Telegram Web Link
የ Dereje Senay ባለቤት ደውላልኝ ስለነበር በዛውም ደረጄ የገዛት በግን ለማየት ቤቱ ሄጄ ነበር ። ደሬ ወገቡን ይዞ እየተንጎራደደ መንኮራኩር ሊያመጥቅ እንደተዘጋጀ ሳይንቲስት :) ትንሽ በተመስጦ ሲያብሰለስል ቆየና 

"ይገርምሀል ይሄ በግ እንደ ሌሎቹ በጎች ተራ በግ አይደለም...እንዲሁ ትኩር ብዬ ስመለከተው ትምህርቱን ሚኒስትሪ ተፈትኖ ያቆመ ይመስለኛል😃" አለኝ።

"ደሬ በጉ ነው የተማረው? " አልኩት የሰማሁትን ባለማመን 

"Yeah Definately !..." ...

"እያወራህ ያለኸው ነገር አልገባኝም "

"This is beyond Nature.. .ከተፈጥሮ ክንውኖች ውጭ የሆነ ክስተት ነው።...ለምን ይሄን እንዳልኩህ ታውቃለህ ?

ለበግ ሻጩ ቀለል አድርጌ ለበጉ 3000 ብር አይበቃውም ወይ? ብዬ ስጠይቀው በጉ ኮስተር ብሎ ገላመጠኝ....ሃሃሃ...በግ ሲገላመጥ ከዚህ ቀደም በዓለም ታይቶ ይታወቃል? ...ደግሞ መገላመጡስ ይሁን 3000 ብር ትንሽ ብር መሆኑን እንዴት ሊያውቅ ቻለ ?"

የደሬ ደህንነት ግራ አጋብቶኝ ትኩር ብዬ ሳየው ቆይቼ 

"እኔ ምልህ? ...ያ በዓል ሲደርስ አዕምሮዬን የሚያቀዣብረኝ በሽታ አለብኝ ያልከኝ ነገር አልተሻለህም ማለት ነው?" ...

"ያመኝ ነበር እንዴ?"

"አዎ ! ድብን አድርጎ ያምሀል ... ገንዘብ ስታወጣ የመርሳት ችግር እንዳለብህ ከዚህ ቀደም ነግረኸኛል "

"...እንዴት እንዲህ ትለኛለህ? " ቱግ ብሎ ጠየቀኝ።

"እና የተማረ በግ ገዛሁ ስትል ትንሽ አታፍርም ?...ጭራሽ ቁጥር የሚያውቅ በግ ገዛሁ እኮ ነው ያልከኝ! "

"ማ ...እኔ? ...

ሆ!...እኔ እኔና አንተ ከተገናኘንባት ቅፅበት አንስቶ ስለ በግ አውርቻለሁ ? "

ደሬ በሁኔታው ፈፅሞ አሳዘነኝ። እሱ ከቆመበት አለፍ ብላ የጠባብ ክፍላቸውን በር ደፍ ተደግፋ ወደ ቆመችው ምስኪን ባለቤቱ ተጠግቼ ...

"ደሬ ምን ሆኗል? " አልኳት.. .

"ቅድም ከ Assaye derbe ጋር በግ እንግዛ ብሎ ወትቶ ነበር ። በጉን ገዝተው ሲመለሱ አሳዬ ጠርቶኝ ባለቤትሽ ገብዘብ ካወጣ በኋላ ትክክል ስላልሆነ ገብቶ ይረፍ ብሎኝ ነበር ። ቢጨንቀኝ እኮ ላንተም ደውዬ ቤት እንድትመጣ ያደረኩህ ሚኪ?" ...እንባዎቿ በመንታ አይኖቿ በኩል ቁልቁል ተምዘገዘጉ ..

ባለቤቱ ስላሳዘነችኝ እቅፍ አድርጌ አፅናናኋት! ..." ደረጄ ድንገት የዛሬ ወጪውን ሲረሳው ወደ ቀድሞ ማንነቱ ሊመለስ ስለሚችል አትረበሺ ...ዛሬን አይተነው ...የሚብስበት ከሆነ ነገ ህክምና እንወስደዋለን። እኔም እኮ ሳዋራው የተማረ በግ ገዛሁ ምናምን እያለኝ ነበር ። አልኳት.. .

"የሚሻለው ይመስለኛል ። ግድ የለሽም ይሻለዋል.. .ቅድምም ሳዋራው እኮ ትንሽ የመርሳት በሽታው መለስ እያለለት ነበር" 

ዋሽተህ አስታርቅ በሚለው የአባቶች ብሂል ፈርቀዳጅነት  ተነሳስቼ ዋሽቼ ላፅናናት ሞከርኩ ።

"እርግጠኛ ነህ ተሽሎታል ?" 

"ተሽሎታል ። "

"እና ምን ሆኖ ነው ወገቡን ይዞ የሚንጎራደደው?"

"ድንገት አማራ ክልልን የደፈሩት የሱዳን ወታደሮች ጉዳይ አሳስቦት ይሆናል "

"ሚኪ እውነት ደረጄ ተሽሎታል ?" በስልምልም አይኖቿ እየተመለከተች ደግማ ጠየቀችኝ።

"ምን ሆነሻል ?...ተሽሎታል አልኩሽ እኮ.. .አሁን ማስታወስ ጀምሯል "...

"እየው ደግሞ ወደኛ እየመጣ ነው "

ዞር ስል ደሬ ወገቡን ሳይለቅ ቀጥ ብሎ ወደኛ አቅጣጫ መጥቶ ቆመ ። ቆሞ ለደቂቃዎች አሰበ ...

"እኔ ምልሽ? " አላት ባለቤቱን 

"ወዬ የኔ ጌታ "

"ሚኪ ምን ሆኖ ነው ዛሬ የቀረው?😃 እኔ የገዛሁትን በግ ላለማየት ምቀኝነት ይዞት ነው አይደል? "

ተሽሎታል ያልኩት ደሬ አጠገቤ ቆሞ ሚኪ ለምን አልመጣም ማለቱ አስደንግጦኝ አንገቴን ደፋሁ.. .

"ታድያ አሁን ህክምና መሄድ የለብንም ትላለህ? " ቀና ስል የደሬ ሚስት አይኖች በፍርሀት እየተቁለጨለጩ ነበር ...

"የበጉን ገመድ ፈተሽ ደሬን አስረን ነው ሆስፒታል መሄድ ያለብን "....

ሚስቱ ወደ ተገዛው በግ አቅጣጫ ተንደረደረች :)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael_Aschenaki
፣____የመንደር ወግ_____ ፤

"ሳቅ ብለን ፤ አብረን ሳቅ እንበል"
የመንደር ሎሬት የተከበሩ ጋሽ በረደድ
ጋሽ በረደድ ቤት መጥተዉ አስጠሩኝ። ስወጣ ከበር ተቀብለዉ ፤ ሊገዙ
እንዳሰቡት በግ ዙሪያዬን እየዞሩ ከቃኙኝ ቡኃላ ፤ ላቴን ማንሳት ሲቀራቸዉ "አይ
ቁመና!" አሉ። "ትንሽ ብልጠት ጎሎህ የዥል ገፅ ያዝክ እንጂ ቁመናስ ነበረ። በኛ ግዜ ብትኖር ፤ 'ክቡር ዘበኛ' ሰተት ነበር የምትል ፤ አይ መለሎ!" አሉ ፤
ፈገግታቸዉን እያሳዩኝ። "ሞዴል ሊያረጉኝ ነዉ እንዴ?" ግር ባለዉ ድምፅ፤ የግዴን ቀለድኩ። "አይ ድምጥ አሉ!" 'ፅ'ን ፊደል በ 'ጥ' እየተኩ " ድምጥህ ቁጭ የ'ምንሊክ ወሰናቸዉን'፤ እስኪ ደግመህ ጠይቀኝ?"
ደገምኩላቸዉ፤ "ደግ ዛዲያ ባረግህስ ምን ያንስሃል? አብሶ ፍራፍሬ ብታለማ ፤ ይህን የብቅል አዉራጅ ቁመናህን እየተጠቀምክ፤ ይህን ረጅም ክንድህን ከዛፍ ዛፍ እየወረወርክ፤ ይህን፡ቢዘፈንለት የማያንስዉ የእግር ቅልጥምህን እየሰነዘርክ... አረ እንዲያዉም ካሻህ በዚህ ቅልጥምህ ምድር ቆመህ የኮሪያ ካራቴ ሰንዝረክ ፍሬ እያረገፍክ... ፤ጥሩ ሞዴል አርሶ አደር ይወጣህ ነበር። " ኮስተር ብለዉ ሲመክሩኝ ሳቅ ያዘለ ገፄን የግድ አኮሳተርኩ። " አይ ገበሬ ለመሆን ሳይሆን ይሄ ጥሩጥሩ እየለበሱ በመድረክ ለይ ለሰዉ የሚታዩትን አላዩም?"ጠየኳቸዉ።
" ከንቱ !ልብስ የተሰጣበት አሸንጉሊት መሆን ኖሯል ምኞትህ? " ፊታቸዉን
አጨፍግገዉ ቀጠሉ "የአንተ መሻት ከሆኑት መሀል ፤ ባለፈዉ አንዱ በቴሌብዢን ሲያወራ ሰምቼዉ፤ እኔ የይች የደርጊቴን 9 ጣሳ ጠላ ጠጥቼ እንደነሱ ነገር አልስትም" ስስቅ አዩኝና "ሙት ! የይች የደርጊቴ ጎረቤት ፤ የባዚቴ ትንሹ አፍ ያልፈታዉ ልጅ ፤ እሱ ሲኮለታተፍ መስማት ጣዕም አለዉ። ያ አጊጦ መጥቶ ከተለፋደደዉ ይልቅ። "
እየተሳሳቅን ወደታች ወረድን፤ እሳቸዉም ወጉን ቀጠሉ "ይቺ መንደር ጥንት ጥንት ሳይዘሩባት ታበቅል ነበር። ሞሎቶልህ የተከልክ እንደሆን ፤ እሸት በቆሎ ብትተክል ገሚሱ እሸት ለይ ጤፍ ፣ ገሚሱ ለይ ስንዴ ፣ ገሚሱ ለይ ማሽላ ያዝል ነበር። የበቆሎዉ አገዳ ደግሞ እንደ ሸንኮራ ግጠህ ብትበላዉ ትችል ነበር። ዛዲያ ለከብቶቻችን ክብር ስለነበረን ለ'ነሱዉ እንተወዉ ነበር። አቤት ደጉ ዘመን!" በሀሳቡ የሰመጡ ከመሰሉ በኃላ ወጋቸዉን ቀጠሉ " ጓሮዬ ለይ ሽንኩርት አለማ ነበር። ዛዲያ የሽንኩርቱን ሽፍንፍን ልጬ ሳበቃ ዉስጡ ለይ አንዳንዴ ሎሚ ፤ አንዳንዴ መንደሪን አገኝ ነበር። ያሁን ልጆች እቃ ዉስጥ ደብቃቹ ስጦታ የምትሰጣጡበትን ዘዬ ምድሪቱ ነዉ ያመጣችዉ። " መገረሜ ምንም ሳይመስላቸዉ ቀጠሉ " ትልቀቱንስ ብትል ፤ አንዱ የሽንኩርት ራስ ከ ህፃን ልጅ ራስ ይገዝፍ ነበር።" "አረ ጋሽ በረደድ... " አልኩ የሚነግሩኝ ማመን ሲከብደኝ፤ "ይሄ ደንቆህ ነዉ? እንዲያዉም አያቴ ሲነግሩኝ፤ በነሱ ዘመን 'እንጀራ የወደብቅህ እንደሆን እንጎቻ ትመርቅልህ ነበር' ብለዉኛል"
" ማነች ምትመርቀዉ ?" እየሳቅኩ ጠየኳቸዉ
" ምድሪቱ ነቻ! ለምሽቴ ይህን ከነገርኳት ዕለት ጀምሮ ለብዙ ግዜ ምጣድ
ባሰማች ቁጥር እንጀራ ወደመሬት ትጥልና እንጎቻ ትጠብቅ ነበር። ዛዲያ አልሆን ሲላት ከነአያቴ ወረፈችኝ። እኔም ለስለስ ብዬ" ተይ አለሜ ጡር አትናገሪ ዘንድሮ እንጀራዉስ መች እንጀራ ሆነና ነዉ እንጎቻ የሚመረቀዉ? የፈረንጅ መዳበሪያ ነፋፍቶት መልከኛ ሆነ እንጂ ከጥንቱ እንደማይስተካከል ተዘንግቶሽ ነዉ?" አልኳት። " ዘወር ብለዉ አይተዉኝ ቀጠሉ "እሷ ታዲያ በጄ አላለችም። እንዲያዉም ሲብስባት 'ከነ አያቶት ይነፉ' አለችኝ።" ሳቄን እንደምንም ያዝኩት። "የሜዳ አህያ ይንፉትና!" አልቻልኩም በረጅሙ ሳቅኩ። "ጉድ እኮ ነዉ አግብቼ ምኖረዉ" አሉኝ ጥርሳቸዉን እያሳዩኝ። ትዝ ሲለኝ ጠየኳቸዉ ፤ " ለምን እንደፈለጉኝ አልነገሩኝም እኮ?" አልኩ፤ ያ ሁሉ ሙገሳቸዉ ትዝ ብሎኝ እየጓጓዉ
"ከዘኑዬ ቤት ፖፖዬ እንድታወርድልኝ ነበር።" አሉኝ እኔም እንደሚስታቸዉ በዉስጤ ተሳደብኩ "ጋሽ በረደድ ከነአያቶት ይነፉ!"
ይቀጥላል...
የሚቆም ታሪክ የለም...

@getem
@getem
@paappii

#nicola nas
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ
መልካም በዓል!
ሚያዚያ 11/2012
@Mykeyonthestreet
ያለፈ የሚባል የለም፤ በዛሬ ዉስጥ የሚላወስ ትላንት እንጂ...
ዞሮ ዞሮ ከያለፈዉ የቀጠለ
****
ክፍል 2
*
"ሳቅ ብለን ፤ አብረን ሳቅ እንበል!"
የተከበሩ የመንደር ሎሬት ጋሽ በረደድ
... ያ ሁሉ ሙገሳ ፖፖዬ ለማዉረድ እንደነበር ስረዳ ነደድኩ። የሆነዉ ሆኖ ግን ከጋሽ በረደድ ጋር ወደ እትዬ ዘኑ ቤት መሄድ ቀጠልን። በመንገዳችን ለይም እትዬ አለሜ ማስክ አርገዉ ፤ ነጭ ጓንት አጥልቀዉ ጎመን ይቀነጥሳሉ። ዘበናይነታቸዉን አድንቄ ሳልጨርስ ፤ በቅንጠሳቸዉ መሀል አጠገባቸዉ ካኖሩት ብልቃጥ ወደ እጃቸዉ ይደፉና ያፋትጋሉ። ግር ብሎኝ ወደ እሳቸዉ አተኮርኩ።
አወቅኩት ፤ ሳኒታይዘር! ጋሽ በረደድም እንደኔ እያስተዋሏት ኖሮ " አንቺ አለሜ" ተጣሩ ። "እመት " አሉ ፤ እትዬ አለሜ።
"ባልተቤትሽ ባይረስ ሲያገሳ እንዲዉል ነዉ ይህን የምትቀቢለት?" አሉ፤
በእጃቸዉ በብልቃጥ ወደተቀመጠዉ ሳኒታይዘር እየጠቆሙ። "እርሶ እንደወዉ... ለራሶት ሊሞቱ አንድ ሀሙስ ነዉ የቀሮት፤ ምናለ ደግ ደጉን ቢያወሩ? " አለ እትዬ አለሜ " ወግጅ ፤ አንቺ ከገጠር ዘንቢልሽን ይዘሽ ፤ እደተንከረፈፍሽ ስትመጪ እኔ ገና ከ'ናቴ ጀርባ አልወረድኩም ነበር። ይሄ ተዘንግቶሽ ነዉ? " አሉ ወደ'ሷ እያዩ። "አዬ..." እትዬ አለሜ ሳቁ፤ "ባንቀልባ ታዝለዉ የነበረዉን ማስታወሶ ድንቅ ነዉ" አሽማጠጥዋቸዉ።
" ስማኝ ሸግዬ" ፈገግ ብለዉ ወደ'ኔ ዞሩ ፤ግን ዛሬ ሰዉ ሁሉ ለምንድነዉ
የሚያቆላምጠኝ? እትዬ አለሜ ቀጠሉ " አጤ ልብነ ድንግል ምድርን ጦር አዉርጅ እያለ ሲያስገርፍ ፤ ጋሽ በረደድ "ተዉ ምድሪቱ የተቆጣች እንደሆን ጉድ ይፈላል!" ብለዉ ይመክሩ እንደነበር ሰምተሃል?" ጭንቅላቴን በአሉታ ወዘወዝኩ። "ወመዘክር ተሰንዶ ተቀምጧል አሉ ፤ የእሳቸወ ምክሮች።" ማስካቸዉን አስተካክለዉ ቀጠሉ"ምክራቸዉ ደሞ መሬት ጠብ አይል ኖሮ እንዳሉት አህመድ
ከነጦረኞቹ መጥቶ ምድሪቱ ለይ ጉድ ፈላ።" አሉ "አስታዉስ እስኪ ይህን ታሪክ
አልነገሩህም?" ደግመዉ ጠየቁኝ፤ ደግሜ ጭንቅላቴን በአሉታ ወዘወዝኩ። "
እንግዲያዉስ አፄ ቴድሮስን አጉል ምክር መክረዉ ፤ በወኔ ሞልተዉ
ወደማይችሉት ባለጋራ እንደሰደዷቸዉም አልሰማህማ? " " ምን ትያለሽ አንቺ ሴት!" ጋሽ በረደድ ተቆጡ እትዬ አለሜ እንዳልሰሙ ሁሉ አይናቸዉን ከ'ኔ ለይ ሳይነቅሉ ቀጠሉ "ቅም አያቴ ለአያቴ ነግረዋቸዉ ፤ አያቴ ደግሞ ለ'ኔ ሲነግሩኝ 'ጋሽ በረደድ አጤ ቴዎድሮስን
በምላስ ደልለዉ ወደመቅደላ የሰደዷቸዉ ፤ ከአጤ ዩሀንስ ሰላሳ ጠገራ ብር
ተሰቷቸዉ ስለ ነበር ነዉ' ብለውኛል" አሉኝ ድምፃቸዉን ሆነ ብለዉ የሹክሹክታ
እያረጉት። "በል ና! ታሪክ ሲዛነቅ ቆሜ አላይም!" ጋሽ በረደድ እያካለቡ ወሰዱኝ፤ የእትዬ አለሜ ቀጭን ሳቅ'ም ሸኘን።
በመንገዳችን ላይም ንዴታቸዉ በእኔ ለይ እንዳይጎፈላ እየተጠነቀቅኩ ጠየቅኩ
"እኔ ምለዉ ጋሼ እርሶ ለምን አይጠነቀቁም? እትዬ አለሜን አሏያትም?" "ከአለሜ ጋር መንገዳችን ይለያያል እንጂ እኔም እጠነቀቃለዉ ። ሌት እንየተነሳዉ አየቱል ኩርሲይ ቀራና ዳዊት እደግማለዉ ። ዛዲያ አላሁና እግዜሩ ሲያብሩ ከጭንብልና ጓንት አይልቁም ትላለህ?" የብልጣብልጥ ፈገግታ አሳዩኝ። " እርሶ ጋር እራሳቸዉን አክስመዉ ነዉ የተዋሃዱት?" ሳቅ ብዬ ጠየቅኩ። "ምን አልክ አንተ አፈዛርጢ! ለዚህ ቂጣ ለቀደደዉ አፍህ ለከት አበጅለት እንጂ ፤ አጓጉል ከመለኮት ጋር የምትዳፈረዉን ነገር ያልሰማዉ እንዳይመስለህ " በቁጣ አጉረጠረጡብኝ፤ ኩም አልኩ።
አኳሃኔን አይተዉ ከአፍታ በኃላ እሳቸዉም በመጠኑ ለስለስ ብለዉ ቀጠሉ። "
እንዳንተ ያለዉ ከማስተዋል የራቀዉ፤ ብዙዉ ሰዉ 'ርስበ'ርስ የሚጋጩ
ይመስለዋል። ግን እንዲያ አይደለም። ካወቅክበት በነሱ ልፊያ ዉስጥ ልብህ
ይሰፋ እንደሆን እንጂ ፤ እግዜሩን ትተህ አላሁን ፤ አላሁን ትተህ እግዜሩን ማንሳት
ተላላነት ነዉ።" እኚህ ሰዉዬ ይፈላሰፋሉ ልበል ፤ ሀሳባቸዉ ባይዋጥልኝም ደነቀኝ። እሳቸዉም መገረሜን ከፊቴ ለይ አንብበዉ " ሌላ ቀን በሰፊዉ አወጋሃለዉ ። አሁን ዘኑዬ ጋር እንዝለቅና ፖፖዬ'ዬን አዉርድልኝ ።"
*

ቆሙ ያልናቸዉ ታሪኮች በዛሬ ግርዶሽ ዉስጥ የሚላወሱ እንጂ ሌላ ምንድናቸዉ?
ይቀጥላል....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#nicola nas
"በመጨረሻ ሁላችንም ሰላም እንሆናለን። ፀሃይ ለሁላችሁም ብርሃኗን
ትፈነጥቃለች፤ ደመናውም ይገፈፋል"
የ100 ዓመቱ አዛውንት ካፒቴን ሙር
-------------
ካፒቴን ቶም ሙር ይባላሉ፤ እድሜያቸው 99 ዓመት የሞላ የቀድሞ የእንግሊዝ
ጦር አባልና የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ የተሳተፉ አርበኛ ናቸው።
የአንድ መቶ ዓመት ዕድሜአቸውን ለማክበር የተወሰኑ ቀናቶች ሲቀሯቸው የኮሮና ቫይረስ ሃገራቸውንና ዓለምን መናጥ ጀመረ። ይሁን እንጂ ካፒቴኑ "የ100 ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የአትክልት ሥፍራዬን ስፋት አንድ መቶ እጥፍ እጓዛለሁ። እግረመንገዴንም ለእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት/NHS/ ሠራተኞች ድጋፍ የሚሆን 1,000 ፓውንድ እሰበስባለሁ" ብለው ጉዟቸውን
ጀመሩ። በካፒቴኑ በጎ ሃሳብ ልባቸው የተነካ ሰዎች ከመላው ዓለም እጃቸውን ዘረጉ። 1,000 ፓውንድ ለማሠብሠብ ያቀዱት ካፒቴን ጉዟቸውን ሲያጠናቅቁ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ሠበሠቡ። መላው እንግሊዛዊ በሽማግሌው ካፒቴን ድርጊት ልቡ ተነካ። በ24 ሰዐት ውስጥ 500,000 የሚደርሱ ሰዎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን Knighthood እንዲሰጣቸው ፔቲሽን ተፈራርመዋል።
መልካም ለመሆን ቅን መሆን ብቻ ይበቃል። ሌላው ያንን ተከትሎ የሚመጣ
ነው። 👏
----------
Capitain Moore said to everyone struggling during the
coronavirus pandemic that “at the end of the day we shall all
be ok. The sun will shine on you again and the clouds will go
away”.

ምንጭ: ።ዘ-ኢንዲፔንደንት

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun ango
''የባለቅኔው ኑዛዜ መግቢያ በጥቂቱ''
ሃሳብዎን በዚህ ይላኩልን! @Mykey21
@gebriel_19
@Nagayta
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#ወግ_ብቻ

ታክሲ ውስጥ ገብታ ልትቀመጥ ስትል ከወደኋላዋ ድምፅ ሰማሁ "ጡ.....ጥ"
ከሷ ፊት ስለተቀመጥኩ በመገረም ዞር ስል በሀፍረት ጥሬ አክላ አገኛታለሁ ያልኳት ባለድምፅ እኔ ላይ አፍጣ "ምነው? ስምህ ነው እንዴ?" አለችኝ ።
"ስም ያለው ሞኝ ነው" ደገመችኝ። (ገፅ 21)
ሰውና ጠመንጃ
ገበሬው ከሾፌሩ ግራሶ ተቀብሎ አልሰራ ያለውን ጠመንጃ እየጠራረገ ነው። የአፈሙዙ አቅጣጫ ወደሱ መሆኑ ያሳሰበው ሾፌር
" አፈሙዙን ወደዛ አዙር እንጂ "
" ምነው በሰራልኝና ባነበቀህ" (ገፅ 80)
"#ውልብታ" ከአለማየሁ ገላጋይ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፮
ቀጥያለሁ....

በትዝታ ንጉደት ህመሜን ታማችሁ ኋላዬ ነውና አሁን ላለሁበት ምክንያት
አሁንም ከጎኔ ሁኑ በደም ዜማዬን እየሰማችሁ
ትዝታ ከፉ ነው መቼም ያሰቃያል የኔ ስቃይ ሲበዛ ከፍ ያለ ንዝረት በአካሌ ላይ ሀይለኛ ምት ያደርሳል ነርቬን ነክቶ የንዝረቱን መልስ በአፍንጫዬ ቀዳዳዎች ይመለሱልኛል መልሶቹም ጠብታዎቼ ናቸው ንዝረቱ ክፉ የሆነነ ህመም ውስጥ ስለሚከተኝ ፋታ ለመውሰድ ዜማን እከፍታለሁ ስቃዬም በረድ ሲል ዜማውን ቀነስ አድርጌ በትዝታዬ እጮሀለሁ
ወደ ትዝታዬ ተመልሻለሁ .....
ፍቅሯ በመቅሰፍቱ እየመታኝ ይገኛል ሁሉ ነገሬን ነጥቃ እሷ ዘንዳ አስቀምጣዋለች ስትመጣልኝ ነው እራሴን ማገኘው
ፊያሜታዬ ነፍሴ ሆናለች....
በቃ ከሚከተሉኝ ጓደኞቼ የበለጠ እሷን ከጎኔ አድርጌ መንቀሳቀስ ጀምሬያለሁ እኔ ካለሁ እሷ አለች ባለሁበት ቦታ ሁሉ ከጎኔ አድርጌ ይዣት መዞር ጀምሬያለሁ
ተማሪውም አውርቶ አውርቶ ሰለቸው መሰል አሁን ስለ እኔ እና ስለሷ መወራቱ ቆሟል ተለምደናል እኔ እና እሷም ተላምደናል
ብዙ ቀናቶች ሆኑን አሁንም ከኔ ዘንድ ነች
ፊያዬ እንዴት እንደሆነ ባልነገረቺኝ ሁኔታ ቢዝነሱን ተቆጣጥራዋለች
ሙሉ በሙሉ በሚቻል መልኩ ሴት ተማሪዎች በእቅዴ ውስጥ አስገብታልኛለች
ከኔ ጋ ከሚሰሩት ወንዶች ሁሉ ብዙ ገቢ ምታስገባልኝ እሷ ሆናለች
ካፒታሌም በደንብ ጨመር ብሏል ....
ለሷ ምቆርጥላትን ነገር ሙሉ ለሙሉ ትቼዋለሁ አሁን ላይ እኔ ማለት እሷ ስለሆነች የኔ የሆነው ሁሉ የሷ ሆኑአል በቃ
ምታመጣልኝን ገንዘብ ለራሷ እንድትጠቀመው ነግሬያታለሁ በቃ ግድ የለኝም ገንዘቡ አሁን ላይ ለኔ ምንም ነው እሷ ደሞ ብዙ ነገሬ ናት
ኑሮዬን ከቤተሰቤ ጋ ቢሆንም የራሴ የምላት ቆንጅዬ ቤት ነበረቺኝ ብዙ ነገሮቼን ማስቀምጠው በቤቴ ነው ምቆዝምባት ትንሽ መሸሸጊያ ቤት ነበረቺኝ
ፊያሜታዬን እዛ ይሻት ለመሄድ ወሰንኩ ቀኑን እኔ እና እሷ ብቻ እንድናሳልፈው ከሰዉ አይን እራቅ ብለን በትንሿ ቤቴ ትልቅ ፍቅር ውስጥ ለመግባት አሰብኩ
ከሷ ጋ.....
ወደ ማታ ደወልኩላት ዛሬ አኩርፋብኛለች ትንሽ ደብሮኝ ነው ኘለቺኝ
ቶሎ ለመናገር ወስኜ አፈነዳሁት ምንም ሳታቅማማ ተስማማች
ግን ምን አባህ አስበህ ነው ብላ በጣም አሳቀቺኝ ጥያቄው ስለገባኝ እኔም ያን ያህል መፍጠን እንደማልፈልግ ነግሬ ቃል ገብቼ ለነገው የፍቅር የድግስ ቀኔ ማሰብ ጀምርኩኝ
ምን ማድረግ እንዳለብኝ ባላውቅም ቤቴ ባለችበት ንፁህና ቆንጆ ስለሆነች ስለ ቤቴ ማሰቡ አላደከመኝም
ብቻ እስኪነጋ ቋምጫለሁ በእቅፌ እስካሞቃት ጓጉቻለሁ እኔ እና እሷ ብቻ
በቃ አይኔ ላይ ነው.....
ትንሽ ዜማ ልክፈት ወደ ንፁህ ቤት ከመግባቴ በፊት ትንሽ ጠብታዎቼን ላፅዳ
                  ትናንትናን ጥሶ ዛሬን ተንተርሶ
                  ነገንም ተውሶ አምናንም አድሶ
                  ይመጣል ትዝታሽ ጓዙን አግበስብሶ
አዎን በትናንት ጥሰት ውስጥ ዛሬን ተንተርሼ ትውስታ መመለሻዬን ዛሬ በትናንቱ ትዝታዬ ከትቼ ነገዬን ማስተካከል ስለምፈልግ ነው እንዲህ  በስቃይ ውስጥ ያለሁት
ትንሽ ትዝታዋን ስሻ ጓዙን ጠቅልሎ መቶ ያሰቃየኛል
በቃ ትዝታ ስቃይ ነው አቦ
እመለሳለሁ......

               እቀጥላለሁ....
     ብላቴናው በደም ቀለም

@wegoch
@wegoch
@wegoch
''የባለቅኔው ኑዛዜ''
ክፍል ፩
ፋሲካ ከበደ እንደፃፈው


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#ወግ_ብቻ

ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)

፨፨፨

አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና <ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም> አሉኝ... <<ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።>>



ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!>>
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።



ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!

፨፨፨

ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ

...ዋጋ የነሱት(ያሳጡት)ነገር ዋጋ ያስከፍላል...!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
የጥላቻ ንግግርን በጋራ እንከላከል።

Oromiffa Version:

https://forms.gle/AWq3CWKwKQqvpNoV9

Amharic Version :

https://forms.gle/oMa2WHCrENvFdL3R9

English Version:

https://forms.gle/ZzJ3Kmzafu1S7o479

Thank you for your support!
''የባለቅኔው ኑዛዜ''
ክፍል ፪
ፋሲካ ከበደ እንደፃፈው
አቅራቢ @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የደሜ ዜመኞች

   ክፍል - ፯
  ቀጥያለሁ......

አይነጋ የለ እንደ መንፈቅ የረዘመብኝ ሌሊት ነግቶልኛል
በአይነ ህሊናዬ ስስለው የነበረውን ነገር ከፊያዬ ጋ ለማድረግ ጓጉቻለሁ
ዛሬ ለኔ የፍቅር ቀን ነው
አንድ ነገር አብዝተን በጓጓንለት ቁጥር ላሰብነው ሁኔታ ማድረግ የምንፈልጋቸው ነገሮች ይበዛሉ
እኔም በላፈልኝ ሌሊት ውስጥ አይደለም በአንድ ቀን በሳምንታት እድሜ አድርገን ማንጨርሳቸውን ነገር ሳብሰለስልና ስመኝ ነበር ........ ፍቅር ነዋ ነገሩ
እሷ ያለችበት አለም ይሁን እንጂ የትም እደርሳለሁ
ተመስገን...
ፈጣሪ ምወደውን ቀዝቀዝ ያለ አየር በቅዝቃዜው ወላጆች በደመና ልኮልኛል
መሬቱንም ለማረስረስ ካፊያ ይጥል ጀምሯል
ዝናብ ከመምጣቱ በፊት ብዙ ሚሰሙን ነጎድጓዶች አሉ
በኔም ስሜት ነጎድጓዱን በተሰመኝ ትላልቅ ስሜቶች ወክዬዋለሁ ዝናቡም ቀስ እያለ ይመጣ ይሆናል ልቤን ዘንባ በፍቅሯ ካረሰረሰችልኝ
ወጣ አልኩና የፍቅሯ ዝናብ የልቤን ሀገር እንዲያረሰረስልኝ ተማፀንኩ
ፊቴን ቀና አድርጌ ሌት ያልተኛውን አይኔን በዝናብ ኣራስኩት
ጠብታዎቹ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ወደ ውስጤ ሲያስገቡ ተሰማኝ
በጠብታው ምት ውስጥ ከዝናቡ በፊት ካፊያ ነው ሚመጣው
ፊያም ባትዘንብልኝ እያካፋችልኝ በመሆኑ ተመስገን አልኩኝ
ወደ ፊያ ተፈተለኩ.....
እጇን ከደረቷ ከታ ኩምሽሽ ብላ ቆማለች ዝናቡ ፀጉሯን አርጥቦ በለበሰችው ጃኬት ይንፎለፎላል
ጉርዷም በስብሷል
እዛ እረጅም ፀጉር ላይ ዝናቡ የሙጢኝ ብሏል የብዙ ኮረዶችን ፀጉር ያረጠበው ዝናብ በፊያ ፀጉር ላይ በማረፉ ደስ ሳይለው አይቀርም
ሌላ እኮ ናት ልጅቷ
ከፀጉሯ እየተንሸራተቱ በሚወድቁት ጠብታዎች የረጠበው ግንባሯን ጠጋ ብዬ ሳምኩት
አሙቀኝ ብላ አቀፈቺኝ ስላስጠበኩአት ተናዳ እኔን ለማርጠብ ፈልጋ ነው
ከላይ ብትቀዘቅዝም ከውስጡአ ሚወጣው ሙቀት አንገቴን ፈጀው
የያዝኩትን ጥላ ዘረጋሁት
እጆቻችንን አጥብቀን አቆላለፍናቸው ....
የሷን ባላውቅም የደም ዝውውሯ እስኪሰማኝ እጄን አጥብቃ ይዛኛለች ...        ፍቅር ነዋ
ወደ ትንሿ ቤቴ መክነፍ ጀመርን
እንግዳዋ በሬን በራሷ እጅ ከፍታ ገባች
ባላሰብኩት ፍጥነት ጃኬቷን እስከ ጉርዷ አውልቃ ከፍሬሼ ገብታ በብርድ ልብሱ ተጠቀለለች
ቤቴን ዙሪያዋን እየቃኘችው ነው
ጨለምለም ካለችው ቤቴ ቤት ለእንቦሳ ሳትል ዘው ብላ ገብታለች
ደማቋ ብርሀኔ ከፍራሼ ውስጥ ገብታ ቤቴን አብርታልኛለች
ቤቴን ስትቃኝ እኔም በተራዬ የብርሀኗ ምንጭ ከየትኛው ውበቷ ላይ እንዳለ ስቃኛት ነበር
አትገባም እንዴ አለቺኝ
እኔም በራሴ ቤት ና ግባ ተብዬ በመግባቴ ደስ ብሎኛል
ለፀጉሯ ሚድረቂያ ፎጣና እረዘም ያለ ሹራብ ሳቀብላት እጄን ጎተት አርጋ ከጀርባዋ እንድሆን አዘዘቺኝ
እኔም ጉብ አልኩባት
በብርድ ልብስ በሞቀው አየር ውስጥ እግሬን ወደ ውስጥ ሰደርኩት
እግሯ እግሮቼን ሲነኩት ቅዝቃዜዋ ጣቶቼን አስደነገጡአቸው
ወገቧ ከሆዴ ጋ የሙጢኝ ተጣብቋል
ከላይ ከለበሰችው ሸሚዝና ከውስጥ ሱሪዋ በቀር ምንም የለም
እኔም ወደ ትእዛዟ ገባሁ...
ፀጉሯን በፎጣው ማድረቅ ጀመርኩ ዳሌዋ ጋ ሊደረስ ትንሽ የቀረው ፀጉሯን አፍተለትለው ገባሁ
ፎጣው በዝናቡ ውሀ ይደርቃል እኔም ማላውቀው ነገር ትንፋሼን ያደረቅው ጀምሯል
የቀዘቀዘ ሞቃት ሆነቺብኝ እዛው መሞቅ ጀመረች
እኔም በአንገቶቿ ስር ጭምር እየገባሁ ፀጉሯን እየያወጣሁ ተያያዝኩት
በዙ ነገሮች የልቤን ምት ጨመሩት
እግሮቻችን ተጠባብቀዋል
ዳሌዋ ከወገቤ በታች የሙጥኝ ተጣብቋል እጆቼ በሳሱ ገላዉቿ ላይ ስልጣን አጊተዋል
ቤቴ ወሬ ናፈቃት ምትሰማው የሁለት ሰዎች ፈጣን ትንፋሾችን ነው
ከወገቤ በታች ጭንቀት ወጠረ
ፀጉሯ እስኪበቃው ደረቀ ወደዛ ወረወርኩት  ለስ
እጆቼን መሰስ አድርጌ ከጀርባዋ ላይ ጣልኩት ጀርባዋ ሙቅ ነው ለስላሳ መዳፎቼ ትልግ ግዳጅ ላይ ናቸወቀ
ኋላዋ አስፈራኝ እኔም ፈራሁ ጀርባዋ ከበደኝ ለሆነ ፈተና ዝምታዋ እንደመጣ ገባኝ
አልቻልኩም እናንተዬ በጣም የበዛ ደም እየፈሰሰኝ ነው አሁን ላይ ትንሽ ዜማ ላጫውትላችሁ
            ውብ አለም የሌለሽ እንደው ይጨንቀኛል
            ይህ ፍቅርሽ ስንቴ ገሎ ስንቴ አድኖኛል
                              ጎሳዬ ነው ትንሽ ፋታ እንውሰድ እንጂ
አዎ በገሎ ማዳን ውስጥ ነው ብዙ ሞቶች ከብዙ ድህነቶች ጋ ትግል የሚያደርጉት
መተ ተብዬ ዛሬም እየኖርኩ ነው አሁንም ተመልሼ መሞቴ አይቀርም ግን ከእንግዲህ ከሞቴ ሚያስነሳኝ ሰው ስለሌለ በዛው መቅረቴ ነው
አዳኜ እሷ ስለነበረች ከእንግዲህ ሞት እንጂ መዳን በኔ ዘንድ የለም        ስቃይ ብቻ
       
                   እመለሳለሁ......
           ብላቴናው በደም ቀለም

@wegoch
@wegoch
@wegoch
''የባለቅኔው ኑዛዜ''
ክፍል ፫
ፋሲካ ከበደ እንደፃፈው

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ረመዳን ከሪም!
@Mykeyonthestreet
#ወግ_ብቻ
.
እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ 1926 አንድ ታዋቂ የሩሲያ ደራሲ በድብርትና በሐዘን
ስሜት በመሰቃየቱ ህክምና ለማግኘት ወደ ስነ ልቦና ሐኪም ጎራ አለ።
.
.
ከምርመራው በኋላ
የሐዘን ስሜት የሚያጭሩ ተረቶችን ከማንበብ ታቅቦ በምትኩ ደስታና ሳቅ የሚፈጥሩትን
እንዲያነብ ሐኪሙ መከረው። እንዲያውም አስቂኝ የሆኑትን የሚኻኤል ዞሼንኮን (Mikhail
Zoshchenko) ድርሰቶች ቢያነብ በጤናው ላይ አመርቂ ለውጥ እንደሚያመጣ አበክሮ
አስረዳው።
.
ግና ደራሲው የሰጠው መልስ ሐኪሙን በድንጋጤ እንዲዋጥ አደረገው-
«ሚኻኤል ዞሼንኮ ማለት እኔ ነኝ» ብሎ።
.
.
አሜሪካዊው ጸሐፊ አልበርት ሐበርድ
«ለሌሎች የመጽናኛ እና የደስታ ስሜት ፈንጣቂ የሆኑ ብቁ ሰዎች ብዙ ጊዜ ራሳቸውን
ለማጽናናት ሳይቻላቸው ይቀራሉ» ይለናል። ራስህ የፈጠርከው መድሃኒት ለሌሎች ፍቱን
ሆኖ ያንተን በሽታ ለማርከስ ሲሰንፍ እንደማለት ነው።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፍም በሆነ ገላ ቤቴን ባበራው ውበት መካከል ውስጥ ነኝ
ለትንሽ ደቂቃዎች በጋለ ገላ ታስሬ ነበረ ፈተና ይሁን እውነተኛ ስሜት ምንም አላወኩም ፈተና ከሆነ እንዳለፍኩት እርግጠኛ ነኝ
ደሞም ፈተና ነው.....
ከውብ ፀጉሯ ብድግ ብዬ ጀርባዋን እየሳሳሁለት ትቼው ተነሳሁ ትናንት የገባሁት ቃል የጋለው ገላዬን አቀዝቅዞልኛል
ንዝረቴን አቁሞልኛል       ቃል ነዋ
ለእግሯ የሚሆን ካልሲ ላመጣላት ወደ ውስጥ ገባሁ
ባለችበት አገኘሁዋት ምን እናድርግ አለቺኝ ያመጣሁላትን እየተቀበለቺኝ
ቤቴ ድምፅ ሰማች ከችኩል ትንፋሾች ነፍስ ያለው ቃል ሰማች
አራበሽም አልኩአት ብድግ ብላ እኔ ነኝ እንደውም ሰርቼ ማበላህ አለቺኝ
ሙያዋ ሊፈተን መሆኑ ነው እንግዲህ
አስቀድሜ ቤቴን ሙሉ ስላደረኳት ምንም ይጎድላል ያልኩት ነገር የለም
አንድም ነገር ሳረዳት ሁሉንም እያንጎዳጎደች አውጥታ አዘጋጀች
እዚ ቤት ምትኖር ሌላ ሴት አለች እንዴ ብላ ጎሸም አደረገቺኝ
በል እንጀራ ገዘተህ ና እሺ ሚሰራውን በምን ልንበላው ነው አለቺኝ
እኔም ፈጠን ብዬ ወጥቼ ሁለት እንጀራ ከሰፈሩ ገዝቼ መጣሁ
እውነትም ፍጥነቷ ወሬ ላይ ብቻ እንዳሎነ ተረዳሁ ከመቼ ከትፋ ከመቼ ምን ብላ ሽንኩርቱን አቁላልታ ቲማቲሙን ስትጨምር ደረስኩባት
ምን እንደምትሰራ ያወኩት የባልትናውን ሽሮ ስትጨምር ሳያት ነው
ወፍራምና እረዥሙ ሹራቤ ለሷ የተሰራ ይመስል ውበቱ ጨምሯል
ያደረኩት ጸጉሯ ግርማውን ተላብሷል
የኔ እመቤት ቤቴን ማሞቅ ላይ ነች ጉድ ጉድ ስትል በቃ ሀሴቴ ከፍ አለ ሚስቴ እንድትሆን ተመኘሁዋት
ግን ቤቴ መተሽ ሽሮ ሰርተሽ ነው ምታበዪኝ አልኩአት ወደ እሷ ጠጋ እያልኩኝ
ማቀፍ ስለፈለኩ ነው ወሬውን ጣል ያደረኩት
ይው ስጋው እንዳያልቅብህ ብዬ እኮ ነው አለቺኝ መቼም ወሬዋ አይጣል ነው
እኔም በከፈተችልኝ መንገድ ገባ አልኩና ቅድም ትቼው የሄድኩት ጀርባ ተመልሼ ተጠመጠምኩበት
ወገቧን በእቅፌ አስገባሁት
ቆይ ላቅምስህ ብላ በማማሰያው ቀንጥባ ሰጠችኝ በአንገቷ ስር እርመሰመሰው ገባሁ ከንፈሮቼ እረጠቡ
አንገቷን ቀና አድርግ ጥርሷን ነክሳ ፈገግ አለች
መዞር ስለፈለገች እኔም ፈቀድኩላት
እጇቹአን አንገቴ ላይ እንደ ማህተም አጥብቃ አሰረቻቸው ወገቧን ይበልጥ ወደ እኔ አስጠጋሁት
ግንባሮቻችን አገጣጠምናቸው ከናፍርቷ ቀያይ ናቸው ዳር ዳሩ ላይ ጠቆር ያለው መስመር የበሰለ ኢንጆሪ አስመስሏቸዋል
ኢንጆሪን መተው ከባድ ነው ባህታዊ እንኳን ከባእቱ የሚያስት ውበት ከፊቴ ድቅን ብሏል
አይኖቼን ከይኖቿ ነቅይ ወደ ከንፈሯ በድጋሚ ጣልኩት ከንፈሬን አስከተልኩት
ደስ የሚል .......
ከተጣበቅንበት ያላቀቀን የሽሮዋ ተክ ተክ የሚል ድምፅ
ደረሰ አለቺኝ ደግማ ከንፈሬን እየሳመቺኝ
ሁሉንም አዘጋጅተን ወደ ገበታችን ቀረብን
ነጭ ወይን ከፈትኩኝ ለክብሯ ብዬ
ሽሮ በወይን አለቺኝ
ወደ ጂፓሴ ጠጋ ብዬ  የጥልዬን ክፉ አይንካሽ ሚለውን ዜማ ከፈትኩት
ጠጋ አልኩና የልቤን በዜማው አልኩአት
የመጀመሪያውን ጉርሻ ከአፌ ላከችለኝ ብርጭቆቻችንን አገጫጨናቸው
ለፍቅር ....
ከትዝታዬ ተመልሻለሁ ያልጨረስኩላችሁን የጥልዬን ዜማ ፋታ እንውሰድበት
                      የልቤን ልንገርሽ
                     ሳልደብቅ ገልጬ
                    በጣም እወድሻለሁ ከሂወቴ አብልጬ
                   መከራና ስቃይ ግድ የለም ይቆየኝ
                   እግዜር በጥበቡ ካንቺ ብቻ አይለየኝ
አዎ አሁንም መከራና ስቃይ በኔ ላይ ቢፈራረቁም ግድ የለም ይቆዩኝ ስሜቱ ቢከብድም አንቺን ከማገኝሽ ከትዝታሽ ይኸው የማገኝሽ እስኪመስለኝ በትዝታሽ ውስጥ ነኝ የኔ እመቤት
             
                     እመለሳለሁ......
                ብላቴናው በደም ቀለም
@wegoch
@wegoch
@wegoch
''የባለቅኔው ኑዛዜ''
ክፍል ፬
ፋሲካ ከበደ እንደፃፈው

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#ሱዳን__ገባ_አሉ__ማ__ኮሮና

ኮሮና "ጠቃልዬ ሱዳን ገብቻለሁ" አለ አሉ።......የኔ ሀሳብ አይደለም (አትኮሳተሩብኝ) አሉ ነው። ....አንድ ጠበል ቦታ ሰይጣን የያዘው አንድ ሰው አባ በመስቀል ግንባሩን ብለው "ማን ነህ አንተ?" ሲሉት "ኮሮና" አለ አሉ። ልብ አድርጉልኝ እኔም የሰማሁትን ነው ኃላ አብርሃም አለ ብላችሁ ትዝብታችሁን እኔ ላይ እንዳትጥሉ ......ከዚያ በኃላማ ሰው ሁሉ መላ አካላቱ ጆሮ ሆኖ ወደ ፀበል ቤቱ አተኮረ አሉ (አሉ ነው ልብ አርጉልኝ)......አባ ቀጠሉ "ምንድን ነው አላማህ?"አሉት አሉ በጆክ የያዙትን ፀበል አንዴ ካከናነቡት በኃላ እሱም እየተንቀጠቀጠ "ያው ህዝቡን መጨረስ ነዋ አዋቂ አልል ህፃን አልል......."አባ ይሄኔ አላስጨረሱትም በመስቀል አናቱንና አንድ ጆክ ፀበል ደረገሙበት እየተብረከረከ "ጥንቃቄያችሁስ አይረባም ነበር በፀሎታችሁ አቃጠላችሁኝ እንጂ" አለ አሉ አባም "የት አባክ አንተ ከይሲ......እሸኝሀለው ዛሬማ አንላቀቃትም" አሉት አሉ......ይሄኔ ውጪ ያለው ምእመን ሳኒታይዘር ነሽ አልኮል ነሽ አውጥቶ እጁን ተቀባባ አሉ.......አሁን ትወጣለህ አትወጣም እያሉ በመስቀል ሲደበድቡት በፀበል ሲጠምቁት ብዙ ካስቸገረ ኃላ "ሱዳን ገብቻለሁ በቃ" አለ አሉ።ህዝቡ ደስ አለው ጥቂቶች እንደውም ሳኒታይዘር ፣አልኮል የያዙበትን እቃ እንደ ኳስ ወደ ላይ አጉነው እየመቱ ሲያሽቀነጥሩት ታይተዋል አሉ....(አሉ ነው ግን)......ገሚሱም ተቃቅፎ በእንባና ሳቅ ፊቱ ተጥለቅልቆ ታይቷል አሉ.......ሰው እኮ ግርም ይላል ከፈጣሪ ደጃፍ ሄዶ የሰይጣንን ቃል ሰምቶ ይቦርቃል፤ኮሮና ህዝቡን ሊያዘናጋ ይሆን ወይስ እውነት ሱዳን ገባ እንጃለት........እና እላችኃለው ይሄንን ወሬ የሰማሁት ከእናቴ ነው ....ከቤት ስትወጣ እንደ አልቃይዳ ተሸፋፍና በፊት ጭንብል ላይ ነጠላዋን በነጠላዋ ላይ እጇን አድርጋ (ቫይረሱ እጇን ፈልቅቆ የሚገባ ነበር የመሰላት....ጥንቃቄ ላይ እኮ እሳት ነች) ....ነበር ።ስትመለስ ግልጥልጥ ብላ ፈገግ ብላ መጣች። እማ የእጅ ውሀ ላቅርብልሽ ስላት "ተወው ባክህ...ኤዲያ" አለች በማን አለብኝነት ኮራ ብላ.....እንዴ ምን ተገኘ እማ ስላት "ኮሬና ተጠቃሎ ሱዳን ገባ አቡዬ ...የኢትዮጵያ አምላክ መች ጥሎን ይጥለንና..." .......ግራ ገብቶኝ እንዴት? ማን ነው ያለው? ስላት "ፀበል ቦታ አስለፍልፈው ወደ ሱዳን ሸኙት" አለችኝ። ምን አልሽኝ እማ? የት ፀበል ቦታ ነው? "ኧረ ምኑን አውኩት የት ደብር እንደሆነ ብቻ አሉ ነው "ብላኝ እርፍ.......ይሄኔ ነው መሸሽ...ደስታም ጥርጣሬም ለሁለት ሰንጥረውኝ አለ አይደል የጭንቀት ፈገግታ ፈገግ አልኩ.....

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@wegoch
@wegoch
@paappii
#የደሜ ዜመኞች
     
    ክፍል - ፱
   ቀጥያለሁ......

ቤቴ በውብ ንግስት ጣፋጭ በሆነች ሽሮ ከምርጥ ወይን ጋር ከምሰማው ጥዑም ዜማ ጋ ሌላ ሆነናለች
የሁሉም መሰረት ደሞ እሷ ናት
ባማሩ እጆች የተሰራውን ምግብ በወይኑ እያወራረድን በውብ ዜማ ተመስጠን በልተን ጨረሰን
ዛሬ ሁሉም ነገር ደስታ ብቻ ነው
ከትዝታዬ መለስ ልበል አንዴ ብቻ ስሙኝ አደራ እንዳታዝኑብኝ      እሺ
ባሰብኩት ሁኔታ በጣም ህመሜ ብሶብኛል ይህን ምፅፍላችሁ ቃሌ ድምፅ ሆኑአችሁ እንድትሰሙኝ ብቻ ሳይሆን ወደ ትዝታዬ ለመመለስ የማደረግው ፍቱኑ መዳኒቴም ጭምር ነበር
ከአፍንጫዬ ሚወጣው የደም ጠብታ ዛሬ መልሱን አገኘ አባቴ ሀዘኑን እንኳ ሊደብቅ አልተቻለውም
ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ ከተራመዱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን እግሮቼን በእንባው አራሳቸው
እንባው መዳኒት ሆኖኝ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከጉልበቴ ስር ባነሳው ምንኛ ሀሴት ባደረኩ
ላተርፍህ ብችል.... ሊጨርሰው አልቻለም ነፍሴን ልስጥህ... በሀዘን ሳግ ሆኖ እንባ እየቀደመው ምንም ሊያወራኝ አልቻለም
የኔ አባት አለኝ በእንባው የራሳቸውን ጉልበቶቼን ይዞ
ያ አዝማሪ ጀግና የስንኞች አባት ስንት ዜማ ባንቆረቆረበት ልሳኑ አፉ ለኔ እንዲህ ቃል ሲያጥረው ማየት ምንኛ ህመም ነው
ለስቃይ የፈጠረኝ ሰው.....
ልጅህ የደም መርጋት በሽታ አለበት ብለውታል ሲመስለኝ ምሄድበትንም ቀን አያይዘው ሳይነግሩት አልቀሩም
ማንባት የለመደው አይኔ ዛሬ ሲቃ በሌለው ድምፅ ዘለላውን ብቻ ዱብዱብ ያደርገው ጀምሯል
ለምን እንደማለቅስ አላውቅም ምን አልባት ለአባቴ ስል ይሆናል እንጂማ እኔ ወደ ማርፍበት አለም ልጓዝ ነው ከዚ ካለሁበት ከስቃይ ምድር ለቅቄ
አድሎኝና ብዙ ጊዜ ኖሮኝ ከዚ በባሰ ስቃይ ውስጥ ሆኜ እንኩዋ ውብ ትዝታዎቼን ብነግራችሁ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበረ
ግን በቃ ምን አባቴ ላድርግ......
ግን ምነግራቹ ነገር አለኝ
ዛሬ ይሄን ምፅፍላችሁ በደም ቀለም ብቻ አይደለም
በደምና በእንባ ዘለላዎቼ እየጠቀስኩ ነው ማጫውታችሁ
እንባዬ ለአባቴ ነው ደሜ ደሞ ለፊያዬ
ደሞ አልፈራሁም
ስሞት እኮ ለዘላለማዊ ህይወቴ ውልደቴን እያበሰርኩ ነው
አልቅሼ ነው የመጣሁት አልቅሼ ነው ምሄደው ለዛም ነው እንባዬ
ደሞ እጅግ ደስ ብሎኛል ወደ እሷ እየሄድኩ ነዋ እዚ በትዝታ ከምዋትት እዛ በፍቅር መላእክት እርዳታ ብፈልጋት ይሻለኛል
መንገዱ ላይ ነኝ አዎ መንገድ ላይ ነኝ
ሞት እንደ ንፋስ ሽው ሲል እየተሰማኝ ነው መልአከ ሞት ለቀም ሊያደርገኝ አሰፍስፎ ቆሙአል
እኔም ከሱ እጅ ለመግባት እየዳዳሁ ነው ወደ እሷ ለመጓዝ
ውልብ ትልብኝ ገባች እኮ እናንተዬ
አረ እስቅላችሁ ጀመር   አለም ነው
እዛ እንገናኝ እንጂ እናንተ ሳመጡ ሰራግችን አይደገሰም በእውነት ስላችሁ
ሀዘን ደስታ ስቃይ ምን አይነት ስሜት ነው እናንተዬ
እዚ የጀመርኩትን ውብ ትዝታዎቼን እዛው ስትመጡ ከእሷ ጋ እንጨርስላቹሀለን
መቼም ከዛ አይቀር
ለመጨረሻ ጊዜ ሁለት ዜማዎችን አጫውታላቹሀለሁ
አንደኛውን አሁኑኑ ሁለተኛውን እሷን ፍለጋ ልሄድ ስለሆነ የዛን ሰአት አካፍላቹሀለሁ
ስወለድ አባቴ 15 አዝማሪ አምጥቶ ድል ባለ ዜማ ነው የተቀበለኝ ሲዜምልኝ እንደመጣው እያዜምኩ ነው ምሄደው
ስሞት አዝማሪዎች ባይኖሩም
በምከፍተው ዜማ አዝያሚው ሲያዜም እኔ እና መልአከ ሞት እዝማቹን እየተቀበልን ጉዞአችንን እንቀጥላለን
ኋላ ሳታመሰግነን እንዳትሉኝ ደሞ በጣም እወዳቹሀለሁ
ሰማይ ቤት አባቴ በጣም ስለሚናፍቀኝ እዛ ለማገኛቸው አዳዲስ ጓደኞቼ ደሞ የሱን ትዝታ ከመላእክት በምዋሰው ብዕር አወጋቸዋለሁ
ልዩነቱ እዛ ምንም ስቃይ የለም
በጸአዳ ባጌጠ ደስታ ውስጥ ሆኜ ነው አባቴን እና እናንተን ምጠብቀው
ግን
ይሄ የደሜ ዜማ ነው ባማሩ ትዝታዎች በስቃይ ምፅፈው
         አልፈራሁም ደሞ ማርያምን
 ዜማውን ተጋበዙልኝ
                   ልምጣ ወይ ልቅር ምን ይሻለኛል
                  ከፍቅርሽ ሚያስጥል ማን ዘንድ ይገኛል
                  ስለት አለብኝ ከርቤ እና እጣና
                  ለመተያየት እንዲያበቃን
       ማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ
                                ቴዲ ነፍሴን ስሙልኝ አቦ
አዎ ማድርበት ምሸሸግበት ጥግ አጥቻለሁ ሁሉም አንቺን በማጣቴ የሆነ ነው
ልምጣ ወይስ ልቅር እያልኩ ስባዝን ይኸው በጊዜው እራሱ ከተፍ ብሎልኛል
ፀሎቴም ተሰምቶ ስለቴን እዛው ለመላእክት እሰጣለሁ ካንቺ ላገናኘኝ ፈጣሪ እንዲሰጡልኝ

                 ሊፈፀም ሰአቱ ደርሷል
                        እቀጥላለሁ....
          ብላቴናው በእንባ ዘለላ ከደም ቀለምጋ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/25 03:18:44
Back to Top
HTML Embed Code: