Telegram Web Link
የአንድ እቃ ወይም ጉዳይ ዋጋ የሚለካው፣ በእቃው ወይም በጉዳዩ ሳይሆን፣ እቃው ወይም ጉዳዩ ባረፈበት ሰው ማንነት ነው።

ከዮቶር መፅሐፍ የተወሰደ

👉👉@temuabiy👈👈
👉👉@temubiy👈👈
👉👉@temuabiy👈👈
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7 እነሆ የተለያዩ ጉዳዮችን አካታ ለንባብ በቅታለች!
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7.pdf
3.5 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰
ለውብ ቀን
💚
በዓለም ውስጥ ደስታም ሆነ ውድቀት የለም!
አንድ ንጽጽር ብቻ ነው ያለው በአንተ ውስጥ ደስታም ወድቀት ወይም ሀዘን ብለህ
የምታነፃፅረው። እና ሌላ ምንም ነገር የለም!
በጣም የሚያስጨንቅ ሰው ከፍተኛ ስሜት ሊኖረው ይችላል.። ይህን ስታነፃፅን የሚመጣ
ስሜት እንጅ ሌላ ምንም የለም።
እምነት ሲኖርህ ግን አምላክ በሁለት ቃላቶች ደስታን እና ፍሰሀን ብሩህነትን ይሰጠሀል በ"
ቃል ኪዳን እና ተስፋ "

ውብ ቀን

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
ከአልሙስጠፋን ተከታዩ ሳርኪስ እንዲህ ሲል ጠየቀው:- አስቀያሚነት ምንድን ነው፤ መምህር
፤ ስለ አስቀያሚነት ስትናገር አልሰማንህም።
አልመስጠፋ መናገር ሲጀምር ቃላቱ እንደ አለንጋ ይጋረፍ ነበር፦
አንድ ሰው በርህን ሳያንኳኳ በአጥርህ አልፎ ስለሄደ ብቻ እንዴት ለእንግዳ አይመችም ብሎ
ያማሀል? ፈፅሞ በማታውቀው እንግዳ ቋንቋ ያናገረህ ሰውስ እንዴት ደንቆሮ ነው
አያስተውልም ብሎ ሊናገርህ ይችላል?
እንደዚሁ ሁሉ ፈፅሞ ልትገባበት ያላሰብከውን የአንድ ሰው ልብ ከውጭ ሆነህ እንዴት
አስቀያሚ ነው ማለት ትችላለህ?
አስቀያሚነት የምንለው የዐይናችን የተንሸዋረረ መለኪያነትና ጆሮአችንን የደፈነውን ኩክ
እንጂ ሌላ አይደለም!!!

ወዳጄ የራሷን ትውስታ ለማየት ከምትፈራ ነብስ በቀር ማንንም ነገር አስቀያሚ አትበል!!!!!

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ዛሬ በአሜሪካ የነበረኝ ውሎ …
(አሌክስ አብረሃም)

ርእሱ ትንሽ ጉራ ያለበት ይመስላል አይደል? ….ደግ አደረኩ ! ዛሬ ጁላይ ፎርዝ ነው የአሜሪካ የነፃነት መታሰቢያ በዓል …አሁን ራሱ ይሄን እየፃፍኩ የርችቱ ድምፅ አሜሪካ ሳይሆን ሶሪያ ያለሁ እስኪመስለኝ ያሸብረኛል ….ስራ የለ ትምህርት የለ በቃ ዘና ነው …መዝናናትን ፈረንጅ ይዝናና …ብር ነው አለ …ይሉኝታ ነው የለም ! ብር ካለህና ይሉኝታ ከሌለህ አለም አስር ነው! እኛ አበሾች ብሩ ሲኖር ይሉኝታ ቀፍድዶ እየያዘን መች እንዝናናለን …..(የፈረደበት ሶደሬ እንኳን ከምትወዳት ልጅ ጋር ሂደህ ከመሳሳምህ በፊት 360 ድግሪ ቸክ ማድረግ አለብህ!) ታዲያ ወደከተማው ዋና ክፍል (ዳውን ታውን ይሉታል )…ተያይዘን ሄድን ከተማው አብዷል …እዚህና እዛ ባንዲራ ነው …መጠጥ ነው …ዳንስ ነው …መሳሳም ነው … በተለይ ሴቶቹማ ሌላ ነገር ነው የሚያደርጋቸው …(ሴቶቹን ምን አሳየህ የሚል ይኖራል ጥሩ ጥያቄ ነው …ተሳስተው እንዳይስሙኝ ራሴን ለመጠበቅ ነው
)
ያልተለበሰ አይነት አለባበስ የለም …ጎራዴ ሁሉ የታጠቀ ፈረንጅ አየሁ …ባጠገቤ ቀዥለል ቅዥለል ሲል ‹‹ገብርየ ቀስ›› አልኩ በልቤ ! የድሮ ረዥም ቁመህ ጠብቀኝ ጠብመንጃ (የእውነት ይሁን አይሁን እንጃ) ይዞ የሚንጎማለል ነፍጠኛ ፈረንጅም አጋጥሞኛል ….እንደአሊ ባስትኒ ከበሮ እየደለቀ የሚዞር ጢማም የቴክሳስ ሰውም አጋጥሞኛል ….የእነሱ የፀሃይ ወቅት እየገባ ስለሆነ በዚህ ሰዓት በተለይ ሴቶቹን(ምናባቴ ይሻለዋል ይሄ ዓይኔ) እምየ ማሪያም የት ላይ እንደሳመቻቸው ሁሉ ጠጋ ብሎ ማየት ይቻላል ….ሁሉ በግልጥ ነው !!
ግልፅነትና ተጠያቂነት በአሜሪካ አለ …ሲሏችሁ ቅኔ ነው ወዳገር ቤት ለማምጣት መንገድ በመዝጋትና ድንጋይ በመወርወር መንግስትን አታስቸግሩ ….ግልገል ሱሪና የሆነች እራፊ የለበሰች ሴት እስከጆሮ ግንዷ ፈገግ ትልልሃለች ግልፅነት ይባላል ጥግብ እስከምትል ማየት ትችላለህ እቤትህ ለማየት ሁሉ ፎቶ ማንሳትም ትችላለህ ….ፈገግ አለችልኝ ብለህ ጫፏን ብትነካ ተጠያቂነት እንደምርጊት ይጫነሃል ! ይሄው ነው ሒሳቡ !
ምን ላይ ነበርኩ ….አዎ ታዲያ እንዲህ እየተደሰትን አለ አይደል በዓሉ የኛ እንዲመስለን ‹‹አድዋ ነህ ብለናል አደዋ ነህ ›› እያልን ስንዞር አንዲት ክንፍ ብቻ የጎደላት መለዓክ የምትመስል ሴት በነገርኳችሁ አለባበስ ፊቴ ተገተረች …‹‹አንተ ክፉ ከኔ ራቅ›› ብየ አማተብኩ …እሷ ግን የበለጠ ቀረበችኝ(በዚህ ሁኔታ ፀሎቴ ባለመስመሩ እግዜርን አልተቀየምኩትም) በደረቷ ልክ እንደቤተክርስቲያን ሙዳየ ምፀዋት አይነት ትንሽ የጣውላ ሳጥን ነገር አንጠልጥላለች ….በውስጤ ‹‹እዚህም አገር ለአገራቸው ዋጋ ከፍለው የተቸገሩ አርበኞች ይኖሩ ይሆን እንዴ ለነሱ ገንዘብ እያሰባሰቡ ሆናል ››አልኩ …ልጅቱ ግን ቀልጠፍ ብላ
‹‹ በናይጀሪያ በከተሞች መስፋፋት ምክንያት ጫካዎች በመመናመናቸው ዘሩ ሊጠፋ የተቃረበ ‹ካርቶፒ ምናምን› የሚባል የጫካ ሸረሪት ዘር ለመታደግ ገንዘብ እያሰባሰብን ነው ከቻሉ ይርዱን ›› ብላኝ እርፍ ….የሽረሪቱ ፎቶ የታተመበት ወረቀት ሁሉ ሰጠችኝ …እኔ እቤቴ ባገኘው በመጥረጊያ ወላ በጫማ ነበር ….ናይጀሪያ የሚገኝ ጫካው የተመነጠረበት ሸረሪት ለመታደግ ሆሆ . . .
ሃሳቤ ተንደርድሮ አገሬ ላይ አረፈ …በዚህ ክረምት ቤታቸው ፈርሶ ልጆቻቸውን ይዘው በየመጠለያው ያሉ እናቶች …አቅመ ደካሞች …አማራ ክልል …ሱማሌ …ጌዲዮ …ኦሮሚያ …ከዳር እስከዳር …አለም ለሸረሪት ነብስ ሁሉ የሚጨነቁ ሰዎች አላት አገሬ ግን …..ሃሳቤ አይቆምም በዚች ሰዓት …የመን ሶሪያ ሊቢያና ብዙ ብዙ ቦታ ያሉ ነብሶች ሁሉ …. ናይጀሪያ ራሱ ቦኮሃራም ፍዳቸውን የሚያበላቸው ድህነት ያስመረራቸው ስንት ሚሊየን ህፃናት ይኖሩ ይሆን … ይሄን እያሰብኩ አንዲት ፊቷ በፀሃይ አለርጅክ የተዥጎረጎረ ነጭ ፈገግ ብላልኝ አለፈች ….ሸረሪት ሸንቶባት ይሆናል አልኩ በሃሳቤ ! ዝም ብሎ የናይጀሪያው ሸረሪት አበሳጭቶኛል!

@Wegoch
@Wegoch
መርታት፤ መረታት፤ መገገም
(በእውቀቱ ስዩም)

የሆነ ጊዜ ላይ ረከቦት ጎዳና፤ ባንዱ ካፌ ውስጥ፤ ቡን ስጠጣ፤አንድ ጎረምሳ ወደ ተቀመጥኩበት መጣ፤ልጁ ግድንግድ ነው፤ጎልያድ ዳዊትን አዝሎ ያክላል፤ እኔ ደሞ እንደምታውቁኝ ነኝ፤ከፊቴ ሲቀመጥ የሚጥሚጣ ብልቃጥ አከልኩ፤ ግብዳው ብዙ ሳይቆይ የምነት ክርክር ጀመረ፤በተቻለኝ መጠን ወደ ክርክሩ ላለመግባት ተግደረደርኩ፤ ሰውየው ግን አልከራከርም ብለው ንቀኸኝ ነው ብሎ ሊደበድበኝ ይችላል፤ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ የነደደ ክርክር ውስጥ ራሴን አገኘሁት፤ሰውየው አረፋ እየደፈቀ ተተጋተገኝ፤
ጎረርህ በሉኝ ብትፈልጉ ! አስር ቀቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልጁን መፈናፈኛ አሳጣሁት፤ መግብዳው ክርክክራችንን ያሳረገው እንዲግ በሚል ቃል ነው፤
"‘ ልታሳምነኝ አትድከም ! እገግምብሃለሁ”
አሁን ሳስበው፤ አስተምረዋለሁ ያልሁት ያ ግብዳ ሰውየ ትልቅ ቁምነገር አስተምሮኛል ፤ ባፍለኝነቴ ፤የሰው ልጆች ለሀቅ እና ለምክንያታዊነት የሚኖሩና የሚሞቱ ይመስለኝ ነበር፤ሰዎች በውይይት የሚያምኑ ይመስለኝ ነበር፤ አዋቂ ባላዋቂ ላይ የሚበረታ፤፤ እውነት የያዘ ሰው ሀሰተኛውን የሚረታ ይመስለኝ ነበር፤ እየኖርኩ ስሄድ ይሄ እምነቴ ጥሎኝ ሲመንን ታዘብኩት፤ አብዛኛው ሰው ለውነት ደንታ የለውም፤ አብዛኛው ሰው፤ ስለ እውቀት ስለተጨባጭ መረጃ ግድ አይሰጠውም፤ በተፈጥሮ ይሁን በልማድ እንጃ፤ አብዛኛው ሰው ችኮ መንቻኮ ነው፤ ልብ አድርቅ ነው፤ የውይይት አላማ ከላይ ከላይ የእውቀት ልውውጥ ቢመስልም ውስጥ ውስጡን መሸናነፍ ነው ፤ሽንፈት መራራ ፍሬ በሚያስለቅምበት አገር ውስጥ ደሞ፤ ማንም መሸነፍ አይፈቅድም፤ ብታሸንፈው ተሸነፍኩ አይልህም፤ ተዘርሮም ይፎክርብሃል! ይገግምብሃል!
ቀኛማች በላይነህ የተባሉ ባላባት በዳግማይ ምኒልክ ጊዜ ነበሩ፤በዘመናቸው፤ ከስራቸው ጋራ የማይመጣጠን አንጀባ ስለሚያበዙ " ቁንን በላይነህ" የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቱዋቸው ነበር፤የሆነ ጊዜ ላይ ከሸገር ወደ ጎንደር ይሄዱና ባንድ ደብር ውስጥ ይስተናገዳሉ፤ቁንን በላይነህ ፊደል ያልቆጠሩ ጨዋ ቢሆኑም በሊቃውንቱ ፊት የተማሩ ለምምሰል ተጋጋጡ፤ ዳዊት እየደገምኩ ነው ለማለት ዳዊት ገለጡ፤ ግን የማያውቁትን ዳዊት ገልብጠውት ነበር የያዙት፤
ይህንን የሾፈ አንድ ደብተራ ሳቁን በጋቢው ለመጨቆን እየሞከረ፤
“ጌቶች ዳዊቱን ዘቅዝቀው ነው የያዙት” ቢላቸው፤
))“ጠላቴን እንዲዘቀዝቅልኝ ብየ ነው! ጠፍቶኝ እንዳይመስልህ ” አሉት ይባላል፤
ቁንን በላይነህ አላዋቂ ናቸው፤ግን አላዋቂነታቸውን አምነው ማረም አይፈልጉም፤ ማንን ደሰ ይበለው ብለው!?ተሸንፈው፤አሸናፊ መስለው ቆመዋል! ገግመዋል!
ታዋቂው የታሪክ ፀሀፊ ተክለፃድቅ መኩርያ በግለታሪካቸው ላይ አንዲት ገጠመኝ ጠቅሰዋል፤ ገጠመኚቱን በኔ አማርኛ ሸክሽኬ ሳቀርባት ይቺን ትመስላለች፤ የሃይለስላሴ ባለስልጣኖች በደርግ ወጣት መኮንኖች እየተለቀሙ በሚታጎሩበት ቀውጢ ወቅት ፤ ሁለት ወጣት ታጣቂዎች ተክለፃድቅ ቤት ድረስ ይመጡና በቁጥጥር ስር ያውሉዋቸዋል፤ በገዛ መኪናቸው፤ይዘዋቸው በሚሄዱበት ጊዜ አንዱ ታጣቂ ለጉዋደኛው_-_
“ከተማ ይፍሩ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት አስር ሚሊዮን ብር በኪሱ ተገኘ” ይላል፤(ከተማ ይፍሩ የዘመኑ ባለስልጣን ነው)
“ይሄን የሚያክል ገንዘብ በኪስ ሊያዝ አይችልም” አሉ ተማራኪው ተክለፃድቅ፤
“ባይኔ በብረቱ ያየሁትን” አለ ወታደሩ፤
“ይህን ጊዜ” ይላሉ ተክለፃድቅ መኩርያ “ ይህን ጊዜ ዝም አልኩ፤”
ዝም ባይሉ ኖሮስ?
ታጣቂው ይገግማል!
ጠመንጃውም ያስገመግማል፤
አስከሬን ይለቀማል
እና ይሄ ማን ይጠቀማል?
አንዳንዴ በፌስቡክ ማለቂያ አልባ ክርክር ውስጥ ዘልየ ለመግባት ሲቃጣኝ እኒህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤አንዳንዴ ዝም አልክ ማለት እውነቱን ከመናገር ተቆጠብክ ማለት አይደለም፤ሃይልህን ቆጠብክ፤ሰላምህን ቆጠብክ፤ ህይወትህን ቆጠብክ ማለት ነው፤

@Wegoch
@Wegoch
#ጥንዶቹ_ለሰርጋቸዉ ቀን ያዘጋጁት #የጥሪ_ካርድ ማተሚያ ቤቱ ትልቅ ስህተት እንደሰራ ያወቁት ሁሉም ካርዶች ለተጋባዦች ተበትኖ ካለቀ በኋላ ነበር!

ማተሚያ ቤቱ እንዲያትም የተሰጠዉ ጥቅስ 1ኛ ዮሐ 4:18 ላይ ያለዉን ቢሆንም '1ኛ' የሚለዉን በመርሳታቸዉ ያተመዉ ዮሐ 4:18 ላይ ያለዉን ነበር። (1ኛ የምትለዋ በመረሳቷ መፅሐፉ ከ1ኛ የዮሐንስ መልዕክትነት ወደ የዮሐንስ ወንጌል ተቀየረ ማለት ነዉ።)

እንዲታተም የተፈለገዉ 1ኛ ዮሐንስ 4:18
"በፍቅር ፍርሃት የለም ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አዉጥቶ ይጥላል.. " ይላል

ማተሚያ ቤቱ ያተመዉ ዮሐንስ ወንጌል 4:18
"አምስት ባሎች ነበሩሽ አሁን ካንቺ ጋር ያለዉም ባልሽ አይደለም..." ይላል!
💍 💍 💍

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን
💚
ጊዜ የሚባል ነገር የለም!
ያለፈውን እና የወደፊቱን አታያውቁም ሁልጊዜም ሁሌም ነው!

ኤካርት ውስብስብ ጽንሰ-ሐሳቦችን በተጠና የቋንቋ ማብራራት የሚችለው የአብርሆት
መምህር ነው እላለሁ።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህንን የአሁንነትን ሀይል" መጽሐፍ በማንበብ አንድ ምዕራፍ
ውስጥ አንባቢዎች ዓለምን በተለየ እይታና በእውቀት ሰላምና ደስታ ውስጥ የመኖር
ችሎታን ያስገነዝባል።

ስለአሁን እና ስለወደፊቱ ማሰብ ካቆማችሁ እና በ አሁንነት ውስጥ ካላችሁ ጥሩ ስሜት
እንዲሰማችሁ ታደርጋላቹህ።

አሁን ያለህን ጥልቅ ስሜት ተገንዘብ አሁን ህይወትዎ ትልቅ ትኩረት ስጡ አሁን
በሚኖሩበት ቦታ እና አሁኑኑ የሚያጋጥሙትን ተፅእኖዎች ለመቋቋም በሚያስችልዎት ጊዜ
ውስጥ ነህና አሁን ያለዎትን ጥልቅ ስሜት ይገንዘቡ።

ኤካርት ሰዎች በየቀኑ በዕለታዊ ኑሯቸው እንዴት ማሰብ እንደሚጀምሩ በመፅሀፉ ይናገራል።

አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት ለሚደርጉት ነገር በፍርሀት ወይም በተስፉ ይጠብቃሉ።
ይሄ ግን ይላል ኤካርት "ራስን በራስህ ላይ መጣበቅ" ወይም ሙሉ በሙሉ "ምክንያታዊ"
በሆነ አዕምሮ ሁኔታ ውስጥ መውደቅ ነው።

እነሱ ሙሉ ጊዜውን ከመቀበል ይልቅ ወደፊቱ ለማሰብ ይፈልጋሉ። አሁንነትን ይዘነጋሉ።

ከአሁንነት ውጭ ስትሆን እርጋታን ታጣለህ ብስጭት የጥፋተኝነት ስሜት፣ ሀዘን፣ ድብርት፣
ቁጣ፣ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ወዘተ የመሳሰሉት አሉታዊ ስሜቶች ይከሰታሉ።

እንደ ኤክሃርት ሀሳብ አዕምሮዎቻችን ዋነኛው ጠላታችን ነው እና በአዕምሮ እና በነፍስ
መካከል ልዩነት ያደርገዋል።

አዕምሮችን ዋነኛው ጠላታችን ነው! በአዕምሮ እና በነፍስ መካከል ልዩነት እንዲፈጠር
ያደርጋል።

ማሰብ ማቆም አለመቻል አስደንጋጭ ነገር ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው እየተሰቃየ ስለሆነ
ይህንን አናውቀውም። ስለዚህ እንደ የተለመደ ነገር ይቆጠራል።

የአሁንነት ኃይልን ካነበብኩ በኃላ ዘመናዊው የሰው ልጅ በአደገኛ በሽታዎች እየተሰቃየ
እንደሆነ ተረዳሁ
አሁን ለእኔ በጣም ግልጽ ነው! በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በጭንቀት በመንፈስ ጭንቀት
እና በመሳሰሉት ችግሮች ይሠቃያሉ?
በእኛ ተጨባጭ እና በሚንቀሳቀሱ አስተሳሰቦች ላይ ስንመጣ በሰላም
እንኖራለን።

የሚያሳዝነው ብዙ ሰዎች እንዴት አሁንነት ላይ እንደሚያቆሙ አያውቁም።

በመጽሐፉ ላይ እንደሚነግረን የሚያስጨንቁ ሐሳቦችን ለማሸነፍ የመጀመሪያው እርምጃ
አዕምሮዎን እንዲመለከት ወይም እንድንረዳ ማድረግ ነው።


እናም የአሁንነት ሀይል መፅሀፍ ስታነብ ከምትረዳቸው ነገሮች ባሻገር ኑሮህን እንዴት
ጤናማና ደስተኛ ኑሮ መኖር እንደሚቻል ያሳያል።

"ሁሉም አሉታዊነት የሚመነጩት በአይምሮአዊ ግኝት እና የአሁንነትን በመከልከል ነው."
የዛሬው ሁኔታ ምንም ይሁን ምን! እንደመረጡት አድርገው ተቀብሉት።

ይቀጥላል……………


የተገማሸረ ውብ ቅዳሜ ይሁንልን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለሰንበቲታችሁ
💚
እግዚአብሔር መልካም ሆኖ በሰጠን ጊዜ ውስጥ እኛም መልካም እንሁን!
እግዚአብሔር እኛ እንድናውቀው የሚሻ የፍጥረተ ዓለም ፈጣሪ ነው፡፡ እኛ ሁላችን በዚህ
ያለነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የእርሱን ብርታት፣ ፍቅር፣ ፍትህ፣ ቅድስናና ርህሩኅነት
እንድንለማመድና በእርሱም እንድንታመን የእርሱ የመሻት መልካምነት ነው።


ይህንን ሁሉ መልካምነት ሸቶልናል አምላክ እግዚአብሔር ደግ ሆኖ በሰጠን ህይወት
ውስጥ ደግ እንሁን!


እግዚአብሔር ፍቅር ሆኖ በሰጠን ፍቅር እኛም እንዋደድበት!
እግዚአብሔር ለሚጠሩት፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፣የሚፈሩትንም ከመልካም
ነገር አያጎድላቸውም የልባቸውን መሻት ይፈጽምላቸዋል)ጩኸታቸውን ይሰማል
ያድናቸዋልም"(መዝ 145፡18-19)
ራሳችንን በደግነት በመልካምነት በቅንነትና በፍቅር ራሳችንን እንስጥ።

"እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በመከራም ቀን መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም
ያውቃል"(ናሆ 1:7
ፍቅርም ያብዛልን
መልካም ዕለተ ሰንበት

(( ጆኒ,)))💚💛

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
መዳን በራሱ ጊዜ ትምህርት ነው!
በጎነትን ፣ ራስን መካድ ያስተምራል፣ የቅንነትን ስሜት ያዳብራል፣ የሐቀኝነትን፣ ብልህነትን
እና አእምሮን ያዳብራል።

በፍቅር የተሰጠን መዳን ረቂቅ ነውና።


መልካም ቀን!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
በየዕለቱ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓታት የሚያልፉት በእንቅልፍ ፣ በንቃት አልባነት ውስጥ ነው ። አንድ ሰው ለስልሳ ዓመታት ቢኖር ሃያዎቹን ዓመታት የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው ። እናም የህይወታችን ሃያዎቹ ዓመታት የሚያልፉት በንቃት አልባነት ውስጥ ነው ። ብዙ ግዜ እንቅልፋችሁን ተኝታችኋል ፤ ነገር ግን እንቅልፋችሁ እንዴት እንደሚመጣ ፣ መቼ እንደሚመጣና ምን እንደሆነ መናገር አትችሉም ። እንቅልፍ እስከሚመጣበት ሰዐት ድረስ ንቁ ሆናችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ ። እንቅልፋችሁ በመጣ ጊዜ ግን ሙሉ በሙሉ ንቃት አልባ ናችሁ ። እንቅልፍ ሁልግዜም የሚያገኛችሁ ንቃት አልባ ሆናችሁ ነው ። ለቋችሁ እስከሚሄድ ድረስም ንቃት አልባ ናችሁ ። ጠዋት ላይ እንቅልፋችሁ ትቷችሁ ሲሄድ ንቃተ ህሊናችሁ ይመለሳል ።



📜  ሌሊቱን ለስምንት ሰዓታት ማንቀላፋታችሁን ስትናገሩ ለስምንት ሰዐታት መተኛታችሁን ታውቃላችሁ ማለት አይደለም ። ለስምንት ሰዓታት ማንቀላፋታችሁ የሚያሳየው ንቁ በነበራችሁበት የመጨረሻው ቅፅበትና ጠዋት ላይ እንደገና ንቁ በሆናችሁበት ቅፅበት መሃል ያለው ክፍተት ነው ። አለዚያ ግን እንቅልፍ ውስጥ ስትሆኑ ተመልሳችሁ የምትሄዱት ወደ እንስሳትና እፀዋት አለም ነው ።



📜🤔 ንቁ እንደሆናችሁ በምታስቡበት ቀሪው የቀን ጊዜ ላይ እንኳ ሙሉ ለሙሉ ንቁ የምትሆኑት አልፎ አልፎ ነው ።

የመንገድ ላይ ተጓዦችን ቆም ብላችሁ ብትመለከቱ አብዛኞቹ በእንቅልፍ ልባቸው እየተራመዱ መሆኑ ይሰማችኋል ። አጠገቡ ለሌለው ሰው ሲያወራ ፣ እጆቹን ሲያወናጭፍ ፣ ከንፈሮቹን ሲያንቀሳቅስ ታያላችሁ ።

ለማነው የሚያወሩት? ንቁ ናቸው? የሆነ አይነት ህልም ውስጥ ናቸው ። አጠገባቸው ማንም የለም ታድያ የሚያወሩት ከማን ጋር ነው? .... ።



📜 🤔 ራሳችሁን ብትመለከቱ ለሁሉም ግዜያት ንቁ እንዳልሆናችሁ ትደርሱበታላችሁ ። ንቃት የሚመጣው አልፎ አልፎ ነው ። አንድ ሰው ደረታችሁ ላይ ስለት ቢያስቀምጥ ፣ በነዛ ቅፅበታት ውስጥ ህልውናችሁን ታውቃላችሁ ። ንቁ የምትሆኑት ይህንን በመሰሉ ቅፅበታት ውስጥ ብቻ ነው ።

ተጨማሪ ምሳሌ ልስጣችሁ...

ይቀጥላል...

@Ebdusocratus
@wegoch
@Wegoch
ለውብ ቀን
💚
ፍቅር ማለት ራስን በሌላ ሰው ማንነት ውስጥ ማግኘት ማለት ነው!


የስነ ልቦና ጠበብት እንደሚሉን እኛም እንደተረዳነው ኦክስጅን ለሰውነታችን
የሚያስፈልገውን ያህል ፍቅር ደግሞ ለአዕምሯችን ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን እውነት ሊቀይር
የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡

ፍቅርን በአግባቡ ባጣጣምነው ቁጥር አካላችን አልፎ ተርፎም ስሜታችን የበለጠ
ጤነኛነት ይሰማዋል። በተቃራኒው ደግሞ ከፍቅር በሸሸን ቁጥር መረጋጋት ይሳነናል፡፡


ፍቅርን የማያውቁም ሆነ በፍቅር ህይወታቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች በህይወታቸው
ድብርት፣ ብስጭት ሲጫጫናቸው የመመልከት አጋጣሚው ሰፊ ነው፡፡
የብዙ ሰዎች ድብርት ዋነኛው መንስኤ ፍቅር ማጣት ነው። ስለዚህ በፍቅር መኖሩ ነው
ለህይወት መልካም ግብ አንዳንድ ምሁራንም ፍቅርን ሲገልፁ፦

ጨለማን ጨለማ አያጠፋውም!
ጨለማን ማጥፋት የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው!


ጥላቻንም ጥላቻ አያጠፋውም ጥላቻን ማጥፋት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።


ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም፤ ውይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ
አልተወለደም፤ ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው።


የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ፤ ፍቅርንም መማር ይችላል፤ እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ
ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው።
ፍቅር ግን ፈውስ ነው!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ዛሬ ማክሰኞ /2/2011. ምሽት 11:00 ፮ ኛው እንድቅትዮን የሥነ ፅሁፍ ምሽት እንቁላል ፍብሪካ ከእምቢልታ ሆቴል ገባ ብሎ በሚገኘው በ ገንት መናፈሻ ይጠብቁን!!

@getem
@getem
@getem
2024/09/28 03:22:39
Back to Top
HTML Embed Code: