Telegram Web Link
ከደዌአችንን እንፈወሳለን፡፡ የመንፈስ ችግራችንን እንደ እውነት ከተቀበልንና ከደዌአችን ጋር መኖርን ካስቀደምን ሞት ቅርባችን ነው፡፡ መሞት ብቻ ሳይሆን ቀባሪ ያጣንም እንሆናለን፡፡

@wegoch
@wegoch
እሷ ማሪያ ትባላለች።
እናቴ ነች።
በዚያኛው በኩል የምታዩት ምስል ደሞ አባቴ ሴፍ ይባላል።
ከኔ ውጭ አንድ ሴት ልጅ አላቸው።
የልብስ ስራ በመስራት ቤተሰቡን ያስተዳድር ነበር። በአንድ ወቅት ጓደኞቹ ወደ ቤት መጡ።
ጀርመን ጠረፍ አካባቢ ስራ አለና እንሂድ አሉት። ባለው ገንዘብ ቤተሰቡን ማስተዳደር የከበደው ሴፍ ወሰነ። አብሮ ሄደ። እዚያ እንደደረሰ ግን ጥሩ ገንዘብ መላክ ጀመረ። እኛም ዘና አልን። እየቆዬ ግን ገንዘብ መላክ አቆመ። ምነው ሲባል በ1942 የሃገሬው መንግስት በማስገደድ ወደ ውትድርና እንደላከው ሰማን። በተመሳሳይ ጀርመን በከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገባች። የቤተሰቡ ጭንቀት
ከፍተኛ ነበር። ከሁለት አመታት በኋላ እናታችን ማርያ ዊናንዶ በመባል የሚጠራው ታዋቂ ሰውን ለመጠየቅ እድል አገኘች። እሱም "ሴፍ ደህና ነው። በፀደይ ራት ይመጣል" አላት። እናታችን እየበረረች መጣች። ትፍለቀለቃለች።
ቤቱን ማስተካከል ጀመረች። ግቢውን አረንጓዴ ለማድረግ ለፋች። ምክንያቱም
ፀደይ እየገባ ነው። ለአባታችን አምራ ለመታየት ተቆነጃጀች። ሁሉም ተደረገ።
ግን ፀደይ አለፈ፤ በቃ መጥቶ ሄደ፤ ድጋሜ ክረምቱ ሊገባ ነው። አባታችን ሴፍ ግን አልመጣም።
በአመቱ እናታችን አንድ ደብዳቤ ደረሳት። "ውድ ማሪያ፤ ባለቤትሽ ሴፍ በባለፈው
አመት በሬቨንፐርክ አርፏል" ይላል።
ነገር ግን እናታችን ማሪያ ከደብዳቤው ይልቅ የዊናንዶን ተስፋ መረጠች።
አባታችን አንድ ቀን ከጎኗ ሆኖ እንደሚያጫውታት አመነች።
26 አመታትን ይመጣል እያለች ጠበቀች። አባታችን በዛው ቀረ።
በየትኛውም ፀደይ ወራት እንደማይመጣ አወቅን። ከሁሉም ተስፋዎች የሚያመው የማይሆንን ነገር መጠበቅ መሆኑን አወቅን።

@wegoch
@wegoch
@paappii
የተለያዩ ሰዎች ቁጣቸውን (አለመስማማታቸውን) የሚገልፁባቸው መንገዶች። አብረናቸውም ለመኖር የሚረዱ ሙያዊ ምክሮች።
---------------
ሰው ከሰው ጋር ሲኖር ግጭት መከሰቱ የማይቀር ነው። ሁላችንም ከሥራ ባልደረባዎቻችን፣ ከቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኛችን ጋር ፍትሃዊ የሆኑ ክርክሮች እና ግጭቶችን እናስተናግዳለን። አንዳንድ ሰዎች ግጭትን ወይም አለመግባባትን በቀላሉ ተረድተው በጥበብ ነገሩን ማብረድ ሲችሉ ሌሎች ደግሞ ጭራሽ ትንሿን አለመግባባት አስፍተው ወደ ትልቅ ፀብ እንዲያመራ የማድረግ ባህሪይ አላቸው።

አለመግባባትን ተረድቶ እንደየሁኔታው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሰዎችን ባህርይ መረዳት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ለዚህም እንዲረዳ ቁጣን እና አለመስማማትንም በሚገልፁባቸው መንገዶች ረገድ ሰዎችን በ 4 ዋና ዋና ክፍሎች ያስቀምጧቸዋል። እያንዳንዱንም ሰዎች በጭቅጭቅ ጊዜ እንዴት ጭንቅላታቸውን ማንበብ እንደምንችል እና ምላሻችን ምን መሆን እንዳለበት እንደሚከተለው ይነግሩናል።

1. ነጭናጫ ሰዎች (Behavioral Anger)።

እነዚህ ሰዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ እና ሰዓት የምቆጡ ሰዎች ናቸው። ቁጣቸውንም በቃል ወይም አካላዊ በሆነ መልኩ ይገልፃሉ። ቁጣቸው በጣም አስፈሪ ብሎም እቃዎችን በመወርወር እና በመሳሰሉት ብስጭታቸውን ሊገለፅ ይችላል።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ በራሳቸው መተማመን ዙሪያ ክፍተት ያለባቸው፣ ስለነሱ መጥፎ ነገር ሲነገራቸው በቀላሉ የሚከፉ ሰዎች ናቸው። ምንም እንኩዋን ነገሮች ፈታኝ ቢሆኑም እራስዎ ተረጋግተው ነገሩን ለማረጋጋት ይሞክሩ እንጂ እሳትን በእሳት አይዋጉ። ምክንያቱም ቁጣቸውን የበለጠ ስለሚያባብስ። ተረጋግተው የተቆጡበትን ነገር እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጡት ይጠይቁ። ጥፋተኛው ማን እንደሆነ፣ ትክክል ወይም ስህተት የሆነ ማን እንደሆነ ለማስረዳት አይሞክሩ ምክንያቱም ጭንቅላታቸው በጊዜው ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ ለመወያየት ዝግጁ ስላልሆኑ። ለወደፊቱም ምቾት የማይሰጣቸውን ነገርም በተቻለዎ መጠን አይነካኩባቸው።

2. ኃይለ-ቃል ወርዋሪ፣ በነገር የሚጎሽሙ (Verbal Anger)።

እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ኃይለ-ቃሎችን በአሽሙር፣ በነቀፋ፣ እና መመሳሰሉት የቃላት ጦሮች በመወርወር ነው። አላማቸውም የሌሎችን ስሜት እና ስነ-ልቦና በመንካት ቁጣቸውን እና ቅሬታቸውን ለመግለፅ ነው ። ከተረጋጉ በኋላ ግን ብዙውን ጊዜ የሀፍረት እና የጸጸት ስሜት ይሰማቸዋል።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

የነዚህ ሰዎች አላማ ስሜትዎን እና ስነ-ልቦናዎን መጉዳት መሆኑን ተገንዝበው ለኃይለ-ቃላቸው ብዙም ቦታ እንዳይሰጡ ለራስዎ በደንብ ይንገሩት። ይህንም ሲያደርጉ አላማቸውን ማክሸፍ ይችላሉ።አንዳንዴም እንደሁኔታው እያዩ በወረወሩት ቃል ዙሪያ ቀልድን ፈጥረው ለመመለስ ይሞክሩ። ይህን ማድረግ በቃሉ አለመጎዳትዎን ያስገነዝባቸዋል፣ አንዳንዴም በመካከላችሁ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ይረዳል። ቃላታቸው ጠንክሮ ግን መስመር ሲያልፍ፣ ክስ ባልተሞላበት ነገር ግን በሰከነ እና ፈርጠም ባለ መንገድ መስመር እንዳለፉ ይንገሯቸው። ሁሉም ካልሰራ ግን ዝምታን መርጠው በራሷቸው ጊዜ እንዲበርዱ ዕድልን ይስጧቸው።

3. ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እና ለውጥ ለማምጣት የሚቆጡ (Assertive anger)።

እነዚህ ግለሰቦች ቁጣቸውን አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ይጠቀሙበታል። ሁኔታውን በጥሩ ሁኔታ እና በንፅፅር እያደረጉ በረጋ እና በዘመናዊ መልኩ ከሌሎች ጋር ያላቸውን ችግሮች በግልጽ ይነጋገራሉ። ከዚያም ከሌሎች ወገኖች ጋር ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ይወያያሉ።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ሆን ብለው እርስዎን መጉዳት ፈልገው ሳይሆን የነገሩን መለወጥ በመሻት ነው። ብዙ ጊዜም የሚፈልጉት ለውጥ አውንታዊ ለውጥ በመሆኑ ለመረዳት ይሞክሩ እና መረዳትዎን ይግለጹላቸው። ከእርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ለመስጠት ይሞክሩ፣ ለውጡንም ለማምጣት አብረው ለመተባበር ይሞክሩ።

ለምሳሌ በስራ ላይ ያለ ፕሮጀክትን እርስዎ እያጓተቱ መሆኑን አለቃዎ በምክንያት ቢገልፅልዎ፣ የነገሩን አሳሳቢነት መረዳትዎን እና እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ አብረው ይስሩ፣ ነገሩንም ለማሻሻል ቆራጥነትዎን ይግለፁላቸው።

4. በአፍ መስማማትን እየገለፁ ግን በሚያደርጉት ተግባራቸውን አለመስማማትን የሚያሳዩ (Passive aggressiveness)።

እነዚህ ሰዎች ያልተስማማቸው ነገር ሲኖር ፊት ለፊት መግለፅ (መጋፈጥ) አይወዱም። በቃላት ከመግለፅ ይልቅ መቃወማቸውን ቀስ እያሉ በድርጊታቸው መግለፅን ይመርጣሉ። ይህንም በማድረግ ሳይታወቅባቸው ሊያታልሉዎ ይሞክራሉ። አንድን ነገር በጋራ ለመስራት እቅድ ሲያዝ ባይስማሙበትም እሽታን ይገልፃሉ፣ ነገር ግን በሁዋላ እቅዱን ለማዳከም የሚረዷቸውን መንገዶችን ያፈላልጋሉ።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

በነገሮች ላይ ከነዚህ ሰዎች ጋር ሲስማሙ፣ ፍርጥም እና ጠንከር ባለ መልኩ ውሳኔዎችን ለማስቀመጥ ይሞክሩ። ውሳኔዎችን ለማዳከምም የሚያደርጉዋቸውን እንቅስቃሴዎች በንቃት እያዩ ወደዉሳኔው ለማምጣት ይሞክሩ። አለበለዚያ ግን ግልፅ በሆነ መልኩ ድርጊታቸው እንደማይስማማዎት በግልፅ አፍረጥርጦ መንገር ያስፈልጋል።


@wegoch
@wegoch
@paappii

ምንጭ: sewasew
ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፤አለቃውም መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን
አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም፤በማለት ፍቃድ
ይነፍገዋል!! ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፤ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው
ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤ አለቃውም”ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው
ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤ በማለት ይወቅሰዋል፤ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር !! አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም፤ ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን
ብነግርህ ትረዳኝ ነበር፤ አለቃውም ”ምን አለህ? ሲለው ወታደሩም ንግግሩ ቀጠለ....
«#እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ »!!
ጓደኝነት ፀጋ ነዉ ለሁሉም ሰዉ አልተሰጠም

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ከዙኪ ገፅ የተወሰደ
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል መኮንን)
#ይነበብ
ውድ የቴሌግራምና ፌስቡክ ጓዶች እንዴት ናችሁ?

መቼም በዚህ ሰዓት 'ሰላም ነው?' የሚለውን ቃል ከአንደበታችን እንዳናወጣ በሀገራችን እየሆነ ያለው ነገር ያስረናል፡፡

አዎ፡፡ እኛ ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን ጎን ነን !!! ኢትዮጵያ ምንጊዜም ድል ታደርጋለች፡፡ አዎ እኛ ከንግግር በዘለለ አንድ ነገር በጋራ ብናደርግስ ፡ ብለን ወሳኝ ጉዳይ ለማከናወን ተነስተናል፡፡

ይህ ጥሪ ለሁላችሁም ነው ህዳር 20 እሁድ እለት #የግጥም_አብዮት እና የ #ግጥም_ብቻ ከተሰኙት ግሩፕ ጋር ለመልካም ነገር ዘምታችሁ #ደሜን_ለሀገሬ እያላችሁ ትለግሱ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እኔ ከኢትዮጵያ ጎን ነኝ የሚል ሁሉ ደሙን ሰጥቶ አለሁልሽ ይበላት፡፡ መልካምነት ዋጋው ትልቅ ነው ወደ ህይወታችን ይዞ የሚመጣው በረከትም አያልቅም፡፡ ኑ ለመልካም እንዝመት! ሩቅ ያላችሁ በየትኛውም ክፍለ ሀገራት የሚገኙ #ለመልካም_ዘማቾች ቀኑን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቀይ መስቀል በመሄድ እለቱን ያስቡ፡፡

በዚህም መሰረት ፦

ህዳር 20 (እሁድ )
ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
ስቴዲየም ወደሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ግቢ ውስጥ እንገናኝ 🙏🙏🙏

*
Telegram
@Tkida and @gebriel19

#ለመልካም_ዘማቾች
#የግጥም_አብዮት
#ግጥም_ብቻ

📍📍📍 በዚህ ዘመቻ ላይ አብረን እንዘምታለን የምትሉ ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ ፡፡ #Share

📍📍📍 ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ሁሉ ቢያንስ ለ10 ሰው ይህንን በማካፈል ዘመቻውን እንቀላቀል/እንደግፍ 🙏

@getem
@getem
Huawei የቴሌኮም ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ እሰራ በነበረ ጊዜ ቻይኖችን
በጣም የሚያማርራቸው ነገር ቢኖር የዓመት በዓሎቻችን ብዛት ነበር።
አዲስ ዓመት አክብረን ወዲያው መስቀል ይመጣል። እኛም መስቀሉ የተገኘበት
ምናምን ነው ብለን ፈቃድ እንጠይቃለን። አለቃም ይሁን እሺ ይሁን ብሎ ይፈቅዳል። ከዛ ገና ላይ ፈቃድ ፈልገን ምክንያቱን ሲጠይቀን ጂሰስ የተወለደበት እለት መሆኑን ነግረነው መልካም በዓል ብሎ ሸኘን። ወዲያው ጥምቀት መጣና ጂሰስ መጠመቁን ምክንያት በማድረግ ፍቃድ ጠየቅነው። እየመረረው ፈቀደ። ፋሲካ ደረሰ። አለቃን ሰብሰብ ብለን ከአርብ አስከ ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ፈቃድ እንዲሰጠን ጠየቅነው። በምሬት: _"ጂሰስ ምን ሆነ ደሞ?" አለን።
"ሞተ" አልነው።
"ግልግል" አለ
ወዲያው አንዱ ከመሃላችን ''ኧረ እሑድ ይነሳል"

@wegoch
@wegoch
@paappii
#Alex mamz
መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው!

" አንድ ጥበበኛ ወጣት እጅግ በሚያምርና ዕይታን በሚስብ ወንዝ ዳርቻ ተቀምጦ ሳለ በንፋስ ተገፍቶ ወደ ውሃው የወደቀ እጅግ በጣም አስፈሪ ጊንጥ ይመለከታል ።

የጊንጡ ህይወት እንዳያልፍ ብሎ በማሰብም ይታደገው ዘንድ ወስኖ ሊያወጣው እጁን ወደ ወንዙ ሰደደ። ጊንጡ ግን ህይወቱን ሊታደግ ለሚጥረው ሰው ምላሹ መንደፍ ሆነ። በጊንጡ አፀፋ የተደናገጠው ወጣት በቅፅበት የሚነዝረው እጁን አነሳ።

ነገር ግን አንዲትም ደቂቃ ሳይዘገይ ስቃዩን እንደተሸከመ ለሁለተኛ ጊዜ የዚያን ጊንጥ ህይወት ለማዳን እጁን ዳግም ሰደደ። አጅሬ ጊንጥም ለሁለተኛ ጊዜ ተናደፈ። ወጣቱ በሲቃ ውስጥ ሆኖ እየተዝለፈለፈ የተነደፈ ጣቱን በጨርቅ ጠቅልሎ ለሶስተኛ ጊዜ እጁን ወደ ጊንጡ ከመሰንዘር አልቦዘነም።

ይሄን ጊዜ ድራማዊ የሚመስለውን ትዕይንት በቅርብ ርቀት ሆኖ ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው በመገረም እንዲህ ሲል ጮኸ

« አንተ ሰው! ምን እስኪያደርግህ ነው የምትጠብቀው ? እየነደፈህ ለምን ልታድነው ትጥራለህ ? ለምን አትገድለውም ?» ይለዋል።

ወጣቱ ግን ለዚያ ግለሰብ የሚሆን ጆሮ ያለው አይመስልም ። ላመል እንኳን አንገቱን ወደ ሰውየው ሳይመልስ ጊንጡን ለማዳን ጥረቱን ቀጠለ ። በመጨረሻም ተሳክቶለት ጊንጡን ከሞት ታደገው።

ከዚያም ቀድሞ ጊንጡን ስለመግደል ምክር ለግሶት ወደ ነበረው ግለሰብ እያማተረ እንዲህ ሲል በጩኸት ተናገረ

« ስማኝ ወዳጄ ... መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው ፤ የኔ ባህርይ ደግሞ ማዘንና ማሰብ ሆነ ። ታዲያ ስለምንድን ነው የኔ ባህርይ ከርሱ ባህርይ የከፋ እንዲሆን የምትመክረኝ ? » አለው።

//

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ እንዲህ እንደ ጊንጡ በመናደፍ እያቆሰሉህና እያደሙህ ፤ እየገዘገዙህና እየሸረከቱህ የሚመሳሰሉ ሰዎች ቢኖሩም እምነትህ ባጎናፀፈህ መልካም ሥነ ምግባር ልትገራቸውና ልታቀርባቸው ግድ ይልሃል። በዙሪያህ ያሉ አካላት ወደ እልህና አላስፈላጊ ስሜት ውስጥ እንድትገባ ቢያደርጉህና ያልሆነ ሥነ ምግባር ውስጥ እንድትዘፈቅ ቢወተውቱህም ጆሮ ልትቸራቸው አይገባም ። “

【እርካብና መንበር 】
ከ ዲ ራ አ ዝ
[ገፅ : 103 - 104 ]

@wegoch
@wegoch
@paappii
አስቾኳይ የእርዳታ ጥሪ ለ እህታችን !!
★ በቅንነት ሼር ሼር ሳያድርጉ እንዳያልፉ

የሕይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና

#ETHIOPIAN || ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትበላለች የ 11class ተማሪ ነች በ ባሌ ጎባ ነዋሪ ስትሆን በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለት #ኩላሊቶቹዋ ከጥቅም ውጪ ሆነው ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛልች ።

ውድ ወገኖች ለእህታችን በሃኪሞች በተነገረው የቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ #የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር መሄድ ይኖርበታል ለህክምና በጠቅላላ 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን ብር)ያስፈልጋታል ውድ ወገኖች ወገን ለወገን ደራሽ ነውና ለህታችን #ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጆቻቹ እድትዘረጉለት ዘንዳ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኳን ለሚረዱ ሰው ሼር በማድረግ እድተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን!

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር
+251925386501

እንዲሁም ቤተሰቡዋ ጋር

0920942369
0912823605

በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ !! በቅንነት ሼር ያድርጉ
ፊት ለፊቴ ቡና እየጠጡ ኬክ የሚበሉት ጥንዶች ሸ ር ሙ ጣ ሊሉኝ ይችላሉ። የማለትም መብት አላቸው. . . ሁሌ ከማንም ጋር ስለሚያዩኝ. . .ሁሌ እነሱ
ስለማይለዋወጡ. . .፤ የልቤን ጓዳ የሚፈትሽ ወንድ በማጣቴ የሚያገኘኝ ሁሉ ቢያውቀኝ እያልኩ ጭኔን እከፍትለታለው. . .በጋለ ስጋው ይ ቦ ረ ቡ ረ ኛ ል! ምን አልባት. . .እዛ ጥግ ትንሽ እህቱን ስፕራይት የሚያጠጣት የሚያምር ነጭ ጫማ ካኪ ሱሪ፣ ነጭ ቲ-ሸርት በቀይ ጃኬት የለበሰው ባለ ሉጫ ፀጉሩ ቀይ ወጣት፣ ወደ'ሷ አትዪ ይላት ይሆናል. . . እህቱን! መቁላላቴን አይታ እንዳትባልግበት. . . ዛሬ ዛሬ የልጅነት ትውስታዎቼ - ጓደኞቼ. . . በመንገድ ሲያዩኝ ፊታቸውን ያዞሩ
ይሆናል፣ መንገድ ይቀይራሉ። ልቅነቴ እንደ ጉንፋን የሚጋባ እየመሰላቸው. . .
ያቺ ከርታታ እናቴን ካየዋት ስንት ጊዜዬ? ለምንድነው ድምጿ እንኳን የማይናፍቀኝ? ተቀይማኝ ይሆን. . .አባቴ ሞቶ ለቅሶ ስላልደረስኩ. . .ለበዓል እንደእኩዮቼ ባሌንና ልጄን ይዤ ሄጄ ቤቷን ስለማላደምቅ? ወጓን ስላላሳየዋት? .
. . ያኔ የህይወቴን መጨለም አልረዳ ስትለኝ. . .ልቤ ለዛ ቀይ ልጅ መሟሟቷ
አልገባ ሲላት. . .እሱን ለመርሳት መጠጥ ስጀምር አምሽቼ ስገባ. . . ማልቀስ ጀመረች፣ መጨረሻዬ ይኼ ነው ወይ አለችኝ. . .ለምን አትረዳኝም? አለመረዳቷ
የእናትነት ውለታዋን ይፍቀው ጀመር. . . . አደበዘዘው? እኔንጃ. . . ሸሸኋት ፍቅሬን
ወዳየኋት ቦታ ሔድኩኝ. . .ከወንድሜ ጋ ' እሱጋ እንድረጋጋ ላኩኝ. . . ፍቅሬ እየጨመረ. . .ፍቅሬ እየደበዘዘ የልቡን ባላቅም አፉና አካሉ ወደ ቀድሞዋ
ፍቅረኛው ተ ሸ ረ ሸ ረ! የኔም ልብ ውልቅልቁ ጠፋ. . . ዛሬ ዛሬ. . . የምወደው ሙዚቃ አስጠላኝ! ብቸኝነቴን ለመሸሽ በየካፌው በረንዳ ከአንዱ ጋር ቡናዬን አጣጥማለሁ ቡናው ልቤን ሲነካው ደስ ይለኛል የምሞት እየመሰለኝ. . .በዝናብ ውሽንፍር በቀኑ መጨለም የሚደበዝዘውን አስፓልት
አያለሁ. . .ማንም ይሄድበታል መንገዱ ፣ ልክ እንደ'ኔ ሰውነት. . .

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#mesfin
Forwarded from Sunset Hiking (Cherinet K.)
View over #Jema's #Gorge from #Portuguese_bridge.

#Sunset_Hiking 🌇 is hosting another day hike (round trip) to Portuguese bridge (#Debre_Libanos) by Nov 29, 2020 (ህዳር 20, 2013) 🇪🇹- round 2

Activities
🏔#Hiking
🎸 #Live_music_performance (with #Zamir_Acoustic_Band)
🧘‍♀ #Yoga_Intro (with #Meron_Mario)

What to see 👁 👁
#Waterfall
#Jema Gorge
#Cave
🦍 #Gelada_Baboon

#Package_Includes
🥗 #Lunch (Traditional #Agelgil)
🍂 #Photography
🚍 Transportation
💧Bottled water
💐Snack
🟢Entrance fee
🌺 Guide

💵 Hiking #Cost only 500 birr

📍 📍 📍 Location- 110 km North of Addis (around Fiche) with Max. Elev of 2450 m.

🛫Departure: Piasa (Taitu Hotel) at 12:30 LT

Tickets 🎫 🎫 🎫 available 👇
@Cherinet_K (0911759127)

NB. Okay for #beginners.


For more join
Group - https://www.tg-me.com/sunsethike
Channel - https://www.tg-me.com/sunsethiking
Photogrpahy - https://www.tg-me.com/sunsetphotography
ፍቃዱ ወደ ትምህርት ቤት እንሂድ ሊለኝ አያቴ ቤት መጣ። በርግጥ በወቅቱ አያቴ ጋር ሄጄ የነበረው ፍቃዱ መኖሪያቤታችን መጥቶ ትምህርት ቤት እንሂድ ሊለኝ ይችላል በሚል ስጋት ነበር ። ሆኖም አልተሳካልኝም ( ያ የነገር ሜንጦ የሆነ ልጅ አንገቱን እያሰገገ አያቴ በራፍ ድረስ ከተፍ አለልኝ ። ደግሞ እኮ ሚካኤል አለ ይላል ? ቅዱስ ሚካኤል ስዕሉ ላይ እንዳለው ጋንጩር አናቱ ላይ ቆሞ ይርገጠውና 😞!!) አያቴ በረንዳ ላይ ካለች አንዲት ብርኩማ ላይ ተቀምጣ ... ዜና ታዳምጣለች ። (በዛ ሳምሶናይት ቦርሳ በሚመስል ቴፕ ዜና ስትሰማ ታድያ ራሷን በሀዘኔታ ትነቀንቃለች። የዛች ቴፕ ታሪክ እጅግ የቆየ ከመሆኑ የተነሳ ከሆነ ጊዜ በኋላ ቤቴ በሙዚየምነት እንደማስቀምጣት አውቃለሁ )
"ሚኪያሴ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ጠንቀቅ እያልህ ልጄ ! ዛሬ ልጆችን ወስደው አዲስ አበባ መለመኛ እያደረጓቸው ነው። አይንህን አውጥተው መለመኛ ያደርጉሀል ። በዛ ላይ ያንተ አይን ቀድሞውንም የወጣ ነው ዋጋም የለህ ! ...ደግሞ እንዳንተ ያለውን ቆንጆ ነው የሚወስዱት አሉ " ... ይሄን ስትለኝ ድንጋጤ በመላ አካሌ ሲሰራጭ ይታወቀኛል። የልጅነት ልቤ በከባድ ፍርሀት ተውጣ ቅዝቅዝ ትላለች ።
"ደግሞ ምንድነው የያዛችሁት?" እንደ ጎረምሳ ደረት የሰፋ መነፅሯን አውልቃ አየችን።
"ቢራቢሮ እየገደልን እንሂድ ብለን እኮ ነው" ፍቄ መለሰ።
"ስሙ! በየመንገዱ ቢራቢሮ እንግደል ብላችሁ ስትሯሯጡ አንዱ ደንባራ ሹፌር መጥቶ እንዳይድጣችሁ ። "
"እሺ"
"እሺ ይላል እንዴ ደግሞ ? ምን ያለው ትንኩሽት ነው ይሄ ልጅ ። አስቀምጡ ልምጩን!" ...አያቴ አንባረቀች።
"ይሄ ልጅ አባቱ እንዲህ እንደሚያደርግ ቢያውቅ የሚለቀው ይመስልሀል? አንተስ እንደው አንደኛውን ለይቶልሀል !"- ...ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አያቴ ፍቄን አትወደውም። ሌባ ነው እጁ አይፆምም ትላለች ብዙ ጊዜ። ደግሞ ቤታቸው ቅርብ ስለሆነ አብጠርጥራ ባህሪውን ታውቅበታለች ። ስራው ከልጅ ሳይሆን ከሰላሳ ዓመት ጎረምሳም አይጠበቅም ብላ ብዙ ጊዜ ስታማርረው እሰማታለሁ ። በርግጥ ፍቄ ሌባ ብቻ ሳይሆን ነገረኛም ጭምር ነው። እኔም ከሱ ጋር ጓደኛ የሆንኩት ወድጄው ሳይሆን ከአንድ ክፉ አደጋ ራሴን ለመጠበቅ ነበር።
አንድ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት እየሄድን...ማንም የሌለበት ጠባብ ሸለቆ ውስጥ ስንደርስ ከኪሱ የተጠቀለለ ወረቀት አወጣና ለኮሰው። ለኩሶ አጨሰው። ግራ ገብቶኝ አየሁት... ገና የአራተኛ ክፍል የሆንን ፈልፈሎች ሲጃራ ስናጨስ ከተገኘን ጉድ ነው መቼም ! ...ደግሞ ወረቀቱ በሲጃራ መልክ ተጠቅልሎ ይሰራ እንጅ የሚገዛው ኒያላ ስ አልነበረም።
"ይቅርብን አልኩት!"
"ባክህ አትፍራ ... እንካ.. ." ብሎ እጁን ሰደደልኝ። ተዟዙሬ አካባቢዬን በፍርሀት ቃኘሁትና ተቀበልሁት።
ወረቀቱን ሳብ ...ሳብ ሳደርገው ጭሱ ጉሮሮዬ ላይ ተሰክቶ አልወርድም እያለ አሳለኝ። አንዴ አጭስበት ይለቅሀል አለኝ... እንደገና አንድ ጊዜ ሳብብብ ሳደርገው ታድያ ከየት መጣ ያልተባለ ድምፅ ጆሮዋችን ላይ አቃጨለ።
እናንተ ጉዶች ????
...ዞር አልን...ዞር ስንል የፍቄ እናት አፀዱ ነች።... ፍቄ ከስሬ ብን ብሎ ተሰለበ (ተነነ ብል ይቀለኛል። ሰው ቅዱስ ሲሆን ብቻ ሳይሆን እርኩስም ሆኖ ወደሰማይ ማረግ ይችላል ለካ !) ... እኔም ደንብሬ ስለነበር እሱን ተከትዬው ከነፍኩኝ።
"አይቻችኋለሁ ። ማታ ትመጧታላች.....ሁ ...." የአፀድዬ ድምፅ ከርቀት ተሰማኝ።
ታድያ በዛኑ ቀን ከትምህርት ቤት መልስ እየተሸማቀቅን ቤት ገባን...አፀዱ ቀስ ብላ ፍቄን ያዘችውና በማማሰያ አንቆራጣ ቀጥቅጣው ጥፋቱን እዛው ላይ ረሳችለት ። እኔ ጋር ግን ጉዳዩ ገና ተጀመረ እንጂ አልተፈፀመም ነበር ።
ፍቄ በጠዋቱ ቤት ይመጣና ዳቦ እና ሻይ ስጠኝ አለበለዚያ ለአባትህ ሲጋራ እንዳጨስን ልንገርብህ ይለኛል።
ያቺን ናፒ የምትባለውን ቆንጆ ልጅ ሁለተኛ ካንተ ጋር ሳይሆን ከኔ ጋር ነው መሄድ ያለባት
እንዴ ለምን ? ናፒ እኮ የኔ ጓደኛ ነች
አንተ ሲጃ ……………….
ቃሉን መጨረስ አይጠበቅበትም እሺ ይሁንልህ ብዬው ህመሜን እውጣለሁ ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ ...
ፍራንክ ከቤት ይዘህ ና ብሎ ያስጨንቀኛል።
ህይወቴን በሴራው ጠፍንጎ ሳልወድ በግዴ ጓደኛው አድርጎኝ አረፈው።
እናም በሰዓቱ አያቴ ስትቆጣንም በአይኑ መልከት አደረገኝ። አርጩሜውን አንሳ ማለቱ እንደሆነ ገብቶኛል።
አርጩሜውን ባነሳው አያቴ ልትራገም ሆነ ።
እንቢ ብለው ሲጃራ አጨስን ብሎ ለአባቴ ሊያንሿክክ ሆነ ።
በዚህ ሁለት አጣብቂኞች መሀል ቆሜ ጩኸቴን አቀለጥሁት ። ኡ ኡ ኡ ይ እባብ እባብ እባብ
እግሬን እያነሳሁ ክፉኛ ስወራጭ ፍቄ ስሬ አልነበረም ። ያኔ አፀድዬ ስታየን ጊዜ እንደነበረው ተኖ ተሰለበ ። አያቴ ግራ ተጋብታ በረንዳው ላይ ቆማ ታየኛለች ። በዚህ ደስታ መሀል ሆኜ በረዥሙ እፎይ ከማለቴ ለጥቆ አንድ ሲደብረኝ የኖረ ድምፅ ከጀርባዬ ተከተለ ።
“ሚኪያስ አርጩሜውን አንሳው 🙂 ወይም ሲጃራ … !” (ሚካኤል አስጨናቂ )

@wegoch
@wegoch
@paappii
ስንብት
'
'
ብዙ ጊዜዬን ከማሳልፍበት ብዥታ ወጥቼ ራሴን ገዝቼባቸዋለሁ ብዬ ባሰብኩባቸው የህይወቴ ጥቂት ቀናት የማልመው በብሩህ ፀሃያማ ቀን ስለመሞት ነበር ። ቃጠሎ ባልበዛበት ለስስ ባለ ፀሃያማ ቀን ፤ እንደ ጥቅምት ባለ ቀን መሞት ። የሃምሌ ቀናት የጨለማ ኑሮ ላሳለፍኩ ለእኔ በብራ ጥቅምት መሞት የመጨረሻው ብሩህ ምኞቴ እና ታላቅ ደስታዬ ነበር ። ዛሬ ድንገት ከድብታዬ እንደ መባነን ያለ ስሜት ተሰማኝ እና ማዳበሪያ አገልድሜ የጠበኩት በባዶ እየሄድኩ የፈለኩት ያ የጥቅምት ፀሃያማ ቀን መድረሱን አወቅሁ። በርግጥ ከሆነ ጊዜ በፊትም ይህ የጥቅምት ቀን የመጣ መስሎኝ ሞቴን መንገድ ዳር ፈልጌው ነበር ። ግን ቀኑ እና ሞቴ ሳይገጣጠሙ ቀርተው እስከ ዛሬ አለሁ ። ቀኑ ልክ እንደዛሬው ደማቅ ረፋድ ነበር ። የሚፈቀር የፀሃይ ብርሃን አየሩ ላይ ተንሰራፍቶ ነበር ። ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ ልክ እንደ ዛሬው ልከኝነት እና እርግጠኝነት ውስጤን ሞልተውት ነበር ። የመሞቻ ቀኔ መሆኑን አምኜ የደስታና ሃሴት አየር እየቀዘፍኩ የመሞቻ ቦታዬን ልመርጥ ከተጋደምኩበት ተነሳሁ ።
በመንገዴ በሞቴና በህይወቴ መካከል ያለውን ልዩነት የማያስተውሉ በማይገባኝ
ምክንያት ወደተለያየ አቅጣጫ የሚራወጡ ሰዎች ቢገጥሙኝም እንደሁልጊዜው ጉዞ ላይ ስለነበሩ ልብ ብሎ ያየኝ አልነበረም ። ወጪ ወራጁ ፤ አላፊ አግዳሚው " እብዱ"ብሎ በወል ስም ይጠራኛል። ባጠገባቸው ሳልፍ የሚደነብሩ ሴቶች ፤ ፈንጠር የሚሉ ወንዶች ሁሉም እብድ በሚል የሚያሸሽ ስም መኖሬን የዘነጉ ሁሉ በዚህ የማዕረግ ስም ስለሚጠሩኝ እኔም ድሮ እናትና አባቴ ያወጡልኝን ስም ዘንግቼዋለሁ። ለእነኝህ በዙሪያየ ለሚርመሰመሱ ፍጡራን የማስደነግጥ እና የማስፈነጥር እድፋም ተንቀሳቃሽ በድን ነኝ ። በርግጥ ከመላመድ ብዛት ዝምተኛ ባህርዬን ያወቁ አንዳንዶች ያገለደምኩትን ማዳበሪያ የተቀባሁትን ከሰል ወይንም የተሸከምኳቸውን ሃይለንዶች አይተው ከአጠገቤ ሲፈረጥጡ " አይናካም ......" ብለው ያረጋጓቸዋል ። ግን የሁሉም ድርጊት ደንታ ሰጥቶኝ አያውቅም ። ብዙ ጊዜም መንቃት የሚቻልበት በማይመስለኝ ህልም መሳይ ረጅም ጥልቀት መኻል እንዳለሁ ስለሚሰማኝ የማያቸው ሰዎች ሁሉ ደቃቃ ይሆኑብኛል ..... የሆኑ ትናንሽ .... ልክ እንደ ጉንዳን ፤ድምፃቸውም ዝግ ያለና የማይሰማ ። እንደዚህ ሆነው ሳያቸው ሁሌ ከምቀመጥበት አስፋልት ጠርዝ ከሚገኝ የስልክ እንጨት ስር ሆኜ እጄን ሰድጃ በሁለት ጣቴ ይዤ ላንጠለጥላቸው እለፋለሁ ። ያኔ ጉንዳንነታቸው ይብስብኛል ። ማነሳቸው ይጎላብኝና በተቀመጥኩበት እጄን እዘረጋለሁ ። ግን
ደርሼ አልደርስባቸውም የሚናገሩ ቢመስለኝም አፋቸው ይንቀሳቀሳል እንጂ
የሚያወጡት የጠራ ድምፅ አይሰማኝም ። ሁሌም በዙሪያዬ የነበሩ ሰዎች እንደዛ
ትንሽ ቢሆኑና ከጥቃቅን ጉዳያቸው ልቄ ከፍ ብዬ ያልተስተዋልኩ ብሆንም እኔ የሚሰማኝ ግን ከግዝፈቴ ብዛት ከእይታቸው መራቄ ነበር ። እና በዚያ የሞቴ ቀን ነው ብዬ በነቃሁበት እለት በመንገደኛው መኻል እየተመላለስኩ ለብዙ መአት ጊዜ የተቅበዘበዝኩበት ሰፈር የታረዝኩ የተጠማሁበት መንገድ ላይ ጥሩ መሞቻዬን አሰስኩ። በመጨረሻ ተሳክቶልኝ መንገድ ዳር የነበረ በጠፍጠፋ አራት ማዕዘን ድንጋይ የተዘጋ የቆሻሻ መውረጃ ጉድጓድ አገኘሁ ። አስፋልት ዳር በሚገኝ የቆሻሻ መተላለፊያ ጉድጓድ ውስጥ መሞት በጣም ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ ተሰማኝ ። በህይወት እያለሁ ምንም ያልፈየዱልኝ ሰዎች ለራሳቸው ጉዳይ ብለውም ቢሆን ይሄን ጉድጓድ በመቆፈራቸው ጥሩነታቸውን እንደቸሩኝ አሰብኩ ።
ጉድጓዱ ዳር ተንበርክኬ ክዳኑን መግፋት ጀመርኩ ። እህል ከቀመስኩ ስንት ቀናት እንዳለፉ ረስቼው ነበር የድንጋይ ንጣፉን ማንሸራተት ቋጥኝ የመግፋት ያህል ሲከብደኝ ግን ያላዳመጥኩት ከባድ ረሃብ እንደተጠናወተኝ አወቅኹ። ለትንሽ ቅፅበትም ድንጋይ መግፋቴን ገትቼ በባዶ ሆድ ላለመሞት ፍርፋሪ ላገኝ ወደምችልበት በቅርብ ርቀት ወደማገኝ ምግብ ቤት አይኔን ላኩ ። በምግብ ቤቱ
በረንዳ ላይ ተኮልኩለው የሚመገቡ ሰዎች አይን ከአይኔ ጋር ቢጋጭ በሚል
ተስፋ ትንሽ ደቂቃዎችን በዚያ ያሉ ሰዎችን ስመለከት ቆየሁ ። ከቆይታ በኋላ አይቶኝ ረሃቤና ፍላጎቴ ገብቶት የሚጠራኝ እንደሌለ ስረዳ አይኖቼን መልሼ ያለ የሌለ ጉልበቴን ሰብስቤ የተውኩትን የድንጋይ ንጣፍ መግፋቴን ቀጠልኩ። ከስንት ግፊያ በኋላ ፈቀቅ ብሎ በተከፈተው የጉድጓዱ ክፍተት በኩል የታፈነ እና የሚገፋተር ቆሻሻ ሽታ ተንኖ ወጥቶ ያጎነበሰ ፊቴን አፈነኝ ። መጀመሪያ አካባቢ የቆሻሻውን ሽታ ተጠይፌ ፊቴን ማዞር ፈልጌ ነበር ። ወዲያው ግን የመጣሁበት አላማ ሞት መሆኑ ትውስ ሲለኝ የድንጋይ ንጣፉን ወደ ጎን ገፍቼ የቆሻሻው ጉድጓድ ውስጥ ጭንቅላቴን ቁልቁል ደፈቅሁ። ጉድጓድ ውስጥ ጭንቅላቴን አስቀድሜ ስገባ ሙሉ በሙሉ ለመግባት አስቤ ቢሆንም ያገመደልኩትን ማደበሪያ ከጉድጓዱ ውጪ የሆነ ነገር ጠልፎት እግሮቼ
ተንጨፍረው ውጪ ቀሩ ። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ደቂቃዎች አልፈው በቆሻሻው ታፍኜ አፍ አፍንጫዬ እና ጆሮዬ ተደፍነው አይኖቼ ተጋርደው አስቀያሚ ሽታ ያለው
የቆሻሻ ባህር ውስጥ ቆየሁ ። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ከአላፊ አግዳሚው መኻል ወደ ጉዱጓዱ የሚመጡ ኮቴዎች ድምፅ የተዘፈቅኩበትን ቆሻሻ አልፎ ጆሮዬ ሲደር ታወቀኝ ። ከገባሁበት ጎትቶ ሊያወጣኝ የደፈረ አልነበረም ። ግን ክብ ሰርተው ቁልቁል የሚያዩኝ ብዙ ሰዎች ንግግር ይሰማኛል ። " ራሱ እኮ ነው የገባው .... አሁን አይቼዋለሁ ከፊቴ ነበረ .... መጥቶ ጉዱጓዱን ከፍቶ ገባ" ትላለች አንዷ
" አፈር ልብላ ሰው ደብድቦ ጨምሮት ነው?" ትጠይቃለች ሌላኛዋ " ኧረ ማን ይደበድበዋል ! እብድ እኮ ነው ራሱ ገብቶ ነው " ይመልሳል ሶስተኛው " ውይ እብድ ነው እንዴ ? ደህና ሰው መስሎኝ " የቅድሟ አዛኝ መሳይ ጠያቂ እንዲህ በማንነቴ እየተከራከሩ እብድ መሆኔን ሲያውቁ ሞቴን አቃልለው ቀድመው የሰጡኝን ርህራሄ ከመግፈፋቸው በፊት መታፈኑ ስላንገሸገሸኝ ተረባርበው ከገባሁበት እንዲያወጡኝ ፈልጌ ነበር ። " ውይ እብድ ነው እንዴ ? ደህና ሰው መስሎኝ " ን ስሰማ ግን ከነእርሱ የጭካኔ ክርፋት የምምገው ቆሻሻቸው እንደሚሻል አሰብኩ ። ከእነዚህ ፍጡራን መገላገል አለብኝ ። ግን የተሻለ መሞቻ መምረጥ ነበረብኝ ። በእነርሱ ቆሻሻ ታፍኜ መሞት አልነበረብኝም ። ይሄንን እያሰብኩ በሰመመን ውስጥ ሆኜ ቁልቁል የሚያዩኝን ሰዎች አዲስ የተቀላቀለ የሚመስል ሌላ ሰው
" ለምን አናወጣውም ? ፌስታል አለ? በፌስቴል እናውጣው ፌስታል ፈልጉ" ሲል ሰማሁትና አጎንብሼ በተደፈቅኩበት ፈገግ ለማለት ሞከርኩ ፤ ፈገግ ስል ድድር ቆሻሻ ጥርሴ ላይ ተጋገረ ። ከእኔ ነፍስ የበለጠ በውሃና ሳሙና የሚፀዳ የሚነኩት ቆሻሻ ሲጠነቀቁ ላዬ የተዘፈኩበት ቆሻሻ የእነርሱ አይመስልም ። የነፍሴን ዋጋ ከእጃቸው ንፅህና ጋር ሲያነፃፅሩ በስንት ሃጢያትና ወንጀል የተጨማለቁ አይመስሉም ። ፌስታል የሚፈልገው ሰውዬ ድምፅ እየራቀኝ ሄደ ። ይመስለኛል ፌስታል ሊገዛ ነው ። ወዲያው አንድ ሌላ ሰው " ለምን ቆማችሁ ታዩታላችሁ እናውጣው እንጂ" ሲል ተሰማኝ " ቆሻሻ ነው ፌስታል ሊገዛ ነው " ብሎ መለሰለት ሌላ ሰው " ያማችኹዋል እንዴ ! ሰውዬውኮ እየሞተ ነው ፤ እናውጣው እንጂ " ብሎ ከእግሮቼ ጋር የተንከረፈፈ አንድ እጄን መጎተት ጀመረ ። ወዲያው እግሬን ሌላ ሰው ሲይዘኝ ታወቀኝ ። እግሬን የያዘው ሰው በፌስታል እጁ ላይ ጠቅልሏል ። አራት
አምስት የሚሆኑ ሰዎች ከጉድጓዱ አወጡኝና መሬቱ ላይ ተቀመጥኩ ። ቆመው የሚያዩኝን ሰዎች አንዴ
ገርምኳቸው እና የመሞቴን ሃሳብ እንዳመከኑብኝ ሳስብ ተመልሼ ወደ ጉድጓዱ ለመግባት ፈልጌ ታገልኳቸው ።
"ድጋሚ ሊገባ ነው ... አትልቀቀው" ተባብለው ጥፍንግ አድርገው ያዙኝ። ወዲያው ከየት እንደመጣ ግራ የሚያጋባ ዶፍ መዝነብ ጀመረ ። የከበቡኝ ሰዎች በሙሉ ያንፏቀኩትን የድንጋይ ንጣፍ መልሰው ጉዱጓዱን ከድነው ተበተኑ። ብቻዬን ቀረሁ ፤ ብቻዬን ዶፍ መሃል ቀረሁ በብራ የጥቅምት ቀን የመሞት
እቅዴን ዝናቡ አከሰመብኝ የዛን ጊዜ ከተወለድኩ ጀምሮ አልቅሼ የማላውቀውን ለቅሶ አለቀስኩ ። እንባዬ ከዝናቡ ጋር ተባብሮ እላዬ ላይ የነበረውን ቆሻሻ አጠበልኝ። የዛን እለቱ ሞቴ አጎጉቶኝ ከተመለሰ በኹዋላ ታዲያ እንደ ዛሬዋ አይነት ቀን ስጠብቅ ነፍሴን ከጉድፍ ባቃለሉ ሰዎች መኻል ብዙ ኖርኩ ። በመጨረሻ ግን የናፈቀኝ ደማቅ ፀሃያማ ቀን ደርሶ መሞቻዬን ለመምረጥ ተነሳሁ። ጥሩ መሞቻ የመሰለኝ ቦታ ላይ ደርሼ ከተማውን አንዴ ቁልቁል አየሁት ። ከዚህ ሆኜ ሳያቸው ሰው የሚባሉ ፍጡራን ከጉንዳንም አንሰዋል ። ቀኑ ደስ ይላል ፤ በመጨረሻ ለስ ብላ የወጣች ፀሃይ ፣ ቀዝቀዝ ብሎ የሚነፍስ ነፋስ ፣
ለመውጣት የምትታገለኝ ነፍስ ፣ በቃኸኝ ያልኩት ስጋዬ አንድ ላይ ተገናኝተናል ።
እጆቼን ዘርግቼ አየሩ ላይ ተደፋሁ እግሮቼ ከቆሙበት ተነቀሉ ። የለበስኩት
ማዳበሪያ እንደ ክንፍ በላዬ ላይ ተንሳፈፈ ከሩቅ ለሚያየኝ ወፍ ነው የምመስለው ። ወደ ታች እየተምዘገዘኩ ነው ። ወደታች እየወረድኩ አየር ላይ ነኝ በወፎች እጅግ ቀናሁ ለካ መቅዘፍ እና መብረር ከመኖር ይበልጥ ደስ ይል ነበር ። ምናለ ወፍ ሆኜ ብፈጠር የሚል ምኞቴን ሳልጨርስ በሃይለኛ ግጭት ከመሬት ጋር ተላተምኩ ። ጭንቅላቴ ደንዝዟል ቢሆንም የሚፈሰኝ ትኩስ ደም ይሞቀኛል። መላ ቅጡ የጠፋው ህመም መኻል ነኝ ። ሰዎች ተሯሩጠው ደረሱ ።
" ምን ሆኖ ነው?"
" ከፎቁ ላይ ወድቆ . ... ከላይ ነው የወደቀው ከ 21 ኛው ፎቅ ..0 አይተርፍ "
" ሰው ገፍትሮት ይሆን ?"
" አይመስለኝም .... እብድ ነው"
እብድ ነውን ስሰማ በደም ተሸፍኜ በተንጋለልኩበት ፈገግ አልኩ ። የእብድ ሰው ነፍስ ዋጋ የወረደ መሆኑን ባውቅም ከ'ደህና ሰው' ነፍስ ጋር ያለውን ትክክለኛ ምንዛሬ ሳላውቅ መሞቴ ልክ እንዳልነበር አሰብኩ ። በመጨረሻ ፈገግታዬን እንኳን ሳልሰበስብ ሁሉ ነገር ጨለመ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሰው መሆን አይቀርም
(በእውቀቱ ስዩም)

-መስከረም 2፤ 1967-
ከስድስት የማያንሱ አፍላ መኮንንኖች ወደ ቤተመንግስት ዘው ብለው ገቡ! ከጥቂት ደቂቆች በሁዋላ አዛውንቱን ንጉሰነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴን በቤተመንግስት ቢሮአቸው አፈፍ አስነስተው አንዲት ውራጅ ቮልስ ዋገን ውስጥ ቀረቀሯቸው:: ከኒህ አፈናቃይ ወጣት መኮንኖች አንዱ መቶ አለቃ ፍቅረስላሴ ወግደረስ ይባላል ፤ በጊዜው የነበረውን ስሜቱን ካመታት በሁዋላ አስታውሶ ሲፅፍ “ ለብዙ አመታት ስጠብቀው የቆየሁት ምኞቴ ሲፈፀም በማየቴ ደስ አለኝ “ ይላል ፤
-ከአስራ ስድስት አመታት በሁዋላ -
“ የሰሜኑ ኮከብ “ ብሎ ራሱን የሚያንቆለጳጱሰው የኢሀአዴግ ጦር አዲሳባን ተቆጣጠረ፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሬድዮ “ የመንግስት ባለልጣናት በአርባ ስምንት ሰአት ውስጥ እጃችሁን እንድትሰጡ” እሚል አዋጅ አስነገረ፤ በስልጣን ላይ የነበሩ ሁሉ አዋጁን ሰምተው አንድ ዳንግሌ በግ ተሰልፈው በመሄድ ገበሩ፤ ከኒህ መካከል አንዱ በጠቅላይ ምኒስትር መአረግ የቆየው ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ ነበር፤ በቀጥታ ወደ መከላከያ ምኒስተር ነዳ፤ እዛ ሲደርስ የግቢው በር አሜት በጠማው ህዝብ ተከቧል” አንዳንዶች ከንፈራቸውን በአዘኔታ ሲመጡ አንዳንዶች የስድብ ናዳ ያወርዱብኝ ጀመር “ ይላል፤ ከአመታት በፊት፤ አረጋዊው ንጉስ ፤እንደ ጃንጥላ ታጥፈው፤ በቮልስ ተጠርዘው “ ሌባ ! ሌባ! “ የሚል ርግማን ሲይስተናግዱ ታዝቦ የተደሰተው ሰውየ ዛሬ ደግሞ በተራው ከውርደት ጋር ተጋፈጠ !
የጊዜው ሃይለኞች ፤ እንኩዋን ደህና መጣህ ብለው ተቀብለው፤ ለመጭው ለሃያ አመት ወደሚማቅቅበት እስር ቤት ወረወሩት! በተራቸው በመፍለጥ በመቁረጥ በማፈን እና በመዝፈን ላይ ተሰማሩ! ዛሬ እኒያ ሃያላን በተራቸው ክንዳቸው ልሟል:: ጉልበታቸው ደክሟል ፤
" ሰባሁለት ሰአት ሰጠናችሁ፤ሰባሁለት መረቅናችሁ” የሚል ሃያል ተነስቶባቸዋል ! ያኔ ሃይለስላሴን ሲወድቁ ጠብቆ በዘለፋ ያጠናገረ፤ በፍቅረስላሴ ላይ የስድብ ናዳ ያወረደ ሰፊ ህዝብ በተረኛ ወዳቂዎች ውርደት ይጨፍራል፤ የልግጫ ሜም ይሰራል!
በፈረቃ መከባበር እያቃተን በፈረቃ እንዋረዳለን! ስልጣን ላይ የሚወጣ ሁሉ ዳፍንታም ነው፤ ጉልበት አላፊ ጠፊ ፤ ድልም ያንድ ሰሞን መሆኑን ማየት አይችልም!
ጣይቱ ብጡል ከስልጣን ስትወርድ ያንጎራጎረቺው ግጥም የሁሉም የቀድሞ ሃያላን ድምፅ የሚወክል ይመስለኛል፤
“እምቢልታ ማስነፋት ነበር አመላችን
ነጋሪት ማስመታት ነበር አመላችን
ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ተራችን “

@wegoch
@wegoch
የባል ገበያ
(ክፍል አንድ)
ሜሪ ፈለቀ

እንዴት ተጣበሳችሁ?” ብላ ዛሬም አፋጠጠችኝ። ምን ቀን አቅለብልቦኝ ቋንቋውን የምማረው ለቪዛ መሆኑን እንደነገርኳት እንጃ……

“እስቲ መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝ።” ጥያቄዋን ሽሽት እንጂ የሷን የጠበሳ ታሪክ የመስማት ጉጉት ኖሮኝ አልነበረም። እንኳን ተጠይቃ እንዲሁም ምላሷ ሞት አያውቅም።

“እኔማ ዴቲንግ ሳይት ላይ ነው የጠበስኩት። …… እኛ ክላስ ከሰላምና ከኤልሳ በስተቀር ሁሉም በ ‘balshemeta.com‘ ዴቲንግ ሳይት ነው የጠበሱት። …” አፀደ ስታወራ መወራጨቷ እና ቅብጥብጥነቷ ልትበር የምታኮበኩብ ያስመስላታል። …… ያንጨፈረረችው ፀጉሯ ሳይቀር እየፈጠነች ከከንፈሯ ከምታግተለትላቸው ቃላት ጋር ብን ትን ይላል። ቢሆንም ወሬዋ ጆሮና ቀልቤን ጠለፈው…… በዴቲንግ ሳይት የውጪ ሀገር ሰው መጥበስና ወደውጪ ሀገር ለመውጣት መታተር የኔ ብቻ ታሪክ ነበር የመሰለኝ።

“እና ሁላችሁም ቋንቋውን የምትማሩት አግብታችሁ ከሃገር ለመውጣት ነው?”

“አወና! አንቺም እንደዛው አይደል?”

“እ…ሱ…ማ ነው! በተመሳሳይ መንገድ ለተመሳሳይ ዓላማ አንድ ክፍል መገኘታችን ገርሞኝ ነው።” አልኳት

አንባቢ እህቴ ሆይ የምፅፍልሽ ዶሮ ፣ ሽንኩርት ፣ ቄጤማ፣ መከለሻ…… ስለሚሸመትበት የበዓል ገበያ አይደለም። በቆዳ ቀለም፣ በእድሜ፣ በዜግነት፣ በኑሮ ደረጃ ፣ በቁመት፣ በውፍረት……… ብቻ ባሻሽ መስፈርት ባል የሚሆን ወንድ ስለሚሸመትበት የገበያ ማዕከል እንጂ…… ለመገበያየት የሚያስፈልግሽ አውድማው ላይ ዘው ብሎ መዝለቅ ብቻ ነው።… …
balshemeta.com dating site ‘ ይሰኛል መደብሩ። (ሄዋኔ ይሄን ፅሁፍ አንብበሽ ስትጨርሺ የጎልጉል ፍለጋ ሳጥን ውስጥ ‘ፈልግ‘ን እንደምትጠነቁዪ በመጠርጠር በዚህ ተረክ ውስጥ የተጠቀሰው የሳይቱ ስም ተቀይሯል። …… ሃሃሃሃ)

የዳሌ ቁጥርሽ ሳይቀር ስለራስሽ የጠለቀ ጥያቄ እና የመልስ ሳጥን ይከታተልልሻል። … … ይሄ ብቻ በቂ አይሆንም። ባልሽ እንዲሆን የምትፈልጊውን ሰው ገላው ላይ ያለ የማሪያም ስሞሽ ጭምር በመጥቀስ መስፈርትሽን ታኖሪያለሽ። …… አክለሽ አምስት ቄንጠኛ ፎቶግራፎችን ትለጥፊያለሽ። (በእርግጥ የፎቶው ቄንጥ ግዴታ አይደለም።) አከተመ። ገበያው ውስጥ መሰስ ብለሽ ገብተሻል። …… በተለያየ የዓለማችን ክፍል ካሉ ወንዶች(አብዛኛዎቹ አዛውንቶች እና ለአዛውንትነት የቀረቡ ናቸው) መልዕክቶች ይደርሱሻል። …… የመረጥሽውን ታናግሪያለሽ።

በተመሳሳይ መንገድ አንድ አሜሪካዊ አግብታ የሄደች ወዳጄ (እንደመታደል ሆኖ እኩያዋን ነው ያገኘችው።) በጠቆመችኝ መሰረት በአንድ ያበደ ቀን ሸመታው መሃል ዘመትኩ። …… ከእብድ እስከ ስድ፣ ከአይንአፋር እስከ አደንቁር፣ ከአዋቂ እስከ ልብ አውላቂ፣ ከአስተዋይ እስከ ደም–አፍይ… …… ሳምንታት ከፈጀ አሰልቺ የንግግር ልውውጦሽ በኋላ ከሁለት ሰወች ጋር በቋሚነት ተግባብቼ ማውራት ስለቻልኩ ከሳይቱ ወጥቼ በቫይበር እና በፌስ ቡክ ማውራት ጀመርኩ። አንደኛው ፎቶግራፍ ካለመለጠፉም በላይ እንዳየውም ሆነ እንዲያየኝ ፍላጎት የለውም። የሚፅፍልኝ ቁምነገር ግን ችላ እንድለው አላደረገኝም።

አንደኛው ፈረንሳዊ ጎልማሳ ነው። ከእርሱ ጋር በስካይፒ አወራን። መወሰን ስለነበረብኝ መረጥኩ።…… ከወራት በኋላ ልቀበለው ቦሌ አየር ማረፊያ ተገኘሁ። ……

በአካል የማያውቁትን ሰው ፍቅረኛዬ ብሎ አስቦ ለመቀበል መሄድ የሆነ የማያውቁት ሰው ቀብር ላይ ተገኝቶ ከሬሳው ቀድሜ ጉድጓድ ውስጥ ካልተነጠፍኩ ብሎ ለያዥ ለገናዥ እንደማስቸገር ያለ የቂልነት ዓይነት ስሜት ነበር የፈጠረብኝ። …… ሳየው ምንድነው የማደርገው? አቅፈዋለሁ? እስመዋለሁ? ኸረ ከነጭራሹ በአካል ሳየው ባላውቀውስ? …… በአካል ስንገናኝ ቢያስጠላኝስ? …… እሱስ ካገኘኝ በኋላ ባስጠላው? እኔን ለማግኘት አህጉር ማቋረጡ ቢፀፅተውስ? ………

ክብ ፊቱንና አፍንጫና አይኑን ያጣበበ ሰፊ ጉንጩን እንዳየሁ አወቅኩት። …… ሳይደናገር ሻንጣውን እየገፋ በፈገግታ ወደኔ አቅጣጫ ቀረበ። ሲስቅ ጉንጩ ይንጠለጠልና ሊወድቅ እየመሰለኝ ልደግፍለት መዳፌን ማቅረብ እየቃጣኝ ከብዙ የመተቃቀፍ ሰላምታ በኋላ ሆቴል ደረስን። …… በእርግጥ ከጠበቅኩት ክብደት በላይ አንድ ጎረምሳ ያህል ጨምሮብኛል።(ወደ 30 ኪሎ የሚሆን)

ከፊት ለፊቱ ሲታይ ጥቅጥቅ ብሎ ሙሉ የሚመስለው ፀጉሩ የመሃል አናቱ አመላለጥ የሚቀመጠው በቂጡ ሳይሆን በአናቱ አስመስሎታል።……

አብረን በነበርንባቸው ሳምንታት ለመላመድ ጊዜ አልፈጀብንም። ቁጥብ፣ ስነስርዓታም እና ፈገግታም ነው። ሳቄ ሊያመልጠኝ እየታገለኝ ልለምደው ያልቻልኩት የአልጋ ላይ ባህሪውን ነበር። … …… ጉዳዩን እየከወነ እንደላንቲካ ተኮሳትሮ ሲያፈጥብኝ ከፀበኛው ጋር መንገድ ላይ ድንገት የተፋጠጠ እንጂ ፍቅር እየሰራን አይመስልም። በየመሃሉ የመሳደብ አይነት ምላሱን ብቅ ጥልቅ የማድረግ ልምዱ ሳቄን ያታግለኛል። …… ወደ ሀገሩ ሊመለስ በረራው ሰዓታት ሲቀሩት እንደተለመደው በምላሱ ‘እየተሳደበ‘ ሲተጋ … የጠጣሁት ወይን ተደምሮ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ። ……… ይሄኔ ተበሳጨ። …… ብስጭት ግን በእንግሊዘኛ አይመስጥም። …… ‘ኤጭ‘ ሳይባል ብስጭት ምኑን ብስጭት ሆነ? ‘ኤድያ‘ ካልገባበት ምኑን ተበሳጨ?

ትጋቱን አቁሞ ታሪክ ይሉት ትንግርት አወጋኝ። …… ከአመታት በፊት በአደጋ የዘር ፍሬውን ላጣ ጓደኛው የቀኝ ፍሬውን መለገሱን እና ከዚያ ወዲህ ለመርካት እንደሚቸገር የነገረኝን ቀልድ ነው ብዬ እንዳላልፍ እንባ ካዡ አይኖቹ የምሩን መሆኑን ተረድቻለሁ።…… የሰማሁትን እርግጠኛ መሆኔን በመጠራጠሬ ነክቼ ‘ይሄንን ነው የለገስከው?‘ ማለት ሊቃጣኝ ስዳዳ… … ገበያ እንደቀረበ ቲማቲም ፍሬዎቹን ለቀም አድርጎ ሰብስቦ

“አየሽ አንዱ ፍሬ የለም። እንቺ ነክተሽ አረጋግጪ! ” አለኝ። ‘ንኪ‘ ያለኝ የሎሚ ፍሬ ይመስል ቀለል አድርጎ

“አንዳች መዓት ይንካህ!” አልኩኝ በሆዴ እየዘገነነኝ…… ለአራት ሳምንታት አብሬው የነበርኩት ሰው ሳይሆን የሆነ የሚሸክክ ፍጡር ሆነብኝ። …… ምኑ እንደዘገነነኝ አላውቅም። ፍሬ— አልባ መሆኑ? አሁንም አሁንም አፍንጫውን እየሞዠቀ ቆለጡን እየነካካ ማለቃቀሱ? ብቻ የሰውነቴ ቆዳ ሽፍ እስኪል ሸከከኝ…… ጥዬው ብሄድ ደስ ባለኝ።

👉🏽👉🏽👉🏽አልጨረስንም👈🏽👈🏽👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
🌟Blend'N Magazine is here as expected with its 5th edition with more special and fresh contents starring international photographer Aida Muluneh and research institute N.E.R.D ... make sure you subscribe to get the latest updates. Read online on www.blendn.ml
Subscribe | Join | Contact
Blend'N Magazine
2024/09/24 08:31:10
Back to Top
HTML Embed Code: