Telegram Web Link
የአህመዲን ጀበል
ፎቶ??????????????

ሰው የሚፈረጀው ፎቶ አብሮ በመነሳት ከሆነማ እነሆ አህመዲን ጀበል ከዋልድባ ገዳም ና
ከወልቃይት የመብት ተሟጋቾች ጋር አብሮ የተነሳውን ፎቶ አይተናልና ከወልቃይትና
ከዋልድባ ገዳም የመብት ትግል ጀርባ አህመዲን ጀበል ተጠርጣሪ ነው በሉኛ !!!! ኧረ ጎበዝ
ዘሎ በግምት መፈረጅ ይብቃ !!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እድል ከሌለህ ...
«ዘውድአለም ታደሠ»

የሰው ህይወት በምን እንደሚቀየር አይታወቅም። ትናንት ማምሻውን ከጓደኞቼ ጋር አንድ አነስተኛ ግሮሰሪ ሰብሰብ ብለን አንድ ሁለት ስንል (አንድ ሁለት ያልነው መጠጥ አይደለም የኢትዮጵያን ብሔረሰቦች እየቆጠርን እንጂ ... ማይ ብራዘር የኢትዮጵያን ብሐረሰብ ቆጥረህ አትጨርሰውም። መቁጠር ስትጀምር ራሱ አዳዲስ ብሔረሰቦች ይፈልቃሉ)
የብሔር ቆጠራው ትክት ሲለን የሆነ የሆነ ነገር መጠጣት ጀመርን። (ለነገሩ የሰሞኑ ሁኔታ እንኳን አልኮል በረኪና ያስጠጣል) 
ድንገት ታዲያ ጥግ ላይ ተቀምጦ ዋሊያ ቢራ ያዘዘ ጎልማሳ ቆርኪውን እንዳየ ከመቀመጫው እንደካንጋሮ ተስፈንጥሮ ተነስቶ በደስታ መጮህ ሲጀምር ሁላችንም እየሮጥን ሄደን ተጠመጠምንበት። «ቤት ደርሶት ነው .. መኪና ሳይሆን አይቀርም ...» ምናምን እየተባባልን ቆርኪው ላይ ያረፈውን እጣ ለማየት ተሟሟትን።
ዘንድሮ ቢራው ሁሉ እጣ በእጣ ሆኗል። ይሄ ህዝብ በእጣፈንታው ተስፋ መቁረጡን ምታውቀው እጣ ይደርሰኛል ብሎ ዋሊያ ና ጊዮርጊስ እያፈራረቀ ሲጠጣ ስታየው ነው። ፀልየው ሁሉ ቢራውን ሚከፍቱ አሉ። ያው እድል ነውና በየቀኑ አንድ ሳጥን ቢራ የሚፈጅ ተስፈኛ ባዶውን ወጥቶ እንደዚህ አይነቱ ምስኪን አንድ ቢራ ጠጥቶ ቤትና መኪናውን ያፍሳል።
ጥግ ላይ የነበሩ ጎረምሶች ተደስተው ሰውዬውን ወደላይ አንስተው መጨፈር ጀመሩ ... ቤቷ በአንድ እግሯ ቆመች። እድለኛው ሰውዬ ባልጠበቀው እድሉ እየፈነደቀ ቆርኪዋን ጨብጦ ይዞ ጎረምሶቹ ትከሻ ላይ ሆኖ ይፈነድቃል። ባንኮኒውን የተደገፉ አንድ አዛውንት ቢራ ወዳቀረበችው አስተናጋጅ አፍጥጠው «እኔ ቢራ ድገሚኝ እያልኩ ስጮህ ቆርጦሽ ነው ለሰውዬው የሰጠሽው? ከውካዋ!» እያሉ ይሞልጯታል። 
ደስታው ትንሽ ጋብ እንዳለ ጎረምሶቹ በአንድ ግዜ ሚሊየነር የሆነውን እድለኛ ምናባሽከትከሻቸው አውርደው በጉጉት «ምንድነው የደረሰህ? ቤት ነው? መኪና ነው?» እያሉ ሲያዋክቡት ወደአስተናጋጇ ዞሮ 
«ነፃ መጠጥ ደርሶኛል» ብሎ ቆርኪውን ሰጥቷት ቢራውን በደስታ ማጣጣም ጀመረ።
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
Forwarded from SPACE COMPUTER
📖መጽሐፍትን ለማረሚያ ቤትና ለታራሚዎች እንለግስ በሚል በአዲስ ብሔራዊ ቲያትር የኪነ ጥበብ ምሽት ዕለተ ዕረቡ መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ ።
@tebeb_mereja

በዕለቱም ከወጣት እስከ አንጋፋ የጥበብ ባለሞያዎችን አካተናል።

📓ገጣሚና ደራሲ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)
📓ገጣሚ ታገል ሰይፉ
📓ገጣሚና ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ
📓ገጣሚት ምልዕቲ ኪሮስ
📓ገጣሚት ትግስት ማሞ
📓ገጣሚ ልዑል ሀይሌ
📓ገጣሚ ሚካኤል አስጨናቂ
📓ገጣሚ ምንተስኖት ማሞ
📓ገጣሚ ሀብታሙ ማሞ
📓ገጣሚ ውብሸት ታዬ
📓ገጣሚ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
📓ገጣሚ ዋሲሁን በላይ
📓ገጣሚ ያደል ትዛዙ
📓ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን
📓ኮሜዲያን አሰፋ ተገኝ
📓ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ መድረኩን በአጋፋሪነት እየመራ ለወገኖቻችን "መጽሐፍትን ለማረሚያ ቤትና ለታራሚዎች እንለግስ" በሚል በብሔራዊ ቲያትር መስከረም 23 ዕለተ ዕረቡ 2011 ዓ.ም ከ11:30 ጀምሮ የስነ -ጽሁፍ ምሽት ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ዝግጅቱን በማስተባበር ፣ የአዳራሽ ወጭን ጨምሮ አንዳንድ ወጭዎችን በመሸፈን ፣ በዕለቱ ዕለት በማስተባበር የምትፈልጉ

ሙሉጌታ አንበርብር 0927732850
ሰላማዊት በለጠ 0912484072
ኤፍሬም ጀማል 0911204141
ብሩክ አማረ 0912938993

ብላችሁ በመደወል ብናወራ ደስ ይለናል።

#የመግቢያ ሁለት መጽሐፍ እና ከዚያ በላይ መጽሐፍት ብቻ!!!


@tebeb_mereja
@tebeb_mereja

@lula_al_greeko
👆👆👆ልዩ የስነ-ጥበብ እና የኪነ-ሕንፃ ሀገር አቀፍ አውደ-ርዕይ በመርካቶ ልደታ፡ፍሊንትስቶን ህንፃ ውስጥ ከነገ መስከረም11-13 ድረስ በየሀ-በሻ ኪነ ህንፃ

መግቢያ በነፃ

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja

@lula_al_greeko
(አንዱአለም ቡኬቶ ገዳ)

እንደምን ከረማችሁሳ?! የኢሃዲግ መንግስት ከሰሞኑ እንዳስከፋችሁ ሰማሁ ……! አይዞን!… መንግስት ሰላማዊ ዜጎችን መግደሉ ያለ እና የነበረ ቢሆንም ቢያንስ እኔ እንዳየሁት በጠሚ አብይ ዘመን ወታደሩ ወደ ሰላማዊ ሰልፈኞች ቆሞ ይተኩስ የነበረውን የተዘበራረቀ አካሄድ በመተው አሁን በሆዱ አስፓልት ላይ ተኝቶ አነጣጠሮ በመተኮስ ወጣቶችን መግደል መጀመሩን ማስተዋል ችያለሁ፡፡ይህም እንግዲህ አንድ እድገት መሆኑ ነው…!
ፖሊስም" ሟች ሰልፈኞች የተገደሉት ባንክ ሊዘርፉ ስለነበር ነው" ከሚለው ባህላዊ ሰበብ በመላቀቅ "እነኚህ ደቃቃ ወጣቶች የሞቱት ለአይን እንኳን ከሚያስፈራ ድልብ አየርወለድ ኮማንዶ ጠመንጃ ለመንጠቅ ሲሞክሩ ስለነበረ ነው…. "በማለት አዲስ ምክንያት ይዞ ብቅ ብሏል(ተሳልቋል) ፡፡….ዛሬ ደግሞ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ሸገር ራዲዮ ላይ
በዚሁ ጉዳይ ይመስለኛል ለውይይት ሲጋበዙ" ጉሮሮዬ እምቢ ብሎኛል" ብለው የእነ ፍቅርአዲስና ሃሊማን ምክንያት ሰጥተው ላሽ ብለዋል፡፡
ይሁና እንግዲህ ምን ማድረግ ይቻላል……!? እኛም እስቲ ወደ ዛሬው ጉዳያችን እንለፍ፡፡ እንግዲህ ከሰሞኑ እንዳስተዋላችሁት እኔና ጓደኞቼ አንድ አዲስ ንቅናቄ ለማቋቋም ደፋ ቀና እያልን ነው፡፡ (በነገራችን ላይ የፖለቲካ ድርጅት
ማቋቋም እዚህ ፌቡ ላይ ተጎልቶ እንደመተቸት ቀላል አይደለም ለካ!?....ድካሙን ካየሁ በኋላ ለማን አዘንኩ መሰላችሁ …!?..የምሬን ነው ለኢሃዲግ ከልቤ አዘንኩ!…..እኛ አንድ ፓርቲ/ንቅናቄ ለማቋቋም እንዲህ የደከምን ኢሃዲግ ይሄን ሁሉ የውሸት ተቋዋሚ ሲያቀቋቀምና ሲደግፍ እንዴት እንደደከመ አሁን ነው የገባኝ….! በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ ንቅናቄ ለመሰረታችሁት የአብን ወጣቶች
ምንም እንኳን የፖለቲካ አቋማችን ለየቅል ቢሆንም ላመናችሁበት ነገር ለመታገል የለፋችሁት ልፋት ገና አሁን ስለገባኝ አድናቆቴን ለመቸር እወዳለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ የንቅናቄያችን ስም ኢ.ብ.ን ይባላል፡፡ ሲተነተን የኢትዮጲያዊ ብሄርተኝነት ንቅናቄ ማለት ነው፡፡በፈረንጅኛው Movement for Ethiopian Nationalism.(MEN) ይባላል፡፡ ይህ ንቅናቄ አሁን ገሃድ ወጥቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይደግ እንጂ ሃሳቡ ከአመታት በፈት እኔን ጨምሮ በሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን ወጣቶች ዘንድ ሲንሸራሸር የቆየ ነው፡፡ ከስያሜው መረዳት እንሚቻለው ኢብን የብሄርተኞች እንቅስቃሴ ሲሆን ብሄርተኛ የሚለው ቃል ግን አሁን በህዝባችን ዘንድ ብሄር ለሚለው ቃል ከሚሰጠው ትርጓሜ የራቀ ነው፡፡ እኛ "ብሄር" የምንለው ሀገር ከሚለው ቃል ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ባለው አረዳድ ሲሆን "ብሄርተኝነትም" ህዝቦች ቀደም ብለው ከሚጋሩት ታሪክ ፡የግዛት አንድነት ሉአላዊነት ቋንቋ ፡ባህል ፡ሃይማኖት ወዘተ የሚመነጭ ሀገርን
ከምንም ነገር በላይ ከፍ አድርጎ ማፍቀር እና ለዚህም ልዩ ቦታ መስጠት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ እሳቤ ነው፡፡
ኢብን ን ለምን አሁን ላይ ማቋቋም አስፈለገ? ሁላችሁም እንደምታውቁት በሀገራችን ለባለፈት 27 አመታት በነበረው የፖለቲካ አካሄድ ብዙ አይነት ጉዳት የደረሰ ቢሆንም በተለየ ግን
በኢትዮጲያዊ ብሄርተኝነት ስሜት ላይ የደረሰውን ያህል አስከፊ ጉዳት በምንም ላይ አልደረሰም፡፡ መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ አንድ ቅኝ ወራሪ ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ኢትዮጲውያን ማንነታቸውም ረስተው ብሄራዊ ስሜታቸው እልም ብሎ ጠፍቶ በወረደ መንደራዊ እና ጎጣዊ አስተሳሰብ ስር እንዲወድቁ… ሀገራዊ ስሜታቸው እንዲሟሽሽ …ባንዲራ እኮ ጨርቅ ነው እየተባሉ ምንም አይነት የሀገር ፍቅር እንዳይኖራቸው ሆነው እንዲቀመጡ
በተለያየ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እርስ እርሳቸው እንደጎረቤት ሀገራት ህዝቦች እየተያዩ እንዲኖሩ ክልሎች እና በውስጣቸው የሚኖሩ ህዝቦች ክልልነትን እንደ ሉአላዊ ሀገርነት በመቁጠር ከክልሌ ውጣልኝ እስከማለት የደረሰ አስቂኝ ድንቁርና ውስጥ እንዲዘፈቁ አድርገዋቸው ቆይተዋል፡፡ የዚህንም የተንሻፈፈ የመሃይም ፖለቲካ ገፈት ተራው ህዝቡ በየቀኑ እየቀመሰው ይገኛል፡፡ ዛሬ የኢትዮጲያን ባንዲራይዞ በአደባባይ መገኝት በተለይ በአንዳንድ
ክልሎች በራስ ላይ ተወግሮ የመገደልን አደጋ እንደመጋበዝ የሚቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ዛሬ እኮ ህዝብ በተሰበሰበት ወደ መድረክ ንግግር ለማድረግ የሚወጣን ተናጋሪ(አክቲቪስት) "ስለ እንትን ብሄር እንጂ ስለ ኢትዮጲያ ብታወራ ችግር ይገጥምሃል" ብለን የምንመክርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ዛሬ እኮ ሀገሩን ለመገንጠል የሚሯሯጥን የክልል ፕሬዝዳንት ለመውጋት የዘመተን የሀገር መከላከያ ጦር አውግዘን "የእንትን ብሄር
ወታደር በዚህ ጦርነት ላይ ብትሳተፍ ውሻ ውለድ" ብለን የምንገዝት አሳፋሪ ወጣቶች ተፈጥረናል…..በዚሁ ዘመቻም መከላከያችን እድል ፊቷን ለደቂቃዎች ያዞረችበት ሲመስለን እና ሀገራችን ወደመፈራረሱ ጫፍ ስትደርስ ጮቤ መርገጥ የሚያምረን ከንቱ ወጣቶች ተፈጥረናል፡፡ ዛሬ ይህቺን ሀገር እንደሀገር ያቆሟትን ንጉስ ሃውልት እራሳቸው ከቆረቆሯት ከተማ ላይ ነቅዬ እወረውራለሁ የሚል ወጣት ተፈጥሮ
ፖሊስ ሃውልቱን ከቦ ሲጠብን የሚያድርባት ሀገር እያየን ያለንበት ሁኔታ
ውስጥ ነን፡፡ ይሁን እንጂ

ነገሮች በእንዲህ አይነት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እያሉም ቢሆን ሀሉም የራሱን ጎሳና ብሄረሰብ ጥቅም ህልውና እና ፍላጎት ቅድሚያ እየሰጠ መደራጀት በመቀጠሉ ለጊዜውም ቢሆን ሀገራችንን የሚያስተዳደረው የፖለቲካ ድርጅትም
ቢሆንም በጎሳ የተደራጀ ስብስብ በመሆኑ አሁን ላይ ያሉት ሌሎች ሀገራዊ የፖለቲካ ድርጅቶችም ቢሆኑ በዋናነት
የተደራጁት በዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስረአት እና ዲሞከራሲን
እንዲሰፍን ለመታገል እንጂ በቀጥታየኢትዮጲያዊ ብሄርተኝትን ህልውና ለማረጋገጥ ባለመሆኑ ይህንን በቀጥታ በኢትዮጲያዊ ብሄርተኝነት
እሳቤ የሚመራ ንቅናቄ ለመመስረት ተገደናል፡፡ ይህም ንቅናቄ በአሁኑ ሰአት እጅግ በርካታ አባላትን በማቀፍ ወደ
ተግባራዊ እንቅስቃሴ የገባ ሲሆን ለኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
ሃሳባችንን አሳውቀን የአባላት መመዝገቢያ ቅጽ ወስደን እና ጊዜያዊ
ቢሮ ከፍተን በሰፊው አባላትን እየመዘገብን እንገኛለን፡፡ በንቅንቃያችን ለመሳተፍ ቀዳሚው መስፈርት የሀገር ፍቅር ብቻ ሲሆን ሌሎች ግዴታዎችን ደግሞ በአካባቢያችሁ ያሉ የንቅናቄያችን
አስተባባሪዎችን በማነጋገር እና መስፈረቶችን ሟሟላት የምትችሉ
መሆኑን በማረጋገጥ አባል መሆን ትችላላችሁ፡፡ ስለንቅናቄያችን የበለጠ ለመረዳት የንቅናቄውን ጊዜያዊ ፕሮግራም ማንበብ የምትችሉ ሲሆን "በምኖርበት አካባቢ የንቅናቄው አስተባባሪ መሆን እፈልጋለሁ "የምትሉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን በውስጥ
መስመር ልታነጋግሩኝ ትችላላችሁ፡፡ለጊዜው ንቅናቄውን በተመለከተ የሚሰጥ መግለጫ በእኔ ፔጅና በኢብን ስም በሚከፈት ፔጅ ብቻ የሚገለጸው ብቻ ሲሆን በቅርቡ የሌሎች አስተባባሪ አባላትን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን፡፡

መልካም ቀን
ኢትዮጲያ ትቅደም!

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
daregot magazine 3.pdf
6.8 MB
ዳረጎት ሶስተኛውን መጽሔት በሰላም አጠናቆ ለ አንባቢ አድርሷል። መልካም ንባብ!!!

@daregot
@daregot
# ሞረሽ ----- #ሞረሽ!!!!
-------------
ህዝብ ሚዛን አልባና "ጨዋ" ሲሆን ወደጎተቱት የሚሳብ ሃረግ ነው። ጎታቹ ጉልበት ይኑረው
እንጂ አንተን እውነትህ ጋር ጥሎህ ሽብልል ይላል።
የማይሙ ነገውን አለማወቅ አይደንቅም። አገር ልቀጥል-ልጥፋ እያለች በምትቃትትበት
በዚህ የጭንቅ ሰኣት ዳር ላይ ቆሞ የሚመመለከት ንፍዝ "ሙህር ነኝ" ባይ፥ ሃሞቱ የፈሰሰ
ወጣት ነኝ ባይ ማየት እንዴት ያማል!!!!
---------
ወደ ግንባሩ ብቅ ብለህ የሴረኞችን ጉንጉን ማፍረስ ላይ አትተባበርና ነገህ እንዴት
እንደሚመር ታየዋለህ። "በምንአገባኝ" ጦስ የሚመጣ መዘዝ የሚያስከፍልህ ዋጋና መከራ
"የምንአገባኝን" ያክል ቀላል አደለም።
ጆሮህን አቁም!!! የልጆችህንና ታናናሾችህን አገርህን ጠብቅ!! የሺህ ዘመን ባለታሪክ አገር፥
ጣልያን ያልበታተናት አገር፥ በኛ ዘመን አትፈርስም!! ታፍራና ተከብራ የኖረች ኢትዮጵያ፣ በኛ
የጥበቃ ዘመን ውርደት አትከናነብም!!
------
ይህችን ሃገር እንደ ሃገር ለማስቀጠል የዚህ ዘመን ባለእዳዎችና ተረኞች እኛ ነን።
ሊያፈርሷት ካቆበቆቡት ሆዳሞችና ባንዳዎች እኛ ቀጣይነቷን የምንሻ ልጆቿ በብዙ እጥፍ
እንልቃለን። ይሁን እንጂ አልሚ የአጥፊን ያክል ትኩረትና ብርታት የለውምና አንተ
ተጋድመህና በሞቀ ብርድ ልብስ ታፍነህ ስታንኮራፋ፣ ሴረኛው ተንኮል ሲሸርብ አዳሩን
እንቅልፍ በአይኑ አይዞርም!! አንተ አገር አማን ብለህ ተጋድመህ፥ አጥፊህ ጓሮህንና
ማሳህን በሃሳብ ገመድ ይሸነሽናል፥ ይከፋፈላል!!
---------
ይሄ ጊዜ ወደፊት የምንመጣበት ነው። ይሄ ጊዜ ምን አገባኝ ብለን ራሳችንን በብርጭቆ
ውስጥ የምንደብቅበት የዝንጋኤ ሰኣት አደለም!! ጫጫታ ጠላሁ ብለን የምንመንንበት
የንስሃ ወቅት አደለም።
---------
አይንም፥ ጆሮም አገርን ወደማስቀጥል!!!!


(( ያሲን መሀመድ )))

ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
:::::::::
ብዙዎች ገና ሲያዩት ይበሳጫሉ! ገና የፊቱን ገፅ ሲመለከቱ በቅናት ይብሰለሰላሉ! ከእያንዳንዷ እርምጃው ውስጥ እንከንን ይፈልጋሉ! ... እንደ ዲዮጋን ፋኖስ ይዘው በእሱ ውድቀት ውስጥ የራሳቸውን ስኬት ለማግኘት ይባክናሉ! በፍፁም ጥሩ ነገሩን መስማት አይፈልጉም! እንቅልፍ የላቸውም! ቀን ከሌት ሴራ ሲሸርቡ ያድራሉ! ...
እሱ ግን የአባቱ ልጅ ነው! ደራሲው እንዳለው ጭብጨባ የማያስኮፍሰው እርግማን የማያከስመው የአራዳ ልጅ! መሳሪያ የተሸከሙትን በማይክ የሚዘርር ምትሀኛ... በምስራቅ ሲሉት በምእራብ
የሚገኝ አብሪ ኮኮብ።
...
ብዙዎች እሱን መሆን ይመኛሉ! ነገር ማንም እሱን መሆን አይችልም! ብዙዎች እንደሱ ዝነኛ መሆን ይፈልጋሉ... ነገር ግን ዝናን መሸከም አቅቷቸው ይወድቃሉ!
...
ማንም በንጉሱ ፊት የመቆም የሞራል ብቃት የለውም! የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እንደ ቴዲ አፍሮ አይነት ሰው ለመፍጠር ለሚቀጥሉት መቶ አመታት በአይነቱ አዲስ የሆነ የማህበረሰብ ጥናት ካደረጉ በኋላ ትውልዶቻቸውን እንደ አዲስ ማነፅ ይጠበቅባቸዋል ምክንያቱም ቴዲ ክስተት ነው...

[Dagmawi Dagmawi]

@lula_al_greeko
@getem
@getem
ሰው መሆን በቂ ነው!!!!
ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ሀገራችን ኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪ የለውጥ ሂደት ላይ መሆኗ እሙን ነው፡፡ በአንፃሩ አንዳንዴ የሚታዩ አሳዛኝ ክስተቶች በዜጎች ልቦና ውስጥ ስጋትን ማጫራቸው አልቀረም፡፡ ቀደም ሲል ከሶማሊያ ክልል የተፈናቀሉ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን እንባ በወጉ ሳናብስ በተለይዩ የሀገራችን ክፍሎች በተነሱ መሰል ግጭቶች የንፁሃን ህይወት ተቀጥፏል፣በሽህዎች የሚቆጠሩ ዜጐች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናትም በቡራዩ እና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ግፍ ሁሉንም ዜጋ ከልብ ያሳዘነ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ በየትኛውም ክልል በማንኛውም ዜጋ ላይ ዘርን መሰረት ያደረገ ከየትኛውም ወገን የሚፈፀም ጥቃት በፅኑ ሊወገዝ ይገባዋል፡፡ ይህንን አይነት አስተሳሰብም ሆነ ተግባር የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሰባኪያን፣ከፖለቲከኞች፣ ከጥበብ ሰዎች እና ከተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው፡፡ ተግባራችን የአስተሳሰባችን ውጤት ነውና
የሚከተሉትን ነጥቦች (እንደመነሻ) ማጤንና ሃሳቦቹን በህዝባችን ውስጥ ማስረፅ ግጭቶቹን በዘላቂነት ይፈታል የሚል እምነት አለኝ፡፡
1. የሰው ልጆች በሙሉ የአንድ አባት ልጆች ነን፤መርጠንና ፈልገን የተፈጠርንበት ዘር የለንም፡፡ በጥረታችን እና ልፋታችን ያገኘነው ጎሳም የለንም፡፡ ብዝኃነታችን የፈጣሪያችን ተሰጥኦ ነው፡፡እንተዋወቅ ዘንድ የተለያዬ ጎሳና ዘር ሆነን ተፈጥረናል፡፡ትውውቃችን የእድገትና የብልፅግናችን ምስጢር ነው፡፡ የአንዱ ባህልና የተከማቸ የዘመናት ዕውቀት
ከሌላ ወገኑ ባህልና ለዘመናት የተከማቸ ዕውቀት ጋር ሲደመር ሁለቱም ካሉበት የእድገት እርከን ከፍ ለማለት፣ የተጋረጡባቸውን ተግዳሮቶች ለማለፍና አስተማማኝ ብልፅና ላይ ለመድረስ መሰላል ይሆናቸዋል፡፡የመተዋወቁ ፋይዳም ይኼው ነው፡፡ "እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን
(ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ።" አንኒሳእ (1) "እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ ፡እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ።" አል ሑጁራት (13)
2. ማንም ዘር ከማንም አይበልጥም ፤ማንም ጎሳ ከማንም አይልቅም፡፡ ማንነታችን የሚለካው በግለሰባዊ ስብዕናችን እንጂ በዘር ግንዳችን አይደለም፡፡ የሚያስከብረንም የተስተካከለ አስተሳሰባችንና በጎ ተግባራችን እንጂ የ‹‹ማን ልጅ››ነታችን ፈፅሞ ሊሆን አይችልም፡፡
‹‹የሰው ልጆች እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩል ናቸው፡፡›› ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)
‹‹ስራው ወደ ኋላ ያስቀረው ዘሩ ቀዳሚ አያደርገውም፡፡›› ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) 3. ከየትኛውም ማንነታችን በፊት የሚቀድመው ሰውነታችን ነው፡፡ ከብሄር ማንነታችን በፊት ሰዎች ነን፡፡ ከኢትዮጲያዊነታችን በፊትም ሰው መሆናችን ይቀድማል፡፡ ስለ ተጨማሪ ማንነታችን ለመነጋገር ሰውነታችን ላይ በፅኑ ማስመር ይኖርብናል፡፡ የብሄር፣የቋንቋም ሆነ
የሀይማኖት ማንነታችን ተከብሮልን የምንኖርባት ሃገር መገንባት ይቻለን ዘንድ በቅድሚያ በሰውነታችን ልንከባበር ግድ ይለናል፡፡ እንዲህ ማሰብ ስንችል የተፈፀመን ግፍ ለማስቆም የፈፃሚውን ማንነት አንጠይቅም፤በግፍ ከተጎዳው ጎን ለመቆም የተጎጂውን ማንነት አናጣራም፡፡ ሰው በመሆናችን በቻ ለሰዎች መኖርን እንማራለን፡፡ በአንፃሩ ሃገሪቱ ውስጥ ለሚመጣ ብልፅግና ተጠቃሚ ለመሆን "የኔ" የምንለውን ወገን ፍለጋ አንማስንም፡፡ ሁሉም የሀገራችን ሰዎች "የኛ" ናቸውና ለሁሉም ብልፅግና እንታትራለን፡፡ 4. ፍትህ ዘር ወይም ኃይማኖት የለውም፡፡ ከፍትህ እና ከእውነት ጎን መቆም የሰውነት ክብር
እውነተኛ መገለጫው ነው፡፡ የሰዎችን ዘር ወይም ኃይማኖት ግንዛቤ ውስጥ ሳናስገባ ለሰውነታችን ብቻ ክብር ሰጥተን ሲበደሉ በደላቸውን ስናስወግድ፣መልካም ሲሰሩ
ስናበረታታና ሲሳሳቱ ስናርም ያኔ ጠንካራ ህብረተሰብ እንገነባለን፡፡ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በወጣትነት ዘመናቸው በቁረይሽ ባላባቶች ይፈፀም የነበረን ዝርፊያ ለማስቆም ከአቻዎቻቸው ጋር ያደረጉት ስምምነት ‹‹ሒልፈል ፉዱል›› በመባል ይታወቃል፡፡ነቢይ ከሆኑ በኋላ ይህንን ስምምነት በኩራት ያወሱት ነበር፤ባዕድ አመላኪያን ጋር የተደረገ ስምምነት ቢሆንም በነቢይነት ማዕረጋቸው ቢጠሩ እንኳ ጥሪውን እንደሚቀበሉ ይገልፁ ነበር፡፡ ፍትህን
ለማስፈን የተደረገ ስምምነት ነበርና!
5. በሁሉም ብሄር ውስጥ በእኩይ ተግባር የተጠመዱ ግለሰቦች ወይንም ቡድኖች ይኖራሉ፡፡ ተጠያቂ የሚሆኑት እነኚያው ግለሰቦች ወይንም ቡድኖች እንጂ አጠቃላይ የዛ ብሄር አባላት አይደሉም፡፡ ስለሆነም የአንድ ግለሰብንም ሆነ ቡድን ወንጀል ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለው፣ ነገርግን የዚያ ግለሰብ ወይንም ቡድን ዘር ወይንም ጎሳ አካል የሆነ ግለሰብ ጋር ማዛመድ ፍፁም ኢ-ምክንያታዊ ተግባር ነው፡፡ ጅምላ ፍረጃ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ያደርሳልና የሚያስከትለውን ጉዳት መተንበይ አይቻልም፡፡ የተከበረው ቅዱስ ቁርዓንም
ማንም ግለሰብ በሌሎች ሃጢአት እንደማይጠየቅ ሲያውጅ አንዲት ነፍስ፦
"የሌላይቱን ሸክም (ኃጢአት) አትሸከምም" አል አንዓም (164) ሲል ይህንኑ መርህ ያፀናል።
6. መረጃን ማጣራት እና በማስረጃ የመደገፍ ባህል በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡የተሰማ ሁሉ አይወራም። የተፃፈ ሁሉ አይሰራጭም። ጥርጣሬ ሁሉ እውነት አይደለም፡፡ በተለይ መረጃው ህዝብን ከህዝብ ሊያጋጭ የሚችል ሆኖ ሲገኝ መልሶ መላልሶ ማሰብ ግድ ይላል፡፡
የተገኘውን ሁሉ በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎችም ሆነ አፍ ለአፍ መቀባበል ሀገርን ለአደጋ ይጥላል፡፡ ግጭትን ከማራገብ ይልቅ ማርገብን ቅድሚያ መስጠት ትልቅነት ነው። "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ህዝቦችን እንዳትጎዱና በሰራችሁት ነገር ላይ ተፀፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ።" አል ሑጁራት (5) 7. ታሪክ የትውልድ ትምህርት ቤት እንጂ የግጭት ማዕከል ሊሆን አይገባም፡፡ የቅዱስ ቁርዓን 1/3 ኛ ያክሉ በታሪክ መሞላቱ የአንድን ህዝብ ለውጥ እውን ለማድረግ ታሪክ ያለውን ሚና በግልፅ ያመላክታል፡፡ እንደ ማንኛውም ህዝብ ያሳለፍናቸው የስኬትና የልዕልና ታሪኮቻቻን ለወደፊት ብልፅግናችን አወንታዊ ግብዓት ሆነው ያገለግሉን ዘንድ እናወድሳቸዋለን፡፡ በአንፃሩ የውድቀትና የእርስ በእርስ እልቂት ታሪኮቻችን ደግሞ ዛሬም ሆነ ነገ ዳግም አይደገሙ ዘንድ እንማርባቸዋለን።
አለቀ። የታሪክ ሚናው ይኼው ነው። ታሪክ ዛሬያችንን ሊያቃና እንጂ ሊያደናቅፍ ፣ ነጋችንን ሊያለመልም እንጂ ሊያከስም ፈፅሞ አይገባውም፡በመጨረሻም ፅሁፌን በሙፍቲ ሐጅ ዑመር ድንቅ ቃል ቋጨሁ። " ሰውነት ከሁሉም ይቀድማል።" አላህ ሆይ! ሃገራችንን እና ህዝባችንን ጠብቅልን!


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ጀውሓር እና እምነቱ!!! (በታሪክተንታኙ ኢብራሒም ሙሉሸዋ)
---------//////////----------/////////--------/////////---—
ወንድሜ ጀውሓር ሙሀመድ ላይ የሚደረግ ዘመቻ ሌሎች ሙስሊም ያለሆኑ ኦሮሞ አክቲቪስቶች ላይም እየተደረገ እንደሆነ እያየህ በምን አግባብ ነው ጀውሓር ሙስሊም ስለሆነ ብቻ ዘመቻ ተከፈተበት ብለህ የምትነግረኝ?
ጀውሓር ላይም ይሁን ፀጋዬ ላይ፣ ታማኝ ላይም ይሁን ሀብታሙ ላይ ያላግባብ የሚደረግ የስም ማጥፍት ዘመቻን (character assassination)ን ስትቃወም እየተደረገ ያለው አግባብነት የሌለው ተግባር እንደሆነ ነጥቦችን እያነሳህ ተቃወም እንጂ በሙስሊምነታቸው ወይም በክርስትያንነታቸው የሚል ውሀ የማይቋጥር መከራከሪያ ማምጣት ለማናችም አይጠቅምም።
ጀውሓር ላይ የሚደረግ ተራ አሉታዊ ቅስቀሳ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳለ ግልፅ ነው። ጀውሓርን ለቡራዩው ጭፍጨፍ ተጠያቂ ለማድርግ የሚደረግ ግርግር አያሳምነኝም። ነገር ግን ጀውሓር እንደ አንድ የፓለቲካ ስብዕና ጠላትም ወዳጅም ያለው በመሆኑ ሊገጥመው የሚችል ነገር መሆኑን መቀበል እንዳለብንም አምናለው። ጀውሓር ላይ ላለው ዘመቻ የሀይማኖት ከለላ ለመስጠት መጣር ሀይማኖትን ማርከስ እንጂ ጀውሓርን መታደግ አይደለም። የጀውሓር መዳኛው የሚሰራው ተግባር ብቻ ነው። በውሸት
የሚከፈተበት ዘመቻ በሚኖር ጊዜ በእውነተኛ ተግባሩ ይመክተዋል። ጀውሓር ላይ የሚከፈትን ዘመቻ እንደማልቀላቀል ሁሉ ጀውሓርን ባልሆነ አቅጣጫ ‘ለማዳን’ መሞከርንም አልደግፍም። የጀውሓር ሙስሊምነትና ኦሮሞነቱ የሚያናዳቸው ሰዎች የሉም አልልም። በዚህ የተነሳ ጥላቻቸውን በግልፅ ሲያሳዩ ባየው ግዜም በግሌ አወግዛቸዋለው እታገላቸዋለሁም።
እንዲያው በደፈናው ግን «ሰዎች ጀውሓርን የሚጠሉት ሙስሊም ስለሆነ ነው።» ብለህ አትንገረኝ— ወንድሜ።
አሁን ካለው የዘመኑ አስቀያሚ የብሽሽቅ ፓለቲካ ሀይማኖቶቻችንን መታደግ ያለብን ይመስለኛል። እስልምናም ሆነ ክርስትና የችግሮቻችን መፍትሄ እንጂ እራሳቸውን የችግሩ አካል
እንዳናደርጋቸው እንጠንቀቅ!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሁን የተባልኩትን ነው የሆንኩት!
«ዘውድአለም ታደሠ»

ዳንኤል ጎበና "ሰርቅ. ዳ" በሚል የብእር ስም የፃፈው “የቃየን መስዋአት” የሚል ለኔ የምንግዜም ምርጥ ልቦለድ አለ። ልብወለዱ ውስጥ ደግሞ “ልኡል” የሚባል አንድ በፍቅር የወደቅሁለት ገፀባህሪ ይገኛል። ልኡል ድሮ መሬት ላራሹ ብሎ ለፍትህ የታገለ፣ ወታደር ሆኖ ሐገሩን ያገለገለ በሰብአዊነት የተሞላ ወጣት ነበር። ነገር ግን ልኡል በተለያየ
ምክኒያት ተገፍቶና ብዙ በሆነለት ህዝብ ክፋት ተስፋ ቆርጦ ለሰው ህይወት ደንታ የሌለው ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ሆነ። የሆነ ግዜ ታዲያ አብሮት ይጓዝ የነበረ ሌላኛው ገፀባህሪ ለምን እንዲህ ጨካኝ ሆንክ?»
ሲለው ልኡል ... «ሁን የተባልኩትን ነው የሆንኩት! የረገጥኩት ኩርባ፣ የጨበጥቁት ጉድባ፣ እሾህና ቆንጥሩ ቧጭሮ ቧጭሮ ቧጭሮ አስቀያሚ አደረገኝ» ብሎ መልሶለት ነበር።

አሁን በጥላቻ ተሞልተው የኔ የሚሉትን ወገን እያወደሱና ሌላው ላይ ልክ የሌለው ጥላቻና ሞትን የሚያውጁ፣ ለሰው ነፍስ ግድ የሌላቸው ሰዎችን ሳይ "ልኡል" ነው ትዝ የሚለኝ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች የሆነ ዘመን ላይ በሰዎች ሲቆስሉ ኖረው
በማህበረሰቡ ላይ ቂም የቋጠሩ፣ ነፍሳቸው በእሾህና አሜኬላ እየተቧጨረች፣ በደላቸውን ላለመርሳት እለት እለት ቁስላቸውን እየፈነቀሉ እንደአዲስ የሚታመሙ፣ ሰርክ እየጮሁ ማህበረሰቡ ህመማቸውን እንዲረዳላቸው የሚጥሩ፣ ምስኪኖች ይመስሉኛል። በዚች አለም ላይ በጥላቻ ውስጥ እንደሚኖር በስቃይ የተሞላ ሰው
ይኖር ይሆን?

እንዲህ አይነት ሰዎችን ስናይ ከመረረ ጥላቻና ቁጣቸው ጀርባ አልሽር እያለ የሚያሰቃያቸው ሃዘን እንዳለ ብናስብ መልካም ይመስለኛል።
ሲሳደቡ እየተሳደብን፣ ሲጠሉን እየጠላን ህመማቸውን ከዚህ በላይ ባናከፋውና ለጥላቻቸው ተጨማሪ ምክኒያት ባናዋጣ እንዴት ጥሩ ነበር!

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤
ግልባጭ ለቲም ለማ
.
እንደኢትዮጵያዊ ኖረን እንደብሔረሰብ እየሞትን ነው::
.
(በድሉ ዋቅጅራ፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ መስከረም፣ 12፣ 2011)
.
የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ አሁን ሀገራችን ውስጥ ያለውን ዝብርቅርቅ የህዝብ ስሜት፣ የፍቅርንና የመደመርን ተስፋ፣ የጥላቻንና የመበተንን ስጋት ስመለከት፣ የተቀመጡበትን መንበር ሰይጣን እንኳን ይመኘዋል ብዬ አላስብም፡፡ በመሆኑም ለሀገርዎና ለወገንዎ ሲሉ ራስዎን ከሚናወጠው ማእበል ውስጥ ጨምረው፣ ከዚህ የጥፋት ማዕበል ህዝቡን ይዘው ለመውጣት ለሚያደርጉት ደፋ ቀና ባለእዳዎ ነን፡፡
.
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የግማሽ ምዕተዓመት እድሜን ያሳለፍኩት በአምባገነን መንግስታት ጭቆናና በህዝቦች የአልገዛም ባይነት በምትናጥ ሀገር ውስጥ ነው፡፡ ወጣቶች ላልተማረው ህዝባቸው ነጻነት ሲሉ መፈክር ይዘው፣ አምባገነንነትን ሲቃወሙ በየጎዳናው ወድቀዋል፡፡ የአጼ ሀይለስላሴን ንጉሳዊ አገዛዝ የተቃወሙ ወጣቶች፣ ‹‹መሬት ላራሹን›› እየዘመሩ፣ ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው በየጎዳናው ሞተዋል፤ በወታደራዊው ደርግ ጨካኝ
አምባገነን ስርአትም እንዲሁ፣ ‹‹የዲሞክራሲን›› ጥያቄ ያነገቡ ወጣቶች የቀይ ሽብር ሰለባ ነዋል፡፡ በቀደም በእኔና በእርስዎ ዘመን፣ በኢትዮጵያ ታሪክ አስጎምጅቶን የቀረውን የ1997 ምርጫ ውጤት መጭበርበር ተከትሎ፣ ወጣቶች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች መስዋእትነት ከፍለዋል፤ በየእስርቤቱ የዘግናኝ ቶርቸር ሰለባ ሆነዋል፤ሀገራቸውን ጥለው ሲሰደዱ የተሳካላቸው ውቅያኖሱን ተሻግረው፣ ያልተሳካላቸው የባህር ሲሳይ ሆነዋል፤ በአይሲኤስ የታረዱ ወገኖቻችንን ላይ የደረሰው በኢትዮጵያ ታሪክ በአምባገነን መሪዎቻችን የደረሰብን ጥቃት ቁንጮ እንደሆነ ለዘመናት እንዲቆይ፣ ከዚያ የከፋ በደል እንዳይደርስብን ምኞቴ ነው፡፡
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከላይ የዘረዘርኳቸው ወጣቶች፣ ዜጎች ኢትዮጵያውያን ሆነው በኖሩባት ሀገ፣ር ኢትዮጵያዊ ሆነው የተሰዉ ናቸው፡፡ ‹‹መሬት ላራሹ›› ለኢትዮጵያውያን
ነበር፡፡ ‹‹ህዝባዊ መንግስት››ና የዲሞክራሲ ጥያቄ ለኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ ‹በ1997ቱ› ምርጫ የተከፈለው መስዋእትነትም ለኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ በቀደም ቄሮዎች፣ ፋኖዎችና ሌሎች የከፈሉት መስዋእትነትም፣ ‹‹ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው! ኢትዮጵያዊነት ሲያሻን የምንበትነው ገበያ አይደለም!›› በሚለው ቲም ለማ እየተመራ ለኢትዮጵያውያን የተከፈለ መስዋእትነት ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ለዘመናት ለኢትዮጵያውያን በተከፈለ መስዋእትነት፣
በእርስዎ፣ በቲም ለማና በገዱ በሚመራው የብአዲን አመራር ቆራጥ ትግልና መሪነት፣ ከሁለት አስርት በማትዘል ቀሪ እድሜዬ (ያውም ካደላት) አየዋለሁ ብዬ ያልጠበቅኩት ለውጥ አካል ለመሆን በቅቻለሁ፡፡
.
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ መስዋእትነት የተገኘ ለውጥ፣ ሌላ አምባገነን እግር ስር ሲገባ በተደጋጋሚ ተመልክተናል፡፡ በ66 መስዋእት ሆኖ አብዮትን ያፈነዳው ወጣት፣ ለውጡን ለደርግ አሳልፎ አስፋልት ላይ ቀርቷል፡፡ በ1983 እምቢ ብሎ ደርግን የጣለው ትውልድ፣ ‹‹ደርግን እኔ ነኝ የጣልኩት›› ለሚለው ተጋዳላይ ምቾትና ልእልና አገልጋይ ሆኖ ሃያ ሰባት አመት ኖሯል፡፡ አሁን በቄሮ፣ በፋኖና በህዝብ ትግል የተገኘው ለውጥም መርዶና ብስራቱ እየተደባለቀ፤ በፈገግታ ነቅተን፣ ሲመሽ በሳግ እናንቀላፋለን፡፡ የጀመርነው ህልም ቅዠት ሆኖ ያልቃል፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች ሰዎች እየሞቱ ነው፡፡ ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ላለፉት ሶስትና አራት ወራት የሀገራችን ፀሀይ ያለሞት ወጥታ የጠለቀችበት ጊዜ መኖሩን እንጃ፡፡ የዛሬ እናቶች ልጆቻቸው ፊታቸው ሲገደሉ
ያያሉ፤ ህፃናት ወላጆቻቸው ሲገደሉ ያያሉ፡፡ የሚያሳዝነው በዚህ ለኢትዮጵያውያን ለውጥ በተከፈለ መስዋእትነት በተገኘ ለውጥ እየሞቱ ያሉ ሰዎች፣ ኢትዮጵያዊ ሆነው በኖሩበት
እድር፣ ብሔረሰብ ሆነው መሞታቸው ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ መቼም ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር ምን ማለት እንደሆነ፣ ከልቤ ነው የምልዎት፣ ከእርስዎና ከቲም ለማ በላይ የሚያውቅ የለም፤ ‹‹ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት
ኢትዮጵያ ነን›› ማለትስ ይኸው አይደል! ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር ማለት እንደእኔ ክስታኔ ሆኖ፣ ኦሮሚያ እምብርት አሰላ ተወልዶ ማደግ ነው፡፡ አባቴ የጡት ልጅ ነበረው - ወንድማችን፡፡ ክርስቲያኗ እናቴ የአርሲዎቹን ፈጫሳ ትፈጭስ ነበር፡፡ ሙስሊሞቹ የጎረቤታችን ኦሮሞዎች
መስቀልን ከእኛ ጋር ለማክበር ሲጓጉ ለጉድ ነው፡፡ … ያ ነው እንደኢትዮጵያዊ መኖር፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር ሱማሌ ክልል - ጂጂጋ ላይ ኦሮሞዎችና አማሮቹ ከሱማሌዎቹ ጋር ‹‹አበሽ!›› እና ‹‹ዋሪያ›› እየተባባሉ ይኖሩት የነበረው ኑሮ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሆኖ መኖር ማለት አዋሳ ላይ ሲዳማዎችና ወላይታዎች በአንድ እድር ስር፣ የታመመ እየጠየቁ፣ የተቸገረ
እየረዱ፣ የሞተ እየቀበሩ ‹‹ዳኤ ቡሽ›› እና ‹‹ሎ ዳይኤ›› እየተባባሉ የኖሩት ኑሮ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር ማለት እዚህ አዲስ አበባ ጠርዝ ላይ፣ አሸዋ ሜዳ ጋሞዎችና ኦሮሞዎች ቡና እየተጠራሩ፣ ያንዱን ልጅ አንደኛው እየቀጣ - ልጆቻቸውን በጋራ ያሳድጉበት
የነበረው ኑሮ ነው፡፡
.
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እነዚህ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩ ዜጎች ኢትዮጵያዊ ሆነው አልሞቱም፡፡ ጅጅጋ ላይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩት ኦሮሞዎች - ኦሮሞ ብቻ ሆነው ሞቱ፡፡
ቤንሻንጉል ላይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩ አማሮች አማራ ብቻ ሆነው ሞቱ፡፡ አዋሳ ላይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩ ወላይታዎች ወላይታ ብቻ ሆነው ሞቱ፡፡ አሸዋ ሜዳ ላይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩ ጋሞዎች፣ ሲልጤዎችና ጉራጌዎች ብሄረሰብ ሆነው ሞቱ፡፡ ጉጂ ላይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የኖሩ ጌዴኦዎች ጌዴኦ ብቻ ሆነው ሞቱ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እንኳን ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመሞት፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመስደድም መንገድ ጠፋ፡፡ ሶማሌ ክልል ጥሪት አፍርተው፣ ወልደው ከብደው የኖሩ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞ ሆነው ተሰደዱ፡፡
ቤንሻንጉል የኖሩ ኢትዮጵያውያን አማራ፣ አዋሳ የኖሩ ኢትዮጵያውያን ወላይታ… ሆነው ነው የተሰደዱት፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆነን ኖረን ብሔረሰብ ሆነን እየሞትን፣ እየተሰደድን ነው፡፡
.
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በጎሳ መጋዝ ለሀያ ሰባት አመታት በተበጣጠሰች ሀገር፣ በአመጽ የመጣን ለውጥ፣ ጠመንጃ ሳይሆን ፍቅርና ይቅርታን፣ ጥላቻን ሳይሆን መደመርን ይዞ፣
ከግብ ማድረስ እጅግ ከባድ ኃላፊነት ነው፡፡ ለዚህ ሃላፊነት ደግሞ ከእርስዎና ከቲም ለማ በቀር ቁርጠኛና ዝግጁ መሪ አልነበረም፡፡ ህወሀት-ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት ዓመታት በመሰሪ የጎሳ ፖለቲካ ሸንሽኖ፣ እንደኢትዮጵያዊ እንዳንኖር ብዙ ሞክሯል፡፡ የብሔር ብሔረሰብም
መብታችን ቢሆን ለእሱ ባለን አዎንታዊና አሉታዊ አመለካከት እየተሰፈረ የሚሰጠን እንጂ የሰብአዊ መብታችንን፣ የብሄረሰባዊ ድርሻችንን ያህል አልነበረም፡፡ ህወሃት-ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት ዓመት በጥላቻና መከፋፈል የተለወሰ የብሔር ፖለቲካ አላማ በልዩነታችን ደምቀን፣ በፍቅር ተቃቅፈን ኢትዮጵያዊ ሆነን እንዳንኖር ለማድረግ ነበር፡፡ አልተሳካለትም፡፡ ይሁን እንጂ እንደኢትዮጵያዊ እንዳንኖር ማድረጉ ባይሳካለትም፣ እንደኢትዮጵያዊ እንዳንሞት አድርጎናል፤ እንደብሔረሰብ ገዳይና ሟች እየሆንን ነው፡፡
.
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በሀገራችን ታሪክ እንደእርስዎ ህዝብ የተቀበለው መሪ አላየሁም፡፡ በ1997 የመረጠውን መሪ የተነጠቀው ህዝብ፣ አሁን ህዝብን መርጦ የመጣ መሪ አግኝቶ ሲነሳ ለምን አይደሰትም!? እንደሚያውቁት የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅር ባይ ነው
የአንደበትን ብቻ ሳይሆን የውስጥን ሞራ ያነባል፡፡ እርስዎን የተከተልዎት ሞራዎን አንብቦ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቃል አንድም በግብር ይገዝፋል፤ አንድም ቧልት ሆኖ ይጠፋል፡፡ በዚህ በኩል እርስዎ ቃልዎን ህያው ሊያደርጉ ተግባር - ነፍስ እፍ ሲሉበት፣ በሌላ በኩል ዝርፊያ፣ ግድያና መፈናቀል ቃልዎን ገድሎ ለመቅበር ጸረ ለውጥ ሀይሎች ጉድጓድ ይቆፍራሉ፡፡
.
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ ለውጥ እንዲጠለፍ ወይም እንዲጨነግፍ በፍፁም አይፈልግም፡፡ የሚሆነው ግን ከፍላጎታችን ተቃራኒነቱ እየጠነከረ ነው፡፡ እኔም ‹‹ሾላ በድፍን›› ቢበዛ፣ ቀና ያለ አንገቴ በትካዜ እያዘነበለብኝ ተቸገርኩ፡፡ ‹‹ምን እየሆነ ነው ያለው? ፖሊሶች በቆሙበት እንዴት ሰዎች ይገደላሉ? ይቃጠላሉ? ይሰቀላሉ? የለውጡ ሀይል ያልሆነ (ያልተደመረ) ፖሊስ አለ ኢትዮጵያዊነት የልብ ነው የከንፈር? . . . . በርካታ ጥያቄዎች ይመጡብኛል፡፡ ከህሊናዬ በምክንያት ሳባርራቸው፣ ምክንያት ከማይደርስበት ልቦናዬ ይሸነቀራሉ፡፡ እኔ ፊደል የቆጠርኩት መጠራጠር በወለደው መብሰልሰል ስወጠር፣ ያልተማሩ ወገኖቼ፣‹‹እየሞትን አንደመርም›› ብለው፣ አዲስ አበባን
በሰላማዊ ሰልፍ አጨናነቋት፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ነገ፣ ከነገ ወዲያ ምን ይመጣል? በፍፁም ይህን ማሰብ አልፈልግም፡.
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሀገሬን ሰው ለውድቀት ከሚያመቻቹት መጥፎ ባህላችን አንዱ ስም ጠርቶ መሸለም እንጂ፣ ስም ጠርቶ መርገም አለመቻላችን ነው፡፡ አንዳንዴም ቢሆን ጥሩ የሰራን በስሙ ጠርተን፣ አሞካሽተን እንሸልማለን፤ መጥፎ የሰራን ግን ስም ጠርተን አንረግምም፤ እድር አቁመን፣ ስብሰባ ጠርተን፣ ‹‹አንዳንድ ሰዎች፣ አንዳንዶቻችሁ›› እያልን ለወንጀለኛና ለግፈኛ ምሽግ ሆነን ነው የምንኖረው፡፡ ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እባክዎን በጎ
የሰራን መሸለሙን ጋብ አድርገን፣ አጥፊዎቻችን በስም ጠርተን ሸንጎ አቁመን እንርገም፡፡ ይህ ህዝቡን ከጥርጣሬ፣ ለውጡን ከውጣ ውረድ ለማውጣት ይረዳል።ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፡- ይህ በህይወቴ የተመለከትኩት - የተሳተፍኩበት እውነተኛ ለውጥ ነው፡፡ እንዲቀለበስ አልሻም፡፡ ለልጆቼ ፍሬውን እፈልገዋለሁ፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊም ከዚህ የተለየ ፍላጎት እንደሌለው እርግጠኛ ነው፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን ሀሳቦች ከግምት ያስገቡልኝ ዘንድ ከህዝቡ መሀል ቆሜ በክብር እጠይቅዎታለሁ፡፡1ኛ. ከለውጡ ዋዜማ ጀምሮ የነበረው ለውጡን የመቆጣጠርና የመምራት ሙሉ አቅምዎን ይቀጥሉ፡፡ አንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግድያና ዝርፊያ፣ ፖሊስ ባለበት የሚፈፀም በመሆኑ፣ ለውጡን የመቆጣጠር አቅም እንደሌለዎ፣ ህዝቡ እየተጠራጠረ ነው፡፡ ይህን ስሜት በጨቅላው ለመቅጨት፣ የህግ የበላይነትን ያረጋግጡ፡፡ የአራት ወር ምክርና ዝክር ለሰለጠነ ሰው ከበቂ በላይ ነው፡፡ ምክር ያልገራውን አውሬያዊ ባህሪ በህግ መታረቅ አለበት፤ ለህዝቦች ሰላምና ለለውጡ ስኬት ሲባል፡፡
.
2ኛ. ስም ጠርተን መሸለም ብቻ ሳይሆን፣ ስም ጠርተን መርገም - መጠየቅ እንጀምር፡፡ እንደሚያውቁት ለዚህ ለውጥ ሲታገሉ የኖሩ ጀግኖቻችንን ስም እየጠራን፣ ባንዲራ እያውለበለብን፣ በአደባባይ ጉንጉን አበባ አጥልቀንላቸዋል፡፡ ልክ እንዲሁ ምክርና ዝክር ያላረማቸውን፣ የህዝብ ልጆች የተሰዉለትን ለውጥ ለመቀልበስ፣ በወገንና በሀገር ላይ የተነሱትን ስም ጠርተን እንርገም፤ ፋይል ከፍተን ለህግ እናቅርብ፡፡ በእንዲህ ያለው የለውጥ ሂደት ጉንጉን አበባ የሚጠልቅላቸው ጀግኖች ብቻ ሳይሆኑ፣ ካቴና የሚጠልቅባቸው የለውጥ አደናቃፊዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ የአብዮታዊ ለውጥ አካል ነው፡፡ እነማን ከየቦታው ሰዎችን አፈናቀሉ? እነማን አዋሳ ላይ ገደሉ፣ አቃጠሉ? እነማን ሻሸመኔ ላይ
ሰቀሉ? እነማን አሸዋ ሜዳ በተፈጸመው ተጠርጥረው ታሰሩ? እውነት ከየአንዳንዱ ጥቃት ጀርባ እንደሚባለው በገንዘብ ሽብሩን የሚደግፉ ሰዎች፣ ወይም ቡድኖች አሉ? ካሉ እነማን ናቸው?
.
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በህይወት ዘመኔ እንዲህ ለቤተመንግስት የመቅረብ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ እርስዎ ብቻ አይደሉም፣ ወደታች ወደህዝቡ የመጡት ህዝቡም በእርስዎ ውስጥ አድሮ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነ ያህል ነው የሚሰማው፡፡ እና ይበርቱ! ከጎንዎ ነን፡፡ ይህን ለውጥ ከግብ ከማድረስ ውጪ እርስዎም ሆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ ሰነባብቼ ደግሞ ወደ አንጎሌ የመጣውን፣ ውቃቢዬ የፈቀደውን ከመፃፍ አልቦዝንም፡፡ እስከዚው ባሰቡት፣ በወጠኑትና በጀመሩት ሁሉ ፈጣሪ ይርዳዎ፡፡

አክባሪዎ
በድሉ ዋቅጅራ ከስድስት ኪሎ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/29 21:29:04
Back to Top
HTML Embed Code: