Telegram Web Link
ስንቀራረብ ምነው ተራራቅን?
-
በመንገዴ ላይ ግድግዳ ላይ የተለጠፈ አንድ ማስታወቂያ አየሁ። ''1234'' ላይ A ብለው ቴክስት በማድረግ የትዳር አጋርዎን ያግኙ ይላል። በሥራ፣ በትምህርት ቤት፣ ታክሲ ውሥጥ በመሳሰሉት የዕለት ለዕለት መገናኛዎቻችን ላይ ይህንን የማግኘት ፀጋ ተነፈግን ማለት ነው? ይህን ያህል ማኀበራዊ መስተጋብሮቻችን ተንኮታኮቱ? ወይስ በጣም ስንዘምን ሳንደክም፣ ሳንለፋ፣ ለፀባያችን የተስማማ፣ የምንፈልገውን መመዘኛ ያሟላ ባል/ሚስት የማግኘት ፀጋ ታደልን? እራሴን ጠየቅሁ።
-
ዘመኑ የቴክኖሎጂ የሥልጣኔና የመረጃ ነው እንላለን። ልክ ልንሆን እንችላለን።
ቴክኖሎጂ ኑሮን ያቀላል እንላለን፣ ይህም እውነት ሊሆን ይችላል። ግን ምን
ድረስ ነው ኑሮ መቅለል ያለበት? የት ጋር ነው በቃህ ይሄ ደሞ ሕይወቴ ነው የምንለው? ለእኔ የቴክኖሎጂ መራቀቅ የት እንደሚያደርሰን ማሰቡ ከራሴ በላይ በስሬ ለማያቸው ቲንኤጀሮች ያስፈራኛል። በዕድሜያቸው ማወቅ ከሚገባቸው ነገር እጅግ አልፈው እንደሄዱ አስባለሁ። ያለው የማኀበራዊ ሚዲያው ብዛት እረፍት አልሰጠንም። በኪሶቻችን ባስቀመጥናቸው ስልኮቻችን ውስጥ ራሱን የሰወረ ጋኔን የሠለጠነ ይመስለኛል።
.
.
የመረጃ ዘመን ነው። የምንፈልገውን መረጃ በአንድ ደቂቃ ፍጥነት፣ በተወሰኑ
ድንቆላዎች ርቀት እናገኛለን። ስለሁሉም ነገር ስለሰማን ሁሉንም ነገር ያወቅን
ይመስለናል። በእያንዳንዱ ነገር ላይ ጥልቅ የሆነ ዕውቀት የለንም። በወፍ በረር የቃረምነውን እያድበሰበስን አዋቂ ለመምሰል እንቸኩላለን። የምናውቀው ግን ግልብ ነው። ይሄኔ አይደል ''ደፋር ህፃናት ጎዳናውን ሞሉት'' ማለት።
-
የምንወዳቸውን የውጪ ፀሀፍት መጽሐፎች በ50 ሳንቲም በቀን እየተከራየን ማንበብ አይጠበቅብንም። ትላልቅ ቤተመጽሐፍት ድረስ መድከም፣ ከውጪ ማስላክ አይኖርብንም። ስልኮቻችን ውስጥ ማንንም ማግኘት እንችላለን። ግን እንደድሮው ለንባብ ዋጋ አንከፍልም። ማሰላሰል ማሰብ አንፈልግም።
-
ከምንበላው፣ እስከምንለብሰው፣ ከሚያስፈልገን እስከተመኘነው ደጃችን ላይ የሚያመጡልን መተግበሪያዎች ተፈልስፈዋል። ጓደኛ ለማፍራት ሰፈርና መንደር ገጠመኝና ሌላም ሌላም አያስፈልገንም። የማህበራዊ ሚዲያው አለልን። እነዚህ መገናኛዎች ላይ ክንፍ በሚያደርግ ፍቅር እንወድቃለን። ዳሩ ፍቅራችን ለሳምንት ነው። ሳቃችን የሀሰት፣ አድናቆታችን የለበጣ ነው። እንናናቃለን። ኑሯችን ብልጭልጭ ነው። የምንመኘው እልፍ ነው። የምንወደው እስከወደዱን ነው። የምናነባው ለሚያስቀው ነው። የምናለቅሰው አንጀት ለሚበላው ነው። የምንከተለው የሚስቅብንን ነው። የምንደግፈው የደመነፍሱን የሚደናበረውን ነው። የምናምነው በእጆቻችን ጠፍጥፈን የሰራነውን ነው።
-
ኑሮ በቀለለ ቁጥር እየከበደ ነው። በሰለጠንን ቁጥር የጓደኞቻችንን ሕመም
የማናዳምጥ፣ በደስታቸው የማንካፈል ባካኝ ሆነናል። ትምህርታችን የጋን ውስጥ መብራት ነው። አስተማሪዎቻችን ለመማር ራሱ አይመጥኑም። ፕሮፌሰሮች ከአያቶቻችን የተሻለ የሕይወት መረዳት የላቸውም። ባለዲግሪዎቻችን እንግሊዝኛ ያፍራሉ። ዩኒቨርስቲዎቻችን ከምርምር ተቋምነት ወደግርግር ተቋምነት ከዞሩ ሰነባበቱ።
-
''መልካም ዜና ለወላጆች....'' ''ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን...'' ''...ተቸግረዋል? እንግዲያውስ ይዘዙን...'' የዘመናችን መልኮች ሆነዋል። መዘመን መልካም ነው። ይህ ሲሆን ግን ለተገባው ሕይወታችን ፊት ነስተናል።
በግብዝነታችን የዋሆቻችንን ገድለናል። መልካሞቻችንን መድረሻ አሳጥተናል። ራሳችንን ለመከላከል እንፈጥናለን። በሰዎች ለማፌዝ ቅርብ ነን።
-
ከስክሪኖቻችን ጀርባ ተቀምጠን ልብ እንሰብራለን። የምናወጣት እያንዳንዷ ቃል የት ደርሳ ምን እንደምትፈጥር ግድ አይሰጠንም። ስንሳለቅ አንጠነቀቅም።
በሰው ተክለቁመና፣ አፈጣጠርና ሕመም ሳይቀር ሳይቀፈን እንስቃለን። ለፍርድ
ችኩል ነን። ለማጀገንም ለማውገዝም አሰፍስፈን እንጠብቃለን። ስንደሰት
ባለክንፍ ነን ...እንደቢራቢሮ ። አቁሳይ ሀምሳእግርነታችንን እስኪያስፈልገን
አናሳይም።
-
በጣም ገጠር የሚባል ቦታ ሰርቼ አውቃለሁ። photoshop፤ sarcasm
ምናምን የማይረዳ ብዙ ሕዝብ አለን። ያየውን ቀጥታ የሚያምን ስልክ ካለው
ሕዝብ አብዛኛው ነው። ይህንን ሳይረዳ ፌስቡክ ክፈትልኝ ብሎ ወደዓለማችን
የሚገባ ብዙ ነው።
-
ራስን የማጥፋት ምጣኔ ለምን አሻቀበ? አመጽና አጥፊነት ለምን ተበራከተ? አንጠይቅም። ስታትስቲክስ በመደርደር ጊዜ አናጥፋ እንጂ መልሱን ሁላችንም
እናውቀዋለን።
-
በሥልጣኔ አምናለሁ። ቴክኖሎጂ እጅግ መልካም ነው። የልብ ሰዎቼን ያገኘሁት
እዚሁ ነው። አንዳንዴ ግን አዝናለሁ። በእናንተም በራሴም።
-
ስንቀራረብ ምነው ተራራቅን? ሰው ስንሆን ምነው ልባችን በደነ?
-
ይህ ሁሉ ለቃላቶቻችን እንጠንቀቅ ለማለት ነው። Speak life የማይረባንን ንቀን እንለፍ። ለሁሉም ነገር መመላለስ፣ ለሁሉም ነገር እኔን ስሙኝ ማለት አያዋጣም።
.
.
በመጨረሻም winston Churchill
'' by swallowing evil words unsaid, no one has ever harmed his stomach''

@wegoch
@wegoch
@paappii

#henock bekele
አንዲት ልጅ ነበረች ማቅመሻ የምላት- ክፍል 2

©ጓዴ ጥላሁን

ያወረደችብኝን መዓት መመከቻ አጣሁ፡፡ ባወጣ ባወርድ ስድብ ከየት
ላምጣ፡፡ ነገ በእጥፍ የምመልሰው ስድብ ከጓደኞቼ በዱቤ ጠየቅኩ፡፡
አልተባበሩኝም፡፡ እንደውም ጦስህ ለኛ እንዳይተርፍ ወዲያ ሂድ ብለው
ኩቲ አደረጉኝ፡፡
‹‹ …. ስሚ ድሮስ በትምህርት ያልተበዘበዘ ጭንቅላት ከስድብ ውጭ
የሚያውቀው የለም፡፡››
“……. እኔ አልተሳደብኩም፡፡…›› ብላ መለሰች
“……... እና እስካሁን ቅቤ እየቀባሽኝ ነበራ… ግድ የለም እሱ የላይኛው
ይፍረድ….” በሙግት ያጣሁትን ስም በማሳቀል ለማምጣት ጣርኩ፡፡
“……. ይህ ስለ ተሰማህ አዝናለሁ ይቅርታ፡፡››
“…….. አሄሄ ተይኝ እስቲ ይሄን ወግቶ በቅቤሽን… እሱ ይፍረድ ብቻ…››
እያልኩ በሶት አደባባይ አደረግኩት፡፡
“…… እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም ካልተስማማሁህ ቀላል
ፎርሙላ አለልህ፡፡ ፐሮፋይሌን ክሊክ አድርገህ አንፍሬንድን ተጫን፡፡…..”
“…… አሁን ገና ጨዋታዋን አመጣሻት እስቲ አስቲ ድገሚያት
ፎርሙላዋን?” ወዳ እና ፈቅዳ ስለላከችልኝ አንፍሬንድ አደርግሻለሁ ስላት
በታቦት አማላጅ እንደምትታረቀኝ ገምቼ…..
“…… ፎርሙላውን ከፍ ብለህ ማንበብ ትችላለህ እኔ አልደጋግምም፡፡
ይልቅ ጉድለትህ የቀመር ብቻ አይደለም፡፡ የቋንቋም ጭምር ነው፡፡ ቀመሩን
እኔው እሰራዋለሁ አንተ ቋንቋህን አሻሽል…..”” አለችና አንፍሬንድ አድርጋኝ
አረፈች፡፡
ሳስበው ግን ገመናዬን የምትዘራብኝ መሰለኝ እዚችው በአቦ በስላሴ ብየ
ልታረቀት አሰብኩ፡፡
‹‹….. እየውልሽ እቴቴ አንች! ማነሽ የአይን አበባ…መቼም ሰው ሆኖ
የማይስት እንጨት ሆኖ የማይጤስ የለምና ጉዳችንን ሰው ሳይሰማው
እናዳፍናት፡፡›› ብየ አስተዛዘንኩና ደግሜ ፍሬንድ ሪኳስት ላኩላት፡፡
ተቀበለችኝ፡፡
(ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
ሽንፈት ሰው ፊት ሲሆን ለምን ይገዝፋል ?

©በረከት ታደሰ

ወደ ሐሴት የሚወስደው መንገድ ሩቅ አይደለም፡፡ እሷ ነች! የደስታዬ ርቀቱ
በቅርበቷ ልክ ይሰፈራል፡፡ ተያይዘን... ተቃቅፈን... በሞላ ቦታ አንድ ወንበር
ላይ ለሁለት የመቀመጣችን ሚስጥር መራራቅን ፍራቻ ነበር፡፡ ስንዝር ለምን
እንራራቃለን? መተቃቀፍ ስንችል? በትንሽ የተናቀ ርቀት እያደር አይሰፋም?
ጓደኞቻችንን እንሰለቻቸው ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ አንድ ቦታ ላይ ተቆጣጥሮ
መቀመጣችን ይሰለቻቸዋል፡፡ ጥለውን ይሄዳሉ፡፡ የማናስታውሳቸውን
ጉዳዮች እናወራለን... ዝምታችንም ሹክሹክታ አለው፡፡ ቀኑ እንደ ገለባ
ይበንናል፡፡ ሽታው እንደ ውድ ሽቱ በሚጣፍጥ ዝምታ...
~
የመጀመሪያ አመት ተማሪ እያለሁ ነበር... ገና ዩንቨርስቲን በግምትና
በምኞት ነው የማውቀው... ከብልቃጥ አለሜ ወደ ውጭ የፈሰስኩበት
የመጀመሪያ አጋጣሚዬ ላይ ለስላሳ እጆቹን ዘርግቶ የተቀበለኝ ፍቅር ነበር፡፡
ተፈጥሮ እና አጋጣሚ አሲረው አገናኙን፡፡ እንጂማ የሁለት አለም ሰዎች
ነበርን... ፍፁም እንለያይ ነበር፡፡ እኛን እያነካካ በእኛ አለማወቅ የሚያፌዝ
አንድ አካል ነበር፡፡ እኛ ደግሞ ሎሌዎች ነን... ለገፈተረን የምንንደረደር
የተፈጥሮና የአጋጣሚ ሎሌዎች፡፡ ተላመድን... ርቀት ናድን፡፡ ነገ የሚባል ቀን
አልነበረንም፡፡ ሁሉም አሁን... አሁን... አሁን... የተሸመደደ ፍቅር አልነበረም...
አሁናችን ላይ ጣኦቶች ሆነን የምንዋብ፡፡ ስንቴ እናፈቅራለን?
~
እንደ የትኛውም የፍቅር ታሪክ ቀድሜ ያፈቀርኳት እኔ ነበርኩ... ቀናቶቼን
ፊቷ ዘርግፌ አስገዝቻለሁ... አልባከኑም!
ቆየ... በእንደዚሁ አይነት አካሄድ ቆየን... የሰለቸኀት ይመስለኛል፡፡ ሙሉ
እኔነቴን ሰጥቻት ሌላ የማታውቀውን ፍቅር ልሰጣት አልችልም፡፡ እየቆየ
<እወድሻለሁ> የሚለው ቃል በልቧ ረከሰ፡፡ እንደ የትኛውም መግባቢያ
ተራ ቃል ሆነ... ቃል በግዜ ርቀት እንደሚያረጅ አየሁ፡፡ መልሷ <ዝም>
ነበር፡፡ አዲስ ነገር አልነበረኝም... ምን ፍለጋ ትመጣለች? ያለ አዲስ ጉዳይ
ፍቅር ራሱን ችሎ እንደማይቆምም ያኔ አየሁ፡፡ ሙሉነቴን ገልጬ
አሳይቻታለሁ... የምትመኘው ነገር አልነበራትም፡፡ What more can i
give up?
~
አለሙ ግራ ነው! ከሰጠኸው በላይ ይጠይቅሀል... ዙሪያህ መክሰርህን
ይሰብክሀል፡፡ ፍቅረኛዬ አልነበረችም... ተራ ወዳጅም አልነበርንም፡፡ ከሁለቱ
መሀል የሚወዛወዝ ቀጭን መስመር ላይ ግን ቆመናል፡፡ እወድሻለሁ ለሚል
የሻገተ ቃል መልሱ <ዝም> ነበር፡፡
~
ከእርሷ የተቀበልኩት አንዳች ፍቅር የለም፡፡ ቃል አውጥታ <<እኔ ላፈቅርህ
አልችልም ብላኛለች፡፡>> ከቀን ወደ ቀን ምን ፈልጋ እንደምትመጣ ሁሉ
ግራ ይገባኛል... ምናልባት ቶሎ ራሷን መስጠት እኔጋ ያላትን ዋጋ
የሚቀንሰውም መስሏት ይሆናል፡፡ የሁለትዮሽ ፍቅር ከሚመስል ነገር ወደ
አፍቃሪ ተፈቃሪ መንገድ ውስጥ መቼ እንደገባን እንኳ ማስተዋል ያቅተኛል፡፡
ያየን ሁሉ <ናቸው> ብሎ የሚገምተው እና እኛ <የሆንነው> ይራራቅ ነበር፡፡
ከቀን ወደ ቀን ተራራቅን... ከአካል ሳይሆን በሀሳብ... ተቃቅፎ መራራቅ
በየትኛው ቃል ይገለፃል? ቃል አለው? ተፅፎ እፎይ የሚባል አይነት?
~
ሌላው ተከድኖ ይብሰል!
የማፍቀር ዋጋው ህመም ነው፡፡ ታመህ የምትገዛው ደስታ ፍቅር ይባላል...
<ትላንትና ነገ የራሳቸው ጉዳይ!> ብለህ የማለፍ ግድየለሽ ልቡናን
ፈልፍለህ ትፈጥራለህ፡፡ የአወዳደቅ ጥሩ የለውም... በፍቅር መውደቅ ግን
እየቆየ የሚደምቅ ጌጥ ነው፡፡ ልደግመው ብፈልግ የማልችልበት አይነት
አወዳደቅ፡፡ በልቤ የሚያብረቀርቁ የነበሩ የማፍቀር ድፍረት አንዳንዶቹ
ስወድቅ ረገፉ...
<እሷ> ውስጥ ያለ ሌላ ቀለም ውበት በምን ይገለፃል፡፡ ይሄስ እድለኛነት
አይደል? በኑሮህ አሻራ ላይ የፍቅር ጣት ይነካሀል፡፡ አንተ እድለኛ ነህ...
ትወዳለህ... ትርቃለህ... ሰፌድ መሳይ ጉዞ ነው፡፡ ክብ... ግን የማይገጥም፡፡
አንዱ ከአንዱ የሚለያይ ይመስልሀል... ግን በፍፁም፡፡ መንገዴ
አያሳፍረኝም! እኔነቴ ጋር ፀብ የለኝም፡፡ እኔ የአጋጣሚዎቼ ውጤት ነኝ...
እኔ መንገዴን መስላለሁ፡፡
~
ህይወት ሸጋ ፈጣሪ ነች! ነገህ ላይ ደግሞ ሌላ አይነት መቀራረብና
ማፍቀርን ትፈለስፋለች፡፡ ካለመኖር ውስጥ ጣዕም መዝዛ ከምላስህ ጫፍ
ታኖራለች፡፡ ጉዞው ወደ ምንምነት ስለሆነ እሱም ይደርቃል፡፡ ደግሞ ሌላ...
ደግሞ ሌላ... ደግሞ ሌላ...

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 4

ጥብቅ ቁጥጥር በማዕከሉ እንዲደረግ ትዕዛዝ ተላልፏል ሁሉም በሮች በተለያዩ መንገዶች በእይታ ውስጥ ናቸው ዛሬ ከማዕከሉ ጎብኚም የበገና ተማሪዎችም የሉም ከቀሩት ትንሽ የፅዳትና የጥበቃ አባላት ውጪ ማዕከሉ ውስጥ ዛሬ የበገና ድርደራ አይሰማም በተለይ ትላልቅና ነባር በገና የሚገኙባቸው ክፍሎች ተጨማሪ ሀይል ተመድቦ በእይታ ውስጥ ናቸው ከበገና ማዕከሉ በተጨማሪ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ያለው መንገድ ሰው ዝር እንዳይልበት ተደርጓል
ጴጥሮስ የለኮሰውን ሲጋራ ይዞ ይንጎማለላል የለበሰው ጥቁር ጃኬት ከዛ ግዙፍ ቁመቱ ጋር ተዳምሮ ሚፈለገው ዘራፊ እሱ ይመስላል ወደዚ ከተማ ከመጣ በሁዋላ ይሄን የበገና ማዕከል ብዙ ጊዜ ተመላልሶበታል ዛሬ ግን ለጉብኝት ሳይሆን ማዕከሉን ሊጎበኙ ከሚመጡ ዘራፊዎች ማዕከሉን ሊታደግ ተገኝቷል
በማዕከሉት ውስጥ ያሉት ስዕሎችና ቅርፃ ቅርፆች ስበውታል ዛሬ ምን ፍለጋ እንደሚመጡ ባያውቅም ግምቱ ከማዕከሉ መሀል ክፍል ከሚገኘው ትልቁ በገና ላይ እንደሚሆን ጠርጥሯል ከአምስት የሚበልጡ ጠባቂዎች ለመካከለኛው ክፍል ብቻ መድቧል ካሳሰበው ምንም ቢሆን እንደሚያደረግ አውቆቷል ስዕሎቹን እየተመለከተ ሲዘዋወር ትንባሆ ማጨስ የተከለከለ ነው የሚለውን ፅሁፍ አይቶ ፈገግ አለ ከፅሁፍ በላይ ህጉ እዚ ቆሙአል ብሎ ለራሱ ነገረው በራሱ ተማምኗል እሷም አስደንቃዋለች በሶስት ወር ያልደረሰበትን አልያም ከዛ በላይ ጊዜያት ለማወቅ ሊፈጅበት የሚችለውን ጊዜ አቅልላለታለች የጭንቅላት ጨዋታ ብዙ ባይችልም ቡጢ የሚሰነዝረው ከአይምሮው በሚመጣ መልእክት ነው ብሎ ያስባል ጭንቅላቱ በጣም እንደሚሰራ ያውቃል ይሄን ሶስት ወር ግን ጭንቅላቱ ቆሙአል እጆቹም ሚሰነዝሩት ቡጢ የለም እንደ ቀድሞው አባሮ ሚይዘው ሌባ የለም ከእግር የፍጥነት ሩጫ ቆንጆ የጭንቅላት ጨዋታ እንደተዋወቀ ገብቶታል ቡጢውን ለመሰንዘር እንደ ሶልያና አይነት ከእግር ሩጫ በፈጠነ አስተሳሰብ የሚያስብ አጋር ያስፈልገው እንደነበረ ገብቶታል ዛሬ እጆቹ ለቡጢ ተዘጋጅተዋል ቀላውንም ለቆ ኢላማውን ከመታ ድፍን ሶስት ሆኖታል የእጅ ሽጉጡን ከጀርባው አውጥቶ በመዳፉ ዳበሰው
ዛሬ የናፈቁትን ነገሮች ማድረግ ሊጀምር እንደሆነ አውቋል ድል ከቀናው እንጀለመደው ወደ ሚወደው ባር ሄዶ ኦሪዮ በእስፕራይት ለመጠጣት ጓጉቷል መሸትሸት እያለ ነው ብዙዎቹ ቀስ ባለ እርምጃ ይራመዳሉ እሱ ብቻ ቆሞ ለምን ይህን ሁሉ ነገር እንደሚያስብ አልገባውም እስካሁን አልታየችውም ለነገሩ ካለቦታዋ ምትገኝ አይነት አይደለችም አለ በልቡ አሁንም ግን አይኖቹ ሶልያናን ይፈልጋሉ

የምሽቱ ፀሎት በውሀው ጉርጓድ ዙሪያ ተጀምሯል ጨረቃ ዛሬም እንደደመቀች ናት ኮኮቦችም ከሰማዩ ላይ በዝተዋል ጀርባዋን ከብዷታል ጭንቀት ሊያጠቃት መሆኑ አስደንግጧታል ምንም ነገር ግን እንደማትፈራ ታውቃለች ምንም ቢመጣም ለመቀበል መፅሀፍ ቅዱሷን ገለጠች
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል (ምሳሌ12:25)
ለነሱ ያነበበች ቢመስላትም ዛሬ ለሷም ጭምር ቃሉ እንደሚጠቅም ልቧ ነግሯታል
ምታደርገው ነገር ሁሉ ለሷ ትክክል ነው አሁንም ልቧ ልጭንቅላቷ መልእክት ይልካል ጨረቃ ልጆቿን የትም ጥላ አትሄድም በማትበራበት ጊዜ እንኳ ለልጆቿ እየታየች ብርሀኗን ትሰጣለች ሁሌም አብሬያችሁ ነኝ
ሁሉም መጽሀፍ ቅዱሳቸውን አውጥተው ማንበብ ጀመሩ
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል (ምሳሌ12:25)
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
የድምፃቸው ሀይል ያስደነግጣል የፀሎት ማሳረጊያ የሆነውን የጉርጓዱን ውሀ እየተጎነጩ በሰልፍ ደረጃውን ወረዱ
ብቻዋን የቀረች አንድ ሴት ግን አለች

መቁነጥነጥ ጀምሯል ከነጋ ያጨሰውን ሲጋራ እሱም አያውቀውም አስሬ ሰአቱን ይመለከታል አሁንም እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አደረገ ጃኬቱን ወደ ላይ እንደሰበሰበ ረጋ ያለ የበገና ድርደራ ይሰማው ጀመረ ጆሮው ቆመ ከመቅፅበት ረጋ ያለው ድርደራ መፍጠን ጀመረ አይኑን ጨለመው የማዕከሉ ሀይል ተቋርጧል ብዙ ግርግር ተፈጠረ የበገና ድርደራው ይበልጥ መፍጠን ጨምሯል ብዙዎቹ ጠባቂዎች የእጅ ባትሪዎቻቸውን አብርተዋል ስልኩን አውጥቶ ቁጥሮች መታ በፍጥነት ተጨማሪ ሀይልና የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች እንዲላከኩ አዘዘ በፍጥነት የበገናውን ድምፅ ወደ ሚሰማበት አቅጣጫ ተፈተለከ

ይቀጥላል....
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
"ወንድአገረድ ናት ይላሉ"
[ ዶ|ር ዮሴፍ ወርቅ ነህ ]
.....True story.....

እያንዳንዷ የሽፋሏ ፀጉር በቄንጥ ነው የተደረደረችው ። አንዷ ተመዛ ብትወድቅ
ከውበቷ የሆነ ነገር የምታጎድል ትመስላለች። ቆንጆ ናት ። ልቅም ያለች ቆንጆ ። የተስተካከለ ቁመና አላት ። የፋንታ ጠርሙስ ብቻ ነው እንዲ ተመጥኖ በቅርፅ ሲሰራ ያየሁት ወደህክምናው ክፍል ገባችና ጠርዙ ላይ ቂጢጥ አለች። ቁጭ ስትል ራሱ የተንዘረፈፈ ቢጫ ቀሚሷን በቄንጥ ሰብሰብ አርጋ ነው ። ለወንበሩ የሳሳችለት ትመስላለች። ካርዷ እጄ ላይ ስለነበር በስሟ ጠራኋት
" ማርያማዊት እንዴት ነሽ "
" አለሁ "
" ምን እንተባበር "
" ምንም " መሬት መሬት እያየች
" ግዴለም | ነፃ ሁኚ ። የሆንሽውን ንገሪኝ። ከሀኪም ምንም የሚደበቅ ነገር
የለም እሺ "
" እሺ "
" ምንሽን አሞሽ ነው "
" አልታመምኩም " ፍርሃቷ ሆስፒታል የመጣች ታካሚ ሳትሆን | የተማረከች
የጠላት ወታደር ነው ምትመስለው
" ታዲያ እዚህ ለምን መጣሽ ሜሪ "
" መውለድ አልቻልኩም "
" ታዲያ ይሄ እኮ አያስፈራም ። ምን ያህል ጊዜ ሞከርሽ ለመውለድ "
" አልሞከርኩም " ግራ መጋባት ጀመርኩ
" ባለትዳር ነሽ ? "
" አይደለሁም " ለምን እንደሆነ አላውቅም ። ልቤን ግን ደስ አለው ። እንኳን ባል አልኖራት
" ምን ያህል ጊዜ ግንኙነት አድርገሻል "
" ድንግል ነኝ " ቀጭን የእምባ መልዕክተኛ በአፍንጫዋ ጠርዝ በኩል አሳብራ ከናፍሯን ሰንጥቃ ገባች ። ከንፈሮቿ ለመርገብገብ ያሰፈሰፉ የቢራቢሮ ክንፎች ነው ሚመስሉት ነርሷን በምልክት ጠራኋትና በቀስታ ወደሳይካትሪ ክሊኒክ ሊንክ እንድትደረግ
ስነግራት ማሪያማዊት ተስፈንጥራ ተነሳች ። " አልሄድም | ሁላችሁም የአዕምሮ ህመምተኛ ነው ምመስላችሁ " ስታጉረጠርጥ የእቴጌ ጣይቱ አይን እንደሷ አያስፈራም ! ያ ሁሉ አይናፋርነት እንደመስከረም ዝናብ ተንቸፍችፎ በነነ ። ስትጮህ ራሱ ለጠብ ሳይሆን ለማህሌት የተቀለፀ ድምፅ ነው ያላት ብቻችንን ማውራት እንደምትፈልግ ስትነግረኝ ሲስተር በሩን ከፍታ ወጣችላት ።
ከዛ በኋላ ማውራት የጀመረች የእኔ እምባ ከአይኔ ጋር ሲተናነቅ ነው ያቆመችው ቀሚሷን ከፍ አርጋ አሳየችኝ ። ነዘረኝ ። የድንጋጤ ንዝረት ። በህይወቴ እንደዛ ደንግጬ አላውቅም ። ብዙ አሰቃቂ ነገሮችን አይቼ አውቃለሁ ። እንደዚህ ግን ተሰምቶኝ አያውቅም ማርያማዊት ወንድም | ሴትም ናት ። ሁለቱንም የመራቢያ አካላት ፊትና ኋላ
ተሰልፈው አየኋቸው ። እሷ ስሜቴን ለማንበብ አይኔ ላይ አፍጥጣለች ። የመሳቀቋ መጠን አባቷ እናቷን ሲደበድብ የምትመለከት ህፃን ልጅ ነው ምትመስለው
" ማርገዝ እችላለሁ ዶክተር ? "
አዕምሮዬ ውስጥ መልስ ሳይሆን ጥያቄ ነው ያለው
" ከማን ? "
ብዙ ብዙ አወራችኝ ። መውለድ ካልቻለች ራሷን ማጥፋት እንደምትፈልግ , በህይወቷ ከልቧ ስቃ እንደማታውቅ | እንዲህ አይነት ልጅ መውለዱን ሲያቅ
አባቷ ከእናቷ ሸሽቶ እንደጠፋ | እናቷ ከሰው ደብቃ ብቻዋን እንዳሳደገቻት | አጎቷ ሊደፍራት ሞክሮ በድንጋጤ ራሱን እንደሳተ | አጎቷ ይሄን እውነት ከሚያውቅ ሺ ወንዶች እየተፈራረቁ ቢደፍሯት ትመርጥ እንደነበር | ከአዲስ አበባ ሸሽታ
የማያውቋት ሰዎች መሀል ለመኖር ሶዶ እንደገባች | ከሶዶ ሀዋሳ ድረስ በማያውቃት ሀኪም ለመታየት እንደመጣች | ሰይጣን ክፉ እንደሆነ | ሰዎች ከሰይጣን በላይ ክፉ እንደሆኑ | እግዜር ከሁሉም በላይ ክፉ እንደሆነ | ማርገዝ ከቻለች አንድ ወንድ ጨርቅ እስኪሆን አስክራ አብራው ማደር እንደምትፈልግ | ማንም ሰው እንዲያውቃት እንደማትፈልግ | ሰው ይሄን ሚስጥሯን ከሚያውቅባት እንደጴጥሮስ ዘቅዝቆ ቢሰቅላት እንደምትመርጥ | ከእናትና አጎቷ ቀጥሎ ይሄን ሚስጥር ያካፈለችው ሶስተኛ ሰው እኔ እንደሆንኩ ምንም ከማለቴ በፊት እያለቀሰች ክፍሉን ለቃ ወጣች። ሲስተር ቀስ ብላ ገባችና መስማት ማልፈልገውን ነገር ነገረችኝ
" ዶክ ይህቺን ልጅ ሀገር ምድሩ እኮ ነው ሚያቃት ። ወንድአገረድ ናት ይላሉ "
ከፋኝ 😟

[ነጋቲ]

@wegoch
@wegoch
@paappii
ልብምታት

°°ከጥቁርና ነጭ ማስታወሻ የተወሰደ°°

በዘመነ ቁንጣናም ተወልዶ መሞት እንዴት ይቀፋል? አስተማሪ መሆን
እንዴት ይቀፋል? ነጭ ጋውን እንዴት ያስጠላል በማሪያም? አንዳንዴ ነጭ
ጋውኔን ተጣብቆ አልላቀቅ እንዳለኝ ወንድ አየዋለሁ... ከኀላዬ ሞልቶኝ...
አንገቴንም... ደረቴን ይዳብሳል... ወርዶ አይወርድም... ከባቴ ነው
የሚመለሰው... በአረማመዴ ልክ ይራመዳል... ሲቆሽሽ አውልቄ የምጥለው
ልፍስፍስ ትንፋሻም... አየው አየውና ንፁህነቱ ይጠፋኛል! በያዝኩት ብዕር
ላዩ ላይ የሆነኛ ፅሁፍ እጭራለሁ... ቆሸሸ ማለት ነው? እና ምኑን ንፁህ
ነበር? ንፅህና ያለመቆሸሽ ዋስትና ከሌለው ምን ያደርጋል? ሲገባኝ ግን
ንፁህ ማለት ቆሽሾ የጨረሰ ነው... ከዚያ ወዲያ የማያድፍ ፍፁም፡፡
የንፅህና ጥጉ እስከመጨረሻው በማደፍ መዝለቅ ነው፡፡
ለዚያ ነው እንከን የለሽ ወንድ አልወድም... መስለው ሊያጭበረብሩኝ
ሲጥሩ ኦቾሎኒ የሚታክል ጢኒጥዬ ልቤ በሳቅ ትነጥራለች፡፡ ከሚያበራ
ንፁህ አይን ስር ያሸመቀ ስድ እይታ ማውጣት እችልበታለሁ... ከሚያምር
ከንፈር እና መልክ ላይ የጥቁርን ጥላ የሚመስል... ከመጥቆር የጠቆረ
ማንነት አላየሁም? ካልካድኩ የጠለዘኝ ብዙ ነው... ምን አስካደኝ? እሱ
እሱ ተደምሮ እዚህ ላይ የደረስኩ እኔው ተመራማሪ እኔው መመራመሪያ
የሆንኩ ነገር ነኝ፡፡


ስንሸዋወድ የሚነጋ ነገ ላይ ነቃሁ! ሞሽላቃ ፊት ነው የማየው... ሁሉም!
ሌላውን አይደለም ራሳቸውን ሰርቀው... እኔነታቸውን ገድለው... ራሳቸው
ላይ አመንዝረው... በራሳቸው ቀንተው... ራሳቸውን ዋሽተው... ከራሳቸው
ውጭ አምልከው... ሲያበቁ... ጥቁር ሰይጣንን ለመሸሽ ነጭ እግዜር ጋር
የሚሄዱ... ከአንዱ ሲጠጉ ከአንዱ የራቁ የሚመስላቸው ፃድቃን መሀል
ራሴን ማየት እወዳለሁ፡፡
ወደ ቤተ ክርስቲያን ልሄድ ነው... በሩ ጋር ደርሼ ልስም፡፡ ስስምስ? ላብ
ያጠቆረውን ደጀ ሰላም... ሁሉ የሳመውን ስስም... የማልስመው የለም!
የማይስመኝ የለም! እግዜርን የወደደ ይወደኛል... የተመኘኝንም
የተመኘሁትንም... የናኩት የናቀኝ... ማንም ሳያውቅ... እኔና እግዜር ብቻ
የተመሳጠርን አይነት፡፡ ደጋግሜ ስማለሁ...
ደጀ ሰላም ላይ የተሳለ ስንት ከንፈር አለ? ለእኔና ለእግዜር የሚታየን...
ለማንም የማንናገረው... አፋችንን ሸፍነን ወዳጅኛ የምንስቅበት አሳሳም፡፡
ልስም ነው የምሄደው! እግዜርን አይደለም! ህዝቡን... ምናልባት አንድ
አለም የሚያክል መዝገብ ይኖራል... <ከመ ወከንፈር ውስጠ ልብየ
አለሙ> የሚል ርዕስ ያለው፡፡ ከልብ የተሳሙ ከንፈሮች ዝርዝር እንደ
ትውልድ ቆጠራ የተፃፈበት... ልክ አብርሀም ይስሀቅን ወለደ... ይስሀቅ
ያዕቆብን ወለደ አይነት አወራረድ የሚወርድ፡፡ እመኑኝ እሩቡ የኔ ስም ነው፡፡
ሊያ... ሊያ... ሊያ... ሊያ... የሚል፡፡ ቁልቁልም የሚፃፍ... ፀሀፊው <በአት>
የሚባል አንድ እጅ ያለው የማይበር መልአክ ነው፡፡ ይሄንን አስብና
የመጃጃሌ ነገር ገርሞኝ ፈገግ ስል አንዱ ደግሞ ሲያፈጥብኝ አየዋለሁ...
ነጭ እግዜር ሲቀርቡ ጥቁር ሰይጣን አይሸሽም፡፡ ይልቁኑ ከቀረበን በላይ
ይቀርብና በቀዝቃዛ ምላሱ ግንባራችንን ይልሳል፡፡ ይሄ ልጅ ባየኝ አይን
ብዙዎች አይተውኛል... መንገዱን አውቀዋለሁ... ስሄድ እንደሚከተለኝ...
መጨረሻውንም ጭምር... ሲኦል እሳት መሆን የለበትም! የሚሆነው
በሚታወቅና በሚደጋገም አለም ውስጥ መጨመር መሆን ነበረበት፡፡
በስልችት እሳት...


ሲራክን ሳየው ቆንጆ አይደለም... ላገኛቸው ከምችላቸው ወንዶች ምኑም
ነው እሱ... ጫማ የማይቀይር መናጢ ነው ሲጀመር፡፡ እና ለምን
ወደድኩት? እኔና እሱ ግልባጭ ነን... ተቃራኒ ነን! ያልሆንኩትን ነው...
ያልሆነውን ነኝ...
የመበላለጫ ምክንያቶቻችን ሲቆጠሩ እኩል ካልመጡ ልቀጣ፡፡
ግድ የለሽነቱን ወድለታለሁ፡፡ የስልችት ፍዘቱን... ሳስተምር እየነቃ የሆነ
ነገሬን ያያል...
<የሆነ ነገር> ግን ምንድነው?
የአካል ስም ከሌለው የሆነ ነገር እንዴት existence አለው ልንል
እንችላለን፡፡ ካለውም ደግሞ የማንጠራቸው ግን ያልተስተዋሉ እልፍ
ስሜቶች የሉም? አሉ አይደል? እነሱን ያስተምረኛል ሲራክ፡፡
በየ አስቀያሚነት ውስጥ... በየ ማስጠላት ውስጥ ያለ ህይወት ነቃቅላ
የጨረሰችው ውበት ይታየኛል፡፡
እውነት ፊት ለፊት ሲታይ አይስብም! በቀዳዳ በኩል እንጂ... በጨረፍታ
ነው ውበት መልኩ የሚጎላው... ግልፁማ ግልፅ ነው... ወደ የት
ይመራል? መልስ ያለው ጥያቄ ጥያቄነቱ ምኑ ላይ ነው?


የህላዌ ጉዞ ወደ ምንምነት ነው... ወደ ኪሳራ ቀስስ እያለ ይጎተታል...
ከቀን ወደ ቀን ይጓዛል... ከውበት መልክ ላይ አንድ ፍሬ እየነቀለ... ከውብ
እኛነታችን አንድ እርምጃ እያራቀን... እየቀነሰን...፡፡
ይህች አለም ውብ ታሪክ የላትም! ውቦችን የማጥፋት ታሪክ እንጂ!
ካበቀለችው ውበት ይልቅ የምትቀጥፈው እልፍ ነው... ጉዞዋ ወደ መርገፍ
ነው!
(ቆንጆ ነበረች...) ጠዋት ነበረች! በቅንጣትነቷ ውስጥ መግዘፍን
ታውቅበት ነበር ይሉኛል?


@wegoch
@wegoch
@wegoch
"ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል እኔ ግን ወሎዬ ይግደለኝ እላለሁ ብዙ ጊዜ:
.
.ወሎ አንድ እስላም አንድ በግ ያርዳል አርዶ ክርስቲያኑ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይላል እርሱ ቢስመ አላህ ኢረ አማን ኢረ አሚን ..
.
አንድ ቃል ነው በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንደ ማለት ነው።
.
አንዱን በግ አርደው ይሄ በወዲህ በኩል ይጠብሰዋል ያም በወዲያ በኩል ይጠብሰዋል ከዛ በሰላም በፍቅር ይመገባሉ: ይሄ በየትም ሀገር ላይ የሌለ ብስለት ነው "

(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን)
@wegoch
@wegoch
@poem_with_mela
በየነ ከሰሞኑ ምን ሆነ?

(በእውቀቱ ስዩም)

(ይህ ፅሁፍ ካስራ ስምን አመት በታች ለሆኑ አንባቢያን እርም ነው)
እኛ ኮረና ፈርተን ባደፈጥንበት ጊዜ ጉዋደኛችን በየነ የገነት አበባ
የመሰለች ልጅ ጠበሰ ፤ ልእልት ትባላለች! ለሁለት ወራት ያክል ደጅ
ካስጠናችው በሁዋላ ድንግልናዋን ሰጠችው፤ ውሸቴን ነው! ድንግልናዋን
የነበረበትን ቦታ አስጎበኘችው::
ከዚያ ጠፋች፤
በስንት መከራ እንደገና አገኛት፤
“በዩ ! ግልፅ እንድሆንልህ ትፈልጋለህ?”
አለቺው ፤
“ አዎ! “
“ በጣም በጣም ግልፅ? ”
“አ..ዎ “
አለ ልቡ እየፈራበት
“ የምኝታው ነገር ይቅርብን! አልቻልክበትም ”
‘ እስካሁን እንዳልጎዳሽ ብየ ለኮፍ ለኮፍ ነው ያደረኩሽ ፤ አሁን አንድ
እድል ብቻ ስጭኝ! ሌቱን ሙሉ በደስታ ላስለቅስሽ” አለ በየነ በልምምጥ!
“ ርግጠኛ ነህ?”
“ አቡነ ዘራብሩክን! ለክፉ ቀን ቆጥቤው ነው እንጂ የፍቅር ሸማኔ ነኝ”
“ እስቲ እናያለን! ”
ከዚያ ራት በሉ ፤ ተጫወቱ፤ ወይን ጠጡ፤ ሶፋ ላይ ተሳሳሙ! በየነ
ከራባቱን አንስቶ ወረወረ፤ ሸሚዙን አውልቆ አሽቀነጠረ፤ ለመጀመርያ ቀን
ውሃ ዳር የቆመ የዋና ተማሪ መስሎ ርቃኑን አልጋው ዳር ተገተረ፡፡
ልእልት ፤ አልጋው ላይ ጋለል ብላ ፤ አንድ እግሩዋን ወደ ምእራብ አንድ
እግሩዋን ወደ ምስራቅ አሰማርታ የየወፍ መንደፍያ ባላ መስላ
ጠበቀችው፡፡
በየነ ለሰኮንዶች ያክል ወልመጥ ወልመጥ አለና እንደ ተወጋ ሰው
አአአአአአአ ብሎ ደረቱዋ መሀል ተገነደሰ!
በረረረረጂሙ ተነፈሰችና " it is ok " አለቺው፤
በረጅም ትንፋሽዋ ውስጥ ካዳመጠው ቅሬታና ብግነት አንፃር it is ok
የሚለው ቃሉዋ የሚያፅናና አልነበረም ፤
በየነ ለጥቂት ደቂቃ ያህል ድምጡን አጥፍቶ ከቆየ በሁዋላ ፤ አንጀት
በሚበላ ድምፅ እንዲህ አለ፤
“ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ፤ የሰራ አከላቴን ሰቅዞ ይዞት ነው እንጂ፤
በደናው ቀንማ በድቼ በድቼ እማባራ ሰው አልነበርኩም”

@Wegoch
@Wegoch
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 5

በህይወቱ እንደዚህ በፍጥነት ሮጦ አያውቅም ድካሙ የታወቀው የበገናው ድምፅ የሚሰማበት ቦታ ላይ ሲደርስ ምንም ሰው አለመኖሩና የበገናው ድምፅ የወጣው ከክፍሉ ካለው ትልቁ የድምፅ ማጉያ መሆኑን ሲረዳ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግራ ገባው ሙሉ ለሙሉ የማዕከሉ ሀይል እንዳልተቋረጠ ሲረዳ ከቅድሙ በላቀ ፍጥነት ወደ ሀይል ክፍሉ አመራ ብዙዎቹ የተመደቡት ጠባቂዎች አልተረጋጉም አሁንም የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ለማወቅ ወዲ ወዲያ ይላሉ
ጴጥሮስ ወደ ሀይል ክፍሉ የሚወስደውን ኮሪደር በፍጥነት አቋረጠ በሩን በርግዶ ሲገባ የእጅ ሽጉጡን ከመቅጽበት አውጥቶ ደቀነ በያዘው የእጅ ባትሪ ሙሉ ክፍሉን ቃኘ አንዳንድ የሀይል ቆጣሪዎች በርተዋል ሌሎቹ ግን ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል ጠጋ ብሎ የጠፉትን ቆጣሪዎች አበራ ወዲያው ያለበት ክፍል መብራት በራ በክፍሉ ውስጥ የሚገኙትም ማሽኖች መስራት ጀምረዋል ሀይሉን ይመልስ እንጂ ወደ ውስጡ የገባውን ብስጭት እንዴት መመለስ እንዳለበት አላወቀም
ሲበር የመጣበትን ኮሪደር እያዘገመ አቋረጠው ሙሉ ለሙሉ የማዕከሉ ሀይል ተመልሷል ዘግይተውም ቢሆን ተጨማሪ ሀይሎችና የሀይል ሰራተኞች በማዕከሉ ተገኝተዋል
ጴጥሮስ ወደ መሀከለኛው ክፍል ሲገባ ያየውን ነገር ማመን አቅቶታል ጠርጥሮት የነበረው ነገር ተከሰተ ዛሬም አነስ ያለች መጽሀፍ ቅዱስና ያቺ ትንሽ ሳንቲም ተቀምጦ አገኘ ቀና ሲል ከበገና ማዕከሉ የሚገኘው ባለ በሩ በገና ተከፍቶ አጊንቶታል ርዝመቱ እስከ 8 ሜትር ድረስ የሚጠጋው በገና አነስ ያለች በር ነበረችው ከበሯ ላይ
አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀሉ መዝ 42/43-4
የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበታል ጴጥሮስ በውስጡ ምን እንደሚያስብ ባያውቀውም ከተከፈተው በር ውስጥ የተወሰደ አንድ ነገር እንዳለ አውቋል የሀይሉ መቋረጥ እንደተፈጠረ በተነሳው ግርግር ውስጥ የተፈፀመ ስህተት እንደሆነ ገብቶታል አይኖቹ ደም ለበሱ
ማዕከሉን የሚያናውጥ ዜማ መሰማት ጀመረ ጴጥሮስ ሚሆነውን ለማወቅ አልቻለም ጆሮዎቹ ግን ዜማውን መስማት ጀምረዋል
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
ዜማው ያስፈራል በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ዛሬ ሌላ ያገኘው አዲስ ነገር ቢኖር ይህንን ዜማ ነው በፍጥነት ማዕከሉን ለቆ ወጣ የማትረባ የሚለው ድምፅ ከልቡ ወደ ጭንቅላቱ ሺ ጊዜ ይመላለሳል

ሁለቱንም ዜማ የከፈቱላችሁ ሲገቡና ሲወጡ ፍንጭ ላለመስጠት ነው አላስተዋልክም እንጂ ሁሉንም የካሜራ ቅጂዎች ብትመለከታቸው ኖሮ ተመሳሳይ ወዴ በሁሉም ቦታዎች ላይ ተጠቅመዋል መጨረሻ ላይ የሰማኸው ዜማ በሁሉም ዝርፊያ በተፈፀመባቸው ማዕከሎች ውስጥ ተቀድቶ ተቀምጧለሰ ከመለከለኛው ማዕከል ውሰጥ ያስቀመጥካቸውን 5 ጠባቂዎች ከፊት ለፊት ማንሳት ነበረብህ ደሞ ጥቅሱ ምን እንደሚል አንብበኸዋል ከጀርባው ሆና ብዙ ብታወራለትም ጀርባውን ሰቶ የለኮሰውን ሲጋራ ጦፎ ይምገዋል አይኖቹ ቅድም ሲፈልጓት የነበረችውን ሶልያናን ለማየት ፈልገዋል ዞሮ ተመለከት የለበሰችው ጥቁር ባርኔጣ አይኖቿን ሸፍኗቸዋል
ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው እንደ ሰማይ ጸዳል ያበራሉ
ዳን 12:13
የመጽሀፍ ቅዱሱ ጥቅስ እንዲህ ነው ሚለው ከኛ በላይ ብዙ እንደሄዱ ሊነግሩን ፈልገዋል አስተውለከው ከሆነ አንድ ሌላ ጥቅስ ጨምረውበታል
ጥበብ ጻድቅ መሆኗ በስራዋ ተረጋግጧል
ማቴ 11-19
መጽሀፍ ቅዱሱን ስመረምር ያገኘሁት ጥቅስ ነው ንቃ እንጂ ጴጥሮስ ፈዞ ሚመለከታትን ሰው ጮኸችበት እየሰማት እንደሆነ ቢያውቅም የሆነውም የነገረችውም ነገር አስገርሞታል 40 ቁጥርን ለምን ዘለልሻት አላት ስቦ ያስገባውን የሲጋራ ጢስ መልሶ እያወጣ
ነገሩ ያስደነገጣት አይመስልም ያልደረስኩበት አንድ ነገር ስለነበረ ነው ነገ ጠዋት ሁሉንም እነግራችኋለሁ 6 ቁጥርን ደሞ አንተ ረስተሀታል መሰለኝ አለችው የምፀት ሳቅ ስቃ ጥሏት ሊሄድ ወሰነ....

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
"መጻሕፍ የሚነበበው የተለያየ የሰው ልጅ ሐሳብ ለማግኘት ሲባል ነው። ኒውተን ምን አለ? ፓይታጎረሰስ? እዩለርስ ምን አውጠነጠነ?…አደራጅቶ ከማሰብ ውጪ ዕውነት ለተመረጡ ሰዎች አትሰጥም። ከአንድ አንባቢ የሚጠበቀው የተቃረኑ ሐሳቦች የሚኖሩበት ሰፊ ልቦና ብቻ ነው።"
.
.
.
"ዕውነት ልክ ከአፈር እንደሚገኝ ወርቅ ከሰዎች ሐሳብና ከልምድ ዕራስህ የምታነጥረው ዕውነት ነው። ልብ ብለህ ከሆነ ኒውተንና ኢዩለር ይሄንኑ በአንድ መንገድ ገልፀውታል። ከተቀረው ሰው የተለየ አሻግሬ የማይበትን ቁመት ያገኘሁት ያለፉት ጠንካራ ሰዎች ትከሻ ላይ በመቀመጤ ነው ብለው ነበር። የራስህን ዕውነት የእነሱ ሐሳብ ትከሻ ላይ ሆነህ ለመመልከት መጣር…"



"የብርሐን ፈለጎች" በዓለማየሁ ገላጋይ (171/2)
@wegoch
@wegoch
አሁን እኔና አንቺ መደበር ነበረብን ዕድሜያችን ተደምሮ እንኳን አንዲት ሴት
Menopause ላይ የምትደርስበት ዕድሜ የለንም'ኮ። ምንድነው ሁላችን
የደከምነው? መች ኖርን ገና? አማኞች ልክ ይሆኑ የሚያስብል መንፈሳዊ
ካልሆነ ከምንም የጋራ የማይሆን ጫና አለብን። ያኔም ወጣት እንዲህ
ነበር? መጎርመስ ፈልጌ ነበር'ኮ፤ እንደ ማሙሽ ፀጉሬን ማሳደግ፤ እንደ
ፋሲካ ሙሉ ሱሪዬን ከጉልበቱ በታች ቀድጄ ግሊሲሪን ተለቅልቄ አቧራ
እየተጠነቀቅኩ መሄድ፤ ሳይሞቀኝ ደረቴን ከፍቼ ድድ ማስጫ መቀመጥ፤
በበራችን ላይ ያልፉ እንደነበሩ ሁለት ቀያይ ጥንዶች ደግሞ የወደድኳትን
ወገቧን አቅፌ ሰዉን ረስቼ ከንፈሯን እየሳምኩ መሄድ። ለማደግ እንዴት
ቸኩዬ እንደነበር'ኮ። ሲያዝኑ አናያቸውም ነበር ይሆን ወይንስ ጨርሶ
አያዝኑም ነበር? አሁን እኛን የሚያዩ ልጆችስ ሲያድጉ እንደኛ መሆን
ያምራቸው ይሆን? ልጆች ከዕድሜያቸው ፈጠን ብለው እንደትልቅ አክት
ሲያረጉ ልነግራቸው ልጮህባቸው ያምረኛል። "its a trap
motherfuckers enjoy ur fuckin ልጅነት" ልላቸው እፈልጋለሁ። ግን
ያኔ እንደዚ ሲሉኝ ሰምቼ ነበር? ቀደም ብዬ አቧራ ላይ መንደባለል
አላቆምኩም? ሚኒስተሪ ሳልፈተን ደስ ያለችኝ የመሰለችኝ ሴት
አልጠየቅኩም? ሴጋ ምን እንደሆነ ለማየት ትንሽ አልተጣደፍኩም? ዛሬ
የጓደኛዬ ታናሽ ወንድም እንዴት እየኖርኩ እንደሆን ገብቶት ነው "እኔ ከዚ
ሰፈር ልጆች ጋር መጃጃል ሰልችቶኛል እንዳንተ መሆን ነው የምፈልገው"
ያለኝ፤ ቦታ ቀይረኝ ልለው ያምረኛል፤ ነፍስ ስጠኝና እኔ ላይ ስታየው
ያማረህን ህይወት ኑረው። እኔ አንተን ሆኜ ትናንት የተሸወድኩትን
ላስተካክል ልለው ያሰኘኛል። ብዙ ኖሬ እመስላለሁ ይሄን ስል። ምንድን
ነው የሆንነው? በምንም የማንደሰት ሳቂታ ቆንጅዬ ትውልዶች የሆንነው?
"አንድ ጓደኛዬ ነበር ነፍሱን ይማርና" ማለት አልነበረብኝም'ኮ ስንት
እኩዮቼ ናቸው ጨክነው የሄዱት። ስንት የልጅነት ጀግኖቼ ናቸው ይሄን
ህይወት ጥለው የሮጡት? ከበላናቸው ልደቶች የሄድንባቸው ቀብሮች
ለምን በዙ? አሁን ባለሁበት ዕድሜ በነበሩ ጊዜ ቢደብራቸው ቢደብራቸው
ካርታ ተጫውተው ቀናቸውን ይሸውዱ ነበር'ኮ። ቀኖቻችን አልታለል ያሉን
ስለአዳዲስ ድብርቶቻችን እንኳን እንደ deja vu እየተሰማን ድብርትን ራሱ
ስንቴ ሰለቸነው? "ፈታ እንበል" ብለን ከጠጣን በሁዋላ የሚታዘበን
አለመኖሩን ስናውቅ የምናለቅሰው ለምንድን ነው? ምንድን ነው
የተፈጠረው?

©Tesfamariyam tafesse

@Wegoch
@Wegoch
@Mahletzerihun
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_፪_ቁጥር_፮_.pdf
6.1 MB
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

ቅፅ2- ቁጥር-6


በአውደብሩኀን ገፃችን ከ አርቲስት ዘሩባቤል ሞላ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

በርካታ አስገራሚ ፣ አስተማሪ እና አዝናኝ ፅሁፎች የተካተቱበ

ያንብቡት እና ብዙ ያትርፉበት📝

ቅንነት ድል ያደርጋል!

Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine
ራሺያ ውስጥ አንድ ሰነፍ ወታደር አለ፡፡ በቃ ኢላማውን ጠብቆ ተኩሶ መትቶ
አያውቅም፡፡ ሁሌ ይተኩሳል፤ ሁሌ ይስታል፡ ከእለታት አንድ ቀን አለቃው በጣም ተናደደና ሠራዊቱን ሰበሰበ፡፡
“ጓዶች፤ ይሄ ወታደር በተደጋጋሚ ኢላማውን ያልጠበቀ ተኩስ በመተኮስ
ይታወቃል፡፡ ወታደር አልሞ የጠላቱን ልብ በጥይት ካልነደለ ምኑን ወታደር ይባላል?” አለ የሰነፉን ወታደር ክንድ ይዞ፡፡ ተሰብሳቢው በሆታ “ኧረ አይባልም” አለ፡፡ “ይሄ ሰነፍ ስንፍናውን እንዳያጋባብን ሊቀጣ ይገባል፡፡ ቅጣቱንም ራሱ በራሱ ይወስዳል…” ይልና ራሱን እንዲያጠፋ ይወስናል፡፡
ሰነፉ ወታደርም ሰወር ካለ ስፍራ ይገባና ጥይት ይተኩሳል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ
ግን ሰነፉ ወታደር ይመለሳል - ወደ ካምፑ፡፡ አዛዡ ቱግ ብሎ “አንተ ራስህን አጥፋ ብዬህ አልነበረ?” ሲለው...
“ጌታዬ ራሴን ስቼው ነው!” አለ 😄

@wegoch
@wegoch
@paappii

@lencho_bedada
የሥዕል አውደርዕይ በ #አሊያንስ ኢትዮ- ፍራንሲስ
#ኃይሉ_ክፍሌ፡፡
አጋፋሪ፡ #ፍሬህይወት_ደምሴ፡፡
Art Exhibition @ alliance ethio-Francis
By Hailu Kifle
Curated by Frehiwot Demissie
.
.
@seiloch
@seiloch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል-6

ድንብሩ በጣዋቱም ቀጥሏል ሁሉም የምርምራ ክፍሉ ሀላፊዎች እጃቸውን አአፋቸው ሰቅለው ስለ ማታው ታሪክ ያወራሉ ከመገረማቸው በላይ አድናቆትም የሚገልፅ ንግግር ከአፋቻው ይሰማል ሶልያና ወደ ክፍሉ እስክትገባ ድረስ ወሬው እንደቀጠለ ነበረ ጥቁር ባርኔጣዋን እንዳወለቀች ቀጥታ ወደ ንግግሯ ገባች ከፊታችሁ ከቆምኩት እናተም ከፊቴ የተቀመጣችሁት በመጀመሪያ አንድ ነገር ማወቅ አለባችሁ ማንም በማንም ላይ እጅ የመቀሰር መብት የለውም ማታ ያደረግነው የሁላችንም እንቅስቃሴ ቢታይ ከሁላችንም ላይ ከእያንዳንዳችን ላይ ብዙ ጥፋት ሊገኝ እንደሚችል እወቁ በኛ ስህተት ብቻ ሳይሆን በዘራፊዎች የጭንቅላት ጨዋታ እንደተሸነፍን ማወቅ አለባችሁ አንድ መርማሪ የሚፈልገውን ወንጀለኛ ከፊቱ ሲያገኘው በፍጥነት ሮጦ እንደሚይዘው ሁሉ አንድ መርማሪ ከፊቱ ያለውን ዘራፊ በጭንቅላት ጨዋታ ጭምር መብለጥ ይኖርበታል አንዳንዴ እኮ መርማሪው ሳይለፋ መርማሪው ሽጉጥ ይዞ ሳይሯሯጥ በጭንቅላት ጨዋታ ብቻ አንድን ወንጀለኛ በራሱ ፍቃድ ወደ መርማሪው እንዲመጣ ማድረግ ይችላል ሀይል ሳይጠቀም ሚመጣን ዘራፊ በሀይል መያዝ አይቻልም ምክንያሁም ሀይል በነሱ ላይ እንደሚሰነዘር ስለሚያውቁ እነሱም ካለሀይል ሚመጡት መተው ሚመቱ አይነት ሰዎች አይደሉም እነሱ ለዛ እኮ ነው ደደብነታችንን ሚነግሩን
ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው እንደ ሰማይ ጸዳል ያበራሉ ዳን 12:13
ትናንት ጥለውልን የሄዱት ጥቅስ ነው በአንድ ትንሽ ዜማ እና ሀይል በማቋረጥ ይሄንን ሁሉ ሀይል ያታለሉት
ስራው ሚናቅ ቢመስላችሁም ማድረጉ ግን ከባድ ነው ጴጥሮስ እስካሁን ተበሳጭቷል አሁንም ግን ጆሮ ሰቶ ያዳምጣታል
ትልቁ እስክሪን በራ
ቀጣዩ ባለተራ ማነው ሁለት ቁጥሮች ወደ እስክሪኑ መጡ 6 እና 40 ቁጥር
ከትልቁ የስዕል አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ስድስቱ ጨረቆች የተሰኘው ስዕል ቀጣዩ አላማቸው ይሆናል
ጥለውልን በሚሄዱት ሳንቲም ውስጥ ጨረቃ የሚል ፅሁፍ እናገኛለን ሳንቲሙን በደንብ ስትመለከቱት 6 ጨረቆች ዙሪያውን ከበውታል ሁሉም አይኑ ከትልቁ እስክሪን ላይ ነው ይህ ስዕል ይሄን ይመስላል ስዕሉን ልብ ብላችሁ ስትመለከቱት ከምናየው ትልቅ የጨረቃ ምስል ሌላ ዙሪያውን 6ት ጨረቆች እናገኛለን ይህ ስዕል እድሜው ከ120 አመት በላይ ያስቆጠረ ነው አሁንም ግን ብርሀን ይሰጣል ስዕሉን በጨለማ ክፍል ብትመለከቱት በጣም የሚያበራ ሆኖ ታገኙታላችሁ ዛሬ ሀይል እንደማይቋረጥ አምናለሁ ንግግሯን ሁሉም የተረዱት ይመስላሉ ዛሬ እርምጃቸው ሁሉ በማስተዋል እንዲሆን ነግራቸዋለች ወደ ጳውሎስ ተራመደች የስዕሉ አዳራሽ የሲጋራ ጭስ አይቀበልም በጣም የሚረብሽ ድምፅ ልንሰማ ስለምንችል ሲጋራ ይዘህ እንዳገባ ከስዕሎቹ ነው ነየተነገረኝ ፈገግ ብላ አለፈችው ከነጋ እሱም ፈገግ አለ
የስዕል ማዕከሉ ዛሬ ስራ አይሰጥም ከስዕል ማዕከሉ ጀምሮ ዙሪውን በሙሉ ከተፈቀደላቸው ሰዎች በስተቀረ ማንም አይንቀሳቀስም በሁሉም ክፍሎችና ኮሪደሮች ጭምር ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉ ሰዎች ተመድበዋል ጳውሎስ ዛሬ ወደ ሚጠብቀው የስዕል ቦታ አመራ እውነትም ውብ ነው የስዕል አድናቂ ባይሆንም ተገዶም ቢሆን ስዕሉን አድንቋል ዛሬ ይሄንን ስዕል ከእጁ ማንም ሊወስድ እንደማይችል አምኗል

እንደተለመደው ከውሀው ጉርጓድ ዙሪያ ተሰብስበዋል ጨረቃዋ ነገ ትጠፋለች ዛሬ ግን ጨረቃ ብጠፋባትም ምትፅናናበትን ምትኳን ስለምታገኝ ተደስታለች ጨረቃዋን እያየች አንቺንም ቢሆን መስረቄ አይቀርም አለቻት ምቾት ተሰምቷታል ጥሩ እቅድ እንዳወጣች አውቃለች በእጇ የያዘችው ትልቅ ስዕል ላይ የጨረቃ ምስል ይታያል እቅዷ ተሳክቶ በውሸት አስላ የያዘችውን ስዕል ዛሬ በእውነተኛው ቀይራ የራሷ ታደርገዋለች መጽሀፍ ቅዱሷን ገለጠች
''በጠባቡ በር ግቡ''፤ ምክንያቱም ወደ ፊት የሚወስደው በር ትልቅ መንገዱም ሰፊ ነው በዚያ የሚሄዱት ብዙ ሰዎች ናቸው
ማቴ7:13
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
ድምፃቸው ያስገመግማል ሁሉም ከጉርጓዱ ውሀ በእጃቸው ጠጡ ፀሎቱ አልቋል እንደተለመደው ተርታቸውን ይዘው ደረጃውን ወረዱ

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
እስኪ ተውኝ ፍቅር ድሮ ቀረ። አሁንማ አይስክሬም ይመስል የትም መላላስ
ብቻ ሁኗል። ሙዚቃችንም ቅጥ አጥቷል። ሳም ላርግሽ፣ ሳሚኝ ነው። ይህ
ነው የጥበብ ምች፣ እርቃኗን አብዳ ስትሄድ። ጥበብ እኮ እንደ ሀገር ቤቷ
ሙሽራ የተሸፋፈነች፣ ገልጠው ሊያዩአት 'ሚፈሯት 'ሚሳሱላት ነበረች።
ድሮ ፍቅር የሚገለጠው በቤቱ እቃ በቡኑ በፍንጃሉ፣ በአዘመራው በከብቱ
ተወክሎ ነበር። ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ይሆነኝ ዘንድ የጥንት ሙዚቃ
ልጋብዛችሁ።
*
እሱ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የደገኛ
በስንዴ ለውጭኝ ካንችው ማኛ
አንች ደገኛ። (ማኛ እንግዲህ ያ ድንቡሼ ገላ መሆኑ ነው)
*
እሷ
የማነህ ብልጣ ብልጥ ቆዳህ ሞኝ መሳይ
ነጭ ጤፍ በስንዴ ልለውጥህ ነው ወይ?
ልትለውጥ ነው ወይ? (እዩትላችሁ ሴቶች'ኮ ፍትህ አያውቁም። አሁን
ምናለበት ሁለቱም የእግዜር ስራ ነው። ለምን ታወዳድረዋለች? ሲሰፈር
ሲለካ እኩል ነው!)
*
እሷ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የቆለኛ
ማኛ በጥሬ ምኔ ሞኛ
አንተ ደገኛ። (ይህም ያው ነው ሴቶች ብልጣብልጥ መሆናቸውን ማሳያ
ነው lol የለም ስቀልድ ነው ሲግደረደሩ ነው!)
*
እሱ
ስንዴ በነጭ ጤፍ መሳ ለመሳ ነው
መውቀጡ ካቃተሽ አለን የለመድነው። (ሃሃ እኛ እኮ ዘለን ወቀጣ ስንወድ
ማንም አይመስለን፣ አያክለን)
*
እሷ
ምነው መቸኮልህ ከወቀጣው ላይ
ቅድሚያ በገበያው ተስማምተናል ወይ? (ሂሂ 'ይችን ሙድ ለመሃሙድ'
አሉ። ፤ይሁን ፍቃድህ ፍቃዴ ነው' ማለቷ ነው። ቢጨከን ቢጨከን በወቀጣ
የሚጨከን ነውን?)
*
እሱ
ስንዴ ጤፍ ይበልጣል ማለቱን ትተሽ
እንዳ'ገር እንደወንዝ አምጭው ላምጣልሽ (ሃቅ ሸክሽኪ እንሸክሽክ ማለቱ
ነው)
ተው ተው
ተይ ተይ (እዚህ ላይ መጓተት አለ)
*
እሱ
ቆለኛ ደገኛ መባባሉን ትተን
ያለሽን ያለኝን በአንድ ላይ አስማምተን
ነጩን ጤፍ እንጀራ ስንዴውን ዳቦ አርገን
ብንበላ ይሻላል በአንድ ላይ ተስማምተን።
*
እሷ
አሁን ባልኸው ሃሳብ እኔም እስማማለሁ
ካልህስ በበኩሌ ዳቦም እወዳለሁ። (ሃሃ... እስከዚች ድረስ ነው ፈንጠር
ፈንጠሯ... ቀድሞም'ኮ ነግሯት ነበር። አመል ሁኖባት እንጅ)

©ጥላሁን ሀገሬ

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
አንዳንዴ ጋሽ ስብሐት ቤት ውስጥ ገነት ሲሆን ታየዋለህ ብር ሲኖረው
.
.
ወዲያው የስም ዝርዝር መጻፍ ይጀምራል : "ለእከሌ ይሄን ያህል ብር ፣ ለእከሌ ይሄን ያህል ብር ፣ ለእከሌ ይሄን ያህል ብር" ይልና
.
.
ሁልጊዜ ግን የሚረሳት አንድ ስም አለች. . . እርሷም የራሱ ስም ነች። እናም ለራሱ ይሄን ያህል ሳይል አከፋፍሎ ቁጭ ይላል።
.
.
አንዳዴ ደግሞ የራባቸው ደራሲያን ይመጣሉ : የኔ አይነት ስራ የሌላቸው ፣ በንባብ ላይ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ምናምን : እነርሱ ሁለት ዓይነት አቀባበል ነው ያላቸው በጋሼ ዘንድ
.
.
የመጀመሪያው "ቶሎ በይ እስኪ እግሩን ቶሎ ይታጠብ ፣ ምሳም አቅርቢለት" አብርሃም ይሆናል። ብላ ፣ ሚጠጣ ትፈልጋለህ ፣ ሚቃምስ" ይልሃል ብር ያለው ጊዜ
.
.
ብር የሌለው ጊዜ ደግሞ ሌላ ነው አቀባበሉ "እና እኔ እግዚአብሔር ነኝ እዚህ መጥተህ የራበው ፊት የምታሳየኝ ውጣልኝ ፣ ውጣልኝ ከዚህ ቤት" ይልሃል።
.
.
ምክንያቱም የለውማ !!
.........

(ደራሲና ኃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ አብሮት ከጋሼ ጋር በቆየባቸው ጊዜያት የታዘበውን የቅንነት መንፈስ በአንድ ቃለ መጠይቅ ከተናገረው በጥቂቱ)

@poem_with_mela
@wegoch
@wegoch
ካፌ ቶክ ልዩ የመዝናኛና የኪነጥበብ ዝግጅት ታህሳስ 30 በልዩ የገና መሰናዶ ይካሄዳል።

ወጣቶች ሀሳባቸውን በነፃነት ያንሸራሽራሉ ባለ ተሰጦዎች ስራዎቻቸውን ወደ ታዳሚው ያደርሳሉ ጨዋታዎችና ጥያቄዎች ያሸልማሉ።

ትኬቶች መሸጥ ጀምረዋል። ትኬቶቹን ለማግኘት በ0901118033 0932566694 እንዲሁም በ0922457627 ሀሎ ይበሉ።

የዝግጅቱ ቦታ ለትራንስፖርት አመቺ በሆነው በሜክሲኮ ቡናና ሻይ ካፌና ሬስቶራንት አንደኛ ፎቅ።

ሀሳቦች ያሸንፋሉ
ባለ ተሰጦዎች ይበረታታሉ!

@cafetokk
@getem
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 7

ጳውሎስ እንደዛሬው ተቁነጥንጦ አያውቅም ሆዱን ቆርጦታል ሲጋራ ካጨሰ ሰአታት አልፈዋል እጁን ይበላው ጀምሯል ጣቶቹን ወደ ኪሱ ሰደዳቸው ቀጥታ ወደ ጭንቅላቱ ሶልያና የተናገረችው ቃል አቃጨለበት አይኖቹ ትልቁ የስዕል አዳራሹን ቃኙ ሶልያና የለችም ስዕሎቹ ግን ቦታቸውን ይዘዋል
ቅር ብሎታል ደስ ያላለው ነገር አለ አንድ ሰው ከሩቅ ሲጠራው ተመለከተ አንድ ችግር እንደተፈጠረ አውቋል በፍጥነት ተራመደ ድንገት የስዕል ማዕከሉ የአደጋ ጊዜ አላርሞች መጮህ ጀመሩ ጳውሎስ እርምጃውን ገታ አደረገ በፍጥነት ወደ ስዕሉ አመራ በቦታው ይገኛል አይኖቹ ወዲ ወዲያ ይራወጣሉ ዛሬ መደናገር የለም ሁሉም በያለበት ቆሞ የሚሆነውን ይመለከታል
በአጠገቡ ከሚገኘው ትልቅ መስታወት ውስጥ አንዳች ነገር ሲወጣ ይታየዋል አይኖቹ ሙሉ በሙሉ በመስታወት ወደ ተሸፈነው ስዕል ላከ
ከመስታወቱ ውስጥ ቀስ እያለ ወደ ላይ የሚወጣ ጭስ ተመለከተ በፍጥነት የስዕል ማዕከል ተቆጣጣሪዎችን ጠራ ጭሱ ይበልጥ እየገዘፈ ስዕሉን ሸፈነው ይሄ ስዕል የራሱ የሆነ መግቢያ እንዳለውና ከመስታወት ውስጥ የሚወጣው ጭስ ስዕሉን ከአደጋ ለመከላከል የተገጠመ ሲሆን ውሀ ከመስታወት ውስጥ ካልገባ አልያም እሳት ካልተነሳ በምንም ታምር ይሄ ከመስታወት ውሰጥ የሚታየው ጭስ እንደማይወጣ ተቆጣጣሪዎቹ አስረዱት ያላቸው አማራጭ ወደ ክፍሉ መሄድ እንደሆነና መስታወቱን ምንም አይነት ጥይት ሊበሳው እንደማይችል ስለሰማ ወደ ተባለው መንገድ ተፈተለከ ከመስታወቱ የሚወጣው ጭስ ይበልጥ በዝቷል ስዕሉ ጭራሽ ሊታይ አልቻለም ጳውሎስ ከፊቱ ሚመራውን ጠባቂ እየከተለ ወደ ስዕሉ መግቢያ አመራ ከኋላው የሚከተሉትን መርማሪዎች ቦታ ቦታ እንዲይዙ ነግሯቸዋል ወደ መስታወቱ የሚያወጣውን ሊፍት ያዙ ጳውሎስ እንዴት የዚ መንገድ መረጃ እንዳልተሰጠው አላወቀም ወደ መስታወቱ ሲገቡ ስዕሉ ከቦታው ሳይጠፋ አገኙት ጳውሎስ ረጋ ብሎ መተንፈስ ጀመረ ማንም በመስታወቱ ውስጥ የለም
ወደ ማዕከሉ ተቆጣጣሪ ዞሮ ችግሩን ጠየቀው ካለ ምክንያት እንደዚ እንደማይሆን አስረግጦ ነገረው ጳውሎስ ከጆሮው ላይ የመጣው አሁንም የሶልያና ንግግር ነው
ሀይል እንደማያቋርጡ እርግጠኛ ነኝ ብላቸው ነበረ በፍጥነት የማዕከሉ ሀይል እንዲቋረጥ ተደረገ ጳውሎስ ያየውን ማመን አቃተው ያበራል የተባለው ስዕል ምንም አይነት ብርሀን አይሰጥም በፍጥነት ወደ መውጫው ተንደረደረ ሀይል መቋረጡን ሲያውቅ ወደ ታች የሚወርድበት ሊፍት እንደማይሰራ ተረዳ ያመለጡትንም ዘራፊዎች ሊይዝ እንደማይችል ገብቶታል በተመሳሳይ ስዕል ቀይረው ስዕሉንም ማረጋገጥ የሚቻለው ሀይል አጥፍቶ ጨለማ ውስጥ ስለሆነ በዚ ሀይል መቋረጥ ሰበብ የማምለጥ ዘዴያቸው እንደቀየሱ ተረዳ
መስታወቱን ነረተው የእጅ ባትሪውን አውጥቶ ስዕሉን ተመለከተው ብሽቅ ለራሱ ስድቡን ደገመው ከፊትለፊቱ በስዕሉ ላይ የተቀመጠውን ጥቅስ አገኘ
ሌሊቱ እየተገባደደ ነው ቀኑም ቀርቧል
ሮሜ13:12
ከጥቅሱ ላይ አይኑን የነቀለው ተቋርጦ የነበረው ሀይል ሲመለስ ነው ቀጥታ ወደ ማዕከሉ እንደተመለሰ የእጅ ስልኩን አውጥቶ ደወለላት ስልኳ አይሰራም እንደዘገየ ቢያውቀውም ሁሉም መንገዶች ላይ የፍተሻ ሀይሎች እንዲሰማሩ አዘዘ
የስዕል አዳራሹን ለቆ መዎጣት እንደጀመረ ጥቅሱን ብቻ አንብቦ መውጣቱን አስተዋለ ሳንቲሙስ በፍጥነት የወረደውን ደረጃ ወቶ ወደ ሊፍቱ አመራ ጨርሶ እንደገባ ምርመራ የሚያደርጉትን ባለሙያዎች አስቁሞ የተቀየረውን ስዕል ይመለከት ጀመረ ዳር ዳር ላይ ያሉትን የጨረቃ ትናንሽ ስዕሎች ሲፈትሽ አንድ ጎድሎ አገኘ ጠጋ ብሎ ሲመለከት 40 ቁጥር በግዕዝ ታትሞበታል የጠፋቻት ቁጥር አሁን እሱ አጊቶታል ረጋ ብሎ ማሰብ ጀመረ

ይቀጥላል....
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul Mekonnen 📷)
Art exhibition by #Fasika_Kebede
at fendika cultural center


ውሕደት የ ስዕል ትርኢት
#ፋሲካ_ከበደ
ታህሳስ 27 ቀን 2013 ከ ምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በካሳንቺስ #ፈንድቃ የ ባህል መዓከል

ትርኢቱ እስክ ጥር 11 የሚቆይ ይሆናል..

@seiloch
@seiloch
2024/09/23 23:20:16
Back to Top
HTML Embed Code: