Telegram Web Link
# መገንባት_የማፍረስን_ያክል_ቀላል_አደለም !!
----------
አዲስ አበባ "የኛ" እንጂ "የኔ" ብቻ አደለችም። ወደዛች ከተማ ወዳገራችን ክፍል ሁላችንም ተራ በተራ ሄደናል፥ መጤ የለም!! ጣፋጭ የዱር ፍሬ የሚለቅም ሞኝና ስግብግብ እረኛ ይመስል ቀድሞ ባየ ሁሉን ነገር "የኔ
ብቻ ናት" የምትሉ ስራ አጦችና ነገን የማታዩ አንድ የታሪክ ሁነት ላይ የተቸከላችሁ ፍዝዞች አርፋችሁ ተቀመጡ። አገሬን አትበጥብጡ!! አገር ትዳር ስትመሰርት እንደምታስመዘግበው የግል ንብረት ስትፈልግ "የራሴ ብቻ ነው" ብለህ ይዘህ እንድምትሮጠው አይነት መናኛ ሸቀጥ አደለም። አገር ደምና አጥንት ነው። አደለም መናገሻው አዲስ አበባ፥ እዛ ጫፍ አንተና አንተ ብቻ የምትኖርበት ሰማይና መሬት "የኛም" ነው። ወዳጄ አገር አጥንትና ደም ነው!!
ይሰማሃል፥ አገር በዴቦ እንደሚታረስ የአርሶ አደር እዳሪ እርሻ አደለም። እንደ ምጣድ ዳቦህ ያሻህን ሰማይና መሬት "የኔ ብቻ ነው" እያልክ የምትሸነሽነው ሁሉ አጥንት-ጉልጥሚት ነው። ሁላችንም ሞተንበታል!! ስለሆነም በዚህ አገር ሁላችንም በሁሉም ቦታ ባለ መብት ነን። የቁርጡ ቀን አይምጣ እንጂ ከመጣ የትህነግ የተንኮል የመሬት ሽንሸና ገመድ እንደ ቅኝ ገዦች መስመር ይሰራል ብለህ እንቅልፍህን አትጣ፥ አይሰራም!! ህዝቡ አልቆ መሬቱ ነዋሪ
ያጣል እንጂ "የኔ ብቻ ነው" ስላልክ ማንም ከቆመበት ንቅንቅ አይልም። ጊዜያዊ መፈነቃቀሉና ሽሽቱ እውነት አይምሰልህ!! የገፋኸው ሁሉ ሊገፋህ ይመጣል። የሚበጀው ነገር አገር ምድሩ "የኛ ነው" ማለት ብቻ ይሆናል። እኛ ማለት ሁላችንም ነን። የኔ ብቻ ይሉት ፈሊጥ ለሞኝና ብልጥ የዱር ፍሬ ለቃሚ እረኞች ብቻ ይሰራል። የሞኞች አገር ዘመኑን ሁሉ በመናጥ ይኖራል። ሊቅ-ደቂቃኑ እኔ ልብለጥ እንጂ አብረን እንብለጥ አይሉም!! ራሳቸውን ያነግሳሉ እንጂ አንተን አያነሱም። ለራሳቸው በብዙ ይጎርሳሉ እንጂ አንተን ትንሽ እንኳን አያልሱም። በመሆኑም የውድቀት እንጂ የስኬት ታሪክ የላቸውም።
ሞኞችና አቅመ-ቢሶች ግብራቸው መናቆርና መጠፋፋት እንጂ ባህልና ታሪክ በጋራ ማቆም የሚችል የመቻቻያ ጫንቃ የላቸውም። እንደ ህዝብ እኒህን መሰል ህዝቦች የማፍረስ እንጂ የመገንባት ታሪካቸው ትልቅ አደለም። ለምን ቢባል መገንባት የማፍረስን ያክል ቀላል አደለም!! ለምን ቢባል እነሱ የስልጣኔው ዘመን ዋጋ ከፋይ እድለ-ቢሶች ነቸዋ!!


((( ያሲን መሀመድ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የኢትዮጱያ ፖለቲካ ዘፈን ነው። የኢትዮጱያ ፖለቲካ ዝላይና ጩኸት ብቻ ነው። የኢትዮጱያ ህዝብን ችግር ማዳመጥ እና ጊዜ ወስዶ መፍታት አልነበረም። 😔 የሆነ ቡድን ይደራጃል ፣ ወረቀት ይበተናል ፣ ይጨፈራል ያሸነፈ ይመስለዋል። ማሸነፍ ያ አደለም። ማሸነፍ የህዝብን ልብ ነው። የተሰበሰበውን ሁሉ ሁለት ጥይት ብትተኩስ ትበትነዋለህ ነገር ግን እኛ ማሸነፍ የምንፈልገው በ #ፍቅር ብቻ ነው።

#ኢትዮጱያዊነትብቻይለምልም
#ፍቅር ያሸንፋል

አበቃ

ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ


@Wegoch
@Getem
@Mykeypictures
❤️ፍቅር ይባላል የኛ ባንዲራ

@Getem
@Wegoch
@Mykeypictures
ስለ ምኒሊክ ሃውልት ስንናገር !!!!!


እንደነገርኳችሁ ምኒልክና የሱ ዘመን አርበኞች በጀግንነት የአድዋን ድል ባይጎናፀፉ ኖሮ አባቶቻችን በባርነት ቀንበር ተይዘው እንደ ምእራብ አፍሪካ ዜጎች ገበያ ላይ ተደርድረው ለነጭ የሚፈነገሉ ሸቀጦች በሆኑ ነበር ። ግና ምኒልክ ከነ ግብረ አበሮቹ በሰራው የጀግና ስራ አባቶቻችን እንደ እቃ ከመሸጥ አምልጠው እኛም ከባሪያነት ተርፈን ዛሬ የነፃነት ልጆች መሆናችንን አለም ይመሰክራል እኛም ሁሌም በኩራት እንናገራለን ።አባቶቻችን በዚያ ዘመን የእምየ ሚኒሊክን ሃውልት መሃል አራዳ ላይ ያቆሙት የሃውልት ወልፍ ስለነሸጣቸው አይደለም ። ሃውሉትም የአንድ ሚኒሊክ መታሰቢያም አይደለም ። መታየትና መጤን ያለበት ነገር ቢኖር ለሃውልቱ መገንባት ምክንያት የሆነው ሃገራዊ የጋራ ጉዳይ ነው ። ለሃውልቱ መገንባት ምክንያት የሆነውም የምኒሊክ ግለ ስብእና ታሪክ አይደለም ። ይልቁንስ
በምኒሊክ ዘመነ መንግስት የተሰራውን ሃገራዊ የጀግኖች ታሪክ ለማስታወስ እንጅ ።በዚያ ሃውልት ዘንድ ጀግናው ባልቻ አባ ነፍሶ ፤ ጉበና ዳጬ ከጀግንነታቸው ጋር በአይነ ህሊናየ
ይታዩኛል ። በዚያ ሃውልቱ ስር የወሎው ራስ ሚካኤል ከወሎየዎች ጀብዳዊ መስዋእትነት ጋር ተስለው ይታዩኛል ። ሃውልቱ ስር አድዋ ላይ የወደቁ መላ የኢትዮጲያ ህዝቦች ዘርና ጎሳ ሳይለዩ ከጀግንነታቸው ጋር መስዋእት ሲሆኑ ይታወሰኛል ። ሃውልቱ መታሰቢያ ሃውልት ነውና ያንን ሁሉ ኢትዩጲያዊ ሃውልቱ ላይ በመልክ በመልኩ ማስቀመጥ አይቻልም። የትም ሃገር የዘመን መንፈስ ባንድ መሪ ይገለፃል ። በኢያሱ ጊዜ ፤ በዮሃንስ ጊዜ ፤ በቴዎድሮስ ጊዜ እየተባለ የዘመን መንፈስ ይገለፃል ። የምኒሊክ ሃውልትም የዘመን መንፈስ ማሳያ ነው ። የምኒሊክ ዘመን ዋነኛ መንፈሱ ቅኝ ግዛትን ነቅሎ የመጣል መንፈስ ነው ። ያንን የአድዋ
ድል ሃያል መንፈስ ለትውልዱ ኩራትና ክብር ይሆነው ዘንድ የሚኒሊክ ሃውልት መቆሙ መቼውንም ቢሆን ትክክል ነው ። ለምኒሊክ ሃውልት መቆም ምክንያት የሆነው ገድል የኦሮሞው የጉበና ዳጬ ፤ የባልቻ አባ ነፍሶና የብዙ እልፍ ሺህ ኦሮሞዎች ነው ። የንጉስ ሚካኤል የገበየሁ የአሉላና የባልቻ የገድል ታሪክ ነው ። ከሃውልቱ ጀርባ እንኳን ለኢትዩጲያን ቀርቶ ለጥቁር ህዝቦች ሞልቶ የሚፈስ የነፃነት መንፈስ ቆሞበታል ። ስለሆነም ሃውልቱ
የእገሌ ነው የእገሌ አይደለም የሚለው ከንቱ ክርክርም ሆነ ሃውልቱን ከአንድ ብሄር ማንነት ጋር ለማያያዝ መፍጨርጨር ባልቻንም ሆነ ገበየሁን ከመካድ እኩል ነው ። በዚህ ሰአት ስለ ሚኒልክ ሃውልት እያነሱ እንካ ስላንቲያ መግጠም የሚጠቅመው ለከሰሩት የጫካ ወንበዴዎች ብቻ ነው ። በዚህች ሁለት ቀን ብቻ ኦሮሞና አማራን የሚያጋጩ በሺህ የሚቆጠሩ fake accounts ተፈልፍለው አስጠያፊ የዘረኝነትመርዝ እየረጩ ነው። ወጣቶች በእነዚህ fake accounts እየተገፉ ስሜታዊ እርምጃ እየወሰዱ ነው ።
ጠላቶቻችን የባንዲራና የሃውልት የቤት ስራ ሰጥተው እያባሉን ነው ። በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች መሃከል የተሰራውን ድልድይ በማፍረስ ሸለቆው ውስጥ ሊያዳፍኑን የወሰኑ በላኤ ሰቦች በዚህ ሁለት ቀን ፌሽታ ላይ ናቸው ። እንደ ቀትር እባብ አፈር ልሰው ለመነሳት ሴራና
ሸራቸውን አጥብቀው እየሰሩ ነውና ከመቼውም በላይ ያንን ሰው በላ ቡድን ተመልሶ እንዳይዘፍንብን ከስሜታዊነት ፅዱ መሆን ግድ ይለናል ። ቄሮ ወንድሞቻችን ያኔ በክፉ የጀመሩትን መስዋእትነት የኦሮሞ ልጅ ደም የኔም ደም ነው ብለን አብረን ዘምተን ለድል
የበቃነው የአብዲሳ አጋን የባልቻ አባ ነፍሶን የበላይ ዘለቀን የንጉስ ሚካኤልን ኢትዩጲያ አስበንና ወደን እንጅ ለጎጠኝነትና ለብሄራችን ብቻ ቢሆን ኖሮ ማንም የማንም አጋዥ አይሆንም ነበር ። ነፍሰ በላው ቡድንም ብቻንን ነጥሎ ለመቅበር ይቻለው ነበር ። የትግሉን
ህመም በጋራ ታመን ስናበቃ ፈውሱን ለየብቻ ለማጣጣም መታከት ከግለኝነት የሚመነጭ ሌላ በሽታ ነው ። ስለሆነም ጠላቶቻችን የኛን መለያየት እውን እንዲሆን ሌት ተቀን እያሴሩብን መሆኑን ላፍታ ሳትረሱ እጅግ ጥቃቅን በሆኑ የልዩነት ሃቲቶች በመመሰጥ የተገኘውን ትልቅ ሃገራዊ እድል ለቀን ጅቦች አሳልፈን እንዳንሰጥ ቆም ብለን ብናስብ ሸጋ
ሳይሆን አይቀርም ለማለት ያህል ነው ። ሻሎም!!!


ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ዘገር ፤
ቄሮም ሆነ ፋኖ ፤
እንደ አፍሪካ ባሪያ ታስሮ ይሸጥ ነበር

((ከባሪያ ፍንገላ/ከመሸጥ ያተረፈን
ሚኒሊክ ይመስገን )))

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወደ ኋላ ስንራመድ(ልዑል ሀይሌ)


አንዳንዴ ትልቁ ለውጣችንን ወደፊት ምንም ያህል ተራምደን ስናጣው በኋልዮሽ እርምጃ ተመልሰን መነሻችንን መመርመር ትልቁ ብልሃት ይመስለኛል። አሁን ዐይናችንን ጋርዶ ከሚያፋጀን ብሔር፣ጎሳ፣ዘር ማንዘር ትንሽ ወደ ኋላ ስንራመድ ሐገር የምትባለውን ትልቅ ጥላችንን በአንድነት አሰባስባ ያስተቃቀፈችንን ውድ ሐብታችንን ስናገኝ ዘረኝነትን እንጠየፋለን። ከዚህ ትንሽ ወደ ኋላ ራመድ ስንል ደግሞ ከአህጉራዊነት
ብሎም ከአለማዊነት አልፈን ሀይማኖታችን ላይ ቆመን መፅሐፍ ቅዱስን ገልጠን መንፈሳችንን ገዝተን ኦሪት ዘፍጥረት ፪፥፯ ስናነብ እንዲህ
ይለናል "እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።" ይህ ነው መነሻችን አፈሩን እኛ እንደምናስበው ቀይ፣ጥቁር፣የሸክላ...ወይም ከእገሌ ክልል ከእንትና ክልል ተብሎ የተወሰደ ሳይባል ተለውሰን የከበረ እስትንፋስ እፍ የተባለብን የአዳም ልጆች ነን። ይሄንን ስናስተውል አሁን ላይ ምን ያህል ከክብራችን እንደወረድንና ራሳችንን ለማጥበብ እየተሯሯጥን መሆናችን ይገባናል። እስቲ ኑ አብረን ወደኋላ እንመለስ ዘርም ከተቋጠርን አይቀር ለምን ፮ወይም ፯ ትውልድ ድረስ ብቻ ቆጥረን እንቋጨው? ኑ እስከጥግ ድረስ
እንቁጠር የመጨረሻው ትውልዳችን ስም ሲመሳሰል የዘር ግንዳችን ከአንድ ቦታ የሚመዘዝ መሆኑን ስንመለከት አሁን የምንጋጭበት የጎሳ፣የዘር ነገር እንጠየፈዋለን። ስለዘር ስለጎሳ ከመገዳደላችን በፊት እስቲ አንድ ጥያቄ እንጠያየቅ "ማን ነው ሀገር መርጦ የተወለደ?..ማን ነው ቀለም መርጦ የተወለደ??"...ለዚህም ነው የተሰጠንን ነገር አክብረን ጠብቀን የምንኖረው ሌላው ሰውም ያለውን ነገር እንድናከብርለት የሚያስገድደን ሐቅ ይህ ነው። እኔ ዓለሜ፤ ሐገሬ ብዬ የተቀበልኳት በውስጤ የሳልኳት ባደግኩበት ማህበረሰብ ውስጥ የቦረቅኩባት፣ የተደሰትኩባት፣ ያዘንኩባት፣ በንፁህ ድህነትጨ በቁራሽ እንጀራና በእፍኝ ቆሎ ከወንድም እህቶቼ፣ ከጓደኞቼ ጋር ተካፍዬ
የበላሁባት ክፉም ደግም ያየሁባት የኔን ዳና ተከትላ የመጣች የተገነባሁባት ክብርት ማንነቴ ናት!..ከዚህችው ቁንፅል ማንነት ተነስቼ ሰብዓዊነትን እግሯ ስር ሆኜ ከ፮ ዓመቴ ጀምሮ ስለተማርኩባት ሸገር (አዲስ አበባ)...ተናገር ከተባልኩ እንዲህ እናገራለሁ... አዲስ አበባ
በሚዛናዊ አስተሳሰብና ሰውን በስብዕናው ብቻ መመዘንን አስተምራ ያሳደገችን እናት ከተማ ናት። ከዜሮ ክላስ ጀምሮ "የዜግነት ክብር"ን ጉሮሯችን እስኪሰነጠቅ ሰርክ የዘመርንባት፤በንፁህ ድህነት አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት የኖርንባት። ሀገር ማለት ሰው፣ሰው ማለት ሐገር ማለት እንደሆነ በፍቅር ያስተማረችን፤ ጉያዋን ሽቶ የመጣውን ወገን (እኔንም ጨምሮ)ፊት ሳትነሳ ከመሶቧ የምታቋድስ የኢትዮጵያዊነት
ትልቋ ትምህርት ቤት መሆኗን እመሰክራለሁ። ነገር ግን ይህ ማለት
ስለሌላው ምስክር መሆን አልችልም ማለት አይደለም። እኔ ለ፮ ዓመት
ከኖርኩባት እና ከቤተሰቦቼ ተነስቼ ስለ ትግሬ መልካምነት አፌን ሞልቼ እመሰክር ዘንድ እገደዳለሁ።እኔ ፭ኛ ክፍል ከአጠገቤ ይቀመጥ ከነበረው ምርጥ ጓደኛዬ ገዜ ተነስቼ ስለኦሮሞ መልካምነት አፌን ሞልቼ እመሰክር ዘንድ እገደዳለሁ።እኔ አብረውኝ ከተማሩት ብዙ
ጓደኞቼ እንዲሁም ከወዳጆቼ አማኒ፣ባያ፣እሱቤ ተነስቼ ስለ አማራ
መልካምነት አፌን ሞልቼ እመሰክር ዘንድ እገደዳለሁ። ከምርጥ ጓደኛዬ አሴ ተነስቼ የጉራጌን መልካምነት አፌን ሞልቼ እመሰክር ዘንድ እገደዳሁ። ከዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ወቅት ከማህበረሰቡ ሁሉ ባገኘሁት እንክብካቤ እና ከምርጥ ጓደኛዬ ተስፋ ተነስቼ የአርባምንጭን ብሎም የደቡብን መልካምነት አፌን ሞልቼ እመክከር ዘንድ እገደዳለሁ። ሌሎቹንም አካባቢዎች በወዳጆቼ ዓይን ስላየሁ አፌን ሞልቼ መመስከር እችላለሁ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ምን ያህል መልካም እንደሆነች፤ ምን ያህል ውድ እንደሆነች የትም ሳልሄድ ሸገር ላይ ሆኜ እንድረዳና ነገሮችን በሚዛናዊ መንገድ አይ ዘንድ አድርጎኛል ብዬ አስባለሁ።
ስለዚህ ሁሉንም ባሕልና ቋንቋዎችን አከብራለሁ እኔም የማውቃቸውን
ሁለት ቋንቋዎች(ትግርኛ እና አማርኛን) እንዲያከብርልኝ እፈልጋሁ። እኔም በማውቃቸው ቋንቋዎች ተጠቅሜ ስለ ሰብዓዊነት፣ስለ አፍሪካዊነት፣ስለ ኢትዮጵያዊነት ሰብኬ ህዝብን ማስተሳሰር ግድ እንደሚለኝ አአውቃለሁ። ነገር ግን ባንዲራን በተመለከተ ከአረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ውጪ እንደማልቀበል አፌን ሞልቼ እናገራለሁ።


ሰብአዊነት ይቅደም!!...ኢትዮጵያዊነት!!

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ትልቅ ሆቴል ውስጥ ሪሴፕሽን ሆኖ የሚሰራ የምንቀራረብ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ በስራ ላይ ሳለ ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ቦርሳ የያዘ ሰው ይመጣና 9 ቁጥር ተይዞ እንደሆነ ጠየቀው፡፡ ክፍሉም አልተያዘም ነበርና ቁልፍ ተቀበለ፡፡ ባለቦርሳውም ሰውዬ አስተናጋጁን 9 ቁጥር ሻማ፥ ቢላ፥ አፕል እና ብርጭቆ እንዲያመጣለት ጠየቀ፡፡ ወዳጄም እየተገረመ የተባለውን ያቀርብለታል፡፡ ሰውዬም እየሳቀ ወደ ክፍሉ ይገባል፡፡ ባጋጣሚ 9 ቁጥር ክፍል ጎን ያለው ሪሴፕሽኑ ክፍል ነበርና ጓደኛዬ ሌሊት ላይ በጣም አስደንጋጭ ነገር ሰማ፡፡ የእንሰሳት ጩኸት፥ ኡኡታ፥ የህፃን ልጅ ለቅሶ፥ የሚሰባበሩ እቃዎች ድምፅ፡፡ በዚህ የተረበሸው ጓደኛዬ እስኪነጋ ጠብቆ የተፈጠረውን ለማወቅ ጓጓ፡፡ ጠዋት ላይም ባለቦርሳው ሰውዬ በሙሉ ፈገግታ ቁልፍ ሲያስረክብና አስተናጋጁ ምን እንደተፈጠረ ለማየት ሮጦ ሲገባ......ሁሉም ነገር ባለበት እንጂ የተቀየረ ነገር የለም፡፡ አልጋው በስነስርአት ተነጥፏል፡፡ ብርጭቆውም፥ ቢላውም፥ አፕሉም ሻማውም ባሉበት ተቀምጠዋል፡፡ ይህም የሆነው ግንቦት አንድ ቀን ነበር፡፡ በ ነገሩ የተገረመው ወዳጄ ግራ እንደተጋባ ወራት አለፉት፡፡
ከአንድ አመት በኋላ በዚያው ተመሳሳይ ግንቦት አንድ ቀን ባለቦርሳው ሰውዬ ተመልሶ መጣ፡፡ በድጋሜም 9 ቁጥር አልጋ ተይዞ እንደሆነ ጠየቀ፡፡ በዚህም አመት ክፍሉ ስላልተያዘ ቁልፍ ተሰጠው፡፡ በድጋሜም 9ቁጥር ሻማ፥ ብርጭቆ፥ ቢላ እና አፕል አምጡልኝ አለ፡፡ አመት ሙሉ ግራ የተጋባው ጓደኛዬም የማወቅ ጉጉቱ እየጨመረ የተባለውን አቀረበለት፡፡ በዚያም ሌሊት እነዛኑ የሚረብሹ ድምፆች ሰማ፥ የሚያለቅሱ ህፃናት፥ የእቃዎች መሰባበር እና የእንሰሳ ድምፆች፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ወደ ክፍሉ የሚወጣ ወይ የሚገባ ሰው መኖር አለመኖሩን ሲከታተልም አነጋ፡፡ ሲነጋ ባለቦርሳው ሰውዬ እንደተለመደው ከፈገግታ ጋራ ቁልፍ ሲያስረክብ ጓደኛዬ ሮጦ ቢመለከት ምንም ነገር የለም፡፡ አልጋው ባግባቡ እንደተነጠፈ፥ እቃዎቹም ምንም ሳይነኩ በተቀመጡበት ነበሩ፡፡
በዚህ ባለቦርሳ ሰውዬ ሚስጥር እጅግ ግራ የተጋባው ወዳጄ አመቱን ሙሉ በጉጉት ሲጠብቅ ከረመና ግንቦት አንድ ደረሰ፡፡ እንደተለመደው ሰውዬው ከነቦርሳው መጣና 9ቁጥር ክፍልን ያዘ፡፡ እንደተለመደው 9ቁጥር ሻማ፥ ብርጭቆ አፕልና ቢላ ጠየቀ፡፡ እንደተለመደው ሌሊቱን ሙሉ አስፈሪ ድምፆች ሲሰሙ አደሩ፡፡ ሲነጋ እንደተለመደው ቁልፍ ሲያስረክብ 9 ቁጥር ክፍል ምንም አይነት ምልክት አልተገኘበትም፡፡ በዚህ ጊዜም አስተናጋጁ ይህንን ሚስጥር ከራሱ ከሰውዬው ሊጠይቅ ወሰነ፡፡
“አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር “
“ጠይቀኝ” አለ ሰውዬው በፈገግታ::
“ለምንድነው ሁልጊዜ ግንቦት አንድ ብቻ የምትመጣው?
ለምንድነው ሁልጊዜ 9 ቁጥር ክፍልን የምትይዘው?
9 ቁጥር ሻማው አፕሉ ቢላውና ብጭቆውስ ምን ያደርጉልሃል?
ሌሊት ላይ የሚሰሙት አስፈሪ ድምፆችስ የሚመጡት ከየት ነው?”
አለና ጠየቀው፡፡
ሰውዬም እየሳቀ
“ለማንም የማትናገር እና ሚስጥር የምትጠብቅ ከሆነ እነግርሃለሁ” አለው፡፡
ጓደኛዬም “ለማንም አልናገርም ንገረኝ” ሲል መለሰ፡፡
ሰውዬም ለማንም እንዳይናገር አስማለና ሚስጥሩን ነገረው፡፡
.
እነሆ ጓደኛዬም ሚስጥር ጠባቂና መሃላውን አክባሪ በመሆኑ የባለቦርሳውን ሰውዬ ሚስጥር ምንነት ለኔም አልነገረኝም
.
(ምንጭ፥ ሳነብ ያገኘሁት)

@wegoch
@wegoch
ሞኝ አትሁን!!
--------
ጠላትህ የሚበላህ እሳት ሳይሆን እሳቱን የለቀቀብህ ሴረኛ ነው!! ከእሳት ቃጠሎ እንደምንም ልትተርፍ ትችላለህ። የቃጠሎውን መንስኤ ለይተህ እስካላወቅክ ድረስ ዳግም ከመቃጠል አትድንም። ኦሮማራን በክፉ እያቀጣጠሉ ያሉ አመድ ምርቱ ሰው በላዎች በሁሉም ቦታ በሽሽሽ ናቸው። ፈተናችንና መከራችን ይህች ግርግር ብቻ አደለችም። ግጭቱና ግርግሩ መልኩን እየቀየረ ይሄ ህዝብ ፍዳውን እንዲበላ የማይፈነቀል ዲንጋይ፣ የማይወረወር መከራ አይኖርም። ይሄን ጊዜ በብልሃትና በማስተዋል ማለፍ ከምንም ጊዜ በላይ ያስፈልጋል!! ወጣት ልብ በል!! ወጣቶች ሆይ ዘራፍ አትበሉ፥ ከትናንት ዛሬ ይበልጣል። ከትናንት ነገ ይበልጣል። ለሞት አትቸኩሉ፥ ሞት የሞኖርን ያክል ትእግስት አይፈልግም!! አንድነትና መተለቅ የመበተንና የመጣፋፋትን ያክል ቀላል አደለም። የሚሆነው ሁሉ አይሁን አንልም። ግን ግን በመጥፎ እንዳይሆንና የጋራ መንገዳችንን እንዳይዘጋብን፥ ዳግም ነገን በቁርሾ አዙሪት እንዳይመልሰን ይሁን!!
ከነገሩ በስተጀርባ ተመልከት!! ከጥፋት የሚያተርፍ ሴረኛው ብቻ ነው።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የቀኑን ገራሚ #አስለቃሽ ጭስ እያሰብን አመሻሹ ላይ እያነባን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። 😭😭😭

የአስለቃሽ ጭሱ ሰለባዊች እስቲ እጃችሁን አውጡ 😀

@wegoch
@Mykeypictures
ሰው የወደደውን አርማ የማውለብለብ መብት ካለው እዚህ ሰልፍ ውስጥ "የኢትዮጵያን ባንዲራ አጣን።" ብለን የምናጉረመርም ሰዎች የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው ብለን ያመንንበትን ባንዲራ ይዘን ወጥተን እንዳናውለበልብ ማን ከለከለን? የመጡት የኦነግ ታጋዮች ናቸው ብለን እያሰብን እንጂ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ብለን ብናስብ ወጥተን ኢትዮጵያን ይወክላል ያልነውን ባንዲራ እያውለበለብን ለምን አልተቀበልናቸውም? እኛ የወደድነውን ሌሎች እንዲወዱልን ሌሎች የወደዱትን መጥላት አይጠበቅብንም።

(በላይ በቀለ ወያ)

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ሰላም የሆነ ቀን ነበር

አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ፍፁም በሆነ ፍቅር እንግዳዎቹን ተቀብልዋል።
ኢትዮጱያችን ለዘላለም ትኑር።

#Peace
#Love
#Union

@Getem
@Wegoch

@Mykeypictures
@Mykeypictures
@Mykeypictures
ኢትዮጵያ
ብዙ መሬቶች የተያዙት በቤተክርስቲያን እና በመስጂዶች ነው ግን አንድም አማኝ የላቸውም ነጠላ ለብሰህ ውዳሴ ማሪያምህን ይዘህ ወደ ቤተክርስቲያን ብትሄድ ውሸት ነው....ቁርአን ይዘህ ሙስበሀህን እየቆጠርክ ወደ መስጂድ ብትሄድም ውሸት ነው። ቅዳሴ የሚያሰማውም አዛን የሚለውም ስለ ሰላም መስበክ አለበት እስኪ ሁለት አንቀጽ ልናገር "ጠላታችሁን መርቁ እንጂ አታሳድዋቸው" ባይብል "አንዲትንም ነብስ ያጠፋ የሰውን ልጅ ሁሉ እንዳጠፋ ይቆጠራል" ቁርአን። ታድያ ይሄንን ሁሉ ግፍ ፈፃሚው አካል የትኛው እምነት ተከታይ ነው? እምነት የሌላቸው አውሮፓውያን እንኳን ለእንስሳ ያላቸውን ክብር እንዴት እኛ ለሰው ልጅ መስጠት ያቅተናል? ሀገር ሰላም እንድትሆን እኮ መከላከያ ሰራዊት አያስፈልግም ራሳችን ለራሳችን በቂ ነን. ...ወደ መረጋጋት መምጣታችን አይቀርም መጥፎው ነገር
ሰው ከሞተ አካሉ ከጎደለ በኃላ መሆኑ ነው።

((( ሸሪፍ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ጥቁር ታሪክ! አሳፋሪ ድርጊት!
«ዘውድአለም ታደሠ»

ኦሮሚያም ሆነ ሌላው ክልል ተስፋ የቆረጠ ዱርዬ፣ ግርግር አስነስቶ ለመዝረፍ ፣ ሴት በመድፈር የወሲብ ሱሱን ለመወጣት ይሞክራል! አሁን በአዲስ አበባ ዙሪያ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ወንጀል የተፈፀመው “ቄሮ” የሚባል ስም ህጋዊ ባደረጋቸው ወንበዴዎችና ሌቦች የተፈፀመ ነው። ስለዚህ ጥያቄያችንና ቁጣችን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ወይም ቄሮ በሚል ስም ተደራጅተው ለመብታቸው ከታገሉ ወጣቶች ጋር ሳይሆን ቄሮ ነኝ እያሉ ሐገር እያፈረሱ፣ ሴት እየደፈሩ፣ ካሉ ያለምንም ፖለቲካዊ አጀንዳ ከተሰባሰቡና ውንብድናቸውን ያለከልካይ ከሚፈፅሙ ዱርዬዎች ጋር ነው።
አሁን የከተማው ህዝብ፣ በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ህይወታቸው ከባድ አደጋ ላይ ወድቋል። አንባገነን ነበር ባልነው በቀድሞው ኢህአዴግ ዘመን እንኳ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲህ ሆኖ አያውቅም። አቶ ለማ የሚመሩት የክልል መንግስት ጉዳዩን በቸልታ እያየው ነው። የክልሉ የፖሊስ ሃይል ምንም ሊያደርግ አልፈለገም። የፌደራል መንግስትም በዝምታ ህዝቡ ላይ ሞት ፈርዷል። የምናከብራቸው የኦሮሞ ህዝብ መብት ተሟጋቾችም ደፍረው ድርጊቱን ለማውገዝ ሞራል አጥተዋል። 
ባሁን ሰአት ኦሮሚያ ክልል እየተመራች ያለችው በመንግስት ሳይሆን በተደራጁ ተስፋ የቆረጡ ጎረምሶች ነው። ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም። እየተደረገ ያለው ግን የኦሮሞን ስም የሚያጎድፍ፣ «ኦሮሞ ሐገር ከመራ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች» ሲሉ ለኖሩ ሰዎች የልብ ልብ የሚሰጥ፣ ከታጣቂ ጋር ሲፋለሙ ህይወታቸውን ላጡ ወጣቶች ዘልአለማዊ ስድብ የሚሆን፣ ለዲሞክራሲ ዋጋ የከፈሉ የኦሮሞ የነፃነት ታጋዮችን ገድል በዜሮ የሚያባዛ አሳፋሪና ታሪክ የማይረሳው ሃጢአት ነው። ምን እንደምል አላውቅም። እያየንና እየሰማን ያለነውን ነገር እንኳን ለመፃፍ ደግሞ ለማሰብ ራሱ አቅም የለኝም!
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ለጊዜው የማስተማሪያና የማንቂያ ቃላት ዋጋ አጥተውብናል።ከትናንት ነገ ይሻላል
ብንልም ሁሉም በስሜቱ ሲነዳ እያየን ነው! ከሞት ህይወት ይበልጣል ብንልም
የምንሞትበትን መንገድ የሚመርጠው በቁጥር አይሏል!"
ካልደፈረሰ አይጠራም ይሉት ብሂል ጎጅና አጥፊ ነው፥ ግን ብዘው ሰው ወዶታል!!
-------
በላ ልበልሃን የናፈቀው አይሏል፥ ዳሩ እናቶች፣ እጻናትና አዛውንቶች ከቶ ይሄን ማየትም
መስማትም አይከጅሉም!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መንግስት እንደሀገር ሽማግሌ መምከር ሳይሆን፣ ህግ ማስከበር
አለበት! (በድሉ ዋቅጅራ)
.
እየሆነ ያለው በፍጹም ከሰብአዊነት ውጭ ነው፡፡ ሰው እንኳን በወገኑ ላይ እንዲህ ያለውን ዘግናኝ ግፍ አይሰራም፡፡ጅጅጋ፣ አዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ . . . . ቡራዩ/ አሸዋ ሜዳ! . . . ግድያን፣ ዝርፊያን፣ የእናቶችንና እህቶችን መደፈር . . . . የእለት - ተእለት መዝገበ ቃላችን አካል እየሆነ እየለመድነው ነው። ያስፈራል፡፡ . . . ህግ የሚያስፈልገው ደካሞችን ከጉልበተኞች፣ ሰላማዊ ዜጎችን ከግፈኞች ለመጠበቅ ነው፤ መንግስት የሚያስፈልገው ደግሞ ህግን ለማስፈጸም ነው፡፡ በየሰዉ ውስጥ ያለው የአውሬነት ባህርይ በመንግስት የህግ ሉጋም ከግልቢያው መገታት አለበት፡፡ መፈክርና ምክር ለሰለጠነ ሰው ነው፡፡ . . . በእያንዳንዱ የዜጎች ጥቃት ተጠያቂዎችንና የተሰጠውን ፍትሀዊ ፍርድ መንግስት ለህዝቡ እስካልገለጸ ድረስ፣ በየጥቃቱ ማግስት የሚሰጥን
ትርጉም የለሽ መግለጫ የግፉ አካል እስኪመስል ድረስ እየተደጋገመ ነው፡፡

@gebriel_19
@wegoch
@wegoch
በዚህ ጊዜ በተለያየ ቦታ ግጭት ፣ ዘረፋና ፣ ግድያና ደፈራ የሚያካሒዱ አረመኔዎች "ችግራችሁ ምንድን ነው?" ተብለው ቢጠየቁ "ድንቁርና!!!" ከማለት ውጪ ምን አይነት መልስ መስጠት ይችላሉ?!!! ድንቁርና ደሞ በመማር ፣ በማወቅ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ተምረው አውቀው የደነቆሩ እንጢቆች አሉና። ከድንቁርና መላቀቅ የሚቻለው በኔ ላይ ሊደርስ የማልፈልገውን በሌሎች ላይ እንዲደርስ አልፈልግም ። በሚል ሰዋዊ እሳቤ ብቻ ነው ። በእህቴ በእናቴ ፣በአባቴ ፣ በወንድሜ ፣ በሚስቴ ፣ በቤተሰቤ ላይ እንዲደርስ የማልፈልገውን ነገር በሌሎች ቤተሰብ ላይ እንዲደር አለመፈለግ እና አለማድረስን የሚያህል ምን እውቀት አለ?! የፈጣሪን አምሳል የሆነውን ሰው ወደ አውሬነት የሚለወጥበት ብቸኛው አስማት እና ግማት ድንቁርና ብቻ ነው። ሰው ሆነን ስናስብ ሰው ሁሉ ብሔሩን እና ዘሩን ፈልጎ እንዳልተፈጠረ ፣እናትና አባቱን መርጦ እንዳልተወለደ ይገባናል። መደንቆር ፈልጎ የደነቆረ ሰው እንጂ እንዲደነቁር ተደርጎ የተፈጠረ ሰው የለም። ከድንቁርናዎች ሁሉ የላቀ ድንቁርና ደሞ መደንቆርም መምረጥ ነው። አቤቱ በድንቁርና ያልፈጠረን ከድንቁርና ይሰውረን።

በላይ በቀለ ወያ

@lula_al_greeko
@getem
@getem
አብይና የ25 አመት በሽታ !!!!!


አስር ጊዜ አብይ ላይ እጅ መቀሰር ምን ዋጋ አለው??? የገዛ ህይወቱን አስተካክሎ መምራት የማይችል ፤ ቤቱንና ማጀቱን በስርኣት መምራት የማይችል ሁሉ ዘሎ ስለ ሃገር
አመራር ትንታኔ ሲሰጥ ስትሰማው ያሳፍራል ። አብይ እኮ መለኮት አይደለም ። 25ኣመት የዘረኝነት ጡጦ ሲጋት የኖረን ትውልድ በ4ወር ዘረኝነቱን ካላስወገደ ብለህ አትመፃደቅ ። ይህ ሁሉ ኪሳራ የመጣው በወያኔ ብቻ ነው ። ዛሬም ነገም ልትወቀስ የሚገባት ኦነግንም ወደዚህ ፅንፍ ገብቶ ጨካኝ ወጣቶች እንዲወለዱ ያደረገችው ወያኔ ብቻ ናት። 25 አመት የተጨማለቀውን ጭንቅላት አብይ በ4ወር ውስጥ ካላፀዳ ብለህ በፌስ ቡክ የስድብ ውርጅብኝ አታውርድ ።25 ደንዳና የጥላቻ አመት ። 25 አስጠሊታ የቂምና ጥላቻ ዘመን ።
የ25 አመት የቁርሾና በቀል ጎልማሳን በ4ወር መገልበጥ ይቻላልን ????እርግጥ ነው በገዳዩች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ይወሰድልን ማለት የሁላችንም ድምፅ ነው ። ፖሊስም የወሰደው እርምጃ የነውር ነውር ነው ። ግን ደግሞ እዳውን ሁሉ አብይ ላይ ለመደፍደፍ መቸኮል ግን ግብዝነት ነው ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የኔ የዘር ሀረግ ሲመዘዝ
።።።።።
(በላይ በቀለ ወያ)

አባቴ በቀለ ወያ የወለጋ ኦሮሞ ነው። እናቴ ፅጌ ገብረ እግዚአብሔር ደሞ የአድዋ ትግሬ ናት። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው " በምን ቋንቋ ተግባብተው ተጋቡ? በምን ስሜት ተሳሳቡ ? በምን ቋንቋ ተጀናጅነው ተማምነው አብረው ተኙ? በምን እምነት እኔን ጨምሮ አራት ልጆችን ወለዱ?" እላለሁ። መልሱ ግን ቀላል ነበር። በእናትና በአባቴ ዘመን ከቋንቋ ይልቅ ፍቅር ፣ ከዘር ይልቅ ኢትዮጵያዊነት ያግባባ ነበር። አንድም ቀን ስለዘር ሀረጋቸው ነግረው አላሳደጉንም። ሁሌም ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ምስክር ሆነው አሳድገውናል። በዚህም በልጆቻቸው ዘንድ የተመሰገኑ ናቸው!!!
።።።።
እድሜና ጤና ይስጣችሁ። ሀገር ሰጣችሁን እንጂ ዘረኝነትን አላወረሳችሁንም።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/29 23:24:41
Back to Top
HTML Embed Code: