Telegram Web Link
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!(የቀጠለ)

ሰይጣን ይሁን ራሴ ወይም ፈጣሪ ለሀጥያት በቀጠሩልኝ ቀን ከአለቃዬ ጋር ባለግኩ። ይኸው ነው ሀጥያቴ!

ጨው የሌለው አልጫ ወጥ አልጫ ወጥ የሚል ትዳር ውስጥ ፀጥ ለጥ ብዬ እንድቆይ ባለእዳ ያደረገኝ ሀጥያቴ ይኸው ነው!! ይኸው ነው ብዬ አቀለልኩት?

ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ስልኬ ባትሪ ጨርሶ ባሌ ሲደውል ስልኬ ዝግ ነበር። ካልጠፋ ቀን ስልኬ በዘጋ ቀን ስንት ቀን ባልተሰማኝ ያለፍኩት የአለቃዬ እጅ ሲነካኝ ንዝረቱን እንቢ ማለት አልቻልኩም። ካልጠፋ ቀን ባሌ የዛን ቀን ቢሮዬ ድረስ ዘለቀ። ምን የሚሏት ባላጊ ነኝ ግን? በዘመኔ ከባሌ ውጪ አንድ ሰው ብሞክር እሱንም የቢሮ ጠረጴዛ ላይ? እኔን ብሎ ባላጊ ! ቅሌቴ በዚህ አላበቃም።

ተያየን። ጠረጴዛው ላይ በግማሽ አካሌ ተጋድሜ ሰማይ የእኔን እግሮች ምሰሶ አድርጎ የቆመ ይመስል እግሮቼን ወደላይ ወጥሬ ሰድሬ አለቃዬ ከእግሮቼ መሃል ሆኖ ሲለፋ ባሌ በሩን ከፍቶ ሲገባ ተያየን። (አንባቢ ሆይ እዚህጋ ለምትስሉት ምስል እኔን ተጠያቂ እንዳታደርጉ:: ሁኔታውን በምስል ለመከሰት ታስቦ እንጂ አንባቢን ክፉ ለማሳሰብ ያልታሰበ!)

ለወትሮ ጨዋ ነበርኮ። ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ጨዋነቱን እረስቶ ሳያንኳኳ ዘው ይላል? አፌን ከፍቼ ብዙ ቆየሁ። ድንጋጤው ይሁን የአለቃዬ ልፋት ወይም ሁለቱም አፌም ተከፍቶ አይኔም ፈጦ ብዙ ሰከንዶች አለፉ!! ባሌ ቀስ ብሎ እንደገባ ሁሉ ቀስ ብሎ ወጣ! አለቃዬ በድንጋጤ የተጋለጠ ንብረቱን ለመሸፋፈን ይተረማመሳል። (ይሄ ደግሞ የሚስቱን ምጣድ በቂጡ ነው እንዴ የሚያስስላት? እሱ የበጨጨ ቀይ ፣ ቂጡ የብረት ምጣድ ቂጥ የሚመስለው!)

ከአንድ ሰዓት በላይ ቢሮዬ ተቀመጥኩ። ተጎለትኩ። የማስበውን አላውቅም። ወደቤት እንደማልሄድ አውቀዋለሁ። አይኑን አላየውም። ግን ወዴት ነው የምሄደውስ? ብቻ አላወቅኩትም። ቦርሳዬን አንስቼ ወጣሁ። ደርቄ ቆምኩ። ባሌ እየጠበቀኝ ነበር። ልክ ምንም እንዳላየ፣ ድሮ እንደሚያደርገው ሁሉ ዘሎ ከመኪናው ወርዶ በሩን ከፈተልኝ። ልሩጥ? መኪና ውስጥ ልግባ? ምን ላድርግ ደረቅኩ!

"ወደቤታችን እንሂድ አይደል?" አለኝ ቁጣም ፍቅርም ፣ ልስላሴም ምሬትም ባለው ድምፅ። አሁንም ምን እንደምለው ግራ ገባኝ። መሮጥ ፈለግኩ። ማምለጥ ! መሸሽ። ገብቶታል። አጠገቤ ደርሶ እጄን ያዝ አደረገው። ሲመጣ እያየሁት ደርሶ ሲነካኝ በረገግኩ። አብሬው ተራመድኩ።

"ስንት ጊዜያችሁ ነው?" አለኝ በፀጥታ ሲነዳ ከቆየ በኋላ

"ምኑ? ማለቴ? " ተንተባተብኩ

"ስታደርጉት የነበረውን ስታደርጉ ስንተኛ ጊዜያችሁ ነው?"

"የመጀመሪያችን"

"ትወጂዋለሽ? በፍቅር ትወጂዋለሽ? ከኔ በላይ ትወጂዋለሽ? "

"ኸረ አልወደውም!" እያልኩት ለምን አይሰድበኝም? ለምን አይጮህብኝም? ለምንድነው ምንም እንዳላደረግኩ ተረጋግቶ የሚጠይቀኝ? እያልኩ አስባለሁ ።

"ፍቅራችን ይህን ማለፍ አይችልም?" አለኝ። ዝም አልኩ።

"ይህን ማለፍ የሚችል ፍቅር የለንም?" አሁንም ዝም አልኩ።

"ይችላል። በደንብ ይችላል!!" ራሱ መለሰ። ድምፁ ውስጥ አማራጭ የለውም::

እቤት ስንገባ አፉ ከመለጎሙ ውጪ ከዛ ቀን በፊት ከሚያደርገው ምንም ዝንፍ ያላለ አመሻሽ አመሸን። አስፈራኝ! ብዙ ክፉ ሀሳብ አሰብኩ። ለዓመታት አቅፌው የተኛሁት ባሌ እንቅልፍ ሲወስደኝ ሲጥ አድርጎ የሚገድለኝ መሰለኝ። እያበድኩ መሰለኝ! ባልጌያለሁ አይደል? ቅድም ባሌ ስባልግ አይቶኝ የለ? ወይስ ቅዠት ነው?

ልክ አይደለማ! ሚስቱ ስትማግጥ በዓይኑ አይቶ ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን ምኑ ነው ልክ? ንዴቱ ይቅር እንዴት አላስጠላውም? ለምን ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም? ጭጭ አለ። እያጎረሰኝ እራት በላን!! ሶፋው ላይ እግሮቹ መሃል አስቀምጦ አቅፎኝ የጀመርነውን ተከታታይ ፊልም አየን! እሱ አየ እኔ ዓይኔ ቴሌቭዥኑ ላይ እየተንቀዋለለ ቅዠት እሰፍራለሁ::

ከቅሌቴ በፊት

እንደአብዛኛዋ ኢትዮዽያዊ ሴት ዮንቨርስቲ ጨርሼ እስክወጣ "ወንድ ልጅ ኡፉ ነው::" ተብዬ ነው ያደግኩት:: (ምኑጋ እንደሚፋጅ አልነገሩኝም) ይሄ ወንድ የሚሉት ፍጥረት ከአላማ የሚያስተጏጉል... ወደፊትሽን ሊቀጭ አሰፍስፎ የሚጠጋሽ አሰናካይ .... ከብልግና ውጪ ሀሳብ የሌለው ክፉ ፍጡር .... (እንደአላብዛኛዋ ሴት ያሉኝን አምኜ ወይም ፈርቼ ይሄን እርኩስ ፍጡር ስሸሽ አድጌ አላማሽ ነው ያሉኝን ትምህርቴን ተመረቅኩ)

ከዩንቨርስቲ ተመርቄ ስራ እንደጀመርኩ ያ ኡፉ ነው የተባልኩት ወንድ ድንገት በህይወቴ አንገብጋቢ ፍጥረት ሆኖ መጪ ሂያጅ "መቼ ነው የምታገቢው?" ይለኝ ገባ! እሱ በህይወቴ ስለሌለ ከህይወት ወሳኙ ክፍል እንዳመለጠኝ አይነት!!

ስሸሸው ኖሬ ኖሬ ስፈልገው ብቅል የሚል ያስመስሉታል!

እንደአብዛኛው ሀይማኖተኛ ቤተሰብ እንዳላት ኢትዮዽያዊ የባል መስፈርቱ "እግዜርን የሚፈራ" ተብሎ ተምሪያለሁ:: 100 ሺህ እግዜርን የሚፈራ ወንድ ቢኖር ከነዚህ መሃል የኔን ባል የምመርጥበትን መለኪያ አላስተማሩኝም:: ... ከመቶ ሺወቹ የተገኘው ... የቀደመ ... ወይም ይሄን ገፍታሪ መኮሳተሬን የደፈረ...

መጣ! እግዜርን የሚፈራ .... እጅግ ደግና መልካም! ጨዋ የጨዋ ዘር .... አወቅኩት! ለመድኩት!! ወደድኩት!!

"የተባረከ! መሬት የሆነ ወንድ! እድለኛ ነሽ" ተባልኩ::

ቤተክርስቲያን ቆሜ በህመሙም በድካሙም በፎከቱም ..... ላልለየው ብዬ ቃል ገባሁ:: ውብ ነበር:: የመጀመሪያዬ .... የመጨረሻዬ ... ህይወቴ .. ዓለሜ ... ተባባልን!! ኖርን ኖርን ኖርን ..... ሁለት ዓመት .....

የወደድኩት ባሌን ሳይሆን ትዳርን እንደሆነ ገባኝ ... እንዴት? አላችሁ? እሱን ላላገባችሁ እና ለፍሬሽ አግቢዎች አብራራለሁ ያገባችሁ (ቢያንስ 5 ዓመት የሆናችሁ) ገብቷችኃል::

"ልጅ እንውለድ አይደል ፍቅሬ? " አልኩኝ የሆነ ቀን

"ልጅ መውለድ እንደማልችል አልነገርኩሽም እንዴ?" አለኝ ልክ ውይ የላክሽኝን ቲማቲም ሳልገዛ ረስቼ መጣሁ እንደሚባለው ዓይነት ቅልልል አድርጎት .....

(በነገራችሁ ላይ አልጨረስንም)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
እሱ ስለ እሷ


ታሪክ አታሳጣኝ ብላ የምትፀልይ ይመስል የሚተረክ ማንነት አይጠፋትም።ትኖራለች፡ኖራለች።
ድንገት ነው የጠየኳት"ህይወት ውለታ እንድትውልልሽ ብትፈልጊ ምን ትጠይቂያታለሽ?"
"ፈጣሪዬ ብቻ ተስፋዬ እስኪሆን ድረስ በወጀቧ አስረድታ እንድታጠነክረኝ"አለችኝ።
ትገርመኛለች…ብርቱ ናት፤ፈሪም ናት፤ችኩል ናት፤ቀላል ናት።የአጠገቧን በቀረባት ሰዓት ለማድረግ ትቸኩላለች፤አታሳድርም…የዛሬ ልጅ ናት።በየቀኑ የተወለደች ይመስል ለዛሬዋ ህይወትን አትነፍግም።

እኔስ የትዝታ አድናቂ የነገ ናፋቂ ነኝ።ግን አንቃረንም።
"ነበር?ነበር ማን ነው …ንገረኛ…ትላንት የሚባል ቀን ነው?እኔ እስከዛሬ ትላንት በሚባሉ የዛሬ ጥርቅሞች ውስጥ እንደኖርኩ ማን ለነበር ተንታኞች በነገራቸው" በለስላሳ ዛቻዋ እንዲህ ትለኛለች።
…ያልተለመደውን የምትኖር ወይ የተለመደውን ባልተለመደ መንገድ የምታስኬድ ብዬ እንዳልፈርጃት ግራ ይገባኛል ግን በመደናገር ትገርመኛለች…ግን ቀላል ነች።ቀላል ተብለው የተተዉትን ስሜቶች ትኖራቸዋለች።

ለሷ ሁሌ ዛሬ ነው፤ዛሬም ሁሌ ነው።ያላት ይናፍቃታል…"ናፍቆትን ማነው በእርቀት ውስጥ ላለው ነገ የሰጠው"ትላለች።ዛሬን እየናፈቀች ትኖራለች።
አቅፋው የምተኛው ይናፍቃታል…ሸለብ ካረገኝ ትቀሰቅሰኝና "ናፈከኝ" ትለኛለች።
ስታወራ ድምፅህን መስማት አላለችኝም።ስታወራ የምታወጣቸውን ቃላት ግጥምጥም አድርጌ በአይምሮዬ እየሳልኩት ስታወራ ፈዝዤ ልይህ እንጂ።
የአምስቱን የስሜት ህዋሳት ስራ ማዋዋስ በሷ ነው ያየውት።ትንንሽ ከንፈሮቿን በፍጥነት ይያንቀሳቀሰች ሀሳቧን አራግፋ ስታበቃ ዝምምምም ትላለች።ዝምታዋ የንግግሯ ቅጥያ ነው፤ አይጎረብጥም።የዝምታዋ ውበት ያወራኝ ይመስል ዝምታዋን እንዳደምጠው ፍቃዴን ወስዳዋለች።
ቀጠለችና "ናፈከኝ" አለችኝ። "አንተን ማቀፍ እኮ አይደለም(ለግላጋ ፀጉሯን በእጆቿ እያጫወተች) አጠገቤ መሆንህን እየማግሁ ቅርበትህን ማሽተት አለችኝ"… መዳሰስን ስራ አስፈትታ። ኑሮዋን ታስተጋባለች…ተጋባብኝ መሰለኝ እኔም ያለቃላት የምትገልፃቸውን ማድመጥ ናፈቀኝ።ጆሮዬን ድርጊት ላስደምጠው ናፈቀኝ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#heaቨን
እሱ ስለ እሷ ፪

ፈሪ ነች።ምንድነው የሚያስፈራሽ ስላት "ክፉ ሰወች እና ሁኔታዎች ሳይሆኑ የዋህነቴን ሊጠቀሙበት የሚመጡ ጥሩ ሰወች" ብላ እራሴን በመጠርጠር ውስጥ ታወዛግበኛለች።
ንፁህም ናት።እንደ ሰው የሚጠቀስ ከመልካም ተቃራኒ ደካማ ጎን ቢኖራትም አብዝታ ስለማትጠቀማቸው ንፁህ ነፃነት አላት።
"መልካምን የመተግበር ሙሉ መብት እያለን በተቃራኒው መድከም ምንድነው?" ትለኛለች። ለመምረጥ መድከምን አትወደውም።
በሚጋባ ፈገግታ የታጀበውን ፊቷን ወደእኔ መለስ አረገችውና "ሰው ያስባለን የመምረጥ ነፃነታችን አይደል!" አለችኝ።በግርምት "አዎ" አልኳት።ነፃነቷን ሳታዛባ ምርጫዋን አቅንታበታለች።

"ሁሉም መንግስተ ሰማያት መሄድን ይፈልጋል ግን ማንም መሞትን አይፈልግም" ያለችኝ በትውስታ መጣብኝ።"የምትናፍቀውን ስጦታ ለማግኘት አንተ ጋር መሞት ያለባቸው ነገሮች አሉ።" ደጋግማ ከምትለኝ በከፊል ከምረዳቸው ሀሳቦቿ አንዱ ነው።በምሳሌ ስታስረዳኝ "ታመህ የምትገዛው ደስታ ፍቅር አይደል… መታመም መንገድ ነው" ብላኝ ነበር።


መንግስተ ሰማያት መግቢያ በልብ ቢሆን የሰልፉን መጀመሪያዎች ለመቀላቀል ትመረጣለች ብዬ አስባለው።
ትገርመኛለች።አንዴ ያነገሰችውን አትጥልም፣ቦታ አትነፍግም፡ለጠቀማትም አታደላም። የጎዷትን ስታስብ አትታወክም።"ተስፋ ሀያል ነው…አይገርምህም ሰው ተስፈኛ ነው …ዛሬ ቢሰበርም ነገ ይዞ የሚመጣውን ለማየት ይጓጓል…ሰው ቢጎዳውም ሰውን መድሀኒት አርጎ የሚሾም እድለኛ ነው" አለችኝ።


"የዛሬ ልጅ ሆይ …ተስፋ ካልሽኝ አይቀር ስንጋባ የት ነው የምንኖረው?" አልኳት።እንደጠየኳት የዝናብ ጠብታዎች ይረግፉ ጀመር።
የጠየኳትን ጥያቄ ሳትመልስልኝ ዣንጥላውን ለመዘርጋት ስታገል አስቆመችኝ።
"ዝናብ እወዳለው ትላለህ ሲዘንብብህ ግን ዣንጥላ ትዘረጋለህ? …የምትወደውን ተለማመደው" አለችኝ።

ዝናብ የመውደዴ ምክንያት እሷ ናት።ዝናብ ትወዳለች።ከዝናቡ በፊት ላለው ነጎድጓድ ትኩረት አትሰጠውም። ። አለምልሞ፣ አጥቦ ፣አፅድቆ ለሚሄደው ዝናብ ግን ብዙ ታወራለታለች።ዝናብ ጅማሬ ቢሆንስ፡ያለችኝን አስታውሳለው።

ከትውስታዬ ስመለስ መልሼ ጠየኳት "የት ነው የምንኖረው?"

"ዛሬ አለችኝ።ነገን ስናልም ዛሬ እንዳያመልጠን ።የዛሬ ዝናብ እንዳያመልጠን" አለችኝ።

አንዳንዴ የለበስኩት አፈር ሲታየኝ ከሷ ልሸሽ ብሞክርም "ወርቅህ አፈር ነክቶታል ሲሉህ ትጥለዋለህ?" ብላ በእንስፍስፍ ከእቅፏ ትስገባኛለች።
ነፍሷን አርጥቦ የወሰደውን ዝናብ የኔንም ነፍስ አርጥቦ የምድር በደሌን ሊያጥብልኝ ነው መሰለኝ እሷን እያየው የዝናቡ ድብደባ ደበዘዘብኝ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#heaቨን
ኳስ የማይመለከቱም ሰዎች ቢሆኑ እዚች አለም ላይ እስከኖሩ ድረስ ታላቁን ክርስቲያኖ ሮናልዶ አለማወቅ አይችሉም። በአንድ ወቅት ጋዜጠኞች ለክርስቲያኖ ቃለ መጠየቅ ሊያደርጉለት ቤቱ ሄዱ ፣ እንዲህም ሱሉ ጠየቁት፦
በህይወትህ በጣም የምታከብረዉ እና ትልቅ ዉለታ ዉሎልኛል ብለህ የምታስበዉ ሰዉ አለ??

ሮናልዶ: "አዎ የ14 አመት ልጅ እያለዉ የስፖርቲንግ ሊዝበን መልማዮች ተጨዋች ለመመልመል ሰፈራችን ይመጣሉ። በአንድ ጨዋታ ላይ ብዙ ጎል ያገባ ተጫዋች ይመርጣሉ ተባለ ፣ ታዲያ እኔና ጓደኛዬ ፣ አንድ ቡድን ነበርን። ጨዋታዉ ተጀምሮ ሊያልቅ አከባቢ ሁለታችንም አንድ አንድ "Goal" አግብትን ነበር። የመጨረሻዉ ፊሽካ ከመነፋቱም በፊት ጓደኛዬ በራሱ ወደ ግብነት ሊቀይረው የሚችለው ንፁህ አጋጣሚ አገኘ ፣ እሱ ግን ሁሉንም ካለፈ ቡሃላ ለራሱ ማግባት ትቶ ኳሱን ለኔ አቃበለኝ። እሱ ቢያገባዉ ይመረጡት ነበር እሱ ግን ራሱን ትቶ እኔን አስመረጠ። ከጨዋታዉ ቡኃላ ለምን እንዲ አደረክ ብዬ ስጠይቀዉ "አንተ ከኔ የተሻልክ ስለሆንክ ይገባሃል" አለኝ። በሂወቴ ትልቁ ባለዉለታዬ እሱ ነዉ።"
ጋዜጠኞቹ ይሄን ነገር ለማረጋገጥ የጓደኛዉ ቤት ይሄዱና ጓደኛውን ስለዚህ ጉዳይ ይጠይቁታል።

ጓደኛዉም: "እዉነት ነዉ ብጊዜዉ እሱ ከኔ የተሻለ ተጫዋች ነዉ። ያኔ እኔ ጎሉን
አስቆጥሬ ተመርጬ ቢሆን የሱን ያህል ስኬታማ አልሆንም ነበር።" ጋዜጠኞቹ: "እና አሁን ኳስ ተጫዋች ነህ?? ወይ ምንድነዉ የምትሰራው?" ሲሉ ይጠይቁታል

ጓደኛዉ: "ኳስ ተጫዋች አይደለሁም።" ምንም ስራ የለኝም" ሲል ይመልሳል።
ጋዜጤኛ: "ታዲያ እንዲ የሚያምር ቪላ ቤት እና ድልቅቅ ያለ ሂወት ከየት ነዉ??"

ጓደኛዉ: "ያኔ ዉለታ የዋልኩለት ጓደኛዬ ነው እንዲ አንቀባሮ የሚያኖረኝ።" ታዲያ ይሄ የአለማችን ፈርጥ፣ ምርጥ ስብዕናው ጥንካሬ በመላበስ የበርካታ
ሪከርዶች ባለቤት፤የእግር ኳስ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው፣ በየሄደበት ክለብ በስኬት ማማ ነጋሹ።
ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጀምሮ በማን.ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድና በበርካታ የሊግ ዋንጫዎችና በሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሸብርቆ በሁለቱም ክለቦች የበዙ ጎሎችን አስቆጥሮ በተለይ በማድሪድ ቤት የክለቡ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ አሁንም በጁቬ ምርጥ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። ዛሬ ልደቱ ነው መልካም ልደት!

@wegoch
@wegoch
@paappii
ቢል ጌትስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም በነበረበት ወቅት ካንተ የሚበልጥ ሀብታም አለ ወይ? ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ የሚል አስገራሚ ምላሹን ሰጥቶ ነበር
<<ከብዙ ዓመታት በፊት ኒውዮርክ ኤርፖርት ውስጥ ጋዜጣዎችን ሳይ አንዱ
ጋዜጣ ላይ የተፃፈውን ርዕስ ወደድኩትና ጋዜጣውን ልገዛው ፈለኩ ነገር ግን
ምንም ገንዘብ አልነበረኝምና ጋዜጣውን አስቀምጬው ስሄድ የተመለከተኝ አንድ
ጋዜጣ ሻጭ ጥቁር ልጅ ጠራኝና 'ይህ ጋዜጣ ያንተ ነው ውሰደው' አለኝ። ምንም ገንዘብ የለኝም ልገዛክ አልችልም ስለው ምንም ችግር የለውም ውሰደው ብሎ ጋዜጣውን ሰጠኝ ከሦስት ወር በኋላ እዛው ኤርፖርት ሄድኩና ከዛ ጋዜጣ ሻጭ ልጅ ጋር ተገናኘን በአጋጣሚ አሁንም ጋዜጣ ልገዛ ፈልጌ ገንዘብ አልነበረኝም አሁንም ልጁ ጋዜጣውን በነፃ ሰጠኝ አሁንስ ደግሜ ልቀበልክ አልችልም ብለው አትጨነቅ ውሰደው ሰጥቼሃለሁ ብሎ ጋዜጣውን በነፃ ለሁለተኛ ጊዜ ሰጠኝ። ከ19 ዓመት በኋላ ሀብታም እንዲሁም ታዋቂ ሰው ሆንኩ በዚህን ጊዜ ልጁን አግኝቼ ብድሩን ልመልስለት ማፈላለግ ጀመርኩ ከአንድ ወር ፍለጋ በኋላ አገኘሁት ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ ብዬ ጠየኩት እሱም <<አዎ ዝነኛው ሀብታም ቢልጌትስ ነህ>>አለኝ። እኔም ከብዙ ዓመታት በፊት ሁለት ጋዜጦችን በነፃ ሰጥተኸኛል እናም ብድርህን ልመልስልህ እፈልጋለሁ ስለዚህ የምትፈልገውን ሁሉ ንገረኝና ላድርግልህ አልኩት እሱም <<ምንም ነገር ብታደርግልኝ ብድሬን መመለስ አትችልም>> አለኝ። እኔም በጣም ተገርሜ ለምን አልኩት እሱም <<እኔ የሰጠሁህ ደሀ እያለሁ ካለኝ ላይ ቀንሼ ነው አንተ ግን የምትሰጠኝ ሀብታም ሆነክ ከተረፈክ ላይ ነው ስለዚህ ብድሬን ልትመልስ አትችልም>> አለኝ። እኔም በእርግጠኝነት ያ ልጅ ከእኔ የበለጠ ሀብታም መሆኑን ተረዳው።

@wegoch
@wegoch
@paappii

From Daniel bekele page
ወንድ አያቴና ቅዳሜ

በልጅነቴ የተወሰኑ አመታትን በአያቶቼ ቤት እኖር ነበር።ከእነርሱ ቤት ከነበረኝ እድገቴ ይልቅ የወንድ አያቴ(አባባ፣አባዬ) እውነት መሳይ አፈታሪኮች ናቸው ይበልጡን ትዝ የሚሉኝ።የሚገርመው እስከአሁን ካስቆጠርኩት እድሜዬ እኩል አንዳንድ እኩያ እምነቶቼ በአያቴ ተረቶች የተገሩ እና የተፀነሱ መሆናቸው ነው።

የአባዬ ጨዋታዋች እና ሰው ነቃብኝ የሚል ሀፍረት የማያውቁት መሰረተ ውሸት ተረቶች ለጨቀላ አይምሮዬ የተስማማው ይመስል ከሴት አያቴ (እታቴ)ይልቅ ከእርሱ እግር ስር አልጠፋም ነበር።ለነገሩ ከእጁ መፅሀፍ ወይም ጋዜጣ ስለማይጠፋ የፈለገውን አልተገናኝቶም እውነት መሳይ ታሪኮች ቢሰነዝር ሁሉም ያምነዋል፣ተማሩ የተባሉትም።አንዳንዴ የውሸት ተረቶቹን ምንጭ እራሱን ማድረግ ሲሰለቸው "ፀሀፊው እንትና" "ፈላስፋው እንትና" እንዳለው ብሎ ያላሉትን ማላከክ ይቀናዋል።ግን ከሁሉም የሚገርመኝ እራሱ በፈጠራቸው እነኚ አፈታሪኮች አብሮን እንደአዲስ እንደሰማ ሰው ከት ብሎ የሚስቀው ልማዱ ነው።እነዚህ ከዘመነ "ማስተዋል" ተብዬው በኋላ ያሉኝ ግመገማ መሳይ ትውስታዎች ናቸው።እየተወላገድኩ በምሄድበት በዛ ጨቅላነት ግን ቁጥር አንድ አጨብጫቢው እንደነበርኩ እታቴ አጫውታኛለች።ሌሎቹን ባህሪያቶቼን ስትነግረኝ "በጣም ጠያቂ ነበርሽ" ትላለች ፤ "እናም መልሶች እንዲሰጥሽ ለሁሉም ጥያቄዎችሽ አባትሽን(አያትሽን ማለቷ ነው) እናጋልጠው ነበር ከዛም በእናንተ ንትርክ እንዝናና ነበር"ብላኛለች።


ከአባዬ ጋር ከምገጥመው ንትርክ የማይረሱ ትውስታዎቼም ቅዳሜ ዋነኛው ነው።

ቅዳሜ የተወለድኩበት ቀን ነው።ይህን በጨቅላነቴ ከእናቴ አፍ ስለሰማውት አውቀው ነበር።
አንድ ቀን እንደተለመደው አያቴ አባባ መፅሀፉን አንጠልጥሎ፣በጋቢው ተጠቅልሎ ከማለዳ ፀሀይ እየኮመከመ እኔም ስለቅዳሜ ያለኝን ጥያቄ ላቀርብለት በትንሽዬ አይምሮዬ ስሰናዳ ተገጣጠምን። "እሺ ቡጡዬ(አሁንም በዚህ ኮረዳነቴ ቡጡ እያለ ነው የሚጠራኝ)ተነሳሽ" አለኝ።ትንንሽ አይኖቼን በትንንሽ እጆቼ እያሻሸው "አው አባባ"አልኩና ተንደርድሬ ከእግሩ ስር ያረፍኩበትን ሳላስተውል ዝፍዝፍ አልኩ(እቴት እንደነገረችኝ)።
ያደረ ጥያቄዬን በልጅነት አይምሮዬ አለመርሳቴ አሁን ላይ ሳስበው የቅዳሜ ሚስጥርን ማወቅ እንደነበረብኝ ከላይ የተፃፈልኝ ይመስለኝና ፈገግ እላለው።
ከዛማ ሽቅብ እያየውት "አባባ …አባ አባ… እ… እ… ማሚ(ማሚ አትበይ እማ ነው የሚባለው ንትርኩ ዛሬ ትዝ አላለውም) ለምንድነው ከቀኖች ኡሉ መርጣ ቅዳሜ የወለደችኝ? እኔኮ አሙስ ነበር የምፈልገው" አልኩት።ሳቅ አለ።ሳቁ ኤጭ ይኚ ጥያቄዎችሽ የሚል ሀሳቡን እንዲደብቅለት ይመስላል(እቴት እንደነገረችኝ)።
ነገር ግን እሱ አባባ ነው መልስ አያጣም ፤ቢያጣ ቢያጣ እንኳ ያላስፈቀደበትን ሀሳብ ብድር ይገባል (ከመፅሀፎቹ)።ጥያቄዬ ቢያሰለቸውም አላውቅም አይልምና ወሬውን ለማሳመር አቀማመጡን አስተካከለ።
እኔም "ቀድሞ የሚሰጠኝን ርህራሄ ከመንጠቁ በፊት" የሚል ሀሳብ የመጣልኝ ይመስል አይኖቼን ሽቅብ 'መልስልኛ አላሳዝንም' በሚመስል አፈጠጥኩበት።አያቴ ተመቻችቶ እነዛን ተረቶቹን አዋቅሮ ሲጨርስ ቀጠለ።
"ቡጡ ይኧውልሽ 'ቅዳሜ' ማለት 'ቅድመሰንበት' ነው።ሰንበት ደግሞ የእረፍት ቀን ነው፤ስለዚህ ባንቺ ቀድመን ልባችንን ልናሳርፍ ፈለግንና ለእናትሽ ነገርናት"አለኝ።ለትንሽዬዋ እኔ መልሱ ተልቆብኝ ይሆን እንጃ ሌላ ጥያቄ ፈጠረብኝ። "እእ አባባ ሰንበት ምንድን ነው?"

በውስጡ አዪዪዪ ያለ ይመስል ትንሽ አሰብ አደረገና ከሰጠኝ ትርጉም ውስጥ ሰንበትን ለማስወገድ ወሰነ።

ብዙ ጊዜ ሳስቸግረው ከጥፋቴ ሊሰበስበኝ ሲያስብ አንድ አፈታሪክ ጣል ያረግብኛል።እንደውም ትዝ የሚለኝ ለእንግዳ የቀረበ ብርትኳን እየበላው ሳስቸግር የዋጥኳቸውን የብርትኳኑን ፍሬ በግምት ቆጠረልኝና "ሆድሽ ውስጥ ይበቅላሉ" ካለኝ ጀምሮ ብርትኳን አጠገብ ድራሼም አይገኝም ነበር።ያህንን በሚመስል ታሪክ ስለቅዳሜም እንዲ አለኝ።…


ቆፍጠን ባለ ድምፅ" ይገርምሻል ቡጡዬ የቤተሰባችን አንድም አባል በምንም ነገር ተቀድመን ተበልጠን አናውቅም።ሁሌም ቀዳሚ እንደነበርን ነው።እናም ይህን እኛ አያቶችሽ ለእናትሽ እንዳወረስናት ትልቅ መለያ እንዲሆን አስባ ቅዳሜ ወለደችሽ።ቅዳሜ ማለት 'ቀዳሚ ' 'ቅደሚ 'እንደማለት ነው። በነገራችን ላይ የሳምንቱም የመጀመሪያ ቀን ነው አንዳንድ ምሁራን ይላሉ" ብሎ ብቻውን ላለመጠቆር እነሱ ላይ በትንሹ አሳቦ ጠቆመ።
አይ አባባ! የሚገርመው አሳመነኝ ቀጣይ ጥያቄ ሳልጠይቅ ተቀበልኩት።
ከማመንም አልፌ እውነታ እየመሰለኝ በነገሮቼ ቀዳሚ ለመሆን ይበልጡን እተጋ ጀመርኩ።በዛው ለምዶብኝ በእድገቴም ስገፋ መትጋትን መለያ አረኩት።አይ አባዬ! ይን አስቦ ተረቱን ባይነግረኝ እንኳ
በእድሜ እየላቅሁ ስመጣ በሰባቱም ቀናት ውስጥ ትርጉም የምሰጠው እኔው እራሴ እንደሆንኩ ሳስብ የሁሉም ቀናት ተመሳሳይነት ይጎላብኛል፤ ግን አባባ እና እነዛ ተረቶቹ ባለውለታዬ ሆነዋል።በጨቅላ አይምሮዬ ላይ የፃፈው አያቴም የራሱን ታሪኮች ሲከተል ስላየው በቅዳሜ መቅደምን ካስተማረኝ ይበልጥ 'መከተልን' ስላወኩበት ከአሁኑ ማስተዋሌ የልጅነቴን ንፁህ እምነት እናፍቀዋለው።

መልካም ቅዳሜ💜
ቅዳሚት💜

@getem
@getem
@paappii

#heavቨን
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የቀጠለ #3 )

"ልጅ ልሰጥሽ ስለማልችል ትተይኛለሽ?" አለኝ

"ስንጋባም መውለድ እንደማትችል ታውቅ ነበር?"

"አዎ "

"ለምን አልነገርከኝም?"

"እንዳላጣሽ ፈርቼ። ብነግርሽ ኖሮ ታገቢኝ ነበር?"

"ምርጫ አልሰጠኸኝምኮ! ከልጄና ከፍቅርህ እንድመርጥ ምርጫ አልሰጠኸኝም! ራስህን ራስህ መረጥክልኝ!! "

"እኔ ብሆን ልጅ አልሰጠሽኝም ብዬ አልተውሽም! ይሄን የሚሻገር ፍቅር አለኝ። "
(ከዚህ በላይ የሚሆን ፍቅር ከሌለሽ ተይኝ የሚል መልእክት ነው ያለው።)

የዛን ቀን ባሌ የሆነ መገኘቱ ከልቤ ላይ ግምስ ሲል ታወቀኝ። ግን ምንም አላልኩም። እንዴት እንደሆነም ለራሴ መግለፅ ይከብደኛል። በቃ ግምስ ብሎ ተናደብኝ። ፈልጌው ነው? የሆነ ሴትነቴን አታሎ የቀማኝ መሰለኝ። ግን ዝም አልኩ።

በሆነ መንገድ ራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበታል!! ቆይ መውለድ ትችላለህ ወይስ አትችልም? ተብሎ ይጠየቅ ነበር? እንደማይችል ሲያውቅ ሊያሳውቀኝ ይገባ የነበረው እርሱ አልነበር? ግን በቃ ይችልበታል። ማጣራት ነበረብኝ ብዬ ራሴን ወቀስኩ። ዝም አልኩ።

'እናት ልታደርገኝ ስለማትችል በቃኸኝ!'ይባላል? አይባልም! መሃን ስለሆነ ፈታችው ሲባል ጆሮ ላይ ጭው ይላል አይደል? ዝም አልኩ!

ለአመታት ዝም አልኩ። ስራ ይሸኘኛል። ከስራ ይመልሰኛል። ቁርስ ያበስልልኛል። ምሳ አበስላለሁ። እራት ያበስላል። እሱ ምንም ዝንፍ ያለ ነገር የለውም። ደከመኝ ያልኩ ቀን እግሬን አጥቦ አሽቶ ያስተኛኛል። ሲለው እንደሰርግ ቀኔ ተሸክሞ ወደአልጋ ይወስደኛል። ሞከርኩ። የተጋባን ሰሞን ይሰማኝ እንደነበረው ሲነካኝ ደስ የሚለኝን ፣ ሲስመኝ አልጋው የሚያምረኝን እሳት ላመጣው ታገልኩ። አቃተኝ!

ምንም ሳያወራ እራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበት የለ? እሱ እንዲህ ጥሩ እየሆነልኝ እኔ ለምን እንደሱ መሆን አቃተኝ እያልኩ ራሴን ረገምኩ። ፍቅሬ ስላለቀ ራሴን ወቀስኩ::

ፍቅር መስራት ፍቅር መስራት መሆኑ ቀርቶ ስራ መስራት ሆነብኝ። በአፌ እንቢ እንዳልለው የምሰራው ስራ አለኝ በሚል ሰበብ እሱ እንቅልፍ እስኪወስደው እየጠበቅኩ መተኛት ሆነ ልምዴ። ማምለጥ ያቃተኝ ቀን እሱ ላቡ ጠብ እስኪል ሲለፋ እንባዬን እንዳያይ እታገላለሁ። (አንዳንዴ የኔ ባል ብቻ ነው የገነት በር ይመስል የማህፀን በር ላይ እንዲህ የሚተጋው? የሚል ሀሳብ ይመጣልኛል። ተፈጥሮ እንኳን እንዴት አይነግረውም? ደርቆ እያታገለው በምራቁ እያራሰ የሚጋጋጠው የዘለዓለም ህይወት ሊያተርፍበት ነው ወይስ የስጋ ደስታ?)

እንደደነዘዝኩ ብዙ ዓመት ዓመትን ደረበ።
በትዳር ብዙ የቆየች አብራኝ የምትስራ ሴትን "እሱ ነገር እንዴት እየሄደልሽ ነው?" ብሎ መጠየቅ ያምረኝና ስንቴ ከአፌ እመልሰዋለሁ።

ከብዙ እንዲህ ያለ ቀናት በኋላ አለቃዬ ሊያማልለኝ ጀመረ። የሆነ እለት እጄን ሲነካኝ ባሌ ድሮ ሲነካኝ የሚሰማኝ እሳት ተሰማኝ። ባልሰማ አለፍኩት። ግን ሰምቼዋለሁ! ወላ ፈገግ ብያለሁ ለራሴ 'ለካ የሆነ ነገር ጎድሎኝ አይደለም።' አልኩ:: ጭራሽ ይሄ ነገር ከመሽኛነት ውጪ ለራሴ ጥቅም ላላውለው ነው ብዬ ተስፋ ቆርጬ ነበራ!! ባለግኩ!

ከቅሌቴ በኋላም እሱ ዝንፍ ያለ ነገር የለውም። ሳይናገር ራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበት የለ? ዝምታው "አየሽ ብትሄጂብኝም ስለማፈቅርሽ እንዳጣሽ አልፈልግም" የሚል መልእክት አለው።

ዛሬ ልፋቱ ይቅርብኝ ያልኩ ቀን ያለ ምንም ቃል "ምነው ለኔ ሲሆን ነው? ለማንም ጠረጴዛ ላይ አንጋለሽው አልነበር?" የሚል መልእክት ያስተላልፍልኛል። እንዴት ነው ግን ሳያወራ መልእክቱ የሚደርሰኝ? እናቴ ቤት ሄድኩ።

የሆነውን እና የሚሰማኝን ሁሉ ለእናቴ ነገርኳት። ከሁሉም አብልጣ የሰማችኝ ከአለቃዬ ጋር መባለጌን ነው። ዘገነንኳት።

"ይሄን ጉድሽን ለራስሽ እንኳን ደግመሽ እንዳትናገሪ! በይ ሂጂና ይቅርታ ጠይቂው! እንዴት ያለው እግዚአብሄር የባረከው ነው? ከነዚህ በደልሽ ልቀበልሽ ማለቱ? ደሞ ካንቺም ብሶ ቤትሽን ለቀሽ ትወጫለሽ?" አለችኝ። እሱ ይቅርታ እስክጠይቀው አልጠበቀም። እናቴ ቤት ድረስ መጣ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስሞኝ ይዞኝ ተመለሰ።

ስንኖር .....ስንኖር ብዙ ስንኖር ነው የስልኩን መልእክት ያገኘሁት።

የሆነ ስርየት የሆነልኝ የመሰለኝ። እነሆ ሀጥያቴ በሀጥያቱ ታጠበ ......

የሚገርመው አልጨረስንም ...

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ሄድ፣ ሄድ፣ ሄድ መለስ. . . ደሞ ጎርደድ መለስ ድሮ ክፍል ውስጥ አስተማሪ ጥያቄ ጠይቆ የሚመልስ ተማሪ በሚፈልግበት ቅፅበት የሚሰማኝ ስሜት ነበር። የራስ ጋር ክርክር "መልሱ ይሄ ነው፣ መልሺ። እርግጠኛ ነሽ መልሱ እንደዚህ ነው ግን? እኔንጃ፣ መሰለኝ። ማንም እጁን አላወጣም፣ እጅሽን አውጪ። አውጥተሽ ስህተት ከምትሆኚ ባታወጪሽ? ምን ታጫለሽ? ግን መልሱን ካወቅሽውሽ? ግን ለምን በፍቃድሽ ራስሽን በሌሎች ለመዳኘት ታጋልጫለሽ? አለመታየት ማንን ገደለ? . . . " በራስ አለመተማመን እና የስህተት ፍራቻ ተዳቅለው (ማን እንዳዳቀላቸው እንጃ lol) በፈጠሩት ጥርጣሬ የማውቀውን ነገር ሳልመልስ እቀራለሁ። ምናልባትም የእድሜ ጉዳይ የሚቀይረው ነገር ይሆናል ብዬ አምን ነበር። እውቀቴ እየሰፋ ሲመጣ በራስ መተማመኔም ይጨምራል አይነት ነገር።

* * *
post ከዛ delete ወዲያውኑ "አስቂኝ ነገር አይደል ለምን አጠፋሽው? there is so much going on, የመቀለጃ ጊዜ ነው አሁን? ደሞ you were being insensitive ለእነዚህ ሰዎች። እርግጠኛ ነኝ ላንቼ ብቻ ነው የታየሽ offen-ሱ። በዛ ላይ ደግሞ you are sharing too much፣ ስላንቺ ህይወት ማን ይሄን ያክል interest ይኖረዋል? ሰፋ አድርገን ደግሞ እንየው። ለምንድነው ሶሻል ሚዲያ ላይ ያለሽው? ምንድነው purpose-ሽ? what are you trying to accomplish? what are you getting? how does this post tie in with that purpose? ሁሉም ነገር በምክንያትና በpurpose ነው ያለው ግን ማነው? I am so annoying! ይኸው፣ አጠፋሁት! case closed"
* * *
send a message፣ unsend
"እንዴ መለሰ አልመለሰ እያልኩኝ ለምን እጨናነቃለሁ? ባልልከውስ ኖሮ? ግን
you wanted to share that with him . . . "

* * *
ትልቅ እሆናለሁ፣ አለምን ለውጣለሁ. . . ግን ባትለውጪሽ? "what makes you so special ቆይ? እስቲ ተይኝኝኝ . . . "
* * *
የሚያደናብሩ ድንበሮች፣ እየተገነባ ያለ ማንነት፣ የስህተት ፍርሀት . . . ሄድ ከዛ
መለስ . . .አንድ ቀን ደፍሬ እሄድ ብቻ ይሆናል። ይሄም ይጠፋ ይሆናል lol

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Hewan Hulet Shi
የሁለት ሰዓቱ ጦርነት!
((Maggie)) #1


እኛ ቤት ዘወትር ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሰላምና ፀጥታንን ማግኘት ማለት በድቅድቅ ጨለማ ያለባትሪ(ኧረ በባትሪም ይሁን!) መርፌ እንደመፈለግ ነው.

ብርሀን ከሚጓዝበት ፍጥነት ቀድመው ወሬ ሚያራግቡ የሀገራችን ሚዲዎችን ጨምሮ እነቢቢሲ እነአልጀዝራ....አላዩትም እንጂ ...እስከዛሬ ከዘገቡት የጦርነት ዘገባ ዎች ይልቅ በእጥፍ ገበያን(ተመልካች) ሚያመጣለቸው ትኩስ ወሬ የመሆን አቅም ያለው ጦርነት ነበር!

ይህንን ያወኩት..... ባለፈው ትንሹ ወንድሜ የአማርኛ መምህራቸው 'ዜና የሚሆን ዘገባ አዘጋጅታቹ ኑ' የሚል የቤት ስራ ሰጥታቸው .......... አቡሻዬም (የ4ኛ ክፍሉ እንቦቅቅላ) ...... ይህንን የሁለት ሰዓቱን የኛን ቤት ጉድ ዘግቦ ሄዶ ..በኮልታፋ ምላሱ አንብቦ (እዚጋ... እኔ አልነርኩም ሲያነብብ! ገምቼ ነው!) "መክዲዬ አማሊኛ አሽልካሽል አመጣውኮ!" እያለ ምላሱን በወለቀው የፊት ጥርሱ እያሾለከ የነገረኝ ግዜ ነበር!

ኧረ እንደውም የሆነ ግዜ ጦረነቱ ከኛ ቤት (ከግንባሩ!) በወሬ ደረጃ ሾልኮ ወጥቶ (በጎረቤታችን ምሬት የወለደው ወሬ አማካኝነት...... አቡሻዬም ሊሆን ይችላል!) ለሰፈሩ ያንድ ሰሞን የቡና ማድመቂያ ሆኖ ነበር!

ፀሀይ ስታሸልብ የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ወደቤት የሚከትትበት ግዜ ነው። ከየስራው ከየትምህርትቤቱ ከየቡዘናው ብቻ ከየትም ይሁን በጦርነት ግዜ "ክተት!" እንደተባለ ጦረኛ ይከትታል....

እስከ 1:59 ደቂቃ ድረስ... የጋብቻ አማካሪዎች ፣የስነልቦና ባለሞያዎች ፣የፍቅር ክሊኒክ መካሪዎች.....እንዲፈጠር የሚለፉለትን አይነት ቤተሰብ ሆነን እናሳልፋለን... እራት ይቀርባል... ቡና ይፈላል... ሽር ጉዱ.... የ"ውሎ እንዴት ነበር" ጥያቄው.... ቀልድና ጨዋታው.... ጉሸማው.... ያቡሻዬ የትምህርት ቤት ውሎ ትረካው.... የ"እዚጋ እንጀራ ይጨመር ...ወጥ አንሷል....ሚጥሚጣ አቀብዪኝ" ትዕዛዙ ................ ብቻ ምን አለፋቹ በየቲቪው ላይ የምናየውን አርአያ (ሞዴል!) ቤተሰብ እንሆናለን

ችግሩ ሚመጣው 2:00 ሰዓት ሲሆን ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Maggi
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Meba)
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_2_ቁጥር_7_edited85.pdf
4.9 MB
#ቅንድልዲጂታልመጽሄት
ቅጽ-2 ቁጥር-7 ተለቀቀ
ያንብቡና ብዙ ያትርፉት
ቅንነት ድል ያደርጋል!
Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

Kendel on youtube
http://www.youtube.com/channel/UCMvSL9y2zS3KGmUfXEgSM_w
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የቀጠለ #4)

ባሌን እንዲህ እፍፍፍ ያስደረገችውን ሴት ለማየት "የተለመደ" ቦታቸው ባሌን ተከተልኩት። ከስራ እኔን እቤት ካደረሰ በኋላ ነው የወጣው። የጀበኛ ቡና የሚሸጥበት ቤት? ይሄ ነው የተለመደ ቦታቸው? መኪናውን አቁሞ ወረደ። ታክሲውን አስቁሜ በዓይኔ ተከተልኩት።

ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣች ከነበረች ሴት ጋር በፈገግታ ተጠባበቁ። የሚሉት አይሰማኝም። ተንጠለጠለችበት። ወገቧን ይዞ ወደላይ ተሸከማት። አነሳት አይደል? አዎ በትክክል! እግሮቿን አንጨፍርራ ተንጠለጠለችበትኮ! ምን ዓይነቷ ቀለብላባ ናት? ለወትሮ እሱስ ቢሆን ቅልብልብ ሴት አይወድም አልነበር እንዴ?

ሁለት ቀን ነው ያልተገናኙት ምንድነው ባህር አቋርጠው ከርመው የሚመጡ የሚያስመስሉት? ወደመሬት ከመለሳት በኋላ ሳመችው። ከንፈሩን ሳመችው። እጅ ለእጅ ተቋልፈው ትንሿ የጀበና ቡና መሸጫ ቤት ውስጥ ገቡ።

ይሄ ሁሉ አልጎረበጠኝም። ባሌ ማመንዘሩን ማረጋገጤ ደስ ብሎኛልኮ! ደስታዬን ምን ሸረፈው ታድያ? ቆንጆ ናት! የባሌ ወሽማ ቆንጆ ናት! የባሌ ወሽማ ባትሆን ኖሮ መንገድ ባገኛት "ስታምሪኮ!" የምላት ዓይነት ቆንጆ ናት

የባል ወሽማ ቆንጆ ስትሆን ደስ የማይል ስሜት አለው። 😜

"እዚህ ነው የምትወርጂው? ምንድነው?" ሲለኝ ባለታክሲው እንደመባነን አደረገኝ። የእናቴን ቤት አድራሻ ሰጠሁት።

"እማ ባሌ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት አለው!" አልኳት አባዬ እስኪወጣ የባጥ የቆጡን ስቀባጥር ቆይቼ

"እርግጠኛ ነሽ?"

"አዎን "

"በይ ስሚኝ ልጄ ሴት ልጅ የተለየች የሚያደርጋት ብልሃትዋ ነው። ባልሽን ልቡ ወደቤቱ የሚመለስበትን ጥበብ ዘይጂ .." አላስጨረስኳትም!

"እህህ እማ ....አጥፍቼም የኔ ሃላፊነት ነው! አጥፍቶም የኔ ሀላፊነት ነው? ምንም አልገባኝም! የቱ ነው የሚያሳስብሽ? የኔ ያለባል መቅረት ነው የሚያሳስብሽ ወይስ የኔ ደስተኛ መሆን? እኔ ስለሚሰማኝ ስሜት አንድም ቀን ግድ ሰጥቶሽ አያውቅም። ግድ የሚሰጥሽ ትዳር ውስጥ መቆየቴ ብቻ ነው!! እየኖርሽ ካልሆነ በትዳር መኖር ትርጉሙ ምንድነው? "

"አይ ልጄ እኔና አባትሽ 40 ዓመት በትዳር ስንቆይ ለመለያየት ምክንያት የሚሆን ፈተና ስላልገጠመን ይመስልሻል? በብልሃትና በትዕግስት አልፈነው ነው"

"እማ እስኪ ዛሬ እንኳን በጭንቅላትሽ ሳይሆን በልብሽ ስሚኝ? ደስተኛ አይደለሁም እኮ ነው የምልሽ! ሌላ ሴት ጋር ሲሄድ የመገላገል ስሜት ነው የተሰማኝ! የኔ ደስተኛ መሆን አያሳስብሽም? "

ዝም አለች! ደነገጠች። ለወትሮው የምትለው የማታጣው እናቴ ዝም አለች።

"እሺ ትዳርሽን አስመልክቶ እንዲህ አድርጊ እንዲህ አታድርጊ አልልሽም። አንድ ልጄ ነሽ! ከምንም በላይ ደስታሽ ያሳስበኛል። ደስታ ግን አንቺ እንደምትዪው ባል ወይም ሌላ ሰው የሚሰጥሽ ነገር አይደለም። ደስታን ውስጥሽ ፈልጊው። የቱጋ እንዳጣሽው አስቢና። ፍለጋሽን ከዛ ጀምሪ!" አለችኝ በመጨረሻ! አልገባኝም! ወይም እንዲገባኝ አልፈለግኩም።

"ተይው በቃ ሲጀመርም ላንቺ መንገር አልነበረብኝም!" ብያት ወደቤቴ ተመለስኩ። ስደርስ ባሌ እቤት ነበረ። እኚህ ደግሞ እንደዛ ሲንጠላጠሉ ሁለት ቀን የሚበቃቸው አይመስሉምኮ ለሁለት ሰዓት ነው እንዲያ ሚመሳቀሉት?

"የት ሄደሽ ነው? የምትሄጂበት ቦታ እንዳለሽ ባውቅኮ አደርስሽ ነበር።" አለኝ

"እናቴጋ ሄጄ ነው" አልኩት ከንፈሬን ሊስመኝ ሲጠጋ ጉንጬን አቀብዬው

"ምነው ደህና አይደለሽም? "

"እናቴጋ ለመሄድ የሆነ ነገር መሆን አለብኝ? "

"ከዓመት በዓል ውጪ እናትሽጋ የምትሄጂው ሲከፋሽ ነው ብዬ ነው።" (ነግሬው አውቃለሁ? አላውቅም! እኔ ራሴ ያስተዋልኩት አሁን እሱ ሲለኝ ነው። በምን አወቀ?) ዝም አልኩ። ምንም እንዳልተፈጠረ እራት ያሰናዳልኝ ገባ! የእውነቱን ነው? እንዴት ነው እየበደለም እየተበደለም ያው ራሱ ሰውዬ መሆን የሚችልበት? ነውስ እሱም እንደእኔ እኩል ለኩል ነን ብሎ ነው የሚያስበው?

"እኔ በልቻለሁ" አልኩት። .....ብቻውን በላ

"ደክሞኛል ዛሬ!" ብዬ የጀመርነውን ተከታታይ ፊልም ሳላይ ወደመኝታ ቤት ገባሁ። እኔ ካላየሁ እንደማይቀጥለው አውቃለሁ። ተከትሎኝ ወደአልጋ መጣ። ጀርባዬን ሰጥቼው ትንፋሼን ሰብስቤ አንሶላውን ገልጦ ሲገባ ሰማዋለሁ። ከጀርባዬ አቀፈኝ። አንገቴ ስር በስሱ ሳመኝ። ሁሌም እንደሚያደርገው አንድ እግሩን ታፋዬ ላይ ጭኖ እጆቹን በጡቶቼ ዙሪያ አቆላልፎ አቅፎኝ ተኛ። 1 ደቂቃ .......2 ደቂቃ ......3 ......5 ......10 .....20 ... ተኝቷል።

ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ያልነካካኸኝ ይባላል?

.........አታፍጡብኝ አልጨረስንም......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
የሁለት ሰዓቱ ጦርነት!
((Maggie)) #2


ከ dining room ( ቡፍፍፍፍፍ! ሙድ ስይዝ ነው ባካቹ! ዳይኒንድ ሩም ምናምን የለም! ለምን እንደሆነ ኋላ ትደርሱበታላቹ) .....ለማንኛውም የቱ ጋ ነበርኩ?? ....አዎ..... በልተን ጠጥተን ወደ ቲቪ (እንደምን ዋልሽ አለም!) ልንል ስንሰበሰብ ይሄኔ ቅድም አንድ የነበረው ቤተሰብ ወደ ሁለት ጎራ ይከፋፈላል.

"ዜና ነው ምናየው!" እና "የለም! ቃና ነው ምናየው!" በሚል ሁለት ጎራ! ይሄኔ ነው ክትክቱ ሚጀምረው! ያንጋፋዎቹ ፓርቲ "ዜና" ሲል "የጎረምሳዎቹ ፓርቲ ደግሞ "ቃና" ይላል (እዚጋ አቡሻዬ ወደ አልጋው ስለሚሄድ እዛው ሆኖ ይታዘበናል. ልክ እኛ እንትናና እንትና ሲከታከቱ በራድዮ ሆነን እንደምንሰማው!)

"ሀገራችንን እየኖርባት ....ስላለችበት ሁኔታ የማወቅ መብትም ግዴታም አለብን!" ብለው ይከራከራሉ አንጋፋዎቹ( እናት አባት ና አያታችን(ያባታችን አባት))

"ኖ! እኛም አዕምሮዋችንን ማዝናኛ ቃናን ማየት አለብን! ሀገችን ሰላም ብትሆን አይደል እየኖርንባት ያለነው!" ጎራምሶቹ! (እኔ ታናሽ እህቴ መስኪ እና "3 አመት ትበልጣታለህ እንጂኮ ያው እኩያ ናቹ!" እሚባልለት ታላቅ ወንድሜ ቃልአብ)
..
... ወይ ውሳኔ ይወሰንና አንድ ተጨማሪ ቲቪ ከነዲሹ ይገዛልን! (11ኛ ክፍሏ መስኪ)

"ይች! ቅሪንዳምስ! ደሞ እነዚየን እኛን ቲያቅታቸው ቋንቋችንን ወስደው ሚያጃጅሉንን ከፍተሽ ጥናት ወድያ ሰንብች ልትይ ነው!" (አያቴ ነበሩ)

"አቦ! እዛ ውጪ ላይ ስራ ከመፈለግ የተረፈንን ግዜ ዘና ምንልበት ደና መደበርያ የለ እዚ ደሞ...እናንተ ......" (ምርር ብሎ ቃልዬ ነበር)
ባለፈው አመት ለመአረግ አስር ጉዳይ በሆነ ውጤት ተመርቆ ስራ መቀጠር ያልቀናው ወንድሜ!

"ሆዳቹን ልቻል? መዝናኛቹን?? ኢትዮጵያ ውስጥኮ ነው ያላቹት እናንተ!! በቀን አንዴ በስንት ውጣውረድ ሚበላበት አገር! ወዲያ አምጣ ሪሞቱን!" እማዬ ነበረች

አንጋፋዎቹ ፓርቲ ...."ዜና ይታይ!" የሚለው አቋማቸው ያሸንፍና (በጉልበት).... ያኮረፍን መኝታቤታችን ስልካችንን ወይ ያችን ግቢ እያለ ይጠቀምባት የነበረችውን የቃልዬ ላፕቶፕ ይዘን እንገባለን .......እየጎረበጠን የተስማማን ደግሞ እዛው ሆነን ዜና እናያለን.
..............

......

አንድ ቀን ታድያ ይህ የዘወትር ጦርነት ማብቂያውን አገኘ!

"እንዴት" አትሉም????


ይህንን ንትርክ ለማርገብ አስቦ ይሁን እንቅልፉን እየነሳነው ተቸግሮ እንጃ! ቻናሉን ለመቀር አሳማኝ ነው ምንለውን መከራከርያ እያነሳን ስንከራከር አቡሻዬ ከመኝታቤቱ መጥቶ መሀል ላይ ቆመና

"ቆይ ለምን "ዤ"ን እና "ቃ"ን አውትታቱ ..."ናና" አድልጋቱ አንድ ላይ አታዩም!" አለን እየተኮላተፈ

በዚ ግዜ አባቴ አንድ ነገር እንደበራለት ሁሉ...... አቡሻ ይህንን በተናገረ በማግስቱ የቤተሰብ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Maggi
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul Mekonnen 📷)
Do you need to Hold on the memorable #pictures you love ? Get yours and your beloved pictures #painted on leather.

Order perfectly wooden framed #painted_pictures and present it for:
#Graduation
#Birthday
#Anniversary ...

Contact us @gebriel_19
Or give us a call 0984740577

@seiloch
@seiloch
የሁለት ሰዓቱ ጦርነት!
((Maggie)) #3

መክሰስ ሰዓት ላይ አንዳንዳችን በሰዓቱ አንዳን ዳችን አርፍደን ተገኘን.

ኩሽናችን በር ላይ ... ግማሹ ድንጋይ ላይ ሌላው በርጩማ ላይ ... የተረፈው ያለቀ መክተፊያ ላይ ...... ተቀምጠን (አባ ብቻ ነበር መደገፊያ ያለው ወንበር ላይ የተቀመጠው እና አያቴ ዊልቼራቸው ላይ) ...አቡሻን እኔ አቅፌው ተኮልኩለን ከተቀመጥን ቦሀላ

"እእእ! የሁለት ሰዓቱን የጭቅጭቅ መንስኤ ፈትተን መፍትሄ እንድናቀርብ ነው የሰበሰብኳቹ?" አለ አባ!

እማ አፏን በሽሙጥ አጣመመች!
..
የሚወጣውን ወጣ የሚወርደው ወረደ የሚጨቀጨቀው ተጨቀጨቀ የሚያርረው አረረ... የሚፈተፈተውን ተፈተፈተ እና....... ይህ ውሳኔ ተወሰነ


ማታ ከ2:00 - 3:00 ሰዓት የዜና ሰዓት!
ከ3:00 እስከ ፈለግንበት ሰዓት የጎረምሶቹ! በተጨማሪ (የማታውን የሰዓት ቅነሳ መሰረት በማድረግ ) ቀን ከ7:00 - 8:00 ስዓት የዜና ሰዓት! እንዲሆን

አባዬ ከወንበሩ ተነስቶ ያቡሻን እጅ እየሳመ.... "አቡሻዬ እንዳንተ አይነት እውነተኛ ታዛቢኮ ያስፈልገናል... አመሰግናለው ልጄ!" ብሎት ወደ ቤት ገባ.

.........................................

ብዙ አቡሻዎች አያስፈልጉንም ትላላቹ??

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Maggi
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የመጨረሻ ክፍል ሊሆን የሚችል)

"እናውራ? ማውራት አለብን!" አለኝ አምስት ለሊቶች ሳይነካካኝ አቅፎኝ ካደረ በኋላ። አምስት ጠዋቶች ከንፈሬን ሳይስመኝ ደህና ዋዪ ካለኝ በኋላ:: አምስት አመሻሾች ደረቱ ላይ አቅፎ ግንባሬን ሳይስመኝ እንዴት ዋልሽ ካለኝ በኋላ....

"Finally" አልኩኝ ይህን እንዲለኝ ስጠብቅ እንደነበር በደንብ እያሳበቅኩ

"እንዴ? እንድናወራ እየጠበቅሽ ነበር? ማውራት ፈልገሽ ከነበር ለምን እናውራ አላልሽኝም?" ዝም አልኩ። እንዲህ ነኝ! ራሴን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ የማውቀው ከእናቴ ጋር ስሆን ብቻ ነው። እንዲህ ሲለኝ እንዲህ ብዬው በነበር የምለው ካለፈ በኋላ ነው። እንዲህ ማለት ነበረብኝ የምለው አለማለቴ መዘዝ ከመዘዘ በኋላ ነው። በተለይ ስናደድና ስከፋ ሰዎች የልባቸውን ብለውኝ ከሄዱ በኃላ ነው .... በራሴ ብስጭት እያልኩ 'እንዲህ ባልኩ ኖሮ' የምለው..

"ይሄ እኮ ነው ችግርሽ ምንም ሳታወሪ እንዳዳምጥሽ ትፈልጊያለሽ። ምንም ሳትጠይቂኝ መልስ ትጠብቂያለሽ። ለግምት እንኳን የራቀ ስሜት እያሳየሽኝ በልብሽ ያመቅሽውን ስሜት እንድረዳሽ ትጠብቂያለሽ::" እንዲህ ድምፁን ጮክ አድርጎ አውርቶ አያውቅም። መናደድ ይችላል ለካ! አሁንም ዝም አልኩ። በረዥሙ ተነፈሰ እና ደግሞ በራሱ ድምፅ ማውራት ጀመረ።

"እ የምነግርሽ ነገር አለ ......" እያለ እንዴት እንደሚነግረኝ ይታሽ ጀመር።

'አውቃለሁ' ልለው አስባለሁ ግን አፌ አያወጣውም። ሊነግረኝ ሲጨነቅ አየዋለሁ። እንደማውቅ ልነግረው እጨነቃለሁ። በመጨረሻ ከአፉ የወጣው ሊናገር የፈለገው እንዳልሆነ በሚያስታውቅ ሁኔታ 'ቆይ ሌላው ይቆይና ...' የሚል ለዛ ባለው ድምፅ

"ወደሽኝ ታውቂያለሽ ግን? በፍቅር? " አለኝ።

ደነገጥኩ። ምንድነው ያስደነገጠኝ? እንለያይ ወይም ከሌላ ሴትጋ ግንኙነት አለኝ እንዲለኝ ስጠብቅ ወድጄው እንደነበር ስለጠየቀኝ? ዝም አልኩ። አሁን ግን ያለመናገር አባዜዬ ሳይሆን መልሱን ስለማላውቀው ነው። ወድጄው የማውቅበትን ጊዜ ለማስታወስ ወደኋላ ተጓዝኩ። እሩቅቅቅቅቅቅ ነው።

"ይመስለኛል!" የሚል ቃል ነው ከአፌ የወጣው።

አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ። መሬት መሬቱን እያየሁ እንባው መሬቱ ላይ ጠብ ሲል አየሁት። ለማረጋገጥ ቀና አልኩ። በአስር አመት ውስጥ እህቱ የሞተች ጊዜ ካልሆነ ሲያለቅስ አይቼው አላውቅም። ዘልዬ ላቅፈው ፈልግያለሁ። እንባው መሬቱ ላይ ከመድረሱ በፊት በጣቶቼ ከጉንጩ ላይ ልጠርግለት። አታልቅስ ብዬ ልለምነውም እፈልጋለሁ። ከአፌ አይወጣልኝም። አስለቃሽዋ ራሴ ሆኜ ማባበል ትርጉም የሚሰጥ ነገርም አልመስል አለኝ። ለሰራሁትም ላልሰራሁትም ሀጢያት ይቅርታ ጠይቄው ለቅሶውን ላስቆመው እመኛለሁ። ውስጤ ሲታመስብኝ ይታወቀኛል።

"ስራ አልቆ መጥተህ እስክትወስደኝ በናፍቆት የምታመም የሚመስለኝ ጊዜ ነበር፣ ስትስመኝ ከመሳሳቴ መቼም የማልጠግብህ የሚመስለኝ ጊዜ ነበረ ፣ልታገባኝ ሽማግሌ የላክህ ቀን በዓለም ላይ የደስታ መጨረሻው ያ መስሎኝ ነበር ፣ መጀመሪያ ቢሮዬ መጥተህ ያየሁህ ቀን ልቤ በአፌ የምትወጣ መስሎኝ ነበር ፣ እራት ልጋብዝሽ ያልከኝ ቀን ምን ብለብስ ልትወደኝ እንደምትችል ስለብስ ሳወልቅ....... ተቀብቼ የማላውቀውን ሊፒስቲክና ኩል ስቀባ አንድ ሰአት ነበር የፈጀብኝ ፣ የሰርጋችን ቀን ማታ መቼም ከእቅፍህ እራሴን እንደማላርቅ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር ፣ ከልክ በላይ ስታቀብጠኝ በምድር እንደእኔ እድለኛ ሴት እንዳልተፈጠረች ያሰብኩባቸው ጊዜያት ብዙ ነበሩ ፣ ይሄ ሁሉ ፍቅር ከነበረ አዎ አፍቅሬህ አውቅ ነበር። ግን እውነተኛ ፍቅር ቢሆን ያልቅብኝ ነበር? ፍቅር ያልቃል?"

ራሴን ሳብራራ አገኘሁት። አውርቼ ስጨርስ ፈገግ እያለ እንደሆነ አየሁት። ከተናገርኩት ምኑ ነው ደስ የሚያሰኘው? ድንገት ተስፈንጥሮ አቀፈኝ። ግንባሬን ፀጉሬን አንገቴን እየሳመ

"ፍቅር አያልቅም! በጥላቻ ወይ በቂም ግን ይሸፈናል። " እያለኝ ደስ መሰኘቱን ቀጠለ።

ግራ ገባኝ። ምንድነው እየሆነ ያለው? አትሳቅ ተብሎ ሳቁን ለመቆጣጠር እንደሚታገል ሰው ያላለቀ ፈገግታ ፈገግ እያለ ተነስቶ መንጎራደድ ጀመረ። ዓይኖቼን አብሬ ከማንቀዥቀዥ ያለፈ ማድረግ የቻልኩት የለም።

"ጠይቂኝ እስኪ? ምንድነው እንዲህ የሚያስፈጥዝህ በይኝ? ለዛሬ እንኳን ደስታዬን ሙሉ አድርጊው! ለሚሰማኝ ስሜት ግድ አላት ልበል?" አለኝ

እያለ ያለው እንደገባኝ እርግጠኛ አይደለሁም። የቅድሙ እንባውን ከማይ ደስታውን ሙሉ የሚያደርገው የኔ መጠየቅ ከሆነ ሺህ ጊዜ ብጠይቀው ግድ አልነበረኝም።

"ምንድነው ደስ ያሰኘህ?"

"እነዚህን ቃላት ካንቺ አፍ ለመስማት ስንት ቀናት መናፈቄን ታውቂያለሽ? ፈጣሪዬን ለምኜው እንደማውቅ ታውቂያለሽ? ካንቺ አፍ የተሰማሽን ስሜት የሚገልፅ ቃል ፈልቅቆ ከማውጣት ....... "
አልጨረሰውም ቃል ጠፋው::

"ለምን አትጠይቀኝም ነበር? ዛሬ እንደጠየቅከኝ?ለምን ..."

"ለመልሱ ዝግጁ አልነበርኩም ነበር።" አለ ችኩል ብሎ!! ቀጥሎ

"ሁሌም እወድሻለሁ ስልሽ 'እኔም' ነበር መልስሽ። የዛሬ አራት ዓመት ህዳር 7 ጠዋት እወድሻለሁ ስልሽ 'እኔም' ማለቱ ሲያስምጥሽ አየሁ:: እያስጨነቅኩሽ እንደሆነ ስለገባኝ እወድሻለሁ ማለቱንም ተውኩት::"

ምን ልበለው ዝም አልኩ። ተቀምጦ ዝም አለ። እናቱ የሚወደውን ነገር ልትገዛለት ወጥታ መመለሷ እርቆበት በደስታና በጉጉት እንደሚቅበጠበጥ ህፃን እያደረገው ተቀመጠ።

"እኔኮ ግን ባትነግረኝም እንደምትወደኝ አውቃለሁ::" ብዬ ያሰብኩት ነው ያመለጠኝና ቃል ሆኖ የተናገርኩት

"(ፈገግ እንደማለት ብሎ) ቃሌን የሚተካልሽ ነገር አጊንተሽ አይደለም? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ስጦታ የገዛሽልኝ? የዛሬ ሰባት ዓመት የልደቴ ቀን...."

(ሰባት ዓመት ሙሉ ሲዘንጥ የሚያደርገውን ሰዓት እያሳየኝ:: እሱ ባለፈው ወር ጫማ ገዝቶልኝ ነበር::)

"መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ፈልገሽ የሳምሽኝ? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ባንቺ ተነሳሽነት ፍቅር የሰራ....." ቃሉን ሁላ ሳይጨርስ ተቀበልኩት

"ያስጠላኛል::" ዛሬ ምን ሆኜ ነው የማስበው የሚያመልጠኝ?

መጀመሪያ ደነገጠ:: ከዛ ከት ብሎ ሳቀ:: ከሶፋው ተነስቶ እግሬ ስር ቁጢጥ ብሎ .... እጆቹን እግሬ ላይ አድርጎ ወደ ላይ እያየኝ እየተንፈቀፈቀ ሳቀ.... ቡፍ ይላል እያረፈ....

"ምንም የሚያስቅ ነገርኮ አልተናገርኩም::"

"(ጭራሽ ከት ብሎ እየሳቀ) እንደሱ አድርገኝ ..... አዎ እሱጋ በለው ..... ብለሽኝ የነበረበት ዘመን እንደነበረ ትዝ ብሎኝ ነው::" ብሎኝ መንፈቅፈቁን ቀጠለ

"የቱጋ መቼ እንዳስጠላኝ አላውቅም::" አልኩት እንደማፈር እያደረገኝ

"ለኔ ያለሽ ስሜት የቀነሰብሽ ቀን" አለኝ ኮስተር ብሎ ቀጠል አድርጎ "ለምን በግልፅ አልነገርሽኝም? እያስጠላኝ ነው ማድረግ አልፈልግም ለምን አላልሽኝም?"

"ባሌ አይደለህ? ሴክስ ማድረግ አልፈልግም ይባላል?"

"ባልሽ መሆኔኮ አንቺን የማስደሰት ሀላፊነትም አብሮ ይሰጠኛል:: abuse እያደረግኩሽ እንድደሰት መብት አይሰጠኝም::" አለኝ:: ምንጣፉ ላይ በቂጡ ተቀመጠና እንደመተከዝ እያለ....

"ልነግርሽ የሚገባ ነገር አለ!" አለኝ

"አውቃለሁ!" አልኩት። ግራ ገባው። እንዴት እንዳወቅኩ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሬ ነገርኩት።

"እንዴት አልጠየቅሽኝም? እንዴት አስቻለሽ?"

"አንተ ስንት ዘመን ሁሉ አስችሎህ ዝም ብለኸኝ የለ?"

"እንደዛ ነው የምታስቢው? ምናለ በይሆናል ራስሽን ከምትቀጪ ብትጠይቂኝ
ና የሚሰማኝን ብታውቂው? እኔኮ በዓይኔ ነው ያየሁሽ። የምጠይቅሽ ጥያቄ አልነበረኝም። ራስሽን ይቅር ያላልሽው አንቺ ነሽ። እኔ ገና ድሮ ይቅር ብዬሽ አልፌዋለሁ።"

"ምን ያህል ጊዜያችሁ ነው?"

"ካወቅኳት?" በጭንቅላቴ ንቅናቄ 'አዎ' አልኩት

"ከተዋወቅን ስድስት ወር ገደማ። .......ስለፍቅር ማውራት ከጀመርን አንድ ወር .......ከሳምኳት ሁለት ሳምንት ......." ከዛስ የሚለውን አይኔን አፍጥጬ እጠብቀዋለሁ።

"አድርገን አናውቅም። ታምኚኛለሽ?"
'አዎን' አልኩት በጭንቅላቴ ንቅናቄ:: ..... ዝም ተባባልን!! ..... ወርጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ:: .... ምን እያሰበ እንደሆነ ልጠይቀው እፈልጋለሁ:: ግን ከአፌ አይወጣልኝም:: አቅፎ ትከሻው ላይ አስደገፈኝ:: ዝም ተባብለን ብዙ ከቆየን በኃላ ... .... አቅጣጫውን ቀይሮ ከፊቴ ተቀመጠ:: በጣቶቹ አገጬን ደግፎ ቀና አድርጎኝ አይኖቹን አይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ

"ፍቅሬ እኔ ስላበድኩልሽ ያላንቺ ፍላጎት የራሴ አድርጌ ላቆይሽ እንደማልችል አውቃለሁ:: ምንድነው የምትፈልጊው? መለያየት ከሆነ የምትፈልጊው am ready now. ቢከብደኝም ልለቅሽ ዝግጁ ነኝ!! ምንድነው የምትፈልጊው? እንደገና መሞከር ነው የምትፈልጊው? Am ready ... አሁን ግን እኔን ወይም ቤተሰብሽን ሳይሆን ራስሽን ሰምተሽ ራስሽ ወስኚ .. .... የፈለግሽውን ጊዜ ያህል ውሰጂ የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ የለብኝም::" አለኝ

"እሷስ?" (ኤጭ ዛሬ ምንድነው ችግሬ የማስበውን የማወራው?)

"(ሳቅ አለ) እሷ ስላንቺ ታውቃለች ጣጣዬን እስክጨርስ ላለመገናኘት ተስማምተናል::"

"ለመወሰን ብዙ ጊዜ ቢፈጅብኝስ?"

"10 ዓመት ጠብቄሽ የለ? እጠብቅሻለሁ::" አለኝ:: ከጀርባዬ መጥቶ እግሮቹ መሃከል አድርጎኝ ካቀፈኝ በኃላ "ያ የሚያስጠላሽንም ነገር አናደርግም (ድክም ብሎ እየሳቀ) ሆ ሰው ፍሰሃ ያስጠላዋል? (ቡፍ ካለ በኃላ) ራስሽ ፈልገሽ ያውም 'እባክህ ፍቅሬ' ካላልሽኝ አናደርግም" ብሎኝ እጁን በቱታዬ ስር ሰዶ ወገቤን አቀፈኝ::

ይሄ ሰውዬ ዛሬውኑ እባክህ ሊያስብለኝ ነው እንዴ?

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ
ጥበብ ይናፍቀኛል፤ ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል፤ ድንቁርና ያስፈራኛል።
©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

👇JOIN (ተቀላቀሉን)
https://www.tg-me.com/tsegaye_gebremedihen
ባሌ እንዳመነዘረብኝ .... (ርዕሱን ቀይሩት ስትፈልጉ ግን የቀጠለ ነው) .... #6

"እስክትወስን እጠብቃታለሁ::" ይለኛል። ሁሌም የምንገናኝበት ቦታችን 'የምናውራው አለ' ብሎኝ ተገናኝተኝ የጀበና ቡናችንን እየጠጣን።

"እኔስ? በፍቅርህ የነሆለለ ጅል ልቤስ? ምን ላድርገው? እስከመቼ ጠብቅ ልበለው? ከሚስቱ እስኪታረቅ ልበለው እስኪለያይ? ንገረኝ የቱን ነው የምጠብቀው?" እንባዬ የአይኔን ድንበር አልፎ ተንዠቀዠቀ። ይሄን ያልኩት ብዙ ስለሷ እና ስላወሩት ከነገረኝ በኋላ ነው።

ሚስት ያለው ሰው ወድጄ ለምን ታረቁ የማለት መብት አለኝ? እሱስ የጠላችው ሲመስለው እኔጋ የወደደችው ሲመስለው እሷጋ እየሄደ በልቤ የመቀለድ መብት አለው? ማናችን ነን ልክ? ወይስ ማናችን ነን ትንሽ የተሳሳትን?

የሆነ ቀን እዝችው ቤት ቁጭ ብለን የተሰነጣጠቀ ስኒ ረከቦቱ ላይ አይቼ ተነስቼ አመጣሁት። አሳየሁት።

"ይሄን ስኒ አየኸው ውዴ ብዙ ተሰነጣጥቋል። ግን አልፈረሰም። አንዴ ብቻ ቢወድቅ ግን ይፈረካከሳል።" ብዬው ስኒውን ለቀቅኩት እንክትክቱ ወጣ። "የኔ ልብ ይሄ ስኒ እንደነበረው ነው። የምታነካክተው ከሆነ ከነስብራቱ ይቆይ ተወው።" ብዬው ነበር። የዛን ቀን ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሳመኝ። አልሰብረውም እጠብቀዋለሁ እንደማለት ያለ መሳም።

ከቀናት በፊት

"ለሚስቴ ካንቺጋር ያለኝን ነገር ልነግራት ወስኛለሁ። ከርሷ ጋር ያለኝኝ ነገር ጨርሼ ልምጣልሽ። እያደረግነው ያለነው ነገር ልክ አይደለም። ካንቺ ጋር ቆይቼ እቤት ስገባ ልፈነዳ ነው የምደርሰው።" አለኝ።

ዛሬ መጥቶ

"እስክትወስን እጠብቃታለሁ::" ይለኛል። ከቃሉ ይልቅ ውሳኔዋ መመለስ(አብሮ መኖር) እንዲሆን ተስፋ ማድረጉ። ለማሰብ መዘጋጀቷ እንዴት እንዳስቦረቀው ሳየው ልቤ ደረቴ ስር እንደዛ ስኒ እንክት ስትል ታወቀኝ። ተነስቼ ሮጥኩ። እየጠራኝ ተከተለኝ። ሮጥኩ ታክሲ እስካገኝ ሮጥኩ።

"አየህልኝ? ካልጠፋ ሰው ....ካልጠፋ ወንድ ባለትዳር? 'አላገባም! ካሁን በኋላ መውደድ አልችልም' ስልህ .......'ጊዜ ሀዘንሽን ያደበዝዘዋል። ... የሆነ ቀን የሆነ ሰው ወደ ህይወትሽ ይመጣል። ... ልብሽ ተሰብሮ እንደነበር ያስረሳሻል። .... ትወጃለሽ። ልብሽ እንደገና ሙሉ ይሆናል። ..' ያልከኝ። "

ሆስፒታል አልጋ ላይ ከተኛ ወራት ላለፉት ይስማኝ አይስማኝ እርግጠኛ ላልሆንኩት አባቴ ነው የምለፈልፈው።

"መጣ! ... ያ ሰው ወደ ህይወቴ መጣ ... ወደድኩት። .... ባለትዳር ነው አባ! ... ይሄን ዘመን ሁሉ ቆይቼ ካልጠፋ ሰው ልቤን የሰጠሁት የሚወዳት ሚስት ላለችው ሰው ነው:: ... አንተ እንዳልከኝ ልቤን ሙሉ አላደረገውም። አነከተው።" ተንፈቀፈቅኩ።

በራሴ ተናደድኩ። በፈጣሪ ተናደድኩ። በዓለም ተናደድኩ። በማላውቃት ሚስቱ ተበሳጨሁ። በሱ በራሱ ተናደድኩ። በአባዬም ስለማይሰማኝ ስለማያባብለኝ ተናደድኩ። ለሁሉም መልሴ እናባ ነው። ከአንጀቴ እየተሳበ የሚያንፈቀፍቀኝ እንባ።

"ለምን እንድወደው አደረገኝ? ሳለቅስኮ ነው ያገኘኝ? እንባዬን ጠርጎ አባብሎኝኮ ነው የተዋወቀኝ ...... አላሳዝነውም? .... እዛው እንባዬ ላይ መልሶኝ ይሄዳል?"

የህፃናት ማጫወቻ ቦታ ልጄን እያጫወትኩ ነበር።

"እማ እዛኛው ላይ መጫወት እፈልጋለሁ?" አለኝ ልጄ መጥቶ

"ባባዬ እኔኮ ከፍታ ያመኛል::" አልኩት የከፍታ ፍርሃቴን ለ6 ዓመት ልጄ ማስረዳት እየቸገረኝ። ቀና ብዬ መጫወቻው ላይ ልጆቹን አየኋቸው። አብዛኛዎቹ ከአባታቸው ጋር ነው መጫወቻ ላይ የወጡት ። ጉድለቴን ሊነግሩኝ ...... የልጄ አባት ምን ያህል እንዳጎደለኝ ሹክ ሲሉኝ ..... እንባዬ አይኔን ሞልቶ ደፈራረሰ።

"ይቅር በቃ ሌላ ጨዋታ እጫወታለሁ::" አለኝ የኔ የልጅ አዋቂ ጭንቀቴ ገብቶት።

"እኔ ይዤልሽ ልውጣ?" አለኝ የሚያባብል ድምፅ ከጀርባዬ ........ እሱ ነበር። ምንድነው የሆንኩት? የተሰማኝን ያወቀልኝ መሰለኝ። ውስጤ ያለውን የሰማኝ:: አዎ ማለት አቃተኝ። በጭንቅላቴ ንቅናቄ እየነገርኩት እንባዬ ተከታተለ። ልጄ እንዳያየኝ እያቻኮለ ብድግ አድርጎ ትከሻው ላይ ሰቅሎት ይዞት ሄደ። ተንፈቀፈቅኩ።

"ከሞተ አራት ዓመቱ ነው።" አልኩት ሳይጠይቀኝ። "እንዴት ነው የማይመለስን ሰው መጠበቅ ማቆም የሚቻለው? እንዴት አድርጌ ነው መናፈቅ ማቆም የምችለው:: እንዴት ነው ከርሱ ውጪ ህይወቴን መቀጠል የምለምደው? " እያልኩት እነፋረቅ ጀመር። አባበለኝ። እንደህፃን አባበለኝ። ... ብዙ ጊዜ እንደሚያውቀኝ:: .... ... አልቃሻ ብሆንም ለማላውቀው ሰው አላለቅስም ነበር:: እሱ ግን ባልገባኝ ምክንያት ቀለለኝ::

"የታል ያንተ ልጅ?" አልኩት

"ብቻዬን ነው የመጣሁት። ልጅ የለኝም ከነጭራሹ ..... ህም .... መውለድም አልችልም::" አለኝ መተንፈስ የፈለገ ይመስል ነበር። ልጄ እየተጫወተ እኔና እሱ ብዙ አወራን።

"ሚስቴ ትጠላኛለች። ልጅ ልሰጣት ስለማልችል ትጠላኛለች። .....ልጅ መውለድ እንደማልችል ሳልነግራት ስላገባኋት ትጠላኛለች። ....ለምን እዚህ እንደምመጣም አላውቅም። .....ልጆች ሲጫወቱ አይቼ እመለሳሉሁ። " እያለ ዝብርቅ ያለ ወሬ አወራኝ።

እዚህ ቀን ላይ ነው የመለሰኝ። ለቅሶዬ ላይ። እሱን ካወቅኩት በኃላ አላለቀስኩም ነበራ። ...

"እዚህ ነሽ እንዴ?" እያለች ታላቅ እህቴ ወደአባዬ ክፍል ስትገባ እየተነፋረቅኩ እንደሆነ አየችኝ።
በሩን ዘግታ የአባዬ አልጋ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠች። ያለኝን ነገርኳት።

"ያንቺ ካለውኮ ተመልሶ ይመጣል::" አለችኝ።

የምትለው ግራ ገብቷት እንጂ ያለችው ምን ማለት እንደሆነ አልመነዘረችውም።

ለኔ ካለው? ለኔ ካለው አማራጩ እሆናለሁ። የመጀመሪያ ምርጫው እሷ ናት። እሷን ካጣ እኔጋ ይመለሳል? ለኔ ካለው ትርጉሙ ይሄ አይደል? ለኔ እንዲለው እሷ እንድትጠላው ቁጭ ብሎ መመኘት? ለኔ ካለው እንዲፋቱ መፀለይ? ትርጉሙ ይሄ አይደል? ቢለያዩና በቃ ጨርሻለሁ ብሎኝ ቢመጣ ስለወደደኝ ነው ወይስ አማራጭ ስላጣ ብዬ የምቀበለው?..... ለኔ ካለው የሚባል ነገር ምንድነው? እጣዬ ከሆነ ማለት ነው?

ከወራት በፊት የህፃናት መጫወቻው ቦታ ስንለያይ ስልክ ሳንለዋወጥ ... ስማችንን እንኳን ሳንተዋወቅ ቻው የተባባልን ሰዎች ከሱቄ ባሻግር ያለ የጀበና ቡና መጠጫ ቤት ቁጭ ብዬ ቡና ስጠጣ ሲገባ ሳየው ... እንደዛ አስቤ ነበር:: ምናልባት እጣ ፈንታ ነው:: ተዋወቅን ... አወራን .. በተደጋጋሚ ቡና ጠጣን.... የሆነ ቀን እኔም ስለባሌ እሱም ስለሚስቱ ማውራት ትተን ስለራሳችን ስናወራ ራሳችንን አገኘነው:: ....

ምኑጋ ነው የወደድኩት? ምኑጋ ነው ልቤን የከፈትኩት? ልክ እንዳይደለ አውቅ አልነበር? እያወቅኩ የቱጋ ነው የተረታሁት?

......... ...... እንክትክት ያለ ነሆለል ልቤን ከየት ወዴት ልሰብስበው? ሚስቱን ፈቶ እስኪመጣ ጠብቅ ልበለው?

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
መቻቻል የጥንት ባህላችን ነው!
((Maggie))


እሁድ 'ለት ነው.....
ሳይሰስት ያደለው የፍቅረኛውን አንገት አቅፎ ቤተስኪያን ይስማል (ያየውትን ነው እንግዲ! እግር ጥሎኝ ቤተስኪያን ልሳለም ስወጣ አዝመራ ላይ እንደተሰማሩ ጥማድ በሬዎች ተጣምሮ ነው ማየው) .... ተኩል ያደለው ብቻውን ሄዶ ይስማል......ያላደለው እንደኔ እዚ አልጋው ቮካል እየሰራበት እንቅልፉን ይለጥጣል. ....... ስለአልጋዬ ካነሳው አይቀር...... አልጋዬ ቴዲአፍሮን የሚያስንቅ ሙዚቀኛ ነው. ላይቭ ነው ሁሌ ሚያዜምልኝ.....ደግሞ ባንዶቹ! ..አይጦቹ በላይ በኮርኒሱ ሆነው ያጅቡታል.... እሱ ደግሞ በተገላበጥኩ ቁጥር ያንቋርራል. እኔ ሚያሳስበኝ እንቅልፍ መንሳቱ እንዳይመስላቹ.... እንቃፌን ቀላል እለጥጠዋለው! የፖለቲካ ምህዳራችን እንኳ እንደኔ እንቅልፍ አይለጠጥም!..............እንደው እድል ቀንቶኝ ሚስት ያገባው እለት እንዴት እንደምሆን ብቻ ነው....አስቡትማ.... 'የኔ ማር የኔ ውድ እኔኮ እንዴት እንደማፈቅርሽ'..... ብዬ ሳልጨርሥ .......እእእውውውይ! ቃቃቃቃቃቅ!..... ድድድድድድድድ ሲጢጢጢጢጥ.... ሲል!
..............
.....ታድያ እሁድ ለት በኦርኬስትራ ና ቮካል የታጀበ የአልጋዬን 'መልካም ጠዋት(good morning!)' ተቀብዬ ማመራው ወደ ፍሪጄ ነው! በሩን ስከፍት የበረሮዎች ሬስቶራንት የሞቀ የራት ግብዣ ላይ ደርሳለው! (አሁን በነሱ ቤት 'ጣይ ጠልቃለች አሉ! ሁሁሁ) ...........እንደውም አንዱ በርሮ "ፍሬንድ! እስቲ በሩን ዘጋ አድርጊው ...ላይቱን ደብዘዝ አድርጌ ከሚስቴ ጋ ሮማንስ ልሰራ ነበር" ሚል መልክት ሚያስትላልፍ ይመስላል... በዛ ደቂቃ ሁለት ነገር አስገረመኝ......... 1ኛ.በረሮው ቅዝቃዜውን የሚችል አንጀት ከየት አምጥቶ ነው? 2ኛ.በረሮው ወንድ መሆኑን እንዴት አውቄ ነው??? (ምናልባት ተለቅ ስላለ??ምናልባት ተጎኑ ያለችው እየተሽኮረመመች ስለሆነ.....) እያልኩ እየተፈላስፍኩ........

ትላንት ያስተረፍኩትን ሙቅ(አጥሚት) አውጥቼ ማሞቅያው ላይ ጥጄው... ፊቴን ልታጠብ ሄድኩ.....ስመለስ እላዩ ላይ ደርቆ አገኘውት! ሙቀቱ ያለሰልሰዋል ስል ለካ ፍሪጁ አድርቆት ኖሯል .......ለኔ አጥሚት ሲሆን ብቻ ነው እንዴ የሚሰራው ብዬ ፍሪጄን ላኮርፈው ስል................ የጨረስኩት የወተት ጣሳ ውስጥ ባለፈው ያስቀመጥኩት ሩዝ ትዝ አለኝ......... ልቀቅል ስከፍተው የቅድሙ በረሮ ይሁን ሌላ እንጃ..... በቅድሙ አስተያይት አየኝ... ዝም ብዬ ሳስብ " ጀለስካ! ምነው በበረኪና ካልሆነ አልለቅም አልሽኝ! ....ጫጉላዬን መጥፎ ትዝታ ልታደርጊብኝ አሥስበሽ ነው እንዴ??" ሳይለኝ አቀርም.

ሼፍ እንትና እንዳለው ሁለት ኩባያ ሩዝ ባራት ኩባያ ወሀ ቀቅዬ እየበላው... አንድ እንትን መጣ.... ምን አትሉም????? ጉንዳን ነዋ! ጠረቤዛው ላይ ከተበተነው ስኳር መሀል ተለቅ ያለውን መርጦ ተሸክሞ ሊሄድ! አይ ጉንዳን! በላባደሮች ቀን እውቅና ሊሰጠው ሚገባ ፍጥረት! (ሙድ ስንይዝ ኮ ነው! የላባደሮች ቀን ብለን ምናከብረው... ማርያምን!) የጉንዳን ተወካዮች ምክርቤት በዚ ትልቅ ቀልዳችን ሆዳቸውን ይዘው ሳይስቁ አይቀሩም!

ደግሞ አለች የቤቱ እመቤት! ተኝታ ነው ምትወለው! ምን ቸገራት እሷ. ይኸው እነንትና ባንድ እስኪከፍቱ ድረስ ዝምምም! ድመቴ! ባጠገቧ ፋሽንሾው የምታሳይን አይጥ "ወይ ስታምሪ ፣ እንቺኛዋ ትንሽ ወፈር ብለሻል..ዳይት ጀምሪ፣ አንቺ ትንሽ ጅራትሽን አሳጥሪው ፣አንቺ ደግሞ ትንሽ ጥርስሽን ሞረጂው " እያለች አስተያየት ምትሰጥ!! .........እሷ የምታውቀው ስመገብ ፊቴ ቁጭ ብሎ ሚስኪን አይን እያሳዩ እና እግር እየላሱ ፍርፋሪ መለመን! ከሩዙ ሁለት ማንኪያ ብሰጣት.. አሽትታው ሄደች!... "ስጋ ና ወተት ስጠብቅ ጭራሽ ሩዝ! ስግብግብ!" በሚል አይነት አረማመድ! (ቦዘኔ ድመት! እእህ!)

ጓደኛዬ ባለፈው ሊጎበኘኝ መጥቶ " ቆይ አንተ አሁን ብቸኛ ነኝ ብትል ማን ያምንሀል???" አለኝ
"እንዴት?"
"እነዚን ሁሉ ጉድ በነፃ አስጠግተህ እየኖርክ "
"አሁንማ ኮ አስጠግቼ አይደለም....... አስጠግተውኝ ነው!"

ከቤቱም ከዱሩም እንስሳጋ ተቻችለን ስንት ዘመን ኖረንን ምነው አሁን እኛ ለኛ ሲሆንን እርስበርሳችን መቻቻል አቃተንሳ!!!???

ኧረ መቻቻልኮ የጥንት ባህላችን ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የመጨረሻ ክፍል!! )

(አልጨረስንም እኮ ብትሉም ጨርሰናል። ጨርሰናል ብትሉም ጨርሰናል)

"አልቻልኩም:: .... አልቻልኩም!" ሁለት እጆችዋን ጨብጣ ደረቴን እየደበደበች ታለቅሳለች:: ጉንጮቿ እና ከንፈርዋ ይንቀጠቀጣሉ። አንጀት የራቀው ሆድዋ ይርበተበታል።

እየደጋገምኩ "እሺ" ከማለት ውጪ የምለው አጣሁ። ድብደባዋን ስታበቃ ንፁህ ያልሆነው መሬት ላይ በነጭ ሱሪዋ ተቀመጠች።

"ላናግርህ እፈልጋለሁ" ብላ ሱቋ ጠርታኝ ነው ሱቁን ዘግታ በእንባዋ እየቀጣችኝ ያለችው።

ከመምጣቴ በፊት ወይም ከጠዋት ጀምሮ አልያም ያለፈውን ቀናት በሙሉ እያለቀሰች እንደነበር አብጦ ለመከፈት የቸገረው አይኗ ያሳብቅባታል። ቅጣት ነው!! ፈጣሪስ ቢቀጣኝ ከዚህ በላይ በምን ቢቀጣኝ ነው ከዚህ የባሰ ህመም የሚያመኝ?

"እመነኝ እየወቅስኩህ አይደለም:: እረዳሃለሁኮ .... መደበቂያ ስትፈልግ .... የምትተነፍስበት ባጣህ ጊዜ አገኘኸኝ ....ጉድለቴን ስታውቀው ስላሳዘንኩህ ያፅናናኸኝ መስሎህ ፍቅርህ ውስጥ ደበቅከኝ። በትዳርህ ተስፋ ስትቆርጥ ልብህን የምታዘው መስሎህ ነው እወድሻለሁ ያልከኝ። ....እኔ ነኝ እንጂ ከንቱዋ እሷን እንደምታፈቅራት እያወራኸኝ ለሷ ባለህ ፍቅር ውስጥ ዘፍቄ የተዘፈዘፍኩ::" አለችኝ በየመሃሉ ሳግ እያቋረጣት

ይሄ ነገሯ ነው እሷ ውስጥ እንድጠለል ያደረገኝ። ራሴን እንዳልወቅስ የምታደርገኝ ነገርዋ ...... ራሴን ይቅር እንድለው የምታደርገኝ ...... ነገርዋ ራሴን እንድወደው የምታደርገኝ ነገሯ ....... ሰብሬያት እንኳን እኔ መጥፎ ስሜት እንዲሰማኝ ከማድረግ ራሷን ትኮንናለች ከዚህ በላይ ቅጣት ካለ ንገሩኝ?

አንዳንድ ሰዎች አንድ ሺህ ነገር አውርተሃቸው አንድ ሺውንም ይሰሙሃል። የቱንም ግን ላይረዱህ ይችላሉ። እሷ ሁለት ቃል አውርቼ ያላወራሁትንም 200 ቃል ደምራ ትረዳኛለች። ያ ነው እሷጋ ያስከንፈኝ የነበረው። የሆንኩትን ልነግራት ስጀምር እንዴት እንደሆነ በማይገባኝ ሁኔታ እኔ እንደተሰማኝ ...እንደዛው አድርጋ .... ትጨርስልኛለች:: እሷም እዛው ስቃይ ላይ እንደነበረች ........ የታመምኩትን እንደታመመች ... የተናደድኩትን ተናዳው እንደነበር ........ ልክ እንደዛው ........ ጥፋቴን እንኳን አጥፍታው የነበር እስኪመስለኝ እኔ እንደሚሰማኝ አድርጋ ትገልጽልኛለች።

ለምን ለሚስቴ መውለድ እንደማልችል እንደደበቅኳት ስትጠይቀኝ። ሌላ ሰው ሲሰማው ውሃ የማያነሳ ራስ ወዳድ ምክንያቴን ሳስረዳት

"አንዳንዴ የምትወደውን የማጣት ፍርሃት ምክንያታዊ እንዳትሆን ያደርግሃል። አሁንህን ለማዳን ነገህን ታበላሻለህ!" ነበር ያለችኝ።

"እረዳሃለሁ እሺ ... ትወዳታለህ!! ...እኔንም ትወደኛለህ። ....እሷ ሳትወድህም ትወዳታለህ! የተናደድክባት ጊዜም ትወዳታለህ። የበቃህ የመሰለህ ጊዜም ትወዳታለህ። ..... እኔ እንድጎዳብህ እንደማትፈልግም አውቃለሁኮ" ደግሞ አቁማ ድምፅ አውጥታ ታለቅሳለች።

"እኔስ ባሌንም ዛሬም ድረስ እወደው የለ ከዛ ደግሞ አንተንም ወደድኩህ አይደለ? አልፈርድብህም እሺ! ልብህ እሷጋ ነው:: አንተ አታዝበትም።"

ይኸው ከራሴ ጋር እንኳን እንዴት ነው ሁለት ሰው መውደድ የቻልኩት እያልኩ የምጣላበትን ሀቅ እኔን ሆና ታብራራልኛለች።

"እኔ ግን መጠበቅ አልችልም! አንተ እሷን ጠብቃት። የጥበቃህ መጨረሻ ምንም ቢሆን እባክህ ስወድህ ተመልሰህ እኔጋ አትምጣ! እኔ አሁን የሚሰማኝ ህመም እንዲያምህ አልመኝልህም ስለዚህ ትዳርህ ይስመርልህ። ባይሆንም ግን አትምጣ።"

መሬቱ ላይ ከነሱፌ አጠገቧ ተዘፈዘፍኩ። ላቅፋት እጄን ስዘረጋ ጥቅልል ብላ ውስጤ ተሸጎጠች። እናቱ ከገረፈችው በኋላ መልሳ ስታባብለው እንደሚብስበት ህፃን ህቅ ብላ አለቀሰች። ቁጥሩን ለማላውቀው ያህል ጊዜ ደጋግሜ ይቅርታ አልኳት። ይቅርታ ባልኳት ቁጥር ህቅታዋ ከአንጀቷ ድረስ እየተሳበ ህቅ እያለች ታለቅሳለች።

"አታስብ እሺ ምንም አልሆንም:: አሁን አባዬ ነቅቶ የለ? ህይወት ሁሉንም አትሰጥም አይደል? .... አልረሳህም ግን እተውሃለሁ።"

እንዴት ነው እንባዋ ሸሚዜን እያጠበው ፈገግ የምትለው? እያለቀሰች የምትስቀው? እየታመመች ደህና እንደሆነች የምትሆነው?

"ሂድ በቃ!" አለችኝ ከእቅፌ ወጥታ .... ልነሳ ስል ደግሞ ያዝ አድርጋኝ ...

"ቆይ ትንሽ ደቂቃ ልይህ.. " ጉንጬን አገጬን አንገቴን ፀጉሬን ስትነካካኝ ቆይታ

"እሺ በቃ ሂድ ...." አለችኝ ድክም ባለ ድምፅ

እየተንፏቀቅኩ ተነስቼ በሩጋ ከደረስኩ በኋላ ዞሬ አየኋት መሬቱ ላይ ኩርምት ብላ ጉልበቶቿን አቅፉ ሳያት ራሴን ጠላሁት። ምንድነው ያደረግኩት? ምንድነው ያደረግኩት? እንዴት ክፉ ነኝ?

እቤት ደርሼ መኪናውን ካቆምኩ ቆየሁ ግን አልወረድኩም። የሆነ ቦታ መጥፋት አሰኘኝ። ብቻዬን የምሆንበት ቦታ!! ባዶ ሆንኩ .....ባዶ .... ፀፀት ብቻ የሞላበት ባዶ ጭንቅላት ..... ህመም የበዛበት ባዶ ልብ !

ወደኃላ ተመልሼ ህይወቴን ማረም ብችል ከየት ነው የምጀምረው? ስህተቱ ይበዛል .... ባለትዳር ሆኜ ሌላ ሴት ስቀርብ? አይደለም ከዛ በፊት ሚስቴ እንድትጠላኝ ያደረጋት ውሸቴን .... እሱም አይደለም:: ለውሸቴ ሰበብ የሆነችኝ እውነቱን ስነግራት የተወችኝ የድሮ ፍቅረኛዬን? .... እሷም ጋር አይደለም .... ለመካንነት ሰበብ የሆነኝ የሞተር ሳይክል አደጋ.... ይሄን ሁላ ባጠፋው ... እኔ አልሆንማ!! ....

ስቆይባት በሩን ከፍታ ብቅ ስትል አየኋት:: እግሬን እየጎተትኩ ወርጄ ወደቤት ገባሁ::

"ምነው ደህና አይደለህም?"

"ደህና ነኝ" ካልኳት በኋላ መልሼ "ደህና አይደለሁም!" አልኳት እየተቆጣሁ እንደሆነ እየታወቀኝ።

"ምን ድረስ ነው ግን የምወድሽ? እንዴት አድርጌ ወድጄሽ ነው በህይወቴ ውስጥ አንቺ እስካለሽበት የሌላ ንፁህ ሰው ህይወት ማመሳቀል እንኳን ቢሆን ሁለቴ ሳላስብ የማደርገው?"

ያልኳት አልገባትም ዝም አለችኝ። አልፋኝ ሄዳ ተቀመጠች። እሷን ምን አድርጊኝ ብዬ ነው የምቆጣት? ዝም ተባብለን ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ

መቼም እለዋለሁ ብዬ የማላስበው ነገር የአፌን በር ለቆ ሲወጣ ራሴን ሰማሁት::

"ለተወሰነ ጊዜ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ!" የተገረመች መሰለች::

"ሁለታችንም ብቻችንን ጊዜ ያስፈልገናል::"

ጨርሰናል!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
2024/09/23 22:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: