Telegram Web Link
💋💋 የሚነበብ ከንፈር 💋💋
(ሜሪ ፈለቀ)


ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም።

"ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው?

"አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ እሷ ልትነግረኝ እንጂ እኔ ያስጠራኋት አይደለም የሚመስለው።

" ለምንድነው ያስጠሩኝ ዶክተር? ችግር አለ?” ለምንድነበር ያስጠራኋት? እህህህህ ዓይኗን ከከንፈሬ ላይ ካልነቀለች ለምን እንደፈለግኳት በምን አውቃለሁ? ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደትያትረኛ ተንጎራደድኩ(ተንጎማለልኩ።) እኔ ያየኋቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ትያትሮች ላይ ተዋናዩ ታሪኩ ላይ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የሌለውና አስፈላጊነቱ የማይገባኝ መንጎራረድ  መድረኩ ላይ አንድ ሶስቴ ይንጎማለላል። እንደዛዛዛዛ አደረግኩ። እኔ ግን ዓይኗን ሽሽት ነው። ለምን እንደጠራኋት አሁን መጣልኝ። 

ህሊና እኔ በማስተምርበት ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። እንኳን እንደእኔ አይነቱን ዓይንአፋር እኔ ነኝ ያለ ጀግና ወንድ ብርክ የሚያሲዝ ህልም መሰል ውበት አላት። እኔ እሱ አልነበረም ችግሬ። ቆንጆ ትሁን ፉንጋ ከሴቶች ጋር ተከባብሬ የኖርኩ ሰው ነኝ። አይደርሱብኝም። አልደርስባቸውም። የህሊና ጉዳይ የተለየ ነው። በገባሁባቸው አራት ክላሶች ሁሌ ከፊት ነው የምትቀመጠው። እሱም ባልከፋ! እነኚህ አደንዛዥ ዓይኖቿን ከከንፈሬ ላይ ለደቂቃ አትነቅልም። በስህተት መስሎኝ ተከታተልኳት…… ሃሃሃሃ አቃቂያለችኝ እንጂ ሁላ…… የመጀመሪያ ቀን እቤቴ እንደገባሁ ከንፈሬን በመስታወት አየሁት። ሆ! …… ለዓመታት በልበ ሙሉነት ያስተማርኩት ሰውዬ መንተባተብ እጀምራለሁ። ላብ ያጠምቀኝ ይጀምራል።…… አንዱን ቀን ክላሱን ሳልጨርስ አቋርጬ ወጣሁ። ሆሆ!

ምንድነው የምላት? እባክሽ ዓይኖችሽን ከከንፈሬ ላይ ሰብስቢልኝ? ማስተማር ስላቃተኝ ዓይንሽን አሳርፊልኝ? ምን አስበሽ ነው እንደዚህ የምታደርጊው?  ኡፍፍፍፍ……

"ዶክተር?” አለችኝ ጀርባዬን ሰጥቻት ለብዙ ደቂቃ መቆሜ ግራ ገብቷት መሰለኝ። ደሞኮ ድምፅዋ ራሱ የሆነ የፈጣሪ ምህረት የሚመስል ለዛ አለው።

"አቤት! እ…… እ…… የጠራሁሽ…” መንተባተብ ሲያስጠላ! ኸረ ዶክተር ትልቅ ሰው አይደለህ ምን ያንተባትብሃል? ራሴን ገስፃለሁ።

"ዶክተር ከንፈርዎትን ካላየሁ አልረዳዎትም።” ምን አለች? ምን አለች? ምን…… ምን?ጆሮዬ ሲሰማ ስቶት ነው።

"አቤት?” አልኳት ዓይኖቿን ሳልፈራ ተጠግቻት። ሳቅ እንደማለት አለች። መሰለኝ።

"ትንሽ የመስማት ችግር አለብኝ። ሲያወሩ ከንፈሮትን ካላነበብኩ ሁሉንም ቃላት ላልሰማ እችላለሁ። ባጋጣሚ ለሁሉም መምህሮቼ ስናገር  ለርሶ ሳልነግር ቀርቼ ነው።”

የባሰው መጣልህ!! 🤔😀

@wegoch
@wegoch
#ነገ 10:00 ሰዓት ጦቢያ ግጥም በጃዝ 100ኛ ወር ክብረ በዓል ይደረጋል

የት:- ኤሊያና ሆቴል
መግቢያ :- 150 ብር

@wegoch
@Nagayta
ለሰንበታችን!
💚


ጋዜጠኛ : - ካንተ የመሥራት አቅም አንፃር የሠራሁዋቸው ሥራዎች ወይም የፃፍኩዋቸው
መፅሐፍት በቂ ናቸው ብለህ ታምናለህ ?
ጋሽ ስብሐት : - አዎ በቂ ናቸው። በተጨማሪም በየሳምንቱ በጋዜጣ ላይ የማወጣቸው
ፅሁፎች ቢሰበሰቡ ብዙ መፅሐፍት አይወጣቸውም?
ጋዜጠኛ : - ሌላ ምን ሠራህ?
ጋሽ ስብሐት: - ኖርኩ !

* * *
( - አይ ጋሽ ስብሐት እውነቱን ነው ከመኖር የበለጠ ምን ሥራ አለ?! )
* * *
[በአንድ ወቅት አሁን ስሙን ከዘነጋሁት ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገው ኢንተርቪው የሰጠው
ምላሽ ነበር]


@wegoch
@wegoch
@Nagayta
ለውብ ቀን!
💚

#ትላንት በዚሁ በቻናላችን ቤተሰቦች የተዘጋጀ Hiking ተዘጋጅቶ ነበር ወዴት..? ካላቹኝ ሰሜን ሸዋ ከደብረብርሃን ወደ ደብረ ሲና በሚወስደው መንገድ የሚኒሊክ መስኮት የምትባል እጅግ እጅግ ውብ ቦታ እዚህ ቻናል ላይ ካሉት ቤተሰቦችና ሌሎች ሆንን ባልሳሳት 125 እንሆናለን ረጅምና ፈታኝ የእግር ጉዞ አድርገን ነበር በጣም የሚገርመው ልክ ቦታው ላይ ስትደርሱ ግን ያን ሁሉ ድካማቹን የሚያስረሳ ተአምር ታያላቹ ...ሀሴት ታደርጋላቹ ፣ ትፈነጥዛላቹ ብቻ የላያቹት ሂዱ ና እዩት እውነት ትወዱታላችሁ !

ትላትና ይሄንን ጉዞ አድርጌ ወደ ቤቴ ከመሸ ስመለስ አንዱ ወዳጅ ምን አለኝ አንተው መፈንጠዝ አበዛህሳ ቢለይኝ ጊዜ......የጫሌው ሼይኽ(ረዐ) ያሉትን ትዝ ቢለኝ ላኩለትና ረፍት ወሰድኩኝ....
*
*
*
እኔ ያየሁትን አይተኸው በነበር
አዳልቀኝ ሳልልህ ታዳልቀኝ ነበር
እንኳን ልለምንህ ትለምነኝ ነበር


ድምቅምቅ ያለ ሳምንት ይሁንልን !💚


@wegoch
@wegoch
@Nagayta
ለውብ ቀን!
💚

እነሆ ውብ አንቀፅ
-------------------------

“አይ ስንታየሁ ! ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ልክ የለውም። ሲጠጣ እንደ ዓሣ፣ ሲወድ እንደ
ዻጉሜ ውሻ፣ ሲቸር እንደ ንጉሥ፤ ሲያጣ እንደ ቤተክርስቲያን አይጥ ነው። ለነገ የሚለው
ነገር ከቶ የለውም። የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከልክ በላይ መሆን አለበት። ከእርሱ ጋር
እንዲስቁ - ሲስቅ። ከእርሱ ጋር እንዲያለቅሱ ሲያለቅስ - ይፈልጋል። ሕይወትን ካልኖርኸው
እንዴት ልታውቀው ትችላለህ ? የሚል ፈሊጥ አለው። ኃጢአት ነው የሚለው ነገር ያለው
አይመስለኝም። ሕይወት ያለ ኃጢአት አትሰራም፤ ከኃጢአት ባሻገር ምንም የለም። ሕይወት
በራሷ ፍፃሜ ናት ባይ ነው። እና ይኖረዋል። ”

- - -
- በዓሉ ግርማ ፅፎት በየካቲት 1975 ዓም ዕትም እና በኋላም በ"ጭጋግና ጠል"
የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ መፅሐፍ ውስጥ ከተካተተው፣ “የፍፃሜ መጀመሪያ”
ከተሰኘው ብቸኛ አጭር ልብ ወለዱ የተቀነጨበ።

@wegoch
@wegoch
@Nagayta
የስነ ፅሁፍ ምሽት በአዳማ f.r.i.e.n.d.s house ቅዳሜ ምሽት ከ12 ሰአት ጀምሮ አዳማ ኮሌጅ ከዮሀና ሆቴል አጠገብ
@getem
@getem
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (“ናካይታ” (Nagayta))
# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 102ኛ ምሽት ጥር 6 ዕሮብ

ቦታ:- ራስ ሆቴል
መግቢያ :-100 ብር
ሰዓት: 11:00

@wegoch
@balmbaras
ጥር 8, በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል
ክፍት የስራ ቦታ መፅሐፍ
ይመረቃል !
ለውብ ቀን!
💚

የጧቱ ፍንዳታ
💣💣


አዲስ አባባ። ከሩፋኤል ወደ ፒያሳ ለመጓዝ የታክሲ ወረፋ ይዣለሁ። ተራየ ደርሶ ከፊት
ካለው ጋቢና ተቀመጥኩ። ጉዞ ተጀመረ። መንገዱን ገና ከማጋመሳችን አካባቢው በከፍተኛ
የፍንዳታ ድምጽ ተናወጠ። ሾፌሩ ሁለት እጆቹን ከመሪው ላይ አንስቶ የታክሲው ጣሪያ ላይ
ሰቀላቸው። በግዳጅ ከዘመተበት የጦር ቀጠና አምልጦ ለባላንጣው ጦር እጅ በመስጠት
የተማረከ ምልምል ወታደር መሰለ። እኔም በተራየ ያበደረውን ሰው አይቶ በድንጋጤ
እንደሚሸማቀቅ ዜጋ ሾፌሩን እያየሁ ሁለት እጆቼን ጆሮዎቼ ውስጥ ወተፍኳቸው።
በአካባቢው ይስተዋል የነበረው የትራፊክ እንቅስቃሴ ለቅፅበት ቀጥ አለ። «አዲስ አባባ/
ፊንፊኔ/ሸገር/በረራ/ ወ.ዘ.ተ የቀንና የማታ ጭልፊቶች ስለበዙ መስታወት ከፍተህ
ሞባይል አትጎርጉር» ተብሎ የተነገረኝን ምክር ዘንግቼ አንገቴን በመኪናው መስኮት መዝዤ
በማውጣት አየሩን ቃኘሁት። የነዋሪው የፊት ገፅታ ለአፍታ ያህል ፍርሃት የጎበኘው
ይመስላል። በነገራችን ላይ አካባቢውን ያናወጠው ፍንዳታ የመኪና ጎማ ነበር ።
ሞባይሌ ሳይሰረቅ የመኪናውን መስታወት ዘግቼ ከዚህ በታች የመጣልኝን ሃሳብ ከጎኔ
ለነበረው ጓደኛየ እንዲህ አወራሁት :-
.
.
ከሴፕቴምበር አስራ አንዱ የሽብር ጥቃት በኋላ አሜሪካን መራሹ ኃይል በአፍጋኒስታን
የመሸጉ ኃይሎችን ድባቅ ለመምታት በሚል በዘመኑ አሉ የተባሉ የጦር መሳሪያዎችን
በግዙፍ የጦር መርከቦቹ ጭኖ ሀገር የማውደም ተልዕኮውን ለማሳካት ጥሮ ነበር። ወቅቱ
መቀመጫውን ኳታር (ደውሐ) ያደረገው የአልጀዚራ የዐረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ አያሌ
አድማጭ ተመልካቾችን በማፍራት ሰፊ ተቀባይነት ያገኘበት ነው። የዲሽ ሳህኖች የቤት
ቆርቆሮ ላይ እንደተሰጣ ብቅል እዚህም እዚያም እንደ አሸን ፈልተው የሚታዩበት ጊዜ ነበር።
በዚያ ወቅት ከተስተዋሉ ክስተቶች መካከል የማይረሳኝ የሶሪያና የስፔን ጣምራ ዜግነት
የነበረው ጋዜጠኛ ተይሲር ዐሉኒ ነው። የአፍጋኒስታን ሰንሰለታማ ተራራዎች ላይ እንደ ጦጣ
እየወጣ ዘገባዎችን የሚያስተላልፍ ብርቱ ጋዜጠኛ። የታንክ አፈ ሙዝ ላይ ተቀመጦ መረጃ
የሚያቀብል ትንታግ ጋዜጠኛ። በቀንደሃር ግዛት በምትገኝ የገጠር መንደር ውስጥ ያቀረበው
ዘገባ በህሊናየ ማህደር ላይፋቅ ተቀምጧል። ጋዜጠኛው ዘገባውን እያስተላለፈ ካለበት ቦታ
ትንሽ ፈንጠር ብሎ ነጫጭ አህዮች እየነዱ የሚጫወቱ ህጻናት ይታያሉ። ስፋቱ አንድ
ኮንዶሚኒየም ማቆም የሚችል የተደረመሰ መሬት በአቅራቢያው አለ። ይህ ስንጥቅ መሬት
ጥልቀቱ ከሶስት ሜትር በላይ ነው። መሬቱ የተደረመሰው በአሜሪካ መራሹ ኃይል
አማካኝነት ከሰማይ ቁልቁል በሚጣል ፈንጅ ነው። ተይሲር ዐሉኒ ወደ ህጻናቱ ተጠጋ።
ስለአፍጋኒስታን ህዝብ አይበገሬነት በአግራሞት ተውጦ ይናገራል። «አፍጋኒስታን ገራሚ
ሀገር ናት። ህዝቡ ከድህነት እና ኢማን ውጭ ሌላ አንዳች ነገር የለውም» ብሎ የተናገረው
ድምፁ እስከ አሁን ድረስ በጆሮየ ያቃጭላል። ወደ ህጻናቱ ይበልጥ ቀረበ። ሰማዩ ቅኝት
በሚያደርጉ የጦር ጀቶች ድምፅ እየታረሰ ነው። ተይሲር ዐሉኒ አርጩሜ ይዞ አህያ
የሚነዳውን ህጻን እየጠየቀው ነው። «እዚህ አካባቢ ስትጫወቱ አትፈሩምን?» እያለ። ህፃኑ
ፈገግ ብሎ «ለምደነዋል፤ በዚህ የተደረመሰ መሬት ላይ የፈጋውን ፈንጅ በቅርብ ርቀት ሆነን
ስንመለከት ከቁብ አልቆጠርነውም» አለው።
እኔ ግን መሃል አዲስ አባባ ሩፋኤል አካባቢ የፈነዳ የመኪና ጎማ ልቤን በፍርሃት አንደኛው
ሰማይ ላይ ወስዶ ሲመልሳት እንዴት እንደነበርኩ እኔና እኔን የፈጠረኝ ብቻ ነን
የምናውቀው። የበሬ ግንባር የምታህል አካባቢ በመኪና ጎማ ፍንዳታ እንዲህ ከተናጠች
እርጥብና ደረቁን የማይለየው ጦርነት ቢከሰት ኖሮ በጭንቀት ወደሰማይ ያረገችው ልቤ
መመለሻዋ ይርቅ ነበር።
የኃይማኖትም ሆነ የፖለቲካ የፌስ ቡክ አርበኞች ሆይ!
ኳስ በመሬት አድርጉ። ሀገር አረጋጉ። በቃል አትዋጉ። ፈጣሪ የማንችለውን ነገር
እንዳያሸክመን ሰበብ አትሁኑ። ጦርነት ይቅርና የመኪና ጎማ በፈነዳ ቁጥር እንደ ህጻን
ዳይፐር የምንፈልግ የፈሪ ስብስቦች ብዙ መሆናችንን አስቡ። የአባቶቻችንን የጀግንነት ወኔ
የወረሰ ትውልድ ያለ ይመስል ቀረርቶ አታብዙ። የጦርነት መጨረሻው በፈረሰች ከተማ
መሃል ከሞት ተርፈው የመድፍ ቀለሃ ላይ ቡና የሚወቅጡ ሰዎችን ማየት ብቻ ነው። እሱም
የሚሆነው የቡና ማሳው ተቃጥሎ ካልወደመ ነው። ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ብቻ ሳትሆን
የፈሪዎችም ጭምር ናት። ስለዚህ እየፈራን የመኖር መብታችንን በናንተ ጀግንነት ለመሸፈን
አትሞክሩ። ጀግንነታችሁን የማጋባት ግዴታ የጣለባችሁ አካል ያለ ይመስል ፌስቡኩን
የሽምቅ ውጊያ ቀጠና አታድርጉት።


አሁን ርዕሱን መለስ ብላችሁ አንብቡትማ ... ያስጨንቃል አይደል? የፌስ ቡክ አርበኞችም
ወግ ከዚህ የዘለለ አይደለም።

ምንጭ:- መሀመድ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን!
💚

በሃሳብ መንገድ ላይ
Written by ተመስገን


ሰውየው በሺ ከሚቆጠሩት የእምነት ክፍሎች ያንደኛው ‹ፓስተር› ነበር፡፡
‹ነቢያችን› እያሉ ይጠሩታል፡፡ ‹አጋንንት ያስለቅቃል፣ ሕሙማን ይፈውሳል›
በማለት የሚመሰክሩለት ብዙ ናቸው፡፡ እሱ ግን ከዛም በላይ ሃይል እንዳለው
ይሰማዋል - ሙታንን የማስነሳት፡፡ ‹‹እግዜር በህልሜ ተገልጦ ለዚህ ተግባር
እንደ ተመረጥኩ ነግሮኛል›› ባይ ነው፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ይህን ችሎታውን
የሚያሳይበት አጋጣሚ ድንገት ብቅ አለለት፡፡… በየሶስት ዓመቱ በታላቁ
ስታዲየም የሚዘጋጀው ታላቅ ጉባኤ፡፡
የዚያን ቀን ፓስተራችን ስለ ታላቁ አምላክ ሃይልና ስልጣን በታላቅ መንፈስ
ሰበከን:: ቀጥሎም ሙታንን የማስነሳት ተዓምር እንደሚከናወን አበሰረን፡፡
አዳዲስ አማኞች እንዳይደናገጡ ካሳሰበ በሁዋላም…
‹‹ከናንተ መሃል ሞቶ መነሳት የሚፈልግ እጁን ያውጣ›› ሲል ጠየቀ፡፡ በሺ
የሚቆጠሩ ሰዎች ብድግ አሉ - ‹‹…‹እኔ!›፣ ‹እኔ!›… እያሉ፡፡ አራት የተመረጡ
ምዕመን ወደ መድረኩ ወጡ:: ፓስተሩም ያዘጋጀውን መሳሪያ አስመጥቶ
በየተራ ገደላቸው፡፡ ከአፍታ ጸጥ፣ እረጭ በኋላ ወደ መጀመሪያው አስከሬን
ጣቱን ቀስሮ፡- ‹‹በየሱስ ስም ተነስና ቁም!›› በማለት አዘዘ፡፡… አልተነሳም፡፡
እንደገና ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፡፡ አልተንቀሳቀሰም፡፡ ‹‹ምናልባት ዱዳ
የነበረ ሰው ይሆናል›› … ሲል አሰበ፡፡ ወደ ሁለተኛው ሟች ተጠግቶ እንደ
በፊቱ ተጣራ፡፡… አልሆነም፡፡ ሶስተኛውንና አራተኛውንም ሞከረ:: ያው ነው::
ሽጉጡን ወደ ራሱ አዙሮ ቃታ ሳበ፡፡ እሱም አልሰራም፡፡ ጥይቱ አልቋል፡፡
የተኩስ ድምፅ የሰሙ በጥበቃ ላይ የነበሩ ፖሊሶች ባይደርሱ ኖሮ፣ ‹ነቢያችን›
እንደ ማርያም ጠላት ተቀጥቅጦ ይሞት ነበር - በተከታዮቹ፡፡… እንደ ሞሶሎኒ፡፡
… ወስደው አሰሩት፡፡ እስር ቤት እያለ አንድ ቀን እግዜርን ህልሙ ውስጥ
አገኘው፡፡
‹‹ምነው ‹ጉድ› አደረግኸኝ?››
‹‹ምን አጠፋሁ?››
‹‹ሙታንን ታስነሳለህ ብለኸኝ አልነበር?››
‹‹በደንብ እንጂ!››
‹‹ታዲያ ምነው አቃተኝ?››
‹‹የአንተ ጥፋት አይደለም››
‹‹ያንተ ነው?››
‹‹የኔም አይደለም››
‹‹እና?...››
‹‹… ጥፋት ሳይሆን ፍላጎት ነው፡፡… የመብት ጉዳይ!››
‹‹ማለት?››
እግዜር ትንሽ አሰበና የሆነውን ነገረው፡፡
‹‹ኦኬ፣ ኦኬ… አይሲ›› አለ ፓስተሩ… በመደነቅ፡፡ ‹‹… ታዲያ እኔ መታሰር
አለብኝ?›› ለማለት አፉን ከመክፈቱ ባነነ፡፡ … የሆነው ነገር ምን ነበር?
* * *
ካለፉት ሳምንታት ባንደኛው አዲስ አድማስ ርዕሰ አንቀጽ ያደረጋት አሪፍ
‹ታሪክ› ነበረች፡፡… ሰውየው ያጠፋው ወይም የበደለው ነገር የለም:: ሌሎች
ሰዎች ግን ወደ እሱ እየጠቆሙ ‹‹እሱ ነው፣ እሱ ነው!›› በማለት ጣታቸውን
ቀሰሩበት:: ሰውየውም መንገደኞቹን እየተመለከተ ‹‹ምናልባት ያጠፋሁትን
ረስቼ ይሆናል እንጂ ይኸ ሁሉ ሰው እንዴት ይሳሳታል?›› በማለት አሰበና
በማያውቀው ነገር ራሱን ጥፋተኛ አደረገ፡፡
ወዳጄ፤ ኢ-ፍትሃዊ በሆነው ቶታሊቴሪያን (Totaliteriam) ሥርዓት፤ እንደ
ራስህ ሳይሆን እንደ ሌሎች እንድታስብ ትገደዳለህ፡፡ ታላቁ ፈላስፋ ባሩክ
ስፒኖዛም በወጣትነቱ የገጠመው ፈተናም ተመሳሳይ መንፈስ ነበረው፡፡
ሆላንድ በስደት የኖረው የአይሁድ ማህበረሰብ ዕምነት ተቋም
(Synagogue) የልጃቸው ታላላቅ ሀሳቦች ተናነቃቸው፡፡ የውሸት ክስ
ቀምመው ከጉባኤ መማክርቱ ፊት አቆሙት፡፡… እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ1656
ዓ.ም፡፡ …ያኔ ሃያ አራት ዓመቱ ነበር፡፡
‹‹እግዜር እንደ ሰው የሰብዓዊ አካላት (Matter) ውቁር ሊሆን ይችላል፣
መላዕክቶች የቅዠት ምስል (Hallucination) እንጅ እውን ሆነው የሚገለፁ
ፍጥረታት አይደሉም፣ ነፍስ የምንለው ህላዌ ሰብ ከስጋና በሕይወት ከመኖር
ተነጥሎ ለዘለዓለም የሚቆይ ተዓምረ ክስተት አይመስለኝም፣ ከሞት በሁዋላ
ሕይወት ስለመኖሩ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ነገር የለም›› ብለህ ለጓደኞችህ
የተናገርከው እውነት ነው ውሸት ሲሉ ጠየቁት፡፡ ‹‹ምን እንደመለሰላቸው
አልታወቀም፡፡›› ይልና ፀሐፊው፤ ነገር ግን ለወደፊቱ ግላዊ ሀሳቡን በውስጡ
ይዞ፣ ቢያንስ በሌሎች ሰዎች ፊት ለአይሁዳዊ እምነት ታማኝ መስሎ
እንዲታይ፣ ለዚህም በየዓመቱ አምስት መቶ ዶላር ምንዳ ሊሰጡት
መወሰናቸውን እንዳሳወቁት ያትታል፡፡
ስፒኖዛ ግን የዕድል (fate) ጉዳይ ሆኖ አፈጣጠሩ ለአይሁድ ትልቅነት ሳይሆን
ለዓለም በመሆኑ መደለያቸውን አጣጥሎ በፀናው ሀሳቡ ቆመ፡፡ ጉባኤውም
ሕገ ደንባቸውን መሰረት አድርጎ ‹ይገለል› (Excommunicated ይሁን)
የሚል ፍርድ አሳለፈበት፡፡
በታላቅ ስነ ሥርዓት የተከናወነው የዚህ ፍርድ ሂደት እስራኤልን፣ አምላኳንና
ሕገ መጽሐፏን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ መሆኑን ይዘረዝራል:: በፈላስፋው
ላይ ከተላለፈው የእርግማንና የውግዘት መዓት በተጨማሪ ከማንኛውም
እስራኤላዊ ጋር በጽሑፍም ሆነ በቃል ግንኙነት እንዳያደርግ፣ ማንኛውም
ዓይነት አገልግሎት እንዳይሰጠው፣ ከማንም የማህበረሰቡ አባል ጋር በአንድ
ጣራ ስር እንዳይኖር፣ እሱ ካለበት ቦታ ቢያንስ አራት ሜትር መራቅ
እንደሚገባና ጽሑፎቹን ማንበብ ክልክል እንደሆነ ይደነግጋል::
ስፒኖዛ በታላላቅ ሀሳቦቹ ምክንያት ከሚወዳቸው ወገኖቹ ተገለለ፣ ራቀ፣ ከስራ
ተፈናቀለ፣ ብቸኛ ሆነ፡፡ ይህም ሳይበቃ በአንድ የማህበረሰቡ ሥነ መለኮት
አጋፋሪ የግድያ ሙከራ ተደረገበት፡፡ ተረፈ እንጂ፡፡
‹‹There are few Places in this world where it is safe to be a
philosopher›› በማለት የጻፈው ያኔ ነው፡፡ ፍሬደሪክ ኒች፤ ኢየሱስን
‹‹የመጨረሻው ክርስቲያን በመስቀል ላይ የሞተው ነው›› ብሎ ሲጽፍለት ብዙ
ሊቃውንት ስፒኖዛን እንዴት ‹ረሳው?› በማለት ተገርመዋል፡፡
ወዳጄ፡- በዚህ ዘመን ሕገ ደንብ፣ ሕገ መንግሥት ወዘተ በሚል ሽፋን ታላላቅ
ሀሳቦችን ለማኮላሸት መሞከር አይቻልም፡፡ የአንዱንና የሁሉን ዜጋ መብት
የማያከብር ሕግም ሆነ ደንብ አለም አቀፋዊ፣ ሰብዓዊ፣ ተፈጥሯዊና
ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ባገናዘቡ ሕጎች ሊሻሻል ወይም ሊተካ ግድ ነው፡፡
በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት ቀርበው ‹‹ወንጀሉን
የፈፀምነው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ነው›› የሚል አስደንጋጭ
መልስ ሲሰጡ ሰምተን አፍረናል፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ምን ማለት
እንደሆነ አልገባቸውም።
* * *
ወደ ጨዋታችን ስንመለስ፡- አስከሬኖቹ ያልተነሱት በዚህ አጭር ዕድሜ
በክልል ተፈርጀን፣ እየተጨቃጨቅን ከምንኖር እስከ ዕለተ ምፅዓት ሁሉም
እኩል በሆነበት መካነ መቃብር መቆየት ይሻለናል በማለታቸው ነበር፡፡
በነገራችን ላይ ‹‹ብዙ ጠንቋዮችና አዋቂ ነን ባዮች ጋ ሄጄ የተለያዩ ነገሮችን
ነግረውኛል:: ማናቸውም ግን ፖሊስ መሆኔንና ላስራቸው እንደመጣሁ
ሊያውቁ አልቻሉም፡፡›› በማለት የፃፈልን ማን ነበር?
ሰላም!!

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/27 00:18:09
Back to Top
HTML Embed Code: