Telegram Web Link
ለውብ ቀን
💚
መዳን በራሱ ጊዜ ትምህርት ነው!
በጎነትን ፣ ራስን መካድ ያስተምራል፣ የቅንነትን ስሜት ያዳብራል፣ የሐቀኝነትን፣ ብልህነትን
እና አእምሮን ያዳብራል።

በፍቅር የተሰጠን መዳን ረቂቅ ነውና።


መልካም ቀን!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
በየዕለቱ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓታት የሚያልፉት በእንቅልፍ ፣ በንቃት አልባነት ውስጥ ነው ። አንድ ሰው ለስልሳ ዓመታት ቢኖር ሃያዎቹን ዓመታት የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው ። እናም የህይወታችን ሃያዎቹ ዓመታት የሚያልፉት በንቃት አልባነት ውስጥ ነው ። ብዙ ግዜ እንቅልፋችሁን ተኝታችኋል ፤ ነገር ግን እንቅልፋችሁ እንዴት እንደሚመጣ ፣ መቼ እንደሚመጣና ምን እንደሆነ መናገር አትችሉም ። እንቅልፍ እስከሚመጣበት ሰዐት ድረስ ንቁ ሆናችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ ። እንቅልፋችሁ በመጣ ጊዜ ግን ሙሉ በሙሉ ንቃት አልባ ናችሁ ። እንቅልፍ ሁልግዜም የሚያገኛችሁ ንቃት አልባ ሆናችሁ ነው ። ለቋችሁ እስከሚሄድ ድረስም ንቃት አልባ ናችሁ ። ጠዋት ላይ እንቅልፋችሁ ትቷችሁ ሲሄድ ንቃተ ህሊናችሁ ይመለሳል ።



📜  ሌሊቱን ለስምንት ሰዓታት ማንቀላፋታችሁን ስትናገሩ ለስምንት ሰዐታት መተኛታችሁን ታውቃላችሁ ማለት አይደለም ። ለስምንት ሰዓታት ማንቀላፋታችሁ የሚያሳየው ንቁ በነበራችሁበት የመጨረሻው ቅፅበትና ጠዋት ላይ እንደገና ንቁ በሆናችሁበት ቅፅበት መሃል ያለው ክፍተት ነው ። አለዚያ ግን እንቅልፍ ውስጥ ስትሆኑ ተመልሳችሁ የምትሄዱት ወደ እንስሳትና እፀዋት አለም ነው ።



📜🤔 ንቁ እንደሆናችሁ በምታስቡበት ቀሪው የቀን ጊዜ ላይ እንኳ ሙሉ ለሙሉ ንቁ የምትሆኑት አልፎ አልፎ ነው ።

የመንገድ ላይ ተጓዦችን ቆም ብላችሁ ብትመለከቱ አብዛኞቹ በእንቅልፍ ልባቸው እየተራመዱ መሆኑ ይሰማችኋል ። አጠገቡ ለሌለው ሰው ሲያወራ ፣ እጆቹን ሲያወናጭፍ ፣ ከንፈሮቹን ሲያንቀሳቅስ ታያላችሁ ።

ለማነው የሚያወሩት? ንቁ ናቸው? የሆነ አይነት ህልም ውስጥ ናቸው ። አጠገባቸው ማንም የለም ታድያ የሚያወሩት ከማን ጋር ነው? .... ።



📜 🤔 ራሳችሁን ብትመለከቱ ለሁሉም ግዜያት ንቁ እንዳልሆናችሁ ትደርሱበታላችሁ ። ንቃት የሚመጣው አልፎ አልፎ ነው ። አንድ ሰው ደረታችሁ ላይ ስለት ቢያስቀምጥ ፣ በነዛ ቅፅበታት ውስጥ ህልውናችሁን ታውቃላችሁ ። ንቁ የምትሆኑት ይህንን በመሰሉ ቅፅበታት ውስጥ ብቻ ነው ።

ተጨማሪ ምሳሌ ልስጣችሁ...

ይቀጥላል...

@Ebdusocratus
@wegoch
@Wegoch
ለውብ ቀን
💚
ፍቅር ማለት ራስን በሌላ ሰው ማንነት ውስጥ ማግኘት ማለት ነው!


የስነ ልቦና ጠበብት እንደሚሉን እኛም እንደተረዳነው ኦክስጅን ለሰውነታችን
የሚያስፈልገውን ያህል ፍቅር ደግሞ ለአዕምሯችን ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን እውነት ሊቀይር
የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡

ፍቅርን በአግባቡ ባጣጣምነው ቁጥር አካላችን አልፎ ተርፎም ስሜታችን የበለጠ
ጤነኛነት ይሰማዋል። በተቃራኒው ደግሞ ከፍቅር በሸሸን ቁጥር መረጋጋት ይሳነናል፡፡


ፍቅርን የማያውቁም ሆነ በፍቅር ህይወታቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች በህይወታቸው
ድብርት፣ ብስጭት ሲጫጫናቸው የመመልከት አጋጣሚው ሰፊ ነው፡፡
የብዙ ሰዎች ድብርት ዋነኛው መንስኤ ፍቅር ማጣት ነው። ስለዚህ በፍቅር መኖሩ ነው
ለህይወት መልካም ግብ አንዳንድ ምሁራንም ፍቅርን ሲገልፁ፦

ጨለማን ጨለማ አያጠፋውም!
ጨለማን ማጥፋት የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው!


ጥላቻንም ጥላቻ አያጠፋውም ጥላቻን ማጥፋት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።


ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ውይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ
አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው።


የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ
ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።
ፍቅር ግን ፈውስ ነው!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ዛሬ ማክሰኞ /2/2011. ምሽት 11:00 ፮ ኛው እንድቅትዮን የሥነ ፅሁፍ ምሽት እንቁላል ፍብሪካ ከእምቢልታ ሆቴል ገባ ብሎ በሚገኘው በ ገንት መናፈሻ ይጠብቁን!!

@getem
@getem
@getem
ተገረም
❤️
ታላቁ ፈላስፋ አርስቶትል «ፍልስፍና የሚጀምረው በመገረም ነው» ይለናል። ይህ አስደናቂ
ገለጻ ማንኛውም ተመራማሪ ዘንድ የግድ ሊኖር የሚገባ የህይወት ስንቅ ነው። በየቅጽበቱ
ከሚለዋወጠው የዓለም ነበራዊ ሁኔታ ጋር እየተጋፈጠ «አግራሞት» በውስጡ
የማይሰርጸው አካል አዲስ ነገር መፍጠር አይቻለውም። ውስጡን የጥያቄዎች ሱናሚ
የማይንጠው ሰው ለህይወት የሚያበረክተው አዲስ ነገር ቅንጣት አይኖረውም።
.
.
«መገረም» በአራት ፊደላት ተዋቅራ የቆመች ቀላል ቃል ናት። ግና ጥልቀቷ መጨረሻ
የለውም። አዋቂ ስለ አንድ ጉዳይ አሊያም ሥረ ነገር ምርምር ሲያከናውን ብዙ ይማስናል።
አግራሞትን የሚያጭሩ ጥያቄዎች ይሰነዝራል። ከራሱ ጋር በሃሳብ ይፋለማል። እሰጣ ገባ
ውስጥ ይገባል። ውስጣዊ ኃይሉን ያፈረጥማል። ይህን ወሳኝ ሂደት መሻገር ያልቻለ አዲስ
ነገር ለማቅረብ ይሰንፋል። ኃይል ያለው ዕውቀት ላይ ነው። ዕውቀት ደግሞ የጥያቄዎች
ውጤት ነው። «ለምን?» ወይም «እንዴት?» የሚሉ ጥያቄዎች ህብር ፈጥረው ያመጡት
ሐብት ነው። እነኝህ ጥያቄዎች ከህይወት መስክ ውስጥ ሲነጥፉ በሰው እና በአህያ
መካከል የተሰመረው ድንበር ይጠፋል።
.
.
ጥያቄዎች የዕውቀት ሙዳየ ቃላት ናቸው። ጥርጣሬ የምርምር መወጠኛ መሳሪያ ነው።
ቋሚ የሆነ ዕይታ የማሰላሰል መክፈቻ ቁልፍ ነው። ዘውታሪ የሆነ ንባብ የማይቋረጥ ስጦታ
ነው። ስለዚህ አይምሮ የማይቋረጥ ጥያቄ ሊያመነጭ ግድ ይለዋል። እንዲሁ በጭፍኑ እጅ
ከመስጠት ጥርጣሬን ማስቀደም ይሻላል። የህይወትን ሙሉ ገጽታ ከብዙ አቅጣጫዎች
ለመቃኘት ጥልቅ እና ተከታታይ ንባብ ወሳኝ ነው።
.
.
ሁሌም ጠያቂ ሁን። የሆነ ቀን ፈላስፋ ትሆናለህ። በሃሳብ የሚናጥ ማንነት አዳብር። አንድ
ቀን አዋቂና አሰላሳይ ትሆናለህ። ሕይወትን ከብዙ ማዕዘናት ለመመልከት ጥረት አድርግ።
የሆነ ጊዜ የፈጠራ ሰው ትሆናለህ። ሁሌም የማይጠግብ አንባቢ ሁን። አንድ ቀን በህይወት
ውስጥ ለሌሎች እንደ ኦክሲጂን አስፈላጊ ትሆናለህ።
.
.
አይምሮህን ስርዓተ-ትምህርት ብቻ እያነበቡ የህይወት ዘመናቸውን ለሚገፉ ታካች ምሁራን
አታስረክብ። እነርሱ የወጡት ከሁሉ አቀፍ መሃይምነት ወደ ከፊል መሃይምነት ነውና።
የሚኖሩት ባለፈው ዘመን ንቅፈ ክበብ ውስጥ ነው። ዕውቀት ከልደት እስከ ሞት መሆኑን
ዘንግተዋል። የህይወት ጥያቄ ማሳረጊያ እንደሌለው ረስተዋል። አውቃለሁ ብሎ ያሰበ
በርግጥም አላወቀም።
.
.
ፍልስፍና «ሐራም» ነው የሚልህን ሰው ጆሮ አትስጠው። ምክኒያቱም ምኞቱ የርሱ
የምንግዜም ተማሪ ሆነህ አራት በአራት ክፍል ውስጥ ወሽቆ ማስቀመጥ ነውና። ፍልስፍና
ያልታየን ነገር መመርመር ነው። የተሸፈነን ነገር ለመግለጥ ማሰብ ነው። ግና በምን መልኩ
መያዝ እንዳለብህ የግድ መማር ይጠይቃል። ፍልስፍናን እንዴት ማስተናገድ እንደምትቸል
ጠንቅቀህ ማወቅ ሳትችል ዘው ብለህ አትግባ። ለመማርም አታንገራግር። ፍልስፍና እንደ
ውቅያኖስ ሰፊና ጥልቅ ዓለም ነው። በዳርቻው ጥርጣሬን ብታገኝም በጥልቀቱ ምቾትን
ትጎናጸፋለህ።
.
.
ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን ድርና ማግ ፈትተህ ይበልጥ ለማወቅ ያስችልህ ዘንድ ሁሌም
«የሚገረም» ሰው ሁን። በተወሳሰበ የህይወት ተጨባጭ ፊት ተራ ሰው አትሁን። መገረም
በውስጡ ከሌለው እና ድግግሞሽ ከበዛበት የህይወት እንቅስቃሴ ከመምራት ተቆጠብ።
የህይወትን ሚስጢራት በመገረም እንጂ እንዲሁ ማወቅ ከቶም አይቻልም። አርስቶትል
«ፍልስፍና በመገረም ይጀምራል» ሲል ምንኛ እውነትን ተናገረ !!!
.
መገረም ከሌለ ስልቹ ትሆናለህ። ለሰዎች አስተሳሰብ እጅ ትሰጣለህ። የሚባለውን ሁሉ
ታምናለህ። የሰጡህን ትቀበላለህ። ያጎረሱህን ወሬ ታመነዥጋለህ። መገረም የሌለበት
ህይወት አይነቱ አንድ ነው። አዲስ ነገር የሚባል አይኖርም። እድገትና ለውጥ አይታሰብም።
ግርምት አልባ ከሆንክ የአስተሳሰብ ጀብዱ ከውስጥህ አይኖርም። አንተም ሆንክ ማሰብ
የማይችለው ፍጡር አንድ ትሆናላችሁ። አይምሮ የተፈጠረው ለመገረም እንጂ እጅ
ለመስጠት አይደለም። እናም ተገረም !

ውብ ቀን💚!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚
"ሰዎች በይበልጥ አመስጋኝ ከሆኑ የህይወት ድንቅ ነገሮችን ያያሉ"
ጥዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ፈጣሪ ሌላ አዲስ ቀን ስለሰጠህ አመስግን
ሌላ አዲስ ጣዕም ነው! በረከቱም እንዲበዛ መልካም ሥራ ስራበት መልካነት መልሶ
ይከፍላልና።
ሌላ ቀን እንዳየው ስለፈቀደልህ አመስግን ምንም ይሁን ምን እምነት ይኑራችሁ
በማመንችሁ ጠንካራ ሁኑ ተስፋ ይኑራችሁ የተሻለውና ምርጡ ገና ይመጣል።
ልብህ በመልካም ውዳሴ የተሞላ ይሁን አመስግን
ይሄ አዲስ ቀን ነው አዲስ ብርሀን አዲስ እድል ወደ መልካም የምትሄድበትን ለአዲስ ቀን
ተመስገን

ውብ ቀን!!💚

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለምሽታችን
💚
ለእኔ ሙዚቃ አንድ ሁኔታን ወይም ድብርትን ፣ ብስጭትን ፣ መደበትን የመፈወስ መንገድ
አለው። ብዬ አስባለው በብርሃንና በጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳን ልብህ ያበራል ሙዚቃ



ሙዚቃ ካለ ብቸኝነት ከንቱ ነው! አጽናፈ ሰማይን ለሰው ነፍስ ሀሴትን ይሰጣልና።
ለህይወት እና ለሁሉም ነገር ሞቅ ያለ እና ግርማ ይፈጠል!
ሙዚቃ የመፈወስ ኃይል አለው!
ሙዚቃ በዓለም ላይ በጣም ጥሩ ግንኙነት ፈጣሪም ነው። ምንም እንኳን ሰዎች
የሚዘምሯቸውን ቋንቋ የማይረዱ ሰወች እንኳን ቢሆንም እንኳ በሚሰሙበት ጊዜ ጥሩ ጥሩ
ስሜትንና ግንኙነትን ይፈጥራሉ።


በኛ ሀገር ደረጃ ማርዬ ና ማህሙድ አህመድ ለኔ ድንቆች ናቸው። ጥሩ ስሜት ፈጣሪዎች
ናቸው። እንዲህ አብረው ሳያቸው እንዴት ደስ እንደለኝ። እረጅም እድሜና ጤና ይስጣቸው
አቦ።

ሁለቱን ❤️ትንግርቶቼን አንድ ላይ ሳያቸው የሁለቱንም አንድ አንድ ለምን አላንጎራጉርም ስል ነሸጠኝ....ይሄው

ሸጋ ምሽት!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚
ኢማም ሻፊዒይ:—

"የኔ ሃሳብ ትክክል ነው፤ ነገርግን ስህተትም ሊሆን ይችላል። የሌሎች ሰዎች ሃሳብ
ስህተት ነው፤ ነገርግን ትክክልም ሊሆን ይችላል።"


ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ አባት እንደ ሀገር ሽማግሌ እንደ ሀይማኖት መሪ
የመንፈስ ከፍታ ላይ የሚገኙ ግን በተገቢዉ ያለተዘመረላቸዉ ናቸዉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ
ኡመር እንድሪስ ፡፡ አዎ በነገዉ እለት ተገቢዉ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡ በእርግጥ የክብር
ዶክትሬት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ረክሶ አይተነዋል እንዲህ ቦታዉን ሲያገኝ ደስ ይላል፡፡

ቢያንስቦት እንጂ........

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን
💚
እውነት ለሁላችንም አንድ መስላ ብትታየንም እንደህይወት ምልከታችን እና እምነታችን
የተለያዩ ትርጉም እንዲሁም ዋጋ እየሠጠናት ለመኖር እንገደዳለን።


ሁለት ሠዎች በመንገድ ሲሂዱ ሜዳ ላይ እጅግ የተዋቡ የከበሩ ድንጋዬችን በመሀርብ
ውሥጥ ተደርገው ተጥለው ያገኛሉ።
ይሁንና በአከፋፍሉ ላይ መሥማማት አልቻሉም አንዱ ቀድሜ እኔ ነው ያየሁት አብሌጬ
መውሠድ ጽገባኛል ሲል
ሌላኛው ከረጢቱን ቀድሜ አንሥቼያለው አብላጫ ይገባኛል በማለት መጣላት ጀመሩ
በመጨረሻም ሙላ ናሡሩዲን ዘንድ ሂደው በሡ ዳኝነት ለመካፍል ተሥማምተው ይሄዳሉ
ናሥሩዲን ጉዳዬን ካዳመጠ ቡሀላ ጥያቄ አቀርበ እነዝህ የከብሩ ድንጋዬች ያለአድልኦ
በእኩል መካፍል ትፍልጋላቹ ።
ለምሆኑ እንደሠው ነው ውይሥ እንደፍጣሪ እንዳካፍላቹ የምትፍልጉት ?
ሁለቱም በአንድ ቃል እንደፍጣሪ አካፍለን በማለት ተናገሩ ።
በዚህ ግዜ ናሥሩዲን ለአንዱ ዘጠኝ ለሌላው ሶሥት ሠጥቶ ያካፍላቸዋል
ሦሥት ብቻ የተሠጠው ግን ንዴቶን መቆጣጠር አልሆለነትም ነበርና እንዴት እንደፍጣሪ
አካፍለን ሥንልክ እንዲህ ታደርጋለህ በማለት አፍጠጠበት ።
ናሥሩዲን ግን ፍገግ ብሎ፦ በፍጣሪ ዘንድ እኩል ተብሎ የሚታሠበው በሠው
ከሚታሠበው በእጅጉ እንደሚለይ አታውቅንም ?
እኩል የሚለው ሀሣብ የሠው እንጂ የፍጣሪ አይደለም በማለት አሠናበታቸው።


ማንኛውም በሠው ዘንድ ትክክል ተብሎ የሚተላለፍው ፍርድ በፍጣሪ ዘንድ እንዲህ ነው
ብሎ ማሠብ የዋህነት ይሆናል
በፍጣሪና በሠው መካከል የምናገኝው መሠርታዊ ልዩነትም ይህው ነውና ።


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/27 21:28:43
Back to Top
HTML Embed Code: