Telegram Web Link
ወቀሳ!

ወቀሳ ግላዊ ነው ፤ በተለይ የወቃሹ ሁኔታ ይወስነዋል ፤ የወቃሹ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አቋሙ ይወስናል፡፡ አንዳንዴ ያልተመጣጠነ ወቀሳ ያጋጥማል እንዴት በኔ ጫማ አትቆምም አይነት አጉል ሙግት ያጋጥማል፡፡ ለምሳሌ በታሪክ አጋጣሚ ከአንድ ዲታ ጋር ቡና ልትጠጡ አንድ ጠረጴዛ ላይ ልትቀመጡ ትችላላቹ ፤ እናም ያ ዲታ ስለመኪና ዘይት መወደድ ውጥር አደርጎ ሊሞግታቹ ይችላል አረ እንዳውም እንደሱ ስላልመረራቹ ሊወቃሳቹ ይችላል እንዲህ ብሎ ድሮም እኮ ሃበሻ……….፡፡ አሁን ለጎዳና ተዳዳሪ በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ስቶቫችን ተበላሸ ፍሪጃችን ስራ አቆመ ብትሉት እንዴት ይሰማችኋል፡፡ ና እና እሪ እንበል መብራት እኮ መሰረታዊ ፍላጎት ነው ብትሉት እንዴት ይገባዋል ፤ ከገንዳ ላይ ማንጎ የሚግጠው ያ ምስኪን ለሱ መሰረታዊ ፍላጎት እኛ ዝናብ ሲዘንብ ጥቅልል ብለን የምንተኛበት መጠለያ ነው፤ መብራት አይደለም፡፡ እዛ በጭሶች መሃል ተሸሽጋ እራፊ ጨርቅ አድርጋ አላፊ አግዳሚውን ለማማለል የምጥጥረው ያቺ ሴት ለሷ መሰረታዊ ፍላጎት ኔትወርክ ሳይሆን ወንድሟቿ የሚበሉት ነገር ማግኘት ነው፡፡ ወቀሳ ግላዊ ነው አንዳንዴ እንዲህ ያጋጥማል ታናሽ ወንድም ስራ ፍለጋ ተንከራቶ ተንከራቶ እግሩ እየተንቀጠቀጠ ቤት ሲገባ ታላቅየው የታሸገ ውሃ ይዞ ሲጉረመርም ያገኘዋል ታናሽ ምን ሆነህ
ነው የምታጉረመርመው ሲለው አሁን ይሄ የታሸገ ውሃ ኮንቴንቱን አይተኽዋል
ካልሺሙን እየው 14.3 ነው ሶዲየሙን እየው 4.80 ነው አይገርምም ይለዋል
ታናሽ ገርሞት ዝም ቢል ታላቅ ወቀሳ ይጀምራል እንዲህ ብሎ ለስሙ ዲግሪ
አለህ እንዴት የታሸገ ውሃ ኮንቴንት አታይም………. እንግዲህ አንዳንዴ እንዲህ ነው፡፡ ሰውን ስንወቅስ መጠንቀቅ አለብን

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tewodros Tezera
(ቤካ)

በአንድ ወቅት አንድ አባትና ልጅ በአንድ ተራርቀው በተተከሉ ዛፎችና ዋርካዎች ባሉበት ስፍራ እየተዘዋወሩና እየተዝናኑ ሳለ ልጅየው በተደጋጋሚ ወደ ሰማይ ቀና እያለ ያያል ታዲያ ይሄን ያየ አባት መጀመሪያ ቀና ብሎ ሰማዩን አየና ወደ ልጁ መለስ ብሎ

"የኔ ልጅ ከቅድም ጀምሮ እንቅፋት እስኪመታህ ድረስ ቀና እያልክ የምታየው ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
ልጁም" አባቢ ሰማዩ ላይ ዝም ብላ የምትሽከረከዋን ቆንጆና ትንሿን ወፍ አይተሀታል?" ብሎ ጠየቀው፡፡ አባትየውም በድጋሚ አንገቱን ቀና አድርጎ ሲመለከት መጀመሪያ ሰማዩን ስትዞር የነበረችው ወፍ አሁንም ሰማዩን ስትዞረው ያያል ከዛም አንገቱን ጎንበስ አረገና " አዎ አየዋት የኔ ልጅ ምነው?" አለው፡፡

ልጁም " ይሄ ሁሉ ዛፍና ዋርካ እያለላት አማርጣ አንዱ ላይ እንደመቀመጥ ለምን እራሷን ታደክማለች?" ይልና መልሶ ይጠይቀዋል፡፡
አባትየውም ትንሽ አሰብ አደረገና "የኔ ልጅ ምናልባት ይቺ ወፍ ቆንጆ ስለሆነች ሁሉም ዛፎች እንድትቀመጥባቸው ስለሚፈልጉ ዛፉ ሁሉ አይናዋጅ ሆኖባት ይሆናል ፤ ምናልባትም የትኛው እሾሀማው ዛፍ እንዳልሆነ እያረጋገጠች ይሆናል" ብሎ ይመልስለታል፡፡
ልጁም ትንሽ ከቆየ ቡሀላ " ግን እኮ አባቢ ቆንጆ የሆነችው እኮ እንደኔ ትንሽ ስለሆነች አደል?" ይለዋል መልሱን ከሰማ ቡኃላ ምን እንደሚለው እያሰበ፡፡

አባትየውም በጥያቄው ተገርሞ " አዎ የኔ ልጅ" ይለዋል
" ስለዚህ ሳድግ እንዳሁኑ ቆንጆ አሎንም ማለት ነው፡፡ እንደዛ ከሆነ ደሞ ይቺም ወፉ ቶሎ የሚመቻትን ዛፍ ፈለጋ ካልተቀመጠች በኃላ ቁንጅናዋ ሲጠፋ መቀመጫ ታጣለች ማለት ነው እኮ፡፡ እና ደሞ እሾህ ያለውንም ዛፍ ቶሎ ካለየች እኮ ቡኃላ ሲደክማት የማቶደውና መጥፎ እሾህ ላይ ልትወድቅ ትችላለች አይደል?" ይለዋል ትክክል እንደሆነ እንዲነግረው ጥያቄውን አስከትሎ፡፡

አባትም " ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ፡፡ ነገር ግን ደሞ እኛ ያሰብነውና የሷ የምትሽከረከርበት ምክንያት ሊለያይ ስለሚችል ባለማረፏ አትፍረድባት እሺ" ብሎ ይመልስለትና " እስኪ ዛሬ ከውሏችን ምን ተማርክ "ብሎ ይጠይቀዋል

" ከወፏ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ ነገር ግን በጣም የተረዳሁት ነገር የሚሆነውና የሚታየው ሊለያይ ስለሚችል በማንም ላይ አጄን መጠቆሞና መፍረድ እንደሌለብኝ ተምሬያለሁ " አለው፡፡

""ማንም ሰው በ አምስት ጣቱ ሚጠቁም የለም ፤ በ አንድ ጣቱ ጠቆመ ማለት ደግሞ አራቱን ጣቶቹ ወደራሱ ቀሰረ ማለት ነው!!!!!!!""""

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
ጃን ዳሌ
◦◦◦◦◦◦◦◦◦
ናዊአብርሃም ( @nawi1 )
.------------------------------------------
.
.
በበረነዳ ልጅቷን ለማየት ትወጣለህ፤አትኖርም።
ጨረቃን ለማየት ታንጋጣለህ፣አትኖርም።

ምክንያቱስ?

ጨረቃ
ለ ኒል አርምስትሮንግ ድንግልናዋን የሰጠች ናዋዥ አፍቃሪው ናት። በቃ!! በጨረቃም ተስፋ ትቆርጣለህ ። አልጋህ ላይ ትወጣለህ፤ የኔ የምትለው እንቅልፍህንም በናፍቆቷ ቁማር ትበላለህ ።

በመጨረሻም በትግል ፣ በጨበጣ አሸንፈህ ዕንቅልፍህን ታስመልሳለህ ፤ እንቅልፍህ ውስጥ እሷ ትኖራለች። አይ ጨረቃ ...እሷም ትኖራለች። ይሄኔ ጨረቃ በመሬት ዙሪያ መዞሯን ትጠራጠራለህ።'
. . .

ንቃቴ ኖረ አልኖረ ግድ ሳይሰጣት በማን አለብኝነት ጭንቅላቴ ውስጥ ትንጎዳጎዳለች።

ይህቺን ልጅ በጣም እየጠላኋት ነው። እነደ ቄንጠኛ አስተናጋጅ ትከሻዬ ላይ አንጠልጥዬ ጠረሙሱ ላይ እንዳለው ቆርኪ ጭኖቿን መክፈት እና ከያዘችው እርካታ ሙላውን መጎንጨት እያማረኝ ነው።

ይህቺን ልጅ እየጠላኋት ነው። ህልሜን ትመስለኛለች ።

ለህልሜ ብሶል ሰሜኑ እሷው ናት።በየትኛውም የአልጋዬ ማዕዘን ራሴን ባሳርፍ ሕልሜ ውብ ገላዋን ይጎትታል ። ህልም የሚታዘዝላት ይህች ሴት ማናት? (ከሚጎትታቸው ውብ ገላዋ መሀል ያ ዳሌዋ ቀርቶብኝ እንደሆነ ጠዋቱ ይደማምንብኛል)

ይህን ዳሌዋን ምናቤ የትም ሆኜ ምንም ነገር ላይ ይስለዋል።
ታዲያ አንዴ የት ሳለው ጂኦሎጂ እየተማርን ሰሌዳው ላይ ፣ ታዲያ ሎሬት ሜትር አርቲስቱ፣ ምናቤ የሳለውን የልጅትን ሕቁር አልባ ገላ እየኮመኮምኩ ድንገት የመምህሩ ማጥፊያ የያዘ እጅ ግራ ቂጧ ላይ አርፎ ሳየው ምናባዊ ቅናት ለበለበኝ ።

"አቦ አትደብረኛ ! . . .ያንተ ጂኦሎጂ፣ የመሬት . . .የአፍር እና አለቶች ምርመራ ምናምን ... ይሄን ዘርቅ ወደዛ አቦ ..." ብዬ ምናባዊ ዘለፋ ወረወርኩ

የኔ ጂኦሎጂ ከልጅት ዳሌ ነው፤ ጅንን ዳሌ . . . በቃ ምን አለፋችሁ ጃን-ዳሌ አልኩት፣ ታላቅ ዳሌ እንደማለት ያለ ነው።የምዋምነው ይህ ተፈጥሮ የቸረቻት አምሐ አሳይመንት ተብሎ
ቢሰጠኝ ( አዎ individual ነው መሆን ያለበት!) ያበደ አርጌ ነበር የምሰራው።🙈🙈

መምህሩ ቀድሞኝ ጨረሰና ከክላስ ወጣን ። ከህነፃው ወርጄ ቀጠን የምትለውን የእግር መንገድ ይዤ ወደ ዶርም ስኳትን ልጅትን አየኋት ያ ስጦታዋ፣ ውበቷ ፣ አዳምን ሁሉ ማሰብ እንዲያቆም የሚያደርገው ያ ቂጧ የት ሄደ ?
ደነገጥኩ . . . ወይኔ እኔና ጂኦሎጂ በቂጧ ሰበብ ያቺ ሱሪ እንደመጋረጃ ቁልቁል የምትለቅ ፣ የተላገች ቂጤ ተቃጠለች። መዋመኔ ሁሉ እንደ ጤዛ ረገፈ ። ተዓምር አያልቅ. . . ያ ዳሌ የትገባ በጊዮርጊስ ??
በኋላ የጊቢው አዳም ሁሉ ሲፈልግ ሲፈልግ ከርሞ ያ ቂጧን የት አገኘነው? የጊቢው ቆሻሻ የሚቃጠልበት ቦታ በሲሶ እየተቀጣጠለ ያለ ስፖንጅ ሆኖ አገኘነው። 🙊🙊

የኋላ ኋላ ያንን ስፖንጅ ተጠግተን አየነው እንዳሉት ከሆነ ጡጫ የሚያክል ጉድጓድ በግራ ቂጧ በኩል መኖሩንና ምናልባትም አይጦች በልተውባት ሊሆን እንደሚችል መላምታቸውንም በዛው አስቀምጠዋል፤ ጥቂት የሚባሉ ተባዕት ተማሪዎች ደሞ በዛ አይጥ በበላችው ሽንቁር ዙሪያ ነጭ ነገር እንደሚታይና ይህም በኮላ ቂጧን መልሳ ለመጠገን ያደረገችው ሙከራ ውጤት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አያይዘዋል። ( አሂሂሂ! እኔስ እየጨሰች ያለች ቂጤን በምን ልጠግናት? ወይኔ እኔ !! ቂጧን ብዬ ቂጤን አጣሁ።)
ከዛች ቀን ቡኋላ ለልጅቷ ያለኝ መቁነጥነጥ ስርዓት ይዞ ሲቀመጥ አስተዋልኩ ።

ከሷ በኋላ ጃን ዳሌ ሳይ ጃን እስንፖንጅ አለመሆኑን እጠራጠራለሁ።

እና ሰሞኑን አይቼ የወደድኳትን ልጅም መጠርጠር ጀምርያለሁ ። (መቼም የሚፈርድብኝ አይኖርም) እኔ 4 ተኛ እሷ ደሞ 3ተኛ ዓመት ተማሪዎች ነን። ቆንጆ ናት ፣ ሀቅ ነው። ቀይ ናት ፀሃይ ከነካት . . .እፍ . . እፍ. . . እንደተባለ ረመጥ ይባስ ትቀላለች።

ባወራት ብዬ እመኛለሁ። (እሱ ገላሽ ሰፖንጅ ይሆንን ? ብዬ ልጠይቃት እንደሆን እንጃ) . . . ሰበብ አጣሁ . . . ደሞ በእኔ ባች የሆነ እዛው ጊቢ ውስጥ ወንድም አላት ። (አይወደኝ ይሆን እላለሁ፣ ውይ ግን ስወዳት ማርያምን) እንዴትም ብዬ ስልኳን አፈላልጌ የሆነ ፍቅሬን የሚገልፅ የፅሁፍ መልዕክት ስለማስቀመጥ አሰብኩ ። (ውይ በናትሽ አውሪኝ . . . አንቺን ማውራት ብቻ ያኖረኛል እኔን . .. የሚል ግጥም ልፅፍላት አማረኝ ) እንዳማረኝ ቀረ ብዕሬ ለሷ መንጠፉ ገረመኝ (ሳልወዳት አልቀረሁም)

በህይወትህ ያለህን ሁሉ ሚስጥር ከነገርከኝ ያንተ እሆናለሁ ብትለኝ ... አንድም ሳላስቀር በሰንጢው ምላሴ ሆዴን ዘረግፍላታለሁ። እወዳታለሁ ።

ባትወደኝም ቅር አልሰኝም ። እሷው ትሰኝ ምክንያቱም ከኔ በላይ የሚወዳት አይኖርም ። (የሚጠረጥረኝ ቢኖር በከንቱ አይድከም!!)

Body of a woman, white hills, white thighs,
you look like a world, lying in surrender.
My rough peasant's body digs in you
and makes the son leap from the depth of the earth.
◦ ◦ ◦
//'Body of a Woman//
pablo neruda
---------------🌸🌸🌸-----------

---------------------------------------
በእግዜር ይዣችኋለሁ አንብባችሁ ዝም አትበሉኝ የልጅቷን ስልክ ጀባ በሉኝ🙏🤣🤣🤣
--------------------------------------------


@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብርዬ)
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስነጥበብ መማር ለምትፈልጉ ሁሉ የወጣ ማስታወቅያ

.
.
@seiloch
-----------------------
ያፈቀሩ ነፍሶች ❖
------------------
//✍️ ናዊአብርሃም
//
(@nawi1)
//ነሐሴ 4/2012 ዓ.ም//
------------✦✣✦-------------
የሰንደሉ ጢስ ይግተለተላል። ስስ ደመና ይሰራና ደሞ መልሶ አየር ላይ ተፈትሎ ወደ ቀጭን ክርነት ይለወጣል፤ ቀጭኑ ክርም እየተበተነ ሄዶ ከነጩ ኮርኒስ ላይ ተንሳፎ ይሰወራል ።
በሌላኛው አልጋ ጥግ ደሞ ከተንቀሳቃሽ ስልኩ ለስለስ ያለ የዘሪቱ ዜማ ከጢሱ ጋር ተዋህዶ ሽቅብ ይተማል ።

" ያኔ ስንቀራረብ ደስታዬ ነበር ያንተ መሆኔ
የኔ መሆንህ መኖርህ ጎኔ
ያኔ ስወድህ አልጠረጠርኩም
ያኔ ስንተሳሰብ አልጠረጠርኩም
እንደምርቅህ
እንደምትርቀኝ
እንደምለይህ
. . . "

የደከመ ለቅሶ ይሰማል ፤ ከአይኗ የሚቀልጡ ፍል እምባዎች ጉንጮቿ መሃል ደርሰው ይረጋሉ ፤ በምፀት ስትስቅ ተሰነጣጥቀው ይረግፋሉ።
" በርቺ ሄዋን !! " ትላለች ። እንባ የቃላቶቿ ማፅኛ ፣ ሁለት መንታ እንባ ደግሞ የንግግሯ መደምደሚያዎች ሆነዋል ። የህሊናዋ ጩኸት ተከድኖ የነበረው አነደበቷን ደርሶ በረገደው ።

(። ይህ ምልክት ሁለት መንታ እንባ ነው)

" እሱ ማለት የውበቴ ጣዖስ፣ የህይወቴ ሮማን ፣ የትዝታዬ ከሙን ነው ። ትዝታው ቅመም ብቻ አይደለም፤ ልክ እንደ ባህር ነው፤ ረጋ ሲሉት ደርሶ ይፈላል። ናፍቆቱ ሲጠና በልቡ ልቤ ላይ የሚሳብ እፉኝት ነው።
ናፍቆቱ ይናደፋል ። ሳቁ ፣ ቡትቶ ልቤ ላይ የሚርመሰመስ ቅማንዥር ይሆንብኛል ። ፍቅሩ እነደ ሸለመጥማጥ የምናቤ ጢሻ ውስጥ የሚሽሎከለክ አውሬ ነው ። እሱ ላይ ቅንጣት ታክል አቅም የለኝም ።ፍቅሬ ለሱ ፍልፈልን እንደሚጋፈጥ መርዘ ከንቱ ጊንጥ ነው። ሌላ ብለምድ እንኳ ገላ መዋስ ነው ሚሆንብኝ .....አፈቅረዋለሁ። "

ሜሮኑ እንባዋ ከ ሰንደሉ ጢስ ጋር የፍቅር ሰቆቃዋን አዝሎ በበሩ አናት እየተጎተተ ወጣ ።

ነፋሳት እየተቀባበሉት ሄዶ ከወዳጇ ቤት የሲጋራ ጢስ ጋር ተላተመ። ይሄኔ ልክ እንደጢሶቹ ስሜቱ ተደበላለቀ።

ማልቀስ እየከጀለው ባዶ ወንድነት አፈነው ። መለያየት ልክ እንደሱ ላሉ ዳተኞች ሽቅብ ነው። ሲጋራውን መጠጠው ፣ ወረተኛ ሳንባው ጢሱን አቅፎ ገፋው። ሰውነቱ ደርሶ ይርዳል ፣ ልቡ ይናድበታል።

አይኑ እሷን ይስላል ። ምናቡ ያዳፈነውን ትዝታ 'እፍ! እፍ!' እያለ ይገልጣል።
የሰንደሉ ጢስ ሰሌዳ ላይ በሲጋራው የጢስ ብሩሽ እንዲህ ትዝታውን ይለቀልቃል።

● ● ●
ጎንደር ፋሲል ግቢ

' እንዳየኋት አልደነገትኩም ። በፍቅር ህይወቴ ውስጥ ትፈጠራለች ብዬ ከነመፈጠሯ የማላስታውሳት ሴት ነበረች ። ከፍቅረኞቿ ጋር ስትጣላ አቅፌ የማባብላት ፣ የማልቀናባት ወንድ ነበርኩ ። እንደ ወንድም ቀርባታለሁ እንዳልል የሚያግደኝ . . . በፍቅር ትፈልገኝ ይሆን? የሚል ጥያቄ ብቻ ነበር።

አብረን ክብረ በዓላትን ግራ ቀኙ ባለየለት መልኩ እናከብር ነበር ..እንጠጣለን ..እንጫወታለን እንሰክራለን ። ጨዋታዋ መቼም አይወራ ዕፀ መፍዙዝ ነው ፤ ስንኝ በጉንጯ ናት ፤ ግጥሟ ሁሉ አጃኢብ ነው።

እንደ አብዛኛው ሴቶች ረጋ ያለ ወንድ ላይ ማዕበል ናት። ስትቀርብ ልክ የላትም ፤ ፍቅር ከቶ የሚይዛት አትመስልም። ያጋጣሚ ሆኖ የፍቅር ክንድ አድቅቆኝ ' ፍቅር ይቅር! ' ብዬ መነሳቴ ነበር። እሷም እኔም ለፍቅር ልባችን አብጦ የፈነዳ ነበርን ።

እሷ ' ፍቅር ሴትን አይዛትም።' ባይ እኔም ብቸኝነቴን ደን አድርጌ እሸሸግበት የተጠጋሁ የፍቅር ሽፍታ!

ፍቅር ተዓምራትን ሳይታክተው ያበጃልና

ነገሮች ተቀየሩ ....' እኔ ' ስል እሷ የሚለው መጎተት ጀመረ ። ቤተሰብ ያወጣልን ስም አስጠላን ስንኳረፍና ስንጣላ ብቻ እንጠቀምበት ጀመር ። አልጠግባት አልኩ ፣ አልጠግበኝ አለች ። በጊቢው ጎዳና ዳር ያሉ አበባ እና ዛፎች በአጠገባቸው ስናለፍ ለፍቅራችን ያረግዳሉ ፣ በቅጠሎቻቸው ያጨበጭባሉ፤ ያፏጫሉ ።
"አባ ሳመኝ ?" እስማታለሁ ። የማያፍር ፍቅር እነዴት ደስ ይላል!

ቀጫጭን እጆቿን ወገቤ ላይ ታስራለች ደሞ ትፈታና ሮጥ ብላ ቀድማኝ ወደ እኔ ዞራ ትዘፍናለች ። ትቀብጣለች ። ታሳሳለች። (ትናፍቃለች...)
ቀጥለን ወሬ እየቆረስን ቡና እንጠጣለን። ( ቁጭ ብለን ባወጋንባቸው ቦታዎች ስሜን ትፅፋለች ፤ የልጆቻችንን ስም ትፅፋለች ።)

....ነፋስ እያካለበ አምጥቶ የለጠፈባትን ቅጠል ከፀጉሯ ላይ አንስቼ ግንባሯን እስማለሁ ፤ ቀዝቃዛ ወራት የጣሉትን የዝናብ ጠብታ ከከናፍሯ ላይ በከንፈሬ እለቅማለሁ። አጭር ቁመቷን በክርኔ አግዤው አንጋጥጬ እስማታለሁ። ደሞ ተንሸራታ ቁልቁል እስማታለሁ ። ቂጧን ጨብጣለሁ ፤ ጡቷን እነክሳለሁ ።

' አበድኩልህ !' ትበል እነጂ አብጄ እነደቃተትኩላት ትዘነጋለች።
የፍቅር ጥም ሲለበልበን ከጊቢ እንወጣለን ።
እበደት ለአፍታ ይገታል። ወይ እሷ ! ወይ እኔ! '
.
.
ቤቱ ቁጭ ብሎ ሲያስብ ጊቢ ሲመለስ ከፍቅሩ ጋር የተመላለሰባቸው መንገዶች ፣ ቁጭ ብለው ያወጉባቸው ስፍራዎች ለብቻው እንዴት እሾህ የተበተነባቸው እነደሚሆኑበት ሲያስብ ... ክፉኛ ልቡ ይርዳል።

" she gave me peace
in life time of war ..... "
I miss her, all day and night!!!

----▪️▪️▪️◈◈✣✣✣◈◈▪️▪️▪️----
--------------------
@Abelard1
--------------------
●●●

@wegoch
@wegoch
@wegoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
beki፪፬ Get፩፪:
" እ............ናት"


በዚህ ምድር ላይ ትዝታ የሚባለው ነገር ብትፈልገውም ባትፈልገውም ከአይምሮህ አውልቀህ የምትጥለው ነገር አይደለም፡፡ የሚገርመው ደሞ በተለይ መጥፎ ትዝታ ከሆነ ለምን እንደሆነ ባላውቅም የምታየው ፤ የምትሰማው ፤ የምምትበላውና የምትጠጣው ሁሉ እሱን ያስታውስሀል፡፡

ትዝታ ቢሸሹት የማይሸሽ ፤ ቢርቁት የማይርቅ ጥላ ነው፡፡ እኔም ብሸሸው ከማይሸሸኝ ጥላዬ እየራኩ ጅል መባልን አልፈለኩም፡፡ምንም እንኳ የሚያኮራ ታሪክ ባይኖረኝም ትዝታዬን መፃፌ ግን ለውጥ እንደሚያመጣ ስለገባኝ ብዕርና ብራናዬን ዘረጋሁ፡፡

በ14 አመቴ ነበር እንደ ጓደኞቼ ወጣ ወጣ ማለት ነው የጀመርኩት፡፡ አንዲት ወጣትነቷን እያገባደደች ያለች እናት አለችኝ፡፡ አባቴን ከነመፈጠሩም አላውቀውም፡፡ እስከዛሬ እሱን እንድፈልገው የሚያደርገኝ ነገር ስላላጋጠመኝ አባቴስ ብዬ አንስቼባት አላውቅም፡፡ እናቴ ብቻዋን ያለደጋፊ ስታሳድገኝ በአቅሟ የማታደርግልኝ ነገር አልነበረም፡፡
"ልጄ ታውቃለህ እግዛብሄር ስለነገ
እንድጓጓ ሲፈለግ የሁሉ ነገር መፅናኛዬን አንተን ሰጠኝ፡፡ የኔ ልጅ ተስፋዬኮ አንተ ብቻ ነህ ፤ የሰው ልጅ ተስፋ የሚያደርገው ነገር ሳይኖረው በምድር ላይ መንቀሳቀስ የማይችል ብቸኛ ፍጡር እንደሆነ እወቅ፡፡ ምናልባት ምንጩ ከየት እንደሆነ በማይታወቅ ብር በፀሀይም በጨረቃም የሚቅሙና የሚያጨሱ ሰዎችን አይተህ 'እነሱ ያለ ተስፋ እየኖሩ አይደል? ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል ፤ አመነኝ የኔ ልጅ እንደ ወይራ ከሚጨሰው ጭስ ጀርባ ቅንጣት የምታክል ተስፋ አትጠፋም ፤ ፈጣሪ ደሞ እንኳን ለኛ ለደካሞቹ ይቅርና ፃድቁ ኖህን እንኳን ያለተስፋ አልተወውም" አለችኝ በ'ናትነት አንደበት፡፡ ይህን ሁሉ ነገር አለምክንያት አልነበረም የተናገረችው፡፡

በጠዋት ከቤቴ የወጠሁት ትምርት ቤት ለመሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሰፈሬ ገና ሳልወጣ በ5 በ6 አመት የሚበልጡኝን ጓደኞቼን አገኘዋቸው፡፡ ሁሉም ዩኒፎርማቸው አውልቀው ወደ ፑል ቤት ሊሄዱ ሲሉ ነበር ያገኘዋቸው፡፡ " አንተ ፋራ ነህ እንዴ ሳምንት ከሳምንት ክላስ ምትገባው ? ፤አስተማሪው እራሱ እንዳንተ ከሰኞ እስከ አርብ አሄድም እኮ" አሉኝ ተራ በተራ ኋላ ቀርነቴን እየነገሩ፡፡ የዛን ቀን እኔም ዩኒፎርሜን አውልቄ አብሬአቸው ወደ ፑል ቤት ሄድኩ፡፡ ሁሌ ሰው እንዳያውቅብን ፑል ቤት እንላለን እንጂ ፑል ልንጫወት አልነበረም የምንሄደው ፤ ከፑል ቤቱ ጀርባ በኮሽም የተከበበ ቦታ ላይ ድንጋይ ደርድረን እንቀመጥና ከየት እንደሚያመጡት የማላውቀውን ሲጋራና ሀሽሽ እናጨሳለን፡፡ ታዲያ ይሄን ጊዚ እናቴ ተከትላኝ እንደወጣች አላወኩም ነበር፡፡ ሲጋራውን ጣትና ጣቴ መካከል አርጌ አፌ ውስጥ ስከተው እጅ ከፍንጅ ያዘችኝ ፡፡ " የኔ ልጅ ና ተነስ ወደ ቤት እንሂድ" አለችኝ፡፡ሲጋራ ለሷ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት እንሆነ አውቃለው፡፡ እቤት ከገባን ቡሀላ በተረጋጋ መንፈስ ልክ ምንም እንዳላጠፋሁ ተስፋዋ እንደሆኑኩ ትነግረኛለች፡፡
መረጋጋቷ ሁሌም ያስፈራኛል ግን አንድም ቀን ፈርቻትም ሆነ አክብሬአት የምታዘኝን ነገር እሺ ብያት አላውቅም፡፡ የራሴን ልብስ ለማጠብ በጀርባዋ ጀሪካን ተሸክማ እያየዋት ፤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ለአፌ እንኳን ላግዝሽ አልላትም ነበር፡፡ ሁሌም የሚገርመኝ እንደ እናት ከአንገቷ እንኳን ለምን እንደማትረግመኝ ነው፡፡

አንድ ቀን እግሬን ዘርግቼ ቴሌቪዥን እያየው ሳለ አይኗ ደም መስሎ ጉንጮቿ ቀላልተው ሰላም ሳትለኝ ያረጀች ሶፋችን ላይ አንገቷን ደፍታ ተቀመጠች፡፡ ምን ሆና እንደሆነ ማወቅ ፈልጌአለሁ ፤ ነገር ግን አጉል ጉርምስና ይዞኝ ዝም ብዬ ተቀመጥኩ፡፡ ትንሽ እንደቆየን እንባዋ መሬት ላይ ይንጠባጠብ ጀመር፡፡ አሁንም ምንም አልተነፈስኩም፡፡ አይኗ ወደሷ እንድዞር ይጎትተኝ ጀመር፡፡ እንደምንም ፊቴን ዘወር ሳደርግ አይናአይኔን እያየች ማልቀስ ጀመረች " አሺ ምን ላርግ የኔ ልጅ? አንተን ለማሳደግ የማልፈልገውን ሁሉ ሆንኩ ፤ አሁን ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም ፤ አዎ በብሩ ተማምኖ ሊደፍረኝ ሲሞክር ዝም ማለት አልቻልኩም" አለችኝ፡፡ ከስራም ሌላ ቦታም ጭምር እንዳትቀጠር አድርጎ እንዳባረሯት እንደ ህፃን እያለቀሰች ነገረችኝ፡፡ ምንም ሳልናገር ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ወደ'ናቴ መስሪያ ቤት መሄድ ጀመርኩ፡፡ እናቴ እንደሁልጊው ድምፇን ላለመስማት የወጣው መስሏት እንደተቀመጠች ማልቀሷን ቀጠለች፡፡ አኔ ደም እንደጠማው ያንቀዠቅዠኝ ጀመር፡፡ እንደመሮጥም እንደመራመድም እያልኩ የመጀመሪየውን አስፓልት በደመነፍስ አለፍኩት ፤ ሁለተኛው አስፓልት ላይ ለመድረስ ሶስት እርምጃ ብቻ በቂዬ ነበር፡፡

ከ አንድ ወር ከሳምት ቡኋላ እራሴን አንድ አልጋ ላይ አገኘውት፡፡ እናቴ ወንበር ላይ ተቀምጣ በእግሬ በኩል አንገቷን ጋደም አድርጋ ተኝታለች፡፡ መልኳ ፍፁም ተቀያይሮብኛል ፤ ሰውነቷ ብዙ ቀን ምግብ እንዳላገኘ ያስታውቃል ፤ ከንፈሯ እንደ ሞተ ሰው ነጭ ሆኗል ፤ ምን ሆኜ እንደሆነ ማወቅ ፈልጌአለሁ ፤ ከዛ በፊት ግን ጉሮሮዬ በጣም ስለደረቀ ውሀ መጠጣት ነበረብኝ። አጠገቤ ሀይላንድ ውሃ ተቀምጧል ፤ እናቴን ከምቀሰቅሳት አልኩና እጄን ለማንቀሳቀስ ስሞክር ጣቴ ብቻውን ይንቀሳቀሳል፤ በድጋሚ ለማንሳት ሞከርኩ አሁንም ጣቴ እንጂ እጄ ጠቅላላ ንቅንቅ አልልም አለኝ ። ደንግጬ እናቴን ለመጥራት ስሞክር ምላሴ ተሳሰረ ፤ቃላቶችን ከአፌ ማውጣት አልቻልኩም። ወስጤ ትንፋሽ እንዳጠረው ሲወጣጠር ይሰማኛል ። እናቴን ከእግሬ ላይ ለመቀስቀስ ስጥር እግሬ ከታፋዬ ጀምሮ ምንም መልስ አይሰጠኝም ። አሁን ሀይሌና ጉልበቴ እንባዬ እንደሆነ ተረዳሁ ። ማንም ሊሰማቸው የማይችላቸውን ቃላቶች ማውጣት ጀመርኩ ። እናቴ ከተኛችበት ተነስታ መጀመሪያ እያለቀሰች የነበረች ይመስል አይኔን ስታይ እንባዋ እንደጎርፍ ይወርድ ጀመር ። ግንባሬን ፤ እጄን ፤ ጉንጬን ፤ ከንፈሬን የማትስመኝ ቦታ አልነበረም ፡፡ የሷ እንባ ከኔ እንባ ጋር ተዳምሮ ፊቴን አራሰው ። እሷ አቅፋኝ እኔ ጠልቻት አላቅፍም ያልኩ ይመስል እጄን ዘረግቼ እየተላቀስን ሳለ ዶክተሩ ህመምተኞችን ለማየት ሲገባ ተመለከተን።
" ምን ሆነሻል ወ/ሮ ውቢት ያን ሁሉ ነገር ተነጋግረን እንዴት እንደዚ ታደርጊያለሽ" አለና ከደረቴ ላይ አነሳት ።ምን እንደተነጋገሩ ማወቅ ፈለኩ ግን እንዴት ብዬ ልወቅ፡፡
"ዛሬ ወይም ነገ ወደቤቱ ይዘሽው መሄድ አለብሽ፡፡ እዚ መተኛቱ ምንም የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም፡፡ ይልቅ ከዚ ቡኋላ ዊልቸር ስለሚያስፈልገው አሱን መግዛት ይኖርብሻል" አላት የተኛው ስለመሰላቸው አጠገቤ ሆነው ነበር ሲያወሩ የነበረው፡፡

አንድ ቀን እንደ ልጅ አዝኜላት የማላውቅላት እናቴ ስለኔ እንባዋን እያፈሰሰች ትናገራለች፡፡
"ዶክተር..... አኔኮ አሁን እቤት ሲገባ የማበላው ምግብ እንኳን የለኝም ፤ ሌላው ቀርቶ የቆሸሸ ልብሱን እንኳን የማጥብበት ሳሙና የለኝም አኮ ዶክተር" ቀን በቀን የምታለቅስበት ድምጿ ተዘግቷል፡፡
እኔ ላልቅስልሽ እናቴ ፤ እኔ ልሰቃይልሽ ብዬ ላፅናናት እፈልጋለው ግን እንዴት ብዬ፤ በዚ በኩል ህሊናዬ ይኮሮኩመኛል
' ፈጣሪ ጤናና ጉልበቱን ሰቶህ አይዞሽ ያላልካት ሰውዬ ዛሬ ሁሉን ሲነሳህ ነወ ስቃዯ የታየህ? ' ይለኛል፡፡
'ምናለ..... ያኔ እንደጠላት ስገላምጣት ህሊናዬ በኮረኩመኝ ኖሮ ፤ ምናለ አንዴ እንኳ ......አንዴ እንኳ ከአፌ እሺ የሚል ቃል አሰምቻት አንደበቴ ቢዘጋ 'ብዬ ተመኘው፡፡
"እሺ ወ/ሮ ውቢት እኔ የላዳና ለትንሽ ቀን የምቶን ገንዘብ እሰጥሻለው። አንቺ ግን ዊልቸሩን መግዛት ካልቻልሽ አንድ ማድረግ ያለብሽ

ነገር አለ" አላት፡፡ እንባዋን እንድጠራርግ በሰጣት ሶፍት አይኗን እየጠራረገች " ለልጄ ምንም እንደማደርግ ታውቃለህ ዶከተር .....ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?" አለችው፡፡ ተስፋ
በማያጣው አይኗ ዶክተሩን እያየች፡፡
"ከምንም ጊዜ በተለየ አሁን ልጅሽን በደንብ መረዳት ይኖርብሻል ፤ ምክንያቱም እንዳይናገር አንደበቱ ተዘግቷል ፤ ተራምዶ የሚፈልገውን ነገር እንዳያደርግ እግርና እጁ ፓራላይዝድ ሆኗል ፤ ስለዚህ እንድ ልትግባቡበት የምትችሉበት መንገድ ጭንቅላቱና ጭንቅላቱ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ እንድትሰጪው የሚፈልገው ነገር ካለ በአይኑና በቅንድቡ በመጠቆም ሊያሳይሽ ይችላል ፤ የማይፈልገው ነገር ካለ ደሞ ጭንቅላቱን በመወዝወዝ ሊነግርሽ ይችላል፡፡" አላትና ከኪሱ ብር ቆጥሮ ሰጣት ፤ እሷም አመስግና ተቀበለች፡፡ እናት ከመፅዋችነት ወደ ተመፅዋችነት ስትዘዋወር እንደማየት የሚያም ቁስል የለም፡፡
"ስለዚ አሁን ታክሲ ይዤ መጥቼ ወደቤት ይዤው መሄድ እችላለው?"
"አዎ በደምብ ትችያለሽ" አላትና ወደ ሌላ ህመምተኛ ሄደ፡፡
እሷም ወደኔ ተመለችና ግንባሬን እየሳመች "አሁን ቶሎ ተመልሼ እመጣለው እሺ የኔ ልጅ" አለችኝና በድጋሚ ግንባሬን ስማ ሄደች፡፡

ከዚ ቡሀላ ምናይነት ሂወት እንደሚኖረኝ እያሰብኩ ሳለ ብዙም ሳትቆይ እናቴ ተመልሳ መጣች፡፡
"በቃ የኔ ለጅ ታክሲ የዤ ስለመጣው ወደ ቤት እንሂድ" አለችኝና ከወገቤ ቀና አድርጋ እግሬን ወደመሬት አወረደችው፡፡ አግዙኝ እንኳን ሳትል እስከዛሬ ሸክም የሆንኩባትን ልጇን ልትሸከመኝ ነጠላዋን ወገቧ ላይ ስታስር ሳይ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡
" ለምን ታለቅሳለህ የኔ ልጅ ወደ ቤት ልንሄድ እኮ ነው፤ እባክህ አታልቅስ" ትለኛለች እንባዬን ከጉንጬ ላይ እየጠራረገች፡፡ እኔን ለማፅናናት ትስቃለች... አይኗ ግን እንባን እንደ ምንጭ ያፈልቃል፡፡

እግሯን ሸብረክ አርጋ ከወገቧ ዝቅ አለችልኝ፡፡ ለልጇ ዝቅ ማለት የማይታክታት እናት.......
እጅና እጄን በትከሻዋ አሳለፈችና እንደ ህፃነቴ በጀርባዋ አዘለችኝ፡፡ ሆስፒታል ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ በኔ እያዘኑብኝ ይሁን ለ'ናቴ እያዘኑላት ይሁን.....ከንፈራቸውን ይመጣሉ፡፡

ቤታችን በር ላይ ስንደርስ ሹፌሩ ከመኪናው ወርዶ አቅፎ ሲያስገባኝ ጓደኞቼ ሁሌ የምንቀመጥ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው አየዋቸው፡፡ የኔን አይን ተከትላ እናቴም አየቻቸው፡፡ አንዳቸውም ግን ከተቀመጡበት አልተነሱም ነበር፡፡ ሰውን ሰው መሆኑን የምትለየው በችግርህ ጊዜ ነው....... ትለኝ ነበር እናቴ፡፡

እቤት ገብተን ጤነኛም ሆኜ እተኛባት የነበረችው አሮጌ ሶፋችን ላይ አስተኙኝ፡፡ ለሁለት ቀን ያህል በየደቂቃው እየመጣች እንደራበኝና ሸኖ ቤት መሄድ እንደምፈልግ ትጠይቀኛለች፡፡አሁን ከቤታችን ብዙም የማይርቅ ሻይና ቡና ቤት ውስጥ ስራ ልትጀምር ነው፡፡ ነገር ግን እኔን ለማን ጥላ ልትሄድ እንደሆነ ግራ ገብቷታል፡፡

ጠዋት ተነስታ ቁርሴን አብልታ ልብሴን መቀያየር ጀመረች፡፡ምን ልታደርግ እንደሆነ አልገባኝም፡፡
"የኔ ልጅ አሁን አብረን ስራ ቦታ እኔዳለን እሺ፤ በዛውም ትናፈሳለህ" አለችኝ፡፡ ጥለሽኝ ሂጂ ማለት አልችልም ፣ ስራ መስራቷ ደሞ ግድ ነው፡፡

ትንሽ ስትጎዳጎድ ከቆየች ቡኋላ ብር የሌለው ቦርሳዋን በእጇ ይዛ እንደለመደችው ጀርባዋን ሰጠችኝ፡፡ ውሀና ዱቄት ሲሸከም የኖረ ጀርባ ዘንድሮም ድንጋይ ከመሸከም የሚያድነው ሰው አጣ፡፡ የበደሌ ቅጣት ከዲያብሎስ ቅጣት በልጦ ሳይ እስከዛሬ እናቴ የምትነግረኝ ተስፋ እንደ ገለባ በኖ ሲጠፋ ታየኝ፡፡

እናቴ እኔን በመሸከሟ ምን እንደሚያስደስታት አለውቅም ፤ የሷን ደስታ ያህል ታቦት የሚሸከሙ ካህናት እንኳን ደስ የሚላቸው አይመስለኝም፡፡ የሷን ደስታ ተቃራኒ የኔ ልብ እንደ ትኩስ ቁስል ይደማል ፣ ለንስሃ እንኳን የማይሆን ማርፈድ እንዴት ሰው ሊያረፍድ የችላል?፡፡

ተሸክማኝ ሄዳ ተሸክማኝ ትመጣለች ፣ እኔን ተሸከማ ስራ መመላለስ ከጀመረች ሁለት ወር አለፋት፣ ቅጣቴ በእንባዬ ይካስልኝ ይመስል ጀርባዋን በተደገፍኩ ቁጥር ማንባት ከጀመርኩ እኔም ሁለት ወር አለፈኝ፡፡

እንደተለመደው አኔ ድንጋይ ልጇን ተሸክማ ከስራ ከተመለስን ቡኋላ ልብሷን ልትቀያይር ወደ ጓዳ ገባች ሁሌም ልብሷን ስትቀይር መጀመሪያ መጋረጃ ትጋርዳለች፤ ለወትሮ ግን መጋረጃውን ከድካም ብዛት አልጋረደችውም ነበር፡፡

........ሹራቧን አወለቀችው ፤ ቲሸርቷን አወለቀችው ፤ ጀርባዋ ጠቅላላ ቆስሏል ፣ ባንድ በኩል ሲላጥ ሲደርቅ ሲላጥ ሲደርቅ ጠባሳ የሆነ ጀርባዋን ባዝሊን ትቀባለች ።

' ሞትን ይመኟታል ነገር ግን ማንም አያገኛትም ' የተባለው ቃል በኔ እንደተፈፀመ ገባኝ ፤ ምክንያቱም እራሴን ለማጥፋት እንኳን ምንም አይነት ጉልበት የለኝም፡፡ አይኔ እያየ የናቴ ጀርባ ከመቁሰልም አልፎ ሲጎብጥ እንደማየት ምን ሞትን የሚያስመኝ ነገር አለ?፡፡

ከአንድ አመት ቡኋላ ቀን በቀን እየሞትኩ ስለነበረውና ስላለው አሳፋሪ ታሪኬ እንድፅፍ ነው መሰለኝ ቀኝ እጄ ተፈታ ። እናም እናትህን ለምታንገላታ ፤ እናትህን ለምትገላምጥ ላንተ ፤ ስያሜ ታቶላት"" እ'........ናት የተባለችውን ሴት እንደኔ እንዳታደርጋት ይሄን ፅሁፍ ፃፍኩልህ፡፡


(የጌትነት ልጅ)
(@mar_yamye)

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
#ህዩድ
፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲

ናዊአብርሃም
( @nawi1 )

፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬፬

ዛሬ ያለወትሮዬ በጠዋት ከአልጋዬ ወርጄ ፊት ለፊቴ ያለችው ትንሽዬ የመስታውት መስኮት አጠገብ በባዶ እግሬ ሄጄ ቆምኩ ። የክፍሉ ወለል እጅግ ይቀዘቅዛል ። (ቢሆንም ከልቤ ቀዝቃዛ መውጅ አይበልጥም ) ስሱን ደብዘዝ ያለ ሰማያዊ መጋረጃ ገለጥኩ ፤ ከመስኮት መስታወቱ ወዲያ ያካፋል።(ከመስታወቱ ወዲህ ግን ልብ የሚሰነጥቅ መብረቅ ያጀበው ዶፍ ይጥላል።)
መስታወቱ ላይ ነቁጥ የዝናብ ጠብታዎች እዚህም እዚያም ተበትነዋል።

ትንሽ ፈንጠር ብሎ ካለው አንድ ለጊቢው የሆነ የፅድ ዛፍ መርፌ ቅጠሎች ላይም እኚሁ ነቁጥ የውሃ ኳሶች አሉ።( ዛሬ ግን ወትሮ እንደማያቸው የገና ዛፍ መብራቶች አልመሰሉኝም ፣ይልቁንም ዛሬ አብረውኝ እያነቡ ይመስላሉ።) ሳቢ የኔ መልካም ሰው . . .

ሀዘኔን መርሳት አልቻልኩም፣ የምርም ብቻዬን ነው ያለሁት ) ሳቤላ የኔ እናት ፣ የኔ መምህርት ፣የኔ ሕቱም ፍቅር ፣ ቀሚስሽን ይዤ አብረን የኳተንባቸውን መንገዶች ወጥቼ ላፈጥባቸው እፈልጋለሁ ።

ግን ዳንዎቻችንን መንገዶች ዘንግተዋል ፣ ዝናብ አጥቧቸዋል፣ ሌሎች ተረማምደውበታል፣ በአውራ ጎዳናው የፃፍነው ታሪክ ላይ ሌሎች ታሪካቸውን ደርበው ፅፈዋል። (ልቤ ላይ ግን ሌላ ታሪክ ላይደረብ ተከትቧል። ቢደረብም ድምቀቱ ይረታል።)

ከቤት እግርሽ ሲወጣ አብረን የምንከተል ንስቲት ውብ አልቦዎችሽ ፣ ዛሬ ላይ የእግሮችሽን ነቢር መነጠቃችን ከጎዳናው እንድንርቅ አድርጓል።
ቆይ እኔ 'ምልሽ እማ . . .

"የትዕዛዛቴ ሀሉ ማሰሪያዉ ፍቅር ነው ።" ያለ አምላክ እንዴት ወላጃችንን ፣ አንቺን ባከበርን ፣ በወደድን እንዲሁም በታዘዝን መናችን ፍቅርሽን ይነጥቀናል ? ስለምን ይቀማናል ? በፋንታው ማንን እንካችሁ አለን?

እኔ እሱን አልወድም፣ እኔ ቀማኛ አምላክ የለኝም። እኔ ለሱ አለሰግድም ፣ እንደውም ሀልዮቱን ክጃለሁ ። የትኛውም ቄስ መጥቶ ሥርዓተ ቄደር እንዲፈፅምልኝ አልፈልግም። ንስሀም ከቶ አልገባም።
ልቤን በቁሜ ነጥቆ ፣ እምቡዝ አድርጎኛል። እኔ በጭራሽ ማረኝ አልለውም። ሲያሻው ገሃነም ይወርውረኝ ። እማዬ ፣ የኔ ሳቤላ ናፍቀሺኛል . . . ናፍቀሽናል።
ባንቺ ብዙ አነባሁ ፣ ሀዘኔን መቋጫ አጣሁ ።

ቤተሰቡ ተከትሎሽ አንቀላፋ፣ በቁሙ አንቀላፋ። ባዶ ሆነን ራሳችንን አገኘን ።

ልቤ ከልቧ ከልብ የሆነ መልስ ትሻለች።
ብዙዎች እንደሚሉት ይሄን ልቤን ለተጫናት ሀዘን እውነት መድሃነቱ ጊዜ ብቻ ነው? እውን ልክ ናቸው? እንጃ እኔ አልመስልህ ብሎኛል። ኡፍፍፍ . . . ፍፍፍ. . ሁሁሁ!! ታመምኩ እማዬ. . .

ያለፈው ወር ትክ ብለሽ ታይው የነበረው ፣ እንደ ልጅሽ መመንደጉ ገርሞሽ ትነካኪው የነበረው ፅጌሬዳ፣ አበባው እንባ አቅሯል። ግዑዝ ሁሉ አብሮኝ እያነባ ይመስለኛል።

የአምስተኛ ክፍል ውዳኤ መንፍቅ ላይ ለባቢ ገዝተሽ ማንበብ የጀመርሽለትን ያ እንደውም " አስደናቂው የይቅርታ ቅርስ" የሚለው መፅሐፍ? . . . እሱን መፅሃፍ አንብቤ ጨረስኩለት እኮ. .

አኔት፣ ሉሲየን፣ ዳኒ ሁሉም ደስ ብለውታል ፤ ጓደኞቹ ሆነው ነበር ግን መፅሃፉን ስጨርስለት ተጠፋፉ መሰል እራሱ ደግሞ እያነበበው ነው ። በተለይ ዳኒ ይናፍቀዋል፣ እሱን ስለሚመስለው ይመስለኛል፣ ትዝ ይልሽ የለ? የዳኒ እናት እሱን በወሊድ እያለች መሞቷን አንቺ ነበርሽ ያነበብሽለት።

ያኔ አጠገባቸሁ ፊዚክስ እያጠናሁ ቀልቤ ግን ከእናንተው ጋር ነበር። ኧረ ከዛ ቡሃላ ስንት ነገር ተፈጠረ መሰለሽ ዳኒ ገደል ወድቆ . . .ግን ተርፏል። አኔት እህቱ የቤቱ ስራ አጨናንቋት ተሰቃየች ።ብቻ ግን ደህና ናቸው።እኛም ደህና ነን።

እማዬ . . . መፅሃፉን የፃፈችው 'ፓትሪሺያ ሴንት ጆን' ደሞ ሴት መሆኗን ማህሌት ነግራው. . ." እኔ ደሞ የማዬ ዘመድ ነው ምትመስለኝ!" አለን። ያህን ሉጫ ፀጉሩን እያሻሸ . .

"ለምን?" ብላ ስትጠይቀው

" ትመስለኛለች፣ ፀጉሬን እየነካካች የምታባብለኝ . . .ነገር . . . " ብሎ ዝም አለ።

እውነት አለው! አንቺ የህይወት ኑረት ውስጥ እንድንበረታ የፃፍሽልን ነው 'ሚመስለኝ ፣ እኔም በበኩሌ ፀሃፊዋ አንቺ ትመስይኛለሽ። የኛ ሳቤላ ፣ የኛ ደራሲ።

አባዬ ደሞ ያ እረፍ ብለሸው የተወውን ነገር ተደብቆ ያደርጋል። ሳያየኝ ፣ እኔ ግን አይቼዋለሁ።
እኛን ሲያይ አንቺ እንዳለሽ ሁሉ ለመሆን ይታገላል። ሊያስቀን ይሞክራል ፣ ማሂ እና ባቢ ዝም ይሉታል። እንዳይደብረው ብዬ ትንሽ ፈገግ እላለሁ። እቤት ብዙ አይቀመጥም። ከስራ መጣ ወይ ይተኛል ፣ ወይ ደሞ ሰፈር ውስጥ ከሙሌ ፊልም ቤት ፊት ለፊት ካለችው ግሮሰሪ ገብቶ ይቀመጣል። አንዳንዴ ከ"ቲቶርያል" ክላስ ደንገዝገዝ ሲል አምሽቼ እመለሳለሁ፤ እናም በግሮሰሪው በኩል ሳልፍ ካለ ጠርቶኝ
እንድጠብቀው በእጁ ምልክት ይሰጠኛል ፤ ከዛ አብረን ቤት እንገባለን ።

የሆነ ቀን ውድቅት ላይ እያጠናሁ
ምን ተፈጠረ መሰለሽ . . . ከመኝታ ክፍላችሁ የቀዘዘ ማቃሰት የሚመስል ድምፅ ሰማሁ። በመጀመሪያ አባዬ በእንቅልፍ ልቡ ነው ብዬ ትኩረቴን ወደማጠናው ትምህርት አዙሬ ነበር። ነገር ግን ይሄ ድምፅ ቀደም ከሰማሁት ድምፅ ትንሽ ከፍ ብሎ ተደገመ። ይሄኔ ግራ ተጋባሁ ፣ ማታ ማሂ እራት አቅርባልኝ በልቼ፣ በለሊት ተነስቼ ለማንበብ ስል በጊዜ ነበር የተኛሁት፤ ከአባዬ ጋር አልተገናኘንም ነበር።

ሁሉም ተኝተው እኔ ብቻ የነቃሁ መስሎኝ ነበር። ማሂ ከመተኛቴ በፊት ከለሊቱ 10:00 እንደቀሰቅሳት ነግራኝ እንደተኛች ነበር። ባቢም ተኝቶ ነው ከጎኑ ተነስቼ ወደ ሳሎኑ ጠረጴዛ እና ወንበር ያመራሁት።

ለሶስተኛ ጊዜ ያህ የመዛበር ድምፅ ከመኝታ ክፍላችሁ መጣ።

" ምንድን ነው? አባዬ የት ነበር ማታ ? የኛን ሳቤላ ገና በአንድ ወሯ . . . እንዴት ? "ብዬ በንዴት ጦፍኩ።

ቀጥ ብዬ ወደ ክፍሉ አመራሁ ። ልክ ክፍሉ አቅራቢያ ስደርስ

" ሳቢ የኔ! . . .የኔ እ.....ና ..ት !! ምነው ጥለሽን . . . የኔ አመለወርቅ . . ምን ልሁነው . . ."

የአባዬ የለቅሶ ሲቃን ሰማሁት።

አባዬን ከቀብርሽ ዕለት ቡሃላ ሲያለቅስ ማግኘቴ ይሃ ሁለተኛዬ ነበር። (ለአባዬም ለልጆቹም እናት ነበርሽ) ወደ ወንበሬ ተመልሼ ስቅስቅ ብዬ አነባሁ። አባዬን አግባብ ባልሆነ መንገድ መጠርጠሬም ጭምር አስለቀሰኝ።

ሳያየኝ ሲያደርግ አየሁት፤ ያልኩሽንም ማሂ መኝታ ክፍላችሁን ስታፀዳ አግኝታበት ነበር፤ የሲጋራ ቁርጥራጮች ክምር።

"አማኔ !! "

"አቤት ማሂ! "

"ቁርስ ደርሷል።"

(መጣሁ ሳቢን መሳይ ፣ መጣሁ እታለሜ።)

መስኮቱን ዘግቼ፣ ስሱን መጋረጃም መለስኩ።
ክፍሉ እንደመጨለም አለ።
◦ ◦ ◦
07/09/2013 ዓ.ም
--------------------------------------------

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
ወድጄ እኮ አዉቃለሁ። 'ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ፍቅር ደርሶብኛል' ይል የለ
ከያኒዉ። የእዉነት!! ብዙ ጊዜም የወደድኩ መስሎኝ ከስሜቴ ጋ ድብብቆሽ
ተጫዉቼ ያለፍኩባቸዉ ጊዜያት ቁጥር አልባ ናቸዉ። የመጣዉን ጊዜ ሳየዉ
ያለፈዉ ቀላልነቱ በደንብ ታየኝ። ብዙ ጊዜ ለመዉደድ አልታገልም። ለመወደድም
እንደዛዉ። ዝም ብሎ ፍስስ ... ልስልስ ያለ ነገር እወዳለሁ። መያያዝ እንጂ
መተናነቅ አይስበኝም። ከተወኝ ጋ ፊትህን መልስ ብዬ ዳኛ ፊት አልቆምም።
እንዲያዉም እንዲያዘልቅለት ፣ በመሄዱ እንዳይቆጭ ሱባኤ እገባለት ይሆናል።
ሂሂሂ! መታገል ያደክመኛላ!! ከወደደኩት ጋ መቋሰል አልሻም። መድሐኒቴ ብዬዉ
ከነበረ ሰዉ ህመም አልሸምትም። ሲደላ ብዙ ነገር ቀላል አይደል? ትዉት
ሲያደርጉት ትዉት ፤ ራመድ ሲሉ ሰበር ሰካ አይደል የሚሆነዉ? ቢኳሉት ድምቅ ፣
ቢለብሱት ስክት ይል የለ? ይገርማል። ዉስጣችን ስንት የተሸመነ ስሜት ያላቸዉ
ማንነቶችን ይዘን እንደምንዞር። ቀላል ነዉ ያሉት ከአለት ሲጠነክር ምን ይሉታል?
...
የመጀመሪያዎቹ ሰሞን እንደ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ትከሻ ለትከሻ ተሻሽቶ
የማለፍን ያክል ነበር ቅርርባችን። ከሁለት ምልልስ ያልዘለለ ሰላምታ ብቻ።
ስንቆይ እንደ ጆንያ ያለ እህል እንደማይቆመዉ ያለፈገግታዉ መቆም አቃተኝ።
ከእናቷ ተለይታ እንደምትያዝ ጥጃ ሲለቋት ወደ እናቷ ጡት እንደምትሮጠዉ፤
ነግቶ ምድር ከሰማይ ስትላቀቅ ወደ እሱ ለመሄድ መደፋት ቀረሽ መጣደፍ
ዉስጥ እገባለሁ። ፈገግ እላለሁ። ስለማገኘዉ ፣ ላወራዉ ስለሆነ ፣ ሲስቅ
ልሰማዉ ስለሆነ እና በእሱ ዙሪያ ስለማገኛቸዉ መልካም ነገሮች ሁሉ እያሰብኩ
እፈግጋለሁ። ምን እየሆንኩ ነዉ ብዬ ራሴን መታዘቢያ ጊዜ እስከማይኖረኝ።
ህልሞቻችንን አንድ ላይ ላስር ቸኮልኩ። ስቸኩል ነገር ሳትኩ። የሆነ ነገሬ ጎደለ።
የቱ ጋ? እንጃ!!
...
ብዙ ያልነገርኩት ናፍቆት አለኝ። ሲተኛ ስለተናደድኩባቸዉ ፤ አሁን በነቃ አሁን
በነቃ እያልኩ ስላሰብኩባቸዉ ምሽቶች ፣ ሲደክመዉ ስለሚያምር ድምፁ ፣
ስለሚያስቀኑኝ ትዝታዎቹ ፣ አካላቸዉ መሆን ስለምመኛቸዉ ህልሞቹ
አልነገርኩትም። ገና መቼ ወድጄዉ ጠገብኩ? የመዉደዴ ሀገር መሃል ይዤ
የቆምኩት ያልተቀባባ ፍቅር ነዉ። አልኳልኩትም። ስላልኳልኩት አያምር ይሆናል።
ነበርን ለመባባል ደርሰናል? መቼ ተራምደን የመራራቅ ኩርባ ጋ ደረስን? አንተ
ሆይ ያዘኝ! አንተ ሆይ ያዘኝ። የምፈራዉን መታገል እያደረኩት ነዉ። ፊትህን መልስ
እያልኩ ... ሱባኤ ልገባ ነዉ። ከቀናኝ እንደ እስከዛሬዉ ቀኔ ላይ ልኩለዉ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Ruth Habte Mariyam
Hiking to "Koremash", Menelik armory depot.

📅Hiking Date :- may 30, 2021 (ግንቦት 22, 2013)

🛫Departure:- Piyasa tayitu hotel

Departure Time - 1:00Am Local time 🚩

💵 contribution per person:- 600 ETB and for foreign 20 dollar

🧲 Package 🧲

🚍 - Transportation
🔴 breakfast 🍛
⚪️ Bottled water
🔵 entrance with Guide
🔴 photograph 📷
⚫️ Lunch 🥙

Activities:
🔅trekking, historical place visitation, talent performance(if any) and fun game.

Suitable for:
🔻 medium
🔸 average fitness
🔹 average basic skill required

NB.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!

for more join the
👉channel @sunsethiking
👉📷 @sunsetphotography

🎫 reservation @Paappii (0922303747)
ጆተኒ ስንጫወት ተዋወቅን። በቃ ዝምብሎ ወደደኝ። ጭራሽ አንድ ሰሞን ምንም ባለወቁት ምክኛት የዘዉተር ጋባዤ ሆኖ ቁጭ አለ። እንደዉ ቁጭ ብለዉ ሲቀዱት ቢዉሉ የማያልቅ ብር ይዞ በጡሃት ቤት ይመጣና ይጠራኛል። ቁርሳችንን ከሃሰን ቤት ድንች በብስኩት እንጀምርና። ምሳችንን አስፓልት ሄደን ጥብስ። ፑል እንደፈለግን እንጫወታለን የሚከፍለዉ እሱ። ማሙዬ ደግነቱ ገዛኝ። ብሩን ዝም ብሎ ይበትናል። ምንም አያሳዝነዉ። ይሄ መዝናናት ታዲያ ለሁለት ሳምንት ተከታታይ ቆየ። ታዲያ አንድ ቀንም እንዲዉ እንተለመደዉ ከማሙዬ ጋር ቀኑን ሙሉ ፈታ ስንል
ዉለን ሲመሽ ተለያየን እና ወደቤት ገባዉ። ወደቤት ገብተን 30 ደቂቃ አልቆየንም ከዉጪ የሚያስደነግጥ ጩሀት ተሰማ። ተደናግጠን ምንድነዉ ምን ተቃጠለ ብለን ስኖጣ ማሙዬ ላንቃዉ እስኪቀደድ ይጮሃል። እናቱ አባቱ በጃንሆይ ግዜ የገዙትን ቀበቶ
ወገቡ ላይ እያሳረፈች ፖሊስ ጥሩልኝ እያለች ትጮሃለች። 'ምን ሆነሽ? ምን
አድርጎ ነዉ' ሲሏት ብር እየሰረቀኝ።
እኔ ራቼ ክዉ ለካ ሁለት ሳምንት ሙሉ የሚጋብዘኝ ከእናቱ በሚሰርቀዉ ብርር
ነዉ ለካ ብሩ የማያሳዝነዉ የራሱ ስላልነበረ ነዉ። በላቡ ስላላመጣዉ። ስላልለፋበት። እንዴት እንደመጣ ስላለወቀ። ያን ብር ማምጣት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ስላልገባዉ። የሱ ስላልነበረ ነዉ ለካ እንደዛ የሚበትነዉ። እናት መደብደቡን በመሃል ገታ አደርጋ 'እሺ ብሩ የታል? ብላ ጠየከች ድምፁ እየተቆራረጠ 'ተዝናንበት' ከማን ጋር' እናት አሁንም ጠየቀች የራቼ ነብስ ልቶጣ
ማሙዬ አሁንም በሚቆራረጥ ድምፅ 'ከ ራ' መዳኒያለም ድረስ ወደ ዋላ ዞር አልኩ። 01 ያለዉ አጎቴ ናፈቀኝ

@wegoch
@wegoch
@paappii
#Rache_Tesfaye
፬ኛ ክፍል...

ሂሳብ አስተማሪያችን፣ ቲቸር አበራሽ ማስተማር ደብሯት ነው መሰለኝ <<ዛሬ ትምህርት የለም፣ ወረቀት አውጡና እኔን ሳሉኝ>> ብላ ዴስክ ላይ ተደላድላ
<<ሰመመን>> የሚል መፅሐፍ ማንበብ ጀመረች። ከስዕል ደብተር ላይ ሉክ ቀድጄ መሳል ጀመርኩ። ቀና ብዬ አያታለሁ እንደገና ጎንበስ ብዬ እስላለሁ። እንደገና በአትኩሮት አያታለሁ። አጎንብሼ እስላታለሁ። መጨረሻ ላይ ከብዙ ልፋት በኋላ፣ አፍንጫዬን አልቦኝ ስዬ የጨረስኩትን ስዕል <<አበራሽ>> ብዬ ከስር ፅፌበት ላሳርም እየሮጥኩ ሄድኩ።
አጠገቧ ደርሼ <<ቲቸር! ቲቸር! ሳልኩሽ። ጨረስኩ!>> አልኋት። የምታነብበውን መፅሐፍ ከድና፣ የሳልኩትን ስዕል ከእጄ ተቀብላ ተመለከተች። ወዲያው ፊቷ ተቀያየረ። <<አንተ! እኔ ይህቺን እመስላለሁ?! አንተን እኮ ነው ምጠይቅህ?! ይህቺን እመስላለሁ ወይ?!>> ብላ አንባረቀችብኝ። በቁጣ ሳትመለስ አለንጋዋን መዥርጣ እስኪበቃት ለጠለጠችኝ። ይኸው ከዚያ በኋላ ስዕል የደረሰበት ደርሼ አላውቅም።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun Girma Ango
ሴት ነኝ
ፍስስ እንደ ወንዙ ፣ ልስልስ እንደ ምን? ልስልስልስልስልስልስ
...........መልኬን እኔው በአይኔ አይቼው ባላውቅም፤ ያዩኝ ግን ቆንጆ ነሽ
ይሉኛል። አይኔ ሰበርበር ለማለት ከንፈሬን ለዝምታ ቢመድቡትም፤ አንገቴን
ለአንገት ልብስ ለአናቴ ጽጉር መሸፈኛ ሻሽ እና ነጠላ ለመልበስ
ቢነግሩልኝም.......
በመንገድ ባጠገባቸው ሳልፍ እንደ አውራ ዶሮ እንደሚቆሙ አውቃለው፤
በተሸፈነ ልብሴ ውስጥ በጡት መያዣ የታሰሩ ጡቶቼን፤ ከአንጀቴ
የተጣበቀ እምብርቴን ያዩታል። እጃቸውን በቀጭን ወገቤ አሳልፈው
ሊያቅፉኝ ይሻሉ፤ይሄንንም አውቃለሁ፤ አቅፈውኝም ይሆናል።ከለበስኩት
ዘርፋፋ ቀሚስ የተሞናደሉ ጭኖቼ ፤ የተሳሉ ባቶቼ ስር ያለውን ሌላ
ሴትነቴም .....እንደ እሳት ቢሞቁት ፥ቢሞላላቸው ይመኛሉ። ሞቀውትም
ይሆናል፤ ከጭኖቼ ሳይገቡ ጠፍተውም ይሆናል።
ልብሴም ሲወልቅ ፤ ማስያዣዬም ቢለቅ ፤ በሀመሮች መልክ ስታይ
ገላዬም ሲራቆት የጎሳዬ ዘፈን ለኔ እንደሆነ አውቃለሁ። ቆዳ እና ኮባም
ባላገለድም በዘመነኛ ፒኪኒ ፤ ብርቱካን የሚመስል አካሌ ሲታይ ቀላሁ
እንጂ ......ከልብስ በፊት ፤ ከልብስ ስር እንዲህ ነኝ ፤መልኬ ይህ ነው
ባይ ነኝ።
ሴትነቴ በልብስ መሸፈንም የማይመጣ ፤ በመራቆትም የማይወጣ ነው።
ለብሼም አይተውኛል አውልቄም አተኩረውብኛል። ለብሼ
ገፈው ተኝተውኛል ፤ ስራቆትም ለስሪያቸው ሲሳይ ነኝ። ከኔ መልበስ እና
መሸፈን አይደለም ፤ ከኔ ማማር እና ማስቀየምም አይደለም ግን ያረቀቁት
እምነት አለ ፤ የተቀበሉት ሃሳብ አለ፤ ከዛ የወጣ ሁሉ ይጠፋል አይነት
ነገር፤ እንጂ.......
ፍስስ እንደ ወንዙ ፣ ልስልስ እንደ ምን? ልስልስልስልስልስልስ
...........መልኬን እኔው በአይኔ አይቼው ባላውቅም፤ ያዩኝ ግን ቆንጆ ነሽ
ይሉኛል። ሲፈጥረኝም ቆንጆነት ምን እንደሆነም ባይታወቅ ከጡጦቼ ጫፍ
ህይወት የሚቀጥል ፤ ከእንብርቴ ስር የሺህ ትውልዶች ማደሪያ ፣
በማህጸኔ ዘመን እና ነገን የተሸከምኩ
ሴት ነኝ።

#Beza_Tezera

@wegoch
@wegoch
@MahletZerihun
ቅልጥፍናህ ብልጠትህ የሆነች ሴት ወስዳብህ ታውቃለች ? እትት ግትት
ብለህ ብዙ ሴት እንዳላሰመጥክ ይህቺኛዋ ጋር ስትሆን ግን አፍህ
ተቆላልፎብህ ያውቃል ? ተጫዋቹ እገሌ እንዳልተባልክ ከዚህችኛዋ ጋር
ስትሆን ግን ተጫወት እንጂ አንተ ተብለህ ታውቃለህ ? ብዙ ወንዶች
ደፍረው የማይቀርቧቸውን ቆንጆ ሴቶች ቀርበህ እንዳልበላህ አሁን ከሷ
አጠገብ ስትሆን አንደበትህ ከተሳሰረ ወዳጄ ማመም አልፈለክም እንጂ
እልም ያለ ፍቅር ውስጥ ነህ...አሪፍ አሪፍ ጭዌ ተጫውተህ የብዙ ሴቶች
ልብ እንዳላሸፈትክ ሴቶችን ለአጭር ድርሰት ካልሆነ ለሌላ ቀርበህ
የማታውቅ አሁን ከዚህችኛዋ ስትሆን ምላስህ ከተሳሳረ ወዳጄ ፍቅር ጉድ
ሰርቶሀል...ወደድኩሽ ህይወቴ ምናምን የሚሉት ጭዌ የማይመስጥህ ልጅ
ቸኮሌት, አበባ, አሻንጉሊት መስጠት ከጀመርክ ፍቅር በሚባለው በሽታ
ተለክፈሀል ማለት ነው...ፍቅር ባለጌ ነው አንተነትህን ያሳጣሀል
ያልነበረህን ሌላ ማንነት ነው የሚሰጥህ የክለብ ቤንች ላይ የምታነጋ
ሰውዬ በአንዴ ቀዳሽ ሊያረግህ ይችላል ተጫዋቹን ዝጋታም ጉረኛውን
ትሁት በቃ ፍቅር እንደዚህ ነው አድርገህ የማታውቀውን ነገር
ያስደርግሀል...ያልተለመደ ባህሪዬን ያዩ ጀለሶቼ ፍቅር ይዞሀል አሉኝ ፍቅር
ስለማይገባኝ አረ ወፍ ስለ ምን ፎንቃ ነው የምታወሩት እኔ አላፈቀርኳትም
እላለው ከሌሎች ሴቶች በተሻለ በብዙ ነገር የህይወት ፍልስፍናችን
ስለሚመሳሰል እንጂ እኔ አልወደኳትም እላቸዋለው...አድርጌው
የማላውቀውን የሼክስፒር መፅሀፍ ገዝቼ መስጠቴ አምላኬን አኩርፌው
church መሄድ አቁሜ የነበርኩ ልጅ ከሷ ጋር መሄድ መጀመሬ እና
ከፀለይኩ አመታት አልፎኝ የነበርኩ ልጅ ከእኔ እድሜ ቀንሰህ ለእሷ
ጨምርልኝ ብዬ ወደ አኮረፍኩት አምላክ መፀለዬ እንዴት ነው ይሄ
አፈቀርካት የሚያስብለኝ

#Henok_G/medhin

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
የዋይፍ/የሚስቴ አባት ደውለው <<ልጅ ጥላሁን እንደምን ነህ? ባለፈው ያበደርኳችሁን ብድር መቼ ልትከፍሉኝ አስባችኋል?>> ብለው ጠየቁኝ። ለቤት
ለማስጨረሻ የሚሆን ገንዘብ ከተበደርናቸው አንድ አመት ይሆነዋል።
<<እንዴት ነዎት ፋዘር? ኧረ እንከፍላለን። #$=$&=$#&$ ችግሮች ስላሉብን
እንጂ እንከፍላለን>> ብዬ የባጥ የቆጡን ዋሸሁ። እሳቸውም <<አይ ችግርስ
ካለባችሁ እታገሳለሁ።>> ብለውኝ ተሰነባብተን ወደ ስብሰባ አዳራሽ ገባሁ። ከስብሰባ እስክወጣ ለወሬ ቸኩዬ፣ ስልኬን መዥርጬ የፅሁፍ መልዕክት ወደ ሚስቴ መፃፍ ጀመርሁ...<<ስሚ እንጂ....ሼባው ብድሩን writeoff ያደርግልናል ብለሽኝ አልነበር እንዴ? ኧረ ደውሎ ፈራንካውን አዘጋጁ እያለ ነው። እኔማ#$=$&=$#&$ ችግር አለብን ብዬ ዋሽቻለሁ። ስለዱባዩ ሽርሽር ዕቅድ ትንፍሽ እንዳትዪ። ድንገት ከደወሉልሽ ቃላችን አንድ ይሁን።>> ከዚያ <<Send>> ቁልፍ ተጭኜ ስብሰባዬን መከታተል ጀመርኩ። ከደቂቃ በኋላ
መልዕክት ስልኬ ላይ ገባ። <<እኔ የዓለም ባንክ አይደለሁም ዕዳ የምሰርዝላችሁ Writeoff የማደርግላችሁ/። ዱባይ ለዱባይ ሽርሽር ከምትዞሪ ዕዳሽን ክፈዪ ብሎሻል
በላት>> ይላል - አባቷ ናቸው። አለቆቼ አዩኝ አላዩኝ ብዬ የፃፍኩትን መልዕክት ለካስ ለአባቷ ነው የላክኩት። ወይኔ ጥላሁን! ወይኔ! አሁን ምን ብዬ ነው ዐይኗን የማየው

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun girma ango
የኔ ህይወት አሁን ላይ ነው ያለው. በቃ የአሁኗ ደቂቃ ወደትላንት ሳልቀር ወደ ነገም ሳልሸረፍ ሙሉ በሙሉ የምኖርባት ብርቅ ግዜዬ ናት.ለእንደኔ አይነት ሰው ህልም ቃልኪዳን እና ትዝታ አይሰሩም ተስፋስ ምንድነው? ..ትልቁ ህልሜ አሁኔን በሚያስቀና መልኩ መኖር ነዋ! ቃልኪዳኔን ከነገ ጋር ሳይሆን ዛሬን እንደሙሽራ ንግስት ሆኖ ከመኖር ጋር ስላደርግኩ.ትዝታዬ የአሁን ግዜ ድርጊቴ ነው. እያደረኩት እናፍቀዋለውና. ዛሬ ያደረግኩት ነገር ካስደስተኝ እሰየው... ካሳዘነኝም ይሁና! እንጂ ሌላ ዛሬ የሚሆን ነገዬ ላይ እንደተስቦ እንዲንጠለጠልና መላ ህይወቴን 'ዘመን መቁጠር'ብቻ እንዳያዲያደርገው አልፈቅድለትም. ባይሆን የሚያስተምረኝን ትምህርት በመቅሰም እተባበረዋለው..... ተስፋዬም ቢሆን ዛሬዬ ውብ እንዲሆን ከመመኘት ጋር ነው. ማነው ተስ ፋን ለነገ ብቻ የሰጠው? ትዝታንና ናፍቆትምስ ለትናንት ብቻ ያደለው ማን ይሆን? ቃልኪዳንስ ፤ህልምስ ከዛሬ ጋር መሆን አይችሉም ያለው ማነው? የሰማይ አባቴ ስንኳ ነገ ለራሱ ክፋቱ ይበቃዋል! ብሎ አሳርጎልኛል... ህልሜም ትዝታዬም ናፍቆቴም ተስፋዬም ቃልኪዳኔም ዛሬ ናት.

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Magi
በቀደም 'ለትኮ ነው ቀሽቷ ጓደኛዬ (ቀበጥም ናት) "ለቆንጆ ሴት ተብሎ በወንዶች መካከል ሰላማዊ ፉክክር የተጀመረው መቼ ነው" ብዬ ጠይቄያት የመለሰችልኝ መልስ እንዲ ነበር
.
.
"በአዳም ግዜ ነው እንዳልል እሱ ብቻ ወንድ ነበር... ስለዚ የሚሆነው በልጆቹ በአቤልና በቃየን ነው! .... ቃየን ሁሉን ከታደለው አባቱ አዳም ጥንካሬን ና መሬት አርሶ እዝዕርት ማብቀልን ሲወርስ አቤል ደግሞ ማማለልልን ሮማንቲክነትን ወረሰ. እንግዲ ከዚ ነው የተጀመረው. አቤል በማማለል ጥበቡ ተጠቅሞ ቆንጆይቱን ሲያሰምጥ... ቃየን ደግሞ ተበላ! የሰገጤ ነገር መቼም በጉልበት ነው የሚያምነውና.... በቅናት ተነሳስቶ አቤልን ግድል!
እንግዲህ ከዛ ግዜ ጀምሮ አዳምን ሳይጨምር(በርግጥ እሱም ተቀናቃኝ ቢኖረው ያደርገው ነበር) ያዳም ዘር በሙሉ ለሔዋን ልጆች መፎካከር ጀመሩ ይባላል"

ሳቅኩኝ! ታሪኩ ሳይሆን ያሳቀኝ እንዴት ነገሮችን አገናኝታ እንዲ መሳጭ ታሪክ አውርታ አፌን እንዳስከፈተቺኝ ገርሞኝ

ቀጠለች
.
.
"በሰላማዊ መንገድ የሆነበትን ግዜ እንኳ እርግጠኛ አይደለውም... ግን ሳስበው በሎጥ ዘመን ይመስለኛል. ... ሚስቱ የጨው አምድ ከሆነች ግዜ ወዲህ ሎጥ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ዋሻ ገባ ከዛም ዘራችን እዳይጠፋ በሚል ሰበብ ሁለቱንም የለምንም ተቀናቅኝ በላ..... "

አቋረጥኳትና

"እህህህ! ይሄ ታድያ ከፉክክር ገር ምን ያገናኘዋል?"

መልሷ ይሄ ነበር

" መምህር ሁሉንም አያስተምርም!"

ሃሃሃሃሃ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Magi
ትዝታ ዘ ዳሞት
ዳሞት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በነበርነበት ጊዜ እውቅ ገጣሚ
ነበርሁ።
ያኔ ፍኖተሰላም የዞን ከተማ ሳትሆን ወረዳ ነበረች።
በወረዳው የግጥም ውድድር ተዘጋጀ።
እሳት የላስን ገጣሚያን ከመላ ዳሞት በባትሪ ተፈልገን ምርጥ የተባለ
ስራችንን ከአዘጋጁ ኮሚቴ አስገባን።
የሚሊኒየም በዓል በፍኖተሰላም ስታዲዬም ሲከበር የግጥም አሸናፊዎችን
ስም ለመጥራት ፕሮግራም መሪው ማይኩን ተቀበለ። 3ኛው የወጣው
ተጠራ።
የኔ ስም የለም። ተሸለመና ተቀመጠ።
2ኛ የወጣ ተጠራ። አሁንም የኔ ስም የለም። የተጠራው ተፎካካሪዬ
ተሸለመና ተመልሶ ተቀመጠ።
1ኛ የወጣውን ከመጥራቱ በፊት ሰስፔንስ ለማድረግ ሞከረ። አሁን
ማልጠራ ከሆነ የጥበብ ዛር አኩርፋ ማቱን እንዳታወርድብን ጠለይሁ።
ከአፍታ ቆይታ በኋላ የዳሞቱ ሎሬት ስም ተጠራ። ስሙም የኔ ነበር።
ከመድፍ ያልተናነሰ ድምፅ በጭብጫቦ ተሰማ።
ይሄ ምትሃታዊ ገጣሚ ማን ይሆን ሲል ሁሉ አይኑን አፈጠጠ።
ያኔ እንዳሁኑ በርገር ስላልነበር አልወፈርንም ነበርና
ኮሰረቱ ጓድ ወጣና ሽልማቱን ሲወስድ ሁሉም ከቅምጡ ተነስቶ ድጋሜ
ቡሬ ድረስ የተሰማ ጨ ብጫቦ ተጨበጨበ።
ሽልማቱንም በእጃችን አስገብተን ተቀመጥን።
12ኛ ክፍል እያለሁ ሌላ እኔ ነኝ አንደኛ ያለ ገጣሚ ተነሳና እበልጥሃለሁ
ሲል ወደ እኔ መጣ።
መብለጥ እንጂ መበለጥ ያልተለማመደው ጓድም የሚቀመስ አልሆን አለ።
ግጥማችንን ይዘን ወደ አማርኛ መምህራችን ዘንድ ሄድን።
የአማርኛ መምህራችንም የሁለታችንን ግጥም ካነበበ በኋላ
የኔን በቋንቋ ውበት እንደሚልቅ የወደረኛዬ ደሞ በጭብጥ የተሻለ እንደሆነ
ምስክርነቱን ሰጠ።
በጊዜው ጭብጥ የሚለውን ቃል አልተዋወቅሁትም ነበርና
"የጭብጦ እንጂ የጭብጥ ውበት አላውቅም። ተበልጠሃል ተበልጠሃል
አበቃ"
አልሁትና ተለየሁት።
#ተጣፈ
በዳሞቱ ሎሬት የልደት ቀን ዋዜማ ከላህ ወንዝ ወዲህ ማዶ ፍኖተሰላም

#Tilahun_Agere

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
... ድግግሞሽን ማን ያስቀራታል? 'የሆነ ወቅት' የሚባል ነገር የላትም። ከተኖረ ይደጋገማል...

.. ደግሞ የአንደኛው ክፍል ድግግሞሽ ይደበዝዛል... ይረሳል...ይቻላል ... ይተዋል...ይታለፋል። መተው እንዴት እድለኝነት ነው?! መርሳት ምን ያህል ፈውስ ነው?! ማለፍን የሚያክል ...?

... "በቃ ቻለው! ትሰማለህ? ለምን ቻል አታደርገውም?" ማለትን የለመደባቸው ሊታዘንላቸው በተገባ! መቻልን በቀመሱና እንዲህ ሲሉ ባልተሰሙ!

... በሞኝነትህ ሰምን ችለህ የነበርከው ሰውዬ 'መቻል'ን ስትረዳ ሐሳብ ማገላበጥ ሲያቃጥል!... ብስብስ ሐሳብህን ከመቻል መጋዘንህ እየቀናነስክ ስትበላና መዋጥ ሲሳንህ፥ ሲያበግን! (ኢሄን ነገር ምንም አይፍቀው። አኝከው ሲለቁት ከተወጠረበት ሄዶ ይለጠፋል። ደሞ ሌላ ቀን ለተራው አሳስቦ ይተኛል! ተቻችሎ...)

..<መቻል አስተማሪን ማን አስተማረው?>
ገርሞኝም አላባራ!
(አዌ እሜ)
@awezeru
@awezeru
@wegoch
@wegoch
2024/11/05 23:15:03
Back to Top
HTML Embed Code: