Telegram Web Link
~~ ሞካሪና አስሞካሪ ~~
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።" አልኩት
"እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?"
"እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……"ድንግል መሆን አልፈልግም።" አልኩት
"ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? " "አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……… "ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ ሰማሁ። መሞከር ፈልጋለሁ።" "አይ አይ አይ…… ጥሩ አይደለም ማሬ ስሞትልሽ አትሞክሪ።" አለኝ እያንገፈገፈው "ልንገርህ ብዬ እንጂ መሞከሬ አይቀርም። እነቤቲ ዛሬ እንቅማለን ብለዋል…… "ሳልጨርስ ቀድሞ "እሺ በቃ ፍቅሬ እሺ…… መሞከር ከፈለግሽ እኔም አብሬሽ እሞክራለሁ። ከኔጋ ቃሚ…… " ጫቱንም ፍራሹንም ሰጠኝ።…… መቃም በፈለግኩ ቁጥር ከስራ እየቀረ አብሮኝ ቃመ። ወራት ነጎዱ………"ልመረቅ ስለሆነ ስክር ማለት እፈልጋለሁ ክለብ ውሰደኝ" አልኩት……
"እሺ እንደፈለግሽ ሁኚ እጠብቅሻለሁ።" አለኝ…… መጠጡን ቀዳልኝ…
እንደፈለግኩ ሆንኩ……
ሰዓታት ነጎዱ……
"ማጨስ እፈልጋለሁ።"
"እማ ስካሩ አይበቃም? ፕሊስ ጭሱ ይቅር? "ለአፉ አለኝ እንጂ የፈለግኩትን
ሳልሞክር ማቆሚያ እንደሌለኝ ያውቃል።
"እሺ ገዝቼልሽ ልምጣ? " "አልፈልግም የተጨሰ ግማሽ የደረሰ ሲጋራ ነው ማጨስ የምፈልገው።… እንደውም ያን ሰውዬ ስጠኝ እለዋለሁ።" "እሺ እሺ በቃ የተጨሰ አይደል ማጨስ የምትፈልጊው? በቃ እኔ አጭሼ ሰጥሻለሁ።…… ከሌላ ሰው ከንፈር ተውሰሽ አታጨሺም! " አጭሶ ሰጠኝ። አጨስኩ።… እስክመረቅ በጨፈርኩ ቁጥር የተጨሰ ሲጋራ አቀበለኝ። ዓመታት ነጎዱ…… ብዙ ዓመታት…… እንደተመረቅኩ ከሃገር ወጣሁ።……
ተራራቅን…… ከጊዜ በኋላ መገናኘት አቆምን።… አገባሁ…… ወለድኩ…… ለበዓል ወደሃገር ቤት ተመልሼ ሳለሁ መንገድ ላይ አየሁት።…… ደነዘዝኩ። ያ ሊነኩት የሚያሳሳ ቆዳው ከስሎ…የሚያንጠራራ መለሎ ቁመናው ጎብጦ… የሚያኮራ ደልዳላ አካሉ ኮስምኖ… አይሆንም እሱ አይሆንም! "አቁምልኝ! አቁምልኝ! "ጮህኩኝ ባሌ ላይ… ዘልዬ ወረድኩ እና እጁን ይዤ አስቆምኩት። "እማ አንቺ ነሽ ስካሬ እያስቃዠኝ ነው? " አለኝ ከቃላቶቹ እኩል የርካሽ መጠጥ ጠረን እየተፋ "አባ አንተ ነህ? ምን ሆነሃል? በየሱስም ምን አገኘህ? ታመህ ነበር? በየሱስ ስም…… ደህና ነህ? ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?" "አንቺ እማ! አንቺ ነሽ የተከሰትሽው! ሌላ ማን አለ አንቺ "… የሆነ የአዳም ረታ መፅሃፍ ውስጥ ያለሁ ገፀ ባህሪ የሆንኩ መሰለኝ። እንጂማ እኔ በእውነታው ይህችን ሴት ልሆን አልችልም። በሱስ ምክንያት በተደጋጋሚ አማኑኤል ሆስፒታል እንደነበረ ነገረኝ። በዛ ምክንያትም ስልክ ኖሮት ስለማያውቅ
ላገኘሁ እንዳልቻልኩ አብራራልኝ……
"እማ አንቺ ማለት የምትበር ቢራቢሮ ነበርሽ…… ነፃ የሆንሽ… ነፃነትሽን
የምትወጂ… ካልሞከርሽ የማታረጋግጪ…… ሁሉን ሞከርሽ እኔን ጨምሮ ሁሉን ተውሽ! ሁሉን አስሞከርኩሽ ከሁሉ ተጋባሁኝና ቀረሁ። " አለኝ።
አይ አይሆንም የአዳም አንዷ ገፀባህሪማ ሆኛለሁ።…… ነፃነት? ሌላውን የገደለ
ነፃነት? በሌላው ባርነት ላይ የቆመ ነፃነት? የአባን ገፅ ያከሰለ ነፃነት?
……… አይሆንም ውሸት ነው። እኔማ እውን አይደለሁም…

@getem
@getem
@paappii

#meri_feleke
ይሄን ሰው ምን ነካው ?
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ከእንቅልፌ በነቃሁ ቅፅበት ታናሽ ወንድሜ ከአልጋዬ ግርጌ ቆሞ ውዳሴ ማርያም ሲደግም አየሁት ። አይኔን ባለማመን ደግሜ ፣ ደጋግሜ አሻሸሁት ። ራሱ ታናሽ ወንድሜ ነው ! ያ መጠጥ ከማብዛቱ የተነሳ ዛሬ ምንም አልቀመስሁም አንድ ካሳ ቢራ ብቻ ነው ብሎ የሚሽኮረመመው ፣ ጫት ቅሞ ጉንጩ ውስጥ ሲወጥር የዛች የትግሪኛ ዘፋኟን ሪች መቀመጫ😜 የሚያሳህለው ፣ የሺሻ ጎማ በመጎተት ከኤርታሌ እስለ ሱማሌ የሚሰማ ቱርርርርርር የሚል ድምፅ የሚያወጣው ወንድሜ ነው እየፀለየ ያለው 🙂
የማየው ነገር ህልም እንዳይሆን ተመኘሁ ። ደስ ሲል ደግሞ ህልም አይደለም ! እናቴ በሁኔታው ተገርማ አይኖቿ ሲበሩ ይታወቀኛል ። በሰፈር ሽማግሌ ፣ በንሰሀ አባት ፣ በፖሊስ እና ፌደራል ተሞክሮ ጠባይ ሳይገዛ የኖረው ወንድሜ እነሆ በመጨረሻም በራሱ ጊዜ እንዲህ ለፈጣሪው ተንበረከከ ! አቤት ጠሎት ! አቤት ስግደት ! እጁን እያጣመረ ፣ ከወገቡ ሸብረክ እያለ ሲሰግድ ላየው ዛሬውኑ ጣዲኡ አቡዬን ታልሆንኩ ብሎ የወሰነ ነበር የሚመስለው ።
ደግሞ ከፀሎቱ ብኋላ በላስቲክ አድርጎ ውጭ ካስቀመጣት ፀበል ተጎነጨ ። አቤቱ ማረን ጌታችን አለ ! በስልኩ የቴዎድሮስን መዝሙር ከፈተ !
ያ በማይክል ጃክሰን ዘፈን የቤታችንን ሴራሚክ ያነቃንቅ የነበረው ፣ የሰፈሩን ከለቦች ከራሱ ሸሚዞች በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀው ፣ ዲጄ ልሆን ነው ብሎ ላፕቶፕ በጀርባው አዝሎና ጠጉሩን አንጨባሮ ሲንበጫረቅ የኖረው ወንድሜ መዝሙር አዳመጠ ። ደግሞ መዝሙሩን በቅጡ ባያውቀውም በስሜት ነበር የሚዘምረው ።
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን ! የሚለውን መዝሙር
እናታችን ነሽ ማርያም ባንቺ አይምጡብን ! 🤣🤣እያለ ይዘምራል ። ኽረ ይሄንስ ማን አየበት ? ይሁን ነው የሚያስብለው ! ደግሞ ባንቺ አይምጡብን የሚለው ባንቺ አይምጡብኝ የምትለው የናቲ ማን ሙዚቃ ትውስ እያለችው እንደሆነ እናውቃለን ። ቢሆንም ዋናው ለመዘመር በስሜት መመሰጡ ነው ። ከሀሽሽ ጡዘት ወደ መዝሙር ምሳጤ መግባት እጅጉን አስደማሚ ነገር ነው ።
ጭራሽ ይባስ ብሎ ወንድምዬ እስቲ ተነስ እና እምነት ልቀባህ ብሎ ተመለከተኝ ።
"ማታ ራሴን አሞኛል ብለህ አልነበረምን ?🙂 ና ልቀባህ ትድናለህ ! "
ጆሮዬን አላመንሁትም ። በሌባ ጣቴ ኮረኮርሁት ። የሆነ ቢጫ ኩክ ዘኝዬ ወጣሁ ። ታናሼ ያ “ ጀለስ እስቲ ለውሎ ገንዘብ ቦጭቅ “ የሚለኝ ወንድሜ እምነት ልቀባህ አለኝ ።
ተነስቼ ግንባሬን አቀረብሁለት ። በስመ ስላሴ አንጣረ ገፁን አማትቦ ቀባኝ እና የስራ ሰዓት ደረሰብኝ ብሎ ጥሎን ተፈተለከ ።
ቅፈላ ይል የነበረው ወንድሜ ስራ ሲል ............
እናቴ የምታየውን ባለማመን እንደ ፀሀይ የበራ አይኗ ይበልጡን ቦግ አለ ። እየሱስ ዳግም ሊመጣ ነው አልያም ዓለም አሁኑኑ ልትጠፋ ነው ብላ የሰጋችም ነገር መስለኝ ።
ወድያው ከሰዓታት በኋላ አንዲት ሸጋ መልከ ግቡ ወጣት ቤታችን መጣች !
አመጣጧ ወንድሜን ፈልጋ ነበር ። "ማታ ሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ስላለ ወንድምህ እንዳይቀር ንገረው" አለችኝ ። ዓይኖቿ እንደ ቤተክህነት ጉልላት የተንጎማለሉ ናቸው ። ፈገግታዋ ገዳይ ነው ። 😍
እሺ እነግረዋለሁ !
አመስግናኝ ወጣች ። ዝቅ ብላ አመስግኛለሁ ስትል ከመሬት ላይ ኮብልስቶን ነክሳ ለመመለስ ምንም ያህል አልቀራትም ነበር ። አቤት ውበት ! አቤት ትህትና !
ወንድሜ እሷን አይቶ መሆን አለበት ሀይማኖተኛ ለመሆን የወሰነው ።
ስምሽን ማን ልበለው ?
ሊያ !
ሊያ ! እጅግ ደስ የሚል ስም ።
በድጋሚ አጎንብሳ (ይቅርታ መሬት ልሳ 😀) አመሰገነችኝ ። ጀርባዋን ሰጥታኝ ስትሄድ እስከ መታጠፊያው ድረስ በአይኔ ሸኘኋት ።
አመሻሹ ላይ በጠባቧ የቤታችን በር በኩል አንድ ዘግናኝ ሲጃራ የተቀላቀለበት የአንቡላ ሽታ ሰተት ብሎ ገባ !
አቤት ቅርናት ! አቤት ግማት !
እናቴ የዚህ ሽታ ክፉ ትርታ በልቧ አለባት ። ህይወታችንን አመሳቅሎ እናቴን ተስፋ ያስቆረጣት ይህ አይነቱ ግማት ነው ።
ታናሽ ወንድሜ ጥንብዝ ብሎ ሰክሯል ።
አይ ሰይጣን ! ደግሞ ተመልሶ ሰፈረበት ። እናቴ ተስፋዋ ሲጠልም እና በደስታ ሲፍነከነክ የዋለ ፊቷ ክስም ሲል ይታወቀኛል ።
"አንተ ደደብ አህያ ከበሩ ላይ ዞር በልልኝ አለኝ !"
ያ ሁሉ የጠዋት እንክብካቤ አይኔ እያየ ገደል ገባ ። ውሻ አለኝ ቀጥሎ !
እልሄን ውጬ ዝም አልኩት ።
"ሊያ ! እኔ እንደዛ እያፈቀርኩሽ ሌላ ጓደኛ አለኝ ልትይ አይገባም ነበር !" ልትፈርስ አንድ ሀሙስ የቀራት የቤታችን ግድግዳ በወንድሜ ቡጢ ተነረተች ። የእናቴ ልብ ከግድግዳው እኩል ሲወዛወዝ ተሰማኝ ።
ምስኪን እማዬ !!🙂

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚

“ቆመን ጠበቅናቸው፤ ጥለውን
አለፉ”


“ከብረው ይቆዩኝ ከብረው
ባመት ወንድ ልጅ ወልደው!
አምሣ ጥገቶች አሥረው…!”
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አሳማ፤ በጐች በብዛት ወደተሰማሩበት የግጦሽ
መስክ ጐራ ይላል:: እረኛው “ምን ሊያደርግ መጣ” በሚል ጥርጣሬ
ያስተውለዋል፡፡ አሳማው ወደ በጐቹ ለመቀላቀል ይሞክራል፡፡ እረኛው ያደፍጥ
ያደፍጥና ፈጥኖ ተጠግቶ አሳማውን ይይዘዋል፡፡ ከዚያም፤
“ለምን መጣህ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
አሳማውም፤
“ከበጐች ልመሳሰል” ሲል ይመልሳል፡፡
“ተመሳስለህስ?”
“እንደ በጐች ልኖር”
“ኖረህስ?”
“እንደ በጐች እንድታኖረኝ!?”
“አንተን እንኳን ለዚህ አልፈልግህም አያ አሳማ”
“እንግዲያ እንዴት እንድኖር ትፈልጋለህ?”
“አይ፤ ኑሮው ይቅርብህና ወደ ተገቢው ቦታ ብወስድህ ነው የሚሻለው፡፡”
ብሎ፤ እየጐተተ ወደ እንስሳ ማረጃው ቦታ ይዞት ሊሄድ ይጐትተዋል፡፡
አሳማው፤ መወራጨት፣ መንፈራገጥ፣ ማጓራት መጮህ ይጀምራል፡፡
ይሄኔ ከበጐቹ መካከል አንዱ ብቅ ይልና፤
“አያ አሳማ?” አለ በለጋስ ጥያቄ ቅላፄ፡፡
“አቤት” አለ አያ አሳማ፡፡
“ምንድነው እንደዚህ የሚያስጮህህ? እኛ ሁላችንም ’ኮ በጌታችን
እየተጐተትን ወደ ሌላ ቦታ እንወሰዳለን፡፡”
“ነው፡፡ ግን የእኔ ይለያል” አለ አሳማ፡፡
“እንዴት?” አለ በጉ፡፡
“አይ አያ በግ፣ የሁለታችን ለየቅል ነው!”
“እኮ እንዴት?”
“ጌታህ አንተን የሚፈልግህ ከቆዳህ ሱፍ ለመሥራት ነው፡፡ እኔን የሚፈልገኝ
ግን ለሥጋዬ ነው - ጠብሶ ሊበላኝ”
አያ አሳማ፤ እንደፈራው እየተጐተተ ሄደ፡፡
***
በአዲሱ ዓመት ከእንዲህ ያለ ምርጫ ይሰውረን፡፡ ለጥብስ ይሁን ለሱፍ፣ ዞሮ
ዞሮ መታረድ ላይቀር ምርጫውን በቅናት መልክ ከማሰብ ይሰውረን፡፡
አራጁንም መሆን ታራጁንም መሆን በፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ አሰቃቂ ነው፡፡
“አውራ ዶሮ ጮኾ መንጋቱን ነገረኝ
ዛሬ ማታ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ”
እንዳለው አንዱ የእኛ ገጣሚ፤ የታራጅና አራጅ ምፀት የምንነጋገርበት
እንዳይሆን አዲሱ ዓመት ልቡን ይስጠን፡፡ አዲሱን ዓመት የእኩልነት
ያድርግልን!
“ይገብር ካላችሁ ዝንጀሮም ይገብር
የንጉሥ አይደለም ወይ የሚጭረው ምድር” የምንልበት ዘመን ይሁንልን!
“ከብረው ይቆዩኝ ከብረው
ባመት ወንድ ልጅ ወልደው
አምሣ ጥገቶች ወልደው…”
ስንባል ሞቅ የሚለን፣ ከጭንቅ የሚገላግለን የአዎንታዊነት ምርቃት
እንዲሆንልን እንጽና፣ እንጽናና፡፡
የአቦ - ሰጡኝ ሳይሆን የትግል ዓመት እንዲሆንልን ልብና ልቡናውን ይስጠን!
የችግር ማውሪያ ሳይሆን የመፍትሔ መፈለጊያ ዘመን እንዲሆንልን አንጐሉን
ይስጠን!
የመለያያ ሳይሆን የመዋሃጃ፣ የመተሳሰቢያ ዘመን እንዲሆን በጐ አመለካከቱን
አያጨልምብን!
ዕድሜ የጊዜ ሳይሆን፤ የመጠንከር አቅም - የመገንባት፣ እርምጃችንን
የማትባት ይሆንልን ዘንድ እርዳታው አይለየን፡፡
ሽቅብ እየተመነደግን እንጂ ቁልቁል እያደግን እንዳንሄድ፣ ድላችንን
አስተማማኝ ያድርግልን፡፡
ፀሐፊዎቹ እንዳሉን፤
“አንድ ግዙፍ የብርቱካን ዛፍ እናስብ፡፡ በስሎ የተንዠረገገ ብዙ ብርቱካን
አለው፡፡ ወደ ታች፣ በሰው ቁመት ያሉትን ብርቱካኖች በብዛት ለቀምኳቸው፡፡
ከዚያ በላይ ያሉትን ለመቅጠፍ ቁመት አጠረኝ፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ
የብርቱካን እጥረት አለ ልል ነው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን አንድ አዋቂ ሰው
አንድ ቴክኖሎጂ ፈጠረ፤ መሰላል የሚባል፡፡ ወደ ማይደረሱት ብርቱካኖች
መድረሻዬን አበጀልኝ:: ችግሬ ተቃለለ፡፡ ቴክኖሎጂ ወደ ኃይል ምንጭ
መዳረሻ/ ማግኛ ስርዓት ነው፡፡ ያኔ እጥረት ያልነው ነገር፣ አሁን በሽ - በሽ፤
ነው ያሰኘናል፡፡” (“አበንዳንስ”፤ በፒተር ዲያማንዲስ እና ስቲቨን ኮትለር)
ስለ ዕጥረትና ስለ ዕጦት የምናስብበት ዓመት እንዳይሆን መሰላሉን
የሚሰጠን አዋቂ ይዘዝልን፡፡
በሁሉም ዘርፍ ለድል ያብቃን፡፡
የጀመርነው ለውጥም ይቅናን፡፡ ኑሮም ይታደገን!
በጐ እንድንመኝ፣ በጐ እንድናገኝ፤ በጐ እጅ ይስጠን!
“አይቀጭጭ ትልማችን፣ አይራብ ህልማችን!
አይሙት ሐሞታችን፣ አይቃዥ ርዕያችን!
አይንጠፍ ጓዳችን፣ አትምከን ላማችን!
አይክሳ ቀናችን፣ አይላም ጉልበታችን!!
ከሁሉም ከሁሉም አይጥፋ ሻማችን!”
ብለን የምንመኝበትን የህይወት ፀጋ አይንሳን!!
በአንድ ወቅት ታዋቂው የእስፖርት ሰው ይድነቃቸው ተሰማ፣ ሱዳን ከእግር
ኳሱ አምባ ጠፍታ ከርማ ወደ ሜዳ ስትመለስ ያሳየችውን ድንቅ እርምጃ
በተመለከተ የሰጡት አስተያየት፤ ማስገንዘቢያ፣ ማስጠንቀቂያና የእግር ኳሱን
ሂደት ማሳያ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ደግሞ ዋና ማሳሰቢያ ነው!
“ቆመን ጠበቅናቸው ጥለውን አለፉ!” ነበር ያሉት፡፡ ከዚህ ይሰውረን!
እንደ አዲስ ዓመት ምላሽ “ከብረው ይቆዩን ከብረው” የምንባባልበት
እንዲሆን እንመኛለን”
መልካም አዲስ ዓመት!!

#ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ


@wegoch
@wegoch
‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የኪነ
ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

የኢፌዲሪ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ከተስፋ ፊልም
ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በተፈጥሮ፣ በዘመንና የሰው ልጆች
ግንኙነትና መስተጋብር ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ››
የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በብሄራዊ
ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ላይ #ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ሥነ-ጽሑፍና ተፈጥሮ፣
#የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬ ስብሃት ሙዚቃና ተፈጥሮ፣# ሀኪም አበበች
ሽፈራው የባህል ሕክምናና እፅዋት፣ #ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ኢስላምና
ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ሽብሩ ተድላ ደግሞ በእንስሳት ዙሪያ፣ #ደራሲ አለማየሁ ዋሴ
(ዶ/ር) ቤተ ክርስቲያንና ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ታደሰ ደሴ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ
አለማት በእንስሳትና በእጽዋት አያያዝና ተሞክሯቸው ዙሪያ በሚል
ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን #ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ #ደራሲና ጋዜጠኛ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ #ፕ/ር ሰብስቤ ደምሴ፣ በተመሳሳይ ርዕስ ስራዎቻቸውን
ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
#ገጣሚ ረድኤት ተረፈና ገጣሚ #ተዋናይ ተፈሪ አለሙ ግጥሞቻቸውን የሚያነቡ
ሲሆን፣ ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የተሰኘ የ15 ደቂቃ አጭር ተውኔት
እንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ገልጸዋል::

@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚


“ ትዕግሥት ትመስለዋለች። ስታጠና እንደ ነበረችው ረዥም ቀሚሷን ለብሳ፥ በነጠላ
ጫማ አጭር ቁመቷ ይብሱን ተጋልጦ፥ በፈገግታ ጉንጮቿን እያሠረጎደች አቤል መኝታ ቤት
ድረስ በምሽት ከተፍ!
“ምነው አቤል? ሰው ለምን ታስቸግራለህ? እኔንስ ለምን በፍቅር ታሠቃየኛለህ? ለምን
ግልፅ አትሆንልኝም? ማፍቀር'ኮ ነውር አይደለም” ስትለው …
አቤል ግልፅነቷ እየገፋፋውና የተከዘው ገፅታዋ እያሳዘነው፥ “እኔ ምን አደረግኩሽ ታዲያ?
ደግሞ ተበዳይ አንቺ ሆንሽ እንዴ? እኔ ምን ያህል እንደ ተቃጠልኩ ውስጤን ገልጠሽ
ባየሽው!” አላት።
“አትዋሸኝ አቤል! እውነቱን ንገረኝ። ስታየኝ ግንባርህን የምታኮማትርብኝ፥ ዘግተኸኝ
የምታልፈው ለምንድነው? ፍቅር ነው ጥላቻ?”
“የጥላቻ ነገር ለምን ታነሻለሽ? በእኔና በአንቺ መሐል ጥላቻን ምን አመጣው? የማደርገው
ሁሉ የፍቅር ነው።”
“ታዲያ እንዲህ በዕውር ፍቅር እንዴት እንዘልቀዋለን፥ አቤል? ሁለታችንም ውጥረት ላይ
ያለን ተማሪዎች ነን። እኔን የገና ማዕበል እየጠበቀኝ ነው። አንተም መመረቂያ ዓመትህ
ነው። ግልፅ ካልሆንን እኮ ሁኔታችን ለሁለታችንም ግብ መሰናክል ነው።” …
… ከእንቅልፉ ባነነ። እንቅልፍ ዓይን መጨፈን ብቻ በሆነና፥ ከትዕግሥት ጋር ካገናኘው
ሕልሙ ላለመንቃት ዕድሜ ልኩን አይኑን በጨፈነ ምን ነበረበት! …”


ሰመመን | ከሲሳይ ንጉሡ | 1978 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 113-117

ውብ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
"ጤና ይስጥልን" ልዩ እትም ለእናንተ

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 17/01/2013
።።።።። መደረቢያ ።።።።።።።

ከዛ ከኛ ቤት ከባሰ አመዳም ደሃ ጎረቤታችን ቦቸራ ሳረግዝ…… ለአባዬ ውርደቱ ሆንኩ። በየሴሚስተሩ አንደኛ እየወጣች ስሙን የምታስጠራው ልጁ በአንድ ቀን ስህተት አፈር ከድሜ ገባች።
… ወራት ነጎዱ… ትምህርቴን ከ11 ተውኩት። ልጄን ገጠር አክስቴጋ ሄጄ
ወለድኩ።…… የአባዬ ውርደት የነበረው ሌባው ወንድሜ የቤቱ ኩራት ተባለ።……
ሰርቆ እቃ ቢያመጣ እንጂ ልጅ ይዞ አልመጣማ……!!! ከሩቅ ያኔ ቀጥሎ……
እኔ ነኝ ያለ በቅሌቱ መንደር ያወቀው ሀብታም እጄን ለትዳር ጠየቀ። ከነ ልጇ
አንቀባርሬ አገባታለሁ አለ። ደስተኛ እሆን እንደሆነ አይደለም የተጠየቅኩት። ሽማግሌዎቹ ከቤት እንደወጡ ምን ያህል እንዳኮራሁት ነበር አባቴ የነገረኝ። …… ጊዜው ግድ አለው?… ወራት ነጎዱ… ድል ባለ ሰርግ ተዳርኩ።… ልጄን እና የበደነ ልቤን ይዤ ብዙ ቅምጥ ያለው ባሌ ቤት ገባሁ። ገነቴ እኔ ጭኖች መሃል ተለጠፈች እንጂ በእድሜ ቁጥሬ እንደገባኝ የአባዬ መደረቢያ ናት። በሱ ሚዛን የማይሆን ሰው አክሱም ሲጎበኛት " ያለእናት አሳድጌሽ አዋረድሽኝ። የሰፈር መሳለቂያ አደረግሽኝ። ማቅ አለበሽኝ።" እያለ ነጠላ ወጉን የሚለቅባት ፤ በሱ ልኬት ክብሩን የሚመጥን ሰው አክሱም
ሲጎበኛት "አኮራሽኝ ልጄ… ወግ ማዕረግ ክብር አሳየሽኝ።" እያለ ድርብ ወጉን
የሚጠርቅባት…… ክብርም ሆነ ማቅ የትኛው የሰውነት አካል ላይ እንደሚንሳፈፍ ባይገባኝም። የእኔ ገነት ግን የአባዬ አንገት ላይ ጣል እንደሚደረግ መደረቢያ ትመስለኛለች። አንዴ ማቅ ሆና የምታንቀጠቅጠው … ሌላ ጊዜ ክብር ሆና የምታሞቀው…… ቅርብ ያኔ ለታ… ሀብታሙ ባሌ በወንጀል ታስሮ የምኖርበትን ቤት ጨምሮ ንብረቱ በሙሉ ተወርሶ ወደ ቤት ስመለስ። አሁንም አባቴን የሰፈር መጠቋቆሚያ አደረግኩት። ትንሽ ከአሁን ቀድሞ……
ልጄን ጥዬ አረብ አገር ሄጄ ብር መላክ ስጀምር። ድሮምኮ ልጄ መኩሪያዬ ናት
አለኝ አባቴ………… ጊዜው አብሮ ምን እንደሚያንገዋልል መች ቅም ይለዋል?… አመት ነጎደ…… የምሰራበት ቤት ሴትዮ በቃሽኝ ባሌ ዓይኑ አርፎብሻል ብላ
አባረረችኝ።…… ስራ ማግኘት አልቀለለኝም። ውበቴን ያየ ደላላ በሙሉ አረብ ባጫውት ብዙ ብር እንደምሸቅል መከረኝ። አባቴን የምጠላው ጊዜ ይበልጣል።…… ግን መገላገል በማልችለው ዓይነት ልክፍት የሱ ኩራት መሆን እፈልጋለሁ። አሁን ደግሞ ከእርሱ በተጨማሪ የልጄ ኩራት ለመሆን ነፍሴን እሰጣለሁ። አሁን እለት……
አንደኛ ደረጃ ሸርሙጣ ሆንኩ።…ለአባዬና ለልጄ ክብሬን መሰረት ድንጋይ ጥዬ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገነባሁ።…… አባቴ ክብር ደረበ።…… ከአንገቱ ቀና ብሎ
በኩራት ሰፈር ውስጥ ተንቀዋለለ።… "ልጄ ካሰችኝ! ፐ ከወለዱ አይቀር አንድ
የእኔን ልጅ ዓይነት ነው እንጂ… " እያለ የወግ አልበሙን ለቀቀ።……ክብሬን ደጋግሜ መሬት አንጥፌ ለልጄ በቋሚነት ወጪ የሚሸፍንለት ሚኒባስ ገዛሁ።………
በቃኝ አልኩ። ለአባቴ ክብር ልደርብ እኔ ደጋግሜ ተዋረድኩ። የእርሱ ኩራት ለመሆን ደጋግሜ ተናቅኩ።…… በቃኝ አልኩ። ያለኝን ይዤ ሀገሬ እገባለሁ። በቀረኝ ዘመን ራሴን ላክብር…… ደወልኩ።
"አባዬ ልመጣ ነው። ጠቅልዬ ልመጣነው።… ለልጄ እናት ልሁነው።… ባለኝገንዘብ የሆነውን ሰርቼ እንኖራለን።"
"እንድች ብለሽ እግርሽን ወዲህ እንዳታነሺ…… ተዋርደሽ አዋረድሽኝ!! እዛ ምን እንደምትሰሪ ጉድሽን የአይናለም ልጅ መጥታ ነገረችኝ።…ቤት አለኝ ብለሽ
እንድች እንዳትሞክሪያት ነው የምልሽ…… "
……... ጨርሰናል!!………

@wegoch
@wegoch
@paappii
መማር ያሳፍራል ፣ ሀገር ያኮላሻል !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ጋሽ አድማሱ ሁሌ የሚናገሯት ነገር ነበረቻቸው ። "ሰውን ደደብ አትበሉ ... ሰው ደደብ እና ደንቆሮ ብሎ መሳደብ ነውር ነው።" ይላሉ :)
ሰው ደደብ ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ጌቱን ከሆነ ብቻ ነው ብለው ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፉተታ ያክሉባታል :)
በርግጥ ጋሽ አድማሱ ልክ ናቸው ። ሰው ደደብ ተብሎ አይጠራም እንጂ ጌቱ ግን አንድ ክፍል ተማሪ ሙሉ ከመቀመጫው ተነስቶ ያጨበጨበለት ደደብ ነበረ ።
ያኔ ተማሪዎች ሳለን " አበበ በሶ በላ " ተብሎ መነበብ የነበረበትን ዓ.ነገር "አበበ በሶ በዳ" ብሎ በማንበቡ የተነሳ አማርኛ መምህራችን እንዳይሞትም እንዳይድንም አድርገው የደበደቡት ነገር መቼም አይረሳኝም ።
ጌቱ ከዛ ግርፊያ በኋላ ጭራሽ ይባስ ብሎ ድንጉጥና የለየለት ነፈዝ ሆነ ። ወላጅ በየዓመቱ አነሰ ቢባል አስራ አራት ጊዜ ያመጣ ነበር ። በስተ መጨረሻም አባቱ መመላለስ ቢታክታቸው አዲስ ለትምህርት ቤቱ ብዙም የማይርቅ ቤት ተከራይተው እንደነበር ታሪክ ያስታውሰናል (ምን ታሽሟጥጣለህ? ፅሁፌን ለማጣፈጥ የፈጠርኳት ግነት መስሎህ ከሆነ ተፎግረሀል ዝናዬ :) )
እናም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ትምህርት ለሱ እንዳልተፈጠረ መልዐክ ሹክ ያለው ጌቱ ትንሿ ከተማችንን ለቆ በረሀ ለስራ መግባቱን ሰማን። ብዙዎቻችን የክፍሉ ተማሪዎች ገና በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ከገዛው ፓስቲ ላይ አንድ አንድ ጉርሻ የሚለቅብን ጌቱ ከመጥፋቱ በላይ የፓስቲው ትውስታ ብቻ እያናወዘን የመጀመርያ ድግሪ ትምህርታችንን ቋጨን ።
ጋሽ አድማሱ ከዚህ ሁነኛ ክስተት በኋላ ታድያ ዘወትር ከግቢያቸው ፊትለፊት ካለችው ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የጠዋት ጠሀያቸውን እየኮመኮሙ ያገኙትን ፈልፈላ ሁሉ ትምህርት ካልወደዳችሁ እንደዛ የመዝገቡ ልጅ( ጌቱን ማለታቸው ነው 😊!) ...በረሀ ትገቡና አንድ ደም ያቅበዘበዛት ወባ ነድፋ በሽተኛ ሆናችሁ ትቀራላችሁ እያሉ ይመክሩ እንደነበር ትዝ ይለኛል ።
እነሆ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የዓለም ሁኔታ እንደ ቂጣ ተገልብጦ ቁጭ አለ ።
እኛ ብዙዎቻችን ተምረን የመንግስት የወር ጡረተኛ ባርያዎች ስንሆን ጌቱ ግን የራሱን ግዙፍ የንግድ ማዕከል ከፍቶ የናጠጠ ቱጃር መሆኑን ሰማን ።
ለመካሪ ዘካሪያችን ጋሽ አድማሱ የአረቄ ብር ለመስጠት ሶስት ጊዜ ከራሳችን ጋር ረዥም ስብሰባዎችን የምንወስደው ከጌቱ ይልቅ እኛ ኢንጅነርና ዶክተሮቹ ነበርን ።
ከረዥም የመጥፋት ዓመታት በኋላ የተመለሰው ጌቱ ሀገር ቤት በገባን ቁጥር የመንገድ ሊፍት እየሰጠና በየመሸታ ቤቱ ውስኪ በማውረድ ሞራላችን ላይ ዳርት መጫወቱን ቀጠለ ።
ጋሽ አድማሱም አነሰ ቢባል በቀን በትንሹ የሁለት መቶ ብር ድጎማ ከጌቱ ይደረግላቸው ጀመር ።
በዚህ በመስቀል ወቅት ታድያ ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ሀገር ቤት የሄድኩት እኔ ከኋላዬ "አንተ ደደብ ! እዚህ ድረስ መተህ እንኳ እኔን ለመጠየቅ ኮራህ አይደል ?" የሚል ሰቅጣጭ ድምፅ ሰምቼ አንገቴን አሽከርክሬ ዞር ብል ጋሽ አድማሱ ጥርሳቸውን በረዥም ችፍርግ እየፋቁ ሲላላጡብኝ አየኋቸው ።
"ምን እንደ አህያ ወ*ላ ይገትርሀል? ነፈዝ ! ... ድድብናህ አሁንስ ቅጥ አጣ ! ምናለ ከዛ ጎበዝ ጌቱ ሰው መጠየቅን ብትማሩ? "
በድጋሚ የምሰማውን ድምፅ ማመን አልቻልኩም ።
ዘግቻቸው መንገዴን ቀጠልኩ ።
ለመጀመርያ ጊዜ በመማሬ የተፀፀትኩባት ቀን ዛሬ ሆነች :)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
~~ ነዋሪ እና አስነዋሪ ~~

"ዛሬ ጋባዥ እኔ ነኝ! " እላለሁ ሁሌም። እንደተገረፈ ሰው ምን ያስለፈልፈኛል?
"ወየው ሂዊዬ አንቺ ማለትኮ…… " ይሉኛል።…… በቃ ይኸው ነው!!…… ያለኝን እታጠባለሁ። ያቆለጳዽሱኛል። ዘወር ስል ስጋዬን ዘልዝለው እንደሚያሰጡት አውቃለሁ። አንዷ ከመሃከላችን ሳትኖር አብሬያቸው እንደማደርገው። ከአንዱ የቦሌ ውድ ካፌ ወደ ሌላው እየተገላበጥን ራሳችንን መዘረር፤ በማያስቀው ሁሉ ጥርስ ማስቸገር ፤ ባስ ያለ ቀን መቃም ፤ መረር ያለ ቀን ቁርስ ተገባብዞ እየተላዘዙ መለያየት ፤ ልብ የተገዛ ቀን ደግሞ ከአንዱ ሞል ወደአንዱ
እየተንዛለሉ መሸመት…… ስለያቸው ፀጉሬን እየነጨሁ እበሳጫለሁ። ሁለተኛ እላለሁ። ምን ቀን ነው የገጠምኩት…… አማርራለሁ።…… እቤት የዋልኩ ቀን… በእነሱ ሂሳብ ወይ ጠብሾኛል አልያም ዥልጥ እየሆንኩ ነው። ያቺ የፊቷን አመድ በዘመናዊ አመድ የምታብሰው ሀና "ሂዊ እኮ ድሮም ከኛ ጋር ውላ እንጂ ታጥቦ የተቀሸረ እርጥብ ናት… ሃሃሃሃሃ ብር ብቻ!… እስኪ ቤተሰብ እንቀያየር? " ትላለች…… ይኸው ዥልጥ አለመሆኔን ለማስመስከር እዠለጣለሁ። ብሄራዊ ውጪ ላይ ተቀምጬ ያዘዝኩትን ጥብስ ፍርፍር እየበላሁ። " ዛሬ የመጨረሻዬ ነው! ቢቀርስ? ጓደኛ ባይኖረኝስ? እኚህ ምን ጓደኛ ናቸው? እነሱን ለመተው
በሚያስችል መጠንማ ራሴን አከብረዋለሁ።" ሰሃኑ ላይ ግማሽ የጥብስ ፍርፍር እንደቀረ ጠገብኩ። እጄን በሶፍት እየጠረግኩ ሳለ "ልብላው? " የሚል ድምፅ አዞረኝ! ከእድሜያቸው በላይ ችግር ያስረጃቸው ሽማግሌ ናቸው። ያስተረፍኩትን እህል ነው ልብላው ያሉኝ።…እዛ አካባቢ መኪናዬን ሳቆም እየመጡ እንደሚለምኑኝ አዛውንት ናቸው ብዬ አስቤ ብር ልሰጣቸው ቦርሳዬ ውስጥ ገባሁ።"አይ ብር አይደለም የምፈልገው። እህሉን ልብላው ከበቃሽ?" አሉኝ ደግመው። ኩራታቸውን ርሃብ እንደነጠቃቸው በሚያሳብቅ አኳኋን…… ተነሳሁ።……ተቀመጥኩ።… የሆነ ነገር ሆንኩ። "ይቀመጡ አባባ ይቀመጡ አልኳቸው።" "እባክሽ ልጄ ምን ሆነህ ነው? ዓይነት ጥያቄ ከምትጠይቂኝ እህሉ ይቅርብኝ።" አሉኝ። "አልጠይቆትም!! ከእኔ የተረፈውንም አይበሉም። ይኸው አስተናጋጁ የሚፈልጉትን አዘው ይብሉ!" ዓይናቸው ሸሸኝ።…… አዘው መብላት ጀመሩ። ሀና ደወለች። "እ? ዛሬ ምሳ የት ይበላለት? " "ሲኦል ብሉ ስትፈልጉ…… am out! " ኡፈይይይይይይ ስልኩን ስዘጋው ተነፈስኩ። ቦርሳዬ የነበረኝን ብር በሙሉ አውጥቼ ሰጠኋቸው። አላመኑኝም። "እየቀለድሽብኝ ነው ልጄ? ምን አልኩሽ? " "አይደለም አባ…… ምንም አልጠይቆትም! ሊነግሩኝ የሚፈልጉ ቀን ግን በዝህች ስልክ ይደውሉልኝ።" በሶፍት ላይ ፅፌ አቀበልኳቸው። እጄን ተቀብለው አገላብጠው ሲስሙኝ ትኩስ እንባቸው እጄ ላይ ተንጠባጠበ።
…… ጨርሰናል………


@wegoch
@wegoch
@wegoch
የፈጣሪ የመገኛ ስፍራ በእያንዳንዱ የሰው ልብ ውስጥ ነውና


የሰዎችን ቀልብ መስበር የፈጣሪን ክብር እንደ ማጉደል ነው።

ሱፊዎች

ውብ ጁመዐ 💚

@wegoch
@wegoch
ነብስ ይማር

@getem
‹‹ሲስተርሊ- ብራዘርሊ››
(ከሕይወት እምሻው)
-----------------------
ከዶ/ር መረራ ኢንትሮዳክሽን ቱ አፍሪካን ፖሊቲካል ሲስተምስ ክላስ ስንወጣ ‹‹
ዛሬ ተሳክቶልኝ ኤፊን ላስተዋውቅሽ ነው›› አለኝ ክብሮም፡፡ ክብሮም፣ በእሱ ቤት ‹‹ንፁህ›› ጓደኛዬ ነው፡፡
(በነገራችን ላይ…ንፁህ ጓደኛ ሲባል ያስቀኛል፡፡ ወንድና ሴት ‹‹እሱ እኮ ንፁህ
ጓደኛዬ ነው…እሷ እኮ ንፁህ ጓደኛዬ ናት›› የሚባባሉት ወንድና ሴት ሆነው
ለፍቅርና ለድሪያ ስላልተፈላለጉ፣ ለስጋ ፍላጎታቸው እጅ ስላልሰጡ፣ ለ‹እንስሳዊ›
ስሜታቸው ባሪያ ስላልሆኑ ልዬ ፍጡር እንደሆኑ እንዲታወቅላቸው
ስለሚውተረተሩ ይመስለኛል፡፡ የጉብዝና አክሊል ድፉልን ለማለት ሲያሽቋልጡ
ይመስለኛል፡፡ አለ አይደል….‹‹ እዩንማ…እሷ ባለሽንቁር፣ እኔ ባለቃጭል
ብንሆንም መደራረግ አንፈልግም…በሌላ ነገር አንፈላለግም….ግንኙነታችን
ንጹህና ቅዱስ ነው….ልዩ ፍጡሮች አይደለንም? እንደነ ቀነነኒሳ ወርቅ ሜዳሊያ አይገባንም አይነት ነገር…)
እና ክብሮም በእሱ ቤት ንፁህ ጓደኛው ነኝ፡፡ ሰፊ ዳሌ፣ ትላልቅ ጡቶች
ቢኖሩኝም፣ የወር አበባ ባይም ከወንድ ጓደኞቹ ለይቶ የማያየኝ ጓደኛው፡፡
በእኔ የቀቢፀ ተስፋ ምስኪን ቤት ግን የወደፊት ባልና ሚስት ነን፡፡ በእኔ ቤት ግን
ኬቢ የምመካበት ባሌ፣ የምሳሳላቸው ልጆቼ አባት ነው፡፡ በህቡእ እወደዋለሁ፡፡
ኪቢዬ ኦክስጂኔ! ሳልነግረው አፈቅረዋለሁ፡፡ ‹‹በመጨረሻ ከኤፍሬም ጋር ልታስተዋውቀኝ ነው…?›› አልኩና መለስኩለት ፡፡ ‹‹እህ! ድሬ ሁለት አመት ውጣው ነው እንጂ ድሮ ነበር ማስተዋውቃችሁ፡፡ ትወጂዋለሽ….›› አለኝ ዘወትር በክፍሎች መሃከል ወደምንቀመጥባት ለእኛ
የተሰራች የምትመስለኝ የድንጋይ ወንበር ላይ ቀድሞኝ ሄዶ እየተቀመጠ፡፡
‹‹ትወጅዋለሽ›› አባባሉ ሌላውን ነገር ካለበት ሁኔታ ይለይ ነበር…የሆነ አፅንኦት… የሆነ ትኩረት ነበረው፡፡
ቁጭ ካልን በኋላ ትናንሽ አይኖቹን በትላልቅ አይኖቼ እያየሁ ‹‹ በአካል አንገናኝ እንጂ በዚህ ሁሉ አመት ወሬ ማውቀው ማውቀው ነው ሚመስለኝ….ለነገሩ ያንተ
ቤስት ፍሬንድ ከሆነ ምክንያት አለው….ላልውደው አልችልም›› አልኩት፡፡ ‹‹አሃሃ….ለነገሩ ልክ ነሽ…ኤፊ ከግምት በላይ አሪፍ ልጅ ነው…ትወጅዋለሽ…..›› ሶስት አረፍተነገር ሳንመላለስ ሁለት ጊዜ ‹‹ትወጅዋለሽ›› ፣ ያውም በ‹‹ እርግጠኛ ነኝ…አብራችሁ ትሆናላችሁ›› ስልት ማለቱ በእሱ ቤት ንፁህ ጓደኛ የመሆናችን አንዱ ማረጋገጫ ነው፡፡ አዲስ መረጃ ባይሆንም ልቤ እንደጎማ
ተነፈሰች፡፡ ግን ወሬ አላቆምኩም፡፡
‹‹ምነው ትወጅዋለሽ ትወጅዋለሽ አበዛህ? ልታጣብሰን አስበሃል እንዴ?›› አልኩና ፊቱን ለስሜት ለውጥ በሚመረምር አኳሃን አበክሬ ፈተሽኩ፡፡ ሲደነግጥ ወይ ሲያፍር፣ ወይ የደበቀው ነገር ሲታወቅበት እንደሚሆነው ቀይ ፊቱ አልደፈረሰም፡፡ ሲከፋ ወይ ቅር ሲሰኝ እንደሚሆነው አይኖቹ ይበልጥ አልጠበቡም፡፡ ያልተለወጠ ፊቱን እያየሁ መልሱን ሰማሁ፡፡ ‹‹እና ታዲያስ…ኤፊን አግኝተሽ ነው?›› አለኝ፡፡ ምንም ተስፋ የለኝም፡፡
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
የዚያኑ እለት ከሰአት ፤ በወሬ ከገነባሁት በአካል ከማላውቀው ኤፍሬም ጋር
ተዋወቅን፡:፡ ገና ለገና ኬቢን ስለምወደው…. ኤፍሬምን የመሰለ ልጅ በደብዛዛው ገልጬ፣ አገኘሁት ብዬ ማለፍ ፍትህ ማጓደል ነውና ዘርዝሬ ልንገራችሁ፡፡ ኤፍሬም ፣ ‹‹እስቲ አለሁ የሚል ወንድ ያንበርክከኝ›› ብላ በትእቢት ተወጥራ የመጣችን ሴት ባንዴ የሚያርበደብድ መልካና ቁመና አለው፡፡ እመኑኝ፤ የማያምር ነገር የለውም፡፡ አባቴ ይሙት፣ ጆሮዎቹ ሳይቀሩ ያምራሉ፡፡ የእግሮቹ ጣቶች እንኳን ያምራሉ ( ድሬ ለምዶበት ነው መሰለኝ በአዲስ አበባ
ብርድ ቄንጠኛ ነጠላ ጫማ አደርጎ ነው የመጣው) ፤ ቁርጭምጭሚቱ እንኳን
ያምራል (ከቁምጣ ረዘም፣ ከመደበኛ ሱሪ አጠር ያለ ‹‹ሚዲ›› ቱታ ነው የለበሰው)፡፡ ሰውነቱ ለሚበላው የሚጨነቅ፣ መንቀሳቀስ የሚወድ መሆኑን ይነግረኛል፡፡ ግን ደግሞ ሌት ተቀን ብረት እያነሳ በአንድ ደረት ላይ ሰላሳ ሶስት ቦታ ፈርጣማ ጡት አውጥቶ የመጠጥ ቤት ቦዲ ጋርድ ከሚመስል ሰው ጋር (በጣም የምጠላው ሰውነት…አቦ ቦርጭ ሁላ ይሻለኛል) የማይመሳሰል አይነት ነው፡፡ አለባበሱ ዘመነኛ፣ ወንዳወንድነቱ ግን የድሮ ነው፡፡ አለ አይደል…ስኪኒ ሱሪ አድርጎ መጥቶ ልክ ግሩም ኤርምያስ የአምባሳደርን ሱት ለብሶ ሲመጣ እንደሚሰራው ነው የሚሰራው…ሴት የሚያቅበጠብጥ ወንዳወንድነቱ ስኪኒ ከሚለብሱ ወንዶች የማይገኝ ህልም ነው፡፡ በዚያ ላይ ንፅህናው ያስገርመኛል….ሁሌም ልክ ከሻወር ሲወጣ ያገኛችሁት የሚመስል ንፅህና አለው…አባቴ ይሙት በልጅነቱ ንፍጥ ምናምን ተጠርጎለት ያደገ ሁሉ አይመስለም…ይህንኑ ልብሱን ለብሶ…ሽር ብትን ብሎ ከእናቱ ማህፀን
‹‹ወክ›› አድርጎ የወጣ እንጂ እንደሌሎቻችን በምጥ ተደናብሮ፣ አምርሮ እያለቀሰ…በምናምን ተሸፍኖ የተወለደ አይመስልም፡፡ ሲያወራ የረጋ፣ ግን ደግሞ ተጫዋችም ነው፡፡ ጋግርታምም አይደል፣ ቀለብላባም አይባል….ብቻ በሁሉ ነገሩ ምትሀታዊ በሆነ መልኩ በሁለት ሊያስጠሉ በሚችሉ ፅንፍ ማንነቶች መሃከል አማካይ ነጥብ ላይ በምቾት ተቀምጦ፣ እንደኔ ያለችውን ሴት ለማሳሳት ተሰርቶ የተዘጋጀ የምርጥ ወንድ ሰርቶ ማሳያ ነገር ሆነብኝ፡፡ እመኑኘ፣ ልጁ ትንሽ ፊት ቢሰጡት መነኩሴን አለማዊ የሚያደርግ፣ ጭምትን የሚያሳብድ ያልተለመደ አይነት መስህብ አለው፡፡ እንዲህ ያለን ወንድ፣ ያውም በገዛ ጓደኛው ‹‹አብራችሁ ሁኑ›› የሳምንታት ግፊት እየተገፉ እንዴት ብሎ መቋቋም ይቻላለል? እንዴትስ ብለው ለእንዲህ አይነቱ ሰው በሴት- ያውም በፍቅር እጦት በተጎሳቆለች የሴት ልብ- ላይረቱልት
ይቻላል? ህእ….ልወደው ነው እንዴ?

@wegoch
@wegoch
@paappii
‹‹ሲስተርሊ-ብራዘርሊ››
(ከሕይወት እምሻው)
ክፍል ሁለት
-----------------
ህእ….ልወደው ነው እንዴ? አዬ..በምን እድሌ? አይደለም፡፡ እስካሁን ያወራሁላችሁ ሁሉ ስለ ኤፍሬም አይኔ
ያየውን፣ አንጎሌ የመዘገበውን እንጂ አብላልቼ፣ ሳላስበው ለልቤ የነገርኩት፣
ልቤም ከእኔ የተቀበለውን የውደጂው ጥሪ ተቀብሎ ንዝንዙን የጀመረበት…ልክ
ኬቢን የወደድኩበት መንገድ የሚመስል አይደለም፡፡ (አያችሁ….አይንና አንጎል
ገለልተኞች ናቸው፡፡ ሊስት ይዘው ሰው የሚመዝኑ…ይሄ አሪፍ ነው ይሄ ይደብራል
የሚሉ……ልብ ግን …ልብ ግን አንዴ ከወደደ ወገንተኛ ነው….ዝርዝር ሳያወጣ… ምክንያት ሳይደረድር በቃ ወደድኩት ብሎ ግግም የሚል…ግድፈት የሚያይ አይን የሌለው…የሚያመዛዝን አንጎል የሌለው ደደብ ነገር ነው ልብ፡፡ …) አዎ ልጁ ድንቅ ነው፡፡ መልከ-መልካም ነው (በሰፊው እንዳየሁት…በሰፊው እንዳወራሁት) ጨዋ ነው (ለሳምንታት እንደቃረምኩት) ደስ ብዬዋለሁ ( በአስተማማኝ መረጃዎች ላይ ተመሰርቼ እንደገመትኩት) ግን ምን ያደርጋል…. ሺህ ጊዜ ቢያምር፣ የት አባቱን ያህል ቢያማልል፣ ለአመታት
ቢያነሆልል አንድ ነገር ግን ይጎድለዋል፡፡ ኬቢ አይደለም፡፡
--------------------
ይሄ በሆነ በወር ከምናምኑ በኬቢ ‹‹ሞክሪው›› ግፊት ተነድቼ፣ በኤፍሬም አሪፍነት እና ‹‹ወደድኩሽ›› ጉትጎታ ይሉኝታ ተይዤ፣ ኬቢን በልቤ ዙፋን አደላድዬ እንዳስቀመጥኩ፤ ከኤፍሬም ጋር ፍቅር የሚመስል ነገር ጀመርን፡፡
እዚህና እዚያ ቡና እና ማኪያቶ፡፡ ክትፎና ሽሮ….እዚህ እና እዚያ ሶቶ ተያይዞ
መሄድ….እንደ ፍቅረኛ ፊልም ገብቶ ፊልምና ፖፕ ኮርኑን ትቶ ከንፈርን መቃመስ፡፡ የከረረ ግንኙነት አልነበረም፡፡ ፍቅር አልሞካከረኝም፡፡ ከመሳሳም ያለፈ ነገር አላደረግንም፣ ያቺ አመፀኛ ልቤ መች ፈቅዳ፡፡ ከኤፍሬም ጋር ውለን ስንለያይ ቤት ስገባ አይናፍቀኝም፡፡ አጠገቤ ከሌለ ትዝ አይለኝም፡፡ ሳገኘው ግን አይከፋኝም፡፡ ለጥቂት ሳምንታት ይሄ ስሜት ምን እንደሆነ ውሉ ጠፋኝና ቤቴ ስገባ መስታወት ፊት ቆሜ ራሴን ‹‹ምናባሽ እያደረግሽ ነው?›› ብዬ መጠየቅ ጀመርኩ፡፡ እስከዛሬም ደፍሬ መጠየቅ አልፈለግኩም እንጂ መልሱ ሩቅ አልነበረም፡፡ ኬቢ ለኤፍሬም አንፀባራቂ ትሪ ላይ አድርጎ፣ አሳልፎ ከሰጠኝ በኋላ፣ በእሱ ፈንታ ከኤፍሬም ጋር ስውል…ጊዜዬን በሙሉ ስቀማው እስከዛሬ በዝቼ በመገኘቴ ምክንያት ታይቶት የማያውቀው ታላቅ ክፍተት ይፈጠራል ብዬ በማሰብ ነው፡፡ ከእጁ ስወጣ ከመዳብነት ወደ ወርቅነት እቀየራለሁ ብዬ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እስከዛሬ አስተውሎት በማያውቅ ሁኔታ ይወደኝ እንደነበር…ይፈልገኝ እንደነበር የሚረዳበትን መልካም የቅናት አጋጣሚ እፈጥራለሁ ብዬ ነው፡፡ አላሳዝንም? አላሳዝንም፤ ምክንያቱም ከሳምንታት ቸልተኝነት እና ‹‹እንዴት ነው ተመቻቻሁ አይደል?›› የሚሉ ልብ ማቁሰሎች በኋላ ፤ እሰቲ ዞር ስል ዋጋዬ ከታየው ብዬ….ከቀኖቼ የሚበዙትን ለኤፍሬም ፍጆታ ማዋል ስጀምር፣ ከኤፍሬም ጋር ብቻ ወጣ ገባ ማለት ስጀምር፤ ኬቢ በጣም መደወል ጀመረ፡፡ ‹‹ ጠፋሽ…ላወራሽ ምፈልገው ጉዳይ አለ›› ብሎ እንደመለማመጥ ሁሉ ሰራው፡፡ በርትቼ ትንሽ ባንገላታው እወድ ነበር…ግን ያቺ ገለልተኝነት የማታውቅ…ላፈቀረችው ሰው የቀናት ጭካኔን የማትፈቅድ ስቱፒድ ልቤ እምቢ አለችኝ፡፡ ‹‹ሲሪየስ ትመስላለህ…ሰላም አይደለህም እንዴ ኪቢዬ?›› አልኩት አንዱን ቀን ካልተገናኘን ብሎ ሲወጥረኝ፡፡
‹‹እኔ ደህና ነኝ…ዛሬ እንገናኝ….›› አለ ጥድፍ ብሎ፡፡
‹‹ዛሬ?››
‹‹አዎ…ምነው….›
‹‹አይ ኤፊ ጋር ነኝ….››
‹‹ማለት ከእሱ በፊት ወይ በኋላ አግኚኛ!›› (ልጁ ብሶበታል….አርባራቱ ታቦቶች ፀሎቴን ሰምተው በእጄ ሊያስገቡት ይሆን…?) ‹‹አይ…ኬቢዬ ከስራ እንደወጣሁ አርሊ ሄጄ እዛው ላድር ነበር…›› የኤፍሬም ‹‹ ከከንፈር እንውረድ›› ጉትጎታ ቢበረታም፣ ‹‹እሺ በቃ ዝም ብለሽ ነይና እደሪ…አይ ስዌር አልነካሽም›› ልምምጥ የዘወትር ስንቄ ቢሆንም፤ ለኤፍሬም ከንፈሬን እንጂ ሌላ ነገር አልሰጠሁትም፡፡ አድሬ አላውቅም፡፡ የማደር አጭር እቅድም የለኝም፡፡ ኬቢን ለምን ‹‹ላድር ነው››› እንዳልኩት ጥንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ያበጠው እንዲፈነዳ ነው፡፡ ኬቢ በሆዱ ያለውን ፍቅር (እሱ ባያውቀውም) ቶሎ እንዲወልደው ‹‹ከኤፍሪም ጋር እየተኛሁ ነው›› የሚል የምጥ መርፌ መውጋቴ ነው፡፡ ‹‹ላድር?›› ከልክ በላይ ጮኸ፡፡ (ሰምሯል ሃሳቤ ሰምሯል….ሆኗል ምኞቴ ሆኗል…..) ‹‹ምን ያስጮህሃል…?›› ‹‹ማደር ጀምራችኋል እንዴ….?›› (ለምንድነው እንደዚህ የሚጮኸው? ቀና…….? ተቃጠለ? እርር ድብን ብሎ አስረክቤ መጣሁ አስረክቤ ወርቅ አምባሬን ከእጄን እያለቀሰ መዝፈን ጀመረ….?) ‹‹ቦይፍሬንዴ መስሎኝ….›› አልኩ ትንሽ ወጠር ብዬ፡፡ ‹‹ቢሆንስ…ቢሆንስ…ገና በወር ከምናምን…ገና ምንም ሳታውቂው….›› ‹‹ምንም ሳታውቂው? አንተ አይደለህ እንዴ ላንቺ ከእሱ በላይ ሰው የለም ብለህ ስትገፋኝ የነበርከው….?ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?›› (አሁን እኔም መጮህ ጀመርኩ፡፡ የከረመች ‹‹እንዴት ለጓደኛው አሳልፎ ይሰጠኛል›› ብስጭቴ እድል
አግኝታ ወጣች፡፡) ቀጥሎ ምን እንደሚል ለመገመት ስሞክር፣ ‹‹ይሄ በስልክ አይሆንም…ያለሽበት መጥቼ መነጋገር አለብን….ቀልዴን አይደለም…የት ነሽ?›› አለኝ፡፡ የት ነሽ ነው ያለኝ? (ፈንጠዚያ አለም ላይ ነኝ የኔ ኦክስጅን፡፡፡፡ ከደመና በላይ እየተንሳፈፍኩ በምንም በማንም የማልረበሽበት ውብ የፈንጠዚያ አለም ላይ ነኝ ኬብዬ ማለት አማረኝ፡፡)
በአካል አግኝቼው ሁሉ ነገር ሲፍረጠረጥ…እወድሻለሁ ሲለኝ…ለአመታት የጎመጀሁትን ከንፈሩን ሲሰጠኝ ፣ ለአመታት ያለምኩትን ፍቅር ሲያሳየኝ ታየኝና ሳላቅማማ ተስማምቼ አንዱ ካፌ ተገናኘን፡፡ ተረጋግቶ፣ በአመለጠችኝ….ከሌለ ተኛች ፀፀተ አለንጋ ተገርፎ፣ ….አንገቱን ደፍቶ
እና ያፈቀረ ወንድን የልብ ስብራት ይዞ ይጠብቀኛል ብዬ ነበር፡፡ ግን ቱግ እንዳለ
ነበር፡፡ ቀይ ፊቱ ደፍርሷል፡፡ አይኖቹ ይባስ ጠበዋል፡፡ የአሸናፊነት ስሜት ውስጥ እየዋኘሁ፣ እንደዋዛ ጉንጩን ሳም አደረግኩትና ተቀመጥኩ፡፡ (ከደቂቃዎች በኋላ እንደ ፍቅረኛ ከንፈሮቹን እንደምስም እያሰብኩ…ያውም ለመጀመሪያ ጊዜ…) መግቢያም ያልነበረው ወሬያቸን ከስልክ ጥሪው ቀጥታ ቀጠለ፡፡ ‹‹ለምንድነው አብራችሁ የምታድሩት?›› ብሎ ጀመረ፡፡ ሳቅኩ፡፡ በልቤ እያዘንኩለት..ግን ደግሞ….በዚያች የእሱ ባሪያ በሆነች ልቤ እየራራሁለት ሳቅኩ፡፡
(ተነካ እንዴ ይሄ ልጅ?) ‹‹እንዴ ምን ማለትህ ነው?››› ‹‹ምን ታደርጋላችሁ አብራችሁ ስታድሩ…..?›› ‹‹ኬቢዬ..ትላንት ነው እንዴ የተወለድከው?›› ብየ እንደገና ሳቅኩ፡፡‹‹ምእራፍ አትቀልጂ…ጥያቄዬን መልሺልኝ…›› ‹‹ያው አልጋው ላይ ካርታ እንጫወታለና…ሌላ ምን እናደርጋለን?!›› በማሾፍ መለስኩለት፡፡ ፊቱን እጆቹ ውስጥ ቀበረና ቀና ብሎ አየኝ፡፡ ተለዋጭ እና የተሻለ መልስ የሚጠብቅ ይመስላል፡፡ የጀመርኩትን መጨረስ አለብኝ፡፡ ያደፈረስኩትን ማጥራት አለብኝ፡፡ መቅናቱን እንዲናዘዝ፣ ማፍቀሩን ይፋ እንዲያወጣ መገፍተር አለብኝ፡፡ ‹ምን ይመስልሃል…?ዊ ፋክ….በቃ….!›› አልኩት፡፡ እንዲህ ስድ መሆኔን፣ ኬቢ ላይ እንዲህ መባለግ መቻሌን ማመን አቃተኝ፡፡ ግን ይሄ ግልብ መልስ ከልክ በላይ አንድዶት፣ ይሄንን ድብብቆሽ ቶሎ የሚያፈርስና ‹‹እወድሻለሁ›› የሚያስብለኝ፣ ለአመታት የጠበቅኩትን ልጅ በደቂቃዎች የሚሸልመኝ ስለመሰለኝ እንደዚያ አልኩ፡፡ ልቡ በተሰበረ ሰው አኳሃን አየኝ፡፡ እመኑኝ፤ አግኝቼዋለሁ፡፡

@wegoch
@paappii
ሲስተርሊ ብራዘርሊ
ከሕይወት እምሻው
ክፍል ሶስት
---------------
እንዲህ ስድ መሆኔን፣ ኬቢ ላይ እንዲህ መባለግ መቻሌን ማመን አቃተኝ፡፡ ግን
ይሄ ግልብ መልስ ከልክ በላይ አንድዶት፣ ይሄንን ድብብቆሽ ቶሎ የሚያፈርስና
‹‹እወድሻለሁ›› የሚያስብለኝ፣ ለአመታት የጠበቅኩትን ልጅ በደቂቃዎች
የሚሸልመኝ ስለመሰለኝ እንደዚያ አልኩ፡፡
ልቡ በተሰበረ ሰው አኳሃን አየኝ፡፡
እመኑኝ፤ አግኝቼዋለሁ፡፡ በድንገት ቀና አለና ‹‹ምእራፍዬ፣ በጣም አዝናለሁ…ይሄ ሁሉ የኔ ጥፋት ነው…አንቺ ምንም
አላረግሽም›› አለኝ፡፡
አላልኳችሁም? ኑዛዜው ተጀመረ….!
‹‹ምንድነው ጥፋትህ?›› አልኩት ቀስ ብዬ አይን አይኑን እያየሁ፡፡
‹‹የማፈቅራትን ልጅ በድድብናዬ ለሌላ አሳልፌ መስጠቴ፡፡ ጅልነቴ፡፡ ላንቺ ያለኝን
ፍቅር ለማወቅ ይህን ሁሉ ዘመን መፍጀቴ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን አንቺን እንዲህ ማሰቃየቴ›› ሊለኝ ነው ብዬ ሳስብ…፡ ‹‹እኔ ነኝ ገፋፍቼ እዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የከተትኩሽ….ለማንኛውም…አሁን
እውነቱን ሳውቅ ነው በድፍረት ልንገርሽ ብዬ የመጣሁት›› ያው ነው፡፡ እኔ ቀጥታ የሚለኝን ነገር አሰብኩ እሱ ግን ዙሪያ ጥምጥሙን ጀመረ፡፡ ታግሼ ማስጨረስ አለብኝ፡፡
‹‹ምንድነው እውነቱ?›› አልኩኝ እንደመሽኮርመም እየሰራኝ፡፡
‹‹እሱ ኢት ኢዝ ኖት ኢምፖርታንት!››
‹‹ማለት…›› ‹‹በቃ እሱን እንተወው…ዋናው ነገር አንቺ ከኤፊ ጋር መሆን የለብሽም››
‹‹እኮ ለምን?››
‹‹በቃ አይሆንም አልኩሽ››
‹‹ምንድነው በቃ አይሆንም አልኩሽ ማለት…ድንገት ምን ተፈጠረ?›› በዙሪያ
ጥምጠሙ ትእግስቴ እያለቀ ጠየቅኩ፡፡
በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ የደፈረሰ ፊቱ ይበልጥ እየደፈረሰ ‹‹በቃ….አንቺ ከእሱ ጋር
መሆነን የለብሽም›› አለ፡፡
‹‹ኬብ!›› አልኩት በንዴት ጮክ ብዬ
‹‹እ››
‹‹ቀንተህ ነው አይደል?››
ፊቱ ላይ ከፍተኛ ግራ መጋባት፣ መወናበድ አየሁ፡፡
‹‹ም…..ን?›› አለኝ እጅግ በደነገጠ ሰው ሁኔታ፡፡
‹‹ኢትስ ኦኬ…ንገረኝ…..››
‹‹ምንድነው ምነግርሽ?››
‹‹እውነቱን…››
‹‹ምንድነው እውነት የመሰለሽ?››
‹‹ቀንተህ ነው ወይ…..››
‹‹በማ…በማን ነው ምቀናው?››
‹‹በኤፊ….ከኔ ጋር ስለሆነ ….››
‹‹ምእራፍ አትዘባርቂ!››
‹‹ምን ማለት ነው አትዘባርቂ..?››
‹‹እንደሱ አይደለማ!››
‹‹እንዴት ነው ታዲያ?››
‹‹ምክንያቱ ምን ያደርግልሻል? በቃ እሱ ላንቺ አይሆንም ካልኩ አታምኚኝም?››
‹‹ትላንት ያለሱ ሰው አልተፈጠረም ያልከውን ሰው ዛሬ ከመሬት ተነስተህ ላንቺ አይሆንም ስትለኝ ለምንድነው ማምንህ? ይልቅ ዋናውን አውነት ንገረኝ….›› ‹‹ከመሬት ተነስቼ አይደለም!››
‹‹እና ከምን ተነሳህ….›
‹‹እሱን ዛሬ ላወራሽ አልፈልግም››
ነገሩ ሁሉ ሊማሊሞ ዳገት ሆነብኝ፡፡ ተዳከምኩ፡፡ ተናደድኩም፡፡
‹‹በቃ ልትነገረኝ ካልፈለግህ ተነስና ሂድ!›› አልኩት በመሰላቸት፡፡ ‹‹አልሄድም…ህጻን አትሁኚ…›› ‹‹ማነው ህጻኑ? እኔ? ማትሄድ ከሆነ እውነቱን ንገረኝ›…እኔ የምጠረጥረው፣ የማውቀው ነገር አለ፡፡ ከፈራህ ይሄው ልጀምርልህ….ምእራፍዬ…በል››
‹‹ምን? ምንድነው ምጠረጥሪው?››
‹‹ዝም ብለህ የምልህን በል….››
‹‹ሆሆ…ምን ሆነሻል?››
‹‹ምእራፍዬ በል››
ፊቱ ላይ የንዴት ሳቅ ተስሎ ዝም ብሎ አየኝ፡፡
‹‹በላ››
‹‹ምን?››
‹‹የምልህን ድገም….››
‹‹በናትሽ….››
‹‹አለዛ ሂድ….››
‹‹ወይ ጉድ….ምን አይነት ጨዋታ ነው? እሺ….ምን ልበል?..››
‹‹ምእራፍዬ….››
‹‹ምእራፍዬ…..››
‹‹እኔ ከኤፊ ጋር እንድሆኚ የማልፈልገው….››
ዝም አለ፡፡ ‹‹ኬቢ…ድገምልኝ….እኔ ከኤፊ ጋር እንድትሆኚ የማልፈልገው በል››
እያቅማማ ‹‹እኔ…ከኤፊ ጋር እንድትሆኚ የማልፈልገው›› አለ
የሚቀጥለውን አረፍተ ነገር ከአፌ አውጥቼ ድገመው ከማስባሌ በፊት በረጅሙ ተነፈስኩ፡፡ በጥልቀት አየሁት፡፡ ነገሮች ሊቀየሩ ነው፡፡ ሕይወቴ ሊቀየር ነው፡፡ በአዲስ የፍቅር ፀሃይ ፀዳል ልደምቅ ነው፡፡ አይኔን ጨፍኜ ታላቁን አረፍተነገር ከአፌ አወጣሁ፡፡
‹‹ራሴ ስለማፈቅርሽ ነው….››
አይኖቼ እንደተጨፈኑ ይሄ ሕይወቴን የሚቀይር አረፍተነገር በምወደው ልጅ
አንደበት እስኪወጣ ድረስ ልቤ አታሞ እየመታች፣ መላ ሰውነቴ ውሃም እሳትም
እየሆነ ጠበቅኩ፡፡
ሰከንዶች አልፈዋል፡፡
ፍፁም ፀጥታ፡፡
አይኖቼን ከፈትኩ፡፡
ፍጹም በድንጋጤ እና በሃዘን የደረቀ የኬብ ፊት ጠበቀኝ፡፡ ይሄን ፊቱን
አላውቀውም፡፡ ሁሉ ነገር እንዳበቃለት፣ አይሳሳቱት አይነት ስህተት መሳሳቴ ገባኝ፡፡ ስንት ደቂቃ በሚጎረብጥ ዝምታ እንዳሳለፍን አላውቅም ግን መጀመሪያ
የተናገረው እሱ ነበር፡፡ ‹‹እህህህህም…ምእራፍዬ…ኤፍሬም ካንቺ ጋር ከጀመረ በኋላ…ከአንድ ሁለት
ሴቶች ጋር ሲቃበጥ ስላየሁት ነው….ማለቴ….እኔው ራሴ ገፋፍቼ …አስግድጄ ከእሱ ጋር አድርጌሽ እንዲህ አይነት ነገር ሲሰራሸ ፀፀት ተሰምቶኝ ነው›› አለ፡፡ ሰምቼዋለሁ ግን መልስ የመስጠት ፍላጎትም አቅምም አልነበረኝም፡፡ በኤፍሬም ብልግና ልቤ ተሰብሮ አይደለም፡፡ እንኳን ከአንድ ሁለት ከሃያ ሁለት ሴት ጋር ሲዳራ ቢውልና ቢያድር ግድ የለኝም፡፡ምክንያቱም ልብ የሚሰበረው ልብን በሰጡት ሰው ብቻ ነው፡፡ ብዙ ስብራት የሚመጣው አብዝተው በሚያፈቅሩት ሰው ነው፡፡ እንደ ኤፍሬም አይነቱማ አልፎ ሂያጅ ነው፡፡ እኔ
በኤፍሬም እንደተጠቀምኩበት ቢጠቀምብኝም ምን ይገርማል? እኔ ኬቢን በሚመኝ አፌ በሽንገላ ከሳምኩት እሱ ደግሞ በዚያው አፉ ቢዋሸኝ ፍትህ
ተዛብቷል? አይመስለኝም እምባ ባዘሉ አይኖቼ አየዋለሁ፡፡ ‹‹ምእራፍዬ…አንቺ እኮ ለእኔ….ከእህትም በላይ ነሽ…..የምወዳት እህቴ ላይ
እንዲህ ያለ ነገር ሲያደርግ ዝም ማለት አልቻልኩም…ማለት….››
የምወዳት እህቴ፡፡ እህህህ፡፡
ሳላስበው አቋረጥኩት፡፡ ‹‹በፊት…በፊት ለእኔ እንዲዚህ አይነት ስሜት እንደማይሰማህ አውቅ ነበር…
ከኤፊ ጋር ከሆንን ጊዜ ጀምሮ ግን የቀናህ መስሎኝ ነበር….ማለት…ልክ እንደኔ ….ሳታውቀው የምታፈቅረኝ……››
የዝምታ ተራው የእሱ ሆነ፡፡ በሃዘን ያየኛል፡፡ ቀጠልኩ፡፡ ‹‹ግን እንደዛ አስበኸኝ አታውቅም አይደል…ይሄን ሁሉ አመት አንዲትም ጊዜ?›› አልኩት፡፡ መልሱን ማወቅ የማልፈልገውን ጥያቄ ለምን ጠየቅኩ? ወሽመጤ ተቆርጦ እንዲቆርጥልኝ? ላያዳግም ፍቅሩ እንዲወጣልኝ? አቀረቀረና ፣ ሳግ በሚመስል በታፈነ ድምጹ ‹‹እኔ..እኔ እንደ እህቴ ነው ማይሽ….በዚያ ላይ ደግሞ….››አለኝ፡፡:
በዚያ ላይ ደግሞ ነው ያለው?
‹‹በዚያ ላይ ደግሞ ምን?› አልኩት
‹‹ሳምሪን…ሳምሪን እንደምወዳት የምታውቂ መስሎኝ…..›› እንዳቀረቀረ፡፡
አረ ተው ኬቢ፡፡ የሞተ ሰው ይደበደባል? የደከመን ገድሎ ፉከራው ምንድነው
አለች ያቺ ጂጂ፡፡ ቀን ቢጥለኝ በወደቅኩበት በካልቾ ያጣድፈኝ?
ሳምሪን አውቃታለሁ፡፡ የእኔና ኬቢ የማስተርስ ክላስ ውስጥ ናት፡፡ እንኳን
እንደሚወዳት በስርአቱ አይቷት እንደሚያውቅ እንኳን አላውቅም፡፡ እኔ የማውቀው ቆንጆ ሴት እንደሚወድ ነበር፡፡ እኔ የማውቀው ሸንቃጣ ሴት
እንደምታቅበጠብጠው ነው፡፡ ቁንጅና ስለማይጎድለኝ ምንም ያህል ጊዜ ይፍጅ
አንድ ቀን አይኑ ውስጥ እንደምገባ አስብ ነበር፡፡ልክ እንደሚወደው ሸንቃጣ
ለመሆን ገመድም እራትም እዘል ነበር፡፡ ምስኪን ምእራፍ፡፡ ሳምሪን አሰብኳት፡፡ ያቺ ሁለመናዋ ከስብ የተሰራ የስብ ክምር…የሰው ጮማ፡፡ ከእኔ በምን በልጣ የማፈቅረው ልጅ ልብ ገባች? እንዴት መግቢያ ፈተናውን አልፋ ራሷን በልቡ ከንቲባነት አወጀች? ቀና ብዬ ላየው አልቻልኩም፡፡ የሃፍረቴ መጠን በኪሎ ቢመዘን አራት ግብዲያ የጭነት መርከቦች ችለው አይጭኑትም፡፡ እዚያው ከተቀመጥንበት
ሳያየኝ መ…….ጭ ብዬ ወደ ማርስ መሄድ ተመኘሁ፡፡ በቅርብ ጊዜ ሳይንቲስቶች ሰው በደንበኛው ሊኖርበት ይችላል ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ግን ሚሊዮን ሰው ቢኖርበት ምን ዋጋ አለው፡፡ ኬቢ አይኖርም፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii
👏👏ጠቅላይ ሚንስትሩ ተሸለሙ።👏👏
ዛሬ 30/01/12 ጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፉ። ኢትዮጵያና አፍሪካ አሸነፈች ተባለ። በዚህ ጊዜ ምን እንደ ተሰማቹህ አላውቅም እኔ ግን እኔ በሆንኩ ብዬ አሰብኩ (የብዙዎቻችን እንደምንል አምናለሁ)። ታድያ ቅናት መሆኑን ሳስብ እራሴን ታዘብኩ። የርሱ ደስታ የሁላችንም መሆኑን ለምን አላመንኩም። አንድ ሀሳብ ግን ቅናቴን አጠፋው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ርዕሰ ብሔርነታቸው ለኢትዮጵያ ነው። በቦታው ላይ በመሆናቸው ብቻ ግን ይህን አላመጡትም ብዙ ሆነው ያለፉ አሉና። ቦታውን ሲያገኙ እራሳቸውን ከማገልገል በላይ ለሀገር በማደር እርሳቸውንም ሀገርንም ለማገልገል በመቻላቸው ነው እንጂ።
ሽልማቱ የሀገር ነው፤ ስንል ግን በየቦታቸው፣ በየወንበራቸው፣ የሚገባውን ነገር ለሰሩ ጭምር ነው። ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ 5 ሚልየኑ እራት ሲናገሩ ያልተባበራችሁን አይሳካም ያላችሁም አመለጣችሁ በሚል እንቁልልጭ ብለዋቸዋል። ዛሬ የተሰማኝ ያ ነው። የኔም ሽልማት ነው ብዬ እንዳላስብ፤ በአቅሜ፣ በቦታዬ የሰራሁት ስለሌለ ሸመመኝ። የሰራችሁ ግን ከጠቅላይ ሚንስትሩ እኩል እንኳን ደስ አላችሁ።
ለባለቤታችሁ ታማኝ ባሎችና ሚስቶች፤ ለሰፈር ሰላም የሆናችሁ አባቶችና እናቶች፤ ለመንጋችሁ የተጨነቃችሁ የሀይማኖት አባቶች፤ ለኔ ይድላኝ ያላላችሁ የፖለቲካ አካላት፤ በየመስሪያ ቤቱ ዐይን የሆናችሁ ሰራተኞች፤ ቤታችሁን የምትንከባከቡ እናቶች ሽልማቱ ይገባችኋል። በተቃራኒው ለቆማችሁ ደግሞ ከስራቹህ ልትመለሱ ልትቀኑ ይገባል። ምንም ያልሰራን ደግሞ መታጠቅ ይኖርብናል።
ሽልማቱ ግን ለሚገባቸውና ለኢትዮጵያ አንዴ ብቻ ተሰጠ።
መልካም ነገ።

@wegoch
2024/09/27 11:23:00
Back to Top
HTML Embed Code: