Telegram Web Link
"እሁድና ተከራዮቹ"
እሁድ ረጅም ቀን ነው ከሚሉት ወገን አይደለሁም! እሁድ ጠዋት ያጋባኃቸውን ሙሽሮች ከሰዓት አፋትቻለሁ እያልሁም አቃቂር አላወጣለትም:: እሁድን እወደዋለሁ! እስኪመጣ እናፍቀዋለሁ! እንዳያልቅብኝ እሳሳለታለሁ! እሁድ መጥቶ በጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ተግባሮቼ የታቀዱ ናቸው:: ቅልጭብ ያለች እቅድ! የማትፈርስ የማትታደስ!

ዛሬም እንደወትሮው ከእንቅልፌ የነቃሁት የጅጂን ለስለስ ያለ ሙዚቃ እያዳመጥኩ ነበር:: ጉራማይሌ ትላለች:-

"ጉራማይሌ ልጁ:
ጉራማይሌ ቋንቋው:
ጉንፌን አዉልቄ ለበስሁኝ ቦላሌ::"

ያን ጉራማይሌ ልጅ አሰብሁት:: ምን አይነት የአማላይነት ጥበብ ቢኖረው ነው ጉንፍ የሚያስወልቅ? ያውም በዛ ዘመን? ያዉም የጂጂየን! ጉራማይሌ ወንድ መሆን አማረኝ! ቦላሌ አስወላቂ (ጉንፉ በኛ ዘመን ከወለቀ ቆይቷል ብዬ ነው)

የተከራየሁበት ቤት ብዙ ተከራዮች ከመኖራቸው የተነሳ በስም አይደለም በ መልክ እንኳን አንተዋወቅም:: የሚገርመው ግን ለዛ ሁሉ ተከራይ አንድ ማረፊያ ቤት (ሽንት ቤት ሲቆላመጥ) ብቻ ነው ያለው:: ታዲያ የተከራይ መከራ የሚጀምረው ሻዉር መወሰድ የፈለገ ጊዜ ነው:: በርግጥ ብዙ አማራጮች አሉት:: ወይ መዘፍዘፍያዉን ይዞ ቤቱ መታጠብ:: አሻፈረኝ ካለ ደግሞ ሰው የማይኖርበትን ሰዓት ጠብቆ ማረፊያ ቤት ዉስጥ ዉሃዉን በጀሪካዉ አስገብቶ መታጠብ ነው:: ይሄኛው የብዙወቻችን ተከራዮች ቁጥር አንድ ምርጫ ነው:: ይህንን አማራጭ መጠቀም ከፈለጉ ግን ከሻወር እንደወጡ ጥሩ መአዛ ያለው ሽቶ ሊኖርወት ግድ ይላል:: ካልሆነ ከማረፊያ ቤት ይዘዉት የሚወጡት መአዛ ቀኑን ሙሉ ስያጅብወት ይዉላል::

አረ ይሄ ሁሉ ስቃይ ለምኔ ያሉ ደግሞ ክረምት ሲመጣ ዝናብ ሲዘንብ ጠብቀው የሚታጠቡ እንዳሉ ሰምቻለሁ:: አሉባልታ ነው:: የአሉባልታው ባለቤት ማነው? ካላችሁ ደግሞ አያንቱ ነች:: (አያንቱ የግቢያችን ደንበኛ ወሬ ለቃቃሚና አከፋፋይ ነች):: እሷ የምታወራው ዉሃ በጨው ነው ይሏታል (ጨው እዉነቱ ሲሆን ዉሃው ደግሞ እሷ በብዛት የምትጨምረው ዉሸት መሆኑ ነው!)

አሁን በቀደም ለት ከግቢው በር ደገፍ ብዬ እንደልማዴ ጂጂየን እያደመጥሁ ብታገኘኝ ጠጋ ብላ ወሬ ጀመረችልኝ::

ከወሬ ወሬ "ስማማ ኤልያስ ዛሬ ማታ ያየሁትን ጉድ አታምንም!
"የምን ጉድ ነው አያንቱ?"
"ሌሊት ዝናብ ሲዘንብ አገር ሰላም ብዬ ልብስ ማጠቢያ የሚሆን ዉሃ ለማቆር ከፍቼ መዉጣት.. "
"እሽ "... አነጋገሯ ጉጉትን የሚጭር ነው:: እናም ተሳክቶላታል:: እሽ አባባሌ ቶሎ ንገሪኝ በሚል ቅላፄ ነው::
"ከዛማ ይች ሄለን....በስማም ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ!" ብላ ሶስት ጊዜ አማተበች::
"እኮ ንገሪኛ ምንድን ነው እሱ? ሄለን ምን?" ልቤ ልትወጣ ደረሰች:: የሄለን ስም መነሳቱ ደግሞ ይበልጥ ልቤ እንዲመታ አደረገው::
" አረ እንደው ተወኝማ!" ወይኔ ኤልያስ ነገር ቆስቁሶ የምን ተወኝ ነው? ያዉም የሄለን ስም ተነስቶ! ሆሆ!
" ንገሪኛ!" መቆጣት ቢያምረኝም ቅሉ ዉጤቱ ጥሩ እንደማይሆን በመገመት ተዉኩት::
"ሄለን እ.ራ.ቁ.ቷ.ን ሁና እ.ራ.ቁ.ቷ.ን (ደገመችው) በሚወርደው የዝናብ ዉሃ ገላዋን እየታጠበች! ቱ ቱ ቱ ወይ ዉርደት" ብላ ሶስቴ ወደ መሬት ተፍታ እራሷን ያዘች:: እራቁቷን የሚለዉን ቃል እያንዳንዷን ሆሄ እየቆጠረች ነበር የገለፀችው::
"ከምርሽ ነው አዩ? (አቆላምጬ እንደጠራኃት ያወኩት ዘግይቼ ነው)
"እኔ ልሙትልህ ኤልያስ! ብታይ እርቃኗን እኮ ነው:: እራፊ ጨርቅ እንኳን አላደረገችም"

ሄለን ወደ ሽኖ ቤቱ በሚወስደው መንገድ ላይ የመጨረሻው ዶርም ተከራይ ነች:: ሴተ ላጤ ከመሆኗ በላይ ጠይምም ቀይም ያልሆነች (ቸኮሌታማ ከለር የሚሉት አይነት የቆዳ ቀለም አለ አይደል? አወ ልክ እንደሱ አይነት):: ከንፈሮቿ ሲከፈቱ የተፈለቀቀ ጥጥ የሚመስሉ! የሚያምሩ ጥርሶች ከሚያምር ፀጉር ጋር የታደለች:: ብልጣብልጥ ትንንሽዬ አይኖች ያሏት:: ትንንሽ አይኖችሽ የዉበት መግለጫ አይደሉም ያለው ማነው? ሂዱና የሄሉን አይኖች እዩ:: ትናንሽ አይኖች የዉበት ኩራዝ መሆናቸውን ያያሉ:: በቁመቷ አጠር ብላ ወደ ኃላዋ ሞላ ያለ (ሞንደል ሞንደል የሚሉት አይነት ዳሌ) ያላት ቆንጅዬ ሴት ነች:: የሆነ ቀን ከወሬ ወሬ ቆንጆ ነኝ ብለሽ ታስቢያለሽ ስላት: እንክት! ያዉም 100.1% ብላኝ አረፈች:: ይች ናት ሄለን እንግዲህ:: በራስ መተማመን ጥግ ድረስ:: ነጥብ አንድ የተባለችው ምን እንደሆነች ለማወቅ አመታት የሚወስድብኝ ይመስለኛል:: በዛ ላይ አስተሳሰቧስ ብትሉ:: ስልኳን ከልጆች ወስጄ መደዋወል ከጀመርኩ ቆይቻለሁ:: በጥርስና በዳሌ ተስቦ የሄደው ወንድነቴ የጭንቅላቷ አድናቂ ሆኖ ከተቀመጠ ሰነባብቷል:: የትኛዉም ርዕስ ላይ ሰፊ ትንተና የመስጠት: የማዳመጥ: ጣፋጭ ቃላትን ከአንደበቷ የማዉጣት ልዩ ተስጦ አላት:: ስለ ሃይማኖት ካነሳችሁባትማ ገለፃው ቀላል አይሆንም:: ደንበኛ የኢየሱስ ባሪያ ናት! ተይዣለሁ ወገኖቼ እሱ ይርዳህ በሉኝ!

በአያንቱ ቦታ እኔን ለምን አላደረከኝም ብዬ ፈጣሪን ወቀስሁት:: ያን ገላ ለማየት አይደለም ሌሊት በዝናብ: እድሜ ልኬን ፆም ፀሎት ምህላ ብይዝ ያንሰኛል ብያለሁ:: አሁንም ቢሆን መቼ ተስፋ ቆረጥሁና:: በዝናብ የመታጠብ መንፈስ በቀላሉ አይለቅም ብዬ ሌሊት ዝናብ በዘነበ ቁጥር ወደ ሸኖ ቤት መሮጤን አላቆምሁም:: ግን ባገኛት ምን ላደርግ ነው? እንጃ!

የሆነው ሆኖ እኔም በቅርቡ የገዛኃትን ጥሩ መዓዛ ያላት ዶዶራንት ተማምኘ ሸኖ ቤት ዉስጥ ለመታጠብ ወሰኘ ወደዛው አመራሁ:: ከሻወር በኃላ የናፈኳትን እሁድ ለመኖር ጓጉቻለሁ:: ጉዱ የመጣው ታጥቤ ልጨርስ ስል ነው:: አንድ የሰማይ ስባሪ የሚያክል ሰው ከፊቴ እንደጅብራ ተገትሯል (ሰው ቶሎ ቶሎ ተጠቅሞ እንዲወጣ በማሰብ ሸኖ ቤቱ በር የለዉም:: ወደ ሸኖ ቤቱ ትንሽ ጠጋ እንዳሉ ሰው አለ ብሎ መጠየቅ ግዴታ ነው:: ካልሆነ ከማይሆን ነገር ጋ ይፋጠጣሉ)

ይሄ ጎልያድን የሚያክል ሰው ግን ሰው አለ የለ! ምን የለ! ዝም ብሎ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ ከፊቴ ቆሟል:: ብዙም ሳይቆይ:-

"ቆይ አንተ ቆዳህን ነው እንዴ የምትልጠው? እዚህ ከጌባህ ስንት ሰዓት ሆነህ? እኛ ስንት ሲራ ያለን ሰወች አንቴን በመጠበቅ ጊዜያችንን እንጊደል እንዴ?"
አፉ ሲያወራ እንደሚኮላተፍ የገባኝ ቆይቶ ነው:: በወሬው መሃል ከ እግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ እየደጋገመ ያየኛል:: ለክፋቱ ደግሞ እርጥብ ሙታንታየን አዉልቄ ነበር:: ( እኔን ብሎ ቦላሌ አስወላቂው ሃሃሃሃ ) በትረ ምርኩዜን እያየብኝ እንደሆነ ሳስብ ፈጥኘ በእጆቸ ለመሸፈን ሞከርሁ:: አዳምና ሔዋን እርቃናቸውን መሆናቸውን ሲያዉቁ በቅጠል ሸፈኑት ሲባል ምን አይነት ፋርነት ነው ከነሱ ዉጭ ሰው የለ:: ምን አሳፈራቸው? በዛ ላይ ለዛ ነገር ሲፈላለጉ ያን ቅጠል ማዉለቁ ሌላ ስራ እኮ ነው! ምን እሱ ብቻ በየጊዜው ቅጠል መበጠሱስ? እያልሁ የቀለድሁት የጅል ቀልድ መሆኑ የገባኝ አሁን ነው:: አረ ያች ቅጠል ሆይ ወዴት ነሽ? ለአሁኑ እጄን እንደቅጠል ከመጠቀም ዉጭ አማራጭ አልነበረኝም:: ሰዉየው ይባስብህ ብሎ እዛው እጄ ላይ አፍጥጦ ቁጣዉን ቀጠለ::

"ስማ እዚህ ቤት ኢኮ እኩል ተከራይተን ኔው የሚኖረው:: አንቴ ከአከራዮቹ ጋ ስለቴግባባህ ቄኑን ሙሉ ሽንት ቤት ዉስጥ ሜዋል አሌብህ? ለኔገሩ ሚጣ ጋ የጀሜርሄው ነገር ቢኖር ነው እንጅ እንዲህ ሰው ኒቀህ የሊብ ሊብ አይሰማህም ነበር!" (ሚጣ የአከራያችን ልጅ ናት:: ስለምንግባባ ከዶርሜ አትጠፋም)
"አረ በፈጣሪ ዞር በልልኝ:: በቃ ጨርሻለሁ ይሄው ልወጣ ነው:: አንተ ስርሀት የለህም እንዴ?" መቆጣት አማረኝ ግን ደግሞ አምርሮ ቢመጣስ? ሮጬ እንኳን እንዳላመልጥ እንዲህ የተላጠ ዶሮ መስዬ ወዴት! ችዬ እገጥመዋለሁ እንዳልል የዳዊትን ያክል ጠንካራ እምነት የለኝም:: ቢኖረኝስ ወንጭፍና ጠጠሩ ከየት ተገኝቶ::

የኃላ ኃላ የሚበቃዉን ያክል ተናግሮ (ጩሆ ማለት ይቀላል) ከዚህ በኃላ ሸኖ ቤት ዉስጥ እንዳልቆይ ቀጭን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኝ ከፊቴ ዘወር አለ:: ጥላው እራሱ እንደዚህ ከባድ መሆኑ የገባኝ ሲሄድልኝ ነው:: እየተጣደፍሁ ሙታንታየን ለብሼ ስበር ወደ ዶርሜ ገባሁ::

"ምርጡን ቀኔን ያበላሸዋል እንዴ ይሄ ድንባዣም!" ድምፄ እንዳይሰማ ቀስ ብዬ በለሆሳስ ነው የምሳደበው:: በቃ ቤት መቀየር አለብኝ:: ሰው ብሩን ከፍሎ ይሳቀቃል? ቶሎ ቤት መፈለግ አለብኝ:: ግን ሄለንስ? አሁን ክረምቱ እየገባ ስለሆነ ይችን ሁለት ወር ትንሽ ልታገስ::

ስልኬን አንስቼ ሰዓቴን ተመለከትሁ:: 2:30 ይላል:: ይሄ ሁሉ ነገር ተፈጥሮ ገና ሶስት ሰዓት እንኳን አልሞላም:: ወይ እሁድ ለካስ እንዲህ አይነት ረጅምምምም ቀን ነው:: ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ!!


ተፃፈ #በEludaa

@wegoch
@wegoch
@paappii
ለረመዳን እመጣለው አብረን እናፈጥራለን።

አላህ እራሱ ዱዓዬን የሚሰማኝ ከጎንሽ ስሆን ነው።

Ramadan Kareem Habibiti🖤

................................

Ramadan Kareem Beteseb!
................................
@ribkiphoto
@wegoch
@wegoch
የድርቁን ነገር ብዙ ተማክረን ነበር፤ እኔስ ከብቶቼን ይዤ ሸሸው። የልጅ ምክር የማይሰሙ ጎረቤቶቼ ግን ሲያፌዙብኝ ነበር። ይኸው ረሀብ መጣ የነገርኳቸውም ደረሰ። አሁን ከዚ ግጦሽ አጭጄ ብሰድላቸው ስንት ከብት ይተርፍ ይሆን?
ሚስኪን ከብት በፌዘኞች ጥፋት ለሚሰዋ!
..................
2013, ድንባሮ
@ribkiphoto
@wegoch
@wegoch
.................
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ (ክፍል 6)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

...ከመተኛቴና ከመነሳቴ በፊት ለሱ ዕድሜን መለመን የዘውትር ፀሎቴ ሆነ።እኔምኮ እሞታለሁ...ግን ከሱ መቅደምን ሻትኩኝ።በልቤ ይገባው አይገባው ባላውቅም ትልቅ ቦታን ሰጠሁት።ቀስ በቀስ የስዩምን ቦታ እያጣበበው እንደሆነ ታወቀኝ።እየራቋት የሚሄዱ የብርሀን ጭላንጭል ቀስ በቀስ እንደምትደበዝዝና እንደምትጠፋው ላቆመው ያሰብኩት ጎጆ መሰረቱ እየተወላገደና እየነካከተ ሲከስም ይታወቀኛል።

ስዩም ሲደውል አንስቶ ማናገሩ ከምንም በላይ ቀዝቃዛ ስሜት እና እኔ ነኝ ያለ ድብርት ውስጥ ይጥለኛል።ድምፁ 'ተኮንነሻል አንቺ ከንቱ!'የሚል የገሀነም ጥሪ ይመስለኛል።ልብ ካላዘዘ አካል ግዑዝ አይደል?ዐይን ሌላ ሲያማትር አይደል የትዳር የመፍረሻ ደወሉ የሚያቃጭለው?ሌላን ሰው መንካት...ሌላን ሰው መሳም...ከሌላ ሰው ጋር አካል መጋራት አይደለምኮ የመወስለት ማስረጃው።የመወስለት ንጋት ወገግ ብሎ የሚታየው ልብ ለሌላ ሲመታ ነው።

የኔም ልብ ለስዩም ማዜሙን እየተወ ደም የሚረጨው ለዳንኤል ሆነ!ለሚሞተው ታካሚዬ...እኔም በሁለቱ መሀል መሰነጉ የተመቸኝ ይመስል ዝምታዬን አስታመምኩት።እጄ ላይ እየሟሟ እያየሁት...ቫይረሱ እያሸነፈው እየወደቀ እያየሁት...መድሀኒት አልፈልግም እያለ እያስለቀሰኝ እንኳን የውስጤን ለሁለት መከፈል የወደድኩት ይመስል ዝም አልኩ።

አንዳንዴ ለኔ ያለው ጥልቅ ፍቅር ነው ወይስ ጥልቅ ጥላቻ ብዬ ግራ እስከሚገባኝ ድረስ ያቆስለኛል።በነጋታው ነፍስ በሚያለመልም ንግግሩ ይጠግነኛል።

መድሀኒቶቹን ሰብስቦ ያመጣና ዐይኔ እያየ የቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይጥላቸዋል።ምርርርርር ብዬ እያነባሁ አይቶ እንዳላየ ጥሎኝ ይሄዳል ።በቀጣዩ ቀን የጣለውን እጥፍ መድሀኒት ያመጣና ፊት ለፊቴ እየዋጠ "ከንግዲህ አላስለቅስሽም እመኚኝ"ሲል ምሎ ተገዝቶ ይሄዳል።ትናንት ያለቀስኩትን አምስት እጥፍ የሚሆን እንባ አፍስሶ

"ቆይ እኔ ግን ምናይነት ሰው ነኝ?ለምን አትገይኝም? በናትሽ ግደይኝና ፅደቂ!"አንተን ብሎ አፍቃሪ!እስኪ መጀመሪያ ዕድሜህን አስላ!'ብለሽ ተቆጭኝ!አልገርምሽም ግን?እየሞትኩ ስወድሽ ምንድነው 'ሚሰማሽ?መሞቱ አይቀርም ብለሽ ችላ ብለሽኝ ነው ወይስ መፈቀሩ ተስማምቶሻል?ምናይነት ሴት ነሽ ኧረ?እኔስ ምናይነት ደነዝ ነኝ?"

ምናይነት ፍቅር ነው ይሄ በማርያም!ዛሬ እንደዚህ ብሎ በነጋታው

"ባላውቅሽ የምሞተው ከዐመት በፊት ነበር ዶክተር።አንድ ዐመት የኖርኩት በዚህ መድሀኒት እንዳይመስልሽ...ባንቺ ነው።ፈጣሪን ነገን አሳየኝ ብዬ የምማፀነው ላየው የምናፍቀው አንድ ጥሩ ነገር ስላለ ነው ግዝሽ።እናቴኮ በሽታዬን አታውቅም ዶክተር።አንቺን ማፍቀሩ ነው በሽታዬ የሚመስላት።ታውቃለች እንዴት እንደምወድሽ።ይህን ጠጠር የምውጠው አንቺን ለማየት ነው በቃ''ይልና እያየሁት መድሀኒቱን ይውጣል።

በሌላ በኩል ስዩም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው።አይቀሬው ሰርግ ደግሞ ከ 15 ቀናት በሁዋላ ይደገሳል።ሙሽሪት አካሏ ቬሎ ልቧ ማቅ ለብሶ አበጀሽ የኛ ሎጋ ሊባልላት ነው።ሁሉም ደስተኛ ሆኗል ።ከኔና ከዳኒ በቀር።እናቴ "ላይቀርልሽ አታለቃቅሺብኝ"አይነት ንግግር ተናገረችኝ።ለነገሩ ልክ ናት።ሁለት ነገሮች አይቀሬ ናቸው።አንድም ሰርግ...አንድም ቀብር...በጥቁር ቬሎ ላግባ ይሆን?


ይቀጥላል።

በማዕዶት ያየህ

12/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
ጎረቤታችን ናቸው። አለም ለእነሱ መዋደድ ግድ የሚሰጠው ይመስላቸዋል ወይ ሰው ባለበት ለፍቅራቸው ምስክርነት መናገር ፍቅር ያጠናክራል የሚል እውቀት ጭንቅላታቸው ውስጥ ሰርጿል ።
እንዴት እንደሚከባበሩ ፣ እንደሚዋደዱ አንዳቸው ለአንዳቸው ስጦታ እንደሆኑ በሆነ ምክንያት ሰብሰብ ስንል መዘብዘብ ይጀምራሉ። የልጃቸውን ልደት አዘጋጅተው ማታ ከቤርሳቤት ጋ ሄድኩ ፤ ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ እና ቤርሳቤት ማህበራዊ ህይወት ስለምትወድ ሄድን ። የተገናኙበትን እለት ለዘጠነኝ ጊዜ ሳያዛነፍ ሳይጨመር እየተቀባበሉ ተረኩልን ። ለዘጠነኛ ጊዜ ሰምተነዋል ሳንል ሁሌም ሲነግሩን የምንጠይቀውን ጥያቄ የምናጨበጭበውን ጭብጨባ አጨበጨብን ።
ድንገት እናንተ የት ነው የተገናኛችሁት አለችን ኤልሳ ። ከቤርሳቤት ጋ ተያየን። ፈጠን ብዬ ፦ አዳማ የ leadership ስልጠና ስሰጥ ቢሮዋ ወክሏት ሰልጣኝ ነበረች ። ተከይፌባት በሰበባ-ሰበብ ስልኳን ተቀበልኩ ። ደጅ ጠንቼ እትት ብዬ ይሄው አንድ ልጅ ወለድን
አልኩኝ፤ አለቀ። ውሸት ብዙ አይጎተትም ብዙ ካልተጠና በቀር ቤርሳቤት ዝም አለች።
የአወራሁት ውሸት ነበር ። ለካ ሁሉ እውነት አይወራም ። ለካ የሚከደን ገጠመኝ አለ። ለካ ለራሳችን ደግመን የማንነግረው የሚጎመዝዝ እውነት አለን። እውነታው ፦ ከቤርሳቤት ጋ የተገናኘነው ጭፈራ ቤት ነው የተገናኘን ቀን ነው የተናፋነው ፤ ወሲባችን ፍቅር አልነበረውም ፤ ከአንድ ዙር መፋተግ በኋላ፤ አንድ ዙር ፍቅር አልባ ወሲብ እንዳለቀ ፊቴን አዞርኩ ሲጋራዬን ለኮስኩ ፤ ፊቷን አዙራ ስልኳን መነካካት ጀመረች ። ሁለታችንም ጀብረር ብለን ነበር። ምንም ያላወራው ይመስለኛል ፤ እርግጠኛ ነኝ ከዚህ በኋላ አንገናኝም ፤ በአንድ ቀን የምትጋደም ፣ ከሴተኛ አዳሪ ገንዘብ ባለመቀበል ብቻ የምትበልጥ ወይም የምታንስ ልጅ ማን ቁምነገር ይሰጣታል። አስክሮ ፣ እትትት ብሎ የሚቾምስ አለሌ ሸሌ ወንድ ለቁምነገር እንደማይሆን እርግጥ ነው። ተኛን !
ሳንተቃቀፍ ተኛን።
እኩለ ለሊት እንዳለፈ ይመስለኛል አመመኝ ከተኛሁበት አልጋ ተስፈንጥሬ ከአልጋዬ ብዙ
ሳልርቅ ወለሉ ላይ አስመለስኩ ።
ከመቅፅበት ተነስታ ከጎኔ መጥታ ልቤን ያዘችልኝ ፤ ከሆዴ ጀምሮ አማጥኩኝ ፣ አማጥኩኝ አቅም አነሰኝ እና ጥምልምል አልኩ ፤ መታገል ፣ ማጓራት ብቻ የሚወጣ ግን የለም ውሃ ጠጣ ብላ ሰጠቺኝ ፤ ትንሽ ጠጣሁ አፍታ ሳይቆይ የጠጣሁትም ውሃ ወጣ ። ቀና በል ፥ ይሸትኻል አለቺኝ ፤ ትውከቱ እንዳይሸተኝ ቀና እያደረገችኝ ፤ እሷን ተደግፌ ቀና አልኩ ጨርቅ አምጥታ (ከውስጥ የለብስኩትን ቦዲ) ውሃ ነክራ አንገቴን ፣ ግንባሬን አራሰችልኝ ፤ ቅዝቅዝ አለኝ ። ቀስ ብዬ ጠቅልል ብዬ ተኛሁ ፤ ስትንጎዳጎድ እንቅስቃሴዋ ይሰማኛል ፤ አቅሜ ተዳክሞ ስለነበር ለጥ አልኩ ። ጠዋት ስነቃ እና ማታ የሆነውን ሳጤነው ሁኔታዋ እና እንክብካቤዋ አንጀቴን በላው።
ትውከቴ ከቦታው የለም ፤ እንዴት አልተፀየፈችውም ፤ ማን ስለሆንኩ አንደዚህ
ተንከባከበቺኝ ?! አብረን ቁርስ በላን ። ስለማታው ሁኔታ ምንም አላወራንም ፤ አፈርኳት ፤ ውለታዋ ቆጠበኝ። ከዛ ቀን በኋላ አብረን ነው የምንውለው። ተልካሻ ስፍራ ፤ በማይረባ ሁኔታ እንዴት እንደዚህ ግጣሜን ላገኝ ቻልኩ ።
በሁለት ወር ከአስራምስት ቀን ዳግም ለሁለተኛ ቀን ተዋሰብን ፤ ያኔ ሰውነቴ ተቀብሏት
ነበር ፤ ሰውነቷ ተቀብሎኝ ነበር እናም ተዋሃድን ፤ የሚዋደዱ ሰዎች ሲዋሰቡ ወሲቡ
ውህደት ነው ፣ የነፍስ ቁርኝት ፤ ተቆራኘን።
ውድ ቦታ እና ቅዱስ ቦታ ብቻ ነው ትክክለኛ ሰው የሚገኘው ያለው ማነው? ህይወታችን የሚመዘነው በምናገኘው ደስታ ነው ።
ዛሬ አምናታለሁ ! የምትንዘላዘልበትን ምክንያት ደፍኜዋለሁ ፤ ፍቅሬ እንድትታመነኝ ሰርቷታል
። እንደትላንት እንዳልሸረሙጥ ከእሷ ጋ ያለኝ ነገር ይጋርደኛል ። ሰው መቼ በተገናኘበት ስፍራ ብቻ ይመዘናል ፤ ያለንበት ስፍራ ሁሌ መቼ ልካችን ሆኖ ያውቃል። አጀማመራችን ሳይሆን አካሄዳችን ነው የማንነታችን ማሳያ ። ይሄ በልባችን የተፃፈ የምንኖረው እውነት ነው ። ይሄን እውነት መግለፅ ረብ ለሌለው ትዝብት መጋለጥ ነው። ሁሉ እውነት አይነገርም። አንዳንዴ አንዳንድ ውሸት ከእውነት ይበልጣል ።


@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
መማረር +ማማር =( ውበት )

ካሊድ አቅሉ


አተኩሬ አየዋት ለዛ ያለው ወሬ እያወራች ቢሆንም በመሀል ቀልቤ ተሰርቆ መልክዋ ላይ አተኩርዋል ከአይን የገዘፈ ልብ ላይ ሚጫወት ነፍስ ያለው ውበት ይታይባታል በድምፆችዋ ጅረት ታግሼ ለደቂቃዎች ገነትን ላይ እራሴን ጥዬ ከምንጭዋ ተጋርቼ የመጣው ይሰማኛል። ንፋሱ ቀልባችንን ላለመረበሽ በስሱ ሚነፍስ ፍቅር አቀጣጣይ ማራገቢያ ይመስላል።

"የት ሄድክ " አለችኝ ሽምጥ የጋለበውን ቀልቤን አይታ
"አለው" አልኩዋት ወደ ምድር ለመመለስ ሳልንደረደር ወርጄ

" ሰማዩን አየህው ፀሐይ ልትገባ ስትል እንዴት እንደ ቀላ "አለችኝ

" አዎ ደሞም እኮ ልትወጣ ስትልም ሰማይ ታቀላለች" አልኩዋት ትዝብቴን ጠቆም ለማረግ ከዛም ቀጠልኩ ...

" ንዳድዋን ስትለቅ ውላ መጥለቂያዋ ሲቃረብ ውበትን , መስከንን, እና ደብዘዝ ብሎ መጉላትን ታሳያለች ጠዋት ልንሞቃት ወተን እናንጋጣለን ቀትር ሲቃረብ እናማራታለን ብቻ የፀሐይ ጉልበት እና ውበት ሁሌም ይደንቀኛል ። ማማር ለካ እያስደሰቱ ብቻ ሳይሆን እያማረሩ ማለፍ ነው ። ውብ ነገር ምንፈልገውን ገነት እንደሚሰራልን ሁሉ የምንርቀውንም ገሀነም ያጎናፅፈናል ። "

ብዬ መልስዋን ለመስማት ጆሮዬን አዘጋጀው ...

" ሆ በል ተነስ ፀሐይን ቁጭ ብለን ስናማ ጨረቃ መጣችብን " ብላ የሁለት ማክያቶ ሂሳብ ጠረጵዛው ላይ አኑራ ቦርሳዋን ይዛ ተነሳች ...............

@wegoch
@wegoch
@paappii
እብድ አይፈቀርም ያለው ማነው?
-----------------------------------------

እንዲህ አልነበረምኮ ውላችን!ሊጠፋ እንደሚችል አልገመትኩም።ዩኒቨርስቲ ልንሄድ ምደባ የምንጠብቅ ሰሞን አንድ እብድ ሰፈራችንን ተቀላቀለ።እቁብ መጣልና የእድር መዋጮ መክፈል ላይ አልተሳተፈም እንጂ የማህበራዊ ህይወታችን አንዱ አካል ሆነ።ስሙን ሲጠይቁት "እንጃ"ነበር መልሱ።በዚያው ስሙ "እንጃዬ"ሆኖ ፀደቀ።

ቁርሱን አንዱ ቤት...ምሳውን ሌላ ቤት እየጠለፈ፣ራቱንም የራራ እያበላው ተጎራብተን መኖር ጀመርን።የሰፈሩ ጎረምሶች ተረባርበው መጠነኛ የላስቲክ ጎጆ አቆሙለት።

እና በመሀል እኔ የ 19 ዓመቷ ተስፈኛ ተማሪ ከእንጃዬ ለጠየቁኝ ሁሉ 'እንጃ!' የሚያስብል ፍቅር ነደፈኝ።ሲያመጣው ልክ የለው!
"አጃኢብ!....የሰለሞን ልጅ እብድ አፈቀረች"ተባለ።እብደቴ ሰርተፊኬት አገኘ።እናቴ ደነፋች!አባቴ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ።እገድላታለሁ ብሎ በእናቱ ስም ምሎ ሽጉጥ ደቀነብኝ።እኔም የልብ ልብ ተሰማኝና ጨርቄን ሳልል ማቄን እንጃዬ ቤት ከተምኩ።
እንጃዬ ብዙ አያወራም።ሳቅ ብቻ ነው መልሱ።ከስንት አንዴ ካወራም ምንም ይበሉት ምን "ይገርማል"ብቻ ነው የሚለው።
"እንጃዬ ግን ትወደኛለህ?

"ይ...ይገርማል"

"አባቴ'ኮ ሽጉጥ አወጣብኝ እንጃዬ ምን ላድርግ?"

"ሽጉጥ...ሽ...ሽጉጥ"መርበትበት የጀምራል።ሽጉጥ ካየ አልያም ስለሞት ከተወራ እንጃዬ የባሰ ሕመም አለበት።እኔም ነውር አልፈራም ነበር ቲሸርቴን አውልቄ ፊት ለፊቱ እቀመጥና ምላሹን ስጠብቅ

"ይ...ይገርማል "ይለኛል ። በዘመድ አዝማድ ብመከር አልሰማ አልኩ።እረዱኝ አልኩ።የዪኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሲሆን ጎንደር መመደቤን አወቅሁ።ጉዱ የመጣው ይሄኔ ነው።'እንጃዬን ትቼ የትም አልሄድም' አልኩ።ቤተሰቡና ዘመድ አዝማዱ ተረባርቦ የእንጃዬን ቤት አፈረሰው ። እሱ እንደነሱ ክፋት አያውቅ

"ይ...ይገርማል"ብሎ ዝምምም ነው።ክፍሌ ውስጥ ተቆለፈብኝ።አባቴ ቀኑ ሲደርስ ልብሴን በሻንጣ አስይዞ በግድ ጎንደር ሊልከኝ ሲል እጄን በምላጭ ከትፌ ራሴን ለመግደል ሞከርኩ።እናቴ ተንሰፈሰፈች...ግን ምንም ማድረግ አልቻለችም።ያው ተለክፌ አይደል?

እንዳወራ ቢፈቀድልኝ እኮ እንጃዬ ማለት መልዓኬ ነበር። እንደቅዱስ ገብርኤል ሰላምና ደስታን አብሳሪዬ!እሱ የቤት ኪራይ የለበት...የቀለብ ሸመታ አያስጨንቀው...ልብስ ልግዛ አይል ልጠብ የለ...የልጆቹ ነገር አያሳስበው... የቤተሰብ ክብር አይል!ብቻ በዚያ ኑረት ውስጥ ለኔ ብቸኛው ጥሩ ነገሬ እንጃዬ ብቻ ነበር።
የሆነ ምሽት ታዲያ ታላቅ ወንድሜ እና አባቴ ሊገድሉት ሲያሴሩ፣መልዐኬን ሊነጥቁኝ ሲዶልቱ ሰማሁ።ወፈፍኩ!ጨርቄን መጣል ቀረኝ።አብሮ እንደኖረ ቤተሰብ ሳይሆን መንገድ ላይ እንደተገኘ የማይታወቅ ሰው አቀለልኳቸው።ከስፍራቸው አነሱብኝ።የአባቴን ሽጉጥ አንስቼ ጭንቅላቴ ላይ ስደቅነው ወንድም ተብየው

"እስኪ ምላጩን በመሳብ ተባበሪን እስኪ!በፈጠረሽ ይህን ካረግሽ ውለታሽን አንችለውም!" አለኝ።አባትየው ግን ወደማባበሉ ዞረ።

"ህሊናዬ በፈጠረሽ እንዳታደርጊው ያስጠይቅሻል"ሲል ተማፀነኝ።እኔ ግን ብሶብኝ እርርርርፍ!

"ኧኧኧረ!ያስጠይቀኛል?አንተ እንጃዬን ስትገድል መላዕክት አይደሉ 'ሚቀበሉህ?"
እናቴ ከጓዳ ብቅ ብላ የያዝኩትን ስታይ በሚሰቀጥጥ ጩኸት ቤቱን አደበላለቀችው።አንጀቴ ተንሰፈሰፈ።የዚያን ቀኑን የእናቴን ሁኔታ ሳስብ ነው ምን ያህል ልክ እንዳለፍኩ የገባኝ።ልክፍቱ ግን አልተወኝም።

ስህተቴ ማፍቀሬ አልነበረም።ስህተቴ እብድ ማፍቀሬም አልነበረም።ስህተቴ ሰው እንደሚለው ከሆነ ደፋርነቴ ነበር።ለካ አንዳንድ ስሜቶች መዳፈናቸው የግድ ነ መሰለኝ!እንጃ!

መንደርተኛው ''ጉድ ጉድ ጉድ! ለየላት በቃ ይች ልጅ?እብድ አፍቅራ ራሷን ልታጠፋ?ምነው ደህና ልጅ አልነበረች?አይይ!ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ'' ሲለኝ ትልቁን ዳቦዬን ይዤ እንጃዬ ቤት ከተምኩኝ።ዳቦዬ ተባረከች።በእብዱ ካህን የክብር ካባዋን ገፈፈች።ለካ እንጃዬ ዳቦ መባረክ ያውቃል።የኔ ንፁህ!ጣጣችንን ጨርሰን እርቃኔን ከጎኑ ስጋደም ብርግግ ብሎ ተነሳ።ደንግጬ

"ምነው እንጃዬ?"ስለው

"ይ...ይገርማል"አለኝና መልሶ ተኛ።

ጠይም መልክ ከንፅህና ጋር ሲዋሀድ እንደዚህ ነው የሚያምረው?ገላውን የሰፈሩ ወጣቶች በሳምንትም ሆነ በሁለት ሳምንት አንዴ ያጥቡታል።ዳሩ እሱ ባይታጠብም ንፁህ ነው።ተባዮቹ ራሱ እሱጋ የሚመጡት ከየትም የማትገኝ ንፁሕ የደም ጠብታን ፈልገው ይመስለኛል።እርጋታ የሚዘዋወርበት ...ምቀኝነት የማያውቅ እንደ ምንጭ ውሀ የጠራ ደም ከሱ ሰውነት በቀር ሌላ የትም ያለ አይመስለኝም።ዝምታው ለሰሰሰስስስስ ያለ ንፋስ ነበር።ከቀትር ፀሀይ ቀጥሎ የሚመጣ!የሚያበርድ የሚያቀዘቅዝ...እያነቃ የሚያደነዝዝ ዓይነት!!

ልብ ከደነደነ ለካ ሽጉጥ እሾህ ይሆናል!ተተኩሶ የሚገድል ሳይሆን ወግቶ የሚነቀል ቀላል ህመም...እዚያ ሞገደኛ ስሜት ፊት ምንም ነገር ኮስሶብኝ ነበር...ቤተሰብ ኮሰሰብኝ...ሽጉጥ ኮሰሰብኝ...ክብር ኮሰሰብኝ...ዕውቀት ኮሰሰብኝ...ተስፋ ብቻ ነበር የገዘፈብኝ።እንጃዬ ስሜቴን ያውቃል ፣ፍቅራችን የጋራ ይሆናል የምትል የሞኝ ተስፋ!

ከዚያች ምሽት በሁዋላ ታሪኬ መልኩን ቀየረ።ብናስራት ራሷን ታጠፋለች በሚል ስጋት ቤት ውስጥ የሚቆጣኝ ቀርቶ ቀና ብሎ የሚያየኝ ስለሌለ ነፃነቴን እስከጥግ ኖርኳት።ቁርስ ከእንጃዬ ጋር...ምሳም ከሱ ጋር...ራትም እንደዛው...አልፎ አልፎ አዳሬም እዛች የፈራረሰች የላስቲክ ቤት ውስጥ ሆነ።እናቴ ጭንቅ ጥብብ ቢላት
"ህሊናዬ በፈጠረሽ አዳሩ እንኳን ይቅርብሽ...በፍርሀት እሞትብሻለሁ "

"እሜ እንጃዬን ነው የፈራሽው?ይልቅ አባቴንና ወንድሜን ፍሪያቸው"

"እሺ ቢያንስ..."
"ቢያንስ ምን?"አቀርቅራ ዝም አለችኝ።ጭንቀቷ ገባኝ።የዳቦው ነገር አሳስቧት ነበር።

"እሜ የኔ ክብር የሄደው ገና እንጃዬን ሳፈቅር ነው"አልኳት።የኔ አንጀታም!ብርድ ልብስ ሸጥታ ሸኘችኝ!ከዛ ንፁሕ ሰው ጋር ሞቆኝ የሰላም እንቅልፍ ተኛሁ።
የወር ደሜ እንዳልመጣ እያወቅሁ፣ ፀንሼ ሊሆን እንደሚችል እያወቅሁ፣ለሁለተኛ ጊዜ ሽጉጥ ሊደቀንብኝ እንደሚችል እያወቅሁ ዝምታን መረጥኩ ።ሆዴ ገፋ...ራሴው ፈቅጄ በፈፀምኩት ነገር ወንድሜ ፍቅሬን ሊገድልብኝ ሽጉጥ ይዞ ወጣ።እኔስ የዋዛ ነኝ?በረኪናዬን አንጠልጥዬ እየጮህኩ ተከተልኩታ!መንደርተኛው ግልብጥ ብሎ ከቤቱ ወጣ!ሌላ ወሬ ተገኘለት!

"ጉድ በል ሀገር!ህሊና የጋሽ ሰለሞን ልጅ ከእንጃዬ አረገዘች"ተባለ።ቡና እስከ ስምንተኛው እየተጣደ የምቦጨቅበት ርዕስ ተገኘ።በረኪናውን ሲቀሙኝ ዐለሙ ዞረብኝ...እናቴ ወንድሜን መማፀን ጀመረች።
"ዞር በይ እማዬ ፊት ለፊቷ ነው የምደፋላት!"ይላል።እንጃዬ ግራ ገብቶት በዝምታ እያየኝ አለቀሰ።

"ሽሽ...ሽጉጥ"አለ።
ሳለቅስም አባባሁት መሰለኝ።ያልተያዘው አፌ ብቻ ስለነበር የቻልኩትን ያህል ጮሄ ድምፄ ሰለለ።ወንድሜ በምልጃ ብዛት ምላጩን ሳይስብ ወደቤቱ ገባ።ከዚያች እርጉም ቀን በሁዋላ...ያ ሽጉጥ ከተደቀነበት በሁዋላ እንጃዬን በከተማው አየሁት ያለኝ የለም።ግን ተሳስቻለሁ እንዴ?የዛን ንፁህ ሰው ልጅ መግደል ነበረብኝ?
ስህተቴ ማፍቀሬ አልነበረም...ስህተቴ እንጃዬን ማፍቀሬም አልነበረም...ስህተቴ ልጄ አይደለችም...ስህተቴ የተገኘሁበት ቦታ ነበር።ስህተቴ ሰፈሩ ነበር።ለምኩራብ(ለልጄ)ስለአባቷ ሳወራት ገነትን እየጎበኘሁ ይመስለኛል።ስፍፍፍ እላለሁ።

"የዛሬ 6 ዐመት መኖር ጥሞኝ ነበር"እላታለሁ።
በማዕዶት ያየህ


@wegoch
@wegoch
@tizur_12
.....
ለእኔም እኮ አይገባኝም፤ ቆይ በሕይወታችን የምንፈልገው ትልቁ ነገር ፍቅር ነው አይደል? ያውም ጥልቅና ነጋሪ የማያስፈልገው እንዲው በአይን ብቻ የሚገባን? ይህንን የሁሉን መሻት እኮ ነው የኔ ሆኖ ያገኘሁት፤ ታዲያ ለምንድነው ማመሰገኑ የቸገረኝ? ለምን ይሆን ልቤን የጭነት ያህል የሚከብደው? ለምንድነው አሁንም ያልሞላ ክፍተት እንዳለ የሚሰማኝ?

ያኔ....
እሱ ወላጆቹን በሞት አጥቶ በሀዘን የተሰበረበት ጊዜ ነበር፤ በዛ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ሆኖ የኔን አብሮነት ሲሻ የራስህ ጉዳይ የምልበት አቅም አልነበረኝም ግን ያውቀዋል አፍቅሬው አልነበረም።
በቆይታ እሱም ሀሳቡን የሚቀይር እኔም ልቤ የፈቀደውን የማደርግ መስሎኝ ነበር። ጊዜያት ባለፉ ቁጥር የሱ ፍቅር ሲጨምር እኔ ለሱ ያለኝ ክብርና የጓደኝነት መውደድ እንዳለ ከመዝለቁ ውጪ ልቤን ለፍቅር ማስረከብ አቃተኝ።

ራሴን እኮ እጠይቀዋለው "ያልወደድሽለትን አንድ ነገር ጥቀሺ" ብባል አፌ ይተሳሰራል እንጂ ይህ ነው የምለው አንዲት ሳንካ እንኳን የለበትም፤ ግን አላፈቀርኩትም።

ምንም ቢጠየቅ በሚገርም ብስለት ነገሮችን ያብራራል፤የእይታው አድማስ፣ የምልከታው ጥግ "ለካ ይህም አለ እንዴ?" እንዳስባለኝ ነው።

ቁጥብ ነው እናም ኮስታራ፣ ስክን ያለ፣ ልክ እንደ ውሀ የሚጋባ አይነት የእርጋታ መንፈስ ያለው፤ የልጅ አዋቂ።
በፊት በፊት ሰዎች የዚህ አይነት የስብዕና ጥልቀት የሚኖራቸው ከህይወት ብዙ ሲቀስሙ ይመስለኝ ነበር፤ እሱ ባለበት የእድሜ ልክ እንዴት ላስበው እችላለው?
በዚህ ለይ ደግሞ አፍቃሪነቱ፣ አይኑ ለይ የማየው መውደድ፣ አይን ያዝ ከሚያደርግ ግርማ ሞገሱ ጋር ልብን የመቆጣጠር ሀይል አለው፤ታዲያ እኔን
ማሸነፍ ለምን ተሳነው?

ብዙ ጊዜ ሁሉን እርግፍ አድርጎ ስለመተው እና ብቻዬን ስለመሆን አስባለው፤ እሱ ያንን እንዳደርግ አይፈቅድልኝም እንጂ።
"ራሴን አጠፋልሽና ትገላገያለሽ" ያለኝን ባሰብኩት ቁጥር ልቤ ይጨነቃል ለነገሩ እንደዛ ባይለኝም እንኳን ያንን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ ነኝ፤ ለሱ የመኖሩ ምክንያት ነኛ!
አንዳንዴ "ቆይ መውደድ ያልቻልኩት ሁሌም ቅርቤ ስለሆነ በእጅ የያዙት ሆኖብኝ ነው? ሳጣው እንደ እሳት ሊያንገበግብኝ?" ብዬ አስባለው።
ነገር ግን ተጣልተን በቆየንባቸው ጊዜያት ከፋኝ እንጂ ያንን ፍቅር ግን አልታመምኩትም።

አከብረዋለው፣ ለሱ ያለኝ መውደድ ከልብ ነው፤ አንዲት እንቅፋት እንኳን በህይወቱ እንድታጋጥመው አልፈልግም፤ ሳቁ ነው የሚናፍቀኝ፤ የወደደውና የሚያስፈልገው እንዲሆንለት ነው ምኞቴ፤ ይህን ለመሰለ ስብዕናው መቼስ ቢያንስበት እንጂ አይበዛም።

ፍቅር ግን ተሰርቶ አይመጣም አይደል? "ይህንን ሰው መውደድ አለብኝ!" ማለት ነበረብኝ? ብልስ ይሆንልኛል?፤ ነው ወይስ ልክ እንደ ተሰማኝ ማስመሰል አለብኝ? ማንም ሰው እኮ ከራሱ አያመልጥም።
እንዳልወደድኩት ማሰቡ ለራሱ የጥፋተኝነት ስሜት ይፈጥርብኛል ግን እውነታው እሱ ነው ካልሆነ ከራስ ጋር ድብብቆሽ ይሆናል።
ፍቅር ደግሞ ይሰጠናል እንጂ በስራ አናመጣውም፤ በማንቆጣጠረው ልክ ውስጣችንን ሞልቶት እናገኘዋለው ያኔ ከዛ ሰው ጋር መሆን አማራጭ የሌለው ብቸኛው ውሳኔያችን ነው።

ግን ማናችን ነን የተሳሳትነው?
ያ ጥልቅ ስሜት ሳይሰማኝ ለሱ ስል ባላመንኩበት ህይወት ውስጥ እየዳከርኩ የራሴን ስሜት ለማዳፍን የምሞክረው፣ በገዛ ህይወቴ ለይ የመወሰን ስልጣኔን የተነጠኩት፣ ደስተኛ እንደማልሆን እያወኩኝ በተቀመረልኝ አብሮነት ውስጥ ማለፍ ግድ የሆነብኝ እኔ? ወይስ.....
ያለ ልክ የሚያፈቅራት ሴት እሷ ጋር ያ ስሜት እንደሌለ እያወቀ እንኳን መውደዱ ያልቀነሰበት፣ ከሷ ጋር ለመሆን የሷ መኖር እንጂ መልካምነቷ ግድ የማይሰጠው፣ የነገው ህይወቱ ከሷ መኖር ጋር የተሳሰረበት፤ እውነተኛው አፍቃሪው እሱ?
ማናችን ነን ልክ?.....የቱስ ጋር ነው የተሳሳትነው?
.
.
ለዚህ እኮ ነው... ለኔም አይገባኝም የምለው።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mahlet
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 7)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሰው በደስታ ብዛት የሚያደርገው ጠፍቶት እናንተ እዚያ ደስታ ላይ ሳትፈልጉ የክህደትን ቀዝቃዛ ውሀ እንደምትቸልሱበት ማሰብ ይከብዳል አይደል?በረሀብ ሰውነቱ ከመነመነ ህፃን ላይ ወተት እንደመንጠቅ፣ጉልበታቸው የሚንቀጠቀጥን አዛውንት ገፍትሮ ቦታቸው ላይ ሄዶ እንደመቀመጥ፣ የነፍሰጡርን ጭንቅ እንደማየት ያህል ይጨንቃል።

ስለስዩም ተጨነቅሁ...ስለእናቴ ተጨነቅሁ...ስለዳንኤል ተጨነቅሁ...15 ቀናት ለቀሩት ሰርጌ የኔ ስሜት ከበረዶም የቀዘቀዘ ነበር።ቤተ ዘመዱ እረፍት አጥቶ ይዋከባል...ሙሽራው በሀሴት ይገባበት ጠፍቶታል።ሚዜዎቹ ሽርጉዳቸው ለጉድ ነው።የኔ በሀሳብ መሰነግ "ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ"በሚባል የአባባል ካባ ተድበስብሶ ጠያቂ አጣ።እናቴ በበኩሏ ጭንቀቴ ቢገባትም ምንም ማድረግ እንደማይቻል አምና የሰርጉን ዝግጅት እያሽሞነሞነችው ነው።

በሰርጉ ዝግጅት ምክንያት ስራ ከገባሁ ዛሬ 10 ኛ ቀኔ በመሆኑ ዳንኤልን ለ 10 ተከታታይ ቀናት አላየሁትም።ስጨነቅ ደሲለዋል መሰለኝ ስልኬን አይመልስም።የጽሁፍ መልዕክቶቼም ምላሽ አያገኙም።እንዳብድ ነው እንዴ የሚፈልገው?

መከረኛው ሰርግ ቀናት ሲቀሩት የሚዜና የጓደኛ ትውውቅ በሚል ሰበብ ሰው እንዲሰባሰብ ተወሰነ።ያው እንደምስል መቀመጥ እንጂ እንደሙሽራ የውበቴ፣የአለባበሴ...የሰርጉ ጭፈራ የመሳሰሉት ነገሮች ላይ በሰፊውና በትኩረት ማውራቱ ባይሳካልኝም እዚህ ላይ ዋናዋ ተዋናይት እኔ እንደመሆኔ መሳተፌ የግድ ነበር።

"ሙሽሪት ኧረ ፊትሽን ፍቺው!ያለላርጎ ዘፈዘፍሽው'ኮ ሃ...ሃ...ሃ...መዳር እንደዚህ የሚያስደብር ከሆነማ I will stay single forever....ሃ....ሃ....ሃ..."ትላለች ከሚዜዎቼ አንዷ የሆነችው ሶልያና።

"ባክሽ ተያት የወጉ ነው...ስንት የሚያሳስባት ነገር ይኖራል ጎጆ ወጪ ነች'ኮ አንቺ ደግሞ" ትቀጥላለች ሌላኛዋ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተጠራው ሰው ቀስ በቀስ ቤቱን መሙላት ጀመረ።ሁሉም መጥተው አንድ ሰው ብቻ ጎደለ።የወንዱ ሙሽራ ስር ሚዜ...

ሁሉም እርስበራሱ ማን ይሆን እያለ በሹክሹክታ ይነጋገራል ።ስዩም አብሮአደግ ጓደኛውን የመጀመሪያ ሚዜው እንደሚያደርገው ነግሮኛል ።

"ሙሽር ስር ሚዜህ ዘገየሳ ምነው?"የተሰበሰበው ሁሉ በየተራ ስዩምን ይጠይቁታል ።

"ይመጣል ይመጣል!አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው ያረፈድኩት ብሎኛል እየመጣ ነው ተጫወቱ"ይላል ፈገግ እያለ።በመሀል ሰረቅ እያረገ ሲያየኝ የተዘፈዘፈ ፊቴ ስቅቅ ያረገኝና ድንጋጤና ሀፍረት የተነባበረበት ፈገግታዬን እለግሰዋለሁ።መጨነቄ ገብቶታል።ግን አልጠየቀኝም።ቢጠይቀኝስ ምን እላለሁ?

'ላንተ የነበረኝን ፍቅር ዳንኤል የሚባል መልዐክ በክንፉ ሰብስቦ ወሰደብኝ' ልለው ነው?ወይስ ደግሞ

'ስዩም ከዚህ ጋብቻ የምታተርፈው ፀፀትን ብቻ ነው ....ልቅርብህ ...ልቤ ውስጥ የነበረህ ቦታ አሁን በሌላ ተይዟል...በሀሳቤ ከወሰለትኩብህ ቆየሁ....ከማገጥኩብህ ሰነባበትኩ...ሰርጉ እንዲራዘም የፈለኩት ለዚህ ውስልትናዬ ዕድሜ ለመጨመር እንጂ የሰርጉ ሽርጉድ ፋታ ነስቶኝ አልነበረም።የምትመጣው ልታስረኝ እንጂ ልታገባኝ አልመስልሽ አለኝ...ጣቴን እንጂ ሌላ የተመኘ ልቤን በወርቅ ቀለበትህ አታስረውም....
ላረኩብህ ነገር ምንም ብትቀጣኝ ሲያንሰኝ ነው...ለማደርስብህ የሞራል ስብራት ጌታ መጥቶ 'ከመሀላችሁ ሀጥያት የለብኝም የሚል ይውገራት' ቢል እንኳን ምድር ላይ ያለው ሰው ሁሉ ከኔ ክህደት አንፃር ፃድቅ ነውና ማንም ይወግረኝ ዘንድ ፈቃዴ ነው' ብለው ኩነኔዬ ይፋቅልኝ ይሆን?እንጃ!

ዘመናይ ማርዬ...
ዘመናይ ማርዬ...
ስም አወጣሁልሽ...
ሁለት ልብ ብዬ...
ወላዋይት ብዬ...

የኛ ሙሽራ ዶክተሪቱ...
ማን ያውጣሽ ከመዓቱ...

የሚል ይመስለኛል ለሰርጉ የተከፈተው ዘፈን!

ይቀጥላል!

በማዕዶት ያየህ

15/04/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 8)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።


ቆይ ግን እግዜር አይስትም አይደል?🤔እኔን የፈጠረኝ በ system ችግር አይደለም አይደል?ለምንድነው ደስታ እኔጋ ሲደርስ ራሱን የሚያጠፋው ብዬ ማበድ ቀረኝ።ምን አይነት ከንቱ ነሽ ጊዜ?ይቺም ፈተና ሆና ስታለቃቅሺ ቢያይሽ እዮብ እንዴት ይሆን የሚታዘብሽ?

ስር ሚዜው መጣ ተባለ።የሁሉም ዐይን እሱን ለማየት አሰፈሰፈ ።የኔ ዐይኖች ግን ለምንም ስላልጓጉ ይቅርታ ጠይቄና በራስ ምታቴ አሳብቤ ክፍሌ ገብቼ ልቀረቀር ስል አንድ ድምፅ መለሰኝ።

"ሙሽሪት ወዴት ነው?እንግዳ አትቀበይም እንዴ?"የሚል የመልዐኩ የዳንኤል ድምፅ!ዞር ያልኩበት ፍጥነት ቢለካ ከብርሀን ፍጥነት ሳይወዳደር ይቀራል?ዐይኔ የሚያየውን ለማመን አዳገተው።አፌን ከፍቼ ቀረሁ።ዳንኤል ሙሉ ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሶ ከስዩም ጎን ቆሟል።ሁለቱም በፈገግታ ተሞልተው ያዩኛል ።የኔ ድንጋጤ ግን ልክ አጧል።ጴጥሮስ ራሱ መቼም አልከዳህም ያለውን ጌታ በአንድ ሌሊት ሶሰት ጊዜ አላውቀውም ብሎ ሲሸመጥጥ እንዲህ የደነገጠ አይመስለኝም።ምንድነው እነዚህ ሰዎች ከጀርባዬ የጠነሰሱት?እናቴን ባይኔ ፈለኳት...አየሁዋት...ደንግጣለች።ዐይኗን አይቼ ስለጉዳዩ የምታውቀው አንዳች እንደሌለ ተረዳሁ።

"እንግዲህ ሲጠበቅ የነበረው ስር ሚዜዬ ይኸው!"ሲል ስዩም ቤት ውስጥ ያለው ሁሉ ሞቅ አርጎ አጨበጨበ።ጭንቅላቴ ላይ አንዳች የበረዶ ግግር የወደቀብኝ ይመስል ከቁሜ ወድቄ ሶፋው ላይ ዘጭ አልኩበት።የዚህን ሶፋ ውለታ መቼም ከፍዬ አልጨርሰው!በዚህ ግርግር ውስጥ እጅጉን የተጠቀምኩት በዙሪያዬ ካሉት ሰዎች በላይ እሱ ከአጠገቤ በመሆኑ ነው። መሬት ላይ ብዘረርስ ኖሮ?እንደዛ ከቁሜ ወድቄም የኔን ጥያቄአዊ አስተያየትና ድንጋጤ ምክንያት ከእናቴና ከዳንኤል ውጭ ያወቀ አልነበረም መሰለኝ እንግዳ የሆነ አስተያየትና ጥያቄ አልገጠመኝም።ወይም እኔ አላስተዋልኩም መሰለኝ።የሁሉም ትኩረት ሚዜው ላይ ነበር።ሴቶቹ በውበቱና በግርማሞገሱ እየተደነቁ እርስበርሳቸው ይንሾካሾካሉ።ቀሪዎቹ የወንድ ሚዜዎች በቁመናው ስላስከነዳቸው ነው መሰለኝ በግርምት ተውጠው ያዩታል።

"እንኳን ደስ አለሽ ዶክተር!"አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ።ከምኔው የተቀመጥኩበት እንደደረሰ አላውቅም።ክው አልኩ።የሰላምታውን አፀፋ ረስቼ ዐይኖቹ ላይ አፈጠጥኩ።ያ አስማታም ዐይኑ ትኩርርርር አርጎ እያየኝ ነው።ያ የሚያርበተብተው አስተያየት...

መታመሙን አሁን ገና ከልቤ አመንኩ።ምን አይነት ድንበር ዘለል ፍቅር ነው ለሚያፈቅሩት ሰው የሰርግ ሽርጉድ ላይ እስከመገኘት የሚያደርሰው?እንዴት እንዳስበው ፈልጎ ነው?ይሄ ምናይነት የዞረ ድምር ነው?እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህንን ማድረግ ቀርቶ አስበዋለሁ?ኧረ ማንም ይህንን አያስብም!ማንም!

"አ...አ...መሰግናለሁ ግ...ግን ምንድነው እየሆነ ያለው አልገባኝም"አልኩት።ሲያየኝ የሚሰማኝ መርበድበድ አሁን በድንጋጤና ግራ በመጋባት ተተክቷል።እሱም ገብቶታል።ያው ዳንኤል አይደል?ፊት ቀርቶ ልብ ማንበብን የተካነ አይደል?

"በሁዋላ አስረዳሻለሁ...አሁን ጊዜው የመደሰት እንጂ የጥያቄ አይደለም።ተደሰቺ ሙሽሪት"አለና በጂፓሱ ከሚደመጠው የሰርግ ዘፈን ጋር አብሮ እያንጎራጎረ ከፊት ለፊቴ ካለው የሶፋ ወንበር ላይ ተቀመጠ።

"አይዞሽ ሙሽሪት ...
አይበልሽ ከፋ አይበልሽ ከፋ...
ሁሉም ያገባል በየወረፋ በየወረፋ..."

ሲል ለኔ የሚሰማኝ

"አይዞሽ ሙሽሪት
አይበልሽ ከፋ አይበልሽ ከፋ
ሁሉም ይሞታል በየወረፋ በየወረፋ..." እንደሚል ሆኖ ነው።

ተደሰቺ ማለት ምን ማለት ነው?ይህ ቃል እኔ የማላውቀው ሌላ ዳንኤልኛ ትርጉም አለው እንዴ?ፍቅር እንደዚህ ነው እንዴ በሞቴ?እንደዚህ አስተሳሰብ አዛብቶ ለእብድ አምስት ጉዳይ ያደርጋል በክርስቶስ?ሲገባኝ ለኔ ፍቅር እግዚአብሔር ነው።ፍቅር ክርስቶስ ነው።ራስን ገድሎ ሌላን ማዳን እንጂ ሰውን በቁም መግደል ከመቼ ወዲህ ፍቅር ሆነ?ከመቼስ ጀምሮ መሲሁን ወከለ?

የምር ይህ ሰው እንደሚለው ይወደኛል?እንጃ!ከወደደኝ ለምን ያሳዝነኛል?ለምን ያቆስለኛል?ይህ እንደሚያም ጠፍቶት ነው?ለሱ የሚሰማኝ የሆነ ውሉን የማላውቀው ሞገደኛ ስሜት እንዳለ ቃል በቃል ሳልናገር መረዳት አቆቶት ነው አጨብጭቦ ሊድረኝ የተሰናዳው?ዕድሜ ዘለዐለሜን ሰው ስመርቅ "ከዳንኤል ዓይነት ሰው ፈጣሪ ይሰውራችሁ!"እንድል ይፈልጋል ልበል?

እናቴ በዐይኗ ምልክት ሰጥታኝ ወደክፍሏ ሄደች።ተከትያት ገባሁ።በጥያቄ ልታጣድፈኝ ተዘጋጅታ ጠበቀችኝ። ከመግባቴ ለሴኮንዶች እንኳን ሳትታገስ

"ሚጡ ምንድነው ነገሩ? ልታብራሪልኝ ትችያለሽ?"

"አልችልም ምክንያቱም ምንም አላውቅም"

"እንዴት አታውቂም? "

"እንደዚህ ነዋ እማዬ ልክ እንደዚህ?"እምባዬ አመለጠኝ።ሳግ ፋታ ነሳኝ።ያልጠበቀችውን ስሆንባት ደነገጠችና

"ቀስ በይ ሚጥሻ ሰው ይሰማሻል!"አለች ድምፁዋን ዝቅ አድርጋ ጠቋሚ ጣቷን ከንፈሯ ላይ አድርጋ!እንደጮህኩ አልታወቀኝም ነበር።

"Who cares!ምናገባኝ ይስሙአ!እማ የነሱ ወሬ ከኔ ስብራት ይበልጣል?ማንም....ማ...ንም ምንም ቢል አሁን ከ...ከደማው በላይ ልቤ መቼም አይደማም ገባሽ?"የባሰ ጮህኩ።

"እሺ በቃ እሺ!ልክ ነሽ አንቺ...እኔኮ የማይሆን ነገር አውርተው የባሰ እንዳታዝኚብኝ ብዬ ነው።እንጂማ ተራ ሀሜት እኔ እናትሽ ግድ እንደማይሰጠኝ ታውቂያለሽ...ነይ እስኪ ጋደም በይና እናውራው"እቅፏን እየጠቆመች እተኛበት ዘንድ ጋበዘችኝ።እቅፏ ፈውሴ ነው።እጇ የሆነ ዓይነት የመድሀኒትነት ይዘት አለው።ስትነካኝ ሰላሜ ሲበዛ ይታወቀኛል ።


እቅፏ ላይ ተጋድሜ መነፍረቅ ጀመርኩ።ከከፋኝ ሳላለቅስ እንደማይወጣልኝ ስለምታውቅ ዝም በይ አላለችኝም።እላዩአ ላይ ጣል ያረገቻትን ፎጣ በጥርሴ ነክሼ ምርርርር ብዬ አለቀስኩ።መነፍረቁ ሲበቃኝ ቀና ብዬ

"እምዬ ተጫወተብኝ ይሄ የተረገመ!"አልኳት።

"ማነው እሱ?"

"ዳንኤል!"አልኩ ጥርሴን በእልህ ነክሼ።

"ምን ብሎ ነው የተጫወተብሽ?"

"እወድሻለሁ ብሎ ዋሸኝ!ሰ...ሰ ...ሰራልኝ!እምዬ ይቅር በይኝ ዋሽቼሻለሁ"እምባዬን ላስቆመው ተሳነኝ።

"ምንድነው የዋሸሺኝ እስኪ ተረጋጊ ሳታለቅሺ ንገሪኝ"አለች እንባዬን እያበሰች።

"ሰ...ሰርጉ ይራዘም ያልኩሽ እ...እውነትም የመዘጋጃ ጊዜ አጥቼ አልነበረም።ምክንያቴ ሌላ ነበር"

"ምክንያትሽ ዳንኤል ነበር አውቃለሁ"ስትለኝ እምባዬ ደረቀ።ወሰን በ
የሌለው ድንጋጤ መዳፉ ውስጥ ከቶ ሲያሸኝ ተሰማኝ።

"ም...ምን?ምንድነው የምታውቂው እማ?ደ...ደግሞስ ሳልነግርሽ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?ማወቅሽንስ ለምን አልነገርሽኝም? ይህንን ሁሉ ጊዜ ለብቻዬ ሁሉንም ስጋፈጥ ዝም ያልሽው ልጄ ምን ያህል ጠንካራ ናት ብለሽ experiment እየሰራሽብኝ ነበር?"በጥያቄ ላይ ሌላ ማለቂያ የሌለው ጥያቄን እየደረብኩ አዋከብኳት።


ይቀጥላል

#ማዕዶት #ያየህ

16/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 9)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ቆይ ራስሽ አልነበርሽ እንዴ የነገርሽኝ?"ስትለኝ እያወራን ያለነው በአንድ ዓይነት ቋንቋ አለመሆኑ ተገለጠልኝ ።

"ምኑን ነው ደግሞ እኔ የነገርኩሽ እምዬ?"

"ለዳንኤል የፍቅር ስሜት ምላሽ ሳይሰጡ መቀመጡ የህክምናው አንድ አካል ነው አላልሽኝም ራስሽ?"

"እእእእ....እ...እሱን ነው እንዴ 'ምትይው?አዎ ነግሬሻለሁ ልክ ነሽ ኧረ እኔ ነኝ ደነዟ"አልኩ ምንተ ሀፍረቴን እየተቅለሰለስኩ።ለዳንኤል ስሜት እንዳለኝ እንዴት አወቀችብኝ ብዬ ስጨነቅ እሷ ለካ ያሰበችው ሌላ ነበር! 'አይ እምዬ! ቀልቤን ገፈፍሽው የስራሽን ይስጥሽ' ስል በልቤ

"ለሱ ስሜት እንዳለሽምአውቃለሁ!"ብላ እጥፉን ቀልቤን ገፈፈችው።ብርግግ ብዬ ተነሳሁና

"ምን አልሽ?ም...ምንድነው ያልሽው?"አልኳት ወገቤን ይዤ።ተውረገረግሁባት ቢባል ይቀላል።አላፍርምኮ ልክድ ነው?

"ምነው ዋሸሁ?" ስትናገር ከልክ በላይ ዘና ብላ ነው። ወዲያው ቀጠል አረገችና

"እናትሽ'ኮ ነኝ!እ?ይህን ዕውነት የመካድ ሀሳቡ አለሽ?" ስትለኝ

"ሁሁሁሁሁፍፍፍፍፍፍፍፍ!የለኝም" በረጅሙ ተንፍሼ አልጋው ላይ ከቁሜ ወደቅሁበት።አፍታም ሳልቆይ ፈትለክ ብዬ ተነሳሁና

"እና እያወቅሽ ነው ይህን ሁሉ 'ምታደርጊው?" በድጋሚ ጮህኩ።

"አዎ" አሁንም ዘና ብላለች።እኔ ግን ባሰብኝ

"እውነት ነበር ለካ!"አልኩኝ።

"ምኑ?"

"አባዬ እናትሽ አንዳንዴ ክፉ ናት ያለኝ...እንዴት ለማላፈቅረው ሰው ልዳር መሆኑ ሰላም ሰጠሽ?"ስል ፊቷ ተለዋወጠ።አትኩራ ለሴኮንዶች አየችኝና ለዘብ ባለ አንደበት እንዲህ አለችኝ...

"እየውልሽ ሚጥሻዬ...አባትሽ ክፋትና ለራስ ማወቅ የሚባሉት ሁለት ሀሳቦች ይምታቱበት ነበር።ለሞት ያበቃው ከልክ ያለፈ ርህራሄውና ሰው አማኝነቱ እንደሆነ ታውቂያለሽ።ስለራስህ አስብ...ላንተ ሳትሆን ለሰዎች መሆን አትችልም ማለቴ ክፉ ያስብለኝ ነበር።የዋህነቱን ስለሚያውቁ ሞልቶ የተረፋቸው ሳይቀሩ ችግረኛ መስለው አበድረን ይሉታል።አበድሮ አይረካም ነበር...የሁዋላ የሁዋላ እሱ ራሱ ነፍሱን አስይዞ በማይሆን ብድር ውሀ ሆኖ ቀረ እንጂ..."እንባዋን ታግላ ማስቀረት ተሳናት።

"...ሰማሽ ሚጡ ለራስሽ እወቂበት!ያንቺን አጥር በጅምር ትተሽ የጎረቤት አጥር ስታጥሪ ጎረቤትሽ ጀሌውን ልኮ በጀርባ ያዘርፍሻል።በሁዋላ አብሮሽ የጠፋሽን ንብረት ሊያፋልግሽ ይመጣል።ከዘረፈሽ ገንዘብ የሩቡን ሩብ 'ለአንዳንድ ነገር ትሁንሽ' ብሎ ሸጎጥ ያደርግልሻል።ብታምኚም ባታምኚም የምትኖሪበት ዐለም Reality ይህ ነው"

አሁን ደግሞ እንባዋ ቆሞ ወደሆነ ወደማላውቃት አይነት አስፈሪ ሴት ተቀየረችብኝ።የምትነግረኝ ነገር ከኔ ህይወት ጋር ምን እንደሚያገናኘው ባላውቅም ልክ መሆኗን አልክድም።ለህይወትሽ የሚበጅሽ ስዩምን ማግባቱ ነው ለማለት ነው ይሄ ሁሉ? ራሷን አረጋግታ ስትቀመጥ ጨከን ባለ አንደበት እንዲህ አለችኝ።

"ዕውነታውን ተጋፈጭው ጊዜ!"

"የምኑን ዕውነታ?"

"የዳንኤልን ሞት መቀበል ከብዶሻል አውቃለሁ።"

"ማን ያውቃል እኔ ቀድሜው እንደማልሞት?እ?"

"እየውልሽ ሚጥሻዬ..."ልትቀጥል ስትል የክፍሉ በር ተንኳኳ።

"ይግቡ"አልኩ በደመነፍስ።ዳንኤል ነበር።እናቴ ሲያለቅሱ የቆዩ ዐይኖቿን እየጠራረገች

"ልጅ ዳንኤል!ና ግባ እስኪ"አለችው።ገብቶ ከጎናችን ተቀመጠ።ዝምታ በመሀከላችን ነገሰ።እናቴ

"እ...እናንተ መነጋገር ሳይኖርባችሁ አይቀርም እኔ ልሂድ!"ብላ ስትነሳ እጇን ይዤ በተማፅኖ አስተያየት

"እማ አትሂጂ አብረሽኝ ሁኚ!"አልኳት።ከዳንኤል ጋር ለብቻችን አንድ ክፍል ውስጥ የመቀመጡን ሀሳብ አልወደድኩትም።እምዬ እንዴት እንዳሰበችው አላውቅም።

"ስጋትሽ ገብቶኛል ግን ሁለታችሁም ላይ ዕምነት አለኝ።በነፃነት አውሩ"ብላ ጥላን ወጣች።እኔኮ ግን እሷ የምታምነኝን ያህል ራሴን አላምነውም።ከመውጣቷ

"አታስቢ ዶክተር! ከበሽታዬም በላይ ስብዕናሽ ወሰኔን እንዳላልፍ ያስገድደኛል"አለኝ።ምን ዐይነት ጦር የሆነ ንግግር ነው?

"እ...እኔ እንደዛ አላልኩም...ለማለት የፈለኩት..."ጠቋሚ ጣቱን ከንፈሬ ላይ አድርጎ በምልክት ዝም እንድል ነገረኝ።ዝም አልኩ።ትኩርርርርርር አርጎ ሊያየኝ ነው ብዬ ስፈራ ጣቱን አነሳና በዝግታ ሳቀብኝ።

"አሃሃሃ...ሃሃሃሃሃ...ሃሃሃ"

"ምን ያስቅሀል?"

"ትፈሪኛለሽ አ?ምኔ ነው ሚያስፈራሽ ቆይ?"

"ኧ...ኧረ እኔ አልፈራህም!ለምን እፈራሀለሁ?"ነጭ ውሸት ዋሸሁ።ሲጠጋኝ እፈራለሁ...የሆነ የማላውቀው ንዝረት መላ ሰውነቴን ይሰማኛል...በአካል ስንራራቅ ደግሞ ንዝረቱ ወደጭንቅላቴ ይወጣል...የምናብ ንዝረት...ከሀሳብ ተነስቶ ሰውነትን የሚያናውጥ ንዝረት።ይሄንን ይመስለኛል "ኤክስፐርቶቹ" የስሜት ፍቅር የሚሉት።የስሜት ፍቅር ሲራራቁ የሚደበዝዝ አካላዊ ቅርርብ ላይ ብቻ የተመሰረተ "ፍቅር-ቅብ" እንጂ ፍቅር አይደለም ሲባል ሰምቻለሁ። ምናውቄ?ኧረ በሆነልኝና ዳንኤል በጊዜ ሂደት የምረሳው የሆነ ጊዜ ላይ በህይወቴ የተከሰተ ጥሩ ነገር ሆኖ ባለፈልኝ!

"እህህህህም!ካልሽ እሺ...ግን ከአንደኛ ሚዜ'ኮ ምንም አይደበቅም...ንገሪኝ?"

"ያምሀል ግን?ንክ ነገር ነህ አይደል? "አልኩ ሌባ ጣቴን ጭንቅላቴ አካባቢ ከጆሮዬ ከፍ አድርጌ ቡለን እንደማላላት እያጠማዘዝኩ።

"እንግዲህ ሐኪሟም አንቺ ነሽ እኔ ምናውቄ!"

"ቀልዱ እዚህ ጋ ቢያበቃና ወደቁምነገሩ ብንገባስ?"አልኩ በመሰላቸት።

"በዛች ቀን ከጎንሽ መሆን እፈልጋለሁ!በሰርግሽ ቀን!ደስታሽን ባልካፈል ይፀፅተኛል" ከምሩ ነው?

"ኧረ ተው የኛ ክርስቶስ!ፍቅርህስ የት ገባ?የመኖሬ ምክንያት ነሽ የተባልኩትስ?ወይስ ስሜቱ ሰርጌ ላይ አንደኛ ሚዜ እስከመሆን አጀግኖሀል??ፍቅርህ የት ሄደ?"እየጮህኩ አፈጠጥኩበት።የሚደነግጥ ዐይነት አይደለም።

"እሱንማ ሸጥኩት"

"ዳንኤል ክፉ ነገር እንዳደርግ አታስገድደኝ እባክህን!"የደም ስሬ ሲግተረተር ይሰማኛል።

"ምን?ልትገይኝ ነው?ትንሽ ነውኮ የቀረኝ ታገሺ ሰበብ እንዳልሆንብሽ"

"እስኪ እየኝ"አልኩ ዐይኑ ላይ አፍጥጬ።ጉንጭና ጉንጩን በሁለት እጆቼ ይዤ አፈጠጥኩበት።

"ንገረኝ"

"ምን ልንገርሽ?"

"ውሸት ነው በለኝ"

"ምኑ?"

"አ...አሁን የሚሰ...ሰማኝ"...እንባዬን ማን መቶ ተው ይበልልኝ!

"ምንድነው የሚሰማሽ?" ትኩርርርርር ብሎ አየኝ።

"ታውቀዋለህ...ሳ...ሳ..ልነግርህ ታውቀዋለህ" እንባዬን በአይበሉባው ጠረገና

"እባክሽን ተይ ጊዜ!"አለኝ እጆቼን ከጉንጮቹ እያስለቀቀ

"ምኑን ልተወው?"

"የሚሰማሽን"

"አንተ ትተኸዋል?"በድጋሚ እንባዬ ወረደ።

"በፍፁም ልተወው አልችልም"

"እንጥፋ"አልኩ ሳላስበው።

"ከዛስ?"ፈገግ አለ።

"ከዛማ በቃ አብረን እንኖራለን!"

"አንቺ ሴት ጅል ስትሆኚም ያምርብሻል ልበል!?"

"መብትህ ነው በል!በነካ አፍህ እንጥፋ ላልኩህም እሺ በል"

ይቀጥላል

ደራሲት:- ማዕዶት ያየህ

@wegoch
@wegoch
@paappii
የአጠባውን ጉዳይ አልተነጋገርንም....የማቆሸሹን ነገርም አልተማከርንም። በውርጩ ቀን ውሃ ውስጥ ዋልኩ...በፀሀይ ቀን ለመልበስ እና ለመሽቀርቀር ግን አልታደልኩም። ምክክሩም ክርክሩም የሚመጣው ያንን ስሞክር ነው። የምረታውም ያኔ ነው።
...........
ፎቶ: አዲስ አበባ/ 2014
@wegoch
@wegoch
@wegoch
@ribkiphoto
..........
እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደልጅ
ስናዘግም በቀትር ያልታዘበን ማን ነበር?
ከእነኚህ ትንፋሽ አልባ ግትሮች ውጭ
የእኔና ያንተን መኮራረፍ የዘነጋስ ማን ነበር?

የእኛ ጉልበት ከግትሩም ከህያውም እየላቀ ያጨነቀው ማንን ነበር?
...........
ፎቶ: Dire Dawa/ March/2022
@wegoch
@wegoch
@ribkiphoto
..........
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ (ክፍል 10)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ነፍሴም ስጋዬም እሽታውን አሰፍስፈው ሲጠብቁ በዚያ ጦረኛ ዐይኑ ሲያተኩርብኝ ቆይቶ

"አይሆንም ጊዜ"አለኝ።

"ል...ል...ለምን?"ከንፈሮቻችን መነካካት እስኪቀራቸው ቀርቤ አፍጥጬ ጠየቅሁት።

"ትጎጃለሽ"

"ከዚህ በላይ ምንም አይጎዳኝም"

"ሞቴ ከዚህ በላይ እንደማያስለቅስሽ እርግጠኛ ነሽ?"አለኝ እንባዬን በድጋሚ እየጠረገ።

"አስሬ ሞ...ት ሞ...ት አትበልብኝ ካንሰር የያዘህ ይመስል!...የምትሞትበትን ቀን የነገረህ አለ?ንገረኝ አለ?"ቆጣ አልኩ።

"የስጋ ሞትን'ኮ ይዘገያል እንጂ ሁላችንም እንሞተዋለን We don't have to be cancer patients to die.No one is eternal on this stupid planet."

(ለመሞት የግድ የካንሰር ታማሚ መሆን አይጠበቅብንም።እዚህ ደደብ ዐለም ላይ ዘለዓለሚዊ ማንም የለም) ማለቱ ነበር።

"እና ምንድነው 'ምትለኝ ዳኒ?"

"My inside is already dead"

(ውስጤ ከሞተ ቆየ)

"እኔ ያንተን ስጋዊ ሞት ለመቋቋም የሚሆን ፅናት እንዳለኝ ብነግርህ የሞተው ውስጥህ አይነሳም?"

"የኔ ውስጥ ክርስቶስ ነው እንዴ ከሞተ በሁዋላ የሚነሳው?"

"እሺ የገደልኩት እኔ ነኝ እንዴ?"

"ማንን ውስጤን?"

"እ"

"ኧረ ቫይረሱ ነው ኪ...ኪ...ኪ...ኪ...ኪ"
በዚህ ሰዓት ሲስቅ ታድሎ!

"ታድለህ በናትህ!ሳቅህ ሲታዘዝልህ!እስኪ የሆነ ነገር ንገረኝ ምናልባት እስከወዲያኛው ደህና እሆን ይሆናል።"

"ምን ልንገርሽ?"

"እንደምትጠላኝ"

"እንኳን አንቺን ቀርቶ አንቺን ማፍቀሬን ራሱ ለአፍታ ጠልቼው አላውቅም"

"እና ምናባህ ነው አርጊ 'ምትለኝ?"እንባዬን እያዘራሁ ክንዱ ላይ ደካማ ቡጢ አሳረፍኩበት።

"ደስተኛ ሁኚ"

"እንዴት?"

"ልክ እንደዚህ..."ብሎ ጉንጬን በስሱ ሳመኝና ከተቀመጠበት ተነስቶ ሊሄድ ሲል እጁን ይዤ አስቆምኩት።ዘወር ሳይል

"በጣም ቆየሁ ዶክተር !ሰዎች አጉል ጥርጣሬ እንዳይገባቸው"አለኝ በር በሩን እያየ።አውቅበት የለ!ወደኔ ያልዞረው እያለቀሰ ስለሆነ ነው።ተነሳሁና ፊት ለፊቱ ስቆም አንገቱን ደፋ።አገጩን ይዤ ቀና ሳደርገው በምን ቅፅበት እንዳፈሰሰው ግራ የሚያጋባ የእንባ ማዕበል ፊቱን አጥለቅልቆታል።ምናይነት ሰው ነው ይሄ እንባውም ፈገግታውም አሽከር ሆነውት እንዳሻው የሚያዝዛቸው?

"ለማን ነው የምታለቅሰው?"

"ላንቺ"

"እኔ ምን ሆንኩ?"

"የሞተ ሰው ማፍቀርሽ አሳዝኖኝ ነዋ!"

የምለው ሲጠፋኝ እኔም እንባዬን አዘነብኩት።ሳግ ትንፋሼን ከላይ ከላይ እየነጠቀ ያሰቃየኝ ጀመር።ለደቂቃዎች አቅፎኝ አለቀሰ።ደረቱ ላይ ተለጥፌ በትኩስ እንባዬ ሸሚዙን አራስኩት።ለቅሶው ተገስ ሲልልን ተፋጠጥን።እኔም የሱን አስተያዬት ኮረጅኩና አንዳችን ሌላችንን የምንሸመድድ ይመስል ዓይኖቻችንን ለአፍታ ሳናርገበግብ ተያየን።ከእንግዲህ በሁዋላ አትገናኙም እንደተባሉ ሰዎች ነበር የተያየነው።ጮክ ያለ...ጠለቅ ያለ...ከቃላት ምልልስም በላይ ጉልበተኛ አስተያየት አይቶኝ ከክፍሉ ወጣ።

ፊቴን ታጥቤ ከመቀመጤ ስዩም መጣ።

"ደህና ነሽ ጊዜ?ምሽቱን ሙሉ ፊትሽ ጥሩ አልነበረም"

"ኧረ ደህና ነኝ...ትንሽ ራሴን ስላመመኝ ነው አታስብ ስዩሜ"

"ታካሚሽ በጣም ነው የሚያከብርሽ"

"ማን ዳንኤል?"

"አዎ!እሱን ስር ሚዜዬ በማድረጌ ዕድለኛ ነኝ።ከማንም በላይ ምርጫዬ ትክክል መሆኑን ነው ያረጋገጠልኝ"

"የምን ምርጫ"

"የሚስት ምርጨረዬን ነዋ!እንዲያውም በጊዜ ማግባቴ በጀህ እንጂ እጠልፍልህ ነበር እያለ ሲያስቀኝ ነበር ሂ...ሂ...ሂ..."

"ማን?"ክው አልኩ።

"ዳንኤል ነዋ!ምን ሆንሽ ግዝሽ?ስለማን ነው የምናወራው?"

"አ...አይ ዳ...ዳንኤል ባለትዳር መሆኑን አላውቅም ነበር ለዛ ነው"

"እየቀለድሽ ነው?እንደምታውቂ ነግሮኛልኮ" ምንድነው እየተፈጠረ ያለው?

"ም...ምናልባት ለኔ አለመንገሩን ረስቶት ይሆናል።ግን እንዴት ነው ባለትዳር ሊሆን የቻለው?አልኩ ሳላስበው።

"ለምን አይችልም?"ኮስተር ብሎ ጠየቀኝ።

"No...የህክምና ዶክመንቶቹ ላይ Marital Status Single እንደሚል አስታውሼ ነው።"ለካ ስዩም ወደውጪ ከሄደ በሁዋላ ነው የኤች.አይ.ቪ ህሙማንን ማከም የጀመርኩት!

"ምናልባት የማናውቀው ነገር ይኖራል።ስለሱ ልልሽ የምችለው ነገር ግን በጣም smart እንደሆነ ነው።'ትኩረትና ጊዜዋን ሳትሰስት ለሰጠችኝ ሀኪሜ በደስታዋ ቀን ከጎኗ ከመሆን የላቀ ልሰጣት የምችለው ስጦታ የለኝም' አለኝ።ታውቂ የለ አንደኛ ሚዜ ላረገው የነበረው ዘመኑን አንደነበር።ዳንኤል ላናግርህ እፈልጋለሁ ሲለኝ ከዘሜ ጋር አብረን ነበር ያገኘነው።አልክድም መጀመሪያ ሀሳቡ ጎርብጦኝ ነበር።አብሮ አደግ ጎደኛዬን ትቼ አይቼው እንኳን የማላውቀውን ሰው ያውም ስር ሚዜ ማድረግ የማይታሰብ ነበር።በሁዋላ ግን ራሱ ዘሜ ነው ወትውቶ ያስማማኝ።እንደዚህች ዓይነት የሰው መውደድ ያላት ሚስት ስለሰጠኝ ፈጣሪ ይመስገን።"አለና ወደኔ ተጠጋ።ስሜቴን ሸከከኝ የሚለው ቃል አይገልፀውም።በዚህ መሸከክ ላይ ደግሞ የዳንኤል የባለትዳርነት ሀሳብ ተደምሮ አዕምሮዬን እንደቅቤ ቅል ናጠው።

ስዩም ሊስመኝ ሲጠጋኝ ትንፋሹ የሲኦልን ወላፈን ሆነብኝ።ያ የዳቢሎስ የኩነኔ ጥሪ ዳግም አቃጨለብኝ።ብርግግ ብዬ ስነሳ ደነገጠና...

"ምነው?"አለኝ።

"እ...እንትን ነው...እንግዶቹ ሄደው አለቁ እንዴ?"

"ኧረ አሉ...ምነው?"

"ጥያቸው ጠፋሁኮ!ሄጄ ልቀላቀላቸው" ብዬ በነፍስ ድረሽ የተባልኩ ይመስል ክፍሉን በፍጥነት ለቅቄው ወጣሁ።

ወደ ሳሎን ሳመራ እጄ እየተንቀጠቀጠ ነበር።ቆም ብዬ ራሴን አረጋጋሁና እንግዶቼን ተቀላቀልኩ።ሁሉም ወይኑን እየተግነጨ የቡድን ወሬውን እያሟሟቀ ነው።ዙሪያ ገባውን ቃኘሁት።ዓይኔን አንድ ነገር ሳበኝ።ጥግ አካባቢ ያለው ስፋ ላይ ዳንኤል ከትዝታ(የቅርብ ጓደኛዬ ናት)ጋር ተቀምጦ ያወራል።ከልቧ ያስቃታል።አንድ እጇን በእጁ ይዞ በሌላኛው ወይኑን ጨብጦ ፉት እያለ የሆነ ለኔ የማይሰማኝን ነገር ይነግራታል።አሁንም ትስቃለች።ሳቋ ከልቧ መሆኑ ከልቤ አናደደኝ።ምን እያላት ነው እንደዚህ የምትገለፍጠው?😡

ሄድኩና ከአጠገባቸው ተቀመጥኩኝ።

"ሰላም ዶክተር"አለኝ ዘና ብሎ።

"ሰላም ክቡር አርክቴክት"አልኩት ብሽቅ ብዬ።ንዴቴ ግራ የገባት ትዝታም

"ግዝሽ ደህና ነሽ?"አለችኝ።

"ኧረ...ሁሉ ሰላም!እንዲህም ደህና ሆኜ አላውቅም ትዙ"


ይቀጥላል

ደሞ ትንሽ ተረጋጉ አታዋክቡኝ!

ማዕዶት ያየህ(@tizur_12)

21/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 11)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አስተያየቴና ቁጣ የቀላቀለ ንግግሬ ግራ ያጋባት ትዝታም

"በሉ ተጫወቱ እኔ ነፋስ ተቀብዬ ልምጣ" ብላ ከመሀላችን ተነስታ ሄደች።አፈጠጥኩበት...አፈጠጠብኝ

"ምን?"አለ ግንባሩን ከስክሶ እጆቹን እያወናጨፈ።

"አንተ ራስህ ምን?"

"እንዴ ምን ሆንኩ?"

"ከዚህ በላይ ምን ትሆን?"

"ከምኑ በላይ"

በግልምጫ ከአፈር ደባልቄው በተቀመጠበት ትቼው ተነሳሁ።ምንም ነገር እንዲያብራራልኝ አልፈለግሁም።ልሰማውም ትዕግስት አጣሁ።በንዴትና በሌላ በማላውቀው ጤነኛ ባልሆነ ስሜት እየተነዳሁ ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቼ ከቆይታ በሁዋላ ከስዩም ጋር እጅ ለእጅ ተያይዤ ስመለስ ዳንኤል በቦታው አልነበረም።ሰው ሁሉ እስኪታዘበኝ ጮክ ብዬ

"ዳኒ የት ሄደ?"አልኩ።ገሚሱ ዙሪያ ገባውን ይቃኛል።ገሚሱ ደግሞ ቀደም ሲል ተቀምጦበት የነበረውን ወንበር እየጠቆመ "አሁን'ኮ እዚህ ጋ ነበር...ምናልባት ስልክ ሊያናግር ወጦ ይሆናል"ይለኛል።በሚያወዛግብ ፍጥነት እየተራመድኩ ወደ በረንዳ ወጣሁ።

የበረንዳውን የመደገፊያ አጥር ተደግፎ ቆሞ ጠርሙስ ሙሉ ውስኪውን እየለጋ ይተክዛል።ጠርሙሱን መንትፌ እያፈጠጥኩበት

"ምን ማድረግህ ነው?"አልኩት።

"ት...ተይ እን...ጂ ዛሬ እ...ንኩዋን ል...ጠጣ ዶ...ክተር....የደ...ስታ ቀን ነ..ውኮ ዛሬ...አይደለም እንዴ?"


"በምን ቅፅበት ነው እንደዚህ የዘበዘብከው ቆይ?"የነጠቅሁትን ጠርሙስ ሳየው ውስኪው ከግማሽም አልፏል።ደነገጥኩ አይገልፀውም።

"እ...እየውልሽ ማነሽ የኛ ምሁር....የኛ ዶክተር"

"እሺ የኛ አርክቴክት "ደግፌ እንዲራመድ ልረዳው ስል አመናጨቀኝ

"ልቀ...ቂኝ ብየሻለሁ ሙሽሪት...ብት...ከበሪ አ...አይሻልሽም?ሰው እ...እንደዚህ ሆነን ቢ...ያየን ም..ኒላል?ኧ?"

አስችለኝ ብዬ ዝም አልኩ።

"ምንድነው ጊዜ ችግር አለ?"ከሁዋላዬ የመጣው የስዩም ድምፅ ነበር።

"ኧ...ትንሽ ጠጥቶ ነው ሳይጣላው አይቀርም"አልኩ በአንድ እጄ ዳንኤልን ደግፌ ጠርሙሱን የያዘውን ሌላኛውን እጄን ከፍ አድርጌ እያሳየሁት።

"My God!ምንድነው addiction አለበት እንዴ?"

"ኧ...የ...ምን add...iction ነው?የኔ ሱ...ስም በሽ...ታም አን...ድ ነገ...ር ብቻ ነው....እ...ሱም ምን መ...ሰለህ"በደመነፍስ አቋርጬው።

"በቃህ ዳንኤል በቃህ!ለመሆኑ መድሀኒትህን እየወሰድክ ነው?"በዚህ የለየለት ስካር ውስጥ ሆኖ ይሄንን መጠየቄ እኔ ራሱ መስከሬን ነው የሚያሳየው።ለነገሩ ፍርሀቴ አስክሮኛል።ባላቋርጠው ምን ሊል ነበር?ያመመኝ የሚስትህ ፍቅር ነው ሊል?በኢየሱስ ስም!

"የም...ን መ...ድሀኒት ነው ም...ትይው አንቺ...ሴትዮ...እ...እኔ በሽተኛ ነኝ እንዴ?"ስዩም ላይ አፈጠጠበት።ስዩም ግር ብሎት

"ኧረ በፍፁም!You r so good"ሲል መለሰ።ምፀት መሆኑ ነው መሰለኝ።


"ስዩሜ በናትህ ቤት አድርሼው ልመለስ እናቱ ይሄኔ ተጨንቀዋል።እንዲህ ሆኖ ብቻውን መድረስ ይከብደዋል።"

ስዩም ነገሮችን በበጎ ጎናቸው የማየት አባዜው ከፍ ያለ ስለሆነ ትንሽ ቅር ቢለውም እስክመለስ ከእንግዶቹ ጋር እንዲቆይ ተነጋግረን ወደ ቤት ገባ።እንደገባ የያዝኩትን ውስኪ ዐይኔን ጨፍኜ በቁሜ ሶስት አራት ጊዜ በጉሮሮዬ አወረድኩት።

"በ...ስመአብ አቺ! እንዴ...ት ነው ምጠጪው?😳"

"ዝም ብለህ ተራመድ!" እየተደነቃቀፍን ወደ መኪናዬ አመራን።ገብተን ከጎኔ ተቀመጠና

"እ...እኔ ነ...ኝ የምነዳው"አለኝ እጄን ይዞ።

"ልቀቀኝ አትጃጃልብኝ"

"አላ...ሳዝንሽም?"

"ለምን ታሳዝነኛለህ?ንገረኝ እስኪ ለምን ልዘንልህ?"

"ሟች ነኝ'ኮ...አንቺ ደግሞ ነፍሰ ገዳይ"

"እንዴት ነው እኔ ነፍሰ ገዳይ የምሆነው?"

"አየሽ አ?በቃ አትወጂኝም...ከኔ መሞት በላይ ያ...ንቺ ነፍሰ ገዳይ መባል ነው የሚጨንቅሽ!ክ...ክፉ ነሽ ክፉ!"እንባው መንታ መንታ እየሆነ መውረድ ጀመረ።

"በፈጠረህ!...ስለሞት አታውራብኝ"

"የፈጠረኝማ ረ...ስቶኛል"

"እሺ በቃ አሁን እንሂድ"ብዬ ሞተሩን ላስነሳው ስል

"በናትሽ...ስ...ስሞትልሽ..."

"ምንድነው?"

"እ...እናቴ እንደዚህ ሆኜ እንዳ...ታየኝ"

"So what?"

"የ...ሆነ ቦታ ጥለ...ሽኝ ጊቢ "

"የት ነው የሆነ ቦታ?

"አ...አላውቅም የሆነ ሆ...ሆቴል ነገር"

"እ...እንዴ ማዘር አ...አትጨነቅም?"

"ደ...ውዬ እነግ...ራታለሁ"

የመኪናዬ ጎማ ወደመራኝ ሄድኩ።ሆቴል ያለበት አካባቢ ስንደርስ ቆምኩና አትኩሬ አየሁት።ፊቱ ብዙ ስሜት ይታይበታል።ተስፋ...ተስፋ ማጣት... ሀዘን...ስቃይ...ጨለማ...ደግሞ እንደገና ብርሀን...ሞት...ወዲያው ደግሞ ትንሳኤ...

"ደርሰናል ዳኒ"

"እ?"አለኝ ብንን ብሎ።በጥቂቱም ቢሆን አሁን ስካሩ ተገስ እያለ ነው።

"ደረስን?"

"አዎ ደርሰናል...እኔ ልቅደምህና Room book ላስደርግ"ብዬ ልወርድ ስል እጄን ያዘኝ ። ጥያቄአዊ አስተያየቴን ሰነዘርኩ

"ይቅርታ"አለኝ አንጀት በሚበላ አስተያየት።

"ምንም አይደል"

"መቼ እንዳትጠይኝ ይህንን ብቻ ነው የምጠይቅሽ"

"እንዴት እጠላሀለሁ?"

"ከኔና ከሱ ማንን ነው የምትወጂው?"

"ማነው እሱ?

"ስዩም ነዋ"

"ሰዐቱ እየሄደ ነው room ልያዝልህ"ትቼው ልወርድ ስል በድጋሚ ያዘኝ።

"መልሺልኝ"

"ስር ሚዜው አይደለህ ለምን ራሱን አትጠይቀውም ምን ያህል እንደምወደው?"

"ካንቺ አፍ መስማት ነው ምፈልገው"

"እየውልህ ዳኒ"

"ወዬ"

"እየመሸ ነው room ልያዝልህና ልሂድ "

"ልክ ነሽ ባልሽ ይጠብቅሻል"

ምን እንደሰማኝ አላውቅም ጉንጩን ሳምኩት።

"ሴቷ ይሁዳ ነሽ አንቺ"

"ማለት?"

"ስመሽ ለስቃይ የምትሸጪ!ደግነቱ ስቃዩ ደስ የሚል መሆኑ ነው...አልገረፍም ...አልቸነከርም...አልሰቀልም....ክፋቱ ደግሞ ያው እኔጋ ምፅዓት እንጂ ትንሳዔ የለም...ሂጂ በቃ room ያዢ"

የአልጋ ከፍዬና የክፍሉን ቁልፍ ይዤ ስመለስ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዶታል።

"ዳኒ ተነስና ገብተህ ተኛ room ይዣለሁ" ዝምምም...

"አንተ ሰካራም ተነስ ግባና ነኛ ነው'ኮ እምልህ"አልኩት ትከሻውን እየወዘወዝኩ።ዝምምምም


"ዳኒ ተነስ ትዕግስቴ እያለቀ ነው።"ዝምምምምም...


ይቀጥላል

(የሚቀረው አንድ ክፍል ብቻ ነው)

በማዕዶት ያየህ(@tizur_12)

24/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
እኔስ ወደ ቤቴ ነበር የምጓዘው። አብሮኝ ያለውንም አለየሁትም ነበር።
ነገር ግን ሞገሱ ከቦኛል። በፅሞናም እራመዳለው።
የኤማሁስ መንገድም ለፅሞና የተሰጠ ነውና።
ፅሞናም ከእርሱ ብቻ የሚገኝ ነውና ልቤም ፍሰሀ አደረገች። መንፈሴም ተረጋጋልኝ።

........................
Photo: Addis Ababa/April/2022
© Ribka Sisay
@ribkiphoto
@wegoch
@wegoch
.......................
እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 11 የመጨረሻ ግማሽ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማን አይዞሽ እንዳለኝ እንጃ ዕይታዬ ከስርቆት ወደ ማፍጠጥ ተዘዋወረ።እየተጫወተብኝ ያለው ጨዋታ ቀመሩ ዐይኖቹ ውስጥ የተፃፈልኝ ይመስል ፍጥጥጥጥ አድርጌ ባየውም ቀመሩ አልገባኝም።

ይስቃል...ይዘፍናል...ይዘላል....ይጨፍራል...ይህን ሁሉ ደስታ የምር የሚወደኝ ከሆነ ከየት አመጣው?ከግርግሩ(ከሰርጉ) ማብቂያ በሁዋላ ድንገት ካይኔ ተሰወረብኝ።የት ገባ ብዬ መጠየቅም ፈራሁ።ሙሽራ ነኛ!'ባሌ' ካለ ምን ጎደለኝ?

ከወከባው ፈንጠር ብዬ ደወልኩለት።ድክምምምም...ስልልልል ባለ ድምፅ መለሰልኝ።

"ሀይ ዶክተር"

"ድምፅህ ልክ አይደለም ልበል?"

"በይ...በጣም ደክሞኛል ብታይ"

"እንዴት አይደክምህ እንዲያ እየዘለልክ!?"

"ምነው አጨፋፈሬ ይደብር ነበር እንዴ?"

"ኧረ አንተ ምን በወጣህ የኔ ካህን!ምን ያልተካንክበት ነገር አለ አንተ ቆይ?ማፍቀር ላይ ተክነሀል...ማስመሰል ብትል ሰውን ማትከን የግልህ ነው...አንተኮ ትለያለህ ሸዋዬ ትሙት"

"በእናትሽ ስም ምለሽ ክህነቴን ካፀደቅሽውማ የምር አድናቂዬ ነሽ ማለት ነው ሃ...ሃ...ሃ"

"በል በቃህ ዳንኤል...የያዝከው ጨዋታ ግልፅ አልሆነልኝም...የሚሆንልኝም አይመስለኝም....ከዚህ በሁዋላ በቻልከው አቅም እንዳላይህ ተጠንቀቅ! ቢበቃን ይሻላል!አንተ በኔ ህይወት ውስጥ ስም ስጭው ብባል እንኳን ስህተቴ ብዬ የምጠራህ ሰው ነህ!"መልስ ሳልጠብቅ ንግግራችንን ጆሮው ላይ አቋረጥኩት።

ከመቼውም በላይ አሁን ልክ እንደሆንኩና መስመር እንደያዝኩ ተሰማኝ።ራሴን ታማኝ ባለትዳር ሴት አድርጌ ሾምኩት።የማትበገረዋ ዶክተር...ኮስታራዋን ሀኪም ከተኛችበት የቀሰቀስኳት መሰለኝ።ለጊዜውም ቢሆን ጭንቀት ሽው ያለበት ሰላም ተሰማኝ።ዳንኤልን እንደአንድ አላስፈላጊ እጢ ከሀሳቤ ቆርጬ እንደጣልኩት ተሰማኝ...እሱን ቆርጦ መጣል ያን ያህል ቀላል ባይሆንም!


በማግስቱ ጠዋት የጊቢያችን በር በሀይል ተንኳኳ።ሀይሉ የሰው ሳይሆን የዳይኖሰር ይመስላል።ልብ ብዬ ሳዳምጠው ደግሞ እየጮኸ የሚያወራ ሰው ድምፅም የሰማሁ መሰለኝ።በደመነፍስ እየተነዳሁ ከፈትኩት።ስዩም ግራ በመጋባትና በድንጋጤ ተውጦ ከሁዋላዬ ይከተለኛል።

ልክ በሩን ስከፍተው ዕድሜዋ በእናቴ ዕድሜ የሚሆን ደርባባ ባልቴት ከአንዲት ሕፃን ጋር ከፊት ለፊቴ ቆማለች።የሴቲቱን ፊት ልክ እንዳየሁት የሆነ ዳንኤልን የሚመስል ነገር እንዳላት ለማስተዋል ደቂቃ አልፈጀሁም።እሷም ፋታ አልሰጠችኝም።

"አንች ነሽ የማሙሽ ሀኪም?"ደንግጬ ዝም አልኩ።ጮክ ብላ ደገመችው...

"አንች ነሽ ወይ ነውኮ 'ምልሽ አትናገሪም?"

"ይ...ይቅርታ ማነው ማሙሽ?" ሁኔታዋ እጅግ ያስደነግጣል።

"ዳንኤል! "ስሙ ሲጠራ መብረቅ እንደመታው ሰው ድርቅ ብዬ ቀረሁኝ።ስዩምም የሚካሄደው ነገር አልገባው ቢል አፈጠጠብኝ።በለሆሳስ

"ስዩሜ አንተ ግባ እኔ ላናግራቸው"አልኩት።ክርክርና ንዝንዝ ጠላቱ አይደል?ሳያቅማማ ወደቤት ተመለሰ።
እንደምንም ቀልቤን ሰብስቤ ለሴቲቱ መለስኩላት።

"አ...አዎ"

"የባባ ሀኪም አንቺ ነሽ?ጊዜ ማለት አንቺ ነሽ?"አለቺኝ ህፃኗ።የምለው ጠፋኝ. ...ዳንኤል ልጅ አለው ወይስ ሌላ ዳንኤል የሚባል ታካሚ አለኝ?ኧረ የለኝም።

"ነይ ተከተይኝ"አለችኝ ባልቴቲቱ እጄን ይዛ እየጎተተች።

"ቆይ እንጂ እናቴ ወዴት ነው 'ምከተልሽ?"እጄን በሀይል ከእጇ መንጭቄ አወጣሁት ።መለስ ብላ ወደኔ ቀረበችና

"አንቺ ግን ሰው ነሽ?የምር ሰው ነሽ?ምነው መወደድ እንዲህ ጨካኝ ያረጋል?ወየው ልጄጄጄጄጄጄን!እኔ ልድከምልህ ልጄጄጄጄጄን"ማልቀስ ስትጀምር የቆምኩበት ሁሉ ዞረብኝ።ቀጠለች

"ምናይነት አንጀት ነው ኸረ የወለደሽ?ኧረ እንዴት ያለሽውን ጉድ ነው የጣለብኝ!ልጄን ነጠቅሽን....አንድ ልጄን ገና በደንብ ሳልመርቀው. ....እኔ ልቃጠልልህ ልጄጄጄጄጄን...አሁን ነይ ተከተይኝ አታስጩኺኝ"ያስለቀቅሁዋትን እጄን መልሳ ይዛ ጎተተችኝ።ድጋሚ ለመመንጨቅ የሚሆን ጉልበት አልነበረኝም።አዕምሮዬ 'ዳንኤል ምን ሆነ?'በሚል ሀሳብ ተሞልቶ ሰውነቴን ማዘዝ ተሳነው።ወደቀልቤ የተመለስኩት የመንደሩን የኮብልስቶን መንገድ ጨርሰን በባልቴቲቱ መሪነት ዋናው የአስፋልቱ መንገድ ላይ ደርሰን ታክሲ ውስጥ እንድገባ ስታዘዝ ነው።

ወዴት ነው የምትወስደኝ?

ስለየቱ ዳንኤል ነው የምታወራኝ??

ሕፃኗ ልጅስ ማናት የማናት??

ጥያቄዎቹ ጭንቅላቴን ሊያፈነዱት ደረሱ።በጥያቄ ከመፈንዳት ቁርጥን አውቆ መፈንዳት ብዬ

"ዳንኤል ምን ሆኖ ነው?አሞት ነው?"
መልስ የሰጠኝ የለም።ቢጨንቀኝ ወደ ህፃኗ ዞሬ

"ሚጣዬ ዳንኤል ምንሽ ነው?"ስል ጠየቅሁዋት።

"ልጄ"አለችኝ።ዕድሜዋን ስገምተው ከ5-7 ዐመት ትመስለኛለች።

"የዳንኤል አባት ማነው ስሙ?"የማረጋገጫ ጥያቄዬ ነበር።

"ዳንኤል ደለጀ ምንይሁን"
የኔው ጉድ ነው😳

ባልቴቲቱ በዝምታ እያለቀሱ ነው።የምናወራውንም የሚሰሙ አልመሰለኝም።

"እና ልጅሽ...ማለቴ ዳንኤል ምን ሆኖ ነው?"ስላት ከነዚያ የሚያማምሩ የልጅ አይኖቿ የእንባ ጎርፍ መውረድ ጀመረ።አቀፍኳት...አንጀቴ ተላወሰ።ባልቴቲቱ ገርመም አድርጋ አየቻትና ወዲያው ዘወር ብላ

"ዝም በይ አንች የገፊ ዘር ልጄ ላይ አታሟርችበት"አለች።ልጅቱ ከላይ ከላይ ከሚነጥቃት ሳግ ጋር በሀይለኛው እየታገለች ታክሲው የሆስፒታላችን በር ላይ ሲደርስ ለቅሶዋን አቆመች።ባልተረዳሁት ተውኔት ውስጥ ዋነኛዋ ተዋናይት ሆኛለሁ።ከቤቴ የወጣሁት በሌሊት ልብሴ መሆኑን ራሱ ያስተዋልኩት ሆስፒታሉ ጊቢ ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ ዐይኑ እኔ ላይ ሲሆን ነው።ትዕዛዝ እንደሚጠብቅ ሮቦት ተገትሬ መቆሜን ያስተዋለችው ሴቲቱም

"ምን ይገትርሻል ተከተይኝ እንጂ!"ብላ በማንባረቅ ወደ ድንገተኛ ክፍል የሚወስደውን ኮሪደር ተከትላ ፈጠን ፈጠን እያለች ተራመደች።ልክ ባለፈ መደንዘዝ ውስጥ ሆኜ ተከተልኳት።ህፃኗ ሴትዮዋን ተከትላ ከፊት ከፊቴ ቱስ ቱስ እያለች ትራመዳለች።እፍፍፍ ቢሉባት የምትወድቅ ነው የምትመስለው።አረማመዷ ትክክል አይደለም።እንቅልፍ እንደራቃት ግልፅ ነው።

የድንገተኛ ክፍሉ በህክምና ፈላጊዎች ተጨናንቋል።ከዚያ ሁሉ ሰው መሀል ዳንኤልን አንዱ አልጋ ላይ ተጋድሞ ሳየው በቁሜ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም።ተዝለፍልፌ ልዘረጋ ስል አንዷ ነርስ አፈፍ አድርጋ ያዘችኝና

"ምነው ዶክተር ሰላም አይደለሽም እንዴ?"አለችኝ።

"ሲ...ሲስተር ይሄ 'ፔሸንት' ም...ምን ሆኖ ነው?"ወደዳንኤል ጠቆምኳት።አየት አረገችውና

"በጣም ያሳዝናል ዶክተር!ለ 20 ቀን የሚሆነውን መድሀኒት ነው ባንዴ የዋጠው...ተስፋ ያለው አይመስለኝም"ብላ በቆምኩበት ጥላኝ ወጣች።እየተጎተትኩ ወደ አልጋው ሳዘግም የሆነ ነገር እግሬን ወደሁዋላ ይስበዋል።ትናንት ማታ በስልክ የተናገርኳቸው ቃላት...

ያቺ ብላቴና የተኛበት አልጋ ጠርዝ ላይ ያለውን የዳንኤልን እጅ ጠቅጥቃ ይዛ እንባዋን ለጉድ ታዘንበዋለች።እንደልማዱ አይኖቹን ሳያርገበግብ ቡዝዝዝዝዝዝ ብሎ አያትና ወደኔ ዞረ።ደነገጥኩ።ዐይኑ ይበላኝ ይመስል ውስጤ ' ወጠሽ ሩጪ አምልጪ' የሚለኝ ነገር መጣ።

የተከለብኝን ዐይኑን አንስቶ ወደእናቱ ዘወር አለና የሆነ ምልክት ሲሰጣት ህፃኗን ይዛ ከክፍሉ ወጣች።በድጋሚ አየኝ።ወደኔ ቅረቢ የሚል ዐይነት አተያይ...ስፈራ ስቸር ቀረብኩትና የአልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ።እያማጠ 4 ቃላትን ወረወረልኝ።

"አ...ንቺ ም...ንም ስህተት አልሰራሽም"

ከዚህ በላይ ልሰማው አቅም አጣሁ እየሮጥኩ ከክፍሉ ወጣሁና በረንዳው ላይ ቆምኩ።
2024/09/22 17:37:39
Back to Top
HTML Embed Code: