Telegram Web Link
ለውብ ቀን
💚
ውጤቱ ምንም ይሁን እውነት ለመናገር አትፍራ ብቻህንም ብትሆን ሁልጊዜም ለራስህ
እውነተኛ ሁን ።
ሰዎች ካንተ የሚጠብቁትን ሳይሆን ልብህ የሚያቀውን እውነት ተከተል
ምናልባት የእውነት መጀመሪያ መሪር ሊሆን ይችላል
ነገር ግን በመጨረሻ እውነት ነጻ ያወጣሃል
መፅሀፉም እንደሚለው "ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው”
አበው አባባል ደግሞ " ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል"


ሸጋ ቀን ይሁንልን!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ፍቺ
(ቡሩክ ካሳሁን)

ወደ ቢሮዬ በሩን ከፍቼ ልገባ ቁልፌን አውጥቼ ብሞክር በሩ ክፍት ነው፡፡ ሌባ ነው መቼስ በዚ ጠዋት እያልኩ ቀስ ብዬ ስገባ ፀሐፊዬ ያለወትሮዋ በጠዋት ገብታ አገኘዋት፤‹ምነው ያስቀየምኩሽ ነገር አለ እንዴ? በጠዋት መጣሽ› አልኳት፤ እርሷ ግን በደማቅ ፈገግታ ተቀበለችኝ፡፡ ኦኬ ዛሬ ቀኑ ሰላሳ መሆኑን አወኩኝ፡፡ ‹ሰላም የባለጉዳይ ወረቀቶችን እንደ ቅደም ተከተላቸው አምጪልኝ› ብያት ገባሁ፡፡ የወረቀት ናዳ ፊቴ አምጥታ ቆለለችው፡፡ ከላይ ያለውን አነሳው ጉዳዩ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ደንበኛዬ ከባለቤቷ መፋታት ትፈልጋለች ባልየው ግን የሙጥኝ ብሏል እኔም እንደጠበቃ ብችል ባልየውን ካልቻልኩ ዳኛውን አግባብቼ ላፋታቸው ቆርጬ ተነሳው፡፡ በቅድሚያ ባለቤትየውን አናገርኩት፤ ባልየው መፋታት አይፈልግም ችክ ያለ ሰውዬ ነው እንደውም ችክ ከማለቱ የተነሳ አንዴ ተሳስቶ የተናገረውን ቃል እራሱ እንደ እዝጌር ቃል ሰማይና ምድር ይለፉ እንጂ አልቀይርም የሚል አይነት ሰው ነው፡፡ ደውዬ የሚስቱ ጠበቃ እንደሆንኩና ስለፍቺው ጉዳይ ላነጋግረው እንደምፈልግ ነገርኩት ‹ስለምን ፊቺ ነው ምታወራው?› በስልኩ አንባረቀብኝ፤ እሱን ተገናኝተን ብናወራ አይሻልም ብዬ አንድ ካፌ ቀጠርኩትና ተገናኘን፡፡
‹ሰላም አቶ ኩራባቸው?›
‹ነኝ›
አስተናጋጇ መጣች ‹ምን ልታዘዝ› ብላ ወደኛ አቀረቀረች
‹ለኔ ግማሽ ሊትር ውሀ አምቺልኝ› አልኳት
ኩራባቸውም ‹ለኔ ወተት በሻይ አምቺልኝ› አለ ካነጋገሩ ወተት በቡና ለማለት እንደፈለገ ያስታውቃል ብቻ ደረቅ ነው አላልኳችሁም በቃ ደረቀ፡፡ አስተናጋጇ ተገርማ ደግማ ብትጠይቀውም ጋሽ ኩሬ ‹ባንገቴ ቢላዋ ወተት በሻይ› አለ እኔም መጥቶለት ሲጠጣው ለማየት ቴዲ አፍሮ አልበም ሊያወጣ ነው እንደተባለ ሰው በጉጉት መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡
‹እሺ ወደጉዳያችን ስንገባ ጠበቃ ምንተስኖት እባላለው የወ/ሮ ሰብለ ጠበቃ ነኝ እና ወ/ሮ ሰብለ ፍቺ መፈፀም ትፈልጋለች› አላስጨረሰኝም
‹እኔ አልፈልግማ›
‹ጥሩ ነው ግን የሷ ፍላጎትን መጠበቅ ነው የኔ ስራ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፀም በማለት ቀድሜ ላናግርህ ፈለኩ›
እስተናጋጇ ለኔ ውሀዬን ለሱ ደሞ ሻይና ወተት አምጥታለት ወተት በሻይ ያወራርድ ጀመር (ጉጉቴ ወጣልኝ)
አስተናጋጇ ዞር እልዳለች
‹ፍቺ ብሎ የምን ሰላማዊ ነው ምታወራው እኔኮ ሰብሊን ልፈታት አልፈልግም ያለ እሷ መኖር አልችልም›
‹ተው እንደሱ አይባልም አንተ ከሷ ውጪ አደል እንዴ የተወለድከው ስለዚህ ከሷ ውጪ ትኖራለህ ማለት ነው፡፡ ደሞ ጥሩ መልክና ቁመና አለህ ወላድ በድባብ ትሂድ ይሄ ቀረሽ ማትባል ሴት ታገባለህ ለምን ችክ ትላለህ፡፡ (በሆዴ አቤት መቼም ነፍሴ አይማርም ይሄን የመሰለ ሰው ለእንጀራዬ ብዬ መልከህ ቁመናህ እላለው ይሄ ዝንጀሮ አልኩኝ)
‹አንተ ማታውቀው ብዙ ነገር አለ እሷ ማለት ለኔ የህይወቴ መነሻ እና መድረሻ ናት እኔና እሷን ማንም አይለየንም ከሷ ከምለይ ሀገር አቃጥላለው›
ይህን ጊዜ ብልጭ አለብኝ ‹ሀገር አቃጥላለው ላልከው አታስብ በውሀ ጥም ተቃጥሎ የሰለጠነ በቂ ፌደራል ያላት ሀገር ውስጥ ስለምትኖር ሞክረውና በአግባቡ ራሱ ክብሪት መጫር እንዳትችል ነው ሚያረጉህ፤ ማንም አይለየንም ላልከው ደግሞ ፍርድ ቤት ሚባል የህግ አካል አለ ጥሩ አድርጎ የተቀላጠፈ አገልግሎት የሚሰጥህ በሀሳቤ ማትስማማ ከሆነ የህግ አካላትን በመዘንጋት ብዬ ራሱ ዘብጥያ ላወርድህ እችላለሁ›
‹ጭራሽ ልታስፈራራኝ ነው እንዴ የመጣኸው በቃ እንደውም አ.ል.ፈ.ታ.ት.ም!!! ከሰብልዬ ጋ አልፋታም አራት ነጥብ›
‹ተው አንተ እንደዚ ችክ ብለህ ሰብልዬ ሰብልዬ አትበልብኝ በዛብህም መጨረሻው ያላማረው እንደዚ ችክ ብሎ ሰብልዬ ሰብልዬ ሲል ነው አንተ እንቢ ብትልምኮ ፍቺው አይቀርም ልፋ ቢልህ ነው እንጂ›
‹ነው እና ለምን መጣህ ዳግመኛ እንዳታገኘኝ›
ብሎኝ ተነስቶ ሊፈረጥጥ ሲል ቀኝ እጁን ግጥም አርጌ ‹እና ባለ ካፌዎቹን እግዜር ይስጥልኝ ብለካቸው ልትወጣ ነው?! እዚ ካፌ ያስከፍላሉ ሂሳቧን› አልኩት፡፡ እጄን ከእጁ ላይ መንጭቆ ካስለቀቀ በኋላ የነተበች 100 ብር ጠረጴዛው ላይ ወርውሮ ሄደ፡፡ ‹ኸረ የበረረ መኪና ይብላክ› አለኩኝ በሽቄ፡፡
ይሄ ሰውዬ 50 ብር ለማይሞላ አገልግሎት 100 ብር መክፈሉ ንብረት ክፍፍሉን አስቀድሞ ሀብት ማውደም ላይ እንዳለ ተረዳሁ፡፡ ተነስቼ ልወጣ አልኩና ጡር ፈርቼ ካስተናጋጇ መልስ ተቀብየ ወጣሁ፡፡
አይደርስ ነገር የለም የቀጠሮ ቀን ደረሰ እና ፍርድ ቤት ቆምን፡፡ እሰጥ አገባውም ባጭሩ ይሄንን ይመስላል

ዳኛ ‹በቀረበው የፍቺ ሃሳብ ባለቤት ትስማማለህ›
ኩራባቸው ‹በፍፁም አልስማማም ክቡር ፍርድ ቤት እኔ ከሰብለጋ እስከ…› እያለ ፉፋውን ሊነፋ ሲል ዳኛው መች አስጨርሰውት
‹ይበቃል የአመልካች ጠበቃ የምትለው ነገር አለ› አሉ ዳኛው
‹አንጀቴን ነው ያራሱት ክቡር ዳኛ› ልል ካሰብኩ በኋላ ፍርድ ቤት መሆኑ ሲታወሰኝ እንደመባነን ብዬ ‹እኔ ክቡር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ባለቤትየው በዚህ ሃሳብ ቢስማማ ነበር የሚገርመው ሲጀመር እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድ ነገር ላይ መስማማት ቢችሉ ቀድሞዎኑ ፍቺ ለምን አስፈለገ? አንዳቸው ለአንዳቸው ግልብጥ ናቸው፡፡ ተቃርኖ ይቀናቸዋል፤ ይገርሞታል የቤት ሰራተኛቸው የነሱን ዘውድና ጎፈርነት ለማቻቻል ወጥ በስኳርና ወጥ በጨው መስራት ነው የቀራት፡፡ በስተቀኝ ያሉት ጎረቤታቸው እትየ አስካል በነሱ እረፍት የለሽ ጭቅጭቅ የተነሳ የእድሜ ልክ የጆሮ በሽተኛ ሆነዋል፤ በስተ ግራ ያሉት ጋሽ ዱለቻ ነጋ ጠባ ሲጨቃጨቁ ‹ምነው የአስካልን ጆሮ በሰጠኝ› እያሉ ፈጣሪን መለመን ጀምረዋል፡፡ ለነዚህ ሰዎች ፍቺ ማለት ሰርግ እንደማለት ነው፡፡ እንደውም አልፋታም ብሎ ከመቃወም ደግሰው ነበር መፋታት የነበረባቸው፡፡ አመሰግናለሁ ክቡር ፍርድ ቤት፡፡
ኩራባቸው ‹የምናገረው አለኝ ክቡር ፍርድ ቤት›
ዳኛ ‹ቀጥል›
ኩራባቸው ‹እኔ ሚስቴን በጣም ነው የምወዳት ከመንከባከብ ያለፈ አንዳች ነገር አጉድዬባት አላውቅም…›
‹ሌላ ሚስት ካለህ ነው እንጂ…› ሰብልዬ አላስጨረሰችውም አቋርጣው ገባች ‹ሌላ ሚስት ካለህ ነው እንጂ አሁን ያልከው በሙሉ ከኔጋ እንዳልሆነ መቼም ይሄ ድንጋይ ልብክ ያውቀዋል…›
ባልና ሚስቱ ጭቅጭቃቸውን ጀመሩ፡፡ ፍርድ ቤቱ ገበያ ሆነ፡፡ ዳኛው በመዶሻቸው ጠረጴዛውን ነድለው ነድለው እንዳልነበር አደረጉት፤ ዳሩ ማን ሰምቷቸው ያ ደረቅ ሰውዬ ድርቅ ብሎ ይጨቃጨቃል፡፡ ተዉ ቢባሉ ቢሰሩ አቃቱ ያን ግዜ ዳኛው ‹ምነው የእትየ አስካልን ጆሮ በሰጠኝ› ብለው አረፉት፡፡


ሰኔ 2009 ዓ.ም
@wegoch
@wegoch
@burukassahunc
ለውብ ቀን
💚
ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል!
ዴል ካርኒጌ
ፈገግታችን የስሜታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ በሰዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖም አንዘንጋ፡፡
ብሩህ ፈገግታ፣ እወድሃለሁ፣ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል የሚሉትን ቃላት ይወክላል፡፡
እያሻሸነው ፍቅራችንን የምናሳየው ውሻችን ሳይቀር ከሩቅ ሲመለከተን ጭራውን እያወዛወዘ
የሚሆነውን የሚያሳጣው ለምን ይመስላችኋል?
የህፃን ፈገግታም ከልብ የመነጨ ስለሆን መሰል ተፅዕኖ አለው።
አዎ! በካርኒጌ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል።
---------------------------------------------

ሳቅና ፈገግታ ሰደቃ ነው ብለው
ነግረውኝ ሼሆቼ ስንቱን ቀን ሰደኩት
በውብ ሳቅ ሸኝቼ!!!

ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለቅዳሚታችን
💚
ለውብ ቀን
ከሁሉም በላይ ራሳችሁን አትዋሹ ራሱን የሚያዋሽና ውሸቱን የሚያደምጥ ሰው
በዙሪያውና በውስጡ ያለውን..እውነት እንኩዋን ማክበር አይችልም::
በዚህም ለራሱም ሆነ ለሌሎች ያለውን አክብሮትያጣልእናም
ክብር-የለሽ ከሆነ ማፍቀርም ያቆማል።
ዶስቶቭስኪ

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
የአንድ እቃ ወይም ጉዳይ ዋጋ የሚለካው፣ በእቃው ወይም በጉዳዩ ሳይሆን፣ እቃው ወይም ጉዳዩ ባረፈበት ሰው ማንነት ነው።

ከዮቶር መፅሐፍ የተወሰደ

👉👉@temuabiy👈👈
👉👉@temubiy👈👈
👉👉@temuabiy👈👈
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7 እነሆ የተለያዩ ጉዳዮችን አካታ ለንባብ በቅታለች!
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7.pdf
3.5 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰
ለውብ ቀን
💚
በዓለም ውስጥ ደስታም ሆነ ውድቀት የለም!
አንድ ንጽጽር ብቻ ነው ያለው በአንተ ውስጥ ደስታም ወድቀት ወይም ሀዘን ብለህ
የምታነፃፅረው። እና ሌላ ምንም ነገር የለም!
በጣም የሚያስጨንቅ ሰው ከፍተኛ ስሜት ሊኖረው ይችላል.። ይህን ስታነፃፅን የሚመጣ
ስሜት እንጅ ሌላ ምንም የለም።
እምነት ሲኖርህ ግን አምላክ በሁለት ቃላቶች ደስታን እና ፍሰሀን ብሩህነትን ይሰጠሀል በ"
ቃል ኪዳን እና ተስፋ "

ውብ ቀን

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
ከአልሙስጠፋን ተከታዩ ሳርኪስ እንዲህ ሲል ጠየቀው:- አስቀያሚነት ምንድን ነው፤ መምህር
፤ ስለ አስቀያሚነት ስትናገር አልሰማንህም።
አልመስጠፋ መናገር ሲጀምር ቃላቱ እንደ አለንጋ ይጋረፍ ነበር፦
አንድ ሰው በርህን ሳያንኳኳ በአጥርህ አልፎ ስለሄደ ብቻ እንዴት ለእንግዳ አይመችም ብሎ
ያማሀል? ፈፅሞ በማታውቀው እንግዳ ቋንቋ ያናገረህ ሰውስ እንዴት ደንቆሮ ነው
አያስተውልም ብሎ ሊናገርህ ይችላል?
እንደዚሁ ሁሉ ፈፅሞ ልትገባበት ያላሰብከውን የአንድ ሰው ልብ ከውጭ ሆነህ እንዴት
አስቀያሚ ነው ማለት ትችላለህ?
አስቀያሚነት የምንለው የዐይናችን የተንሸዋረረ መለኪያነትና ጆሮአችንን የደፈነውን ኩክ
እንጂ ሌላ አይደለም!!!

ወዳጄ የራሷን ትውስታ ለማየት ከምትፈራ ነብስ በቀር ማንንም ነገር አስቀያሚ አትበል!!!!!

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ዛሬ በአሜሪካ የነበረኝ ውሎ …
(አሌክስ አብረሃም)

ርእሱ ትንሽ ጉራ ያለበት ይመስላል አይደል? ….ደግ አደረኩ ! ዛሬ ጁላይ ፎርዝ ነው የአሜሪካ የነፃነት መታሰቢያ በዓል …አሁን ራሱ ይሄን እየፃፍኩ የርችቱ ድምፅ አሜሪካ ሳይሆን ሶሪያ ያለሁ እስኪመስለኝ ያሸብረኛል ….ስራ የለ ትምህርት የለ በቃ ዘና ነው …መዝናናትን ፈረንጅ ይዝናና …ብር ነው አለ …ይሉኝታ ነው የለም ! ብር ካለህና ይሉኝታ ከሌለህ አለም አስር ነው! እኛ አበሾች ብሩ ሲኖር ይሉኝታ ቀፍድዶ እየያዘን መች እንዝናናለን …..(የፈረደበት ሶደሬ እንኳን ከምትወዳት ልጅ ጋር ሂደህ ከመሳሳምህ በፊት 360 ድግሪ ቸክ ማድረግ አለብህ!) ታዲያ ወደከተማው ዋና ክፍል (ዳውን ታውን ይሉታል )…ተያይዘን ሄድን ከተማው አብዷል …እዚህና እዛ ባንዲራ ነው …መጠጥ ነው …ዳንስ ነው …መሳሳም ነው … በተለይ ሴቶቹማ ሌላ ነገር ነው የሚያደርጋቸው …(ሴቶቹን ምን አሳየህ የሚል ይኖራል ጥሩ ጥያቄ ነው …ተሳስተው እንዳይስሙኝ ራሴን ለመጠበቅ ነው
)
ያልተለበሰ አይነት አለባበስ የለም …ጎራዴ ሁሉ የታጠቀ ፈረንጅ አየሁ …ባጠገቤ ቀዥለል ቅዥለል ሲል ‹‹ገብርየ ቀስ›› አልኩ በልቤ ! የድሮ ረዥም ቁመህ ጠብቀኝ ጠብመንጃ (የእውነት ይሁን አይሁን እንጃ) ይዞ የሚንጎማለል ነፍጠኛ ፈረንጅም አጋጥሞኛል ….እንደአሊ ባስትኒ ከበሮ እየደለቀ የሚዞር ጢማም የቴክሳስ ሰውም አጋጥሞኛል ….የእነሱ የፀሃይ ወቅት እየገባ ስለሆነ በዚህ ሰዓት በተለይ ሴቶቹን(ምናባቴ ይሻለዋል ይሄ ዓይኔ) እምየ ማሪያም የት ላይ እንደሳመቻቸው ሁሉ ጠጋ ብሎ ማየት ይቻላል ….ሁሉ በግልጥ ነው !!
ግልፅነትና ተጠያቂነት በአሜሪካ አለ …ሲሏችሁ ቅኔ ነው ወዳገር ቤት ለማምጣት መንገድ በመዝጋትና ድንጋይ በመወርወር መንግስትን አታስቸግሩ ….ግልገል ሱሪና የሆነች እራፊ የለበሰች ሴት እስከጆሮ ግንዷ ፈገግ ትልልሃለች ግልፅነት ይባላል ጥግብ እስከምትል ማየት ትችላለህ እቤትህ ለማየት ሁሉ ፎቶ ማንሳትም ትችላለህ ….ፈገግ አለችልኝ ብለህ ጫፏን ብትነካ ተጠያቂነት እንደምርጊት ይጫነሃል ! ይሄው ነው ሒሳቡ !
ምን ላይ ነበርኩ ….አዎ ታዲያ እንዲህ እየተደሰትን አለ አይደል በዓሉ የኛ እንዲመስለን ‹‹አድዋ ነህ ብለናል አደዋ ነህ ›› እያልን ስንዞር አንዲት ክንፍ ብቻ የጎደላት መለዓክ የምትመስል ሴት በነገርኳችሁ አለባበስ ፊቴ ተገተረች …‹‹አንተ ክፉ ከኔ ራቅ›› ብየ አማተብኩ …እሷ ግን የበለጠ ቀረበችኝ(በዚህ ሁኔታ ፀሎቴ ባለመስመሩ እግዜርን አልተቀየምኩትም) በደረቷ ልክ እንደቤተክርስቲያን ሙዳየ ምፀዋት አይነት ትንሽ የጣውላ ሳጥን ነገር አንጠልጥላለች ….በውስጤ ‹‹እዚህም አገር ለአገራቸው ዋጋ ከፍለው የተቸገሩ አርበኞች ይኖሩ ይሆን እንዴ ለነሱ ገንዘብ እያሰባሰቡ ሆናል ››አልኩ …ልጅቱ ግን ቀልጠፍ ብላ
‹‹ በናይጀሪያ በከተሞች መስፋፋት ምክንያት ጫካዎች በመመናመናቸው ዘሩ ሊጠፋ የተቃረበ ‹ካርቶፒ ምናምን› የሚባል የጫካ ሸረሪት ዘር ለመታደግ ገንዘብ እያሰባሰብን ነው ከቻሉ ይርዱን ›› ብላኝ እርፍ ….የሽረሪቱ ፎቶ የታተመበት ወረቀት ሁሉ ሰጠችኝ …እኔ እቤቴ ባገኘው በመጥረጊያ ወላ በጫማ ነበር ….ናይጀሪያ የሚገኝ ጫካው የተመነጠረበት ሸረሪት ለመታደግ ሆሆ . . .
ሃሳቤ ተንደርድሮ አገሬ ላይ አረፈ …በዚህ ክረምት ቤታቸው ፈርሶ ልጆቻቸውን ይዘው በየመጠለያው ያሉ እናቶች …አቅመ ደካሞች …አማራ ክልል …ሱማሌ …ጌዲዮ …ኦሮሚያ …ከዳር እስከዳር …አለም ለሸረሪት ነብስ ሁሉ የሚጨነቁ ሰዎች አላት አገሬ ግን …..ሃሳቤ አይቆምም በዚች ሰዓት …የመን ሶሪያ ሊቢያና ብዙ ብዙ ቦታ ያሉ ነብሶች ሁሉ …. ናይጀሪያ ራሱ ቦኮሃራም ፍዳቸውን የሚያበላቸው ድህነት ያስመረራቸው ስንት ሚሊየን ህፃናት ይኖሩ ይሆን … ይሄን እያሰብኩ አንዲት ፊቷ በፀሃይ አለርጅክ የተዥጎረጎረ ነጭ ፈገግ ብላልኝ አለፈች ….ሸረሪት ሸንቶባት ይሆናል አልኩ በሃሳቤ ! ዝም ብሎ የናይጀሪያው ሸረሪት አበሳጭቶኛል!

@Wegoch
@Wegoch
መርታት፤ መረታት፤ መገገም
(በእውቀቱ ስዩም)

የሆነ ጊዜ ላይ ረከቦት ጎዳና፤ ባንዱ ካፌ ውስጥ፤ ቡን ስጠጣ፤አንድ ጎረምሳ ወደ ተቀመጥኩበት መጣ፤ልጁ ግድንግድ ነው፤ጎልያድ ዳዊትን አዝሎ ያክላል፤ እኔ ደሞ እንደምታውቁኝ ነኝ፤ከፊቴ ሲቀመጥ የሚጥሚጣ ብልቃጥ አከልኩ፤ ግብዳው ብዙ ሳይቆይ የምነት ክርክር ጀመረ፤በተቻለኝ መጠን ወደ ክርክሩ ላለመግባት ተግደረደርኩ፤ ሰውየው ግን አልከራከርም ብለው ንቀኸኝ ነው ብሎ ሊደበድበኝ ይችላል፤ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ የነደደ ክርክር ውስጥ ራሴን አገኘሁት፤ሰውየው አረፋ እየደፈቀ ተተጋተገኝ፤
ጎረርህ በሉኝ ብትፈልጉ ! አስር ቀቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልጁን መፈናፈኛ አሳጣሁት፤ መግብዳው ክርክክራችንን ያሳረገው እንዲግ በሚል ቃል ነው፤
"‘ ልታሳምነኝ አትድከም ! እገግምብሃለሁ”
አሁን ሳስበው፤ አስተምረዋለሁ ያልሁት ያ ግብዳ ሰውየ ትልቅ ቁምነገር አስተምሮኛል ፤ ባፍለኝነቴ ፤የሰው ልጆች ለሀቅ እና ለምክንያታዊነት የሚኖሩና የሚሞቱ ይመስለኝ ነበር፤ሰዎች በውይይት የሚያምኑ ይመስለኝ ነበር፤ አዋቂ ባላዋቂ ላይ የሚበረታ፤፤ እውነት የያዘ ሰው ሀሰተኛውን የሚረታ ይመስለኝ ነበር፤ እየኖርኩ ስሄድ ይሄ እምነቴ ጥሎኝ ሲመንን ታዘብኩት፤ አብዛኛው ሰው ለውነት ደንታ የለውም፤ አብዛኛው ሰው፤ ስለ እውቀት ስለተጨባጭ መረጃ ግድ አይሰጠውም፤ በተፈጥሮ ይሁን በልማድ እንጃ፤ አብዛኛው ሰው ችኮ መንቻኮ ነው፤ ልብ አድርቅ ነው፤ የውይይት አላማ ከላይ ከላይ የእውቀት ልውውጥ ቢመስልም ውስጥ ውስጡን መሸናነፍ ነው ፤ሽንፈት መራራ ፍሬ በሚያስለቅምበት አገር ውስጥ ደሞ፤ ማንም መሸነፍ አይፈቅድም፤ ብታሸንፈው ተሸነፍኩ አይልህም፤ ተዘርሮም ይፎክርብሃል! ይገግምብሃል!
ቀኛማች በላይነህ የተባሉ ባላባት በዳግማይ ምኒልክ ጊዜ ነበሩ፤በዘመናቸው፤ ከስራቸው ጋራ የማይመጣጠን አንጀባ ስለሚያበዙ " ቁንን በላይነህ" የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቱዋቸው ነበር፤የሆነ ጊዜ ላይ ከሸገር ወደ ጎንደር ይሄዱና ባንድ ደብር ውስጥ ይስተናገዳሉ፤ቁንን በላይነህ ፊደል ያልቆጠሩ ጨዋ ቢሆኑም በሊቃውንቱ ፊት የተማሩ ለምምሰል ተጋጋጡ፤ ዳዊት እየደገምኩ ነው ለማለት ዳዊት ገለጡ፤ ግን የማያውቁትን ዳዊት ገልብጠውት ነበር የያዙት፤
ይህንን የሾፈ አንድ ደብተራ ሳቁን በጋቢው ለመጨቆን እየሞከረ፤
“ጌቶች ዳዊቱን ዘቅዝቀው ነው የያዙት” ቢላቸው፤
))“ጠላቴን እንዲዘቀዝቅልኝ ብየ ነው! ጠፍቶኝ እንዳይመስልህ ” አሉት ይባላል፤
ቁንን በላይነህ አላዋቂ ናቸው፤ግን አላዋቂነታቸውን አምነው ማረም አይፈልጉም፤ ማንን ደሰ ይበለው ብለው!?ተሸንፈው፤አሸናፊ መስለው ቆመዋል! ገግመዋል!
ታዋቂው የታሪክ ፀሀፊ ተክለፃድቅ መኩርያ በግለታሪካቸው ላይ አንዲት ገጠመኝ ጠቅሰዋል፤ ገጠመኚቱን በኔ አማርኛ ሸክሽኬ ሳቀርባት ይቺን ትመስላለች፤ የሃይለስላሴ ባለስልጣኖች በደርግ ወጣት መኮንኖች እየተለቀሙ በሚታጎሩበት ቀውጢ ወቅት ፤ ሁለት ወጣት ታጣቂዎች ተክለፃድቅ ቤት ድረስ ይመጡና በቁጥጥር ስር ያውሉዋቸዋል፤ በገዛ መኪናቸው፤ይዘዋቸው በሚሄዱበት ጊዜ አንዱ ታጣቂ ለጉዋደኛው_-_
“ከተማ ይፍሩ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት አስር ሚሊዮን ብር በኪሱ ተገኘ” ይላል፤(ከተማ ይፍሩ የዘመኑ ባለስልጣን ነው)
“ይሄን የሚያክል ገንዘብ በኪስ ሊያዝ አይችልም” አሉ ተማራኪው ተክለፃድቅ፤
“ባይኔ በብረቱ ያየሁትን” አለ ወታደሩ፤
“ይህን ጊዜ” ይላሉ ተክለፃድቅ መኩርያ “ ይህን ጊዜ ዝም አልኩ፤”
ዝም ባይሉ ኖሮስ?
ታጣቂው ይገግማል!
ጠመንጃውም ያስገመግማል፤
አስከሬን ይለቀማል
እና ይሄ ማን ይጠቀማል?
አንዳንዴ በፌስቡክ ማለቂያ አልባ ክርክር ውስጥ ዘልየ ለመግባት ሲቃጣኝ እኒህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤አንዳንዴ ዝም አልክ ማለት እውነቱን ከመናገር ተቆጠብክ ማለት አይደለም፤ሃይልህን ቆጠብክ፤ሰላምህን ቆጠብክ፤ ህይወትህን ቆጠብክ ማለት ነው፤

@Wegoch
@Wegoch
#ጥንዶቹ_ለሰርጋቸዉ ቀን ያዘጋጁት #የጥሪ_ካርድ ማተሚያ ቤቱ ትልቅ ስህተት እንደሰራ ያወቁት ሁሉም ካርዶች ለተጋባዦች ተበትኖ ካለቀ በኋላ ነበር!

ማተሚያ ቤቱ እንዲያትም የተሰጠዉ ጥቅስ 1ኛ ዮሐ 4:18 ላይ ያለዉን ቢሆንም '1ኛ' የሚለዉን በመርሳታቸዉ ያተመዉ ዮሐ 4:18 ላይ ያለዉን ነበር። (1ኛ የምትለዋ በመረሳቷ መፅሐፉ ከ1ኛ የዮሐንስ መልዕክትነት ወደ የዮሐንስ ወንጌል ተቀየረ ማለት ነዉ።)

እንዲታተም የተፈለገዉ 1ኛ ዮሐንስ 4:18
"በፍቅር ፍርሃት የለም ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አዉጥቶ ይጥላል.. " ይላል

ማተሚያ ቤቱ ያተመዉ ዮሐንስ ወንጌል 4:18
"አምስት ባሎች ነበሩሽ አሁን ካንቺ ጋር ያለዉም ባልሽ አይደለም..." ይላል!
💍 💍 💍

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን
💚
ጊዜ የሚባል ነገር የለም!
ያለፈውን እና የወደፊቱን አታያውቁም ሁልጊዜም ሁሌም ነው!

ኤካርት ውስብስብ ጽንሰ-ሐሳቦችን በተጠና የቋንቋ ማብራራት የሚችለው የአብርሆት
መምህር ነው እላለሁ።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህንን የአሁንነትን ሀይል" መጽሐፍ በማንበብ አንድ ምዕራፍ
ውስጥ አንባቢዎች ዓለምን በተለየ እይታና በእውቀት ሰላምና ደስታ ውስጥ የመኖር
ችሎታን ያስገነዝባል።

ስለአሁን እና ስለወደፊቱ ማሰብ ካቆማችሁ እና በ አሁንነት ውስጥ ካላችሁ ጥሩ ስሜት
እንዲሰማችሁ ታደርጋላቹህ።

አሁን ያለህን ጥልቅ ስሜት ተገንዘብ አሁን ህይወትዎ ትልቅ ትኩረት ስጡ አሁን
በሚኖሩበት ቦታ እና አሁኑኑ የሚያጋጥሙትን ተፅእኖዎች ለመቋቋም በሚያስችልዎት ጊዜ
ውስጥ ነህና አሁን ያለዎትን ጥልቅ ስሜት ይገንዘቡ።

ኤካርት ሰዎች በየቀኑ በዕለታዊ ኑሯቸው እንዴት ማሰብ እንደሚጀምሩ በመፅሀፉ ይናገራል።

አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት ለሚደርጉት ነገር በፍርሀት ወይም በተስፉ ይጠብቃሉ።
ይሄ ግን ይላል ኤካርት "ራስን በራስህ ላይ መጣበቅ" ወይም ሙሉ በሙሉ "ምክንያታዊ"
በሆነ አዕምሮ ሁኔታ ውስጥ መውደቅ ነው።

እነሱ ሙሉ ጊዜውን ከመቀበል ይልቅ ወደፊቱ ለማሰብ ይፈልጋሉ። አሁንነትን ይዘነጋሉ።

ከአሁንነት ውጭ ስትሆን እርጋታን ታጣለህ ብስጭት የጥፋተኝነት ስሜት፣ ሀዘን፣ ድብርት፣
ቁጣ፣ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ወዘተ የመሳሰሉት አሉታዊ ስሜቶች ይከሰታሉ።

እንደ ኤክሃርት ሀሳብ አዕምሮዎቻችን ዋነኛው ጠላታችን ነው እና በአዕምሮ እና በነፍስ
መካከል ልዩነት ያደርገዋል።

አዕምሮችን ዋነኛው ጠላታችን ነው! በአዕምሮ እና በነፍስ መካከል ልዩነት እንዲፈጠር
ያደርጋል።

ማሰብ ማቆም አለመቻል አስደንጋጭ ነገር ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው እየተሰቃየ ስለሆነ
ይህንን አናውቀውም። ስለዚህ እንደ የተለመደ ነገር ይቆጠራል።

የአሁንነት ኃይልን ካነበብኩ በኃላ ዘመናዊው የሰው ልጅ በአደገኛ በሽታዎች እየተሰቃየ
እንደሆነ ተረዳሁ
አሁን ለእኔ በጣም ግልጽ ነው! በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በጭንቀት በመንፈስ ጭንቀት
እና በመሳሰሉት ችግሮች ይሠቃያሉ?
በእኛ ተጨባጭ እና በሚንቀሳቀሱ አስተሳሰቦች ላይ ስንመጣ በሰላም
እንኖራለን።

የሚያሳዝነው ብዙ ሰዎች እንዴት አሁንነት ላይ እንደሚያቆሙ አያውቁም።

በመጽሐፉ ላይ እንደሚነግረን የሚያስጨንቁ ሐሳቦችን ለማሸነፍ የመጀመሪያው እርምጃ
አዕምሮዎን እንዲመለከት ወይም እንድንረዳ ማድረግ ነው።


እናም የአሁንነት ሀይል መፅሀፍ ስታነብ ከምትረዳቸው ነገሮች ባሻገር ኑሮህን እንዴት
ጤናማና ደስተኛ ኑሮ መኖር እንደሚቻል ያሳያል።

"ሁሉም አሉታዊነት የሚመነጩት በአይምሮአዊ ግኝት እና የአሁንነትን በመከልከል ነው."
የዛሬው ሁኔታ ምንም ይሁን ምን! እንደመረጡት አድርገው ተቀብሉት።

ይቀጥላል……………


የተገማሸረ ውብ ቅዳሜ ይሁንልን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለሰንበቲታችሁ
💚
እግዚአብሔር መልካም ሆኖ በሰጠን ጊዜ ውስጥ እኛም መልካም እንሁን!
እግዚአብሔር እኛ እንድናውቀው የሚሻ የፍጥረተ ዓለም ፈጣሪ ነው፡፡ እኛ ሁላችን በዚህ
ያለነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የእርሱን ብርታት፣ ፍቅር፣ ፍትህ፣ ቅድስናና ርህሩኅነት
እንድንለማመድና በእርሱም እንድንታመን የእርሱ የመሻት መልካምነት ነው።


ይህንን ሁሉ መልካምነት ሸቶልናል አምላክ እግዚአብሔር ደግ ሆኖ በሰጠን ህይወት
ውስጥ ደግ እንሁን!


እግዚአብሔር ፍቅር ሆኖ በሰጠን ፍቅር እኛም እንዋደድበት!
እግዚአብሔር ለሚጠሩት፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፣የሚፈሩትንም ከመልካም
ነገር አያጎድላቸውም የልባቸውን መሻት ይፈጽምላቸዋል)ጩኸታቸውን ይሰማል
ያድናቸዋልም"(መዝ 145፡18-19)
ራሳችንን በደግነት በመልካምነት በቅንነትና በፍቅር ራሳችንን እንስጥ።

"እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በመከራም ቀን መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም
ያውቃል"(ናሆ 1:7
ፍቅርም ያብዛልን
መልካም ዕለተ ሰንበት

(( ጆኒ,)))💚💛

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/27 23:18:48
Back to Top
HTML Embed Code: