Telegram Web Link
ሁሉም ጋቢና ከተቀምጠ መኪናው ከጭቃ አይወጣም! ሰብሰብ ብላችሁ በመኪና ስትሄዱ በጭቃ ከተቀረቀረ የተወሰነው ሰው ወርዶ መግፋት አለበት፡፡ ሁሉም "አይ እኔ ውስጥ ነው የምቀመጠው" "ታየኝ እኮ ጭቃ ሲነካኝ" ካለ ተቀርቅራችሁ መቅረታችሁ ነው፡፡ ሌላው አማራጭ ሌላ መኪና መጥቶ ከጎተተ ብቻ ነው፡፡ አሁን የኢትዮጲያ ሁኔታ ጭቃ ውስጥ እንደተቀረቀረ መኪና ነው፡፡ የተወሰነው ያህል ዜጋ ወርዶ ለመግፋት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡ ተራ እየወሰድን ልንገፋ እንችላለን፡፡ ግን አንዱ
መጀመሪያ ላይ መጀመር አለበት፡ሌላውም መቀጠል አለበት፡፡ በፉክክር ማንም የመጀመሪያ አልሆንም ካለ ጭቃ ውስጥ መሰንበታችን ነው፡፡


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
👆👆👆👆 ይቺ ሸጋ ስዕል ብዙ ታስብላለች ፣ ታፈላስፋለች ፣ ታመራምራለች.....ታስደምማለች .....እናም አበቦቼ......ስዕሉን በደንብ አበጥራቹ እዩትና.....የተሰማቹን እናንተ ያያችሁትን እኛ ያለየነውን ነገር አሳዩን.......እየጠበቅናችሁ ነው....

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch

ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንላቹ!!!!!!!!
ስንት እናቶችና ህጻናት ቢንገላቱ ክፉዎች እጃቸው ይሰበሰባል?
-------
ብርሃን ነጣቂዎች ጎልብተዋል። ክፋት ደግነትን ድል ነስቷል። እኩልነትንና ፍትህን ተገዳዳሪ
በእናቶችና ጨቅላ ህጻናት እንባ ውስኪ የሚጋቱ ብርቱ ሰካራሞች ከትናንት እስካሁን
በማሸነፍ ላይ ናቸው።
"ደጉን ሰው" ብዙሃን ቢፈልጉትም በሴራ የሰለጠኑ ዳህጣን የሚዘውሩት እንሽሽ ነፍጥ
አንጋች ሁሉ አገሩ ስትጠፋ ዳር ቆሞ ማየትን መርጧል።
የአፍሪካ ኩራት ነኝ የሚለው የጸጥታ ሃይል ድርብ አገርና ድርብ ወገን ያለው ይመስል
በክፋት ሃይሎች ካልተመራሁ ብሎ የደጉን ሰው መንገድ ከክፉዎች ሊጠብቀው አልቻለም።
ይሄ ሃይል ወገኑ በታሪኩ ያልሆነውን ሲሆን ቆሞ ያያል።
ሌላው ቀርቶ የነዚህ እናቶች፣ የነዚህ ህጻናት አንገት እንዲቃና ሰላም እንዲመጣ፣ ትቢያ
ኑሯችን በትቢያ እንጀራ ዘመን እንዲሻገር ታዲያ ማን ይምራን? መቃብራችን ላይ ቆማችሁ፥
ትውልዱን ሁሉ ጨርሳችሁ ትመሩን ይሆናል!!!!
ስልጣን ንዋይ ሲሆን የእናቶችና ህጻናት ደም እንደ ዥረት ቢፈስ፥ የእናቶችና ህጻናት መከራ
ለዘመናት ባያባራ ለክፉዎች ደንታቸው አደለም። በመሆኑም እናቶችን እየገደሉ፣ ህጻናቶችን
እየደፈሩ "ሰላም ጠፋ፥ ሰላም እናስከብር" ብለው ዳግም ሊገድሉን ወደ ወንበሩ ሊመጡ
የሚፈልጉ አሉ።
አብይ አህመድ ሆይ የይቅርታና መደመር እሳቤህ በእኩልነትና አንድነት ለሚያምኑ፣ ከሰላም
ለሚያተርፉ ነገን ናፋቂዎች እንጂ በብዙሃን ደምና ላብ የምቾት ስካርና ቅምጣን
ሰውነታቸውን ለነጠቃቸው ክፉዎች ፍጹም አይሆንም። እናማ እልሃለሁ፥ እሳት አታስበላን!!
እደግመዋለሁ ይቅርታ በመኖር ለሚያምን፥ በይቅርታ ለሚፈዎስ መለኮታዊ ሰው፣ ከሰላም
ለሚጠቀም ሰብኣዊነቱ ላልነጠፈ ላብ-አደር ሰው እንጂ በብዙሃን መከራና ስቃይ ለሚደሰቱ
እንባና ደም ቁርሱ ጭራቅ ዳህጣኖች አደለም!! ስለሆነም የምትሄድበት የሰላም መንገድ
ወደማይቀረው ሞት እየወሰደን ይመስላልና ዘይቤህን ቀይር!!
ቆመን የምንጠብቀው የእናቶች ሞትና ስቃይ ይብቃው!!!!
ሰው በላው ነግቶ ሲመሽ ክንዱ በርትቷል፥ የምንፈልገው አብይ በማንፈልገው ሰቃቂ
ትርኢት ተጋርዷል!! ጦርነቱ በህዝብ ፍላጎትና የአብይን ትእዛዝ በዝምታ ሽባ በሚያድርጉ
አሻጥረኛ "ጓዶች" ብሎም የጥፋትን እሳት እየለኮሱ በሚያፋጥኑ ጥቂቶች መካከል ሆኗል።
እሳቱ ነግቶ ሲመሽ እናትና ህጻናትን አመድ ካደረገ በጥቅል ጦርነት ተሸንፈናል!! ስንት
እናቶችና ህጻናት ቢንገላቱ ክፉዎች እጃቸው ይሰበሰባል? የስካሁኑ ካልበቃ መች ይበቃል?
ሞትን ቆመህ አትጠብቅ!!

((( ያሲን መሀመድ ))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
👆👆👆👆 ይቺ ሸጋ ስዕል ብዙ ታስብላለች ፣ ታፈላስፋለች ፣ ታመራምራለች.....ታስደምማለች .....እናም አበቦቼ......ስዕሉን በደንብ አበጥራቹ እዩትና.....የተሰማቹን እናንተ ያያችሁትን እኛ ያለየነውን ነገር አሳዩን.......እየጠበቅናችሁ ነው.... @balmbaras @Lula_al_greeko @wegoch ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንላቹ!!!!!!!!
Berry👇👇👇👇
Ene demo mitayegn kejerbaw yalew tkur yehiwetua behazen yelemola mehonu ena alfo alfo dem yemesele key kelem lemenor stl yekefelechw meswatnet keza betechemari yetezeberareku gn wedetach miwerdu kelemat alu enesu demo hiwetua west yalew tsefa eywerede eyetemuatete mehedun yasayal....Lelaw aynua west kucht tkaze ndet ytayal sigaraw demo westua yalewn ndet mtaswetabet ymeslegnal

Eyosias:👇👇👇
i mean this girl looks like she is in the rular area....that keeps her culture...but those western culture like cigaretes esuan ke bahlua eyawetuat new

Îñnocent:👇👇👇
Selu endmemslg tarik bahel wag yazahe Hager gen bezu tikure nagrohe tabsawohe alwat berhanme tasfa segarwe damo nado endmeylk esat eyabnana tayto endmetfa gume ergtaga yaltonbat nager.

Tezu 👇👇👇
መጀመርያው . . . ,

ይቺ ሴት . . ቆንጆ ፣ የተማረች ፣ ሰዎች ሁሉ
ያደነቋት ሴት ነች . . . .

ስዕሉ ግን ከዚህ ሁሉ ጀርባ ያለውን ታሪኳን ሚነግ
ረኝ መሰለኝ . . .

የዝች ሴት ጀርባዋ ወይም ያለፈ ታሪኳን ሳየው
በጣም ውስጤን አመመው ፍፁም አስፈሪ ነበር
ከጥቂት ደስታዎች በቀር . . ከጀርባዋ ዝቅ ብለህ
በንሹም ቢሆን ነጥቶ ምታየው ንጣት ውልደቷን
ያሳየኛል . . ምንም አላማወቆን የወለዷት ሰዎች
ፈቅደውም ይሁን ሳይፈቅዱ የወለዷት እሷ አታው
ቅም አንዳንዴ አለማወቅ በራሱ ደስታ ይሰጣል
አዎ ትንሿ ንጣት ልጅነቷን አሳየኝ ባዶ የዋ ልቧን
አሳየኝ . . . .ከዛን ግን አስፈሪ ጥቁር ጫካ እና
አስፈሪ ጊዜያቶችን አስልፋ ነበር ብዬ አሰብኩ
አልፎ አልፎ ያሉት ፈካ ያሉና ነጣ ያሉት ቀለማት
ነገን ተስፋ ለማረግ ስሞክር የተፈጠሩ ደስታዎች
ጉጉቶች አድርጌ ወሰድኳቸው. . . . .

. . ,አንገቷ ላይ ያለው ሃብሏ ዛሬን ፣ነገን፣ ትላንትን
(ያለፈውን ፣ አሁን ያለውን ፣ ሚመጣውን) ያስተሳ
ሰረ ድልድይ አድርጌ ወሰድኩት . . .. . . .

. . . ፊት ለፊት የተሰራው ፀጉሯን የታሪኳን ብዛት
አየሁበት ያላለቀው ፀጉሯ በጆሮዋ ውስጥ ያየሁት
ነፍሳት ሚመስል ነገር በውበቷ እንደሚማረኩና
በውበቷ ብቻ የሚያደንቋትን ሰዎች መስሎ
ታየኝ . . . እና አሁን ያላትን ታሪክ ለመፍታት
እየታገለ መሰለኝ . . . .

. . . . በትከሻዋ ያለው ትንሽዬ ንጣት ዛሬዋ
መሰለኝ . . . ከትላንቱ የሚሻል ይመስላታል
ነገር ግን የጆሮዋ ቀዳዶች አሁንም እየፈሰሰ
ያለ ማንነት እዳላት ይሳማታል

. . . .ፊትለፊቷ ነገዋ ነው ሲጋራዋ አይተከው
ከሆነ በእጆ አልያዘችውም. . . በአፏ ነው
አጥብቃ የያዘቹ ነገዋ በከፊል ያስፈራታል
ግን ገና አልያዘችውም . . . ሲጋራው ጫፍ
ላይ ያለውን እሳት ኡፍ ባለችው መጠን ይነዳል
ከተወችው ግን ይጠፋል . . እና ሲጋራውን
ያየሁት በሷ ውስጥ ያለው ነገዋ በትንፋሿ እንደ
ሆነ ነው. . . . አይኗ ነገን በጥርጣሬ ነው
ሚያየው አፍንጫዋ ጥሩ ሽታ የለውም

ግን ግን በቀኞ በኩል ያለው ሰማያዊ ከረል ድቅድቅ ካለው ጨለማ መሃል ብርሃን እንዳለ
እየነገራት ነው. . . ውሳኔው የሷ ነው

የመጀመርያ አረዳዴ እንዲህ ነው


🙏🙏 ለተሳተፋቹ የእናተን እይታ እና ምልከታ ላከፈላቹን እጅግ በጣም እናመሰግናለን !!! በትንሹ ከላይ ያሉትን የግጥም ብቻ እና ወግ ብቻ ቤተሰቦች ምልከታዎችን አቅርበናል ሌሎቻቹም ብትነግሩን ደሰ ደስ ይለናል!!!! ለተሳተፋችሁት ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@getem
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ
አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ

‹‹እናት ብዙ ሻንጣ የለሽም አይደል? እባክሽ ይህቺን ስኳር ያዢልኝ? የእኔ እህት….ኪሎ በዝቶብን ነው…ይህችን ቡና ትይዥልኛለሽ?....እመቤት… ያንቺ አልሞላም አይደል…እባክሽ እነዚህን ጫማዎች ያዢልን…›› እያሉ ብዙ ሰዎች ያዋክቡኛል፡፡ ቦሌ አየር ማረፊያ አስመራ የሚወስደኝን አውሮፕላን ለመሳፈር ሻንጣ ማስረከቢያው ጋር ቆሜያለሁ፡፡ የማንን ወስጄ የማንን እንደምተው ለመወሰን ስቸገር ትርምሱ ይበልጥ ባሰ፡፡ ብዙ ላስቲክ ንብርብር እንጀራዎች፣ የቆዳ ጫማዎች እና ጃኬቶች፣ ቅንጡ የአበሻ ልብሶች፣ ቡና፣ ስኳር፣ በላውንደሪ ላስቲክ የተጠቀለለ ከነመስቀያው ያለ ሙሉ የወንድ ልብስ….እቃ በአይነት አይነት ካንዱ ሻንጣ ተቀንሶ ሌላው ውስጥ በግድ ይጠቀጠቃል፡፡ በሃይል ይጎሰራል፡፡ ይተርፋል፡፡ ደግሞ ይወጣና ወደሌላ ሻንጣ ይወሰዳል፡፡ ምንድነው ይሄ ሁሉ ሸክም? ሻንጣዬን ካስረከብኩ በኋላ ተራዬ ደረሰና የኢሚግሬሽን መስኮቱ ጋር ፓስፖርቴን ሰጥቼ ቆምኩ፡፡
- አስመራ ነው የምትሄጅው? አለችኝ ሚጢጢዋ ክፍል ውስጥ የተቀመጠችው የኢሚግሬሽን ሰራተኛ፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ትህትና በከፍተኛ ሁኔታ
ጨምሮ ጭራሹን ይህችን ማህተም የመምታት፣ ፎቶ የማንሳትና ፓስፖርትን የመመርመር አፍታ በ ትንንሽ ጨዋታ ወደ መሙላት ፍላጎት አድጓል፡፡
- አዎ አልኩኝ ቶሎ ብዬ
- ዘመድ አለሽ እዛ?
- የለኝም፡፡
- እና ዝም ብለሽ?
- አዎ…ለጉብኝት…የድሮ ሃገራችን አይደል ብናየው ደስ አይልም?
- እሱስ ደስ ይላል… የሂጂ ማህተም ተመቶልኝ አለፍኩ፡፡ አስመራን ልጅ ሆኜ በአባቴ ወሬ፣ አደግ ብዬ በበአሉ ግርማ ኦሮመይ፣ አሁን አሁን ደግሞ በቴሌቪዥን እንጂ ረግጫት አላውቅም፡፡ ግን አውቃት ይመስል፣ ዘመድ ያለኝ ይመስል ሌላ ቦታ ስሄድ ከሚኖረኝ ስሜት የተለየ ስሜት እያስተናገድኩ ነው፡፡ በአብዛኛው ጉጉት ነው፡፡ የበአሉ ግርማ አስመራ እንደ ጠበቅኳት አግኝቻት ታስደስተኝ ይሆን ወይስ ከግምቴ አንሳ ቅር ታሰኘኝ? በአንድ ሰአት ተኩል ውስጥ አውቃለሁ፡፡
----
አስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ከማረፋችን እልልታው ቀለጠ፡፡ እልልታው ዛሬም ከአመታት በኋላ ከዘመድና ወዳጅ ጋር ለመገናኘት የቋመጡ ሰዎች መሳፈራቸውን ነገረኝ፡፡ ከአውሮፕላን ስወጣ ደስ የሚያሰኝ ነፋሻማ አየር ተቀበለኝ፡፡ የአስመራ አየር ማረፊያ ትንሽና በዘመናዊነት ስሌት ቢታይ ሚዛን የማይደፋ ነው፡፡ ግን ንጹህ ነው፡፡ ተሳፋሪዎች ኢሚግሬሽን በር ጋር ደርሰን ሰልፍ ልንይዝ ስንል ሁለት ወጣት ሴቶች ፓስፖርት እንድንሰጣቸው ጠየቁን፡፡ ሰጠን፡፡ አንደኛዋ ባዶ ገፅ ፈልጋ ማህተም ስታደርግ ሌላኛዋ ደግሞ በእስኪብርቶ ቀን
እና ሌላ ነገር ፅፋ ፈረመችበት፡፡ ፓስፖርቴ ሲመለስልኝ ከፍቼ አነበብኩት፡፡ ‹ለአንድ ወር እንድትቆይ ተፈቅዶላታል‹ ይላል፡፡ ቪዛዬ ይሄ ነው? ለቪዛ እንደማንከፍልም እንደማንጉላላም ቢነገረኝም ይሄን ያህል ይቀላል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ በቅለቱ ተገርሜ ወደ ፊት ገስግሼ ልሄድ ስል ቀድመውኝ ከሄዱ ሰዎች ጀርባ እንድሰለፍ ተነገረኝ፡፡ ተሰለፍኩ፡፡ ሰልፉ አይሄድም፡፡ ብዙ ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ሰልፉ አሁንም አይሄድም፡፡ ከ20 ደቂቃ በላይ ከቆምኩ በኋላ ተራ ደረሰኝና ከመስታወት ጀርባ ለተቀመጠችው ሌለ ወጣት ሴት ፓስፖርቴን አስረከብኩ፡፡ ቀና ብላ
አየችኝና ፓስፖርቴን ከፍታ ምልክት የተደረገበትን ቦታ መፈለግ ጀመረች፡፡ ወዲያው ፊት ለፊቷ በተቀመጠው በፕላስተር በተለጠፈ ኮምፒውተር ላይ በግራ እጇ ፓስፖርቴን ከፍታ እንደያዘች በቀኝ እጇ አንድ አንድ
ፊደል እየለቀመች ቀስ ብላ መተየብ ጀመረች፡፡ ጉጉቴን አልተረዳችም፡፡ ተቁነጠነጥኩ፡፡ ቃ--ቃ….ቀና ብላ እይት…ቃ….ቃ….ቀና ብላ እይት…ቃ…ቃ….ፓስፖርቴን እይት፡፡ ዘልአለም የቆምኩ መሰለኝ፡፡ ምንድነው ይሄን ሁሉ ሰአት የምትፅፈው? ለምን በሁለት እጆችዋ አትፅፍም? ሃሳቤን ሳልጨርስ ድንገት ቀና አለችና ቶሎ ቶሎ በትግርኛ ታወራኝ ጀመር፡፡ ‹‹ሕይወት….xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx
xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx?….››ከስሜ በስተቀር አንዲት ቃል አልያዝ ብሎኝ እንደ ቂል ዝም ብዬ አያታለሁ፡፡
- ትግርኛ አልችልም እናት…አልኩ እና አቋረጥኳት፡፡ የሚያምር ፈገግታ ፈገግ አለችና….
- ካዲሳባ ነው? አለችኝ፡፡
- አዎ…ካዲሰባ…አልኩ ደስ ብሎኝ፡፡
- የት ነው የምትገቢው? አማርኛዋ ይጣፍጣል፡፡
- አስመራ…አልኩ ቆፍጠን ብዬ…
- አይደለ….ዘመድ አለ ወይስ ሆቴል?
- እ…ዘመድ የለም፡፡ ሆቴል፡፡ ሆቴል ነው ምገባው፡፡ ጎንበስ አለች፡፡ እንደገና ልትተይብ ነው? ቃ--ቃ….ቀና ብላ እኔን እይት…ቃ….ቃ…. አሁንም ድንገት ፓስፖርቴን እንደያዘች ተነሳችና ከጀርባዋ ያለችውን ትንሽ በር ከፍታ ሄደች፡፡ እንዴ? ምንድነው ነገሩ? ሁለት ደቂቃ ቆይታ ተመለሰችና እንደገና መተየብ ጀመረች፡፡ አዬ! ማደሬ ነው። ሌሎች ሰልፎች እየተንቀሳቀሱ ይሆን ብዬ ግራና ቀኝ አየሁ፡፡ ያው ነው፡፡ ሌሎቹ መስኮት ውስጥ ያሉት ሴቶችም እንዲሁ ፓስፖርት ይዘው ሲወጡ አየሁ፡፡ ቆይቶ ክፍላቸው ውስጥ ፓስፖርት ስካን የሚያደርጉበትም ሆነ ሌላ መሳሪያ ስለሌለ ለፎቶ ኮፒ ወይ ስካን ለማድረግ እንደሚሄዱ ገመትኩ፡፡ ጉልበት በሚቆጥብ አኳሃን ቆሜ ሳለ ማህተሟ ጓ! ሲል ሰማሁ፡፡ በመጨረሻ ግቢ ተባልኩ፡፡
- አመሰግናለሁ አልኳት ፈገግ ብዬ፡፡
እሷም ፈገግ ብላ ‹‹ መልካም ጊዜ! ›› አለችኝ፡፡ ከአውሮፕላን ማረፊያው ስወጣ አየሩን በረጅሙ ሳብኩ፡፡ አዲስ ሃገር
ስሄድ የከተማውን ሽታ ለማወቅ የማደርገው የተለመደ ነገር ነው፡፡
አንዳንድ ከተሞች አበባ አበባ ይሸታሉ፡፡ አንዳንድ ከተሞች ቅመም ቅመም ይሸታሉ፡፡ አንዳንድ ከተሞች ባህር ባህር ይሸታሉ፡፡ አንዳንድ ከተሞች ደግሞ ብዙ አይነት ነገር ይሰነፍጣሉ፡፡ አሰመራስ? አስመራ ንፁህ ንፁህ ነው የምትለው፡፡ ንፁህ ንፁህ ብቻ፡፡ አብርሃም አፈወርቂ አስመራ ፃእዳ እያለ ሲዘፍን ውሸቱን አልነበረም፡፡ አስመራን ያየ ሁሉ ስለንፅህናዋ አውርቶ የማይጠግበው አለነገር አይደለም ብዬ ገመትኩ፡፡ ስሜን ይዞ ይጠብቀኛል ያልኩት ሰው መዘግየቱን ያወቅኩት ንፁሁን ሽታ ምጌ ምጌ ስጨርስ ነው፡፡ የት ሄደ? በምሽት በሰው ሃገር ለማን ትቶኝ ሄደ? አስር ደቂቃ በላይ ጠብቄው ሲቀርብኝ አንዱን ወዲህ ወዲህ የሚል ረጅምና ቀይ ወጣት ጠጋ ብዬ
- ይቅርታ…አማርኛ ትችላለህ? አልኩት
- ሰላም እህቴ…አዎ እችላለሁ…ምን ላግዝሽ ? አለኝ ቅልጥፍጥፍ ባለ አማርኛ፡፡
ጎሽ!
- ታክሲዬ ቀረብኝ…ስልክ ትደውልልኛለህ? አልኩት በማስተዛዘን፡፡
- ምን ችግር አለ? ቁጥሩን አምጪ…አለኝ ቶሎ ብሎ፡፡ ቁጥሩን ሰጥቼው ስልኩን የሚስጥር ቁጥር ሲያስገባ የስልኩ ስክሪን ሴቨር የጠቅላይ ሚንስትሬ ፎቶ መሆኑን ሳይ ፈገግ አልኩ፡፡ ደውሎ በትግርኛ ሲያወራ የሚለውን ለመገመት እየሞከርኩ አየዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ትግርኛ ትንሽ ትንሽም ቢሆን ይገባኛል ብዬ አስብ ነበር፡፡ የኤርትራው ይለያል ልበል?
ጨርሶ ዘጋ፡፡
- እ? እየመጣ ነው? አልኩት
- አዎ…ትንሽ ዘግይቶ ነው…ይመጣል…ያዲሳባ ልጅ ነሽ? አለኝ
- አዎ…
- አዲስ እንዴት ናት?
- ምንም አትል አልኩ የሰሞኑን ነገር እያሰብኩ…
- እኔ አዲሳባ ነው የተወለድኩት…አለኝ ቶሎ ብሎ
- ተው ባክህ! የት አካባቢ? በጉጉት ጠየቅኩት
- ቄራ! ጦርነቱ ሲመጣ ነው እዚህ የመጣሁት…
- ፐ! ታዲያ አሁን አትመጣም?
- አዎ እመጣለሁ…ገንዘብ እያጠራቀምኩ ነው፡፡ አለኝ ወደ ቢጫ ታክሲ መኪናው እያሳየኝ፡፡ ዘናጭ ሁንዳይ ናት፡፡
ሳቅ ብዬ ዝም ስል
- ኤረፖርት ስራ የሚደርሰን በሁለት አመት አንዴ ነው….ስራ ስላለኝ ተቼሽ ልሄድ ነው ይቅርታ….አለኝ ግር አለኝ፡፡
- በሁለት አመት አንዴ? ለምን? አልኩ ሳይነግረኝ እንዳይሄድ ተጣድፌ
- ዘጠኝ መቶ ምናምን መኪና ነው ያለው…ብዙ ስራ ስለሌለ በሁለት
አመት ነው ሚደርሰን…ለአስራ አምስት ቀን…ቆይ.. መጣሁ አንዴ….
ሄደ፡፡ ባለፈው የቦሌ ቢጫ ታክሲዎች በሳምንት ሁለቴ ስሩ ሲባሉ ለአቤቱታ ኢቲቪ መሄዳቸውን አስታውሼ በንፅፅሩ ተገረምኩ፡፡ ከሌላ 10 ደቂቃ በኋላ ፊልሞን መጣ፡፡ ፊልሞን አስመራን ሊያሳየኝ የተዋዋልኩት ወጣት ነው፡፡ ስለመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቆኝ በቀይ መርቼዲሱ ፍስስ እያልን ወደ ከተማ ገባን፡፡ አስመራን በጭለማ ተዋወቅኳት፡፡ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶቿን፣ ሶቶ ተያይዘው የሚሄዱ ጥቂት ወጣት ፍቅረኞቿን፣ መንገድ ላይ በዝተው የሚታዩ ባለ ከዘራ አዛውንቶቿን፣ ሰፋፊ ሻማ ቀሚስና ነጠላ ለባሽ አሮጊቶቿን፣ ብዙ ቢጫ ታክሲዎቿን፣ ቀይ አውቶብሶቿን እና እነዛ ዝነኛ ዘምባባዎቿን ለመጀመሪያ ጊዜ አየኋቸሁ፡፡ ነግቶ በብርሃን እስካገኛቸው በጭለማ ተዋወቅኳቸው፡፡
(ይቀጥላል)

@paappii
@wegoch
#ልጆች_ጥላቻን_አያውቁም_ካላስተማርናቸው የሚለውን የEBS ማስታወቂያ ሠምቼ  የእህቴን ልጅ ስለፍቅር እየተፈላሰፍኩበት ፍቅርን ላስተምረው አሰብኩና እስኪና #አኪያሞስዬ ብዬ ፍልስፍናዬን መጀመሪያ መንገድ ሳመቻች በልጅነቴ አዋቂዎች በመጡ ቁጥር  የሚያሰለቹኝ ጥያቄ ትዝ አለኝና
 
አኪዬ ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለ ስለው?
= ሐይለኛ! ሠው የሚፈራኝ አለ

እኔም ፈራሁት! ዕልሙን ጀመርኩለት መሠለኝ ድንጋጤዬን ላብ አጀበው ቆይ ለምን? አልኩት
= በዕቃቃ ባልና ሚስት ስንጫወት  ሁሌ ሄምዳን ከእኔ ፊሊን ነው ባሏ የምታረገው ኃይለኛ ስላልሆንኩ
አለኝ ከየት መጣ የሚባል የሳቅ ማህበል ቢያናውጠኝም
እንደምንም አፍኜ ቆይ እሺ ኃይለኛ ስትሆን ምን ታረጋለ?
= ሄምዳንን አገባና የዕቃቃ ልጆች ወልጄ መጫወት

#ማርያምን¡ አሁን አልቻልኩም ጥርሴና ድምፄ ባማይታወቅ ኃይል ተፈንቅለው ቤቱን አጥለቀለቁት እሱም አፍሮ ነው መሠለኝ ማሚ እያለ የእናቱን ጉያ መሸገ  ሳቄ ግን እምባን እየጋበዘ ጥንብዝ ብሎ እራሱን ሳቀ አይ ልጅነት በቃ ባዶ እኮ እንደነ እገሌ Activist ባዶ ምንም የማያውቅ እንደው እነሱስ ክፋት ያውቃሉ እሱ ክፋት የለ ምን የለ ባዶ ባዶ ባዶ አለች ቤቲ ጂ
ግን አውንም አባብዬ ከእናቱ ጉያ እጄ ስር አስገባውና አሁንም ፍቅርን ላስተምረው ቆይ ኢንጅነር አቶንም? 
= አረ ቢገሉኝስ ሲል

ጭው አልኩ የሆነ ትንሽ አካል ውስጥ የተደበቀ ትልቅ ሠው መሠለኝ ይሄ ለኔ አዲስ ነበር እኔ የማውቀው ሚዲያውን ያጥለቀለቁት በትልቅ አካል ስር ያሉ ትንሽ ሠዎችን ነበር ጉዴ ፈላ ዛሬ ለታሪክ ነው ያለወትሮዬ ያፈላሰፈኝ ብዬ ለመቀጠል አልኩና እኔም ያልገባኝን ኢንጂነሩ ለምን? በማን? እንዴት? ለሚሉት ጥያቄዎች የተሳሳተ ሶፍትዌር መጫን ስላልፈለኩ አቅጣጫዬን ቀይሬ እሺ ዶክተርስ መሆን? ስለው
= እንደ ዶ/ር አብይ ከሆነ አልፈልግም አለ

በጣም ጓጉቼ ምራቄ ጆሮዬን እየሞላ ማነው አፌን እየሞላ ለምን እንዴ? አልኩ እየተለሳለስኩ
= እንዴ በድንጋይ ቢሉኝስ ደግሞ እኮ ቄ* ቢገለኝስ

ሲል አንተ የልጅ ቡዳ ብዬ በሀገራችን ልማድ የልጅ አዋቂዎች የመጨረሻ ህጣቸውን ቁጣ አከናንቤ የፍቅር ሌክቸሬን ፖለቲካዊና ታሪክ ቀመስ ኮርስ ሰጥቼ ለቀኩት
አሁን ቅስሜም ሻይ ልጠጣ የያዝኩት ብርጭቆም ተሰብሯል እንግዴ ሠው ልጅና ትውልድ እንደሚወልደው ሁሉ ሚዲያም አሉባልታም ትውልድና ልጅን ይወልዳሉ በዚህ ዕድሜው #አባይ_አባይ የሚለውን ዘፈን ሳይጠግብ የአባይ ግድብ ኢንጂነርን ሠው እንደገደላቸው አውቋል ማነው እንደሞቱ።
ዶ/ር የልጅነት አዋጅ የሆነ ምኞት ብቻ እንዳልሆነ ማወቁ ሳያንስ በመልክም በጥልቀትም ስለማያቃቸው እኚ መሪ ጠላቶች ግን የሠማውን ጠንቅቆ ዕውቀት አርጎታል
ምናልባት እናቱ፤ ምናልባትም አባቱ፤ አሊያ  ወተት ከተከራዩዋት ሴትዮ፤ ወይ ደግሞ ት/ቤት ከሚመላለስበት ላዳ ሹፌር ወይ ከላዳዋ ሬዲዮ ይሄን አሉባልታ  ሠምቶ ይሆናል ብቻ ከየትም ይስማ ግን ይሄ ልጅ ተቀርጿል ሁለቱን የፕላኔታችን ድንቅ የስራ ዘርፎች ደግሞ ላይመለስ ጠልቶና ፈርቷቸዋል አይለኛም የመሆን ሃሳቡ ምንጩ ክስተቶች በትውልድ ውስጥ ፣ ወሬዎች በትውልድ ላይ ፣ ሚዲያዎች በትውልድ ጫና ላይ የሚያሳርፉትን የጥላቻ፣የፍራቻ፣የክፋት በትር ያሳያል ዛሬ ኃይለኛ የሆነ ልጅ ነገ መግደል ለሱ ከዕቃቃ ጨዋታ ላይዘል ይችላል መዘርፍ የዕቃቃ ሚስቱን ከመቀማት ውጪ ሌላ ትርጉም አይኖረውም ምክንያቱም በጎዎቹ ምኞቶች ጥላሸትን ተኩለውበታልና
ሁሌም የምናወራውን የምንከፍተውን በልጆቻችን ፊት ልንመርጥ ይገባል ያ ማስታወቂያ እንድየው የኢቲቪው  #ምርጥ_ምርጡን_ለሕፃናት እንደዣ ነው ነገሩ
ወዳጄ አንድ ስትራመድ እርምጃክን ሁለቴ እየተራመድ የሚከተል ትንሽ ትውልድ እንዳለ አስብ !!!
ግን እኔ ሳድግ ምን ነበር ያልኩት  ምን ነበር እእ እንደ #ውቤ_ቢጫው መስከር ያውም በልኬ አረቄ እሱ እስካሁን ቦታውን ስላለቀቀ ትውልድ አልተተካምጉድ እኮ ነው
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ኢትዮጵያ_ከአሉባልታ_ውጪ_በክብር_ለዘላለም_ትኑር!!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
:- ተክለ ዮሀንስ
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና ምፅዋ ወግ
አስመራ- ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ
(ክፍል ሁለት)
---…..------
hiwot emishaw
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ለስድስት ቀን ቆይታዬ በፊልሞን አማካኝነት ወደተያዘልኝ አምባሳደር ሆቴል ገባሁ፡፡ የእንግዳ መቀበያውና በኋላ ያየሁት በስተግራ ያለው ሻይ ቤት ነገረ ስራው ሁሉ የፒያሳውን ቶሞካ አስታወሰኝ፡፡ ሞቅ ባለ ሁኔታ የተቀበለኝ አስተናባሪ ሻንጣዬን ይዞ ክፍሌን የሚያሳየኝ ጎልማሳ መድቦልኝ አሳንሰሩ ጋር ሄድን፡፡ እጅግ ጥንታዊ ነው፡፡ ተሸራርፈው ያለቁ ከሚመስሉ ድርድር ቁልፎች ውስጥ አንዱን ተጫነው፡፡ የተጫነው ቦታ ቀይ መብራት በራ፡፡ ‹‹እየመጣ ነው›› አለኝ ጎልማሳው ፈገግ ብሎ፡፡ ድምፁ ግን ተምዘግዝጎ ይከሰከስ ይመስል ያስፈራል፡፡ ክፉኛ ያጓራል፡፡ ያቃስታል፡፡ በመጨረሻ ደረሰና ገባን፡፡ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ሶስት መካከለኛ ስፋትና ክብደት ያላቸው ሰዎች ቢይዝ የሚሞላ አይነት ጠባብ፡፡ እያቃሰተ አምስተኛ ፎቅ ደረስንና ክፍሌን ከፍተን ገባን፡፡ ረጅምና ሰፋ ያለ ኮሪደር ተቀበለኝ፡፡
በስተቀኝ ከአዲስ አበባ ቤቴ ሳሎን የሚስተካከል ሰፊ መታጠቢያ ቤት አለ፡፡ ሮዝ ቀለም ባላቸው ሴራሚክ የመታጠቢያ ቤት እቃዎች አሸብርቋል፡፡ ሰፊ ሮዝ ገንዳም አለው፡፡ ከእሱ ቀጥሎ ጠበብ ያለ ሳሎን ውስጥ ቢጫ የቆዳ ሶፋ ተቀምጧል፡፡ ሌላ ነገር የለውም፡ በስተግራ ደግሞ ሰፋ ያለ መኝታ ክፍል አለው፡፡እቃዎቹ ዘመናዊ አይደሉም፡፡ አልጋው ይንቋቋል፡፡ ወንበሩ ያቃስታል፡፡ ኮመዲናው ይንገዳገዳል፡፡ ኮመዲኖው ላይ ያለው ቴሌቪዥን ዘመን ያለፈበትና በድብደባ ምስል የሚያመጣ ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ቢሆንም ማረፊያዬ ንፁህና ቁጭ በሉብኝ በሉብኝ፣ ተኙብኝ ተኙብኝ፣ እረፉብኝ እረፉብኝ የሚል አይነት ነው፡፡ የመኝታ ቤቴን መስኮት መጋረጃ ከፈትኩ፡፡ ዝነኛው…ከልጅነታችን አንስቶ የአስመራ ፖስትካርድ ላይ የምናየው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ካቴድራል ከነ ሙሉ ግርማው ይታያል፡፡ በደስታ መጮህ አማረኝ፡፡ ከነደስታዬ አልጋው ላይ ሄጄ ዘፍ አልኩ፡፡ ፍራሹ ሰመጠ፡፡ አልጋው አቃሰተ፡፡ ማታ ላይ ፊልሞን እና የሃያ አመት ወጣት የሆነው ወንድሙ እራት ይዘውኝ ወጡ፡፡ ነጮች የሚበዙበት ለቅንጦት የቀረበ ቤት መሆኑን ስመለከት ከፋኝ፡፡ - እኔ ማየት የምፈልገው ሁሉም ሰው የሚሄድበትን ቦታ ነው..እንደዚህ አይነት ቦታ አታምጣኝ አላልኩም? አልኩት- ለዛሬ ብቻ ነው…ከነገ ጀምሮ እንዲህ አይነት ቤት አንሄድም አለኝ ፊልሞን፡፡ ፊልሞን ጥርት ያለ አማርኛ ቢናገርም ወንድሙ ሳሚ ግን ጆሮውን ቢቆርጡት አይሰማም፡፡ ቢነቀንቁት አይናገርም፡፡ እድሜውን ላገናዘበ አስገራሚ አይደለም፡፡ ከሳሚ ጋር በእንግሊዝኛ፣ ከፊልሞን ጋር በአማርኛ፣ ከአስተናጋጆቹ ጋር ( ፊልሞን በይ በይ እያለኝ ) በሚያስቅ ቁርጥርጥ ትግርኛ ሳወራ ዞረብኝ፡፡ አስመራ ውስጥ ስቆይ አማርኛን በተመለከተ ያገኘሁት ስብጥር አስገራሚ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ምንም እንኳን ከአርባ የዘለለ እድሜ ቢኖሩም አማርኛን ጨርሶ አያውቁም፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ቅኔ መዝረፍ ሲቀራቸው እንደ ውሃ ኩልል የሚል አማርኛ ያወራሉ፡፡ ብዙዎቹ ከ25 አመት በታች የሆኑ ልጆች አማርኛ አይችሉም፡፡ አንዳንድ በአስራ ቤትና እስከ ሃያ መጨረሻ ያሉ ደግሞ አቀላጥፈው ይናገራሉ፡፡ ፊልሞን ይህንን ሁኔታ እንዲያስረዳኝ ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡፡ ‹‹አየሽ ኤርትራ ውስጥ በተለይ አስመራ ውስጥ ሶስት አይነት አማርኛ ተናጋሪዎች አሉ፡፡ አምቼ፣ ሰምቼ እና አብይቼ ይባላሉ›› ብሎ ጀመረ፡፡ ‹‹አምቼ ኢትዮጵያ ተወልደው፣ ኢትዮጵያ አድገው፣ ኢትዮጵያ ኖረው ስንጣላ እዚህ የመጡ ናቸው፡፡ እነሱ እዛ በመኖራቸው አማርኛ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሰምቼ የሚባሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ቲቪ በተለይ ቃና እያዩ አማርኛን ብዙ ጊዜ በመስማት የቻሉ ናቸው፡፡ አብይቼ የሚባሉት ደግሞ ዶክተር አብይን ከመውደዳቸው የተነሳ እሱ የሚለውን ለመስማት አማርኛ መማር የጀመሩ ናቸው…›› ብሎ አስረዳኝ፡፡ ከዚህ በኋላ የተለያዩ ሰዎች ምፅዋም አስመራም በአማርኛ ሲያወሩኝ ይሄኛው አምቼ ነው…ይሄ አብይቼ ነው…ይህች ደግሞ ሰምቼ እያልኩ መቦደን ጀመርኩ፡፡
-------
እንዴት አደርሽ አስመሪና? በነጋታው አስመራን በብርሃን ለማየት ማልጄ ነቃሁ፡፡ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ካቴድራሉ ደወል ሲደውል ሰማሁ፡፡ በኋላ እንደሰማሁት ይሄ ደወል በየሰላሳ ደቂቃው ይደወላል፡፡ የአካባቢው አጃቢ ሙዚቃ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ቁርሴን ሆቴሌ በልቼ ወጣሁ፡፡ ፊልሞንን ሶስት ሰአት ላይ አግኝቼ መደበኛ ጉብኝቴን እስክጀምር አላስችል ብሎኝ መራመድ ጀመርኩ፡፡ ካቴድራሉ ደረጃዎች ላይ ብዙ ሰዎች ተቀምጠው አየሁ፡፡ ጥቂቶቹ ጋዜጣ ይዘዋል፡፡ በኋላ ላይ እንደተነገረኝ በኤርትራ አንድ ለእናቱ የሆነውን ሃዳስ ኤርትራን ነው የሚያነቡት፡፡ ሌሎቹ አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ያወራሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ዝም ብለው አላፊ አግዳሚ ይቃኛሉ፡፡ ያልተለመደ ሆነብኝ፡፡ አስፋልቱን ተሻግሬ አንዱ ደረጃ ላይ ተቀምጬ እንደገና አየኋቸው፡፡ ጋዜጣ የሚያነቡ፣ ከሌላ ሰው ጋር የሚያወሩ፣ አላፊ አግዳሚውን የሚቃኙ፣ ዝም ብለው የተቀመጡ እንጂ ብዙ ከተማ እንደተለመደው ስልካቸው ላይ ያቀረቀሩ ሰዎች የሉም፡፡ በስተቀኝ ወዳለው የአውቶብስ ፌርማታ ተመለከትኩ፡፡ ያው ነው፡፡ ሞባይላቸው ላይ የማያቀረቅሩት ኤርትራ በሞባይል ስልክ ኢንተርኔትን ማቅረብ ስላልጀመረች ነው፡፡ እየቆየሁ እንደተረዳሁት አስመራ ለኑሮ ውድ ከተማ ብትሆንም የኢንተርኔት ብርቅነትና ውድነት ግን አቻ የለውም፡፡ በከተማው በብቸኝነት ኢንተርኔት አገልግሎት የሚያቅርቡት ተቋማት የኢንተርኔት ካፌዎች ሲሆኑ በቁጥር ብዙ በአገልግሎት ግን ውስን እና ውድ ናቸው፡፡ እየተቆራረጠ ጨጓራ ለሚልጥ ኢንተርኔት በሰአት ወደ አርባ ብር ገደማ ያስከፍላሉ፡፡ የባህር በር ያለው ሃገር ምንም እንኳን በሞባይል ባይሆንም በተገኘ ጊዜ ግን ጀት የሆነ ኢንተርኔት ይኖረዋል የሚለው ግምቴ አፈር የበላው ወይ ከቤተሰብ ለመገናኘት፣ ወይ እንደ ገበቴ ውሃ የሚዋልለውን የሃገሬን ሁኔታ ለመከታተል በሰአት 40 ብር ለኢንተርኔት ካፌዎች ስከፍል ነው፡፡ ያም ሆኖ ስልክ ላይ የሚያቀረቅር ህዝብ አለመኖሩ ከተማዋን ሕይወት ሰጥቷታል፡፡ ካፌ ስትገቡ ሰው አብሮት ካለው ሰው ጋር ይጫወታል እንጂ ስልኩ ላይ አያቀረቅርም ፡፡ ቢራ ይዞ ከወዳጁ ይስቃል እንጂ ስልኩን አስሬ አይነካካም፡፡ ከመንገድ ኬክ ቤት ተቀምጦ ኬኩን በሻይ እያማገ ከአልፎ ሂያጅ ውስጥ የሚያውቀውን ሰው አይቶ ና ተቀመጥ እያለ ያግደረድራል እንጂ ከቅርብ ሰው ተነጥሎ ከሩቅ አይገናኝም፡፡
የሆነ ደስ የሚል..እኛ ያጣነው እነሱ ግን የያዙት ነገር እንዳለ ተሰማኝ፡፡ ፌስቡክን ከፍቶ ወሬ የማየት ጉጉቴ ሰቅፎ ቢይዘኝም እፎይታ ግን ተሰማኝ፡፡ ፊልሞን እስኪመጣ ቁጭ ብዬ አላፊ አገዳሚውን ስመለከት ሌላ ነገር አስተዋልኩ፡፡ ሁሉም ሰው እቃውን ይዞ ላይ ታች የሚለው በተመሳሳይ ከቃጫ የተሰሩ ከረጢቶች ወይ ደግሞ በተሸለሙ ዘምቢሎች ነው፡፡ ዘምቢል ትዝ ይላችኋል? ፊልሞን ሲመጣ ጠየቅኩት፡፡ ‹‹እዚህ ሃገር ፌስታል ተከልክሏል፡፡ አስር አመት ሆኖታል›› አለኝ፡፡ አስመራን እየወደድኳት ነው፡፡ አስመራን በጣም እየወደድኳት ነው፡፡
(ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
ቲፎዙ ካለህ!!!

# # ብትወድቅም አልፏል ትባላለህ፤
# # መጨረሻ ብትወጣም አንደኛ ወጣ ትባላለህ፤
# # ብትንተባተብ አፌ ቁርጥ ይበልልህ ትባላለህ፤።
# # ንግግርህ ድፍርስ ቢመስልም እንደ በጋ ጅረት ኩልል አድርጎ አፈሰሰው ትባላለህ ።
# # ግራ ቢገባህ ቀኝ ቀኙን አሳያቸው እኮ ተብሎ ይወራልሃል።
# # ምላስህ ቢተሳሰርም ንግግሩ አፍ የሚያስከፍት ነበር ትባላለህ ።
# # ሰነፍና ሃኬተኛ ብትሆንም ሌትና ቀን የሚለፋው ታጋይ ትባላለህ።
# # ንፉግ ብትሆንም አባ መስጠት ትባላለህ።
## ጅራት ብትሆንም ራስ ነው ተብሎ ይታወጅልሃል ።
## ፉንጋ ብትሆንም ""ማማሩ ልክ የለው "" ተብሎ ይሰበክልሃል ።
እናም ዋናው ነገር የቲፎዞ ብዛት ነው ያሰኝሃል ። ባይሆን በቲፎዞ የተሰቀለ ተመልሶ በቲፎዞ
ይፈጠፈጣል ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ፓንዲ(ልዑል ሀይሌ)
.
ክፍል ፩
.
“ዛሬ የምንማማረው ስለ ኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ነው” ይላል አጠር ያለው መላጣ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን “ዛሬ የምማረው ስለ ፓንዶራ ጥልቅ ዓይኖችና የሰውነት አቀማመጥ ነው”(እኔ) አቤት ፓንድዬንኮ ስወዳት ለጉድ ነው፡፡ ይኸው ስለምወዳትምኮ ነው ሁሉም የክፍላችን ተማሪዎች(እሷን ጨምሮ) ስለ ኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ሲማሩ እኔ ስለ እሷ አቀማመጥ በተመስጦ የምማረው…
“ኢትዮጵያ የምትገኘው በምስራቃዊው የአፍሪካ ቀንድ ሲሆን በሰሜን ኤርትራ ፤ በምስራቅ ጅቡቲና ሶማሊያ ፤ በምዕራብ ሱዳን፤ በደቡብ ደሞ ኬንያ ያዋስኗታል” (አጭሩ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን) “ፓንዶራ የምትገኘው በክፍላችን ሁለተኛው መደዳ አራተኛው ወንበር ነው፡፡ ከፊት እነ ጀሚላና ቶማስ፤ ከኋላ እነ ሳምሶንና ትዕግስት፤ በግራዋ
በኩል ከድር በቀኟ ደሞ እኔ አፍቃሪዋ እናዋስናታለን” (እኔ) የሌሎቹን ባላውቅም እኔ ግን የሷ አዋሳኝ በመሆኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡ በርግጥ አንድም ቀን እንደምወዳት ነግሬያት ወይም በሰፊው አጫውቻት ባላውቅም እንደዚሁ ሳያት መዋሉ በራሱ በደስታ
ያንሳፍፈኛል፡፡ ከፓንዲ ጋር እንድቀመጥ የረዳኝ ይሄ ደግሞ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን ስለሆነ ውለታውን ለመመለስ በሚል የኔን የፍቅር ውሎ
ከሱ ትምህርት ጋር እያዛመድኩኝ ቀኑን ሙሉ አሰላስላለሁ፡፡ በዚህም ጂኦግራፊ ትምህርቴን ሁሌም እንደደፈንኩኝ ነው፡፡ምክንያቱም ሳጠና ከፓንዲ ጋር እያዛመድኩኝ ስለሆነ መቼም አልረሳውም….እንዴት ብዬ?….ጂኦግራፊን ከፓንዲ ጋር አዛምጄ ….ፓንዲ እንዴት ትረሳለች?..ኧረ በጭራሽ!! ፓንዲን እርሳት ከምትሉኝ ራስህን እርሳ ብትሉኝ ይቀለኛል፡፡
ለነገሩ ራሴንማ ከረሳሁት ቆየሁኝ…..ምግብ ዘግቶኝ እኛ ቤት ያለወትሮው እንጀራ መሻገት ጀምሯል፡፡ (እኔ ነበር የማወድመው ለካ!) ልብስም ከሰፈራችን አንደኛ ለባሽ የነበርኩት ልጅ አሁን ግን ከዩኒፎርሜ ውጪ ምንም አይነት ልብስ መልበስ አስጠልቶኛል፡፡ ምክንያቱም ፓንዲን ያገናኘኝ ይሄ ዩኒፎርም ስለሆነ አልቀይረውም፡፡ ፓንዲን
ልቀይራት?!..አይደረግም!! …..ደሞም ልብስ ሆኖ የሚያሞቀኝ ምትሃታዊ ፍቅሯ ወዴት ሄዶ?!....ደብተሮቼን እንዳለ ብታዩዋቸው በተወጉ የልብ ቅርፆች ያሸበረቁ ናቸው፡፡ ሁሉም አስተማሪዎቻችን የየራሳቸውን ትምህርት በፅሁፍ ሲያስገለብጡን ‘P’ የሚለውን ፊደል በተለየ ውበት ተለቅ አድርጌ
በጥንቃቄ ነው የምፅፈው….ብቻ ምን ልበላችሁ እንቅስቃሴዬ ሁሉ በፓንዶራ ዙሪያ ነው፡፡…….በዚህ ሃሳብ መሀል እያለሁ የሆነ ነገር ሲነካኝ ተሰማኝና ብንን አልኩኝ(ጂኦግራፊ አስተማሪያችን ነበር ተጣርቶ አልሰማ ስለው በቾክ ወርውሮ ከገባሁበት ጣፋጭ ህልም የቀሰቀሰኝ)
“በል እንጂ መልስ!!”…..በድንጋጤ የማደርገው ነገር ሲጠፋኝ የክላሳችን ተማሪዎች በሙሉ ሳቁብኝ…..ድዳቸው ለሙቅ…..ለነገሩ እነዚህ ሙቅም ሙድም አይገባቸውም……ግልፍጥ ሁላ ጥርሱን
መክፈቻ ያድርገኝ?…. “አንተንኮ ነው!!... በዓለም በቆዳ ስፋት ትንሿ ሃገር ማናት?”
ሲለኝ ወዲያው በድንጋጤ ከአፌ የመጣልኝ የምወደው ቃል አሟለጨኝ
“ፓንዶራ!....” አልኩና የክላሱ ተማሪ ሲያፈጥብኝ “ፓንዶራ የምትባል ሃገር” ስል መምህሩ የሹፈት ሳቅ ሳቀና “ፓንዶራ የት ነው የምትገኘው? …” ሲለኝ ካጠገቤ ልለው አሰብኩኝና መልሼ ዋጥኩት “እዚህ (በአፌ ወደ ፓንዶራ አቅጣጫ እያመለከትኩኝ) ምዕራብ አፍሪካ” ስል መምህሩ በንዴት በሱ ክላስ እንዳልገባ አስጠንቅቆ ወደ ውጪ አስወጣኝ፡፡ ቆይቼ
ስሰማ ፓንዶራ ሳይሆን አንዶራ የምትባል ሃገር አውሮፓ ውስጥ እንደምትገኝ አወቅኩኝ፡፡እኔ ታዲያ መች አወቅኩኝ የኔዋ ፓንዲን እንጂ ሀገሪቷን ከየት አመጣታለሁ ምን አይነት ክፉ አጋጣሚ ነው? …… ከፓንዲ ጋር ያቆራኘሁት ጂኦግራፊ አለመማር ማለት ወፌ ላላ ተሰቅሎ 400 ጅራፍ መገረፍ ማለት ነው፡፡ ….ለነገሩ ፓንዲ እንደሆነች ሁሌም
ከጎኔ አለች ስለዚህ ከሌላ ትምህርት ጋር ለምን አላቆራኛትም አልኩና ከባይሎጂ ትምህርት ጋር ማቆራኘት ጀመርኩኝ…
ቻው ቻው ጂኦግራፊ!!....አንተ መላጣ አስተማሪ ምን ይዋጥህ?…ምንም!!..ባይሎጂ አስተማሪያችን እንደ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን መላጣ አይደለም፡፡ ደስ ሲል!!... ሴት ነች ፀጉሯ ወርዶ ወርዶ ሲቆጨው መሰለኝ ተመልሶ ወጥቶ ከጆሮዋ በላይ ተሰንቅሯል፡፡
መምህርታችን ጋዋኗን አውልቃው አታውቅም …እስከዛሬ በሌላ ልብስ
አይቻት አላውቅም፡፡ ወይ ማን ያውቃል እንደኔ ጋሽ ፎንቃ ሰፍሮባት ይሆናላ!!....በኔም ስለደረሰ አልፈርድባትም ታፍቅር…..ብቻ ግን ያንን
የፓንዲን ስም ያቀለለውን ጂኦግራፊ አስተማሪያችንን አፍቅራ እንዳይሆንና ፊልድ እንዳልቀይር!!...ለነገሩ ምኑ
ይፈቀራል!...በቴሌስኮፕ ካላየችው
ለዓይኗም አይሞላ!!....ቴሌስኮፕ ደሞ እኛ ትምህርት ቤት የለም ደስ ሲል!!...ምን ይዋጥህ ጂኦግራፊ አስተማሪያችን ….ምንም!..... “ዛሬ የምንማማረው ስለ ሴክሹዋል ሪፕሮዳክሽን” ስትል 'ቱ! ቲቸር ምን አይነት ባለጌ ነች?' እያሉ በሳቅ በመጎሻሸም በእፍረት ያዩዋታል
ከፊታችን የተቀመጡት እነ ቶማስ… .ግማሹ የክላሱ ተማሪዎች ደሞ
በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ምዕራፍ በመድረሱ ዓይናቸው ተጎልጉሎ ሊወጣ ምንም አልቀረውም “ሴክሹዋል ሪፕሮዳክሽን ማለት ዘርን ለመቀጠል ስለሚረዱ የመራቢያ አካላት የሚያጠና ነው፡፡ ለምሳሌ በሰው ልጅ ስናየው ሴቷም ወንዱም የየራሳቸው የመራቢያ አካላት አሏቸው፡፡ እስቲ ከወንዱ የመራቢያ አካል እንጀምር!!...” ስትል ክፍላችን በተቃውሞ ሹክሹክታ ታመሰ “ምንድነው ሚያንሾካሹካችሁ?” ….የክፍላችን ደፋር ተናጋሪ ቢኒያም ተነስቶ ፀጉሩን እየጠቀለለ “አይ ቲቸርዬ!..ማለት ቅድሚያ ለሴቶች በሚለው ህግ መሰረት ከሴቶች ቢጀመር አሪፍ ነው!!” ሲላት ባይሎጂ አስተማሪያችን በንዴት “ና ውጣ!!..ከዚህ በኋላ በኔ ክላስ እንዳላይህ!...” ቢኒያም ከወጣ በኋላ ቀጠል አድርጋ “የወንድ የመራቢያ ክፍል ዘር ሲያዘጋጅ ሴቷ ደሞ እንቁላሉን ታዘጋጃለች ማለት ነው፡፡….የወንዱ የመራቢያ አካል (ባይሎጂ መፅሀፍ ገለጥ ገለጥ አደረገችና) ከፍ
አድርጋ ወደኛ አዙራ መለመላውን ስታሳየን ሴቶች በኩራት ሲሳለቁብን እኛ ወንዶች በመሸማቀቅ አጀብናት፡፡ “ለነገሩ ፎቶ አስነስቶ ያዋረደንኮ በየሰፈሩ ቱቦ በጠራራ ፀሐይ የሚሸናው ወንድ ነው ምናለ ምች ባጣመመለት!!...መዘዝ አድርጎ ሲያወጣውኮ ሻሞላ የመዘዘ ጀግና የሆነ ነው ሚመስለው” ይላል የክፍላችን ሰቃይ ተማሪ ከድር ከጎኔ
ስለሆነ ሹክሹክታውም ይሰማል፡፡
በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ የክፍላችን አብዛኞቹ ሴቶች የኛን በማየታቸው
ተደስተው ይሁን ምን ይሁን ሲገለፍጡ ፓንዲ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብላ ትከታተላለች….አይ ፓንዲ! ጨዋ!! የጨዋ ልጅ!! የጨዋ የልጅ ልጅ ልጅ!!....ለዚህ እኮነው የምወዳት
ጨዋነቷ!...


(ይቀጥላል......)

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ቅንጥብጣቢ የአስመራ እና የምፅዋ ወግ አስመራ-ከተወራላት በላይ የምታምረው ከተማ

(ክፍል ሶስት)
አዲስ አበባ እና አስመራ በብዙ ነገር የተለያዩ ከተሞች ይሁኑ እንጂ በተለይ የድሮዋን አዲስን ለሚያውቅ ሰው የአስመራን መልክ መገመት የሚከብድ አይመስለኝም፡፡ እስቲ ድፍን ፒያሳን አስቡ፡፡ ብሄራዊ ቲያትር አካባቢን፣ አምባሳደር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢን ጨምሩ፡፡ ሜክሲኮ የድሮውን ካምቦሎጆ ሰፈር አክሉ፡፡ አይን የሚጣጥበረብር መስታወት ያላቸውን ረጃጅም ፎቆች አንሱና ከአራት ፎቅ በማይበልጡ የድንጋይ ዝም-ያሉ ህንፃዎች ተኩ፡፡ ከዚያ መንገዶቹን ሰፋ ሰፋ አድርጉና በጣም ረጃጅምና ያልተጎሳቆሉ የዘምባባ ዛፎችን ትከሉባቸው፡፡ እነዚህ መንገዶችን ሙልጭ አድርጋችሁ ጥረጉ፡፡ መጥፎውን ሽታ አስወግዱ፡፡ የእግረኛ መንገዱን በጣም አስፉ፡፡ እዚህም እዚያም ያሉትን የግንባታ ስራዎች አጥፉ፡፡ በየቦታው የተከመረውን አሸዋና ብሎኬት አንሱ፡፡ የካፍቴሪያ ወንበሮችን ከሰፋፊ እግረኛ መንገድ ጥግ ጥግ አስቀምጡ፡፡ በጥድፊያ ወዲህ ወዲህ የሚለውን ህዝብ ቁጥር በጣም አሳንሱና ቀስ ብሎ እንዲራመድ አድረጉ፡፡ አሁን ያሰባችሁትን ቦታ በአይነ ህሊናችሁ ሳሉ፡፡ አስመራ በአብዛኛው ይሄን ትመስላለች፡፡
እያሰቡ መሄድን (ቢያሻ ሜዲቴት እያደረጉ) የምትፈቅድ፣ ንፁህ እና
ለኑሮ ምቹ ከተማ ነች፡፡ ጫጫታ የላትም፡፡ የመኪና ጥሩምባ አያንባርቅባትም፡፡ አቧራ አይበዛባትም፡፡ የመኪና ሰልፍ አያጨናንቃትም፡፡ እዚህም እዚያም የሚሰሩ አዳዲስ ግንባታዎች በጭራሽ አይታዩባትም፡፡ አብዛኛው የከተማ ክፍል በዩኔስኮ ቅርስነት ስለተመዘገበ አዲስ ግንባታ ማካሄድ ክልክል ነው፡፡ በዚህ የተነሳም አስመራ በአመዛኙ ጣሊያን ኤርትራ ለሃምሳ አመታት ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ ያነፃት ትንሽዋ ሮማን ሆና ቆይታለች፡፡ ያም ሆኖ በቅኝ ግዛት ዘመን የሃገሬው ሰውና ጣልያኖች ይኖሩባቸው የነበሩ ሰፈሮች ልዩነት ዛሬም ድረስ ጎልቶ ይታያል፡፡ ልክ እንደ አዲስአበባዎቹ ካዛንችስና ፒያሳ የህንፃዎቹ ውበት፣ የመንገዶቹ ስፋት፣ የቤቶቹ ጥበትና የፎቅ ብዛት ዛሬም ልዩነቱን ያሳብቃል፡፡ አባሻውልን (የአስመራ ጨርቆስን) አይቶ መሃል አስመራን ላየ ይሄ ልዩነት ዛሬም አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ፊልሞን ያለ እረፍት ሲያዞረኝ በአብዛኛው በእግሬ፣ በትንሹ በመኪና ያልዳሰስኩት የአስመራ ክፍል ያለ ለማለት ይከብደኛል፡፡ ከሲኒማ ኢምፔሮና ሮማ እስከ ብረት ተቀጥቅጦ ሁሉን ነገር እስከሚሆንበት መደብር፣ ከአስመራ ማዘጋጃ ቤት እስከ የ119 አመታት የእድሜ ባለፀጋው አልቤርጎ ኢታሊያና ሆቴል (በድሮ ስሙ ከረን ሆቴል)፣ በሽሮ እና አሳ ምግቡ ከሚታወቀው ቤት ምግቢ አስመራ እስከ ፋሚሊ ፒዛ ቤት፣ ከአባሻወል አስከ ኤርትራ ትልቁ ፖስታ ቤት፣ ከየአኬንሪኮ ኬክ ቤትን የሚመስለው ጆርዲኒዮስ የጥንት ኬክ ቤት (1960 የተቋቋመ) እሰከ ዶክተር አብይ በለስ የበላበት የምፅዋ መውጫ መንገድ ድረስ አካለልኩት፡፡ ሁሉንም ላወራችሁ ስለማልችል ፣ በዚህ ሁሉ ዙረቴ የታዘብኳቸው ጥቂት ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
1. (አ)ብይ በሃገሩ አይከበርም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአስመራ እንደ ድሮ የህንድ መሪ ፊልም ተዋናይ ነው፡፡ አሚታ ባቻን ነገር፡፡ ፎቶውን በየቦታው ማግኘት ብርቅ አይደለም፡፡ ፎቶ ቤቶች ላይ ከአዲስ ሙሽሮች በላይ አብይ አምባሻ በትሪ ሲያስይዝ የሚያሳይ ፎቶ ይገኛል፣ ፀጉር አስተካካዮች ጋር ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ሲተቃቀፍ የሚያሳይ ፎቶ ይለጠፋል፡፡ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ ከቅዱሳን ስእሎች አጠገብ ፎቶውና ጥቅሶቹ ተቀምጠዋል፡፡ በሰዎቸ ስልክ ላይ ስክሪን ሴቨር ሆኖ ያገለግላል፡፡ ምስሉ ተለበዶ በመንገድ ላይ ይሸጣል፡፡ አብዛኛዎቹ ያወረራኋቸው ሰዎች ለእሱ ያላቸው ፍቅር ጥልቅና ያልበረደ ነው፡፡ ‹‹ታድላችሁ›› ይሉኛል ስለሱ ማውራት ሲጀምሩ፡፡ ‹‹እግዜር ላከላችሁ›› ይሉኛል ስለሱ አውርተው ሲያበቁ፡፡
2. ህዝቡ ቀና እና እጅግ ተባባሪ ነው እንደገርኳችሁ አስመራን ከላይ እስከታች ሳስሳት ነው የከረምኩት፡፡ ነገር ግን አንድም ቦታ፣ አንድም ጊዜ ‹‹እዚህ መግባት አይቻልም፣ ተመለሱ፣ ዝግ ነው፣ አይፈቀድም›› አልተባልኩም፡፡ ሲኒማ ሮማን ውስጡን ለማየት ስንጠይቅ ምንም እንኳን ሰዎች ፊልም እያዩ ቢሆንም ቀስ ብለን እንድንገባ ተባብረውናል፡፡ ማዘጋጃ ቤት እስከ ቢሮዎቹ ድረስ ዘልቀን ስንገባ ‹‹የት ናችሁ…ከየት ናችሁ›› ብሎ ያዋከበን የለም፡፡ መንገድ ጠፍቶብኝ ግራ ስጋባ አማርኛ ባይቸሉ እንኳን ወይ ለሚችል ሰው ያስረከቡኝ፣ ወይ ጉዳያቸውን ትተው ራሳቸው እጄን ይዘው ያደረሱኝ ብዙ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆኔን ሲያውቁ የመጀመሪያ ጥያቄያቸው አንድ ነው፡፡
‹‹አስመራ እንዴት ናት?› ‹‹ቤላ ናት›› አላለሁ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ተመሳሳይ ጥያቄ ይጠይቁኛል፡፡ ‹‹ከአዲሳባ ትበልጣለች?›› ያኔ በውበትና ለኑሮ በመመቸት እንደምትበልጥ አስረግጬ እነግራቸዋለሁ፡፡ ብዙ ከኢትዮጵያ የሚመጣ ሰው አስመራ ፎቅ ስለሌለ ቅር እንደሚሰኝና ኋላ ቀር ከተማ ናት ብሎ እንደሚያስብ ይነግሩኛል፡፡ ለእኔ መዘመን ንፁህ መሆን እና ለሰው ኑሮ የሚመች ከተማ መሆን እንጂ ፎቅ መገንባት ብቻ አለመሆኑን ጨምሬ እነግራቸዋለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ሲስማሙ ሌሎቹ ደግሞ በአዲሳባ እንደሚቀኑ ይነግሩኛል፡፡ ምን ይደረጋል? ሰው የሌለውን ነው ሚመኘው፡፡
3. ሁሉም ሰው አነጣጥሮ መተኮስ ይችላል ሁሉም ኤርትራዊ የውትድርና ስልጠና ወስዷል፡፡ ይሄንን በተለይም ከማርቲን ፐላውት ‹‹Understanding Eritrea: Africa’s Most Repressive State ›› መጽሃፍ ቀደም ብረዳም በየምግብ ቤቱ፣ በየመንገዱ፣ በየሆቴሉ፣ በየአውቶብሱ ስሳፈር ትዝ እያለኝ እገረም ነበር፡፡ ለምሳሌ በአውቶብስ እየሄድኩ አውቶብሱ ውስጥ 30 ሰው ቢኖር ከ30ዎቹ ጠመንጃ መተኮስ የማልችለው እኔ ብቻ ነኝ እያልኩ አስቤ ፈገግ እል ነበር፡፡ ነገሩ የብሄራዊ አገልግሎት ውጤት ነው፡፡ ማርቲን ፕላውት ስለዚህ ጉዳይ አጀማመር ሲያወራ እንዲህ ይላል፡፡ …እ.ኤ.አ በ1995 የኤርትራ መንግስት ብሄራዊ አገልግሎትን የሚመለከት አዋጅ አወጣ፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት ማናቸውም ከ18 እስከ 50 አመት ያለ ኤርትራዊ ብሄራዊ አገልግሎትን የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ በተለይ ከ18 እስከ 40 ላሉ ሰዎች ይሄ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው፡፡ ማርቲን እንደሚለው የኤርትራ መንግስት ብሄራዊ አገልግሎትን የወጣቶችን የስራ ባህል እና ፍቅር መገንቢያ፣ የሃገር ግንባታ ብቸኛው አማራጭ ብሎ ያስቀምጠዋል፡፡ እንግዲህ ብሄራዊ አገልግሎትን የሚያስፈፅመው የመከላከያ ሚንስቴር ሲሆን አገልግሎቱን ላለመስጠት መኮብለል ወይ ደግሞ ሰበብ እየፈጠሩ ከምልመላ ራስን ለማግለል መሞከር ከባድ ቅጣት ያስከትላል፡፡ በኤርትራ ፓስፖርት ማውጣት ዛሬም እጅግ ብርቅ ከሆነባቸው ምክንያቶች አንዱ ይሄ ነው፡፡
መፅሃፉ እንደሚለው አዋጁ በወጣ ጊዜ የብሄራዊ አገልግሎት የጊዜ ገደብ 18 ወር ሲሆን ስድስቱ ወር በሰራዊትነት ማገልገል ቀሪው 12 ወር ደግሞ መንግስት በሚመድበው ቦታ ተገኝቶ ለነጻ የሚቀርብ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን አገልግሎቱ በ18 ወር የተወሰነ ሳይሆን ላልታወቀ ጊዜ የሚቆይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከአዋጁ ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ ብሄራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ብዙ ኤርትራዊያን አሉ፡፡ ሃያ አመት በላይ ማለት ነው፡፡ ከብሄራዊ አገልግሎት ቢወጡም ተጠባባቂ የሰራዊት አባል መሆን ግድ ነው፡፡ በዚህ የአገልግሎት ዘመን የኪስ ገንዘቡን በተመለከተ ግልፅ መረጃ ማግኘት ከባድ ቢሆንም በወር ከአምሰት መቶ ናቅፋ (ወደ አንድ ሺህ
የኢትዮጵያ ብር) ይከፈላል የሚለው ሳያስማማ አይቀርም፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ከመውረዱ በፊት ይሄ ግዴታ መቼ እንደሚነሳ የተጠየቀው መንግስት ኢትዮጵያ በማናቸውም ሰአት ትወረናለች የሚለው ስጋት እስካለ የመነሳት እድሉ አነስተኛ መሆኑን ተናግሮ ነበር፡፡ አሁን ይነሳ ወይ ይቀንስ ይሆን? በነገራችን ላይ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሴት ልጅ በኤሪቲቪ የብሄራዊ አገልግሎት እየሰጠች እንደምትገኝ ሰምቻለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ አንድ
የኢንተርኔት ካፌም ተቀጥራ ትሰራለች ብለውኛል፡፡
4. እንጀራው! ብዙዎቻችን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትጣላ የጤፍ ዋጋ ሰማይ እንደነካ ሰምተን ነበር፡፡ እውነት ነው፡፡ ይጋነን ይሆን አላውቅም እንጂ በአንድ ወቅት አንድ ኩንታል ጤፍ ከ6- 8ሺህ ናቅፋ ደርሶ እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ በብር ስትመቱት እስከ 16 ሺህ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ ከእርቁ ወዲህ ግን ጤፍ እንደልብ ስለሚገባ ዋጋው አሽቆልቁሎ አንድ ሺህ አምሰት መቶ ናቅፋ ደርሷል፡፡ ወደ ሶሰት ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው፡፡ እኔን የገረመኝ ግን በአስመራ ምግብ ቤቶች ያገኘሁት እንጀራ በሙሉ በስፋቱ የአዲሰባን እንጀራ በእጥፍ የሚበልጥ (ሰፌድ ያህላል)፣ በውፍረቱ ለአነባብሮነት የሚቀርብ፣ በጣእሙ ደግሞ እጅግ የሚያሰደስት ሆኖ ማግኘቴ ነው፡፡ እንደሰማሁት ይሄ ምንም ያህል ጤፍ ቢወደድ ቀድሞም የነበረ ነገር ነው፡፡ በእርግጥ ምግብ በአስመራ ምግብ ቤቶች መመገብ እጅግ ውድ ነው፡፡ መካከለኛ ደረጃ ላይ አለ የሚባል አንድ ምግብ ቤት (ለምሳሌ አዲሰባ ላይ በፅጌ ሽሮ ደረጃ የሚመደብ) አንድ ሽሮ (ሽሮውም በጣም ብዙ ነው) በወፍራም እንጀራ በትንሹ እስከ ሁለት መቶ ብር ያስከፍላል፡፡ አሳም ከቀይ ባህር እንደማይመጣ ውድ ነው፡፡ በአጠቃላይ ንፁህ ግን ቅንጡ ያልሆነ ቤት መመገብ የሚፈልግ አንድ ሰው ለምግብ በቀን ከአምሰት መቶ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል፡፡
5. ሰአት እና ቀን ኤርትራዊያን የቀን አቆጣጠራቸውን በፈረንጅኛ አድርገዋል፡፡ አሁን አመቱ 2018 ሲሆን ወሩም ጥቅምት ነው፡፡ ሰአትም የሚቆጥሩት እንደ ፈረንጅ ነው፡፡ ‹‹ነይ…ጠዋት 8 ሰአት ላይ ቁርስ እንብላ አይነት››፡፡ ሆኖም ቀኑ በአውሮፓ ዘዬ ይቆጠር እንጂ የወራቱ ስሞች ግን መስከረም፣ ጥቅምት….እየተባሉ ይቆጠራሉ፡፡ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአላት እንደ መስቀል፣ ገና እና ፋሲካ እንዲሁም ቅዱስ ዮሃንስ በሰፊው ይከበራሉ፡፡ ዘመን የሚቀየረው ግን ጥር ላይ ከፈረንጆቹ ጋር ነው፡፡
6. መስቀል እና ደመራ
አስመራ መስቀል ትልቅ በአል ነው፡፡ ደመራ የሚደመረው ግን በመስቀል እለት ጠዋት ላይ ነው፡፡ የዘንድሮው በአል ተሳታፊ ለመሆን ሄጄ ነበር፡፡ መዝመሮቹ በትግርኛ ይሁኑ እንጂ ምቱ አንድ፣ አኳሃኑ እንደ እኛው ነው፡፡ ዘማሪዎች ነጫጭ ለብሰው በከበሮ ታጅበው ደመራው ወደ ተደመረበት የቀድሞው አብዮት አደባባይ የአሁኑ ሃርነት ወይም ነፃነት አደባባይ ይተማሉ፡፡ ትእይነቱ በህዝብ ቁጥር ይነስ እንጂ እንደ አዲስአበባው ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን ቀልቤን የሳበው አንድ ነገር ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ባንዲራ የያዙ ተሳታፊዎች፣ ዘማሪዎች እና መደበኛ ሰዎች ከኤርትራ ባንዲራ አጠገብ የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘዋል፡፡ ይጨፍራሉ፡፡ ያውለበልባሉ፡፡ እኛ እዚህ በባንዲራ አውርድ ስቀል የሰው ሕይወት ስንቀጥፍ ከወራት በፊት በጠላትነት የምናየው ሃገር ህዝብ ከባንዲራው እኩል የእኛን ባንዲራ ሲያውለበልብ ሳይ ተገረምኩ፡፡
7. ዮፍታሄ እና ቡና በዝንጅብል ስለ ዮፍታሄ ራሱን የቻለ ወግ መፃፍ ይገባኛል፡፡ ዮፍታሄ በእጅ ስራ የተካነ ሰው ነው፡፡ ዘናጭ ቦርሳ ከጆንያ እና ሳጠራ አሽሞንሙኖ ይሰራል፡፡ ከፖስታ ቤት አጠገብ ባለው ትንሽዬ እና የተጨናነቀች የስራ ክፍሉ ውስጥ የሚውለው ዮፍታሄ የ47 አመት ጎልማሳ ሲሆን ቁጭ ጃንሆይን ይመስላል፡፡ እጥረቱ፣ ቅጥነቱ፣ ግርማው ቁጭ ጃንሆይን፡፡ ከሰራልኝ ውብ ቦርሳ በላይ የወደድኩት ግን ጨዋታውን ነው፡፡ ለዛው! አቤት ለዛው! በዚያ ላይ ደግሞ ወደ ህይወቴ ያመጣው አዲስ ጣእም፡፡ ይህ ጣእም ቡና በዝንጅብል ነው፡፡ ወይ ሲጥም! ካላመናችሁ ሞክሩና እዩት፡፡ …እንግዲህ ከእርቁ ወዲህ ፣ አሁን አሁን በአስመራ የአዲስ አበባ እና ሌላም ታርጋ ያላቸው የኢትዮጵያ መኪኖቸን ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ ብዙ ሰው ከኢትዮጵያ በመኪና መጥቶ ይጎበኛታል፡፡ የንግድ ሃሳብ ይነድፋል፡፡ አንዳንዱም ንግዱን ቀድሞ አጡፎታል፡፡ ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ቢራዎች፣ አምቦውሃ፣ ብዙ የታሸጉ ውሃዎች አስመራ ማግኘት ብርቅ ያልሆነው፡፡ ከዚህ የተረፈው ደግሞ ቀይባህርን ያያል፡፡ ምፅዋን ይጎበኛል፡፡ የሆነው ሆኖ ምንም እንኳን በርከታ የሃገሬ ልጆች የምፅዋን አስቸጋሪ መንገድ በቅንጡ መኪናዎች ለመሄድ ቢወስኑምእኔ ግን 42 ናቅፋ ከፍዬ በመንግስት አውቶብስ ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ ለምን? ለእናንተው ወሬ ይዞ ለመምጣት፡፡ ጉዞ ወደ ምፅዋ በሚቀጥለው ክፍል፡፡

@paappii
@wegoch

By- hiwot emishaw
ፓንዲ(ልዑል ሀይሌ)
.
ክፍል ፪
..
ፓንዲ ማለትኮ የኔ ባይሎጂ የኔ ዘር ቀጣይ!!(በባይሎጂኛ)….ፓንዲን ከባይሎጂ ጋር እያነፃፀርኩኝ ለመረዳት እየሞከርኩ ባለበት ሰዓት ባይሎጂ አስተማሪያችን ሳላስተውላት አጠገቤ ደርሳ “ባይሎጂ መፅሃፍህን ለምን አላመጣኸውም?” ስትለኝ በድንጋጤ ጀርባዬን ከሚለጠልጠው ትልቁ ቦርሳዬ ውስጥ አንድ ከጀርባው የትምህርት
ሚኒስቴር አርማ ያረፈበት ቢጫ መፅሐፍ በኩራት መዘዝ አድርጌ ወንበሬ ላይ ሳስቀምጠው አማርኛ መፅሐፍ ሆኖ ተገኘ…..አይ ዕድሌ! ዛሬም የተለመደው ቁርጥ ውሳኔ ሰለባ ሆንኩኝ ጆሮዬ ስለተላመደው ትዕዛዟን እስክትጨርሰው ሳልጠብቅ ወደ ውጪ ወጣሁኝ “ካሁን
በኋላ!...” ያው በኔ ክላስ እንዳትገባ ነው መጨረሻው…..አይደለም ባንቺ ክላስ ባለፍሽበት አላልፍም….ድሮም ሴት አስተማሪ አትሆነኝም!!.....ባይሎጂንም እርም!!... ምን ዓይነት ነገር ነው ፓንዲና የትምህርት ዓይነቶቼ የሚገጣጠሙት
መቼ ይሆን?…ይህቺ ልጅ በቃ ትምህርት አይሆናትም!.... በነገው ለታ ፓንዲን እንደምንም ከሽማግሌው የማትስ ትምህርት ጋር ላዛምዳት ሞከርኩኝ… ….ከወትሮው በተለየ መልኩ ከቤት አምጥቼው የማላውቀውን ሂሳብ መፅሀፌን ከሰፈራችን ባለሱቅ በወሰድኩት ካኪ ወረቀት ለብጄ ደብተሬንም በስርዓት ይዤ መጣሁኝ፡፡ ማትስ አስተማሪያችን መነፅራቸውን በግራ እጃቸው እያስተካከሉ በቀኝ
እጃቸው ሰሌዳው ላይ f(x)=y ብለው ፃፉና በ ‘x’ ቦታ የፈለጋችሁትን ነገር ማስቀመጥ ትችላላችሁ!!(እኔም ፓንዲን ቁጭ!) በ ‘x’ ቦታ ፓንዲን አስቀመጥኳት ግን ‘f’ ምን ያህል ይታመናል ቢቀማኝስ ‘f’ ማለት ፊሊሞን ነው….እሱን ከፓንዲ አጠገብ ላሰቀምጠው ይሄን ይብላ!! ......አስተማሪው ቀጥለዋል ለምሳሌ y=x+2 ቢሆን f(x)=x +2 ይሆናል ማለት ነው ስለዚህ በ ‘x’ ቦታ 1 ብናስገባ የ f(x) ውጤት 3 ይሆናል ሲሉን ደስ አለኝ ምክንያቱም የ ‘f’ አስተዋፅዖ ከማፍጠጥ የዘለለ አይደለም፡፡ ውጤት ላይ ምንም ተፅዕኖ አይፈጥርም፡፡ ስለዚህ ፊሊሞን ቢያፈጥ ፉአድ ቢያፈጥ ፓንዶራ ውጤቷ የሚመሰረተው በኔ
‘y’ በሚመጣው ቁጥር ነው፡፡ ስለዚህ ፊሊና ፉአድ ውሃ በላችሁ!!....ፓ ማትስ ምርጥ ትምህርት ነው ለካ!!....ለካ ለበጎ ነው እነዚያ አስተማሪዎች ያባረሩኝ ፓንዲን ለመግለፅ ምርጡ ትምህርት
ማትሳችን ነው!! ስፈልግ ራሴን የፓንዲ ህይወት ውስጥ እደምራለሁ ስፈልግ
ጠላቶቿንና እንደነ ፊሊሞን ዓይናቸውን የሚጥሉባትን ዕድሜ ለሂሳብ እቀንሳቸዋለሁ፤ ስፈልግ በማባዛት የክላሱን ተማሪ በሙሉ በፓንዲ
አጥለቀልቀዋለሁ፤ ስፈልግ አካፍላታለሁ….አአ ይህቺ ሂሳብ እንኳ
ትቅር ፓንዲን ለማንም ማካፈል አልሻም ፓንዲ የኔ ብቻ ነች፡፡ የኔ ብቻ!!...ሂሳብ አስተማሪያችን X ውስጥ ቁጥሮችን እያቀያየሩ እያሰሉ ያሳዩናል እኔ ግን በ x ቦታ ፓንዲን ብቻ አስቀምጬ በሃሳብ
አሰላስላለሁ፡፡ የሂሳብ ክፍለ ጊዜያችን እንደተደወለ የዕረፍት ሰዓታችን ደርሶ ወደ ውጪ ንፋስ ለመቀበል ወጣሁኝና በቅርብ ርቀት ሆኜ ፓንዲን ሰረቅ አድርጌ
እያየኋት ልቤ በሃሴት ትጨፍራለች፡፡ ፓንዲ ከጓደኞቿ ጋር ስትጫወት አያችኋት ……ሳቋኮ ልብን ይሞላል ታድላ!!. ..ታድዬ!!.. ዕረፍቱ ሲደወል ቀድሜያት ወደ ክላስ ገባሁኝ…ቀጣይ የምንማረውን የትምህርት ዓይነት ፕሮግራም ከቦርሳዬ ላወጣ ቦርሳዬን ባወጣው ቀለለኝ…..ከዛ ከፍቼ ሳየው ያለወትሮዬ ዛሬ ገና ያመጣሁት በካኪ
ወረቀት የለበድኩት ማትስ መፅሃፌ በቦታው የለም፡፡ ዴክሴ ስር ብበረብርም ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ከዛ ቀስ ብዬ አለቃው ጓደኛዬ ስለነበር ማትስ መፅሀፌ እንደጠፋብኝ ከነምልክቱ ነገርኩትና በሩን
ዘግቶ የሁሉንም የክፍላችን ተማሪዎች ቦርሳ መፈተሽ ጀመርን፡፡ ከፊት ያሉትን ሁሉ እየፈተሽን ስንመጣ ታዲዮስን ስፈትሸው በካኪ የተለበደ አዲስ መፅሃፍ አጋጠመኝና ደስ ብሎኝ ገልጬ ሳየው ለካ ኬሚስትሪ መፅሐፍ ነው፡፡ ተውኩትና ፍተሻዬን አጠናክሬ ቀጠልኩኝ፡፡ እያልኩኝ እያልኩኝ ስፈትሽ ስፈትሽ የኔ ዴክስ ላይ ደረስኩኝ….ፓንዲ ጋ….ኧረ! ፓንዲን መፈተሽ ማለት ራሴን መፈተሽ ማለት ነው፡፡ ፓንዲ መፅሐፉን ወሰደችው ከምል እኔ ነኝ የወሰድኩት ብል ይቀለኛል፡ ስለዚህ እሷን ሳልፈትሻት ላልፍ ወሰንኩኝ ጓደኛዬም ሊፈትሻት ሲል በምልክት እንዲዘልላት ነገርኩትና ሌሎቹን መፈተሻችንን ቀጠልን….. የአዝመራ ቦርሳ ውስጥ ያገኘሁት አምባሻ ከማትስ መፅሐፌ አይተናነስም ነበር፡፡ አስጎምጅቶኝ በቃ ተገኝቷል ልል ነበር…
የሚደቅሳ ቦርሳ ሲከፈት በጭኮ ክላሱን አወደው….. ሁሉንም ተማሪዎች ብንፈትሽም ማንም ጋር ሊገኝ ስላልቻለ ፍተሻው ዋጋ ቢስ ሆነብን፡፡ ተማሪው ሁሉ ግን ሲያጉረመርም ነበር እኛ ተፈትሸን
ለምንድነው እሷን ማትፈትሿት? …(ፓንዲንኮ ነው) …..ፓንዲ የኔ ፍቅር የኔን መፅሐፍ ልትወስድ?….አይደረግም!!.

.(ይቀጥላል......)

@lula_al_greeko
@getem
@getem
የመጀመሪያው የሰርግ ቻናል በኢትዮጵያ!
@Wedding_Vibe_in_Ethio
@Wedding_Vibe_in_Ethio
🍾ለሙሽሮች፣ለደጋሾች በቀላሉ ሃሳቦችን ፣ አዳራሾችን ከነዋጋቸው፣ አዳዲስ የሙሽራ የሚዜ ልብሶች የሚገኙበትን ሱቆች ፣ፎቶ እና ቪዲኦ በቀላሉ ከነ አድሻራቸው ፣ የመኪና ኪራይ ከነ ዋጋው ከነ አድራሻው ፣ ዲኮሮች ከነ አድራሻቸው ፣ የድግስ እቃ አከራዮች ከነ አድራሻቸው ፣ የሙዚቃ ባንዶችን ፣ የሰርግ ዲጄዎችን ከነ አድራ

@Wedding_Vibe_in_Ethio
@Wedding_Vibe_in_Ethio
@ተስፈማርያም በየነ 🙂
😂😂😂

Who loves this green nigga ??🤔

ጢንዚዛ ውስጤ ነው!😍

ይህ ነገዱ ከነፍሳት? ዘር የሆነ አስደናቂ ፍጥረት፤
ሳይንቲፊክ ኔሙ..ፓናሮቪስገርቢስገላውዲዏስ
ጠርጢዯስ..ቅብርጥስዬ ምናምን ሊሰኝ ይችል
ይሆናል።
ማን ያውቃል? Google it!
ብቻ..የአህያና የድመት ያህል ይመስጠኛል!!
oh man! .. አረንጓዴ ቀለሙ.. እርጋታ የተሞላ
በት ዘንካታ አረማመዱ .. ጩጬ ቀንዶቹና ሽልም ቦርጩ.. ምናምን።

Defence Mechanisሙ ኩሱ ነው አሉ። አንዳንድ እበላ ባይ ገደል ሆድ Prediተሮች ድንገት ሊያጠቁት
ከመጡ..ተዝናንቶ ኩሱን(ሰገራዉን)"ጀባ" ይላቸዋል።
ተክለፍልፈው እንደመጡ.. ቀርንቷቸው "እፍ" "እፍ"
"አበስኩ ገበርኩ" እያሉ ወደ መጡበት ይቀዱታል።

Googleን ሳስስ.. ኩሱ Acidic እንደሆነ
ጠቆመኝ። ማረጋገጥ ነበረብኝና ቀመስሁት!
እውነትም ኮምጠጥ ይላል!

ተባእቱ ጢንዚዛ ግድንግድ ቀንዳም ነው።
አሁን ግን የምትመለከቷት.. እንስት ጢንዚዛ
ሳትሆን አትቀርም። ያው ማወቅ ስለነበረብኝ..
ፑናኔዋን ለመሾፍ..ገልብጬ ጥልቅ ምርመራ
ባካሂድም!! ሸቀጧን አጣሁት።

በቀደምለት ተባዕቱ ባናቴ ሽው ብሎኝ አለፈ።
ሸቀጥ ልሸምት ሱቅ መሄዴን ገትቼ ልይዘው
ተጣደፍሁ! ነገር ግን አልቻልሁም። ላይ ታች
ግራ ቀኝ አቅበዝብዞኝ አመለጠ።

ደሞ እንደ ንብ "ሲሳይ ነው" ይሉታል።እውነት ሳይሆን
አይቀርም። ማን ያውቃል አንዳች አይነት force field (aura) የሚሉት ነገር አጅቦትስ ቢሆን?

ስለ ሲሳይነቱና ለጩጬነት ፍቅረኛዬ ሰላማዊትይይዬ
ስለገዛሁላት ሰማያዊ ፖኒተር (የፀጉር ጌጥ)ሌላ ጊዜ አወጋለሁ።

@tekuye17
@wegoch
ፓንዲ(ልዑል ሀይሌ)
.
ክፍል ፫ (የመጨረሻ ክፍል)
.
እኔ አሻፈረኝ እጄን አልሰድም ብዬ በአቋሜ ስፀና አለቃችን በፊት አውራሪነት የሚመራው ፈታሽ ቡድን ተሰማርቶ የፓንዲ ቦርሳ ተፈተሸ፡፡ ሲፈተሸ የተገኘው ነገር ግን ሲደብር!!....በካኪ ወረቀት የተለበደ አዲስ ማትስ መፅሐፍ
የክፍላችን ተማሪ በአግራሞት ሲያሽካካ ይሰማኛል፡፡ …አለቃችን ቀጥሎ በነገርኩት ሚስጥራዊ የመፅሐፌ ምልክት ሊያጣራ ፍተሻውን ሲያደርግ የመፅሐፉ 100ኛ ገፅ ላይ የተፃፈው ስሜ መፅሐፉ የኔ መሆኑን ሲያረጋግጥልኝ በድን ሆንኩኝ፡፡ ፓንዲም እንደ አለት ቆማ ቀረች ከዓይኗ ዕንባ በብዛት ይፈሳል… .ተማሪው በሙሉ ሌባ! ሌባ! ይላታል….ይዘልፋታል.. እውነት ግን ፓንዲ ነች?……ለካ ላቦሮ ነች!!......ለደቂቃዎች
የተፈጠሩትን ነገር እያስታወስኩኝ አንጎሌ ተበጠበጠ መጨረሻ ላይ ራሴን ስላመመኝ ወደ ቤቴ አስፈቅጄ ሄድኩኝና በግምት ለ3 ሰዓታት ያህል ተኛሁኝ፡፡ ለ3 ቀናት ያህልም አሞኝ ከትምህርት ቤት ቀረሁኝ፡፡ በ3ኛው ቀን የቤት ሰራተኛችን ሰው እየጠራኝ እንደሆነ ነግራኝ ወደ
ውጪ ስወጣ…..ፓንዲ ነች… ፓንዲ እንደድሮ አታምርም ውበቷ ከስሞ ከንፈሯ ደርቆ ፊቷም ግርጥት ብሏል፡፡ ከቤታችን በር ፊት ለፊት ባለው ግንብ ተደግፋ እንዳቀረቀረች ቆማለች፡፡ ….ወደሷ አቅጣጫ ትንሽ ሄድ አልኩኝና ተመልሼ ደሞ ቆም ብዬ ለመመለስ እያሰብኩኝ ባለበት ሰዓት ስትጠራኝ አላስቻለኝም ወደሷ ሄድኩኝ….ከዛ ሰላም ካለቺኝ በኋላ
“ያሬድ መፅሐፍህን የወሰድኩብህ መስሎህ ተቀይመኸኛል አይደል?” “ደሞ እንዲህ ስትዪ አታፍሪም?!....ቆይ ስታዪኝ ማየት የተሳነው እመስላለሁ እንዴ?…ደሞ ቤቴን ማን አሳየሽ?” “ፊሊ ነው ያሳየኝ እንዳመመህ ስሰማ ልጠይቅህ በዛውም እውነታውን ልነግርህ ነው የመጣሁት…..በርግጥ ላታምነኝ ትችላለህ……እኔ ግን አይደለም ልወስደው ያንተ ቦርሳ ምን አይነት እንደሆነ አይቼው አላውቅም፡፡”
አይ ፓንዲ ሌባ! ሌባ ነች!! ማትስን አመሰግናለሁ ሌብነቷን ስላረጋገጥክልኝ …..ማትስን ከልቤ እወደዋለሁ!..ይህቺ አጭበርባሪ ባይኔ በብረቱ መፅሐፌ ከቦርሳዋ ሲወጣ እያየሁት አልወሰድኩም ብላ ድርቅ!...ምኗ ፈጣጣ ነች?!!....ለካ እውነቱን ነው ጂኦግራፊ
አስተማሪያችን የፓንዶራን ስም ሳነሳለት በሱ ክፍለ ጊዜ እንዳልገባ የወሰነብኝ………ባይሎጂ ስለ ሴክሹዋል ሪፕሮዳክሽን ስንማር ሁሉም ሲገለፍጡ ዝም ያለችው ለካ እንዴት እንደምትሰርቅና የማን ቦርሳ ምን ያህል ይዟል የሚለውን ስታጠና ነው፡፡ ይህቺ ሌባ! “ምን አይነት ሰው ነሽ በናትሽ?…ካይኔ በላይ ምን ምስክር አለኝ?…… አልሰረቅሺኝም አይደል?….ታዲያ ተከራይተሸኝ ነዋ መፅሐፌ ቦርሳሽ ውስጥ የተገኘው?…..” ስላት ዕንባ ካይኗ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ
“ይኸውልህ ያሬድ እኔ የድሃ ልጅ ነኝ አስተዳደጌ ግን መጥፎ ምግባር አላስተማረኝም በሃይማኖት የታነፅኩኝ ሴት ነኝ፡፡ መስረቅ ደሞ አምላኬ ስለማይወደው መቼውንም የምጠየፈው ተግባር ነው፡፡ …..ያኔ መፅሀፉ ሲወሰድ ካስታወስክ እረፍት ሰዓት ላይ ሁለታችንም ፊት ለፊት ቆመን ነበር ወደ ክፍል ስንገባ ደሞ ቀድመኸኝ የገባኸው አንተ ነበርክ ታዲያ በምን ጊዜዬ ነው ያንተን መፅሐፍ የምሰርቀው…..ስለዚህ እመነኝ ማርያምን አልወሰድኩም!!” አለችኝና ጉንጯ በዕንባ ራሰ… በዚህ ሰዓት ፓንዲ በጣም አሰዘነቺኝ… ..እውነትም ለካ ወደ ኋላ
ተመልሼ ሳስታውስ እረፍት እንደተደወለ በረንዳ ላይ ተከትያት ወጥቼ ስገባ ደሞ ቀድሚያት ነው የገባሁት….ደሞኮ ማርያምን አለችኝ….. “አሁን አምኜሻለሁ!!....ያኔ የተከሰተውንም በሚገባ አስታውሻለሁ…… ግን ማነው ታዲያ ሰርቆ ያንቺ ቦርሳሽ ውስጥ ያስገባው?…” “እኔ ምናውቃለሁ!...ምን አይነት ክፉ ሰው ነው በናትህ?…” “እሱን እናጣራዋለን ለማንኛውም አይዞሽ አልኳትና ዕንባዋን ለመጥረግ እጆቼን ልኬ ለመጀመሪያ ጊዜ ያንን የምሳሳለትን ጉንጯን በመንካቴ ልቤ በሀሴት ዘለለች፡፡ ፓንዲ! የኔ ቆንጆ!...ለመጀመሪያ ጊዜ እጆቼን ትከሻዋ ላይ ጭኜ ሰፈሯ ድረስ እያወራን ሸኘኋት…ህመሜንም
በዛው ሽኝት!!.....ወደ ሰፈር ስመለስ በፈገግታ ታጅቤ እንደ አዲስ የተፈጠርኩኝ ያህል እየተሰማኝ ነበር…ፓንዲ!...ምስኪን እሷን ሌባ ያልኩበት ምላሴ ይቆረጥ!…ፓንዲ የኔ ታማኝ!!...ለካ ነገሮች ሁሉ የሚሆኑት ለበጎ ነው…በቅፅበት ፓንዲን ሌባ አድርጎ አሳይቶኝ የነበረው አጋጣሚ በቅፅበት ሲቀየር ሳይ ደስ አለኝ፡፡…. በነጋታው ክላስ ውስጥ ከፓንዲ ጋር ስንገናኝ እንደድሮ ፊቷ በርቶ ነበር፡፡ የኔም ፊት ከወትሮው በተለየ መልኩ ወዝቶ ደስ በሚል ስሜት ተቃቅፈን
ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ …..የተሰረቀውን መፅሐፍ በፓንዲ እንዲሳበብ ማን እንዳደረገ ማጣራት
እንዳለብን ተመካከርን ዕቅዳችንንም ከ3 ቀናት በኋላ ተግባራዊ ልናደርግ ወሰንን ከዛ በኋላ ከፓንዲጋ ምርጥ ጓደኛሞች ሆነን…ጥሩ ጊዜ አሳለፍን በዚህም
የክፍላችን መነጋገሪያ ርዕስ ሆንን ….አጠገብ ላጠገብ እየተቀመጥን ተያይተን እንኳን የማናውቅ ልጆች እንደዚህ ስንዋደድ ሲያዩ ተገርመውብናል፡፡ በነጋታው ፊሊሞን ጠርቶኝ ወደ ትምህርት ቤታችን ሜዳ ወስዶኝ መፅሀፉን እንደወሰደው ሲነግረኝ በንዴት ተነስቼ ልተናነቀው ሳስብ.. “ተረጋጋ መጀመሪያ ልብ ብለህ አድምጠኝ!!” “ባክህ ዞር በል ሌባ! ደሞ አታፍርም?!” “ስታስበው ቆይ ለምን ይመስለሃል እዚህ ጠርቼ እውነታውን
የነገርኩህ?” “ያው ይደረስበታል ብለህ ስላሰብክ ነዋ!” “አትሳሳት ጓደኛዬ!...ይልቅ እውነቱን ልንገርህ….ፓንዲን ትወዳታለህ
አይደል?” “በጣም አንተም እንደምትወዳት አውቃለሁ!!” “ማነው ያለህ? እኔ ለራሴ ካጠገቤ የምትቀመጠውን ዳናዊትን እንዴት
እንደማናግራት ጨንቆኛል…..ድሮ ታስታውሳለህ ምርጥ ጓደኛዬ ነበርክ
ምንም እንኳ በትንሽ ነገር ብንኮራረፍም ….የሆነው ሆኖ ሁኔታህን ሳየው ፓንዲን ለማናገር እንደፈራህና እንደምትወዳት ስለገባኝ እንድታናግራት መንገድ የሚከፍትልህን ነገር ሳሰላስል የመጣልኝ ዘዴ ይሄ ነበር.. ..አለቃችንንም ሁሉን ነገር አስረድቼው እንዲተባበረኝ አደረግኩት ካላመንከኝ ሄደህ ጠይቀው….ይሄ ስለጓደኝነታችን የከፈልኩት መስዋዕትነት ነው…ፓንዲንም አንድ ቀን አብረን እንነግራታለን…” ሲለኝ በጣም ገረመኝ ፊሊሞንንን እንዲህ ትልቅ ሰው አድርጌ ገምቼው አላውቅም ነበር፡፡ እኔም ምሰጋናዬን አቅርቤለት ወደ ክፍላችን ሄድን።

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ቅንጣቢ የምፅዋና አስመራ ወግ
ክፍል 4

‹‹የት ነው የሚሄደው? ›› ይሉኛል መአት ሰዎች እየተፈራረቁ፡፡ በትግርኛ ነው የሚጠይቁኝ፡፡ በግምት ነው የምመለሰው፡፡ ከንጋቱ 11.45 ላይ አስመራ አውቶብስ ተራ ላይ ያረጀ ኮሰተር አውቶብስ ውስጥ ብቻዬን ተቀምጬ ሲያገኙኝ ሌላ ምን ሊጠይቁኝ ይችላሉ? ከአዲስ አበባ አውቶቢስ ተራ ጋር ሲነፃፀር በውክቢያም በስፋትም እጅግ ያነሰውን አውቶቢስ ተራ ውስን ትእይንት እያየሁ በተጠየቅኩ ቁጥር ‹‹ምፅዋ›› እያልኩ ያለመታከት እመልሳለሁ፡፡ ደብረዘይት የተመረተ ብስኩት፣ ትግራይ ላይ የታሸገ ውሃ፣ አዲስ አበባ የተቆላ ዳቦ ቆሎ፣ አስመራ ላይ የተዘጋጀ አምባሻ፣ ሌላም ሌላም በየፈርጁ የሚሸጡ ልጆች የሚሸጡትን ነገር እያስተዋወቁ በሻንጣቸው ወይ በብጣሽ ካርቶን ሰልፍ ይዘው በትእግስት የሚጠብቁትን ተሳፋሪዎች ይዞራሉ፡፡ የምፅዋ መኪና ላይ ያለምንም እንግልት ያስገባሻል ተብሎ ገንዘብ እንድሰጠው የተነገረኝ ልጅ እዚህ እንኳን ሊሞላ ከእኔ በቀር አንድ ሰው ያልጫነ አሮጌ መኪና ውስጥ ጥሎኝ ከሄደ 30 ደቂቃዎች በማለፋቸው መንቆራጠጥ ጀምሬያለሁ፡፡ ፈልጌ አላገኘው እቃዬን ለማን ትቼ? ደውዬ አላዋራው ስልክ ከየት አባቴ አምጥቼ ?(ኤርትራ ስገባ ሲም ካርድ ለማግኘት ብፈልግም እንደ ብዙ መንግስት የሚያቀርበው አገልግሎት እንኳን ለውጪ ሰው ለሃገሬውም ሰው ብዙ ጣጣ ፈንጣጣ እንዳለው ስሰማ ተውኩት).. የኤርትራን መሬት ከረገጥኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የባይተዋርነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ሆድ ሊብሰኝ ሲጀምር ሁለት ለአውቶብስ ተራ በሚበዛ መልኩ የዘነጡ ሰዎች አውቶብሱ በር ጋር መጡና በተለመደው ሁኔታ የት ነው አሉኝ፡፡ ‹‹ምፅዋ›› ብዬ መለስኩ፡፡ የአውሮፓን ብርድ ታሳቢ በማድረግ የተሰራ የሚመስል ውፍራም ሱፍ ካፖርታ የለበሰው ጠና ያለው ረጅምና ቀይ ሰውዬ (እድሜውን ስመለከት ልክ እንደ ነፃነት መለሰ ዘፈኑ ሰውዬ ውብ ካፖርታ ያደረገ ከመሆኑ ባሻገር በጊዜው ዶጅ የነዳ እና አረንቻታ የጋበዘ የሚመስል) ተጨማሪ ነገሮች በትግርኛ ጠየቀኝ፡፡
- ትግርኛ አልችልም አልኩ በሃፍረት ፈገግ ብዬ፡፡
- ኢትዮጵያዊ ነሽ? አለኝ ትክ ብሎ እያየኝ
- አዎ….መልስ ሳይሰጠኝ አብራው የነበረቸውን ሌላ ዘናጭ ሴት ይዞ ወደ አውቶብሱ ገባና ከፊቴ ባለው ወንበር ላይ ተደላድለው ተቀመጡ፡፡ ውድ ሽቷቸው አወደኝ፡፡ ተመስገን…ሶስት ሆንን! ደቂቃም ሳይቆይ ሁለቱም ጀርባቸውን ከሰጡኝ አቀማመጥ ዞር አሉና ያዩኝ ጀመር፡፡ ምን ፈልገው ነው?
- ኢትዮጵያ ከየት ነሽ? ማለቴ ከየት ስቴት? አለኝ ሰውየው፡፡ ስቴት? ይቀልዳል እንዴ? አማርኛው በከባድ የእንግሊዝኛ ተፅእኖ ውስጥ የወደቀ ነው፡፡ ኤርትራዊ ዲያስፖራ እንደሆነ ገመትኩ፡፡
- አዲሳባ…አልኩ
- ኦህ! ናይስ…እኔ አሜሪካ ነው ምኖረው ኦርጅናሊ ፍሮም ኤርትሪያ! ዚስ ኢዝ ማይ ሲስተር! አለና ሞቅ ያለ ፈገግታ እያሳየኝ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ፡፡ ሁለቱንም በደንብ ተዋወቅኩና ወሬ ጀመርን፡፡ ጨዋታቸው ቢጥመኝም የሰአቱ መግፋት ግን አሳሰበኝ፡፡ ሰአቴን አየሁ፡፡ አስራ ሁለት ተኩል አለፏል፡፡ ሌላ ሰው አልገባም፡፡ ምፅዋ ከአስመራ በርቀት ቅርብ ብትሆንም በመንገዱ ከባድነት ግን ሩቅ እንደሆነች በተደጋጋሚ ተነግሮኛል፡፡ 105 ኪሎሜትር 3 ሰአት የሚፈጅበት መንገድ ነው፡፡ ያለኝ አንድ ቀን ነው፡፡ መወሰን ነበረብኝ፡፡ ጓዜን ያዝኩና
- ሌላ አውቶብስ ልፈልግ ነው፡፡ ይሄ የሚሄድ አይመስለኝም… አልኳቸው በሃሳቤ ተስማምተው አብረን ከወረድን በኋላ ቀድሞ ይሄዳል የተባለውን መደበኛ አውቶብስ ለመሳፈር ሰልፍ ያዝን፡፡ ከብዙ ጥበቃ እና ድካም በኋላ ሶስት ሰአት ሊሞላው ትንሽ ሲቀረው የተሳፈርንበት አውቶብስ ጉዞውን ጀመረ፡፡ መንገዱ በደህና ደረጃ ያለ አስፋልት ቢሆንም እጅግ ጠመዝማዛ ስለሆነ ጉዟችን ጥንቁቅና ቀስታ የበዛበት ነው፡፡ ደስ የሚለው አስፈሪ መጠማዘዝ በሚጠይቅ መንገዶች ላይ በሙሉ ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጡ መኪናዎችን ቀድሞ የሚያሳይ መስታወት ተተክሏል፡፡ ( ደስ የሚልና ኢትዮጵያም ቢለመድ ብዙ ሕይወት የሚያተርፍ ነገር ነው፡፡ የእኛ ነገር ነቅለን ቤታችን ካልወሰድነው…መቼስ በየጉርባው ላይ የሚቆም መስታወት ጠባቂ ወታደር አንቀጥር ነገር…..) …መልከአ ምድሩ ሰሜን ኢትዮጵያን፣ መንገዱ ደግሞ ዝነኛው ሊማሊሞን አስታወሰኝ፡፡ ተራራ እየወረድን ነው፡፡ በምጥ እንዞራለን፡፡ በምጥ እንታጠፋለን፡፡ በዝግታ እንሄዳለን፡፡ ተራራው አለቀ ሲባል ሌላ ተራራ ላይ ነን፡፡ ወረድን ስንል አሁንም ከፍ ያለ ቦታ ነን፡፡ ደግነቱ መንገዱ በመኪናዎች አልተጨናነቀም፡፡ ባሁኑ ጊዜ የኤርትራ ኢኮኖሚ ከወደብ ይልቅ በማእድን ማውጣት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ስለሰማሁ ምናልባት በዚያ ምክንያት ይሆናል ብዬ ገመትኩ፡፡ ምናልባት ይሄ መንገድ ወርቅ እና ዚንክ ወደሚታፈስበት የሃገሪቱ ክፍል አይመራ ይሆናል የሚል ግምት ወሰድኩ፡፡ ግማሽ ሰአት አካባቢ ከሄድን በሁዋላ አየር ንብረቱ ከደጋ ወደ ወይና ደጋ፣ የእፅዋቱም አይነት እንዲሁ ተቀየሩ፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀውን እኔም አሰመራ ውስጥ የተዋወቅኩትን የኤርትራ የቱሪዝም መሪ ቃል አስታወስኩ፡፡ <<Eritrea: three seasons in two hours>> ይላል፡፡ ‹‹በሁለት ሰአታት ሶስት ወቅቶችን ይዩ›› አይነት ነገር፡፡ ምፅዋ ስደርስ ይሄ መሪ ቃል አውነት እንደሚሆን አልተጠራጠርኩም፡፡ሹፌራችን ለትዝታም ለዝላይም የሚሆኑ ሙዚቃዎችን ቀላቅሎ እያጫወተልን ነው፡፡ የአማርኛ ሙዚቃዎች ይበዙታል፡፡ ኤፍሬምና ጥላሁን እንዲሁም ኤፍሬምና ጥላሁንን አስመስለው የዘፈኑ ዘፋኞች ደጋግመው ይመጣሉ፡፡ ከአንድ ሰአት ተኩል የውረድ እንውረድ የቁልቁለት አስቸጋሪ ጉዞ በኋላ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ100 ኪሎሜትር ጉዞ ለቁርስ ቆምኩ፡ ጋህተላይ ትባለለች ከተማዋ፡፡ በረድፍ ከተደረደሩ ቁርስ ቤቶች እና በርከት ያሉ የገጠር መንደር ቤቶች ውጪ አይን የሚገባ ብዙ ነገር የላትም፡፡ አሁንም አሁንም ነፋስ እየተንደረደረ ከሚያፍን አቧራዋ በተጨማሪ በሃይል ትሞቃለች፡፡ ወደ ሶስተኛው ወቅት መግቢያ መሆኗን ጠረጠርኩ፡፡ ተሳፋሪው በሰልፍ ሲወርድ እኔ ጋር ግቡ እኔ ጋር ግቡ ብለው የሚሻሙ ባለ ቁርስ ቤቶች መጡ፡፡ እኔም አብዛኛው ሰውና ሹፌሩ የሚገቡበት ቤት ተከትዬ ሄድኩና ለነፍስ የቀረች የምትመስል አንዲት ብቸኛ ዛፍ ስር ካለ ፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ፡፡ በዛፏ ምክንያት ትንፋሽ ባገኝም ሙቀቱን ግን አልቻልኩም፡፡ ከአስመራ ጀምሮ ስቀንስ የነበረውን የልብሴን ድርብርብ በአንድ ቀነስኩና ሙቀቱን ማማረር ጀመርኩ፡፡ አጠገቤ የተቀመጠው ባለ ካፖርቱ ሰውዬ ( ካፖርቱን ከ50 ኪሎ ሜትር በፊት አውልቋል) ‹‹በዚህ ከተማረርሽ ምፅዋ ምን ልትሆኚ ነው?›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ዛሬ የሙቀት መጠኗ 38 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሆነ የተተነበየላት ምፅዋ ስደርስ ምን ልሆን ነው? ቀዝቃዛ ኮካ እና ስልስ በዳቦ አዝዤ ተቀመጥኩ፡፡ አንዲት እርምጃዋ ሸክም እንደተሸከመ ሰው ሁሉ ቀስ ያለ ጠና ለለች ሴት ይዛልኝ መጣች፡፡
- አመሰግናለሁ አልኳት በትግርኛ ብዙ ነገር አለችኝ፡፡ ቋንቋ እንደማልችል ስታውቅ እየታገለች፣ በጣም በተቆራረጠ ሁኔታ በአማርኛ ታወራኝ ጀመር፡፡ እንግድነት እንዳይሰማኝ በመጣሯ ደስ አለኝ፡፡
- ከአዲስ አበባ ነው የመጣሁት አልኳት ከየት መጣሽ ስትለኝ
- እኔ አዲስባ አላውቅም…ሕይወቴ ሙሉ እዚህ …አለችኝ
- አሁንስ አትመጪም? አልኳት ፈገግ ብዬ
- አይ…እሱ እግዜር ያውቃል..እናንተ ግን እንኳን በደህና መጣችሁ….
- አሜን
- የእኔ አማርኛ ጠፋ…
- አረ ጎበዝ ነሽ…ለመሆኑ እ
2024/09/29 17:38:00
Back to Top
HTML Embed Code: