Telegram Web Link
*Israel Ad fernando

Love has no boundaries
............. ደፂ በኢትዮጵያዊያን ብር ሊዝናና ወጀ ቻይና አቀና። ቻይናን ቀኑን
ሙሉ እየዞረ ይቺን ሀገር ከጀሌዎቹ ጋር አስተዳድሮዋት ቢሆን ኖሮ እንዴት
እንደሚግጣት እያሰበ ምራቁን ሲውጥ ዋለ። ሲዞር ውሎ ስለራበውም
ጓንዡ ከምትባል የቻይና ግዛት ከሚገኙ ምግብ ቤቶች ውስጥ ወደ አንዱ
ገባ። ገብቶም ምግብ ከሜኑው ላይ በግምት አዘዘ። የመጣለትም locust
ነበር ያመጣችለት አስተናጋጅ ቻይናዊ በጣም ውብ ነበረች። ደፂም ምንም
ለመብላት ቢፀየፍ አዳማዊ ባህሪው ተነስቶበት ለፍቅሯ ሲል በላ። ከስራ
ስትወጣ ጠብቆ አዋራት። ፍቅረኛው ከሆነች የራሷ ሬስቱራንት
እንደሚከፍትላት እና ለስራዋም ኢትዮጵያ ገበሬውን ያስቸገሩ አምበጦችን
እንደሚያመጣለት ነግሮ በጥቅም አሰራት። እስዋም በማድረግ አቅሙ እና
የትግል ታሪኩን ሰምታ ተማረከችለት።


ደፂ ደስታ በደስታ ሆነ የጥላሁን ገሰሰን "እሩቅ ምስራቅ ሳለሁ ጃፓኗን
ወድጄ..." የሚለውን ዘፈን ለ አብርሀም ገ/መድህን ከፍሎ "...ቻይናዋን
ወድጄ..." የሚል cover አሰርቶ ሌት ከቀን እሱን መስማት ሆነ ስራው።

ከእለታት አንድ ከወደ ቻይና ስልክ ተደውሎ በወቅቱ ከዶሮ በተነሳ ወረርሽኝ
ምክንያት እጮኛው እንዳረፈች ተነገረው። ደፂም ተሰበረ። ካፅናናኝ ብሎ
ለጌታቸው ደውሎ የተፈጠረውን አጫወተው ጌች "ድሮስ የቻይና እቃ
አይበረክትም ብሎ" አላገጠበት... ደፂ ሰው ለማሰር ካዘጋጀው ጨለማ
ክፍል ውስጥ እራሱ ገብቶበት ለብዙ ቀን በዚያ ቆየ።
:
:
ከዚ ሁሉ ጊዜ በኋላ Covid ከወደ ቻይና ተነስቶ ኢትዮጵያ ገባ። ህዝቡም
በበሽታው ተሸብሮ ጥንቃቄ አበዛ ከጊዜያት በኋላ ግን ጥንቃቄ ማድረጉን
አቋመ። ግን ከቻይና የተነሳ ወረርሽኝ ሰው እንደሚገል በሚወዳት ፍቅረኛው
ያየው ደፂ ሳይዘናጋ ማስክ እና ጉዋንቱን በሚገባ እስከ አሁን ያረጋል.....

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሰው የሚባል የለኝም ሲል "እኔ እያለሁ ብዬ ጓደኛ ሆንኩት። እያለቀሰ.. እየረገመ
...እያማ... እየጮሀ ..ዝም እያለ እየሳቀ ሁሉን አወራኝ። አልታዘብኩትም። ሁሉም
ላይ አንተ ልክ ነህ አላልኩትም። ልክ አይደለህምም አልወጣኝም። ነው ያልኩትን አወራሁ። ረሳ ተፅናና ማማረር ተወ "ነገ መልካም ቀን ነው ይል ጀመረ"
ተመስገን አልኩ። እንደ ጥሪው ደግሞ እንዳመጣጤ መገናኘታችን ሰመረ አልኩ። ደግሞ ለህይወት አንድ ጓደኛ አገኘሁ አልኩ። አሳቀኝ ተረዳኝ አሰበልኝ ደስ አለኝ።
.
ቆየን ቆየን ሀሜቱም ንዴቱም አለቀ ስለራሳችን ማውራት ያዝን እንዲህ
ብታረገው። እንዲ ብታደርግ። ይሔ ልብስ ያምርብሀል። ይሔ ጫማሽ ያምረኛል። ዛሬ ዘንጠሀል። ዘንጠሻል ....ግላዊነት የነገሰባቸው ሙገሳ አድናቆት ከላይ ጀመረ።
.
ማሰብ ጀመርኩ ወዴት እየሔድን ነው ? ያስብ ገባ። ፍቅረኛዬ ባረጋትስ? ከድሮ
ቦታችን ካፌ ተቀየረ ከድሮ በላይ አብረን ረጅም ሰአት እንቆያለን። የረባ ነገር
አይወራም። ድንገት ዝም ዝም ስንባባል ሁለታችንም በልቦናችን "ፍቅረኛዬ ቢሆንስ?" አይን ላይን ስንጋጭ መሽኮርመም የመድሀኒአለም ያለህ !
.
አንድ ቀን ይመችሽ እንደሁ ላውራሽ "ፍቅር ይዞኛል አለ" ክው አልኩ። ማን
ይረዳኛል እንዳንቺ? ማን ሰው አለኝ ? ጓደኛዬም ሚስቴም ሁኚ ሲል .. ቀድሞ
በልቤ ያወራሁትን ያወቀብኝ ይመስል አፈርኩ። ደነገጥኩ። ዝም ዝም እንሒድ
እሺ እንሒድ ወደቤቴ ሸኘኝ የመጨረሻዋ ቻው ላይ እወድሻለሁ ጨመረበት! እንዴት እንደሆነ አላቅም ያን ቀን አንድ ሰው አጣሁ። ያን ቀን አንድ ጓደኛ አጣ !
.
.
እወድሻለሁ ያለያያል ?! እወድሻለሁ አለያየን !

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Betelhem Tachbel
Forwarded from Ribka Sisay
ሊድ እና ሌንስ ፩.pdf
18.4 MB
ሊድ እና ሌንስ ፩ ................. በሚታየኝ እና ባስቀረሁት፤
በሚገባኝ እና ባሰፈርኩት፤
ክስተት እና ምስጠት መጠን... ................ @getem @seiloch @wegoch @ribkiphoto
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 1

ሁሉንም ትታቸው ወደ ውጪ ወጣች የገለጠችውን መጽሀፍ ቅዱስ በቀዩ ክር ምልክት ሳታደርግ ጠረቀመችውው ከአጠገቧ ያለውን የውሀ ጉርጓድ ተመለከተች እንደምትፈልጋት ሆናላታለች ክብ አይኖቿ ወደ ሰማዩ ተመለከቱ በጨረቃ ብርሀን አይኖቿም አበሩ ውስጧ የሆነ ነገር ሲብላላ ይሰማታል ደሟ ሲራወጥ ልቧም ፍጥነቷን ጨምራለች
በዚ ምሽት ጨረቃ ይበልጥ እንደምታግዛት አምናለች ሰማዩ ላይ ምንም ሊጋርዳት የሚችል ደመና አይታያትም ብርሀኗን ሊከልላት በአጠገቧ የሚያንዣብብ ነገር ካለ ጠርጋ ለማፅዳት ዝግጁ ነት በውስጧ ጨረቃ ነኝ ብርሀኔን ከመስጠት ያሰብኩትን ከማድረግ የሚያግደኝ ነገር የለም ቀዝቃዛውን አየር ማግ አደረገችው ብዙ ኮኮቦች ከሰማዩ ታዩት ዘወር ብላ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ጠራቻቸው ከኋላዋ ተኮለኮሉ አሁን እንደ ሰማዩ እኛም እናምራለን በውስጧ ምታወራውን ነገር ሰማዩም ሚሰማው ይመስል ምሽቱ ይበልጥ አማረ ሙሉ ጨረቃ ሙሉ ልብ ሙሉ ሰማይ ሙሉ ብርሀን ከፀጥታው የተነሳ የሁሉም ልብ ምት ይሰማል አንድ አይነት ምት አንድ አይነት ፍጥነት ቅዝቃዜው ሚያስቆማቸው አይመስልም አይናቸው ከሰማዩ ፈጧል ኮኮቦች ኮኮብ ያያሉ ጨረቃም ጨረቃን ታያለች አይኗን ነቅላ የዘጋችውን መጽሀፍ ቅዱስ ከፈተች አማተበች አይኗን ጨፍና እጇን ወደ ኪሷ ከታ ከእጇ ማይጠፋውን ሳንቲም አወጣች አይኗን ገልጣ መጽሀፉን ታነብ ጀመረ
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የላንም የለውም (ዮሐ15-13)
ይህን ሰማይ ካለጨረቃ አስቡት ጨረቃም ኖራ ካለ ኮኮብ አስቡት ይጠባበቃሉ አብረው ይታያሉ ጨረቃ የሆነ ነገር ቢደርስባት ልጆቿ ከዋክብት ዝም አይሉም ኮኮቦችም አንድ ነገር ቢደርስባቸው እናት ጨረቃ ዝም አትልም አለም ላይ ግዑዝ የተባለው ነገር ህይወት ላለው አካል ህይወት አይሰጥም ህይወት ያለውም ለግዑዙ ህይወት ሊሆን አይችልም ግዑዝ ለግዑዝ ህይወትም ከህይወት ያምራል እኛም ከእኛ ሌላ ማንም የለንም ከእናንተ አንድ ከሚጎል የኔ ህይወት ይጉደል የኔ ህይወትም ከሚጎድል የእናንተ ህይወት ይጉደል መጽሀፍ ቅዱሱ ተዘጋ አሜን የሚል ድምፅ አስተጋባ

ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት

ድምፃቸው ከነጎድጓድ ያስደነግጣል ዜማው ያስፈራል አንድ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሰው የሚዘምረው ይመስላል ጥቁር ባርኔጣቸውን አስተካከሉ በተሰበሰቡበት የውሀ ጉርጓድ ውስጥ የጨረቃዋን ነፀብራቅ በውሀው ውስጥ ይመለከታሉ መጽሀፍ ቅዱሳቸውን ከሸጎጡበት ቦርሳ ውስጥ አወጡ ሁሉም በአንድ ድምፅ
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (ዮሐ15-13) አሜን
ድምፃቸው ይበልጥ አስተጋባ መጽሀፍ ቅዱሱ ተዘጋ ከተሰበሰቡበት የውሀ ጉርጓድ በመዳፋቸው እጠለቁ ጠጡ በደተርታ ደረጃውን መውረድ ጀመሩ የጊቢው ፀጥታ ያስፈራል ተቃጥሎ ያለቀው እንጨት ጭስ ወደሰማይ ይወጣል የመኪና ሞተር ድምፅ ተሰማ ሁሌ ስህተት እነርሱ ጋር የለም መንገዱን ተያይዘውታል ጥቁሩ መኪና ቀዝቃዛውን አየር መቅደድ ይዟል መኪናው ውስጥ ያለው ፀጥታ ያስደነግጣል የምሽቱ ፀሎት ይበልጥ ግርማ አላብሷቸዋል አነስ ያለች የጃዝ ምት ያላት ዜማ ከመኪናው ትሰማለች
ሹፌሩ ቦታውን አውቋል ቅድም ያበራት የነበረችው መኪና አሁን በዝግታ የንቀሳቅሳት ጀምሯል
መቆሚያውን ይቃኛል
ከመኪናው የነበሩት ሰዎች አሁን የሉም ከህንፃው ውስጥ የአደጋ ጊዜ አላርም ድምፅ መጮህ ጀምሯል
ታላቁ የከተማው ባንክ የሚል ትልቅ ፅሁፍ ከህንፃው ላይ ይነበባል የጃዝ ምት ያለው ዜማ አልቆ ወደ ኦፔራ የተጠጋ ዜማ ከመኪናው መሰማት ጀምሯል
ጨለማው ዜማው የአላርሙ ድምፅ ተጨምሮ ምሽቱ አስፈሪ ሆኑዋል
ከህንፃው የሚጮኸው አላርማን ከመኪናው የሚወጣው ዜማ የገጠመ ይመስላል ብዙ ፍጥነቶች
ንዳው ከሹፌሪ ጎን ድምፅ ተሰማ
በጣቶቿ የዜማውን ድምፅ ከፍ አደረገችው

ህይወትስ ወዴት ናት ሰማዩስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው

ይቀጥላል.......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ሚስጥር_ኪስ
~
~
የፈዘዘ ጂንስ ሱሪ አነሳሁ... ለምን ዘንጣለሁ? ለቅሶ ቤት እየሄድኩ መሆኔን
ረሳሁት? መልበስ ግን አማረኝ። 'ቋ' ብዬ ብሄድ... እያሱ ነበር 'ቋ' ብለሽ
ነይ የሚለኝ። አዝኜም የሚያምርብኝ አይነት ብሆን... በስህተት ያማረብኝና
ልረዳው የማልችል ብመስል። ለበስኩት... ያምራል! ኢያሱ ይወደው ነበር
ይሄንን ሱሪ "ያ ነገር ተጨነቀኮ" ይለኛል። መስታወቴ ፊት ዞሬ ነገሬን
አየሁት ተጨንቋል። ኪሱ ጋር የእያሱ ሰፊ እጅ ስንቴ ጠብሶኛል...
የሚያመኝም አይመስለውምኮ ጧ! ያረገውና የጅል ፈገግታ ፈገግ ይላል።
ሲስቅ የታች ከንፈሩ ከላይኞቹ ጥርሶች ስር ስለሚወሸቁ ጅል
ያስመስለዋል። የከንፈር ቀለሜን አነሳሁ... ስቀባው አማረ ግን ደመቀ...
እንዲማ ሆኜ ብሄድ “ምን ልሁን ነው የምትለው?“ ነው የሚሉኝ... በጣቴ
ጠርጌ አደበዘዝኩት። ያልታቀደበት ማማር እስኪመስልልኝ ተጨነኩ...
ቢሆንልኝ ኢያሱ እንደሚወደው አይነት ሆኜ ብቀብረው። ከመቃብር ሳጥኑ
ውስጥ የሞኝ ሳቁን ሲስቅ አስቤው አሳዘነኝ።
~
~
ጫማዬ ያንቀራፍፈኛል... የተረከዜ ሹል ጠጠር መሀል እየተወሸቀ የዝነጣ
መንገዳገድ ያንገዳግደኛል። የተጠየፍኩ አይነት አረማመድ ያራምደኛል።
ቤቱ አልጠፋኝም። ከሩቅ ነው ቤቱን የጠቆመኝ ቆርቆሮዋም ሰፈሩን።
በዚሁ ሰፈር በእግሬ እያለፍኩ ነበር ... ያኔ ከተገናኘን ሁለት ወር ቢሆነን
ነው። ክላክስ ሰምቼ ስዞር ኢያሱ ነው። ሞኝ የሚያስመስለውን ፈገግታ ፊቱ
ላይ ዘርቶ ሲጠራኝ። ከሌሎቹ እሱ ይቀለኛል ቢያንስ የሚያወራው እውነት
ነው። ለእውነቱ አያሳንሰኝም... ከእኔ ጋር መሆኑን ሚስቱ ብትሰማ አንዴም
ሳይከራከራት ያምናል። ሚስትና ልጆች እንዳሉት አልደበቀኝም...
የተሰማውን ይናገራል። ውሸት አያውቅም... የሚደብቀው እውነት ነው
ያለው ኢያሱ።
"ነይ ግቢ"
"አንተ ጉደኛ ምን ታረጋለህ እዚ?"
"ቤቴ እኮ ያውና ጥቁር ብረት በር ይታይሻል?"
"እእእ"
"እሱ ነው። "
"ደፋር ነህ ባክህ። አሁን ለሚስትህ ቤትህ መጥቼ ጉድህን ብነግራትስ?"
"ምን ይጠቅምሻል?"
"አንተ ብር እንድትሰጠኝ ለማስገደድ"
"ስጠኝ ብለሽ አትጠይቂኝም ምን እሷ ጋር ያደርሳል?"
"እምቢ የለኝም ብትልስ"
"ቤቴም መጥተሽ ስትናገሪ 'እምቢ የለኝም' ነዋ የምልሽ"
ጥቁር ብረት በር ያለበት ቤት ውስጥ ድንኳን አለ... ከድንኳኑ የሚወጣ
"ህምምምምምምም" የሚል ድምፅ ይሰማኛል። በሩ ሙሉ ለሙሉ
ተከፍቷል... ኢያሱ ሲወጣ አልቃሽ እንዲገባ ይመስላል። ከሌሎች
ሀዘንተኞች ጋር ተቀላቅዬ ገባሁ... አብሬያቸው ተቀመጥኩ። ቅድም
ያልተሰማኝ ሀዘን አሁን ሆዴ ጋር አለ። "እያሱዬ" ብዬ ልጩህ? ሚስቱና
ልጆቹ ከሩቅ ጋቢ ለብሰው ፈዘዋል... አካባቢያቸው ቀና ያለ ሰው
አይታይም... ንግግር የለም። ሁሉም የሚጨንቅ መወዛወዝ በትንሹ
ይወዛወዛሉ። አውቀውት አይመስልም... የኢያሱ ጉድለት የፈጠረው ሚዛን
መሳት ይሆናል የሚያወዛውዛቸው። ሚስቱ ወፍራም ናት (እንኳን የታባቷ)
አዝናለች (ማዘኗ አናደደኝ)። ሰው ከቧታል... ብቸኛው እንደ ሰው የሚያየኝ
የነበረውን ኢያሱን ስትካፈለኝ የኖረች ዘጠዘጥ ነች። እሷም ጫጩቶቿም
ደበሩኝ... ከእነሱ በኋላ ባውቀውም በማፍቀር ህግ መቅደምና መዘግየት
የለም።
ከአጠገቤ እየቆረጠ የሚያየኝ ወጣት አለ... ወደ እኔ ዞሮ መልኩን ሳይጎዳ
ይነፋረቃል። እያለቀሰ እንኳን አይኑ ታፋዬ ላይ ይንከራተታል።
~
~
"ዝገኝ እንጂ?" ድግስ የሚጋብዝ ነው የሚመስለው። በትሪ የሚታደለው
ንፍሮ የመግባቢያ ርዕስ ስለሆነው ደስ ብሎታል።
"እሺ" ቆነጠርኩ
"ጋሼን ታውቂያቸዋለሽ?" አዎ የዚን ጅንስ ቂጥ በጥፊ ያሳሱት እሳቸው
ነበሩ ብለው ይገባዋል? በሆነ እግዜርኛ መመርመሪያ ቢፈተሽ ጉንጬ ላይ
ድንክ ፂሞቻቸው ቧጭረውኛል ብለው ቀባጣሪ ይለኛል። መስማት
አይደለም ማውራት ነው የፈለገው... ሰማዋለሁ ይሄንን ጩጬ።
"በአይን አዎ"
"እኔን ከልጅነቴ ያውቁኛል... ብዙ ተምሬያለሁ ከእሳቸው" ያላስተማሩህ
ስንት ቆንጆ ነውር አለ መሰለህ...
"ትግባባቸው ነበር?"
"በጣም! እህቴ ናት እሷ" ወደ ኢያሱ ሚስት ጠቆመኝ። የዚች ሴትዮ
ወንዶች እኔ አካባቢ ምን አይተዋል?
"ኦኬ"
"እንዴት ያሉ ሰው መሰሉሽ..." ለምን አይተወኝም? ኢያሱ ሲወራለት
አያምርበትም። የጓዳ ገድሉ አይስብም... ምኑም እሱን አይመስልም። ወይ
ቤተሰቡ ጋር ራሱን አይደለም ወይ የሞተው እያሱ ሌላ ነው። ይፈተሽ
ፈገግታው... ጅልነት ካለበት ራሱ ነው። ምን ይለኛል ይሄ?
~
~
ይሄ ልጅ ያወራልኝን እያሱ አላውቀውም። ሲጀመር ጋሼ ነው 'ሚለው...
ጋሼ ደግሞ እንዳወራልኝ ከሆነ የሰፈር አለጥላጭ ወጥ ነገር ነው። ኢያሱ
በትንፋሽ ቀለም የሰራውን መልኩን ይቦጫጭረዋል ይሄ ነፍስ ያላወቀ
ጩጬ። በእርሱ ቤት ጠበሳ ነው... ሊጎርር ነው... መቃብር ሀውልት ጋር
ሄዶ ደረስኩልህ ጋሼ ብሎ ሊሟዘዝ ነው። ከምንም በላይ የኢያሱን የቆሸሸ
ቁንጅና ሊያበላሽ ሳይታወቀው እየተሯሯጠ ነው። የኢያሱን መልክ ልቤ
ውስጥ ፈልገዋለሁ... ይሄ ፈልፈላ ባወራልኝ ቁጥር ደግሞ እየተጠራጠርኩ
ነው። ብወጣስ? ወጣሁ...
አይከተለኝም አውቃለሁ። ሰው ያፍራል...
~
"ለትንሽ ቀብሬህ ነበርኮ" እምባዬ ተቀምሞ እንደተዘጋጀ ነገር ፍስስስ አለ።
በጣቴ ጠርጌው አየሁት... ጣቴ ላይ ከነበረው ከንፈር ቀለም ጋር ተዋህዶ
ቀጭን ደም ይመስላል።
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 2

ከተሰቀለው ትልቅ ስክሪን ውስጥ የሚታዩት ፎቶዎች ባለፉት ሶስት ወራት ውሰጥ በተመሳሳይ ቀን ከተሰረቁት ትላልቅ ድርጅቶችና ባንኮች ውስጥ ተቀምጠው የተገኙት የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ተመሳሳይ የሆኑት ሳንቲሞች ናቸው መጽሀፍ ቅዱሶቹን ከመመርመሩ የተነሳ ሰባኪ ሊሆን ምንም አልቀረውም ከሳንቲሙ ላይ ያለው ምስል ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከስሩ የራስ ቅል ያለው ምስል ይዟል ሲገለብጠው ጨረቃ የሚል ፅሁፍ ታትሞበታል
በህይወቱ እንዲህ አይነት ውስብስብ የሆነ ነገር አጋጥሞት አያውቅም ከትላልቅ ባንኮች ውስጥ ገንዘብ እንጂ ማስታወሻና ቁርጥራጭ ወረቀቶች ጠፉ የሚል ዜና የሰማው ካለፈው ሶስት ወር ጀምሮ ነው ይሄን ያህል ገንዘብ ይሄን ያህል ሀብት የሚል መረጃ አልደረሰውም ዛሬም ከተደወለለት ሰአት አንስቶ ስለጠፋው ማስታወሻ ነው እየተነገረው ያለው የባንኩ ሀላፊዎች ሚሊየን ብር ቢጠፋ ከማስታወሻው ጋር ሊወዳድር እንደማይችል አስረግጠው ነግረውታል ከባንኩ ትልቁ ካዝና ውስጥ አንድ ማስታወሻ ጠፍቷል ካዝና ቁጥር 18 በቀን 18 ተሰረቋል የሚል ማስታወሻ ፃፈ እራሱ ሲዞር ይሰማዋል ዛሬም ምንም መረጃ የለም የተገኘው አንድ ሳንቲምና ተገልጦ የተቀመጠ መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው
ነፍሴ ሰላምን ከሚጠላው ጋር ብዙ ጊዜ ኖራለች
መዝ120-6
እስከዛሬ ተቀምጠው የተገኙትን ጥቅሶች መዝግቦ ይዟቸዋል የዛሬውንም መዝግቦ ያዘ የተቀመጠውን መጽሀፍ ቅዱስ በያዘው ከረጢት ውስጥ ጨመረው
ከሀሳቡ ብንን አለ ከፊቱ ከሚገኘው ትልቅ ስክሪን ላይ ቅድም ፅፎ የያዘው ጥቅስ ተቀምጧል
ከአቅማችን በላይ ስለሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ጥናትና በተለያዩ ምስጢራዊ ምልክቶች ላይ ጥናት ካደረገች ሴት ጋር ላስተዋውቃችሁ በጣም ትረዳናለች በሩ እስኪከፈት ድረስ አይኑን ከእስክሪኑ ላይ አልነቀለም ጥቁር ባርኔጣ ያደረገች ሴት ከበሩ ወደ ውስጥ ግርማ ባለው እርምጃ መግባት ጀመረች እጇ ላይ አንድ መጽሀፍ ቅዱስ ይታያል ከመጽሀፉ ላይ የተንጠለጠለው ቀይ ክር ወደ ታች ወርዷል በክፍሉ የተሰበሰበው ሰው አይኑን ከአዲሷ ሴት ተክሏል ውብ ናት እድሜዋ ወደ 50ዎቹ ይጠጋል ድምጿን ሞረድ አደረጋ እራሷን አስተዋወቀች እጇን ልካ ባርኔጣዋን አወለቀች ከጀርባዋ የሚያበራው ስክሪን ፀጉሯን ይበልጥ አሳመረው #ሶልያና እባላለሁ ከዚህ በሁዋላ ከምርመራው ቡድን ጋር አብረን እንሰራለን ድምጿ ይመስጣል አፉን የከፈተም አለ ባርኔጣዋን መልሳ አድርጋ ከክፍሉ ወጣች ሁሉም እየተነሳ ተከተላት
ክሩን ከዳዊት መዝሙር ምዕ120 ብታደርጊው ሳይሻል አይቀርም ከኋላ የሚያስቆም ድምፅ ሰማች ቁጥር ስድስትን እረስተሀል አለችው ፍጥነቷ ገርሞታል አብረሽን ስለምሰሪ ደስ ብሎኛል በጣም ታስፈልጊናለሽ እጁን ዘረጋላት ወንጌል አስተማሪ አይደለሁም እንጂ አነስ ያለች ፈገግታ አሳይታ ጨበጠችው ጴጥሮስ እባላለሁ ቆንጆ ስም አለህ ባክህ ልትለየው ፈልጋለች ቡና ወይስ ያለመስማማቷን ገለፀችለት ሊያስገድዳት አየልፈለገም ጠጋ ብሎ ደሞ የሳንቲም መርማሪ እንዳያመጡብኝ የምፀት ሳቅ ስቆ ጥሏት ሄደ ተረጋግታ ተራመደች

ሁሉም ከአስፈሪው ክፍል ተሰብስበው በመስታወት ውስጥ ከተቀመጠው ማስታወሻ ላይ አፍጥጠዋል የእናታቸው መዘግየት አሳስቧቸዋል ከክፍሉ የሚወጣው ዜማ አስፈሪ ነው
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
የሚያዩት ማስታወሻ የበገና መዝሙር ደብተር ይላል ጠርዙ ያበራል ማንም ሊነካው አልፈቀደም ካዠከቸነገራቸው ትዕዛዝ ሊወጡ አይቹልም ቆመው መጠበቅ ይዘዋል ሌሊቱ ለመንጋት እያዘገመ ነው ጨረቃ አሁንም አለች

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሸት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ዳዊት በበገ
_____________

የሥራ ቀጠሮዬ ጋ ለመድረስ እየተጣደፍኩ ነው። ከጠዋቱ 2:30 ከመሆኑ በፊት መድረስ አለብኝ። አንድ "እብድ" (ድርጊቱ ለዚህ መገለጫ ይመጥናል ብዬ ነው) ከፊቴ ይታየኛል። አላፊ አግዳሚውን በድንጋይ እያስፈራራና በስድብ እያከናነበ ነው። ማንም የሚናገረው የለም። ጥቂቶች ከሩቁ መንገድ እየቀየሩ ያፉታል። ጥቃት ያደርስብኛል የሚል ስጋት አልነበረኝም። ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ምንም አይነት ስሜት ሳላሳይና መንገዴን ሳልለቅ አልፌያለሁ።
ዛሬም ላደርግ የሞከርኩት ይህንኑ ነበር።
አጠገቡ ልደርስ አምስት እርምጃዎች ያክል ሲቀረኝ የዚህ ሰው መላ አትኩሮት
እኔ ላይ እንዳረፈ ታወቀኝ። እንደዚህ አይነት አትኩሮት በቦታው ላይ ሆኖ
ለሚረዳው ይረዝማል። ስድስተኛው የስሜት ህዋሴ ችግር እንዳለ ቢጠቁመኝም የመፍራትም ሆነ የማወላወል ስሜቴን ግን ዋጥ አድርጌው ነበርኩ። አጠገቡ ለመድረስ አንድ ርምጃ ሲቀረኝ መንገዱን በክብር ለቆ አሳለፈኝ። ይሆናል ብዬ ያልጠበኩት እና ከዚህ ቀደምም ሆኖ የማያውቅ ክስተት ነበር። አልፌው ሁለት ሶስት ርምጃ እንዳለፍኩ ደግሞ ስሜ ተጠራ። የጠራኝ ራሱ ነበር። ከስሜ በፊት ግን አንድ ተጨማሪ ቃል ነበረው። ደግሞ እስኪጠራኝ ድረስ ነው መሰል ርምጃዬን ልገታ አልፈለኩም። ደግሞ ጠራኝ፦
"ቲቸር ኄኖክ!" አሁን ግን ቆምኩ። ዞርኩ። በእጁ ይዞት የነበረው ድንጋይ አሁን እጁ ላይ የለም። ያ የእብደት ገጽታም እንዲሁ። እየቀረበኝ ሲመጣ ፊቱ ላይ የሚነበበው መራራ እውነት በላይ ታላቅ ትህትና ተስሎበት አየሁ። ይህን መልክ አውቀዋለሁ። ባስተማሪነት ዘመኔ ተማሪዬ ነበር። በተማረበት የሚሰራ ማነው?! …እኛው! ባስተማረበት የማይሰራም እኛው…"ቲቸር አወከኝ?"
እንዳወኩት ጭንቅላቴን ከፍና ዝቅ በማድረግ ገለፅኩለት።
✸✲✵
አውቄዋለሁ። የማወቅ መስመር ያገናኘን በመደበኛው የትምህርት መድረክ ላይ ነበር። እንዲህ አይነቱ እውቀት በህይወት መንገድ ይገኛል።
ሰው ታውቃለህ?
ሰው ታውቂያለሽ?
ሰው አውቃችሁ ታውቃላችሁ ያወቃችሁትስ ያውቃችኋል?!
ያወቃችሁት ሰው ከሆነ ልታደርጉለት የምትሹትን ነው የምታደርጉት? ወይስ እሱ እንድታደርጉለት የሚሻውን?! እኮ ምንድነው የምታደርጉት?!

ለሠላምታ የዘረጋሁለትን እጄን በሁለት እጁ እንደጨበጠ ነበር እንዲህ ያለኝ፦
"ይገርምሃል ቲቸር፣ 'ንቡር ጠቃሽ' ዘይቤ ያስተማርከኝ ዛሬም ድረስ ይገርመኝል።
በተለይ ያቺ ግጥም!! 'የዳዊት ወንጭፍ' ምናምን የምትለዋ! … እንዳልገባኝ ግን
ታውቃለህ?!"

አላውቅም! እኔ የማውቀው ያስተማሩኝን መሸምደዴና የሸመደድኩትን ማስተማሬን ነበር።
አላውቅም!
ግጥሟ "የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ" በተሰኘው የብላቴን ጌታ ጸጋዬ ገብረ
መድህን ግጥም ላይ ለዘይቤው መገለጫ ይሆን ዘንድ ተመዞ የወጣ አፄ
ቴዎድሮስን ከቀደምቱ ዳዊት ታሪክ ያጣቀሰበት ክፍል እንደሆነ ግን ርግጠኛ
ነበርኩ።
"ዳዊት በበገና እንዲያ
ማልቀስ ማላዘን መያዙ
ይህ የጎሊያድ ውላጅ
ቢበዛበት ነው መዘዙ
ምንጩ እንደ አሸን
እየፈላ አገር ምድሩን ማንቀዙ
ቸግሮት ነው መጋፈጡ
ከስንቱ መወናጨፉ
በባላንጣው ሳቢያ ምክንያት
የራሱን ወገን ማርገፉ…"

የበቀቀን ዘይቤ።
ዛሬ እሱ ነው ንቡር ተጠቃሹ። እንደዳዊት የራስን ወገን አርግፎ በፀፀት እያነቡ በገና መደርደር…

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ኄኖክ ሥጦታው ናሁሰናይ
ዕውነቱንም ፡ አውቄያለሁ ፡ ሀቁን ፡ ሳይሆን!

°°°Elfarus°°°

አይዞኝ ፡ ጀግና ፡ ቢወድቅ ፡ ጀግና ፡ ካላገዘው ፡ ምኑ ፡ ጀግና ፡ ነው?
ከስሜትሽ ፡ ስትነቂ ፣ እውቀትን ፡ ስታረግፊ ፣ ማንነትሽን ፡ ስትይዢ ፣
እውነትን ፡ ትገዛታለህ ፡ አትሸጣትም ፡ ላይ ፡ ስትደርሺ ፡ የዛኔ ፡ ሞቼም ፡
ቢሆን ፡ ሁሌም ፡ አጠገብሽ ፡ ነኝ ፡ አሁንም ፡ ቢሆን ፡ በቅርበት ፡ አይሻለው
፡ የኔን ፡ ጥበቃ ፡ በቸርነቱ ፡ ለአንቺ ፡ እንዲደርስ ፡ ሁሌም ፡ እማፀነዋለሁ።
"አፈቅርሃለው ፡ ይህም ፡ እስከዛሬ ፡ ከነገርኩ ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል።"
ስለወደቅሽም ፡ አይክፋሽ ፡ ሁሉንም ፡ ነገር ፡ አልደበኩሽምና። ብርታቴን ፡
እንደ ፡ ትምህርት ፡ ቤት ፡ ውድቀቴን ፡ እንደ ፡ ትምህርት ፡ እንድትማሪበት
፡ ነበር ፡ ሁሉን ፡ በየፈርጁ ፡ መንገሬ ፡ ለስጋሽ ፡ ሳይሆን ፡ ለአንድ ፡
ለነፍስሽ ፡ ነበር።
በጊዜ ፡ ሂደት ፡ የማይደረስበት ፤ የማይሰለችም ፡ ነገር ፡ የለም!
የሆነው ፡ ሁሉ ፡ የሚሆን ፡ ነው ፤ የተደረገው ፡ ሁሉ ፡ የሚደረግ ፡ ነው!
ዐዲስ ፡ ነገር ፡ የለም!
ትላንትናን ፡ ያየ ፡ ስለነገ ፡ ያውቃል ፡ ታሪክን ፡ ያስተዋለ ፡ ከጠቢብ ፡
ይልቃል ፡ ነውና ፡ አስተውዪ።
አይዞሽ ፡ የሰማይ ፡ ስርዓት ፡ በምድሩ ፡ ሳንኖረው ፡ አናመጣውም ፡
እንደፊቱ ፡ ዝቅታን ፡ ብንይዝ ፡ ስጋችን ፡ እናሸንፋለን ፤ በነጻነት ፡ እማ ፡
ሁሉም ፡ ጠቢበኛ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ትዳርም ፡ ያፋታል ፡ ያዳራል ፡ ሁሉም ፡
ማርከሻ ፡ አለው ፡ በማለት ፡ ስብዕና ፡ ያስረክሳል። እውነትን ፡ መኖር ፡
አይደለም ፡ መናገርን ፡ ይፈራ ፡ እና ፡ ሀቅን ፡ ይይዛል ፡ ፈጣሪ ፡ ግን ፡ ሀቅ
፡ ሳይሆን ፡ እውነት ፡ ነውና ፤ ማን ፡ ግን ፡ በፈጣሪ ፡ ፊት ፡ የተሰጠች ፡
ነፍስ ፡ ሊያፋታ ፡ ይችላልን ፡ ፩+፩=፪ ፡ የሆነውን ፡ የእግዚአብሔር ፡
እውነት ፡ እንዴት ፡ ተደርጎ? አይዞኝ ፡ አንድ ፡ ሚስጥር ፡ ላስታውስሽ ፡
ለሁሉም ፡ ነገር ፡ እባክህ ፣ ይቅርታ ፣ አመሰግናለሁ ፡ ሚሉትን ፡ ያዢ ፡ እና
፡ ማሸነፍ ፡ ትችያለሽ ፡ ይቅርታንም ፡ ብነፍግሽ። በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡
ግን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል ፤ ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ።
ይህ ፡ ለንፁህ ፡ ፍቅርሽ ፡ ሁሌም ፡ መሰክራለሁ ፡ ለሚፈርሰው ፡ ለዚህ ፡
በስባሽ ፡ ጡትና ፡ ቂጥሽ ፡ ከቶ ፡ አልተገዛውም። የገዛኝ ፡ የተገዛልኝ ፡
ማንነትሽ ፡ ነውና ፡ ልብሽ ፡ ቢቆሽሽ ፡ በጊዜ ፡ ሁናቴ ፡ ማንነት ፡ ቢፍቅ ፡
ስሜትሽ ፡ በዓለም ፡ ዕውቀት ፡ አይሎ ፡ ከቶን ፡ እምነትና ፡ እውነትን ፡
አይቀድምምና ፡ አይዞሽ ፡ ለነፍስሽ ፡ መኖር ፡ ስጀምሪ ፡ እግዚአብሔር ፡
ይረዳሻል። ነፍስሽ ፡ በመግዛቷ ፡ ነፍሴን ፡ ተገዝቷልና።

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል -3

ሌሊቱ አድካሚ ሆኖበታል ብቻውን ነው ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰ መንገዱ ይበልጥ ረዘመበት አረፍ ለማለት አስቧል ምሽቱን አላረፈም እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም አይኖቹ ደም ለብሰዋል ሲጋራውን ማግ አደረገው የደረቀውን ጥቁር ከንፈሩን በምላሱ አራሰው ጭንቅላቱ ውስጥ ምን እንደሚመላለስ ግራ ገባው ቀና ብሎ ጨረቃዋን ተመለከታት ጨረቃን ይወዳታል ለምን እንደሆነ ባይገባውም ሶልያና የሚል ድምፅ ከጆሮው ያቃጭል ጀምሯል ሀሳቡን አሎደደውም ከጆሮው ሚሰማውን ነገር ለማጥፋት ከሲጋራው በደንብ ሳበለት ከደረት ኪሱ አነስ ያለችውን የማስታወሻ ደብተሩን አወጣ አሁንም ሶልያና የሚለው ድምፅ ይሰማዋል ወረቀቱን ገለጥ አድርጎ ሶልያና ብሎ ከማስታወሻ ደብተሩ ላይ ፃፈ 54 አመቱን ከደፈነ ድፍን 5 ወር ሆኖታል በዚህ ሶስት ወር እንዳየው መከራ ከተወለደ ጀምሮ አይቶ እንደማያውቅ ለልቡ ነግሮታል ወረቀቶቹን ገለጠ እስከዛሬ ያገኛቸውን ጥቅሶች ይመለከት ጀመረ አብዛኞቹን ደጋግም ከማንበቡ የተነሳ በቃሉ ይዟቸዋል
ለመጀመሪያ ጊዜ በማስታወሻ ደብተሩ የያዘውን ጥቅስ አነበበ
ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል
የሐዋርያት ስራ 20:35
እንደዚ አይነት ጨዋታ በመርማሪነት ዘመኑ አይቶ አያውቅም ባያቸው የወንጀል ፊልሞች ውስጥ እንዳልተመለከተ አውቋል ጥቅሱን ደግሞ አነበበው ለሱ የሰጡትን ጭንቀት አስታወሰው ሲጋራውን ከአፉ አውጥቶ ተመለከተው እንዳለቀው ሲጋራ ሲያገኛቸው እንደሚጨርሳቸው አሰበ
አሁንም ምንም ባለማግኘቱ ተበሳጭቷል ሌላ የስልክ ጥሪ ሳይሰማ አይኑን እስኪጨፍን ጓጉቷል

ጠዋቱን አትወደውም የሷ አለም ያለው ከምሽቱ ነው ከፊቷ የተቀመጠውን መስታወት ለልጆቿ ከፍታ ለማሳየት ወስናለች ውስጡ ያለውን ነገር እሷ ማወቋ ብቻ በቂ አይደለም መስታወቱን ከፈተች የበገና መዝሙር ማስታወሻ ደብተር የሚለውን ማስታወሻ አወጣች ማስታወሻውን ቀስ አድርጋ በእጇ ዳበሰችው ዛሬ ማታ ወደ ትልቁ የበገና ማዕከል የምንሄድ ይሆናል ለእያንዳንዳቸው እያቀበለች ማስታወሻውን አሳየቻቸው ከአንድ ገፅ በስተቀር ሙሉ ማስታወሻው ምንም ያልተፃፈበት መሆኑ ሁሉንም አስገርሟቸዋል
በአንደኛው ገፅ ላይ ያለው ስዕል የሳባቸው ይመስላል በገና እየበገነ ያለ አንድ ሰው ተስሎበታል በገናው ላይ እንዲ የሚል ፅሁፍ አለ
አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ
መዝ42/43-4
ከስዕሉ ላይ ያለው ሰው ዘማሪው ዳዊት መሆኑን ሁሉም አውቀዋል ዛሬ ማታ ከበገና ማዕከሉ ውስጥ የሚወጣው በገና አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ የሚል ፅሁፍ እንዲኖረው ግድ ይላል።
ስልኳ ላይ ተደጋጋሚ መልዕክቶችና ጥሪዎችን አስተናግዳለች አንድ መልእክት ብቻ ተናግራ ወጣች በዛሬው ምሽት ላይ አሷ አትገኝም ተቃውሞ የለም ግን ትንሽ ግራ መጋባት ከፊታቸው ይታያል

ከእንቅልፉ ሲነቃ ሚወደውን ቡና ስለጠጣ ተነቃቅቷል ሌቱን ፈጠው ያደሩት አይኖቹ ትንሽ እረፍት እንዳገኙ ያስታውቃል ዛሬ ምን እንደሚፈጠር ባያውቅም ያለፉትን ሶስት ወራት በዚ ቀን ብዙ ነገሮች እንደተፈጠሩ ያውቃል አይኖቹ ትናንት የተዋወቃትን ሴት ይፈልጋሉ የሷ እርዳታ በጣም እንደሚያስፈልገው ያውቃል
ከምርመራ ክፍሉ ሲገባ ሲፈልጋት የነበረችው ሴት ከእስክሪኑ ፊት ቆማ እያወራች አገኛት ቀስ ብሎ ገባ ከትልቁ ስክሪን ላይ የተደረደሩ ቁጥሮች አሉ ቁጥሮቹ ብዙ አልጠፉትም አስሩ የመጽሀፍ ቅዱስ የሚስጥር ቁጥሮች የሚባሉት ናቸው። 1 22 40 4 12 10 6 3 7 21 ከዛሬ ሶስት ወር በፊት ከጠፋው ትልቁ ቤተ መፃህፍት ውስጥ ከተሰረቀው ሚስጥራዊ ብራና ጋር አብረው የጠፉት ቁጥሮች ናቸው
ማብራሪያውን ቀጥላለች እነኚህን ቁጥሮች የመጽሀፍ ቅዱስ ሚስጥራዊ ቁጥሮች ከመሆናቸው በተጨማሪ ከተሰረቁት ነገሮች ጋር የታታዥነት አላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤተ መፅሀፍቱ እንነሳ ይህ ቤተ መፅሀፍት በከተማው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተ መሆኑን እናውቃለን ስለዚህ 1 የሚለውን ቁጥር ቤተመጽሀፍቱ ይወስዳል። ለሁለተኛ ጊዜ የተሰረቀው የንጉሱ ማስታወሻ ሁለተኛው የንጉሱ ማስታወሻ እንደሆነ ይታወቃል ተቀምጦበት የነበረውን ሳጥን ስናይ በሳጥኑ ላይ ሁለት የሚል ቁጥር እናገኛለን 2-2 ስናገናኛቸው 22 ይሆናል ስለዚህ የንጉሱ ማስታወሻ 22 ቁጥርን ይወስዳል። የዛሬ ሁለት ወሮ አካባቢ የተሰረቀውን የወርቅ ብዕር ደሞ እናገኛለን ብዕሩ 4 ቀለሞችን የያዘ ነው ስለዚህ 4 ቁጥሩን ብዕሩ ይወስዳል ማለት ነው። ሁሉም አፉን ከፍቶ እያዳመጣት ነው ብዕሩ በጠፋ በነጋታው የጠፋው መጽሀፍ 12ቱ መአድናት የሚል መጽሀፍ ነው ይህ ማለት 12ቁጥር መጽሀፉ ወሰደ ማለት ነው። ልክ የዛሬ ወር የጠፋው የወርቅ ሜዳሊያ በላዩ ላይ በግዕዙ 10 የሚል ቁጥር በሜዳሊያው ላይ ታትሞ እናገኛለን ስለዚህ የወርቁ ሜዳሊያ 10 ቁጥርን ይወስዳል። እነዚህ ሚስጥራዊ የመጽሀፍ ቅዱስ ቁጥሮች ተብለው የተቀመጡት ቁጥሮች ካርታም ጭምር ናቸው በቀላሉ ለዘራፊዎቹ ምልክት ይሰጣሉ
ትናንት የጠፋው ማስታወሻ በሶስት ሰዎች የተሳለ ስዕል ውስጡ ይገኝበታል በስዕሉ ላይ ላይ ያለው ሰው መዝሙረኛው ዳዊት ነው ማስታወሻው ደሞ 3 ቁጥርን ይወስዳል ማለት ነው። በስዕሉ ላይ ያለው ምስል በገና ይዞ እየደረደረ ያለ ምስል ነው። የቀሩን ሁለት ቁጥሮች ደሞ 7 እና 21 ናቸው። ልብ ብሎ እያዳመጣት ስለሆነ 40 ቁጥርን ለምን እንደዘለለቻት አልገባውም ማስታወሻውን አውጥቶ ሁሉንም ነገር መዝግቧል 40 ቁጥርን ግን ሊያገኛት አልቻለም ቀና ብሎ ከደገና መስማት ጀመረ
7 ቁጥርን ልውሰድ ከስዕሉ ላይ የሚታየው በገና ይዞ የሚደረድር ሰው ነው ቀጥታ በሀሳባችን ሊመጣቸው የሚገባው ነገር ትልቁ የበገና ማዕከል ነው ከትልቁ ስክሪን ላይ የበገና ማዕከሉ መግቢያ ምስል ተደቀነ እንደምታዩት መግቢያው ላይ ትላልቅ ሰባት የበገና ቅርፆች ይታያሉ ስለዚህ የበገና ማዕከሉ 7 ቁጥርን ይወስዳል ማለት ነው። በብርሀን ፍጥነት ሁሉም ከተቀመጠበት ተነሳ ቀጣዩ አላማ ትልቁ የበገና ማዕከል እንደሆነ አውቀዋል

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፎቶና ውዴታ
(በእውቀቱ ስዩም)

ፌስቡክ የተቀላቀልኩ ወደ 2012 አካባቢ ነው፤እና ያኔ ከቤተሰቤ እና ከጎረቤት በቀር የሚያውቀኝ አልነበረም፤ የፌስቡክ አጠቃቀም ራሱ በቅጡ አልገባኝም ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ ሁለት ሄክታር ቶክሲዶ ሱፌን ግጥም አድርጌ ለብሼ ፤ ጆፌ አሞራ እሚያህል ክራቫት ጣል አድርጌበት፤ ፎቶ ተነሳሁና ፌስቡክ ላይ ለጠፍኩ ፤ ከዚያ ፈንድሻ እየበላሁ የህዝቡን ምላሽ ብጠብቅ ብጠብቅ ምንም የለም፤ ደብረማርቆስ ዘመድ ጠይቄ ስመጣ አስካለ የተባለች ልጅ “ላይክ “ አድርጋዋለች ፤ ያኔ የላይክ ምልክት የነበረው አውራ ጣት በጣም ግብዳ ነበር ! መንገድ ዳር ይዘኸው ብትወጣ”ሊፍት’ የሚሰጥ መኪና ማስቆም ሁሉ ትችላለህ! ከመደሰቴ የተነሳ “ ፎቶየን ስለወደድሽው አመሰግናለሁ “ የሚል መልክት ሰደድሁላት ፤ ኢንቦክስ የላክሁላት መስሎኝ ግድግዳየ ላይ እንደለጠፍኩት ያወኩት “ በውቄ የዛሬውን ግጥም ደግሞ ርእሱን ብቻ ነው የለጠፍከው ’’ እሚል አስተያየት ሳነብ ነበር፤ አትፍረዱ ! በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ፅላሎ ወረዳ ከሚኖር የብእር ጉዋደኛ ጋር ደብዳቤ ስለዋወጥ ያደግክሁ ሰውየ ፤ኢንቦክስ ቢደናገረኝ አይገርምም ፤


ሴቶች በጠቅላላው፤ ቆንጆ ሴቶች በተለይ፤ ፎቶ ለጥፈው ውዴታ( ላይክ) ለመሰብስብ ችግር የለባቸውም፤ ፎቶ ሲነሱ ደሞ ፤ የሳምንት እቅድ ነድፈው በቂ በጀት መድበው በደንብ ተዘጋጅተው ነው፤ የመታወቂያ ጉርድ ፎቶ ለመነሳት ድሮን ሳይቀር እሚከራዩ አሉኮ! የኔ እናት የሩቅ ዘመድ ሲሞትባት ሀዘኑዋን ለመግለፅ ፊትዋን ትነጭ ነበር ፤ የዘንድሮ ዝነኛ ሴቶች “በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን “ የሚል መልክት የሚያስተላልፍ ፎቶ ለመለጠፍ ፤ አራት ሰአት ሙሉ የቁንጅና ሳሎን ውስጥ ይቆያሉ፤

ሰዎች ነን፤ እንድንወደድ እንፈልጋለን! አንድ ሺህ ጉዋደኛ ኖሮህ አስር ሰው ብቻ ፎቶህን ከወደደው ይደብርሀል ፤ ከወደዱህ በላይ ጭንቅላትህን የሚቆጣጠረው ጥግ ላይ ቆመው፤ እንደ ሙናየ መንበሩ ከንፈራቸውን አጣመው፤ ባላየ የሚያልፉህ ሰዎች አሳብ ነው ፤

ለማንኛውም ብዙ ሺህ ሰው ፎቶህን እንዲወድልህ ትፈልጋለህ? አማላይ ወይም ያንድ አሙስ ሰለብሪቲ መሆን አይጠበቅህም! የሚጠበቅብህ ይህ ነው፤ አዋሽን የሚያህ ያህል ባንዲራ ልበስ ፤ ግንባርህ ላይ ኤርትራን የሚያካትት የኢትዮጵያ ካርታ ተነቀስ! ከጀርባህ የታወቀ ባለታሪክ ሀውልት ወይም የገዳም ወይም የመስጊድ ምስል ቢኖር ቢኖር አይከፋም ፤ የኢትዮጵያ ፊደል ምልክት ያለበት ቲሸርት ልበስ! የኢትዮጵያ ቁጥሮች የተፃፉበትን ሰሌዳ ደግሞ እንደፍሬው ሃይሉ አኮርድዮን አንገትህ ላይ አንጠልጥል! በቀኝ ክንድህ ላይ ከቅዱስ መፅሀፍ የተወሰደ ጥቅስ ጣል አርግበት ! ግራ ክንድህስ ለምን ስራ ይፈታል ? ደም ለግስበት!

@wegoch
@wegoch
አንዲት ልጅ ነበረች ማቅመሻ የምላት

°°°ጓዴ ጥላሁን°°°

ከዘማናት በአንዱ ፌስ ቡክ ላይ ተጥጄ ሳለሁ አንዲት ልጅ የወዳጅነት
ግብዣ ላከችልኝ፡፡ እኔም አይመርጤ ነበርኩና ሳልወላዳ ተቀበልኳት፡፡ ያኔ
መቼስ ልጅነቱም አለ ሴት ልጅ ፍሬንድ ርኩዌስት ስትልክልኝ ላግባህ
ያለችኝ ያህል ደስታ ሞትኩ፡፡
ለ 30 ደቂቃ ያህል በቻት ሞንሟና ወሬ ሲያወራኝ የነበረውን አብሮ አደጌን
በጓጉነቸር ቁልፍ ጠርቅሜበት ወዲያውኑ
‹‹Hi sweet››
ስል ቻት አደረግኳት፡፡ ወዲያው ፈጣን ኢንቦክስ አየሁ፡፡ ሞባይሌን የመስበር
ያህል ተጭኜ ሜሴጁን ከፈትኩት፡፡
‹‹ምነው ዝም አልክ››
አለ ቀድሞ ሲያወራኝ የነበረው ወዳጄ፡፡ ፊቴ ባገኘው በብሎኬት አንጉጄ
እንደ ምጥለው አልተጠራጠርኩም፡፡ ያን ማድረግ ስላልቻልኩ ብሎክ
አደረግኩት፡፡ ደገምኩና
‹‹Hi honey››
ብዬ ላኩላት፡፡ ግራ ገባት መሰለኝ የጥያቄ ምልክት የአፍሪካን ካርታ
አስመስላ ሰደራ ላከችልኝ፡፡ ተናደድኩባት፡፡ ሳይለዋት ወዳጅነት ጠየቀችኝ፡፡
ለሷ ስል አብሮ አደጌን ቦለኩት እና ምን ያንቀባርራታል፡፡ መጣችብኝ እንጂ
አልመጣሁባት ይህቺን ይወዳል እንቆቆው ጓዴ
‹‹ምናባሽ ይለጥጥሻል አንቺ…››
ብየ ላኩ፡፡
‹‹ What??? Is that really you? ›› ስትል ላከች
‹‹ ዞር በይ የእንጭቅ ልጅ ምናባሽ ያመጻድቅሻል….›› ስል የተበተ ምላሽ
ሰጠኋት፡፡
‹‹If I am not mistaken your profile reads as you are
university instructor››
ስትል መለሰች፡፡
‹‹…..እና ምናባሽ ላንጉትልሽ? አንዳንቺ ጎልያድ የሚያህል ሰውነት ይዤ
አስረኛ ክፍል እንድንከባለል ጠብቀሽ ነበር….? “ ስል ዛጥ አደረግኳት
‹‹`… such rude words are not expected from you.›› ብላ ምክር
አዘል ምላሽ ላከች፡፡
‹‹…. ዝጊ ባክሽ ይቺ የመሃይምናን መጽናኛ ናት፡፡ ወዲያ እብሪትሽን
ሰብስቢ…›› ስል ጨመርሁላት፡፡
ለተወሰነ ጊዜ ዝም አለች፡፡ አፏን ያዘጋሁ መስሎኝ ኩራት ኩራት አለኝ፡፡
‹‹….. ልክ አስገባሁሽ፡፡ እንዲህ ነን እኛ፡፡ ማንቀጥቀጥ ከዘራችን ነው፡፡
አንቺና ጎሬዋ መስሏት ዘንዶ አፍ የገባችው አየጥ አንድ ናችሁ፡፡…›› ብዬ
እስከ ዶቃ ማሰሪያዋ አስታጠቅኳት፡፡
ዝም አለች፡፡ ጨመርኩላታ
‹‹….. ተቅበዝብዘሽ ሪካስት ላክሽ፡፡ ሂሳብሽን ስሰጥሽ ይሄው እንደቆረበች
መነኩሴ አፍሽን ያዝሽ፡፡ ለወደፊቱ ትምህርት ይሁንሽ፡፡ እርሜ ናት በይ….››
አልኩና ማስጠንቀቂያ አከልኩ፡፡
አሁን መለሰች፡፡ ጫማ ስማ ማረኝ ልትለኝ እንደ ሆነ አልተጠራጠርኩም፡፡
ኮራ ብዬ አነበብኩት
‹‹…. Are you really university instructor? ›› የሚል ነበር
‹‹…. አሁንም አልመከር አልሽ፡፡ ምነው የኔ መምህርነት ወዘወዘሽ መሆን
አምሮሽ እንደሆን እርምሽን አውጭ፡፡ አታገኚያትም፡፡ እንኳን አንቺ ደንቆሪተ
ገዳም ዘር አዝርቶችሽም አያገኟት፡፡ እንቁልጭልጭሽ …››
‹‹……you can’t talk about my families , because you don’t
know them…›› አለች፡፡
‹‹…. ዝጊ ባክሽ ስለ ቤቶችሽ ለማወቅ አንቺን ማየቱ ይበቃል፡፡ ጥጃ አባቷ
በሬ እናቷ ላም…››
‹‹….. Better to stop here. Bye…›› ብላ ተሰናበተችኝ፡፡
‹‹….. የታባሽ ትሄጂ፡፡ ነይ ተመለሽ፡፡ የአመት ቀለብሽን ልስፈርልሽ፡፡…››
‹‹…..Sorry to say this sir, you are not suiting me. Neither
your joke nor your deal is not comforting me….››
‹‹…. ወይ ጠንቆን አለማወቅ፡፡ ማይምነት እንዴት ይጎዳል ጃል፡፡ ተናግረሽ
ልብሽ ወልቋል ቋቋቴያም፡፡ ደደብ መሀይም ሶስት አመት ዩኒቨርስቲ ተምሬ
በማዕረግ ተመርቄ ነው ለዚህ ወግ ማእረግ የበቃሁት አህዮ፡፡ ጓደኞችሽ
ጎጆ ቀልሰው ወልደው ከብደው ይኖራሉ አንቺ ገና ሃይስኩል ኳስ
እያነጠርሽ ትራገጫለሽ….››
‹‹….I am not ashamed of being high school student in my
eighteen. I don’t also think your graduation should you to
tyranny….››
‹‹….. ኧረ ተይ ተመከሪ!! ከብረት ግንብ ጋር አትላተሚ፡፡ ልድገምልሽና
ይቁረጥሽ ሶስት አመት ዩኒቨርስቲ ተምሬ ክቡር ሚኒስትሩ ከዚያ ሁሉ መንጋ
መሃል በስሜ ጠርተው አገላብጠው ባይስሙኝም ፈገግ ብለው ነው
በማእረግ የመረቁኝ፡፡ ተመራቂ ሲባል ጥቁር ቆብ ደፍቶ ጋዋን ደርቦ ዘጥ
ዘጥ የሚለው ሁሉ እኩል አይምሰልሽ፡፡ የማእረግ ተመራቂ ነኝ እርር
በይ….››
ብታይ ብታይ እንግሊዘኛ የማይደማኝ ስሆንባት በአማርኛው ጀመረችኘ፡፡
‹‹… ስማ ዩኒቨርስቲ መግባት በየትኛውም መስፈርት የምሁር መገለጫ
ሆኖ አያውቅም፡፡ ኮሌጅ ሳይገቡ ዓለምን የቀየሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
ልቁጠርልህ ሶቅራጥስ፣ ዲዮጋን፣ ፓይታጎረስ፣.. ስለ ሌሎቹ እንዳልተርክ
ጊዜ ያጥረኛል፡፡ እና ወዳጄ ዩኒቨርሲቲ የቆየህበትን አግዝፈህ አትየው፡፡…››
ለመጀመሪያ ጊዜ አነጋገሯ ጎረበጠኝ፡፡ ግን አልተጠቃሁላትም
‹‹…. ያጣ ወሬ ነው ባክሽ፣ እኝ በይ... ሶስት ዓመት ዩኒቨርስቲ ተምሬ
ክቡር ሚኒስትሩ……›› አብዝቼ ወጣሁላት፡፡
‹‹….. ሶስት ዓመት እንደቆየህኮ ነገርከኝ፡፡ ለሰው አንዴ ነው የሚነገረው፡፡
ስማ ማቱሳላ 969 ዓመት ኖረ፡፡ ግን ምንም አልሰራም፡፡ ኅጻኑ ቂርቆስ ግን
በ3 ዓመቱ እናቱን ከጥፋት አዳነ፡፡ ያንተን ያህል 3 ዓመት ኒቨርሲቲ መግባት
አላስፈልገውም›› ሶስት ዓመት ዩኒቨርስቲ ብትቆይ የህዝብ ሃብት
ከማባከን ውጭ ምንም አልጨመርክም፡፡በሚንስትር መጨበጥም ይህን
ያህል የሚያስፎክር መስሎ አልታየኝም፡፡ ሂትለርና ሙሶሎኒም ሚንስትር
ነበሩ፡፡…››
ያኔውኑ ዲግሪዬን የተነጠቅኩ መሰለኝ፡፡ የሞት ሞቴን
‹‹….. ስሚ ምንም ብትይ የመሃይም ወሬ አልሰማም፡፡….›› ከዚህ በላይ
ማውራት አቃተኝ
IGNORANT
+
AROGANT
=
YOU
ብላ ላከች፡፡ መቅኒየ ነው የፈሰሰው፡፡ ስንቱን ወሽክቼ በአንድ ፎርሙላ
በዜሮ አባዛችኝ፡፡ የተረሳ ስድብ ከመዝገብ ቤት ስፈልግ
Ethiopia=free of petrol
you=free of mind
ብላ ደገመችኝ፡፡
‘ይህቺን ቀምሰህ ውሃ ጠጣ’ ራሴን ማሻሸት ጀመርኩ……..

ይቀጥላል....

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
ስንቀራረብ ምነው ተራራቅን?
-
በመንገዴ ላይ ግድግዳ ላይ የተለጠፈ አንድ ማስታወቂያ አየሁ። ''1234'' ላይ A ብለው ቴክስት በማድረግ የትዳር አጋርዎን ያግኙ ይላል። በሥራ፣ በትምህርት ቤት፣ ታክሲ ውሥጥ በመሳሰሉት የዕለት ለዕለት መገናኛዎቻችን ላይ ይህንን የማግኘት ፀጋ ተነፈግን ማለት ነው? ይህን ያህል ማኀበራዊ መስተጋብሮቻችን ተንኮታኮቱ? ወይስ በጣም ስንዘምን ሳንደክም፣ ሳንለፋ፣ ለፀባያችን የተስማማ፣ የምንፈልገውን መመዘኛ ያሟላ ባል/ሚስት የማግኘት ፀጋ ታደልን? እራሴን ጠየቅሁ።
-
ዘመኑ የቴክኖሎጂ የሥልጣኔና የመረጃ ነው እንላለን። ልክ ልንሆን እንችላለን።
ቴክኖሎጂ ኑሮን ያቀላል እንላለን፣ ይህም እውነት ሊሆን ይችላል። ግን ምን
ድረስ ነው ኑሮ መቅለል ያለበት? የት ጋር ነው በቃህ ይሄ ደሞ ሕይወቴ ነው የምንለው? ለእኔ የቴክኖሎጂ መራቀቅ የት እንደሚያደርሰን ማሰቡ ከራሴ በላይ በስሬ ለማያቸው ቲንኤጀሮች ያስፈራኛል። በዕድሜያቸው ማወቅ ከሚገባቸው ነገር እጅግ አልፈው እንደሄዱ አስባለሁ። ያለው የማኀበራዊ ሚዲያው ብዛት እረፍት አልሰጠንም። በኪሶቻችን ባስቀመጥናቸው ስልኮቻችን ውስጥ ራሱን የሰወረ ጋኔን የሠለጠነ ይመስለኛል።
.
.
የመረጃ ዘመን ነው። የምንፈልገውን መረጃ በአንድ ደቂቃ ፍጥነት፣ በተወሰኑ
ድንቆላዎች ርቀት እናገኛለን። ስለሁሉም ነገር ስለሰማን ሁሉንም ነገር ያወቅን
ይመስለናል። በእያንዳንዱ ነገር ላይ ጥልቅ የሆነ ዕውቀት የለንም። በወፍ በረር የቃረምነውን እያድበሰበስን አዋቂ ለመምሰል እንቸኩላለን። የምናውቀው ግን ግልብ ነው። ይሄኔ አይደል ''ደፋር ህፃናት ጎዳናውን ሞሉት'' ማለት።
-
የምንወዳቸውን የውጪ ፀሀፍት መጽሐፎች በ50 ሳንቲም በቀን እየተከራየን ማንበብ አይጠበቅብንም። ትላልቅ ቤተመጽሐፍት ድረስ መድከም፣ ከውጪ ማስላክ አይኖርብንም። ስልኮቻችን ውስጥ ማንንም ማግኘት እንችላለን። ግን እንደድሮው ለንባብ ዋጋ አንከፍልም። ማሰላሰል ማሰብ አንፈልግም።
-
ከምንበላው፣ እስከምንለብሰው፣ ከሚያስፈልገን እስከተመኘነው ደጃችን ላይ የሚያመጡልን መተግበሪያዎች ተፈልስፈዋል። ጓደኛ ለማፍራት ሰፈርና መንደር ገጠመኝና ሌላም ሌላም አያስፈልገንም። የማህበራዊ ሚዲያው አለልን። እነዚህ መገናኛዎች ላይ ክንፍ በሚያደርግ ፍቅር እንወድቃለን። ዳሩ ፍቅራችን ለሳምንት ነው። ሳቃችን የሀሰት፣ አድናቆታችን የለበጣ ነው። እንናናቃለን። ኑሯችን ብልጭልጭ ነው። የምንመኘው እልፍ ነው። የምንወደው እስከወደዱን ነው። የምናነባው ለሚያስቀው ነው። የምናለቅሰው አንጀት ለሚበላው ነው። የምንከተለው የሚስቅብንን ነው። የምንደግፈው የደመነፍሱን የሚደናበረውን ነው። የምናምነው በእጆቻችን ጠፍጥፈን የሰራነውን ነው።
-
ኑሮ በቀለለ ቁጥር እየከበደ ነው። በሰለጠንን ቁጥር የጓደኞቻችንን ሕመም
የማናዳምጥ፣ በደስታቸው የማንካፈል ባካኝ ሆነናል። ትምህርታችን የጋን ውስጥ መብራት ነው። አስተማሪዎቻችን ለመማር ራሱ አይመጥኑም። ፕሮፌሰሮች ከአያቶቻችን የተሻለ የሕይወት መረዳት የላቸውም። ባለዲግሪዎቻችን እንግሊዝኛ ያፍራሉ። ዩኒቨርስቲዎቻችን ከምርምር ተቋምነት ወደግርግር ተቋምነት ከዞሩ ሰነባበቱ።
-
''መልካም ዜና ለወላጆች....'' ''ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን...'' ''...ተቸግረዋል? እንግዲያውስ ይዘዙን...'' የዘመናችን መልኮች ሆነዋል። መዘመን መልካም ነው። ይህ ሲሆን ግን ለተገባው ሕይወታችን ፊት ነስተናል።
በግብዝነታችን የዋሆቻችንን ገድለናል። መልካሞቻችንን መድረሻ አሳጥተናል። ራሳችንን ለመከላከል እንፈጥናለን። በሰዎች ለማፌዝ ቅርብ ነን።
-
ከስክሪኖቻችን ጀርባ ተቀምጠን ልብ እንሰብራለን። የምናወጣት እያንዳንዷ ቃል የት ደርሳ ምን እንደምትፈጥር ግድ አይሰጠንም። ስንሳለቅ አንጠነቀቅም።
በሰው ተክለቁመና፣ አፈጣጠርና ሕመም ሳይቀር ሳይቀፈን እንስቃለን። ለፍርድ
ችኩል ነን። ለማጀገንም ለማውገዝም አሰፍስፈን እንጠብቃለን። ስንደሰት
ባለክንፍ ነን ...እንደቢራቢሮ ። አቁሳይ ሀምሳእግርነታችንን እስኪያስፈልገን
አናሳይም።
-
በጣም ገጠር የሚባል ቦታ ሰርቼ አውቃለሁ። photoshop፤ sarcasm
ምናምን የማይረዳ ብዙ ሕዝብ አለን። ያየውን ቀጥታ የሚያምን ስልክ ካለው
ሕዝብ አብዛኛው ነው። ይህንን ሳይረዳ ፌስቡክ ክፈትልኝ ብሎ ወደዓለማችን
የሚገባ ብዙ ነው።
-
ራስን የማጥፋት ምጣኔ ለምን አሻቀበ? አመጽና አጥፊነት ለምን ተበራከተ? አንጠይቅም። ስታትስቲክስ በመደርደር ጊዜ አናጥፋ እንጂ መልሱን ሁላችንም
እናውቀዋለን።
-
በሥልጣኔ አምናለሁ። ቴክኖሎጂ እጅግ መልካም ነው። የልብ ሰዎቼን ያገኘሁት
እዚሁ ነው። አንዳንዴ ግን አዝናለሁ። በእናንተም በራሴም።
-
ስንቀራረብ ምነው ተራራቅን? ሰው ስንሆን ምነው ልባችን በደነ?
-
ይህ ሁሉ ለቃላቶቻችን እንጠንቀቅ ለማለት ነው። Speak life የማይረባንን ንቀን እንለፍ። ለሁሉም ነገር መመላለስ፣ ለሁሉም ነገር እኔን ስሙኝ ማለት አያዋጣም።
.
.
በመጨረሻም winston Churchill
'' by swallowing evil words unsaid, no one has ever harmed his stomach''

@wegoch
@wegoch
@paappii

#henock bekele
አንዲት ልጅ ነበረች ማቅመሻ የምላት- ክፍል 2

©ጓዴ ጥላሁን

ያወረደችብኝን መዓት መመከቻ አጣሁ፡፡ ባወጣ ባወርድ ስድብ ከየት
ላምጣ፡፡ ነገ በእጥፍ የምመልሰው ስድብ ከጓደኞቼ በዱቤ ጠየቅኩ፡፡
አልተባበሩኝም፡፡ እንደውም ጦስህ ለኛ እንዳይተርፍ ወዲያ ሂድ ብለው
ኩቲ አደረጉኝ፡፡
‹‹ …. ስሚ ድሮስ በትምህርት ያልተበዘበዘ ጭንቅላት ከስድብ ውጭ
የሚያውቀው የለም፡፡››
“……. እኔ አልተሳደብኩም፡፡…›› ብላ መለሰች
“……... እና እስካሁን ቅቤ እየቀባሽኝ ነበራ… ግድ የለም እሱ የላይኛው
ይፍረድ….” በሙግት ያጣሁትን ስም በማሳቀል ለማምጣት ጣርኩ፡፡
“……. ይህ ስለ ተሰማህ አዝናለሁ ይቅርታ፡፡››
“…….. አሄሄ ተይኝ እስቲ ይሄን ወግቶ በቅቤሽን… እሱ ይፍረድ ብቻ…››
እያልኩ በሶት አደባባይ አደረግኩት፡፡
“…… እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም ካልተስማማሁህ ቀላል
ፎርሙላ አለልህ፡፡ ፐሮፋይሌን ክሊክ አድርገህ አንፍሬንድን ተጫን፡፡…..”
“…… አሁን ገና ጨዋታዋን አመጣሻት እስቲ አስቲ ድገሚያት
ፎርሙላዋን?” ወዳ እና ፈቅዳ ስለላከችልኝ አንፍሬንድ አደርግሻለሁ ስላት
በታቦት አማላጅ እንደምትታረቀኝ ገምቼ…..
“…… ፎርሙላውን ከፍ ብለህ ማንበብ ትችላለህ እኔ አልደጋግምም፡፡
ይልቅ ጉድለትህ የቀመር ብቻ አይደለም፡፡ የቋንቋም ጭምር ነው፡፡ ቀመሩን
እኔው እሰራዋለሁ አንተ ቋንቋህን አሻሽል…..”” አለችና አንፍሬንድ አድርጋኝ
አረፈች፡፡
ሳስበው ግን ገመናዬን የምትዘራብኝ መሰለኝ እዚችው በአቦ በስላሴ ብየ
ልታረቀት አሰብኩ፡፡
‹‹….. እየውልሽ እቴቴ አንች! ማነሽ የአይን አበባ…መቼም ሰው ሆኖ
የማይስት እንጨት ሆኖ የማይጤስ የለምና ጉዳችንን ሰው ሳይሰማው
እናዳፍናት፡፡›› ብየ አስተዛዘንኩና ደግሜ ፍሬንድ ሪኳስት ላኩላት፡፡
ተቀበለችኝ፡፡
(ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
ሽንፈት ሰው ፊት ሲሆን ለምን ይገዝፋል ?

©በረከት ታደሰ

ወደ ሐሴት የሚወስደው መንገድ ሩቅ አይደለም፡፡ እሷ ነች! የደስታዬ ርቀቱ
በቅርበቷ ልክ ይሰፈራል፡፡ ተያይዘን... ተቃቅፈን... በሞላ ቦታ አንድ ወንበር
ላይ ለሁለት የመቀመጣችን ሚስጥር መራራቅን ፍራቻ ነበር፡፡ ስንዝር ለምን
እንራራቃለን? መተቃቀፍ ስንችል? በትንሽ የተናቀ ርቀት እያደር አይሰፋም?
ጓደኞቻችንን እንሰለቻቸው ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ አንድ ቦታ ላይ ተቆጣጥሮ
መቀመጣችን ይሰለቻቸዋል፡፡ ጥለውን ይሄዳሉ፡፡ የማናስታውሳቸውን
ጉዳዮች እናወራለን... ዝምታችንም ሹክሹክታ አለው፡፡ ቀኑ እንደ ገለባ
ይበንናል፡፡ ሽታው እንደ ውድ ሽቱ በሚጣፍጥ ዝምታ...
~
የመጀመሪያ አመት ተማሪ እያለሁ ነበር... ገና ዩንቨርስቲን በግምትና
በምኞት ነው የማውቀው... ከብልቃጥ አለሜ ወደ ውጭ የፈሰስኩበት
የመጀመሪያ አጋጣሚዬ ላይ ለስላሳ እጆቹን ዘርግቶ የተቀበለኝ ፍቅር ነበር፡፡
ተፈጥሮ እና አጋጣሚ አሲረው አገናኙን፡፡ እንጂማ የሁለት አለም ሰዎች
ነበርን... ፍፁም እንለያይ ነበር፡፡ እኛን እያነካካ በእኛ አለማወቅ የሚያፌዝ
አንድ አካል ነበር፡፡ እኛ ደግሞ ሎሌዎች ነን... ለገፈተረን የምንንደረደር
የተፈጥሮና የአጋጣሚ ሎሌዎች፡፡ ተላመድን... ርቀት ናድን፡፡ ነገ የሚባል ቀን
አልነበረንም፡፡ ሁሉም አሁን... አሁን... አሁን... የተሸመደደ ፍቅር አልነበረም...
አሁናችን ላይ ጣኦቶች ሆነን የምንዋብ፡፡ ስንቴ እናፈቅራለን?
~
እንደ የትኛውም የፍቅር ታሪክ ቀድሜ ያፈቀርኳት እኔ ነበርኩ... ቀናቶቼን
ፊቷ ዘርግፌ አስገዝቻለሁ... አልባከኑም!
ቆየ... በእንደዚሁ አይነት አካሄድ ቆየን... የሰለቸኀት ይመስለኛል፡፡ ሙሉ
እኔነቴን ሰጥቻት ሌላ የማታውቀውን ፍቅር ልሰጣት አልችልም፡፡ እየቆየ
<እወድሻለሁ> የሚለው ቃል በልቧ ረከሰ፡፡ እንደ የትኛውም መግባቢያ
ተራ ቃል ሆነ... ቃል በግዜ ርቀት እንደሚያረጅ አየሁ፡፡ መልሷ <ዝም>
ነበር፡፡ አዲስ ነገር አልነበረኝም... ምን ፍለጋ ትመጣለች? ያለ አዲስ ጉዳይ
ፍቅር ራሱን ችሎ እንደማይቆምም ያኔ አየሁ፡፡ ሙሉነቴን ገልጬ
አሳይቻታለሁ... የምትመኘው ነገር አልነበራትም፡፡ What more can i
give up?
~
አለሙ ግራ ነው! ከሰጠኸው በላይ ይጠይቅሀል... ዙሪያህ መክሰርህን
ይሰብክሀል፡፡ ፍቅረኛዬ አልነበረችም... ተራ ወዳጅም አልነበርንም፡፡ ከሁለቱ
መሀል የሚወዛወዝ ቀጭን መስመር ላይ ግን ቆመናል፡፡ እወድሻለሁ ለሚል
የሻገተ ቃል መልሱ <ዝም> ነበር፡፡
~
ከእርሷ የተቀበልኩት አንዳች ፍቅር የለም፡፡ ቃል አውጥታ <<እኔ ላፈቅርህ
አልችልም ብላኛለች፡፡>> ከቀን ወደ ቀን ምን ፈልጋ እንደምትመጣ ሁሉ
ግራ ይገባኛል... ምናልባት ቶሎ ራሷን መስጠት እኔጋ ያላትን ዋጋ
የሚቀንሰውም መስሏት ይሆናል፡፡ የሁለትዮሽ ፍቅር ከሚመስል ነገር ወደ
አፍቃሪ ተፈቃሪ መንገድ ውስጥ መቼ እንደገባን እንኳ ማስተዋል ያቅተኛል፡፡
ያየን ሁሉ <ናቸው> ብሎ የሚገምተው እና እኛ <የሆንነው> ይራራቅ ነበር፡፡
ከቀን ወደ ቀን ተራራቅን... ከአካል ሳይሆን በሀሳብ... ተቃቅፎ መራራቅ
በየትኛው ቃል ይገለፃል? ቃል አለው? ተፅፎ እፎይ የሚባል አይነት?
~
ሌላው ተከድኖ ይብሰል!
የማፍቀር ዋጋው ህመም ነው፡፡ ታመህ የምትገዛው ደስታ ፍቅር ይባላል...
<ትላንትና ነገ የራሳቸው ጉዳይ!> ብለህ የማለፍ ግድየለሽ ልቡናን
ፈልፍለህ ትፈጥራለህ፡፡ የአወዳደቅ ጥሩ የለውም... በፍቅር መውደቅ ግን
እየቆየ የሚደምቅ ጌጥ ነው፡፡ ልደግመው ብፈልግ የማልችልበት አይነት
አወዳደቅ፡፡ በልቤ የሚያብረቀርቁ የነበሩ የማፍቀር ድፍረት አንዳንዶቹ
ስወድቅ ረገፉ...
<እሷ> ውስጥ ያለ ሌላ ቀለም ውበት በምን ይገለፃል፡፡ ይሄስ እድለኛነት
አይደል? በኑሮህ አሻራ ላይ የፍቅር ጣት ይነካሀል፡፡ አንተ እድለኛ ነህ...
ትወዳለህ... ትርቃለህ... ሰፌድ መሳይ ጉዞ ነው፡፡ ክብ... ግን የማይገጥም፡፡
አንዱ ከአንዱ የሚለያይ ይመስልሀል... ግን በፍፁም፡፡ መንገዴ
አያሳፍረኝም! እኔነቴ ጋር ፀብ የለኝም፡፡ እኔ የአጋጣሚዎቼ ውጤት ነኝ...
እኔ መንገዴን መስላለሁ፡፡
~
ህይወት ሸጋ ፈጣሪ ነች! ነገህ ላይ ደግሞ ሌላ አይነት መቀራረብና
ማፍቀርን ትፈለስፋለች፡፡ ካለመኖር ውስጥ ጣዕም መዝዛ ከምላስህ ጫፍ
ታኖራለች፡፡ ጉዞው ወደ ምንምነት ስለሆነ እሱም ይደርቃል፡፡ ደግሞ ሌላ...
ደግሞ ሌላ... ደግሞ ሌላ...

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 4

ጥብቅ ቁጥጥር በማዕከሉ እንዲደረግ ትዕዛዝ ተላልፏል ሁሉም በሮች በተለያዩ መንገዶች በእይታ ውስጥ ናቸው ዛሬ ከማዕከሉ ጎብኚም የበገና ተማሪዎችም የሉም ከቀሩት ትንሽ የፅዳትና የጥበቃ አባላት ውጪ ማዕከሉ ውስጥ ዛሬ የበገና ድርደራ አይሰማም በተለይ ትላልቅና ነባር በገና የሚገኙባቸው ክፍሎች ተጨማሪ ሀይል ተመድቦ በእይታ ውስጥ ናቸው ከበገና ማዕከሉ በተጨማሪ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ያለው መንገድ ሰው ዝር እንዳይልበት ተደርጓል
ጴጥሮስ የለኮሰውን ሲጋራ ይዞ ይንጎማለላል የለበሰው ጥቁር ጃኬት ከዛ ግዙፍ ቁመቱ ጋር ተዳምሮ ሚፈለገው ዘራፊ እሱ ይመስላል ወደዚ ከተማ ከመጣ በሁዋላ ይሄን የበገና ማዕከል ብዙ ጊዜ ተመላልሶበታል ዛሬ ግን ለጉብኝት ሳይሆን ማዕከሉን ሊጎበኙ ከሚመጡ ዘራፊዎች ማዕከሉን ሊታደግ ተገኝቷል
በማዕከሉት ውስጥ ያሉት ስዕሎችና ቅርፃ ቅርፆች ስበውታል ዛሬ ምን ፍለጋ እንደሚመጡ ባያውቅም ግምቱ ከማዕከሉ መሀል ክፍል ከሚገኘው ትልቁ በገና ላይ እንደሚሆን ጠርጥሯል ከአምስት የሚበልጡ ጠባቂዎች ለመካከለኛው ክፍል ብቻ መድቧል ካሳሰበው ምንም ቢሆን እንደሚያደረግ አውቆቷል ስዕሎቹን እየተመለከተ ሲዘዋወር ትንባሆ ማጨስ የተከለከለ ነው የሚለውን ፅሁፍ አይቶ ፈገግ አለ ከፅሁፍ በላይ ህጉ እዚ ቆሙአል ብሎ ለራሱ ነገረው በራሱ ተማምኗል እሷም አስደንቃዋለች በሶስት ወር ያልደረሰበትን አልያም ከዛ በላይ ጊዜያት ለማወቅ ሊፈጅበት የሚችለውን ጊዜ አቅልላለታለች የጭንቅላት ጨዋታ ብዙ ባይችልም ቡጢ የሚሰነዝረው ከአይምሮው በሚመጣ መልእክት ነው ብሎ ያስባል ጭንቅላቱ በጣም እንደሚሰራ ያውቃል ይሄን ሶስት ወር ግን ጭንቅላቱ ቆሙአል እጆቹም ሚሰነዝሩት ቡጢ የለም እንደ ቀድሞው አባሮ ሚይዘው ሌባ የለም ከእግር የፍጥነት ሩጫ ቆንጆ የጭንቅላት ጨዋታ እንደተዋወቀ ገብቶታል ቡጢውን ለመሰንዘር እንደ ሶልያና አይነት ከእግር ሩጫ በፈጠነ አስተሳሰብ የሚያስብ አጋር ያስፈልገው እንደነበረ ገብቶታል ዛሬ እጆቹ ለቡጢ ተዘጋጅተዋል ቀላውንም ለቆ ኢላማውን ከመታ ድፍን ሶስት ሆኖታል የእጅ ሽጉጡን ከጀርባው አውጥቶ በመዳፉ ዳበሰው
ዛሬ የናፈቁትን ነገሮች ማድረግ ሊጀምር እንደሆነ አውቋል ድል ከቀናው እንጀለመደው ወደ ሚወደው ባር ሄዶ ኦሪዮ በእስፕራይት ለመጠጣት ጓጉቷል መሸትሸት እያለ ነው ብዙዎቹ ቀስ ባለ እርምጃ ይራመዳሉ እሱ ብቻ ቆሞ ለምን ይህን ሁሉ ነገር እንደሚያስብ አልገባውም እስካሁን አልታየችውም ለነገሩ ካለቦታዋ ምትገኝ አይነት አይደለችም አለ በልቡ አሁንም ግን አይኖቹ ሶልያናን ይፈልጋሉ

የምሽቱ ፀሎት በውሀው ጉርጓድ ዙሪያ ተጀምሯል ጨረቃ ዛሬም እንደደመቀች ናት ኮኮቦችም ከሰማዩ ላይ በዝተዋል ጀርባዋን ከብዷታል ጭንቀት ሊያጠቃት መሆኑ አስደንግጧታል ምንም ነገር ግን እንደማትፈራ ታውቃለች ምንም ቢመጣም ለመቀበል መፅሀፍ ቅዱሷን ገለጠች
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል (ምሳሌ12:25)
ለነሱ ያነበበች ቢመስላትም ዛሬ ለሷም ጭምር ቃሉ እንደሚጠቅም ልቧ ነግሯታል
ምታደርገው ነገር ሁሉ ለሷ ትክክል ነው አሁንም ልቧ ልጭንቅላቷ መልእክት ይልካል ጨረቃ ልጆቿን የትም ጥላ አትሄድም በማትበራበት ጊዜ እንኳ ለልጆቿ እየታየች ብርሀኗን ትሰጣለች ሁሌም አብሬያችሁ ነኝ
ሁሉም መጽሀፍ ቅዱሳቸውን አውጥተው ማንበብ ጀመሩ
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል (ምሳሌ12:25)
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
የድምፃቸው ሀይል ያስደነግጣል የፀሎት ማሳረጊያ የሆነውን የጉርጓዱን ውሀ እየተጎነጩ በሰልፍ ደረጃውን ወረዱ
ብቻዋን የቀረች አንድ ሴት ግን አለች

መቁነጥነጥ ጀምሯል ከነጋ ያጨሰውን ሲጋራ እሱም አያውቀውም አስሬ ሰአቱን ይመለከታል አሁንም እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አደረገ ጃኬቱን ወደ ላይ እንደሰበሰበ ረጋ ያለ የበገና ድርደራ ይሰማው ጀመረ ጆሮው ቆመ ከመቅፅበት ረጋ ያለው ድርደራ መፍጠን ጀመረ አይኑን ጨለመው የማዕከሉ ሀይል ተቋርጧል ብዙ ግርግር ተፈጠረ የበገና ድርደራው ይበልጥ መፍጠን ጨምሯል ብዙዎቹ ጠባቂዎች የእጅ ባትሪዎቻቸውን አብርተዋል ስልኩን አውጥቶ ቁጥሮች መታ በፍጥነት ተጨማሪ ሀይልና የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች እንዲላከኩ አዘዘ በፍጥነት የበገናውን ድምፅ ወደ ሚሰማበት አቅጣጫ ተፈተለከ

ይቀጥላል....
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
"ወንድአገረድ ናት ይላሉ"
[ ዶ|ር ዮሴፍ ወርቅ ነህ ]
.....True story.....

እያንዳንዷ የሽፋሏ ፀጉር በቄንጥ ነው የተደረደረችው ። አንዷ ተመዛ ብትወድቅ
ከውበቷ የሆነ ነገር የምታጎድል ትመስላለች። ቆንጆ ናት ። ልቅም ያለች ቆንጆ ። የተስተካከለ ቁመና አላት ። የፋንታ ጠርሙስ ብቻ ነው እንዲ ተመጥኖ በቅርፅ ሲሰራ ያየሁት ወደህክምናው ክፍል ገባችና ጠርዙ ላይ ቂጢጥ አለች። ቁጭ ስትል ራሱ የተንዘረፈፈ ቢጫ ቀሚሷን በቄንጥ ሰብሰብ አርጋ ነው ። ለወንበሩ የሳሳችለት ትመስላለች። ካርዷ እጄ ላይ ስለነበር በስሟ ጠራኋት
" ማርያማዊት እንዴት ነሽ "
" አለሁ "
" ምን እንተባበር "
" ምንም " መሬት መሬት እያየች
" ግዴለም | ነፃ ሁኚ ። የሆንሽውን ንገሪኝ። ከሀኪም ምንም የሚደበቅ ነገር
የለም እሺ "
" እሺ "
" ምንሽን አሞሽ ነው "
" አልታመምኩም " ፍርሃቷ ሆስፒታል የመጣች ታካሚ ሳትሆን | የተማረከች
የጠላት ወታደር ነው ምትመስለው
" ታዲያ እዚህ ለምን መጣሽ ሜሪ "
" መውለድ አልቻልኩም "
" ታዲያ ይሄ እኮ አያስፈራም ። ምን ያህል ጊዜ ሞከርሽ ለመውለድ "
" አልሞከርኩም " ግራ መጋባት ጀመርኩ
" ባለትዳር ነሽ ? "
" አይደለሁም " ለምን እንደሆነ አላውቅም ። ልቤን ግን ደስ አለው ። እንኳን ባል አልኖራት
" ምን ያህል ጊዜ ግንኙነት አድርገሻል "
" ድንግል ነኝ " ቀጭን የእምባ መልዕክተኛ በአፍንጫዋ ጠርዝ በኩል አሳብራ ከናፍሯን ሰንጥቃ ገባች ። ከንፈሮቿ ለመርገብገብ ያሰፈሰፉ የቢራቢሮ ክንፎች ነው ሚመስሉት ነርሷን በምልክት ጠራኋትና በቀስታ ወደሳይካትሪ ክሊኒክ ሊንክ እንድትደረግ
ስነግራት ማሪያማዊት ተስፈንጥራ ተነሳች ። " አልሄድም | ሁላችሁም የአዕምሮ ህመምተኛ ነው ምመስላችሁ " ስታጉረጠርጥ የእቴጌ ጣይቱ አይን እንደሷ አያስፈራም ! ያ ሁሉ አይናፋርነት እንደመስከረም ዝናብ ተንቸፍችፎ በነነ ። ስትጮህ ራሱ ለጠብ ሳይሆን ለማህሌት የተቀለፀ ድምፅ ነው ያላት ብቻችንን ማውራት እንደምትፈልግ ስትነግረኝ ሲስተር በሩን ከፍታ ወጣችላት ።
ከዛ በኋላ ማውራት የጀመረች የእኔ እምባ ከአይኔ ጋር ሲተናነቅ ነው ያቆመችው ቀሚሷን ከፍ አርጋ አሳየችኝ ። ነዘረኝ ። የድንጋጤ ንዝረት ። በህይወቴ እንደዛ ደንግጬ አላውቅም ። ብዙ አሰቃቂ ነገሮችን አይቼ አውቃለሁ ። እንደዚህ ግን ተሰምቶኝ አያውቅም ማርያማዊት ወንድም | ሴትም ናት ። ሁለቱንም የመራቢያ አካላት ፊትና ኋላ
ተሰልፈው አየኋቸው ። እሷ ስሜቴን ለማንበብ አይኔ ላይ አፍጥጣለች ። የመሳቀቋ መጠን አባቷ እናቷን ሲደበድብ የምትመለከት ህፃን ልጅ ነው ምትመስለው
" ማርገዝ እችላለሁ ዶክተር ? "
አዕምሮዬ ውስጥ መልስ ሳይሆን ጥያቄ ነው ያለው
" ከማን ? "
ብዙ ብዙ አወራችኝ ። መውለድ ካልቻለች ራሷን ማጥፋት እንደምትፈልግ , በህይወቷ ከልቧ ስቃ እንደማታውቅ | እንዲህ አይነት ልጅ መውለዱን ሲያቅ
አባቷ ከእናቷ ሸሽቶ እንደጠፋ | እናቷ ከሰው ደብቃ ብቻዋን እንዳሳደገቻት | አጎቷ ሊደፍራት ሞክሮ በድንጋጤ ራሱን እንደሳተ | አጎቷ ይሄን እውነት ከሚያውቅ ሺ ወንዶች እየተፈራረቁ ቢደፍሯት ትመርጥ እንደነበር | ከአዲስ አበባ ሸሽታ
የማያውቋት ሰዎች መሀል ለመኖር ሶዶ እንደገባች | ከሶዶ ሀዋሳ ድረስ በማያውቃት ሀኪም ለመታየት እንደመጣች | ሰይጣን ክፉ እንደሆነ | ሰዎች ከሰይጣን በላይ ክፉ እንደሆኑ | እግዜር ከሁሉም በላይ ክፉ እንደሆነ | ማርገዝ ከቻለች አንድ ወንድ ጨርቅ እስኪሆን አስክራ አብራው ማደር እንደምትፈልግ | ማንም ሰው እንዲያውቃት እንደማትፈልግ | ሰው ይሄን ሚስጥሯን ከሚያውቅባት እንደጴጥሮስ ዘቅዝቆ ቢሰቅላት እንደምትመርጥ | ከእናትና አጎቷ ቀጥሎ ይሄን ሚስጥር ያካፈለችው ሶስተኛ ሰው እኔ እንደሆንኩ ምንም ከማለቴ በፊት እያለቀሰች ክፍሉን ለቃ ወጣች። ሲስተር ቀስ ብላ ገባችና መስማት ማልፈልገውን ነገር ነገረችኝ
" ዶክ ይህቺን ልጅ ሀገር ምድሩ እኮ ነው ሚያቃት ። ወንድአገረድ ናት ይላሉ "
ከፋኝ 😟

[ነጋቲ]

@wegoch
@wegoch
@paappii
ልብምታት

°°ከጥቁርና ነጭ ማስታወሻ የተወሰደ°°

በዘመነ ቁንጣናም ተወልዶ መሞት እንዴት ይቀፋል? አስተማሪ መሆን
እንዴት ይቀፋል? ነጭ ጋውን እንዴት ያስጠላል በማሪያም? አንዳንዴ ነጭ
ጋውኔን ተጣብቆ አልላቀቅ እንዳለኝ ወንድ አየዋለሁ... ከኀላዬ ሞልቶኝ...
አንገቴንም... ደረቴን ይዳብሳል... ወርዶ አይወርድም... ከባቴ ነው
የሚመለሰው... በአረማመዴ ልክ ይራመዳል... ሲቆሽሽ አውልቄ የምጥለው
ልፍስፍስ ትንፋሻም... አየው አየውና ንፁህነቱ ይጠፋኛል! በያዝኩት ብዕር
ላዩ ላይ የሆነኛ ፅሁፍ እጭራለሁ... ቆሸሸ ማለት ነው? እና ምኑን ንፁህ
ነበር? ንፅህና ያለመቆሸሽ ዋስትና ከሌለው ምን ያደርጋል? ሲገባኝ ግን
ንፁህ ማለት ቆሽሾ የጨረሰ ነው... ከዚያ ወዲያ የማያድፍ ፍፁም፡፡
የንፅህና ጥጉ እስከመጨረሻው በማደፍ መዝለቅ ነው፡፡
ለዚያ ነው እንከን የለሽ ወንድ አልወድም... መስለው ሊያጭበረብሩኝ
ሲጥሩ ኦቾሎኒ የሚታክል ጢኒጥዬ ልቤ በሳቅ ትነጥራለች፡፡ ከሚያበራ
ንፁህ አይን ስር ያሸመቀ ስድ እይታ ማውጣት እችልበታለሁ... ከሚያምር
ከንፈር እና መልክ ላይ የጥቁርን ጥላ የሚመስል... ከመጥቆር የጠቆረ
ማንነት አላየሁም? ካልካድኩ የጠለዘኝ ብዙ ነው... ምን አስካደኝ? እሱ
እሱ ተደምሮ እዚህ ላይ የደረስኩ እኔው ተመራማሪ እኔው መመራመሪያ
የሆንኩ ነገር ነኝ፡፡


ስንሸዋወድ የሚነጋ ነገ ላይ ነቃሁ! ሞሽላቃ ፊት ነው የማየው... ሁሉም!
ሌላውን አይደለም ራሳቸውን ሰርቀው... እኔነታቸውን ገድለው... ራሳቸው
ላይ አመንዝረው... በራሳቸው ቀንተው... ራሳቸውን ዋሽተው... ከራሳቸው
ውጭ አምልከው... ሲያበቁ... ጥቁር ሰይጣንን ለመሸሽ ነጭ እግዜር ጋር
የሚሄዱ... ከአንዱ ሲጠጉ ከአንዱ የራቁ የሚመስላቸው ፃድቃን መሀል
ራሴን ማየት እወዳለሁ፡፡
ወደ ቤተ ክርስቲያን ልሄድ ነው... በሩ ጋር ደርሼ ልስም፡፡ ስስምስ? ላብ
ያጠቆረውን ደጀ ሰላም... ሁሉ የሳመውን ስስም... የማልስመው የለም!
የማይስመኝ የለም! እግዜርን የወደደ ይወደኛል... የተመኘኝንም
የተመኘሁትንም... የናኩት የናቀኝ... ማንም ሳያውቅ... እኔና እግዜር ብቻ
የተመሳጠርን አይነት፡፡ ደጋግሜ ስማለሁ...
ደጀ ሰላም ላይ የተሳለ ስንት ከንፈር አለ? ለእኔና ለእግዜር የሚታየን...
ለማንም የማንናገረው... አፋችንን ሸፍነን ወዳጅኛ የምንስቅበት አሳሳም፡፡
ልስም ነው የምሄደው! እግዜርን አይደለም! ህዝቡን... ምናልባት አንድ
አለም የሚያክል መዝገብ ይኖራል... <ከመ ወከንፈር ውስጠ ልብየ
አለሙ> የሚል ርዕስ ያለው፡፡ ከልብ የተሳሙ ከንፈሮች ዝርዝር እንደ
ትውልድ ቆጠራ የተፃፈበት... ልክ አብርሀም ይስሀቅን ወለደ... ይስሀቅ
ያዕቆብን ወለደ አይነት አወራረድ የሚወርድ፡፡ እመኑኝ እሩቡ የኔ ስም ነው፡፡
ሊያ... ሊያ... ሊያ... ሊያ... የሚል፡፡ ቁልቁልም የሚፃፍ... ፀሀፊው <በአት>
የሚባል አንድ እጅ ያለው የማይበር መልአክ ነው፡፡ ይሄንን አስብና
የመጃጃሌ ነገር ገርሞኝ ፈገግ ስል አንዱ ደግሞ ሲያፈጥብኝ አየዋለሁ...
ነጭ እግዜር ሲቀርቡ ጥቁር ሰይጣን አይሸሽም፡፡ ይልቁኑ ከቀረበን በላይ
ይቀርብና በቀዝቃዛ ምላሱ ግንባራችንን ይልሳል፡፡ ይሄ ልጅ ባየኝ አይን
ብዙዎች አይተውኛል... መንገዱን አውቀዋለሁ... ስሄድ እንደሚከተለኝ...
መጨረሻውንም ጭምር... ሲኦል እሳት መሆን የለበትም! የሚሆነው
በሚታወቅና በሚደጋገም አለም ውስጥ መጨመር መሆን ነበረበት፡፡
በስልችት እሳት...


ሲራክን ሳየው ቆንጆ አይደለም... ላገኛቸው ከምችላቸው ወንዶች ምኑም
ነው እሱ... ጫማ የማይቀይር መናጢ ነው ሲጀመር፡፡ እና ለምን
ወደድኩት? እኔና እሱ ግልባጭ ነን... ተቃራኒ ነን! ያልሆንኩትን ነው...
ያልሆነውን ነኝ...
የመበላለጫ ምክንያቶቻችን ሲቆጠሩ እኩል ካልመጡ ልቀጣ፡፡
ግድ የለሽነቱን ወድለታለሁ፡፡ የስልችት ፍዘቱን... ሳስተምር እየነቃ የሆነ
ነገሬን ያያል...
<የሆነ ነገር> ግን ምንድነው?
የአካል ስም ከሌለው የሆነ ነገር እንዴት existence አለው ልንል
እንችላለን፡፡ ካለውም ደግሞ የማንጠራቸው ግን ያልተስተዋሉ እልፍ
ስሜቶች የሉም? አሉ አይደል? እነሱን ያስተምረኛል ሲራክ፡፡
በየ አስቀያሚነት ውስጥ... በየ ማስጠላት ውስጥ ያለ ህይወት ነቃቅላ
የጨረሰችው ውበት ይታየኛል፡፡
እውነት ፊት ለፊት ሲታይ አይስብም! በቀዳዳ በኩል እንጂ... በጨረፍታ
ነው ውበት መልኩ የሚጎላው... ግልፁማ ግልፅ ነው... ወደ የት
ይመራል? መልስ ያለው ጥያቄ ጥያቄነቱ ምኑ ላይ ነው?


የህላዌ ጉዞ ወደ ምንምነት ነው... ወደ ኪሳራ ቀስስ እያለ ይጎተታል...
ከቀን ወደ ቀን ይጓዛል... ከውበት መልክ ላይ አንድ ፍሬ እየነቀለ... ከውብ
እኛነታችን አንድ እርምጃ እያራቀን... እየቀነሰን...፡፡
ይህች አለም ውብ ታሪክ የላትም! ውቦችን የማጥፋት ታሪክ እንጂ!
ካበቀለችው ውበት ይልቅ የምትቀጥፈው እልፍ ነው... ጉዞዋ ወደ መርገፍ
ነው!
(ቆንጆ ነበረች...) ጠዋት ነበረች! በቅንጣትነቷ ውስጥ መግዘፍን
ታውቅበት ነበር ይሉኛል?


@wegoch
@wegoch
@wegoch
"ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል እኔ ግን ወሎዬ ይግደለኝ እላለሁ ብዙ ጊዜ:
.
.ወሎ አንድ እስላም አንድ በግ ያርዳል አርዶ ክርስቲያኑ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይላል እርሱ ቢስመ አላህ ኢረ አማን ኢረ አሚን ..
.
አንድ ቃል ነው በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንደ ማለት ነው።
.
አንዱን በግ አርደው ይሄ በወዲህ በኩል ይጠብሰዋል ያም በወዲያ በኩል ይጠብሰዋል ከዛ በሰላም በፍቅር ይመገባሉ: ይሄ በየትም ሀገር ላይ የሌለ ብስለት ነው "

(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን)
@wegoch
@wegoch
@poem_with_mela
በየነ ከሰሞኑ ምን ሆነ?

(በእውቀቱ ስዩም)

(ይህ ፅሁፍ ካስራ ስምን አመት በታች ለሆኑ አንባቢያን እርም ነው)
እኛ ኮረና ፈርተን ባደፈጥንበት ጊዜ ጉዋደኛችን በየነ የገነት አበባ
የመሰለች ልጅ ጠበሰ ፤ ልእልት ትባላለች! ለሁለት ወራት ያክል ደጅ
ካስጠናችው በሁዋላ ድንግልናዋን ሰጠችው፤ ውሸቴን ነው! ድንግልናዋን
የነበረበትን ቦታ አስጎበኘችው::
ከዚያ ጠፋች፤
በስንት መከራ እንደገና አገኛት፤
“በዩ ! ግልፅ እንድሆንልህ ትፈልጋለህ?”
አለቺው ፤
“ አዎ! “
“ በጣም በጣም ግልፅ? ”
“አ..ዎ “
አለ ልቡ እየፈራበት
“ የምኝታው ነገር ይቅርብን! አልቻልክበትም ”
‘ እስካሁን እንዳልጎዳሽ ብየ ለኮፍ ለኮፍ ነው ያደረኩሽ ፤ አሁን አንድ
እድል ብቻ ስጭኝ! ሌቱን ሙሉ በደስታ ላስለቅስሽ” አለ በየነ በልምምጥ!
“ ርግጠኛ ነህ?”
“ አቡነ ዘራብሩክን! ለክፉ ቀን ቆጥቤው ነው እንጂ የፍቅር ሸማኔ ነኝ”
“ እስቲ እናያለን! ”
ከዚያ ራት በሉ ፤ ተጫወቱ፤ ወይን ጠጡ፤ ሶፋ ላይ ተሳሳሙ! በየነ
ከራባቱን አንስቶ ወረወረ፤ ሸሚዙን አውልቆ አሽቀነጠረ፤ ለመጀመርያ ቀን
ውሃ ዳር የቆመ የዋና ተማሪ መስሎ ርቃኑን አልጋው ዳር ተገተረ፡፡
ልእልት ፤ አልጋው ላይ ጋለል ብላ ፤ አንድ እግሩዋን ወደ ምእራብ አንድ
እግሩዋን ወደ ምስራቅ አሰማርታ የየወፍ መንደፍያ ባላ መስላ
ጠበቀችው፡፡
በየነ ለሰኮንዶች ያክል ወልመጥ ወልመጥ አለና እንደ ተወጋ ሰው
አአአአአአአ ብሎ ደረቱዋ መሀል ተገነደሰ!
በረረረረጂሙ ተነፈሰችና " it is ok " አለቺው፤
በረጅም ትንፋሽዋ ውስጥ ካዳመጠው ቅሬታና ብግነት አንፃር it is ok
የሚለው ቃሉዋ የሚያፅናና አልነበረም ፤
በየነ ለጥቂት ደቂቃ ያህል ድምጡን አጥፍቶ ከቆየ በሁዋላ ፤ አንጀት
በሚበላ ድምፅ እንዲህ አለ፤
“ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ፤ የሰራ አከላቴን ሰቅዞ ይዞት ነው እንጂ፤
በደናው ቀንማ በድቼ በድቼ እማባራ ሰው አልነበርኩም”

@Wegoch
@Wegoch
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 5

በህይወቱ እንደዚህ በፍጥነት ሮጦ አያውቅም ድካሙ የታወቀው የበገናው ድምፅ የሚሰማበት ቦታ ላይ ሲደርስ ምንም ሰው አለመኖሩና የበገናው ድምፅ የወጣው ከክፍሉ ካለው ትልቁ የድምፅ ማጉያ መሆኑን ሲረዳ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግራ ገባው ሙሉ ለሙሉ የማዕከሉ ሀይል እንዳልተቋረጠ ሲረዳ ከቅድሙ በላቀ ፍጥነት ወደ ሀይል ክፍሉ አመራ ብዙዎቹ የተመደቡት ጠባቂዎች አልተረጋጉም አሁንም የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ለማወቅ ወዲ ወዲያ ይላሉ
ጴጥሮስ ወደ ሀይል ክፍሉ የሚወስደውን ኮሪደር በፍጥነት አቋረጠ በሩን በርግዶ ሲገባ የእጅ ሽጉጡን ከመቅጽበት አውጥቶ ደቀነ በያዘው የእጅ ባትሪ ሙሉ ክፍሉን ቃኘ አንዳንድ የሀይል ቆጣሪዎች በርተዋል ሌሎቹ ግን ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል ጠጋ ብሎ የጠፉትን ቆጣሪዎች አበራ ወዲያው ያለበት ክፍል መብራት በራ በክፍሉ ውስጥ የሚገኙትም ማሽኖች መስራት ጀምረዋል ሀይሉን ይመልስ እንጂ ወደ ውስጡ የገባውን ብስጭት እንዴት መመለስ እንዳለበት አላወቀም
ሲበር የመጣበትን ኮሪደር እያዘገመ አቋረጠው ሙሉ ለሙሉ የማዕከሉ ሀይል ተመልሷል ዘግይተውም ቢሆን ተጨማሪ ሀይሎችና የሀይል ሰራተኞች በማዕከሉ ተገኝተዋል
ጴጥሮስ ወደ መሀከለኛው ክፍል ሲገባ ያየውን ነገር ማመን አቅቶታል ጠርጥሮት የነበረው ነገር ተከሰተ ዛሬም አነስ ያለች መጽሀፍ ቅዱስና ያቺ ትንሽ ሳንቲም ተቀምጦ አገኘ ቀና ሲል ከበገና ማዕከሉ የሚገኘው ባለ በሩ በገና ተከፍቶ አጊንቶታል ርዝመቱ እስከ 8 ሜትር ድረስ የሚጠጋው በገና አነስ ያለች በር ነበረችው ከበሯ ላይ
አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀሉ መዝ 42/43-4
የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበታል ጴጥሮስ በውስጡ ምን እንደሚያስብ ባያውቀውም ከተከፈተው በር ውስጥ የተወሰደ አንድ ነገር እንዳለ አውቋል የሀይሉ መቋረጥ እንደተፈጠረ በተነሳው ግርግር ውስጥ የተፈፀመ ስህተት እንደሆነ ገብቶታል አይኖቹ ደም ለበሱ
ማዕከሉን የሚያናውጥ ዜማ መሰማት ጀመረ ጴጥሮስ ሚሆነውን ለማወቅ አልቻለም ጆሮዎቹ ግን ዜማውን መስማት ጀምረዋል
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
ዜማው ያስፈራል በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ዛሬ ሌላ ያገኘው አዲስ ነገር ቢኖር ይህንን ዜማ ነው በፍጥነት ማዕከሉን ለቆ ወጣ የማትረባ የሚለው ድምፅ ከልቡ ወደ ጭንቅላቱ ሺ ጊዜ ይመላለሳል

ሁለቱንም ዜማ የከፈቱላችሁ ሲገቡና ሲወጡ ፍንጭ ላለመስጠት ነው አላስተዋልክም እንጂ ሁሉንም የካሜራ ቅጂዎች ብትመለከታቸው ኖሮ ተመሳሳይ ወዴ በሁሉም ቦታዎች ላይ ተጠቅመዋል መጨረሻ ላይ የሰማኸው ዜማ በሁሉም ዝርፊያ በተፈፀመባቸው ማዕከሎች ውስጥ ተቀድቶ ተቀምጧለሰ ከመለከለኛው ማዕከል ውሰጥ ያስቀመጥካቸውን 5 ጠባቂዎች ከፊት ለፊት ማንሳት ነበረብህ ደሞ ጥቅሱ ምን እንደሚል አንብበኸዋል ከጀርባው ሆና ብዙ ብታወራለትም ጀርባውን ሰቶ የለኮሰውን ሲጋራ ጦፎ ይምገዋል አይኖቹ ቅድም ሲፈልጓት የነበረችውን ሶልያናን ለማየት ፈልገዋል ዞሮ ተመለከት የለበሰችው ጥቁር ባርኔጣ አይኖቿን ሸፍኗቸዋል
ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው እንደ ሰማይ ጸዳል ያበራሉ
ዳን 12:13
የመጽሀፍ ቅዱሱ ጥቅስ እንዲህ ነው ሚለው ከኛ በላይ ብዙ እንደሄዱ ሊነግሩን ፈልገዋል አስተውለከው ከሆነ አንድ ሌላ ጥቅስ ጨምረውበታል
ጥበብ ጻድቅ መሆኗ በስራዋ ተረጋግጧል
ማቴ 11-19
መጽሀፍ ቅዱሱን ስመረምር ያገኘሁት ጥቅስ ነው ንቃ እንጂ ጴጥሮስ ፈዞ ሚመለከታትን ሰው ጮኸችበት እየሰማት እንደሆነ ቢያውቅም የሆነውም የነገረችውም ነገር አስገርሞታል 40 ቁጥርን ለምን ዘለልሻት አላት ስቦ ያስገባውን የሲጋራ ጢስ መልሶ እያወጣ
ነገሩ ያስደነገጣት አይመስልም ያልደረስኩበት አንድ ነገር ስለነበረ ነው ነገ ጠዋት ሁሉንም እነግራችኋለሁ 6 ቁጥርን ደሞ አንተ ረስተሀታል መሰለኝ አለችው የምፀት ሳቅ ስቃ ጥሏት ሊሄድ ወሰነ....

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/29 21:27:40
Back to Top
HTML Embed Code: