Telegram Web Link
ዛሬ በብሄራዊ ትያትር የተከፈተ የስእል ኤግዚቢሽን ነው። ሰአሊው አወቀ ይባላል...እውነት እውነት እላቹሃለው ስምን መላእክት ያወጣዋል...እሱ ጋር በልኩ ተሰፍቶ ልክክ ብሎ ጠልቋአል.....!!

ስእል የጥበብ ቁንጮ ነች!!!!!

ዛሬ እኔ አረጋገጥኩኝ ....እያጋነንኩኝ ከመሰላቹ ምንም እንደውም አላልኩም......ገብታቹ አረጋግጡ እጃቹን በአፍ የሚያሲዝ ጥበብ ተመልክታቹ ትመለሳላቹ!!

መግቢያው በነፃ ነው.......በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር አርት ጋለሪ 14 ቀን የሚቆይ......የምትችሉ ነገ የረፍት ቀን ስለሆነ ከወዳጃቹ ጋር ጎራ በሉና ተደመሙ!!!

ከዚህ በታች በፎቶ እኔጋ ያስቀረዋቸው ስላሉ አንድ ሶስቱን ግርግዳው ላይ እለጥፈዋለው..!!

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት ይሁንላቹ!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የልቦለዴ ጉዳይ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
አንድ ልብወለድ ፅፌ ልብወለድ ውስጥ እኩይ ባህሪ አላብሼ የፃፍኩትን ሰውዬ የየትኛው ብሔር ተወላጅ እንደማደርገው ግራ ገባኝ። በዚህ ሰአት የየትኛውንም ብሔር ስም ሰጥተህ ልቦለድ ብትፅፍ ራሱ ብሔረሰቡ ስሎጋን ይዞ ቀኑን ሙሉ ነው ሲያወግዝህ ሚውለው
ስለዚህ ከየትኛውም ብሔረሰብ ጋር ላለመጣላት ልቦለዱን ኡጋንዳ ውስጥ የተፈፀመ ታሪክ አድርጌ ፅፌዋለሁ። የዋና ገፀባህሪው ስም "ኡዙሉጳዮቃ" እኩይ ገፀበህሪ የያዘውን ሰውዬ ደግሞ “ፓሬንጮባጎፓ" የሚል ልሳን የሚመስል ስም ሰጥቻቸዋለሁ
ባሻዬ ባሁን ሰአትኮ ብሔር ብሔረሰቦች ከሚጠምዱህ የሪፐብሊካኑ ጋርዶች እንደጀበና በሰባብሩህ ይቀላል
ለማንኛውም ደና እደሩ። አሁን እንደብሔሬ ሰአት አቆጣጠር አራት ሰአት ስላለፈ ልተኛ😂


@wegoch
@yeyhudaanbesa
@wegoch
እንግዲህ በትንሹ ይሄን ይመስላል......እኔን ገርሞኛል እናንተን ይግረማቹ የሚሉት የመንገድ ላይ ነጋዴዋችን ለዛሬ አፋቸውን ተውሼ

እኔን ገርሞኛልና እናንተም ....ጎብኝታቹ ይግረማቹ....አጃኢብ ነው ...እውነትም አወቀ ቀለሙ...አወቀው ቀለሙን...ቀመመው ጥበቡን....

ሰላም እደሩልኝ !!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የክፉዎችን ያክል ዝም ያሉ ደጎች ቢያሴሩ ምድሪቱ መልኳ ምን ይሆን? አራት አምስት
አያቱን ለመቁጠር ድፍረት የሌለው እራስ-ፈር ሁሉ የዘር መስመር ሲያሰምር፣ ሲገነባና
ሲያሴር ይውላል፥ ያድራል።
እራስን በኢኮኖሚና ፖለቲካ ከፍ ማድረግ አንድ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ፣ ዘርን በማንጠርና
በማንዘርዘር ፖለቲካዊ ሸቀጥ ማሻቀጥ በድምር ውጤቱ ኪሳራ ነው።
ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎህን አሳድግ፥ ተደራጅ፣ የጋራ ቋጠሮህን መሰሎችህን ሳብ
ሰብስብበት እንጂ ሌሎችን ለመበተንና ለማራቅ መሳሪያህ አታድርገው። የመጥሎና
መገፋት ትርክት ቁጭት ብትኖችን የመሰብሰብ ሃይሉ አሌ የማይባል ጉልበታም ቢሆንም
ኢትዮጵያን መሰል ዘረ-ቁልፍልፍ ለሆኑ ህዝቦች አዙሪተ-በደሉ ዘመን ተሻጋሪ ነው።
በእኛ ዘመን እንደሆነው ለመጭ ትውልድ መገፋፋትንና ቁርሾን አታውርስ። የመጠላለፍ
ታሪክ ሰሪ የየዘመኑ ሰው የመሆኑንን ያክል የመጠላለፍና የመጠላላት ትርክት አክትሞ ለሰው
ሁሉ የሚበጅ ኢኮኖ-ፖለቲካዊ ስርኣትም የሚበጀው በዘመን ቅብብሎሽ በሚፈጥሩ
አብርሆት በገራላቸው ሰዎች መሆኑንም አትርሳ። ስለሆነም የኢትዮጵያና ህዝቦቿ የፖለቲካ
መጻኢ እድል በእውነትና እውቀት ላይ የተሰመረ መሸጋገሪያ ይሆን ዘንድ ይሄ ትውልድ
አጥፊ ቁርሾና እልኩን ትቶ ስልጡኑን አለም ይመልከት። ሰው ስሜተ-ብዙ ነው። ብዙሃኑ
ከምክንያታዊ ነገ ይልቅ የዛሬ ግንፉል ስሜቱ ሚዛን ያስተዋል።

ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
አልተፀፀትኩም!!!

አልተፀፀትኩም ግን ልምድ አግኝቼበታለው።በፊት በፊት ገና ቆንጆ ሴት ሳይ request
እልክላቸውና ዝም ሲሉኝ ይከፋኝ ነበር ...ተቀብለው ካዋሩኝ ደሞ ስልክ ይኖርሻል?ብዬ
እጠይቃለው አራዳ ሴቶች ኖ የለኝም facebook የምጠቀመው በላፕቶፕ ነው ይሉኛል ፋራ
ሴቶች ደሞ ምን ያደርግልሀል ይሉኛል።
ያው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወንድ ሀይ ብዬ እልካለው ከዛኛው ሰፈር መልስ
እየተመለሰልኝ ከሆነ ስልኬ ቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ያሰማኛል የዛኔ ደስ ይለኝና ቀጣይ
ወሬዬን እመርጣለው...ያው እናንተ ተማሪ ሰራተኛ ?ነው የምትሉት አይደል እኔ ግን
አይደለም።
የማይታዩ ሴቶች ደሞ ሲያበሽቁኝ ፎቶ ላኪልኝ ማለት አጠያየቁ ግራ ይገባኝና ፎቶ ደመቀን
ታውቂዋለሽ? እላታለው ማነው ደሞ እሱ ካለቺኝ ያው ስታዲየም አካባቢ አትመጣም
ማለት ነው ብዬ ወደ ሌላ ጥያቄ ላልፍ ስል ግን ለምን ጠየከኝ ትለኛለች....ፎቶሽን እሱ
አንስቶ እንዲልክልኝ ነበር እላለው እንደዛ ከምትል ላኪልኝ አትልም? አራዳ ሴት እኮ
ትግደለኝ ቢያንስ ስትገለኝ አሻራ ታጠፋለች ፋራማ አቡክታህ ነው የምትሄደው።ማለት ፈርቼ
እኮ ነው ችግር የለውም እልክልሀለው ግን ለማንም እንዳታሳይ ፕሮሚስ? እኔ ግን
ስንተኛው ሰው እሆን ለማንም እንዳታሳይ ተብዬ የተላከልኝ እላለው በውስጤ።
ፕሮሚስ እገባና ይላክልኛል አንድ ሲላክልኝ ጥጋቤ መከራ ነው እስኪ ደግሞ በሌላኛው
ዳይሜንሽን እላለው ያው እናንተም እንደምታውቁት አንድ ብቻ የሚልከው ሰላቢ ነው
አይደል?ይሄ የመጨረሻ ነው ብላ ሌላ ትልካለች በመሀል ግን አጥፋው እሺ የሚል ትእዛዝ
ይደርሰኛል ድሮስ ፕሮፋይል ላደርገው ነው? የአንዲትን ልጅ ፎቶ ግን ፕሮፋይል አድርጌ
አውቃለው ....እዚህ ጋር አምስት ሴቶች የኔን ነው ብለው ያስባሉ።አሁን እያረጀው ስለሆነ
ወደ ተውበት እየገባው እኮ ነው ጠይቄ የላካቹልኝ አመሰግናለው ያላካቹልኝ አስቀያሚ
ስለሆናቹ ነው ሃሃሃሃ ተውበቱን ረሳሁት እንዴ?....ይሄ ሁሉ የምቸከችከው ለምን ይመስልሀል
ገምታ።
ሸጋ ቀን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የልጁን ነገር ምን ወሰናችሁ???

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቤተሰብ ውስጥ ያለ ህፃን እያለቀሰ ያስቸግራል፡፡
ቢያባብሉት፣ እሹሩሩ ቢሉት አሻፈረኝ አለ፡፡ በማባበል እምቢ ሲል ማስፈራራት
ጀመሩ፡፡
“እንግዲህ ዝም ካላልክ ለአያ ጅቦ ልንሰጥህ ነው” አለች እናት፡፡
“ዋ በመስኮት ነው የምወረውርህ!” አለው አባት፡፡
ይህንን ሲሉ ለካ አያ ጅቦ ደጅ ሆኖ ያዳምጥ ኖሯል፡፡ ይጠብቃል … ይጠብቃል
… ይጠብቃል… ልጁ አልተወረወረም፡፡ አሁንም ያዳምጣል፡፡ ተስፋ ሳይቆርጥ
መጠበቁን ቀጠለ፡፡ ምንም ዝር ያለ ነገር የለም፡፡
የልጁ ለቅሶ ግን ቀጥሏል፡፡
አሁንም እናቱ፤
“ዋ! ለአያ ጅቦ ነው አስረክቤህ የምመጣው!!”
አባትም ዳግም፣
“ዛሬ ነግሬሃለሁ ለአያ ጅቦ ነው የምጥልህ” አለው፡፡
ልጁ ማልቀሱን ቀስ በቀስ አቆመ፡፡ አያ ጅቦ ምራቁን እያዝረበረበ፣ ቆበሩን
እየደፈቀ ቀረ፡፡ በመካያውም አንድያውን ጥሎ ለመሄድ፤ “ኧረ የልጁን ነገር
ምን ወሰናችሁ?” ብሎ ጠየቀ፡፡ ቄሱም ዝም፣ ዳዊቱም ዝም፤ ሆነ!
***
አንድ የሀገራችን ዕውቅ ገጣሚ፤ የደርግ ሥርዓት አብቅቶ የኢህአዴግ ሥርዓት
ሲጀምር፤
“ዘመንና ዘመን እየተባረረ
ከምሮ እየናደ፣ ንዶ እየከመረ
ይሄው ጅምሩ አልቆ ማለቂያው ጀመረ” ብሎ ፅፎ ነበር፡፡
ዕውነትም የማያልቅ ዘመን የለም፡፡ አዲስ ሁሉ ያረጃል፡፡ የማይለወጥ
አንዳችም ሥርዓት የለም። የአዲሱ አሸናፊነትም አይቀሬ ነው፡፡ አጠራጣሪው
በየትኛው መንገድ ይለወጣል? የሚለው እንጂ ለውጥ መቼም ቢሆን መቼ
መምጣቱ የማይቀር ሂደት ነው፡፡ ፈረንጆቹ፤
Everything changes
Except the law of change የሚሉት የተፈጥሮ ህግ ነው፡፡
“ከቶም ከለውጥ ህግ በስተቀር የማይለወጥ ነገር የለም” እንደማለት ነው፡፡
እነሆ ለውጥ መምጣቱ ግድ ከሆነ ለለውጥ ዝግጁ መሆን ዋናውና
አስፈላጊው ጉዳይ ነው፡፡ የሀገራችን ሰው አንድ ለውጥ ባገኘ ቁጥር በዚያው
ተወስኖና ያንን ፍፃሜ - ነገር አድርጎ ማሰብ ይቀናዋል፡፡ ሆኖም መሰረታዊ
ችግሩ የጊዜ - ቀመር አለማበጀት (Time - plan አለመኖር) ነው፡፡ መልካም
የጊዜ ግምት ማጣትን የመሰለ ከመርገምት ሁሉ የከፋ መርገምት የለም፡፡
“ጊዜ የስልጣን እጅ ነው” ይለናል፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን። ጊዜ
የሚታዘዘው ሰው ብቻ ነው - ዕውነተኛ ባለስልጣን! ለሁሉም፤ ትክክለኛ ምክር
ሰሚ መሆን ታላቅነት ነው፡-
“ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ …
ምንኛ ታድሏል የሰነፍ አዕምሮ
እንኳን መማር ቀርቶ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና!
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ”
ይሉናል ገጣሚ ከበደ ሚካኤል፡፡ ካልተደማመጥን ወንዝ አንሻገርም፡፡
ካልተጋገዝን አገር አትንቀሳቀስም፡፡ አሉታዊ ገፅታዎቻችንን ብቻ እየነቀስን
በማጉላት ለውጥ የሚመጣ የሚመስለን በርካቶች ነን፡፡ ሀገራችን ለሶስት ሺህ
ዘመን ያጠራቀመችው በቂ አሉታዊ ነገሮች አሏት፡፡ እነዚህን በማጉላት ምንም
አናተርፍም፡፡ ይኸውም ልዩ ዕውቀት እየመሳሰለን የምንደገግ ብዙ ነን፡፡ ስለ
ሰው ክፉ ክፉውን በመናገር፣ ዘራፍ ማለት የአሸናፊነት ስሜት መፍጠሩ
ዕውነት ነው፡፡ ሆኖም በትክክለኛ መፍትሄ ካልታገዘ ጎጂ ባህል ይሆናል፡፡
ለመፍትሄ ያልተዘጋጀ ህብረተሰብ፣ የአፍራሽነት ሥነ-አዕምሮ ይዞ የሚጓዝ
ስለሆነ ከለውጥ ይልቅ ወግ-አጥባቂነትን ያዘወትራል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያለው
ማህበረሰብ ከጅምሩም ተራኪ (Story-teller) ህብረተ-ሰብ ነው፡፡
ከተግባራዊነት ይልቅ አፍአዊነት ይቀናዋል፡፡ አፍአዊነቱም በጥናት ላይ
አለመመስረቱ ደግሞ ነገረ - ዓለማችንን የከፋ ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ነው የወሬ
አገር ሆነን የቀረነው፡፡
ያለምነውንና የተመኘነውን ዲሞክራሲ እስከምናገኝ ብዙ ዳክረናል፡፡ ብዙ
ፈግተናል፡፡ ልጃቸውን ይወረውሩልኛል ብሎ በር በሩን ሲያይ እንዳመሸው አያ
ጅቦ፤ በመጨረሻው ዘጋግተው እንደሚተኙ እንዘነጋለን፡፡ እንደ ህፃኑ ልጅ
የሚያስቸግረውንም የኢትዮጵያ ህዝብ አባብለው እንደሚያስተኙት ግልፅ
እየሆነ ሲመጣ፤ የእኛ ትርፍ “ኧረ የልጁን ነገር ምን ወሰናችሁ?” ማለት ብቻ
ከሆነ አደጋ ላይ ነን፡፡ ዲሞክራሲ ከራሳችን የሚፈልቅ እንጂ ማንም የሚሰጠን
ምፅዋት ወይም ዳረጎት አይደለም!


ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ


ሽብርቅርቅ ያለ ቀን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መንገዱን ያሳጥሩልሀል እኮ...ገብቼ እንደተቀመጥኩ ራሴን ያገኘሁት ከአንዲት ለኔ ቁመት
ትንሽ የቀራት መለሎ አጠገብ ነው።እንዴት አደርሽ? ፀጥ አየሽ ሰላምታ ጥሩ ነገር ነው
ደህና ካልሽ በኋላ አለማናገር ትችያለሽ...ተገላምጣ ደህና አድሪያለው አለቺኝ።እቺ ትንሽ
አይምሮ ቀጣይ ጥያቄ ከየት ታምጣ ከያዝኩት ማስቲካ አንዱን መዝዤ ማስቲካ ልጋብዝሽ?
ፈገግ ብላ በጠዋት ማስቲካ? እንዴ እንቅልፍ ነው እንዴ የጋበዝኩሽ ማስቲካ እኮ
ነው...አመሰግናለው ብላ ወሰደች እኔም አንዱን ጠቅልዬ ስጎርስ ሙሉውን ነው እንዴ
የምታኝከው ?አይ እንደሴቶች ከቦርሳዬ መቀስ አውጥቼ ስድስት ቦታ እቆርጠዋለው.....እንዴ
ሴቶች እንደዛ ያደርጋሉ እንዴ? ያደርጋሉ ግን አንዳንድ ሴቶች ብለሽ ያዠው ስልኬ የአንዲት
ልጅ ምስል ይዞ ብልጭ ብልጭ ይላል እኔ ሳይለንት አደርጋለው አዋራት እንጂ ፍቅረኛህ
ነች? ኧረ አይደለችም እኔ ፍቅረኛ የለኝም።አየህ ወንዶች ስትባሉ ሁላቹም የለኝም ነው
የምትሉት አየሽ እኔ እንዳልኩሽ አንዳንድ ወንዶች ብትይ አሪፍ ነው...እኔ ግን የተሻለች ሳገኝ
ነው የለኝም የምለው ኖርማሊ የለኝም ኖርማሊን ያስገባዋት እንድታምነኝ ነው ሃሃሃ
ተመሳሳይ ጸባይ ነው ያላቹ ብላ ተሟገተቺኝ ግን ነን እንዴ? እኔ አሁን ከአንተ ጋ ተመሳሳይ
ፀባይ ነው ያለኝ? አይመስለኝም ።ለማንኛውም ቁመናሽ ደስ ይላል በተፈጥሮ ነው ወይስ
ተለፍቶበታል? ብዙም አይደለም የተፈጥሮና በምግብ ነው... እዝች ሀገር ላይ መርጠሽ
መብላት መቻልሽ በራሱ ትልቅ ነገር ነው ኖ ለስራዬም እንደዚ መቆየት አስፈላጊ ነው
ሆስተስ ነሽ፣ሞዴል ነሽ፣ማስታወቂያ ነው ምትሰሪው ?ምን አስቸኮለህ እኔ እነግርህ አይደል
...ብራዘር ጃፓን ኤምባሲ ጋር ወራጅ አለ።

💚💛❤️!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
**ህይወት እንደ ገደል ማሚቶ ነው!
አንዲት ትንሽ ልጅ በእናቷ ትናደድባትና " አልወድሽም " ብላ
ትጮሃለች፣ እንዳትገፅፃትም ፈርታ በሩጫ ከቤቷ ወጥታ ርቃ
ትሄዳለች፣ ገደል አፋፍ ላይ ደርሳ አሁንም " አልወድሽም!
አልዎድሽም! " እያለች ትጮሃለች።
የገደል ማሚቶም " አልዎድሽም ! አልወድሽም! " በማለት
አስተጋባ ፣ ከዚህ በፊት የገደል ማሚቶ ድምፅ ሰምታ ባለማወቋ
በሁኔታው እጅግ ትደናገጥና ታድናት ዘንድ ተመልሳ ወደ እናቷ
በመሮጥ በገደሉ ውስጥ " አልዎድሽም! አልዎድሽም !" እያለች
የምትሮጥ መጥፎ ልጅ እንዳለች ትነግራታለቸ።
እናት ነገሩ ስለገባት ልጂቷን ተመልሳ ወደ ገደሉ በመሄድ "
እዎድሻለሁ፣ እዎድሻለሁ!" ብላ እንድትጮህ ነገረቻት፣ ልጂቱም
ተመልሳ በመሄድ እናቷ እንዳለቻት " እዎድሻለሁ! እወድሻለሁ! "
እያለች ስትጮህ የገደል ማሚቶው ያለችውን አስተጋባ ፣ ልጂቷም
አለች ለካ " በህይወት ውስጥ የምታገኘው የሰጠኸውን ነው።"
የሰው ለጅ የዘራውን ያጭዳል፣ አዎ እንክርዳድ የዘራ እንክርዳዱን
ያፍሳል፣ ጥሩ ዘር የዘራ መልካሙን ሁሉ ያፍሳል።
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
2024/09/28 23:29:20
Back to Top
HTML Embed Code: