችሁ መምጣት ብቻ ነው።
ትኬትም ገንዘብም አልሻም...እናንተ መጥታችሁ በታላላቅ ገጣምያን እና ደራሲያን ስራዎች ተደስታችሁ መሄዳችሁ ብቻ ለኔ ክብር ነው ።
አክብሬ ጋብዣችኋለሁ።
አደራ !!
#ሚካኤል አስጨናቂ
የቤቱን ባለቤት እየናቁ እንዴት ቤቱን መውደድ ይቻላል ?

(ካሊድ አቅሉ )

ዊንታ ድምፅዋን ደመቅ አድርጋ አለምን በእስዋ ልክ ፈታች

" በአንድ ሳንቲም ሰውና አንበስ መሆን አንበሳው ካልቀና ወደ ሰው . . . "

ስንቴ ምንኖር መሰላት ? የምር አሁን ካልኖርን መች እውነተኛ ኑሮን እናጣጥማለን ህይወት ትርጉምዋ ማይገባን ደስታን ከገንዘብ ጋር በማስተሳሰራችን ይመስለኛል ያለመርካት እሳቤን ስናሳድድ በሞት እንቅፋት ተደፍተን መቅረት ። የውሸት ኖሮ የእውነት ሞት ።

መለስ አልኩና " እኔ ምልሽ ዊንታ መች ለማግባት ታስቢያለሽ ? "

" እእ ሀብታም ባል ብቻ ይምጣ መልኩ ውስጣዊ ውበቱ አልልም ጥልቅ ነው ምለው " ፈጣሪ እራሱ ሲጣንን ወደ ገሀነም ሲወረውር እንዲ አልፈጠነም ።

መዋደድን ፍቅርን ስብዕናን ህሊናን በሲኖትራክ ስትወጣባቸው ዳር ሆኚ አይኔን ይዤ የምታዘብ ይመስል ቀፈፈኝ ። ፍቅር እኮ ይቀድማል ትዳርን ያሳደገው መዋደድ አይደል ? የቤቱን ባለቤት እየናቁ ቤቱም መናቅ ይቻላል ?

" ያርግልሽ ባይባልም ለሀብት ያለሽ ቦታ ትዳርን ሳይሆን ሀብትን ምታገቢው ያስመስልብሻል ሀብታም ባል ቤት ያለው ድርጅት ያለው ዱባይ ሚያዝናና. . . "

" ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም ያሉት ሁለት ለተራራቁ ዛፎች ነው ጥንድ የቆሙ ዛፎች ከሆኑ እግርን አንድ ላይ ገላን አንደኛው ላይ ማሳረፍ ይቻላል ። "

ልቆቆማት እንዳልቻልኩ ተሰማኝ ግን የተሸናፊ ወግ መሀል ላይ አሸናፊ መምሰል ነው ። ለዘብ ብዬ ቀጠልኩ " አትሸወጂ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አንድ ሰውነት ሁለት ቦታ መክፈል ከባድ ነው ። ለአንዱ ላይ የሚወጣን ሀይል ሁለት ቦታ ከፍሎ ተንገላቶ ማለፍ ነው ። " መድፍ የሆነ መልስ ልካብኝ እሮኬት መልስ ላኩላት አፍዋን ጥያቄዋን መልስዋን ድማሚት እንዳገኘው ከተማ ብን አለ ። ፍርስራሾችዋ ብቻ ሰው ፊት ያንዣብባሉ አስተሳሰብዋ ብን ብሎ ጠፍቶ መልስ ሳይሰጠኝ አካልዋ በድን ሆኑ ጥላኝ መንገዱን ቁልቁል ተያያዛችው ወደ ታች የሚወርደው ገላዋ የስብዕናዋ ማሳያ ሆኖ ታየኝ የሚወርድ እግር የሚወርድ አይምሮ . . . .

@KALIDakelu

ሼር!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፍቅር ና ጦርነት

ክፍል 1

ጳጉሜ 3 2013 ዓ.ም

ከቀን ወደቀን ቢሻለኝም የክረምቱ ብርድ ህመሜን ጨምሮታል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለሠው ድጋፍ መንቀሳቀስ ችያለሁ ሠፈር ውስጥ ዞር ዞር ማለት ጀምሬያለሁ ። እንዲያውም ከሞት ያተረፈኝን ለቤቴ ያበቃኝ አምላክን ለማመስገን ወደ ቤተ-ክርስቲያን እየሄድኩ ነው ። ለዚህ እበቃለሁ እግሮቼ እንዲህ መንቀሳቀስ ይችላሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከ 2 ወር በላይ ከተቀመጥኩበት ዊልቸር እነሳለሁ እንዳሁኑ እንቀሳቀሳለሁ እንደ ሰው ቆሜ እሄዳለሁ ሚል ምንም ግምት አልነበረኝም ታዲያ እኔ አምላኬን ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ከሞት መንጋጋ ያተረፈኝ ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ማንም ለዛነው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለማመስገን ማሰቤ።

ዝናቡ ሚያቆም ባይሆንም ለብርዱ ልብስ ደራርቤ ከቤት ወጣሁ ፧ ከቤታችን በቅርብ የሚገኘው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት ቤተክርስቲያን ስለሆነ ስምልም ረሱ መድዬን ብዬ ነው ለቤታችን ቅርብ ነው 20ደቂቃ ቢፈጅ ነው አሁን ግን ለኔ ከ 45_60 ደቂቃ ሳይፈጅብኝ አይቀርም እራሴን ጠንክር በል ብዬ ጉዞዬን ጀመርኩ ።

መንገድ ላይ ብዙ ሰው ጋር አልተገናኘሁም በዝናቡ ና ገና ጥዋት በመሆኑ ምክንያት ግን ያገኘሁት ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ነው ሚያልፉት ሀዘኔታ ይሁን መገረም ባይገባኝም ምንም ምቾት አልሰጠኝም ። ወደ ቤተክርስቲያን እየደረስኩ ስመጣ ሠውነቴ በጣም ዛለ ድካም ተሰማኝ እንደምንም ብዬ የ ቤተክርስቲያኑን መግቢያ ተሳልሜ ለምእመናን ወደ ተሰራው መጠለያ ገብቼ አረፍኩኝ ። የተጎዳችው እግሬ ህመም መቋቋም አቃተኝ ስልኬን አውጥቼ ስመለከት ከቤት ከተነሳው 50 ደቂቃ ሆኖኛል በጣም አዘንኩ 50 ኪ/ሜ በምጓዝበት እግሬ 50 ደቂቃ ተጓዝኩ ብሎ እንዲህ መሆኑ አናደደኝ አይሰው መሆን ከንቱ በተፈጥሮ ተገረምኩኝ ግን ምንም ቢሆን መጠንከር እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት ። በመጠለያው ትንሽ እንደቆየው ያላስተዋልኩትን ነገር አስተዋልኩ ያለሁበት በሴቶች ቦታ ነበር ድካሜ ሲጠፋልኝ ቦታ ለመቀየር ከተቀመጥኩበት ስነሳ እግሬ አቅም አቶ ወደድኩኝ ። ከየት መጣች ያልተባለች ልጅ "እኔን " ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እኔ ማየው አፍዞኛል መላክ ያየው መሰለኝ ክንፉን የዘረጋ ግን ሴት መላክ ከየት መቶ ፤ ደሞ ማነው መላክን ወንድ ያረገው ብቻ ግራ ገባኝ አምላክ ለኔ የላካት መሰለኝ ባይኔ አካሏን ስቃኘው እንደኔው ፍጡር ናት ፈራሽ ገላ ነው የያዘችው በዛችው ደቂቃ አዘንኩላት ከገነት ተባራ ምድር ላይ ምደክም እንጂ እንደ ሰው የሁለት ሠዎች ውጤት አትመስልም ግን ምን መድረግ ይቻላል እንደኔው ፍጡር ናት ........

ክፍል 2 ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 2

"ወንድም ተጎዳህ እንዴ.. ወንድም " ብላ እጄን ስትይዘው ከሀሳቤ ነቃው እንደምንም በሷ እገዛ አመቺ ቦታ ተቀመጥኩኝ እግሬን እንደ ፈለኩኝ ማንቀሳቀስ እንደማልችል ስትረዳ " እግርህን ሚያምህ ከሆነ ለምን መደገፊያ ክራንች ወይም ሚደግፍህ ሰው ሳትይዝ መጣህ " እንዳ ቀረቀረች ጠየቀችኝ "አይ ተሽሎኝ ነበር እኮ ትንሽ ስንቀሳቀስ ነው ያመመኝ " የእግሬ ህመሙ ሲብስብኝ በእጄ ጠበቅ አርጌ ያዝኩት "አይዞህ አምላክ ይርዳህ" ብላ ለመሄድ ስትዘጋጅ መንቀሳቀስ እንደማልችል ና ከሷውጭ ሊረዳኝ ሚችል ሰው እንደ ሌለ የቤተክርስቲያኑ መውጫ ደረጃውን ለመውጣት እንድትረዳኝ ስጠይቃት እሺታዋን ገልጻልኝ አስከምረጋጋ አብራኝ ቁጭ አለች ።

ለደቂቃዎች ሳናወራ ብንቆይም አለባበሷን አይቼ በዚህ በብርድ እንዲህ መልበሷን ና ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ገርሞኝ "ይህ አለባበስ ለቤተክርስቲያን ይፈቀዳል" ብዬጠየኳት እንዳቀረቀረች ፀጉሯን እያስተካከለች "ሰው ነው እንጂ አምላክ ልብስን አያይም የልቤን ችግር ደሞ እሱ ያቃል " ብላ ለይስሙላ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ውስጥ ሀዘን አለው ፈገግታዋ ውስጥ መጎዳት አለው ፈገግታዋ ውስጥ ብቸኝነት አለው ።

የለበሰችው ልብስ ስስ የሌሊት ልብስ ሲሆን ሰውነቷን በከፊል ያሳያል ፀጉሯ ፊቷን ካልሸፈንኩ ካልሸፈንኩ ሚል ይመስላል እርዝመቱ መጋረጃ እንጂ ፀጉር አይመስልም እግሮቿ በጭቃ ተበላሽተዋል ውበቷን ግን አልቀነሱትም ትኩር ብዬ ከተመለከትኳት በኋላ እንደበረዳት ገባኝና የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ ሰጠኋት ፧ ትንሽ ብትግደረደርም ተቀብላኝ ለበሰችው ሰውነቷ ተፍታታ እንደንጋት ጮራ ፊቷ አበራ "ስምሽ ግን ማነው " ድንገት ጠየኳት ፈገግ ብላ " ፀጋማርያም እባላለሁ " አለችኝ እውነትም የማሪያም ፀጋ በግርምት ላይ ግርምት ጨመረችብኝ አድናቆቴን በሆዴ ደብቄ መሄድ እንደምንችል ነግሬያት ብድግ ስል እሷ ቀድማ ተነስታ ደግፋ አነሳችኝ እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ መንገዳችን ጀመርን ።

የቤተክርስቲያኑን መውጫ አልፈን ዋና መንገዱ ላይ ስንደርስ ካልቸኳለች ቤቴ ቅርብ ስለሆነ እንድታደርሰኝ ጠየኳት ችግር እንደሌለው ነግራኝ መንገዳችንን ቀጠልን ፤ ቤት እስክንደርስ ስለብዙ ነገር አወራን ። በብዛት ስለራሷ ባትነግረኝም ችግር ውስጥ እንደሆነች ነገረችኝ እኔም ምን ሆኜ እንደተጎዳው ብጠይቀኝም በጦርነት ተጎድቼ እንደሆነ ብነግራት ትፈራለች ብዬ በቀልድ አድርጌ አለፍኩት የተለያዩ ነገሮችን እያነሳን እየተጨዋወትን ቤት ደረስን።

የጊቢውን በር ከፍቼ ወደውስጥ ገባን ቤቱን ከቤተሰብ የወረስኩት እንደሆነና ሁሉንም ክፍሎች ዋናውን ቤት ጨምሮ አከራይቼ እኔ ጥግ ላይ ያለችው ቤት ውስጥ እንደምኖጋ እያስረዳኋት እያለ ስልኬ ጠራ ቤቱ ክፍት እንደሆነና አውርቼ እስክጨርስ ገብታ እንድትጠብቀኝ ነግሬያት ስልክ ማውራት ጀመርኩኝ ። በጣም አስፈላጊ ስልክ ስለነበር ሳላስበው ብዙ ደቂቃ አወራው ስልኩን ጨርሼ ወደቤት ስገባ እንደ ህፃን ልጅ ጥቅልል ብላ ተኝታለች መላክ ይተኛል እንዴ ? ደሞ ማማሯ ውበት ማለት አንቺ ብሎ የተዘፈነው ለሷ ይሁን እንዴ ........

ክፍል 3 ይቀጥላል ......

@wegoch
@wegoch
@paappii
@wegoch
@wegoch
@paappii

#Narrated by Rediet

Written bye Ashenafi melesse
Audio
===ቀልዶች በጃንሆይ ዙሪያ===
አፈንዲ ሙተቂ
--------
እስቲ ዛሬ ደግሞ ልዑል ተፈሪ መኮንን “ግርማዊ ጃንሆይ” ከሆኑ በኋላ የተቀለደባቸውን ቀልዶች እናካፍላችሁ፡፡
------------
ሁለት ሰዎች እየተጨዋወቱ ነው፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይወዳል፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይጠላል፡፡ ጃንሆይን የሚወደው ሰውዬ “ግርማዊ ጃንሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ” አለ፡፡ ጃንሆይን የሚጠላው ሰውዬ በጥፊ ከመታው በኋላ እንዲህ አለው፡፡
“አንተን ብሎ እድሜ ቆራጭ! ግርማዊ ጃንሆይ ለዘላለም ይንገሡ አትልም ነበር?”
------------
ግርማዊ ጃንሆይ የአማኑኤል ሆስፒታልን ሊጎበኙ ሄዱ፡፡ አንዱ ሻል ያለው እብድ እንዳያቸው ተጠጋቸውና “ማን ትባላለህ?” አላቸው፡፡
“ሞአ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነን” አሉት ጃንሆይ፡፡
ይህንን የሰማው እብድ ሳቅ እያለ “ጉድ ነው! እኔንም እብደት ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ” አላቸው፡፡
(በርሱ ቤት ጃንሆይ ሊታከም የመጣ እብድ መስሎታል)
------------
እነ ኒል አርምስትሮንግ ጨረቃን ረገጡና ዓለም ጉድ አለ፡፡ የዓለም መሪዎች ወደ ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ ጆንሰን የደስታ መልዕክት ማጉረፍ ጀመሩ፡፡ እንደ አጋጣሚ አሜሪካ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይሥላሴም እንዲህ አሉ፡፡
“ጨረቃ ላይ በመውጣት የሰራችሁት ስራ ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝብም ኩራት ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ተመራምራችሁ ጸሐይ ላይ እንደምትወጡ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኋን”፡፡
ከጃንሆይ አጠገብ የነበሩት ልጅ ይልማ ዴሬሳ ደነገጡ እና “ጃንሆይ ጸሐይ ላይ መውጣት አይቻልም እኮ” አሏቸው፡፡ ጃንሆይም በስጨት ብለው “አንተ ደግሞ አቃቂር ታበዛለህ! እኛ መናገር እንጂ ስለሌላው ምን አገባን? ቢፈልጉ ጸሐይቱ እንዳታቃጥላቸው ማታ ማታ ይጓዙና ይውጡ!”
------------
የዩጎዝላቪያው ማርሻል ቲቶ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ካበቁ በኋላ ለጃንሆይ “ሀገራችሁ ጥሩ ናት። ግን ሰዎቻችሁ በየጎዳናው ይሸናሉ” አሏቸው። በሌላ ጊዜ ጃንሆይ ዩጎዝላቪያን እየገበኙ ሳለ በጎዳና ላይ የሚሸና ሰው አዩ። በዚህን ጊዜም ወደ ሰውዬው እያመለከቱ ለማርሻል ቲቶ “ተመልከት! ያንተም ሰዎች በመንገድ ላይ ይሸናሉ” አሏቸው። ቲቶ በጣም ተናደዱ። ወታደሮችን ጠርተው “እዚያ ወዲያ የሚሸናውን ሰውዬ ይዛችሁ ወደኔ አምጡት” በማለት አዘዟቸው። ወታደሮቹ ሰውዬው አጠገብ ከደረሱ በኋላ ባዶ እጃቸውን ተመለሱ።ቲቶም “ለምን አልያዛችሁትም?” አሉ።
“ይቅርታ ማርሻል የዲፕሎማቲክ መብቱን መድፈር አልቻልንም”
“የምን የዲፕሎማቲክ መብት?”
“ሰውዬው አምባሳደር ነው”
“የየት ሀገር አምባሳደር?”
“የኢትዮጵያ”
---------
ጃንሆይ እና ጸሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከተማ ወርደው መዝናናት አማራቸውና ተያይዘው ወጡ። የተቻለውን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ መሸ። በፒያሳ በኩል ወደ ቤተ መንግሥት በመመለስ ላይ ሳሉ ሲኒማ ኢትዮጵያ ደረሱ። “እስቲ እዚህም ገብተን ትንሽ እንይ” አሉና ወደ ሲኒማው ገብተው ከተመልካቾች ተርታ ተቀመጡ።
በዚያ ዘመን ቴሌቭዥን በየቤቱ ስለሌለ ህዝቡ ወደ ሲኒማ ሄዶ ነው ዜና የሚከታተለው። በዜና ላይ ጃንሆይ የታዩ እንደሆነ ደግሞ ማጨብጨብ የዘመኑ ደንብ ነው። ታዲያ ዜና አንባቢው “ግርማዊ ጃንሆይ ዛሬ የጃፓን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ” አለና ዜናውን በምስል አቀረበው። ይሄኔ በአዳራሹ የነበረው ጠቅላላ ህዝብ አጨበጨበ። አሁንም ሌላ የጃንሆይ ዜና ቀረበ። ህዝቡም አጨበጨበ። ሌላ የጃንሆይ ዜና ተከተለ። ህዝቡ አፍታ በአፍታ ማጨብጨቡን ቀጠለ። ጃንሆይና ጸሓፌ ትዕዛዝ ግን አላጨበጨቡም። ይህንን ያየ አንድ ጎልማሳ ተመልካች ወደ ጃንሆይ ተጠግቶ “ሽሜ! ጉድ ሳይፈላብሽ ብታጨበጭቢ ይሻልሻል” አላቸው።
---------

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 3

እናት ልጇ ተኝቶ በስስት እንደምትመለከተው እኔም ፀጋን በስስት አይን አይኗን እያየኋት በአምላክ አፈጣጠር እየተገረምኩ ቀኑም ሳላስበው መሸ .... ደመናማ ቀን ስለነበር መምሸቱን ያወኩት ሁሌም እራት ምታመጣልኝ ለምለም ስትመጣ ነው ። ለምለም እናቴ ከመሞቷ በፊት የቅርብ ጓደኛዎ ነበረች እናቴ በእድሜ ብትበልጣትም ለምለም በሂወት ብዙ ያየች ሴት ናት በኢትዮ_ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ኤርትራውያን ወደሀገራቸው ሲባረሩ እናቴ ናት ጓደኛዬ የትም አትሄድም ብላ መታወቂያ አውጥታ ያስቀረቻት ፤ አንዳንዴ እናቴ ትዝ ስትላት ....
"ጦርነት መጥፎ አባረረኝ ፍቅር ደጉ አስቀረኝ " ትላለች

ከህክምና ከመጣሁ ጀምሮ ከለምለም ውጪ ሴት ቤቴ ገብቶ ስለማያውቅ እንደ ሌላ ቀን ሳትቀልድ ሳትጫወት
"በል እኔ ልሂድ ስለዚህ ነገር ግን ነገ እናወራለን " ብላ ድምጽ ሳታሰማ ሄደች ።

በለምለም ድርጊት እየተገረምኩ ፀጋን ከእንቅልፏ ልቀሰቅሳ አስቤ እንዴት እደምቀሰቅሳት ግራ ገባኝ ስቀሰቅሳት ልደነግጥ ስለምችል በራሷ ጊዜ እንድትነቃ የTV ድምጽ ጨመርኩት ፤ ትንሽ ደቂቃ ቆይታ ነቃች ፊቷን የሸፈኑትን ፀጉሯን እያስተካከለች ደንግጣ ተነሳች ...
"መሸ እንዴ"
በመስኳት ውጪ ውጪ እያየች
" አይዞሽ መኪና ጠርቼ እስከ ምትሄጅበት እሸኝሻለው "
ስላት ፊቷ ተቀያየረ ቀስ ብላ ተቀመጠች ምን እንደሆነች ብጠይቃትም መልስ አልሰጠችኝም ። ለደቂቃዎች ዝምታ ሰፈነ እዚህ እንድታድር ብፈልግም እንዴት ልጠይቃት ፈራው በኋላ ሌላ ነገር ያሰብኩኝ ቢመስላትስ አይ ይቅርብኝ ብዬ ዝም አልኩ ። በዛች ቅፅበት አምላኬ ፀሎቴን የሰማ መሰለኝ ክረምትን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደድኩ በስራዬ ምክንያት ክረምት ደስ አይለኝም ወታደር መጠለያ ስለሌለን ዝናብ አንወድም እንደውም አንድ የውጪ ዜጋ የኢትዮጵያን ወታደር ካየ በኋላ .."የኢትዮጵያ ወታደር ዝናብ ሲዘንብ ወደቤት ጥይት ሲዘንብ ወደ ሜዳ " ያለው እስካሁን አረሳውም ።

አሁን ግን አስፈላጊ ስዓት የሰማይ ቀዳዳዋች ተከፍተው ሀይለኛ ዝናብ ዘነበ በዚ ዝናብ እሄዳለሁ እንደማትል ገመትኩ ።

ጉሮሮዬን እየጠረኩኝ " ፀጋ ለምን እዚህ አታድሪም " ልቤ እየመታ ጠየኳት ካቀረቀረችበት ቀስብላ ቀና ብላ " አይ ላስቸግርህ አልፈልግም ባይሆን ዣንጥላ አለህ " አለች በሚያምር ድምጿ እንኳን ሰውን እንስሳትን በሚያራራ ቃና እኔን ግን ልቤን አደነደነው ...." የለኝም ያለሽ አማራጭ እዚህ ማደር ነው ደሞዝናብ ነው በዛላይ መሽቷል አንቺ የዛን ያህል ረድተሽኝ አንቺን በዚህ ጨለማ ለጅብ አልሰጥሽም ባይሆን ነይ እራት እንብላ " ሳላስበው ስሜታዊ ሆንኩኝ የበፊቱ መቶ አለቃ አብርሃ ወኔ መጣብኝ

ሳላስበው የተቆጣኋት መሰለኝ ግን በዚህ ጊዜ ያለኝ አማራጭ እሷን እዚህ ማቆየት ብቻ ነው ፤ በማላቀው መንገድ ልቤ እንዳትለቃት እንዳትለቃት ይለኛል ልብን መስማት አደጋ ቢኖረውም ምንም አማራጭ የለኝም ፤ በረጅሙ ተንፍሳ ምንም አማራጭ እንደሌላት እና ባረኩላት ነገር አመስግና እራታችንን መብላት ጀመርን እርቧት እንደነበር ለመረዳት አልተቸገርኩም ከኔ ጋር እራሱ ከተገናኘን 11 ስዓታት ተቆጥረዋል ከዛ በፊት ምግብ ሳትበላ ምንያህል እንደቆየች አምላክ ብቻ ነው ሚያቀው ፍሪጅ ላይ ከነበረ ምግብ ጨምሬ ተመስገን እስክትል ተመገበች ።

የበላንበትን አነሳስታ ስልክ እንዳስደውላት ጠየቀችኝ ስልኬን ሰጥቻት በረንዳ ላይ ሆና ማዋራት ጀመረች ባላሰብኩት መንገድ ንግግሯ ሳበኝ የደወለችው ለሴት ጓደኛዎ ነበር እንዳልሰማት በትግርኛ ነበር ያዋራቻት ።

እድሜ ለእናቴ ጓደኛ ለምለም ና አብዛኛውን የውትድርና ጊዜዬን ያሳለፍኩት ትግራይ ስለነበር ትግርኛ እችላለሁ ። አውርታ ስትጨርስ መኝታዋን አዘጋጅታ ተኛች እኔ ግን እንቅልፍ እንቢ አለኝ እንዴት ይህን ነገር ሰምቼ እንቅልፌ ይምጣ የአንድ ሰው ሂወት እየተበላሸ እያየው እናት ና አባት ልጅ እየሸጡ ፣ በቤተሰብ ችግር ልጅ ሲበደል እያየው እንዴት ብዬ እቺን ነብስ እንዴት እንደማተርፍ እያሰብኩ እንቅለፍ ወሰደኝ ......


ክፍል 4 ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii

@takitafu79
2024/09/22 09:39:27
Back to Top
HTML Embed Code: