Telegram Web Link
-ፅልመት-

ክፍል አራት

ቤተልሄም አልኳት ደንግጣ ትኩር ብላ አየችኝ ፤ከስንት ወር በኋላ ነው የጠራኋት ድሮ ድሮ ለቀልድ ነበር ሙሉ ስሟን የምጠራት ፤ ድሮ ድሮ ቤተልሄም ስላት ጌታዬዋ ነበር የምትለኝ። ዛሬ ቤተልሄም ብዬ ስጠራት ደንግጣ አፍጥጣ ብቻ አይታኝ አጎነበሰች ፤ ጌታዬዋ ማለት የፈለገች ይመስለኛል ግን ደግሞ ከንፈሯ አልላቀቅ ስላላት ነው ወዬ ማለትም ፈልጋለች ፤ ጆሮዋን ጠርቻት ይሆን አይሆን ማመን ስላልቻለች ነው። ቀስ ብላ በለሆሳስ እየተራመደች ጠጋ አለችኝ እረጋ ብዬ ለስለስ ባለ ቃላት ምነው አልኳት? ትኩር ብላ ከወገቤ ብቻ ቀና ያልኩበት የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ቁልቁል በስስት ተመለከተችኝ። ቤት ለምን አትሄጂም ኤዶሜ አትናፍቅሽም አልኳት? አልጋ ላይ እርፍ ብለሽ ፤ ጠንከር ብለሽ ብትመጪ አይሻልም አልኳት ቀስ ብላ በእርጋታ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች። በስስት በመኪናው አደጋ ሳቢያ የተጎዳውን ሰውነቴን እያየች ። "ትንሽ ቀን ነው የቀረን አብረን እንሄዳለን አለችኝ "። አንች እኮ በጣም እየተጎዳሽ ነው አልኳት። አይኗ በፍጥነት ትኩስ እንባ አረገዘ ጭኔ ላይ ያረፈውን እጄን ሳመችው ። እጄን እንደያዘች ፤ "አንተን ለማን ጥዬ" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። እጄ በእንባዋ ራሰ ዘማዊቷ መቅደላዊት የጌታዋን እግር በእንባ ስታጥበው የነበረው የንስሃ እንባ ከቤተልሄም እንባ ጋ ተመሳሰለብኝ ። እጄን ከእጇ በቀስታ ነጥቄ የተሰባበረ ፀጉሯ ላይ አደረኩት ። ፀጉሯን ሳሻሻት ፤ ሆዷ ባባ መሰለኝ ፤ የበለጠ አለቀሰች ፤ ሲቃ እየተናነቃት ተንሰቀሰቀች ። ከሲቃዋ ጋ እየታገለች ፤ ቃላቷ እየተደናቀፈባት "ለእኔ ባረገው !" አለቺኝ ። እንዲህ ያለቀሰችው አባቷ የሞቱባት እለት ብቻ ነው ። አለቃቀሷ ፤ ጉስቁልናዋ ፤ ኩርምት ማለቷ አንጀቴን በላው መሰለኝ አይኔ በእንባ ሞላ ። አቅም አነሰኝ እንጂ እንዲህ እየወደድሺኝ ለምን ካድሺኝ ማለት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ማለት የቻልኩት እንደዚህ ራስሽን የሚያስጥልሽን ፤ በዓይንሽ ሙሉ እንዳታይኝ የሚያደርግሽን ስህተት ውስጥ እንዴት ገባሽ አልኳት ?? ቤተልሄም የአይኗ ሽፋሽፍት በእንባ እንደተጨማለቀ በሃሳብ ሄደች ግሩም ጋ ግሩም እቃ የሚያስረክባት ደንበኛዋ ነው። በቴሌግራም ፤ በሜሴንጀር እቃ ያሳያታል ፤ ይጨዋወታሉ ፤ ይከባበራሉ ። ግሩም ነፃ አይነት ሰው ነው ፤ የፈለገውን የሚቀልድ አይነት ፤ በቤተልሄም ግዙፍ መቀመጫ ላይ ያሾፋል ፤ ብቻውን ይስቃል ፤ ወፍራም መቀመጫ ላለው ምን አይነት ወሲብ
ምቹ እንደሆነ ይቀላብዳል ። ትሰማው ትሰማው እና አንተ ጨምላቃ ትለዋለች። ሌላ የስራ ወሬ ይቀጥላል። ክችች አይልም ። እንደዚህ አይነት ቀልድ እና ጨዋታ ከእሷ ጋ ብቻ እንደሚጫወት ሹክ ይላታል ። ቁንጅናዋን ያስታውሳታል ፤ ያከብራታል ወይ እንደሚያከብራት ያስመስላል።
ከሌሎች አቅራቢዎች የተሻለ በጥሩ ዋጋ ስለሚያቀርብላት ፤የገዛቸውን እቃ ገንዘብ በቶሎ
አምጪ ስለማይላት ሙጥኝ ብላበታለች
ግሩም ምቹ ጊዜ ሲያገኝ ፤እንዴት አጣፍጦ እንደሚዋሰብ ይተርክላታል። ጡቷን እንደሚያምር ጠቆም ያደርግላታል ፤ ከወሲብ ወጣ ያለ ቁምነገርም ጨዋታም ያወራታል። ቁም ነገር ሲያወራት ፤ ሸፋዳነቱን ያስረሳታል ፤ ወሲብ ነክ ጉዳይ አይቀላቅልም በሌላ ቀን ይመጣ እና
ስለወሰባት ልጅ መቁነጥነጥ ፤ ማቃሰት ፤ መሻፈድ እርካታ እያዋዛ አፏን አስከፍቶ
ይተርክላታል። አወሳሰቤ ስቧት ድገመኝ ያላለችኝ የለም እያለ አለስልሶ ይጎርራል ከዛ ወሲባዊ ወሬውን አያስረዝመውም ፤ እሷ ከራሷ ጋ ታግላ ከማስቆሟ በፊት ራሱ ያቆማል ። እንድታወራለት በትንሹ መንገድ ስትከፍትለት ሆን ብሎ እንዳልገባው ይሆናል። እጥረት ደሞ ለፍላጎት መናር አስተዎፅዖ ያበረክትም የለ ከባሎ ሰለሙን ጋ የምትወስበው ወሲብ ባህላዊ ሆነባት ። ከሰለሙን ጋ አልፎ አልፎ ትዋሰባለች ፤ ሰለሙን ከእሷ በፊት ልምድ የለውም ፤ ቅደመ ወሲብ የለ ፤ መላላስ ፤ መማጠጥ ፤ መፋተግ ፤ መጋፈፍ ፤ ኖሮት አያውቅም ። እሱ ሲጨርስ የእሷን ስሜት
አይለካም ። ብዙ ቀን ምልክት ብትሰጠው አልገባው ብሏል። የግሩም ወሲባዊ ትረካ የሰለሙንን ድክመት አጎላባት ። በወሲባዊ ህይወቷ ደስተኛ እንዳልሆነች አስተያየችው።
ከራሷ ጋ ተሟግታ እንደዚህ አይነት ወሬ አታውራኝ ባለትዳር ነኝ እኮ እለዋለሁ ብላ ቃላት
አሰናድታ ሱቋ ሲመጣ ሲያገኛት በጠበቀችው እለት አያወራትም። ተገማች አለመሆን አላማን ለማሳካት ምቹ ነው ። አዕምሯችን የምንመግበው ውጤት ነው። እንዴት ሰው የሚያቀውን ከሰማው ጋ ያወዳድራል ። ለነገሩ ሴጣንስ ቢሆን ሄዋንን የረታት ያላየችውን በማስጎምጀት አይደለምን?
ግሩም እንደሚላት አይነት ወሲብ ከባሏ ጋ ለመዋሰብ አስባ ወደ ቤት ብዙ ቀን አቅዳ ቤቷ
ሄዳ ታውቃለች ። በዚህ መጠን ግልፅ መሆን የመጣችበት ቤተሰብ እና ማህበረሰብ አልፈቀደላትም። ከመሬት ተነስታ አወሳሰባችን እንቀይረው ማለት ከበዳት። አንድ ምሽት ልብስ ሲቀይር ሲራቆት ጠብቃ ፤ ጌታዬዋ አለችው ፤ ሲዞር ስሷን ፒጃማ በዳንስ መልኩ አሸቀንጥራ ፤ ጥላ ተጠመጠመችበት ሳመችው ፤ ፈገግ ብሎ ምን ሆነች ዛሬ አስተያየት ሲያያት ትዝብቱ አስፈራት ፤ በአቀደችው መንገድ አልሆነም ፤ የአዘቦታቸውን አወሳሰብ ተዋሰቡ ግሩም ባለትዳር ሆኖ ሌላ ጋ መሄድ የተለመደ ነው እያለ በጋራ የሚያውቋቸውን ሰዎች እንዴት በትዳራቸው ላይ እንደሚሄዱ በማስረጃ ነገራት። ስትገረም ተራ ነገር መሆኑን እያቀለለ ያሳያት ጀመር። ሴጣንስ ኢየሱስን ሊያስተው ጥቅስ እየጠቀሰ አልነበር ።ታማኝ ብላ የምታከብራቸውን ሰዎች እንደጥቅስ እየጠቀሰ ለብልግናቸው አመቻቻት። አንድ ቀን ሱቋ አመሻሽ ላይ የመውጫዋ ሰዓትን ጠብቆ ፤ ሱቅ እየዘጋጋች ሳለች መጣ ፤ ስለ ስራ ሌሎች ጉዳዮች እያወራት ፤ ወሬውን ጠምዝዞ ወሲብ ቀስቃሽ ወሬ ፤ የሚያሻፍድ ስዕላዊ ትረካ በተካተተበት ሁኔታ እየተረከ አፏን ከፍታ ስትመሰጥ በዝግታ የሱቋን በር ተነስቶ ዘጋው ። አንድ አንዴ የሰውነት ሁኔታ ከቃል በላይ ያግባባል ፤ በደመ-ነፍስ እንደሚታረድ በግ ምንም ሳትናገር ጠበቀችው

ይቀጥላል ......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#adhanom mitiku
ፅልመት -

ክፍል - አምስት
(የመጨረሻ ክፍል)

በቃል ሳይነጋገሩ ተመካክረው እንደተቃጠሩ ነገር በሽፍደት ገላቸው ላይ የጠለቁ ጨርቆችን የተወላለቁት አስጎምብሶ ፀጉሯን እየነጨ ፤ እየሳመ ፤ ቂጧን እየመታ ፤ እንደምታምር እየነገራት ፤ እየሰደባት ፤እያንሿካሿከ ፤ አንገቷን እያነቀ ፤ አስለምኗት ለረጅም ደቂቃ እየገለባበጠ ወሰባት ። እውነቱ ባሏ እንዲ አዋርዶ ሊወስባት አይችልም። በባሏ ላይ መሄዷ የጥፋተኝነት ስሜት ቢሰማትም አልጠላችውም ። ከዛ ግሩም ለሁለት ሳምንት ጠፋ ። አግኝታው ትክክል እንዳልነበሩ መንገር ብታስብም ግሩም ጠፋ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ድሮ እንደሚልክላት የመጡ እቃዎችን በቴክስት ላከላት ። ሱቋ ሄዶ ምንም እንዳልተፈጠረ የስራ ወሬ አዋርቷት ተመለሰ። Slave Sex እያሰሰች መመልከት ጀመረች ።ያየችውን የሚያሳያት ፤ እንዳየችው
የሚያደርጋት ግሩም ብቻ ነው ! ሰሌን መቀመጫዬን እየመታኸኝ ፤ ፀጉሬን እየነጨህ ፤ እየሰደብክ እንዋሰብ እንዴት ትለዋለች ? ግሩምን እሷ ፈለገችው። ግሩም ምንም መወስወስ ሳያስፈልገው ፈለገችው። ተገናኙ እንደፈለገችው ፤ እንዳየችው ለሁለተኛ ጊዜ እሱ በመረጠው ስፍራ ተዋሰቡ ። ከሰለሞን ጋ የምትዋሰበው ለሰለሙን ስሜት ብቻ ብላ ሆነ። ሰሌን እንደምትሳሳለት ፤
እንደምታፈቅረው ፤ እንደምታከብረው የሚያቃት ሁሉ ያውቃል። እች አለም መቼም ግርንቢጥ ነች ምክንያቱ እና ውጤቱ መች ይገናኛል ? ምንአልባት ግርንቢጥ የሆነችው እንደ ቤተልሄም ያሉ ሰውች አቆሽሸዋት ይሆን?? እንደግሩም ያሉ ሰዎች በክለዋት ይሆን ? ወይስ እንደ ሰሌ ያሉ ምልክት የማይገባቸው አልያ ግትር ሰዎች አስተዋፅዖ እያበረከቱ ይሆን ? ለአምስተኛ ጊዜ በእሷ የበለጠ ፍላጎት ፤ በግሩም የቦታ ምርጫ የተገናኙ ቀን ነው ባሏ ሰለሙን ያያቸው።
ቤተልሄም ባሏን ታውቀዋለች ፤ ውስልትናዋን እንደደረሰበት ስድስተኛ የስሜት ህዋሷ
ነግሯታል። ሰሌ በመኳረፍ አያምንም ።የበዛ ኩርፊያ የሚፈታው ችግር የለም የሚያባብሰው እንጂ ይላል። ሰለሞን ቤተልሄምን እንደ ልጁ ኤዶም ነው የሚሳሳላት ፤ መሳሳቱን ተርኮላት አያውቅም ፍቅሩን በምግባር የሚገልጥ ሰው ነው ። ካለ'ኔ ማን አለሽ ሚስቴም ልጄም ነሽ ይላታል። ሰለሞን በሰው ወሬ ባልተረጋገጠ ነገር ፤
ከባድ ባልሆነ ነገር እንዲህ ሊጠየፋት እንደማይችል ታውቃለች። ፊቱን ካጠቆረባት በኋላ ፤ ሰሌ ከጠላት በኋላ ሰውነቷ ቀንሷል፤ ድብርት በልቷታል ። እሷ ራሷ ራሷን ጠልታዋለች። ከተበደለ የበለጠ ፤ መበደሉን የገባው በዳይ ኑሮው ሲኦል ነው። በክፉ ትዝታ ጥልቅ እንዳለች አልጋው ጫፍ ላይ ኩርምት ብላ ጤነኛ ጭኑ ላይ ላመል ያህል እንደተደፋች ዶክተሩ ገባ እንዴት ናችሁ ብሎ ሲገባ የቤተልሄምን ፊት ያጨመላለቀውን የእንባ አሻራ አይቶ በሰለሞን
አደጋ መሰለው። "ምን ሆንሽ ልጅ ቤተልሄም ፤ ተይ እንጂ አሁን ድኖ የለ እንዴ" እያለ በገመተው ጉዳይ ላይ ገሰፃት። በማናውቀው ጉዳይ ላይ ገምተን ማፅናናት ከትዝብት እና ከአስብልሃለሁ ውጪ የሚያመጣው ትርፍ የለም። ከሆስፒታል ከወጡ ከወር በኋላ ፤ከጥፋተኝነት ስሜት ስላልተላቀቀች ነፃ መሆን ሲታገላት ሰለሙን ቤቲሻዬ እናውራ አላት ያቺ የፈራችው እለት ደረሰች ፤ አስባበት አብሰልስላው ፤ አውጥታ እና አውርዳ ከልቧ ብትማከርም ፤ እናውራ ሲላት ሆዷ ባባ ። ፊቷ በሃዘኔታ እያየ ይቅርታ አድርጌልሻለሁ አላት ። ፍቅር የሚለካው ለምናፈቅረው ሰው ይቅር ለማለት እና ለመረዳት በምንሄድበት ርቀት እና ብዛት ነው። ወድቀሽ እምነቴን በላሽብኝ ። ትሆኛለሽ ያላልኩት ቦታ ተገኘሽ። ራስሽን ትበድያለሽ ፤ በዚህ መጠን ትጎሳቆያለሽ ባላልኩበት ደረጃ ፤ ማቅ ከመልበስ የማይተናነስ ፀፀት ውስጥ ራስሽን አድርገሽ ራስሽን ይቅር ማለት አቅቶሽ አየሁሽ ። ሳትነገሪኝ አሳየሺኝ ፤ ስለማውቅሽ ገባሽኝ። ይሄ በእኔ እና በአንቺ መሃል ያለ በእኔ እና በአንቺ መሃል የሚቀር ገመና ነው ። ከፈፀምሽብኝ በደል ያሳየሺኝ ፍቅር ይበልጥብኛል ። ባየሁት ውስጣዊ እና ውጫዊ መቆሳሰል ሳቢያ ብሰቃይም ፈጣሪ እችለው ፤ እማርበት ዘንድ መንገድ ከፍቶልኛል። ደሞም በሌላ ምክንያት ብንጣላ ፤ ብንቆስል ይሻላል እንጂ ፤ ለአንቺስ ዘሙታብኝ ተውኳት ብዬ ስሄድ ፤ አንቺስ ምን አይነት ስሜት ይሰማሻል? ያ ሁሉ ጊዜ ያፈቀርሽኝ ፤ የዋልሺልኝ ለመኖር አንድ ምክንያት እንዳልሆንሽኝ ሁሉ ፤ በአንድ ትልቅ ስህተት በዜሮ ለምን እደረምሰዋለሁ ። ኤዶም ነገ በምን ተጣላቹ ስትለኝ በምንስ እላታለሁ?? ብሎ አይን አይኖን አየ ቤቴልሄም ከብዙ ዝምታ በኋላ "ጌታዬዋ እኔ ካንተ ብለያይ በመለያየቴ ብቻ አይደለም የምጎዳው መተካት ባለመቻሌ ነው። አንተ የምትተካ ሰው አይደለህም ። የእንደዚህ አይነት ክስተት መጨረሻ ወህኒ ቤት ነበር። እወድቃለሁ ባላልኩት መንገድ ወደኩኝ ራሴን እስክጠላው ። መደበቂያ ፤ መኮብለያ እስካጣ ፤ ነፍሴ እስክትጨነቅ ነው መሽቶ በነጋ ቁጥር መፅናኛ ያጣሁት። ይቅርታ መቼ ጠየኩህ ስብራቴን አይተህ ማርከኝ እንጂ። አጥፍቻለሁ ፤ ይቅርታ ስላረክልኝ አመሰግንሃለሁ ። ራሴን በመፀየፍ እንዳልኖር ፤ ትከሻህን ሰጠኸኝ ብላ እግሩ ላይ ወደቀች። አነሳት እና አቀፋት አንገቱ ስር ውሽቅ አለች። አንድ አንድ ውድቀት ትሁት እንድንሆን ያድቦለቡለናል ፤ እንዳንፈርድ ያንፀናል ። አፈቅርሃለሁ ሳይሆን ሳፈቅርህ እኖራለሁ ፤ ነገር ግን ካንተ ጋር መኖር አልችልም። ነገ ሲውል ሲያድር ፤ የሚያስመሽ ጉዳይ ሲገጥመኝ ፤ ስልኬ ቢዘጋ ምን ትላለህ ፤ ምንስ ያስብ ይሆን እያልኩ መሳቀቁ ይገለኛል። ይቅርታ አረክልኝ ማለት እኔ ላይ እምነት ይኖርሃል ማለት አይደለም ፤ እምነት ሲደረመስ እንጂ ሲገነባ ዘመናት ይፈልግል። የቤታችን ምስሶ መተማመናችን ነበር ናድኩት ፤ አይኗ እንባ ግጥም አለ ፤ እንባዋን ለመቆጣጠር ታገለች ፤ አልሆነም አሸንፏት ወረደ ይሄውልህ ጌታዬዋ ፍጡር እንደፈጣሪ አይደለም ይቅር ብሎ አይረሳም ። ፍጡር እንደ ፈጣሪ አይደለም
ለበደልነው በደል ከንስሃ በኋላም ይጠይቀናል ፤ አምላክ ነው ከቀጣን በኋላ ቁስላችንን የማይነካብን ፤ የሚረሳልን ። ነገ ሳስከፋህ በደሌ ውስጥህ ያቃጭልብሃል ። ሰትበድለኝ ጮኬ ስናገር የበደልኩህ ይጮህብኛል ወይ አንተ ታስታውሰኛለህ። ነገ ድንገት ከማንም ጋ በመጋደም ብትጠረጥረኝ እንዴት ትጠረጥረኛለህ ማለት አልችልም፤ አንተም እንዴት በዚህ ተልካሻ ነገር ልጠረጥርሽ እችላለሁ ማለት አትችልም ፤
የትዳራችንን መዓዘን ደርምሼዋለሁ ። ጌታዬዋ ላፍቶ ሄጄ ተከራዮቹን ልቀቁ ብያቸዋለሁ ኤዶሜ ከኔ ጋ ብትሆን ደስ ይለኛል ግን አንተ ደስ እንዳለህ አለችው" እንርግት ፤ ዝም እንዳለ ፊቱ ላይ ምንም ሳይነበብ ቃል ሳያወጣ ቆይቷ አለም እንዲም ነች አለ ።ሌላ ምንም ሳይናገር አንገቱን በእሽታ ነቀነቀ።

-ህይወት ቢቀጥልም ይሄ ፅሁፍ አልቋል -
---- ---- ---- ---- ----

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
የፍቅር ቀን ወይም የአደይ ቀን

'እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የፍቅር ጀግና ለማድረግ በአገራችን ቫለንታይንስ ደይ እየተባለ የሚከበረውን የፈረንጆች በዓል ተውሰን እንደ አገራችን ፀባይ ለማክበር እቅድ አውጥተን ነበር፡፡

የጦር ጀግኖች ብቻ ሳይሆን የፍቅር ጀግኖች ያስፈልጉናል፡፡

ቫለንታይን ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ ክፋት የለበትም፡፡ ተቃቅፈው የሚሄዱ ፍቅረኞች ማየት ደስ ይላል፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘው በመንገድ የሚሄዱ ወጣቶች ትዕይንት የሚናፍቅ ነው፡፡ እኔ ወጣት በነበርኩበት ዘመን እንዲህ ማድረግ ያሳፍረን ነበር፡፡ ልጆቻችን በፍቅር እንዲያፍሩ አልፈልግም፡፡

ፍቅርን ከብልግና አምታተናል፡፡

ይሄን ቫለንታይን ቀን በዓል ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ሦስት ነገሮች ማሟላት አስበን ነበር፡፡

አንደኛ፤ ከየትኛውም የአገራችን ክፍል አስገራሚ የፍቅር ታሪኮችን መሰብሰብና ለብሔራዊ በዓል የሚያገለግለንን ነቅሰን ማውጣት፤

ሁለተኛ፤ ምሳሌ የሚሆኑንን የአበባ አይነትና የአበባ ቀለም መምረጥ፤

ሦስተኛ፤ በታዋቂ ገጣሚ፤ ሙዚቀኛና ኮርዮግራፈር በአሉን የሚዘክር በቀላሉ አድማጭ ሊያንጎራጉረው የሚችል ዜማ መስራት ነበሩ፡፡

ከነዚህ ውስጥ ኮሚቴው ለብቻው የሚወስናቸው የበዓሉን ቀን፣ የአበባው ዓይነትና የአበባ ቀለም ሲሆኑ፣ የተቀሩት ዐላማዎች ግን በጥናትና በህብረት ውሳኔ ይፀድቃሉ፡፡

አገራችንን ከአደይ የበለጠ ምን አይነት አበባ ሊወክላት ይችላል? ከመስከረም ወር የበለጠ ምን የሚያምር ወር አለ? ቢጫ ቀለምስ ውብ አይደለም?

የአገራችን ስም ከተሰራባቸው ቀለማት አንዱ ዮጵ ትርጓሜው ቢጫ ወርቅ ማለት ነው፡፡ ቢጫ የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡ ፀሐይ ከሌለ ሕይወት የለም፡፡ እንደ ፍቅረኞች ፊት የምታበራው ፀሐይ አይደለችም? የተፋቀሩ ሁሉ እየተንቦገቦጉ አይደለ የሚውሉትና የሚያድሩት?

#የስንብት_ቀለማት
አዳም ረታ

@wegoch
@wegoch
@paappii
አንድ ወፈፌ ወንደላጤ ጎረቤት አለኝ። ቀን ቀን ፍፁም ሰላማዊ ሰው ነው። አንገቱን ሰብሮ ሰላምታ ሲሰጥ በከንፈሩ አፈር ቅሞ ለመመለስ ትንሽ ነው የሚቀረው :)
እንደውም አከራያችን እትዬ ዘነብ አንዳንዴ "ልጄ ተው እንዲህ አለቅጥ አታጎንብስ ዲስክህ ይንሸራተታል " ይሉታል።
እሱ ፈገግ ብሎ በሀፍረት ያቀረቅራል ። ጭራሽ የሆነ ጊዜ ላይ ቤቱ ቡና አፍልቶ ጠራን !
በጠባብ ክፍሉ ውስጥ እንደ በግ ኮኮር ተራርቀው የሚገኙ የቤት እቃዎቹን እየገረመመን ተሰየምን።
እትዬ ዘነብ ደግሞ እንደ ሀረር ሰው ቀጥታ ነው ንግግራቸው...ያ ሁሉ የግቢው ሰው በተሰበሰበበት
"አንተ ምነው እቃህን በወግ ብትሰድረው?... " አሉት ... ትንሽ ቆየት ብለው ደግሞ...
"እግዚኦ ያ ምንድነው ሀይላንድ ውስጥ ያለው?" ብለው ጮኹ!
ናደው በድንጋጤ "የቱ ?" ብሎ መለሰ። ሀይላንዱን እኮ አፍጦ እያየው ነው !
"ሀይላንድ ላይ ነው እንዴ የምትሸናው?"
ደነገጥን!
እትዬ ደግሞ አንዳንዴ የሆነ ነገር አይተው ላሽ ቢሉ ምናለበት?
" ኸረ ቢራ ነው እትዬ! ኸረ እንደውም ልቅዳሎት " ብሎ ተነሳ...
እትዬ ሀይላንዱን ሰገራ እንደነካው እንጨት ተጠይፈው ...
"አንተ ሂድ ! ምን ያለው ሰላቶ ነው ባካችሁ?
ላስቲኩን እየው እስቲ? ጎዳና ተዳዳሪ መስሏል እኮ! "
እኛ ለሱ ተሸማቀቅን።
ናደው ወሬውን ለማስቀየስ መሰል... ጀበናውን በእጁ እንደያዘ.. ."አህ ...ህ " ብሎ አቃሰተ ።
"ምነው?" አልኩት እሱ በቀደደው አዲስ ወሬ ለማፈትለክ ...
"ብርድ መቶኛል መሰለኝ..አንዳንዴ ትከሻዬን ይወጋኛል "
"በዚህች ስስ አንሶላ ተሸፍነህ እየተኛክ እንኳን ብርድ መጋኛም ስላልመታህ ፈጣሪን አመስግን " ብለው ቀጠሉ እትዬ.. .
"ስማ ምነው እኔ ቧንቧ ቆጠረብኝ አልኩህ እንዴ? ኣንሶላህን ለቅለቅ አድርግ እንጅ!
አሁን ይሄ አንሶላ ነው ወይስ መሀረብ? ኤድያ!
ከዛች ቀን በኃላ ናደው በማለዳ ተነስቶ አዲስ አልጋ ልብስ ገዝቶ መጣ ... ከሾላ ገበያ ገዝቷት የመጣውን አልጋ ልብስ ለግቢው ተከራይ ሁሉ እያዟዟረ አሳየን።
ሽንጉርጉር አንሶላውን ለሞራሉ ስንል አደነቅንለት ...
እኔ በተለይ ከሱሳ ሱስ አስተርፎ ባዘጋጃት ገንዘብ ይሄን በማድረጉ አሳዘነኝ።
ናደው ቀን ቀን ሰላማዊ ይሁን እንጅ ምሽት ላይ ፍፁም ሌላ ሰው ነው ። ጫቱን ቅሞ.. .አረቄውን መጦ.. .ሀሽሹን በልዞ ሲመጣ ያስፈራል።
ቀን ለሰላምታ መሬት ካላስኩኝ የሚለው ልጅ ምሽት ላይ ደረቱን ገልብጦ የሰማይ ከዋክብትን ልግመጥ ይላል ።
ብቻውን እያወራ ይንገዳገዳል.. .ትንሽ ራመድ...ራመድ ይልና የቤቱን ደረጃ በእንፉቅቁ ይወጣል ።
ለዛን ቀንም ... ለገዛት አንሶላ የፍንጥር ራሱን ሊጋብዝ ፀሀይ ከማዘቅዘቋ በፊት ሹልክ ብሎ ወጣ ።
ከሰዓታት በኋላ እንደልማዱ ደረቱን ገልብጦ መጣ...ደረጃውን በዳዴ ወጥቶ የጠባብ ክፍሉን ቁልፍ ከፈተ ።
ከበሩ በስተግራ ያለችውን ማብሪያ ማጥፊያ በመከራ ተጭኖ አንፖሉን ለኮሰ....
ቤቱ በብርሀን ተሞላች ።
በቅፅበት እሪታውን አቀለጠው ....
"ነብር ...ነብር ....ነብር አልጋዬ ላይ ኡ....ኡ....ኡ..... "
የግቢው ተከራይ ንቅል ብሎ ወጣ ። ይሁንና ከእትዬ በስተቀር የሱን ክፍል የተጠጋ ሰው የለም።
ናደው በተዓምር ይሁን በአስማት የግቢውን አጥር ዘሎ ወጣ ...
እኔ ክፍሌ ውስጥ ሆኜ ድምፄን አጠፋሁ ። ድካም ተጫጭኖኝ ስለነበር.. .ግርግሩን እየሰማሁ እንቅልፍ ይዞኝ እብስ አለ ። ማልዶ
"አሁኑኑ ቤቴን ለቀህ ውጣልኝ!" የሚለው የእትዬ ጩኸት እስኪያባንነኝ ድረስ የት እንዳለሁ አላውቅም።
"ሰውኮ ይሳሳታል እትዬ "
የቤቴን መስኮት ከፍቼ የሁለቱን ግብግብ አያለሁ ... እነ አስኩቲ ጥግ ላይ ሆነው አፋቸውን በመዳፋቸው ሸፍነው ይስቃሉ ።
ሰው ሊባረር ሲል እንዴት ደስ ይላቸዋል? የሚል ንዴት ውስጤን እያንገበገበኝ ነበር ።
እነሱም እኮ ተከራይ ናቸው!
ይሄ በእትዬ የተመዘዘ ሰይፍ ነገ እነርሱ ላይ እንደማያርፍ ምን ዋስትና አላቸው? እያልኩ ተብሰከሰኩ.. .
"ስማ ሚኪያስ !" አሉኝ እትዬ ወደ መስኮቴ ተጠግተው.. .
"ሰላም አይደለም እንዴ እትዬ?"
"ምን ሰላም አለ ? ይሄ ቀውስ ማታ የሰራውን አልሰማህም?"
"ኸረ እንደውም! " ... ካድኩኝ...
"ኸረ እንኳን ያልሰማህ። ይሄ ምናምኑን አጭሶ መጣና ቀን የገዛውን አልጋ ልብስ ዘንግቶት ..."
"አልጋ ልብሱን ረስቶ ምን?"
"አልጋ ልብሱ ላይ ያለውን የነብር ምስል አይቶ አልደነበረ መሰለህ?
አልጋዬ ላይ ነብር ብሎ አንባረቀ እኮ!
ደግሞ እንደ ጤነኛ ሰው አንገት ይሰብራል...አንገቱን ነበር መስበር።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael aschenaki
እንጃ
-----------------------------

ከአመታት በፊት የተለየሁት ባህር ማዶ ይኖር የነበር አንድ ወዳጄ ዘንድሮ አይጠገቡ መንግስት ባደረገለት ጥሪ መሰረት ወደ ሀገር ቤት እንደመጣ ስልኬን አፈላልጎ ደወለልኝ እና ከአመታት በፊት በጀማ ብዙ የሳቅ ድግሶችን ካ'ሳለፍንበት ሰሜን ሆቴል ተቀጣጥረን ተገናኘን።

በጣም ተራርቀን ነበር ምንም አይነት ሶሻል ሚዲያ ላይም አውርተን አናውቅም። ምሳችንን ካዘዝን በኋላ እንዴት ትዝ አልኩህ ግን? ስል ጨዋታ ማስጀመሪያ የሚመስል ጥያቄ ሰነዘርኩ እርሱም ከአፌ ቀበል አድርጎ "አይ ፀጊ አንቺ በቀላሉ የምትረሺ ሰው ነሽ? አልመች ብሎኝ እንጂ ብዙ ግዜ ነው ስልክሽን አፈላልጌ ላገኝሽ እፈልግ የነበረው" አለኝ።

እኔ በቀላሉ የማልረሳው ለምንድነው? ከአይን የራቀ እኮ ከልብ ይርቃል፤ እኔ አሁን በመራራቃችን ምክንያት እረስቼህ ነበር። የግዜ እና የቦታ መራራቅ አይደለም ጓደኝነትን ትዳርን ያረሳሳ የለ አልኩት። ጠፍቶ በመክረሙ ምንም ጥፋተኝነት እንዳይሰማው ለማድረግ በማሰብ። "የአንቺ ግን ሌላው ቢቀር ይሄ ግልፅነትሽ እና ተጫዋችነትሽ የሚረሳ አይደለም።" አለና ደመና ያጠላበት ፈገግታ አስፈገገኝ።

እንዲህ ስንጨዋወት ምሳችን መጣ ባርከን መብላት እንደጀመርን ትክ ብሎ አያየኝ "እኔ የምልሽ ፀጊ ቅዝቅዝ ብለሻል ተጫዋች ነበርሽ እኮ ወይስ የተራራቅን አይነት ስሜት ተሰማሽ?....ነው ወይስ ማደግ ቀልድ እና ሳቅሽን ቀማሽ?...."ሲል ፈገግ ብሎ ጠየቀኝ።
ባክህ እኔ ቀልድ አቁሜአለሁ፤ በዚህ የኑሮ ውድነት ብቀልድስ ማን ይስቅልኛል¿¡ አለኩት የተውኩትን ቀልድ ለማምጣት እየሞከርኩ። ሳቅ ቅርቡ የሆነው ወዳጄም ከትከት ብሎ ከሳቀ በኋላ ኮስተር ለማለት እየሞከረ "የምሬን ነው ፀጊ ምን ሆነሻል?..." አለኝ።

ምን መሰለህ ቀልድ (ቧልት) ከብዙ ሰው ጋር አቀያየመኝ። ቀልድ ለመፍጠር በማደርጋቸው ሙከራዎች ውስጥ ብዙ ቀን እንቅልፍ አልባ ሌሊት አሳለፍኩ፤
ለምን መሰለህ ብዙ ሀበሻ ተጫዋች ሰው ይወዳል ግን ተጫዋች ሰው አያከብርም።
ተጨዋቾች ከሆንክ ስሜት አልባ ያደርግሃል ኩፍስ ለሚለው ወይም ዝም ከሚለው ጓደኛህ ያነሰ ቦታ ይሰጥሃል።
በቤተሰብህ በብሄርህ በገዛ ፊትህ እና በኑሮህ ስታላግጥ አላማህ እሱን ማሳቅ ማጫወት እንደሆነ አይገባውም፤ ይደፍርሃል። በቀልዶችህ መሃል ማስተዋል፣ ማክበር፤ መውደድ የምትቀላቅል አይመስለውም።

በቀልዴ ምክንያት ቁምነገረኛነቴ፣ አንባቢነቴ እና ሰው አክባሪነቴ ሲፌዝበት ያስተዋልኩበት ግዜ ጥቂት የሚባል አይደለም። ማህበረሰባችን ብዙውን ግዜ ከሚጫወት አዋቂ ሰው ይልቅ ዝም ለሚል አላዋቂ ሰው የበለጠ ቦታ ይሰጣል።

ታዲያ ቧልተኝነቴ ካደፋፈረኝ፣ ካስተቸኝ፣ ካስገመገመኝ እና ካስናቀኝ ስራ አይደል አይከፈለኝ ፤ አያሾመኝ ብዬ በሂደት እርግፍ አርጌ ተውኩት! አልኩና የምፀት ሳቄን ፈገግሁ። በትኩረት ሲያዳምጠኝ ቆይቶ እንዲህ አለ "ባለማስተዋላችን ስንት ድምቀቶቻችንን ይሆን ያጣናቸው?!"

ለዚህ ጥያቄው መልሴ እንጃ ብቻ ነው።

እንጃ🤷‍♀
#በፀገነት

@wegoch
@wegoch
@mehalu_aynegerm
አስቱካ አስወጣችልኝ☺️

ይህ ማለዳ ፈገግታዬን ነጥቆኛል ቀኑ የእኔ እስካይመስለኝ ድረስ ገና በጠዋቱ ድብርት ተጫጭኖኝ ነበር ስታሽ አርፍጄ ቢሮ የገባሁት፤ እንደገባሁ ዲስክቶፔን አብርቼ ዩቲዩብ ዘንዳ ጎራ አልኩኝ እጄ ኪይቦርዱ ላይ አስቴር አወቀ "ናፍቆት" ብሎ ፃፈ አይምሮዬ እንዳላዘዘው ስለማውቅ ትንሽ ግርምት ብጤ ጫረብኝ ግን ያው መከረኛ ልቤ በል እንዳለው አላጣሁትም።

አስቱካም ያን መረዋ ድምጿን ታንቆረቁረው ገባች.......ግዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለሁ?
በሆነው ባልሆነው
እናፍቅሃለሁ😔
አሃ..... አልሁ አሁን ቢያንስ ለምን እንደደበረኝ እየገባኝ ነው። በውሃ ቀጠነ፤ አየር ወፈረ የሚናፍቀኝ ያው እሱው ነው፤ ሌላ ማን አለ?😒
አሱ መሆኑን ሳውቅ ደሞ የእሱን ነገር ማሰቤ አይቀር አይደል፤ የእሱን ነገር በአሰብኩ ቁጥር እንደሆነ ልክ እንደ በውቄ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ። ግን የአሁኑን ፈገግታዬን ድብርቴ ደመናማ ፈገግታ አደረገብኝ። ኤጭ!
"በሰጠሽኝ ፀጋ መጠን የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም፤
እኔ ባንቺ ትዝታ እንጂ በተራቢ ቀልድ አልስቅም።"
የሚለውን ስንኝ በውቄ ባይፅፈው ኖሮ እኔ እፅፈው እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ከስንኙ በላይ ደሞ ይህች ትህምክቴ ይበልጥ አስፈገገችኝ መሰል☺️

አይ እሱ..... አሁን ምን ልሁን ብሎ ነው የሚናፍቀኝ?🤔..... ቆይ ለምን አርፎ አይቀመጥም? ለምን አይተወኝም?😶
አሁን በስጨትጨት ማለትም ጀምሬአለሁ።

አስቴር ይህን የፍቅር ትንታግ ልታቀጣጥለው ታጥቃ የተነሳች ይመስል ቀጥላለች
"በል ይግረምህና
ዛሬም እወድሃለሁ
እንጀቴን አስሬ
ይሄው እኖራለሁ"...
አሁን የምር አናደደችኝ ሆሆ.. ይቺ ሴትዬ ደሞ ልታሳብደኝ ነው እንዴ?!😳 ለምንድነው እሱን የሚገርመው ? እራስሽ ይግረምሽ ዛሬማ አልወደውም እሺ! አልሁ ጮኽ ብዬ ሆሆ... ብቻዬን ማውራት ጀመርሁ።😞

ቀዝቀዝ ብላ ቀጠለች ደሞ አለሳልሳ ወደ ልቤ ልትሰርግ☹️
"ርቄ ሄጃለሁ ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ፍቅር....
እውነት ነው😩 አልሁ አሁን ደሞ ለራሴ ብቻ በሚሰማ ድምፅ። 'ርቄያለሁ፣ ሁሉን ርግፍ አድርጌ ትቻለሁ፤ በትዝታ ብቻ እንገበገባለሁ። ግን ለምን? ለምን እንደዚህ ልቀጣ? ምን አጠፋሁ? ምን በደልሁ?😟......ከነዛ ሁሉ የመለያየት ግዚያቶች በኋላም እንዲህ የሚያደርገኝ ፍቅርህ ምን ቢሆን ነው ይህን ያህል?😟....... አሁን ልክ እንደ ሀምሌ ሰማይ አይኔ እንባ ቋጥሯል።😟

"ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይከብዳል
እንደ'ግር እሳት
እንደ'ግር እሳት"....
አረ ተይ ግን አስቱካ ተይ አታቀጣጥዪኝ ተይ...☹️ መከረኛው አይኔ የቋጠረውን እንባ ማዝነብን ያዘው።😭 "አይኔ አበሳ አየ" አለች ያች ሙሾ አውራጅ..... እውነትም እነደ'ግር እሳት አልሁ ሲቃ በተናነቀው ድምፀት......

አስቱ ምን ተዳዋ ሳይወጣልኝ እንደው አትተወኝ....
"በልቤ ወድጄ
በአፌ የሚቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ".........
አሁን ዋሸሽ አስቱ ምንም እንኳን እስካሁን በልቤ ብወደውም፤ ትቼዋለሁ! በአፌም ብረግመው ነው እንጂ አላቀብጠውም፤ ችዬ ባልረግመውም ብቻ አላቀብጠውም። በቃ!😶 ደሞ አሁን እኔ ወዳጁ አይደለሁም፤ ወዳጅነት እንዴት ነው እንዴ?!!! እልህ የተቀላቀለበት ልቅሶና ማጉረምረም.....

"አይቻልም እና
ያንድ አንድ ሰው
ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስማሩት".....
ታሪኬንማ እንደዚህ አትገልብጪው እንጂ?☹️
እሱ እኮ ነው የፍቅር መምህሬ፤ ማለቴ የነበርው..... አሉሁና ስቅስቅ ማለት ጀመርሁ።.......

ታዲያ እሷ ምን ገዷት እኔ ብነፋረቅ ይባስ ብላ ደገመችዋ...
"ርቄ ሄጃለሁ ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር"......
የልቅሶ ሲቃ በተናነቀው ድምፄ አብሬአት ማንጎራጎር ገባሁ። በጉንጮቼ የሚወርደው የእንባ ጎርፍ ፤ ፊቴ ላይ ያሉ አካላቶቼን ይዟቸው እንዳይሄድ ሰጋሁ እና እንባዬን ለመገደብ ሞከርሁ።

"የልቤ ምሰሶ ዘንጉ ተሰበረ
የማይመነጠር ምሽግ የነበረ
ምሽግ የነበረ"......
ልቤ ፍስስ አለብኝ ምሰሶ ተሰብሮም የለ... አሁን ለመንሰቅሰቅ የሚሆን አቅምም ከዳኝ ትክዝ ቅዝዝ ብዬ የእባዬ ቋት ያጠራቀመውን የጨረሰ ይመስል አልፎ አልፎ የምትንጠባጠብ እንባዬን ማበስ ያዝሁ .......

"በፅኑ ትዝታ በራቀው መንገዴ
እስቲ ላሰላስልህ ደሞ እንደልማዴ"......
ልቤ ወዲየው ተነስቶ የኋሊት ጋለበና ወደ አብሮነታችን ግዜ ደረሰ። አሁን ትዝታዬ ፈገግታዬን ሊመልስልኝ ነው☺️.....

"ይኸው ልቤ ጥሎኝ ተነስቶ ሲሄድ
'ባንተ መወስወሱን አድርጎ ልማድ
አድርጎ ልማድ"......
የዘወትር ልማድ አደረገው እንጂ ስል ልቤ ከደረሰበት ትዝታ ፈገግ ሲሰኝ ተሰማኝና ወደ በውቄ ግጥም ተመለስሁ................
"የአሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ እንደ እንጎቻ የሚጥመኝ፥
የቧጨርሽኝ የነከሽኝ አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ፤
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ።"
ወደ ፈገግታዬ ተመለስሁ፤ ብርሃናማ ፈገግታ ፈግጌ😁 ቀኔን ከዚህ ጀመርሁ።

@wegoch
@wegoch
@mehalu_aynegerm
ታሪክሽን አይቀይረውም ትላላችሁ?!

ናይና በምትባል አንዲት ከተማ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋችንን ተዋህዶ በሚያስተምርበት ግዜ ከሰራቸው ብዙ የማዳን ተአምራቶች የመግደላዊት ማርያም በእኔ ልብ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዝብኛል። "እንዴት?"
እንዴት ማለት ጥሩ እርግጥ ነው በአብ ልጅ ክርስቶስ የማዳን ምስጢር እውሮች አይተዋል፣ አንካሶች ሄደዋል፣ ለምፃሞች ነፅተዋል፣ ደንቆሮዎች ሰምተዋል፣ ድውያኖች ተፈውሰዋል፣ ሙታኖችም ተነስተዋል።

ታዲያ የሀጢያተኝቷ መግደላዊት ማርያም ነፍሳዊ ፈውስ ለምን የበለጠብኝ ይመስላችኋል? መልሱ አጭር እና ግልፅ ነው። እውር ስላልሆንሁ የማየቴ ጉዳይ አያሳስበኝም፣ አንካሳ ስላልሆንኩም የመሄዴ ግዜ አይናፍቀኝም፣ ለምፃም ስላልሆንሁ መንፃቴ አይደገኝም፣ መስማቴም እንዳያስጨንቀኝ ደንቆሮ አይደለሁ፣ ድውይም አይደለሁ ፤ አልሞትሁ። ግን ሀጢያተኛ ነኝና ለመግደላዊት ማርያም የተደረገ ፈውስ እኔንም ይናፍቀኛል። ለመግደላዊት ማርያም የተደረገ ተአምር መዳን ብቻ አልነበረም ለትልቅ ክብር መጨትም(መመረጥም) እንጂ .... ወይ ጉድ ዘመኗን ሙሉ ሰባት አይነት ሀጢያት በመስራት ረክሳ የኖረች ሴት የትንሳኤው አብሳሪ ትሆናለች ብሎ ማን ይገምታል?! ማንም ! "ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንኸኝ" እንዲሉ ......

ዛሬ ዛሬ የሰዎችን ሀጢያት መበርበር እና ለሰዎች ሀጢያተኝነታቸውን ለማሳየት መፍጨርጨር መፅደቂያ መንገድ እስኪመስል ድረስ የአኗኗር ባህላችን ሆኗል። የክርስቶስ ቃልም ተዘንግቷል "የቱ?" ነው ያላችሁት? "እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?
ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ።
አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።" ማቴዎስ 7፥1-5 የሚለውን ነዋ። እውነት ግን እኛ ፃድቅ ሆነን ነው?! ሌባው፣ ሱሰኛው፣ አመንዝራው ና ግፈኛው ላይ ለመፍረድ አፋችንን አሹለን የተነሳነው?!....

ይገርማችኋል መግደላዊት ማርያም ይህ ቀረሽ የማትባል ልቅም ያለች ቆንጆ ስለነበረች ሰዎች ያደንቋት፤ ወንዶችም ይከተሏት ነበር። እዩልኝ እንግዲህ ከይሲ ዲያቢሎስ የተጠናወታት ለምን እንደሆን... በሰዎች ጦስ... በከንቱ መወድስ.. በአጉል ትዕቢት እንድትሞላ አደረጓት ከዚያ ሰባት አጋንንት ሰፈሩባትና ሰባት አይነት ሀጢያቶችን በመስራት ዘመኗን ፀንታ እንድትኖር ሆነች። ግን ማርያም መግደላዊት ሁልግዜም መዳንን ትሻ ነበር፣ ውስጧ ሁሌም ያለቅስ ነበር፣ በኢየሱስ እግሮች ላይ ያዘነበችው እንባ ዝም ብላ የዛን ቀን ያማጠችው አይደለም፤ በዘመናት የፈውስ ጥማቷ የተጠራቀመ እንጂ።

ስንቶቻችን ነን አውደምህረት ስር እየተወሸቅን ሀጢያታችንን በነጠላችን ልንሸፍን የምንሞክር?
ስንቶቻችንስ እንሆን በተጠና የአኗኗር ስልታችን በሰወች ፊት ፃድቅ ለመሆን "እኔ እኮ እንዲህ ነኝ" በሚል ዲስኩራችን ስንደነቋቆር የምንኖረው?
አይ ሞኝነት ፅድቅ እንደሆን በእግዚአብሔር የምትፈተሽ ረቂቅ ምስጢር ነች እንጂ እኛ በምንፈልመው ፊልም መች ሆነ ብለን ነው☹️☹️
እግዚአብሔር ደሞ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው።

ስንቶችስ ይሆኑ ለኛ ሀጢያታቸውን ብቻ እያሳዩ ልባቸው የእግዚአብሔር ማዳን በመሻት ታማ በመአልት እና በሌት ምህረትን በመሻት አይናቸው እዥ እስኪያነባ የሚያለቅሱት?!

በዛን ዕለት ኢየሱስ ክርሰቶስ ወደ ፈሪሳዊው ቤት የገባው በፈሪሳዊው ግብዣ ነበር። ያን ፈሪሳዊ ልብ ብላችሁ ካያችሁት እኛል ይመስላል። እሱ የፈለገው ምህረትን አልነበረም፤ ምህረትን መፈለግማ ሀጢያተኛ ነኝ ብሎ ማሰብን ይጠይቃላ። የፈሪሳዊው ፍላጎት ከክርስቶስ እኩል በአንድ ማዕድ መብላት ብቻ ነበር። መግደላዊት ማርያም ግን ክርስቶስ በዛ እንዳለ ባወቀች ግዜ የመዳን ፍላጎቷ ንሮ ወጣ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ይሆናት ዘንድ የአልባስጥሮስ ሽቱ አመጣችለት። ክብሩን ለመግለፅም እግሮቹን በእባዋ አርሳ አጥባ በጠጉሯ ጠረገቻቸው፤ የአድነኝ ተማፅኖዋንም ቃል ሳታወጣ እግሮቹን በመሳም አቀረበች። ፈሪሳዊውም ይህን ሲያይ የክርስቶስን የማዳን ሀይል ባላመነ ልቦናው "ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ አሰበ።”
የልብን የሚያውቅ ኢየሱስም የስምዖንን ሀሳብ ስላወለቀት "እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።”
ብሎ በቸርነቱ ከእራስ ጠጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን ሰባት የአጋንንት ነገድ አስወጣላት።
እንዲህ ነበር ያላት "ሀጢያትሽ ተሰርዮልሻል፤ እምነትሽ አድኖሻልና በሰላም ሂጂ!" ኡህህህ እንዴት የሚያረካ ቃል ነው። አያችሁ ግን ሰው ከግብሩ ይልቅ በእምነቱ ሲድን.....። እኛ ምናምኒት እምነት የሌለንስ ምን ይውጠን ይሆን?!🤔 ማመን ያቃተን ግን የዋሃዎች ስላልሆንን እኮ ነው። እምነት ማደሪያዋ የዋህ ልብም አይደል....።

ታዲያ የመግደላዊት ማርያም ታሪክ መች እዚህ አበቃና፤ እንደውም ከዚህ ጀመረ እንጂ። ጌታ ፈውሶ ብቻ አልተዋትም። እንደምን ይተዋት? እምነቷ ፅኑ ነው! ከሀጢያት ሸክሟ ነፃ ካወጣት በኋላ ከ36ቱ ቅዱሳት እንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት። ማርያም መግደላዊትም ከዚያን ዕለት ጀምሮ ፍፁም ተቀየረች። ጌታን እስከ እለተ ህማሙ ድረስ በሌሊትም በመአልትም በቅንነት አገለገለችው። ጌታችን ስለኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምራ እስከ ማታ ከጎኑ ነበረች፤ ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች። በእግረ መስቀሉ ስር ተደፍተው ሲያለቅሱ ከነበሩ እንስቶችም አንዷ እሷ ነበረች። አቤቱ ምህረትህ የጎበኘውን ምንኛ ባረከው...!

የማርያም መግደላዊት ሐዋርያዊትነት መች በዚህ ያበቃና...... እሁድ ሌሊት ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ፤ ሽቱም ልትቀባ ወደ ጎለጎታ ገሰገሰች። ፍፁም የአምላክ ፍቅር በልቧ ሰርጿልና የሌሊቱ ግርማም ሆነ የአይሁድ ጭፍሮች አላስፈሯትም። ጌታችንም ከፍጥረት ወገን የመጀመሪያ ትንሳኤውን ያየች ትሆን ዘንድ አደላት። አቤት መባረክ!
የዛን እለትም በመቃብሩ ራስጌ እና ግርጌ ገብርኤል እና ሚካኤልን ቆመው አየቻቸው፤ ዘወር ስትል ደሞ የክብር ባለቤት የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አየችው። አላወቀችውምና በእናቱ ስም "ማርያም" አላት "ረብኒ(መምህር ሆይ)" ብላ ሰገደችለት። ጌታም "ሄደሽ ለደቀመዛሙርቴ ንገሪያቸው" ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት። አቤት የፀጋዋ ብዛቱ...... ሰው የተጠየፈውን እግዚአብሔር ምንኛ ወደደው!......

እናንት በሀጢያቴ የምትጠቋቆሙ፣ ገዝፈው በሚታዩአችሁ የእኔ ሀጢያቶች ውስጥ አንሰው የሚታዩአችሁን የራሳችሁን ሀጢያቶች እያተናነሳችሁ የምትኖሩ እናንተ፣ እናንት እግዚአብሔር ቤት መሄዴ የማይዋጥላችሁ አጉል ዶጋ አዋቂ ነን ባዮች፣ የልቤን ሳታውቁ በግብሬ የምትፈርዱብኝ እናንተ ፤ እናንት ሁሌም ከአይኔ ጉድፍ ልታወጡ የምትጥሩ አጥርታችሁ ማየት ያልቻላችሁ በሙሉ..... የማርያም መግደላዊትን ታሪክ የቀየረ ጌታ የሰናፍጭ ታክል እምነት በልቤ ያቆጠቆጠች ቀን የማይምረኝ ነው የሚመስላችሁ?።

በሏ..! ..ታሪክሽን አይቀይረውም ትላላችሁ?!
ድሮ አምስተኛ ክፍል ሳለን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ሁለት ዲያቆናት ነበሩ። ከአብነት ትምህርት የጀመረ ፉክክራቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርቱም አምጥተውት ነበር። በተለይ የሽምደዳ ትምህርቶችን የሚችላቸው አልነበረም። ልጅ እያሱ የት ተወልዶ.. .የት እንደሞተ ከነቦታው ከነ ዓመተ ምህረቱ ዱቅ ያደርጉታል። (በነገራችን ላይ አንድ ቀን ልጅ እያሱ ሀይቅ ዳር ተቀምጠው ሲፍታቱ መኮንኖች ከሩቅ ሾፏቸው ። ያን ጊዜ ልጅ እያሱ በርጫ እያደቀቁ ብን ብለው በምርቃና ፏ ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ቤተ መንግስት አካባቢ ልጅ እያሱ የእስላም ቅጠል ያላምጣሉ ተብሎ እንደተወራባቸው ታሪክ ይናገራል 😂 ልጅ እያሱ አንቱ ለመባል የማያበቃ ልጅነት ነበራቸው። ሀገራችን በዘመኗ ካጋጠሟት የህፃን ባህሪ ካላቸው ንጉሶች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ። በተለይ ጢዝ ያላት እንስት ካዩ ቅቤ እንደላሰ እባብ ይቅበዘበዛሉ ይባላል ። ብዙው የንግስና ዘመናቸው ላይ ሲወሸክቱ ራስ ተፈሪ በርቀት ይጠባበቋቸው ነበር። ራስ ተፈሪ ቤተስኪያን ተመሳም አንስቶ በቤተ መንግስት ዘንድ እጅግ የተወደደ ምግባር ነበራቸው። በንግስና ዘመናቸውም ትንሽ እንኳ ሳት ብሏቸው ከማጀት ሴቶች አንዷን ቢመቻቹ ለፀፀት ቅርብ ናቸው። ከአልጋ ወርደው ደበሎ አንጥፈው ጌታ ሆይ አፉ በለኝ ይላሉ በፍጥነት። ልጅ እያሱ ግን አንዷን ቆንጆ እየቀመሱ የሌላዋ እንስት ገላ ያሻፍዳቸው ነበር )

ወደ ዲያቆናቱ ልመለስ.. .

እንዳለ ተብየው አንዲት ሸጋ ወዶ ጠየቀ። መጀመሪያ ይሄ የማርተሬዛ ሽልንግ የሚደብቅ ተረከዝህን አለስልስ ብላ ኩም አደረገችው ቆንጆዋ!

እንዳለ ከዚህ የሞራል ስብራት በኋላ ሰይጣን በጆሮው አንድ በቀል ሹክ አለው።

ጱጵ የሚል ድምፅ ከጎናችን ሰማን ። ደግሞ ለክፋቱ እኔ ከቆንጆዋ ልጅ ጎን ነው የተቀመጥኩት። ቆንጆ ይፈሳል ተብሎ ስለማይገመት ተሜው ሁላ አይኑን አጉረጠረጠብኝ። አፍንጫዬን በሹራቤ ስሸፍን ደግሞ ከሱ ብሶ ፈስ እንደሸተተው ሰው አፍንጫውን በጨርቅ ይሸፍናል እንዴ? ተባልኩ...ከ አምስት ደቂቃ ለጥቆ ቆንጆዋ ልጅ ሌላ ጋዝ ለቀቀች። ከመቅፅበት ደንግጣ ክፍሉን ለቃ ሮጠች። ዞር ስል ደብተራው እንዳለ ሆዱን እስኪቆርጠው ድረስ ይስቃል።

የፈስ ድግምት ለቆባት መሆኑ ያኔ ገባኝ :)

በዚህ እውቀቱ የቀናው ደብተራው ሸዋ ሌላ ጉድ ይዞ ከተፍ አለ ። 

የበቀል በትሩ አንዲት ምስኪን መምህራችን ላይ አረፈ ። ቲቸር አስካል መክራን ዘክራን አልሰማ ስላልናት ብዙ ጊዜ በአርጩሜ መከራችንን ታበላናለች። ተማሪው ግርፊያዋን ስለሚጠላ እሷንም አብሮ አይወዳትም ነበር። በተለይ ሸዋ ... የክፍል መልመጃ 3/10 ስላመጣ ክፉኛ ጥርስ ነክሶባት ነበር ። የታሪክ ትምህርትን እንደ ውሀ የሚጠጣው ጎበዝ ተማሪ የሂሳብ ትምህርት ግን አናቱን እንደ ሀበሻ አረቄ ይነካዋል። 

በተለይ ማካፈል የሚባል ስሌት በቀን ሶስት ጊዜ አስረድተውት በቀን አስራ ሶስት ጊዜ ይስታል 😑

አሁን በምን ተዓምር ነው 19 /12.... 21 የሚመጣው ። መምህራችን በአዕምሮህ ነው ወይስ በእግርህ አውራ ጣት አስበህ ነው ይሄንን ውጤት ያመጣኸው ብላ ስትጣይቀው.. ." በ 16 ኪዳነምህረት ነች ። በ12 ሚካኤል ነው። እመቤቴንስ እንዴት ረሳታለሁ?" አለ አሉ 😑
በዚህ ጥርስ የነከሰው ሸዋ ዛዲያ አንድ ከሰዓት ላይ አደናግር ድግምቱን አነብንቦ ክፍል ውስጥ እንትፍ እንትፍ አለ።

ቲቸር አስካልዬ እጇ ቄጠማ ሆነባት። እግሯ እንደ ህልም ሩጫ አልታዘዝ አላት።  ጠመኔው ተሰሌዳው እንዴት ታዋህደው?

አይነ አፋር ነች አይነ አፋርነቷ ጎልቶ አንገቷን ደፋች ።

ደግሞ ለዛን ቀን ያለወትሮዋ እንኳን ሂሳብ ዓ ነገር መፃፍ አትችሉም ብላ አማርኛም እያስተማረችን ነበር።

አማርኛ ብላ ለመፃፍ አገርኛ ብላ ስትፅፍ ሳቅንባት ። የግንባሯ ላቦት ተንዠቀዠቀ ። መልሳ መልመጃ ን ለመፃፍ መግለጫ ብላው አረፈች። ከተማሪው ሁሉ የሸዋ ሳቅ ጎልቶ ተሰማ ።

መጨረሻ ላይ የሰራችው ስህተት ሲታከል ደግሞ ክፍሉ በሙሉ እንደ አደዋ ማስጀመርያ መድፍ አጓራ!

አንብቡ አለችን ዓ ነገር ጥፋ.. .

ምድረ ውሪ ተሰሌዳው የጣፈችውን ጥሁፍ እኩል አነበበው።

"አበበ በሶ በዳ !"😆

ድንጋጤ ጨው አደረጋት ። የፃፈችውን ዞራ አነበችው ።

ቂ....ቂ...ቂ ...ቂ...ቋቂ

ሸዋንም ሳቁንም እኩል ጠላኋቸው :)

ሚካኤል .አ 

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
#ጦቢያ

#ዝክረ_አድዋ ልዩ ፌስቲቫል አድዋን በጦቢያ መድረክ ያድምቁ

በነፃ ሀሳብና በሰከነ መንፈስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እናድምቅ!

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የቡና ባንክ ቅርንጫፎች ይገኛል።

የመግቢያ ዋጋ 200ብር
ለበለጠ መረጃ 0919787878

በነገራችን ላይ እኔም ስራዎቼን ይዤ እኖራለው🥰
አያቴ ረጅም ናት : ድሮ ያኔ ትንሽ ልጅ ( ትንሽ ልጅ ሆኘ አውቅ ነበር ?)
እና ያኔ እንግዲህ አጠገብዋ ቆሜ: ቀና ካልኩ : ሽንሽን ቀሚስዋን ገፋ ያደረገ ሆድዋ:
ከወገብዋ በላይ እንዳላይ እየጋረደኝ አንገቴን ወደ ላይ ሰቅየ : አገጨን ወደ ሰማይ አሹየ :
ሳይት : ሳያት አታልቅም ።
ጥቂት እራቅ እልና : እዚያ እ- ላ--ይ የደረሰ አንገትዋን አሻግሬ ፊትዋን እመለከታለሁ ።
ደርባባ ወይዘሮ ናት ። ቀሚስዋ እስከቁጭምጭሚትዋ ይደርሳል ።
አያቴ ?!
አቤት
ቀሚስሽ ለምን መሬት ይደርሳል ?
ረዝሞ ነዋ የኔ ልጅ ።
ታዲያ ለምን ረዘመ : እም ለምን እንኳን አታሳጥሪውም?
ካጠረ ነፋስ እንዳይገልጠኝ ብየ ነዋ ልጄ ።
ነፋስ ቢገልጠው ምን ይሆናል?
እህ! እንዲህ ናትና የዳውዶ መሃመድ ልጅ !
ሴት ልጅ: ንፋስ ቀሚሷን ገልጦባት :
ጭኗን ለመንገደኛ: ከሚያስጎበኝባት
ካፍንጫዋ ሥር : ንፍጧ ቢታይ ይሻላታል ።
አያቴ ምን ነው ያልሽው ?
ወዲህ ነው ልጄ
ወዲህ ? ወዴት ? ምኑ ?
ተይው ልጄ
ምኑን ነው ምተወው አያቴ ?
እርቦሻል እንዴ የኔ ልጅ ? ትላለች በሃዘኔታ
እምምም--- እርቦኛል እንዳልል አልራበኝም : አልራበኝም እንዳልል ደግሞ : ጓዳ ውስጥ
ያለ ወይ ቋንጣ ፣ ካልያም አይብ ፣ ወይ ቃተኛ ፣ ጭኮ ብቻ የሆነ ጎትታ የምታመጣቸው
ድብቅ ጣፋቅ ስንቆች አንዱ: እንዲያመልጠኝ አልፉልግም ።
"አልራበኝም ግን እበላለሁ ።" እላታለሁ ።
አዎ ልጄ: ልጅ ሆዴን አመመኝ እንጂ' ጠገብኩ ' አይልም ።--- እያለች ጓዳ ውስጥ ገብታ :
ከሆነ ቦታ የሆነ ነገር አንጎዳጉዳ: በትላልቅ መዳፎችዋ እና በእረጃጅም ጣቶችዋ የታፈሰ:
አንድ ሠሃን የሚሆን ቆሎ ይዛ :
'ዘርጊ እጅሽን ":- ትለኛለች ።
ዝርግት -
ውውውይ --- ትላለች አጫጭር ጣቶቼን ትንሽየ መዳፌን አይታ
"በቃ በቀሚስሽ ያዥው ። "
ቀሚሴን ከፊት በኩል እስከ ላይ ድርስ ስጎትት ---
"" አይ አይ ምነው--- " ብላ ሳጥኑን ታያለች ።
ከሳጥኑ ውስጥ ሰሃን አውጪ ልትል ፈልጋ ግን አንደበትዋ ተያዘ ።አላመነችኝም ። ሠሃን
ሲሰበር አትወድም የብረት ሰሃንዎችዋን መስጠት አትወድም ።
በይ በቀሚሽ ያዥዋ እንግዲህ። ትለኛለች።
እንደገና ቀሚሴን ከፊት በኩል ይዤ ወደ ላይ በሁለት እጄ አጥፍና : በቀሚሴ ጨርቅ :
ዘምቢል መሳይ የጨርቅ ጉድጓድ እሰራለሁ።
የተገለጡት ጉልበቶቼ እየታዩ : ቆሎውን እቀበላታለሁ ።
በማር የታሸ ሠነፍ ቆሎ ነው ቁርጥም አርጊያት እስኪ --- ትላለች።
አያቴ ቆሎው ግን ለምን ሰነፈ ?
ምንማለትሽ ነው ልጄ ?
ቆሎው ለምን ጎበዝ አይሆንም ነበር?
እርቦሻል እንዴ ልጄ ?
ሌላ ምን ልትሰጠኝ ይሆን እያልኩ
"አልራበኝም ግን እበላለሁ" አልኩ ።
እርቦሻል የኔ ልጅ : ሰው ሲርበው ነው ጥያቄ የሚያበዛው ።
ትለኛለች ።
የተገለጡ ጭኖቼ ሳያሳስቡኝ ቆሎየን ከነጨርቄ በአንድ እጄ ጨብጨ በሌላኛው እጄ:
ለጊዜው ኪስ ሆኖ በሚያገለግለው : ቆሎ ባዘለው የፊት ለፊት ቀሚሴ ጨርቅ ውስጥ
ያለውን ቆሎ እየዝገንኩ ፣ እየቆረጠምኩ ሌላ የጓዳ ሲሳይ እጠብቃለሁ ።
ግን በምን እይዘዋለሁ ? አያቴ ግን ለምን ሰሃን እትሰጠኝም ?
አያቴ
አቤት
ጭኔ እኮ ግን እየታየ ነው ። አልኩ በማስተዛዘን
አያቴ ጓዳ ውስጥ ሆና --- በረጅሙ ትመልሳለች
እህም- ይታያ :- የታየ እንደሆን ምን እንዳይሆን ? !

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Abeba Birhanu
ስለተለየኝ ራሴን የጣልኩ ይመስላቸዋል። ስልኩን ስለማያነሳልኝ ዱካክ እየበላ የሚያሰቃየኝ ነው የሚመስላቸው። አልፈልግሽም ማለቱ ብቻ የመቆም ድፍረቴን የናጠው ነው የሚመስላቸው።
ግን አይደለም !ሁሉን ነገር ተራ ማድረጉ አስደንግጦኝ ነው! አብረን ሳለን ያልወጣንበት የሃሳብ መስመር ፤ያልተንሸራሸርንበት ስፍራ ፤ያላሰስነው ቤርጎ ፤ ያልነገሩኩት ገመና አልነበረም ። ያልሆነው አለመሆን ብቻ ነበር !! በየደቂቃው ከጭንቅላቴ የሚፈልቀውን ዝባዝንኬ ሳላስቀር፤ ባጠገቤ ውል ያለውን ሳይቀር
ነበር የምተነፍሰው። እንዳልቆም አድርጎ ያፍረከረከኝ ፤ ያሳለፍነውን ያገዘፍኩትን ነገር አንድ ሳይቀር ነው አሳንሷት የሄደው። ትረካ የሌለው መለያየት ፤ ውጣ ውረድ የሌለው ፍቺ ፤ የማይተነፈስ ህመም ለማይታይ ጠባሳ ይዳርጋል! እንዴት በዚህ መጠን ተራ ይሆናል ፤ እንዴት እየተፍለቀለቅኩ የምተርከውን ትዝታዬን
እንደዚህ ያባክነዋል። እንዴት ጥሩ ምክንያት አይፈበርክም? አንዴት አካሄዱን ወዝ አያላብሰውም? በዚህ መጠን ተራ አድርጎኝ እንዴት ይሄዳል? እችን ብቻ ነበር የምናክለው ?
አብረን ስንሆን የኔ ነው ብዬ አይደል እርቃኔን የተንጎማለልኩት ? የነበረን ነገር ገብዶብኝ
አይደለ ድክመት እና ስጋቴን መግለጤ?ያሳለፍነውን ውብ ጊዜያት ካለጥንቃቄ በአካሄዱ ተረማምዶበት ነው ያናወዘኝ። እንጂማ መለያየት ተፈጥሮም አይደል ነፍስ ከስጋስ ይለይ የለ ?
መሄዱ አይደለም አካሄዱ ነው መላቅጡ የጠፋ ዱካክ ውስጥ የዶለኝ። አወዳደቃችን ውስጥ የጣያችን ግዝፈት እና ተራነት አሻራ በጉልህ አለ ። ምን አለ አለሳልሶ ቢጥለኝ ፤ ምን አለ ሲተወኝ ይሉኝታ ቢስ ባይሆን ። አብረን በነበረን ጊዜ እንደምወደው እያንዳንዱ ዳናዬ ምስክር ነበር ።
ሰው ለሚወደው አይደለም ላሸነፈው ጠላቱ እንኳ ይራራ የለ? ምን አልባት እኮ የእኔ ብቻዬን የመሆን ፍርሃት ሲያርደኝ መለማመጤን አይቶ ነው ለእኔ
ያለው ስሜቱ የተከለለበት። ምን አልባት ከእኔ የተሻለ ሰው አግኝቶ በእጁ እስኪያረጋት ወረት አውሮት ነው። ምን አልባት እንዲ መሙለጭለጭ ማንነቱ ይሆን ይሆናል። መሄዱ አይደለም ያጎሳቆለኝ ይሄ ማለቂያ የሌለው የምንአልባት ጉዞ ነው ከሰውነት ተራ ያወጣኝ፤ ምንአልባት ቃል ገድፌ የማይወደውን ብዬ ፤ ወይ ምን አልባት ያልዋልኩበትን ነግረውት ይሆን? ወይ የሆንኩትን አገዛዝፈው አሻክረውት ይሆን? ይሄ እና ሌሎች የምን አልባት መላምቴ ነው ጭንቅላቴን ያጣበበው። እንዲህ እንደባተልኩ አልቀርም እረሳሃለሁ ፤ ያኔ እዚህ የዘራሃውን እዛ ስታጭድ መሰስ እያልክ ትመጣለህ ፤ ያኔ የእኔን የምንአልባት የመላምት ችንካርን ትቀምሰዋለህ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
"ስማ.. .ስማ.. .!"
ዞር አልኩኝ። ለ ሰባት ዓመታት በግዳጅ የቆየ ወታደሩ የሰፈሬ ልጅ ነው ። አጎንብሶ ስለነበር አይቼው ልደበቅ አልቻልኩም ። ኩሪ ሰፈራችን መሀንዲስ ውስጥ ከገባበት ቀን ጀምሮ ትዕቢተኛ ውሪዎችን አደብ ስላሲያዘልን እወደዋለሁ። ገና መቀመጫቸውን በቅጡ ሳይጠርጉ ቺክ ለመጥበስ ተፍ ተፍ የሚሉ...ሞተር ሲነዱ ቆሌያችንን የሚገፉ ታደጊዎችን የእጃቸውን ይሰጥልናል።
እሱ እጅ የገባ ፍንዳታ ታዳጊ በጠረባ አየር ላይ ደንሶ ይመለሳል።
ይሁንና በዚህ ተግባሩ ብወደውም ብዙ ጊዜ ብር ስለሚለምነኝ ግን በሩቅ ሳየው ገና እደበቅበት ነበር። ለሶስት ጊዜ ያህል ገንዘብ ጠይቆኝ በአሉታ ስለመለስኩለት ቂም ቆርጭሞብኛል።
ሰሜን እዝ ውስጥ ዓመታትን አስቆጥሯል። ብልግና.. .ማነው ይቅርታ ብልፅግና መንግስት ኢትዮጵያንና ኤርትራን ሲያዋህድ የተፈጠረውን ነገር ያጫወተኝ ቅፅበት አትረሳኝም።
የደስ ደስ ተብሎ ወታደሩ በገፍ ቢራ ቀርቦለት ተፍታታ...የኢትዮ ወታደር ወደ ውሀው ጠንከር ይላልና የቢራ ጠርሙሶችን እንደ ቁልፍ አቅጨለጨላቸው።
የኤርትራ ወታደር ሁለት ቢራ ልፈው ፀጥ እረጭ ሆነ ነገሩ...
የወገን ጦር "እነዚህ ሰዎች ተታርቀንም ሌላ ጉድ ሊያመጡ ነው እንዴ?" ብለው ተጠራጠሩና "ጠጡ እንጅ " አሏቸው በግብዣ መልክ ...
የኤርትራ ወታደሮች ይሄን ጊዜ ነው ...
"ኢትዮጵያ ውስጥ ከሁለት በላይ መጠጣት ይቻላል ወይ ?🤔" ብለው የተገረሙት ።
ኤርትራ ሁለት መሎቲህን ልፈህ ሌላ ቢራ ሊጨምር ካልክ የኢሳያስ መንግስት ጉድጓድ ይጨምርሀል ።
ኤርትራ በመዓቀብ ብዛት ከዘመነኛ ስልጣኔ በትንሹም ቢሆን ተኳርፋለች።
እንደውም ሀሜት አይሁንብኝና የ ATM ማሽን ሲያዩ ብርቅ ሆኖባቸው ሰልፊ የተነሱም ጓዶች አሉ ተብሎ ይወራል 🙄
እዚህ ሸገር ቤተልና 22 የሚገኙ ኤርትራውያን ተዝናኖትን የማይጠግቡበት ምክንያት ይሄ ነው።
አንድ የኤርትራ ወጣት ጀማ ሺሻ ሲነፋ ካያችሁ ጎጆ ቤት የተቃጠለ ሊመስላችሁ ይችላል ።
ደግሞ ጨላ በሽ አላቸው... አሸን ዲያስፖራ በሚልክላቸው ብር ውስኪ ውስጥ ዋኝተን ዛሬውኑ ሻርክ ካልሆንን ይላሉ ። ሀያ ሁለት ሰፈር ኤርትራውያን ሲገቡ ቤት ኪራይ ደመና ልሶ ይመለሳል። የክብሪት ቀፎ የምታክል ክፍል ስድስት ሺህ ብር ለመከራየት እጃቸውን ወደ ኪሳቸው ቀለል አድርገው ነው የሚጨምሩት ።
"ወዬ"
"ወደየት እየሄድክ ነው?"
"ቢሮ "
ፈገግ አለ ...
"ይሄ ኮብልስቶን እንዲህ ፈራርሶ ስታይ ምንም አይሰማህም ? ካሁን በኅላ መኪና በዚህ እንዳያልፍ ድንጋይ እንደርድር "
ትዕዛዙ እንደ ሞዴሊስት ወገብ ቀጠን ያለች ነች። ታናሼ ነው... ታናሼ ነው ብዬ ትዕዛዙን አልንቅ ነገር በዚህ የጅብ ግራ እግር በሚያህል ክንዱ ያደባየኛል 😑
ሸሚዜን ሰብስቤ ድንጋይ መደርደር ጀመርኩ ... ከደቂቃዎች በኋላ ሰዓት እንደረፈደብኝ በምልክት ሳሳየው የፊቱን ሌላ መልክ ገልብጦ አሳየኝ።
እግዚኦ ማስፈራቱ !
ድንጋይ ማጋዜን ቀጠልኩ ። ከሰዓታት በኋላ ቢሮ የደረስኩት ወፍጮ ቤት የተቀጠረ ፈጪታ መስዬ ነበር ።
እንደውም ፊትለፊት የምትቀመጠው ፀሀፊያችን አቧራዬን አይታ "ሳላስብ ፀልዬ የሚለው የያሬድ ነጉ ቀረፃ ላይ ነበርክ እንዴ? የዱባይ አሸዋ መስለካል" ብላ ተላላጠችብኝ።😐
ኩሪ ሰፈር ውስጥ ስለሚውል እንከን ማውጣት አይታክተውም...እኔ ወራትን የተመላለስኩበት መንገድ ኮብልስቶን መንገድ እንደሆነ እንኳ ልብ ያልኩት "የኮብልስቶኑ መፍረስ አይታይህም ወይ?" ብሎ ሲያንባርቅብኝ ነው።
በዛ ላይ ሰፈር ውስጥ ያለ ለቅሶና ሰርግ ላይ በማገልገል ማንም አይደርስበትም...ድንኳኑን ብቻዬን ካልተከልኩት ነው የሚለው !
በየቀኑ ሰፈር በመጣሁ ቁጥር አዳዲስ ነገሮች ይገጥሙኛል ።
ችጋር ያራቆታቸው ደራቃ ተክሎች ሁሉ ውሀ ጠገቡ... ጭራሽ የሰፈራችን ውሪዎች ጋሽ አበራ ሞላ ሆኑብን...መንደሩ እንደመስታወት ያንፀባርቃል።
...
ዛድያ እኔም አመሻሽ ላይ ድንጋይ ሸከማውና የቢሮው ስራ የመጠጠው ጉልበቴን ለማሳረፍ ወደ ቤቴ ከነፍኩ ።
ሆኖም ቀዬ ስደርስ እነዛ ነገረኛ ሽማግሌ ሌባ ጣታቸውን ጠቆሙብኝ። ሰፈሩ በፖሊስና ደንቦች ተወሯል። CCTV ካሜራ ሆነው ወሬ የማያመልጣቸው ባልቴቶች ወገባቸውን ይዘው "ቀ" ፊደልን መስለዋል።
አንድ ብጉራም ፖሊስ ዱላውን አንጠልጥሎ ወደኔ ተንደረደረ ...
"ምንድነው?"
አንዴ ወገቤን ነርቶ አንቆራጠጠኝ ።
"እንዴ በህግ አምላክ !"
"እናንተም ህግ ታውቃላችሁ እንዴ? እስክንድር ነጋ መንገድ እንድዘጉ ያሰማራህ ፋኖ እንደሆንክ ደርሼበታለሁ "
በድንጋጤ አይኖቼ ፈጠጡ ...
ኩሪ ደረቱን ነፍቶ ከፖሊሶቹ ጋር ተጠጋኝ ።
" ስማ መንግስት በአንካሴ የሚሄድ አካል ጉዳተኛ መሰለህ እንዴ? መንገድ በድንጋይ በመዝጋት የሚወርድ መንግስት የለም እሺ?"
ይሄን የሚያወራው ጠዋት ድንጋይ እንደርድር ብሎ ያዘዘኝ ኩሪ መሆኑን በመጠራጠር አይኖቼ ደጋግሜ አሻሸኋቸው 🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael aschenaki
ነግሬህ ነበር እኮ "አንተን ሳስብ ፈገግ ማለት እፈልጋለው እባክህ ሳቄን አትቀማኝ" ብዬ። አልገባውህም ወይም እኔን መረዳት አትፈልግም ነበር፤ ሁሌም እንደምትለው "አታወሳስቢብኝ" አልክና ምንም ያላልኩህ ያህል እረሳህው፤ እኔ ግን አንተ ጋር ዋጋ ማጣቴ ላይረሳኝ ከልቤ ታተመ።
እያወሳሰብኩ አልነበረም ሁሌም ለኔ ያለህን መልካምነት ፍቅርህን ለመፃፍ ብዕሬን ሳነሳ በተለመደው ግዴለሽነትህ ታንሻፍፍብኛለህ ፤እናም የማልፈልጋቸውን መስመሮች አሰፈርክበት። አላወከውም ልስለው የነበረ ድምቀትህን እንዳደበዘዝከው፤ የትዕግስቴ ፅዋ መጉድሉን አላስተዋልኩም ነበር።
ጥሬአለው፤ ስላንተ እንዳይደክመኝ ራሴን ሳበረታ ነበር ደጋግመህ እየወደክ አዛልክኝ እንጂ። ልቤን በእጆቼ ለመሸፈን ብሞክርም የምትሸረሽረውን ፍቅርህን ማስቆም አቃተኝ።
እባክህ ይቅርታ አትበለኝ፤ ስለረሳሁህ ይመስልሀል የተለየውህ? "ያለኔ መኖር ቻልሽበት አይደል" ትለኛለህ፤ ችዬ አይደለም መቻሉን ስጠኝ ብዬ እንጂ።
መሸምደድ በቀረው የንባብ ልክ የፃፍክልኝን መልዕክት ዛሬም እንደማነበው ማን በነገረህ። ይግረምህና ደጋግሜ ከማየቴ የተነሳ ተሰጥኦ ቢኖረኝ ፎቶህን ሁላ እስለው ነበር።

ቁምነገሩ ምን መሰለህ ከኔ ጋር ትሆን ይሆናል አብረህኝ መሆን እንደማትችል ግን አውቀዋለው። እንደምታፈቅረኝ ትነግረኝ ይሆናል እንዲሰማኝ ማድርግ ግን አትችልም ። አንተ እንዲህ ነህ ላይ ላዩን እንጂ ጠልቆ መኖር አታውቅበትም። ወደ አንተ ብመለስ ደጋግመህ ትሰብረኛለህ፤ ስለዚህ "ተመለሽ" አትበለኝ። እንኳንስ ብለህኝ ቀድሞውኑ እግሮቼን በትግል ነው ያቆምኳቸው። እስኪ የተሰጠውን ፍቅርና ክብር ረግጦ ወደ ችላ ባዩ አንተ ልሂድ የሚለውን ልቤን መንገድ አትክፈትለት። ፈጣሪ ክሶኝ የለ በቃ አመስግኜ ልኑር፤ ባለህበት ሰላም ሁንልኝ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mahlet
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
01/07/14
ዛሬ የቀብሯ ማግስት ነው፤ ይህቺ ጎበዝ ይህቺ ብርቱ ይህቺ ትሁት የጨለመችበት ማግስት። ግርግዳ ለይ የተሰቀለው ፎቶዋ ለይ ፀጉሯን ጉንጉን (የትግሬ ሹሩባ) የሚባለውን አይነት ተሰርታ ሰማያዊ ጥለት ባለው የሀገር ባህል ልብሷ ለይ በፈገግታ ደምቃለች። ሰዉ እሷን ማጣቱ አንጀቱን በልቶት እጥፍ ብሎ ያለቅሳል እሷ ግርግዳዋ ለይ ፈገግ ብላ ትመለከታለች። ለወትሮው የሰው ሀዘን የሚነካት ፈጥኖ ደራሽ እንባ አባሽ ነበረች ታዲያ ለምንድነው ዛሬ በዚህ ሁሉ እንባ መሀል ፈገግ ማለቷ?

ቤቷ ስገባ እግሬን መቆም እስኪከብደው ሰውነቴ ራደብኝ፤ ይሄን እልፍኝ አውቀዋለዋ ወጣ ገባ ብላ አስተናግዳናለች እንጀራውን ዘንጠፍ አድርጋ ቆርሳ አጉርሳናለች፣ እሷ ጋር "በቃኝ" የሚለው ቃል እዚህ ግባ አይባልም፤ ሰው በልቶ የሚጠግብ አይመስላትም ማዕዱ ሳይጎድል በላይ በላዩ ለመጨመር አርፋ አትቀመጥም ነበር "እረ ፀጋ በቃሽ" እንላታለን በጀ አትልም መሶብዎን እስክታራቁት ብሉልኝ ነው፤ እጅ ሰፊ ናት። ዛሬ ግን ይሄ ሁሉ እንግዳ ቤቷ ተሰብስቦ ብሉልኝ የለ ቁጭ በሉ የለ ፈገግ ማለት ብቻ።

የደግነት ልክ ናት ሰው መውደድ አይድክማትም "ፀጋ እኮ ፔርሙዝ ተሰብሮባት በጆግ ሙቅ ይዛ መጥታ የጠየቀችኝ ሴት ናት" እያሉ አንዲት እናት ያለቅሳሉ እሷ ያሮጠችበት ቤት ያለተሸከመችለት ሰው የለም። እናቴን አሟት ቡናውን ስኳሩን ከሰሉን...... እየተሸከመች መጥታ ትጠይቃት ነበር።

ያቺ ትንሽዬ ቤት ሁሌም በሰው እንደተሞላች ነበር የዘመድ ማረፊያ መሰብሰቢያ ናት። የራሷን ልጆች ጨምሮ የባለቤቷ የዘመድ ልጆች እሷ ነበረች የምታሳድጋቸው፤ የሁሉ እናት ናት።
እንደውም ከአመት ወይ ቢበዛ ከሁለት አመት በፊት ሰፈር ውስጥ አንዲት ህፃን ከነ ጡጦዋ ተጥላ ትገኛለች። ከዚህ በፊት ልጅ ባገኝ አሳድጋለው የምትል ጓደኛ የነበረቻት ፀጋ ልጅቷን ትውስዳታለች ነገር ግን ህፃኗ ክስት ያለችና ብዙ የጤና ችግር የነበረባት በመሆኑ ጓድኛዋ እንደማትፈልግ ነገረቻት። ልበ ቀናዋ ፀጋ ግን "የእግዚአብሔር ፍጡር ናት እሱ ካዳነ ያድናት ካልሆነም እንደወደደ ያድርግ እኔ ግን የቻልኩትን አደርጋለው" ስትል ሆስፒታል ይዛት ገባች። ለዚች ህፃን ስትል ያላየችው መከራ ያልተጋፈጠችው ስቃይ አልነበረም። ሰው ሁሉ "በማረፊያሽ ሰአት ከልጅ ጋር ለምን ትንገላቻለሽ እዚው ሆስፒታል ጥለሻት ውጪ" እያሉ ቢወተውቷትም እንኳን ለሰው ሟች ለሆነችው ፀጋ የሚታሰብ አልነበረም ፈጣሪም ረዳትና አሳክማት ድና ወጣች ዛሬ ወፍራ ድክ ድክ ስትል ለሚያያት ሰው ታሳሳለች።
በየቤተክርስቲያኑ ጥበቧን ለብሳ ልጇን አቁርባ አዝላ ስትመለስ ሳያት ብርታቷ ያስደንቀኝ ነበር። ማነው ባለተመቻቸ ኑሮ፣ ብዙ ልጆች እያሉት፣ ጉልበቴ ደክሟል በሚልበት ሰአት የተጣለ ልጅ ያውም በሽተኛ ለማሳደግ የሚፈቅድው? ይህቺ ናት እንግዲህ ፀጋ ማለት።

ለልጆቿ ስትል የማትጋፈጠው ፈተና አለነበረም፤ ከነ ስህተታቸው ከነ ጥፋታቸው መደበቂያ መሸሸግያቸው ነበረች "ነብር ናት" ትላታለች እናቴ በጭራሽ አታስነካቸውም ነበር፤አሳልፋ አትሰጥም። ስንቴ በእነሱ ምክንያት ዝቅ ብላለች ፣የስንቱ እግር ለይ ለይቅርታ ወድቃለች፣ ከሰው አንሳለች፣ ተሰድባለች ተንቃለች፣ ተደብድባለች፤ እንዲህ አደረጉ የሚል ቃል ግን ከአፏ አይወጣም "በቃ አጥፍተዋል ልጆች ናቸው" ብላ ስህተታቸውን ሁሉ ድብቅብቅ ታደርግላቸዋለች።
ሁሌም እየስከረ በሚመጣ ልጇ ምክንያት "የስንቱን እንባ አብሰሻል ስንቱን አቃንተሻል የኔንም ልጅ ካላስተካከልሽልኝ ድጅሽ አልመጣም" ብላ ከ ቅድስት ኪዳነ-ምህረት ጋር የተኮራረፈች የዋህ እናት እኮ ናት።

ሁሌም ስታገኘኝ "እናትሽ ልትረሳ ትችላለች አንቺ ግን አስታውሰሽ ለምርቃትሽ ጥሪኝ እሺ አደራ ሳልሰማ እንዳልቀር" ትለኝ ነበር እንዲህ ለምትቀረው፤ እንዴት ጠራታለው? ብትሰማስ የት ትገኝና ነው?
ከእናቴ ጓደኞች ውስጥ ልቤን የምትገዛኝ እሷ ነበረች። ፈገግታዋ፣የአነጋገር ለዛዋ፣ብርታቷ፣ ደግነቷ፣ፍቅሯ.....አይኔ ለይ የሚሳልላት ደርባባ ሴት ናት።
የቀናነቷን ያህል ያለቦታው ለሚነካት የማትመለስ ቁጡ ነብር ነበረች።ስንቱን በሌሎቹ በለመደው ጋጠወጥነት ላሳንስሽ ሲላት አልደፈርም ብላ ልክ ያስገባች ቆፍጣና ሴት።

አሁን አሁንማ ሀገሬን ትመሰለኝ ጀምሯል፤ እጀ ሰፊ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ የሁሉ ማረፊያ መሰብሰቢያ አድባር፣ የደግነት ልክ፣ የቸርነት ሙዳይ፣ የትህትና ተምሳሌት፣ አትንኩኝ ባይ የክብርና የጀግንነት ምሳሌ፣ ሳቂታ ተጫዋች ደርባባ እናት!

ያቺ ትንሽዬ ህፃን ወደፊት አድጋ ሁሉ በተዋት ጊዜ ተቀብላ ተንገላታ በፈጣሪ እርዳታ ሰው ያደረገቻት ሀገር የመሰለች እናት እንደነበረቻት ስታውቅ ምን ትል ይሆን ስል አስባለው? ገመና ከታች፣ ቦርቧራ፣ ትግስቷ የማያልቅ እናታቸውን ያጡት ልጆችስ እንዴት ይችሉት ይሆን? የቤት ምሰሶ፣ የሌት ብርሃን፣ የጎጆ ሙላት፣ ክፉን መሻገሪያ ምርኩዝ፣ የወጣትነት ጌጥ፣ የእርጅና ሞገስ፣ የዘመናት ጓደኛና አጋር የልጆቻቸውን እናት ያጡት አባወራ የሀዘናቸው ጥልቀት እንደምን ያለ ነው?

አንቺ ዘወትር ከልብ የማጠፊ የሁሉ ቁጭት ነሽና ፈጣሪ በመሄድሽ ላጎደልሽበት ሁሉ መፅናናቱን ይስጠው፤ ላንቺ ደግሞ በየ አመቱ ደግሰሽ የምትዘክሪው ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ነፍስሽን በገነት ያሳርፍልሽ!!!
"እወዳቹሀለው" የሚለው ቃል አይደል ከአንደበትሽ ዘውትር የሚፈልቀው እኛም እጅጉን እንወድሻለን!!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mahlet
ከብዙ ለዛ ቢስ ዙሪያ ጥምጥም ወሬ በኋላ ፤በልቧ በሰነደችው ቃላት አማካኝነት ከኔ ጋ በፍቅር መቆራኘታችን ይብቃ አለችኝ። ፈገግ አልኩ ። እሷ ለመለየት የወሰነች እለት እኔ ምን እያሰብኩ ነበር?። ለጓደኛዬ በዚህ አመት እንደማገባት እየነገርኩት ነበር ፤ ባስቀየመችኝ ተብሰልስዬ ለማስተካከል መንገድ እየቀየስኩ ነበር ።
እንለያይ ስትለኝ ፈገግ አልኩ ። እንደዚህ ስፈግ ምን እንደሚሰማኝ እንጂ ምን እንደምመስል አላቅም መለያየት የፈለገችው ሌላ የተሻለ ሰው አግኝታ ሊሆን ይችላል አልያም ድክመቶቼ ከአቅሟ በላይ ሆነውባት ወይ ደግሞ ሰልችቷት ብቻ ውሳኔዋ ከልቧ እንደሆነ ፊቷ ያስታውቃል ።
ፈገግ እንዳልኩ ቡናዬን ስኳር ሳልከትበት ፉት አልኩ ፤ የሚመር ነገር እስክንለምደው እንጂ ባይጣፍጠን እንኳን አይመረንም። ፊት ለፊቴ እንለያይ የምትለኝ ልጅ በፊት ፊቷ ከሁሉ ይለይ ነበር ፤ ከደቂቃዎች በፊት እሷ ግለሰብ ብቻ አልነበረችም ፤ ሃገር ታክል ነበር። እንቅስቃሴዋ ሁሉ ይመለከተኛል ፤ ስልጣን አለኝ ባይ ነበርኩ ።
የልጆቻችንን ስም አውጥተን ፤ ስለ ገቢ ምንጫችን አውጠንጥነን እና አደላድለን ስናበቃ
እንደዋዛ እንለያይ አለችኝ ፤ የአስተሳሰረን የአብሮነት መስመር ግዙፍ መስሎኝ ነበር። መለያየትን የማላቀው ነው የመሰላት። ዘጠነኛ B ክላስ እየተማርኩ ምሳ ልበላ እና ፀጉሬን የምቆረጥበት ፍራንክ ከእናቴ ልቀበል ስመጣ ነው ልቧን ታማ ስታጣጥር የደረስኩት። ሃያ ደቂቃ አልሆናትም ፤ በስስት እያየችኝ ነው የተለየችኝ ፤ በስስት ከሚወደኝ ጋ መለያየት በልጅነቴ እየተነፋረቅኩ ተጋፍጬዋለሁ። መለየት አዲሴ መስሏታል። የካምፓስ ፍቅረኛዬ ፤ ባህር ማዶ የጉልበት ሰራተኛ ለዛውም የአሳማ ስጋ ሻጭ የሆነን ከኔ ጋ አወዳድራ እና ፍቅሬን በሳንቲም አጣፍታው ጥላኝ ሄዳለች። እየለመንኳት ፤ ነገዬ ብሩህ እንደሚሆን እየማልኩላት ፤ ለመለየት ሰበብ ስትደረድር ፤ በፍቅር እና በሎጂክ ሰበቧን ስታገለው ፊት ለፊት እየቺች ነው ጥላኝ መሄድ ያልከበዳት። ከባሏ ጋ ደስተኛ እንዳልሆነች ፤ ልጅ እምቢ እንዳላቸው ስሰማ ፤ የአሁኑን ፈገግታ ነው
ፈገግ ያልኩት ፤ በደስታ አይደለም በግርምት እንጂ። ከእኔ ያጣችውን ሳንቲም ለመሙላት ሄዳ እኔ የነበረኝ ጎደላት። ይሄ ፈገግ ያለ ፊት ስንት መለየት እንዳስተናገደ ፤ ይሄ የምታየው ፊት በመለየት ስንቴ እንደ ተሰበረ ከእኔ በላይ ማን ያውቃል። እንለያይ አለችኝ ! መለያየት እኔ መች ይከብደኛል ? አምኖ አብሮ መኖር ነው እንጂ ፤ አሁን እኔ ቁስሌን ፣ ፍርሃቴን እያወቀች እንለያይ ማለት አለባት? ለምን የለባትም ፤ ማን አዝኖ በፍቅር ይዳበላል። ዝም ብዬ ተረጋግቼ ሳያት ። ይሄን ልነገርህ ነው የመጣሁት አለችኝ። አብረሺኝ ሁኚ ተብሎ አይለመን ፤ አብረሽኝ ሁኚ ብሎ የለመነ ፤ ተለማኙ አብሮ መሆንን እስኪያምን በፍቃድ ራስን ለባርነት አሳልፎ መስጠት ነው !
ዝምታዬ ገርሟት ፤ ዝም ብላ ስታየኝ ፤ ለጠጥ ብዬ እንደተቀመጥኩ ፤ አንዱ እግሬን አንዱ ላይ አነባብሬ ትርጉሙ በማይገባ ፈገግታ አናቴን ነቀነኩት። አልገባትም ማንን አልፈልግም እንዳለች!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
መንገድ ላይ የጀበና ቡና የምትሸጥ ሴት ማፍቀርኮ ችግር የለውም። ችግሩ ፉክክርህ ከግንበኛ፣ ከተራ አስከባሪ፣ ከአናፂ ምናምን ጋር ነው።

የማስተርስ ዲግሪ ሰርቼ...ስምንት አመት ሙሉ የባንክ ስራን ቀጥቅጨ...ያሰብኩትን ሁሉ ጨብጬ...የአልማዝ ልብ ግን ከመንገድ ወያላዎች ለይቶ አያዬኝም። "የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው" የሚለው የእማዬ ምክር እዚህ ላይ አይሰራም። በኑሮ ሰባት እጥፍ የምበልጣቸውን ሰዎች በምላስም በልጨ መገኘት አለብኝ። ችግሩ መሰሎቼ ስላልሆኑ ያ ባለጌ ሽመልስ እንደ ኮሜዲያን የሚታይበት ዳስ ውስጥ የኔ ቀልድ እጅ እጅ ይላቸዋል። አንዳንዶቹማ እያወራሁ በፈጠጣው አቋርጠውኝ ሁላ ሌላ ወሬ ይጀምራሉ። ሽመልስ ማውራት ሲጀምር ግን አልሚ ራሱ ቡና መቅዳቷን ቆም ታደርጋለች (ስትስቅ እንዳያስደፋት መሆኑ ነው። ገና ሲጀምር እንደሚያስቃት እርግጠኛ ነች።) እኔ
በበኩሌ ከሚያሰቀው ነገሩ ብልግናው ስለሚበዛብኝ ሁሌ እንደተሸማቀኩ ነው።
<<አባቴ 'ሽመልስ' ያለኝ ከበቶቼን የሚጠብቅ እረኛ ተወለደልኝ ብሎ ነው። እኔ ደግሞ የህይወቴ ጥሪ ከዚህም በላይ ነው ብዬ ጠፍቼ መጣሁ። እረኝነት እጣፈንታዬ እንደሆነ የገባኝ ግን እዚህም መጥቼ መኪና ሳግድ ነው!>> <<ታዲያ የትኛው ተሻለህ...የከተማው ወይስ የገጠሩ እረኝነት?>> ይለዋል አንዱ ሰው መስሎት።
<<ተመልሼ መግቢያ የለኝም እንጂ የገጠሩ ይሻለኝ ነበር። እዛኮ ቢያንስ ሲደብረኝ አህያ እበ*ለሁ!>> ብሎ በሰላሳ አመት የሰበሰብነውን ቀልብ ይገፈዋል። የፈለገው እንስሳ ጋር ሴክስ ማድረግ ይችላል...እሱ የኔ ጉዳይ አይደለም። ችግሩ ምንም የመጀናጀኛ አየር እየሰጠኝ አይደለም። እሱ ባለበት አይደለም መጀንጀን ወሬ መጨረስ ራሱ አልቻልኩም። <<ባለፈው መኪናዬ ስታክ አድርጋብኝ...>> ብዬ ስጀምር <<አይይ!... አሁን እዚህ ማን ስለመኪና ያውቃል ብለህ ነው?>> ብሎ ያናጥበኛል። <<የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ።>> ብዬ ረጅም ሳክስ ስጀምር <<ቡና በስኳር እየጠጣህ የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ ብትለኝ አላምንህም>> ብሎ ባጭሩ ይቀጨኛል። አሁን አሁን ገና ከሩቅ ሳዬው እንደ ስፔን ኮርማ ተንደርድሬ ልወጋው ሁሉ ያምረኛል። ወዲያው ከሀሳቤ ብንን ስል ፍቅር የት ድረስ እንዳወረደኝ አስብና እገረማለሁ። እንዲህ አብሮ መዋል ሳያናንቀን በፊት በፊት ሽመልስ ይመቸኝ ነበር። መኪናዬን ይዤ ስመጣ ቆንጆ የፓርኪንግ ስፓት እንዳገኝ ይረዳኛል። የሆነ ቀን ከመኪናዬ ሳልወርድ <<እስኪ ቡና እዘዝልኝ>> አልኩት። አንዲት ቀይ ልጅ የጀበና ቡና ይዛ መጣች። ከቡናዋ ጋር ምን እንዳቀመሰችኝ አላውቅም ከዛ ቡኃላ ልክ አይደለሁም። ፈገግ ስትል ብቅ የሚለው የተነቀሰ ድዷ አብስትራክት ስዕል ይመስል በየ ደቂቃው የአንገቴን አቅጣጫ እየቀየርኩ አየዋለሁ። ፓንቷ ውስጥ ሻጥ አድርጋው የምትሔደው ሺቲ በተንቀሳቀሰች ቁጥር በዳሌዋ ሲያስገለምጠን ይውላል። ስትስቅ ድዷ...ስትራመድ ዳሌዋ! እህህ ሁኗል የኔ ኑሮ!
ታዲያ እኔ እሷን...እሷ ደግሞ ሽመልስን እንደምትወድ ለመረዳት ብዙ አልፈጀብኝም። በብልግና ቀልዱ መሳቅ ብቻ አይደለም...ጭራሽ <<ብልግናቸውን የማይደብቁ ሰዎች ጨዋ ነው የሚመስሉኝ>> ብላ ልትደግፈው ትሞክራለች። ፍቅር የሚባለው የበሽታ አይነት ሲይዝ መጀመሪያ የሚያጠቃው መለኪያ ሚዛንህን ሳይሆን አይቀርም። ለኔ አልማዝን አለም ላይ የትም መገኘት የማትችል እንቁ አድርጎ ያሳዬኛል። ለሷ ደግሞ ሽመልስን አርብ ሮብ የሚፆም ጨዋ አድርጎ ያሳያታል። ቢሆንም...ቢሆንም! እሷን የመጥበስ እድሌ ተንጠፍጥፎ እንዳላለቀ ይሰማኛል። አንድ ጧት እንደመጣሁ አምስት መቶ ብር የሻይ ሰጠሁትና ራቅ ወዳለ ሰፈር ላኩት።
አልሚን ብቻዋን አገኘኋት። <<የሆነ ቆንጆ ሬስቶራንት አለ። ዛሬ የሚመችሽ ከሆነ ራት ልጋብዝሽ!>> አልኳት...ስለማመድ የዋልኩት ይሔ መሆኑን ለራሴም ማመን እያቃተኝ። <<ውይ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዛሬ አክሴቴ ከገጠር ትመጣብኛለች። ወይ ሌላ ቀን
እናድርገው?>> <<ኧረ ችግር የለውም። ያን ያህል አንገብጋቢ ነገር አስመሰልሺውኮ!>> ከረባቴን
አላላሁትና መልሼ አጠበኩት። ተነስቼ ወጣሁ። ደሜ ፈልቷል። ውስጤ አላመናትም። ሽመልስ እንደመጣ <<ዛሬ የት ነህ? ከስራ ስወጣ ለምን አንድ ሁለት እንልም?>> አልኩት። <<ውይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዝናቡን እንደምመጣ ቃል ገብቼለታለሁ!>> አለ የሰጠሁትን ብር አገላብጦ እያዬ! አያውቅም ብሎ ስም እየፈጠረ እንደሆነ ገብቶኛል። <<ዝናቡ ዝናቡ?>> <<ዝናቡ ይሔ ባለፈው 'ቶሎ ባይነሳ አፉ ላይ ያለው የጠጅ ሽታ ሊያሰክረኝ ነበር' ብለህ የቀለድክበት>> እውነት ለመናገር ሊያስመልሰኝ ነው የነበረው። <<አስታወስኩት! ታዲያ ለምን እኔ እናንተ ጋር አልመጣም?>> <<ኧረ አይሆንህም!>>
<<ግዴለም! ይልቅ ቆንጆ ጠጅ ቤት ውሰዱኝ!>> ሳይመልስልኝ ጥዬው ገባሁ። ከስራ እንደወጣሁ ባኮረፈ ፊት ይዞኝ መሔድ ጀመረ። ጠጅ ቤት ከገባን ቡኃላ ከሁሉም ተነጥለን የራሳችንን ወሬ ለመጀመር ሁለት ብርሌ ነው የፈጀብን። ያለ ሰበብ እንዳልመጣሁ ገብቶታል።
<<አልሚን ትወዳታለሀ?>> አለኝ ሌሎች እንዳይሰሙን እየተጠነቀቀ! በጥያቄው አልተገረምኩም። <<ፍቅር የሰው ልክ አያውቅም ወዳጄ። ያንንም ያንንም ሲጨብጥበት በቆየበት እጁ ነው የሚጨብጥህ! መጨበጡን እንጂ ማንን እንደጨበጠ አያውቅም። እውር ነው። የሚመመራን ግን እሱ ነው። የምለው ገብቶሀላ?>> <<ይሔ ቢገባኝ የመኪና እረኛ ሁኜ እቀር ነበር ብለህ ነው?>> <<ልልህ የፈለኩት ፍቅር ደረጃ የማይለያይ ደጋሽ ነው። የመኪናውን ባለቤት ከመኪናው እረኛ ጋር ጠጅ ያስጠጣል!>>
ፈገግ አለ። <<ተውልኝ ልትለኝ እንደመጣህ ገብቶኛል። እኔም ልልህ ነበር።>> <<እና ለምን አላልከኝም?>> <<ትርፉ ድካም ነው። እሷ የምትወደው አንተን!...ለምን ጊዜዬን አባክናለሁ?!>> ከስካሬ ነቃ አልኩ። <<እኔን እንዳጫዋች ነው የምታዬኝ። አንተ ስትመጣ ግን ያለባህሪዋ ቆጠብ ትላለች። እንድትወዳት ለማድረግ ትጥራለች። እኔ ምንም አይነት ሰው ብሆን ለሷ አይን አልሞላም።>> እንባ አቀረረ። ይሔን ንግግር እኔ ቀድሜው ባለማለቴ ደስ አለኝ። <<ይገባኛል ስሜትህ>> አልኩት ውስጤ እየተፍነከነከ። ፊቴን ያዘንኩ ላስመስል ሞከርኩ ግን አልቻልኩም። የሚታየኝ የአልሚ ቀሚስ ውስጥ ገብቼ አሸሸ ገዳሜ ስል ነው። ወዲያው ጥግ ላይ የነበረው ዝናቡ እየተንገዳገደ ተነስቶ ወደኛ መጣ። <<አንድ ሁለት መቶ ብር አላችሁ አንዴ?>> አለን
<<ለምንህ?>>
<<አሁን አይደል እንዴ ትዝ የሚለኝ? ለካስ ያቺን ቅንዝራም አልማዝን ቀጥሬያታለሁ! ህእ! >>
ሁለታችንም ደንዝዘን ቀረን። ደመናውን ሳናዬው ዝናቡ ከዬት መጣ? ሰማይ ሳያስገመግም
መብረቁ እንዴት መታን? ብሩን ተቀብሎን ሲወጣ ባለማመን እናየዋለን። በሩ ላይ ሲደርስ ዞር ብሎ <<ጠጅ እስቀምጡልኝ! ጠቅ ጠቅ አድርጊያት እመለሳለሁ>> አለንና በሁለቱም አይኑ ጠቀሰን። በህመም ስሜት አይናችንን ጨፈንን። "የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው!"

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael Azmeraw
"እንደኔ እድለኛ የለም"
.........................

"እንደኔ እድለኛ የለም!" በሚሉ ሰዎች እጅግ እቀናለሁ።የዕድለኝነት ጠረፍ ላይ መድረስ ምንኛ መታደል ነው!!ምናልባትም ለመደሰት ጥቂት ነገር ከበቂ በላይ የሚሆንባቸው ሰዎች ቋንቋ ትሆናለች።በምናብ ብቻ የሚቦርቁ...እየጃጁ እንኳን ወደናታቸው ማህፀን በመመለስ ላይ ያሉ የሚመስላቸው አሉ መሰለኝ!ምናውቄ!

እኔ ለራሴ አዳሜን አስሼ ሳጣው እግዜሩ በ system ችግር ምክንያት ሴት አርጎ የፈጠረኝ የሚመስለኝ...ከማን የግራ ጎን እንደተሳብኩ ለማወቅ ድፍን 10 አመታትን በጀት መድቤና ፖሊሲ ነድፌ የተንቀሳቀስኩ የ36 አመት ሴተ ላጤ ነኝ።

ባስ ካለብኝ በመንገዱ መጨረሻ እጆቹን ዘርግቶ welcome honey የሚለኝ አንድ ጎምላላ የቀጠርኩ ይመስል አበደች እስክባል እጄን እንደ ክንፍ አስመስዬ እራመዳለሁ።ታክሲ ስሳፈር ከጎኔ የተቀመጠውን ሰው የቀለበት ጣት scan አደርጋለሁ።"ታክሲ ላይ ተዋውቀን ለዚህ በቃን..."የሚሉ እድለኞች ትዝ ይሉኝና ጅንጀናዬን እጀምራለሁ።ታክሲ ላይ ባል ሊገኝ😁

"እንዴት ዋልክ ወንድሜ?"እላለሁ።ሀፍረትና ይሉኝታ ሀገሩን እየዞሩ እንቁላላቸውን ሲጥሉ የኔን ቤት ዘለውታል። አንዱ ሙሉ ቶክሲዶውን ግጥም አርጎ ከጎኔ ተቀምጧል።

"እግዚአብሄር ይመስገን..." አለኝ ምን ልትይ ነው?ቀጥይ በሚል አይነት ቅላፄ።

"ደም ባንክ የት አካባቢ እንደሆነ ታውቃለህ?ብትጠቁመኝ..."

"አላውቅም"አለኝ ቀልጠፍ ብሎ!እውቅና ይንሳህ!!!!ከጎኑ የተቀመጠችዋ ባልቴት

"ሆስፒታሉ ግድም ነው"አለች።እኔ መች ባንኩ ጠፋኝ ባሉ እንጂ!አመስግኜ መንገዴን ቀጠልኩ....

ዕድለኝነት በሚሰማቸው ሰዎች የምቀናው ለዚህ ነው።ሙሉ ስላልሆንኩ...ብሶቴን የሚያባብስብኝ አንድ ዜማ አለ።

"ማመን አቃተኝ
የህልሜን ንግስት የኔ አረኩና
ብሩህ ቀን መጣ
ህይወት ሊታደስ ባንቺ እንደገና..."

እንኳን ህይወቴን የሚያድስ ላገኝ የተላጠ ግድግዳዬን በቀለም ለማደስ ከሚመጣ ቀለም ቀቢ ጋር እንድጃጃል እጣ ፈንታ እቶን ላይ የጣደኝ ከርታታ ነኝ...

"...ማን አለ እንደኔ
እድል የቀናው...ቀን የወጣለት
ምኞት ውጥኑ የሰመረለት..."

እነዚህ ስንኞች እኔና ብዙአየሁ(ድምፃዊው) የአርክቲክና የአንታርክቲክን ያህል የተራራቀ የስሜት ድንበር ላይ መቆማችንን ያስታውሱኛል።እንደገና እቀናለሁ!!!አለመታደልን እንደታደልኩ ሳስብ እበግናለሁ።

"...በፍቅርሽ ዜማ
ኑሮ ተቃኝቶ
ብርሀን ተሞላ
የኔ ዓለምማ....."

እኔ ፍቅር የሚያዜምልኝ...አዚሞም ኑሮዬን የሚቃኝ ባገኝ በነዛ ሰዎች አልቀናም ነበር።"እንደኔ ዕድለኛ የለም!"በሚሉት...እኔ አለሜን በብርሀን የሚሞላውን ያንን ጎምላላ ባገኘው ከዚህ በላይ እቀኝለት ነበር።

"....አልፈራም ነገን እንዳምና
አንቺ አለሽና
በፍቅርሽ ከፍ ያደረግሽኝ
እንደደመና...."

እኔ ግን ነገን እፈራዋለሁ።ምክንያቱም ነገዎቼ በሞላ ከዛሬዎቼ አይለዩም።ወራቱም አንድ ነው።የዐለም ዜና እንጂ እኔጋ የህይወት ዜና የለም።አዲስ ነገር የለማ!!!እንደደመና ከፍ የሚያደርግ ትስስር መስርቼ አላውቅም።እንደደመና ከፍ የምለው ሂል ጫማ ስጫማ ብቻ ነው።አሁንም ቀናሁ።በነዛ ሰዎች...."እንደኔ እድለኛ የለም!!"በሚሉት!!!

ተፃፈ በማዕዶት ያየህ(Geez)
17/04/2013ዓ.ም

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#Tizur_12
2024/09/23 00:19:17
Back to Top
HTML Embed Code: