Telegram Web Link
#ወግ_ብቻ
.
"መጻሕፍ የሚነበበው የተለያየ የሰው ልጅ ሐሳብ ለማግኘት ሲባል ነው። ኒውተን ምን አለ? ፓይታጎረሰስ? እዩለርስ ምን አውጠነጠነ?…አደራጅቶ ከማሰብ ውጪ ዕውነት ለተመረጡ ሰዎች አትሰጥም። ከአንድ አንባቢ የሚጠበቀው የተቃረኑ ሐሳቦች የሚኖሩበት ሰፊ ልቦና ብቻ ነው።"
.
.
.
"ዕውነት ልክ ከአፈር እንደሚገኝ ወርቅ ከሰዎች ሐሳብና ከልምድ ዕራስህ የምታነጥረው ዕውነት ነው። ልብ ብለህ ከሆነ ኒውተንና ኢዩለር ይሄንኑ በአንድ መንገድ ገልፀውታል። ከተቀረው ሰው የተለየ አሻግሬ የማይበትን ቁመት ያገኘሁት ያለፉት ጠንካራ ሰዎች ትከሻ ላይ በመቀመጤ ነው ብለው ነበር። የራስህን ዕውነት የእነሱ ሐሳብ ትከሻ ላይ ሆነህ ለመመልከት መጣር…"



"የብርሐን ፈለጎች" በዓለማየሁ ገላጋይ (171/2)
@wegoch
@wegoch
አሁን እኔና አንቺ መደበር ነበረብን ዕድሜያችን ተደምሮ እንኳን አንዲት ሴት
Menopause ላይ የምትደርስበት ዕድሜ የለንም'ኮ። ምንድነው ሁላችን
የደከምነው? መች ኖርን ገና? አማኞች ልክ ይሆኑ የሚያስብል መንፈሳዊ
ካልሆነ ከምንም የጋራ የማይሆን ጫና አለብን። ያኔም ወጣት እንዲህ
ነበር? መጎርመስ ፈልጌ ነበር'ኮ፤ እንደ ማሙሽ ፀጉሬን ማሳደግ፤ እንደ
ፋሲካ ሙሉ ሱሪዬን ከጉልበቱ በታች ቀድጄ ግሊሲሪን ተለቅልቄ አቧራ
እየተጠነቀቅኩ መሄድ፤ ሳይሞቀኝ ደረቴን ከፍቼ ድድ ማስጫ መቀመጥ፤
በበራችን ላይ ያልፉ እንደነበሩ ሁለት ቀያይ ጥንዶች ደግሞ የወደድኳትን
ወገቧን አቅፌ ሰዉን ረስቼ ከንፈሯን እየሳምኩ መሄድ። ለማደግ እንዴት
ቸኩዬ እንደነበር'ኮ። ሲያዝኑ አናያቸውም ነበር ይሆን ወይንስ ጨርሶ
አያዝኑም ነበር? አሁን እኛን የሚያዩ ልጆችስ ሲያድጉ እንደኛ መሆን
ያምራቸው ይሆን? ልጆች ከዕድሜያቸው ፈጠን ብለው እንደትልቅ አክት
ሲያረጉ ልነግራቸው ልጮህባቸው ያምረኛል። "its a trap
motherfuckers enjoy ur fuckin ልጅነት" ልላቸው እፈልጋለሁ። ግን
ያኔ እንደዚ ሲሉኝ ሰምቼ ነበር? ቀደም ብዬ አቧራ ላይ መንደባለል
አላቆምኩም? ሚኒስተሪ ሳልፈተን ደስ ያለችኝ የመሰለችኝ ሴት
አልጠየቅኩም? ሴጋ ምን እንደሆነ ለማየት ትንሽ አልተጣደፍኩም? ዛሬ
የጓደኛዬ ታናሽ ወንድም እንዴት እየኖርኩ እንደሆን ገብቶት ነው "እኔ ከዚ
ሰፈር ልጆች ጋር መጃጃል ሰልችቶኛል እንዳንተ መሆን ነው የምፈልገው"
ያለኝ፤ ቦታ ቀይረኝ ልለው ያምረኛል፤ ነፍስ ስጠኝና እኔ ላይ ስታየው
ያማረህን ህይወት ኑረው። እኔ አንተን ሆኜ ትናንት የተሸወድኩትን
ላስተካክል ልለው ያሰኘኛል። ብዙ ኖሬ እመስላለሁ ይሄን ስል። ምንድን
ነው የሆንነው? በምንም የማንደሰት ሳቂታ ቆንጅዬ ትውልዶች የሆንነው?
"አንድ ጓደኛዬ ነበር ነፍሱን ይማርና" ማለት አልነበረብኝም'ኮ ስንት
እኩዮቼ ናቸው ጨክነው የሄዱት። ስንት የልጅነት ጀግኖቼ ናቸው ይሄን
ህይወት ጥለው የሮጡት? ከበላናቸው ልደቶች የሄድንባቸው ቀብሮች
ለምን በዙ? አሁን ባለሁበት ዕድሜ በነበሩ ጊዜ ቢደብራቸው ቢደብራቸው
ካርታ ተጫውተው ቀናቸውን ይሸውዱ ነበር'ኮ። ቀኖቻችን አልታለል ያሉን
ስለአዳዲስ ድብርቶቻችን እንኳን እንደ deja vu እየተሰማን ድብርትን ራሱ
ስንቴ ሰለቸነው? "ፈታ እንበል" ብለን ከጠጣን በሁዋላ የሚታዘበን
አለመኖሩን ስናውቅ የምናለቅሰው ለምንድን ነው? ምንድን ነው
የተፈጠረው?

©Tesfamariyam tafesse

@Wegoch
@Wegoch
@Mahletzerihun
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_፪_ቁጥር_፮_.pdf
6.1 MB
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

ቅፅ2- ቁጥር-6


በአውደብሩኀን ገፃችን ከ አርቲስት ዘሩባቤል ሞላ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

በርካታ አስገራሚ ፣ አስተማሪ እና አዝናኝ ፅሁፎች የተካተቱበ

ያንብቡት እና ብዙ ያትርፉበት📝

ቅንነት ድል ያደርጋል!

Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine
ራሺያ ውስጥ አንድ ሰነፍ ወታደር አለ፡፡ በቃ ኢላማውን ጠብቆ ተኩሶ መትቶ
አያውቅም፡፡ ሁሌ ይተኩሳል፤ ሁሌ ይስታል፡ ከእለታት አንድ ቀን አለቃው በጣም ተናደደና ሠራዊቱን ሰበሰበ፡፡
“ጓዶች፤ ይሄ ወታደር በተደጋጋሚ ኢላማውን ያልጠበቀ ተኩስ በመተኮስ
ይታወቃል፡፡ ወታደር አልሞ የጠላቱን ልብ በጥይት ካልነደለ ምኑን ወታደር ይባላል?” አለ የሰነፉን ወታደር ክንድ ይዞ፡፡ ተሰብሳቢው በሆታ “ኧረ አይባልም” አለ፡፡ “ይሄ ሰነፍ ስንፍናውን እንዳያጋባብን ሊቀጣ ይገባል፡፡ ቅጣቱንም ራሱ በራሱ ይወስዳል…” ይልና ራሱን እንዲያጠፋ ይወስናል፡፡
ሰነፉ ወታደርም ሰወር ካለ ስፍራ ይገባና ጥይት ይተኩሳል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ
ግን ሰነፉ ወታደር ይመለሳል - ወደ ካምፑ፡፡ አዛዡ ቱግ ብሎ “አንተ ራስህን አጥፋ ብዬህ አልነበረ?” ሲለው...
“ጌታዬ ራሴን ስቼው ነው!” አለ 😄

@wegoch
@wegoch
@paappii

@lencho_bedada
የሥዕል አውደርዕይ በ #አሊያንስ ኢትዮ- ፍራንሲስ
#ኃይሉ_ክፍሌ፡፡
አጋፋሪ፡ #ፍሬህይወት_ደምሴ፡፡
Art Exhibition @ alliance ethio-Francis
By Hailu Kifle
Curated by Frehiwot Demissie
.
.
@seiloch
@seiloch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል-6

ድንብሩ በጣዋቱም ቀጥሏል ሁሉም የምርምራ ክፍሉ ሀላፊዎች እጃቸውን አአፋቸው ሰቅለው ስለ ማታው ታሪክ ያወራሉ ከመገረማቸው በላይ አድናቆትም የሚገልፅ ንግግር ከአፋቻው ይሰማል ሶልያና ወደ ክፍሉ እስክትገባ ድረስ ወሬው እንደቀጠለ ነበረ ጥቁር ባርኔጣዋን እንዳወለቀች ቀጥታ ወደ ንግግሯ ገባች ከፊታችሁ ከቆምኩት እናተም ከፊቴ የተቀመጣችሁት በመጀመሪያ አንድ ነገር ማወቅ አለባችሁ ማንም በማንም ላይ እጅ የመቀሰር መብት የለውም ማታ ያደረግነው የሁላችንም እንቅስቃሴ ቢታይ ከሁላችንም ላይ ከእያንዳንዳችን ላይ ብዙ ጥፋት ሊገኝ እንደሚችል እወቁ በኛ ስህተት ብቻ ሳይሆን በዘራፊዎች የጭንቅላት ጨዋታ እንደተሸነፍን ማወቅ አለባችሁ አንድ መርማሪ የሚፈልገውን ወንጀለኛ ከፊቱ ሲያገኘው በፍጥነት ሮጦ እንደሚይዘው ሁሉ አንድ መርማሪ ከፊቱ ያለውን ዘራፊ በጭንቅላት ጨዋታ ጭምር መብለጥ ይኖርበታል አንዳንዴ እኮ መርማሪው ሳይለፋ መርማሪው ሽጉጥ ይዞ ሳይሯሯጥ በጭንቅላት ጨዋታ ብቻ አንድን ወንጀለኛ በራሱ ፍቃድ ወደ መርማሪው እንዲመጣ ማድረግ ይችላል ሀይል ሳይጠቀም ሚመጣን ዘራፊ በሀይል መያዝ አይቻልም ምክንያሁም ሀይል በነሱ ላይ እንደሚሰነዘር ስለሚያውቁ እነሱም ካለሀይል ሚመጡት መተው ሚመቱ አይነት ሰዎች አይደሉም እነሱ ለዛ እኮ ነው ደደብነታችንን ሚነግሩን
ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው እንደ ሰማይ ጸዳል ያበራሉ ዳን 12:13
ትናንት ጥለውልን የሄዱት ጥቅስ ነው በአንድ ትንሽ ዜማ እና ሀይል በማቋረጥ ይሄንን ሁሉ ሀይል ያታለሉት
ስራው ሚናቅ ቢመስላችሁም ማድረጉ ግን ከባድ ነው ጴጥሮስ እስካሁን ተበሳጭቷል አሁንም ግን ጆሮ ሰቶ ያዳምጣታል
ትልቁ እስክሪን በራ
ቀጣዩ ባለተራ ማነው ሁለት ቁጥሮች ወደ እስክሪኑ መጡ 6 እና 40 ቁጥር
ከትልቁ የስዕል አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ስድስቱ ጨረቆች የተሰኘው ስዕል ቀጣዩ አላማቸው ይሆናል
ጥለውልን በሚሄዱት ሳንቲም ውስጥ ጨረቃ የሚል ፅሁፍ እናገኛለን ሳንቲሙን በደንብ ስትመለከቱት 6 ጨረቆች ዙሪያውን ከበውታል ሁሉም አይኑ ከትልቁ እስክሪን ላይ ነው ይህ ስዕል ይሄን ይመስላል ስዕሉን ልብ ብላችሁ ስትመለከቱት ከምናየው ትልቅ የጨረቃ ምስል ሌላ ዙሪያውን 6ት ጨረቆች እናገኛለን ይህ ስዕል እድሜው ከ120 አመት በላይ ያስቆጠረ ነው አሁንም ግን ብርሀን ይሰጣል ስዕሉን በጨለማ ክፍል ብትመለከቱት በጣም የሚያበራ ሆኖ ታገኙታላችሁ ዛሬ ሀይል እንደማይቋረጥ አምናለሁ ንግግሯን ሁሉም የተረዱት ይመስላሉ ዛሬ እርምጃቸው ሁሉ በማስተዋል እንዲሆን ነግራቸዋለች ወደ ጳውሎስ ተራመደች የስዕሉ አዳራሽ የሲጋራ ጭስ አይቀበልም በጣም የሚረብሽ ድምፅ ልንሰማ ስለምንችል ሲጋራ ይዘህ እንዳገባ ከስዕሎቹ ነው ነየተነገረኝ ፈገግ ብላ አለፈችው ከነጋ እሱም ፈገግ አለ
የስዕል ማዕከሉ ዛሬ ስራ አይሰጥም ከስዕል ማዕከሉ ጀምሮ ዙሪውን በሙሉ ከተፈቀደላቸው ሰዎች በስተቀረ ማንም አይንቀሳቀስም በሁሉም ክፍሎችና ኮሪደሮች ጭምር ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉ ሰዎች ተመድበዋል ጳውሎስ ዛሬ ወደ ሚጠብቀው የስዕል ቦታ አመራ እውነትም ውብ ነው የስዕል አድናቂ ባይሆንም ተገዶም ቢሆን ስዕሉን አድንቋል ዛሬ ይሄንን ስዕል ከእጁ ማንም ሊወስድ እንደማይችል አምኗል

እንደተለመደው ከውሀው ጉርጓድ ዙሪያ ተሰብስበዋል ጨረቃዋ ነገ ትጠፋለች ዛሬ ግን ጨረቃ ብጠፋባትም ምትፅናናበትን ምትኳን ስለምታገኝ ተደስታለች ጨረቃዋን እያየች አንቺንም ቢሆን መስረቄ አይቀርም አለቻት ምቾት ተሰምቷታል ጥሩ እቅድ እንዳወጣች አውቃለች በእጇ የያዘችው ትልቅ ስዕል ላይ የጨረቃ ምስል ይታያል እቅዷ ተሳክቶ በውሸት አስላ የያዘችውን ስዕል ዛሬ በእውነተኛው ቀይራ የራሷ ታደርገዋለች መጽሀፍ ቅዱሷን ገለጠች
''በጠባቡ በር ግቡ''፤ ምክንያቱም ወደ ፊት የሚወስደው በር ትልቅ መንገዱም ሰፊ ነው በዚያ የሚሄዱት ብዙ ሰዎች ናቸው
ማቴ7:13
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
ድምፃቸው ያስገመግማል ሁሉም ከጉርጓዱ ውሀ በእጃቸው ጠጡ ፀሎቱ አልቋል እንደተለመደው ተርታቸውን ይዘው ደረጃውን ወረዱ

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
እስኪ ተውኝ ፍቅር ድሮ ቀረ። አሁንማ አይስክሬም ይመስል የትም መላላስ
ብቻ ሁኗል። ሙዚቃችንም ቅጥ አጥቷል። ሳም ላርግሽ፣ ሳሚኝ ነው። ይህ
ነው የጥበብ ምች፣ እርቃኗን አብዳ ስትሄድ። ጥበብ እኮ እንደ ሀገር ቤቷ
ሙሽራ የተሸፋፈነች፣ ገልጠው ሊያዩአት 'ሚፈሯት 'ሚሳሱላት ነበረች።
ድሮ ፍቅር የሚገለጠው በቤቱ እቃ በቡኑ በፍንጃሉ፣ በአዘመራው በከብቱ
ተወክሎ ነበር። ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ይሆነኝ ዘንድ የጥንት ሙዚቃ
ልጋብዛችሁ።
*
እሱ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የደገኛ
በስንዴ ለውጭኝ ካንችው ማኛ
አንች ደገኛ። (ማኛ እንግዲህ ያ ድንቡሼ ገላ መሆኑ ነው)
*
እሷ
የማነህ ብልጣ ብልጥ ቆዳህ ሞኝ መሳይ
ነጭ ጤፍ በስንዴ ልለውጥህ ነው ወይ?
ልትለውጥ ነው ወይ? (እዩትላችሁ ሴቶች'ኮ ፍትህ አያውቁም። አሁን
ምናለበት ሁለቱም የእግዜር ስራ ነው። ለምን ታወዳድረዋለች? ሲሰፈር
ሲለካ እኩል ነው!)
*
እሷ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የቆለኛ
ማኛ በጥሬ ምኔ ሞኛ
አንተ ደገኛ። (ይህም ያው ነው ሴቶች ብልጣብልጥ መሆናቸውን ማሳያ
ነው lol የለም ስቀልድ ነው ሲግደረደሩ ነው!)
*
እሱ
ስንዴ በነጭ ጤፍ መሳ ለመሳ ነው
መውቀጡ ካቃተሽ አለን የለመድነው። (ሃሃ እኛ እኮ ዘለን ወቀጣ ስንወድ
ማንም አይመስለን፣ አያክለን)
*
እሷ
ምነው መቸኮልህ ከወቀጣው ላይ
ቅድሚያ በገበያው ተስማምተናል ወይ? (ሂሂ 'ይችን ሙድ ለመሃሙድ'
አሉ። ፤ይሁን ፍቃድህ ፍቃዴ ነው' ማለቷ ነው። ቢጨከን ቢጨከን በወቀጣ
የሚጨከን ነውን?)
*
እሱ
ስንዴ ጤፍ ይበልጣል ማለቱን ትተሽ
እንዳ'ገር እንደወንዝ አምጭው ላምጣልሽ (ሃቅ ሸክሽኪ እንሸክሽክ ማለቱ
ነው)
ተው ተው
ተይ ተይ (እዚህ ላይ መጓተት አለ)
*
እሱ
ቆለኛ ደገኛ መባባሉን ትተን
ያለሽን ያለኝን በአንድ ላይ አስማምተን
ነጩን ጤፍ እንጀራ ስንዴውን ዳቦ አርገን
ብንበላ ይሻላል በአንድ ላይ ተስማምተን።
*
እሷ
አሁን ባልኸው ሃሳብ እኔም እስማማለሁ
ካልህስ በበኩሌ ዳቦም እወዳለሁ። (ሃሃ... እስከዚች ድረስ ነው ፈንጠር
ፈንጠሯ... ቀድሞም'ኮ ነግሯት ነበር። አመል ሁኖባት እንጅ)

©ጥላሁን ሀገሬ

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
አንዳንዴ ጋሽ ስብሐት ቤት ውስጥ ገነት ሲሆን ታየዋለህ ብር ሲኖረው
.
.
ወዲያው የስም ዝርዝር መጻፍ ይጀምራል : "ለእከሌ ይሄን ያህል ብር ፣ ለእከሌ ይሄን ያህል ብር ፣ ለእከሌ ይሄን ያህል ብር" ይልና
.
.
ሁልጊዜ ግን የሚረሳት አንድ ስም አለች. . . እርሷም የራሱ ስም ነች። እናም ለራሱ ይሄን ያህል ሳይል አከፋፍሎ ቁጭ ይላል።
.
.
አንዳዴ ደግሞ የራባቸው ደራሲያን ይመጣሉ : የኔ አይነት ስራ የሌላቸው ፣ በንባብ ላይ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ምናምን : እነርሱ ሁለት ዓይነት አቀባበል ነው ያላቸው በጋሼ ዘንድ
.
.
የመጀመሪያው "ቶሎ በይ እስኪ እግሩን ቶሎ ይታጠብ ፣ ምሳም አቅርቢለት" አብርሃም ይሆናል። ብላ ፣ ሚጠጣ ትፈልጋለህ ፣ ሚቃምስ" ይልሃል ብር ያለው ጊዜ
.
.
ብር የሌለው ጊዜ ደግሞ ሌላ ነው አቀባበሉ "እና እኔ እግዚአብሔር ነኝ እዚህ መጥተህ የራበው ፊት የምታሳየኝ ውጣልኝ ፣ ውጣልኝ ከዚህ ቤት" ይልሃል።
.
.
ምክንያቱም የለውማ !!
.........

(ደራሲና ኃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ አብሮት ከጋሼ ጋር በቆየባቸው ጊዜያት የታዘበውን የቅንነት መንፈስ በአንድ ቃለ መጠይቅ ከተናገረው በጥቂቱ)

@poem_with_mela
@wegoch
@wegoch
ካፌ ቶክ ልዩ የመዝናኛና የኪነጥበብ ዝግጅት ታህሳስ 30 በልዩ የገና መሰናዶ ይካሄዳል።

ወጣቶች ሀሳባቸውን በነፃነት ያንሸራሽራሉ ባለ ተሰጦዎች ስራዎቻቸውን ወደ ታዳሚው ያደርሳሉ ጨዋታዎችና ጥያቄዎች ያሸልማሉ።

ትኬቶች መሸጥ ጀምረዋል። ትኬቶቹን ለማግኘት በ0901118033 0932566694 እንዲሁም በ0922457627 ሀሎ ይበሉ።

የዝግጅቱ ቦታ ለትራንስፖርት አመቺ በሆነው በሜክሲኮ ቡናና ሻይ ካፌና ሬስቶራንት አንደኛ ፎቅ።

ሀሳቦች ያሸንፋሉ
ባለ ተሰጦዎች ይበረታታሉ!

@cafetokk
@getem
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 7

ጳውሎስ እንደዛሬው ተቁነጥንጦ አያውቅም ሆዱን ቆርጦታል ሲጋራ ካጨሰ ሰአታት አልፈዋል እጁን ይበላው ጀምሯል ጣቶቹን ወደ ኪሱ ሰደዳቸው ቀጥታ ወደ ጭንቅላቱ ሶልያና የተናገረችው ቃል አቃጨለበት አይኖቹ ትልቁ የስዕል አዳራሹን ቃኙ ሶልያና የለችም ስዕሎቹ ግን ቦታቸውን ይዘዋል
ቅር ብሎታል ደስ ያላለው ነገር አለ አንድ ሰው ከሩቅ ሲጠራው ተመለከተ አንድ ችግር እንደተፈጠረ አውቋል በፍጥነት ተራመደ ድንገት የስዕል ማዕከሉ የአደጋ ጊዜ አላርሞች መጮህ ጀመሩ ጳውሎስ እርምጃውን ገታ አደረገ በፍጥነት ወደ ስዕሉ አመራ በቦታው ይገኛል አይኖቹ ወዲ ወዲያ ይራወጣሉ ዛሬ መደናገር የለም ሁሉም በያለበት ቆሞ የሚሆነውን ይመለከታል
በአጠገቡ ከሚገኘው ትልቅ መስታወት ውስጥ አንዳች ነገር ሲወጣ ይታየዋል አይኖቹ ሙሉ በሙሉ በመስታወት ወደ ተሸፈነው ስዕል ላከ
ከመስታወቱ ውስጥ ቀስ እያለ ወደ ላይ የሚወጣ ጭስ ተመለከተ በፍጥነት የስዕል ማዕከል ተቆጣጣሪዎችን ጠራ ጭሱ ይበልጥ እየገዘፈ ስዕሉን ሸፈነው ይሄ ስዕል የራሱ የሆነ መግቢያ እንዳለውና ከመስታወት ውስጥ የሚወጣው ጭስ ስዕሉን ከአደጋ ለመከላከል የተገጠመ ሲሆን ውሀ ከመስታወት ውስጥ ካልገባ አልያም እሳት ካልተነሳ በምንም ታምር ይሄ ከመስታወት ውሰጥ የሚታየው ጭስ እንደማይወጣ ተቆጣጣሪዎቹ አስረዱት ያላቸው አማራጭ ወደ ክፍሉ መሄድ እንደሆነና መስታወቱን ምንም አይነት ጥይት ሊበሳው እንደማይችል ስለሰማ ወደ ተባለው መንገድ ተፈተለከ ከመስታወቱ የሚወጣው ጭስ ይበልጥ በዝቷል ስዕሉ ጭራሽ ሊታይ አልቻለም ጳውሎስ ከፊቱ ሚመራውን ጠባቂ እየከተለ ወደ ስዕሉ መግቢያ አመራ ከኋላው የሚከተሉትን መርማሪዎች ቦታ ቦታ እንዲይዙ ነግሯቸዋል ወደ መስታወቱ የሚያወጣውን ሊፍት ያዙ ጳውሎስ እንዴት የዚ መንገድ መረጃ እንዳልተሰጠው አላወቀም ወደ መስታወቱ ሲገቡ ስዕሉ ከቦታው ሳይጠፋ አገኙት ጳውሎስ ረጋ ብሎ መተንፈስ ጀመረ ማንም በመስታወቱ ውስጥ የለም
ወደ ማዕከሉ ተቆጣጣሪ ዞሮ ችግሩን ጠየቀው ካለ ምክንያት እንደዚ እንደማይሆን አስረግጦ ነገረው ጳውሎስ ከጆሮው ላይ የመጣው አሁንም የሶልያና ንግግር ነው
ሀይል እንደማያቋርጡ እርግጠኛ ነኝ ብላቸው ነበረ በፍጥነት የማዕከሉ ሀይል እንዲቋረጥ ተደረገ ጳውሎስ ያየውን ማመን አቃተው ያበራል የተባለው ስዕል ምንም አይነት ብርሀን አይሰጥም በፍጥነት ወደ መውጫው ተንደረደረ ሀይል መቋረጡን ሲያውቅ ወደ ታች የሚወርድበት ሊፍት እንደማይሰራ ተረዳ ያመለጡትንም ዘራፊዎች ሊይዝ እንደማይችል ገብቶታል በተመሳሳይ ስዕል ቀይረው ስዕሉንም ማረጋገጥ የሚቻለው ሀይል አጥፍቶ ጨለማ ውስጥ ስለሆነ በዚ ሀይል መቋረጥ ሰበብ የማምለጥ ዘዴያቸው እንደቀየሱ ተረዳ
መስታወቱን ነረተው የእጅ ባትሪውን አውጥቶ ስዕሉን ተመለከተው ብሽቅ ለራሱ ስድቡን ደገመው ከፊትለፊቱ በስዕሉ ላይ የተቀመጠውን ጥቅስ አገኘ
ሌሊቱ እየተገባደደ ነው ቀኑም ቀርቧል
ሮሜ13:12
ከጥቅሱ ላይ አይኑን የነቀለው ተቋርጦ የነበረው ሀይል ሲመለስ ነው ቀጥታ ወደ ማዕከሉ እንደተመለሰ የእጅ ስልኩን አውጥቶ ደወለላት ስልኳ አይሰራም እንደዘገየ ቢያውቀውም ሁሉም መንገዶች ላይ የፍተሻ ሀይሎች እንዲሰማሩ አዘዘ
የስዕል አዳራሹን ለቆ መዎጣት እንደጀመረ ጥቅሱን ብቻ አንብቦ መውጣቱን አስተዋለ ሳንቲሙስ በፍጥነት የወረደውን ደረጃ ወቶ ወደ ሊፍቱ አመራ ጨርሶ እንደገባ ምርመራ የሚያደርጉትን ባለሙያዎች አስቁሞ የተቀየረውን ስዕል ይመለከት ጀመረ ዳር ዳር ላይ ያሉትን የጨረቃ ትናንሽ ስዕሎች ሲፈትሽ አንድ ጎድሎ አገኘ ጠጋ ብሎ ሲመለከት 40 ቁጥር በግዕዝ ታትሞበታል የጠፋቻት ቁጥር አሁን እሱ አጊቶታል ረጋ ብሎ ማሰብ ጀመረ

ይቀጥላል....
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul Mekonnen 📷)
Art exhibition by #Fasika_Kebede
at fendika cultural center


ውሕደት የ ስዕል ትርኢት
#ፋሲካ_ከበደ
ታህሳስ 27 ቀን 2013 ከ ምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በካሳንቺስ #ፈንድቃ የ ባህል መዓከል

ትርኢቱ እስክ ጥር 11 የሚቆይ ይሆናል..

@seiloch
@seiloch
የአረብ ሀገር ጥላቻ የተፈጠረብኝ መቼ ነው?” ብዬ ለማስታወስ ሞከርኩ። ትዝ
የሚለኝ ነገር የለም። ምናልባት ጓደኛዬ ኡስማን ስለሚጠላው እሱ
ሳያውቀው አጋብቶብኝ ይሆን? አይደለም።ልጅ እያለሁ
የጀመረኝ ይመስለኛል። አያቴ በነበረችበት ሰፈር። ባደኩበት ሰፈር፣
በነእማማ ዙበይዳ ሰፈር።
ልጅ እያለሁ ለተወሰነ ጊዜ ሴት አያቴ ታሳድገኝ ነበር። በሰፈራችን
የምንወዳቸው፣ እማማ ዙበይዳ
የሚባሉ ሴት ነበሩ። የሆኑ ደርባባ አሮጊት ሴትዬ። ሰው ዝም ብሎ
ይወዳቸው ነበር። ጎመን መንገድ ላይ ይሸጣሉ። በክረምት ደግሞ በቆሎ
ይሸጣሉ። እማማ ዙበይዳን ሰፈሩ ሁሉ ለምን ይወዳቸው እንደነበር ግን
በትክክል አላውቅም። እኔም እወዳቸው ነበር። ለምን እንደነበር ግን
አላውቅም። “ነይ እስቲ አንቺ
ሰልካካ!" እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ እንደነበር ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ።
እማማ ዙበይዳ ባልም ዘመድም የላቸውም። በምድር ላይ ያለቻቸው ፋጤ
ቀጮ ናት። የሳቸው ብቸኛ ልጅ ፉጤ ቀጮ ጅዳ ሄደች ተባለ። ሰፈሩ ሁሉ
እማማ ዙበይዳ በቃ ሻሩ፣ አሁን ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው ብሎ ተነበየ።
እሳቸውን ያገኘ ሰው ሁሉ “ፋጤ ቀጮ ጅዳ ነው አይደል የሄደችው?”፣
ትደውላለች”፣ “ደህና ናት ታዲያ፣ “አሁን ለመድኩ አለችፖ፣ ግህም፣
“በርቺ በሏት እንግዲህ!
ይለመዳል.ይለመዳል”፣ “ዋናው መበርታት ነውታዲያ”፣ “እ!” እያለ
ከእማማ ዙበይዳ የበቆሎ እሸት
ወይ ጎመን ገዝቷቸው ያልፋል። በበጋ ጎመን በከረምት የበቆሎ እሸት
በመሸጥ ነበር የሚተዳደሩት።
በዚያ ሁሉ የሰፈር ሰው ሳይታክቱ በዚያ እናታዊ ፈገግታቸው ታጅበው ስለ
ልጃቸው ደኅንነት ምላሽ ይሰጣሉ። “እላሙዲሊላ አላሂ ወላሂ ደህና ናት!
ዱዋ አርጉላት." ይላሉ፤ መልሰው መላልሰው።
ሲኖሩ ሲኖሩ.…የሆነ ጊዜ ላይ ልጃቸው ስልክ ደውላ አለቀሰች ተባለ።
“ምን ሆንሽ” ሲሏት አትናገርም
ሲኖሩ ሲኖሩ…የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ መደወል አቆመች ተባለ። ደህንነቷን
የሚነግራቸው ጠፋ። ጎመን ወይ
በቆሎ ለሚገዛቸው የሰፈር ሰው ሁሉ “አረብ አገር ስልክ ማድረግ
ታውቅበታለህ?” እያሉ ይጠይቃሉ።
የተማረ የሚመስል ወጣት ሲመለከቱ ደግሞ “ልጄ! እስኪ ባክህ የጅዳ
ስልክ ቁጥር ጽፈህ አምጣልኝ? ልጄ ናፈቀችኝ ይሉታል። የሷ ስልክ ቁጥር
ግን የላቸውም። አንዳንድ ሰው ነገሩን ሊያስረዳቸው ሞከረ።ኾኖም
ሊገባቸው አልቻለም። የሰፈሩን ሰው መሄጃ መቀመጫ አሳጡት። እርስዎ
ስልኳን ፈልገው ያምጡ! እኛ እንደውልሎታለን” ሲባሉ እኔ ቁጥሯን ከየት
አዉቄ” ነው መልሳቸው። እሷ ካልደወለች
እሳቸው ወደየት ብለው ይደውላሉ? አድራሻዋ አይታወቅ ነገር።
የሰፈሩ ሰው በሙሉ እማማ ዙበይዳ ሲያዝኑ አይቶ አዘነ። እማማ ዙበይዳ
የደግነት ምሳሌ ነበሩ። ፋጤ
ቀጮ እጅግ ስትናፍቃቸው ግን ሰው ሰላም ሳይሉ ማለፍ ሁሉ ጀመሩ።
የሚሸጡት ጎመን ጠወለገ።
ወዲያው ደግሞ ወገባቸው ጎበጠ። ከመቼው በእድሜያቸው ላይ ምዕተ
ዓመት እንደጨመሩ። ሰው የልጁ ናፍቆት እንደ ኤድስ አመንምኖ
ሊገድለው እንደሚችል ያየሁት በእማማ ዙበይዳ ነው።

©Teddy Exubirant

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
እርቃንነት ፀጉሯን እየጎነጎነች ራቁቷን ከባኞ ቤቷ ስትወጣ አይን ለአይን ተጋጠሙ። ደንግጣ ወደ ባኞው ተመልሳ በሩን በፍጥነት ዘጋችው። "ይቅርታ! በጣም ይቅርታ" አላት በሚርበተበት ድምፅ ከበሩ ኋላ ሆኖ። የተዘጋውን በር በጀርባዋ ተደግፋ በረጅሙ ተነፈሰች። "በጣም ይቅርታ!" አላት እንደገና ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ "ለረጅም ጊዜ በሩን ሳንኳኳ አልሰማሽኝም፣ እቃዬን ልወስድ ፈልጌ . . ." . . . . . .ዝምታ . . . . . .
"አይ ምንም አይደል. . . " አለች በዝግታ፣ "ወይም ሌላ ጊዜ ልምጣ ?. . . " መለሰ፣ ጮክ ብሎ። ፎጣ አግድማ፣ በሩን በትንሹ ከፍታና ፊቷን አጮልቃ "አይ፣
እቃህ ከአልጋው አጠገብ አለልህ" አለችውና በሩን መልሳ ዘጋች። በሩን መልሳ ዘግታ ጀርባዋን አስደግፋ ወለሉ ላይ ተቀመጠች። ከእግሩን ኮቴ እያዳመጠች ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተሰማትን የራቁትነት ስሜት አሰበች-- ከመቼውም የተለየ እርቃንነት። ሰውነቷ ላይ ከእሱ የምትደብቀው ነገር አልነበራትም። ይልቁኑም ገላዋን ከማንም ሰው የበለጠ እሱ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ታምናለች። ከሁሉም አቅጣጫ አይቷታል፣ ዳብሷታል፣ ስሟታል። እንዲህ እንዳሁኑ በስሜት ሳይራራቁ በፊት በእሱ presence እርቃኗን ሆና ራቁት ስለመሆኗ አስባ አታውቅም። ዛሬ ግን አይኖቿ ከአይኖቹ ሲጋጠሙ የዛሬውንም እስከዛሬ ያየውንም ራቁት ገላዋ ታስቧት የሀፍረትና የራቁትነት ስሜት ወረራት። እጥፋቶቿን፣ ጠባሳዎቿን፣ ወጣ ገባዎቿን፣ የምትወደውን፣ የምትጠላውን አካላቷን ሁሉ ስለማወቁ አሰበች። He was undeserving of knowing that much about her. He was undeserving of being the only person to know that much about her. But she can't take it back. ከአእምሮው ጓዳ ገብታ እሷነቷን ከሀሳቡ መንጭቃ ልታወጣው ተመኘች። መሄዱን እየጠበቀች ጥያቄዎች በሀሳቧ ይመላለሳሉ "የተሰጠ ነገር ተመልሶ ይጠየቃል? መገለጥ ይመለሳል? ራቁትነት የሚሰማው በመታየት ውስጥ ነው? ባለመታየት የራቁትነትን ስሜት አርቃለሁ?"

@wegoch
@wegoch
@paappii

#hewan huletshi
በሔለን ፋንታሁን
*ሚዛን*

እግሬ መርገጡን እንጂ መድረሻውን አያውቅም ። ዓለምን እንደረሳ መናኝ ልቤ ሁሉ ቀለለበት ፤ ምንምነት ዘልቆ ተሰማው ....ሁሉ ባዶ ...ሆኖ ታየው ... ለብቻው መሆንን ተመኘ ፤ ግና እንዴት ብሎ ... ተፋቅረው እንደተጣሉ ጥንዶች ሁሉ ወዲ ወዲያ ይተረማመሳል ። ከዚህ እዚያ የሚረግጥ ዕልፍ ጫማ የግር ኮቴ ያለሁ ዜማ ...ትርምስምስ ብሏል ጯሂ ብቻ ...ግን ምን እያሰብኩ ነው ?አላውቅም ። ምን እያሰብኩ እንደሆነ አለማሰቤ አሳሰበኝ ...እሰይ ... አሰብኩ ይህንንስ ማን አየበት ... ግን መድረሻዬ ወዴት ነው ? መነሻዬስ ? አላውቅም ... ዝም ብዬ ዝምታን መፈለጌ መልስ ይሆን ? ብቻ አለሁ ። መኖር ደጉ ... ንፋስ እንዳናወጠው ውሃ ሐሳቤ መርጋት አቃተው ። ምን ሆኜ ነው ? እያልኩ እጠይቃለሁ የኔ ላልሆነው እኔነቴ ...ከራሴ ጋር ከገባሁት ሰጣገባ <<
ሚዛን >>በሚል የጎልማሳ ድምፅ አነቃኝ <<እሙዬ ተመዘኛ >> አለኝ ከመሬቱ
የተጣበቀች ሚዛኑን እየጠቆመኝ ...ከራስ ጠቤ ቢገላግለኝም ሐሳቡ የገባኝ
ዘግይቶ ነው ። አካሌን ከሚዛኑ አስቀምጬ ... የቆጠርኩትን ነገረኝ ። አሰብኩ ተመኘሁ የሐሳቤ መመዘኛ ቢኖረኝ ብዬ... አሁንም ግን መድረሻዬን አውቀዋለሁ..."የሐሳቤን ሚዛን ፍለጋ........

@getem
@getem
@paappii
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 8

ሌሊቱን በሙሉ ስልኳ አልሰራ ብሎታል ለምርመራ ክፍሉ ያላስተላለፈውን ከስዕል ማዕከሉ ያገኘውን ሳንቲም በእጁ እፍን አድርጎ ይዞታል እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም የት እንደጠፋች አልገባውም
ከቢሮው እንደገባ በአይኑ ይፈልጋት ጀመረ ግን የለችም ዛሬም ሶልያናን ጥበቃ ለስብሰባ የተቀመጡ ሰዎች እንዳሉ ሲያይ ይበልጥ ለማግኘት ፈለገ በድንገት የምርመራ ክፍሉ ፀሀፊ ወደ እሱ ስትመጣ ተመለከታት ይሄ የሶልያና የስራ መልቀቂያ ወረቀት ነው ትናንተ ልክ እናንተ እንደወጣችሁ ነው ያስገባችው ሶልያና ከእንግዲህ ከእኛ ጋር አትቀጥልም ፀሀፊው ጥላው ሄደች ምንም አልተናገረም የያዘውን ሳንቲም ጭምቅ አድርጎ ያዘው ሲጋራውን እስኪለኩስ ተጣደፈ

ሙሉ ለሙሉ ሀሳቧ ተሳክቷል ያላገኘችው ግን አንድ ነገር አለ እሱም ግዙፉን ጳውሎስ ነው አሁን ወደ ቢሮው ገብቶ መልቀቂያውን ሲመለከት ምን ይሰማው ይሆን እያለች እራሷን ትጠይቃለች ትንሽም ፈርታለች ግን ካገኘችው ደስታ አይበልጥባትም ባሳየቻቸው መንገድ ሄደው እንቅፋቷ ስላልሆኑ ተደስታለች ፈልጋ ያላገኘችው አንድ ነገር ግን አለ ስለፈለገችውም ጭምር ነው የመጽሀፍ ቅዱስ መርማሪ መስላ ከምርመራው ጣቢያ የገባችው ጳውሎስን ከብዙ ጊዜ በሁዋላ ያየችው በቴሌቪዥን መስኮት በወንጀለኞች ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ነው እሷ በምትፈፅማቸው ዝርፊያዎች ውስጥ ግን ጳውሎስ አሳዳጇ ይሆናል ብላ አስባም አታውቅም
ጳውሎስን ደግማ ያየችው የንጉሱ ሁለተኛ ማስታወሻ በተሰረቀ ጊዜ የሰጠውን ቃለመጠይቅ አይታ ነው የድሮ አመሉ አልተወውም አሁንም በሀይል ሁሉንም የሚያገኝ እንደሚመስለው ተረዳች
ለሶስተኛ ጊዜ በፈፀመችው ዝርፊያ ላይ ካስታወሰኝ ብላ ሳንቲሙን እየጣለች መሄድ ጀመረች ጳውሎስ ግን አሁንም ጌታ ተሰቅሎ ያለበትንና ጨረቃ የሚል ፅሁፍ ያለበትን ስዕል ማስታወስ አልቻለም
ያኔ ያሰቃያት ያዛት የነበረውን ጳውሎስ ከፊቱ ቆማ ለማዘዝ ውስጧ በጣም ስለሻተ በቀጥታ የምርመራ ክፍሉ ያወጣውን መወዳደሪያ ፈተና አልፋ ከፊቱ ስትቆም እንኳ ጳውሎስ አላስታወሳትም ከፊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ቆማ ገለፃ ስታደርግ ተሰምቷት የነበረው ስሜት እስካሁን አይረሳትም
ሶልያና የሚለውንም ስም አለማስታወሱ እስካሁን ገርሟታል ይሄን ያህል ሰው እንደሚረሳ ያወቀችው ያኔ ነው ሀይለኛው ጳውሎስ ቁጡ ጳውሎስ ሂድ ስትለው የሚሄድ ና ስትለው የሚመጣ እንደሆነ በማወቋ ተደስታለች ሁሉንም ነገር በእቅዳ መሰረት በመሄዱ ከሷ በላይ ደስተኛ ሰው ማንም እንደማይኖር ገምታለች
ለጳውሎስ ትናንት ከሰጠችው መረጃ በላይ ምንም እሷን የሚያስታውስበት መንገድ አይኖርም በዚህ ካላስታወሳት ግን ከፊቱ ቆማ ሁሉንም ነገር ለመንገር ወስናለች
ሀይለኛው ጳውሎስ ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማው ማወቅ ፈልጋለች ጅልነቱን ለምርመራ ክፍሉ አለመመጠኑን ሌባን ማባረር ብቻ ጥቅም እንደሌለው ወንጀለኛ ወንጀለኛን መቅጣት እንደማይችል እስክትነግረው ቸኩላለች
እስከዛሬ ጥላለት ምትሄደው የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስም እሱን ሊያነቃው አልቻለም
ይሄን ሁሉ አመት እንዴት አንድ ጳውሎስ ይኖራል ብላ እራሷን ጠየቀች በጣቷ ቀሚሷን መዳበስ ጀመረች የለበሰችውን ቀሚስ ሰብሰብ አደረገችው ባቷን በመዳፏ ዳበሰች አሁንም ሲረግጣት ሲደበድባት ይሰማታል ባቷ ላይ ያለውን ጥቁረት ስትመለከት እንባ ባይኗ ሞላ በቀጥታ ተነስታ ከፊት ለፊቷ ከሚገኘው መስታወት ፊት ቆመች ቀስ ብላ በጀርባዋ ያለውን ዚፕ አወረደችው ቀሚሷ ከእግር ስር ሲወድቅ አንድ የእንባ ዘለላ ከአይኗ ወደቀች ትከሻዋ ላይ ያለውን ጠባሳ ዳበሰችው ከጡቷ ስር ያለው ሽርክት የቅርብ ጊዜ ይመስላል ጳውሎስ የሚል ድምፅ ከጆሮዋ ብቅ አለ ዘወር ብላ ጀርባዋን በመስታወቱ ተመለከተች የገረፋት ግርፊያ በአይኗ መጣ መቀመጫዋን በሲጃራ እሳት ሲጠብሳት ያለው ህመም አሁንም ተሰማት ከአይኗ የሚወርደው የእንባ ዘለላ የእንብርቷን ስርጉድ ሲያርሰው ተሰማት አመማት

ይቀጥላል.......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
"በህይወቴ እንዳንች አይነት ቆንጆ አይቼ አላውቅም" ስልሽ

"አትዋሽ ባክህ! የህይወትህ ቆንጆ ሴት እናትህ ነች" ያልሽኝ ግዜ ነበር ሚዛንሽ ከላባነት ወደ ወርቅነት ከፍ ያለብኝ.


2 እንስቶች በህይወቴ ውስጥ አልፈዋል. ሁሉም ግን ልቤን ለማሸነፍ ብቻ ብለው ያዘጋጁትን አርቴፊሻል ማንነት ከአርቴፊሻል ውበት ጋር ለብሰው ነበር የቀረቡኝ. ልክ መሸነፌን ሲያወቁ ጣ ፋጩን ማንነት አሽቀንጥረው ጣል!...... ያኔ ነገር ብልሽት!

አንቺ ግን ገና ከጅምሩ ሳትዘንጭ የሚያምርብሽ ልታይ ልትልይ ሳትይ ጎልተሽ የወጣሽ የተለየሽ ነበርሽ...... ፈገግታና በራስ መተማመን የሰው ልጅ መተክያ የማይገኝላቸው ውድ ልብሶቹ እንደሆኑ አሳይተሺኛል. በዛ ላይ ግልፅ! የት ይቱጋ ግልፅ መሆን እንዳለብሽም የምታውቂ..

ከሞቀ ጨዋታ መሀል ተገልዬ እግርሽ ላይ ስላሉት ጥቃቅን ፀጉሮች፣ ስላልተሰራው ጥፍርሽ፣ ቀለም ስለማያውቀው ከናፍርሽ አስባለው እናም እስከዛሬ ከደቅነኳቸው እግሮች ጥፍሮች እና ከናፍሮች በእጥፍ ይበልጥብኝና ጅልነቴ ጎልቶብኝ እንደቂል ለብቻዬ ስቃለው.

ንግግሮችሽ ላፍታ ካምሮዬ አይሰወሩም.. ትዝ ይልሻል

"በጣም ልዩ ሴት ነሽ... እንደሌሎቹ አይደለሽም" ያልኩሽ ቀን ሸራ ጫማሽን አውልቀሽ የጠቆረና ስንጥቅ የከበበው ውስጥ እግርሽን አሳየሺኝ እናም
.
..
....
" እኔ ልዩ አይደለውም ካብዛኛዎቹ እንዳንዷ ነኝ... ከዚ የባሰ ከፈለክ የገበሬ ሴት ልጅ ወይም ጉልት ጨቻሪዎች ጋር ሂድ...." ያልሺኝን?

...
ልክኮ ነሽ ግን! እኛ ወንዶች መሬት ላይ ያለውን እውነታ ስርዘን በምናባችን የሳልነውን ውበት ላሟላች ሴት እንሰግዳለን... ያቺ ሴት ያንን ምናባዊ ውበት ምታመጣበትን መንገድ ስታቆም መስገዳችን ያቆማል. አዋ! ለውበቱ እንጂ ለኦርጅናሏ እሷ መች ሰገድንና? ለዚኮነው ሴቶቻችን ከጭንቅላታቸው ይልቅ ሰውነታቸው ላይ የሚሰሩት. ምክንያቱም በቀላሉ ተቀባይነትን ስለማያገኙ.
ካልቀጠነች ካልቀላች ፀጉሯ ካልለሰለሰና ካልረዘመ ጥፍሮቿ ካልተሰተካከሉ እግሯ ካልተላጨ ካልቀላ... እንገፋታለን! መገፋት ደግሞ ያምማል! ከምንም በላይ!.... ስለዚ መገፋትን ሽሽት ስንጥቁን ልሙጥ ጥቁሩን ቀይ ከፍዳዳውን ልስልስ ለማድረግ ስትጥር የአምሮዋን ነገር ትረሳለች. አስተዋይነት ልባምነት ምናምን የሚባሉ ሁሉ ወደ ገደል ይገባሉ.

"ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?" ብዬሽ ነበር... ህም! ሰውነቱ ሞላ ያለ ..ዘናጭ... ቁመና ያለው ..cool ... ገንዘብ ያለው.. ..ሙድ የገባው..... ትይኛለሽ ብዬ የጠበቅኩትን በሙሉ ብትንትኑን ያወጣ መልስ ነበር የመለስልኝ.


" አፍቃሪ"

ይህን ብቻ ነበር ያልሽኝ.

"አፍቃሪነት ውስጥ ሁሉም አለ... ማክበር ...መታመን...ፍቅር ራሱ....ትዕግስት... ሁሉም" ደገምሽልኝ

የሆነ ግዜ ላይ 'A woman with beautifull body is good for a night ,but, A woman with beautifull mind is damn good for a life!" የሚለውን አባባል ያረጋገጥኩብሽ ብቸኛ ሴት አንቺ ነሽ. የልቤን መፍቻ ሳልሰጥሽ እንዲው ገብተሻል... አንቺ እውነት ነሽ... እውነት ደግሞ ያው እውነት ነው..... ከእሱ ጋር መኖር እረፍትም ፍሰሀም ነው..... ለእውነት ከእውነት ውጭ ምን ይስማማዋል? ምንም

አንድ እውነት ልነግርሽ ነው
:

:
እውነቴ ሆይ አ.ፍ.ቅ.ሬ.ሻ.ለ.ው.
:::::::::
:::::::::::
"ነፍስሽ ከነፍሴ ጋር በእኩል ተለክታ፣
በእግዜር ጠቃሚነት
በፍቅር መርፌ በደንብ ተሰፍታ፣
ወበቅ ማታስወብቅ ብርድ ማታስመታ፣
ሆናለች ለልቤ እፁብ ድንቅ ኩታ።

ስለዚ አንች እውነት ሆይ እንደኔያለ ድስት እንዳንች ያለ ግጣም ከወዴት ይገኛል?.... እኛው ካልተገጣጠምን? ደግመዋለው

አ.ፈ.ቅ.ሬ.ሻ.ለ.ው.

ተፃፈ by aggie

@wegoch
@wegoch
@paappii
Laphto Contemporary Art Gallery will open an art exhibition by Kirubel Abebe titled "Gestures of Mask-Ulinity" on 16 January 2021. The event which will open at 3:00pm on 16 January will stay open until 16 February 2021. @linkupaddis

@GitemSitem

@seiloch
@seiloch
አንዲት ልጅ ነበረች ማቅመሻ የምላት 3

©ጓዴ ጥላሁን

እነሆ ከማቅመሻ ጋር ወዳጅነታችን ቀጠለ፡፡ ስድቧ ግን እንደ ሽል አእምሮዬ
ውስጥ እያደገ መጣ፡፡ የበለጠ ተአምር ብታሳየኝ ብየ
“.. እስቲ ከጅል ሙገሳ የተሸለ ስድብሽን ወዲህ በይ….” አልኳት፡፡
“... አይ እኔ ፒያኒስት እንጂ ተሳዳቢ አይደለሁም ..” ስትል መለሰች፡፡
“… እስቲ እኔ ሰሞኑን ወደ አዲሳባ ልመጣ ነውና ኪራይ ቤት ፈልጊልኝ…”
አልኳት፡፡
“… እሞክራለሁ…” አለችና ተሰናበተችኝ፡፡
በማግስቱ ተገናኘን፡፡
“… ቤቱ ይመጥንህ እንደ ሆነ አላውቅም፡፡ ኦሎምፒያ አካባቢ ሆስቴል
አግኝቼልሃለሁ፡፡ ባለቤቱ በቅርብ ወደ ውጭ ሄዷል፡፡ ኪራዩም ደህና ነው
4500…. ይስማማህ ከሆነ ልጠይቅልህ?…” አለች፡፡
“… 4500 በዓመት ግድ የለም፡፡ ቆሎ እየቆረጠምኩም ቢሆን
እከፍለዋለሁ፡፡…” አልኳት 4500 ለ 12 እያካፈልኩ፡፡
“… እየቀለድክ ነው ..” ስትል መለሰች
“… ያው በአንዴ ክፈል አይበሉኝ እንጂ አዲሳባ ቤት መከራየትና እኛ ሀገር
ቤት መግዛት እኩል እንደ ሆነ አውቃለሁ፡፡… ቢሆንም ተበድሬም ተለክቼም
መክፈሌ አይቀርም…” አልኩ፡፡
“…. እየቀለድክ መሆን አለበት…” አለች፡፡
“…. ኧረ ወዴት!! ቀድሞ የዚያን ቀን ሰምቼው የማላውቀውን ስድብ እንደ
ችንካር ከቀበቀብሽብኝ በኋላ የቀልድ ሆነ የቁምነገር ቆሌ ርቆኝ አውታታ
ሆኜ እያየሽኝ…..”
“…. እሺ ልወጣ ስለሆነ የምትከራይ ከሆነ ንገረኝና ልንገርልህ….”
“…. ይሆንኮ አልኩ …”
“…. የሁለት ወር ቅድሚያ ክፍያ ስለጠየቁ 9000 ሰጥልሃለሁ… ስትደርስ
ድሪምላይነር ሆቴል ናና በሪሴፕሽኖች አስጠራኝ.. አገናኝሃለሁ….”
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ….. ብየ አቀለጥኩት፡፡ ቤት ውስጥ ወጥ ሲቀቀል
የነበረው ጓደኛየ ማማሰያውን ወድሮ …. ሳፋ ላይ ሲታጠብ የነበረው
ሌላው ወዳጄ ሳሙና እንደተለቀለቀ ምናምንቴውን ከወዲያ ወዲህ እያላጋ
ተንደርድረው መጡ፡፡ ለ5 ደቂቃ ያህል ካረጋጉኝ በኋላ ወደየሞያቸው
ተበታተኑ፡፡ የወደቀውንት ስልኬን አነሳሁና
“… አደራሽን የበደልኩሽን ሌላ ጊዜ እክስሻለሁ፡፡ የዛሬን አውጭኝ፡፡…” ብየ
ላኩላት
“… ምን ማለትህ ነው፡፡ ሰፋ ያለ ነበር እንዴ የፈለግከው .. እኔኮ ያንሳል
ብየ ነበር…”
“… አንዴ አዳምጭኝማ እንጉዳዬ ነሽ፡፡ እየውልሽ አንቺ የማታውቂው ብዙ
ነገር አለ፡፡ አንቺ ለካ ሰው መስዬሽ ነበር እስካሁን ስታወጊ የቆየሽው ፡፡
ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ የጠቀስሽው ቁጥር የትምህርት ክፍላችን አጠቃላይ
በጀት ነው፡፡ በዚህ ብር ወርሃዊ ቤት ኪራይ ሊከራይ ነው የሚባል
ጭምጭምታ እንኳን ቢሰማ ጸረ ሙስናዎች በእሳት ሰረገላ ሲበሩ
መጥተው ቃሌን እንኳን ሳይቀበሉ ነው ላጭተው በእድሜ ይፍታህ አለም
በቃኝ የሚያስወረውሩኝ፡፡ እነሱ እንደሁ ላይ ያላውን አይበሏቸው እንጅ የኔ
ብጤው ላይ ነው በትር የሚያነሱት…. አደራሽን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት
ሟሟያ እንዳታደርጊኝ፡፡…”
“… እሺ ይቅር እያልክ ነው?…”
“… ስነግርሽ ውሾን ያነሳ ውሾን ይሁን በይ በይ… በእኩዮቼ አስፈልጋለሁ፡፡
አንቺስ ምን ቁልቁል አወረደሽ እኔስ ምን ሽቅብ አንጠለጠለኝ….
ያላባታችን!!! በይ በይ ቻው!!
ተሰናበትኳትና ወደ ደባል ጓደኞቼ ቤት ልገባ በር ላይ ስደርስ ሻንጣዬን በር
ላይ አስቀምጠው እንደ ገነት ጠባቂ መልአክ ግራና ቀኝ በሩን ይዘው
ቆዩኝ፡፡
“…. ምንድነው ነገሩ…” አልኩ ግራ እየተጋባሁ
“…. በል ወንድሜ እስካሁን ጓደኝነትህን አክብረን ችለንሃል፡፡ ቤት ኪራይ
ከፍለንም ተሳቅቀንም አንችለውምና ጥግህን ፈልግ፡፡….”
አሉና ቁልፉን በውጭ እንዳለሁ ቆልፉብኝ፡፡ ቁልቁል ሻንጣዬ ላይ
ወደቅኩ……

@Wegoch
@Wegoch
@Mahletzerihun
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 9

ቁጭ ብሎ የሚያስብበት አንድ ቦታ እየፈለገ ነው ከየቱ እንደሚሆን ግራ ገብቶታል ቀጥታ ወደ ቤቱ አመራ የሲጋራውን ሽታ ስለለመደው አዲስ አልሆነበትም ጨልጦ የጨረሰውን የመጠጥ ጠርሙስ ረግጦት ገባ አይኑ ለምዶታል ምንም አይነት የሚቀፍ ስሜት ሊሰማው አይችልም ተበልቶበት ያልታጠበ ብዙ ሳህን ከጠረጴዛው ይታያል ሳይበላ የተወው እንጀራ ሻግቶ ወደ ጠረጴዛው መቅረብ አይቻልም እያወለቀ የሚጥላቸው ብዙ ልብሶች በየቦታው ተንጠባጥበዋል ያላጠፋው ቴሌቪዥን የምሽት ዜና ያሰማል ካነጠፈው ብዙ ጊዜ ያስቆጠረው አልጋው ላይ ተዘረፈጠ የትራሱ ጨርቅ በቀን በቀን በሚያወጣው ለሀጭ ተጨማልቋል አንሶላው ንጣቱን እያጣ ነው መፀዳጃ ቤቱ ብቻ በፅዳት ተይዛለች ሁሌ ገላውን ውሀ ሳያስነካ ስለማይውል ጳውሎስ መፀዳጃ ቤቱን ከሁሉም ነገር በላይ በንፅህና ይይዛታል ብዙ የሚያስበው ውሀ ከጭንቅላቱ ሲፈስ ነው ሚያስጨንቀውን የውስጡን ሀሳብ ጠርጎ ሚያወጣለት ይመስል ሻወር ሲወስድ ከሶስት ሰአት በላይ ይቆያል የቤቱን ትርምስና መቆሸሿን ግን ይወደዋል የምርመራ ጓዶቹን እንኳ ወደ ቤቱ ጋብዞ አያውቅም እሱም የቤት ግብዣ የተባለ ነገር ይጨንቀዋል እንደ ልቡ መሆን ስለማይችል ብዙዎቹን ይሰርዛቸዋል ይልቅ በየ ጭፈራ ቤቶቹ መዝናናት ይወዳል ሚጋብዛቸው ሰዎች ሲኖሩ ከአንዱ መሽታ ቤት ወስዶ ሪዮ በእስፕራይት ያዝላቸዋል በረዶም እንዲያደርጉበት ይነግራቸዋል ጳውሎስ ሰው ከቤት መጋበዝ የሚል ህግ የሱ ህይወት ውስጥ የለም ሴትም ወደ ቤቱ ይዞ አይመጣም ብትንቀኝስ የሚል ፍርሀት አለበት ማታ ማታ ሞቅ ብሎት ይዟት ከሚወጣት ሴት አልያ በስካር መንፈስ ሳያስታውስ ጠዋት ሲነሳ ከአጠገቡ በአንድ አልጋ ከሚያገኛት ሴት በስተቀረ ህይወቱ ውስጥ አንድ ሴት ብቻ ነው የነበረችው እሷም ሶልያና ናት
ከተቀመጠበት አልጋ አንገቱን ወደ ላይ አንጋጦ አይኑን አፍጥጦ ብድግ አለ
በእጁ የያዘውን የመልቀቂያ ወረቀት ሲያነብ ሶልያና ዳዊት የሚል ስም አነበበ ያቺ ህይወቱ ውስጥ አንድ የሚላት ሴትም ሶልያና ዳዊት ነው ስሟ መመሳሰል ይሆናል የሚለውን ሀሳብ ሊሰማው ፍቃደኛ አይደለም ተመልሶ ከአልጋው ላይ ተቀመጠ እጁን ከኪሱ ሲከት ያስቀረውን ሳንቲም ለቀም አደረገው
ክርስቶስ በመሰቀል ላይ እያለ ያለው ምስል ድቅን አለበት ያቺ በህይወቱ ውስጥ የነበረችው ሶልያና መንፈሳዊ ስዕል ትስል እንደነበረ ትዝ አለው ሳንቲሙን ገለበጠው 40ቁጥር በግዕዝ ተፅፎበታል ሚሆነው ነገር እንደ ህልም መሰለው ከዛሬ 30አመት በፊት የሆነው ነገር እንደ ትናንት ይታወሰው ገባ
40ኛ ስዕሏን ስታሳየው የሳለችው ስዕል ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ የሳለችውን ስዕል ነበረ ገና ስዕሉን እንዳሳየችው ስዕሉ ላይ አድርጎት የነበረው ድርጊት ትዝ አለው እሷም ስትታገለው በያዘው ስለት ከጡቷ ስር የወጋት በሙሉ ከአይኑ ተደቀነ
ጭንቅላቱ መስራት ያቆመ መሰለው ከዚህ ሳንቲም በፊት ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎና ጨረቃ የሚል ፅሁፍ ያለበት ሳንቲም ብዙ ጊዜ ከተዘረፉት ማዕከላት ከመፅሀፍ ቅዱሱ ጋር አብሮ እንደሚያገኝ ታወሰው #ጨረቃ-ሶልያና ልቡ በፍጥነት መታች የጨረቃ ሌላኛ ስም ሶልያና እንደሚባል የነገረችው ትውስ አለው የወጡላትም አባቷ መምህር ዳዊት እንደሆኑ አእምሮው ይነግረው ጀመረ። የአባቷን ስም ደግሞ ሲያስታውስ የበገና ማዕከሉ ስርቆት ታወሰው ከስዕል ማዕከሉ የጠፋው የስድስቱ ጨረቆች ስዕል ከአእምሮው ድቅን አለ ያቺ ሶልያና አጠገቡ እንደነበረች ግባው እግሩ ተሳሰረ
እንዴት የሚለው ቃል ከጭንቅላቱ ለሺኛ ጊዜ ተመላለሰ ከዚ ሁሉ ጊዜ በሁዋላ የሚለውም ተያይዞ
ለመጨረሻ ጊዜ የተናገረችው ንግግር ከጆሮው ተደቀነ
የሲጋራ ጭስ ስዕሎችን ሊረብሽ ስለሚችል ሲጋራ ይዘህ አትግባ ከስዕሎቹ ነው የተነገረኝ
ይሄ ንግግር ለሱ አዲስ አልነበረም ያኔም ስዕሏን ስትስል ሁሌ ሲጋራውን ሲለኩስ ትነግረው የነበረ ማስጠንቀቂያ ነው
አሁን ሁሉ ነገር ገብቶታል ጨዋታዋም እንደዛው ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው ልላ ትውስታ ከአይኑ እንዲደቀን አእምሮውን ለመነው በፍጥነት ስልኩን አውጥቶ ቁጥር መታ የምርመራ ክፍሉ ፀሀፊ ስልኩን አነሳችው በከተማው ውሰጥ የሚገኙትን የስዕል ማዕከላት አድራሻና ስም እንድትልክለት ነግሮ ስልኩን ጠረቀመው
ትንሽ ደቂቃ ጠብቆ ስልኩን ከፈተ ሁሉንም መረጃ ልካለታለች በትኩረት ይመለከታቸው ጀመረ የዳዊት ጨረቃ የስዕል ጋለሪ የሚል አድራሻ ላይ አይኑን አፈጠጠ እራሷ ናት በፍጥነት ተራመደ ተራምዶት የገባውን ጠርሙስ አድቅቆት አለፈ ሶልያና መጣሁልሽ አይኑ ደም ለብሷል በሩን ጠረቀመው
ያላጠፋው ቴሌቪዥን በቅርቡ የተከፈተው አዲሱ የዳዊት ጨረቃ የስዕል ማዕከል በድምቀት እየተመረቀ ይገኛል ጳውሎስ በረረ

ይቀጥላል.....
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 10

ከማዕከሉ እንደደረሰ በቀጥታ ወደ መግቢያው ተራመደ የማዕከሉ ጠባቂዎች መግቢያ የሚል ጥያቄ አቀረቡለት ማንም ያስቆመኛል ብሎ አላሰበም መርማሪ ጳውሎስ እባላለሁ ስሙን ከመናገሩ ጠባቂዎቹ በፈገግታ ተቀበሉት ቦታ ተይዞሎታል እባኮ ይከተሉኝ ያልጠበቀው ነገር ሆነበት እንደምመጣ እርግጠኛ ነበረች ማለት ነው ብዙ ነገር አስገረመው
ከማዕከሉ እንደዘለቀ ያየውን ማመን አቃተው የስራ ባልደረቦቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት የከተማው ከበርቴዎችና ቁልፍ ቁልፍ የሚባሉ ታዳሚዎች ከስዕል ማዕከሉ ተገኝተው ስዕሎቹን ይጎበኛሉ ቢዚ ማታለያያ ልታሸንፈው እንደማትችል አውቋል የደበቀችው ጨዋታ እስኪታወቅ ነው ይሄ ሁሉ ሳቅ እና ፌሽታ ለራሱ ብዙ ነገር እየነገረው ነው። ለደቂቃ ከቆመበት ቦታ አልተንቀሳቀሰም ወደ ቦታው ሚመራው አስተባባሪ ቀስ ብሎ አንቀሳቀሰው ስዕሎቹን አንገቱ እስኪዞር ይመለከታቸዋል ባለፉት ሰላሳ አመታት ውስጥ ድንቅ ሰአሊ ሆናለች ድንቅ አታላይም ድንቅ ጨዋታ ፈጣሪም አድናቆቱን የወደደው አይመስልም እስካሁን ልትታየው አልቻለችም አይኖቹ ሶልያናን ይፈልጋሉ
ይሄ ነው የተዘጋጀሎት ቦታ ጌታዬ አስተባባሪው ጳውሎስን አስቀምጦ ትቶት ሄደ ግራ ገብቶታል ከስዕል ከማዕከሉ ያያቸውን የስራ ባልደረቦቹን ጠርቶ የሆነው ሊነግራቸው ጨዋታዋንም ሊያጋልጥ አሰበ ሀሳቡ ብዙም አልቆየም አስተናጋጇ ምን ሚፈልጉት ነገር አለ ብላ እስክትጠይቀው ድረስ ሀሳቡ ማጋለጥ የሚለው ነበረ ጳውሎስ ከሀሳቡ ሳይነቃ ሶልያናን የሚል ድምፅ ለአስተናጋጇ አሰማት እሱም ያለውን አላስተዋለውም ከደቂቃዎች በሁዋላ ንግግር ታደርጋለች እስከዛ ምን ልታዘዘዎ ፈጠን ብሎ ውሀ አላት በዚ ሰአት ከንፁህ ውሀ በቀሮ ሌላ ምንም ሊታየው አይችልም ሁሉን ነገር ከማፍረጡ በፊት እሷን ማነጋገር ፈልጓል አይኗን አያየ ይሄ ሁሉ ጨዋታ ለምን ሊላት ፈልጓል መልስ ካላት።
የተሰቀሉት ስዕሎች እጅግ ውብ ናቸው ውብ ሴት በውብ እጇ የሰላቸው የጳውሎስ የምርመራ ባልደረባ ዮናስ ከጳውሎስ ጆሮዎች ላይ አንሾካሾከ ለካ መልቀቂያ ያስገባችው ይሄን የመሰለ የስዕል ማዕከል ለማስመረቅ ነው ጀግኒት ናት ዮናስ ማውራቱን አላቆመም ጳውሎስ በሽቋል ተነስቶ ስዕሎቹን ማየት ጀመረ አለፍ አለፍ እያለ በሚጠላት ሴት ስለተሳሉ ምንም እንኳ ውብ ቢመስሉ አርክሶ እያያቸው እንደሆነ አውቋል። አንድ ስዕል ላይ አይኑን አተኮረ በገመድ ታስራ ያለች አንድ ሴች ልብ ሲገርፋት ይታያል በደንብ ተመለከተው። እንዴት ነው ወደድከው የሰማው ድምፅ አስደነገጠው ወደዚኛው ስዕል እስክትደርስ እየጠበቁህ ነበረ ልጅቷን ልብ ነው እንዲ የሚያደርጋት ያፈቀረችው ሰው ልብ ነው ሚገርፋት አንዳንዴ የወደድከው ልብ ውብ ይመስልህና ባላወከው ሰአት ተቀይሮ ቆሻሻ ይሆናል ልባቸውን አቆሽሸው አንተንም ያቆሽሹሀል ማትረሳውን ህመም ይሰጡሀል የወደድከው ሰው በጥፊ ይምታህ እንጂ የወደድከው ሰው እግር ይርገጥህ እንጂ የወደድከው ሰው ምራቅ ይትፋብህ እንጂ ሁሉም ክፋት ከቆሸሸው ልቡ የሚመነጭ ነው እያት እስቲ ታሳዝናለች አይደለ እያት ከንፈር ታስመጥጣለች አይደለ ብዙ እንደሷ ተሰብረው ማይመለሱ አሉ እጅግ ብዙ የታሰሩበትንም ፈትተው ሚነሱ ጥቂቶች ይኖራሉ የዚህን ስዕል ጥቅስ አንብበው
ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ ነው
ኤር17:9
ቀጣዩን ስዕል ከተመለከተው ያቺ ምታሳዝነዋ ልጅ የታሰረችበትን ገመድ ፈታ ሚገርፋትን ልብ ስትጨፈልቀው ያሳያል እጇ በደም ተለውሷል ጭካኔ እንጂ ሀዘን የለም ከፊቷ ጨካኝ ልቦች ምንም ያህል ጊዜ ቢቆዩ አንድ ቀን ደግ በነበሩ ልቦች መጨፍለቃቸው አይቀርም 30አመትም ቢሆን ፈገግ አለች ንግግሯ አስገርሞታል አሳምሞታልም ከጎኑ ሆና ስታወራው ተመልሶ ያደረገባትን ግፍ ያስታውስ ጀመረ። ሀይለኛው ጳውሎስ በምፀት ሳቅ ዘወር ብላ አይኖቹን ተመለከተቻቸው ይሄን ስዕል ግዛው ብር ካለህ ካልሆነ ስጦታም ቢሆን እሰጥሀለሁ ታድያ አንዱን ብቻ ልጅቷ ጨካኙን ልብ ስትጨፈለቅው ያለውን ህመሜን ሳይሆን መዳኔን ማሳይበት ስለሆነ ስዕሉን ስሰጥህ ደግመህ ጥቅሱን ማንበብ አትርሳ
በትግዕስት አዛዥን ማሸነፍ ይቻላል
ምሳሌ25:14
ከመድረኩ ስሟ ሲጠራ ጥላው ሄደች ጳውሎስ ምንም ማሰብ አልቻለም ንግግሯን ለመስማት ጓጓ እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ። በዚ ባማረ ምሽት አሸናፊዎች እና ተሸናፊዎች ፊት ለፊት በሚፋጠጡበት ምሽት ስለመጣችሁ አመሰግናለሁ ስዕሎቼንም ስላከበራችሁልኝ ስዕሎቼ ምስጋና ልከዋል ደስ የሚል ፈገግታ ለታዳሚዎቹ ሰጠች
አንዳንዴ ተጥሎ ተሰባብሮ የነበረ ነገር ሲጠገን ተመልሶ ሲተካ ልዩ ይሆኑአል ያንን ስብራት ለመጠገን ያንን የተሰበረ እቃ ለማደስ ስንጥር የውስጣችንም ስብራት ሲድን ይታወቀናል ይሄ ስዕል ከዛሬ 30 አመት በፊት ተሰባብሮ ተበጫጭቆ ተጥሎ ነበረ ከመድረኩ በመስታወት ውስጥ የተቀመጠ አንድ ስዕል መጣ እኔም ልዩ ነኝ ይህ ስዕልም ልዩ ነው ይሄን ስዕል ለመሳል ሶስት ቀን ፈጅቶብኛል ተበጫጭቆ ሲወድቅ ግን ለማደስ ድፍን 30 አመት ፈጅቶብኛል ስዕሉን ለማደስ ያን ሁሉ አመት ፈጅቶ ሳይሆን ስዕሉን በማደስ ተግባር ውስጥ የውስጤን ስብራት ለመመለስ ድፍን 30 አመት ፈጅቷል ስዕሉን ተመልከቱት ወደ ታች ቁል ቁል እየፈሰሰ ያለ ደም ይመስላል ክርስቶስ በመስቀል ሆኖ አለምን ለማዳን ሶስት ቀን ፈጅቶበታል ይሄም ስዕል በመስቀል ሆኖ የተሰቃየውን ስቃይ ያመላክታል አለም ስጢፋ ማይጠፉ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ እንደ ነፍሳችን ሁሉ ነፍስ የሚኖራቸው አንዳንድ በረከቶች ይኖራሉ። ጳውሎስ እራሱን መቆጣጠር አቃተው እንደምንም ከማዕከሉ ለመውጣት ወሰነ የሶልያና ንግግር ቀጥሏል ሁሌም እውነታ ወደ ውሸት ያስሮጣል ያሸሻል ሚነገረን እውነት ከሰራነው ውሸት ሀጥያት ሄዶ ስለሚጥለን ያሯሩጠናል ግን ውሸቱ ነው እውነትን ሚወልደው ሚሮጠው ሰው ውሸቱን ስለማያገኝ ተቅበዝባዥ ይሆናል ባሰመርክለት መስመር መጥቶ እጅህ ስር ሲወድቅ የሚሰማህ ደስታ ልዩ ነው ገራፊ ደብዳቢ ገዳይ ቢያሸነፍ ኖሮ እነዛ ገራፊዎች ክርስቶስን ባሸነፉ ነበረ ግን ሁሌም አሸናፊ ተበዳይ እና ለእውነት የኖረው ብቻ ነው መልካም ምሽት። ከመድረኩ ስትወርድ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አስተጋባ ጳውሎስ ግን የተጨፈለቀውን ልብ ስዕል ይዞ ሸሽቷል በረጅሙ ተነፈሰች

ተፈፀመ
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/29 19:28:12
Back to Top
HTML Embed Code: