Telegram Web Link
እንደግመል ሽንት. . .
________________________
ጓደኛዬ ነው ያስታወሰኝ፤ "የኛ ነገር እንደግመል ሽንት ወደኋላ ሆነ" ብሎ።
የግመል ሽንት ለምን ወደኋላ ይፈሳል? ቸንቸሎው ትንሽ ስለሆነ ነው አሉ።
ግመሎች ሰው ካልረዳቸው በቀር ወሲብ ማድረግ አይችሉም ሲባል ሰምቻለሁ
(አይናለም የጠራሽ የለም!)። ከየት እንደመጣ ግን እንጃ። ሰው የግመል ፒምፕ ለመሆን ፈልጎ የፈጠረው ሰበብ ካልሆነ በቀር ውሸት ነው። ምክንያቱም ናሽናል ጂኦግራፊክ ላይ የሞንጎልያ የዱር ግመሎች ብሎ አይቻለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ሰው ግመልን ከማላመዱ በፊት ማን እያገናኛቸው ተዋለዱና እዚያ ደረሱ? እና ውሸት ነው። ያንን የሚያህል እንስሳ ቸንቸሎው እንዴት ትንሽ ሆነ? አንድ ታሪክ አውቃለሁ ስለሱ፣ እውነት እንደሆን አላውቅም። ፈጣሪ እንስሳትን ሁሉ ፈጥሮ ካበቃ በኋላ ነው ከያሉበት እንዲመጡ አስጠርቶ ቸንቸሎ ያደላቸው አሉ። መጀመሪያ የመጣው አህያ ነበር። First come, first served ተባለና የድሀ እግር የሚያህል ቸንቸሎ ተሰጠው። ቀጥሎ ፈረስ መጣ፣ እሱም ግድንግድ ቸንቸሎ ተሰጠው። እያለ እያለ ሰው መጣ፣ እሱም እስከዛሬ ድረስ ደስተኛ ስላልሆነ እየደበቀ የሚኖርበትን ያህል የተሰጠውን ወስዶ ሄደ። መጨረሻ ላይ በረሀ ለበረሀ ሲዞር የነበረው ግመል መጣ። ፈጣሪ እንስሶቹ ሁሉ የደረሳቸው መስሎት ነበር። ግመልን ሲያይ ደነገጠ። ግመል ጉዱን አላወቀም፣ ድርሻዬን አለ። ፈጣሪም "አይይይ ግመል፣ ምነው ዘገየህ? ካለቀ መጣህ፣ ይቺው ነች የቀረችው!" ብሎ መዳፉ ላይ ትንሽዬ ቸንቸሎ አሳየው።
ግመል ቀወጠው! "አመዳሞቹ እነአህያ ያንን የሚያካክል ወስደው ለኔ ይቺን፣
እንዴ አልፈልግም!" አለ። ፈጣሪም ሊያግባባው ሞከረ፣ "በቃ በረሀ ትዞር የለ፣ የውሃ ጥም መቻያ ሰጥሀለሁ፣ በሱ አካክሰው" ምናምን አለው። ግመል ገገመ። ተናዶ "ትልቅ ቸንቸሎ ነው የምፈልገው፣ ሌላ አልፈልግም" አለና ተናዶ ዞሮ ሊሄድ ሲል ፈጣሪ ተቆጣ።
"ና አንተ!" ግመል አልሰማም አለ። ዞሮ መሄድ ጀመረ። ይሄኔ ፈጣሪ ተናዶ "እናትህን!" አለና ትንሿን ቸንቸሎ ወረወረበት። ቸንቸሎዋም ሄዳ ቂጡ ጋር ተጣበቀች! እናም ሲሸና ወደኋላ ሆነ . . .
ወደኋላ . . . እንደግመል ሽንት . . .

@wegoch
@wegoch
@paappii
#Gemechu Merera Fana 🖤
#ይህ የሆነው ባለፈው ነበር;
አስቤዛዬ ሲሟጠጥብኝ ለመሸመት አመዴ ገበያ ወደተባለው ስፍራ ወረድኩኝ። ወደ ገበያ መውረድ ደስ ይለኛል። ቁምጣዬን ለብሼ ቆለጤን ከግራ ወደ ቀኝ እያማታሁ በገበያው መሀል እባዝነው ጀመር።

አንዲት አትክልት አሻጥር ባታሌ መሳይ እሴት ጋር ተጠጋሁ! ሻሽ አስራለች።
ቅልብልብ የሚል ዓይና ፣ ሰልካካ ሊባል የማይችል አፍንጫ አላት! ከንፈሮቿ
የተንጠለጠሉ ናቸው። አንገቷ ላይ ማህተም አለ። ማህተሙን ተከትዬ ስወርድ መስቀሏ በትልቅ ጡቶቿ
መሀል ተነክሯል! እኔ ልነከርልህ! የተጠጋጋ ያጡት ነው! ቡጉንች ያጡት አደለም አጋፋሪ ጎምላላ ያጡት ነው!
' አባቱ ምን ልታዘዝ ' ብላ ከጡት ላይ የዋለውን ዕይታዬን ደረመሰችብኝ። ለካ
በጡቷ አካባቢ ደፈጣ ሳካሂድ ደቂቃዎች ነጉደዋል! በውበት ዕይታ ግዜ ምንድነው ? የምሰጠኝን ነገርኳት። የግንባሬን አሳዛኝነት ተመልክታ ጥሩ ጥሩ አትክልት ከተተችልኝ! ' እሷ የለችም እንዴ ? ' አለችኝ። ማንም እንደሌለ ገበያ መውረድም ሙዴ እንደሆነ ነገርኳት። ስለ ትዳር አወራን። ለትዳር ጥሩ ምልከታ የላትም! ቀሽም ወንድ እንደበደላት ነገረችኝ። አንዲት ሴት ልጅ አላት! ይህን ሁሉ ስታወራኝ ለቂጤ በርጩማ አቀብላኝ ነበር። አቤት ድምጿ! አቤት አተራረኳ! አቤት ጨዋነት! ቀና ብዬ ገርመም ሳደርጋት በሰላሳዎቹ አጋማሽ ላይ የምትንቀዋለል ደርባባ ሴት ናት!
ጨዋነቷ የገነፈለብኝ ለዚህ ነው አልኩኝ።
ሌላም ግዜ መጥቼ እንደምሸምታት ቃልም ገብቼ ፣ ቁጥሬን ሰጥቼ ተለያየን!
ከስጋ ዘመዴ የምነጠል ያህል ተሰማኝ! የቋጠረችልኝን አስቤዛ አንጠልጥዬ ጋሪ
ላይ ተሳፈርኩኝ! ማታ ጋደም ብዬ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ አካሄድ እያሰላሰልኩኝ! ስልኬ ጮኸች!
የማላውቀው ቁጥርም ነበር!
' አንተ ጨዋታዬ ይህን ያህል መስጦህ ነበር ? '
ቀን የሰማሁት ባለ-አስቤዛ ድምፅ ነበር!
' እንዴ እንዴት ? '
' ሂሳብ ሳሰጠኝ ሄድካ....'
' ወይኔ አዎ! ለምን ሳጠይቂኝ በናትሽ ? '
' ምን ችግር አለው መመለስህ አይቀር! ' አቤት ጨዋነት!
ከትንሽ ወጎች በኋላ ነገ ከስራ በኋላ ደውዬ እንደምሰጣት ነግሬአት ተሰነባበትን! ከአንድ ሸጎጥ ካለች የመንደር ግሮሰሪ ምሽት ላይ ደውዬ ጠራዃት! ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውበት ደርባ ተሽሞንሙና መጣች! ደነገጥኩኝ! ድንጋጤዬን አይታ መሰለኝ ልክ እንደ ረዥም ወዳጅ በእቅፏ ከተተችኝ! ፍርሃቴ እንደ ብናኝ
ከላዬ ረገፈ! አምሽተን! ማለዳ ላይ ተስፈንጥሬ ተነስቼ ቁርስ አስቤዛዋን ያካተተ ዕንቁላል ስልስ ሰርቼላት በላች! ከልቧ ተደመመችብኝ! ሸኘዃት!
አሁንም ሂሳቧን ረሳሁትን ረሳችው!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#noah
ወይዘንድሮ
(በእውቀቱ ስዩም)
.
ወይ ዘንድሮ- አለ ስንዝሮ- አንድ ዶላር በአምሳ ሁለት ብር ዘርዝሮ !እንደማመመጥ! የተሻለ ይመጣል ብለን ስንጠብቅ፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት አዲስ የኮቪድ ጎረምሳ ፈቶ ለቆብናል ፤ በአምናውና በዘንድሮው ኮቪድ መካከል ያለው ልዩነት ምን ብየ ላስረዳችሁ? በልዩሃይል እና በሪፓብሊካን ጋርድ መካከል ያለው ያቅም ልዩነት እንደማለት ነው ፡፡
አምና ሁሉም ቻይና ላይ ነበር ጣቱን ብቻ ሳይሆን አንቴናውን እሚቀስረው! አሁን እያንዳንዱ አገር የራሱን ብራንድ ቫይረስ በማመንጨት ላይ ይገኛል ፡፡
ባለፈው ወዳጄ በየነ ዶክተሮች ምርመራ አድርገውለት
“ ኮቪድ አለብህ”ሲሉት ምን ብሎ መለሰ?
“ የእንግሊዙ ነው የደቡብ አፍሪካው?"
እኔን አይያዘኝ አልልም ! ከያዘኝ የኢትዮጵያው እንዲደደርሰኝ ፀልዩልኝ! አንዳንዴ ሲደብረኝ አዲሳበባ ወይም ማርቆስ ለሚኖር ጉዋደኛየ እደውላለሁ ፤
“ እንዴት ነው ኮቪድ? ”
“ እኔማን ትናንት ይዞ ለቀቀኝ “ ይለኛል
“ ፍቅር እንኩዋ ትንሽ ሳያሽ፥ ሳያከስል፥ ሳያከሳ አይለቅም ! እንዴት ዝምብሎ ይለቅሃል?”እላለሁ በቅናት ስሜት ፤
የሆነ ነገር ትዝ ይለኛል ፤ ድሮ መገናኛ ካልዲስ ካፌ ፊትለፊት ቆሜ የኮንሮባንድ ጫማ ስመርጥ የሆነ መዳፍ ትከሻየን ይነካኛል ፤ ዞር ስል አንድ ሰውየ “ኦ ይቅርታ ከማጅራትህ ሳይህ ከማውቀው ሰው ጋር ተመሳስለህብኝ ነው” ይለኝና ለጥቂት ሰከንዶች ይዞት የነበረውን ትከሻየን ይለቀዋል፤ ሸገር ያሉ ጉዋደኞቼ “ ኮቪድ ይዞ ለቅቀኝ ሲሉኝ “ ይሄ ነው ትዝ እሚለኝ!
እኔ ያለሁበት ከተማ የማስክ አነባብሮ ሁሉ ተጀምሩዋል ! በሰርጀሪው ማስክ ላይ ሌላ ከገበርዲን የተሰራ ማስክ ካልደረብሽ አገልግሎት አታገኝም ፤ ትንሽ ቆይተው፤ ኦክስጂን ራሱ በጉልኮስ መልክ የሚሰጡን ይመስለኛል ፤
ይህንና መሰል ጣጣዎችን ለመርሳት ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ ፤ዩቲውብ ለታታሪ ተመልካች መክፈል ቢጀምር እካሁን መኪና ብቻ ሳይሆን የራሴ መጠበቂያ ድሮን ሁሉ ይኖረኝ ነበር፤ ለመሆኑ ምንድነው እማየው? ፖለቲካ? ለእድሌም አላሳየው! ትናንት በርካታ ቆነጃጅት አንዱን አልባሌ ዘፋኝ ከበው ሲደንሱ አይቼ ዘና አልሁ ! ሌዲ ጋጋ የኢግዚቢሽን ማእከልን ድንኩዋን የሚያክል ቀሚስ በምትለብስበት ዘመን ያገራችብን ጉብሎች በከፊል መለመላ ሲቀውጡት አይቼ ተደነቅሁ ! በእኛ ጊዜ ክሊፕ በአይናፋር ሙድ ነበር እሚሰራው! አለማየሁ እሼቴ ኩኩ ሰብስቤን “ እንግዳየ ነሽ የኔ እንግዳ በበሩ ገብተሽ አረፍ በይ ጉዋዳ” ይላታል፤ እሱዋም እየተሽኮረመመች ያንኑ ትደግምለታለች! ግን ሁለቱም ጉዋዳ ለመግባት አይደፍሩም! ዘፈኑ ጀምረው እሚጨርሱት ከግቢ ውጭ ነው ፤ ዛሬ አስራ ምናምን ወይዛዝርት ሊሞዚን ውስጥ አንዱን ጎረምሳ ከበው ሲደንሱ አያለሁ! መብታቸው እንደሆነ ባምንም በዘፋኙ ላይ የተሰማኝን ቅናት የቀላቀለበት ንዴት መደበቅ አልቻልኩም ! እኔ እዚህ ተኮራምቼ ተቀምጨ የሰው አገር ብርድ እየጠጣሁ ፤ እንዴት ዋናው ሰብአ ሰገጥ ፤ ጨረቃ በመሳሰሉ ኮረዶች ይከበባል? በውነት ፌይር አይደለም!
የሆነ ቁምነገር ነገር ልጨምር! ብዙ ያገሬ ሰው በብልግና ነክ እንቶፈንቶ ቪድዮዎች ሲማረር አየዋለሁ ፤ የሚሻለው አለማየት ነው! እይታ በሌለበት እንዲህ አይነት ቪድዮዎች አይለመልሙም! ግን ያገሬ ሰው ባፉ እያማረረ ባይኑ ይቸክላል! ታድያ ገበያው ካለ ሸቀጡ ለምን አይኖርም?

@wegoch
@wegoch
ወሬ እና ሴት


እኔኮ ግርርርም የሚለኝ ወሬ ሲነሳ የሴቶች ስም ነፋስ እንደሚያነሳው ላስቲክ አብሮ መነሳቱ!

ወሬው ሲወራ እዛ እኛ ሰፈር እንዳለው የነ ጋሽ አለሙ ትልቅዬ ዲሽ ጆሮህን ዘርግተህ አትሰማ ይመስል!

እንደው ቆይ ቆይ ፍረዱኝማ!.....ያለወሬ ጠቅላላው የአለም ህዝብን ህልውና አስቡት ብትባሉ ይዋጥላችዋል???? በተለይ ሀበሻን?


ወሬኮ ለሀበሻ እስትንፋሱ ነው! ቡና እንጠጣው፣ እድሩ ፣ሰንበቴው ዋና ጥቅሙ ምን ሆነና! እኚ ደግሞ ዘመናዊዎቹ እነቴሌቪዥን እነማህበራዊ ሚዲያ የተፈጠሩት ለምን ሆነና? .... በዘመናዊ መልኩ አቀናብረው ያው ውሬ ለማስፋት ነው! እንደውም .......የሀበሻን ህዝብ 3ቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች ምን ምንድን ናቸው በለህ ብትጠይቅ 1.ወሬ 2.ወሬ 3ኛም. ወሬ ብሎ ባይመልስ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል!

ወሬ ህይወቱ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ እሷም ተዘርታ የፀደቀች አንዲት ሴትም ወሬ ወዳጅ ሆና መፈጠሯ ምንም አያስደንቅም!

እንደውም ባለፈው አንዱ የተቀነባበረ ወሬ ማሾለኪያ (ቲቪ) ሲል እንደሰማውት.... ለስለላ እና ለድርድር ስራ( ዲፕሎማሲ) ሴቶች ቁጥር አንድ ተመራጮች እየሆኑ መጥተዋል.

ባል ተብየውስ..... እዛ..... "ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ!" ስትል ትውልና እዚ ደሞ ዞር ብለህ ማታ እራትህን ከምርጥ ቡናህ ጋር እያጣጣምክ ስለሰፈሩ ፣ስለሰዉ፣ ስለባቄላ ዋጋ፣ ስለውስላታዋ የሰፈርህ ሤት፣ ስለልክስክሱ የሰፈርህ ወንድ፣ ማን ተጣላ ማን፣ እርቅ አወረደ፣ ማን ሞተ፣ ማን ወለደ... ሚለውን የተጠራ መረጃ ምታገኘው ከሷው አይደል?

ወሬ እና ሴቶች እጅና ጓንት ባይሆኑ ኖሮ ይች ምድር እንዴት አስቀያሚ ትሆን ነበር ባካቹ!

ወሬውን ሴቶች ባያዳርሱት ኖሮ አፈታሪኮች እዛው ተቀብረው ቀርተው ዛሬ ለኛ ባልደረሱን ነበር! እሱን ተውትና የክርስቶስ ትንሳኤንም ባልሰማን ነበር.

በየቡናችን ላይ የምንፈተፍተው ምርጥ ጭብጥ አጥተን ቡናችን ባልደመቀ ነበር!

አንድን ሰፈር ሰፈር የሚያስብለው በውስጡ የሚንሸራሸረው የወሬ ብዛት ነው! (የሴቶች ህብረት አቋም!)

ወሬኛ ህዝብ ጤነኛ ህዝብ ነው! ብሏል በውቄ! እውነቱን ነው... እንደፈረንጆቹ ቤት ውስጥ ስልክ ሚባል ግድግዳ፣ እእ! ባቡር ውስጥ ወይ መኪና ውስጥ ጋዜጣ ወይ መፅሀፍ የሚባል ግንብ ከጎረቤት መከለያ አጥር በራሱ ላይ አጥሮ ሲቆይ ይኸው ድባቴ ሚባል በሽታ አጥቅቶት እርፍ!...... እኛ አገር ይህ ችግር ሲያልፍም እማይነካካበትን ምክንያት አስቀምጡ ብትባሉ ከሴቶች ውጭ ሌላ ምክንያት ከየት ታገኛላቹ? ለዚ ደሞ ሴቶች ምስጋና ይገባቸዋል!

ባለፈው አንዱ ፕሮፌሽናል ወሬኛ ጓደኛዬ(ጋዜጠኛው ማለቴ ነው) ምን አለኝ መሰላቹ...."ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ይቀጡልን! ጥርሳችችን የነቀልንበትን ሙያ ሰረቁን!" በሚል መሪ ቃል ሴቶች አመፅ ሊያስነሱ ነው....አለኝ
..
....
ታድያስ! እውነት ነው! ከድሮ ጀምሮ ሲነቀፉበት ሲ ሰደቡበት እና ሱብጠለጠሉበት የነበረን ሙያ ሲነጠቁ ማየት አይደለም አመፅ ማስነሳት መንግስት ቢያስገለብጥ አያስደንቅም!

እንደውም...በአለማችን ላይ 7ቱንም ቀኖች 24 ሰዓት ሙሉ ያለማቋረጥ በማውራት ጊነስ ቡክ ላይ ላለመመዝገባችን እንደተግዳሮት አድርጌ የምቆጥረው ሲወራ አሥሠፍስፎ መስማት ሚወድ ግን አውሪውን ማያበረታታው ማህባሰባችን ነው! እንጂማ የት በደረስን! በተለይ ባሁኑ ሁሉም ሰው በወሬ Phdውን በያዘበት ዘመን!

ደግሞኮ ሴት ወሬኞች ከወንድ ወሬኞች የሚለያቸውና ሙያው ልክክ እንደሚልባቸው የሚያሳብቀው በደረቁ አለማራታቸው! ..... ወሬውን ማድመቅያ የተለያዩ ቃናንያላቸውን ድምፆች ፣ ግንነት ፣ የእጅና የፊት ትርኢቶች ካስፈለገም በወሬው መሀል የነበረን ጭፈራም ይሁን ድርጊት ጣል አድርገው ማውራታቸው ለወሬውም ጥፍጥና መጨነቃቸውም ለሙያውም ክብር እንዳላቸው ምርጥ ማሳያ ነው!

የማያምርበትን ሙያ በግድ ካላማረብኝ ብሎ ያለሙያው የሚወጠወጠው ወንዱ ወሬኛማ አይጣል ነው! ክሽን ያለች ወሬ ከሱ መጠበቅ ዘበት ነው! ግን ሲያወሩ ሴት ወሬኞችን ለሚያስንቁ ወንዶች እጅ ነሳለው!

ወሬ ለዘላለም ትኑ ር! ( የሴቶች ማህበር ዋና ዳይሬክተው የወይዘሮ አሰፉ ጥቅስ!)

By #magi

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፕሮፋይሏ!

ስወዳትኮ....ውይ! ቃላት አይበቃኝም ለመግለፅ

ልክ የክርስቶስን ተዐምራት ምድር ብራና፤ ውቅያኖስ ደግሞ ቀለም ሆኖ ቢ ፃፍ እንኳ እንደማይበቃ እኔም እንደዛ ነው ምወዳት! ችግሩ እሷ አታውቅም። የልቤ ሁከት አፌጋ ሲደርስ 'አሀዱ ተብሏል ዝም በሉ' እንደተባሉ ምዕመናን ጭጭ! ይልብኛል

ታድያ በፌስቡክም በቴሌግራምም በቫይበርም በሁለም ጓደኛሞች ነን። አወራን ቢባል የሳምንት ምልልሳችን ተጨምቆ እንደምንም ግማሽ ገፅ ቢወጣው ነው። ብቸኛ መፅናኛዬ በየ5 ቀኑ የምትቀይረውን ፕሮፋይሏ ማየት ነው. ፌስቡክ ላይ ፎቶዋ ዝር ብሎ አያውቅም ለምን እንደሆነ እንጃ! ቫይነርም የሆነ ጥቅስ የያዘ ፎቶ ትሰካበታለች! ቴሌግራም ግን...

እሷ ስቃ ፣ እሷ ስታስብ፣ እሷ አኩርፋ። እሷ አዝና፣ ፀጉሯን በጎን ጎንጉናው፣ ጆሮ ጌጥ አድርጋ ፣ ሳታደርግ፣ ቆማ ፣ተቀምጣ፣ ተኝታም ሊሆን ይችላል.... ብቻ እስክትቀይር በጉጉት እየተበቅኩ ማየት ብቸኛ መፅናኛዬ ነው.

አንዳንዴም ከሷ ተውሼ የኔ ላይ ማድርግ ያምረኝና ደግሞ 'ምን አስበህ ነው አንተ?' ብላ ብትጠይቅኝ ምን ብዬ መልሳለው ለሚለው የራሴው ጥያቄ መልስ ሳጣለት ተወዋለው!

እንድ ቀን ግን እንደለመድኩት 5 ቀን ሞልቶት የፕሮፋይሏን መቀየር በጉጉት እየተጠባባኩ ሳለ... የሆነ የሚፍለቀለቅ የወንድ ምስል ላይ 'የኔ ልዩ' ተብሎ ተፅፎበት አየው..

እንዴ?? ንድድ አለኝ! ስልክህን ጣለው ጣለው አለኝ. መልሼ ግን ፎቶውን አጠናውት.....

ምን ይመስላል! ደግሞ አማረብኝ ብሎ መሳቁ.. ከመሳቁ በፊት ሄዶ የጉንጩን ስርጉድ አያስሞላም! ልትስመው ስትል ድንገት ሳታስበው ከንፈሯን አደናቅፎ ቢጥላትስ?

የሆነ አመዳም! እንደውም ያስታውቃል ሴቶች ሚለቀለቁትን አመድ እንደለመደ! በጤናው አይደለም ፊቱ እንዲ መስታወት የመሰለው! መጀመርያ ሄዶ ይታጠብላት... ባፍንጫዋ ስትተነፍስ ድንገት አመዱ ቦኖ ቢያፍናትስ ቆይ??

ደግሞ ጥርሱስ?? ይሄ ልጅ ቂም አለበት እንዴ?? አይኗን አሳውሮ ሊያስቀምጣት አሥቦ ሳይሆን አይቀርም እንዲ ጥርሱን ያነጣው! ይሄኔኮ እኔ ሙሉ ልብስ የምገዛበትን ገንዘብ አውጥቶ በጨረር ታጥቦ ይሆናል! አሁን እንደው ለሚወዱት ሰው ይህን ያህል መጨከን ምን ይሉታል! ቢመጣ ቢመጣ ባይን ይመጣል??? ጥርሳም!

አቤት አቤት አቤት! ደግሞ ፀጉሩም ተፈርዞልኛል! የህቱን ሻምፖ ቆይ ምን አስጨረሰው? ምናለ ትንሽ ብትጠቀምበት?
....
..........
ድንገት የልቤ ንግስት typing... ስትል አየዋት .....
ልቤ ልትቆም ምንም አልቀራት ነበር. እንኳንም ቶሎ replie አደረኩላት እንጂ 'አይተኸው ዝም ብለኸኛል' በሚል ሰበብ 1 ሁለት ቀን ባለመመለስ ትቀጣኝ ነበር.

"hi መሳይዬ"

"hey!"

በቀጥታ ስለፕሮፋይሏ ላለመጠየቅ ስለውሎዋ ስለጤናዋ ስጠይቅ ዳርዳር ስል ቆይቼ በስተመጨረሻ

"ppw ያምራል!" ብዬ ጀመርኩ

"እመሰግናለው! ናዝሬት ያለው የአጎቴ ልጅኮ ነው"

እኽኽኽኽ!
የሞት ፍርድ ተፈዶበት ምህረት የተደረገለ ሰው እንኳ እንዲ አይተነፍስም.

የሰደበው ልቤ መልሶ
' መጠርጠር ነበረብኝ... እንዲ ያማረው ለካ ዘመድሽ ሆኖ ነው..... ውይ ውይ ውይ! ሰው እንዲ ውበቱን ይደፋበታ........" አንጀቴ ቅቤ ጠጥቶ!

"መሆንም አለበት!"

........

....


Maggie ፃፈችው

@wegoch
@wegoch
@paappii
አንዳንዴ ... አንዳንዴ ብቻ እንደዚህ አስባለሁ። አሁን አይበለዉና የልብ ህመም እንደ ጉንፋን ሁሉንም ሰዉ የሚይዝ ቢሆን ሰዉ ለመጠላላት አቅም ያጠራቅም ነበር? ድንገት ከእንቅልፉ ሲነቃ የአይኖቹን ሽፋሽፍት መግለጥ ቢከብደዉ? ፤ እግርና እጆቹን ማዘዝ ቢሳነዉ? ፤ እየሞተ ይሁን እየነቃ ማወቅ እስኪያቅተዉ ቢሆን ከዛች ቅፅበታዊ መከራ ወጥቶ ሰዉ ይጠላል? እሺ ሰዉ መሃል ተሰብስቦ ደስ ብሎት በፌሽታ እየዘለለ ካለበት ቅፅበት ድንገት መሬት ላይ ተንሸራቶ ቢወድቅ? ፤ አንድ ብርጭቆ ዉሃ አንስቶ ወደ አፉ ማስጠጋት እየፈለገ ቢያቅተዉ? ፤ አንዳንዴ ያለሰዉ የፈለገበት መሄድ ባይችል? ከዚህ ሁሉ የደቂቃዎች ዉጥንቅጥ ሲነቃ ሰዉ ይጠላል? እንዴት አድርጎ?

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#Ruth Habte Mariyam
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!! (ርዕስ ነው!!)

"ቦታችን በተለመደው ሰዓት እጠብቅሃለሁ:: አፈቅርሃለሁ!" የሚል መልዕክት ነው እንዲህ ያስቦረቀኝ!!

እሱ ጏዳ ቁርስ እያበሰለ የሚያማስለው የመጥበሻ ድምፅ ይሰማኛል:: ስልኩ መልእክት ሲቀበል ድምፅ አሰማ ያለወትሮዬ እጅ ጥሎኝ ስልኩን አነሳሁት::

አንደኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው! እኔና እሱ የኛ የምንለው ቦታ ኖሮን አያውቅም!! ከቤታችን ውጪ

ሁለተኛ የተለመደ ሰዓት አላቸው:: እኔና እሱ ለምንም የተለመደም የተመደበም ሰዓት የለንም:: የልደት ቀኖቻችንን እንኳን እረስተነው አልፎ ... 'ለካ ትላንት ነበር' የምንባባልበት ጊዜ አለ::

ሶስተኛና ዋነኛው ታፈቅረዋለች::

ይሄ ሲሰላ ቀመሩ እሱም ከኔ በላይ ያፈቅራታል ማለት ነው!

ደስ ሲል .....

"ምን ተገኘ?" ይለኛል አስሬ የሰራልኝን ቁርስ እያጎረሰኝ

"ምነው?"

"በጣም ደስ ብሎሻል! ይሄን ፈገግታ ካየሁት የማላስታውሰውን ያህል የጊዜ ርዝመት ያህል ዘመን ሆኖ ነበርኮ!" አለኝ የተለመደ የተመጠነ ፈገግታውን እየፈገገ... ዝም አልኩ

እያመነዘርክብኝ እንደሆነ ሳውቅ ነው ደስ ያለኝ! ይባላል? አይባልማ!!
.
.
.
ሊወጣ ይለባብስ ጀመር::

"እሱን ሸሚዝ ቀይረው:: ቅዳሜ አይደል? ፈካ ያለ ነገር ልበስ.. ቆይ እኔ ልምረጥልህ!" ብዬው ቄንጠኛ ሸሚዝ እፈልግ ጀመር ... ተዝረክርኮ ሄዶ የባሌ አፍቃሪ ፍቅሯ እንዲቀንስ አልፈልግማ! ተውቦ ነው መሄድ ያለበት!!

አንዴ ፀጉሩን አንዴ ጫማውን ... ደሞ ኮሌታውን ሳስተካክልለት ግራ ተጋብቶ ያየኛል::

"ዛሬ በጣም ጥሩ ሙድ ላይ ነሽ!" ብሎኝ ከንፈሬን ስሞኝ ወጣ!!

ልፀልይ ሁሉ ቃጣኝ:: ግን እንዲህ ያለው ፀሎት ለእግዜር ነው ለሰይጣን የሚቀርበው?

"በምንዝርናው እንዲፀና አድርግልኝ! ደግሞ ደጋግሞ እንዲያመነዝር እርዳው!! "

እንዲህ ያለው ድርጊት አምላክን አይመለከትም! ለዲያቢሎስ የትብብር ውይም የድጋፍ ጥያቄ ላቅርብ? ያው እኔ ባልጠይቀውም ወጥሮ ማስመንዘር መደበኛ ስራው ነው ብዬ ነው::

የአስር ዓመት ትዳሬ ነውኮ..... የመጀመሪያው ትሁን? እንዳገባ ታውቅ ይሆን? ሄዶ ሲስማት የኔን ከንፈር ልቅላቂ እንደምትስም ታውቅ ይሆን? እቤቱ ሲገባ የሚያስኮንን አፍቃሪ መሆኑን ታውቅ ይሆን? ዛሬም ከ10 ዓመት በኃላ እያጎረሰኝ እንደምበላ ታውቅ ይሆን? ወይስ እሷምጋ ዝንፍ የማይል አስኮናኝ አፍቃሪ ይሆን?

"ውሎህ እንዴት ነበር?"

"ፍቅሬ ለ2 ሰዓት ብቻ ነውኮ የተለያየነው?" አለኝ ከሷጋ እንደመጣ

"እኮ ቢሆንስ "

" እሺ ቆንጆ ነበር!" አለኝ መገረም ሳይለየው

ተጣልተው ይሆን? ተጨቃጭቀው? ለምንድነው የተለየ ፊት የማያሳየው? ምን አይነቷ ናት? ለሁለት ሰዓት እያገኘችው እንዲስቅ ማድረግ ያቅታታል? ወይስ እሷም እንደኔ መፈቀር ደከማት?

ባጠገቡ ሳልፍ መቀመጫዬን ደለቅ አደረገኝ!! እህህህ በቀን ሁለት እሙሙ አይሰለቸውም? ወይስ እሷ አትሰጠውም? እሷ እንደእኔ ሚስት ስላልሆነች ግዴታ የለባትም ይሆን? ወይም እንደኔ በገዛ ሀጢያቷ ስላልታሰረች ካልመሰላት ታፆመዋለች?

እኔ ሳገባው ቄሱ በመከራውም በደስታውም ... በድህነቱም በሀብቱም ... ብለው ያስማሉኝ እንጂ መሳቢያው ውስጥ እንደሚያስቀምጠው ገንዘብ በፈለገ ጊዜ እየከፈተ የሚዘግነው ንብረት እንዲሆን እሙሙዬን ማስያዜን አላስታውስም! (መሀላው የማላውቀው ውስጠ ወይራ ይኖረው ይሆን? ታዲያ የሚስትነት ግዴታዬ እንደሆነ የማስበው ማን ምን ብሎኝ ነው? ዛሬ ይለፈኝ ካልኩት የበደልኩት የሚመስለኝ በየትኛው ህግ ነው?

አንድ ቀን .... ርቆ እንደህልም በሚታወሰኝ አንድ ቀን በሰራሁት በደል .... ራሴን በእዳ አስይዣለሁ!!

"ሁለተኛ ቂጤን እንዳትነካኝ!" አልኩት ኮስተር ብዬ

"እንዴ? ለምን?"

"የራሴው ቂጥ አይደል?"

"አዎ"

"እንደገና ደግሞ የራሴው ሰውነት ላይ አይደል ያለው? ራሴው አይደል የተሸከምኩት?"

"እንዴ ፍቅር ምን ሆነሻል?"

"ሌላ ደግሞ አንዳንድ አንዳንድ ጊዜ ተሸከምልኝ ብዬ አላስቸገርኩህም አይደል? ደሞም ቂጤን በማጣፍት የሚመለስ የተበደርኩት ብድርም የለብኝምኣ?"

"ምንድነው ጉዱ?"

"በነዚህ ከተስማማን በገዛ ቂጤ የማዘው እራሴው ነኝ! ደስ ባለህ ሰዓት እጅህን እየላክ በጥፊ እንድታላጋው አልፈቅድም!! አበቃሁ!!" ብዬው ማሳረጊያ የተለመደ ፈገግታ ፈገግ ብዬ ሄድኩ::

ይቀጥል ይሆናል!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ!(የቀጠለ)

ሰይጣን ይሁን ራሴ ወይም ፈጣሪ ለሀጥያት በቀጠሩልኝ ቀን ከአለቃዬ ጋር ባለግኩ። ይኸው ነው ሀጥያቴ!

ጨው የሌለው አልጫ ወጥ አልጫ ወጥ የሚል ትዳር ውስጥ ፀጥ ለጥ ብዬ እንድቆይ ባለእዳ ያደረገኝ ሀጥያቴ ይኸው ነው!! ይኸው ነው ብዬ አቀለልኩት?

ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ስልኬ ባትሪ ጨርሶ ባሌ ሲደውል ስልኬ ዝግ ነበር። ካልጠፋ ቀን ስልኬ በዘጋ ቀን ስንት ቀን ባልተሰማኝ ያለፍኩት የአለቃዬ እጅ ሲነካኝ ንዝረቱን እንቢ ማለት አልቻልኩም። ካልጠፋ ቀን ባሌ የዛን ቀን ቢሮዬ ድረስ ዘለቀ። ምን የሚሏት ባላጊ ነኝ ግን? በዘመኔ ከባሌ ውጪ አንድ ሰው ብሞክር እሱንም የቢሮ ጠረጴዛ ላይ? እኔን ብሎ ባላጊ ! ቅሌቴ በዚህ አላበቃም።

ተያየን። ጠረጴዛው ላይ በግማሽ አካሌ ተጋድሜ ሰማይ የእኔን እግሮች ምሰሶ አድርጎ የቆመ ይመስል እግሮቼን ወደላይ ወጥሬ ሰድሬ አለቃዬ ከእግሮቼ መሃል ሆኖ ሲለፋ ባሌ በሩን ከፍቶ ሲገባ ተያየን። (አንባቢ ሆይ እዚህጋ ለምትስሉት ምስል እኔን ተጠያቂ እንዳታደርጉ:: ሁኔታውን በምስል ለመከሰት ታስቦ እንጂ አንባቢን ክፉ ለማሳሰብ ያልታሰበ!)

ለወትሮ ጨዋ ነበርኮ። ካልጠፋ ቀን የዛን ቀን ጨዋነቱን እረስቶ ሳያንኳኳ ዘው ይላል? አፌን ከፍቼ ብዙ ቆየሁ። ድንጋጤው ይሁን የአለቃዬ ልፋት ወይም ሁለቱም አፌም ተከፍቶ አይኔም ፈጦ ብዙ ሰከንዶች አለፉ!! ባሌ ቀስ ብሎ እንደገባ ሁሉ ቀስ ብሎ ወጣ! አለቃዬ በድንጋጤ የተጋለጠ ንብረቱን ለመሸፋፈን ይተረማመሳል። (ይሄ ደግሞ የሚስቱን ምጣድ በቂጡ ነው እንዴ የሚያስስላት? እሱ የበጨጨ ቀይ ፣ ቂጡ የብረት ምጣድ ቂጥ የሚመስለው!)

ከአንድ ሰዓት በላይ ቢሮዬ ተቀመጥኩ። ተጎለትኩ። የማስበውን አላውቅም። ወደቤት እንደማልሄድ አውቀዋለሁ። አይኑን አላየውም። ግን ወዴት ነው የምሄደውስ? ብቻ አላወቅኩትም። ቦርሳዬን አንስቼ ወጣሁ። ደርቄ ቆምኩ። ባሌ እየጠበቀኝ ነበር። ልክ ምንም እንዳላየ፣ ድሮ እንደሚያደርገው ሁሉ ዘሎ ከመኪናው ወርዶ በሩን ከፈተልኝ። ልሩጥ? መኪና ውስጥ ልግባ? ምን ላድርግ ደረቅኩ!

"ወደቤታችን እንሂድ አይደል?" አለኝ ቁጣም ፍቅርም ፣ ልስላሴም ምሬትም ባለው ድምፅ። አሁንም ምን እንደምለው ግራ ገባኝ። መሮጥ ፈለግኩ። ማምለጥ ! መሸሽ። ገብቶታል። አጠገቤ ደርሶ እጄን ያዝ አደረገው። ሲመጣ እያየሁት ደርሶ ሲነካኝ በረገግኩ። አብሬው ተራመድኩ።

"ስንት ጊዜያችሁ ነው?" አለኝ በፀጥታ ሲነዳ ከቆየ በኋላ

"ምኑ? ማለቴ? " ተንተባተብኩ

"ስታደርጉት የነበረውን ስታደርጉ ስንተኛ ጊዜያችሁ ነው?"

"የመጀመሪያችን"

"ትወጂዋለሽ? በፍቅር ትወጂዋለሽ? ከኔ በላይ ትወጂዋለሽ? "

"ኸረ አልወደውም!" እያልኩት ለምን አይሰድበኝም? ለምን አይጮህብኝም? ለምንድነው ምንም እንዳላደረግኩ ተረጋግቶ የሚጠይቀኝ? እያልኩ አስባለሁ ።

"ፍቅራችን ይህን ማለፍ አይችልም?" አለኝ። ዝም አልኩ።

"ይህን ማለፍ የሚችል ፍቅር የለንም?" አሁንም ዝም አልኩ።

"ይችላል። በደንብ ይችላል!!" ራሱ መለሰ። ድምፁ ውስጥ አማራጭ የለውም::

እቤት ስንገባ አፉ ከመለጎሙ ውጪ ከዛ ቀን በፊት ከሚያደርገው ምንም ዝንፍ ያላለ አመሻሽ አመሸን። አስፈራኝ! ብዙ ክፉ ሀሳብ አሰብኩ። ለዓመታት አቅፌው የተኛሁት ባሌ እንቅልፍ ሲወስደኝ ሲጥ አድርጎ የሚገድለኝ መሰለኝ። እያበድኩ መሰለኝ! ባልጌያለሁ አይደል? ቅድም ባሌ ስባልግ አይቶኝ የለ? ወይስ ቅዠት ነው?

ልክ አይደለማ! ሚስቱ ስትማግጥ በዓይኑ አይቶ ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን ምኑ ነው ልክ? ንዴቱ ይቅር እንዴት አላስጠላውም? ለምን ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም? ጭጭ አለ። እያጎረሰኝ እራት በላን!! ሶፋው ላይ እግሮቹ መሃል አስቀምጦ አቅፎኝ የጀመርነውን ተከታታይ ፊልም አየን! እሱ አየ እኔ ዓይኔ ቴሌቭዥኑ ላይ እየተንቀዋለለ ቅዠት እሰፍራለሁ::

ከቅሌቴ በፊት

እንደአብዛኛዋ ኢትዮዽያዊ ሴት ዮንቨርስቲ ጨርሼ እስክወጣ "ወንድ ልጅ ኡፉ ነው::" ተብዬ ነው ያደግኩት:: (ምኑጋ እንደሚፋጅ አልነገሩኝም) ይሄ ወንድ የሚሉት ፍጥረት ከአላማ የሚያስተጏጉል... ወደፊትሽን ሊቀጭ አሰፍስፎ የሚጠጋሽ አሰናካይ .... ከብልግና ውጪ ሀሳብ የሌለው ክፉ ፍጡር .... (እንደአላብዛኛዋ ሴት ያሉኝን አምኜ ወይም ፈርቼ ይሄን እርኩስ ፍጡር ስሸሽ አድጌ አላማሽ ነው ያሉኝን ትምህርቴን ተመረቅኩ)

ከዩንቨርስቲ ተመርቄ ስራ እንደጀመርኩ ያ ኡፉ ነው የተባልኩት ወንድ ድንገት በህይወቴ አንገብጋቢ ፍጥረት ሆኖ መጪ ሂያጅ "መቼ ነው የምታገቢው?" ይለኝ ገባ! እሱ በህይወቴ ስለሌለ ከህይወት ወሳኙ ክፍል እንዳመለጠኝ አይነት!!

ስሸሸው ኖሬ ኖሬ ስፈልገው ብቅል የሚል ያስመስሉታል!

እንደአብዛኛው ሀይማኖተኛ ቤተሰብ እንዳላት ኢትዮዽያዊ የባል መስፈርቱ "እግዜርን የሚፈራ" ተብሎ ተምሪያለሁ:: 100 ሺህ እግዜርን የሚፈራ ወንድ ቢኖር ከነዚህ መሃል የኔን ባል የምመርጥበትን መለኪያ አላስተማሩኝም:: ... ከመቶ ሺወቹ የተገኘው ... የቀደመ ... ወይም ይሄን ገፍታሪ መኮሳተሬን የደፈረ...

መጣ! እግዜርን የሚፈራ .... እጅግ ደግና መልካም! ጨዋ የጨዋ ዘር .... አወቅኩት! ለመድኩት!! ወደድኩት!!

"የተባረከ! መሬት የሆነ ወንድ! እድለኛ ነሽ" ተባልኩ::

ቤተክርስቲያን ቆሜ በህመሙም በድካሙም በፎከቱም ..... ላልለየው ብዬ ቃል ገባሁ:: ውብ ነበር:: የመጀመሪያዬ .... የመጨረሻዬ ... ህይወቴ .. ዓለሜ ... ተባባልን!! ኖርን ኖርን ኖርን ..... ሁለት ዓመት .....

የወደድኩት ባሌን ሳይሆን ትዳርን እንደሆነ ገባኝ ... እንዴት? አላችሁ? እሱን ላላገባችሁ እና ለፍሬሽ አግቢዎች አብራራለሁ ያገባችሁ (ቢያንስ 5 ዓመት የሆናችሁ) ገብቷችኃል::

"ልጅ እንውለድ አይደል ፍቅሬ? " አልኩኝ የሆነ ቀን

"ልጅ መውለድ እንደማልችል አልነገርኩሽም እንዴ?" አለኝ ልክ ውይ የላክሽኝን ቲማቲም ሳልገዛ ረስቼ መጣሁ እንደሚባለው ዓይነት ቅልልል አድርጎት .....

(በነገራችሁ ላይ አልጨረስንም)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
እሱ ስለ እሷ


ታሪክ አታሳጣኝ ብላ የምትፀልይ ይመስል የሚተረክ ማንነት አይጠፋትም።ትኖራለች፡ኖራለች።
ድንገት ነው የጠየኳት"ህይወት ውለታ እንድትውልልሽ ብትፈልጊ ምን ትጠይቂያታለሽ?"
"ፈጣሪዬ ብቻ ተስፋዬ እስኪሆን ድረስ በወጀቧ አስረድታ እንድታጠነክረኝ"አለችኝ።
ትገርመኛለች…ብርቱ ናት፤ፈሪም ናት፤ችኩል ናት፤ቀላል ናት።የአጠገቧን በቀረባት ሰዓት ለማድረግ ትቸኩላለች፤አታሳድርም…የዛሬ ልጅ ናት።በየቀኑ የተወለደች ይመስል ለዛሬዋ ህይወትን አትነፍግም።

እኔስ የትዝታ አድናቂ የነገ ናፋቂ ነኝ።ግን አንቃረንም።
"ነበር?ነበር ማን ነው …ንገረኛ…ትላንት የሚባል ቀን ነው?እኔ እስከዛሬ ትላንት በሚባሉ የዛሬ ጥርቅሞች ውስጥ እንደኖርኩ ማን ለነበር ተንታኞች በነገራቸው" በለስላሳ ዛቻዋ እንዲህ ትለኛለች።
…ያልተለመደውን የምትኖር ወይ የተለመደውን ባልተለመደ መንገድ የምታስኬድ ብዬ እንዳልፈርጃት ግራ ይገባኛል ግን በመደናገር ትገርመኛለች…ግን ቀላል ነች።ቀላል ተብለው የተተዉትን ስሜቶች ትኖራቸዋለች።

ለሷ ሁሌ ዛሬ ነው፤ዛሬም ሁሌ ነው።ያላት ይናፍቃታል…"ናፍቆትን ማነው በእርቀት ውስጥ ላለው ነገ የሰጠው"ትላለች።ዛሬን እየናፈቀች ትኖራለች።
አቅፋው የምተኛው ይናፍቃታል…ሸለብ ካረገኝ ትቀሰቅሰኝና "ናፈከኝ" ትለኛለች።
ስታወራ ድምፅህን መስማት አላለችኝም።ስታወራ የምታወጣቸውን ቃላት ግጥምጥም አድርጌ በአይምሮዬ እየሳልኩት ስታወራ ፈዝዤ ልይህ እንጂ።
የአምስቱን የስሜት ህዋሳት ስራ ማዋዋስ በሷ ነው ያየውት።ትንንሽ ከንፈሮቿን በፍጥነት ይያንቀሳቀሰች ሀሳቧን አራግፋ ስታበቃ ዝምምምም ትላለች።ዝምታዋ የንግግሯ ቅጥያ ነው፤ አይጎረብጥም።የዝምታዋ ውበት ያወራኝ ይመስል ዝምታዋን እንዳደምጠው ፍቃዴን ወስዳዋለች።
ቀጠለችና "ናፈከኝ" አለችኝ። "አንተን ማቀፍ እኮ አይደለም(ለግላጋ ፀጉሯን በእጆቿ እያጫወተች) አጠገቤ መሆንህን እየማግሁ ቅርበትህን ማሽተት አለችኝ"… መዳሰስን ስራ አስፈትታ። ኑሮዋን ታስተጋባለች…ተጋባብኝ መሰለኝ እኔም ያለቃላት የምትገልፃቸውን ማድመጥ ናፈቀኝ።ጆሮዬን ድርጊት ላስደምጠው ናፈቀኝ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#heaቨን
እሱ ስለ እሷ ፪

ፈሪ ነች።ምንድነው የሚያስፈራሽ ስላት "ክፉ ሰወች እና ሁኔታዎች ሳይሆኑ የዋህነቴን ሊጠቀሙበት የሚመጡ ጥሩ ሰወች" ብላ እራሴን በመጠርጠር ውስጥ ታወዛግበኛለች።
ንፁህም ናት።እንደ ሰው የሚጠቀስ ከመልካም ተቃራኒ ደካማ ጎን ቢኖራትም አብዝታ ስለማትጠቀማቸው ንፁህ ነፃነት አላት።
"መልካምን የመተግበር ሙሉ መብት እያለን በተቃራኒው መድከም ምንድነው?" ትለኛለች። ለመምረጥ መድከምን አትወደውም።
በሚጋባ ፈገግታ የታጀበውን ፊቷን ወደእኔ መለስ አረገችውና "ሰው ያስባለን የመምረጥ ነፃነታችን አይደል!" አለችኝ።በግርምት "አዎ" አልኳት።ነፃነቷን ሳታዛባ ምርጫዋን አቅንታበታለች።

"ሁሉም መንግስተ ሰማያት መሄድን ይፈልጋል ግን ማንም መሞትን አይፈልግም" ያለችኝ በትውስታ መጣብኝ።"የምትናፍቀውን ስጦታ ለማግኘት አንተ ጋር መሞት ያለባቸው ነገሮች አሉ።" ደጋግማ ከምትለኝ በከፊል ከምረዳቸው ሀሳቦቿ አንዱ ነው።በምሳሌ ስታስረዳኝ "ታመህ የምትገዛው ደስታ ፍቅር አይደል… መታመም መንገድ ነው" ብላኝ ነበር።


መንግስተ ሰማያት መግቢያ በልብ ቢሆን የሰልፉን መጀመሪያዎች ለመቀላቀል ትመረጣለች ብዬ አስባለው።
ትገርመኛለች።አንዴ ያነገሰችውን አትጥልም፣ቦታ አትነፍግም፡ለጠቀማትም አታደላም። የጎዷትን ስታስብ አትታወክም።"ተስፋ ሀያል ነው…አይገርምህም ሰው ተስፈኛ ነው …ዛሬ ቢሰበርም ነገ ይዞ የሚመጣውን ለማየት ይጓጓል…ሰው ቢጎዳውም ሰውን መድሀኒት አርጎ የሚሾም እድለኛ ነው" አለችኝ።


"የዛሬ ልጅ ሆይ …ተስፋ ካልሽኝ አይቀር ስንጋባ የት ነው የምንኖረው?" አልኳት።እንደጠየኳት የዝናብ ጠብታዎች ይረግፉ ጀመር።
የጠየኳትን ጥያቄ ሳትመልስልኝ ዣንጥላውን ለመዘርጋት ስታገል አስቆመችኝ።
"ዝናብ እወዳለው ትላለህ ሲዘንብብህ ግን ዣንጥላ ትዘረጋለህ? …የምትወደውን ተለማመደው" አለችኝ።

ዝናብ የመውደዴ ምክንያት እሷ ናት።ዝናብ ትወዳለች።ከዝናቡ በፊት ላለው ነጎድጓድ ትኩረት አትሰጠውም። ። አለምልሞ፣ አጥቦ ፣አፅድቆ ለሚሄደው ዝናብ ግን ብዙ ታወራለታለች።ዝናብ ጅማሬ ቢሆንስ፡ያለችኝን አስታውሳለው።

ከትውስታዬ ስመለስ መልሼ ጠየኳት "የት ነው የምንኖረው?"

"ዛሬ አለችኝ።ነገን ስናልም ዛሬ እንዳያመልጠን ።የዛሬ ዝናብ እንዳያመልጠን" አለችኝ።

አንዳንዴ የለበስኩት አፈር ሲታየኝ ከሷ ልሸሽ ብሞክርም "ወርቅህ አፈር ነክቶታል ሲሉህ ትጥለዋለህ?" ብላ በእንስፍስፍ ከእቅፏ ትስገባኛለች።
ነፍሷን አርጥቦ የወሰደውን ዝናብ የኔንም ነፍስ አርጥቦ የምድር በደሌን ሊያጥብልኝ ነው መሰለኝ እሷን እያየው የዝናቡ ድብደባ ደበዘዘብኝ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#heaቨን
ኳስ የማይመለከቱም ሰዎች ቢሆኑ እዚች አለም ላይ እስከኖሩ ድረስ ታላቁን ክርስቲያኖ ሮናልዶ አለማወቅ አይችሉም። በአንድ ወቅት ጋዜጠኞች ለክርስቲያኖ ቃለ መጠየቅ ሊያደርጉለት ቤቱ ሄዱ ፣ እንዲህም ሱሉ ጠየቁት፦
በህይወትህ በጣም የምታከብረዉ እና ትልቅ ዉለታ ዉሎልኛል ብለህ የምታስበዉ ሰዉ አለ??

ሮናልዶ: "አዎ የ14 አመት ልጅ እያለዉ የስፖርቲንግ ሊዝበን መልማዮች ተጨዋች ለመመልመል ሰፈራችን ይመጣሉ። በአንድ ጨዋታ ላይ ብዙ ጎል ያገባ ተጫዋች ይመርጣሉ ተባለ ፣ ታዲያ እኔና ጓደኛዬ ፣ አንድ ቡድን ነበርን። ጨዋታዉ ተጀምሮ ሊያልቅ አከባቢ ሁለታችንም አንድ አንድ "Goal" አግብትን ነበር። የመጨረሻዉ ፊሽካ ከመነፋቱም በፊት ጓደኛዬ በራሱ ወደ ግብነት ሊቀይረው የሚችለው ንፁህ አጋጣሚ አገኘ ፣ እሱ ግን ሁሉንም ካለፈ ቡሃላ ለራሱ ማግባት ትቶ ኳሱን ለኔ አቃበለኝ። እሱ ቢያገባዉ ይመረጡት ነበር እሱ ግን ራሱን ትቶ እኔን አስመረጠ። ከጨዋታዉ ቡኃላ ለምን እንዲ አደረክ ብዬ ስጠይቀዉ "አንተ ከኔ የተሻልክ ስለሆንክ ይገባሃል" አለኝ። በሂወቴ ትልቁ ባለዉለታዬ እሱ ነዉ።"
ጋዜጠኞቹ ይሄን ነገር ለማረጋገጥ የጓደኛዉ ቤት ይሄዱና ጓደኛውን ስለዚህ ጉዳይ ይጠይቁታል።

ጓደኛዉም: "እዉነት ነዉ ብጊዜዉ እሱ ከኔ የተሻለ ተጫዋች ነዉ። ያኔ እኔ ጎሉን
አስቆጥሬ ተመርጬ ቢሆን የሱን ያህል ስኬታማ አልሆንም ነበር።" ጋዜጠኞቹ: "እና አሁን ኳስ ተጫዋች ነህ?? ወይ ምንድነዉ የምትሰራው?" ሲሉ ይጠይቁታል

ጓደኛዉ: "ኳስ ተጫዋች አይደለሁም።" ምንም ስራ የለኝም" ሲል ይመልሳል።
ጋዜጤኛ: "ታዲያ እንዲ የሚያምር ቪላ ቤት እና ድልቅቅ ያለ ሂወት ከየት ነዉ??"

ጓደኛዉ: "ያኔ ዉለታ የዋልኩለት ጓደኛዬ ነው እንዲ አንቀባሮ የሚያኖረኝ።" ታዲያ ይሄ የአለማችን ፈርጥ፣ ምርጥ ስብዕናው ጥንካሬ በመላበስ የበርካታ
ሪከርዶች ባለቤት፤የእግር ኳስ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው፣ በየሄደበት ክለብ በስኬት ማማ ነጋሹ።
ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጀምሮ በማን.ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድና በበርካታ የሊግ ዋንጫዎችና በሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሸብርቆ በሁለቱም ክለቦች የበዙ ጎሎችን አስቆጥሮ በተለይ በማድሪድ ቤት የክለቡ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ አሁንም በጁቬ ምርጥ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። ዛሬ ልደቱ ነው መልካም ልደት!

@wegoch
@wegoch
@paappii
ቢል ጌትስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም በነበረበት ወቅት ካንተ የሚበልጥ ሀብታም አለ ወይ? ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ የሚል አስገራሚ ምላሹን ሰጥቶ ነበር
<<ከብዙ ዓመታት በፊት ኒውዮርክ ኤርፖርት ውስጥ ጋዜጣዎችን ሳይ አንዱ
ጋዜጣ ላይ የተፃፈውን ርዕስ ወደድኩትና ጋዜጣውን ልገዛው ፈለኩ ነገር ግን
ምንም ገንዘብ አልነበረኝምና ጋዜጣውን አስቀምጬው ስሄድ የተመለከተኝ አንድ
ጋዜጣ ሻጭ ጥቁር ልጅ ጠራኝና 'ይህ ጋዜጣ ያንተ ነው ውሰደው' አለኝ። ምንም ገንዘብ የለኝም ልገዛክ አልችልም ስለው ምንም ችግር የለውም ውሰደው ብሎ ጋዜጣውን ሰጠኝ ከሦስት ወር በኋላ እዛው ኤርፖርት ሄድኩና ከዛ ጋዜጣ ሻጭ ልጅ ጋር ተገናኘን በአጋጣሚ አሁንም ጋዜጣ ልገዛ ፈልጌ ገንዘብ አልነበረኝም አሁንም ልጁ ጋዜጣውን በነፃ ሰጠኝ አሁንስ ደግሜ ልቀበልክ አልችልም ብለው አትጨነቅ ውሰደው ሰጥቼሃለሁ ብሎ ጋዜጣውን በነፃ ለሁለተኛ ጊዜ ሰጠኝ። ከ19 ዓመት በኋላ ሀብታም እንዲሁም ታዋቂ ሰው ሆንኩ በዚህን ጊዜ ልጁን አግኝቼ ብድሩን ልመልስለት ማፈላለግ ጀመርኩ ከአንድ ወር ፍለጋ በኋላ አገኘሁት ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ ብዬ ጠየኩት እሱም <<አዎ ዝነኛው ሀብታም ቢልጌትስ ነህ>>አለኝ። እኔም ከብዙ ዓመታት በፊት ሁለት ጋዜጦችን በነፃ ሰጥተኸኛል እናም ብድርህን ልመልስልህ እፈልጋለሁ ስለዚህ የምትፈልገውን ሁሉ ንገረኝና ላድርግልህ አልኩት እሱም <<ምንም ነገር ብታደርግልኝ ብድሬን መመለስ አትችልም>> አለኝ። እኔም በጣም ተገርሜ ለምን አልኩት እሱም <<እኔ የሰጠሁህ ደሀ እያለሁ ካለኝ ላይ ቀንሼ ነው አንተ ግን የምትሰጠኝ ሀብታም ሆነክ ከተረፈክ ላይ ነው ስለዚህ ብድሬን ልትመልስ አትችልም>> አለኝ። እኔም በእርግጠኝነት ያ ልጅ ከእኔ የበለጠ ሀብታም መሆኑን ተረዳው።

@wegoch
@wegoch
@paappii

From Daniel bekele page
ወንድ አያቴና ቅዳሜ

በልጅነቴ የተወሰኑ አመታትን በአያቶቼ ቤት እኖር ነበር።ከእነርሱ ቤት ከነበረኝ እድገቴ ይልቅ የወንድ አያቴ(አባባ፣አባዬ) እውነት መሳይ አፈታሪኮች ናቸው ይበልጡን ትዝ የሚሉኝ።የሚገርመው እስከአሁን ካስቆጠርኩት እድሜዬ እኩል አንዳንድ እኩያ እምነቶቼ በአያቴ ተረቶች የተገሩ እና የተፀነሱ መሆናቸው ነው።

የአባዬ ጨዋታዋች እና ሰው ነቃብኝ የሚል ሀፍረት የማያውቁት መሰረተ ውሸት ተረቶች ለጨቀላ አይምሮዬ የተስማማው ይመስል ከሴት አያቴ (እታቴ)ይልቅ ከእርሱ እግር ስር አልጠፋም ነበር።ለነገሩ ከእጁ መፅሀፍ ወይም ጋዜጣ ስለማይጠፋ የፈለገውን አልተገናኝቶም እውነት መሳይ ታሪኮች ቢሰነዝር ሁሉም ያምነዋል፣ተማሩ የተባሉትም።አንዳንዴ የውሸት ተረቶቹን ምንጭ እራሱን ማድረግ ሲሰለቸው "ፀሀፊው እንትና" "ፈላስፋው እንትና" እንዳለው ብሎ ያላሉትን ማላከክ ይቀናዋል።ግን ከሁሉም የሚገርመኝ እራሱ በፈጠራቸው እነኚ አፈታሪኮች አብሮን እንደአዲስ እንደሰማ ሰው ከት ብሎ የሚስቀው ልማዱ ነው።እነዚህ ከዘመነ "ማስተዋል" ተብዬው በኋላ ያሉኝ ግመገማ መሳይ ትውስታዎች ናቸው።እየተወላገድኩ በምሄድበት በዛ ጨቅላነት ግን ቁጥር አንድ አጨብጫቢው እንደነበርኩ እታቴ አጫውታኛለች።ሌሎቹን ባህሪያቶቼን ስትነግረኝ "በጣም ጠያቂ ነበርሽ" ትላለች ፤ "እናም መልሶች እንዲሰጥሽ ለሁሉም ጥያቄዎችሽ አባትሽን(አያትሽን ማለቷ ነው) እናጋልጠው ነበር ከዛም በእናንተ ንትርክ እንዝናና ነበር"ብላኛለች።


ከአባዬ ጋር ከምገጥመው ንትርክ የማይረሱ ትውስታዎቼም ቅዳሜ ዋነኛው ነው።

ቅዳሜ የተወለድኩበት ቀን ነው።ይህን በጨቅላነቴ ከእናቴ አፍ ስለሰማውት አውቀው ነበር።
አንድ ቀን እንደተለመደው አያቴ አባባ መፅሀፉን አንጠልጥሎ፣በጋቢው ተጠቅልሎ ከማለዳ ፀሀይ እየኮመከመ እኔም ስለቅዳሜ ያለኝን ጥያቄ ላቀርብለት በትንሽዬ አይምሮዬ ስሰናዳ ተገጣጠምን። "እሺ ቡጡዬ(አሁንም በዚህ ኮረዳነቴ ቡጡ እያለ ነው የሚጠራኝ)ተነሳሽ" አለኝ።ትንንሽ አይኖቼን በትንንሽ እጆቼ እያሻሸው "አው አባባ"አልኩና ተንደርድሬ ከእግሩ ስር ያረፍኩበትን ሳላስተውል ዝፍዝፍ አልኩ(እቴት እንደነገረችኝ)።
ያደረ ጥያቄዬን በልጅነት አይምሮዬ አለመርሳቴ አሁን ላይ ሳስበው የቅዳሜ ሚስጥርን ማወቅ እንደነበረብኝ ከላይ የተፃፈልኝ ይመስለኝና ፈገግ እላለው።
ከዛማ ሽቅብ እያየውት "አባባ …አባ አባ… እ… እ… ማሚ(ማሚ አትበይ እማ ነው የሚባለው ንትርኩ ዛሬ ትዝ አላለውም) ለምንድነው ከቀኖች ኡሉ መርጣ ቅዳሜ የወለደችኝ? እኔኮ አሙስ ነበር የምፈልገው" አልኩት።ሳቅ አለ።ሳቁ ኤጭ ይኚ ጥያቄዎችሽ የሚል ሀሳቡን እንዲደብቅለት ይመስላል(እቴት እንደነገረችኝ)።
ነገር ግን እሱ አባባ ነው መልስ አያጣም ፤ቢያጣ ቢያጣ እንኳ ያላስፈቀደበትን ሀሳብ ብድር ይገባል (ከመፅሀፎቹ)።ጥያቄዬ ቢያሰለቸውም አላውቅም አይልምና ወሬውን ለማሳመር አቀማመጡን አስተካከለ።
እኔም "ቀድሞ የሚሰጠኝን ርህራሄ ከመንጠቁ በፊት" የሚል ሀሳብ የመጣልኝ ይመስል አይኖቼን ሽቅብ 'መልስልኛ አላሳዝንም' በሚመስል አፈጠጥኩበት።አያቴ ተመቻችቶ እነዛን ተረቶቹን አዋቅሮ ሲጨርስ ቀጠለ።
"ቡጡ ይኧውልሽ 'ቅዳሜ' ማለት 'ቅድመሰንበት' ነው።ሰንበት ደግሞ የእረፍት ቀን ነው፤ስለዚህ ባንቺ ቀድመን ልባችንን ልናሳርፍ ፈለግንና ለእናትሽ ነገርናት"አለኝ።ለትንሽዬዋ እኔ መልሱ ተልቆብኝ ይሆን እንጃ ሌላ ጥያቄ ፈጠረብኝ። "እእ አባባ ሰንበት ምንድን ነው?"

በውስጡ አዪዪዪ ያለ ይመስል ትንሽ አሰብ አደረገና ከሰጠኝ ትርጉም ውስጥ ሰንበትን ለማስወገድ ወሰነ።

ብዙ ጊዜ ሳስቸግረው ከጥፋቴ ሊሰበስበኝ ሲያስብ አንድ አፈታሪክ ጣል ያረግብኛል።እንደውም ትዝ የሚለኝ ለእንግዳ የቀረበ ብርትኳን እየበላው ሳስቸግር የዋጥኳቸውን የብርትኳኑን ፍሬ በግምት ቆጠረልኝና "ሆድሽ ውስጥ ይበቅላሉ" ካለኝ ጀምሮ ብርትኳን አጠገብ ድራሼም አይገኝም ነበር።ያህንን በሚመስል ታሪክ ስለቅዳሜም እንዲ አለኝ።…


ቆፍጠን ባለ ድምፅ" ይገርምሻል ቡጡዬ የቤተሰባችን አንድም አባል በምንም ነገር ተቀድመን ተበልጠን አናውቅም።ሁሌም ቀዳሚ እንደነበርን ነው።እናም ይህን እኛ አያቶችሽ ለእናትሽ እንዳወረስናት ትልቅ መለያ እንዲሆን አስባ ቅዳሜ ወለደችሽ።ቅዳሜ ማለት 'ቀዳሚ ' 'ቅደሚ 'እንደማለት ነው። በነገራችን ላይ የሳምንቱም የመጀመሪያ ቀን ነው አንዳንድ ምሁራን ይላሉ" ብሎ ብቻውን ላለመጠቆር እነሱ ላይ በትንሹ አሳቦ ጠቆመ።
አይ አባባ! የሚገርመው አሳመነኝ ቀጣይ ጥያቄ ሳልጠይቅ ተቀበልኩት።
ከማመንም አልፌ እውነታ እየመሰለኝ በነገሮቼ ቀዳሚ ለመሆን ይበልጡን እተጋ ጀመርኩ።በዛው ለምዶብኝ በእድገቴም ስገፋ መትጋትን መለያ አረኩት።አይ አባዬ! ይን አስቦ ተረቱን ባይነግረኝ እንኳ
በእድሜ እየላቅሁ ስመጣ በሰባቱም ቀናት ውስጥ ትርጉም የምሰጠው እኔው እራሴ እንደሆንኩ ሳስብ የሁሉም ቀናት ተመሳሳይነት ይጎላብኛል፤ ግን አባባ እና እነዛ ተረቶቹ ባለውለታዬ ሆነዋል።በጨቅላ አይምሮዬ ላይ የፃፈው አያቴም የራሱን ታሪኮች ሲከተል ስላየው በቅዳሜ መቅደምን ካስተማረኝ ይበልጥ 'መከተልን' ስላወኩበት ከአሁኑ ማስተዋሌ የልጅነቴን ንፁህ እምነት እናፍቀዋለው።

መልካም ቅዳሜ💜
ቅዳሚት💜

@getem
@getem
@paappii

#heavቨን
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የቀጠለ #3 )

"ልጅ ልሰጥሽ ስለማልችል ትተይኛለሽ?" አለኝ

"ስንጋባም መውለድ እንደማትችል ታውቅ ነበር?"

"አዎ "

"ለምን አልነገርከኝም?"

"እንዳላጣሽ ፈርቼ። ብነግርሽ ኖሮ ታገቢኝ ነበር?"

"ምርጫ አልሰጠኸኝምኮ! ከልጄና ከፍቅርህ እንድመርጥ ምርጫ አልሰጠኸኝም! ራስህን ራስህ መረጥክልኝ!! "

"እኔ ብሆን ልጅ አልሰጠሽኝም ብዬ አልተውሽም! ይሄን የሚሻገር ፍቅር አለኝ። "
(ከዚህ በላይ የሚሆን ፍቅር ከሌለሽ ተይኝ የሚል መልእክት ነው ያለው።)

የዛን ቀን ባሌ የሆነ መገኘቱ ከልቤ ላይ ግምስ ሲል ታወቀኝ። ግን ምንም አላልኩም። እንዴት እንደሆነም ለራሴ መግለፅ ይከብደኛል። በቃ ግምስ ብሎ ተናደብኝ። ፈልጌው ነው? የሆነ ሴትነቴን አታሎ የቀማኝ መሰለኝ። ግን ዝም አልኩ።

በሆነ መንገድ ራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበታል!! ቆይ መውለድ ትችላለህ ወይስ አትችልም? ተብሎ ይጠየቅ ነበር? እንደማይችል ሲያውቅ ሊያሳውቀኝ ይገባ የነበረው እርሱ አልነበር? ግን በቃ ይችልበታል። ማጣራት ነበረብኝ ብዬ ራሴን ወቀስኩ። ዝም አልኩ።

'እናት ልታደርገኝ ስለማትችል በቃኸኝ!'ይባላል? አይባልም! መሃን ስለሆነ ፈታችው ሲባል ጆሮ ላይ ጭው ይላል አይደል? ዝም አልኩ!

ለአመታት ዝም አልኩ። ስራ ይሸኘኛል። ከስራ ይመልሰኛል። ቁርስ ያበስልልኛል። ምሳ አበስላለሁ። እራት ያበስላል። እሱ ምንም ዝንፍ ያለ ነገር የለውም። ደከመኝ ያልኩ ቀን እግሬን አጥቦ አሽቶ ያስተኛኛል። ሲለው እንደሰርግ ቀኔ ተሸክሞ ወደአልጋ ይወስደኛል። ሞከርኩ። የተጋባን ሰሞን ይሰማኝ እንደነበረው ሲነካኝ ደስ የሚለኝን ፣ ሲስመኝ አልጋው የሚያምረኝን እሳት ላመጣው ታገልኩ። አቃተኝ!

ምንም ሳያወራ እራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበት የለ? እሱ እንዲህ ጥሩ እየሆነልኝ እኔ ለምን እንደሱ መሆን አቃተኝ እያልኩ ራሴን ረገምኩ። ፍቅሬ ስላለቀ ራሴን ወቀስኩ::

ፍቅር መስራት ፍቅር መስራት መሆኑ ቀርቶ ስራ መስራት ሆነብኝ። በአፌ እንቢ እንዳልለው የምሰራው ስራ አለኝ በሚል ሰበብ እሱ እንቅልፍ እስኪወስደው እየጠበቅኩ መተኛት ሆነ ልምዴ። ማምለጥ ያቃተኝ ቀን እሱ ላቡ ጠብ እስኪል ሲለፋ እንባዬን እንዳያይ እታገላለሁ። (አንዳንዴ የኔ ባል ብቻ ነው የገነት በር ይመስል የማህፀን በር ላይ እንዲህ የሚተጋው? የሚል ሀሳብ ይመጣልኛል። ተፈጥሮ እንኳን እንዴት አይነግረውም? ደርቆ እያታገለው በምራቁ እያራሰ የሚጋጋጠው የዘለዓለም ህይወት ሊያተርፍበት ነው ወይስ የስጋ ደስታ?)

እንደደነዘዝኩ ብዙ ዓመት ዓመትን ደረበ።
በትዳር ብዙ የቆየች አብራኝ የምትስራ ሴትን "እሱ ነገር እንዴት እየሄደልሽ ነው?" ብሎ መጠየቅ ያምረኝና ስንቴ ከአፌ እመልሰዋለሁ።

ከብዙ እንዲህ ያለ ቀናት በኋላ አለቃዬ ሊያማልለኝ ጀመረ። የሆነ እለት እጄን ሲነካኝ ባሌ ድሮ ሲነካኝ የሚሰማኝ እሳት ተሰማኝ። ባልሰማ አለፍኩት። ግን ሰምቼዋለሁ! ወላ ፈገግ ብያለሁ ለራሴ 'ለካ የሆነ ነገር ጎድሎኝ አይደለም።' አልኩ:: ጭራሽ ይሄ ነገር ከመሽኛነት ውጪ ለራሴ ጥቅም ላላውለው ነው ብዬ ተስፋ ቆርጬ ነበራ!! ባለግኩ!

ከቅሌቴ በኋላም እሱ ዝንፍ ያለ ነገር የለውም። ሳይናገር ራሴን እንድወቅስ ማድረግ ይችልበት የለ? ዝምታው "አየሽ ብትሄጂብኝም ስለማፈቅርሽ እንዳጣሽ አልፈልግም" የሚል መልእክት አለው።

ዛሬ ልፋቱ ይቅርብኝ ያልኩ ቀን ያለ ምንም ቃል "ምነው ለኔ ሲሆን ነው? ለማንም ጠረጴዛ ላይ አንጋለሽው አልነበር?" የሚል መልእክት ያስተላልፍልኛል። እንዴት ነው ግን ሳያወራ መልእክቱ የሚደርሰኝ? እናቴ ቤት ሄድኩ።

የሆነውን እና የሚሰማኝን ሁሉ ለእናቴ ነገርኳት። ከሁሉም አብልጣ የሰማችኝ ከአለቃዬ ጋር መባለጌን ነው። ዘገነንኳት።

"ይሄን ጉድሽን ለራስሽ እንኳን ደግመሽ እንዳትናገሪ! በይ ሂጂና ይቅርታ ጠይቂው! እንዴት ያለው እግዚአብሄር የባረከው ነው? ከነዚህ በደልሽ ልቀበልሽ ማለቱ? ደሞ ካንቺም ብሶ ቤትሽን ለቀሽ ትወጫለሽ?" አለችኝ። እሱ ይቅርታ እስክጠይቀው አልጠበቀም። እናቴ ቤት ድረስ መጣ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስሞኝ ይዞኝ ተመለሰ።

ስንኖር .....ስንኖር ብዙ ስንኖር ነው የስልኩን መልእክት ያገኘሁት።

የሆነ ስርየት የሆነልኝ የመሰለኝ። እነሆ ሀጥያቴ በሀጥያቱ ታጠበ ......

የሚገርመው አልጨረስንም ...

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ሄድ፣ ሄድ፣ ሄድ መለስ. . . ደሞ ጎርደድ መለስ ድሮ ክፍል ውስጥ አስተማሪ ጥያቄ ጠይቆ የሚመልስ ተማሪ በሚፈልግበት ቅፅበት የሚሰማኝ ስሜት ነበር። የራስ ጋር ክርክር "መልሱ ይሄ ነው፣ መልሺ። እርግጠኛ ነሽ መልሱ እንደዚህ ነው ግን? እኔንጃ፣ መሰለኝ። ማንም እጁን አላወጣም፣ እጅሽን አውጪ። አውጥተሽ ስህተት ከምትሆኚ ባታወጪሽ? ምን ታጫለሽ? ግን መልሱን ካወቅሽውሽ? ግን ለምን በፍቃድሽ ራስሽን በሌሎች ለመዳኘት ታጋልጫለሽ? አለመታየት ማንን ገደለ? . . . " በራስ አለመተማመን እና የስህተት ፍራቻ ተዳቅለው (ማን እንዳዳቀላቸው እንጃ lol) በፈጠሩት ጥርጣሬ የማውቀውን ነገር ሳልመልስ እቀራለሁ። ምናልባትም የእድሜ ጉዳይ የሚቀይረው ነገር ይሆናል ብዬ አምን ነበር። እውቀቴ እየሰፋ ሲመጣ በራስ መተማመኔም ይጨምራል አይነት ነገር።

* * *
post ከዛ delete ወዲያውኑ "አስቂኝ ነገር አይደል ለምን አጠፋሽው? there is so much going on, የመቀለጃ ጊዜ ነው አሁን? ደሞ you were being insensitive ለእነዚህ ሰዎች። እርግጠኛ ነኝ ላንቼ ብቻ ነው የታየሽ offen-ሱ። በዛ ላይ ደግሞ you are sharing too much፣ ስላንቺ ህይወት ማን ይሄን ያክል interest ይኖረዋል? ሰፋ አድርገን ደግሞ እንየው። ለምንድነው ሶሻል ሚዲያ ላይ ያለሽው? ምንድነው purpose-ሽ? what are you trying to accomplish? what are you getting? how does this post tie in with that purpose? ሁሉም ነገር በምክንያትና በpurpose ነው ያለው ግን ማነው? I am so annoying! ይኸው፣ አጠፋሁት! case closed"
* * *
send a message፣ unsend
"እንዴ መለሰ አልመለሰ እያልኩኝ ለምን እጨናነቃለሁ? ባልልከውስ ኖሮ? ግን
you wanted to share that with him . . . "

* * *
ትልቅ እሆናለሁ፣ አለምን ለውጣለሁ. . . ግን ባትለውጪሽ? "what makes you so special ቆይ? እስቲ ተይኝኝኝ . . . "
* * *
የሚያደናብሩ ድንበሮች፣ እየተገነባ ያለ ማንነት፣ የስህተት ፍርሀት . . . ሄድ ከዛ
መለስ . . .አንድ ቀን ደፍሬ እሄድ ብቻ ይሆናል። ይሄም ይጠፋ ይሆናል lol

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Hewan Hulet Shi
የሁለት ሰዓቱ ጦርነት!
((Maggie)) #1


እኛ ቤት ዘወትር ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሰላምና ፀጥታንን ማግኘት ማለት በድቅድቅ ጨለማ ያለባትሪ(ኧረ በባትሪም ይሁን!) መርፌ እንደመፈለግ ነው.

ብርሀን ከሚጓዝበት ፍጥነት ቀድመው ወሬ ሚያራግቡ የሀገራችን ሚዲዎችን ጨምሮ እነቢቢሲ እነአልጀዝራ....አላዩትም እንጂ ...እስከዛሬ ከዘገቡት የጦርነት ዘገባ ዎች ይልቅ በእጥፍ ገበያን(ተመልካች) ሚያመጣለቸው ትኩስ ወሬ የመሆን አቅም ያለው ጦርነት ነበር!

ይህንን ያወኩት..... ባለፈው ትንሹ ወንድሜ የአማርኛ መምህራቸው 'ዜና የሚሆን ዘገባ አዘጋጅታቹ ኑ' የሚል የቤት ስራ ሰጥታቸው .......... አቡሻዬም (የ4ኛ ክፍሉ እንቦቅቅላ) ...... ይህንን የሁለት ሰዓቱን የኛን ቤት ጉድ ዘግቦ ሄዶ ..በኮልታፋ ምላሱ አንብቦ (እዚጋ... እኔ አልነርኩም ሲያነብብ! ገምቼ ነው!) "መክዲዬ አማሊኛ አሽልካሽል አመጣውኮ!" እያለ ምላሱን በወለቀው የፊት ጥርሱ እያሾለከ የነገረኝ ግዜ ነበር!

ኧረ እንደውም የሆነ ግዜ ጦረነቱ ከኛ ቤት (ከግንባሩ!) በወሬ ደረጃ ሾልኮ ወጥቶ (በጎረቤታችን ምሬት የወለደው ወሬ አማካኝነት...... አቡሻዬም ሊሆን ይችላል!) ለሰፈሩ ያንድ ሰሞን የቡና ማድመቂያ ሆኖ ነበር!

ፀሀይ ስታሸልብ የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ወደቤት የሚከትትበት ግዜ ነው። ከየስራው ከየትምህርትቤቱ ከየቡዘናው ብቻ ከየትም ይሁን በጦርነት ግዜ "ክተት!" እንደተባለ ጦረኛ ይከትታል....

እስከ 1:59 ደቂቃ ድረስ... የጋብቻ አማካሪዎች ፣የስነልቦና ባለሞያዎች ፣የፍቅር ክሊኒክ መካሪዎች.....እንዲፈጠር የሚለፉለትን አይነት ቤተሰብ ሆነን እናሳልፋለን... እራት ይቀርባል... ቡና ይፈላል... ሽር ጉዱ.... የ"ውሎ እንዴት ነበር" ጥያቄው.... ቀልድና ጨዋታው.... ጉሸማው.... ያቡሻዬ የትምህርት ቤት ውሎ ትረካው.... የ"እዚጋ እንጀራ ይጨመር ...ወጥ አንሷል....ሚጥሚጣ አቀብዪኝ" ትዕዛዙ ................ ብቻ ምን አለፋቹ በየቲቪው ላይ የምናየውን አርአያ (ሞዴል!) ቤተሰብ እንሆናለን

ችግሩ ሚመጣው 2:00 ሰዓት ሲሆን ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Maggi
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Meba)
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_2_ቁጥር_7_edited85.pdf
4.9 MB
#ቅንድልዲጂታልመጽሄት
ቅጽ-2 ቁጥር-7 ተለቀቀ
ያንብቡና ብዙ ያትርፉት
ቅንነት ድል ያደርጋል!
Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

Kendel on youtube
http://www.youtube.com/channel/UCMvSL9y2zS3KGmUfXEgSM_w
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ (የቀጠለ #4)

ባሌን እንዲህ እፍፍፍ ያስደረገችውን ሴት ለማየት "የተለመደ" ቦታቸው ባሌን ተከተልኩት። ከስራ እኔን እቤት ካደረሰ በኋላ ነው የወጣው። የጀበኛ ቡና የሚሸጥበት ቤት? ይሄ ነው የተለመደ ቦታቸው? መኪናውን አቁሞ ወረደ። ታክሲውን አስቁሜ በዓይኔ ተከተልኩት።

ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣች ከነበረች ሴት ጋር በፈገግታ ተጠባበቁ። የሚሉት አይሰማኝም። ተንጠለጠለችበት። ወገቧን ይዞ ወደላይ ተሸከማት። አነሳት አይደል? አዎ በትክክል! እግሮቿን አንጨፍርራ ተንጠለጠለችበትኮ! ምን ዓይነቷ ቀለብላባ ናት? ለወትሮ እሱስ ቢሆን ቅልብልብ ሴት አይወድም አልነበር እንዴ?

ሁለት ቀን ነው ያልተገናኙት ምንድነው ባህር አቋርጠው ከርመው የሚመጡ የሚያስመስሉት? ወደመሬት ከመለሳት በኋላ ሳመችው። ከንፈሩን ሳመችው። እጅ ለእጅ ተቋልፈው ትንሿ የጀበና ቡና መሸጫ ቤት ውስጥ ገቡ።

ይሄ ሁሉ አልጎረበጠኝም። ባሌ ማመንዘሩን ማረጋገጤ ደስ ብሎኛልኮ! ደስታዬን ምን ሸረፈው ታድያ? ቆንጆ ናት! የባሌ ወሽማ ቆንጆ ናት! የባሌ ወሽማ ባትሆን ኖሮ መንገድ ባገኛት "ስታምሪኮ!" የምላት ዓይነት ቆንጆ ናት

የባል ወሽማ ቆንጆ ስትሆን ደስ የማይል ስሜት አለው። 😜

"እዚህ ነው የምትወርጂው? ምንድነው?" ሲለኝ ባለታክሲው እንደመባነን አደረገኝ። የእናቴን ቤት አድራሻ ሰጠሁት።

"እማ ባሌ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት አለው!" አልኳት አባዬ እስኪወጣ የባጥ የቆጡን ስቀባጥር ቆይቼ

"እርግጠኛ ነሽ?"

"አዎን "

"በይ ስሚኝ ልጄ ሴት ልጅ የተለየች የሚያደርጋት ብልሃትዋ ነው። ባልሽን ልቡ ወደቤቱ የሚመለስበትን ጥበብ ዘይጂ .." አላስጨረስኳትም!

"እህህ እማ ....አጥፍቼም የኔ ሃላፊነት ነው! አጥፍቶም የኔ ሀላፊነት ነው? ምንም አልገባኝም! የቱ ነው የሚያሳስብሽ? የኔ ያለባል መቅረት ነው የሚያሳስብሽ ወይስ የኔ ደስተኛ መሆን? እኔ ስለሚሰማኝ ስሜት አንድም ቀን ግድ ሰጥቶሽ አያውቅም። ግድ የሚሰጥሽ ትዳር ውስጥ መቆየቴ ብቻ ነው!! እየኖርሽ ካልሆነ በትዳር መኖር ትርጉሙ ምንድነው? "

"አይ ልጄ እኔና አባትሽ 40 ዓመት በትዳር ስንቆይ ለመለያየት ምክንያት የሚሆን ፈተና ስላልገጠመን ይመስልሻል? በብልሃትና በትዕግስት አልፈነው ነው"

"እማ እስኪ ዛሬ እንኳን በጭንቅላትሽ ሳይሆን በልብሽ ስሚኝ? ደስተኛ አይደለሁም እኮ ነው የምልሽ! ሌላ ሴት ጋር ሲሄድ የመገላገል ስሜት ነው የተሰማኝ! የኔ ደስተኛ መሆን አያሳስብሽም? "

ዝም አለች! ደነገጠች። ለወትሮው የምትለው የማታጣው እናቴ ዝም አለች።

"እሺ ትዳርሽን አስመልክቶ እንዲህ አድርጊ እንዲህ አታድርጊ አልልሽም። አንድ ልጄ ነሽ! ከምንም በላይ ደስታሽ ያሳስበኛል። ደስታ ግን አንቺ እንደምትዪው ባል ወይም ሌላ ሰው የሚሰጥሽ ነገር አይደለም። ደስታን ውስጥሽ ፈልጊው። የቱጋ እንዳጣሽው አስቢና። ፍለጋሽን ከዛ ጀምሪ!" አለችኝ በመጨረሻ! አልገባኝም! ወይም እንዲገባኝ አልፈለግኩም።

"ተይው በቃ ሲጀመርም ላንቺ መንገር አልነበረብኝም!" ብያት ወደቤቴ ተመለስኩ። ስደርስ ባሌ እቤት ነበረ። እኚህ ደግሞ እንደዛ ሲንጠላጠሉ ሁለት ቀን የሚበቃቸው አይመስሉምኮ ለሁለት ሰዓት ነው እንዲያ ሚመሳቀሉት?

"የት ሄደሽ ነው? የምትሄጂበት ቦታ እንዳለሽ ባውቅኮ አደርስሽ ነበር።" አለኝ

"እናቴጋ ሄጄ ነው" አልኩት ከንፈሬን ሊስመኝ ሲጠጋ ጉንጬን አቀብዬው

"ምነው ደህና አይደለሽም? "

"እናቴጋ ለመሄድ የሆነ ነገር መሆን አለብኝ? "

"ከዓመት በዓል ውጪ እናትሽጋ የምትሄጂው ሲከፋሽ ነው ብዬ ነው።" (ነግሬው አውቃለሁ? አላውቅም! እኔ ራሴ ያስተዋልኩት አሁን እሱ ሲለኝ ነው። በምን አወቀ?) ዝም አልኩ። ምንም እንዳልተፈጠረ እራት ያሰናዳልኝ ገባ! የእውነቱን ነው? እንዴት ነው እየበደለም እየተበደለም ያው ራሱ ሰውዬ መሆን የሚችልበት? ነውስ እሱም እንደእኔ እኩል ለኩል ነን ብሎ ነው የሚያስበው?

"እኔ በልቻለሁ" አልኩት። .....ብቻውን በላ

"ደክሞኛል ዛሬ!" ብዬ የጀመርነውን ተከታታይ ፊልም ሳላይ ወደመኝታ ቤት ገባሁ። እኔ ካላየሁ እንደማይቀጥለው አውቃለሁ። ተከትሎኝ ወደአልጋ መጣ። ጀርባዬን ሰጥቼው ትንፋሼን ሰብስቤ አንሶላውን ገልጦ ሲገባ ሰማዋለሁ። ከጀርባዬ አቀፈኝ። አንገቴ ስር በስሱ ሳመኝ። ሁሌም እንደሚያደርገው አንድ እግሩን ታፋዬ ላይ ጭኖ እጆቹን በጡቶቼ ዙሪያ አቆላልፎ አቅፎኝ ተኛ። 1 ደቂቃ .......2 ደቂቃ ......3 ......5 ......10 .....20 ... ተኝቷል።

ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ያልነካካኸኝ ይባላል?

.........አታፍጡብኝ አልጨረስንም......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
የሁለት ሰዓቱ ጦርነት!
((Maggie)) #2


ከ dining room ( ቡፍፍፍፍፍ! ሙድ ስይዝ ነው ባካቹ! ዳይኒንድ ሩም ምናምን የለም! ለምን እንደሆነ ኋላ ትደርሱበታላቹ) .....ለማንኛውም የቱ ጋ ነበርኩ?? ....አዎ..... በልተን ጠጥተን ወደ ቲቪ (እንደምን ዋልሽ አለም!) ልንል ስንሰበሰብ ይሄኔ ቅድም አንድ የነበረው ቤተሰብ ወደ ሁለት ጎራ ይከፋፈላል.

"ዜና ነው ምናየው!" እና "የለም! ቃና ነው ምናየው!" በሚል ሁለት ጎራ! ይሄኔ ነው ክትክቱ ሚጀምረው! ያንጋፋዎቹ ፓርቲ "ዜና" ሲል "የጎረምሳዎቹ ፓርቲ ደግሞ "ቃና" ይላል (እዚጋ አቡሻዬ ወደ አልጋው ስለሚሄድ እዛው ሆኖ ይታዘበናል. ልክ እኛ እንትናና እንትና ሲከታከቱ በራድዮ ሆነን እንደምንሰማው!)

"ሀገራችንን እየኖርባት ....ስላለችበት ሁኔታ የማወቅ መብትም ግዴታም አለብን!" ብለው ይከራከራሉ አንጋፋዎቹ( እናት አባት ና አያታችን(ያባታችን አባት))

"ኖ! እኛም አዕምሮዋችንን ማዝናኛ ቃናን ማየት አለብን! ሀገችን ሰላም ብትሆን አይደል እየኖርንባት ያለነው!" ጎራምሶቹ! (እኔ ታናሽ እህቴ መስኪ እና "3 አመት ትበልጣታለህ እንጂኮ ያው እኩያ ናቹ!" እሚባልለት ታላቅ ወንድሜ ቃልአብ)
..
... ወይ ውሳኔ ይወሰንና አንድ ተጨማሪ ቲቪ ከነዲሹ ይገዛልን! (11ኛ ክፍሏ መስኪ)

"ይች! ቅሪንዳምስ! ደሞ እነዚየን እኛን ቲያቅታቸው ቋንቋችንን ወስደው ሚያጃጅሉንን ከፍተሽ ጥናት ወድያ ሰንብች ልትይ ነው!" (አያቴ ነበሩ)

"አቦ! እዛ ውጪ ላይ ስራ ከመፈለግ የተረፈንን ግዜ ዘና ምንልበት ደና መደበርያ የለ እዚ ደሞ...እናንተ ......" (ምርር ብሎ ቃልዬ ነበር)
ባለፈው አመት ለመአረግ አስር ጉዳይ በሆነ ውጤት ተመርቆ ስራ መቀጠር ያልቀናው ወንድሜ!

"ሆዳቹን ልቻል? መዝናኛቹን?? ኢትዮጵያ ውስጥኮ ነው ያላቹት እናንተ!! በቀን አንዴ በስንት ውጣውረድ ሚበላበት አገር! ወዲያ አምጣ ሪሞቱን!" እማዬ ነበረች

አንጋፋዎቹ ፓርቲ ...."ዜና ይታይ!" የሚለው አቋማቸው ያሸንፍና (በጉልበት).... ያኮረፍን መኝታቤታችን ስልካችንን ወይ ያችን ግቢ እያለ ይጠቀምባት የነበረችውን የቃልዬ ላፕቶፕ ይዘን እንገባለን .......እየጎረበጠን የተስማማን ደግሞ እዛው ሆነን ዜና እናያለን.
..............

......

አንድ ቀን ታድያ ይህ የዘወትር ጦርነት ማብቂያውን አገኘ!

"እንዴት" አትሉም????


ይህንን ንትርክ ለማርገብ አስቦ ይሁን እንቅልፉን እየነሳነው ተቸግሮ እንጃ! ቻናሉን ለመቀር አሳማኝ ነው ምንለውን መከራከርያ እያነሳን ስንከራከር አቡሻዬ ከመኝታቤቱ መጥቶ መሀል ላይ ቆመና

"ቆይ ለምን "ዤ"ን እና "ቃ"ን አውትታቱ ..."ናና" አድልጋቱ አንድ ላይ አታዩም!" አለን እየተኮላተፈ

በዚ ግዜ አባቴ አንድ ነገር እንደበራለት ሁሉ...... አቡሻ ይህንን በተናገረ በማግስቱ የቤተሰብ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Maggi
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul Mekonnen 📷)
Do you need to Hold on the memorable #pictures you love ? Get yours and your beloved pictures #painted on leather.

Order perfectly wooden framed #painted_pictures and present it for:
#Graduation
#Birthday
#Anniversary ...

Contact us @gebriel_19
Or give us a call 0984740577

@seiloch
@seiloch
2024/09/23 19:27:09
Back to Top
HTML Embed Code: