Telegram Web Link
ለውብ ቀን
💚

1
ስኬትህን በራስህ ሚዛን መዝነው፤ በሰውሚዛን ከመዘንከው ሚዛን አይደፋልህምና
ደስታህን በራስህ መስፈሪያ ስፈረው
በሰው ሚዛን ስትሰፍረው አይሞላልህምና።


ውድቀትህን በራስህ አይን እየው በሰው አይከተመለከትከው ጉድጓዱ ይበልጥ ይርቅሃልና።


የራስህን ህይወት በሌላ ሰው እይታ ከተመለከትከው ፈጽሞ እርካታ አይኖርህም ህይወትሀን
ከሰው ጋር እያነጻጸርክ የምትኖርከሆነ እርካታ የሌለው ኑሮ እየኖርክ ነው።


ምክንያቱም በንጽጽር ህይወት ውስጥ ሁሌም የሚበልጥህ አታጣምና።


2

ሰዎች ምክንያታዊ ያልሆኑና ራስ ወዳድ ናቸው።ለማንኛውም ሰውን ውደድ

ውብ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
ዴል ካርኔጌ ፦ እንደሚለው ራስህን ፈልግና ራስህን ሁን አስታውስ አንተን የሚመስል
በምድር ላይ ማንም የለም።


ራስህን ሁን ራስህንም እወቅ በህይወት ስትኖር ራስህን ካወቅክ አሸናፊ ትሆናለህ።


ሌሎችን ለማስደሰት የራስህን ደስታ ማጣት የለብህም


በሌሎች ሰዎች ዘንድ ብንወደድ መልካም ነው። ሌሎች ሃሳባችንን ቢቀበሉልን
መንገዳችንን ቢደግፉልን ፍላጎታችን ፍላጎታቸው ቢሆን እሰየው።


ነገር ግን የሌሎችን አትኩሮት እና እይታን ስንፈልግ እስከመቼ
መንገዳችንን እንስታለን? ሌሎች እንዲወዱን ስንል
ህሊናችንን እንሸጣለን፤ ሌሎች እንዲያዩን ስንል ያለቦታችን
እንቆማል? ከብዙሃኑ ጋር ለመቀላቀል ስንል ማንነታችንን
እንለውጣለን? ልዩ መሆን ለምን ይሆን የሚያስፈራን?


የራስን መንገድ መርጦ፤ የራስን ማንነት ይዞ፤ የራስን
አስተሳሰብ መሪ አድርጎ መኖር ለምን ይሆን ለብዙዎቻችን
የሚከብደን? እንደሚመስለኝ የብዙዎቻችን ችግር
እንደሌላው ለመኖር ስለምንጥር ነው።


ሌሎች የሄዱበት መንገድ ብቻ ትክክለኛው መንገድ ስለሚመስለን፤ ሜዳው ሁሉ መንገድ
መሆን እየቻል አንዲት ቀጭን መስመር ላይ እየተጋፋን ጊዜያችንን እያባከንን ነው።


ራስህን ፈልግና ራስህን ሁን። አስታውስ አንተን የሚመስል በምድር ላይ ማንም የለም።


ከአሸናፊነት ስነ-ልቦና የተወሰደና አንዳንድ ማስተካከያዎችና ሀሳቦች የተጨመረበት።


ውብ ቀን 💚💚💚

@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን
💚💚💚


አብራሪ ክንፍ



የእውነት መኖር ይፈልጋል...
ግኖ ለምንና ለማን ይላል...
የመኖሩ ዋጋ ይረክስበታል፡፡ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝንበታል፡፡ከፍሬው ገለባው ይመዝንበታል፡፡
ከስኬቱ ውድቀቱ ሚዛን ይደፋበታል፡፡መኖሩ ውስጥ የጠለሸው ነገር ሁሉ ነው
የሚገዝፍበት፡፡
ለዚህ ኑሮ የምርስ ሆነ የእውነት መኖር ምን ሊረባ!?ጣዕሙ ተንጠፍጥፎ አልቆ ምሬቱ ብቻ
ተቆልሎ ለቀረበት፡፡
ሰው ሁሉ ይወደዋል፡፡ለሰው ሁሉ ተወዳጅ አሻንጉሊት ነው፡፡እጅ እግሩ ፥ ወገቡ ፥ ወላ
አንገቱ ሳይቀር እየተነቃቀለ መጫወቻ የሚሆን የሚያስደስት አሻንጉሊት፡፡
ያቺ ጎረቤቱ አረጋሽ አለች አይደል፡፡ያቺ እንኳ ቀይ ሐውልት የምትመስል፡፡መንታ ጋን
የሚያክሉት ጡቶቿ፡፡ያቺ የተኮፈሰ ቂጧን እያመሰች ስትሄድ መንደሬው የሚያያት፡፡
< ያለሐሳብ እየበላች ቂጧ እኮ ጉልላት አከለ > እያለ መንደሬው የሚሸረድዳት.....
አዎ እሷ!!!
በሱ አሻንጉሊትነት ውስጥ የማይታከም ፥ የማይድን በሽታ ተክላለች፡፡እንደታመመም
የማያውቀው በሽታ፡፡
ሕጻኑን አሻንጉሊት ፥ ቤቷ ይዛ ገብታ ፥ በሯን ከውስጥ ቀርቅራ ፥ የለበሰችውን አውልቃ ፥
ቀይ ሐውልት ገላዋን እየደባበሰች ፥ እሱንም ልብሱን አስወልቃ በማይገባው ስሜት
እያበደች ታስጨንቀው ነበረ፡፡ሕጻኑን አሻንጉሊት፡፡ለማንም ትንፍሽ እንዳይል
እያስፈራራችው፡፡
የሕጻን አሻንጉሊት እጁን ነቅላ ጭኗ መሐል እየደበቀች ስትስለመለምና ቁና ቁና ስትተነፍስ
እያየ ይፈራታል፡፡እያያት በጭንቅ ይታመሳል፡፡የሕጻን አሻንጉሊት ጭብጡን የምታክል ሕጻን
ልቡ በፍርሐት ትንፈራፈራለች፡፡
ሁሉ ይወደዋል፡፡መጫወቻው ሊያደርገው ነው የሚወደው፡፡የግል የጨዋታ ንብረቱ
ሊያደርገው፡፡ሙሉውን እሱ መውሰድ ባይችሉ ነቃቅለው ይከፋፈሉታል፡፡አንዳንዴ ካንገት
በላይ ጎረቤት ጋር ፥ እስከወገቡ ቤቱ ፥ ከዛ በታች ደሞ እየዞረ ያድራል...
አንድ እሱ ሶስት ቦታ መሽቶ ይነጋበታል።ሲነጋ ራሱን ከያለበት ጠራርቶ ይገጣጥምና አንድ
ሰው ሆኖ ታጥቦ ታጥኖ ይወጣል፡፡
ለነሱ አሻንጉሊት መሆኑን እያወቀ ለራሱ ሰው ሊሆን ይጥራል...
የሆነውን ሁሉ ተቋቁሞ ሰው ሊሆን ይጥራል፡፡ለገዛ ራሱ ርባና ያለው ማንነት ሊገነባ
ይታትራል፡፡
ያውቃል....
ሁሉ ለጥቅማቸው እንደከበቡት፡፡
የልብ ባልንጀርህ ነኝ ያለው አስታጥቄ መቼም አይጠፋሽም፡፡ያ እየሳቀ ሰው የሚገድል፡፡
የዋሕ መስሎ መሰሪው አስታጥቄ፡፡
በባልንጀርነቱ ተገን ተከልሎ ያለውን ሁሉ ወስዶ የካደው፡፡ንብረቱን በቁሙ ወርሶ
የሸመጠጠው፡፡
ይሄ ሁሉ ሲሆን አይቶ ወደውስጡ ነው ያለቀሰው፡፡እንባውን አፍልቶ ውስጡን ነው በፈላ
እንባው ያነፈረው፡፡ወደውጩ ዘለላ እንባ ጠብ አላደረገም፡፡ሊበቀለውም አልሞከረም፡፡
ጭራሽ አላሰበም፡፡
< ከተወሰደብኝ ያለኝ ይበልጣል > አለ፡፡ባለው ጣረ፡፡ባጣው ሳይቆጭ፡፡
አለኝ ያለው ማንን ይመስልሻል!?
አብራሪ ክንፉን ነው፡፡ወዳሻው ሁሉ የሚያከንፈውን፡፡
አንዳዴ ይገርማል ሕይወት፡፡አንዱን በዳይ ፥ ሌላውን ተበዳይ ያደርጋል፡፡አንዱን አስለቃሽ ፥
ሌላውን አልቃሽ ሊያደርግ ያጣምራል፡፡
በዚህ ሁሉ መጎዳቱ ውስጥ ቢያልፍም እሱ ግን አብራሪ ክንፉን ተማምኖ ነበረ የሚኖረው፡፡
ይሄ ስራው ላንቺ ዳተኝነቱና የሚያሸማቅቅ ስንፍናው ሆኖ ነበር የሚታይሽ፡፡ቢገድሉትም
ትንፍሽ የማይል ጅል ሆኖ ነበረ የታየሽ፡፡
" ለመኖር ግድ ሳይሰጥህ እንዴት አፍቅረኸኝ ልትኖር ትችላለህ!? " ብለሽው ነበረ፡፡
" አፈቅርሻለሁ፡፡ይሄን ብቻ አውቃለሁ፡፡ባንቺ ደስተኛ ነኝ፡፡ይሄንን እወቂ፡፡አብረን የምንኖረው
ረጅምና ብዙ ሕይወት ከፊታችን እየጠበቀን ነው......" አለሽ፡፡
" እንዲህ ሆነህ ማን ካንተ ጋር የሚኖር ጅል አለ " ብለሽ ጥለሽው ሄድሽ፡፡
እሱነቱን ከኮረዳ ጓደኞችሽ ወዳጆች ጋር መዘንሽው፡፡መጀመሪያ ከሁሉ የተለየ የመሰለሽና
ወደሱ የሳበሽ ማንነቱ ፥ ቀርበሽ ስታውቂው የጀዘበ ሆነብሽ፡፡
እራት አይጋብዝም፡፡
ጭፈራ ቤት ጎራ ብሎ አያስደንስሽም፡፡
የከበረም ሆነ የረከሰ ስጦታ አይሰጥም፡፡
ዝም ብሎ መኖርን ማፍቀር የሚል ቂል ሆነብሽ፡፡
ላንቺ የተለየ ትኩረት እንደሌለው ገባሽ፡፡( < በእጁ ስለገባሁ ከመዳብ የተቆጠርኩ ወርቅ
ነኝ > ) ብለሽ አሰብሽ፡፡
የፈለገውን አግኝቶ የተኩራራብሽ ወንድ መሰለሽ፡፡
መጠቃትሽን ተቋቁመሽ እየወደድሽው ሄድሽ፡፡
እንደምታፈቅሪው አውቃለሁ፡፡ከሱ በኋላ የሄድሽባቸውን ወዳጆች ሁሉ እሱን እያስታወስሽ
እንደተጣላሻቸውም አውቃለሁ፡፡የሆነ ነገርሽ ዛሬም ወደሱ ተመለሺ እንደሚልሽ፡፡ሴትነትሽ
እንደሚያስቀርሽም ጭምር አውቃለሁ፡፡
አዎ....
ይሄን ሁሉ ስላንቺም ስለሱም አውቃለሁ፡፡ማወቄን ለከንቱ ምግባር አላዋልኩትም፡፡ማወቄ
ያበራልኝ እውነታ መለያየት አለመቻላችሁን ነው፡፡ለአብሮነት የተፈጠራችሁ መሆናችሁን
ነው፡፡
ተጣልተሽዋል፡፡
ልንገርሽ....
የሆነ መጪና ቀጣይ ፥ ከዚህ በኋላ ያለ ዘላለም ድረስ ይወድሻል...
አያገባውም...
ባንቺ ድርድር የለውም፡፡አንቺ ትደራደሪዋለሽ እንጂ፡፡
ነፍስ የስጋ ጓደኛ ነች፡፡አበሮ ተወላጅ ፥ አዳጊና ሟች....
ሲያለቅስ አልቃሽ ፥ ሲስቅ ሳቂ ነሽ፡፡ከአዚምሽ አይፋታም፡፡ከእስርሽ በፈቃድሽ ተተብተቢ፡፡
ፍቀጂ ይኑር፡፡ፍቀጂ ኖሮ ዓለምን ያኑር፡፡ፍቀጂ ይኑርና ሁሉን ይፍጠር፡፡
ልንገርሽ..
እየበደለሽ ኖሮ የሚክስሽ ፥ ከጀርባሽ እየሳተ የሚወድሽ ፥ እየወደቀብሽ የሚነሳብሽ ነው....
.ግን...ደሞ መናኛ ነው!!!
ስለሆነስ..!?
ሁሉን ረስተሽ ውደጂዋ!!!
ሰማይ ያቀርባል ፥ ምድር ያርቃል፡፡ደብተራ ነው፡፡አዙሮ ጥሎ ፥ አዙሮ ያነሳል፡፡መተተኛ ነው፡፡
አንቺ ጋር ግን ምንም የማይችለው እሱ ብቻ ነው፡፡
ይቆምራል፡፡በሌላው ሳይሆን በራሱ፡፡ታውቂዋለሽ ፡፡ ከሚሆነው ለማይሆነው ይለፋል፡፡በሁሉ
ሲከፋ አንቺ ጋር ነው ጭንቁን የሚያራግፍ፡፡
ልንገርሽ....
ሁሉ ሲያሳምመው ፥ መጫወቻ አሻንጉሊቱ ሲያደርገው ፥ ያለውን ሁሉ ሲወስድበት መኖሩን
ትርጉመ ቢስ ሊያደርግበት አልተቻለውም፡፡ተንኮልና በደል የማይሰብረው ቀናነትና ተስፋ
ባለቤት ነው፡፡
ግን....
ያንቺ ከሕይወቱ መውጣት ሁሉን ሻረ፡፡መኖሩን ትርጉመ ቢስ አደረገበት፡፡ድካሙን ሁሉ ፍሬ
ቢስ አደረገበት፡፡
ግን....
የሆነ ነገሩ ያምናል፡፡
እንደምትመለሺለት፡፡
እናም...
ይሄን እያሰበ ይጥራል ዛሬም፡፡
ሰው ለመሆን ይደክማል ዛሬም፡፡
ካለው ያጣው ልቡን አጨቅይቶ እንዳያከፋበት ይታትራል፡፡
ሰማሽኝ....
< አላጣኸኝም!!! አለሁ!!! > በዪው፡፡
መልአኩ መጣ፡፡ሕመሙን ሁሉ ተቋቁሞ ሰው ሊሆን በጣረው ሁሉ ገነትን ሊያወርሰው፡፡
መልአኩ < ይዤህ ልብረር > አለው፡፡
< የራሴ ክንፍ አለኝ > አለው፡፡
< የታለ ክንፍህ...!? > ሲለው ፥ ክንፉን ሊያይ ዘወር ሲል የለሽም፡፡
ክንፉን መቼም እየፈለገሽ ነው፡፡ሲፈልግሽ ነዋሪም ነው፡፡
አታመንቺ፡፡
ስታመነቺ ሌላ ይጠልፈዋል ብዬ አይደለም፡፡
የማንም መሆን አይችልም፡፡
እየጠበቀሽ ነው፡፡
አንቺን፡፡
አብራሪ ክንፉን፡፡
ከቀረሽበት ከገነትም ቢሆን ቀርቶ ይጠብቅሻል፡፡
ነይ አብርሪው!!!

(( ጆ ኒ ))

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለሰንበታችን
💚

☞ ገና ከንቅልፌ ስነሳህ ውብ ቀን እንዲሆንልኝ ስትመኝ የመጀመርያ ተግባሬ መፅሀፍ
ቅዱስ መግለጥ ነው ገልጨ መጀመርያ ያነበብኩትን ሳካፍልህ ሰላሜ ሰላማችሁ ስለሆነ
ነውና እነሆ በረከት፦


አሀዱ

ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት፤ የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው


ክልኤቱ


አሁንም በክርስቶስ ደስታ ወይም በፍቅር የልብ መጽናናት ወይም የመንፈስ አንድነት፥ ወይም
ማዘንና መራራትም በእናንተ ዘንድ ካለ
እርሱን ብቻ ታስቡ ዘንድ አንድ ልብና አንድ ምክርም ሆናችሁ በፍቅር ትኖሩ ዘንድ ደስታዬን
ፈጽሙልኝ


በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ
ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።


ታዲያ ከዚህ በላይ ልቦናህ ክፍት ከሆነ ብሩህ ቀን የሚያደርግ የት ይገኛል ሲቀጥል ድንቅ
ቃል አለ ይህን የሚል


"ለባልንጀራችሁም እንጂ ለየራሳችሁ ብቻ አታስቡ"


"ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል"


ልቦናችሁን ክፍት አድርጋችሁ ተፈወሱ


#ጆኒ


መልካም ሰንበት !!!💚


@wegoch
@wegoch
እቃ ስሜት ፥ ቁስ እውነት ፥ መገልገያ ማንነት ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሕዙናን ልቦች ሳቃቸው
ያብረቀርቃል፡፡ከሩቅ ይሰማል፡፡
ፊታቸው ደስታን ይኳላል፡፡አይናቸው ሐሴትን ያንፀባርቃል፡፡ሁሉን አቅልለው ይኖራሉ፡፡
ይሄ ግልብጡ ነው፡፡የተገላቢጦሹን እየኖሩ ነው፡፡በእግራቸው እያሰቡ በጭንቅላታቸው
እየተራመዱ ነው፡፡በፊታቸው ጠፍተው በጀርባቸው ሲታወቁ ነው ይሄ፡፡
ውስጣቸውን ለቄስ ነው፡፡ብቸኝነታቸው መሪር ነው፡፡የምሩን ይንቦቀቦቁታል፡፡ፈርተው
ይሸሹታል፡፡ሸሽተው ሊረሱት ይጥራሉ፡፡እሱም የተረሳ መስሎ አድፍጦ ኖሮ ድንገት ከተፍ
ይላል፡፡
የዛኔ ነው ጉዱ፡፡
ጭምቱ ይወፍፋል፡፡አዋቂ ነኝ ባዩ ግልብነቱ ይታያል፡፡ግልጽ ነኝ ያለውም መሰሪነቱ
ይገለጣል፡፡ደስተኛ መሳዩ ሐዘኑ መሪር ይሆናል፡፡
ሊበላ የሰራውን ሳይጎርስ ያስታውከዋል፡፡ከጣዕም ይፋታል፡፡ከጥጋብ ይለያል፡፡
ሁሉ በአርቴፊሻል ሲዘነቅ ፥ በተፈጥሮው ይረክሳል፡፡በዕውኑ ይሻግታል፡፡የሰው ፀጉር ሰፍቶ
የራሱን ይላጫል፡፡ቅንድቡን አርግፎ በኩል ቅድብ ያበጃል፡፡
ከወዳጅነት የራቀ ነው፡፡
ቄስ የማይፈታው ውስብሳብ ማጥ ውስጥ ይዘፈቃል፡፡
ቀን ያልቅበታል፡፡ባለቀ ቀኑ ላይ የሚሆንለት ሁሉ ግራ ክስተት ነው፡፡ፍቅሩ ማግኘት ሳይሆን
መመኘትና መናፈቅ ብቻ ነው፡፡መውደዱ ከቅዠቱ የተጋመደ ነው፡፡

#ጆኒ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ስለ ችግኞቹ . . . .
* * *
"ችግኝ መትከል ድሮም የጭሰኞቻችን ስራ ነበር፤ አሁንም እንደዚያው ይቀጥላል። ያሳዘነን ጫማ ተጫምተው መትከላቸው ነው!" - አብን


"እኛን ሸውደው ከጫካ ካስወጡን በኋላ ችግኝ መትከል መጀመራቸው የመንግስትን መሰሪነት የሚያሳይ ነው! ተመልሰን ለመግባት መንገዱ የሚጠፋን
ከመሰላቸው ተሳስተዋል!" - ኦነግ


"ችግኞቹ ሕገወጥ በሆኑና ውክልና በሌላቸው የአንድ ብሔር ተፅዕኖ ባደረባቸው ተካዮች ስለተተከሉ መነቀል አለባቸው! ኃይል የእግዚአብሔር ነው!" - ባልደራስ


"የ130 ዓመታት የችግኝ መትከል ጥያቄያችን በመንግሥት ተጠልፏል! ይሁን እንጂ ሕገመንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን ችግኝ መትከላችን አይቀርም!! -
ዎብን


"መንግሥት እያደረገ ያለው የችግኝ ተከላ ዘመቻ የሚደነቅ ነው! ሥልጣኑ
ሊራዘምለት ይገባል!" - አላየለም ጫሚሶ


"መንግሥት ግን ምር ሁኖ ነው ችግኝ እስክናፈላና እስክንሸቅር ድረስ ጊዜ
ያልሰጠን?! በርቼ!" - ዘርማ


"Wayyoo, bara dhuftuuf shimalaa biliyoonaa lamaa argannee jechuu dha kaa jaranaa?" - Qeerroo


"ወደ ትግራይ የሚያልፍ ችግኝ የጫነ መኪና ያለመኖሩ ለውጡ የውሸት መሆኑን አመላካች ነው" - ፋኖ


"አንድ የሚያመረቅን ችግኝ ሲተከል አላየሁም። ኢህአዴግ ሕዝቡ የሚነግረውን የሚሰማው መቼ ነው ግን?!" - እእእእእ ማን ነበር? 🤔😄

@wegoch
@wegoch
@paappii

#gemechu merara
#ሱሪዋን በመቶ ሀምሳ !!

(ሚካኤል አስጨናቂ )

በመጀመርያ ቀን የእትዬ ዘርፈሽዋል ብቸኛ ቀሚስ ተዘረፈ ! 

ዘርፈሽዋል ተዘረፉ ። አቤት ሀዘን ! አቤት የሰፈሩ ሰቀቀን ! መቼም ከአይነ ህሊናዬ አይጠፋም ። ሰው ነጠላ ዘቅዝቆ ሶስት ቀን ድረስ ሊያስተዛዝን ምን ቀረው ? :)

ከክስተቱ ሶስት ቀናት በኋላ ደግሞ  ለእኔ ብርቅዬ የሆነችው ሱሪዬ በተሰጣችበት ቦታ ላይ ሰዓታትን እንኳ ሳትቆይ መጥፋቷ ታወቀ !

ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ... ሰፈሩ እና መንደሩ ሳይቀር የሀዘን ጥላ አረፈበት። 

"በዛው በማገር ሹራቡ 😊 እያለ.. . ያ ምስኪን አንድያ ሱሪው ተሰረቀችበት!!" እያለ ህፃን አዋቂው ከንፈሩን መጠጠልኝ ። 

"ዛድያ ምፅ!  ማለት ብቻ ምን እርባና አለው?" ያሉ አንድ አዋቂ በማግስቱ ሶስት መቶ ብር መዋጮ አሰባስበው ከተፍ አሉ ። 

እልልልልልልል!  አልኩኝ... ደስ አለኝ ! ማህበራዊ ህይወት የሚባለው የሂደት ሰንሰለት እንደ እንጆሪ ጣመኝ ! ምጥጥጥጥ የሚደረግ ደስታ ... ቢጫ ወባ😃 የሆነ የፍቅር ተዓምር ። 

አላልኩም ቢጫ ወባ መች ትለቅና.. . ደግሞ አመሻሹ ላይ ስንሻው ወዳጄ ከተፍ ብሎ ስድሳ ብርና ነፍ ፍቅር የታከለበት ማፅናናት ለቀቀብኝ ። ምን አይነት ሰፈር ነው ያለኝ ግን? 

ማልዶ ሜክሲኮ እስክሄድና ሁለት የቦንዳ ሱሪዎችን በ መቶ ሀምሳ ብር ከጎዳና እስክገዛ ድረስ ተቁነጠነጥኩኝ። ... 

የማይደርስ የለምና ገና ወፎች ማንጎራጎር ሲጀምሩ ቀጣይ ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ እንዳኮበኮበ አትሌት ሰፈሩን በሶምሶማ ማቆራረጥ ጀመርኩኝ። 

እዚህ ሰፈሬ ውስጥ ሱሪ ስለሌለኝ በቁምጣ እንደንቀሳቀስ ሊያውቁ ይችላሉ እንጂ ሌላ ሰፈር ያሉ ነዋሪዎች በተዓምር ከስፖርት ልምምድ ውጭ ምንም ሊመስላቸው አይችልም ። ይሁንና እኛ ሰፈር ማጣት ብርቅ አይደለም !...አሁን ለምሳሌ ዘይነብ ያ የኤርገንዶ ጫማዋ ሶል ሳስቶ እንደ ምላስ ቀጥኗል ። የጋሽ አብረው ጋቢ ቀድሞ እንደ በረዶ የፈካ ቢሆንም አሁን ግን በእበት ምርጊት የተለበደ የጎጆ ምርጊት መስሏል ።

ማጣት ምናባቱ ዋናው ፍቅር ነው ። እኛ ሰፈር ሁላችንም ድሀ ስለሆንን መንግስተ ሰማያት በረኛ እንደሌለበት ጎል ተበርግዶ እንደሚቆየን ተስፋ አለን ። 

መርሀባ !

"ሱሪ በመቶ ሀምሳ !!"  :) 

ጆሮዬ ነው ? ሶምሶማዬን አቋርጬ ዞርኩኝ ።

አይ ጆርዬ አይደለም። 

ሱሪ በመቶ ሀምሳ እያለ የሚለፈልፍ ልጅ ከኔ ሶስት ሜትር ገደማ ርቆ ቆሟል ።

ድምፁን ደግሞ የማውቀው ይመስለኛል...መልኩም ከርቀት ስመለከተው አዲስ አልሆነብኝም!

ራሱ ስንሻው። ... ስንሻው የሰፈሬ ልጅ ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነው ነጋዴ የሆነው ? ለዛውም እሳት የላሰ ለብላባ ነጋዴ ... ብዙ ድህነት አናታቸው ላይ የጃዝ ፋንፋር የሚያንኳኳባቸው ምስኪኖች ከበውት ይተራመሳሉ ።

ጠጋ አልሁኝ ። ከዛ ሁሉ ግርግር መሀል እንደማይለየኝ አውቃለሁ ! 

አንገቴን ከግርግሩ መሀል አስግጌ ልብሶቹን ሾፍኳቸው ።

ቁጭ የእትዬ ዘርፈሽዋልን የሚመስል ቀሚስ አየሁ።   ደነገጥሁ!

ቀና ስል አንዱ ገብጋባ ድሀ የእኔን ብቸኛ ሱሪ እያገላበጠ ካየ በኋላ "እሺ ቢያንስ በመቶ ብር ሽጥልኝ "ሲል ሰማሁት ። 

ስብሀት ለአብ !

በስሜትና በንዴት የጨበጥሁት ቡጢ ብቻውን የፋሲለ ደስን ግንብ አከለ ። 

ያን ቡጢ ጉንጩ ላይ ካሳረፍሁት መቼም ቀጥታ ከምድር ወደ ሲኦል ይደርሳል ።

ግን ደግሞ አንድ ውለታው ፊቴ ላይ መጥቶ ድቅን አለብኝ ። የሱሪዬን መጥፋት እንዳወቀ ከሱ ቀድሞ ለእርዳታ እጁን የዘረጋ አልነበረም። ስድሳ ብር ሁላ ረድቶኛል ።

በቃ ይሄ ማለት በስድሳ ብር ገዝቶኝ ዘጠና ብር አትርፎ ሸጠውም ማለት አይደል?

ላም ልጅ ወልዳ እንዳትልሰው እሳት እንዳትተወው ደግሞ ልጅ ሆነባት እንዳሉ እኔም ስንሻውን እንዳልቦቅሰው አንጀተ ሰፍሳፋ ለጋስነቱ ጠፍንጎኝ ጨክኜ ዝም እንዳልለው ሌብነቱ አድብኖኝ እየተብሰለሰልሁ ሳለ ያ ከኔ የባሰ ሰፍሳፋ ድሀ ሱሪዋን ከመቶም አውርዶ በ ዘጠና ብር ገዝቶት ሲሄድ አየሁት ።

እነሆ ስንሻው ይሁዳው በ ሰላሳ ብር ትርፍ ሸጠኝ 😭

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#mikael aschenaki
ለውብ ቀን
💚💚💚

☞ ደስታከአየር የሳሳ ነዉ ፣ ፍቅር ከዉቅያኖስ የጠለቀ ነዉ።


ወዳጅነት ደግሞ ከዳይመንድ የጠጠረ ነዉ።


ንፁህ የሆነ ፍቅርን ንፁህ ልብ ብቻ ይቀበለዋል፣


እዉቀትን አእምሮ ብቻ ይቀበለዋል፣ንፁህ እጅ ደግሞ ስጦታን ያበዛል የልብ ወዳጅ ደግሞ
ይህንን …………

ውብ ቀን💚!

@wegoch
@wegoch
ከ ብርዳም ጠዋት ጥግ
~~~~~~~~~~~~~
ጠዋት ነው! እጅግ ጠዋት! አርባ ኪሎ ሜትር ብትሮጥ የማይሞቅህ... ሶስቴ ተከርብተህ... ዘጠኝ ሰው እያቀፈህ... እጅህን በትንፋሽህ አይደለም በኢንኩቤተር የማታሞቀው ከአንታርክቲክ ኀ.የ.የ.መ (ኀላፊነቱ የተወሰነ የእግዜር መሬት) እህት ኩባንያ የሆነ የጠዋት ብርድ፡፡ እሳት ዋጥ ዋጥ የሚያሰኝ ብርቱ ቆፈን፡፡ ቡና መጠጣት ፈለግሁና የሆነ ስሙን የማላውቀው ቤት ገባሁ... ካፌው ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች እንዳሉ ገመትኩ... እጅግ የበረደው (እጁን እግሩ መሀል ከቶ ተከሻውን እንደሰቀለ ትኩስ ነገር ፈልጎ አይኑን የሚያቁለጨልጭ!) በብርድ እና በሙቀት መሀል ግራ የተጋባ (ይሄ እጁን የትም አንጠልጥሎ ረስቶታል፡፡ አንዳንዴ እያስታወሰ ጣቶቹን እያጠፈ ይዘረጋል!) ሶስተኛው ግን የእሷ ጉንጭ ነበር፡፡ እንደገባሁ ተያየን (ብርቅ አይደለም መተያየት) ከዛ እየሳቀች መጣች (እየሳቁ መራመድ ምኑም አይገርምም!) ለሰላምታ ፊቷን ሰጠችኝ 90% ጉንጭ 10% አንገት (ይሄ የተለመደ የሰላምታ ስሌት ነው) ከዛ ጉንጯ ጉንጬን ሲነካ....... እዛጋ ሁሉ ነገር ቆመ! የሚንቀሳቀስ የለም! ምድር አዲስ ታሪክ ፃፈች... የኢያሱ ታሪክ ተደገመ... በገባኦን ምድር ሳይሆን በሆነ ካፌ ውስጥ ጊዜ ለተአምር ቆሟል! ጉንጬ ጉንጯን እንደነካ አዲስ የሙቀት አይነት እግዜር ፈለሰፈ! ስሙ 'አይጰርጩኪማ' የሚባል! ጠዋቱ... ይሄ ሀሳብን ጭምር የሚበርደውን ጠዋት በአንድ ጉንጭ እኔ እሷ እና እግዜር በካልቾ አልነው! ጉንጯ... ይሞቃል! ባለ በግ ብርድ ልብስ አስራ ሶስት በጎች ተሸፋፍነው ተኝተውበት ከሚወጣው ትንፋጋም ሙቀት እጅግ የሚልቅ ሙቀት! ሰጠና ትራስ እንዲያ አይመችም! ጉንጭ የተአምር ውጤት መሆኑ ገባኝ! የሆነ ካፌ ውስጥ ሰአት ቆሟላ! ከጉንጯ ላይ ስስ ላብ የተጋደመ ይመስለኛል... ከእርሷ ጉንጭ ወደ እኔ የሚያልፍ ስሙ 'ሙቀት' ብቻ ያልሆነ ጉንጫዊ ተስፋ ደርቆ ወደቀረው ሰውነቴ በቀስታ ፈሰሰ፡፡ ፈገግ ብላ ነበር? ታዲያ ለምንድነው ከእርሷ ፈገግ ያለ አፍ ተተንፍሶ አገጬ አካባቢ ስስ እንፋሎት እየሰራ ያለ አየር ያለ የመሰለኝ? እስከ አሁን ሰዓት ቆሟል... የበረደው ሰውዬ እጁን እግሩ መሀል እንደወሸቀ (እድል በአድልዎ ሲታደል እሱ እሱን ሆኖ ተፈጠረ እኔ እኔ ከተዓምር ጉንጭ ተጣብቄ ሰአት ቆሟል፡፡) ሁሉ የሰራውን ይሰራል... እጄ በትንሹ አቅፏታል! አስመረት ከጠዋቱ ጋር ተደባልቃ የሀሳብ መስመሬን በጨዋ ደንብ ረበሸችው፡፡ ሰዓቱ ቀጠለ... ሁሉ እነንቅስቃሴ ጀምሮ ጉንጯን እያላቀቀች ሳትስመኝ "እምጵዋ" የሚል ሽወዳ ድምፅ አወጣች፡፡ ቀጣፊ እና ውሸታም አለም በቀርፋፋ አረማመዷ ቀጠለች፡፡
አስመረት..."አንተ! ግን አለህ?"
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችሁ
💚💚💚💚

በፈጣሪ ብርሀን ፍቅር አገኜሁ


☞ ሱፊዝም
የሰው ልጅ በመውደቁ ምክንያት ተስፋ መቁረጥ የሚገጥመው አስቀድሞ በእምነቱ ሳይሆን
በሥራው በመመካቱ ነው እናም ለአእምሮህ ማስተዋልን ለልብህ ደግሞ ፅናትንና ርኅራኄን
መግበው።
ሕይወትን አቅልለህ ስትመለከታት የምትሰጥህ ትርጉም እጅግ ሙሉ ይሆናል፣ ከዓለም
የምትሻው እንዲሁ ጥቂት ሲሆን ከፈጣሪህ የምትካፈለው ደግሞ እጅግ ብዙ መሆን
ይጀምራል። ይሉናል ሱፊዎች ሱፊዝም እስልምና ሀይማኖት የወለደው መንፈሳዊ ተመስጥኦ
ነው።


የእምነቱ አራማጆችም እስላማዊ ተሰጥኦ ነው ይሉታል።
ምንም እንኳን ሱፊዝም መሰረቱ እስልምና ይሁን እንጂ የእምነቱ መሪዎች ወደ ህንድ ሂደው
የሂንዱዝም እምነት በስፋት የወሰዱትና የተቀበሉት እንዳለ ይታመናል


ሱፊዎች ስለ እምነት ሲናገሩ "እምነት ሲናገሩት ቀላል ለማድረግ ግን እጅግ የከበደ ነው "
ይላሉ አንዳንዴ እምነታችን ከእግዚአብሄር በቀር በቀረው ነገር ላይ ሁሉ የምናደርግበት ጊዜ
አለ። በፍርድቤት ስንከሰስ ወይም ስንከስ እምነታችን ሁሉ በጠበቃችን ላይ ይሆናል፤
እንዲሁም ስንታመም ደግሞ የእምነታችንን ታላቅነት በዶክተሮቻችን ላይ ይገለጣል፤
ገንዘባችን እንደሚያድነንና እንደሚጠብቀንም እንታመናለን፤ ዕውቀትና ጥበባችንን ደግሞ
ከችግር እንደምናወጣበት አምነን እንመካለን። እናም እምነታችን ሲመረመር የተመሰረተው
በተፈጠረው ነገር እንጂ በፈጣሪ ላይ አይደለም።


ሱፊዎች እምነትን፣ ፍቅርን ፣ ትዕግስትን፣ ደስታን፣ ተስፋን…አስመልክተው በተለያዩ ጣፋጭ
ወጎችና ትረካዎች ከሚማርኩኝ እንዱ ሩሚ ነው።


#ሩሚ

"መምህር ሆይ! ፍቅርን ፈልጎ ለማግኜት መንገዱን ይምሩኝ ይላቸዋል። ሩሚም "የአንተ
ድርሻ ፍቅርን መፈለግ አይደለም ነገር ግን ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ያገደህንና በልብህ
የገነባኸውን የጥላቻ ግንብ ማፍረስ ነው " ። ለሩሚ ፍቅር ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ
በመሆኑም ይህንን ስጦታ የምናገኝበት ቀላሉ መንገድ ሰጭውን አጥብቆ መፈለግ ነው።


ለዚህም ሩሚ ሲናገሩ፦ በፈጣሪ ብርሀን ፍቅር አገኜሁ፤ ከእሱም ውበት ቅኔን ተቀኜሁ፤
የሰው ልጅ ዓይኖች ሊያዩህ በማይቸሉት ልቤ ውስጥ ሆነህም ዘወትር አሸበሽባለሁ፤ እናም
አንዳንዴ በአንተ ታጅቤ ስወዛወዝ ሰዎች ይመለከታሉ ይህንን ደግሞ ጥበብ በማለት
ይጠሩታል


ሩሚ አንድ ወዳጃቸው ቤት ተጋብዘው እጅግ ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ ሰምተው ሲጨርሱ
ጋባዣቸው፦ "ፍቅር በእርግጥም እውር ነው፤ ሰዎችን ባልጠበቁት ስፍራ ወስዶ
ያገናኛቸዋል" አለ።


ሱፊው ሩሚ አንድ ወዳጃቸው ቤት ተጋብዘው እጅግ ደስ የሚል የፍቅር ታሪክ ሰምተው
ሲጨርሱ ጋባዣቸው፦ "ፍቅር በእርግጥም እውር ነው፤ ሰዎችን ባልጠበቁት ስፍራ ወስዶ
ያገናኛቸዋል" አለ።


ሩሚ ግን እንዲህ በማለት አስተካከሉት፦ "ፍቅረኞች በመጨረሻ የሚገናኙበት ስፍራ
የሚባል ነገር የለም፤ አስቀድሞ አንዳቸው በሌላው ውስጥ ነበሩና "።


በመጨረሻም የምትገርመኝን አባባል ልጨምር


""የሰው ልጅ ሰይጣን ያስተማረዉን ያህል የትኛውም መልአክ አላስተማረዉም"

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለሰንበታችን
💚💚💚

ከነገሥታት አንዱ “ዘመን እንደምን አለች?” ብሎ ጠየቀና፥ ዘመን ማለት አንተ ነህ፥ አንተ
ሰላማዊ ስትሆን እሷም ሰላማዊ ትሆናለች፤ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች ብለው
መለሱለት፡፡


አንገረ ፈላስፋ

መልካም ሰንበት!💚

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚


አራት ዓይኖች አሉህ


እነርሱም...ግራ ዓይንህ..ቀኝ ዓይንህ..አዕምሮህና ልብህ ናቸው


አምስት እንዲሆኑልህ በሕሊና ሥራበት


ማህተመ ጋንዲ

ሸጋ ቀን!💚💚💚

@wegoch
@wegoch
_የማቼቴ መልዕክት ወደ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች_
(ኤልያስ ታረቀኝ)

ለጉረቤቱ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው አንድ ገበሬ ነበር፡፡ ይሄ ገበሬ ዘወትር በጎረቤቱ እንደቀና ነው፡፡ ጎረቤቱ ሲደሰት፣ እሱ ያዝናል፤ ጎረቤቱ ሲያዝን፣ እሱ ይደሰታል!
እና ከእለታት አንድ ዕለት እግዚአብሔር/አላህ ከሰማይ ወርዶ እዚህ ቀናተኛ ስውዬ ቤት ይገባና እንዲህ ይለዋል "አንተ ገበሬ እንደምን አለህ!? እኔ የአለማት ሁሉ ፈጣሪ ጌታ ነኝ! ዛሬ ላንተ አንድ ነገር ላደርግልህ አስቢያለሁና የፈለከውን ጠይቀኝ ወዲያው እሰጥሃለሁ! ነገር ግን ላንተ ያደረኩልህን እጥፍ ደግሞ ለጎረቤትህ አደርጋለሁ" አለው፣ የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል ጎርናና ድምጥ፡፡
...
ሰውዬው ታዲያ ማሰላሰል ያዘ! ብዙ አሰበ! አንድ ስልቻ ወርቅ ስጠኝ ቢል ያ ጎረቤቱ ደሞ ሁለት ስልቻ ወርቅ ሊያገኝ ነው፤ ይሄ ደሞ ለጎረቤቱ ካላው ጥላቻ የተነሳ የማይሆን ነገር ሆነበት፡፡ ይልቅስ ጎረቤቱን በምን አይነት መንገድ መጉዳት እንደሚችል አወጣ አወረደና በሚብረቅረቅ ብርሃን ዙሪያውን ተከቦ ፊቱ ለቆመው ፈጣሪ እንዲህ አለው፡
"አንድ ዓይኔን አጥፋልኝ"
ፈጣሪም ቃሉን ተቀብሎ አንድ ዓይኑን ሲያጠፋለት፣ የጎረቤትዮን ደግሞ ሁለቱንም ዓይኖቹን እውር አደረጋቸው፡፡
ይህ ቀናተኛ ገበሬም ባንድ ዓይኑ ሁለቱንም ዓይኖቹን ያጣውን ጎረቤቱን ባየ ጊዜ በጣም ተደሰተ፡፡

በየአከባቢያችን በጎረቤቶቻቸው ላይ ሸር የሚሸርቡ፣ ተንኮል የሚጠነስሱ፣ መተት የሚያሰሩ፣ በሌላው ሀዘን የሚደሰቱ፣ ሰውን ከመጉዳት ሌላ ጭንቅላታቸው የተሻለ ሀሳብ አስቦ የማያውቅ ክፉ ሰዎች ሞልቷል፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ደካማዎች ናቸው፡፡ አለምንም አስቀያሚና አደገኛ ስፍራ ያደረጓት እንደነዚህ አይነት ከይሲ ሰዎች ናቸው፡፡ በሰው ቁስል የሚደሰት አዕምሮ ያለው ሰው ከእንስሳ በምን ይሻላል? ይልቅ ከእንደዚህ አይነት ሰው መቶ እጅ እንስሳት ይሻላሉ! ምክኒያቱም አንድ እንስሳ የራሱ ወገን የሆነ ሌላ እንስሳ አይጎዳማ! ጅብ አስፈሪ እንስሳ ነው፡፡ ጨካኝም ነው፡፡ ነገር ግን ጅብ ጅብን አይገልም! ጎረምሳ ዝንጀሮ ታዳጊ ዝንጀሮቲን አይደፍርም! ሰው ነው የራሱን ዘር የሆነውን ሰው የሚገድል! ሰው ነው የ9 አመት ታዳጊ ህፃን አስገድዶ የሚደፍር! እባብ በጣም ትፈራላችሁ! እኔ ደግሞ ልንገራችሁ፤ አንዳንድ ሰው ግን ከእባብ የበለጠ መርዘኛ ነው! እባብ እባብን አይነድፍም፤ እባብ ካልነካኸው አይነካኽም! ሰው ግን ከእባብ የከፋ እንስሳ ነው! ማን ነበር 'የሰውን ልጅ ይበልጥ ባውቅኸው ቁጥር ውሻህን እየወደድከው ትመጣለህ' ያለው? ማንም ይበል፤ ብቻ ይሄ ሰው አልተሳሳትም!

ፈጣሪ ሰለሚወድህ/ሽ በጥበቡ ሰው አድርጎ አበጀህ/ሽ! ውሻ አድርጎ ሊፈጥርሽ ይችል ነበር፤ ዝንብ አድርጎ ሊፈጥርህ ይችል ነበር፤ አይጥ አድርጎ ሊሰራኝ ይችል ነበር፤ እሱን ግን ለኛ የተሻለውን ሰጠን፡ ሰው መሆን! ሰው መሆን ክቡር ነገር ነው! አብዛኛዎቻችን ግን ሰው መሆን የከበደን ይመስላል! ወይም ሰው የመሆን ትርጉሙ በቅጡ አልገባንም! ሰው መሆን አልተመቸንም መሰል እንስሳ ከመሆን አልፈን ምንነቱ ወዳልታወቀ ፍጡርነት እየተቀየርን ነው! (ኢቮልሽን

እናንተ ቆንጆዎች፣ በሚዲያ ዜና አዳምጣችሁ ታውቃላችሁ? ስንት ሰው ተፈናቀለ ሲባል ሰማችሁ? ህፃናቱ አያሳዝኑም ወይ ቤት አልባ ሆነው ሲቀሩ? አዛውንቱስ? ስንት ሰው ሞተ ሲባል አዳመጣችሁ? ስንት ቤተክርስቲያን፣ ስንት መስጅድ ተቃጠለ ሲባል ሰማችሁ? አደባባይ ላይ ምስኪን ሰርቶ አዳሪ ተዘቅዝቆ እንደ አረፋ በግ በቢላው ሲታረድ አላያችሁም ወይ? ሀናን ረሳቿት? ከአመታት በፊት ከትምህርት ቤት ስትወጣ ደደብ ጎረምሶች አስገድደው ደፍሯት ለሞት የበቃችው ያቺ ጨቅላ ልጅ እንኳ? የሀና እናት እንዴት ስቅስቅ ብለው እንዳለቀሱ እነዚያ ደፋሪዎች ያውቁ ይሆን? ባሏ ፊት ሰለደፈሯት ነፍሰጡር ሴትዮስ? ሰምታቿል አይደል? የባሏን መሸማቀቅና ሃፍረት ማን ነበር የተረዳለት? ይህን ሁሉ ግፍ ማን የፈፀመ ይመስላቿል? እባብ? ጅብ? ሼይጣን? በፍፁም አይደለም፤ እኔ ልንገራችሁ፤ ይሄ ሁሉ የሚፈፅመው በሰው ነው! እባብ ነፍሰጡር ሴትን ባሏ ፊት አየደፍርም! ጅብ ደካማ አዛውንት፣ ህፃናትን ከክልሌ ውጡ ብሎ አያባርርም! ሀናን ደፍሮ ለሞት ያበቃት ሴይጣን አይደለም! ማርያምን አይደለም! ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ሰው ብቻ ነው! ልታፍሩ ይገባል! Shame on you!

እኔምላችሁ፣
ለሰው መልካም ማሰብ እየቻላችሁ ለምን ክፉ ትመኛላችሁ?
ለጎረቤቶቻችሁ ጥሩ አሳቢ መሆን እየቻላችሁ ለምንስ የጎን ውጋት ትሆንባቿላችሁ?
በፍቅር አብሮ መኖር እየቻላችሁ ለምን በጥላቻ ትገዳደላላችሁ?

በአፋችሁ ፣ በአለባበሳችሁ ሃይማኖት አለን ትላላችሁ፤ ነገር ግን በድርጊቶቻችሁ ከሃማኖቶቻችሁ አስተምዕሮት ተቃራኒ ስትሆኑ ትታያላችሁ!

እኔ ግን ዛሬ ልምከራችሁ:
ክፉ አታስቡ! ሸር አትሸርቡ! ተንኮል አትቀምሙ! መልካም ስሩ! እውነት አውሩ! ጥሩ አስቡ! በጎ በጎውን ተመኙ! በቃ ሰው መሆን እኮ እንዲህ መሆን ነው! ሌላ የለውም! ቀላል ነው!

በሉ አሁን ሰው እንሁን
ፈጣሪም በእኛ ደስ ይበለው

@wegoch
@wegoch
2024/09/27 21:30:30
Back to Top
HTML Embed Code: